Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ያለመላ ግጭት ጅልነት ነው፡፡ የዝግጅት ጊዜ ወስዶ አስቦ፣ ሁሉን አመቻችቶ ነው ትግል፡፡ – Minilik Salsawi

$
0
0

ሆያሆዬ ሳይደርስ ሆያሆዬ .. ዉሮሸባዬ ሳይከፈት እስክስታ..ካለጊዜ ያውራዶሮ ገደል ማሚቱ ከመሆን አንድም ይሰውረን አንድም ያድነን::ምርቃት የማይደርስበት እርግማን እንደክፋት ላይገን ያደባበት የጊዜ ጀግንነት ለመደረብ የምንራወጥበትን ሰከን ብለን በሰውነት ጀግንነት የምንለካ ያድርገን::ጊዜን በአግባቡ እንደ ወርቅ ለመድመቅ ልንጠቀምበት የሚገባዉን ከአንዱ ይህ እይታውን ያደላዋል::የሚገባው በሚገባው ዘመን ላይ የማይገባው በሚያላዝንበት መደድ ላይ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም:: በማንኛውም ደረጃ ላይ ቢሆን በትክክል ጊዜን መጠቀም ልናውቅበት ይገባል፡፡ ከልክ እና ከአቅማችን በላይ ከመጣደፍ ያድነን ፤ ካልሆነ ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ይራመዳሉ ፡፡ የትክክለኛዋ ቅፅበት ሰላይ ልንሆን ይገባል፡፡ የጊዜን መንፈስ አነፍንፈን ማሸተት ግድ ይለናል፡፡ ወደ ድል የሚወስዱንን መንገዶች በዚያ እናገኛለን፡፡ ጊዜው ካልበሰለ ማፈግፈግን ልናውቅበት ይገባል፡፡ ሲበስል ደግሞ ፈፅሞ ወደኋላ ማለት አይገባም: ወደፊት መገስገስ ነው::ታላቅ ቁምነገር ይህ ነው ጊዜን እና ትግልን እያቀናጁ ወደድል መንጎድ ነው::

ጊዜን በትክክል መጠቀም የሚችል ዝግጅትን ዋና ጉልበቱ ያደርጋል፡፡ ድግሱ ከመድረሱ በፊት የምግብ እህሉን፣ የጌሾ ጥንስስ ስንቁን ማደራጀትና በመልክ መልኩ መሸከፍ፣ መጥኖ መደቆስ፣ መብሰያና መፍያ ጊዜውን በቅጡ ለድግሱ ሰዓት ማብቃትን ከሸማች እስከ አብሳዩ ውል ሊያስገቡት ይጠበቃል፡፡እንኳን ከበሰለ በኋላ እንዲሁም መዘናጋት አይገባንም::ያለመላ ግጭት ጅልነት ነው፡፡ የዝግጅት ጊዜ ወስዶ አስቦ፣ ሁሉን አመቻችቶ ነው ትግል፡፡ አንዴ ከገቡ ደግሞ መስዋዕት መኖሩን ሳይረሱ ምንጊዜም ሳያቋርጡ፣ ሳይማልሉና ሳይታለሉ መቀጠል ግድ ይሆናል፡፡

ዘመን የጊዜ ጥርቅምና የቅራኔና የሥምረት ውጤት ነው፡፡ ስለዚህም እንደታሪክ ክፉውንም ደጉንም ማጣጣሚያውና ያንን የመመርመር፣ ከስህተት የመማር፣ ነገን የመተለም ጉዳይ ነው ጊዜን ማወቅ ማለት መጪውንም ምርጫ በጊዜ ማስላት ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ጊዜን ጨበጥክ ማለት ድልን ጨበጥክ ማለት ነው፤ የሚባለው እንዲያው ለወግ አይደለም! ጊዜን እንደመሳሪያ የምንቆጥረው ከዚህ በመነሳት ነው፡፡ ንቃት እና ግንዛቤን በጊዜ እንግዛ ሌሊትን፣ ተስፋንና ንጋትን – ይንገረን፡፡ ይህ ሚጠቅመን በማታ ሩጫ እንዳንጀምር ከነጋ በኋላም እንዳንዘናጋ ነው!


በፋሲጋችን። ዳዊት ዳባ።

$
0
0

እንኳን በደህና ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ ለፈሲጋ በዓል አደረሰን። በአሉን የፍቅር የሰላም ያድርግልን።

Anger at injustice as martin luter king wrote. Is the political expression of love?

የፋሲጋ ሳምንት (ህማማት) ድንቅና አስገራሚም ነው። ፍቅር፤ መሰዋትነት፤ ክህደት፤ ታማኝነት፤ ፅናት፤ፍርደገምድልነት፤ምቀኝነት፤ ተንኮል፤ ደባ፤ አፍቅሮ ሰልጣን፤ አፍቅሮ ንዋይ፤ ሰም ማጥፋት፤ ይቅርታ፤ አብሮ መብላት፤ ጉቦ፤ ተስፋ፤ ሀዘን፤ ደስታ፤ ስቃይ፤ሞት፤ ይሰቀል{Mop Justice}፤ ብቻ ጠቅለል ባለ የዚህን አለም ሂወታችንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሲከወን እናይበታለን።

ህማማቱ ከተፈፀመ ረጅም ጊዜ ሆነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አለም የሰው ልጅም በእጅጉ ተቀይሯል። ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶ በዚህ ምድር ላይ የተመላለሰው በዚህ ዘመን ቢሆንስ ኖሮ ብለን ብንጠይቅ?። የሰው ልጆች ይህ ሁሉ ግፍ እንዲፈፀምበት፤ በመጨረሻም እንዲሞት አይፈቅዱም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ድረስ ተለውጧል ማለት ይቻላል። ሞቱም ሆነ ያን ሁሉ መከራን መቀበሉ ከንቱ አልቀረምና ስለተለገስነው ዘላለማዊ ሂወቱ ብቻ ሳይሆን ምድርን በዚህ ደረጃ ስለቀየረው ደስ ያሰኛል። ይህ ግን ጠቅለል አድርገን በአለም ደረጃ ከወሰድነው ነው። የዘመኑ ሀያል ህዝቦች በአደገ ስብእና ላይ እና ለሰው ልጅ ሂወት ክብር የሚሰጡ በመሆናቸው ነው ። ብቃት ደረጃ ደርሰዋል ባይባልም ፍትህ እንዳይጓደል አሰልሰው የሚጥሩና ለእውነት የሚቆሙ ስለሆነ ነው። አቅሙ ለሌላቸው ተቆርቋሪ መሆንን ስራቸው ያደረጉ ብዙዎች ያለቡት ማህበረሰብ ስለሆነም ነው። በዋናነት ክርስትናቸው ይህንኑ ታላቅ ቁም ነገር መሰረት ያደረገና በሚታይ በሚጨበጥ ስራ የታገዘ ስለሆነ ነው። ነጣጥለን በየሀጉሩና በየአገሩ የሰው ልጅ ምን ደረጃ ላይ ነው ያለው? ብለን ካየነው ግን ግምታዊም ቢሆን የምንደርስበት ድምዳሜ በእጅጉ የተራራቀ በዙም በህማማቱ ዘመን ከነበሩ የሰው ልጆች ከነበራቸው ስብእና ያልተለወጠ ሊሆን ይችላል።

አያድርገውና መመላለሱ በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ ሆኖስ ቢሆን?። ጥያቄው ለበዛው አማኝ አናዳጅ የሚሆን አይመስለኝም። ሲጀመር ጥያቄውን ያስነሱት ሰባኪ ነን ያሉ ናቸው። ዝም ሲባል ይባስ ብለው ትንኮሳ ስለበዙ ነው። አሁንም ለምን ተነሳ ብለው ይሰቀሉ የሚሉና አዋራ ሊያስነሱ ይችላሉ። መነሳት ግን የግድ አለበት። አዎ በዚህ በኛ ዘመን ህማማቱ ኢትዬጵያ ውስጥ ቢሆንስ ኖሮ?።

ከሳሾች፤ አስገዳይና፤ ገዳዬች አሉን። በእርግጥ በሰለጠነው ማህበረሰብ ውስጥ እነዚህን በመንግስት ስልጣን ላይ አናገኛቸው ይሆናል። ቢኖሩም ስልጣናቸው የተገደበ ስለሆነ አይችሉም። በየትኛው የአለም ክፍል ላይ ሊኖሩ ግን ይችላሉ። የውሸት ምስክሮችንም መግዛቱም ሆነ ፈራጆችን ማግኘቱ ቀላል እንደሆነ ከኑሯችን የምናያው ነው። ይህን አይነት እኩይ ወንጀል ቅቤ ቀብተው የሚያሰማምሩና ህዘብን የሚያደናግሩም የካድሬ መአት፤ ጋዜጠኛ ተብዬና አደርባይ ምሁራን ሞልተዋል። በዋናነት በየእምነቱ የቁጩ ሀዋርያቶችም እንዲሁ። ያም ሆኖ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ከጠቅላለው ህዘብ ጥቂቶች ናቸውና እንደህዘብ ከሌሎች የሚያሳንሱን አይሆንም።

መክሰሻውም በገፍ ነው ያለን። ከአስተምሮቶቹ ውስጥ በቀላሉ በመምዘዝና ትርጉም በመስጠት። በእምነቶች መሀል ግጭት በመፍጠር። በሽብርተኛነት፤ በአገር ክህደት፤ መንግስት ላይ በማሴር፤ የህዳሴ ጉዟችንን በማደናቀፍ የሚለው ሁሉ በቀላሉ መክሰሻና ማሰቃያ ሲያልፍም መግደያ ሊሆን እንደሚችል ያለንበት ሁኔታ መስካሪ ነው። አይደለም አገርን አልፎም አለምን የሚያነቃንቅና የሚለውጥ መልካም ሀሳብ ይዞ የመጣው መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሽ የሆነች አገራዊና ህዝባዊ መልክም ሀሳብ ለዛውም ምድራዊ አላችሁ ተብለው ብዙ ንጹሀን ዜጎቻችን እየተገደሉ፤ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው በየማጎርያ መኖራቸው የማንክደው ነው። ያም ሆኖ ይህንኛውም በመንግስት ደረጃ የሚራመድ ስለሆነ እንደ ህዘብ አያሳንሰንም ብለን እንውሰደው።

ዛሬም “ይሰቀል”፤ “ይሰቀል” ልንል የምንችል ምን ያህላችን ነን የሚለው ላይ ብዛታችን ነው አስፈሪም አሳፋሪም ሊያደርገን የሚችለው ። ሲጀመር የመጠየቅ እድሉም ስለሌለን ይሰቀል ማለቱንም አንችልም። ወናው ጉዳይ ይህ ሰው ንጹህ ነው፤ ሰቆቃ ሊፈጸምበት አይገባም ብለን ልንመሰክር የምንችል ምን ያህላችን ነን?። አጥብቀን የምንቃወም፤ ፍትህን የምንጠይቅና ድምጻችንም የምናሰማስ?። ወጋም የሚያስከፍል ቢሆን ለመክፈል የምንፈቅድስ?። ንጽህናውን ልቦናችን እያወቀ እሷስ ብትሆን በመጀመርያ “አጭር ቀሚስ ማን ልበሺ አላት” አይነት አመክነዬ መደርደሩም ሆነ የተካንበት ተጠቂው ላይ ጉድፍ መፈለጉ ዘመንኛ መሆኑ ነው እንጂ ያው “ስቀለው” ውስጥ የሚካተት ነው።

አምላክ በማቲዌስ ወንጌል 25፤31-46 ግልጽ አድርጎ ነግሮናል። አመክንዮ ለመደረድር እንኳ እንዳያመቸን አድርጎ። ለተራቡት፤ ለተጠሙት፤ ለተጨቆኑት፤ ፍርድ ለተጓደለባቸው፤ ለሚሳደዱት፤ ባጠቃላይ ለሰው ልጆች አሁን በምድር ላይ የምናደርገውን ለሱ እንዳደረግነው አድርጎ እንደሚወስደው ነግሮናል። በዬሀንስ 4፤20 ደግሞ አጠገብህ ያሉ ወንድምና እህቶችህን ሳትወድ አምላክን እወዳለው ብትል እየቀጠፍክ ነው ብሎ መፈናፈኛ እንዳይኖር ቁም ነገሩን አጠናክሮ ዘግቶታል። ቃሉን ላመሰጠርው ልሞክር። መንፈሳዊ ስራችን ሲገለፅ ስለውለታ፤ ስለጉልበተኛነት፤ ስለትውውቅ ሳይሆን ስለሰባዊነት፤ ስለፍትህና ስላእውነት ለዛውም ከልባችን ደስ እያለን ብቻ የምናደርገው ይሁን ነው የሚለን።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመጣ አይደል ‘ሀ’ ተብሎ ቀን መቆጠር የተጀመረው። አሁን 2007 ላይ ነን ። በዚህ ረጅም ጊዜ ክርስትናው በአገራችን ብዙ ተከታዬች አፍርቷል። ብዙ አብያተ ቤተክርስትያናትና የአምልኮ ቦታዎች አሉን። ብዙ አስተማሪዎች ሰባኪዎች እንዲሁ። ጿሚው አገሬው ነው። ስሙን ከፍ ከፍ የሚያደርገውም እንዲሁ። በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ሰላት የሚያደርሰውም ያገሬው ግማሽ ነው። ሁሉም አይነት እምነቶቹ ረጅም ዘመንን አገራችን ውስጥ አስቆጥረዋል። ታዲያ ለምን ነፃነት የበዛልን ዜጎች መሆን አልቻልንም?። ማን ሀላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣ? ምንስ ስለጎደለ ነው?።

በዬሀንስ ወንጌል 2፤20 ላይ የአምላክ ቃል “ስራ የሌለው እምነት ሙት ነው ይላል።” በሌላ አገላላጽ ፍቅሩ አለ እንበልና እምነቱና ፍቅሩ መኖሩ የክርስትናው ግማሹ ነው። ሌላኛው ግማሽ ያን እምነትህና ፍቅርህን በስራ ላይ ማዋሉ ነው። እምነታችን ስራ የሌለበት ቢሆን ነው እንጂ ይህ ሁሉ ችግረኛ፤ ይህን ያህል ጥላቻ፤ በዚህ ደረጃ የፍርድ መጓደል። ቆጥሮ መስፈርት የሌለው ተሰዳጅ፤ አድሎ፤ዘረኝነት…. ባጠቃላይ ስቃይና መከራ በአገራችን ባልነገሰ ነበር።

የዘመኑ ስልጣኔ እንደሁሉም ነገር የአምላክን ቃል ማግኘቱንና መረዳቱንም ቀላል አድርጎታል። ኮንቢዩተሬን ስለሌሎች መብት መከበርና ስለነፃነት ስለመቆም ቅዱስ መፀሀፍ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት?። ከሰባ በላይ ጥቅሶች ሰጠኝ። ለፍትህ ስለመቆምስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ከየትኛውም ቁምነገር በበዛ ወደ ሁለት መቶ ቦታዎች ላይ ስለፍትህ ግልፅ አድርጎ ይነግረናል። እንዲሁ በራስ ስለመተማመንና አንገትን ቀና አድርጎ ስለመሄድስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ዘረገፈልኝ። እንዲህ እንዲህ እያልኩ ስጠይቅ አብዝቶ መልስ ሲሰጠኝ በመጨረሻ የደረሰኩበት ድምዳሜ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ አማኝና ፖለቲከኛ ልዩነት የሌለው መሆኑን ነው።

ሲጀምር የበዛነው አይደለንም እያልን በግድ ፖለቲከኛ መባላችን ይሰመርበት። ይህ እንግዲህ ለነጻነት፤ ለመብት፤ ስለፍትህና ስለእውነት የሚጮህው ሁሉም ባይሆን እንኳ የበዛው አማኝ መሆኑን ያውቃሉ። ከዘም በላይ አመነም አላመነም ክርስትናው የሚያዘውን ነው የምናደርገው። እንደሚመስለኝ ፖለቲከኛና ፖለቲካ የሚለው ዘመቻ መልካም በሆነው ስራችን እያሳጣን ስለሆነ ያልተመቻቸው ክፍሎች አሸማቀው ዝም ሊያሰኙን ነው ፍላጎታቸው። የሚገርመው ግን መሳጣቱ የተፈራው ለአምላክ ወይስ ለምእመኑ?።

እወቁት መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር የተመላለሰው በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ። ይህው ፖለቲከኛ ተብሎ ልታሳንሱት የምታስቡት ወገናችሁ በግፍ ለሚገደሉት፤ ፍትህ ለተነፈጉት፤ ከቄያቸው ለሚሳደዱት፤ አገር ለቀው ለተሰደዱት ወገኖቹ መቆምን ደስ እያለው የሚያደርገው፤ የሚታወቅበትና ለምድም ያደረገው ነው። በእርግጠኛነት ካሳዳጆቹ ወገን አይቆምም ። ሌላው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጽዋው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለሁላችንም መዳረሱ አይቀርም። ነገ ለሁላችንም የሚጮህው ይህው ወገን ነው። አለቀ።

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ ክንፉ አሰፋ

$
0
0

ክንፉ አሰፋ
እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።
“ሃሎ”
“አቤት”
“አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ… እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን ልብ… (ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። … ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን ይበ… (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)።

ይህ ጸያፍ ዘለፋ እና ማስፈራርያ እንግዲህ ወያኔ ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ከነውረኛ ስድቡ ባሻገር ደግሞ ቀላል የማይባል ድንበር ዘለል ሽብር ነው። ለዚህ ሽብር ተጠያቂ የሚሆነውም ተላላኪውና ሆድ አደሩ ብቻ ሳይሆን ላኪውም ጭምር ነው። ህወሃትን በመጠለል ልክ እንደ ISIS አንገትህን እቆርጥልሃለው ሲል መናገሩ መንግሥታዊ አሸባሪነት ለለመሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህ ሰው ሲከራከር የነበረው ተሾመ ቶጋም ይህንን ሰምቶ ዝም የሚል ከሆነ የወንጀሉ ተባባሪ ይሆናል።

በዚህ አይነት ማስፈራራት አላማቸውን ማስፈጸም ካሰቡ ግን በጣም ተሳስተዋል። እንዲህ አይነቱ ነገር የበለጠ እልህ ውስጥ ያስገቡናል እንጂ በስራችን ላይ ቅንጣት ያህል ተጽእኖ ሊፈጥሩ አይችሉም። እንደጋዜጠኛ ለመስራት ስንነሳ ፍርሃትን ከእትብታችን ጋር ቀብረነው ነውና ይህንን የምትሞክሩ ተስፋ ቁረጡ ነው የምንላችሁ።

ይህ ሰው ከሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱ ተነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ በተለያዩ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል። ስለዚህ ሰው ጉዳይ ተሾመ ቶጋ (የወያኔ አምባሳደር) ከብራስልስ ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ማስተባበያው ባጭሩ፣ “አለማየሁ ስንታየሁ ሰላይ አልነበረም። ከሆላንድም አልተባረረም። የተሰደደውም ከኢሃዴግ ዘመን በፊት ነው። … ይህ ደጋፊዎቻችንን ለማሸማቀቅ በአሸባሪ የተፈረጁ ሰዎች የሚያወሩት ወሬ ነው።” ይላል።

የሶስት ልህጆች አባት የነበረው አለማየሁ (ዘለቀ ፖላ) የሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱን እና መኖርያ ቤቱን ተቀምቶ ከሄደ ሶስት ወራት አልፈዋል። ጉዳዩን ከሚመለከተው ክፍል በማጣራት የዜናውን እውነተኝነት አረጋግጠናል።

ዜናው በውጭ ያሉ የስርዓቱ ደጋፊዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ በመሆኑ የተሾመ ቶጋ ማስተባበል የግድ ነበር። ውሸት ነው ማለታቸውም አይደንቅም። እውነት ተናግረው ሰምተናቸው ስለማናውቅ። አለማየሁ ስንታየሁ ችግር እንደነበረበት እና አስፈላጊውን ደብዳቤ ከኤምባሲው ተቅብሎ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱን አቶ ተሾመ በቃለ-ምልልሱ አልሸሸጉም።

የተሾመ ቶጋን ውሸት ከሰማሁ በኋላ ጉዳዩን ለማጣራት የሚመለከታቸው የሆላንድ መንግስት አካላትን አነጋግሬአለሁ። ሶስት ክሶች ተመስርተውበት ነበር። አንደኛው ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመመሳጠር አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሃብትን እንዲታፈን በማድረጉ፤ ሁለተኛው ክስ የአሱን ስም በማጭበርበር እና፤ ሶስተኛ የሆላንድ መንግስትን ዋሽቶ የስደት ፈቃድ ከገኘ በህዋላ ለገዢው ፓርቲ ይሰልላል የሚሉ ነቸው።

ጭንቀት ውስጥ በነበረ ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ደውሎ በጉዳዩ ላይ አነጋግሮኛል። ከሚኖርበት አካባቢ እንዳይርቅ በሆላንድ መንግስት ታግዶ በነበረበት ወቅትም ከመገኛኛ ብዙሃን፤ በተለይ ከጀርመን እና ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር እንዳገናኘው ጠይቆኝ ነበር።

ይህ ሰው ወደ ሆላንድ የገባው በ1994 (ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከአንድ አመት በህዋላ) በሰላም ተጓዥ ስም ነበር። ከዚያ ለበርካታ አመታት በስውር ከዚያም በግልጽ ለወያኔ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ አፈወርቅ አገደው በፌስቡክ ገጹ ላይ ስለዚህ ሰው እንዲህ ሲል አስነብቦናል። “ይህን ግለሰብ በአካል አውቀወለሁ። ብዙ የቅርብ ጓደኞቼም ስለሚሠራቸው የስለላ ሥራዎቹ ያውቃሉ። ከራሱ አፍ እንደሰማሁት ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፖላ ነው። እዚህ ስደት የጠየቀበት ስሙ ዓለማየሁ ስንተሰየሁ ነው። የወላይታ አካባቢ ተወላጅ ነው። ተቃዋሚ መስሎ ለህወሓት ኤምባሲ ብዙ የስለላ መረጃዎችን የወያኔ ተቃወሚዎችን በሚመለከት እንደሚያቀብል ይታወቃል። … አንዳንዴ ስብሰባዎቹ ሌሎችን በሚያገልል መልኩ በትግርኛ ሲደረግ ዘለቀ ፖላ ይሳተፋል። ምኑ ገብቶህ ነው በማታውቀው ቋንቋ የምትሳተፈው ስንለው ጆሮዬ ክፉ ክፉውን ስለሚሰማ ለእናንተ ወሬ ለማቀበል ነው ይል ነበር።”

የትንሳኤ በዓል በመላው ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ተክብሮ ዋለ! በካናዳ –የመንበረ ብርሃን ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ቶሮንቶ የበዓል አከባበር የተጠናከረ ጽሁፍ ይዘናል!

$
0
0
“አሁን ግን ክርስቶስ ላነቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተንስቷል። ሞት በሰው በኩል ስለመጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።”

(1ኛ ቆሮ. 15፡ 20-21)
የ2007 ዓ.ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያኖች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። በክርስትና እምነት በተለይ በአገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በታላቅ ሥነ ስርዓት የሚከበረው ይህው የትንሳኤ በዓል በትናንትናው እለት ሌሊት በየአብያተ ክርስቲያናት በተለያዩ የመንፈሳዊ ዝግጅቶች እና የጸሎት ስነ ስርአት በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ታውቋል።

ይህንኑ በዓል በተመለከተ በውጭው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዓሉን በስደት በሚኖሩባቸው ከተሞች በትናንትናው አለት በደመቀ ሁኔታ ያከበሩ ሲሆን በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቶሮንቶ የነበረውን አከባበር በተመለከተ የደርሰን ልናካፍላችሁ ወደድን። (ፎቶግራፎች ይዘናል)

በቶሮንቶ የመንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል የበዓል ዝግጅት መርሃ ግብር መሰረት ትናንት ቅዳሜ ሚያዝያ 3 ቀን 2007 ዓ. ም. ከምሽቱ 6፡00 ሰአት እስከ ሌሊቱ 1:30 ሰዓት ድረስ ብጹእ አቡነ ዲሞጥርዮስ የካናዳ – ኦንታሪዮ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና እጅግ በጣም በርካታ የቶሮንቶ እና የአካባቢው ምእመናን በተገኙበት እና እጅግ ደማቅ በሆነ በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች፤ የወንጌል ትምህርት፤ ማህሌት፤ ጸሎት ወንጌል ምስባክ፤ ኪዳን እና በመጨረሻም የቅዳሴ ሥነ ስርአት ተክበሮ ውሏል።

በቶሮንቶ የመንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሥነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ዲሞጥርዮስ የካናዳ – ኦንታሪዮ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበአሉ ላይ በመገኘት ለተሰበሰበው ምእመናን ቃለ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን የጸሎት ሥነ ስራአቱን በመምራት፤ ለምእመናኑ መንፈሳዊ ትምህርትም ሰጥተዋል። በዝግጅቱ ላይ በበዓሉ የነበሩ ምዕመናን የጧፍ ማብራት ሥነ ስርአት የተካሄደ ሲሆን የደብሩ ታዳጊ መዘምራን “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ” ወረብ በማቅረብ ለበዓሉ ትልቅ ድምቀት ሰጥተውታል።

በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በዓሉ ሰላምንና ፍቅርን የሚሰጥ ይሁንልን ዘንድ እኗኳን ለብርሃን ትንሳኤው አደረሳችሁ በማለት ለምእመናኑ አጠር ያለ መንፈሳዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በዚህ የትንሳኤ በዓል ዝግጅት ላይ ለየት የሚያደርገው የቤተክርስቲያኑ የበአል ዝግጅት ኮሚቴ በጣም ሊደነቅ እና ሊመስገን ይገባዋል። ምእመናን ለበዓሉ ዝግጅት ወደ ቤተክርስቲያኑ ባመሩበት ወቅት ከመኪና ማቆሚያ አንሰቶ በቤተክርስቲያኑ በዓሉን ለማክበር የተመመውን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ምእመናን ቦታ በማስያዝ፤ ፕሮግራሙን በመምራት እና ሥርዓት በማስያዝ ያደርጉት ጥረት እና የተሳካ ዝግጅት በጣም የሚያስመሰግን እና ለሌሎች ጥሩ ትምህርት እና አርአያ ሊሆን የሚችል መሆኑን ተገንዝበናል!!

በዚህ አጋጣሚ -የአቡጊዳ ድህረ ገጽ ዝግጅት ክፍልም እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደርሳችሁ እያለ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል!

20150411_204047 (1)

20150411_204047

20150411_213637

20150412_004519

20150412_004956

20150412_005013 (1)

20150412_005013

ፋሲካ ጾም ሖነ በበላይነህ አባተ

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር ምክር ቤት የተሳካ ጉባኤ አካሄደ

$
0
0

በቅርቡ የሽንጎው ከፍተኛ አመራር አካል የሆነው ምክር ቤት ባካሄደው የሁለት ቀን ስብሰባ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ሁኔታ በሰፊው መርምሮ ለቀጣዩም ትግል ምን መደረግ እንዳለበት መመሪያ በመሰጠት ተጠናቋል።

በተጨማሪም የሽንጎው የተለያዩ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ የቀረቡለትን ሪፖርቶች መርምሮ ትግሉ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን ተጨማሪ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል። በተለይም ደግሞ ሽንጎው በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያካሂደው ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ የተገኙትን መልካም ግንኙነተቶችን እና አበረታች ውጤቶች ከመረመረ በኋላ በዚህ መስክ የሚካሄደው እንቅስቃሴ እጅግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡

የሸንጎው ምክር ቤት የኢትዮጵያን አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ የገመገመ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ውስጥ እጅግ ተጠናከሮ የቀጠለውን ሁለንተናዊ የመብት ረገጣ ፣ በተለይም ደግሞ ባሁኑ ሰአት ዜጎች መሰረታዊ የሆነውን መሪዎቻቸውን በድምጻቸው በነጻነት የመመምረጥ መብታቸውን በትክክል እንዳይገልጹ ገዥው ሕወሀት/ኢህአዴግ እና እንደልቡ የሚያዛቸው የምርጫ የጸጥታና የፍትህ ተቋማት በህዝባችን ላይ በቀጣይነት እያሳዩት ያለውን እጅግ አሳዛኛ ግፍ ባፅጽንኦና በታላቅ ሀዘን ተገንዛቧል።

በዚህ እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ፣ የፖለቲካ መድረኩን ለገዥው ቡድን ባለመተው የህዝባችንን መብት ለማስከበር እጅግ ብዙ መስዋእትነት ለከፈሉ እና በመክፈል ላይ ለሚገኙ ታጋዮች ሁሉ ያለውን አድናቆት አክብሮትና የትግል አንድነት ምክር ቤቱ በድጋሜ አረጋግጧል።

ገዥው ቡድን ሕወሀት ኢህአዴግ የህዝባችንን መብት በሁሉም መልኩ መርገጡን በቀጠለ ቁጥር ህዝባችን ደግሞ በስርአቱ ላይ ያለው ብሶት ቅሬታና ጥላቻ፣ እጅግ እየሰፋ መምጣቱን፣ የሚደርስበት ግፍ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እንደሆነም ብዙ መረጃወችን ምክር ቤቱ ተመልክቷል።ዛሬ ህዝባችን ከዚህ ስርአት መልካም ነገርን መጠበቅ ትቷል፡ በራሱ አነሳሽነት ስርአቱ እንዲወገድለት አምርሮ ይፈልጋል፡ አልገዛም ማለትን በየቦታው እያሳየ ነው። ለመብቱ መቆምን፣ በግልጽ ማሳየቱን ቀጥሏል፤ የፍርሀት ድባብን አፈራርሶ በመጣል ላይ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም በገዥው ሕወሀት ኢህአዴግ ውስጥ የርስበርስ አለመተማመን እና ውጥረትም እየሰፋ መምጣቱን የሽንጎው ከፍተኛ አመራር ምክር ቤት በሰፊው ቃኝቷል።

እነዚህን ሁሉ ባንድ ላይ ስንመለከትም ሀገሪቱ ውስጥ ህዝባዊ የለውጥ አመጽ ሊነሳ የሚችልበት ሁኔታ እጅግ በፍጥነት እየተቃረበ መሆኑን ሽንጎው ተገንዝቧል።
ገዥው ሕወሀት ኢህአዴግ ከላይ ሲታይ ሁኔታወችን የተቆጣጠረና የተረጋጋ ይምሰል እንጂ ከሁሉም ህዝብ፣ ከሁሉም ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት የሀይማኖት ተቓሞች ጋር የገባበት ቅራኔ የራሱን ጥላ ሳይቀር ማንንም እንዳያምን ስላደረገው እነሆ ሌትም ቀንም በመደናበር ካንዱ ስህተት ወደሌላው እየተላተመ ወደ መጨረሻው መቃብሩ እንደተቃረበ እንረዳለን።

ሀላፊነት የጎደለው ሕወሀት ኢህአዴግ ጠባብ ቡድን ከራሱ ስልጣን እና አልጠግብ ባይ ዝርፊያ ባሻገር ለማገናዘብ ባለመቻሉም ሀገሪቱን ራሷን ወደ አደጋ አፋፍ አድርሷታል።

ይህን ሀገራችን የምትገኝበትን ሁኔታ የሚከታተሉ የሀገሪቱ ጠላቶችም የህዝባችንን የለውጥ እንቅስቃሴ ለአደጋና ለራሳቸው ቀጣይ አጥፊ አጀንዳ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ሸንጎ ተገንዝቧል።

ሐገራችንና ህዝባችን ከታሰሩበት የግፍ ሰንሰለት ነጻ ለማውጣትና በምትኩም አንድነቷ በተጠበቀ ኢትዮጳያ ስር ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲአዊ ስርአትን ለመገንባት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሽንጎው ምክር ቤት መመሪያ የሰጠ ሲሆን፣ ይህን ትግል ወደግብ ለማድረስም ሆነ ከላይ የጠቀስናቸውን አሳሳቢ ሁኔታወች ለማስወገድም ያንድነት ሀይሎች ከምን ጊዜውም በላይ በመተባበር በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
ሐገራችን ከምትገኝበት አስከፊ ሁኔታ ሁሉም አሽናፊና ተጠቃሚ ወደሆነበት ስርአት ለመሽጋገር ብሄራዊ መግባባትና ብሄራዊ እርቅ አማራጭ የሌለው እንደሆነ ምክርቤቱ አጽንኦ ሰጥቷል።

የሸንጎው ያመራር ምክር ቤት ዛሬ በሚካሄደው ትግል ውስጥ ያማራጭ ሚዲያን አስፈልጊነት በሰፊው ከተወያየ በኋላ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ያጭር ሞገድ ሬዲዮ ፕሮግራም ባስቸኳይ እንደሚያስፈልግና፣ ይህን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግም በውጭ የሚገኙ እትዮጵያውያን በገንዘብ እና ጊዜያቸውን በማበርከት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

ወቅቱ ለክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በዓሉ የሚመለከታቸውን አንባቢ ወገኖቼን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለትን እወዳለሁ፡፡ የደርግ ጊዜ አንድ ትዝታ አለኝ፡፡ በአብዛኛው በሀገር ወዳድ ደናቁርት የታጨቀው የደርግ መንግሥት ሠለጠንኩ ብሎ ሃይማኖተቢሱንና ሃይማኖተኝነትን ከልካዩን የሶሻሊዝም ሥርዓት ካወጀባት ጠማማ ዕለት ጀምሮ በዓል በመጣ ቁጥር በተለይም የአብዮቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት “እንኳን ደረሳችሁ” ይል ነበር – ያ ለአገራችን ባዕድ የነበረ የአገዛዝ ሥርዓት አንዲት ፊደል ላይ እንዲያ ይጨነቅ የነበረው፣ ሰው ለበዓሉ የደረሰው በራሱ እንጂ በፈጣሪ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነበር፤ የሥርዓቱ አቀንቃኞች በአብዛኛውና በግልጽ ይዞታቸው ሶሻሊስትና ኮሚኒስት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አልነበሩም – አንዳንዶች አምልኮታቸውን በኅቡዕ ያከናውኑ እንደነበርና ልጆቻቸውን ሣይቀር በድብቅ ክርስትና ያስነሱ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው ምንም ዓይነት እምነት ላይከተል ይችላል፡፡ መብቱም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት አልባነትን በግድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በማጫፈር በእምነትና በሃይማኖት ጸንቶ የኖረን ሕዝብ በአንዴ እግዜርን ወይም አላህን ወይም የምታመልከውን ሌላ መንፈሣዊ አካልን ክደህ ኮሚኒስት ሁን ማለት የደርግን ብልህነት ሣይሆን ጅልነት የሚያሣይ ነበር – ሠለጠነች ቢሏት ጊዜ የባሏን መጽሐፍ ያጠበችውን ሴት ዓይነት ጅልነት፡፡ መጨረሻው ባለማማሩ ይከተለው የነበረውንም የአካሄድ ሥርዓት አይረቤነት በእግረ መንገድ መረዳት አይከብድም፡፡ እንዲያው ትዝ ብሎኝ ነው፡፡

ርዕሴን በእንግሊዝኛ ብጽፈው ኖሮ “The Age of Terrorists, Extremists and Deviants” በሚል እንዲነበብ አደርገው ነበር፡፡ ያለንበትን ዘመን ከየአቅጣጫው ስንቃኘው ጥቂት የማይባሉ አክራሪዎች፣ ተስፈንጣሪዎችና አሸባሪዎች ዓለማችንን እያተረማመሱ እንደሚገኙ መገንዘብ አያስቸግርም፡፡ ሌላውን ዓለም ለአሁኑ እንተወውና ወዳገራችን ተስፈንጣሪዎችና ምናምንቴዎች እንመለስ፡፡ በነሱ ነውና መቅኖ አጥተን የቀረነው – “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” የምትለዋን ሐረግ እንድታስታውሱልኝ ግን ልማጠን፡፡

ትናንት አንድ ወዳጄ ቤቴ መጥቶ በላፕቶፑ ከዩትዩብ ያወረዳቸውን አንዳንድ ድንቃድንቅ ቃለ መጠይቆችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አስኮመኮመኝ፡፡ ሁለቱን ተስፈንጣሪዎችና ጠብ ጫሪዎች የተመለከትኩት በዚያን ጊዜ ነው፡፡ አንደኛው ተስፈንጣሪ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ይባላል፡፡ እኔን የታሪክ ተመራማሪ ያድርገኝና የታሪክ ተመራማሪ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ አፄ ቴዎድሮስን እንዴት አድርጎ እንደሚስላቸው ብታዩ ትደመማላችሁ፡፡ አበሻቅጦ፣ አበሻቅጦ ነው የለቀቃቸው፡፡ ሲናገር ደግሞ ታሪክን እንደሚተርክ ሣይሆን በስሜት እየተወራጨና ክፉኛ እየተቆጣ እዚያው እቦታው ላይ ያለ ያህል ሆኖ ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ – በኔ ጥራዝ ነጠቅ ግንዛቤ – ትንታኔውንና ሀተታውን ማቅረብ ያለበት በጥላቻና በበቀል ስሜት እየተንዘረዘረ ሣይሆን የሆነውን ነገር እንዳለ በተረጋጋና አድልዖ በሌለበት ሁኔታ ነው – ታሪክ ነዋ! የዛሬ ሣይሆን የዱሮ ዘመን ድርጊት ነው፡፡ ዛር ከፈረስ የመሆን ወገንተኝነት ለታሪክ ተመራማሪ የሚፈቀድ አይመስለኝም፡፡ ይህ የታሪክ ተመራማሪ ግን አንድ ቦታ ሲናገር እንደሰማሁት አንሻፍፌም ቢሆን እጠቅሳለሁ፤ “ሀፄ ዮሐንስ ምኒልክን ቢያስሩት ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ መታሰር ነበረበት፡፡ ሀገር ከሃዲና ሻጭ ስለነበረ የሀፄ ዮሐንስ መኳንንትና መሣፍንት ‹ይህን ሰው ነገር ሳያመጣ እንሰረው› ሲሉ ሀፄው በምሕረት ማለፋቸውና ‹መኳንንቴ ሊያስሩህ ይፈልጋሉና አምልጣቸው› ብለው የሸዋን ንጉሥ እንዲያመልጥ ማድረጋቸው ትክክል አልነበረም፡፡…” እኔ የታሪክ ተማሪ አይደለሁም፡፡ ባልሆንም ግን እንዲህ ያለ ጭራሽ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ የታሪክ ትንተናና ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ስመለከት የምናደድና ምሁር ተብዬውን የምቃወም መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴን የተቸበትንም መንገድ ስመለከት አዝኛለሁ፡፡ ባህሩ ዘውዴ ኢትዮጵያ በአጸደ ሕይወት ካሏት ብርቅ የታሪክ ተመራማሪዎች አንዱ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ለከት ሊኖረው ይገባል፡፡ ዐፄ ምኒልክንና ዐፄ ቴዎድሮስን ለማቋሸሽና በሕዝብ እንዲጠሉ ለማድረግ ይህን ያህል ዘመቻ ማድረግ ትርፉ ለጊዜው ትዝብት ብቻ ቢሆንም እውነቱ ባለበት ይኖራልና የማስተባበሉን ዋና ኃላፊነት ለባለሙያዎቹ መተውን መርጫለሁ – አልተከታተልኩ ሆኖ እንጂ በጊዜው መልስ ተሰጥቶበትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውዬው ግን በግብዝነቱ አሳዘነኝ፡፡ ደግሞም ሁለት ፀጉር ያበቀለ እንደኔው ትልቅ ሰው ይመስላል፡፡ ለምን ይህን ያህል ርቀት ተጉዞ ራሱን ትዝብት ውስጥ ማስገባት እንደፈለገ አልገባኝም – የእውነት አንጻራዊነት ደግሞ አስደነቀኝ፤ እውነት ሺህ ጊዜ አንጻራዊ ትሁን እንጂ ደግሞ ይህ ሰው ይህን ያህል ማፈንገጡ በሰዎች ተፈጥሮ እንድገረም አስገድዶኛል፡፡ ነገሥታቱን በዘራቸው ምክንያትም ይሁን በሌላ አይጥላቸው ወይም በግድ ይውደዳቸው ማለቴ አይደለም፤ ነገሥታቱ ምንም ጥፋት የሌለባቸው ምሉዕ በኩልሄ ናቸው ማለቴም አይደለም – ሰዎች እንደመሆናቸው እንደማንኛችንም ተራ ዜጎች ያጠፋሉ፤ ያለማሉም፡፡(በነገራችን ላይ ስለትግራይ ነገሥታትም ሆነ መሣፍንት እንዲሁም ስለ ዳግማይ ወያኔ የአስተዳደር በደል አንድም ነገር ትንፍሽ አላለም፤ ይህ ደግሞ ፍጹማዊ አድልዖና ወገናዊነትን ያሳያል፤ ምራቅ ከዋጠና ፈሪሃ እግዚአብሔር ካለው ጨዋ የትግራይ ሕዝብ የተገኘ የታሪክ ተመራማሪ እንዲህ ያለ ጭፍን አስተያየት ይሰነዝራል ተብሎ በጭራሽ አይጠበቅም – በኔ ግምት ንግግሩ ደመ-ሞቃታዊ ግልብ አስተያየት እንጂ በምርምር የተደገፈ እውነተኛ ታሪክ ነው ማለትም ያስቸግራል)፡፡

እኔ እምለው ታዲያ ጥላቻችንንም ይሁን ውዴታችንን የምንገልጽበት መንገድ አግባብ ይኑረው ነው ፡፡ ስንወድ፣ ስንወድ ሰዎች ባልዋሉበት ጦር ሜዳ ሺዎችን እንደገደሉና እንደማረኩ እያስመሰልን የምንኳሽ ፣ ስንጠላ ስንጠላ ደግሞ ጥቁሩን ነጭ፣ ነጩን ጥቁር እያደረግን ጥላሸት የምንቀባ ከሆነ አመክንዮታዊ ተፈጥሯችንን ገደል ከተትነው ማለት ነው፤ እንዲህ ስናደርግ ታሪክ ሣይሆን ኩሸትና ምናባዊ ገድል እየጻፍን ነው – እንደዚህ ያለ ነገር መጻፍ ወይ መናገር ካማረን ደግሞ በታሪክ ትምህርት አሳብበን ሣይሆን በልቦለድ ውስጥ ስሜታችንን መግለጽ እንችላለንና ወደዚያ መግባት ነው – የሰውዬው አካሄድ አህያን ተገን አድርጎ ጅብን እንደመውጋት ነው – ትልቅ የስብዕና ኪሣራ፡፡ ሰው የተባለ ፍጡር ደግሞ እንዲህ እንዲሆን አይጠበቅበትም፡፡ እንስሳ ብንሆንም ማሰብና ማመዛዘን የምንችል የሌሎች እንስሳት አለቃዎች በመሆናችን የማስተዋል ጥበብን እስከዚህን ድረስ በወረደ ሁኔታ ልንነጠቅ አይገባም፡፡ የዘረኝነትን ጭምብል አውልቀን፣ የሆድ አምላኪነትን ምኩራብ አፍርሰን፣ የጥላቻን ግምብ ንደን በሃቅ መፍረድ ካልቻልን ሰው መሆናችን ይቀርና በአንዲት አጥንት ሣቢያ የሰገሌን ጦርነት እንደሚያስታውሱን ውሾች እንሆናለን፡፡ ይህ ደግሞ ከንቱነትና እንደነቢዩ ሰሎሞን አነጋገር ንፋስንም እንደመከተል ያለ ሞኝነት ነው፡፡ ለምኑ ብለን? ነገ ጧት ሁሉም እርግፍ ብሎ ለሚቀረው? አቅል ጀባ መምህር ገብረ ኪዳን! ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትግሬና አማራ ይቅርና የሰው ዘር በአጠቃላይ የሚበጠርበትና የሚበራይበት ዘመን ይመጣል፡፡ ያኔ እውነት የምትነግሥበት፣ ሀሰት የምትዋረድበት አዲስ ዘመን ይብታል፡፡ ያኔ ላለማፈር አሁን ትንሽ ስንቅ መያዝ ይገባናል፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ መስበሩን ካላቆመ ድንጋዩም ቅል ለመሆን እንደሚመኝ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ከኅሊና መታወር አምላክ ይሠውረን!

ታሪክ ሲጻፍ በስማ በለው ሊሆን አይገባም፡፡ የስማ በለው ታሪክ አፈ-ታሪክ(ሌጄንድ) እንጂ እውናዊ ታሪክ ሊሆን አይችልም፡፡ ታሪኩን ወደድነውም ጠላነውም እኛ ግን እንዳለ ማስተላለፍ ይኖርብናል፡፡ አንድ ሃኪም ጠላቱ ታሞ ቢመጣ በመርፌ ወይ በከኒና ሊገድለው እንደማይገባ ሁሉ(በሙያዊ ሥነ ምግባር ኮዱ መሠረት አስቀድሞ መሃላም ገብቷልና) አንድ የታሪክ ቅንጫቢም እኛ ጋ ሲደርስ ስለማንፈልገው ብቻ አንሻፈን መናገሩ ወይም መጻፉ እኛን ለትዝብት ከሚዳርገን ውጪ ታሪኩን አንሰርዘውም፤ እውነት አትሰረዝምና፡፡ ስለሆነም ያ አፈንጋጭ የታሪክ ሰው ራሱን እንዲመረምር በዚህ አጋጣሚ ልጠቁመው እወዳለሁ፤ የጎመን ጥጋብ ያልፋል፤ የጉሽ ጠላ ስካርም ይበርዳል፡፡ ለነገሩ እንኳንስ ብዙም የሚያስደስት ነገር የሌለው የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና ሰማይና ምድርም ያልፋሉ – ሊያውም ይህም ሊሆን የቀረው ጊዜ ከአንድና ሁለት ሐሙሶች የሚዘል አይመስለኝም፡፡ ጤናማ አተያይ ለሁላችን እንዲያድለን ፈጣሪን እለምናለሁ፡፡ ደግሞስ አንዳችን አንዳችንን አበሻቅጠን የት እንደርሳለን፡፡ የሁላችንም ታሪክ በየራሱ የቆመ ሣይን እርስ በርሱ የተጋመደ ነው፡፡ ትግሬ ውስጥ አማራ አለ፤ አማራ ውስጥ ትግሬና ኦሮሞ ሌላውም አለ፡፡ ተማርን የምንል ወገኖች ግን አይፈጥሩ ጠብና ቅራኔ እየፈጠርን ደጉን ባላገር ባናምሰው ይሻላል፡፡ ማወቃችንን በቅጡ እናድርገው፡፡ ልሂቅነት ለዕልቂት ከበሮ ጉሰማ ሣሆን ለዕርቅና ለዕድገት አቅጣጫ ትለማ እናውለው፡፡ ኃላችንን ወደ ማፈርስ ሣይሆን ወደመግናበት አናዙረው፡፡ ጥላቻን መዝራት ይብቃን፡፡ ወደፍቅርና መተሳሰብ አምባ እንውጣና ሌሎች ያበላሹትን እኛ እናቃና፡፡ በተበላሸና በተሰባበረ መንገድ እየተጓዝን ቁስላችን ይበልጥ እያመረቀዘ የሚሄድበትን ሥልት ከመንደፍ ይልቅ በምንፈወስበት ዘዴ ላይ ጊዜና መላ አቅማችንን እናፍስስ፡፡…
ሌላው አፈንጋጭ ወይም ተስፈንጣሪ ደግሞ ያ የሰንበት ጽንስ ተስፋየ ገብረ“ባብ” የሚባለው ነው፡፡ ይህን ሰው አደብ የሚያስገዛ ጠፍቶ ይሄውና ሽብልቁን እየቀበቀበብን ከኛም አንዳንዶቻችን የሚቀበቀብብንን ሽብልቅ ባለማጤን እያጨበጨብንለት መቃቃርንና ግጭትን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየነዛ ይገኛል፡፡ ሼክስፒር እንደሚለው – እጠቅሳለሁ – “To do a great right do a little wrong” እንደሚለው ይህን የእባብ ልጅና አለምነው መኮንን የተባለውን የዲያብሎስ ውላጅ በአንዳች ጥበብ የሚያስወግድ ኃይል ቢኖር በኔ በኩል ድጋፌን እንደማልነፍግ እገልጻለሁ – የንስሃ ዕድሜ እንዳገኝ ከመጸለይ ጭምር፡፡ ሰይጣንን ማስወገድ ወይም ቢያንስ አደብ ማስገዛት ከኃጢኣት አይቆጠርም ባይ ነኝ፡፡ ጠላትን መውደድ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ስትወደው የሚጠላህን መሠሪ ጠላት ከይሁዳ እንጂ ከተራ ጠላት አትመድበውም፡፡ እነዚህን መሰል ፀረ-ሰውና ፀረ-እግዚአብሔር ግለሰቦች ሰባት ጊዜ ሰባ ብቻም ሣይሆን ሰባ ጊዜ ሰባት መቶ ያህልም ይቅር ቢባሉ ተፈጥሯዊ የፀላኤ-ሠናያት ባሕርያቸውን ሊያቆሙ አይችሉም – ተፈጥሮን ደግሞ ተመክሮ አይመልሰውም፡፡ ይሁዳ ምሕረትን እንደማያገኝ ክርስቶስ በአንደበቱ ተናግሯል – “የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፎ የሚሰጥ የወፍጮ መጅ ባንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባህር ቢወረወር ይሻለዋል” በሚል ልዩ አንደበታዊ ማኅተም፡፡ ስለሆነም ተስፋዬ ገብረባብና ይሁዳ አንድ ናቸውና ሞት ቢያንሳቸው እንጂ አያንሳቸውም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጨካኝ ሆኜ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ በፍጹም፡፡ ያጨከነኝ ሥራቸው ነው፡፡

ተስፋየን ይሁዳ ያልኩበት ምክንያት የበላበትን ወጪት በመስበሩና ያደገባቸውን ሁለት ማኅበረሰቦች ለማጋጨት ከራሱ ይሁን ከሌላ ተቀብሎ የተሸከመውን ታሪካዊ ኃላፊነት ሳይታክትና ሳይሰለች እየተወጣ የሚገኝ የእፉኝት ልጅ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ የእምዬ ኢትዮጵያን ጡቶች እየጠባ ቢያድግም አሁን እንደ ቀትር እባብ እየተቅነዘነዘ የሚያደርገውን ስንታዘብ ሰውዬው በማንነት ኪሣራ የተዘፈቀና ያን ለመርሳት በሚያደርገው ጥረትም የሚሠራውን እንደማያውቅ ሰው ትልቅ ጥፋት እያደረሰ መሆኑን ነው፡፡ በውነቱ ሰውዬው በራሱ አንደበት እንዳረጋገጠውና በድረገፆች በተጋለጠው መታወቂያውም እንደተመለከትነው ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ታዲያ ስለኢትዮጵያ ይህን ያህል አብዝቶ መጨነቁ ለምን ይሆን ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ እኔ ለምሣሌ ስለ ኬንያና ታንዛንያ ከሀገሬ በላይ እንቅልፍ አጥቼ አልጨነቅም፡፡ “የራሷ አርሮባት የሰው ታማስል” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ተስፋየ ሀገሬ ናት የሚላት የቀድሞዋ የኛም ሀገር ኤርትራ ብዙ የልማትና የብልጽግና ሥራ እንዲሠሩላት እጆቿን ዘርግታ ልጆቿን እየተማጸነች በምትገኝበት ወቅት ይህ ሰው ስለኢትዮጵያ እንዲህ መባዘኑ ይገርመኛል፡፡ ይህ ሁሉ መቸገሩ አለነገር እንዳልሆነ ደግሞ ለብዙዎቻችን የተሠወረ አይደለም፡፡ አንድ ሰው እንቅልፍ አጥቶ ማደር ያለበት ስለራሱ ጉዳይ መሆን አለበት፤ ከዚያ ውጪ ግን ያልበላውን እንደማከክ ነው፡፡

የሚያስደንቀው ደግሞ ህ ሰው እየባሰበት እንጂ እየቀነሰለት ሲሄድ አለመታየቱና ደህና የሚባሉ ኢትዮጵያውያን ሣይቀሩ የጥፋቱ ተባባሪዎች እየሆኑ መምጣታቸው ነው፡፡ “ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ” ማለት ይሄኔ ነው፡፡ ዘመነ ግርምቢጥ!
በትናንትናው የጓደኛየ የቪዲዮ ግብዣ ኦ.ኤም.ኤን(ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) የተባለ የሚዲያ አውታር ያሠራጨውን አንድ ዝግጅት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞ ወዳጄ በፈቃዱ ሞረዳ ጠያቂ ጋዜጠኛ፣ ተስፋየ ገብረባብ ተጠያቂ እንግዳ ሆነው ነበር “እንግዳ” በሚል ፕሮግራማቸው ይህን ጉደኛ ውሉደ ዲያብሎስ ያሳዩን፡፡ በፈቃዱን ሳውቀው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው፡፡ አሁን ግን ያነሰብኝ መሰለኝ – ግምቴ ትክክል ከሆነ ደግሞ በጣም ነው የማዝነውና የምጨነቀው – በተጣባን ሾተላይ እተክዛለሁ፡፡ በቃለ ምልልሱ እንደተረዳሁት ተስፋየና በፈቃዱ ቀደም ሲል ዐይጥና ድመት ነበሩ – ያ ጥሩ አልነበረም፡፡ ያስታረቃቸው ነገር ሲታይ በፈቃዱ በተወሰኑ ሰዎች ግፊት ምክንያት ዘረኛ እንዲሆን መገደዱን “የሚያበሥር” ግጥም በኢትዮጵያ ዛሬ ድረገፅ ተስፋየ አንብቦ የምኞቱን ሥኬትና የዓላማ መመሳሰል ካስተዋለ በኋላ ሁሉንም ቂሙን/ቁርሾውን እርግፍ አድርጎ በመተው በፈቃዱን ሊወደው እንደቻለ ነው፡፡ ይህ ፍሩዳዊ የምላስ ወለምታ – ኧረ ግልጽ ነው የምን ወለምታ – የሚያሳየን ተስፋየ የሚፈልገው ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ዜጋ እየተነሣ በየፈፋውና በየጢሻው በመውረድ ፍጹም ዘረኛና አንዱ ከአንዱ የማይስማማ ሌባና ፖሊስ እንዲሆን መሻቱን ለዚያ ዓላማ ሥኬትም የማይፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ነው፡፡ ይህ “የሰው ሀገር ሰው” የራሱን የማንነት ኪሣራ ችግር ሳያስወግድ በበጎች መሀል እንደገባ ተኩላ ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚጥሩ ታሪካዊ ጠላቶችን እያገለገለ የሚገኝ ሁለት አፍ እንዳለው ሠይፍና ጎራዴ ሊታይ የሚገባው መሠሪ ጠላት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አደገኛ ሰው በእንጭጩ ካልተቀጨ – አሁንና ዛሬ ‹እንጭጭ› የሚልን ቃል መጠቀም ከቻልኩ – የዞረ ድምሩ ከባድና በቀላሉም የማይፈታ ነው፡፡

ስለተስፋየ አንዲት ነገር በምሳሌ ልናገር፡፡ እንደዛሬው ሣይሆን በዱሮው ዘመን ጦጣን የሰው ልጅ ይይዛታል፡፡ ከሰው ጋር የከረመችዋን ጦጣ ዘመዶቿ ጋር እንድትቀላቀል ወደ ጫካ ቢሰዷት እርሷ ዕውቀቷ አነስተኛና ጦጥኛ በመሆኑ ልትቀላቀል ትሄዳለች፡፡ ነገር ግን በዚያን ደግ ዘመን ማኅበረጦጣ ያቺን ከሰው አምልጣ ወይም ነፃነቷን በሰዎች ይሁንታ አግኝታ የመጣች ጦጣ በቡጢና በክርን እየደለቀ ያባርራታል እንጂ አያስጠጋትም፡፡ ምክንያቱም ሰው ሰው ትሸታቸዋለችና የነሱ ቅርጽ ቢኖራትም በጠረኗ ምክንያት አያስጠጓትም፡፡ የሁለት አገር ሰው ፣ የሁለት አገር ፍጡር መሆን ዕዳ እንግዲህ እንደዚህ ነው – አጣምሞ እንዳይፈጥር ከመጸለይ ውጪ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ሁሉም በጥርጣሬ ዐይን ስለሚመለከተው የማንነት ቀውስ ውስጥ ይዘፈቅና ከሚደርስበት ሥነ ልቦናዊ ችግር የተነሣ የወንጀለኝነትን ባሕርይ በቀላሉ ይላበሳል፡፡ ከዚያም የራሱ ጤናማ ኅሊናና ቀና አስተሳሰብ ስለማይኖረው እንደጠፍ አህያ ያገኘው ሁሉ የፈለገውን ይጭነዋል፤ ወደፈለገውም ይልከዋል፡፡ ሲላላክም መጠነኛ መቁሽሽ ስለሚሰጠው ስለሚያገኘው ድርጎ እንጂ ስለሚሠራው ዕኩይ ተግባር ቅንጣት አይጨነቅም – የሞራልና የሃይማኖት ዕሤቶችም ስለሌሉት ሕይወቱ በብዙ መልክ የተሰነካከለ ነው፤ በመጠጥ የሚናውዝ፣ በሴሰኝነት ካገኘው ጋር የሚከንፍ፣ በቃላባይነት ሁሉንም የሚያስቄም ከንቱ ዜጋ ሆኖ ይቀራል፡፡ ይህ ዓይነት ሰው እንደነዱሽ ነው – ልክ እንደሮቦት፡፡ ይህን መሰል ሰው ወደኅሊናው በቀላሉ አይመለስም፡፡ ቢመለስም ምናልባት እንደይሁዳ ራሱን ይገድል ይሆናል እንጂ በንስሃ ታጥቦና ተጸጽቶ ጥሩ ሰው የመሆን ዕድሉ በዜሮና በአንድ የመቶኛ ስሌት ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ ይሠውር ውድ ወገኖቼ፡፡ በሀገራችን ስንትና ስንት እንደነዱሽ ቀፎ ራስ ሞልቷል መሰላችሁ! ሆዱ ከሞላ እናቱንም፣ሚስቱንም፣ ልጆቹንም ባወጡ የሚሸጥ ገነት ዘውዴንና አለምነው -ገዱ – ልደቱ አያሌውን የመሰለ ብኩን ዜጋ ሞልቷል፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ እነዚህን “ሰዎች” ሳስብ ሰው ሆኜ መፈጠሬን እጸየፋለሁ፡፡ የጠራ ድህነት ወርቅ አይደለም እንዴ እባካችሁ!
ተስፋየ አቅሉን ስቶ የሚራወጠው ኢትዮጵያውያንን ለማደባደብ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የነበፈቃዱ ዓላማ ግን ብዙም አልገባኝም፡፡ “ያልወለድኩት ልጅ ቢለኝ አባባ፣ አፌን አለው ዳባ ዳባ” ይባላል፡፡ ዛሬ ከመሬት ተነስቶ ተስፋየን “ኦሮሞ ነህ” ማለት መንስኤው ግልጽ ቢሆንም ውጤቱን ግን ማጤን ያስፈልግ ነበር፡፡ ተስፋዬ ለዓላማው ሥኬት ካዋጣው ልክ እንደወያኔ የማይሆነውና የማያደርገው ነገር የለም፡፡ የማርስና የቬኑስ ዜጋ ነህ ቢሉትም በደስታ ይቀበላል – እንዲህ ዓይነቱ ነገር በጣም ይስማማዋል(የቬኑስ ዜጋ እንኳን አሁንም ነው – ቬነስ ከወሲብ ጋር እንደምትገናኝ አስቡልኝ፤ ቬኔሪያል ዲዚዝ … ምናምን ከዚያ የመጣ ነው ይባላል፤ የሼክስፒርን ምናባዊ ፍጡር ሸፍጠኛውን ሻይሎክም (በቬኑሱ ነጋዴ ተውኔት) አስታውሱ)፡፡ ይህ ዓይነቱ “ማዕረግ” ለስንኩል ዓላማው ትልቅ እገዛ ያደርግለታል፡፡ ብዙም ባልተማረው ማኅበረሰባችን ውስጥ እንደዚህ ዓይነት የጭቡ ሥራ ምን ዓይነት ዳፋ ሊያስከትል እንደሚችል የቲያትሩ ደራሲያን ሊያስቡበት በተገባ ነበር፡፡ የሚያጣላ አላጣንም፡፡ የብሔር ማንነት ካባ ሳይደረብለት የሚያቆራቁሰን ሞልቶ ሳለ ይህን አሸባሪ ሰው – ይህን ተስፈንጣሪ ወጪት ሰባሪ – ይህን የአእምሮ በሽተኛ ሰው “ኦሮሞ ነህ” ማለት ትርጉምም ስሜትም የሚሰጥ አይደለም፡፡ ቀን ሲያልፍ የሚያስተዛዝብና እሳት የማያጫጭር፣ የማያቀባብርም አጉል ድርጊት መሥራት ሞኝነት ነው፡፡

በፈቃዱ ሞረዳም ትልቅ ሰው ነው፡፡ በጣም የማከብረውና በጦማር ጋዜጣው ስለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ብዙ የደከመ ሰው ነው፡፡ ጉድና ጅራት እንዲሉ ሆኖ አሁን በማንኛውም ምክንያት ይሁን ወደታች ወርዶ ፈፋ ውስጥ ተወሽቆ ከሆነ ከምር አዝናለሁ፡፡ “የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ደጅ ታዬ” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ወደላይ መሄድ ቢያቅት እንኳን ባሉበት መቆየትም ትልቅ ጠጋ ነው፡፡ ሰዎች ሰዎችን ለማሳሳት ሆን ብለውም ሆነ ሳያውቁ አንዳንድ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ እነሱን በጭፍን ከተከተልን ገደል እንገባለን፡፡ እርጥቡን ከደረቅ እየለየን በአስተውሎት ከተራመድን ግን ጊዜ ይፍጅ እንጂ የተሳሳተን ለማረምና ወደ ፍጹም ሰውነት ለመቅረብ ይቻለናል – ፍጹም መሆን በሒሣባዊ ትወራ ይጠጌ አይነኬ ቢሆንም፡፡ ታጥቦ ጭቃ መሆን በታሪክም ይሁን በትውልድ ራስን ዝቅ ያደርጋል፡፡ የበላሁትን ቁርስ ያህል የማውቀው ፍቄ እንዲህ ሆኖ ከሆነ ለማመን ብቸገርም እንደሚመለስ ግን ተስፋ አለኝ፡፡ እርግጥ ነው – ተስፋ መቁረጥ ብዙ ዕዳ ውስጥ እንደሚከት አላጣውም – ቢሆንም ፍቄን በዚህ ጠርጥሬው አላውቅም፡፡ በሥነ ግጥሙ እንደተረዳሁት “በነሱ ግፊት እኔም ዘሬን አሽትቼ ወደዘሬ ተቀላቀልኩ” የሚለው አስተሳሰብ ደግሞ አይሠራም፡፡ እንደተስፋየ አጠራር ኢትዮ-አማሮች የሚባሉት “አክራሪዎች” የፍቄን ጽኑ አቋም አናግተውት ከሆነ ስህተቱ አሁንም ከፍቄ ራስ አይወርድም፤ እንዲያ ከሆነ ዱሮም ፍቄ ባላመነበት ኢትዮጵያዊነት ይዳክር ነበር ማለት ነውና፡፡ ለመሆኑ እነሱ እነማን ናቸው? ስንትስ ናቸው? እነሱ ዘረኛ ቢሆኑ እኛስ ስህተትን በስህተት ልናስተካክል ይገባናል ወይ? የምወደው ፍቄ ያስብበት፡፡ ይህን የምለው በተመለከትኩት ቃለ ምልልስ በግልጽ ሣይሆን በ“ሦስተኛው ዐይኔ” አማካይነት የተገነዘብኩት አንዳች ነገር ስላለኝ ነው፡፡ ግጥሚቱ ቀላል መልእክት አይደለም የታቀፈችው፡፡ “ዘረኛ ሆነው ዘረኛ አደረጉኝ” ትላለችና፡፡

የሁለቱ ሰዎች መታረቅ ደስ ይለኛል፡፡ የታረቁት በፀረ-ኢትዮጵያዊነት የዓላማ ቁርኝት ከሆነ ግን ዕርቃቸው አሳሳቢ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሀገራችን ችግር የዘር አይደለም፡፡ ችግራችን የዴሞክራሲ ዕጦት ነው፤ የመልካም አስተዳደር ዕጦት ነው፤ የተማረና የተመራመረ ዜጋ ሥልጣኑን ያለመያዝና ሕዝባዊ ወደሆነ የዕድገትና ብልጽና አቅጣጫ ያለመግባት ችግር ነው ለዘመናት የተጠናወተን፤ የማይምነት መንሠራፋት ነው አበሳችን፤ የሆዳምነት መንገሥ ነው ችግራችን፤ የራስ ወዳድነት መንፈስ የሃይማኖት ያህል መስፋፋት ነው ራስ ምታታችን፤ በሙስናና በጉቦ መበስበስ ነው ናላ የሚያዞር ማኅበራዊ ነቀርሳችን፡፡ ዘረኝነቱ ጎልቶ የታየው ካለፉት 24 ዓመታት ወዲህ እንጂ ቀደም ሲል ይህን ያህል አሳሳቢ ችግር አልነበረም፡፡ ያገኛትን ትንሽ ቀዳዳ ተጠቅሞ ጎጃሜ ጎጃሜን ዌም ጎንደሬ ጎንደሬን ቢቀጥር፣ ሐረርም ሐረሬን ወለጋም ጊምቢንና ነቀምቴን ይስብ ነበር፡፡ ሁሉም በየፊናው የፈለገውንና የመሰለውን ያደርግ ነበር እንጂ አንድ ዘውግ ተለይቶ የሚወቀስበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡ ይልቁንስ ፈታ እንድትሉ አንድ ቀልድ ቢጠየ ላስታውሳችሁ ከፈለጋችሁ፡- አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጄኔራል ወታደር ለመሆን ያመለከቱ ተመዝጋቢ ወጣቶችን በተርታ አሰልፈው የቅጥር ፎርም ለማስሞላት ወደግቢ ያስገባሉ አሉ፡፡ የሚያስገቡት ታዲያ ኦሮሞ ኦሮሞውን እየመረጡ ነው አሉ፡፡ ስማቸውን ሲጠይቁ ታዲያ ተሰላፊው ስሙን “ደቻሳ” ሲል ጄኔራሉ “ግባ”፣ “ጉርሜሣ” ሲል “ግባ”፣ “ፈይሣ” ሲል “ግባ”፣ “መልካሣ” ሲል “ግባ”፣ “ድንቄሳ” ሲል “ግባ” … “ዓለማየሁ” ሲል “ውጣ”፣ “ስንሻው” ሲል “ውጣ”፣ “ደምመላሽ” ሲል “ውጣ” … እያሉ ሲያስገቡና ሲያስወጡ የታዘበ አንድ “ተንኮለኛ” አማራ እውነተኛ ስሙን ትቶ “እኔሳ” ሲል “ግባ” አሉት እየተባለ በጨዋታ መልክ ሲወራ ሰምቻለሁ፡፡ ነገሩ እንዳልኳችሁ ጨዋታ ነው፡፡ ግን እሳት በሌለበት ጪስ የለምና ይህ ዓይነቱ የዘርና የቋንቋ ልዩነት አልነበረም ብሎ መካድ ከእውነት መራቅ ነው፡፡ ይህን ነገር ታዲያ ሙሉ በሙሉ በአማራ ላይ ብቻ ማላከክ ትልቅ ነውረኝነት ነው፡፡ ሁሉም ያደርገው ነበር፡፡ ሁሉም ተሰዳድቧል፤ ሁሉም ተፈቃቅሯል፤ ሁሉም ተጎሻምጧል፤ ሁሉም በጋብቻ ተሳስሯል፤ ሁሉም አማራ ሆኗል፤ ሁሉም ትግሬ ሆኗል፤ ሁሉም ኦሮሞ ሆኗል፤ በጥቅሉ ሁሉም ሁሉንም ሆኗል፡፡ የትኛው ከየትኛው ይበልጥ ተሰድቧል ወይም ተበድሏል ብሎ ለመፍረድ ደግሞ መሥፈሪያ ቁና ወይም መለኪያ ሚዛን ያስፈልጋል፡፡ ያን ለማድረግ ደግሞ አስፈላጊነቱ አይታየኝም፡፡ ወደፊት መሄድ እየተቻለ ጉድጓድ መቆፈርና ስላለፈ ታሪክ መነታረክ ለምን አስፈለገ? “በቅሎ አባትሽ ማነው” ስትባል “እናቴ ፈረስ ነች” ያለችውን መለሳዊ ያልተገናኝቶ መልስ እናስታውስና ይልቁናስ የሚያዋጣን ነገር ወደኋላ መሮጥ ሣይሆን ወደፊት መገስገስ ነው፡፡ በዱሮ ታሪክ ማላዘን ሥራ-ፈትነት ይመስለናል፡፡ ሥንፍናና ድንቁርናም ነው፡፡ ከዘመን ጋር ለመራመድ ያለመቻል የአስተሳሰብና የአመለካከት ደካማነትም ነው፡፡

ተስፋየ እንደትልቅ ችግር ያነሳውና እርሱ መፍትሔ እንደሰጠው የጠቀሰው በእስካሁን የኢትዮጵያ ልቦለዶች ውስጥ አንድም የኦሮሞ ገጸ ባሕርይ አለመኖሩ ነው፡፡ እዚህ ላይ ከማስገረምም አልፎ አስቆኛል፡፡ በቡርቃ ዝምታና በሌሎች የዐዞ ዕንባ አጉራፊ ድርሰቶቹ የፈጠረውን ክፍተት ይበልጥ ያሰፋ መስሎት ይህን ቢልም ለዚህ ድምዳሜ ያበቃውን የጥናት ውጤት ግን አልገለጸም፡፡ በብዙ ሺዎች የሚገመቱትን የኢትዮጵያ ልቦለዶች ሁሉንም አንብቦ እንዲህ ሊል እንደማይችል መቼም ግልጽ ነው፡፡ ደግሞም ደራሲያን የኦሮሞ ስም እንዳይጠቀሙ የከለከለ አንድም የቀድሞ መንግሥት አላውቅም፡፡ ይህ ወዘና የሌለው ጠብ-ጫሪ ሃሳቡ ብቻ ይህን ተስፋየ የሚባልን ጋኔን ለማውገዝና አክ እንትፍ ብሎ ለመጣል በቂ ነው፡፡

በዱሮ ጊዜ እኔም ነበርኩ፡፡ ስምን በሚመለከት ከመንግሥት ጋር ምንም ትስስር በሌለው ሁኔታ ኅብረተሰቡ ራሱ በልማድ የሚተገብረው የስም አወጣጥ ሂደት ነበር፡፡ የኔ የአክስቴ ልጅ ለምሣሌ ከአማራው አካባቢ ስትመጣ የነበራት እገሊት የሚባል ስም አዲስ አበባ ላይ ስለሚያስቅባት ለውጣለች – ትሠራ የነበረችውም ቡና ቤት ነው ፤ የብዙዎች አማሮች ሴቶች የመጨረሻ መዳረሻ ሴተኛ አዳሪነት ነበርና፡፡ ያኔ አማራ መሆን የተለዬ ጥቅም አያስገኝም ነበር፤ እኔ ራሴ የአማራ ዝርያ እንዳለብኝ የተረዳሁት ብዙ ዘግይቼ በ83ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ቢሆንም የስም ለውጥን በተመለከተ እኔ ራሴ ከመጀመሪያ ስሜ አንዷን ሆሄ ከግዕዙ ወደ ራብዕ ፊደል በገዛ ሥልጣኔ ለውጫታለሁ – ዘመናዊ ለመባል፡፡ እነሸንተሞ፣ እነየዝና፣ እነጓንጉል፣ እነ አዝብጤ፣ እነአንጓች፣ እነጠጂቱ፣ እነወርቅያንጥፉ፣ እነግምብወግሽ፣ እነጉማታ፣ እነባንችይርጉ፣ እነታንጉት፣ እነጉዝጉዝ፣ እነጣፈጡ፣ እነማንጠግቦሽ … ስንቱን ጠቅሼው… እነዚህ አማሮች ሁሉ አዲስ አበባ ሲገቡ ስማቸውን ለመለወጥ ይገደዱ ነበር – “ዝናር ባንገቴ”ና “ዱቤ ክልክል ነው” የሚያስብልባቸውን የአንገትና የፊት ንቅሳታቸውን ለማጥፋት ስንቶች አማራ ሴቶች ገላቸውን በማስፈቅፈቅ መከራቸውን ያዩ ነበር፡፡ ስማቸውንና የፊት ገጽታቸውን እንደዘመኑ ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም እየታከቱ የሚገኙት አዛኝ ቅቤ አንጓቾቹ እነተስፋየ እንደሚሉት መንግሥታዊ ተፅዕኖ ኖሮ ሣይሆን ማኅበረሰቡ ራሱ ስለሚስቅባቸው ክፉኛ ይሳቀቁ ነበር፡፡ መንግሥትማ እንዴት ስምን ቀይሩ ሊል ይችላል? ኦሮሞና አማራው አጤ ምኒልክ፣ ጉራጌ፣ አማራ፣ የመኑና… ኦሮሞው አጤ ኃይለ ሥላሴ፣ አማራና ኦሮሞው መንግሥቱ ኃ/ማርያም፣ ተጋሩ አኅዋትና ፍስሐ ደስታና ጄኔራል አማን አንዶም፣ … በምን ድፍረታቸው ዜጎችን ከዚህ ወደዚያ ወይም ከዚያ ወደዚህ ስማችሁን ቀይሩ ሊሉ ይችላሉ? አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ ነው ነገሩ፡፡ ኤዲያ! ምን ዓይነት ጊዜ ላይ ደረስን ጎበዝ፡፡

ከዚህ መሠረታዊ ጭብጥ አንጻር የወለጋው ሰርቤሳ አዲስ አበባ ሲገባ ወይም የአርሲዋ ጫልቱ ናዝሬት ስትደርስ ኤርምያስና ሉሊት ብለው ስማቸውን ቢቀይሩ ተወቃሹ ማን ነው? ዕቁብ ያልበላን ሰው፣ ዕቁብ ስለመኖሩም የማያውቅን ሰው “የበላኸውን ዕቁብ ውለዳት!” ብለው በማይገባው ነገር ቢከሱትና ቢያደነቁሩት ምን ዋጋ አለው? ፍርድ ከራስ ነውና አማራ ያልሆናችሁ ሰዎች በተለይ ፍረዱኝ፡፡ የዚህን የተስፋየ ገብረባብ ሥውር ተልእኮ ደግሞ አስተውሉልኝ፡፡ ጊዜው የፈቀደው ፋሽን ሆኖ እንጂ ይህ የፈረደበት አማራ ያመጣው ፈሊጥ ሆኖ አልነበረም – አማራ እንደአማራ ሣይሆን በስሙ የነገዱና አሁንም ድረስ ሊነግዱበት የሚቋምጡ ጥቂት ቆሻሻ ዜጎች የሉም ለማለት እንዳልፈለግሁ ግን ተረዱልኝ፤ ክፋትና ደግነት በብሔረሰብና በብሔር የሚገደብ አይደለም፡፡ ደግነቱ “ሥራ ለሠሪው እሾ ላጣሪው” እንዲሉ ሁሉም ክፉዎች ዜጎች በጊዜያቸው የሥራቸውን ያገኛሉ – እንደመለስ ዜናዊና መሰል የከይሲው ልጆች፡፡ እነተስፋየ ተሟጋችና ተከላካይ የለውም ብለው በወደቀ ግንድ ላይ ምሣር ለመቀብቀብ ሌት ከቀን የሚተጉት ዘመናቸው የሰጣቸው ሰይጣናዊ ኃላፊነት በመሆኑ ሕዝብን መከፋፈልና ማበጣበጥ ከዚያም የተላኩበትን መሠሪ ተልእኮ ሲፈጽሙ ከሀገራችን ግልጽና ድብቅ ጠላቶች የሚሠፈርላቸውን ድርጎ መቀበል ዓይነተኛ ሙያቸው ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህ አፈንጋጮች ፀሐያቸው መጥለቋ አይቀርም – የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ደህና የነበርን ሰዎች ግን ከተስፋ መቁረጥ ተቆጥበን ታሪክ የሚያሳየንን ተዓምር በትግስት እንጠብቅ፡፡ ቀኑ ደርሷል፡፡ የነፃነትን መባቻ ቀን የሚያውቅ አንድዬ ብቻ ቢሆንም ቀኒቱ መቅረቧን የምንገነዘብባቸው ብዙ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡

ሰማይ ክፉኛ ሲጠቋቁር፣ ደመናው ሲከብድ፣ ጭቆናውና እንግልቱ፣ ስደቱና ሰቆቃው ሲበረታ የቀኑን መቅረብ መገመት እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሰማይ ጭጋግ መልበስ ጀምሯል፡፡ ተራሮች ደም ቋጥረዋል፡፡ ሸለቆዎች አንዳች ነገር ሊያፈነዱ አቆብቁበዋል፡፡ ወንዞችና ሐይቆች አኩርፈዋል፡፡ … እንደቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ልበልና ልጨርስ – “የቆምን የሚመስለን ይበልጥ እንጠንቀቅ፤ የተቀመጠውን የሚያሳስበው መውደቅ የለምና፡፡” ለማንኛውም ልብ ይስጠን፡፡ እያለንም ሞተንም መኖር እንድንችል ለሚያደርገን አኩሪ ተግባር እንጂ እያለንም ሞተንም የሞት ሞት እንድንሞት ለሚያደርገን አስነዋሪ ድርጊት እንዳንጋለጥ ተግተን እንጸልይ፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

መማር እንችላለን ወይ? አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

ከ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ጀምሮ፤ ለመብት፣ ለነፃነትና በሰላም ሠርቶ ለመኖር ያለው ትግል፤ ሳያርፍ በተከታታይ አሁንም እየተካሄደ ነው። በነዚህ ባለፉት ፵ ዓመታት፤ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤ በትግሉ ከሕዝብ ጎን ተሰልፈው ሕይወታቸውን ሠጥተዋል። ቆራጥ የሕዝብ ጠበቃዎች ወጥተዋል፤ ሕይወታቸውን ላመኑበት ዓላማ በቆራጥነት በመሥጠት በጀግንነት ተቆጥረዋል። ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቷል። በግለሰብ ደረጃ፤ አጥንት የሚሰብሩ፣ ደም የሚነውጡ፣ ልብ የሚነኩ፣ አንጀት የሚያንሰፈስፉ፣ ጀግንነት የተሞላባቸው ተግባራት ተከናውነዋል። ድርጅቶች ተነስተዋል፣ ወድቀዋል። በድርጅቶች ደረጃ፤ ሕዝባዊ ጉዳዮችን መልክ ባለው መንገድ አመቻችተው ባደባባይ አውጥተዋቸዋል። አባሎቻቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለውበታል። መሪዎቻቸው ከፍተኛ መሯሯጥን የኑሯቸው ማዕከል አድርገው መርተውበታል። በወቅቱ በተደረጉት ክንውኖች ላይ ጽሑፍት ጎርፈውባቸዋል። ግጥሞች ተደርሰውባቸዋል። መጽሐፍት ታትመውባቸዋል።

አሁንም እንድትናንቱ ትግሉ ቀጥሏል። አሁንም የነበሩት ጥያቄዎች ባሉበት ቆመዋል። አሁንም መብት፣ የሀገር ሰውነትና በሰላም ሠርቶ መኖር ማዕከላዊ ጥያቄዎች ናቸው። ለምን ወደፊት መሄድ አልተቻለም? ለምን ትግሉ ባህልና ቋሚ ሆኖ አብሮን ይኖራል? ለዚህ መልስ መሥጠት ቀላል አይደለም። በአንድነት፤ በሀገር ደረጃ፤ እስካሁ ካደረግነው ትግል ምን ትምህርት እናገኛለን? የሚለውን በመፈተሽ፤ የመጀመሪያውን ወደ ስኬት ለመሄድ የሚደረግ እርምጃ፤ መራመድ እንችላለን። ይህ የግድ መደረግ አለበት። ባንድ ጽሑፍ፣ ባንድ ውይይት፣ ባንድ ትዕይንተ ሕዝብ፣ ባንድ ምሽት፣ ባንድ ግጥም አይከናወንም። ካለፈው ካልተማርን፤ ያለፈውን ባለፈው መንገድ መድገማችን አያጠራጥርም። ለዚህም ይኼው ፵ ዓመት ባስቆጠረውና እየቀጠለ ባለው ትግላችን፤ እያስመሰከርነው ነው። የሚቀጥለው እንዲስተካከል፤ ያለፈው መመርመር፤ በጎና በጎ ያልሆኑ ጎኖቹ ተለይተው መውጣት፤ አለባቸው። እናም ለኛ ትምህርቱ ቢያንስ አሁን መጀመር አለበት። እስኪ እኔም፤ ለዚህ ከፍተኛ ትኩረት ተሠጥቶት፤ በብዙዎች ብዙ መጻፍ ባለበት ጉዳይ ላይ፤ በኔ አመለካከት ምን ነበርና ምን ትምህርት እንወስዳለን የሚለውን ልነካካ።

የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት የተከሰተው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች በመድረክ ላይ በገሃድ ባልታዩበትና በአንድነት ተሰባስቦ የመታገል ልምዱ ባልዳበረበት ወቅት ነበር። በርግጥ የተማሪ ማኅበሩ፣ የአርሶ አደሮች በየቦታቸው በተደጋጋሚ ያደረጉት እንቅስቃሴ፣ አነስተኛ የነበረው የሠራተኛው ክፍል መነሳሳት፤ ለዚህ የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ያለጥርጥር መሠረቱ ነበር። ትልቁ ክፍተት የነበረው፤ ሀገራዊ ራዕይ ይዞ፣ ታዋቂነትን አንግቦ፣ መዋቅር ዘርጎቶ፣ ልምድና ዝግጅትን አከማችቶ፣ በሕዝቡ ዘንድ መርኀ-ግብሩን አሰምቶ፣ በቦታው የነበረውን ሕዝባዊ መነሳሳት መሪ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖሩ ነው። እናም ትክክለኛ ሕዝባዊ ጥያቄዎች የትግሉን አየር ሞልተው በተመሙበት ወቅት፤ የሕዝቡን መነሳሳት ቀዳዳ ተጠቅመው፤ ሥልጣን ወዳድ ወጣት መኮንኖች፤ ሕዝቡን አግልለው፣ ትግሉን አኮላሽተው፣ ሀገር ወዳድ ተማሪውን ፈጅተው፣ ሀገራችንን ደም በደም ለቃልቀው፣ የደም ጥማታቸውን ካረኩ በኋላ፤ በወራዳውና ሰው በላ አረመኔ መሪያቸው፤ በመንግሥቱ ኃይለማርያም አማካኝነት፤ ለአሁኖቹ ተረኛ ተባዮች አስረከቡን። በዚህ ደርጋማ መንግሥት ዘመን ትግሉ ምን መልክ ያዘ? በዚህ ወቅት ሌሎች ምን ያደርጉ ነበር? ምን እንገነዘባለን ነው ከወቅቱ የምናገው ትምህርት።

በወቅቱ ዋነኛ ተጫዋቾች ከነበሩት የትግል ድርጅቶች መካከል፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ )፣ የመላ ኢትዮጵያዊያን ሶሺያሊስት ንቅናቄ ( መኢሶን )፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ( ኢዲዩ )፣ ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ ( ተሓኤ – ጀብሃ )፣ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ( ሕግሓኤ – ሸዓቢያ )፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ( ኦነግ )፣ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ )፣ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ( ኦብነግ )፤ ነበሩበት። የኤርትራ ታጋይ ድርጅቶችን በነበሩበትና ባሉበት እተዋቸዋለሁ። ቀሪ ነፃ አውጪ ግንባሮችን ደግሞ፤ – ኦነግ፣ ትነግ፣ ኦብነግ – ነፃ ለመውጣት ያደረጉት ትግል ነበርና፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ልተቻቸውና ትግላቸውን ልመረምር መረጃውም ሆነ የሞራል ፍቃዱ የለኝም። በርግጥ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባርን ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ ) በሚመለከት፤ ብዙ የምለው አለኝ። ለምን? የሚለው ጥያቄ ከተነሳ፤ ከነፃ አውጪነቱ ወጥቶ ኢትዮጵያን በሙሉ ወሮ በአምባገነንነት እየገዛ ነውና!

በወቅቱ የነበሩት ድርጅቶች፤ ሲነሱ ሁሉም ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ መብት፣ ሕዝባዊ ተሳትፎ፣ እኩልነት በማለት ነበር። የትግል ዓላማቸው፣ ግባቸውና ዘዴያቸው ምን ነበር? ለምን አልተሳካላቸውም? እኒህ ናቸው በአንድነት በሀገራዊ መልኩ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች። ጎልቶ በትግል መድረኩ ላይ ከፍተኛ ሚና በተጫወተውና በመጠኑም ቢሆን አውቀዋለሁ በምለው በኢሕአፓ ልጀምር።

ኢሕአፓ፤ በተማሪው ትግል ዋናውን ሚና ይጫወቱ የነበሩ ወጣቶች፣ በተማሪ ትግሉ መሪና አስተባባሪ የነበሩ ወጣቶች፤ በተለይም በውጭ ሀገር የነበሩ ታጋይ ተማሪዎችና በሠራተኛው ክፍልም የሠራተኛውን እንቅስቃሴ ይመሩና ያቀናጁ የነበሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያቋቋሙት ፓርቲ ነበር። በትምህርት ዓለም ውስጥ ያጠኑትን የዓለም የፖለቲካ ሂደትና የተገነዘቡትን የፖለቲካ አሰላለፍ በመመርመር፤ በወቅቱ በነበረው የሶስተኛው ዓለም የነፃነት ንቅናቄና በሶቪየት ኅብረት የቅኝ ግዛቶች ድጋፍ በመመሰጥ፤ የሶሺያሊዝም አቀንቃኝነቱን ወስደው፤ ኮሚኒዝም ከነበርንበት አዘቅት የሚያወጣ መፍትሔ ብለን በመውሰድ፤ ትግሉን የሶሺያሊስት ንቅናቄ አድርገን ተነሳን። በወቅቱ የተነሱት ጉዳዮች፤ ማለትም የዴሞክራሲ መብቶች አለመከበር፣ የደሃ ልጅ የትምህርት ገበታ ዕድሉ መነፈጉ፣ ሕክምና ወደ ገጠር አለመዛመቱ፣ የሴቶች በእኩልነት በኅብረተሰቡ አለመገኘት፣ መሬት በጥቂት የመሬት ባለቤቶች ተይዞ ጢሰኛው ባላባቱ በፈቀደለትና በፈቀደው መንገድ የሚነዳው እስረኛ መሆኑ፣ የመሬቱ ባላባት የሆነው የገዥው መደብ አባልና በመሬቱ የሚለፋው ጢሰኛ፤ የትውልድ ሀረጋቸው አንድ አለመሆኑና ቋንቋቸው የተለያየ መሆኑ በሀገሪቱ ያስከተለው የመበላለጥ ልዩነት፣ የሃይማኖቶች በእኩልነት አለመመዘን፣ የሠራተኛው ክፍል በሕግ የሚተዳደርበት ትክክለኛ አሠራር አለመኖሩ፣ የግብር አሰባሰቡ አርሶ አደሩን መበደሉ፤ እኒህ ሁሉ ትክክለኛ ጥያቄዎች ነበሩ። እኒህን በማንሳትና ኮምኒዝምን በማወጅ መካከል የነበሩትን ደረጃዎች በሽምጥጥ በማለፍ የተደረገው ጉዞ፤ ተሰናከለ።

በአንጻሩ ደግሞ፤ ይህ በፖለቲካ ትግል ሂደቱ የተፈጠረው የኢሕአፓ ፓርቲ፤ የሚመረኮዝበት ኢትዮጵያዊ ታሪኩም ሆነ ልምዱ ስላልነበረው፤ መነሻና መድረሻ አድርጎ የወሰደው የሌሎች ሀገር ተመክሮዎችን ነበር። እናም፤ በወቅቱ በሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመረኮዘ መፍትሔ ሳይሆን፤ ሌሎች ያራምዱት የነበረውን የሶሽያሊስት መርህ ተጠቅሞ፤ ከሀገራችን ጋር ባልተቀናጀ መንገድ ለመተግበር ተነሳ። የድርጅቱ ድክመት፤ ፍላጎቱና ጥረቱ ሳይሆን፤ የተጨባጭ ሁኔታውና ያደረገው ጥረት አለመጣጣም ነው። ፍጹም ኋላቀር በሆነች ሀገራችንና የላበደሩ ቁጥር ከዚህ ግባ በማይባልበት ደረጃ በነበረበት ወቅት፤ የሶሻሊዝምን ሥርዓት ለማንገሥ የተነሳው ኢሕአፓ፤ መሠረቱና ዕድገቱ በወጣት የከተማ ተማሪው ላይ ነበር። ይህ ክፍል በቆራጥነት ሕይወቱን ለትግሉ ሠጠ። ደርግ ደግሞ አረመኔነት በተሞላ አሰቃቂ መንገድ ይኼን ወጣት በላው። የዚህ ፓርቲያችን ተመክሮ ባጭሩ እንዲህ ነበር።

በወቅቱ በቦታው ሊያሳድገው የሚችለውን ኢትዮጵያዊ ሂደት ሳይከተል፤ በፍላጎቱ ላይ ብቻ ተመስርቶ ያደረገው ግስጋሴ፤ ውስን ሆኖ ቀረ። የድርጅት መሪዎች ዋና ተግባር፤ ወቅታዊ ለሆነው ጉዳይ ወቅታዊ የሆነ መልስ አዘጋጅተው፤ ተከታዮቻቸውን መምራት ነው። ለነበረው የፖለቲካ ጉዳይ፤ በኢሕአፓ አመራር የተሠጠው ትንታኔና መፍትሔ፤ ደረጃውን የጠበቀና ወቅታዊ አልነበረም። በርግጥ የደርግ በዚህ ድርጅት ላይ የተለየ ትኩረት ማድረጉና የህወሓት ሆን ብሎ ይኼን ድርጅት ለማጥፋት ያደረገው ጥረት ቀላል አልነበረም። ድርጅቱ፤ ዓላማው ላለመሳካቱ ምክንያት ፍለጋ ወደ ውጪ መመልከት የለበትም፤ ዋናው ምክንያት ከውስጥ ነበር። ወሳኝ የነበረው ውስጣዊ ማንነቱ ነበር። የመርኅ መሠረቱና የአመራሩ ችሎታ በቦታው አልተገኙም። እናም ድርጅቱ ሳይሳካለት ቀረ።
የመላ ኢትዮጵያዊያን ሶሺያሊስት ንቅናቄ ( መኢሶን ) እንደ ኢሕአፓ ከተማሪው እንቅስቃሴ የበቀለ ንቅናቄ ነበር። በዚያ ውስጥ ግን የሥልጣን ጥማቱ ያናወዛቸው ግለሰቦች ተሰግስገውበት ስለነበር፤ በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት፤ ተሽቀዳድመው ቤተ መንግሥት በመግባት፤ የደርግ አገልጋይ ሆኑ። ደርግን ተጠቅመን እንነግሣለን ሲሉ፤ ደርግ እንሱን የኢሕአፓ መግደያ መሣሪያ አድርጎ፤ የተማሪውን መከፋፈያ አድርጎ፤ የደሙ መጥረጊያ ጨርቅ አድርጎ ቀደማቸውና፤ ሰለባቸው። ከመኢሶን ከዚህ የበለጠ የምንማረው ያለ አይመስለኝም።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ( ኢዴኅ – ኢዲዩ ) የፖለቲካ መርኀ ግብሩ ዴሞክራሲያዊ እያለ ቢያትትም፤ ከፖለቲካ መስመር ይልቅ፤ ፀረ-ወታደር በመሆን የድሮውን ለመመለስ በችኮላ የተቋቋመ ድርጅት ነበር። በርግጥ የድሮውን የወደዱና የወታደሩን ያለቦታው ዙፋኑ ላይ መቀመጥ ያልተቀበሉ፤ ጄኖራሎች፣ ሀገረ ገዥዎች፣ መሳፍንታትና አምባሳደሮች በችኮላ ተቀላቅለውታል። ከዚያ ያለፈ ግን መርኀ-ግብሩን ተረድተውና ለዓላማው በመቆም የተሰለፉ የነበሩ አይመስለኝም። ባጭር ጊዜ ለነበረው እድገታቸው ተመጣጣኝ አመራር ሠጪ አካልና ማዕከላዊ አሰራር ስላልነበራቸው፤ ከደርግም ሆነ ከሌሎች ታጋይ ድርጅቶች በገጠማቸው ተቃውሞ ተመናምነው ጠፉ። ከዚህ በላይ ስለ ኢዴኅ ማለት አልችልም።
የቀረው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ ) ነው። ከአፄ ዮሐንስና ከትግራይ መሳፍንት ጋር የተያያዘው የትግራይ ወጣቶች የነፃነት ግንባር፤ ምንም እንኳ ከተማሪ ማኅበሩ የመጡ መሪዎችና ተከታዮች ቢኖሩበትም፤ ከጠባብ የትግራይ መሳፍንት ገዥነት ጋር የተያያዘ የነፃነት ትግል ነበር። ስለዚህ ይህን ግንባር ከተማሪ ትግሉ ጋር ማዛመድ ስህተት ነው። የዚህ ነፃ አውጪ ግንባር መሠረቱ የትግራይ ሪፑብሊክን መመሥረትና የአማራ ገዥነትን ማጣፋት ነው። በምንም መንገድ ከማርክሲዝምና ከላብ አደሩ አምባገነንነት ጋር ግንኙነት የለውም። ይህ ትግራይን ነፃ አድርጎ የራሷ ሀገር የመፍጠር ጉዳይ፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ፣ ከሀገር አቀፉ እንቅስቃሴ የተለየና በተቃዋሚነት የቆመ ነበር። ስለዚህም፤ ህወሓት በጠላትነት የፈረጃቸው፤ ደርግን ብቻ ሳይሆን፤ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )ን፣ ኢሕአፓን እና አማራን ነበር፤ አሁንም ነው። የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )ን ስላጠፋው ከቁጥር አስወጥቶታል። ኢሕአፓን በሚችለው መንገድ ወግቶታል። አማራውን አሁንም በማጥፋት ላይ ነው። የዚህ ድርጅት ተግባር ሕዝባዊም፤ ኢትዮጵያዊም አይደለም። ከዚህ የምንማረው ቢኖር፤ ይህ ድርጅት መጥፋት እንዳለበትና ይህም ባስቸኳይ መሆን እንዳለበት ነው።

ለመንደርደሪያ ያህል ይኼን ካስቀመጥኩ በኋላ፤ አጠቃላይ በሆነ መልኩ ወደፊት የሚመለከት መፍትሔ በመጠቆም፤ ጽሑፌን አስራለሁ። የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ቱ ህዝባዊ እንቅስቃሴ መሠረታዊ ጥያቄዎች፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ፣ መሬት ለአራሹ ይሁን፣ የሴቶች እኩልነት ይከበር፣ ሃይማኖት የግል ስለሆነ፤ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይግባ፣ ሁሉንም ሃይማኖቶች እኩል ይመልከት፣ ሕክምና በገጠር ይስፋፋ፣ የድሃ ልጅ ይማር፣ ለተራበው ወገናችን እርዳታ ይደረግለት፣ የገዥዎች ያላአግባብ በሀብት ማላገጥ ይቁም፣ የኑሮ ውድነት ይስተካከል፣ ለሠራተኛው ትክክለኛ ሕግ ወጥቶ በሕገ-ደንብ ይስተዳደርና የመሳሰሉት ነበሩ። እኒህ ሀገራዊ ጥያቄዎች ነበሩ። አሁንም አሉ። አሁንም ሀገራዊ ጥያቄዎች ናቸው። በአንድነት ተነስተን በአንድነት ለማስከበር የምንቆምላቸው ነበሩ። ያኔ አልተደረገም። አሁንም እየተደረገ አይደለም።

የያዝነው ትግል ውጤቱ እንዲቃና፤ እስካሁን ከተደረገው ትግል ተምረን፤ ትግሉን በተስተካከለ መንገድ ማካሄድ አለብን። ጥያቄዎቹ ቀለም ይቀቡና ሌላ መልክ ይያዙ እንጂ እኒሁ ናቸው። ተጎጅው ደግሞ ያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ትግሉ የሕዝቡ ነውና የሕዝቡን ባለቤትነትና የበላይነት መቀበል ዋነኛ መሠረታዊ ግዴታ ነው። ቀጥሎ ደግሞ፤ ያለውን የሀገራችንን የፖለቲካ እውነታ በትክክል ተንትኖ፤ ለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሀቅ ትክክለኛ መፍትሔ ማቅረቡ ነው። በኔ እምነት፤ በኢትዮጵያ ያለው ወራሪ መንግሥት ነው። ይኼን ወራሪ መንግሥት መታገል ያለብን፤ ጥቂት መሠረታዊ የሆኑ ሀገራዊ የትግል ዕሴቶችን በማውጣት፤ አንድ የኢትዮጵያዊያን ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሥርተን በመነሳት ነው። መታገያ ዕሴቶቻችን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት መከበሩ፣ የኢትዮጵያ ሀገራችን ዳር ደንበር መጠበቁ ለሙ መሬቷ ለኢትዮጵያዊያን መዋሉ፣ የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ መብት መከበሩ፣ እና የሕግ የበላይነት መረጋገጡ ናቸው። በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያለነው በአንድነት በነዚህ ሀገራዊ አንገብጋቢ ዕሴቶቻችን ዙርያ በመሰባሰብ መነሳት አለብን።

ከነዚህ አንገብጋቢ ዕሴቶቻችን ውጪ ያለው ጉዳይ፤ በመሠረቱ የሕዝቡን የትግሉ ባለቤትነትና የበላይነት እስከተቀበልን ድረስ፤ በሂደት ሕዝቡ በትግሉ ስለሚያነሳቸውና መፍትሔ ስለሚሠጣቸው፤ ላሁኑ በቆይታ ይታያሉ። እናም በነዚህ ዙርያ ተጠማጥመን እንቅስቃሴውን በአንድነት በአንድ ድርጅት ከውጪ ያለነው እናካሂደው። ካለፈው እንማርና፤ ለዚሁ አንድ ጉዳይ፤ ባንድ ተሰልፈን፤ ቆመን እንቆጠር። መማር ማለት፤ ከትናንት ተሽሎ መገኘት ማለት ነው። መማር ማለት ባሉበት መርገጥ ማለት አይደለም። መማር ማለት ማደግ ማለት ነው።


የማለዳ ወግ …ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት ! ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* ይድረስ ለክቡር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም …
* ኢህአዴግን እንዴት እንምረጥ ?

ትናንት በሁከት ፣ ዛሬ በመፈራረስ በሚመስል አደገኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችው የመን የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ድምጽ ከነኡኡታው ሰላም ይነሳል ። በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ከኢራቅና ሶርያ አይ ኤስ አይ ኤስ ISIS ጽንፈኞች ባላነሰ ከፍ ሲል በሰብአዊው ዜጋ ፣ ዝቅ ሲል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ የውጭ ዜጎች ላይ የተጀመረው ጥቃት ሊያዩት ሊሰሙት ይከብዳል ። በሰላ ገጀራ ፣ ሰንጢ የሰው ፍጡር የመቆራረጥና ፣ በእሳት የማቃጠልን የአውሬ ተግባርን መመልከት ዘልቆ ልብን ይሰብራል ። ይህ ሁሉ ሲሆን ” መንግስት አለን !” ባዮች ኢትዮጵያውያን ፈጥኖ ደራሽ ቀርቶ ጉዳቱን አጥብቆ የተቃወመ መንግስት ባለማየታችን አዝነናል !

በአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ” ኢህአዴግን ምረጡ !” በሚል በማህበራዊ መገናኛ የፊስ ቡክ ቅስቀሳ ዘመቻዎ ባስተላለፉት መልዕክት የፈረደበት መንገድ ፣ ህንጻውንና ግድቡን በፎቶ አሸብርቀው ” እነሆ ሰርተን አሳይተናል ፣ ስራ ላይ ነን !” በማለት “የወሬ የለው ፍሬ ” በሚልና “ስራ እንጅ ወሬ አናውቅም ” የሚል አንድምታ ያለው መልዕክት አስተላልፈው ተመልክቻለሁ ። ለድርጅትዎ ቀናኤ መሆንዎን አልቃወምም ። ዳሩ ግን በስደት ህይዎቴ በድርጅትዎ የሚወከሉ ባለስልጣኖችም ሆኑ ተራ የድርጅትዎ ካድሬዎች የመንገድ ህንጻውንና ግድቡ ከእነ ተሳላጠው የሃገር እድገት እያነሱ በመጣል ከመደስኮር ፣ ለድጋፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከሚደረገው ድግስና የስብሰባ ጥሪ ባሻገር ለዜጋው መብት ማስከበር ቆመው አይቸ ፣ ሰምቸ አላውቅም ። እናም ሀገር የማለት ትርጉሙ ቅጥ አንባሩ ይጠፋብኛል !

በማዲባ ምድር በደቡብ አፍሪካ በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍ እንደ ዜጋ አሞኛል ። ድርጊቱን በአደባባይ የሚያወግዝልን መንግስት ማጣታችን አውጥቸ አውርጀ ለዜጎች መብት ማስጠበቅ ተግቶ የማላውቀው ኢህአዴግን ብመርጥ ሀገሬ ህዝቤ ምን እንደሚሆኑ ማሰቡ አልተሳነኝም ። …እናም መንግስትዎ የምመርጠው ደግሞ እንደ ዜጋ የስደተኛ መብታችን ስላስጠበቀልን እንጅ ግዑዙን መንገድ ስለሰራ ፣ ህንጻውን ስላቆመና ግድቡ ስለገደበልኝ መሆን አለበትን ? ስል ከራሴ የወጣ ፈታኝ ጥያቄ አንገላታኝ… እናም ትናንተም ሆነ ዛሬ ኢህአዴግ ለዜጎች መብት እስካልተጋ ድረስ እንዴት ኢህአዴግን እንምረጠው ? አልኩ ቢቸግረኝ …

የሆነው እና እየሆነ ያለው ቢያከፋኝና ፣ ቢያስጨንቅ ፣ ቢያስጠብበኝ ወቀሳ ቢጢ ልልክልዎ ነሸጠኝ … ! ብዕሩን በቀለም ነከሬና ወረቀቱን አቅርቤ የታወከው ውስጤ እርሙን ያወጣ ዘንድ እንደለመድኩት በማለዳ ወጌ ብሶቴን መተንፈሱን መረጥኩ … ንዴት ብስጭቴ አይሏልና ክብርዎን እንዳልነካ በመጠንቀቅ እራሴን አረጋግቸ ስሞታ ፣ ቅያሞቴን አሳምሬ በማውቀው የአረብ ሀገሩ ስደት በጨረፍታ ልጀምረው ፈቀድኩ … !

ከሁሉ በማስቀደም ከ20 ዓመታት ወዲህ ዘንድሮ ወግ ደርሶን ባለሙያ ወደ አካባቢው መላኩን ባልክድም ፣ ከዚህ ቀደም በአረብ ሃገራት በዜጎች መብት ጥበቃ የገጠመን የባለሙያ ተወካይና የመንግስት ትኩረት እጦት ፈተና ግን እንዲህ በአጭሩ የሚገለጽ አለመሆኑን ከጅመሩ አስረግጨ ልነግርዎ ደስ ይለኛል ! …ግን በአጭሩ ልሞክረው …

እርስዎ የጤና ጥበቃ ሃላፊ ከመሆንዎ በፊት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ላለፉት 20 አመታት በአረብ ሀገር የመ ብት አስጠባቂ ተቆርቋሪ አጥተን ስለመናቅ መዋረዳችን ፣ ስለመገፋት መገደላችን ፣ ስለ ስደቱ አስከፊነት የሚደ ርሰውን በደል በከፊልም ቢሆን በማቀርባቸው መጣጥፎች ባለፈ በአንጋፋው የጀርመን ራዲዮ የዜጎችን ይዞታ ላልሰሜ ለማሰማት ሞክሬያለሁና ” ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራ ል ” የምል ዜጋ አይደለሁም ! እኔን ሆንኩ መሰሎቸ የዜጎች መብት ይከበር ፣ የመብት ጥበቃ ይደረግልን እያልን ድምጻ ችን ያሰማን ቢሆንም ሰሚ በማጣታችን ግፉ ከጠበቅነው በላይ ሆኖ አሁን ድረስ ቀጥሏል …

የእኛ እውነት የእናንተ ስህተት …
====================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
እርስዎ የተኳቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት መጥተው የኮንትራት ስራ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበል ሳውዲዎች ፍላጎት ማሳየታቸ ውን ለሳውዲ ታዋቂ ጋዜጦች መግለጫ ሰጥተው እንደ ሄዱ ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና ጥናት የኮንትራት ስራውን ሲጀመር ከቀሩት ወገኖቸ ጋር በመሆን ህጋዊ የኮንትራት የሁለትዮሽ ውል ሳይደረግ ዜጎችን መላኩ አደጋ አለው በሚል የተቃውሞ ድምጻችን ስናሰማ የስምምነት ህጋዊ ውሉን መፈራረምና አማራጩ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ነው ብንልም ሰሚ አላገኘንም ። በአጭር ጊዜ ህጋዊ ውል በሌለው ስምምነት በኮንትራት ስራ ስም ዜጎች ይላኩ ጀመር ። ከጅምሩ እስከ አሁን ያለውን አሰቃቂ የእህቶቻችን የመከራ ዋይታ መስማት ጀመርን ። እርስዎ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ያለምንም ጥናትና ቅድመ ዝግጅት የተጀመረውን በድርጊቱ ሁሉ ከታመሙት መካከል የምወዳት ሃገሬ እጓለማውታ ስደተኛ አንዱ እኔ ነኝ !

ምንም እንኳን ዛሬ መንግስትዎ ዜጎችን ያለ ሁለትዮሽ ውል ወደ አረብ ሀገራት ለስራ መላኩ ስህተት እንደነበር ማመኑን ሳስበው እታመማለሁ። ዛሬ እውነቱ በሂደት ፍን ትው ብሎ ወጥቶ እኛ የሰጠነው መረጃ ትክክል እናንተ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በኮንትራት ስራ ስም ያለ ውል መላካ ችሁ ስህተት መሆኑን ብታምኑም የዜጎች ህይዎት የተገበረበት የአካሄድ ስህተት አንኳ ይቅርታ አልጠየቃችሁም። ይባስ ብላችሁ አሁንም ባለ ድርሻ አካላት በግልጽ ያልመከሩበት አዲስ ህግ ተረቆ ለትግበራ ጥድፊያ ላይ መሆናችሁ ለዜጎች ታስቦ ነው አልልም ። ያኔ እንደ ዜጋ አግብቶን ስንናገር ባለመሰማታችን እናንተ ተሳሳታችሁ እነደነበር ዛሬ በአደባባይ አመናችሁ ፣ ዛሬም እንደ ዜጋ አግብቶን ረቂቅ ህጉን ባለድርሻ ዜጎች ይወያ ዩበት ስንል ሰሚ አጥተን ” ግመሏ ትሄዳለች ውሻዎች ይጮሃሉ! ” አይነት የተለመደ አካሄድ የተያዘ ለመሆኑ የሚያሳብቁ ኩነቶች ታጅበን እየተጓዝን እንገኛለን ! ከአንድ አመት በፊት ” ስደት ይብቃ !” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየ ም አዳራሽ ከአፍ እስከ ደገፉ የሞሉ ታዋቂ ሰዎችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልብ አሸብሮ ያስለቀሰው ግፍ እንዲፈጸም ምክንያቱ ስህተታችሁ አልነበረምን? ዛሬስ እንዴት ያ ሁኔታ ባለበት እንዲቀጥል ትፈቅዳላችሁ ? ለምንስ አትሰሙም ?

በደቡብ አፍሪካስ ለኢትዮጵያውያን የት አላችሁ?
==============================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ…

ወገን በደቡብ አፍሪካ ለሳምንት በአጣብቂኝ ውስጥ ወድቆ ከአይሲኤስ በማይተናነሱ የደቡብ አፍሪካ አውሬዎ ች በኢትዮጵያውያን ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የት አላችሁ ? ኢት ዮጵያውያን ስደተኞች ሃብት ንብረታቸውን እየተቀሙ ፣ እየተ ዘረፉ ሲሳደዱ ፣ ሲወገሩ ፣ በእሳት ሲነዱና ጭፍጨፋ ሲፈጸምባቸው ማትረፍ ባትችሉም እንዴት ድርጊቱን ማውገ ዝ ተሳናችሁ ? ዜጎች መደፈር የአገር ህመም አልሆን ብሎ ፣ የሀገራቱ ሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊው ግንኙነት እንዳይ ናጋ ይሆን ? እውነት እልዎታለሁ … እርስዎ በከፍተኛ ኃላ ፊነት ያስቀመጠዎ መንግስት ፣ እርስዎም እንደ ውጭ ጉዳይ ኃላፊነትዎና እንደ ዜጋ የዜጎችን መብት ለማስከበር ተቃውሞ ድመወጻችሁን ለአለም አላሰማችሁም ። ይህም ስታደርጉ ትልቁን ሃላፊነት አልተወጣችሁምና አዝኛለሁ !

ከአፖርታይድ የነጻነት እለህ አስጨራሽ ትግል በደ ገፍናት ፣ ለመሪዋ ለማንዴላ መሸሸጊያ ፣ ለታጋይ ፋኖዎቿ መጠጊያና ስንቅ ትጥቅ ያቀበለችው ሃገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ወሮበሎች ተደፍረናል ። በህግና በስርአት በምትመራ በምትባለው ስልጡን አፍሪካዊት ሀገር በደቡብ አፍሪካ ፣ በአለማችን የነጻነት ታጋይ በክቡር ኔልሰን ማን ዴላ ምድር ፣ ነጻነቷን ከወራሪ አስከብራ የኖረችው ሀገር የኢትዮጵያ ልጆች ግፍ ተፈጽሞብናል ። በዘር ጥላቻ የወገን ደም ረክሶ በሰላ ገጀራ አካላቸው ሲጎመድ ፣ ሲቃጠሉን ሲገደሉ እያያችሁ ዝምታን መምረጣችሁ እኔ በግል በመን ግስት ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎኛል ። አፋጣኝ የወ ገን አለኝታነትን አለማሳየታችሁ እኔን ብቻ ሳይሆን ሀገር ወዳዱን ደጋፊዎችዎን ሁሉ ማስቆጣቱን ማምሻውንበፌስ ቡክ በለቀ ቁት ብጣሽ መረጃ ስር የተጻፈውን የሰላ ሂስ ማንበቡ ብቻ በቂ ይመስለኛል ።

ክቡር ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ ዜጎ ቻችን ላይ አፋጣኝ እርምጃ አለመውሰዳችሁ በመስሪያ ቤትዎም ሆነ በመንግስት ተስፋ ያልቆረጥን የነበርንን ጥቂት ” ገለልተኛ ነን!” የምንል ወገኖችን ሞራል እንኳ አልጠበቃችሁትም ። ከእኛ አልፎ ድርጅትዎን ሲደግፉ ያው ግዑዙን መንገድ ፣ ህንጻውንና ግድቡን እያነሱ እየጣሉ “ተንፈላሰሳችሁበት ” የሚሉንን ዲሞክራሲና እድገቱን ከመጥቀስ ፈቀቅ የማይሉት ሳይቀር በስራችሁ አልተደሰቱም። የሚሰደደውን ህልቀ መሳፍርት ዜጋ ድህነት ፣ የኑሮ ውድነትና የአውራ ፖርቲ ፖለቲካ ትንኮሳ ምክንያት አስረግጠው ለማስረዳት በቂ ምክንያት የሚያጥራቸውን ከነፍሳቸው ጋር የታረቁ ደጋፊዎቻችሁን ተቀይመዋችኋል። እነሱን ለማጽናናት ሲባል ቢያንስ
” … የኢፌድሬ መንግስት ና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጎቹ የሚፈጸመውን አሰቃቂ በደል በመቃዎም የደቡብ አፍሪካን አንባሳደር በአስቸኳ ይ ጠርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲዎስድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ ! ይህ ካልሆነ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እስከመቋረጥ የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ያወጣው መግለጫ አስታወቀ !”
ተብሎ በቴሌቪዥንና በራሳችሁ ራዲዮ መስማቱን ናፍ ቀነው የውሃ ሽታ ሆኖ ሳንሰማው ቀረን … እርስዎም ቢሆን መረጃው እንደ ደረሰዎ በትኩሱ በለመድነው ዘመነኛ መረ ጃ ቅበላዎ የረባ መረጃ ስላልሰጡን የለውጥ ተስፋ ያለን ሁሉ ምኞት ከንቱ መሆኑን አሳይቶ የማይጨበጠውን ተስፋ አጨናግፎታል !

እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው …በጥሞና ይስሙኝ !
==========================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
ክቡርነትዎም ሆኑ የሚመለከታችሁ እንዲህ እንደ ተዋረድን ፣ እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመብንን ግፍ የሚመለከት ከእርስዎና ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው ከብዙ በጥቂቱ ሃሳቤ የሚከተለው ነውና በጥሞና ስሙኝ !

1ኛ / የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመባቸው ላለው ግፍና በደል ለድርድር እንደማይቀርብ በማስገንዘብ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በአደባባይ ከዚያም አልፎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠት አለበት ።

2ኛ / ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገችው ሃገር የኢትዮጵያ ዜጎች በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመባ ቸውን ግፍ ህዝብን ያስከፋ ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በሀገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር በግልጽ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፍቀድ ።

3ኛ / ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉትን የደቡብ አፍሪካ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትን ከፍተኛ ኃላፊዎች በመጥራት በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው በደል የሁለቱን ሃገር ግንኙነት እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚያስከትል ከበድ ማስጠንቀቂያ መስጠት ።

4ኛ / በህግና ስርአት በፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማ ትተዳደራለች በምትባለው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ግፍ በዜጎቻችን መፈጸሙን በአጽንኦት ለማስረዳት በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በእርስዎ የሚመራ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄድ ይገባል ።

5ኛ / ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ለጉዳታቸውና ለተዘረፉት ንብረት ካሳ መጠየቅ ።

6ኛ / ወደ ሀገር መመለስ ለሚፈልጉ ተመላሽ ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ፣ ወደ ሶስተኛ ሀገር መሔድ ለሚፈልጉ መብታቸውን ማክበር ይገባል ።

በደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ዜጎች ብርታቱነን ይሰጣችሁ !
የሞቱትን ነፍስ ይማር ከማለት ባለፈ መሄድም ሆነ ክብራች ን መመለስ ባይቻልም ፣ ሀገርና መንግስት አለን ለማለት አፋጣኝ እርምጃ ከመንግስትዎና ከመስሪያ ቤትዎ እንጠብቃለን !

ሀገር ማለት ህዝቡ ነው !

ከሰላምታ ጋር !

አክባሪዎ

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓም

ወያኔዎች የተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ላይሆኑ እንደሚችሉ ገለጹ –ግርማ ካሳ

$
0
0

- እነ BBC፣ CNN የተገደሉት ኢትዮጵያዉያን ናቸው ሲሉ ወያኔዎች ማረጋገጫ የለንም አሉ።

- ኢቢሲ የሊቢያውን ጭፍጨፋ የዘገበው እንደተራ ዜና በሶስተኝንት ነው።

አል ጃዚራ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያንን አይሰስ፣ በሊቢያ ኢሰብአዊና ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እንዳረዳቸው ዘግቧል። CNN “ISIS operatives have beheaded two groups of prisoners, believed to be Ethiopian Christians, in Libya” ሲል፣ BBC ደግሞ “ISIS releases new ‘killing’ video of Ethiopian Christians” በማለት የተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነው የገለጹት።

የወያኔ ቲቪ (ኢቢሲ) በተገደሉ ወገኖቻችን ዙሪያ አጭር ዘገባ አቅርባለች። ሬድዋን ሁሴን የተባለውን ግለሰብን በመጥቀስ የተገደሉት ኢትዮጵያዉያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የለም የሚል መልእክት ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረው። ሕዝቡ “እግዚአ” እንዳይል፣ እንዳይጸልይ፣ ለምን እነዚህ ሰዎች ግድያው የተፈጸመው በኢትዮጵያዉያን ላይ እንደሆነ ለመሸፈን እንደፈልጉ አይገባኝም። እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያዊያን ላይ ምን አይነት ችግር ነው ያላቸው ? በደቡብ አፍሪካም ቢያንስ አለም ሁሉ ያወቀው የሶስት ኢትዮጵያዉያን አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ተልኮ ሳለ፣ በደቡብ አፍሪካ የወያኔ አምባሳደር አንድ ሰው ብቻ ነው የሞተው ብሎ ነው መግለጫ ያወጣው። የአፍሪካ አገሮች ሁሉ የዙማ መንግስት ካይ ጠንካራ አቋም ሲወስዱ ፣ እነ ኃይለማሪያ ደሳለኝ ግን የኢትዮጵያ ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ መሪ ነበር የመሰሉት።

አሁን ደግሞ እነ BBC ፣ እነ CNN ፣ አል ጃዚራ ..ያሉ ትላልቅ የሜዲያ ተቋማት፣ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ናቸው የተገደሉት ሲሉ፣ የወያኔ ቴለቭዥኝ፣ በግብጽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዉስጥ የተኮለኮሉ ካድሬ ሰራተኞችን በመጥቀስ፣ የተገደሉት ኢትዮያዉያን ላይሆኑ እንደሚችሉ ሲነግረን መስማቱ ድጋሚ እንደመታረድ ነው። ለመሆኑ እነ ሬዳውን ሊቢያ ሄደው DNA ሊያጣሩ ነው ?

ሌላው ደግሞ በጣም ያስገረመኝ፣ ያስደነገጠኝና ዉስጤን ያቆሰለው ነገር ቢኖር፣ ዜናው በኢቲቪ/ኢቢሲ የተሰጠው ሽፋን ነው። ሶስተኛ ዜና ሆኖ ነው የቀረበው። አስቡት ሰበር ዜና፣ ብሬኪንግ ኒዉስ ሆኖ ነበር መቅረብ የነበረበት። ግን እንደዝይ አይዴ የቀረበው። ሰዓት ተጠብቆ በሁለት ሰዓት ዜና ነው የተነገረው። መጀመሪያ ስለ ኮሪያ ባለሃብቶች ዘገቡ፣ ከዚያም በአዲስ አበባ ተደረገ ስላሉት የጣና ጉባኤ ዘገቡ፣ በሶስተኛ ደረጃ ነው ከሁለት ደቂቃ በማይበልጥ ስለ ሊቢያው ጭፍጨፋ ደግሞ ትንሽ የተነፈሱት።

ዜናው እንደተሰማ ፕሬዘዳንት ሙላቱ ከኮሪያ መመለስ ነበረባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቭዝን ቀርበው ንግግር ማድረግ ነበረበት። ሕዝቡን የሚያረጋጋ መልእክት መተላለፍ ነበረበት። ህዝቡ ጸሎት እንዲያደርግ፣ ባንዲራ ለሳምንት እንዲዘቀዘቅ፣ በሊቢያ ያሉ ወገኖቻችን ከፈለጋችሁ ተመለሱ ሳይሆን፣ ፈልገው እንዲመለሱ ማግባባትና ማሳመን የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ከወያኔዎች ፣ ትንሽ ቢሆን ሃዘኔታ፣ ሴንሲቲቪቲ የሚባል ንገር አላየንም። አቦ እነዚህ ሰዎች ሰይጣኖች ናቸው። ይግረማቸው ብለው እንደው “ዜጎቿን ከሽብርና ከአሸባሪዎች ጥቃት ለመታደግ የሚያስችላትን አስፈላጊውይን ዝግጁነት ተግባራዊ በማድረግ የሃገሩቱን ሰላምን መረጋጋት እንዲሁም ልማት በአስተማማኝ ለማረጋገጥ ችላለች” እያሉም ተመጻድቀዉብናል። ምን አለ አሁን እንኳ ስለልማት እያወሩ ባያሰለቹን ?

እንግዲህ ወገኖቼ፣ አስቡት ኢትዮጵያውያንን ከሽብር ጠብቀናል እያሉ ነው የሚመጻደቁት። እንኳን ወገኖቻችን ከሽብር ሊጠብቁ፣ እንኳን ወገኖቻችን ሊሰበስቡ፣ እንኳን ወገኖቻችን ለማዳን ሊተጉ፣ ወገኖቻችን ፓስፖርት ሲፈለግ፣ የተለያዩ ሰርቪስ ሲሹ እነርሱን የሚያንገላቱ ናቸው። በአገር ቤት ደግሞ ሰላማዊ ዜጎችን ሽብርተኛ እያሉ የሚያሸብሩ ወንበዴዎች ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን ከአገር የሚሰደዱት በነርሱ አገዛዝ ምክንያት ነው። ኢትዮጵያ ለነርሱና ለዘመዶቻቸው፣ ለጥቂቶች ገነት፣ ለአብዛኛው ህዝብ ግን የምድር ሲኦል በመሆኗ ነው። በስደት ያሉትም ወደ አገራቸው መመለስ የማይፈልጉት፣ ኢትዮጵያ ምን እንደሚጠበቃቸው ስለሚያወቁ ነው። ሕግ የለም። አቤት የሚባልበት ቦታ የለም። ፍርድ ቤት የለም። የብር የመግዛት አቅም ላይ ወጧቷል። ያልታወቀበት ረሃብ፣ ዉስጥ ዉስጡን በጠኔ ሰዉን እየገደለ ነው። ወያኔ ካልተኮነ ሥራ ማግኘት የለም። ኢትዮጵያዉያን በአገራቸው ባሪያና የተጨቆኑ ስለሆኑ፣ የዚህ ዘር፣ የዚያ ዘር እየተባሉ በአገራቸው ስለሚፈናቀሉ፣ የተሻለ ነገር ካገኘን ብለው ነው አገር ጥለው የሚሄዱት። በደቡብ አፍሪካም በሊቢያም ለተፈጠረው፣ በዋናነት፣ ኢትዮጵያውያን በገፍ ከአገር እንዲወጡ የሚያስገድድ ፖለቲካን የሚያራምደው የወያኔ ስርዓት ነው።

እንግዲህ በዚህ ሳምንት የተፈጠሩት፣ ልብን የሚሰብሩ፣ ምናልባትም ለብዙ ሳምንታት በሐዘን አንገታችንን የሚያስደፉ ክስተቶች ወደፊት እንዳይከሰቱ ማሰብና መጸለይ አለብን። አሜሪካኖች አልካይዳ አይርፕላኖች ጠልፎ በአንድ ቀን በጥቂትን ደቂቃዎች ዉስጥ ከሶስት ሺህ በላይ ሰው ሲጨፈጭጭፍባቸው፣ አዘኑ። ግን እዚያ ላይ አላቆመም። ዴሞክራት፣ ሬፓብሊከን ሳይባባሉ እንደ ሕዝብ የአሜሪካን ጠላቶችን ለመፋለም ተነሱ። እኛም እነዚህ ትላልቅ ሐዘኖች ዉስጣችንን ቢሰብሩትም፣ እንደ ሕዝብ ሊያሰባስቡን ይገባል። እንደትሰበርን፣ እንዳዘንን መቅረት የለብንም። አገራችን ዉስጥም እንገደላለን። እንታሰራን። እንደበደባለን። በዉጭ አገርም እንገደላለን። አገር ቤት ያለውን ድህነት፣ በሽታ፣ ሽብር፣ ጭቆናና ግፍ ለመሸሽ ስደት መፍትሄ የማይሆንበት ጊዜ እየመጣ ነው። በመሆኑም ሁላችንም አገራችንን ለስደትና ለመከራ እየዳረገ ያለዉን ዘረኛ ስርዓት እንዲለወጥ ከመቼዉም ጊዜ በላይ መትጋት አለብን። አገር እያለን የምንዋረድበት ምንም ምክንያት የለም።
ከሁሉም በለይ ደግሞ እንደ ህዝብ ንሰሐ እንግባ። እግዚ እንበል። የተጠላን እንታረቅ። በጥንቆላና በመሳሰሉት የተጠመድን ወደ እግዚብሄር ፊታችንን እንመልስ። እግዚአብሄር ከፍርሃት፣ ከራስ ወዳድነት፣ ከጥላቻ፣ ከዘረኝነት፣ ከሙስና ፣ ከጭካኔ ነጻ ወጥተን እንደ ህዝብ እጅ ለእጅ የምንያያዝ፣ አንዳችን ለአንዳችን የምናስብ፣ አንዳችን ሲያመን ሌሎቻችንም የሚያመን፣ የወደቀን ረግጠን የምናልፍ ሳይሆን የወደቀን የምናነሳ ህዝብ ያድርገን !!!!!

አንዳንድ የወያኔ ካድሬዎች ሊከራከሩ የሚሞክሩ አሉ። ከላይ የጻፍኩት ፈጥሬ ሳይሆን ትክክለኛ እንደሆነ ያወቁ ዘንድ የኢቢሲ/ኢቲቪ ሊንክ ከታች አስቀምጫለሁ። ለማወዳደር ይቻል ዘንድ እነ BBC ፣ እነ CNN የዘገቡትን እንዲሁ፡

http://www.ethiopian.tv/ethiopian-news-sunday-april-19-2015/

http://www.bbc.com/news/world-middle-east-32373166

http://www.cnn.com/2015/04/19/africa/libya-isis-executions-ethiopian-christians/

በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር ክንፉ አሰፋ

$
0
0

“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ…ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር… በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።

አስሩን ህጻናት በአንድ መኪና(ትራክ) ውጽጥ አጭቆ ነበር ወደ ሞሉ የወሰዳቸው። የያዘው መኪና ከአራት ሰው በላይ መጫን አይችልም። እመንገድ ላይ ፖሊስ እንዳያያቸው “ሁላችሁም ጎንበስ በሉ።” ይላቸው እንደነበርም ህጻናቱ አጫውተውኛል።
እነዚህ ሕጻናት ሀገሪቱ የምትመካባቸው የነገ ሳይንቲስቶችዋ ናቸው። ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ከፍተኛ፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ታዳጊዎች። በነዚህ ታዳጊዎች እና በወላጆቻቸው ላይ የደረሰው በደል እጅግ ብዙ ነው። ታሪኩ አንድ አሳዛኝ ፊልም ይወጣዋል። ወላጆቹ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ደውለው ይህ በደል ለህዝብ ይፋ እንዲሆንላቸው ቢጠይቁም የራዲዮ ጣብያው ጉዳዩን ባልታወቀ ምክንያት አፍኖታል። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጻፉት የአቤቱታ ደብዳቤም ምላሽ ተነፍገዋል። ጉዳዩ ለሚመለከተው ክፍል ሁሉ አቤት ብለዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
ይህንን በደል የፈጸመው ግለሰብ ከአዲስ አበባ እንዲሸሽ ተደርጎ በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ በአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ቤት መሽጓል። በአሜሪካ የመኖርያ ፈቃድ የለውም። የባንክ ሂሳብ ግን አውጥቶ ገንዘቡን እዚያው አከማችቷል።
የትንግርታዊው “ዶክተር” ሳሙኤል ዘሚካኤልን የሽወዳ ስልት ገና ከአእምሯችን ሳናወጣ፤ ሌሎች የእሱ ደቀ መዝሙሮች ብቅ እያሉ ነው። ስልታቸውን ይቀይሩ እንጂ የሁሉም ቁጭ በሉዎች አላማ አንድ ነው – ህዝብን ማታለል። አንዳንዶቹ ለሽወዳቸው ረቀቅ ያለ ዘዴ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ ዘርካካ በመሆን የዋሁን ህዝብ በዘረፋ ተያይዘውታል።
ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አጭበርባሪ የረቀቀ ስልት ባይጠቀምም ለሌብነቱ የተለየ መንገድ ይዞ ነው ብቅ ያለው። ሰናክሪም መኮንን ይባላል። ይህ ሰው የገዥው ፓርቲ አባል በመሆኑ ለዝርፊያው ምቹ መንገድ እንደፈጠረለት ይነገራል።
የሰናክሬም መኮንን አንድ አዲስ ፕሮጀክት ነደፈ። ከመላው ትምህርት ቤቶች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን አወዳድሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ታዳጊዎችን አሜሪካ በመውሰድ ሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ማስጎብኘት። ከዚህም ሌላ የላቀ ውጤት ላመጡ ህጻናት የላፕቶፕ እና የአይፓድ ልዩ ሽልማት እሰጣለሁ ብሎ ቃል ይገባል። በየትምህርት ቤቱ እየዞረ የትምህርት ቤቶቹን እና ልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም አላማውን አስፈጸመ። ወጪውን ሁሉ የሚሸፍኑ ስፖንሰሮች አገኘ። አዲካ ትራቭል፣ ኦሮሚያ ባንክ እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ የህጻናቱን ወጪ በሙሉ የሚሸፍን በቂ የሆነ ስፖንሰር ተገኘ።
ሰናክሬም የስፖንሰሩን ድጋፍ እና የአስሩን ህጻናት ፓስፖርት ይዞ አሜሪካ ኤምባሲ ለቪዛ ሄደ። በቂ የስፖንሰር ድጋፍ ስለነበረው ያለምንም ችግር የልጆቹን ቪዛ አገኘ።
ጫወታው እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው። ስፖንሰሩን እና ቪዛውን በእጁ ካስገባ በኋላ የህጻናቱን ቤተሰቦች በተናጥል እየጠራ እያንዳንዳቸው የህጻናቱን የትራንስፖርት እና የመስተንግዶ ወጪ እንዲሸፍኑ ጠየቃቸው። ሰውየው በቂ በጀት ከስፖንሰሮች እንዳገኘ በወላጆቹ ይታወቃል። በመጀመርያ የገባውን ቃል አጥፎ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ መጠየቁ ለሁሉም እንግዳ ሆነባቸው። ሁሉም አንከፍልም ሲሉ መለሱለት።
ሰናክሬም ግን አጭር መልስ ሰጣቸው። “ወጪውን የማትሸፍኑ ከሆነ እድሉል ሌሎች ልጆች እሰጠዋለሁ።” ሲል የባሰ መርዶ አመጣባቸው።
ወላጆች አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። በአንድ በኩል ልጆቻቸው ወደ ሂውስተን ለመሄድ ተነሳስተዋል። የልጆቻቸውን ስሜት መጠበቅ ግድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው እያጭበረበራቸው መሆኑን አውቀውታል። ከብዙ ማንገራገር በኋላ ግን ገሚሱ ወላጅ የአውሮፕላን ትኬት፣ የአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የመስተንግዶ እና የኮቴ ከፍሎ ልጆቹን ወደ አሜሪካ ላከ። ሰናክሬም ከውጭ ሃገር ከተቀበለው ዶላር ውጭ ወላጆቹ የከፈሉት ገንዘብ በድምሩ አንድ ሚሊዮን ብር ይጠጋል።
ይህንን ወጪ መክፈል ያየልቻሉ ህጻናትን ተሰረዙ። የነሱ እድል ሌሎች ጥሩ ውጤት የሌላቸው ግን ገንዘብ ላላቸው ወላጆች ተሸጠ። ዘረፋው በዚህ መልኩ ተፈጸመ። አስሩ ህጻናትም ወደ አሜሪካ ተጓዙ።
ወደ ዋና ድራማው ደግሞ ልውሰዳችሁ። አሜሪካ ዋሽንግተን እንደገቡ ለአንድ ቀን ብቻ በማሪዮት ሆቴል ቆይታ ያደርጋሉ። በነጋታው ሁሉም በአንድ ትራክ ተጭነው እዚህ ግባ የማይባል ማረፍያ ውስጥ በቡድን በቡድን ታጎሩ።
የጉዞው ዋና አላማ በሂውስተን የሚገኘውን የናሳ ጠፈር ምርምር ተቋም መጎብኘት ነበር። እሱን እርሱት ብሏቸዋል ሰናክሬም። ለግዜው ወላጆችን ማታለያ አስሩንም በቡድን ፎቶ አነሳቸው። የናሳን ማስክ በፎቶሾፕ እያስገባ አለበሳቸው። ናሳ የሄዱም አስመሰላቸው። ፎቶውንም በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ለጠፈው።

አሁን ልጆቹም ስለናሳው ጉዳይ አያስቡም። ከወላጆቻቸው ተነጥለው ወጥተው በአንድ ሃላፊነት በጎደለው ሰው እጅ ላይ ወድቀዋል። በአንድ ክፍል ወስጥ ተቆልፎባቸው ይውሉና ለተወሰነ ሰዓት በገበያ አዳራሽ ውስጥ ይለቀቃሉ። በአሜሪካን ሃገር በርሃብና ጥማት እየተሰቃዩ ነው። ረሃብ ጸንቶባቸው ሆስፒታልም የገቡ አሉ።
ወላጆቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ*፣ “ሰናክሬም ከእያንዳንዱ ወላጅ የአምስት ኮከብ ሆቴል ሂሳብ ተቀብሎ ሳለ ህጻናቱ ግን ተገቢውን የሆቴል አገልግሎት አላገኙም። ሴቶቹ የማይታወቁ ሰዎች ቤት እንዲያርፉ መደረጉ እና ወንዶቹ ደግሞ በቡድን በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲያድሩ አድርጓል።” ብለዋል።
ምግብን በተመለከተ ተገቢውን ምግብ ሳይመገቡ ለረሃብና ለህመም መዳረጋቸውና ከዚህም የተነሳ በምግብ ማጣት ጉዳት ሆስፒታል መግባታቸው፤ የተወሰኑት ከአቶ ሰናክሬም ተወስደው ወደ ዘመድ ቤት እንዳረፉ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል። በመጀመርያዎቹ ቀናት ማክዶናልድ እየወሰደ ይመግባቸው እንደነበር ልጆቹ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ነው የረሳቸው።
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ደግሞ እነዚህን በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በዋሽንግተን ዲሲ ለልመና መጠቀሙ ነው። “ከሄዱበት አላማ ውጪ በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በየቤተክርስትያኑ እያዞረ ‘ለችግረኛ የሚሆን’ በማለት ኩፖን በማሸጥ አሰማርቷቸውም ነበር።” ይላል ደብዳቤው። ልጆቹን በዚህ መልኩ በልመና በማሰማራት በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሰበሰበ ህጻናቱ ይናገራሉ። በተለይ ዋሽንግተን ዲሲ ያለው ወንጌላዊ ቤተ-ክርስትያን ህጻናቱ በጉባኤው ፊት ቆመው የልመናውን ኩፖን እንዲያሳዩና እንዲሸጡ አድርጓቸዋል። ይህ የሆነው የቤተ-ክርስቲያኗን ፓስተር ሃንፍሬይን በማታለል ነው።
ሕጻናቱ በዚህ መልኩ ተንገላትተው ግን ለመጡበት አላማ ምንም ነገር ሳያደርጉ ሊመለሱ ነው። በአካባቢው ያሉ የቤተሰብ አባላት አንድ ሃሳብ አመጡ። ኢትዮጵያዊው ጠረፍ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶ/ር ብሩክ ላቀውን በጉዳዩ አማከሩዋቸው። ዶ/ር ብሩክም ፈቃደኛ ሆኑ። በወላጆች ትውውቅ የመጡት እኚህ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ህጻናቱ ካረፉበት ስፍራ ድረስ በምሄድ ስለ ናሳ አስረዷቸው።
ህጻናቱም ይህችን እውቀት ይዘው፤ ናሳን በቴለቭዥን እንኳን ሳይመለከቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። የሰናክሬም የናሳ ጉዞ ፕሮጀክትም በዚህ ላይ ተጠናቀቀ። ገቢው አጓጊ ነውና ሰናክሬም አሁንም ሌላ ዙር ሊሰራ ማሰቡ አልቀረም።
የህጻናቱ ቤተሰቦች ግን በመሰባሰብ የጋራ አቋም ላይ ደርሰዋል። ያላግባብ የተወሰደባቸው ገንዘብም እንዲመለስ ጠይቀዋል። ሰናክሬም ግን ሸሽቶ አሜሪካ መሽጓል።
ይህ መረጃ እንደደረሰኝ ሰናክሬም መኮንን በኢሜል አግኝቼው ነበር። ጉዳዩን እልባት እንዲሰጥ፤ የሰዎቹንም ገንዘብ እንዲመልስ በተደጋጋሚ ጠየቅኩት። ይህ ከልሆነ ታሪኩን ለህዝብ ይፋ እንደማደርገውም ነግሬው ነበር። ይህ ጉዳይ ሜድያ ላይ ከወጣ ታዋቂ እንደሚያደርገው ተናግሮ አሾፈብኝ።
ይህንን የማደርገው ለሌሎች ወላጆች ትምህርት እንዲሆን ነው። ጉዳዩን ለበርካታ የሜዲያ አካላት ማሳወቄም ግድ ነው። ለጥንቱ ወዳጄ ሰይፉ ፋንታሁንም የህጻናቱን በደል ነግሬው ነበር። ህጻናቱን አነጋግሯቸዋል። ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚያቀርበው ነግሮኛል።

ወላጆች በጋራ በመሆን ለሚመለከተው አካል የጻፉትን አቤቱታ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።*
* http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2015/04/Letter-to-Ministery-of-Foreign-Affairs-3.pdf

ሰማዕታተ ሊቢያና የሲኖዶሱ መግለጫ በዳያቆን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡

ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?

እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?

‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?

ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡

እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡10426150_882988765098589_5828218667211786615_n

ጨለማው ሳምንት ክንፉ አሰፋ

$
0
0

ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት!

“ወንድሞቼ ያልፍልኛል ብለው ከቤት እንደወጡ እዚያው በበረሃ ቀሩ።” ትላለች እየሩሳሌም። እትብታቸው የተቀበረባትን ሃገር ለቀው ሲወጡ ጣሊያን ለመግባት ነበር ዕቅዳቸው። አውሮፓን አልመው ቀዬአቸውን ለቅቀው የወጡ እነዚህ ወጣቶች ህልማቸው እውን ሊሆን አልቻለም። ከሌሎች 28 ወገኖቻችንን ጋር ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ህይወታቸው አለፈች። ‎ISIS የተባሉ ጨካኞች ሲያርዷቸው በቪደዮ አሳዩን።

የሳምንቱ ሃዘን እጥፍ ድርብ ነው። ኢትዮጵያዊ ላይ ያነጣጠረ እስከሚመስል ድረስ ነው እየተካሄደ ያለው። ብሔራዊ መንግስት ስለሌለን ብሄራዊ ውርደታችን አላቆመም። ከ 700 በላይ ስደተኞችን ይዛ ወደ አውሮፓ ትጓዝ የነበረች ጀልባም በዚህ ሳምንት ነበር በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሰመጠችው። ቁጥሩን ለማረጋገጥ ባይቻልም፣ ከሞቱት ገሚሱ ኢትዮጵያውን እንደሆኑ ከወደ ጣልያን የሚመጣው መረጃ ይጠቁማል።

በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በቁም ሲቃጠሉ እና ሲገደሉ እያየን ነው። በተለይ ደርባን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እስካሁንዋ ደቂቃ በፍርሃት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል።

የመን ያሉ ወገኖቻችንም ምጥ ላይ ናቸው። የመን ያሉ ኢትዮጵታውያን ቁጥር ከምናስበው በላይ መሆኑ እጅግ ይረብሻል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ.ኦ..ኤም እንደሚለው ከሆነ በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር አንድ ሚልዮን ይጠጋል። ሁሉም በጭንቅ ላይ ናቸው። ያለመታደል ሆኖ የሚቆረቆርላቸው መንግስት ግን አላገኙም። ልብ በሉ ከአንድ ሚሊዮን ዜጋ፤ በስልጣን ላይ ያለው መንግስታችን 30 ዜጎቼን በጅቡቲ አድርጌ ወደ ሀገር ቤት አስገባሁ ሲል አብስሮልናል። በእርግጥ ይህ ጉዳይ በሊቢያው ክስተት ከሰጡት ምላሽ አይብስም። የ ISIS አሸባሪዎች ኢዮጵያውያንን አረድን ባሉ ግዜ “ጉዳዩን እናጣራለን” ሲሉ ነበር የቀልዱብንል። ከዚህ ድርጊት የባሰ ምን ሊመጣ ይችል ይሆን? በበረሃ የወደቀን ወገን፣ የትና በምን አግኝተው ነው የሚመረምሩት። አለሁ ባይ አካል ስለሌለን የተረሳን እና የተዋረድን ህዝቦች ነን።

እንደሌሎች ሀገሮች በአለማቀፍ መድረክ የሚከራከርልን አካል ስለሌለን የጥቃት ሰለባ እንድንሆን ተደርጓል። ሃገራችንም ጥርስ የገባች ሃገር ሆናለች።

ይህንን ስረዓት እየሸሹ እየሄዱ አውሬ የሚበላቸውና በረሃ ወድቀው የሚቀሩትን ወገኖች ቤቱ ይቁጠረው። በሳውዲ ጀምሮ የመን ተከትሎ ከዚያም በደቡብ አፍሪካ እና በሊቢያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በተለያዩ አረብ ሃገሮች በቃላት መግለጽ የማይቻል ድርጊት እየተፈጸመብን ነውና ሁላችንንም እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው።

ሰው ወድዶ አይሰደድም። ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ይሰደዳል፣ የተገፋ ህዝብ ይሰደዳል፣ ፍትህ ያጣ ህዝብ ይሰደዳል፣ የተራበ ህዝብ ይሰደዳል። ስደት እስካለ መከራውም ይኖራል።

የሃዘን ቀን ቢታወጅልንም፣ ባይታወጅልንም ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም። በዚህ ጨለማ ሳምንትም ሆነ ከዚያ በፊት በሆነው ነገር ሁሉ ልባችን ተነክቷል። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጠለቀ የሃዘን ስሜት ውስጥ ነን።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አሜሪካዊትዋ ባለስልጣን፣ ዌንዲ ሼርማን መንግስታችን ስኬትን እያስመዘገበ እንደሆነ በዚሁ ሳምንት ነበር ያበሰረችን። ዜጋው ሁሉ ተስፋ ቆርጦ እየተሰደደ በየበረሃው መውደቁን ይሆን ዌንዲ እንደ ስኬት የቆጠረችው?

የማያልፍ የለምና ይህም ጊዜ ያልፋል። እስከዚያው ግን ወዳጅ ዘመዳቸውን ያጡ ሁሉ ፈጣሪ ብርታቱን ይስጣቸው። መፍትሄው ታድያ ፍትሃዊ ስርዓትን እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። ይህ ሲሆን የስደት ምንጩ ይደርቃል።

ሐሙስ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመላው ኢትዮጵያ –ሁላችንም እንነሳ –ግርማ ካሳ

$
0
0

(ይሄን መልእክት እና ሌሎች ተመሳሳይ መልእክቶችን ያሰራጩ። ሕዝቡ መረጃ እንዲደርሰውና የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆን የድርሻዎትን ይወጡ)
ሐሙስ በመላው አገሪቷ፣ በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ደብር ብርሃን፣ ደሴ አርባ ምንጭ አዋሳ …የሥራ ማቆም አድማዎችን ያካተቱ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ። ታክሲዎች አይንቀሳቀሱም። ሰራተኞች፣ ተማሪዎች ፣ አስተማሪዎች ሐሙስ ቀን ወደ ስራችሁ እና ወደ ትምህርት ቤታችሁ እንዳትሄዱ። ሐሙስ የጸሎት ቀን ነው። ሐሙስ ድምጻችንን የምናሰማበት ቀን ነው።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የኢትዮጵያዉያንን ልብ የሰበሩ በርካታ ክስተቶች ተፈጽመዋል። በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ እልቂት ተፈጽሟል። በደቡብ አፍሪካ በሌሎች የአፍሪክ አገሮች ግፊትና ጫና ፣ የጃኮብ ዙማ መንግስት ስደተኞችን ለመጠበቅ በርካታ የጥበቃ ሃይል እያሰማራ ነው። ችግሮቹ አሁን አፍጥው ያሉ ቢሆንም፣ በአንጻራዊነት ነገሮች ትንሽ ጋብ ያሉ ይመስላል። እንደ ናይጄሪያ መንግስት ያሉ ምስጋና ይግባቸዉና።
በሊቢያ ግን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው እልቂት በሌሎችም እንዳይደገም ትልቅ ርብርብ ያስፈልጋል። እጅግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያዉያን በሊቢያ አሁንም ተደብቀው ነው ያሉት። የነርሱ ሁኔታ እጅግ በጣም ፣ በጣም አሳሳቢ ነው። ሁላችንም በየእምነት ቦታችን በጸሎት ወደ እግዚአብሄር መቅረብ አለብን። ከጭራቆቹ ጌታ ወገኖቻችን እንዲታደግ እንጸልይ። እግዚኦ እንበል።
በደቡብ አፍሪካም አሁን ጋብ ቢልም ገና የጠራ ነገር የለም። በጎሮቤት አገር ኬንያ፣ ስደተኞች ይወጡ የሚል ነገር አለ። ነገሮች ትንሽ በስደተኞች ላይ እየጠነከረ መጥቷል። የግድ ኢትዮጵያዉያን በአሁኑ ወቅት መሰባሰብና መያያዝ አለብን።
ወያኔ ሕዝቡ ሐዘኑን እንዲገልጽ፣ በደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ፣ በአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ተቃዉሞዉን እንዲያሰማ ማስተባበር ነበረበት። ሆኖም ነገሮችን መደባበቅና በወገኖቻችን ላይ የደረሰዉን ግፍ አሳንሶ ማሳየቱን ነው የመረጠው። የአለም ትላልቅ የሜዲያ ተቋማት፣ እንደ አሜሪካ ያሉ መንግስታት ፣ አይሰስ የገደለው ኢትዮጵያዉያን ክርስቲያኖችን ነው ካሉ በኋላ፣ ከበርካታ ወገኖች ከፍተኛ ዉግዘት ሲደርስበት፣ ወያኔ፣ ትላንት «ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላጣራሁም» ያለዉን ለዉጦ «አሁን ስላጣራው» በሚል የሞቶት ኢትዮጵያዉያን መሆናቸውን አምኗል። ለመለስ ዜናዊ አሥራ አምስት ቀናት በላይ የሐዘን ቀን ያወጀው ወያኔ፣ ለኢትዮጵያዊኑ ወገኖቻችን ግን 3 ቀን ብቻ የሐዘን ቀን ነው ያወጀው።
ከዝንብ ማር አይጠበቅም እንደሚባለው፣ ብዙም አራት ኪሎ ከተቀመጡት መጠበቁ ፋይዳ የለዉም። ማወቅ ያለብንን ሁላችንም አዉቀናል። እኛ ኢትዮጵያውያን፣ የሚያስብልን፣ የሚያገለግለን፣ የሚያከብረን፣ ለመብታችን የቆመ መንግስት የለንም።
ስለዚህ ኢትዮጵያዉያን ማድረግ ያለብንን በራሳችን ነው ማድረግ ያለብን። የፊታችን ሐሙስም በአገር ቤት መንግስት ያልጠራው፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉትም ለዚህ ነው። የተጠሩት እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ናቸው። ኢትዮጵያዉያን በየእምነታችን፣ በየፖለቲካ ድርጅቶቻችን፣ በየሲቪክ ማህበራችን፣ በየእድራችን፣ ለወገኖቻችን አጋርነት እናሳይ። ቢያንስ ለዜጎቻችን የሚያስብና የሚቆረቆር መንግስት ባይኖርም፣ በጭንቅ ያሉ ስደተኞች የሚወዳቸው ሕዝብ ግን እንዳለ እናሳያቸው።
ወገኖቼ አዎ በጣም አዝነናል። ዉስጣችን ትልቅ ቁስል አለ። ግን አይዞን። ከዚህ በኋላ የባሰ ነገር እንዳይፈጠር ነው መስራት ያለብን። አሁን እምባዎቻችን ጠርገን ፣ ፊታችንን ወደ ፈጣሪ አዙረን፣ መተባበር ነው ያለብን። ኢትዮጵያ ልጆቿ ከርሷ የሚሸሹ ሳይሆን የተሰደዱ የሚመለሱባትና ሌሎች ወደ እርሷ የሚሸሹ ለማድረግ ሁላችንም መነሳት አለብን። ከአሁን በኋላ ዝምታ ይብቃ!!!11169891_809271049157831_3872818494501872465_n

የምሄድበት መንገድ ትክክል ነወይ? አንድነትን ማጥበቅ በጋራ መቆም ቆም ብሎ መቃኘት መሸነፍ አይደለም። –ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

ደጋግመን መፈክር ስላሰገርንና፣ ደጋግመን በቃል ቃል ስለገባን ግባችንን በተግባር እንመታለን ማለት አይደለም፡፡ የምንጓዘው ዓላማችንን አንጥረንና አነጣጥረን መሆን አለበት፡፡ ተግባሩን እንጂ ተደጋጋሚ ወሬውን እንተው፡፡ቃል ስንገባ በስሜታዊነት አይሁን! ቃል ስንገባ በአድር-ባይነት አይሁን! ቃል ስንገባ ለይስሙላ አይሁን! ቃል ስንገባ በእርግጥ አደርገዋለሁ ወይ? ብለን ከልባችን ጠይቀን፣ በአዎንታዊነት እራሳችንን አሳምነን፣ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ቃል የምንገባበትን ጉዳይ ጠንቅቀን እንወቅ፡፡

አላዋቂ እጅ መውደቅ እርግማን ነው፡፡ ነብሴ በእጅህ ናት ብሎ የአላዋቂ ተገዢ መሆን የከፋ መርገምት ነው፡፡ አንዱ ስላረገው ብቻ ሌላው የሚከተልበት፣ እንደ መንጋ ተከታትሎ የሚነዱበት ሥርዓት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቷል፡፡ ቆም ብሎ የምሄድበት መንገድ ትክክል ነወይ? ከተለመደው መንገድ ውጪ ሌላ አማራጭ አጥቼ ነወይ? ማሰብ ያስፈልጋል ። እንደ መንጋ ተከታትሎ የሚነዱበት ሥርዓት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቷል፡፡ ለመንገኝነት አስተሳሰብ ወይም ለወረተኝነት አካሄድ ወይም እንደ አዲስ የትግል ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ መመሪያ፣ ሲወጣ እንደፋሽን መከተልና ሳይመረምሩ መቀበል፣ ከተለመደ ቆይቷል፡፡ ለመጠፋፋት ጊዜ የማይፈጅብን፤ ለመፋቀር ረዥም ዘመን የማይበቃን አያሌ ነን፡፡ ቀድሞም ሆነ ዛሬ እርስ በርስ፣ በፖለቲካ ድርጅትና ድርጅት ውስጥ ያለውን መናቆር፤ ትላንት ገዢዎች ያደርጉ ከነበረው ፍትጊያ ተነስቶ ማየት ቀላል ነው፡፡በኢትዮጵያ ወቅታዊ ምህዳሮች ውስጥ ከጉዳይ ሁሉ ቀዳሚው በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፤ በማህበራዊም መልኩ በራስ መተማመን አንድነትን ማጥበቅ በጋራ መቆም ነው፡፡

በራስ ለመተማመን ቢያንስ በሌሎች መፈራት ሳይሆን መወደድ፣ መጠርጠር ሳይሆን መከበር፤ ይቆይብኛል ብሎ መስጋት ሳይሆን ይሄድብኛል ብሎ መጨነቅ የሚፈጥር መሪ መሆንን ይጠይቃል፡፡ በራስ ለመተማመን ለሁሉም የሀገራችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መፍጨርጨር ሳይሆን ሌሎች የሚሰጧቸውን አማራጮች ለማዳመጥ መትጋትም ግድ ይላል።ይህ የሚከሰተው ከአለማወቅ ወይም ግንዛቤ ከማጣት ሊሆን ይችላል፡፡የአገሪቱ አምባገነን ገዢዎች ያሉት ሁሉ ልክ ነው ከሚል የሎሌያዊነት አመለካከት ሊሆን ይችላል፡፡ ጎረቤቴ ካደረገው ልክ ቢሆን ነው ብሎ ከማሰብም ሊሆን ይችላል፡፡ ሆነ ብሎ ስህተትም ቢሆን ልከተለውና ገደል ሲገባ ልየው ከሚል እኩይ ሀሳብም ሊሆን ይችላል፡፡ የድርጅትንም ኢ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ቆም ብሎ መቃኘትም ያስፈልጋል።መንገኝነት ወረተኝነት በራስ አለመተማመንን ይፈጥራል። #ምንሊክሳልሳዊ


የማለዳ ወግ…ሀዘን የወለደው ደካማ ስሜት ፍርሃት ! በጨለመው ሚያዝያ ፣ የጨነቀ እለት ..ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

በማለዳው አነሳሴ እንደለመድኩት በስደቱ ዙሪያ ገብ የሆነውንና እየሆነ ስላለው ልሞነጫጭር ፣ ልብተከተክ አልነበረም … ከትናንት ከትናንት በስቲያ ጠዋት ፣ረፋድና ተሲያት ፣ ምሽት ፣ በደረቁ ሌሊት እያቅበጠበጠኝ ስልኬን አንስቸ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፒሊ ወደ ማትረጋው ቢንጋዚና ሚስራታ የደዋወልኳቸውን ስልኮች ተመለከትኩ ። ከወዳጆቸ የደረሱኝን ሁለት ሶስት አድራሻዎችና እዚህ ጅዳ ያለ ሊቢያዊ ጓኛየ አድራሻቸውን አፈላልጎ የሰጠኝን ሌሎች ሰብሰብ ያሉ ወንድሞችን አግኝቻለሁና ደጋግሜ ቁጥሮችን አየኋቸው …

የሰበሰብኳቸው ስልኮችን ደጋግሜ የደወልኩባቸው ስለሆኑ መፈላለጉ ጊዜ አይወስድብኝም ፣ ከስልኬ ፊት ለፊት ተደርድረዋልና እየመራረጥኩ … እደውላለሁ … እንቅልፍ ለአመል ያህል ተኝቸ ብንን ብንን ማለቱ ቢያስቸግረኝ ይለይለት ብየ እንደ ቀደመው የማለዳ ወግ ለመጻፍ ሳይሆን ባለፉት መራራ ሁለት የሃዘን ቀናት ያነጋገርኳቸው ሊቢያ የሚገኙ እህት ወንድሞቸን ሳነጋግራቸው በመቅርጸ ድምጼ ያስቀረኋቸውን ድምጾች መልሸ መላልሸ ማደመጥ ይዣለሁ …

“ቤንጋዚ ውስጥ ነን !” ያሉኝ ሌሎች ወንድሞች ጋር ቃለ ምልልስ እያደረግኩ ከሊቢያ አውጡን የሚለውን የድረሱልን እተሰማሁ እያለ ይቆራረጥ የነበረው የስልክ መስመር እራሹን ተቋርጦብኝ ስብተከተክ ፣ ሌሎች በሊቢያ የሚገኙ እህቶችን በሌላ መስመር አገኘሁ ! የአድራሻቸውን መስመር ያገኘሁት የሆነው ያንገበገበው ከእኔ ቢጤ ቅምጥል ኩዌት ከሚገኝ ስደተኛ ወዳጀ ነው ። እንዲህ ይላል ” ሃይ ነብይ እንዴት ነህ በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አድራሻ ማግኝት የሚቻለው በምንድነው ልጆች ይፈልጋሉ ሊቢያ ያሉ …ካንፖኒ ውስጥ ነው የሚሰሩ ፣ ወደ 14 ልጆች መንቀሳቀስ መውጣት አልቻሉም ፣ ችግር በተፈጠረበር ቦታ ላይ ነው ያሉት ፣ ወደ ሀገር መግባት ይፈልጋሉ ” ከመልዕክቱ በኋላ አድራሻቸውን ላከልኝ … ሁሉንም የሰበሰብኳውን አድራሻዎች ደዋወልኩ … አንዳንዴ ስልኩ ይነሳል ፣ አንዳንዴ አይነሳም ፣ አንዳንዴ እያወራን በመካከል ይቋረጣል ፣ አንዳንዴ ከአጠገቤ ያሉትን ያህል የቀረበ ድምጽ ይሰማኛል …

ጥርት ያለው ድምጽና መልዕክቱ …
===================

ንጹህ ድምጹ ከአመታት በፊት በስራ ኮንትራት መጥተው በስራ ላይ ካሉት እህቶቸ እንደሆነ አላጣሁትም ፣ ” እባክህ ከሊቢያ ወደ ሀገራችን የሚያወጣን አካል አፈላልግልን ? ለሚዲያ ሽፋን ሳይሆን ከጭንቅ እንድንወጣ እርዳን ? ምንም ቢሆን ሀገራችን መግባት ነው የምንፈልገውና እርዳን ? የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናውን ሲናገር በዚህ ቁጥር ደውላችው ተረዱ አላለም ፣ ያሳዝናል ፣ ለማን አቤት እንበል? የምትችል ከሆነ እርዳን ? ” በሚለው ተማጽኖ ድምጻቸውና አልፎ አልፎ እኔኑ አላምነን እያሉ በምናደርገው ያልተናበብንበት ውይይት እኒሱ መሆናቸውን እለየዋለሁ !

ተቆራራጩ ድምጽና የተቆራረጠው ተስፋ …
==========================

ተቆራራጩ ድምጽ ደግሞ በሱዳን አድርገው የሰሃራን በርሃ በስቃይ ቆርጠው መጥተው ፣ ባንዷ ሁከት በማይለያት ከተማ የተኮለኮሉ ወንድሞች ናቸው ። በማይገኘው መስመር አልፊ ሳገኛቸው ስሜቴን ይፈታተኑታል ፣ የሆነውን በተባራሪ ወሬ እንጅ እንደ ትርፖሊ ነዋሪ እህቶቸ ክፉ ደጉን አላዩትም ፣ ያ መሆኑ በጀ ! …ብቻ ወደ እንሱ ተስፋ ምድር አውሮፖ ሊሄዱ አስበው ፣ በ28 ( ሰላሳ ናቸውም ይባላል) በጽነፈኛው ደዕሽ ISIS ጨካኝ አራጆች ተፈጸመ የተባለውን ግድያ ሰምተው ተደናግጠው ባንድ አሳቻ ቦታ ተደበወቀዋል ” ወደ ሰላሳ እንጠጋለን ” ብለውኛል ! የሚቀመስ ምግቡ ቀርቶ በረሃ ቆርጠው ቀዝቃዛ ውሃ ጠግበው ያልጠጡ ችግረኞች ናቸው ። የእኒህ ችግረኛ ወንድሞች ስልክ ደከም ያለች ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ይመስለኛል ውይይታችን ብዙም አይሰማም ፣ ችግሩን መገመት አያዳግትም … ብቻ ” የት እንሒድ ? ” ብለው ከሀገር ያስለቀቃቸውን ችግር ፣ ቸነፈርና ድህነት ሳይሆን የአስተዳደር በደልና ስራ አጥነት ለዚህች ቀን አደንዳደረሳቸው የቆመው ጀሮየ ሰምቷል … እኒህኞቹ ወደ ሀገር መግባት አይፈልጉም ፣ እዚያው መቆየት ደግሞ አይፈልጉም … ብቻ ምርጫቸው አለም ችግራችን ሰምቶ ወደ ሶስተኛ ሀገር ያውጣን ባዮች ናቸው ! የተቆራረጠው ተስፋ መልዕክትና ተስፋ … ሲናገሩት ያማል …

ሰማሁት … ሰማሁት ፣ ተስፋየ በተነው !
===========================

ከሞቱት ሰማዕት በላይ ውስጤን ያወከውና ልብን የሚሰብር ሆነው ካገኘኋቸው መካከል በትሪፖሊ ውስጥ በአንድ ሆስፒታል በስጋት ላይም ሆነው ስራቸውን በመስራት ላይ ያሉ 14 የሚደርሱ እህቶች ይገኙበታል ። ከመካከላቸው ያነጋገርኳቸው ከሶስት ባይበልጡም ፣ የሶስቱ ጭንቀት ገላጭ ደረቅ አስተያየት የሁሉንም ይገልጸዋል ፣ በሚወጡበት ጉዳይና ባሉበት ሁኔታ ስንወያይ አልፎ አልፎ ባንግባባም ፣ ስንለያይ ፍላጎቴን አስረድቸ ተግባብተን ነው … ” አየህ ወንድም እኛ ስለታረዱት ወንድሞቻችን የሰማነው በሚዲያ ነው ፣ ከሁለት አመት በፊት ወደ ሊቢያ ትሪፖሊ መጥተን ስራችን እየሰራን ነው ፣ ስራ ላይም ሆነ ቤት ውስጥ ሆነን ሁሌም የጥይት ድምጽ ከከተማ ውጭ ፣ በርቀት እንሰማለን … አሰሪዎቻችንን ወደ ሀገራችን ስደዱን ስንላቸው ከተማ ውስጥ ችግር የለም እያሉ ያጽናኑናል ፣ በእርግጥም እስካሁን ከስራ ቦታ ወጥተን በቅርብ ርቀት ባለው በተዘጋጀልን ቤት እናርፋለን ፣ እስካሁን ችግር የለብንም ፣ አሁን ግን የወንድሞቻችን መታረድ መሪርና አስደንጋጭ ዜና ስንሰማ ሰግተናል ፣ ተሸብረን ጨንቆናል …አንተ ምን ትረዳናለህ ? ለሚዲያ ሽፋን ብቻ ከሆነ አይጠቅመንም ፣ እኛ የምንፈልገው በሰላም ከሊቢያ መውጣት ነው ፣ ጭንቅ ላይ ነን ፣ የሚረዱንን ሰዎች አገናኘን ፣ እባክህ እርዳን ? ” ያሉበትንና የገለጹበትን ድምጽ ደጋግሜ እያዳመጥኩ ተጨናንቄያለሁ ! ” ከሊቢያ እንድንወጣ ብቻ እርዳን !” ብለው ከፍቷቸው አዝነው እየተማጸኑኝ ነበርና እኔም የቻልኩትን ለማድረግ እሞክራለሁ በሚል ቃል ገብቸ ላበረታታቸው ስሞክር አልተቻለኝም …አንዳንዴማ የጨነቀ እለት ይከፋ የል …ከፍቷቸው የሚሰጡት ጥርጣሬ የሞላበት አስተያየት ውስጤን ያውከው ያስቸግረኝ ይዟል … ግን ቻል አደርገዋለሁ ! … ማድረግ መሆን አለመቻል በተስፋ ተሞልቸ ስኖር ተስፋየ በተነው …

የግብጽ ኢንባሲና እህቶች …
===================

ጨለማው ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓም ሰኞ ማለዳ እኩለ ቀን ገደማ ነው ፣ ከማለዳው እስከ እኩለ ቀን የብዙ ወገኖች ትጋት የታከለበት ጥረት ተሳክቶ ሊቢያ ያሉት ወገኖቻችን ይረዳሉ የተባሉ ኃላፊዎች አድራሻ ተገኘ ፣ በአድራሻው ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደወልኩ ፣ ኃላፊውን አግኝቸ ሀገር ቤት መግባት ለሚፈልጉት እያደረጉ ስላለው ጥረት ጠየቅኳቸው ” ጉዳዩ ገና እየተጣራ በመሆኑ መረጃ ልሰጠህ አልችልም ፣ ነገር ግን በተለያዩ የሊቢያ ክፍል ያሉ ወገኖቻችን እየተደዋወልን ነው! ” የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጡኝ ። ያገኘሁትን አድራሻ ለመለጠፍ ባስፈቅድም ፈቃደኛ አይደሉም ! በኢንባሲው መደበኛ ስልክ መስጠት እንደምችል ግን መከረውኛል ። አዎ አለቆቻቸውን ማነጋገር አለባቸው ! አለቆቻቸው ደግሞ የተቸገሩት የሚደውሉና እርዳታ የሚያገኙበት እስካሁን ግልጽ ያለ አድራሻ አላስተላለፉም … ያነጋገርኳቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የግብጽ ኢንባሲ ትሁቱን ዲፕሎማት በተለይም ወደ ሀገር ቤት ለመግባት ፍላጎት ያላቸውን ትሪፖሊ የሚገኙ እህቶች አድራሻ ሰጠኋቸውና አደራ ብያቸው ተለያየን !

አመሻሹ ላይ ወደ ትሪፖሊ ደወልኩ ፣ ስልኩ ተነሳ ! ከሰላምታ በኋላ አድራሻቸውን እንደሰጠሁ ተናግሬ ሳልጨርስ ” አዎ ደውለውልን ነበር ፣ ትሪፖሊ ያሉ አቶ … የሚባሉ ኢትዮጵያዊ አድራሻ ሰጠውናል ፣ ግን የትም አይጥሉንም ? እንዴት ታምናቸዋለህ ? ሁላችንም ተነጋገርንበት ግን ፈራን !” አለችኝ ስልኩን ያነሳችው እህት ከትሪፖሊ …

ያልደረሰንላቸው በሽዎች የሚቆጠሩ በሱዳን አድርገው በርሃውን ቆርጠው ሊቢያ የገቡት የሚያጠቃ፣ ኢትዮጵያውን ክርስትያኖችን ለይቶ የሚያድን የሰው አውሬ በሊቢያ መሽጓል ። አሸባሪው ISIS ይባላል ፣ እንዳሻው አንገት እየቀላ የንጹሃንን ደም በማፍሰስ የሚፎክር ፣ የሚኩራራ እኩይ አውሬ ! አሸባሪው ትናንት በግብጽ ክርስትያኖች ጀምሮ ዛሬ በኢትዮጵያ ክርስትያኖች ደም ማፍሰሱን ቀጥሎ ማን ይነካኛል ብሎ እየፏለለ ይገኛል ። ኃያላኑ አሜሪካና ምዕራባውያን ዝም ጭጭ ብለዋል ! አሸባሪው ISIS የሚደፍረው ጠፍቷል ፣ አለያም ሆን ተብሎ እንዳበደ ውሻ ተለቆ ሰው መፍጀት ይዟል !

ተስፋ መቁረጥ ፣ ስጋትና ፍርሃት …
=====================

የሰሃራ በርሃን ቆርጠው ሊቢያ የተኮለኮሉትን ኢትዮጵያውያን ቁጥር ማንም አያውቀውም ፣ መሸሻ መሸሸጊያ ቢጠባቸው ፣ ችግራቸው ችግር ቢሆንም በሃገር ቤት የመሳደድ መታሰር ፍርሃቻ ሃገር መግባት እንዳላስቻላቸው አጫውተውኛል ፣ የተመዘዘው ስል ጩቤ አላስፈራቸውም .. ! ” ሶስተኛ ሀገር እንጅ ወደ ሃገር አንገባም !” እያሉ ነው ! አደጋውን በተጨባጭ መረጃ ስታስረዳቸው ” በራሴ ወገን ፣ በራሴ ሀገር በእስር ከምሰቃይ ፣ በርሃው ይብላኝ … ” ይሉሃል …ከበርሃው በላይ ያለውን ጨካኝ አሸባሪ ስራ ቢያውቁትም የሀገር ቤቱ የፖለቲካ ትኩሳት ወደ ሀገር የመመለስ ተስፋቸውን አጨልሞታል ! ሀገር ቤት መግባቱ እንኳን ለእነሱ በራሴ ላይ ምን ይፈጠርብኝ እንደሁ የማላውቀው ጎልማሳ የፈለገው ቢያደርጉም ፣ በሰው ሃገር በጨካኞች እጅ ከመውደቅ በሀገር መከራን መቀበል ይሻለል ! ስላቸው ወያኔያዊ መንፈስ የተጠናወተኝ እየመሰላቸው ” እሱ ያንተ ምርጫ ነው ፣ ብቻ ስማችንና ድምጻችን እንዳታወጣው አደራ ! ” ይሉኛል መልሰው ይጠራጠሩና … ፈርተው ! እናም ፖለቲካው የፈጠረው ስጋትና ፍርሃት ታየኝ …

ክህደት ፣ ሸፍጥ ፣ አምነት ማጣት … የወለደው ፍርሃት …
===================================

“ወደ ሃገር እንግባ ” ያሉት ሞልተው ተርፈዋል ፣ ያም ሆኖ እስካሁም በግላጭ የሚታወቅ ለሁሉም ተደራሽ አድራሻ አልተላለፈም ! … የተደረሰላቸው ጭንቀት ፍርሃቱ የራሳቸውን ወገን እስከ መጠራጠር አድርሷቸዋል አይተናል ፣ ለመረዳት ” ፈራን !” እያሉ ነው ! … ክህደት ፣ ሸፍጥ ፣ አምነት ማጣት … የወለደው ፍርሃት ፈሪ አድርጓቸዋል !

ወደ አውሮፖ በጣሊያንና ማልታ በኩል ለመድረስ በአሳር በመከራ እዚህ ጫፍ የደረሰ የሀበሻ ልጅ ደምም ረክሷል ፣ ሃበሻ የሌለበት ፣ የሀበሻ ነፍስ ረክሶ ፣ ነፍሱ የማይጠፋበት ቦታ አይሰማም ። ይህ የባህር አደጋ ብዙ ባይነገርለትም ፣ ተደጋግሞ የእኛን ሰው ነፈወስ ነጥቆታል ፣ አጥፍቶናል ። ቢደደጋገምም ሀዘን ቁጭቱ አልለመድ ብሏል ። እነሆ በሃዘን ላይ ሃዘን ሰምተናል ! የወንድሞቻችን አንገት በተቀላበት የሜዲትራንያን ውቅያኖስ በተሰናከለች የአሻጋጋሪዎች መርከብ / ጀልባ “የሞቱት የተረፉት እነማን ናቸው ? ” ተብሎ ወደ የማይመረመርበትን ትራጀዲ ተፈጽሟል ! ይህን የሰማነው ትናንት ነው ፣ በሀዘን ላይ ሆነን !

ካለሁበት ሳውዲ ኩታ ገጠሟ የመን የሀበሻ ልጅ የድረሱልኝ ድምጽ አባርቶ ባያውቅም ፣ የመን ሰማይ ስር በጦርነት እየታመሰ በመሆኑ የከፋ ዋይታ ድምጽ ይሰማል ፣ ጭካኔያቸውም አይተን የአፍሪካዊ ISIS ያልናቸው ደቡብ አፍሪካውያን ውለታችን ረስተው አመድ አፋሽ አድርገውን ብቻ አልቀሩም ፣ የለየለት የንቀት ግፍ ተፈጽሞብናል ! ይህም ያም ሁሉም ያስፈራል !

ሁለት አስርት አመታት በኩራትና ፍጹም በነጻነት የኖርኩባት ሳውዲ አረቢያ አሁንም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ ከሀገሬ ባልተናነሰ ከከተማ እስከ ገጠር ከተሞቿ በነጻነት ብንቀሳቀስባትም ዛሬ የነጻነቱን ግርማ ከላየ ላይ የለም ! … ቤቱ ፣ ስራ ፣ ቦታው ፣ መንገዱ … ሁሉም ያስፈራል ! ” ፈራን !” ብለው አስፈሩኝ …

ትናንት ማምሻውን ከልጆቸ ጋር ስንጨዋወት የወትሮው አባታቸው አለመሆኔን ተረድተዋልና ” አቤ ምን ሆነሃል ፣ ፊትህ ደስ አይልም! ” እያሉ ጠየቁኝ ፣ ወደ ውስጥ ሳልገባ ” ከእናንተ የሚጠበቀው ጥናት ነው አጥኑ! ” አልኳቸው ፣ መልሴ ያልጣመው የ13 ዓመቱ የበኸር ልጀ ” አቤ እስኪ ላንድ ሰሞን ይህንን የምትጽፈውን ተወውና ዘና በል ፣ ባህር መጫወቻ ቦታ ሁሉም አካባቢ ጥሩ ጥሩ ወዳጆች እያሉህ እዚያም ወስደህንኮ ትጽፋለህ ? ለምን ለራስህ እረፍት አትሰጠውም !” ሲል እህቱ ማሂን እንዳቀፈ ክችም ብሎ አፍጥጦ ጠየቀኝ እዮብ ፣ የመጻፊን ጥቅም ባስረዳውም ” እኛም እኮ አንተ ስትረባበሽ እንረበሻለን ” ሲል ሞገተኝ ፣ መልስ የለኝም ” ልጀ ምን ታይቶት ይሆን ? ” አልኩ ራሴ ለራሴ በውስጤ … ከነጎድኩበት እሳቤ ራሴን በተሎ ሰብስቤ ” አዎ ትክክል ነህ ፣ እስኪ አረፍ እላለሁ ! ” አልኩትና ቃል ገባሁለት …ለአባቱ የፈራ ልጅ !

ፍርሃቱ ባያሸሸኝ ፣ ለልጀ የገባሁትን ቃል ለማክበር ላፍታ ያህል ከማህበራዊ መገናኛ መስመሩ ዘወር ልል አስቤያለሁ ፣ አብራችሁኝ ለተጓዛችሁ ፣ ለደገፋችሁኝ ፣ ለተረዳችሁኝ ፣ ” ራስክን አትቆልል! ” ስትሉ የድርሻችሁን ስታደርጉ የማላያችሁ ወቃሾቸ ጭምር ሁላችሁንም አመሰግናለሁ ! የሰማሁት ሰሞነኛ ልብም ሰባሪ እማኝነት እንዳይቀር አንድተነፍስና ለእረፍት የመሰናበቻ መልዕክቴን በተሰበረ ልብ ካስተላለፍኩ ምንም አልሻም ! የጨለቀ እለት … እንዲህ ነው !

ብቻ ከመግፋት መገፋት ፣ መልካም ነገር ነው ፣ ለሚቀረው አለም ለሚያምኑበት መሞት ደግሞ ሰማዕትነት ነው ! ነፍስ የሚያስምር !

ነቢዩ ሲራክ
የጨለመው ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

ሰበር ዜና ፤ መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ በተገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ::

$
0
0

መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ በተገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ:: ፎቶች ይዘናል ይመልከቱ፤ የBBN ድምጽ ዘገባ እዚህ በመጫን ያዳምጡ
ህዝቡ ካለማንም ነጋሪነት ካለማንም ተቃዋሚ ጣልቃ ገብነት ራሱ በራሱ የሚከተሉትን መፈክሮⶭ አስምቷል።
* የፈሰሰው ደም የውሻ አይደለም
* መከላከያ ስራህ ምንድነው
* የወያኔ ጉልበት እኛ ላይ ብቻ
* ና ና መንግስቱ ናና
* አባረዋቸው አሳረድዋቸው
* 24 አመት ያለ ነፃነት
* ልማት እያሉ አርደውን በሉ
* ውሸት ሰለቸን
መንግስትም ካለ አይ ኤስ እርዳታ ራሱ በራሱ ተነሳሽነት እንዲህ አይነት ርምጃ ወስዷል….ፎቶዎችን ይመልከቱ549444_801129899956477_1424167183876762663_n

1779700_10205326853244676_5905036838038270768_n

10451892_1581605682110629_3821366739563738673_n

11116516_628198803981745_7495811864236154572_n

11149474_628199030648389_5763327639153829987_n

11150899_628199077315051_3781116736708713188_n

11164819_541074082700221_4140580604451079116_n

11174765_1581605698777294_1045119059995972703_n

11179966_541073919366904_4672755513890480893_n

11182282_628198977315061_6221851409112606719_n

11183370_10205326836844266_1103065089018589409_n

በቦስተን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሊቢያ እና በተለያየ ቦታዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች የጸሎት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ!!

$
0
0

በቦስተን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሊቢያ እና በተለያየ ቦታዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች በትናንትናው ምሽት የጸሎት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት፤ በደማቅ ስነ ስርዓት ተካሄደ!!

የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጠራው የሻማ እና የጸሉት ስነ ስርዓት ላይ በቦስተን እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች፤ የመካነ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ምሽት የሁለቱ ቤተክርስቲያን አባቶች የተመራ የጸሎት ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን በሁለቱ አባቶች ሰፋ ያለ ትምህርትም ተሰጥቷል፤ በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው ሕዝብ እንባ በእንባ በመራጨት በወገኑ ላይ የደርሰውን ሐዘን ገልጿል፤ በዚሁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያኖች የደረሰብንን ውርደት እና መከራ በጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕብረት ከወገናችን ጎን መቆም እናዳልብን ያስገነዘቡ ሲሆን፤ በወ/ሮ ራሄል ፍቅራ አብ የቀርበ ግጥምም ቀርቧል፤

በመጨርሻም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሚቀጥለው ቅዳሜ በተዘጋጀው የአንድነት እና የወገን አጋርነት ስብስባ በሚቀጥለው ቅዳሜ ኤፕሪል 25 2015 ከቀኑ 3፡00 PM ሰአት ጀምሮ በ86 Bishop Allen Dr, Cambridge, MA 02139 ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል። 0a1dc9bf588f55c9eb854ac069eb75ea3edf1a181da607cd67a78c37f153ead9.0 2a4962a6d54db7cd2b9663dd65beaa57ce4414f8228972d3bb6f4e9592c1ab7f 3fd16d14bf444eea7084a45af352c541e0650671e94b5e7bbb1e041ff2a7c887 20150422_183244 4b555ccb730e4c86fbc3eabd46af4355e3f314c034f4b02bad6afc9affe56954

ከኢሕአዴግ ጋራ በአንድነት ለመቆም ….. –ግርማ ካሳ

$
0
0

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የኢሕአዴግ መንግስት ላይ ወርደንበታል !!!! ጥሩ ነው ያደረግነው። በተለይም ትላንትና ህዝቡ ተቃዉሞዉን ማሰማቱ በጣም አስደስቶኛል። አርክቶኛል። ሕዝብ ሲናገር መስማት የመሰለ ትልቅ ነገር የለም። ምርጫ 2007 ትላንት የተደረገ ነው የመሰለኝ። በተለየም መሪዎቹ እዚያ ቆመው፣ የሕዝቡን ፉጨትና ጩኸት መስማታቸው ጥሩ ነው። ያለዉን የሕዝቡን ስሜት በአካል መረዳታቸው፣ ምናልባት አይምሯቸው ላይ የሚጭረው ነገር ሊኖር ይችላል።

አፉን ዝም ብሎ የሚከፍተዉ፣ ዱርዬው ሬድዋን ሁሴን፣ወደዚያ ተዉትና፣ ከዶር ቴዎድሮስ አዳኖምና ከአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የሰማነው ነገር አለ። እንደ አይሰስ ያሉትን ለመወጋት አንድ እንሆኑ የሚል ጥሪ ነው ያቀረቡት። በተቃዋሚ ጎራው ያሉት፣ በአገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም የሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን ፣ እንደ አይሰስ እና አልሻባብ ያሉ በአካባቢያችን የሚንቀሳቀሱ ሽብርተኞች ላይ መዝመት እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። ለዚያም ግፊት ያደርጋሉ። (እንደዉም እኔ ኢትዮጵያ በሶማሌያ ያላትን እንቅስቃሴ አጠናክራ ከዚያ አካባቢ ሙሉ ለሙሉ አልሻባብን ማጥፋት አለባት የሚል አቋም ነው ያለኝ) ሁላችንም፣ በአገር ጉዳይ ላይ ከኢሕአዴግ ጋር በጋራ ለመቆም፣ አንድ ሆነን ለመሰለፍ እንፈልጋለን። ነገር ግን እነርሱ ፣ ኢሕአዴግች፣ በአደባባይ ተናገሩት እንጂ፣ ፍላጎት አላቸው ወይ ? የሚለው ነው ቁልፉ ጥያቄ !!!!

ከፈለጉ በሥራቸው ያሳዩን። ቢያንስ እነርሱን የማይጎዳ፣ ግን በነርሱና በተቀረው መካከል መቀራረብን የሚያመጣ ፣ በመካከላችን ያለውን እምነት መስርቶ የሚያጠናክር፣ እርምጃዎች ይወሰዱ። አብረን እንስራ እያሉ፣ እኛ ላይ የሚዘምቱ ከሆነ፣ እነርሱን ለመመከትና ከነርሱ ለመሸሽ እንሞክራለን እንጂ እንዴት ከነርሱ ጋር አብረን እንሆናለን ?

የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ
————————–
የጸረ-ሽብርተኛነት ሕግ አለ። ይሄ ሕግ እዉነተኛ ሽብርተኞች ላይ ያነጣጠረ አይደለም። በመሆኑም ሕጉ ይሻሻል። ሁለት ነገሮች በቶሎ ሊወሰዱ ይችላሉ። እነርሱም ፓርላማው ሽብርተኛ ብሎ ከፈረዳቸው ቡድኖች ዉስጥ ኦብነግ፣ ኦነግን እና ግንቦት ስባትን ሰርዞ፣ አይሰስን መክተት አንዱ ነው።

እነ ግንቦት ሰባት የመንግስት ተቃዋሚዎች እንጂ ሽብርተኞች አይደሉም። እነርሱን ሽብርተኛ ማለት የሽብርተኝነት የጭካኔ መጠን እና ትርጉም ማሳነስ ነው። አሁን አቡበከር አልባግዳዲ፣ አማን አላዛዋህሪ ያሉትና እና እነ ዶር ብርሃኑ ነጋን፣ ጀኔራል ከማል ገልቺ በአንድ መቀመጫ ማስቀመጥ፣ የነ አቡበከርን ግፍ ማሳነስ ነው።

ሁለተኛ ሕግ እንዲሻሻል ፓርላማዉ ወስኖ፣ ሕጉ እስኪሻሻል ድረስ ሕጉ ተግባራዊ እንደማይሆን መግለጽ ወይንም ሰስፔንድ ማድረግ ነው ። በተለይም የሽብርተኝነት ድርጊት የፈጸመና ሊፈጽም ሲል የተያዘ እንጂ መከሰስ ያለበት «ለመፈጸም አሰበ» በሚል ዜጎች መከሰስ የለባቸውም።

ይህ ከሆነ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች አብዛኞቹ ይፈታሉ። ከነእስክንደር ነጋ ጀምሮ በቅርብ እስከ ታሰሩት እስከነ ብርሃኑ ድረስ። በኢሕአዴግ እና በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን መካረር ይቀንሰዋል።

ብሄራዊ መግባባት
——————–

አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች በአደባባይ መዝለፍና ማስፈራራት አቁሞ፣ ከነዚህ ከተቃዋሚዎች ጋር መነጋገር ያስፈልጋል። እነርሱን የሚቃወም ሁሉ የሕዝብ ጠላት አይደለም። በአገር ጉዳይ፣ አንድ እንሁን ካሉ፣ እነርሱን የሚቃወሙትን ፣ አሳምኖና አግባባቶ ከጎን ማሰለፍ ያስፈልጋል።

የለወጥ ፈላጊው፣ እነርሱን እውቅና የነፈጉት ፣ ግን መዋቅሩን ጠብቆ ያለው የአንድነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የትብብር፣ የመድረክ …አመራር አባላት በአገር ጉዳይ ላይ ከኢሕአዴግ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ነው የሚመስለኝ። ኢሕአዴግ እነርሱን እንደ ጠላት ቆጥሮ ሊያጠፋቸው ይፈልጋል እንጂ፣ በቅንነት፣ «እስቲ ያሉንን ችግሮች እንነጋገር» ብሎ በሩን ቢከፍት ለመነጋገር ዝግጁ ናቸው።

ለምሳሌ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የመድረክ መሪ የሆኑትን ዶር መራራ ጉዲናንና ዶር በየነ ጵጥሮስን፣ የእዉነተኛው አንድነት መሪ የሆኑት አቶ በላይ ፍቃዱን እና አቶ ተክሌ በቀለን ፣ ከትብብር አቶ ግርማ በቀለን፣ ከሰማያዊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ከኢዴፓ ዶር ጫኔን ቢሯችው አስጠርተው «እስቲ ምን እናደርግ፣ አንድ ሆነን እንድንቀጥል ? » ለማለትና እንደ ወንድማማቾ በቅንንት ለመወያየት ጥያቄ ቢያቀርቡ ፣ እመኑኝ ፣ እነዚህ መሪዎች ለመነጋገር ፍቃደኛ ነው የሚሆኑት። ከድርጅቶቻቸው በላይ የአገርን ጥቅም የሚያስቀድሙ ናቸው። ግን ይሄን ለማድረግ ትልቅ እና በሳል መሆንን ይጠይቃል።

ምርጫዉ ይራዘም- ወቅቱ የምርጫ ወቅት አይደለም
———————————————————

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይደረጋል። ይህ ምርጫ ለአገር ሰላምና መረጋጋት ሲባል ቢራዘም ጥሩ ነው። የምርጫው ሂደት በጣም ተበላሽቷል። ምርጫው ተዓማኒነት ከወዲሁ አጥቷል። በዚህም ምርጫ ኢሕአዴግ አሸነፍኩ ብሎ ቢወጣ የሚያገኘው ምንም የፖለቲካ ትርፍም ሆነ ሌጂቲማሲ አይኖርም። አብይና ጠንካራ የሚባለውን ድርጅት፣ አንድነትና፣ አግዶ፣ እንደ ሰማያዊ ያሉ የበርካታ ድርጅቶች ተወዳዳሪዎችን ሰርዞ፣ ብዙ ተወዳዳሪዎችን አስሮ፣ ሜዲያውን አፍኖ የተደረገ ምርጫ የእቃ እቃ ጨዋታ ነው። አንዱ ምክንያት ይሄ ነው።

ሁለተኛዉና ዋናው ምክንያት ደግሞ፣ ምርጫዉ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በዉጭ አደጋ ላይ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ መሆኑ ነው። ሁላችንም አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት መረባረብ አለብን። በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም። ምርጫው ዲስትራክት ሊያደርገን አይገባም። በብዙ አገሮች ብሄራው አንገብጋቢ ጉዳዮች ሲኖር ምርጫዎች የተራዘሙበት ሁኔታ አለ።

በመሆኑም አሁን ያለው አገዛዝ ለሁለት አመት ቀጥሎ፣ መስተካከል ያለባቸው ተስተካክለው (የዴሞክራሲ ተቋማትን ገለልተኛ የማድረግ ሁኔታ) ፣ ከሁለት አመት በኋላ በመልካም ሁኔታ ምርጫዉን ማድረግ ይሻላል።

እንግዲህ ከላይ እንዳልኩት፣ ኳሷ ያላችው ኢሕአዴግ አመራሮች ደጃፍ ላይ ናት። አገሪቷ ብዙ ችግሮች አላት። የግድ ኢትዮጵያዉያን መሰባሰብ አለብን። ኢትዮጵያዉያን እንዲሰባሰቡ በር መክፈት የሚችሉት ደግሞ ፣ እነርሱ ናቸው።

ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን፣ ማንም ሳይቀሰቅሰው ትላንትና ከትላንትና ወዲህ ተቃዋሞ ያሰማው ህዝብ እንደገና ሳያስቡት ምን ሊያደረግ እንደሚችል መገመት አለባቸው። ሊቢያ፣ ሶሪያ ከቁጥጥር ዉጭ የሆኑት ሲጀመር ጋዳፊና አሳድ ግትር በመሆናቸው ነው። በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ምሬትና ቁስል አለና፣ እርሱን ማከሙ ላይ ቢበረቱ ይሻላል። ከላይ ያስቀመጥኩት ሐሳቦች የሕዝቡን ቁስል ሊፈዉሱ የሚችሉ፣ በብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮሩ ጠቃሚ ሐሳቦች ናቸው።የሚቋወሟቸውን መፍራትና መጠራጠር የለባቸዉም። ሕዝቡ ከጅምሩ ፀቡ ከድርጊቶቻቸው እንጂ ከነርሱ ጋር አልነበረም። ምነው ደርግ ሲወድቅ በሩን ከፍቶ አይደለም እንዴ ሕዝቡ ያስገባችው ?

እንግዲህ አራት ኪሎ ያሉ አይኖቻቸው ይከፈት ዘንድ፣ በዚያ አካባቢ ያለውን የክፋት፣ የጭካኔና የእልህ መንፈስ ይመታ ዘንድ እጸልያለሁ። የእግዚአብሄር መንፈስ ተናግሯችው፣ ቀና ሆነው፣ ፊታቸው ወደ እግዚአብሄር መልሰው፣ ራሳቸውን ቢያዋርዱ አገር ምንኛ በተባረከች ነበር !!!
ከኢሕአዴግ ጋራ በአንድነት ለመቆም ….. – ግርማ ካሳ

ለሚመራው ሕዝብ ፍቅርን፣ ክብርንና ርኅራኄን የተራቆተው የኢሕአዴግ መንግሥት በፍቅር

$
0
0

‹‹Leadership is Falling in Love with the People You Lead or Serve››

(ቀድሞዋ የማላዊ ሴት ፕሬዝዳት ጆሴ ባንዳ)

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ከትናንትና በስቲያ ከሥራ ወጥቼ ወደ ቤቴ ለመሄድ በተሳፈርኩበት ሃይገር ባስ ውስጥ ያጋጠመኝ እጅጉን ያሰዛነኝ ክስተት ነው፡፡ በተሳፈርኩበት ሃይገር ባስ ውስጥ ወጣቱ ሹፌር የይሁኔ በላይን የአገር ባህል፣ ሞቅ ያለ የበዓል ዘፈን እስከ ጣራው ለቆታል፡፡ ነገሩ ግራ አጋባኝ፡፡ በጉዞአችን መካከልም በአይ ኤስ ታጣቂዎች በግፍ የታረዱት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ገና አልተጣራም በማለት ሲያንገራግር የነበረው መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን የተሠዉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አምኖ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ታዲያ ይህ ሰው በዚህ ኢትዮጵያችን የኀዘን ከል በለበሰችበት የሰቆቃና የዋይታ ቀን ምን ቢሰማው ነው ይህን ዘፈን እስከ ጣራው ከፍቶ እያስጮኸው ያለው ስል ራሴን ጠየኩኝ፡፡

ይህ ሰው ጤነኛ አይደለም ወይስ … የሹፌሩ ነገረ ሥራው እጅጉን ቢከነክነኝ ዞር አልኩና ወንድሜ ይቅርታ ኀዘን አይደለም እንዴ ምናለ ዘፈኑን ብትዘጋው አሊያም ለራስህ ብቻ ብታዳምጥ አልኩት፡፡ መለስ አለና የምን ኀዘን አለኝ ፈርጠም ብሎ፡፡ ነገሩ ግራ አጋባኝ ይህ ሰው በኢትዮጵያ ምድር አይደለም እንዴ ያለው ስል በመጠራጠር ቀና ብዬ አየሁት፡፡ እንዴ ወንድም በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በግፍ የሞቱት፣ የተሠዉት ወገኖቻችን የእኛ ወንድሞች፣ የእኛ ወገኖች አይደሉም፣ ይህ ኀዘን የሁላችንም ኀዘን አይደለም እንዴ አልኩት ንዴትም እልክም በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡

ወጣቱ መለሰና እኛ ታሪክ አናወራም፡፡ ወደፊት ነው የምናስበው፣ ልማት ነው የምናልመው አለኝ፡፡ እንዴ ታሪክ እኮ አይደለም ወንድሜ … አላስጨረሰኝም … በዚህ ሰው ምላሽ ድንጋጤም፣ ንዴትም ይንጠኝ ጀመር፡፡ ከዚህ በላይ ላነጋግረው አልፈለኩምና በእፍረትና በንዴት መካከል ውስጥ ሆኜ ፊቴን መለስኩ፡፡ ኢትዮጵያዊው መተዛዘናችን፣ ያ ከወንድሜ በፊት እኔን ያስቀድመኝ የሚለው ድንቅና አኩሪ ባህላችን የት ገባ አልኩ ለራሴ በለሆሳስ፡፡ ወደየት እየሄድን ነው ስልም ራሴን ጠየኩ፡፡

አፍታ ቆይቼም ይህ ወጣት የዘመኑ ልማታዊ ሹፌርና በአብዮታዊ ዲሞክራሲን የተጠመቀ ጭፍንና መደዴ ካድሬ መሆኑ ሲገባኝ ደግሞ ፍቅርንና ሰብአዊነትን ለተራቆተው ግልብ ማንነቱ አዘንኩለት፣ አፈርኩለትም፡፡ ለሰው ልጆች፣ ለሚያስተዳድረው ሕዝብ ፍቅርና ክብር፣ ሰብአዊነትና ርኅራኄ የተለየው መንግሥታችን እንዲህ ዓይነቶቹን የሰው ሽታ የሌላቸውን የልማት አርበኞች ወይም ካድሬዎች በገፍ እያፈራልን ነውና የነገ ዕጣ ፈንታችን ሲታሰበኝ ለራሴም ለምስኪን ሕዝቤም አዘንኩ፡፡
ለመሆኑ የሆነስ ሆነና ሰብአዊነትን ማዕከል ያላደረገ ልማትስ ጠቀሜታው ምን ድረስ ነው፣ እስከየትስ ነው ሊጓዝ የሚቻለው፡፡ የአገራችን የልማት አጀንዳ እንዲህ ፍቅርን፣ ሰብአዊነትንና ርኅራኄን አሸንቀጥሮ የጣለ ጎዶሎ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ይባስኑ ፍርሃቴና ኸፍረቴ ጨመረ፡፡

ለነገሩ ይህ ልማታዊ ሹፌር አይፈረድበትም፡፡ መንግሥትስ ጠላቶቻችን ሳይቀር የመሰከሩትንና እንደ አሜሪካ ያሉ ወሬ የሚያነፈንፉና መረጃ የማያመልጣቸው ኃያላን አገራት ሣይቀሩ በአይ ኤስ በግፍ ታርደው ሰማዕት የሆኑት ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አገረጋግጠው የኀዘን መግለጫ የላኩበትን የሕዝባችንን መርዶ አምኖ ለመቀበል እንዲያ ሲያንገራግር ታዝበነው የለ፡፡ ይህን ዘግናኝ የሆነ ዜና የዓለም መገናኛ ብዙኃን ሁሉ እየተቀባበሉ ለሁሉም እያደረሱ ባለበት ሰዓት መንግሥት እነዚህ በግፍ የታረዱ ሰዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገና አላረጋገጥንም ሲል ነበር በግልጽ የተናገረው፡፡

ዘግይቶም ቢሆን ይህ ዘግናኝ እልቂት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መሆናቸውን አምኖ የተቀበለው መንግሥት መላው ሕዝባችን በኀዘን ድባብ ውስጥ ገብቶ እምዬ ኢትዮጵያም በደቡብ አፍሪካ፣ በየመንና በሊቢያ በግፍ ለወደቁባትና ለተሠዉባት ልጆቿ የኀዘን ማቅ ለብሳ በምታነባበት የዋይታ ቀናችን መንግሥት ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል እንዳለው፡- ‹‹ምንም ሰብአዊ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጽ፣ ሰው ሰው ማይሸት መግለጫቸውን አስተላለፉልን፡፡ ጥልቅ ኀዘናችንንም ያለ ምንም እፍረት የተራ ፕሮፓጋንዳቸው ማስፈጸሚያቸው አደርገውት አረፉት፡፡

ሕዝቡ ከልቡ አዝኖ በየቤቱ፣ በየጓዳው በእንባ እየታጠበት ያለውን መርዶውን፣ ጥልቅ ኀዘኑን መንግሥት በይፋ እስኪገልጸው በሚል ሰበብም በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያና በኤፍ ኤም ሬዲዮኖቻችን ምንም እዳልተከሰተ ሁሉ የአስረሽ ምቺው ዘፈኖችና በንግድ ማስታወቂያቸው ልባችንን ሲያደሙት፣ ጆሮአችንን ሲያመግሉት ነበር የዋሉት፡፡ በዚህ ለሕዝባችን የዋይታና ሰቆቃ በሆነበት ቀን ‹‹የምን ኀዘን ነው የምን ትካዜ፣ ሁሉም ያልፋል በጊዜው›› የሚል በዋይታችንና በሰቆቃችን ቀን እንዲህ ዓይነት ኢ-ሞራላዊና ሰብአዊነት የጎደላቸው ዘፈኖችን በማሰራጫ ጣቢያዎቻቸው የለቀቁ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቻችን በእውን ለሰው ልጆች ፍቅር፣ ሰብአዊነትና ርኅራኄ አላቸው ብሎ ማለት ይቻላልን?!

ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ወርዷል ማለት ነው፣ መተዛዘንና መተሳሰብስ በኢትዮጵያችን ምድር እንዲህ በጠራራ ፀሐይ ውኃ በልቶታል ማለት ነው?! በዚህች ምስኪን አገርስ ሃይ ባይ መሪ፣ መካሪና ዘካሪ የሃይማኖት አባትና የአገር ሽማግሌ የለንም ማለት ነውን?! በእጅጉን ያሳዝናል፣ ልብንም ይሰብራል!!

በደቡብ አፍሪካ፣ በየመንና በሊቢያ ያለቁ፣ በግፍ የታረዱ ያሉ ወገኖቻችን አይደሉም እንዴ! ምንም ዓይነት ኢሰብአዊነትና ጭካኔ ነው?! በየቤቱ በስደት ከጉያቸው የወጡ ልጆቻቸውን ዕጣ ፍንታ በማሰብ በኀዘን ተኮራምተው፣ በዋይታና በሰቆቃ ውስጥ ለገቡ ምሰኪን እናቶችስ እውን የመገናኛ ብዙኃኖቻችን ስትለቁት በነበረው የአስረሽ ምቺው ዘፈኖቻችሁና የንግድ ማስታወቂያዎቻችሁ ምን መልእክት፣ ምን ዓይነት ምሥራች ነው ልታስተላልፉላቸው የፈለጋችሁት?! በእውነት አፍረንባችኋል፡፡

ይህን ውሎዬን ሲየንገበግበኝ የዋለውን የመገናኛ ብዙኃኖቻችንን ነገረ ስራ እብከነከነኝ ኀዘኔንና ብሶቴን በውስጤ እንደተሸከምኩና በሃይገር ባሱ ሹፌር ሁኔታ እየተገረምኩ ቁጭቴንና እልኬን በውስጤ አምቄ ወደ ቤቴ ደርስኩ፡፡ በመኝታዬ ክፍል ከጥቂት እረፍትም ካደርኩ በኋላም በደረሰባት የመኪና አደጋ የተነሣ በቤቷ የተኛችውን ጓደኛችንን ለመጠየቅ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ወደ ቤቷ አመራን፡፡ ጓደኛችንንም እንኳን እግዚአብሔር አተረፈች በማለት ጤንነቷ አሁን እንዴት እንደሆነ እየጠየቅናት ስንጨዋወት በነበረበት ሰዓት የዚህች ጓደኛችን አከራይ ለጥየቃ መጣች፡፡

ሰላምታ ተለዋውጠን ጓደኛችንን በጋራ ሆነን እያጽናናናትና እንድትበረታም እየነገርናት የሁሉም ሰው መነጋገሪያ ጉዳይ ወደሆነው በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ ስለደረሰው እልቂት ማውራት ተጀመረ፡፡ በመንግሥት የዘገየና ግራ በሚጋባው የኀዘን መግለጫ የበገነው ጓደኛዬም፡- ‹‹መንግሥት ዘግይቷል፣ ተግባራዊ ዕርምጃ መውስድ ይገባዋል፡፡›› በማለት ለጓደኛችን አከራይ ብሶቱንና ንዴቱን ዘረገፈላት፡፡ ይህች ሴትም ኖ ኖ ኖ መንግሥት እኮ ማጣራት አለበት፣ ዝም ተብሎ መግለጫ አይወጣም፡፡ እንደምታውቁት በሊቢያ ኤምባሲ የለንም መንግሥት በግብጽ አገር ባሉት አምባሳደራችን በኩል እስኪያጣራ ድረስ ነው የቆየው እንጂ ብዙዎች እንደሚሉት …፡፡
ይህች ሴት ንግግሯን ፕሮፓጋዳዋን ማለት ይቀላል በፍጥነት ቀጠለች፡፡ ይህ በፌስ ቡክ በስሜታዊነት አስተያየት እየሰጡ የሚገኙ ሰዎች ትክክል አይደሉም ስትልም ፈረደች፡፡ በእጇ የያዘችውን እጅግ ውድ የሆነ ስማርት ስልኳን እየከፈተችም ማብራሪያዋንም፣ መግለጫ ማለቱ ሳይቀል አይቅርም ያለ ምንም ከልካይ ታዘንብብን ጀመር፡፡ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅ እንደሆነች በመግለጽም ስለ ዲፕሎማሲ፣ ስለ ጦርነት፣ አክራሪነት፣ ሽብረተኝነት ትርጉሙን በቅጡ የማታውቀውን የእንግሊዝኛ ቃላትን ያለ ቦታው በመደንጎር ልታስረዳን ሞከረች፣ ብዙ ጣረች፡፡

ወሬዋ ማባሪያ፣ ማቆሚያ ያለው አይመስልም፡፡ በእውቀትና በእውነት ላይ ተመሥርታ ሣይሆን በጥራዝ ነጠቅ ባገኘችው በስማ በለውና እዚህም እዛም በቀራረመችው እንቶ ፈንቶ ወሬዋ እንዲህ ስትራቀቅብን ሳያት ከልቤ ታዘብኳት፡፡ እዚህች አገር ላይ ‹‹ሀብተ ድፍረትንና ሀብተ ንቅትን የታደሉ›› ጸሐፊያንና አዋቂ ነን ባዮች በዝተዋል የሚለው የአንድ ጓደኛዬ ምሬቱና ሮሮው ትዝ አለኝና በዚህች የመንግሥት ምልምል ካድሬ ድፍረትና ንቀት እጅጉን አፈርኩ፣ አዘንኩም፡፡

ክርክራችንና ሙግታችንን ስታዳምጥ የነበረችው መኪና አደጋ የደረሰባት ጓደኛችን በአልጋዋ ላይ ሆና እየተሳቀቀችና የቁስሏን ጥዝጣዜ እንደምንም ውጣ በዓይኗ ጓደኛዬን እየጠቀሰችው ወሬ እንዲቀይር ምልክት ሰጠችው፡፡ ይህች ልማታዊ ካድሬ ግን እንዲህ በቀላል ልትተውን አልፈለገችም፡፡

የእውቀቷን ጥግ ከአፍሪካ እስከ መካለኛው ምሥራቅ፣ አሜሪካና አውሮፓ ድረስ በመሻገር ልታስረዳን ዋተተች፡፡ ቀንድና ጅራቱ የማይለይ ከእኔ በላይ አዋቂ በሚል ታብዮ የፖለቲካ ትንታኔዋ ስሰማና፣ እኛኑ ለማሳመን የሄደችውን ርቀትና ከንቱ ጥረቷን ሳይ ለሷም፣ ይህችን ሴት ለመለመለው የፓርቲዋ የነገ ዕጣ ፈንታው አዘንኩኝ፡፡ ለነገሩ ኢህአዴግ በአንድ ወቅትም ሁለተኛ ክፍል ቢሆንም ፖለሲያችንን እስካስፈጸም ድረስ ችግር እንደሌለበት በግልጽ ነግሮንስ የለ፣ እናም አንፈርድበትም፡፡

‹‹ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ›› እንዲሉ አባቶቻችን የዚህች ሴት ወሬና ፕሮፓጋንዳ እግዚኦ የአንተ ያለህ አሰኘኝ፡፡ የማታ የማታ ከዚህች የሕወሐት አባል ከሆነች ሴት ጋር የነበረንን ውይይት ምሽቱ እየገፋ በመምጣቱ ወሬያችንን፣ ሙግታችንን ቋጭተን መለያየት ግድ ሆነብን፡፡ እናም በሕመምና በሥቃይ ውስጥ የነበረችውን ጓደኛችንን ጥቂት አዋርተናት፣ አጽናንተናት ተሰናብተናቸው ከጓደኛዬ ጋር ጉዞአችንን ወደቤታችን አደረግን፡፡ ወደቤት እየሄድን ሳለንም ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ፡፡

ምን ዓይነት ቀን ዛሬ!! ጠዋት ቢሮ እንደገባሁ የሥራ ባልደረባዬ የሆኑ ቀንደኛ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ሰው ጋር ፌስ ቡኬን ከፍቼ በሊቢያ በአይ ኤስ ታረደው ሰማዕት የሆኑትን ወገኖቻችንን ምስል ሳሳያቸው ኢትዮጵያኖች ላይሆኑ ይችላሉ፣ ኤርትራዊ ወይም ሱማሌያውያን ሊሆኑ ቢችሉስ፣ ደግሞስ እነዚህ ወጣቶች በሰው አገር ከሚንከራተቱ አገራችን በዕድገት ላይ ነች፣ በርካታ ስራ ዕድል አለ ለምን በአገራቸው አይሠሩም እያሉ በወገኖቻችን ደም ላይ ሲሳለቁና ውስጤን ሲያበግኑት ዋሉ፡፡

‹‹አንበሳን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ›› እንዲሉ አበው ይኸው ደግሞ በዚህ ምሽት እሳት የላሰች እፍረትና ይሉኝታ የሚባል ነገር ጨርሶ የፈጠረባት የማትመስል እሳት የላሰች ካድሬ ስትሞግተን፣ ስታደርቀን አመሸች፡፡ ግን እነዚህ ሰዎች እንዴት ነው የሚያስቡት አለኝ እጅጉን አዝኖ፡፡ እንደው ፍቅር፣ ሰብአዊነትና ርኅራኄ የሚባል ነገርስ አያውቁም ማለት ነው፡፡ ሲል መልሶ እኔኑ በመገረም ሆኖ ጠየቀኝ፡፡ ወዳጄ ተወኝ ባክህ እኔም ውስጤ አሯል፣ ተኮማትሯል በማለት ልማታዊው የሃይገር ባሱ ሹፌር ጋር የገጠምኩትን አተካራዬን በአጭሩ ተረኩለትና ተሰነባብተን ተለያየን፡፡

ይህ የእኔና ጓደኛዬ ገጠመኝ መንግሥታችን ለሚመራው፣ ለሚያስተዳድረው ሕዝብ እያሳየ ያለውን አመላከት የሚያንጸባርቅ ለመሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ሕዝብ ደስታውንም ሆነ ኀዘኑን በቅጡ የሚጋራው መሪ ይፈልጋል፡፡ ከሰሞኑ በሀገራችን ላይ በደረሰው መሪሪ ኀዘን ግን ከመንግሥት በኩል እየተስተዋለ ያለው ነገር ሆድ የሚያስብስና ቁጣን የሚቀሰቅስ እየሆነ ነው፡፡ እናም በሥልጣን ላይ ላሉ መሪዎቻችንን ይህን ጥያቄ ደጋግመን ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡ ለምንድን ነው መሪዎች ለምትመሩት፣ ለምታስተዳድሩት ሕዝብ ፍቅር፣ ክብርንና ሰብአዊ ርኅራኄን የጎደላችሁ፣ የተራቆታችሁ፡፡ ለምንድን ነው ለሕዝባችሁ ጥያቄ፣ ቁጣና የእኛንም አድምጡን መልእክቱ ሁሌም እልክና ማስፈራራት የሚቀድማችሁ፡፡

በኃይልና በማስፈራራትስ እስከ መቼ ለመዝለቅ ይቻላችሁ ይሆን?! በሕዝባቸው ዘንድ ‹‹ታላቁ ነፍስ›› በመባል የሚሞካሹት ዕውቁ ታጋይና የህንድ የነጻነት አባት ማሕተመ ጋንዲ፣ ‹‹ከፍርሃት ከሚመነጭ ዐምባገነንነትና ጥላቻ ከሠለጠነበት ኃይል ወይም ሥልጣን ይልቅ ከፍቅር የሚመነጭ ሥልጣን ውጤታማና ዘላቂ እንደሆነ›› በአንድ ወቅት ተናግረው ነበር፡፡

በእውነትም ሕዝብን በመልካም ለመምራት፣ ለማገልገል ሥልጣንን የሚገራ፣ ልጓም ኾኖ የሚቆጣጠር የፍቅር ልብ፣ ቅን ልብ ያስፈልጋል፡፡ የደቡባዊቷ አፍሪካ አገር የማላዊ የመጀመሪያ የሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆሴ ባንዳ፣ በአፍሪካዊው ብርቅዬ ልጅ በማዲባ የለቅሶ ስን ሥርዓትና ሽኝት ላይ ባደረጉት ንግግራቸው፡- Leadership is falling lin love with the people you lead or serve ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡ ይህን ቅን የሆነ ፍቅር ልብ ያልታደሉ፣ ከበጎነት ጋር የተፋቱ፣ ክፋትና ጭካኔ የነገሠባቸው መሪዎች በታሪክ ደጋግመን እንዳየነው የሥልጣናቸው/የኃይላቸው ምንጭ ፍርሃት የሚወልደው ጭካኔና ማንአለብኝነት/አምባገነንነት ነው፡፡ በመጨረሻም በግፍ ለተሰዉ ወገኖቻችን ፈጣሪ አምላክ የእረፍት ቦታን ያድላቸው! ለእኛና ለሕዝባችንም ፈጣሪ ጽናትንና መጽናናትን ያድልን ዘንድ በመመኘት ልሰናበት፡፡

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>