Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አመዳቸው ቡን ብሏል …. ፊታቸው ሁሉ በድንጋጤ ተውጧል::ያልገባውና ግራ የገባው ሙትቻ ስርአት –ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

እስካሁን ወያኔዎች አለመረዳታቸው የሚገርመው እኮ ዘላለም መኖር የለም…ዘላለም መኖር አይደለም ዘላለም ስልጣን ላይ ዘላለም መቀመጥም እንዳሌለ ማወቅ ያስፈልጋል::ቃሊቲን ሳይቀምሱት ቂሊንጦን በካቦነት ሳያገለግሉበት አሊያም ካቦ ሳያንጫጫቸው ወደ ሞት መውረዳቸው ያንገበግበኛል:: አለቅን እኮ ኢሠፓአኮ.. ተባለ:ካለፉት መንግስታት መማር ያልቻለው ወያኔ ራሱን አልፋ እና ኦሜጋ አድርጎ ስለሚቆልል ከፍተኛ ክፍተት እና መንሸራተት እንደተከሰበት በገሃድ እያየን ነው::የዘረፉትን ዘርፈዋል ለምን ስልጣን እንደማይለቁ ያውቁታል የሰሩት ወንጀል የት እንደሚያውላቸው ያውቁታል:: ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት አለ ብሎ ለማመን ያስቸግራል ሕወሓት ከተወገደ ኢሕአዴግ ራሱን ያጠፋል::
ሕወሓትን የሚረከብ ተተኪ እንዳሌለ ይታወቃል::ለጊዜው በተባለው መስመር እንደ ገደል ማሚቱ ነገር እየደጋገም የሚሙልጨለጭ ትውልድ ሕወሓትን ተረክቦ በበረሃ እንደአለፉት ታጋዮች ጥርሱን ነክሶ አንጋፋዎቹን ለማዳን የሚችል ትውልድ አለመኖሩ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል::ወደ እርጅና እና መሰላቸት ውስጥ እየገቡ ያሉት ዘራፊዎቹ የጥጋብ መንፈስ የተጠናወታቸው ሕወሓቶች ስልጣን እስከሞት ድረስ ብለው በመያዝ ለሕዝብ ለማስረከብ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ለሆዳቸው ብለው የተጠጉ ካድሬዎች ሳይቀሩ እያሳሰባቸው ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል::ነገን ለመገመት ግራ በተጋባ ካድሬ የተሞላው ወያኔ መውደቂያ ከመቃረቡም በላይ ሊተካው የሚችል አስተማማኝ ሃይል አለመኖሩ ወደ ክስመት እንዲያዘግም አድርጎታል::
የለውጥ ፈላጊ ሃይሎች የጋራ ፍጥነት በሚጠየቅበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የወያኔ ባልስልጣናት ከነሹምባሾቻቸው ራሳቸውን እያቆለጳጰሱ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርጉት ጥረት በራሳቸው ሽብር ስለሚሸበሩ ውስጣችው መበስበሱ እየታየ ነው::ይህ ወሳኝ ወቅት ሊፈጠር የቻለው የለውጥ ሃይሎች እያቀጣጠሉ ያለው የትግል ነበልባል የፈጠረው ትልቅ ስኬት ተደምሮበት ወያኔን ወደ መጨረሻው ገደል ለመጨመር እየተገሰገስ ይገኛል::ይህ ሁሉ ተጨማምሮበት እርጅናው የተጫጫነው ሞት አፋፍ ላይ ያለው ወያኔ ባለስልጣናቱ አመዳቸው ቡን ብሏል::..ፊታቸው ሁሉ በድንጋጤ ተውጧል::ያልገባው እና ግራ የገባው ስርአታቸው ራሳቸው ግራ አጋብቷችው ዘላለማዊነት እንዳሌለ እየነገራቸው ነው::ሞትም እንዲህ ያደርጋል::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>