በቦስተን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሊቢያ እና በተለያየ ቦታዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች በትናንትናው ምሽት የጸሎት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት፤ በደማቅ ስነ ስርዓት ተካሄደ!!
የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጠራው የሻማ እና የጸሉት ስነ ስርዓት ላይ በቦስተን እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች፤ የመካነ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ምሽት የሁለቱ ቤተክርስቲያን አባቶች የተመራ የጸሎት ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን በሁለቱ አባቶች ሰፋ ያለ ትምህርትም ተሰጥቷል፤ በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው ሕዝብ እንባ በእንባ በመራጨት በወገኑ ላይ የደርሰውን ሐዘን ገልጿል፤ በዚሁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያኖች የደረሰብንን ውርደት እና መከራ በጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕብረት ከወገናችን ጎን መቆም እናዳልብን ያስገነዘቡ ሲሆን፤ በወ/ሮ ራሄል ፍቅራ አብ የቀርበ ግጥምም ቀርቧል፤
በመጨርሻም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሚቀጥለው ቅዳሜ በተዘጋጀው የአንድነት እና የወገን አጋርነት ስብስባ በሚቀጥለው ቅዳሜ ኤፕሪል 25 2015 ከቀኑ 3፡00 PM ሰአት ጀምሮ በ86 Bishop Allen Dr, Cambridge, MA 02139 ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።