Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ማሞ ሌላ ፎቶግራፉ ሌላ የፍራንክፈርቱ የኦህዴድ ስብሰባ በልጅግ ዓሊ


የመረጃ ግብአት …በ5 ኛው ቀን ዘመቻ …የዘመቻ ”ወሳኙ ማዕበል ”አበይት ክንውኖች ዳሰሳ !ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል

* የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

* ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል

* በጦርነቱ መካከል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ። በጥብቅ በታጠረው የሳውዲ ድንበር ወዲህና ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጦረነቱ እሳት መካከል በአጣብቂኝ ውስጥ ስለ መሆናቸው በግል የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በሳውዲ የመን ድንበር በባህር ጠረፎች ከፍተኛ የእግረኛና የባህር ኃይል ሰራዊትና የሜካናይዝድ ጦር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል

* በሳውዲ ድንበር ፣ በጀዛን እና በኤደን የባህር ወሽመጥ በባብ አልመንደብ አካባቢ የባህር ኃይልና የምድር ጦር ዝግጅቱን አስመልክቶ የተጠየቁት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ” በጦርነት ውስጥ እያለህ ይህ መሰሉ ዝግጅት የተለመደ ነው! ” ብለው መልሰዋል

* የምድር ጦር በሚመለከት በአንድ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዠን የተጠየቁት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ በሳውዲ በኩል የምድር ጦር ለማዝመት እስካሁን ውሳኔ አለመደረሱን ጠቁመዋል

* የየመን ፕሬ አብድልረብ መንሱር በሳውዲ ስደት ላይ ሆነው በኢምሬት የየመን አንባሳደር አድርገዋቸው የነበሩትን አህመድ አሊ አብደላ ሳላህን ከስልጣን አባረሩ ። አህመድ አሊ በአባታቸው የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የጦር መኮነን ነበሩ ። በኢምሬት አምባሳደር የተሰጣቸው በፕሬ አብድልረቡ ሲሆን ከነበሩበት ቁልፍ የጦር መሪነት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦታ ለማሸሸት ታስቦ ነበር ። አህመድ የፕሬ አብድልረቡ ወዳጅና የአሁን ሁነኛ ባላንጣቸው የሆኑት የቀድሞው ፕሬ የአሊ አብደላ ሳላህ የብኸር ልጅ ናቸው ፣ ከቅርብ ወራት ጀምሮ አህመድ ከአባታቸው ጋር ሆነው ፕሬ አብድልረቡን ለማውረድ የሁቲ አማጽያንን በመደገፍ መሪውን አሽቀንጥረው የመንን ለዛሬ መከራ እንደዳረጓት ይወነጀላሉ

* ባሳለፍነው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2007 በግብጽ ሻርማ ሸክ የተደረገው የአረብ ሊግ ስብሰባና ውጤቱ የአረብ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው እየተዘገበበት ይገኛል

* እዚህም እዚያም የቃላት ጦርነቱ ተጋግሟል …
===========================

* የሁቲ አማጽያን የሳውዲ መራሹን የጦር አውሮፕላን ጣልን ይላሉ ፣ የሳውዲ መራሹን ጦር ቃል አቀባይ በአንጻሩ የሁቲ አማጽያን ከዚያ የሚያደርሰውን አቅም በመጀመሪያ ቀን የአየር ድብደባ ብቻ አክሽፈነዋል በማለት በተዋጊ ጀቶቻቸው ላይ ጥቃት አለመድረሱን በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል

* በየመን የሁቲ አማጽያንን በሳውዲ መራሽነት የተጀመረው የአየር ድብደባ እንዲያቆም ከሚፈልጉት ሀገራት መካከል ቀዳሚ የሆነችው የራሻው ፕሬ ፑቲን ለአረብ ሊግ ስብሰባ በላኩት ደብዳቤ አረብ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ሰላምን ለማምጣት ከጦርነት ውጭ ያለውን የሰላማዊ መንገድ አማራጭ ይጠቀሙ ዘንድ መክረዋል

* የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዑድ አል ፈይሰል ግን የፑቲንን መልዕክቱን ተቃውመዋል ። በኢራን የሚደገፈውን በሶርያ የአሳድን መንግስት የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ በራሽያ ስንቅና ትጥቅ ይደገፋል ሲሉ የራሻን ተቃርኖ መንገድ ላይ የሰላ ሂስ ያቀረቡት ልዑሉ የራሻው ፕሬ ፑቲን ከአረብ ሀገራት ጋር የቆየ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ንግግራቸውን አርመው አቋማቸውን ይፈትሹ ዘንድ አሳስበዋል።

* ከኢራን እርዳታ በማግኘት የሚታሙት የሽምቅ ተዋጊው የሀማስ መሪዎች ሳውዲን ጭምሮ የ10 አረብ ሀገራትን ዘመቻ ሲደግፉ የኢራንና የሶርያ መንግስት ደጋፊ የሊባኖሱ የሂዝቦላህ መሪ ሸህ ሀሰን ነስርአላህ የሳውዲ መራሹን ዘመቻ በማውገዝ በተለይ በሳውዲ መንግስትን መወረፋቸው የሳውዲን መንግስት አስቆጥቷል

* በሊባኖስ የሳውዲ አምባሳደር አሊ አዎድ አሲሪ ጭብጥ የሌለው ሀሰት ነው ያሉት የሂዝቦላሁ ሀሰን ነስርአላህ ንግግር ሂዝቦላህ የሚወክለውን የኢራን አቋም የተንጸባረቀበት አሳሳች መልዕክት እንደሆነ ለአረብ ኒውስ አስረድተዋል

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

የእነብርሃኑ፣ ፍቅረማርምና እየሩሳሌም የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል

$
0
0

‹‹ተጨማሪ ምርመራ ይቀረኛል›› መርማሪ ፖሊስ
‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ››
ተጠርጣሪዎች
———-
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ሶስቱም ወጣት ተጠርጣሪዎች ችሎት ከመግባታቸው በፊት ሳቅ እና ፈገግ እያሉ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውሏል፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም የአንገት ልብስ (ስካርፍ) ያደረጉ ሲሆን እየሩሳሌም ጥቁር እስከርፍ አድርጋ ነበር፡፡

በመጀመሪያ ወደ ችሎት ተጠርተው የገቡት ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌም ሲሆኑ ከጠበቃ ዳዊት ነጋሽ በስተቀር ማንም መግባት አልቻለም ነበር፡፡ [እኔና ጥቂት ሰዎች ግን ከችሎቱ በር ትንሽ ርቀት ላይ ቆመን የፍርድ ቤት ሂደቱን ለማየት ጥረት አድርገገን በመጠኑ ተሳክቶልናል]
ጠበቃ ዳዊት ከችሎት በኋላ እንደነገሩን ከሆነ፣ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ አለመጨረሳቸውን፣ ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና ይሄንንም በማጣራት ላይ እንደሚገኙ፣ የቴክኒክ መረጃዎች (የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ) እንደሚቀራቸው፣ ለሽብር ተግባር ብር ሲቀበሉ እና ሲልኩ የነበረውን የባንክ ቤት መረጃ እየተከታተሉ መሆናቸውና ቢለቀቁ መረጃዎችን ሊያጠፉ ስለሚችሉ የተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ጠበቃ ዳዊትም መርማሪ ፖሊስ ይቀሩናል ሲል ለፍርድ ቤቱ ያቀረባቸው መረጃዎች ከተጠርጣሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ ሆነው በቃላሉ የሚገኙ ስለሆነ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤትን ጠይቆ ነበር፡፡ ጠበቃው ምክንያቱን ሲያብራራም፣ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ መረጃዎችን ፖሊስ እስከአሁን ሊያገናቸው ይችል እንደነበረ፣ ከባንክ የሚገኝ መረጃም በአጭር ቀናት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን፣ ግብረ አበሮች አሉ ከተባለም ግብረአበሮች የሚያዙት ተጠርጣሪዎችን በመያዝ አለመሆኑና ተጠርጣሪዎቹ ቢለቀቁም የተለየ ነገር እንደማይመጣ ተናግሯል፡፡

መርማሪ ፖሊስም ‹‹የጦር መሳሪያ ተይዟል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከእስር ቢለቀቁ ወደኤርትራ ሰው ወደመመልመል ስራቸው ይመለሳሉ›› የሚል ተቃውሞ በማሰማት የጦር መሳሪያ የታጠቀ የሰው ምስል ለችሎት ማሳየቱንና መሳሪያ የያዘው ግለሰብ ማን እንደሆነ በግልጽ እንደማይታይ ለዚህ ዜና ዘጋቢ ገልጾለታል፡፡

ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌምም ቃላቸውን፣ የፌስ ቡክና ሌሎች መረጃዎችን በምርመራ ወቅት ለፖሊስ መስጠታቸውን፣ መሳሪያ ከተባለው ነገር ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩንና ይሄም በግልጽ እንደሚታወቅ በመግለጽ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› የሚል ሀሳባቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በኋላ ብርሃኑ ተክለያሬድ ከጠበቃ ዳዊት ጋር ወደ ችሎት ገባ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ፣ ብርሃኑ ላይም ‹‹የጦር መሳሪያ ተገኝቷል›› የሚለውን ቃል ሳይደግም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ያረቀበውን ሀሳብ ለችሎቱ ማስረዳቱን ጠበቃ ዳዊት ይናገራሉ፡፡ ጠበቃውም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ያቀበረቡትን የተቃውሞ ሀሳብ ለብርሃኑም አቅርበዋል፡፡

ብርሃኑም በበኩሉ ‹‹ቃላችንን ለፖሊስና ለፍርድ ቤቱ ሰጥተናል፡፡ የቀረ ነገር የለም፡፡ የእስር ሁኔታችን ከህግ አግባብ ውጪ ነው፡፡ ‹‹ጨለማ ክፍል›› በሚባለው እስር ቤት መብራት 24 ሰዓት ይበራል፡፡፡ እኔ የዓይን ችግር አለብኝ፡፡ በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው ከታሰርኩበት ክፍል ወደ ደጅ የምወጣው፡፡ ቤተሰብና የህግ ጠበቃ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ከጠበቃ ጋር ሳልማከር ነው ቃሌን ለፖሊስ የሰጠሁት፡፡ የመብት ጥሰት አለ፡፡ ቤተሰቦቻችንን፣ ጠበቃና ጠያቂዎቻችንን መግኘት ይፈቀድልን፡፡ ሌሎች ከእኔ ጋር የታሰሩ እስረኞች ግን ቤተሰቦቻቸው ሲመጡ ለጥየቃ ይወጣሉ፡፡ በዚህ ላይ ትዕዛዝ ይሰጥበት፡፡ …መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ብሏል፡፡

[የዚህ ዜና ዘጋቢም ብርሃኑ ድምጹን ከፍ አድርጎ አቤቱታውን ለችሎቱ ሲያቀርብ በከፊል ለማየትና ለመስማት ችሏል]
የችሎቱ ሴት ዳኛም የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንዳለበት ጠቁመው፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከሃይማኖት አባቶቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚል ትዕዛዝ በቃል ሰጥተው በብርሃኑም ላይ የ28 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሠጥተዋል፡፡

11051795_1627470747472682_860060966412380416_n

የአባይ ግድብ እና የወያኔ አጣብቂኝ በካርቱም ውል ሲጠብቅ የምንሊክ ሳልሳዊ የሳምንቱ መልዕክት

ጠንካራነትን ብቻ ሳይሆን ደካማነትንም መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ -ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

የራስን እና የተፎካካሪን ስልትና ስትራቴጂ አለማስላት፣ የህዝብንና የሀገርን ፍላጐት አለማስቀደም፣ የመንገዶችን ኮረኮንችና ሊሾነት አለመለየት አባዜዎች ሁሌ እንደተፈታተኑን አሉ፡፡ ባለፉት የትግል ጊዜያት ብዙ አይተናል:: ብዙ ታዝበናል:: ብዙ ጉዳዮች አስደምመውናል:: ጠንካራነትን ብቻ ሳይሆን ደካማነትንም መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ አለመብሰል አለመሰልጠን እንደተገኘው መገስገስ ትግሉን በትንሽ ድል መወጣጠርና በትንሽ ሽንፈት መፍረክረክ ተጋጣሚን መናቅና ወሬን/አሉባልታን እንደ አቋም ወሱድ በሚደረገው ትግል ውስጥ ከባድ አደጋ አለው::የራስን ርእዮት አለም አጥርቶ አለማወቅ እና የፖለቲካ እውቀት ማጣት በሚፈጥረው ድንጋጤ ራስን ፋይዳቢስ ማድረግ ይከተላል::

አለም ወደ ሃያሁለተኛው ክፍለዘመን በሰለጠነ ፖለቲካ እየገሰገሰ ባለበት ዘመን ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን በመጠላለፍ እና በመኮራኮም በሆድ አደርነት እና በስሜታዊነት መሞላት ነገሮች ሁሉ እልህ ተሞልተው ከአዱ አዘቅት ወደ አንዱ አዘቅት መረማመድ ሆኗል::አለመብሰላቸውን እንደ እውቀት ይዘው ግራ የተጋቡ የፖለቲካ እውቀት የሚያጥራቸው ሰዎች በፖለቲካ አለም ትግሉ ሲያደናብራቸው እና ሲያንገዳግዳቸው ሰበብ ስለሚፈእጥሩ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬን እንዲፈጠር መንገድ ይከፍታሉ::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ የምንግደድበት ወሳኝ ወቅ ላይ መሆናችን ብስለታችን እና ጥንካሬያችንን መለካት ይጠበቅብናል::

አለመብሰላችን አለመሰልጠናችን ውይይቱም፣ ድርድሩም፣ ፉክክሩም ሌላውን በማጥፋት ወይም በመጥለፍ ላይ የተመሰረተ ይሆንና ጤናማ ጉዞ አይሆንም፡፡ ጥንትም እንደዚያው ነበር፤ አሁንም ቅኝቱን አልቀየረም፡፡ በዚህ ቅኝት ላይ የመከፋፈል ዜማ ሲጨመርበት ለባላንጣ ሲሳይ የመሆን አባዜ ይከተላል፡፡ ማ ለምን ይህን አደረገ? ምን እየተጠቀመብኝ ነው? ብሎ ማሰብ ያባት ነው!ተፈጥሮውን ማሳየት የሚበጀውና የሚያዋጣው አንዳንዴ ብቻ ነው፡፡በወሳኝ ወቅት ላይ ወሳኝ ትግል እና የሰከነ ፖለቲካ ማራመድ አሌ የማይባል ሃቅ ነው::የማይበጅ ፖለቲካ ወገንን ያሳፍራል:: የአንድነት እና የጋራ ፖለቲካ በበሰለ መልኩ ይዞ በትግል ውስጥ መራመድ ወገነን ያኮራል::ያለዉን የአለም ስልጡን ፖለቲካ እናጢን:;ከኋላቀር ፖለቲካ ራሳችንን እናውጣ::

በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ከ60 በላይ ቆሰሉ :: አውቀው ነው ስደተኞቹን የደበደቡት ለሞቱት 45 ኢትዮጵያዊያ ሳዑዲ ተጠያቂ ናት…መደብደቧን አመነች በግሩም ተ/ሀይማኖት :-

$
0
0

ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም በዛ ካምፕ ውስጥ የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊን መሆናቸው ግን የታወቀ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሄጄ ካምፑን እንዳየሁት እኔም የማውቀው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ብቻ እንደሚያርፉበት ነው፡፡ የሞቱትን ነፍስ ይማር!!!! የተቀሩት ኢትዮጵያዊያንስ እጣ ፋንታ ምን ይሆን? ወገን ድረስ ኡኡኡኡኡኡ!!!!!!

ትላንት ንጋት ላይ በሰሜናዊ ምስራቅ የመን ሀጃ አካባቢ በተደረገ የአየር ድብደባ አየር የ International Organization for Migration (IOM) ካምፕ ላይ ጥቃት ያደረሱት የሳዑዲ አረቢያ የቶር ጀቶች መሆናቸው ታወቀ፡፡ የሳዑዲ መንግስት ባለስልጣናትም ድብደባው በእነሱ ጀት መፈጸሙን አምነዋል፡፡ ድብደባው ግን ሆነጅ ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ የሚያሳይ ፍንጭ አለ፡፡ ቦታው የ UNHCR ካምፕ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የ UNHCR አርማ ያለበት ድንኳን የተጣለበት መሆኑ እና የ UNHCR አርማ እየተውለበለበ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በእስከ አሁን ሁኔታ በጨለማ ሲደበድቡ ቅንጣት ስህተት አልነበረም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አርማውን አላየንም አይባል ድብደባው የተፈጸው ንጋት ላይ ነው፡፡ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ነው እየተመላለሱ የመቱት፡፡ ይሄ ምን ያሳያል እስኪ መንግስት ካለን መብታችንን የሚጠይቅልን ከሆነ ይሄን ይጠይቅ…..እባካችሁ ወገን እያለው ወገን እንደሌለው ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው የትም እየረገፈ ላለው ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ድምጽ እናሰማ፡፡ እባካችሁ የተኙትም ይንቁ ጠግበው ተገልብጠው እያደሩ ወገን እነሱ ባንኮራፉ ቁጥር እየረገፈ መሆኑን ይወቁት ይህን የሰው ልጅ ላይ የደረሰ አሰቃቂ እልቂት ያላየ ይይ ሼር አድርጉ……..በሁኑ ሰዓት የአየር ጥቃቱ ከወታደራዊ ተቋም ወደ ሲቪሉ ህዝብ እየወረደ ነው፡፡ በርካታ ሲቪሎች እየሞቱ ነው፡፡11081390_1571554886449042_1885173302700383718_n
ግሩም ተ/ሀይማኖት

በቤተ መንግስቱ፤ ሰማይ ጠቀስ መንታ ህንጻዎች ሊሰሩ ነው (ዳዊት ከበደ ወየሳ –ዘና ዜና)

መቼም የማይነጥፈው የነዚህ ልጆች ፍቅር –ዳንኤል ፈይሳ

$
0
0

ይሄንን ፎቶ ሳይ ያስታወሰኝ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዕከላዊን ሲኦል ጊቢ የረገጥኩበትን ቀን ነው። በዛን ቀን በጠዋቱ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ብዙዎች ተገኝተናል። ዕለቱም ዞን9ኞችና ጋዜጠኞቹ የማዕከላዊ ሲኦል ቤትን የምርመራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ክስ የሚመሰረትባቸው ቀን ነው። ምን ብለው ይከሷቸዋል ወይስ የሚከሱበት ምክንያት ስለሌላቸው ይለቁዋቸው ይሁን? የሚለው ጥያቄ በአእምሮዬ እየተመላለሰ ነበር።

በዛንው ቀን እንዲሁ አንድነት ፓርቲ በእነሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ የማዕከላዊውን የፀረ- ሽብር ግብረ ኋይል የምርመራ ክፍል ኋላፊ የሆነውን ኮማንደር ተክላይን በ24 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት አላቀረባቸውም ሲል ከሶት በዕለቱም ፍርድ ቤቱ ይዞዋቸው እንዲቀርብ አዞት ስለነበር እነሱም ያሉበትን ሁኔታ ለማየት አብዛኞቻችን( ሁላችንም ያላልኩት ከእኛ ያልተናነሰ በመጭረሻ እንዳየነው የደህንነት ሰዎች በመሀከላችን ተሰግስገው ስለነበር ነው በወቅቱ) ከፍተኛ ጉጉት አድሮብናል።

ኮማንደር ተክላይም እጁን ኪሱ ከቶ ከስንት ሰዓት ጥበቃ በኋላ ብቻውን ተከሰተ አቅርባቸው ያለው ፍርድ ቤትም አለማቅረቡ ትክክል እንደሆነ የሚያስከስሰው ጉዳይም እንደሌለ ፈርዶ ጀግኖቻችንን የማየት ጉጉታችንን ቆረጠው።

በዚህ ተበሳጭተን ከፍርድ ቤቱ ወጥተን የተለያየ ግሩፕ ሰርተን ስለነበረው ነገር እንዲሁም ዞን9ኞችን ከሰዓትም ቢሆን ያቀርቡዋቸዋል ብለን እዛው ለመጠበቅ በምንነጋገርበት ወቅት ከፍርድ ቤቱ የወጣች አንዲት ፒካፕ መጥታ ከፊት ለፊታችን ገጭ እንዳለች ከየት እንደመጡ ያላወቅናቸው ደህንነቶች ከበውን ከመሃል 6 ልጆችን ለቅመውን የተደበቀውን ቦንብ ታወጣለህ እያሉ ፒካፗ ላይ እያዋከቡ ይጭኑን ጀመር።

እየወሰዱንም እንዳለ ክሳችንን እዛው ፈጠሩልን ክሳችንም የነበረው ከተደበቀው ቦንብ ተቀይሮ ወደ ኮማንደር ተክላይን ልትጠልፉት ለማገት እንደተዘጋጃችሁ መረጃው እንዳላቸው እየነገሩንና እያስፈራሩን ማዕከላዊ ሲኦል ግቢ ደረስን ወደ ምርመራ ክፍል እንዳስገቡን ከፊት ለፊታችን ያላሰብነው ነገር ተፈጠረ። እነኛ ስንጠብቃቸው የነበሩ ወጣቶቹ ልጆች ከፊታችን ተሰልፈው በአንዲት ባስ ሊጫኑ መጡ እነሱም እንደተመለከቱን ምን ተፈጠረ፥ ምን ሆናችሁ በሚል በእጅ ለመግባባት መልዕክት መቀያየር ያዝን የነበርንባት ክፍልም ጠባብ ስለነበረች እየተገፋፋም ከነሱ ጋር ሰላም ለመባባል ስንሞክር በሁኔታው የተበሳጩት ደህንነቶች ጋር አርፋችሁ ተቀመጡ በሚል ግብግብና እሰጣ ገባ ውስጥ ገባን ማነው ጀግኖቹን አስከ ግርማ ሞገሳቸው አይቶ የሚቀመጠው ባይሆን ይፎክራል እንጂ። በጣም ደስ ብሎን ስለነበር እነሱን በማግኘታችን እርስ በእርስ የነበረን የአይዞን ባይነት ቃላት ሳንለዋወጥ በምልክት ልውውጦች መግባባታችን ሀሴትን የሚፈጥር የጋራ የትግል አጋርነትን የሚያበስር በ20 እርምጃዎች መሀል የተፈጠረ አሁን በህሊናዬ ሳስበው የሚታየኝ ስዕል የሚያምር በምርጥ ዳይሬክተር የተሰራ የማይም ትወና የሚመስል መስተጋብር ነበረው። ደህንነቶቹ በኢትዮጵያ ምድር እንደሚፈሩ ሁሉ ረስተነው ነበር።

ይሄን ደስተኝ ፍቅርን የሚረጭ ሩህሩህነትን የሚለግስ ፈገግታን ብርታትን የሚያወርስ የፊትና የእጅ እንቅስቃሴ ጣቶቻቸውን እየሳሙ ያሳዩን የነበረው የእንወዳችኋለን መልዕክቶቻቸው የማይነጥፈውን ለብዙዎቻችን የሚተርፈውን ከፊታቸው ላይ የሚነበበውን ለሰው ልጅ ያላቸውን ጥልቅ ክብርና ፍቅራቸውን የተመለከትኩበት ሁሌም ከህሊናዬ እንዳይጠፋ ሆኖ የታተመውን የወዳጅነት የፍቅር ልግስናቸውን። ያኔ ነበር ከማሂና ከኤዶም ፥ ከበፍቄና ናቲ፥ ከአቤላና ዞላ፥ ከአጥኔክስና ተስፍሽ እንዲሁም ከአስሚቲ ከትውልዴ ባለራዕዮች የተመለከትኩት።10407033_645016998932092_2014640865301243473_n

11058668_645016958932096_4398133810331699922_n


የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ የሳምንቱን ዜናዎች እና የዜና ሃተታዎች :-የአቶ በቀለ ገርባ መፈታት –የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አስቂኝ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሎ

$
0
0

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ የሳምንቱን ዜናዎች እና የዜና ሃተታዎች :-የአቶ በቀለ ገርባ መፈታት – የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አስቂኝ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሎ – የድምጻችን ይሰማ የሳንቲም መሰብሰብ እና በራስ ላይ የመቆጠብ የትብብር መንፈግ ጥሪ ተግባራዊነቱ እና ስኬቱ – የትግራይ ምርጫ በሕወሓት እና በአረና መድረክ መካከል የሚደረገው ፍጥጫ – የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ ውሎ እና የሕወሓት ፖሊሶች ..እንዲሁም ሌሎች ዘገባዎችን በሙዚቃ አጀብ ያካተተው የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ ያድምጡት ዘንድ ተጋብዘዋል::

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ!!

$
0
0

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ክሱን ያቀረቡት ወገኖች የአንድነት ፓርቲን በመወከል ክስ ሊያቀርቡ አይችሉም ብሎአል። ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ህወሃት ኢህአዴግ የሰጠውን የፖለቲካ ውሳኔ ማስፈጸሙን የገለጹት የፓርቲው የቀድሞ አመራር አቶ አስራት ጣሴ፣ የዛሬው የፍርድ ቤት ውሳኔም ህግና ደንብን የጣሰ ነው ብለዋል።

የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባላት አሁንም እንዳሉ የገለጹት አቶ አስራት ፣ ሁሉንም የፍርድ ቤት ሂደቶች ካጠናቀቁ በሁዋላ፣ ተቃውሞአቸውን በሌሎች መንግዶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ገልጸዋል። አቶ አስራት ጣሴ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ሃሳብ እንደሌላቸው ገልጸው፣

ትግሉን የሚወስነው የኢትዮጵያ ህዝብና በደሉ ነው ብለዋል። ህዝባዊ አመጽ አንድ የሰላማዊ ትግል መንገድ መሆኑን የገለጹት አቶ አስራት፣ ከዚህ በሁዋላ የሚመጣውን እስከ ሞት የሚደርስ መስዋትነት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ አስራት ሰላማዊ ትግልን የማይቀበሉ ህዝባዊ አመጽን ይጋብዛሉ የሚባለው ትክክለኛ አባባል መሆኑን ገልጸው፣ ህውሃት ኢህአዴጎች ወደ ህሊናቸው ተመልሰው የተካረረውን ጉዳይ ወደ ውይይት እንዲወስዱት መክረዋል።

ገዢው ፓርቲ ፍትሃዊና ነጻ ምርጫ ያካሂዳል ብለው እንደማያምኑም አቶ አስራት አክለዋል።10993446_776696872415249_4423248027273833496_n

ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወጥተናል!! –ተክሌ በቀለ

$
0
0

ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡ እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡

ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!

ታላቋ ምእራብ አፍሪካዊት ሃገር ናይጀሪያ እዚህ የደረሰችዉ ዉድ ዋጋ ከፍላ ነዉ፡፡ከናይጀሪያም በላይ ዋጋ ብንከፈልም በልተዉ በማይጠግቡ በሎች ትግሉ እየተነጠቀ ዛሬም እዛዉ ላይ ነን፡፡ታላቅዋ የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ ሀገረ ኢትዮጵያ በልማት ስም ክብሯ እንዲወርድ እየተደረገች ትገኛለች፡፡እናም በዲፕሎማሲ፤በዲሞክራሲ፤በኢኮኖሚም ይሁን በሁለንተናዊ ልማት የአለም ማህበረሰብ በአፍሪካ ትኩረት ናይጀሪያ ሆናለች፡፡ኢትዮጵያ የምትፈለገዉ ለክፍለአሁጉሩ የደህንነት አጋርነት ብቻ ነዉ፡፡

የናይጀሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና(የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ትብብርና ዉህደት ያስከተለዉን ዉጤትም ልብ ይሏል) የተወዳዳሪ ግለሰቦች ሚና ቀላል ባይሆንም ለናይጀሪያ ተስፋ የሆናት ግን ህዝቡ ነዉ፡፡የኢትዮጵያችንም የለዉጥ ተስፋ ህዝቡ ነዉ፡፡በዚህ ወቅት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍም የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከስሜታዊነት የጸዱ በሳል ወጣቶች ለለውጡ በብዛት ማፍራት ይጠበቅብናል:: ‪- ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

ተቀምጦ ከማላዘን – የወሬ ትውልድ ከመቀፍቀፍ – የስሜት ናዳ ዶፍ ከማዝነብ – ብሎም በባዶ ሜዳ ስንፍናን ከማዛጋት ይሰውረን:: ኢትዮጵያችን አፈና የተንሰራፋባት.. ጭቆና የነገሰባት አገር … ነፃነት በእጅጉ የተሸረሸረባት አገር ከሆነች አመታቶች ተቆጠሩ::ወያኔ ህዝቦች የምንመኘውን ያላሟላ የዜጎችን ነፃነት ማክበር ሸክም ሆኖ የሚያስብ ቢያንስ ቢያንስ በታጋሽነትና በመቻቻል መንፈስ ትችቶችን ለማስተናገድ በቂ ችሎታ እና ዝግጁነት የሌለው አምባገነንነት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሚሰነዘሩ ወቀሳዎችን እና የዜጎችን አቤቱታና የምሁራንን ትችት ለመስማት ተግስት የሌለው በጣም አሳሳቢ ነው። ወያኔ ከዚህና ከዚያ አንድ ሁለት ትችት ብቅ ብቅ ሲሉ ይበረግጋል። አሸባሪ ብለው ለመፈረጅ የሚቸኩሉም ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ጥቂት አይደሉም።በሃሳብ የተለዩትን ሁሉ መወንጀልም ቀላል እየሆነ ነው።የዚህ ሰላባ የሆኑት በአብዛኛው ወጣቶች ናቸው::
ለሃገራዊ እና ህዝባዊ አጀንዳ አንዳችም ልዩና መሰረታዊ ዓላማ ከጀርባው ሳይኖር ወዳጅነትን መፍጠር መባረክ ነው፡፡ ለሀገር ለወገን የሚበጅ እፁብ ነገር ነው፡፡ ስብዕና፣ ዕውቀት፣ ምጥቀተ-ህሊና፣ የጋራ-ቤትን ማፍቀር፤ መሰረታዊ መነሻዎችና ማደጊያዎች ናቸው፡፡ በተለይ ወጣቱ ከመሰረት ከንጣፉ እኒህን ጉዳዮች ማወቅና መገንዘብ መቻሉ ደርዝ ያለው ነገር ነው፡፡ መተሳሰብ፤ መወያየት፣ ማንበብና መናበብ፣ በሥርዓት መኖር፤ የጋራ ምጥቀተ-ህሊና ያስፈልገዋል;የሀገራዊነት መሰረቱ ይሄው ነውና::ይህ ሃገራዊ መሰረት በወጣቱ ውስጥ እንዳይኖር ወያኔ በመሰሪ ተግባሩ እየሸረሸረው ነው::ወጣቱ ለትምህርት ዝግጁ እንዳይሆን ለመንቃት እንዳይተጋ ስለሃገሩ ያገባኛል እንዳይል ራሱን ምንጊዜም ለመለወጥ እንዳይታታር አርቆ ማስተዋል ጐዳና ላይ እንዳይወጣ በስፋት በወያነ እየተሰራ ነው፡፡ በእርግጥ አገር ተረካቢ ትውልድ እንዳይፈጠር ወያኔ በአንድ ለአምስት ስም ከቤተሰብ ጀምሮ በመማሪያ ተቋማት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ዕጁን አስገብቶ ወጣቱ ለአካለሥራ መብቃት ጋር እንዳይበቃ እና ከዘመኑ ስልጣኔ ጋር እንዳይተሳሰር እኩይ ስራዎችን በመስራት ደፋ ወና እያለ ማህበራዊ ዝቅጠት በመፍጠር ይህንን ጥሰው ያለፉትን በማሰር ተግባራት ላይ ተሰማርቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ለተያዘው ትግል ዋና ተሳታፊ እና ትልቅ ስራ ሊሰራ የሚችለው ወጣቱ ነው::ወጣቶች ስሜታዊ እና ያለፉትን አቀንቃኞች የሚከተሉ እንዳይሆኑ በነጻነት ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እንዲበስሉ ማበረታታት ግድ ይለናል::በስፋት እና በግንባር ቀደምትነት ወጣቱን ያላሳተፈ ተግባራዊ ስራ እሰራለሁ አሊያም ወጣቱን ተጠቅሜ ወደ ስልጣን እመጣለው የሚለው ሃሳብ ጊዜ ያለፈበት እንደሆነ በማወቅ ወጣቱ በአገር ጉዳይ ላይ ግቡን የሚመታ እና የሚሳተፍበት ሃገሩን የሚመራበት መንገድ ውስጥ ማስገባት ችላ ሊባል የሚገባው ጉዳይ አይደለም::የዕውር የድንብር አለመሄድ ትልቁ ጥበብ ነው፡፡ ወጣቱ ህይወትን የሚቃኝበት ኮምፓስ ያሻዋል፡፡ ሌሎችን የሚማርክበት ማግኔት ያለው እንዲሆንም እንጠብቃለን፡፡ በዚህ የመረጃ ዘመን መረጃ – የለሽ ትውልድ እንዳይፈጠር ሁሉም ዜጋ አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይገባል፡፡እያንዳንዳችን በሰፋት ከቀድሞ በበለጠ የወጣቱን ዐይን ልንከፍትለት ይገባል::እንዲያው በደፈናው ትውልድን መራገም ማብቃት ይኖርበታል፡፡ተቀምጠን ከምናላዝን ተንቀሳቅሰን ለነገ ለውጥ እናምጣ ነው ጉዳዩ::

የሠላማዊ ትግላችን የፓለቲካ አመራሮችን ውጭ እንዳይወጡ በማገድና በምርጫ ቦርድ ፖርቲዎችን የማፍረስ ሴራ በፍጹም አይቋረጥም፤ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

$
0
0

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፤ ከውጭም፣ ከውስጥም፣ ያላችሁ፦

ሕውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም በማለት በብቸኝነት በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ሚዲያዎች በሕዝቡ እያላገጠ በስተጀርባ ግን የፖለቲካ አመራሮችንና የፖርቲዎችን ሕልውና ማሣደድ ቀጥሎበታል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት የአንድነት ፓርቲን ማፈራረሣቸው አልበቃ ብሏቸው አሁን ደግሞ በትናትናው ዕለት የሰማያዊ ፖርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ውጭ እንዳይመጣ በማንአለብኝነት በእብሪት በመወጠር ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮኘላን ማረፊያ ከልከለው መልሰውታል፡፡ በሃሰት ሚዲያዎች ሕዝቡን አፍኖ በመያዝ አገዛዙን ለመቀጠል እየተውተረተረ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት ቆራጥ የሆኑ የሠላማዊ ትግል አመራሮችንና አባላትን እያዋከበ ትግሉን ለማሰናከል ከመቼዉም ጊዜ በላይ ቀጥሎበታል፡፡ የኢንጂነር ይልቃል የውጭ በሪራ ጉዞ የመከልከል ህገ-ወጥ ድርጊትም ከነዚህ ዕኩይ ተግባራቸው አንዱ ነው፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናትና የቢሮ ኃላፊዎቻቸው በመንግስታዊ መዋቅር ሥልጣናቸዉን በመጠቀም የተለመደውን የማታለልና የህገ-ወጥነት ተግባራቸውን ተግተው ቀጥለውበታል፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ህልውና ቀምቶ ለታማኝ ግለሰቦች በመስጠት የሚደረገውን የነፃነት ትግል ለማኮላሸት በሃሰት በመወንጀል በህገ-ወጥነት አባሎቻቸውን ማሣደድና ማሠር፣ ሃብታቸውን መዝረፍ፣ ግድያ፣ እስር፣ ማዋከብና፣ ከቦታ ማፈናቀል የዕለት፡ዕለት ተግባራቸው ሆኗል፡፡

ውድ ነፃነት ናፍቂ ኢትዮጵያውያን፦

የኢህአዴግ ዘረኛ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና/ስቆቃ ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት፣ በአንድ ድምፅ ፣አገዛዙን መቃወም ይገባናል፡፡ አምባገነኖች በሚያደርሱብን ጭቆና እና አስተዳደራዊ ግፍ ተሠላችተን ተስፋ መቁረጥ በየትኛውም መስፈርት መፍትሔ አይሆንም፤ መፍትሔው ጨቋኙን ኃይል ታግሎ አሸቀንጥሮ መጣል ነው፡፡ ስለሆነም የፖርቲዎችን ሕጋዊ ህልዉና በማሣጣት፣ ሠለማዊ ትግሉን በማደናቀፍና የፖለቲካ አመራሮችን ወደ ወጭ እንዳይወጡ በመከልከልና በተለያዩ የአገዛዙ የውንብድና ድርጊቶች ሠላማዊ ትግላችን ለአንድም ሰከንድ አይቋረጥም! እንዳውም የበለጠ እልህ እንድንገባና ትግላችንን አጠናክረን ድጋፋችንን ለሠላማዊ ትግል ኃይሎች የማቴሪያልና የሞራል ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በትናትናው ዕለት የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ውጭ እንዳይወጣ አገዛዙ በማንአለብኝነት ቢከለክለውም እኛ እዚህ በውጭ አገር ያለን ደጋፊዎችና አባላት በየከተሞች በወጡት የስብሰባ ቀኖች መርሐ-ግብር መሠረት በየዕለቱ በየቦታው በመገኘት መላው ደጋፊያችንና የነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ሁሉም በነቂስ በመውጣት ስብሰባዎቻችንን በደማቅ ሁኔታ ከመሪዎቹ ጋር ከአዲስ አበባ ዘመኑ ባፈራው የጥበብ ውጤት በመጠቀም እንድናከናውን በቂ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ሕዝባችንም በየስብሰባዎቹ በመገኘት ድጋፋን በበለጠ ሁኔታ እንደሚያሣይ አንጠራጠርም፡፡ በዚህ አጋጣሚም ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን፡፡

የአንድነትና የሠማያዊ ድጋፍ ማህበሮች በሰሜን አሜሪካ አስተባባሪ ኮሚቴ

አደባባዮቹ ወጣቶቻቸውን ናፍቀዋል ወራዙት ይአቅቡከ ( ያፈቅሩከ) –ዳነኤል ፈይሳ

$
0
0

ጊዜው 1997 ነው። አብዛኛዎቻችን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፥ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም ተመርቀን ስራ አጥተን ሰፈር ውስጥ የምንውል ስራ አጦችና ( በኢህአዲግ አባባል አደገኛ ቦዘኔዎች) ወጣትነት ጉልበታችንን በስራ ለመፈተን እየተንቀሳቀስን የነበርን ወጣቶች ትኩስ ኋይሎች ነበርን።

በወቅቱ በተነሳው የለውጥ እንቅስቃሴ አንዳችንን ከአንዳችን ሳይለይ በጊዜው የነበርነውን ሁሉ ማርኮን አጥብቀን በመከታተል በሂደቱ በተለያየ መልኩ ተሳታፊ ሆነን አገኘነው። በከፍተኛ ሁኔታ በለውጡ ማዕበል ውስጥ ሁላችንም እየተናጥን ነበር።

ለውጥ!የዚህ ትውልድ አባላት የሆንን በወቅቱ ምንም አይነት ይሁን እንጂ ለውጥ እንፈልግ ነበር። ለውጡም በምንም መልኩ ይምጣ አጠቃላይ መንግስታዊ ለውጥ ተካሂዶ ከማየት ባሻገር በአገር
ግንባታ ውስጥ መሰረታዊ የነበሩትን ጥያቄዎች የሚመልስ ለመሆኑ እርግጠኞች ለመሆን በብዙም አልተጨነቅንም። የተካሄደው የፖለቲካው እንቅስቃሴ ለውጡ ለውጡ እንዲዳፈን የተደረገበት መንገድ ትውልዱን በደንብ አገሩን እንዲያስባት አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ ነገር ጋዜጣ በመስፍን ነጋሽ በኩል ወደ አደባባይ የወጣው የትውልዱ የመጀመሪያ ጥያቄ የነበረው ይህቺ አገር የማን ናት የሚለው ነበር። ይሄንንም ጥያቄውን ሲያውጠነጥን አገሩ የጥቂቶች ሆና ነው ያገኛት ስለዚህም ትውልዱ የኔ የሚላት አገር እንድትኖረው ሻተ።

ምን አይነት ሀገር? የ1997 ምርጫ ትውልዱን ብዙ አስተምሮታል። በህዝብ ዘንድ የነበረው የስርዓት ለውጥ ፍላጎት እንዲዳፈን የሆነው እንደሀገር ምን ስላልነበረን ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በእጅጉ እንዲያብሰለስለው ሆኖዋል። ተብሰልስሎ ብቻ አልቀረም አልቀረም ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ራሱ በመብሰልሰሉ ውስጥ መልሱን አግኝቶት ነበር። ይኸውም የነፃ ተቋማት ያለመኖር ችግር
የለውጡን ፍላጎት እንዳዳፈነው ተረድቶታል።

ስለሆነም ነፃ የፍትህ ተቋማት፥ ነፃ ሚድያ፥ ነፃ የሲቪክ ተቋማት፥ ነፃ የመከላከያ ኋይል፥ ነፃ የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት ኋይል የተገነባች ሁሉም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ የሚፈቱባት
ሀገርን ሽቶዋል። ለመሻቱ ተግባራዊነት ደግሞ በዚህ ወታደራዊ ነፍጥ አንጋቢ አንባገነን ሁሉን ጨፍልቆ መውሰድ በሚፈልግ ስርዓት ውስጥ ሊተገበር እንደማይችል አረጋግጦዋል። የትውልዱ
ጥያቄ ሊመለስ የሚችለው አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ተረድቶዋል። ለውጡ እንዴት ይምጣ? ትውልዱ ባለፉት 10 አመታት በተለያዩ ወቅቶች እርስ በእርስ
በነበረው ግኑኝነት ለውጥ፥ ለውጥ ብሎ ደጋግሞ አንስቶዋል። ይህ ትውልድ አሁን ወጣትነቱ ወደ ማብቂያው እየሄደ ቤተሰብም አፍርቶ ወደ ጉልምስናው መጀመሪያ እየገባ ነው።

በወጣትነቱ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ የወጣትነት ዘመኑ መጨለም ሊጀምር እየዳመነ ነው። ትውልዱ የጥያቄዎቹ እንዲሁም የታሪኩ ባለዕዳ ነው። ያነሳቸውን ጥያቄዎችና የታሪክ ኋላፊነቱን የሚወጣበት ጊዜው አሁን ነው። ወጣትነቱ ከመጨለሙ በፊት ባለታሪክ የሚሆንበት ለነገው ትውልድ ለሱ ልጆች የታሪኩን የተፃፈ ገፅ የሚያነብበት የዕርጅናው ወራት ሲመጣ ለልጆቹ የሚተርከው የተፃፈ ገፅ እንዲኖረው አሁን ወደ አደባባዮቹ የመትመሚያው የመጨረሻው ጊዜ ላይ ነው።

ይህ እንዴት ይሆናል? ለውጡን በምን መልኩ ማካሄድ ይቻላል? ብሎ የደረሰበት መደምደሚያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን በሀገሩ ላይ በመተግበር ወደ አደባባዮቹ መትመም ያንተ የጦርነት አውድማ
አሲንባ ወይም ደደቢት አይደለም በሀገርህ ላይ ያሉት አደባባዮችህ ናቸው። ሀገር እንዳይኖርህ ሀገር አልባ ያደረገህን ስርዕት ከስሩ መንግሎ ማፍረስ ነው። ይህ ሲሆን ያኔ ባለታሪክ ይሆናል ጥያቄዎቹም ይመለሳሉ። ያኔ ታድያ የታሪኩ ባዶ ገፅ እየተገለጠ በሚነበብ፥ በሚተረክ የተፃፈ ገፅ ይሞላል።በጉልምስናህም ዘመን ኩራት፥ ክብር የሰው ልጆች ፍላጎት የሆነው ይኖርሃል፥ በማሻውም እድሜህ ለልጆችህ
የታሪክህን ገፅ እየገለጥክ ያኔ እነሱ በማንነታቸው ኮርተው የኔ ብለው የሚኖሩባትን ሀገር ዲሞክራሲያዊት፥ ፍትሃዊት፥ የነፃ ህዝቦች መኖሪያን፥ የሀገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ የቻልክ አባት መሆንህን ትተርክላቸዋለህ።

አርአያዎች ከየትም አትፈልግ የትውልድህ አባላት የሆኑት ያንተን የነፃነት ውልድ እያማጡ ያሉ አሉልህ። ተመልከት እነ አንዷለም አራጌን፥ ተመልከት እነ ሃብታሙን አያሌውን፥ ተመልከት እነርዕዮትን፥ ተመልከት ተመስገንን ያንተን ምጥ ሲያምጥ፥ ተመልከት እነ ማህሌትን፥ እነ ኤዶምን፥ እነበፍቄን፥እነ ናቲን፥ እነ ዘላለምን እን አቤልን. ……….ለአንተ ትውልድ ጥያቄዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። ምን ቤት አለህና ቤትህ ትገባለህ ያንተ ቤት አደባባዮችህ ናቸው። ለባርነት ማዶ አትመልከት ለነፃነትህ ወደ ራስህ ቤት ተመልከት።

እንደመደምደሚያ ይህ ትውልድ ብዙ ተብሎዋል በጫት የናወዘ፥ ከራሱ ባሻገር አገራዊ ራዕይ የሌለው ወኔ አልባ፥ አደገኛ ቦዘኔና ብዙ አልባሌነቱን የሚነግሩት ማንነት ተደርቦለታል። እሱ ግን እንደዚህ እንዳልሆነ የሚያስመሰክርበት አሁን ታሪክ 2007ን ሰጥቶታል። አብዮቱንት ተሸክመው የሚዞሩት እንኳን አልፈሩም ትውልዱስ ስለምን ይፈራል? እሱ ከትላንት አባቶቹ በምን ያንሳል? እንደ ቱኒዝያ፥
ግብፅ፥ ቡርኪና ፋሶ አቻዎቹ የለውጡ ባለቤት እንደሆነ ያረጋግጣል የሚል እምነት አለኝ አደባባዮቹም የሀገሩን ልጆች ወጣቶቹን ናፍቀዋል።

ወራዙት ይአቅቡከ (ያፈቅሩከ)

የኢህአዴግ ዘረኛ መንግስት ሊያደናቅፍ የሞከረው እና በዋሽንግተን ዲሲ በሰማያዊ እና የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች የተጠራው የሰማያዊ ፓርቲ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!!

$
0
0

የኢህአዴግ ዘረኛ መንግስት በሰማያዊ እና አንድነት የድጋፍ ድርጅቶች አስተባባሪነት በዋሽንግትን ዲሲ ከተማ የተጠራውን የሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ለማደናቀፍ የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ውጭ እንዳይወጣ አገዛዙ በማን አለብኝነት ቢከለክለውም፤ በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ በሽራተን ሆቴል የተጠራው ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያኖች በዛሬው ዕለት በቦታው በመገኘት በአገዛዙ በኩል እየተወስደ ባለው አስከፊ የውንብድና ድርጊቶች ሠላማዊ ትግላችን ለአንድም ሰኮንድ አይቋረጥም! እንደውም የበለጠ እልህ እንድንገባና ትግላችንን እና ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥል ያደርገናል ብለዋል። በዚሁ እለትም በተደረገው ስብሰባ ላይ ከፍተኛ ለሰማያዊ ፓርቲ በተደርገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ ለሰላማዊ ፓርቲ እና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ታጋዮች ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት እና አጋርነት ገልጸዋል!!

በዚሁ ስብሰባ ላይ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በስክይፕ ከአዲስ አበባ በቀጥታ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ወቅታዊ እንቅቃሴና የምርጫ ሁኔታ ምን ላይ እንድሚገኝ በሰፊው ለተሰብሳቢው በማስረዳት እና ከተሳታፊኢዎች ለቀርበላቸው ጥይቄዎች ሰፊ ማብራሪያ አይሰጡ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማሪያም በተጋባዥ እንግድነት ተገኝተው ለስብሰባው ተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የተለያዩ በውጭ አገር የሚገኙ ሚዲያዎች ተጋብዘው የነበረ ሲሆን ከኢትዮቲዩብ እና ከቪኦኤ በስተቀር ኢሳትን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች በቦታው አለመገኘታቸው ታውቋል።

ይሀው ስብሰባ በነገው እለት በቦስተን ከተማ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ከተሞች ስብሰባው በታቀደው መሰረት የሚቀጥል መሆኑን የታወቀ ሲሆን፤ በተለይ የኢህአዴግ ዘረኛ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና እና ስቆቃ፤ እንዲሁም በፓርቲዎች ላይ የሚካሂደው ወከባ እና እንግልት የበለጠ እልህ እና የትግል አጋርነታቸውን አጥናክረው እንድሚቀጥሉ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየገለጹ መሆኑ ታውቋል!!


የአባይን ልጅ ወሃ ጠማው በጎንቻው

አይ ይሄ ልጅ! (አትክልት አሰፋ)

$
0
0

እናት የለው አታነባ፡
ዘመድ ወዳጅ ውስጥ አይገባ፤
ምንም የለው፤ ጠያቂ አልባ፡፡
በከርቼሌ ተከርችሞ፡
ነብሱን ሰጥቶ፤ ውስጡ ታሞ፡
ህመም ቁስሉን ተሸክሞ፤
ስቃይን ሊቀበል፡
ጽናትን ሊካፈል
ባመነበት ሊኖር
ቆርጦ ሊገዳደር፤
ወስኖ ለራሱ፡
አምኖበት ከነብሱ፤
የሚኖረው ያ… ወንድሜ
መጣ ዛሬ በምናቤ፡፡
ወደኋላ ‘ንዳይጎትቱት፡
ብርታቱንም እንዳይነጥቁት፡
ሚስት ልጁን ተሰናብቶ
ሂዱ… ብሎ ተለይቶ፤
የቆረጠው ያ… ወንድሜ
ዛሬ መጣ በምናቤ፡፡
መምህር ነው ለጓዶቹ፡
ኩራት፡ ጋሻ ላጋሮቹ፤
ግምባር ቀደም ተፋላሚ፡
እውነተኛ… ተስፋ አላሚ፤
በከርቼሌ ተከርችሞ፡
ነብሱን ሰጥቶ ፤ውስጡ ታሞ፡፡
ሀገር ብሎ! ሙያ ብሎ! ህዝብ ብሎ!
ብቻውን ነው ተከልሎ
ጨለማ ውስጥ ተጥሎ፡፡

ለብርቱ ሰው (Iron man)
ሲጻፍ ኤፕሪል 2015 ቫንኩቨር (ካናዳ) ነበር

የመረጃ ግብአት…የ”ወሳኙ ማዕበል”ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች በነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* በ9ኛ ቀን በሳውዲ መራሹ ” ወሳኙ ማዕበል !” የአየር ማጥቃት ዘመቻ በየመን ሰማይ በተጠኑ ወታደራዊ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ አየር ድብደባው መቀጠሉን የዘመቻው መምሪያ ቃል አቀባይ ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ ናቸው ፣ ጀኔራሉ በዚሁ መግለጫች በወደብ ከተማዋ በኤደንም የሁቲ አማጽያ አልበገርላቸው ካለው የአካባቢ ሚኒሽያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውን አስረድተዋል

* ከሁቲ አማጽያንን ኤደንን እንዳይቆጣጠሩ በአካባቢው ሚኒሽያ በመሬት ቃታ እየሳበ እንቅስቃቀሴያቸውን ሲያሽመደምደው በሰማይ የህብረቱን ጦር በተጠኑ ኢላማዎች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በሚከወነው ድብደባ አማጽያኑን አቅመ ቢስ አድርጎ እንዳዳከማቸው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል

* ቃል አቀባዩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሰርጎ የሚገባባትን በሚዮን ደሴት Meon Island የሚገኙ የባህርና ሃይሉና የእግረኛው ጦር መሳሪያዊች በሳውዲ መራሹ የአየር ድብደባ ኢላማ ገብተው ተደምስሰዋልም ብለዋል

* በአየር ድብደባው ተስፋ የቆረጡና የተዳከሙት የሁቲ አማጽያን በመገናኛ ብዙሃንን ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን በማሳሳት ላይ ናቸውም ብለዋል ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* በሌላ በኩል እየተካሔደ ስላለው ዘመቻ ማብራሪያ የሰጡት በአሜሪካ የሳውዲ አንባሳደር አድል አልጃብሪ ዘመቻው በጥሩና በመጥፎ መካከል እንጅ በሱኒና በሸአ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ሚካሔድ ጦርነት አለመሆኑን ተናግርዋል። አምባሳደሩ በማከልም የሳውዲ መራሹ አረብ ሃገራት ዋና አላማ በኢራን በሂዝቦላህ የሚመራውን የሁቲ አማጽያን ከስልጣን አስወግዶ ፣ ህጋዊው የፕሬዚ አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው መመለስ ነው ብለዋል ። አንባሳደሩ የቀድሞው የየመን ፕሬዚ አሊ አብደላህ ሳላህን በሚመለከት ሲናገሩ አሊ አብደላ ሳላህ ከሁቲዎች ጎን መሰለፋቸው የተሳሳተ አካሄድ ነው ሲሉ ነቅፈውታል

በሳውዲ የመን ደንበር ድንበር መገዳደል …
============================

* በሳውዲ የመን ድንበር ባሳለፍነው ረቡዕ አንድ ድንበር ጠባቂ በሳውዲ የመን ድንበር ሁለት የድንበር ጠባቂ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ትናንት አርብ ተጨማሪ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ተጠቅሷል ። መረጃውን የድንበር ጦሩ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል አዎል ቢን ኢድ አል በላዊ አረጋግጠውታል

* የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የሟች የድንበር ወታደር ቤተሰቦችን ልዩ የሀዘን መልዕክተኞች በመላክ አጽናንተዋል

ከዘመቻው ድጋፍ እስከ የመንን መልሶ መገንባት ….
================================

* በሳውዲ ታላላቅ ምሁራንና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች በሳውዲ መራሹን የየመን አየር ድብደባ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው

* የመን ከሁቴ አማጽያን ጠርታ የፕሬዚደንት አብድል ረቡ መንሱር ሃዲ መንግስት በሁቲ አማጽያን የተቀማውን ስልጣን ተቀብሎ የመን ስትረጋጋ የባህረ ሰላጤው ባለ ሃብቶች 150 በላይ ፕሮጀክቶችን በመክፈት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ እቅድ መያዛቸው ተጠቅሷል
( መቸ ይመጣ ይሆን? ብቻ ለዚያ ቀን ያድርሰን …)

በየመን የኢትዮ ይዞታና የ” እውነት ፣ ውሸቱ” እሰጣ ገባ
===================================

* በየመን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት እንደደረሰበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምና መስሪያ ቤታቸው ከቀናት በፊት ፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ቢያስታውቁም የተላለፈው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል። በተባራሪ ጥይት በኢንባሲው የሚገኝን አንድ መኪና ጎማ መታ ተብሎ ጥቀሰት ብሎ ማቅረቡ የተጋነነ መሆኑን ከየመን ሰንአ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የኮሚኒቲ ሰራተኞች ለመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ተመላሽ ዜጋዎች በመመዝገብ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል ። የኢንባሲውን መደብደብ ዜና የሰሙት በቦታው ያሉትን የኮሚኒቲ ተወካዮች ሳይቀር በሚኒስትሩ ኢንባሲው ተጠቃ በሚል በቀረበው መረጃ ግራ የተጋቡ እንደነበር የአይን እማኞች ጠቁመዋል

* የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” በየመን ሰነአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት ደረሰበት!” ያሉትን ሰሞኛ ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበት አነጋጋሪ መረጃቸውን ተከትሎ ” ከአውስትራልያ የመጣች ታዳጊ 20 ሚሊዮን… ለገሰች !” እንደተባለችው ታዳጊ ወጣት ስጦታ ገንዘብ ምንጭ ዙሪያ የተደረገውን ያህል ሙግት እሰጣ ገባ የየመኑ ጥቀሰት ባይገንም ” እውነት ፣ ውሸቱ ” ግን ቀጥሏል
( አሜሪካ ቢሆን ይህ ይደምቅ ነበር ያሉኝ አሉ: ) )

* ከቀናት በፊት በኤደን የመን አድርገው ጅቡቲ የገቡት 30 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ተጠቁሟል ፣ ” ወደ ሃገር ቤት መግባቱ ለደህንነታችን ያሰጋናል !” ያሉት ግን ወደ ሶስተኛ ሃገር የሚሻገሩበትን መንገድ በመላ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን እናሰማላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ ናቸው !

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

( Cartoon / From Arabbews newspaper)

—- Nebiyu Sirak wrote —-

የመረጃ ግብአት …
ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል ” በ8ኛው ቀን ክንውኖች …
እና በየመን ሁከትና የኢትዮጵያውያን ይዞታ !
===========================

> ” ኤደን በሁቲዎች እጅ አልወደቀችም! ” የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ
> ” በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ተደብድቧል፣ 2000 ተመዝግበው 30 ጅቡቲ ገብተዋል ” ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም
> በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመግባት ፍላጎት አላሳዩም፣ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው፣ በፖለቲካ የሸሹት የምህረት ጥሪ ይደረግላቸውም እየተባለ ነው

8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ …
========================
ኤደን በሁቲ አማጽያን ስር መሆኗን አልጀዚራና የተለያዩ የአረብ መገናኛ ብዙሀን የጠቆሙ ቢሆንም ትናንት ማምሻውን በሪያድ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር ሆነው ለጋዜጠኞች ስለ 8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ የሰጡት የዘመቻው ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ኤደንን ለመያዝ ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ኤደን ሙሉ በመሉ በሁቲዎች ቁጥጥር ስር አለመውደቋን አስታውቀዋል።።

በ8ኛው ቀን የአየር ጥቃት ዘመቻ መግለጫ የሰጡት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በኤደን አካባቢ እግረኛ ጦር ጀምሯል ወይ ? ተብለው ተጠይቀው ፣ እግረኛ ጦር አለጀመሩን አስረግጠው ተናግረዋል ። በዚሁ መግለጫቸውም በኤደን ዙሪያ ስለተደረገውና እየተደረገ ስላለው የዘመቻው ክንውን ሲያስረዱ በዋናነት በምድርና በባህር የሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እንዳያገኙ መንገዶችን የመዘጋጋት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል። ከዚህ ባከፈ የእግረኛ ጦር ዘመቻ አለመጀመሩን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል ።

“ከወሳኙ ማዕበል” የአየር ጥቃቱን አፋፍሞ በቀጠለበት ሁኔታ በየመን የድንበር ከተማ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው አሲር ክልል በሚያዋስን ድንበር ግጭት መቀስቀሱ ተጠቁሟል። ባልታወቁ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስም ሰልማን አልመልኪ የተባሉ አንድ የበታች ሹም የድንበር ጠባቂ ወታደር መገደላቸውንና 10 ያህል መቁሰላቸውን የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ አስታውቀዋል ። የአየር ጥቃት ከተጀመረ ወዲህ በድንበር ይህን አይነት ክስተት ሲታይ የመጀመሪያው ሲሆን በተባለው ግጭት የሞቱት የድንበር ጠባቂ የቀብር ስነስርአትም ትናንት ሀሙስ በአብሃ ከተማ ተከናውኗል !

*የኢትዮጵያ ኢንባሲ መደብደብና
አሳሳቢው የኢትዮጵያውያን ይዞታ…
======================

በየመን ሰንአ የኢትዮጵየ ኢንባሲ ባሳለፍናቸው ቀናት በጦርነቱ የድብደባ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን የኢፊድሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባሰራጩት መረጃ አስታውቀዋል። በተፈጸመው ድብደባ የተጎዳ ሰው የለም ከማለት ውጭ በጦር መሳሪያ ተደበደበ ስላሉት ኢንባሲ የጉዳት መጠን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ግን የለም ።

በየመንን ሁከት ተከትሎ በኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል ወደ ሀገር ለመመለስ የተመዘገቡት 2000 ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ከተመዘገቡት መካከል 30 ያህል በጦርነት ከምትናጠው ከኤደን ተነስተው ጅቡቲ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መረጃ ያስረዳል። በየመን እያደር የጦርነቱ መባባስ ስደተኞችን የመመለስ ስራውን እንዳወሳሰበው የጠቆሙት ዶር ቴዎድሮስ በሚቀጥሉት ቀናት የተመዘገቡትን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ በተቻለው መጠን እንደሚደረግ አስረድተዋል። በመጨረሻም ባስተላለፉት መረጃ የብዙ ሀገር ዲፕለማቶች የመን ሰንአን ለቀው ሲወጡ ” ከዜጎቻችን በፊት አንወጣም !” ብለው እስካሁን የመን አሉ ላሏቸው የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ምስጋና አቅርበዋል ።

በሌላ በኩል በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ከ5000 ስደተኞች ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በየመን በኩል ወደ ሳወዲ ለመግባት አስበው በተለያዩ የየመን ክልሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አዳዳቢ እንደሆነ ቀጥሏል። ወደ ሶስተኛ ሀገር እንጅ በኑሮው ውድነትና በፖለቲካው አለመረጋጋት ተማረው በ UNHCR የስደተኛ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ግን ወደ መጡባት ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው። እኒሁ በጭንቅ ላይ ሆነው ወደ ሀገር የመግባቱ ነገር እንደ ተሻለ አማራጭ የማያዩት ወገኖች አማራጩ ጥሏቸው ከየመን የወጣው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን UNHCR ወደ ሶስተኛ ሀገር ያሸጋግራቸው ዘንድ የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችን እንዲማጸኑላቸው በተለያዩ አለማት ላሉ ኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው!

በየመን ሁከቱ እያየለ ከሄደና የሳውዲ መራሹ የ10 አረብ ሀገራት የምድር ጦር እግረኛ ማዝመት ከጀመረ ያለውን አማራጭ መጠቀም ባልፈለጉ ኢትዮጵያውያን ላይ የከፋ አደጋ እንዳያጋጥማቸው ስጋት ተደቅኖባቸዋል ። በተለያየ ምክንያት ፖለቲካውን ሸሽት ሀገር ለቀው አሁን አደጋ ላይ ሲወድቁ ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ የእስራት ፍርዱን የፈሩ ዜጎች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል። ይህን መሰሉን ችግር ማቅለል ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከችግሩ ቀጠና ወደ ሃገር ለሚመለሱ ማናቸውም ስደተኞች የምህረት ጥሪ ያቀርብ ዘንድ በዚሁ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ወገኖች ያስረዳሉ !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓም

ታሪክ ይፋረደናል! አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ “እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እንስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል!

አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ናፍቆኝም አይደለም የመጣሁት። የተሰማራሁበት ትግል ሂደት ተሰናክሎ፣ ቀኑ ጨልሞብኝ፣ በሰደት ከነበርኩበት የኑሮ ዝግመት ማምለጫ ስለሆነልኝ ነበር። መጥቼ ደግሞ በአድናቆት ተውጬ ማንነቴን ረስቼ አልቧረቅሁበትም። በርግጥ ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም ኑሮዬን ገፍቻለሁ። ይኼው ከመጣሁ ሰላሳ ዓመታት አልፈዉኛል። የአሜሪካን የዴሞክራሲ ሥርዓት አካሄድ ስገነዘብ፤ ያላቸውን ድክመት ደግሞ በዚያው ጎን ለጎን አጢኛለሁ። ለሀገሬ ከማደርገው መሯሯጥ ጋር፤ በአሜሪካ ሀገር ያለሁበትን ሀገር የፖለቲካ ሀቅ ለማስተካከል፤ እንዲህ መሆን ሲገባው ለምን አልሆነም? እያልኩ ከማማረር አልቦዘንኩም። አሜሪካኖች የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ “ፍጹም ወደ መሆን እያዘገምን ነው።” ብለው ነው የሚያምኑት። “ፍጹም ነው!” አይሉም። በምችለውና ባጋጠመኝ መንገድ ሁሉ፤ ይኼን ፍጹም ወደመሆን የሚጓዘውን ሂደታቸውን፤ በንቃት በመሳተፍ እየረዳሁ ነው።

አሁን በሀገራችን የኑሮ ሀቅ፤ የወሃ ጥማት፣ የምግብ ማጣት፣ በሰላም የገበያ አገልግሎት፣ የመንገድ አለመሠራት፣ የትምህርትና ሕክምና አለመስፋፋት፣ የመናገርና የመጻፍ፣ የመሰባሰብና ተቃውሞን የመግለጽ፣ የአድልዕና ሙስና መንገሥ፤ መሠረታዊ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፤ የፖለቲካውን መድረክ ማዕከላዊ ቦታ አልያዙም። ለዚህ ተጠያቂ የሆነውን መንግሥት በመወንጀል ባንድነት የመነሳት ግዴታችንን በውል አልጨበጥነውም። በርግጥ ከአሜሪካ ጋር የኛን ሀገርና የኛን ሁኔታ እያወዳደርኩ አይደለም። አዎ እንደነሱ በሀብት የበለጸግን አይደለንም። ግን ይኼ ላለንበት ሁኔታ ወሳኝነት የለውም።

የሀብት ጉዳይ ከተነሳ፤ በሀብት ያልበለጸግን መሆናችን አዲስ አይደለም። ከሕዝቡ ጥቅምና ከሀገሪቱ ዕድገት ይልቅ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ቅድሚያ የሠጡ ገዥዎች በነበሩበት ዘመን፤ አጠቃላይ የሀገሪቱን እውነታ ፈትሸው፤ ለረጅሙ የወደፊት ብልጽግና በማቀድ እርምጃ ስላልወሰዱ፤ ድኅነቱ አብሮን ኖሯል። እዚህ ላይ አንዳንዶቹ ያደረጉትን የልብ አስተዋፅዖ በምንም መንገድ ልስት አልችልም። ከነዚህ መካከል ባገኘሁት ዕድል ሁሉ፤ መጽሐፍትን በማገላበጥ ለማወቅ ጥረት ከማደርጋቸው መሪዎች መካከል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብንና አፄ ቴዎድሮስን እጠቅሳለሁ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ምን ነበር? ያሁኑስ ዘመን ከዚያ ዘመን በምን ይለያል?

ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የአሁኑ ዘመን የሚለየው፤ ያኔ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን፤ አፈሩ እንኳ ሳይቀር የተከበረበት ዘመን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ፤ ከሕዝቡ በመጠቀ ደረጃ፤ ከራሳቸው የወቅቱ ክብር ይልቅ፤ የሀገራቸው እድገትና በአካባቢያቸው የተኮለኮሉት የውጭ ጠላቶች እንቅስቃሴ፤ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸው ነበር። የተበታተነች ኢትዮጵያን ለመመለስና የቀድሞ ቦታዋን ለማስያዝ የሕይወታቸው ዋና ማዕከላዊ ትርጉም አድርገው ጣሩ። ለራሳቸው የስም ማስጠሪያ ግንብ ወይንም ቤተክርስትያን ከማሠራት ይልቅ፤ ለሀገራቸው መጠበቂያ የጦር መሣሪያ እንዲያበጁላቸው ነበር የውጭ ሀገር ሰዎችን የጠየቋቸው። ምንም እንኳ አሁን ምሁር ነን ባዮች፤ የአፄ ቴዎድሮስ ጠላቶች በውጭም ሆነ በውስጥ የነበሩት የጻፉትንና ያሉትን ተሸክመው ቢይጥላሏቸውም፤ እኒህ መሪ በተወለዱበት ዘመንና በቦታው የነበራቸውን የፖለቲካ ድርሻ አጢነው ቢመረምሩ፤ ከማንም መሪ የበለጠ ሊያደንቋቸው በተገባ ነበር።

የበዕደ ማርያም መምህሬ ዶክተር ገብሩ አስራት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሠጡት መልስ እጅግ በጣም አርክቶኛል። ከነበሩት መሪዎች ሁሉ አንደኛ አድርገው የሚያደንቁትን ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ እንድትነግራቸው ስትጠይቃቸው፤ ያለምንም ማመናታት “ፄ ቴዎድሮስ ናቸው!” በማለት በኩራት አስቀምጠውላታል። ልክ ድሮ ሲያስተምሩኝ እንዳደነቅኋቸው ሁሉ፤ አሁንም መምሬ ሆነው አገኘኋቸው። ከመሬት ተነስተው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሀገራዊ ሕልውና፤ የመሠረቱን ደንጋይ ያስቀመጡ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው። ከግለሰብ ማንነታቸው ይልቅ፤ የሀገራቸው መሪነታቸው ነበር ልባቸውን የሞላው። ያኔ በሕዝቡም መካከል፤ ከግለሰብ ምንነታችን ይልቅ የስብስብ ማንነታችን ማዕከላዊ ቦታውን የያዘ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያዊነት አፈር የተንከባለለበት፤ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አለመሆን የተወደደበት፣ ከኢትዮጵያዊያን ስም ይልቅ የውጪ ሀገር ስሞች የተመረጡበት፣ ከራሳችን ቋንቋ ይልቅ የውጪ ቋንቋ፣ ከራሳችን እምነት ይልቅ የውጪ እምነት፣ ከራሳችን ምግብ ይልቅ የውጪ፤ ባጠቃላይም ከራሳችን ማንነት ይልቅ የውጪውን መቅዳትና መስሎ መገኘት የጎላበት ክስተት፤ ሀቅ ሆኖ ይታያል። ለምን? ዋናውን ማዕከላዊ ቦታ ይዞ በተጠያቂነት የቆመው ያለው ገዥ ቡድን ነው። ዋና ሥራዬ ብሎ የያዘው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ይኼንንም በትውልድ ማንነት ተክቶታል። እናም ከራሱ የገማን አሣ . . . እንደሚባለው ቆርጦ መጣል ያለበት ገዥው ክፍል ነው።
አሁንም ያኔም ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን ግንዛቤያችን ፈሩን ለቋል። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ የፖለቲካውን ማኅደር አጥለቅልቆታል። ምኑም ሆነ ምኑ የሀገራችን ሀቅ፤ ከዚህና ከዚህ ብቻ እንዲታይ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በገዥው ክፍል ብቻ ሳይሆን በታጋዩም ወገን ያለ እውነታ ነው። በዚህ ተለጉመን፤ መሠረታዊ የመኖርና ያለመኖር የሕልውና አምዶች፤ ቦታ ተነፍገዋል። የፍትኅ መጓደል፣ የትምህርት ጥራትና ዕድገት ወደ ታች ማሽቆልቆል፣ የሕክምና አለመሟላት፣ የምግብ እጥረትና ረሃብን የመቋቋም ዕቅዶች አለመኖር፣ የሴቶችን እኩልነት አለመቀበልና ተሳትፏቸውን አለማሳደግ፣ አድልዕና ሙስና፤ እነዚህ መሠረታዊ የሕልውና ጥያቄ ናቸው። መስመሩ የተዘጋበት የውሃ ፈሰስ፤ ዙሪያውን ይዳስሳል። የተገደበበትን መዝጊያ መጋፋቱን፤ በጎን መፋሰሻ ከመፈለግ ጋር በእኩል ይዳስሳል። ተገድቤያለሁ ብሎ ተስፋ በመቁረጥ አይረጋም። ከግድቡ ጋር ብቻም አይታገልም። ዙሪያውን በሙሉ ነው ጥረት የሚያደርገው። በግድቡ አናት፣ በግድቡ ሥር፣ ከታቆረበት ዙሪያ ይውዘገዘጋል። የታፈነ በመሆኑ ቦርቅቆ ለመውጣት ይፍጨረጨራል።

ወገኖቻችን በየበረሃው መንገላታታቸው፣ እህቶቻችን በአረብ ሀገሮች መጎሳቆላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወገኖቻችን መፈናቀላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወንድምና እህቶቻችን በረሃብ ተጠምደው ለማኝና ሀገሪቱ በሞላ የውጭ ሀገር ምጽዋተኛ መሆናቸው፤ አእምሯችንን በማስጨነቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያናጉት ይገባል። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ውይይቱ ተጧጡፏል። ይህ በምን ዓይነት ውጥረት ላይ መሆናችንን አመልካች ነው። ነገር ግን መፍትሔ አፈላለጉ ላይ ለየብቻ እየሮጥን ነው። ለየብቻ ሮጦ የግብ መሰመሩ ላይ ለየብቻ ነው የሚደረሰው። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ግቡ የማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን የግል መኖሪያ አይደለም። የሁላችንም ነው። ባንድ ላይ መሯሯጥ አለብን። የተጎተቱ ካሉ፤ አብረን መሳብና መሳሳብ እንጂ፤ እኔ ቀድሜ ሄጄ እሸለማለሁ ወይንም ሌሎችን እጎትታለሁ የሚባልበት አይደለም። አብረን ስንነሳ፤ ቀዳሚ ሆነው የቆሙት ሲመሩ፤ የተጎተቱት ደግሞ ሲከተሉ፤ ባንድነት ከግባችን እንደርሳለን። ታሪክ ደግሞ ከኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ተወቃሽ አያደርገንም። ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አለብን። በሕይወት እስካለን ድረስ፤ ሆዳችን መሙላቱን ሳይሆን፤ በሕይወት የኖርንበትን ወቅት ትርጉም መሥጠቱ ላይ ማተኮር አለብን። ቆመን እንቆጠር። አብረን እንሰለፍ። eske.meche@yahoo.com

የኤርትራ ነገር የኛ ጉዳይ ፣ ትችትን በቅኝት ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

ወዳጄ ልጅ ተክሌ የጻፈውን ” የኤርትራ ነገር ፣ የኛ ችግር ፣ መርህ አልባ ፍቅር ” የምትለዋን አየሁ ። መስመር በመስመር ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩ ። ከዚያ ተመለሼ ወዳጄ መሳይ መኮንን በዳላስ ስለ ኤርትራ ቆይታው ያደረገውን ውይይት ተመለከትኩ ፣ እኔ በነበርኩበት በሲያትል ላይ ስላደረገው ውይይትም ለማስታወስ ሞከርኩ ፣ ከዚያ የፕሮፌሰር መስፍን ወለደማርያምን ጽሑፍ በድጋሚ አነበብኩ ፣ ከዚያ ስለ ጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወለድ እና በጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወለድ የተነገሩ እና የተከተቡ ነገሮችን አነበብኩ ፣ ከዚያ ያንዳርጋቸው ጽጌን ንግግር ( ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ የተናገረውን ) ቪዲዮ ሄጄ ተመለከትኩ ፣ ከዚያ ባንድ ወቅት ( ምናልባት ከ 3 ወይም አራት ወር በፊት ) ዔፍሬም ማዴቦ ከውህደቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በ ሎስ አንጀለስ አድጎት የነበረውን ንግግር ለማስታወስ ሞከርኩ ( ስለ አርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደት ) ፣ ከዚያ እኔ ስለ እውነት ስለ ኤርትራ መንግስት የሚሰማኝን አሰብኩ ። ባንድ ወቅት ከወዳጄ መሳይ መኮንን ጋ ባደረኩት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ነበር ያልኩት ። ” እኔ ተኩላ ሊበላኝ ነው ብዬ ለጅብ አላመለክትም !” ፣ ይህንንም ስል ወያኔ ተኩላ ሻቢያ ደሞ ጅብ ነው ማለቴ ነበር ። ታዲያ ዛሬ በኤርትራ በኩል የሚደረገውን ትግል ትደግፋለህ ሆይ ? አዎ ! ለምን ” ሻእብያዎች መላእኮች እንዳልሆኑ ስለማውቅ ፣ ይህም ማለት ሰይጣንነታቸውም የሚያረጅ እና የሚጃጅ መሆኑን ስለምረዳም ጭምር ። የትግሉ አካሄድ ላይ ስህተት አለ ወይ ፣ በደንብ ። ለምሳሌ ወዳጄ ተክለሚካዔል በዚህ ከላይ ባነሳሁት ጽሑፉ ላይ ያለው በሙሉ ፣ እደግመዋለሁ በሙሉ ልክ ነው !!!! ግን ሕዝቡን አያለሁ ። እደግመዋለሁ ከሻዕቢያና ከኛ ብሶት ባሻገር ዔርትራውያኖችን አስባለሁ ፣ ኢትዮጵያውያኖችን አስባለሁ ። ሰው ጥላቻን ለምዶ ነው ጠይ የሆነው ፣ ወይ ብዙ በደል ደርሶበት ወይም ብዙ የጥላቻ ወሬ ተመግቦ ፣ ስለዚህ ያ ሰው ኢ- ጥላቻን ሊማር የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም ።

ለምሳሌ እሳት ያድበሰበሰው ግን የሻቢያን ቁርጠኛነት ወይም ኢ-ቁርጠኛነት ሊነግረን ወይም ሊያስረዳን የሚችሉ ብዙ ተጠይቀው ያልተመለሱ ፣ ወይም ያልተጠየቁ ጉዳዮች አሉ ። ለምሳሌ የአሰብ ጉዳይ አንዱ ነው ፣ የ ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ነገር ሌላው ነው ፣ ስለ ደሚት የሰማነው ነገር የህጻን ልጅ ወሬ ነው የሚመስለው ፣ ኢሳያስ ካሳ ይገባኛል ያለው ስህተት ባይሆንም ፣ ለምንድን ነው ካሳ ይገባኛል ያልከው ? እና ወዘተ ብሎ መጠየቅ ነበረበት ። ግን ይሄንንስ ማን አየበት ከሆነ ነገሩ ፣ መዝለሉ ብልህነት ባይሆንም እንደ ብልጠት ነው የማየው ። ያም ሆኖ ትግሉን እደግፋለሁ ! ለምን አሁንም እደግመዋለሁ ” እኛ ኢትዮጵያውያኖች መሆናችንን ስለማውቅ !” ፣ ታሪክ ራሱን እንደሚደግም ስለማውቅ ፣ የበለጡንን መብለጥ ፣ ያመኑንን ማመን እና መታመን ፣ ያሴሩብን ላይ ማሴር እንደምንችል ስለማውቅ ። ከምንም በላይ ሻዕቢያ ይህንን ለውጥ ለራሱ ሲል እንደሚፈልገው ስለማውቅ ። ለምን ? ” ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የነጻነት ፈላጊነት ባሮ ሜትር ምን እያነበበ እንደሆነ ስለሚረዳ እና ባይፈልገውም እጁን እዚህ ላይ ካልዶለ ፣ እንደሚጎዳ በደንብ ስለሚያውቅ ። ይሄ ኢሳያስ ኢትዮጵያን ይወዳል ፣ ምናምን የሚሉትን ታሪክ ” ተናጋሪውም የተነገረለትም ” ሁለቱም እንደማያምኑበት መናገር ጠቃሚ አይመስለኝም ።

ታዲያ ይሄም ሆኖ ሳለ ትግሉን እደግፋለሁ ! ለምን ? ያለም ታሪክ በአጋጣሚዎች ላይ የተጎለተ ድማሚት ስለሚመስለኝ ። የማልደግፈው ግን ፣ ትግሉ ከዔርትራ ብቻ መነሳት አለበት የሚለውን ነው ። አቅሙ ያላቸው ሰዎች አማራጭ እንዲያዩ እመክራለሁ ። ሰሞኑን ሱዳን አካባቢ አንዳንድ ጠቋሚ እና ጠቃሚ ነገር እያየሁ ነው ። ሌላም ነገሮች ይኖራሉ ። እርግጥ የኤርትራ መንግስት ወዳጄ መሳይ እንደነገረን ተቃዋሚዎች አንድ ሁኑ ሲባሉ አንድ አንሆንም ብለው ስላስቸገሩት ነው አንድ ሳይሆኑ የቀሩት የሚለውን ” እቃቃ መሰል ወሬ ” ፣ እራሴን እየነቀነቅሁ ልክ ነው ልል ስብናዬ አይፈቅድም ፣ ግን ከኛ ባሀሪ ስነሳ ፣ አንድ ሆኖ መስራት ድሮም ስለማይሆንልን ፣ እኛን ማፍረስ ቀላል ቀላል መሆኑን በደንብ እገነዘባለሁ ። ለዚህም ነው በልጅ ተክሌ ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ ለመስማማት የፈለኩት ።

በነገራችን ላይ ልጅ ተክሌን ለማታውቁት ፣ እስከማውቀው ድረስ ” ለአፉ ለከት የሌለው የሚመስል ግን ያልሆነ ፣ የራሱ ሰው ነው “። አንዳንዴ ዝም ብሎ ሲያፈነዳም አስተውያለሁ ፣ ግን ለክፉ የሚሰጡ ናቸው ብዬ አላምንም ። ባጭሩ ፣ ባለ ብሩህ አእምሮ እና ፣ ጨዋታ የሚወድ ሰው መሆኑን ሳላውቅ አልቀርም ። እንደውም ወደፊት ግንቦት ሰባትን ከኔ ጋ ሆነን ገልብጠን ሌላ ድርጅት ለመመስረት እያሰብን ነው ። መነሻው የሃንሽ ደሴቶች ላይ የሆነ ባህር ኃይል ፣ በሁለት ዓመት አዲስ አበባ የሚገባ ምናምን ልበል ? እስቲ ተዉት !

ልጅ ተክሌ በአርበኞች ግንቦት ሰባት ስያሜ ላይ የሰጠው ነቀፋ ተገቢ ነው ፣ አንድም ሁለትም ናቸው የሚለው አባባል ፣ እንደኔ ሚስጥረ ስላሴ ለማይገባው ኩታራ አደገኛ አገላለጽ ቢሆንም ። በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ብርሃኑ ነጋ መሆኑን መቃወሙ አግባብ ይመስለኛል ። ይህንንም ስል ብርሃኑ የመምራት ብቃት የለውም ለማለት ሳይሆን ፣ የቄሳርን ለቄሳር ፣ የየሱስን ለየሱስ እንደተባለው ፣ የሜዳውን ለሜዳ ፣ የ እንትኑን ለእንትን ማለት ብንችል ብዬ ነው ። በተጨማሪ መሪ የሚለው ነገር ከአንድ በላይ ትርጉም ያለው ስለሚያስመስል ፣ ለሱም ሲባል ቢቀር ጥሩ ነበር ብዬ አምናለሁ ። ይህንን ስል ፣ እንደ ብላቴና ነው አስተያየቴን እየጻፍኩ ያለሁት ። ብዙ ውስብስብ ነገሮች እንዳሉ ይገባኛል ። ሲጀመር ኤርትራ ሆኖ መዋጋት በራሱ ውስብስብ ነው ፣ መሰንጠቅ ፣ መካድ ፣ አላስፈላጊ ውሳኔ መስጠት እና ወዘተ ሌላው ነው ። ግን መሪው በቅርብ የሌለበት የለት ተለት ተሰራዊት እንቅስቃሴ ፣ ጸብ ፣ የለት ተለት የትግል ውሎ ፣ ለሊቀመንበሩ ከርቀት በሚደርስ መርጃ መከወን ብዙ ጉዳቶች አሉት ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የመረጃ ፍሰት እና አጠባበቅ ነው ። ለምሳሌ ምክትል ሊቀመንበሩ ከሆነ ለ ዋናው ሊቀ መንበር መረጃ የሚያደረሰው ፣ በእርግጠኝነት በሁለቱ መሃከል ስለሚደረገው ማንኛው አይነት ግንኙነት ሌላ አካል ( ሻብያን ጨምሮ ) ሊሰማ ወይም ሊያውቅ ይችላል ። ምክትል ሊቀ መንበሩ ደሞ ምን ያህል በራሱ ነገሮችን መፈጸም ይችላል የሚለው ነገር ፣ ከፋሲል የኔ ዓለም ጋ ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ በሁዋላ ” በቃ አልተመቸኝም ” ( ቃለ መጠይቁ ላይ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኮ/ ል ታደሰ ጥያቄ ሲጠይቅ ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ምክትል ሊቀመንበር የሆነው አቶ መአዛው ጌጡ ” ስለዚህ ነገር አትጠይቁኝ ፣ ተወኝ ፣ እለፈኝ ” የሚል መልስ ነው የሰጠው ። ብዙ ያልተሩ ነገሮች አሉ ። የዚህ ጽሑፍ አላማውም ፣ ልጅ ተክሌ የጠየቀውን አስባችሁበታል ወይ ለማለት አይደለም ( ምክንያቱም በደንብ እንደምታውቁት ስለማውቅ ) ፣ የዚህ ጽሑፍ አላማው ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት መሰሪ ፖለቲከኞች ያስፈልጉታል ፣ ለዚህ ዘመን እና ትውልድ በሚመጥን መልኩ አይደለም አንዳንድ ውሸቶች እየተሰሩ ያሉት ፣ እውነትም ይሁን ውሸት ጥራቱን ይጠብቅልን ለማለት ። በተጨማሪ እኔም እንደ ተክሌ የፈለኩትን መናገር አልፈራም የሚልም መልክት ለማስተላለፍ ነው ።

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>