Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ዶ/ር አድሃኖም ስለሃገር ጥቅም ይከበር ብለው ያሉት ደስ ሲል ዓቢቹ ነጋ

$
0
0

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከጫካ ከመጡት የወያኔ ጀሌወች በትምህርትም ሆነ በአስተሳሰብ የተሻሉና በደም ያልተጨማለቁ ናቸው ሲባል ብዙ ሰምተናል። በመሆኑም ያስታርቂነትና የመልካም አስትዳደር ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ይሆናል አያሉ ብዙ ሰውች ገምተው ነበር። አስተዋይና የምሁርነት ባህሪ እንዳላቸውም ይነገራል።

አዲሱን ሥልጣን እንደያዙ የሰከነ ፖለቲካና በሎጂክ የተደገፈ የውጭ ፖሊሲ ነድፈው በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ የሚአቀራርብ የፖለቲክ መርሃ ግብር ያሳዩ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር። በቅርቡ በውጭ ሃገር ጉብኝታቸው ጊዜ ዲያስፖራውንና የዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭን አስመልክቶ በዩቲውብ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ በጥሞና አዳምጠነዋል ። የንግግራቸው አንኵኣር መልእክት አንድና አንድ ነው። ኢትዮጵያኖች የሃገር ጥቅምን ፤የኢኮኖሚ እድገትን፤ የማህበራዊ ስራዓትና ብልጽግናን ከሚጎዳ ተግባር እንዲታቀቡ ለዘብ ባል መልኩ አሳስበውናል።

አክለውም በፖለቲካ ልዩነቶች አኣንዱ በግራ ሌላው በቀኝ መሰለፍ ይችላል ብለዋል አውቁ የፖለቲካ ዶክተር። የህ ካንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አና ምሁር የሚጠበቅ የዲፕሎማሲ ቍዋንቍዋ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ዲያስፖራው በየጊዜው በሰላማዊ ሰልፍ፣ በጽሁፋ፤ በመግለጫ፤ በመገናኛ ብዙሃን ወዘተ ወያኔን የሚነግረውና የሚቃወመውም ለዚሁ ዓላማ መሆኑ ይታወቅ። በዚህ ብዙ ጠብ አይኖርም።

ነገር ግን በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በቦንዱ ሽያጭ፤በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚና በልማት ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ የሚአሰማው ለምን ይሆን ብለው ዶክተሩ እራሳቻውን መጠየቅ ይኖርባቸዋል።የህክምና ሙያዎን አልረሱት ከሆነ ለአንድ በሽተኛ ወይም ታካሚ መድሃኒት ከመታዘዙ በፊት ለበሽታውና ለህመሙ መንስዔ የሆኑት ጉዳዮችን መጀመሪያ ማጠናትና ግድ ይላል። የበሽታውን አይነትና በሽታው የተከሰተበት ምክንያት ከታወቀ በህዋላ ህክምናው ይሰጣል። እንደህክምና ጠበብትነትዎ መልሱን ማፈላለግና ታካሚዉን መርዳት የርሶ ፋንታ እንጂ የታካሚዉ አይሆንም። በርግጥ ህክምናው የተሳካ እንዲሆን በሽተኛውም መተባበር የኖርበታል ።

በሃገርቤትም ሆነ በውጭ ተስዶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ ነፃነት፤ ኣንደነት፤ ፍቅር፤ ሰላምና ብልጽግና ሁሉም ቀናኢ መሆኑ በውል የሚአውቁት ይመስለናል። በተደላደል ሃገር እየኖረ፤ ሶስት ጊዘ በቀን እየተመገበ፣ በመኪና እየተንደላቀቀ ፤በጥሩ ቪላ ቤት እየኖረ ፤የተፈጥሮ መብቶቹ ማለት የመጸፍ፤ የመናገር፤ የመቃወም፤ የመሰብሰብ፤ የመሰለፍ፤ በፈለገበት አካባቢ እየተዘዋወረ መኖርና መሰራት እየቻለ በወያኔ ጨምላቃ ፖለቲካ የሚነንጋገረውና የሚቃወመው ለምን ይመስለዎታል። እትበቱ የተቀበረችበት ዉድ ሃገሩ ኢትዮጵያ በገንዛ ልጆችዋ እየተጠቃችና እየፈራረሰች መሆኑን ስለተረዳ ጨርሳ ሳትወድም ከውድቀትዋና ከመፈራረስዋ በፊት ህዝቤንና ሃገሬን ልታደግ ብሎ እንጅ የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጉዳት ከመነሳሳት የመነጨ ስሜት እንዳልሆነ ዶክተሩ ሊገነዘቡት ይገባል። ኢትዮጵያዊው ለሃገሩ ቀናኢ ለመሆኑ የድሮ ታሪኩና ያሁን ተግባሩ ምስክር ናቸው። የተማሩት ድክተር አድሃኖም ይህን የኖረ እውነታ ያጡታል ተብሎ አይገመትም።

በህክምና ሙያ አንደተመረቁ ይነገርልዎቀታል። ዳያስፖራው ለዚህ ኣድናቆቱን የሚነፍግዎ አይሆንም።በአንፃሩ አብዛኛው ዳያስፖራ በተላያየ ሙያ ከፍተኛ ትምህርት፤እውቀትና ልምድ ያካበተ መሆኑን የሚዘነጉት እንደማይሆን ተስፋአለን። የዕድሜዎን ክልል ስናሰላስል በኀይለሥላሤ ዘመን እንደተማሩ እንገምታለን። እስኪ በዚያን ጊዜ የነበረውን የትምህርት ደረጃና በርስዎ መንግስት ጊዜ ያለውን የትምህርት ጥራት አነጰጵረው ፍርድ ይስጡ።

ሐገርም በተስቦ፤ በኤድስ፤ በሳንባ ነቀርሳ ፤በወባ በሽታወች አይታመም እንጂ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ስነምግባር አካሄድ ትታመማለች። ኢኮኖሚው ሖዋላቀር ሲሆን ፤ የሃገር ብልጽግና ባለበት ሲረግጥ ፤ አንዳድ ግዜም ወደ ሁዋላ ሲሄድ፤ የህዝብ ኑሮ ሲጎሳቆል፣ ስራጥነትና ቦዘኔነት ሲሰፍን፤ ዜጎች በሃገራቸው አንደሁልተኛ ዜጋ ሲቆጠሩ፤ በማንኛም የሃገሪቱ ክፍሎች አየተዘዋወሩ መስራትና መኖር ሲከለከሉ፤ ህዝብ መፈናቀል አፈናና እንግልት ሲበዛበት ወይ ወደ ዓመፅ ያመራል ውይ የስራ እድልና አንፃራዊ ሰላም አገኛለሁ ብሎ ወደ አመነበት ሃገር ይሰደዳል። በሃገራችን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በቁንጮነት የሚመሩት በየኣመቱ ወደ አረብ ሃገራት፣ አፍሪካ፣ አዎሮፓ፣ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ አውስትራሊያ፣ አስያ የመሰደደውን የህዝብ ቁጥር በውል የሚአውቁት ይመስለናል። በተባበሩት መንግስታት ግምት 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ አሃጉራት ተበትነው እነደሚገኙ ይዘግባል። በርግጥ እርስዎና ግብራበሮችወ የሃገርን አንጡራ ሃብት እየዘረፋችሁ በተልያዩ የዓለም አቀፍ ባንኮች ካሸሻችሁት ንብረት ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ ኢምንት መስሎ ይታየዎት ይሆናል። አገር የሚገነባውን ኢኮኖሚ የሚፈጥረውን ህዝብ ማጣት ግን እጅግ የከፋ ጥፋት ነው። ይህ ለምን አንደሆነ የሚረዱት ይመስለናል።

ዶ/ር አድሃኖም የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔ የሆኑትን ላእላይና ታህታይ (Basic and Super Structure) ምክንያቶችን መጠየቅና ማወቅ ተገቢ ይመስለናል። ከሙያዎም ሆነ ከሃላፊነትዎ አንጻር ጉዳዩን መመርመርና መረዳት ይጠበቅብዎታል። ለማስታወስ ያህል የሚከተሉትን በጥሞና ይመለክቱና የትኛው ነው የሃገርን ጥቅም የሚጎዳ ሃገርን የሚአጠፋ ስራ እየሰራ ያለው ብለው ይጥይቁ። አስር ሽህ ኪሎሜትር በድሪም ላይነር መጙዝ ሳያስፈልግዎ መልሱን አዲስ አበባ ላይ ያገኙታል።

በመጀመሪያ ሁሉም የሃገርን ትቅም ማስቀደምና ማስጠበቅ እንዳለበት እንስማማለን። ከሁሉም በላይ ግን ይህ ሃላፊነት ሃገሪቱንና ህዝብን እናስተዳድራለን በሚሉት መሪወችና ሃልፊወች ላይ አጅግ የገዘፈ መሆኑን ያለመጠራጠር መቀበል ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ላይ በጉልበት ነግሳችሁ የምታስተዳድሩትንና የምትገዙትን ህዝብና የሃገር ጥቅም የከዳችሁ የመጀመሪወችሁ ተጠያቂ አርስዎና ግብራአበሮችዎ ናችሁ። የመጀመሪያው ሃገር ሻጭና የህዝብ ጥቅም ነጣቂ ማነው ቢባል መልሱን ከጉያው ያገኙታል። ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ፀረ ህዝብና ፀረ ሃገር ድርጊታችሁን እንመለከት።

ለረዥም ዘመናት ነፃነቷዋንና አንድነቷዋን ጠብቃ የኖረችውን ሃገር አካልዋን ገንጥሎ ወደብ አልባ ያደረገ ወያኔ ወይስ ዲያስፖራ። በግራ ወይም በቀኝ አስተሳሰብ ከርስዎና ከቡድንዎ የተለየውንና የተቃወመውን ሁሉ የሚአስር፣ የሚገል የሚአሳድድ ማነው ወያኔ ወይስ ዲያኣስፖራ።

እርስዎ በኤርትሪዊነትዎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 1.9 GPA አግኝተው መግባት ሲፈቀድልዎ አማራዉና ሌላው ህብረተሰብ 2.2 GPA ካላመጣ የዩኒቨርሲቲ በራፍዋን ይረግጥም ነበር። ታዲያ ይህ አማራ ነው ሲጨቁን የኖረ። ይህነው ነፍጠኝነት። ለኀይለሥላሤ መንግሥስት ዕድሜ መለመን የነበረባችሁ አናንተ መሆን አልነበርባችሁም።

ከሃገሪቱ የቀላልና የከባድ ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ 45% በአስመራ አልነበረምን። ከፒአሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር፤ከመርካቶ እስክ ኮተቤ፤ከብሄራዊ ቲአትር እስከ ደብረዚይት ይምግብ ቢቶችን፤የአልባሳትና የወርቅ መሸጫ ሱቆችን፤ ቡናና ሻሂ ቢቶችን፤ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በአብዛኛው በኤሪትራዊያንና በወያኔ የተያዙ አይደሉምን። ማነው ኤርትራኖች ናቸው ትግሬዎች ናቸው ብሎ የጠየቀ። ይህ ሁኔታ በኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ ጊዘ የነበር ሃቅ ነው። በርስዎና በወንበዴው ድርጅትዎ አማካይነት አማራውን፣ ኦረሞውን፣ ጉራጌውን፣ ቤንሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ከምባታውን፤ሃድያውን፤ ሲዳማውን ወዘተ በጎሳው እያሳደዳችሁ የምታፈናቅሉና በሃገሩ ሰርቶ አንዳይኖር የምታደርጉ የመንግሥስት ቀማኞች አይደላችሁምን። ከዚህ የበለጠ የሃገር ትቅምን፤አንድነትንና እድገትን የሚጎዳ ነገር ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራው ይህን ሰርቶአል ካሉ ከነማስረጃዉ ያቅርቡልንና እንተማመን።እኛ እስከምናዉቀዉ ዲያስፖራ ያደረገው ይህን እኩይ ተግባራችሁን የተቃዉሟል። ዲያስፖራው አገርን ከጥፋትና ከዉድመት ለማዳን የሚንቀሳቀስ ይመስለናል ።

አማራው ኦረሞው ወዘተ ልዩ ተጠቃሚ አንደሆነ አድርጋችሁ በመንግሥት ፕሮፖጋንዳ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ፣ በቡድን፤ እንዲሁም መዋቅርና መመሪያ ዘርግታችሁ የጥላቻ ዘር የምትዘሩና የምታናፍሱ አናንተ አይደላችሁም። በመንግሥት አዋጅና መመሪያ የሃገርን ጥቅም እያፈረሰ አገር ማስገንጠሉ አንሶ መሬት እየቆረሰ ለሱዳንና ለሶማሊያ በእጅመንሻነት የሚሰጥ ማን ሆነና ነው ዲያስፖራዉ የሚወቀሰዉ። ነፃነት ባለበት ሃገር ስለሚኖር እኩይ ተግባራችሁን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይቃወማል ለዓለም ህዝብም ያስረዳል። ይህ የሃገርን ጥቅም ማጥፋት ነው የሚባል ከሆነ ዲያስፖራው በጸጋና በኩራት የሚቀበለው ወቀሳ ይሆናል።ይሄ ሁሉ ሃቅ ማይከብድዎት ቢሆን የተሸከሙት የዶክትሬትና የመንግስት ስልጣንና ህሊናዎ እንዴት አይወቅስዎትም ።

ተፋቅሮ ፤ ተጋብቶ፤ተዋልዶ በአንድነት የኖረውን ህዝብ በዘር ሃረጉ በቁዋንቁው እየለያችሁ ለማተራመስ ድፍት ቀና የምትሉ እርስዎና ግብረአበሮችዎ አይደላችሁም እንዴ። ክዚህ የበለጠ የአገረ ጥቅምን ማፈራረስ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራውማ ተው ይህ ትክክል አይደለም አገረ ይበተናል፤ የአገር ጥቅም ይጎዳል እያለ ይጮሃል ። የማንኛው ተግባር ነው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳው። ፍርዱን ለርስዎና ለቡድንዎ ከመተው ሌላ አምራጭ የለም።

በቤንሻንጉል፤በጉራፈርዳ፥ በአፋር፥ በኦረሞ ወዘት በመሳሰሉት ክልሎች እና አካባቢወች አማራውን፤ኦረሞውን፣ ጉራጌውን አፋሩን፣ አኝዋኩን እየነጠላችሁ የምታፈናቅሉ፣ ንብረቱን በመንግስት መምሪያና ልዩ ትእዛዝ የምትቀሙ ህጋዊ ቀማኞች አርስዎና ቡድንዎ አይደሉምን። የሃጋሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ይዛችሁ ኣብዛኛውን የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቁኣማትን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደራጃ ይዛችሁ ይህን ሁሉ ግፍና ኢሰበአዊ ድርጊት በንፁሃንና ሰላማዊ ዜጎችና በሃገሪቱ ላይ የምታዘንቡት ምን ለማትረፍ ነው። እርስዎና ግብረአበሮችዎ የምትፈጽሙት ወንጀልና ግፍ ሞልቶ ከፈሰሰ ውሎ አድሮኣል። አገሪቱ በግፋ ጨቅይታ ልትፈራርስ ተቃርባለች።የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚፈታተን ተግባር አየፈጸማችሁ ዲያስፖርውን የሃገር ጥቅም አፍራሽ አድርጋችሁ ራሳችሁን እንደጲላጦስ ከደሙ ነፃነን ልትሉ ትፈልጋላችሁ። እንደርስዎ ያለ ተማርሁ የሚል ሰው ሎጂክና ፕሪንሲፕለ ትቶ ደም ከውሃ ይወፍራል አያል ዘር የማጽዳት ዘመቻ ሲካሄድ ጀሮዳባልበስ አያለ የሚጎዝ ምንዓይነት ህሊና ነው።

ኤርትራን ያስገነጠላችሁ አናንተ በሁአላም ከኤርትርዊያን ጋር ጦርነት ከፍታችሁ ህዝቡን ያስጨፈጨፋችሁ አናንተ። እምቢ ላገሬ እምቢ ለነፃነቴ ብሎ የዘመተውን አማራ ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ጉርጋጌ፤ ሲድማ፣ ከምባታ ወዘተ ከፊትለፊት አሰልፋችሁ ከ 70-100,000 ሕዝብ አላስጨረሳችሁም አንዴ። ሕዝቡ በደሙ ያስቀራትን ባድመን መልሳችሁ ለሻብያ አልሰጣችሁምን። በዛንጊዜ ኤርትራኖችን ከኢትዮጵያ ምድር ንብረታቸውን ቀምታችሁ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ወደ አስመራ አልመለሳችሁምን።

አሁን ደግሞ አነዚህኑ ኤርትራኖች ከአስመራ ወደ ኢትዮጵይ አንዲመለሱ አድርጋችሁ በመንግሥት መስሪያ ቤት አንዲመለሱ፣ ንብረታቸው ከነወለዱ አንዲመለስ አላደረጋችሁምን። ማነው በኢትዮጵያ ህዝብና ንብረት ላይ አየቀለደ የሚገኘው። ይህ ሁሉ ተግባር የሃገር ጥቅምን መጉዳት አይደለምን። ለነገሩ በአመራር ላይ ያላችሁት አብዛኞቻችሁ ኤርትራኖች ስልሆናችሁ የኢትዮጵያን ጥቅም ታስተብቃላችሁ ተብሎ አይጠበቅም። ዲያስፖራው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳ ነገር እንዳይሰራ ታስጠነነቅቃላችሁ። የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብያደርቅ ማለት ይህ ነዉ።

በስልጣን ወንበር ከትቆናጠጣችሁ በሁአላ እንደ መንግሥት ሀገ መንሥት ኣወጣችሁ። ማንም ሳይጠይቃችሁና ሳያስገድዳችሁ እናምንበታለን ብላችሁ ያወጣችሁትን ሀገመንግሥት አንድ አራተኛወን እንኹዋን በተግባር አልፈፀማችሁም ። በሃገራችን ታሪክ ኢትዮጵያ ያለህግ የምትተዳደርው ክ1991 ዓማተ ምህረት ጀምሮ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለህግ ተገዥ የነበረን ህዝብ ወደኾላ አየወሰዱ በህግ አልባ ስርዓት ከማስተዳደር የበለጠ ወራዳ ስራና ሕገአራዊትነት ምን ሊኖር ይችላል።ከዚህ የበለጠ የሃገረንና የህዝበን ጥቅም የሚጎዳና የሚአፈርስ ምን ነገር ይኖራል ።

በቅርቡ ወደ ሃገርቤት ጎራ ብዬ ሃገሪቱን በሰፊው አይቸ ተምልሻለሁ። እርግጥ ነው ሕንጻ ተቆልልዋል መንገድ ተሰረቶአል፤ የዝቅተኛና የከፍተኛ ትምህርት ቤቶችና ተቐማት እንዳሸን ፈልተዋል፤ ጤና ጣቢአወች ተሰርተዋል፤ የመብራትና የስልክ መስመሮች ተዘርግተዋል፤ የውሃ ቡአንቡወችና የስልክ መስመሮች ጨምረዋል። ይህን ስናይ እሰየው እንላለን። የሚገርመው የሚጠጣ ውሃ የለም፣ ህዝቡ የኤሌክትሪክ መብራት አጦ በሻማ ያመሻል፣ ተማሪወች ከከፍተኛ ትምህርት ተቅዋማት ተመርቀው በቅጡ ስማቸውን መጻፍ አይችሉም ተመርቀውም ቦዘኔ ናቸው፤ምርት ተመርቶ ህዝብ ፆሙን ያድራል። ሁልጊዜ በግብረሰናይ ድርጅቶች እርዳታ ከመጠየቅ አልወጣም።ጤና ጣቢወች ተሰርተው ባልሙያወች የሉም ህዝቡ በበሽታ ይሰቃያል።

ሖስፒታሎቻችሁ የመፀዳጃ ቤት ይመስላሉ።እንዲአውም በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች በሃገር ቤት ካሉት ሆስፒታሎቻችሁ በንጽህና ሳይሻሉ አይቀሩም። የጎዳና ተዳዳሪው ቁጥር በየቀኑ ይጨምራል አሁንማ የመንግሥት ሰራተኛውም ተረጂ ሆንዋል። የዛሬ ሃይ ዓመት 85% የሆነው ህዝባችን በቀን ከ$1 ዶላር በታች በሆነ ገቢ ይኖር ከነበረበት ዛሬም የተቀየረ ነገር የለም። የትላይ ነው የ 11% ኢኮኖሚ እድገቱ። መቸም ምሁሩና ዶክተሩ አድሃኖም ይህን እውነታ በቀላሉ የመረዳት አቅም ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ግዴታም ስላለባችሁ ይህን ሃቅ ያስተባብላሉ ብለን አንጠብቀም።

የሃገር ቅርስና ታሪክ የሃይማኖት ትቁዋማትን፤ ባህልንና ታሪክን ማጥፋት የሃገርን ጥቅምና ማንነት ማጥፋት አይደለምን። ማነው የእስላሙን ህብረተሰብ ከኦርቶዶክሱ ጋር የሚአናቁር። ሌላዉ ቢቀር ከዛሬ ሽሕ ዓመት በፊት ባሕረ ነጋሽ ወይም ነጋሺ የሰራውን እንኩአን ማሰብ እንዴት ያቅታችሁኣል። ማነው አማራውንና ኦርቶዶክሱን እንዳይንሰራራ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብሎ በኦፊሲየልና በመገናኝ ብዙሐን ወጦ በዝና መልክ እያወራ ያለው። ከዚህ የበለጠ የሃገረ ጥቅምንና አንድነት ማጥፋት የበለጠ ምን ይኖራል ይላሉ። አገር ከፈረሰ እኮ አማራውና ኦሮሞው ብቻ አይደለመ የሚጠፋው እንናንተም ጭምር መሆኑ እንዴት አይታያችሁም። የሌሎች ጉአደኞችዎ አርቆ የማሰብ አድማስ የተወሰነ ቢሆን እንደርስዎ ያለ ምሁር እንዴት አደጋዉ አይታየዉም። ይህን ከመሰለ የሃገር ጥቅምን ማወደም የበለጠ ምንሊኖር ይችላልና ነው ዲያስፖራውን የምትወቅሱት።

በሃገርቤትና በውጭ ሃገር ያለው ተቃዋሚና ህዝብ በተደጋጋሚ የሚአቀርበው ጥያቄ የብሔራዊ እርቅንና ሠላምን የአንድነት መንግሥት እናቕቁም እያለ ሲለፍ ይኸው ሃያ ሁለት ዓመት አስቆጠረ። ይህን የተቀደሰ ሃሳብ በእምቢተኝነቱ ፀንቶ የሚገኘው ማነው ። ሃገርን ለአንድነትና ለትብብር የጠራ ተቃዋሚን ዲያስፖራ እንደሽብርተኛ የሚቆጥር መንግሥትና ዶክትሬት ምን ዓይነት ጭንቅላትና መሪ ነው። ዶር አድሃኖም አሁንም ጊዜ አለ አልመሸም ማስተካከል ይቻላል። ከርስዎና ከግብረአበሮችዎ የሚፈለገው ቅን ልቦናና ለሃገር ጥቅም አስቦ መንቀሳቀስ ነው። ለጥፋቱ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም ሃላፊነት ወስዶ ለማስተካከል መስራት ይኖርበታል። ሐላፊነቱ መንግሥት ነኝ በሚለዉ ላይ የከበደ ነዉ።

ሕዝብና ኢግዚአብሔር ሁሉጊዜ ይቅር ባዮችናቸዉ። የሃገር ጥቅም ማጥፋቱን አቁማችሁ የሃገር አንድነትና ጥቅም ማስጠበቅን ቅድሚያ ሰጣችሁ ከሕዝብ ጋር ታረቁ። ካልሆነ ሃገር አገር ሲአርጅ አሜኪላ ይወልዳል እያልን ተቃውሞኣችንን እንቀጥላለን። ለዶ/ር አድሃኖም ካልነቁ መንጋቱን የሚኣበስር መልክተኛ አንልክባቸዋለን።

ቸር ይግጠመን
ዓቢቹ ነጋ ነኝ
ማይ 12, 2013


ተገፊዎች የባህሪ ለውጥ ኣምጡ እንጂ! ገለታው ዘለቀ

$
0
0

ልትታተም ካሰበች ኣንዲት ልቦለድ ጽሁፍ ላይ ኣንድ የምናብ ሰው ከተገረመበት ነገር ተነስተን ኣጭር መልእክት ለማቀበል እንሞክራለን። ይህ የምናብ ሰው ወደ ኣንድ ሃገር ይሄድና በዚያ በኣንድ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ናሽናል ጂኦግራፊ የተሰኘውን የ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ያያል። በወቅቱ ይተላለፍ የነበረው ፕሮግራም የዱር እንስሶች ኑሮ ነው። ይህ የምናብ ሰው ከኣልጋው ጫፍ ላይ ቁጢጥ ብሎ ረጃጅም ጢሙን ቁልቁል እየላገ ይህን ፕሮግራም ያያል። የሚያማምሩ የሜዳ ኣህያዎች መንጋ ረጋ ብሎ ሳሩን ይግጣል። ጥቂት ሳይቆይ ከረጃጅሙ ሳር ውስጥ ሲሹለከለኩ የነበሩ ሶስት ጅቦች መጡ። ኣንዱን ጅብ ቀድሞ ያየው የሜዳ ኣህያ ሩጫውን ሲቀጥል ሌላው ነገሩ ያልገባው ሁሉ ተከትሎ ይሰግር ጀመር።

የሜዳ ኣህያዎቹም ተፋፍገው ሲሮጡ ኣንድ ወደ ሁዋላ ቀረት ያለ የሜዳ ኣህያ ነበርና ኣንዱ ጅብ ከሆዱ ቆዳውን ሊዘነጥል ይጥራል። ይህ የሜዳ ኣህያ እግሮቹን እያወራጨ ለማምለጥ ይጥራል። ትግሉ ከሚሮጡት ጋር ሩጫውን ለመቀጠል እንጂ የሚነክሰውን ጅብ ለመጉዳት ኣይደለም።
ሌሎቹም ጅቦች ተጋገዙና ምን ዋጋ ኣለው ይህን የሜዳ ኣህያ ሆዱን ዘረገፉት።

ያ የምናብ ሰው ተገረመ። ኣየ ኑሮ…………

ወደ ሌላ ኣንዲት ወንዝ ስር ጥሙን ሊያረካ ውሃ ከሚጠጣ ሌላ ያማረ የሜዳ ኣህያ ጋር ካሜራው ወሰደው። ይህ የሜዳ ኣህያ ሁለት የፊት እግሮቹን ፈርከክ ኣርጎ እንዴው እግዜር የሰጠውን ውሃውን በፍቅር ይስባል። ጥቂት ሳይቆይ ኣንድ ሌላ ጅብ ከሁዋላው ዘሎ ከሆዱ ቆዳውን ሊዘነጥል ትግል ጀመረ። ይህ የሜዳ ኣህያ ከወራጁ ወንዝ ጫፍ ላይ ተክሎት የነበረውን ኣፉን ነቀል ኣረገና ወደ ሁዋላ በቅጽበት ዞረ። የሚታገለውን ጅብ እንደሌሎቹ የሜዳ ኣህያዎች በርግጫ ብሎ ለማምለጥ ኣይጥርም። ኣንገቱን ጠምዝዞ ኣንድ ሁለቴ ዞረና ወደ ሆዱ ገብቶ ቆዳውን ሊዘነጥለው የሚታገለውን ጅብ ጉሮሮ ኣስግጎ ኣገኘውና በዚያ ላይና ታች ክችም ባለ ጥርሱ የጅቡን ጉሮሮ ቀርጥፎ ይዞ ትግል ተጀመረ። ኣሁን ጅብ ማጥቃቱን ትቶ ራሱን ለማዳን እየታገለ ነው። ነገር ግን ኣልሆነም። ይህ የሜዳ ኣህያ የዋዛ ኣልነበረም። ጥቂት ደቂቃዎች ከታገሉ በሁዋላ ጅቡ መታገሉን ሲያቆም የሜዳው ኣህያ ሙሉ በሙሉ ከሜዳው ላይ ኣንጋለለውና ያየው ጀመር። ጥቂት ኣሸተተውና ጥሎት ለመሄድ ርምጃ ሲጀምር ኣንድ ሌላ ጅብም መጣ። ያ የሜዳ ኣህያ በሃይል ወደ ጅቡ መሮጥ ሲጀምር ጅቡም ቂጡን ጥሎ ሮጠ።

የምናቡ ሰው ይህን ነገር እያየ ተገረመ። ለካ ይሄ የሜዳ ኣህያ ብቻውን በዚህ ጠራራ ጸሃይ በዚህ ወንዝ ሥር የሚያንቀባርረው የባህሪ ለውጥ ኣምጥቶ ነው። እየተራገጡ መሮጥን ኣቁሞ መናከስ ጀምሩዋል። ይህ የባህሪ ለውጡም ከተጠቂነት ወደ ኣጥቂነት ኣሸጋግሮታል እያለ ይደነቃል…………

በኣንድ ሃገር የሚኖሩ ህዝቦች ኣንዳንዴ ጅብ በሆነ ስርዓት ይጠቃሉ። ጥቂት ቡድኖች ያለውን የሃገሪቱን ሃብት ተቆጣጥረው ኣብዛኛውን ሰው ጦሙን ያሳድሩታል። የኢኮኖሚው ሰፊ ልዩነት ሌሎች የህይወት ዘርፉን ሁሉ ያጠቁትና ያልተመጣጠነው እድገት በፍትህ ፊት፣ በባህልላዊ ቡድን፣ በኣጠቃላይ በኑሮ ዘየ ሁሉ ከባድ የእኩልነት እጦትን ይስብበታል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ቢሊየነር ሁሉ ያላት ኣገር ናት። በሌላ ጥግ ደሞ የ ዓለምን የመጨረሻ ድህነት የሚኖሩ ብዙ ህዝቦችም ኣሉባት፣ ይህ ሰፊ ያልተመጣጠነ እድገት በተወሰነ ደረጃ ቢሳለጥ ኣሁን ያለው የድህነት ገጽታ መልኩን ይቀይር ነበር። የገቢ ኣለመመጣጠን ስንል ሁሉ እኩል ይካፈል ማለታችን ኣይደለም። ሁላችን እኩል በመካፈላችንም ፍትህ ኣይሰራም። ግን ደሞ ለሃብታሙ ህንጻ የሚሰራው ወዛደር ቢያንስ ቤት ኣከራይቶ የቀን ኑሮውን የሚገፋበትን ሊከፍለው ይገባል። ቀን ቀን ኣሸዋና ሲሚንቶ ሲያቦካ ውሎ ለምን ጎዳና ላይ ይወድቃል? መንግስትስ እንዲህ ያለውን ኣስከፊ ስርዓት ለምን በተወሰነ ደረጃ ኣያጠብም? ለምን ፖሊሲ ኣያወጣም?። የካፒታሊዝም ጽንሰ ሃሳብ እኮ እንደዚህ ኣይደለም። ካፒታሊዝም ፍትህ ኣለው። ዜጎች ባላቸው የሥራ ኣቅም እየሰሩ የተለያየ የገቢ መጠን መኖሩ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ ድሃውን ያለልክ ጎድቶ ሃብታሙን ያለልክ ማበልጸግ የካፒታሊዝም ስርዓት ልብ ኣይደለም።

የሚገርመው ስርዓቱ ፍትሃዊ ባይሆንም እነዚህ ዜጎች ኣይናከሱምና ኑሮኣቸው ሁሉ የሚያሳዝን ይሆናል::

ደሞ መንግስት ሥራ ጠፋ ሲሉት ሥራ ንቃችሁ ነው ኣይነት ይናገራል። ተናቀ የተባለው ስራ ምንድን ነው? ብላችሁ ብትጠይቁ ያው የወዛደርነት ሥራ ነው። የመጀመሪያው ጥያቄ ታዲያ ኣሁን ይህ ሚሊዮን ሥራ ኣጥ በቃ ሥራ ኣንንቅም እሺ ወዛደርነቱን እንሥራ ብሎ ቢወጣ ይህንን የሚያስተናግድ ኢንዱስትሪ ወይም የኮንስትራክሽን ስራስ የታለና ነው? የትኛው የፋብሪካ ስራ ወይም የኮንስታራክሽን ስራ በወዛደር እጦት ስራ ኣቆመ?

እውነቱን ለመናገር ኣንዳንድ ሰው ወደ ወዛደርነት ስራ የማይሳበው ገቢው ስላነሰ ወይም ስለማያኖረው ነው። በሃገራችን ውስጥ የሲቪል ኤንጂኔር ስራ ስለምን ተከባሪ ሆነ? ባህላዊው ሲቪል ኤንጂነር (ኣናጺው) የተከበረ ነበር ወይ? ብለን ብንጠይቅ ኣልነበረም:: “ኣናጢ መናጢ” ነበር የሚባለው። ምንም የሌለው ድሃ ማለት ነው መናጢ ማለት። ሁዋላ ላይ ታሪክ ተቀየረና ዘመናዊ ትምህርት ተምረው የመጡ ኣናጺዎች (civil engineers) ገቢያቸው ዳጎስ ያለ በመሆኑና የነሱን ኑሮ ብቻ ሳይሆን የቤተሰባቸውን ህይወት የሚቀይር ገቢ ስላላቸው ተወደዱ።

በድሮ ጊዜ፣

“የኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ
ወሰደሽ ኣስተማሪ…” ይባል ነበር ኣሉ።

በኔ ጊዜ ኣስተማሪ ለትዳር የማይመረጥበት ጊዜ ስለምን ሆነ? ያው ከኑሮው ጋር ከገቢው ኣቅም ጋር ተያይዞ ነው።

ያ የሜዳ ኣህያ ዘይዱዋል። የባህሪ ለውጥ በማምጣቱ ተከብሮ ከተባራሪነት ወደ ኣባራሪነት ተሸጋግሩዋል። የተባረከ ነውና የጅቡን ስጋ ግን ኣይበላም። እነዚህ እንስሳት እንደዚህ የሜዳ ኣህያ የባህሪ ለውጥ ቢያመጡ ያ ጅቡም ቅጠላቅጠል መብላት ይጀምርና የነዚህ እንስሶች መንደር ሰላም ይወርድበታል።መከባበር፣ መተሳሰብ ይመጣና ኣብረው ይኖራሉ። ጅብና የሜዳ ኣህያ ሳይጠራጠሩ ተቃቅፈው ያድራሉ::

ድሆች በኢትዮጵያ ውስጥ የባህሪ ለውጥ ሊያመጡ ይገባል። እነዚህ በሙስና የከበሩ ሚሊየነሮችና ቢሊየነር ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ፊላንትሮፒክ ወይም ሰባዊ የሆነ ድርጀት እንዳላቸው ወይም እንደሚረዱ ኣላውቅም። ርሃብ ሲመጣ ኣለማቀፍ ድርጅቶች ናቸው ስንዴና ዘይት ለማቅረብ ሲሮጡ የሚታዩት።

ዛሬ ሃገራችን ባልተመጣጠነ እድገት ጎዳና ላይ እየነጎደች ነው። ያለው እየጨመረ፣ የሌለው የሚበላው እያጣ ወጣቱ ጢሙን ኣንዠርግጎ የጡረታ ኣባቱን ቤት ሳይለቅ እየኖረ ነው። ካልተናከሰ እንዲሁ ይኖራል።መናከስ ከጀመረ የባህሪ ለውጥ ካመጣ ግን ተከብሮ፣ መብቱ ተጠብቆ ይኖራል።

ኣንድ ጊዜ ትዝ ይላችሁ እንደሆነ የ ኢትዮጵያ ጦር ላይቤሪያ ዘምቶ ነበር። በዚያ ቆይታው ዩናይትድ ኔሽን (UN) ዳጎስ ያለ ኣበል ያስብለት ነበርና ይህንን ኣበሉን የኢትዮጵያ መንግስት እኔ ኣከፋፍላለሁ ብሎ ነው መሰለኝ ይቀበላል። ተቀብሎ ለወታደሮቹ ማካፈል ነበረበት። ይሁን እንጂ ይሄ የጅብ ባህሪ ያለው ኣሰራራቸው ባህሪ ሆኖባቸዋልና ያንን ገንዘብ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያሉ ያቆዩባቸዋል። መንግስትን የሚያህል ትልቅ ነገር የነዚያ የድሃ ወታደሮች ኣበል ኣጓጉታው ኣልሰጥም ብሎ ቆየ። ከተዘራፊዎቹ ኣንዱ መንግስት ዘረፈኝ ብሎ ኣስቆናል። እንግዲህ ይታያችሁ ዩናይትድ ኔሽን ለሰጠው መንግስት ቀንቶ እነዚያን ድሆች ቀማ። ሁዋላ ላይ ግን እነዚህ ወታደሮች ኣምጸው እንደነበር ዜና ሰምተናል። መንግስትም ደንግጦ እሰጣለሁ ብሎ ነበር መሰለኝ። መናከስ በመጀመራቸው እንጂ መንግስት የልፋት ዋጋቸውን ነጥቆ ኣፍንጫችሁን ላሱ ብሎ ነበር።በጠራራ ጸሃይ መንግስት እንዲህ ኣድርጎ ድሆችን የሚቀማባት ኣገር ናት ኢትዮጵያ።

ቸሩን ያሰማን ጃል!

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

አምባገነንነት ሲለመልም ነጻ ፕሬስ ይጠወልጋል በታሪኩ አባዳማ

ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።

ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን የበላይ ሃላፊዎች በጥብቅ ከመቆጣጠር ጀምሮ እያንዳንዱን የሙስና ተግባር ከጀርባ ሆኖ የሚያስፈፅመው የአዜብ የቅርብ ስጋ ዘመድ ፍትሃነገስት ክንደያ እንደሚጠቀስና ግለሰቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው 500 ሳተላይት ዲሾች እንዲገቡና በአዜብ በበላይነት ይመራ ለነበረው የዘረፋ ቡድን ለሰባት አመታት በየወሩ 20ሚሊዮን ከቴሌ በህገወጥ መንገድ እንዲዘረፍ ያደረገና በኋላም ከነገ/ዋህድ ጋር ሆኖ በርካታ ሙስናዎችን በዋናነት በማስፈፀም እንደሚጠቀስ ያመለክታሉ።

በሌላም በኩል የገ/ዋህድ ባለቤት ኰ/ል ሃይማኖት ስትጠቀስ ከሕወሐት አንጋፋ ሴት ታጋዮች አንዷ ናት፤ ከጡረታ ጋር በተያያዘ ከመከላከያ በመልቀቅ በአዜብ የበላይነት በሚመራው የሴቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቢሮ መስራት ቀጠለች። ለዚህ ቢሮ ከአሜሪካ መንግስት ብቻ በአመት እስከ 240ሚሊዮን ዶላር ይለገሳል። ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ወገኖች ሳይሆን የሚውለው የነአዜብ ኪስ ማደለቢያ ሆኖ እንደሚዘረፍ ያመለከቱት ምንጮች ይህም ጉዳይ በፓርላማ ለቀድሞ ጠ/ሚ/ር ተነስቶ « ከእንግዲህ ቁጥጥር እናደርጋለን» የሚል የተድበሰበሰ ምላሽ እንድተሰጠ ያስታውሳሉ። ባልና ሚስቱን በተለያየ ወጥመድ በማስገባት የሙስና ጋሻ-ጃግሬ አድርገው የቆዩት አዜብ እንዲሁም ሌሎቹ ቱባ ባለስልጣናት መጠነ-ሰፊ ዘረፋና ሙስና ጉዳይ ሳይነካ ግልገሎቹን ብቻ (ያውም በአስፈፃሚነት ራሳቸው የመደቧቸውን) ተጠያቂ ማድረግ ተራ ድራማ ነው ሲሉ ምንጮቹ ያጣጥሉታል። በማስረጃነትም፥ 400 ሚሊዮን ብር ለ«ራዲሰን ሆቴል ግንባታ» በሚል ሽፋን በመፍቀድ 150ሚሊዮን ኪሳቸው ከከተቱትና በርካታ ብድሮችን በመፍቀድ (የስጋ ዘመዶቻቸውን ደላላ በማድረግ…) በሙስና የደለቡት አባይ ፀሃዬ ጨምሮ፣ የበታች ሙሰኞች ላይ <ምስክር> ሆነው የቀረቡትና ከአዜብ ጋር በሙስና የሰከሩት አባዱላ ገመዳ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ባለቤት ስብሃት ነጋ፣ የቱጃሩን የቢሊዮን ብድር በግል ከመፍቀድ አንስቶ የታዋቂ ባለሃብቶች <ቀኝ እጅ> የሆኑትና ሚስታቸውን ጭምር በሙስና ያሰማሩት በረከት ስምኦን፣ ሶፍያን አህመድ፣ እንዲሁም ቪላዎችን ከ8 እስከ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ በማስገንባትና በማከራየት የአገር ሃብት የሚዘርፉ ሁሉም የገዢው ትላልቅ ባለስልጣናት የሙስና ጉዳይ በዋቢነት ይጠቅሳሉ። ባጠቃላይ የስርአቱ ቁንጮዎች የሚያናቁራቸው የገዛ ጥቅምን ከማስጠበቅና አንዱ ጎራ ከሌላው በልጦ በሙስና የሚከብርበትን መንገድ ለማመቻቸት ብሎም ሌላኛውን በመጨፍለቅ ስልጣኑን ከነታማኝ ተከታዮቹ አስጠብቆ የሚቀጥልበትን ብቻ እንደሚያልም የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ስርአቱ የአስተዳደር፣የፖለቲካ፣ የፖሊሲ…ወዘተ ልዩነት እንደሌለበት ያሰምሩበታል።

ሌላው ዘብጥያ የወረዱት ባለሃብት አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ናቸው፤ የአቶ ነጋ ባለቤት የቀድሞ የሜጋ ኪነጥበብ ሃላፊ እቁባይ በርሄ እህት ናት። ከጥቂት ወራት በፊት ከሙስና ጋር በተያያዘ አስገራሚ ፍርድ የተሰጠውና ጥፋተኛ ተብሎ የተለቀቀው እቁባይ ያንን አይን ያወጣ «ፍርድ» እንዲያገኝ የተደረገው ከአዜብ በተሰጠ ቀጭን ትእዛዝ ነው ያሉት ምንጮቹ ይህ ሊሆን የቻለው አዜብ ከአቶ ነጋ ጋር ባላቸው የቢዝነስ ትስሥር ጭምር መሆኑን አያይዘው ይገልፃሉ። (ሌላም አሳፋሪ ቁርኝት ቢኖራቸውም ለጊዜው ማለፍ ይመረጣል) ..

በሌላም በኩል የስዬ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ አብርሃ እንዲሁም አይነስውሩ አስመላሽ ወ/ስላሴ ይጠቀሳሉ፤ ምህረተአብ ከስዬ ጋር ተፈርዶበት የተለቀቀው ከአምስት አመት በፊት ሲሆን አሁን ደግሞ ከነገ/ዋህድ ክስ ጋር በተያያዘ አብሮ እንዲቀላቀል ተደርጎዋል።…. አይነስውሩ አስመላሽ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ) በፓርላማ የሕግ ጉዳይ ቢሮን ሲመሩ የቆዩ ናቸው፤ በሕወሐት ክፍፍል ጊዜ እያለቀሱ ፓርቲው እንዳይፈርስ ሲማፀኑ እንደነበር ያስታወሱት ምንጮቹ በተለይ በአንድ ቀን ተፅፎ እንዲወጣ የተደረገውንና አንድ ሰው ለማጥቃት ሲባል ብቻ አዋጅ ሆኖ እንዲፀድቅ የተደረገውን ዋስትና የሚከለክል ሕግ ካረቀቁት አንዱ እንደሆኑ ይገልፃሉ። የአስመላሽ ባለቤት በጠ/ሚ/ሩ ቢሮ ተመድባ በፀሓፊነት የቆየችና በተለይ «ሚስጥራዊ» የሚባሉ ዶክመንቶችንና የአቶ መለስ ፅሁፎችን (በብእር ስም ይወጡ የነበሩትን ጭምር) በመተየብ በታማኝነት ስታገለግል እንደቆየች አመልክተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ጄኔራሎችና የበታች ከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከጥቂት ወራት በፊት ለመጠቆም እንደተሞከረው የሚባረሩ ጄኔራሎች እንዳሉ መገለፁ ይታወሳል። በዚህ መሰረት ከአዜብ ጋር የከረረ ፀብ ውስጥ የገቡት ጄ/ል ታደሰ ወረደን ጨምሮ ሶስት የሕወሐትና ሁለት የብአዴን ጄ/ሎች በሳሞራ ውሳኔ መባረራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። በቅርቡ የተጀመረውና « የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን» በሚል መሪ አጀንዳ የቀጠለው ግምገማ ተጨማሪ የመከላከያ የጦር አዛዦችንና የበታች መኮንኖችን ለማባረር ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ማጠናቀቁ ታውቋል። በሳሞራ የተወሰነው ሌላው ጉዳይ ለመከላከያ ከሩሲያ የመጡ የመሳሪያ ባለሙያዎች በተለያዩ ቦታዎች እንዲመደቡ መደረጉ ሲታወቅ ይህም የሆነው « አገሪቱ ውስጥ ችግር ከተፈጠረ ልንቋቋም አንችልም » በማለት ሳሞራ ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸውና ከአየር ሃይል አንስቶ ያለው ወታደራዊ ክፍል እምነት ሊጣልበት ባለመቻሉ እንደሆነ ምንጮቹ አስረድተዋል። የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን ለአቶ ሃ/ማርያም ይህ ስልጣን እንዳልተሰጣቸው፣ ጄ/ሎች ሲባረሩ ከእርሳቸው እውቅና ውጭ እንደሆነ፣ ውሳኔው በሳሞራ እንደሚከናወን ምንጮቹ አስረድተዋል።

አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ኢትዮጵያና የአፍሪካ አንድነት/ኅብረት በፍቅር ለይኩን

$
0
0

‹‹ኢንሳክሎፒዲያ ብሪታኒካ›› ስለ አፄ ኃ/ሥላሴ ባቀረበው አጠር ያለ ጽሑፍ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹Haile Selassie played a very important role in the establishment of the Organization of African Unity in 1963.››
ዕለታዊው የአዲስ ዘመን የወርኻ ግንቦት 15 ቀን 1955 ዓ.ም ዕትሙ በፊት ለፊት ገጽ ላይ፣ ‹‹ሠላሳ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ጉባኤ በአፍሪካ አዳራሽ ተከፈተ፡፡ ግርማዊ ጃንሆይም የጉባኤው የክብር ሊቀመንበር እንዲሆኑ ተመረጡ፡፡›› በሚል ዐቢይ ርዕስ ዜናና ሰፊ ሐተታን ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡

የሰኞ ማለዳው የግንቦት 19 ቀን 1955 ዓ.ም የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ደግሞ በርእሰ አንቀጹ፣ ‹‹የካዛብላንካና የሞኖሮቪያ የሌሎችንም ብሎኮችና ቻርተሮች ሠርዞ የአፍሪካ አንድነትን የሚመሠርተው ‹የአፍሪካና የማላጋሲ አገሮች ድርጅት ቻርተር› ግንቦት 17 ቀን ለግንቦት 18 ቀን አጥቢያ 1955 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ በአፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ተፈርሟል፡፡ በአራቱ ቀን ጉባኤ ፍጻሜ አዲስ የአፍሪካ ታሪክ፣ አዲስ የዓለም ታሪክ ተጽፏል፣ ተመዝግቧል፡፡›› ሲል የምስራቹን ዜና አስነብቧል፡፡
የትላንትናው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት የ50ኛ ዓመቱን የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን በተለያዩ አገር አቀፍና አኅጉር አቀፍ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅቱን ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመሥረት ግንባር ቀደም ሚና ባላትና ታላቅ አስተዋጽኦ ባደረገችው፣ የኅብረቱም ዋና መቀመጫ በሆነችው በአገራችን ኢትዮጵያ የበዓሉን ዝግጅት የደመቀና ልዩ ለማድረግ ሽር ጉድ እየተባለ ነው፡፡

ይህን በዓልም ባማረና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ራሱን የቻለ የበዓል ዝግጅት ሴክረታሪያት ቢሮ ተቋቁሞ፣ የአፍሪካ ኅብረት የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በዓሉን ዓመቱን ሙሉ ለማክበር፣ የተለያዩ ዝግጅቶችን ቀርጾ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ አይተናል፣ ሰምተናል፣ አውቀናልም፡፡

ከወራት በፊትም በመዲናችን በአዲስ አበባ ዋና ዋና ቦታዎችና አደባባዮች ላይ ‹‹I am African. I am the African Union›› የሚሉ የአፍሪካ ሕዝቦችን ማንነት፣ ታሪክ፣ ቅርስና ባህል የሚያንጸባርቁ፣ የአፍሪካዊነትን ስሜት፣ ኩራትና ወኔ የሚቀሰቅሱ ፖስተሮችን አይተናል፡፡ ከዑራኤል ወደ እስጢፋኖስ በሚወስደውም መንገድ ላይም የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ያቋቋሙ የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ የሆኑ አባቶች ምስልም በትልቁ ተሰቅሎ አይቻለሁ፡፡ ይህ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መልካም ሊባል የሚችል ነው፡፡
ለወደፊቱም በዓሉ በተለያዩ መጠን ሰፊ በሆኑ ዝግጅቶች እንደሚከበርና በበዓሉም ላይም የአፍሪካ አገራት ርዕሳነ ብሔራት፣ ተወካዮችና ባለ ሥልጣናት፣ ዓለም አቀፍ መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለ ሙያዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ደራሲያን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች … ወዘተ በሚሳተፉበት በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የበዓሉ ዝግጅት ኮሚቴ በተደጋጋሚ አሳውቋል፡፡

በዚህ ጽሑፌ ከሰሞኑ መላው አፍሪካና አፍሪካውያን፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና እንዲሁም በአጠቃላይ የአፍሪካ ወዳጆች፣ የመንግሥታቱ ድርጅት፣ የተለያዩ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ታዋቂ ሰዎች አብርውን በደስታ ሊያከብሩት እየተዘጋጁ ስላለው የአፍሪካ ኅብረት የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ስናወራ ልብ ልንለው የሚገባ አንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ፡፡

ይኸውም በዚህ በዓል ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን ትልቅ መሥዋዕትነት የከፈሉትንና ስማቸውን በወርቅ ቀለም በታሪክ ማሕደር የጻፉትን አፍሪካውያን አባቶቻችንን ማስታወስ የሚገባን ይመስለኛል፡፡ ይህ ጽሑፍም ለትላንትናው አፍሪካ አንድነት ድርጅት ለዛሬው የአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን የታገሉትን የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ አባቶቻችንን ታሪክ በተከታታይ በአጭሩ ለማቅረብ ይሞክራል፡፡

ይህ ጹሑፍ የአፍሪካ ኅብረትን የ50ኛ ዓመት ወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በቅድሚያ የአፍሪካ አባት፣ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማትና የጥቁር ሕዝብ የነጻነት ዓርማ፣ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቋቋምና በሂደትም ለኅብረቱ እውን መሆን ትልቁን የመሠረት ድንጋይ ስላስቀመጡት ስለ አፄ ኃ/ሥላሴ ታሪክ፣ ፖለቲካዊ ሰብእና፣ በአፍሪካውያንም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ስለነበራቸው መወደድ፣ ተቀባይነትና ታላቅ ክብር በአጭሩ በማዘከር የታሪክ ማስታወሻውን አሐዱ ብሎ ይጀምራል፡፡
የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ስለ አፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥት ታሪክ በእሳቸው ዘመን ከነበሩ ከተራው የኅብረተስብ ክፍል ጀምሮ እስከ ታላላቅ ባለ ሥልጣናትና የሃይማኖት አባቶች፣ ዲፕሎማቶች፣ የውጭ አገር መሪዎች፣ ታላላቅ ሰዎችና ፖለቲከኞች በቃል ከተናገሩት፣ በጽሑፍ ካስቀመጡት፣ በግል ማስታወሻዎቻቸው ከተዉልን፣ እንዲሁም የአጼ ኃ/ሥላሴንና የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጸሐፍት በመጻሕፍቶቻቸው ካሰፈሯቸው መረጃዎች በመነሣት ነው ይህን አጠር ያለ የታሪክ ማስታወሻ ጽሑፍ ያዘጋጀሁት፡፡

በአጭር ቃል የዚህ ተከታታይ ታሪክ አቅራቢ የአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን ጣእሙንም ሽታውንም አልደረስበትም፡፡ በእሳርቸው ዘመንም አልታሰበም፣ አልተፈጠረምም፡፡
ይሁን እንጂ እንደ ታሪክ ተማሪነቴና ባለሙያነቴ የኢትዮጵያን ታሪክ በሰፊውና በሚገባ ማጥናት ከጀመርኩበት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አንስቶ አሁን እስካለሁበት የትምህርት ሕይወቴና የሥራ ልምዴ እንዳስተዋልኩት፣ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ አፄ ኃ/ሥላሴ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የሚገለጹበት ታሪክ፣ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድም አንቱታን ያተረፉበትን ዝናና ክብር እንዲጎናጸፉ ያደረጋቸው በሳል የሆነ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሰብእና እንዳላቸው ነው የተረዳሁትና ያስተዋልኩት፡፡
በስድስት ዓመታት ውስጥ ለሁለት ጊዜ ‹‹Man of the Year›› የዓመቱ ምርጥ ሰው በማለት የለንዶኑ ታይምስ መጽሔት የመረጣቸው አፄ ኃይለ ሥላሴ ከፍ ያለ ሰብእና የነበራቸውና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ታላቅ መሪና አባት የሚታዩ የተዋጣላቸው ዲፕሎማቲክ፣ እንዲሁም በዓለማችን ከሚገኙ ታላላቅ መሪዎችና ፖለቲከኞች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ የነበራቸው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናትና ብዙዎች ሰዎች ይመሰክራሉ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃ/ሥላሴ ከሀያ በየሚበልጡ የክብር ዶክትሬት ድግሪዎችን ከተለያዩ አገራት መሪዎችና ዩኒቨርስቲዎች ተቀብለዋል፡፡ ምናልባትም አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከምትታወቀበት ድርቅ፣ ራብና የእርስ በርስ ጦርነት ባሻገር በአንጻራዊ መልኩም ቢሆን በአዎንታዊነት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአገራችንን ስም በመልካም እንዲነሣ ምክንያት ከሆኑ የኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አፄ ኃ/ሥላሴ አንዱ፣ ብቸኛውና ዋንኛው ናቸው ብል፣ ብዙም ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡
ይህን ኢትዮጵያን አዎንታዊ በሆነ መልኩ እንድትነሳ በማድረግ ረገድና ዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ የነበራቸውን ተቀባይነት፣ ክብርና ዝና እንዲሁም ለባለ ቃል ኪዳን አገሮችና በኋላም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መመሥረት፣ ለ50ኛ ዓመቱ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉ ዋዜማ ላይ ለሚገኘው ለአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን፣ ንጉሡ አፄ ኃ/ሥላሴ የነበራቸውን ትልቅ ሚና የሚያስታውስ አንድ ያጋጠመኘኝን ታሪክ እዚህ ጋር ማንሳቱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

እውቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላና በርካታ አፍሪካውያን የነጻነት ታጋዮች ለ27 ዓመታት በተጋዙበትና በመንግሥታቱ ድርጅት፣ ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ አድርጎ በመዘገበው በሮቢን ደሴት ሙዚየምና በደቡብ አፍሪካ የአርትና ካልቸር ደፓርትመንት የሚሰጠውን የስኮላር ሺፕ አሸንፌ፣ በተማርኩበት በኬፕታውኑ የዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቆይታዬ ከኢትዮጵያዊነት የነጻነት መንፈስና ከአፄ ኃ/ሥላሴ ጋር በተገናኘ አንድ በእጅጉ ያስደነቀኝ ነገር ገጥሞኝ ነበር፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በዋነኝነት በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲና በኬፕ ታውን ዩኒቨርስቲ በሚገኙ ደቡብ አፍሪካውያንና የሌሎች አፍሪካ አገሮች የተቋቋመ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ (የራስ ተፈሪያን) የተማሪዎች እንቅስቃሴ ኅብረት በሚል መጠሪያ የሚታወቅ በዩኒቨርስቲው ግቢ ቢሮ ተሰጥቶት የሚንቀሰቀስ ማኅበር ነበር፡፡
በነገራችን ላይ በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች እንደታዘብኩት በፖለቲካና በሃይማኖት፣ እንዲሁም ኪነ ጥበብን፣ ባህልንና ታሪክን መሠረት አድርጎ የተቋቋሙና በነጻነት በዩኒቨርስቲው ግቢ ቢሮ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ በተማሪዎች የተቋቋሙ የተለያዩ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ይገኛሉ፡፡

ታዲያ እኔ በተማርኩበት በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ የተማሪዎች ኅብረት እንቅስቃሴ ቢሮ ውስጥ የእንቅስቃሴው ደጋፊዎችና አባላት የሆኑት ተማሪዎች ለኢትዮጵውያን የስኮላር ሺፕ ተማሪዎች ባቀረቡላቸው ጥያቄ መሠረት የአማርኛ ቋንቋን የሚያስተምሯቸው ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ ተማሪዎች ነበሩ፡፡
እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ከእኔ ቀደምው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለምርምር ሥራ፣ ለልምድ ልውውጥና ለተጨማሪ ጥናት ወደ አውሮፓ በሄዱበት አጋጣሚ ለእነዚህ አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ከአንተ በተሻለ ስለ ኢትዮጵያችን የሺህ ዘመናት ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ የነጻነት ተጋድሎና ቋንቋችንን ሊያስተምራቸው የሚችል የለም በማለት ከራስ ተፈራውያኑ የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ጋር አስተዋወቁኝ፡፡

ከዚሁ ማኅበር አባላት ተማሪዎቹ ጋር በተዋወኩበት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚገባ ለመግባባት ቻልን፡፡ ለጥቂት ወራት እነዚህ ወጣት ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ማስተማር ቆይታዬ እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስ፣ ሃይማኖት … ወዘተ ባደርግናቸው ውይይቶች በርካታ ቁም ነገሮችን አንስተን እንነጋገር ነበር፡፡
በአብዛኛው የውይይታችን ማእክል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ፣ ለአፍሪካ የፀረ-ባርነትና የፀረ-ቅኝ ግዛት የነፃነት ትግል፣ በደቡብ አፍሪካ ፀረ-አፓርታይድ ትግል ውስጥ ስለነበራቸው ጉልህ ሚናን በተመለከተ ነበር፡፡ በዚህ ውይይታችን ውስጥ ደግሞ ደጋግመው ከሚነሱት መካከል አፄ ኃ/ሥላሴ አንዱና ዋናው መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

እኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴና የታሪክ ባለሙያነቴ ስለ አገሬ ኢትዮጵያ ታሪክና ስለ መሪዎቻችን ካለኝ ግንዛቤና እውቀት ይልቅ እነዚህ አፍሪካውያን ተማሪዎች ስለ አኅጉራችን አፍሪካና ስለ አገሬ ታሪክ ያካፈሉኝ እውቀታቸውና ያላቸው መረዳት በጊዜው በእጅጉ ግርምትን አጭሮብኝ ነበር፡፡
እነዚህ ተማሪዎች ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህልና የነጻነት ተጋድሎ ውስጥ ያላቸውን ማእከላዊ ስፍራን በተመለከተ የሚያስረዱ በቢሮአቸው ያሰባሰቧቸው መጻሕፍቶችና መዛግብቶቻቸው፣ የምስልና የድምፅ መረጃ ክምችቶቻቸው በእጅጉ ነበር ያሰደነቀኝ፡፡

ከዚህም በላይ ደግሞ ሌላው በእጅጉ ያስደመመኝ ነገር ቢኖር በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በሚገኘው የራስ ተፈሪያኑ ተከታዮች ማኅበር ቢሮ ግድግዳ አንድ ጎን በሁለት የታሪክ መስመር ተከፍሎ በተለያዩ ሰዎች ምስሎችና መረጃዎች አሸብርቆ ያየሁት Wall of Fame እና Wall of Shame የሚለው የቢሮው ግድግዳ ክፍል ነው፡፡
በዚሁ Wall of Fame እና Wall of Shame ወይም ‹‹የታሪክ ዕንቁዎችና የታሪክ አተላዎች›› ተብሎ በተከፈለው ግድግዳ ላይ ‹‹በዎል ኦፍ ፌም›› ምስላቸውና ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ከተለጠፉት መካከል የአፄ ኃ/ሥላሴና የባለቤታቸው የእቴጌ መነን በመጀመሪያው ረድፍ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በዓድዋው ዘመቻ የኢጣሊያንን ወራሪ ኃይል አሸንፈው አዲስ የጥቁር ሕዝቦችን አዲስ ታሪክ የጻፉት የአፄ ምኒልክ፣ እንዲሁም ከእንግሊዞች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን የሠዉት የአፄ ቴዎድሮስ ምስሎችና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

በዚህ ‹‹የታሪክ ዕንቁዎች›› የክብር ግድግዳ ላይ አፄ ኃ/ሥላሴ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በገፍ በወረረች ጊዜ በሊግ ኦፍ ኔሽን፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያቀረቡት አቤቱታና ንግግራቸው በልዩ ንድፍና በአገራችን ሰንደቀ ዐላማ አሸብርቆ በግድግዳው ላይ ይታያል፡፡ ‹‹የዎል ኦፍ ፌምን›› ግድግዳ ካስዋቡ የታሪክ ሰዎች ፎቶግራፎች በአብዛኛው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸቱት በዓይነትም በብዛትም እጅግ ልቀው ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ ‹‹በዎል ኦፈ ፌም›› የታሪክ መስመር ውስጥ ለጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ትልቅ ተጋድሎ ያደረጉ እንደ እነ ማርከስ ጋርቬይ፣ አፍሪካ አሜሪካዊው ማርቲን ሉተር፣ የፓን አፍሪካ አባቶች የጋናው ንኩርማ፣ የኬንያው ጆሞ ኬንያታ፣ ሴኔጋላዊው ሴዳር ሴንጎርና ሌሎችም የአፍሪካ የነጻነት ታጋዮችና መሪዎች በኢትዮጵያ ሰንደቀ ዓላማና በኃ/ሥላሴ ግንባር ቀደም አዝማችነት የክብር ግርግዳውን ተጋርተውታል፡፡

ሌላው አስገራሚው ነገር የንጉሡን የአፄ ኃ/ሥላሴን ልደትና የነገሡበትን ዕለት የራስ ተፈራውያኑ ማኅበር ተከታይ ተማሪዎች እንግዶችን ከውጭ ሁሉ ሣይቀር በመጋበዝ ጭምር የዩኒቨርስቲውን የተማሪዎች ማእክልንና የግቢውን ሜዳ በኢትዮጵያ ሰንደቀ ዓላማ፣ በኃ/ሥላሴና በባለቤታቸው እቴጌ መነን ፎቶ ግራፍ አሸብርቀውና በአፍሪካ የሬጌ ሙዚቃ ስልት አጅበው በታላቅ በሆነ የኢትዮጵያዊነት የነጻነት መንፈስ ቀናቱን ያከበሩ እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡

የማስታውሰው በዩኒቨርስቲው የምንገኘው በጣት የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በአፍሪካም ሆነ በተቀረው ዓለም በድርቅ፣ በራብና በእርስ በርስ ጦርነት ስማችን እየተነሳ የምንሳቀቅበትን ምስላችንን፣ እነዚህ የዩኒቨርስቲው የራስ ተፈራውያን ተከታይ ተማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በግቢው ውስጥ የአገራችንን አረንዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቀ ዓላማ ሰቅለው ሲያከብሩ ስናይ በአገር ፍቅር ናፍቆትና ትዝታ፣ በኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜትና ኩራት ውስጣችን የተናጠበትን አጋጣሚ አልረሳውም፡፡
በእርግጥ የእነዚህ ተማሪዎች እንቅስቃሴና አካሄድ በአብዛኛው ሃይማኖታዊ መልክ ያለውና ኃ/ሥላሴን መለኮታዊ ሰብእና እንዳላቸው አድርጎ የሚያቀርብ ቢሆንም የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ከሃይማኖታዊ መልኩ ይልቅ አፍሪካዊነቱና ፖለቲካዊ አንድምታው በእጅጉ የጎላ ነው፡፡
እነዚህ ደቡብ አፍሪካውያንም ሆነ የሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተማሪዎች ልብም ሆነ በአብዛኛው ጥቁር ሕዝቦች ልብ ውስጥ ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስ፣ ሃይማኖት፣ ነጻነት ትልቅ ተምሳሌትና ማእክል ተደርጋ የምትወሰድ አገር ናት፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ባላት የሺህ ዘመናት የረጅም ዘመን ሥልጣኔ፣ ታሪክና ቅርስ የተነሣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የሆነ የታሪክ እሴት ያላት አገር ለመሆን በቅታለች፡፡ በተለይም ደግሞ መላው አፍሪካንና የጥቁር ዘርን ሁሉ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያነቃነቀው ኢትጵያውያን በዓድዋ ጦርነት ያስመዘገቡት አንጸባራቂ ድል ኢትዮጵያን ከጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ማማ ላይ እንድትወጣ አስችሏታል፡፡

ለአፍሪካ፣ ለአፍሪካ አሜሪካውያንና በጃማይካና በካረቢያ ላሉ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ትግል መለኮስ ይኸው የአድዋው ድል ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው፡፡ የእነ ማርከስ ጋርቬይና የትግል አጋሮቹ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነትና የመብት ጥያቄ ውሉ የሚመዘዘው ከኢትዮጵያዊነት የነጻነት መንፈስ፣ የአባቶቻችን የአይበገሬነትና ቆራጥ የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ነው፡፡
የአፍሪካውያኑ የፓን አፍሪካ አቀንቃኞችና የፀረ ቅኝ ግዛት ታጋዮች የእነ ንኩርማ፣ የእነ ጆሞ ኬንያታ የአፍሪካዊነት ስሜትና ቆራጥ መንፈስ መፍለቂያ ምንጩም ይኸው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከተሸከሙት ክቡር የነጻነት ተጋድሎ አኩሪ ታሪክና ቅርስ የሚመዘዝ ነው፡፡

ከአፄ ምኒልክ የዓድዋው ድል በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኃያላኑ አገሮች እኩል የተሠለፈችው ብቸኛው የጥቁር ሕዝብ አገር ኢትዮጵያ ይህ ገናና የነጻነት ተጋድሎ ታሪኳ ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከአውሮፓ እስከ ኤዥያ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ጃማይካና ካረቢያን ምድር ድረስ ዘልቆ ተሰምቶ ነበር፡፡
ይህ የኢትጵያዊነት የነጻነት መንፈስ ውሉ ሳይቋረጥ በአፍሪካውያንና በጥቁር ሕዝቦች ደም ውስጥ በሚገባ ተዋህዶ፣ በተባበረ ክንድ የጸናችና አንድ የሆነች አፍሪካ በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ደግሞ ትልቁን ሚና በመጫወት ረገድ አፄ ኃ/ሥላሴ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

ይህን ለአፍሪካ አንድነት እውን መሆን ኢትዮጵያና አፄ ኃ/ሥላሴ ያደረጉትን ታላቅ አስተዋጽኦና ተደናቂ ሥራ በተመለከተ በወቅቱ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ የተገኙት የናይጄሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆኑት፣ ክቡር ሰር አል ሃጂ አቡበከር ታፌዋ ባሌዋ እንደሚከተለው ነበር ያሉት፡-
መላው የአፍሪካ መንግሥታት መሪዎችና የመንግሥታት ባለ ሥልጣኖች በአዲስ አበባ ላይ ሊገኙ ለመቻላቸው በግርማዊነትዎ ጥረት ስለሆነ በተለይ ለግርማዊነትዎ እጅግ ከፍ ያለ ክብር የሚያሰጥ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ አንድነት እንዲገኝ የምናደርገው ጥረት ወደፊት የኢትዮጵያን መናገሻ ከተማ የአዲስ አበባ ስም ደጋግሞ የሚያወሳ ስለሆነ የአዲሲቱ አፍሪካ ታሪክ የግርማዊነትዎን ስም በተቀዳሚው ገጹ ላይ አሳምሮ የሚያኖረው ለመሆኑ ጥርጥር የለበትም፡፡
አፄ ኃ/ሥላሴ በ1930ዎቹም ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል እንድትሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ኢትዮጵያንም ብቸኛዋ አፍሪካዊትና የጥቁር አገር ሊግ ኦፍ ኔሽን አባል በማድረግ ጥረታቸውን በሚገባ አሳክተዋል፡፡

በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ምሥረታ ስብሰባ ወቅትም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዜቬልት፣ ከብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችልና ከቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ስታሊን ጋር በያልታ ጥቁር ባሕር ልዩ ስብሳባ ላይ ተሣትፈዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጋራ ስምምነት መሠረትም በኮሪያ ልሣነ ምድር የኢትዮጵያን የሰላም አስከባሪ ኃይል በማሰማራት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በዚህም አፄ ኃ/ሥላሴ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲታወቁ ትልቁን ሚና ተጫውተው አልፈዋል፡፡

ፍቅር፣ ወንድማማችነት፣ ሰላም፣ አንድነትና ኅብረት ለአፍሪካና ለአፍሪካውያንን ወሳኝና ተቀዳሚ ነገር መሆኑ የተረዱት አፄ ኃ/ሥላሴ አፍሪካውያን አባቶችን፣ ፖለቲከኞችንና መሪዎችን በማስተባበር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲቋቋም የላቀ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በወቅቱ ድርጅቱ ሲቋቋም የነበሩ ሰዎች እንደመሠከሩት አፄ ኃ/ሥላሴ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የአፍሪካ መሪዎችን ጉባኤ ስብሰባ በመምራት፣ ይህ የአፍሪካውያን የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የፍቅር ሰነድ ሳይፈረም ማንኛችንም ብንሆን ከዚህ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በጭራሽ አንወጣም በማለት የተኮራረፉና የተለያዩ ፖለቲካዊ ቁርሾ ውስጥ የገቡትን የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በማግባባትና በማሸማገል ንጉሡ ኅብረቱ እውን እንዲሆን ታላቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡

የትላንትናው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት በሁለት እግሩ እንዲቆም በማስቻል የኢትዮጵያ የሺህ ዘመናት ታሪክ፣ ሥልጣኔና ቅርስ፣ የቀደሙ አባቶቻችን ጽኑና አይበገሬ የሆነው የኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ኩራትና መንፈስ እንዲሁም ጥቁር ሕዝቦችን ሁሉ ያኮራውና አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲራመድ ያስቻለው የኢትዮጵያውያኑ የነፃነት ተጋድሎ፣ በባርነትና በቅኝ ግዛት ስር ይማቅቁ ለነበሩ ለአፍሪካ አገሮች ነፃነትና አንድነት እውን መሆን ትልቁን መሠረት ጥሏል፡፡

ይህን የኢትዮጵያንና የኢትጵያውያንን ታላቅ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ብሔራዊ ኩራትና የአባቶቻችንን አኩሪ የነፃነት ገድል ለዘመናዊው ዓለም በማስተዋወቅና ረገድ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት ኃ/ሥላሴ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ክቡር ስምና ዝናና የፈተረላቸውን በርካታ አኩሪ ስራዎችን ሠርተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዛሬ የ50ኛ ዓመቱን የወርቅ ኢዮቤልዩ ልደቱን ለማክበር ዋዜማ ላይ ያለውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ኅብረት እንዲቋቋም ከሐሳብ ወይም ከጽንሱ አንስቶ እስከ ተግባራዊነቱ ድረስ የላቀ ተሣትፎ ነበራቸው ንጉሡ አፄ ኃ/ሥላሴ፡፡

ንጉሡ ቀዳማቂ አፄ ኃ/ሥላሴ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምሥረታ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፡-
በዚህ በዛሬው ቀን በዚህች በዋና ከተማችን በአዲስ አበባ የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ተካፋይ ለመሆን የመጣችሁትን የነፃ አፍሪካ አገር መሪዎች፣ ወንድሞቻችን በራሳችንና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ስንቀበል በጣም ደስ ይለናል፡፡ ይህ ዛሬ እኛ የአፍሪካ ነፃ መንግሥታት መሪዎች የምናደርገው ጉባኤ በዓለም ላይ እስካሁን ድረስ ተወዳዳሪ የለውም፡፡ የዚህን ታላቅ ጉባኤ መደረግና የመላው አፍሪካ አገሮች መሪዎች ተካፋይ በመሆን ለዚህች ክፍለ ዓለማችን በውስጧም ለሚገኙት ሕዝቦቻችን ላለን ጥልቅ አሳቢነት ዓይነተኛ ምስክር ነው፡፡ ባጭሩ ይህ ቀን ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን በመላ ታሪካዊና ታላቅ ቀን ነው … ፡፡
የጊኒ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሴኮ ቱሬም በአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ለአፍሪካ አንድነት ምስረታ ኢትዮጵያና ንጉሡ አፄ ኃ/ሥላሴ ያደረጉትን ታላቅ አስተዋጽኦና ሥራ በተመለከተ ሲናገሩ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

… ኢትዮጵያዊ ታላቅ ሕዝብ ነው፡፡ ስለ አፍሪካ ነፃነት በጀግንነት የተዋጋ፣ ነፃነትም ቋሚ እንዲሆን፣ ሕዝቦቻችን ያለ ምንም የውጭ መንግሥታት ተቆጣጣሪነትና ጣልቃ ገብነት በተገቢ ሥልጣናቸው እየተመሩ የገዛ ራሳቸውን ዕድል እንዲመሩ ያላቸው ሥልጣን እንዲጠበቅላቸው የደከመ አፍሪካዊ ሕዝብ ነው፡፡ ይህ በንጉሠ በአፄ ኃ/ሥላሴ አስተባባሪነትና መሪነት፣ የአፍሪካውያኖችም ጉባኤ የተደረገው በኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ ስለሆነ፣ አዲስ አበባና ኢትዮጵያ አሁንም የበለጠ ከአፍሪካ ታሪክ ጋር የተሳሰሩ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት በአንድ አኅጉር ሕዝቦች ፈቃድ ተነሳስቶ በሚመራው የዕድገት ፍላጎትና ሥራ ሁሉ ሳይቋረጥ ስማቸው ተያይዞ የሚኖር ይሆናል … ፡፡
ለአፍሪካ አንድነት እውን መሆን ከአገራችን ኢትዮጵያና ከአፄ ኃ/ሥላሴ ጋር አብሮ ስማቸው የሚነሡ ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ድርጅቱንም በጸሐፊነት ያገለገሉ ባለ ታሪክ የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ አቶ ከተማ ይፍሩና የድርጅቱ የመጀመሪያ ዋና ጸሐፊ ሆነው የተመረጡት አቶ ክፍሌ ወዳጆ ናቸው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቶ ከተማ ይፍሩ በመላው አፍሪካ አገራት በመዞርና መሪዎቹን ወደ ጉባኤው እንዲመጡ በመጋበዝና በማግባባት ታላቅ የሆነ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አንዳንድ ጸሐፊዎችና ታሪክ አዋቂዎች እንደሚሉትም አቶ ከተማ ይፍሩ ከመሪዎቹ ማረጋገጫ እስከሚያገኙ ድረስ ወደ አገራቸው መሄድ እንደማይችሉ በመግለጽ አፍሪካውያን መሪዎች በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በማድረግ ትልቅ ጥረት ማድረጋቸውን ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡

የዛሬውን መጣጥፌን ከማጠናቀቄ በፊት በቀጣይ ጽሑፌ ስለ ፓን አፍሪካ አመሠራረትና፣ በፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ውስጥ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውን ድርሻ ምን እንደነበር ከታሪክ ማሕደር በማጣቀስ ለመጻፍ እሞክራለሁ፡፡ በጽሑፌም ቀንደኛ ፓን አፍሪካኒስት ስለነበረው የጋናው ዶ/ር ንኩርማ በጥቂቱ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
የዛሬውን አጭር መጣጥፌን ኢትዮጵያ፣ ጀግና ልጆቿና ንጉሠ ነገሥቷ የነበሩት አፄ ኃ/ሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅትና መመሥረትና በኋላም ለኅብረቱ እውን መሆን ያበረከቱትን ትልቅ አስተዋጽኦ ያዘከርኩበትን አጭር የታሪክ ማስታወሻ፣ አፄ ኃ/ሥላሴ በአዲስ አበባ ላይ በተደረገው የግንቦት 15ቀን 1955 ዓ.ም. የአፍሪካ መሪዎች መክፈቻ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ታሪካዊ ንግግራቸው ጽሑፌን ልቋጭ፡፡

ዛሬ የገጠመን ዕድል በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ መቼም ያልተገኘ ትልቅ ዕድል ነው፡፡ በፊታችን የተደቀኑት ችግሮች ያንኑ ያህል ከፍ ያሉና ከባድ ናቸው፡፡ ታሪክና ጊዜ የጣሉብን ከፍተኛ ኃላፊነት ሁላችንም ረጋ ብለን እንድናስብና እንድናመዛዝን ያስገድደናል፡፡ የተነሳንበትን ከፍተኛ ተግባር በመልካም አከናውነን ብንገኝ ስማችንና ተግባራችን በታሪክ መልካም ስም ይኖረዋል፡፡ ተግባራችንን ሳንፈጽም ብንቀር ግን ይታዘንብናል፡፡ ስለዚህ እምነታቸውን የጣሉብንን ሕዝቦቻችን በሚመጡት ጊዜያቶች ውስጥ ከእኛ የሚጠብቁትን ሁሉ ለመፈጸም እንዲያበቃን ሁሉን የሚችለውን ፈጣሪያችን ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሰጠን እናምነዋለን፣ እንለምንዋለን፡፡

ክብር ለአፍሪካ አንድነት ለደከሙ አፍሪካውያን አባቶቻችንና ጀግኖቻችን ሁሉ!
ሰላም! ሻሎም!

አጀንዳ! ፍ.አ

አሸባሪው ማን ነው? ከተስፋዬ ዘነበ

$
0
0

ከሳምንታት በፊት በልእለሀያሏ አሜሪካ በቦስተን ከተማ የደረሰውን በአሸባሪዎች ጥቃት ህይወታቸውን ላጡና ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሃገሪቱ ዜጎች በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ለደረሰው አደጋ ሀዘናቸውን ለመግለፅና የወንጀሉን ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል መመሪያ ሲሰጡ ሰዓታት እንዳልወሰደባቸው ስንመለከት ወራት አልተቆጠረም፡፡በመሰረቱ ይህንን ዘግናኝ ጥቃት የፈፀሙት ፅንፈኛ አክራሪዎች ብዙም ሳይቆዩ በሃገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች ታድነው በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዛቸው ለሕዝቡ ታማኝ የሆነ መንግስት ዜጎቹን ከጥቃት ለመታደግ ምን ያህል እረፍት እንደሌለው የሚያመላክት ነው፡፡
ከላይ እንደመነሻ ያነሳሁት ሃሳብ ለዛሬው ፅሁፌ እንደ መንደርደሪያ እንዲረዳኝ እንጂ እውነተኛው የዲሞክራሲያዊ ስርዓት አራማጆች ለዜጎቻችቸው የሚሰጡት ክብር የሚሳት ሆኖ አይደለው፡፡

ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ከቃል በዘለለ በተግባር የማያውቁት የወያኔ ቡድን፣ ፍትህና እርህትህ፣ ነፃነት ላጣው ሕዝብ ለውጥ ለማምጣት አጥንታችንን ከሰከስን ደማችንን አፈሰስን የሚሉት የዛሬዎቹ አምባገነን መሪዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በኢትዮጲያ፣ ለማስፈን ደከመን ሰለቸን ሳንል ታተርን የሚሉን ጥቂት ዘረኛ ቡድኖች፣ ሃገሪቷንም ሕዝቧንም በሁለት አሃዝ በልማት አሳደግን ብለው ቀን ከሌት የሚደሰኩሩልን ጥቂት የዘረኛ ቡድን ሞኖፖሊስቶች፣ ከወረቀት ያልዘለለ የመናገርና አሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አጎናፀፍን የሚሉን የዛሬዎቹ ተሸባሪ ሽብርተኞች በጀሌዎቻቸው የንፁሃን ደም ማስፈሰስ የሰነበቱበት የሃያ ሁለት አመት ተግባራቸው ቢሆንም በዚህ ሰሞን በባህር ዳር የተፈጸመውን ጅምላ ፍጅት በሙት መንፈስ አራማጁ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ሆነ እሱን በሚመሩት የህውሃት ቡድኖች ምንም አለመባሉ ይህ እኩይ ሰርዓት ምን ያህል የሕዝብ ንቀት እንዳለበት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እውነት ነው፡፡

ስለዚህ ዘረኛ ስርዓት ብዙ ቢባልም በየጊዜው በህዝብ ላይ በሚያደርሳቸው ግድያዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በሃገር ላይ የሚያደርሳቸውን መጠነ ሰፊ ችግሮች በተመለከተ ከሃገርና ከሕዝብ ወገኖች ተቃውሞ ሲደርስበት ወይንም ሰራሗቸው እያለ ከሚመፃደቅባቸው ልማት ተብዬዎችን አስመልክቶ ከሚሰግድላቸው ምህራባዊያን ሃገሮችም ሆነ ከአበዳሪ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚወዛገበው በቁጥር ጨዋታ መሆኑ ስርዓቱ ምን ያህል ግትርና ሞራለ ቢስ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከእድሜው መጀመሪያ ጀምሮ በዚች ሃገር ንፁሃን ዜጎች ላይ ለፈፀመው ፍጅት (ግድያዎች) አንድም ጊዜ በህግ የተጠየቀ አካል ካለመኖሩም ባሻገር የሟቾቹን ቁጥር በማሳነስ በዚህ አሸባሪ ስርዓት የተሰዉ ሰማህታት ቤተሰቦችንና ሕዝብን በመናቅ ሲሳለቁ መመልከት አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ የሆነውም ካለፈው ያልተማረው የወያኔ አምባገነን ቡድን የሆደበት የማደናገሪያ ተልካሻ ስልት መሆኑ ይህ ስርዓት በማን አለብኝነት የንፁሃንን ደም መጠጣቱ እንደቀጠለበት የሚያሳይ እውነት ነው፡፡
የጠለቀ ጥላቻ በዚች ታላቅ ሃገር ላይ ያለው ዘረኛው የህውሃት ቡድን ኢትዮጲያዊ መንፈስን ከሕዝብ ለመንጠቅ አንዱን ከአንዱ ለመለየት፣ በጎጥና በዘር እንዲሁም በእምነት ለመከፋፈል ሌት ከቀን ዘመኑን ሙሉ ለፍቷል፡፡ ሕዝብ አንድነትና ሕብረት እንዳይኖረው ውስጥ ውስጡን ሲያበጣብጥ፣ በዘር በተለከፉ ጀሌዎቹ አንዱን በአንዱ ላይ ለማስነሳት የሽብር ተግባር ሲከውኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መጠሪያው የኢትዮጲያ ሕዝብ የሆነ ግን ደግሞ በሆድ አደር ካድሬዎች በሚመራው የሕዝብ ሃብት በሆነው ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት በኩል የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ በመፈብረክ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበሩን ለማሳየት የሀሰት አታሞ ሲደልቅ ይታያል፡፡

በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ ሸብር ማለት በማንም ይፈፀም በማን ሰላማዊውን ሕዝብ የሚያውክ፣ የተረጋጋ ህይወትን የሚረብሽ፣ የንፁሃንን ህይወት የሚቀጥፍ፣ ሕዝብን ያለፈቃዱ ከቀዬውና ከመንደሩ የሚያፈናቅል፣ የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተቸረውን ነፃነት የሚቀማ፣ በሕዝብና በሃገር ላይ ጥፋትና ውድመትን የሚያስከትል . . . . .ወዘተ ከላይ በመጠኑ የተዘረዝሩት ሁሉ የዚህ ዘረኛ ቡድን መገለጫዎች መሆናቸው እንኳን ከሕዝብ ወገን ለተሰለፉ ነፃነት ናፋቂዎች ቀረቶ ስብእናቸውን ሸጠው ለሆዳቸው ላደሩት ለስርዓቱ ጀሌዎችም ቢሆን የሚጠፋቸው አይደለም፡፡ የሚገርመው ግን ይህው እኩይ ስርዓት በሕዝብና በሃገር ላይ የሚፈፅመውን በደልና ግፍ እንዲሁም ዜጎች የሚደርስባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግርና የሰብአዊ መብት ጥሰትን በብእራቸው ነቅሰው የሚዘግቡትን ለሞያቸው ስነምግባር እንዲሁም ለሕዝብና ለሃገር ቅድሚያ የሚሰጡትን ጋዜጠኞች፣ በህግ አግባብ የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው አማራጭ አሳብ በማስቀመጥ በሰላማዊ መንገድ የታገሉ የህዝብ ልጆችን፣ በተጨማሪም በሃገሪቱ ህገ-መንግስት በተደነገገው መሰረት የእምነት ነፃነታቸውን በዚህ ከፋፋይ ስርዓት ለመነጠቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ፣ መብታቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየሞቱና እየተገረፉ ትግላቸውን ከአንድ አመት በላይ ያራመዱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ መሪዎች፣ እነዚህ ከላይ ልዘረዝር የሞከርኳቸው ፍፁም ሰላማዊ የህብረተሰብ ክፍሎች በአሸባሪውና ተሸባሪው ዘረኛ ቡድን በተቆጣጠረው ነፃነት አልባው የፍትህ ስርዓት በአሸባሪነት ተፈርጀው በየማጎሪያው ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የንፁሃንን ህይወት በጠራራ ፀሃይ የሚነጥቀውና የሕዝብን ሰላማዊ ኑሮ ላለፉት ሃያ ሁለት አመታት የሚያውከው የህውሃት ዘረኛ ብድን በምግባር አሸባሪነቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡

መቼም ህውሃት ውጥረት በነገሰበትና በደል ፅዋው ሞልቶ ተቃውሞ ሲበረታበት የሕዝቡን አመለካከት ለማስቀየር በስልጣን ዘመኑ ብዙ ተልካሻ ምክኒያቶችን ሲሰራ እንደ ነበረ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጲያ አንድነት ለማፍረስና ለመበተን የስርዓቱ ሴረኝነት የበልጥ አግጥጦና አፍጦ የታየበት ጊዜ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በተለይ በአማራው ብሄር ተወላጆች ላይ የከፈተው ጥቃት ኢትዮጲያን እንደ ሃገር ያላት ታላላቅ እሴቶች ለማጥፋት የታለመ መሆኑ ማስረጃ አይቻውም፡፡ ይህንን ተከትሌ የተነሳውን በአለም አቀፍ ደረጃ በነፃ ሃገር ላይ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው በሃገራችውና በወገናቸው ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ የስቆጣቸው ኢትዮጲያዊያን ያሳዩት ተቃውሞና ሆነ ውግዘት አንገቱን ያስደፋው ዘረኛ ቡድን ሰሞኑን ደግሞ የሕዝብን መነሳሳት አቅጣጫ ለማስቀየር የመጣበት መንገድ ግርምትን የሚፈጥር ነው፡፡ በመሰረቱ የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ የሚለውን የአበው ብሂል ያስታውሰናል፡፡ እንደሚታወቀው የስርዓቱ ቁንጮዎች ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር የሰጠሙበት ሙስና፣ ከድሃው ሕዝብ ጉሮሮ ነጥቀው የበለፀጉበት ሙስና፣ ገዢዎቻችን በስልጣን ዘመናቸው በደሃው ሕዝባችን ስም ለምነው ካገኙት ገንዘብ 11ቢሊዮን ዶላር በላይ ነጥቀው ያሸሹበት ሙስና፣ እነኚሁ ዘረኛ ገዢዎቻችን በኢፈርት(EFFORT-Endowment Fund For the Rehabilitation of Tigray)ስም የሃገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ እንደ ሸረሪት ድር ተብትበው የንግድና እንደስትሪውን ካፒታል ሳይጨምር ከ50ቢሊዮን ብር በላይ ቋሚ ሃብት ባለቤት የሆኑበት በጥቂት የህውሃት ሰዎች የሚሸከረከር ሙስና፣ ይህንንና እጅግ ብዙ የሙስና ንቅዘቶች ያለበት ስርዓት የተወሰኑ ጭፍሮቺን የውም በብሄር ለክቶ አስሮ ሙስናን አጠፋለሁ እያለ የዛን መከረኛ ሕዝብ ጆሮ ያደነቁራል፡፡

የአፍሪካን አንድነት ስንመሰርት ነፃ የነበርን ዜጎች ከአምሳ አመት በሗላ የሗሊት ተጉዘን በዘረኞች መዳፍ ስር ወድቆ መገኘት በዜግነት ክብራችን ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል ስለሆነም በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሃገርና የሕዝብ ጥቃት የሚሰማን እስከ ወኔያችን እስከ ቤሄራዊ ስሜታችን ያለን እራሳችንን ሃገራችንን ከግዞት ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል፡፡

በተጨማሪም ግንቦት 17 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት የሕዝብ ይሁንታ በሌለው ዘረኛ ቡድን የሚደርስብንን አፈናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እናጋልጥ፡፡ ከአመት በላይ ድምፃችን ይሰማ እያልን በሰላማዊ መንገድ ስንታገል በአሸባሪነት ተፈርጀን መብታችንን የተነጠቅን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህንን ሰልፍ በመቀላቀል ለለውጥ በአንድነት መቆማችንን እናረጋግጥ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!!
ሞት ለወያኔ!!
Ethiocenter.blogspot.com

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) –ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ


የመለስ ዜናዊ ሌጋሲ ስቶኮልም ስንድሮም በታሪኩ አባዳማ

የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ።

« ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።

በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..

ምንጮቹ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ ሲቀጥሉ ይህን አሉ፤ የነፃ ፕሬስ ህልውና በአገሪቱ ጨርሶ እንዲጠፋ በተደረገበት ተጨባጭ እውነታ፣ የህትመት ዋጋ ጣራ በነካበት ሁኔታ ..«ሰንደቅ» የተባለው ጋዜጣ የሚያሳትመው ሁለት ሺህ ኮፒ ብቻ መሆኑ፣ ማስታወቂያ የሌለው መሆኑ፣ በተጨማሪ በሃገሪቱ ውድ በሚባለው ብርሃነ ሰላም ማ/ቤት መታተሙ እንዲሁም አዘጋጆቹ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመሆኑ ምስጢር ሼህ አላሙዲ መሆናቸውን ያስገነዝባሉ። በዚህን ያክል ኮፒ ትርፍ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮቹ፣ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉና ጋዜጣውም በየሳምንቱ ሼኹን ከፍ-ከፍ አድርገው የሚያሳዩና ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ዜናዎች እያተሙ የማውጣታቸው ምስጢሩ ከገንዘብ ድጋፉ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

በዚሁ ጋዜጣ ላይ በረከት የሚፈልጉትና « ህዝብ ዘንድ መድረስ አለበት» የሚሏቸውን ምስጢራዊ ጉዳዮች ለሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆች የስራ መመሪያ ጭምር ከመስጠት ባለፈ በረከትና ሽመልስ በተለያዩ የብእር ስሞች ፖለቲካዊ ነክ ፅሁፎች እንደሚያወጡ፣ የሚፈልጉትን መረጃ እንደሚያስተላልፉ፣ ምንጮቹ አጋልጠዋል። እንዲህ ሲሉም ያብራራሉ፥ « የእነአበበ በለውና እስክንድር ነጋ ንብረት እንዲወረስ የተለያዩ የብእር ስሞች (ሽመልስና በረከት) በመጠቀም በጋዜጣው ቅስቀሳ ሲካሄድ ከቀየ በኋላ በመጨረሻ በዋና ክስነት ከቀረበው ውጭ «የንብረት ክስ» በሚል ሌላ ክስ ተመስርቶ የንብረት ውርሱ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ። መንግስት የሰጠውን ግዳጅ በመወጣት፣ ነፃ ፕሬስን ሽፋን አድርጎ የተሰማራው ሰንደቅ ጋዜጣ ከጀርባ ያነገበው «አላማ» እንዲሁም አካሄድ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ በማስከተሉ የጋዜጣው የኮፒ መጠን ላለፉት አመታት ሊያድግ እንዳልቻ አስታውቀዋል። በተለይ የጋዜጣው ዋና <አላማ> ተቃዋሚዎችን በአለ በሌለ ጉልበቱ ጨፍልቆ በመምታት በይፋ እንደሚታወቅ አመላክተዋል።

ለዚህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ሁኔታ በአስረጅነት ይጠቅሳሉ ምንጮቹ፤ አብዛኛው አገር ቤት ያሉ ምሁራን አድፍጠው ባሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ገዢውን ፓርቲ በአደባባይ ከሚቃወሙና የተለያዩ የመሟገቻ ሃሳቦችን ከሚያቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ምሁራን አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነው በማለት ይገልፃሉ። ጋዜጣው « ዶ/ር ዳኛቸው የመኢአድ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከኢ/ር ሃይሉ ጋር መምከራቸውን» በማስቀደም አያያዞም « የብአዴን አባል ነበሩ» ሲል በተቃዋሚ ክፍሎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬን ለመጫር መሞከሩን የገለፁት ምንጮቹ በረከት ስሞኦን ያጠናቀሩት ዘገባ መሆኑን አጋልጠዋል። ይህ ዘገባ ጨርሶ ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚገልፅ ማስተባበያ ዶ/ር ዳኛቸው በጋዜጣው እንዲወጣ ከማድረጋቸው ባሻገር በፌስቡክ ባሰፈሩት መልእክት « እኔ የብአዴን አባል ብሆን ኖሮ ወረቀት በታኝ ሆኜ የምቀር ይመስላችኋል?. አባል ሆኜ ድምፄ ሳይሰማ የእነ ህላዌና በረከት ስምኦን ወረቀት በታኝ ሆኜ ልቀር አልችልም!» ብለዋል።

ምንጮቹ በማጠቃለያ ያነሱት፥ ፍሬው አበበ «ተከሰሰ» ተብሎ የተራገበውን ሲሆን፣ ከስምንት ወር በፊት የተዘገበን እና አዜብ በግልፅ ከቤተ መንግስት እንደማይለቁ በተነገረለት፣ሚሚ ስብሃቱ ሳይቀር ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያምን የሚያኮስሥና በአንፃሩ ለአዜብ የወገነ ዲስኩር ማሰማቷና እርሷ ምንም ሳትባል «ጋዜጠኛው ተከሰሰ » የተባለው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ በነበረከት የተቀናበረ « ድራማ» ነው ሲሊ ያጣጥሉታል። ምክንያቱም ሁለት ነው፤ ቀዳሚው በኢትዮጲያ ነፃ ፕሬስ አለ የሚል ስእል በመስጠት እገረመንገዱን <ፍትህ አለ> በሚል እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚቀርበውን አለም አቀፍ ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ብሎም «በእነእስክንድር የተሰጠው ውሳኔ በነፃ የህፍትህ አካላት የተወሰነ ነው» ለማለት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር

የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ

$
0
0

1.እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።

2.አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋ ላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃል በቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስ “በአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውም” አይነት ነገር ይላል።

3.ከዚያ የኛ “ትግል” ትዝ አለኝ። የኛ “ትግል”፤ ትግል ካለን፤ በአሸዋ ላይ የታነጸውን ቤት መስሎ ይታየኛል። በአህያ ቆዳ የተሰራ አይነት ቤት፤ ጅብ በጮኸ ቁጥር የሚንቀጠቀጥ። ዛሬ ስለዚያ ነው የምጽፈው። ስለዚያም ብቻም አይደለም፤ እኛንና ጠላቶቻችንን ስለሚለያዩን ወይም አንድ ስለሚያደርጉን ነገሮች እጠቅሳለሁ።

4.ለምሳሌ፤ ጠላቶቻችን ርኩስ መሆናቸው፤ እኛም የነሱን ርኩሰት ነቅሰን ማውጣታችን፤ እኛን ደርሶ ጻድቅ አያደርገንም። አንዳንዶች እነደዚያ የሆንን ሊመስላቸው ይችላል። ለምሳሌ ግንቦት ሰባት ወይንም መድረክ፤ ኢዴፓ ወይንም ኢህአፓ የኢህአዴግን ጉድ አጋለጡ ማለት እነዚህን ድርጅቶች በርግጠኝነት ከኢህአዴግ የተለዩ ያደርጋቸው ይሆናል እንጂ ያለቅድመ ሁኔታ የተሻሉ አያደርጋቸውም። ኢሳትም ለኛ ግሩም ሆነ ማለት፤ በርግጠኝነት ከኢቲቪ ይለየዋል እንጂ፤ ያለአንዳች ቅድመሁኔታ ከኢቲቪ የተሻለ ያደርገዋል ማለት አይደለም። (ይሄ፤ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ፤ ኢሳትንና ኢቲቪን አላወዳድራቸውም፤ ስለዚህ አንዳንዶቻችን ይቺን ሀረግ መዘን ወደ መደምደሚያ እንዳንከንፍ ወይም በኢሳት ላይ የተነሳሁ አይነት አድርገን እንዳንተረጉመው)። በአጠቃላይ፤ ከጠላቶቻችን የተሻልን ክፉዎች ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን ተራችንን የምንጠብቅ መጥፎዎችም ልንሆን እንችላለን ነው ሁለተኛው ነጥቤ። እንጂ፤ የኢህአዴግን ክፋት ስላጋለጥንና ስለተቃወምን ብቻ የተሻልን ነን ማለት አይደለም። ባለፈው ሰሞን እንደቀልድ በወረወርኩት ጽሁፍ የመጣው ጣጣ ያንን ያሳያል። እኛም ከጠላቶቻችን የተሻልን ላንሆን እንደምንችል ይጠቁማል።

እንደማስታወሻ፡ ካለፈው የቀጠለ

5.ለማስታወስ ያህል፤ ያለፈው ጽሁፌ ሁለት ሀሳቦች ብቻ ናቸው ያሉት። አንደኛ፤ በህዝብ ዘንድ እየተወደደ እየታወቀ ተደማጭነት እያገኘ የመጣው ኢሳት የሚያደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፤ በህዝብ ዘንድ አሉታዊም አዎንታዊም ውጤት ስለሚያመጣ፤ ጥንቃቄ ያድርግ የሚል ነው። ለምሳሌ፤ ከስድስት ከተሞች ውስጥ በአምስቱ ላይ የአንድ ሀይማኖት ብቻ ተወካዮችን መጋበዝ ብልህነት የጎደለው አካሄድ ነው የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፤ ከኢሳት ጊዜያዊ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅትም ባሻገር፤ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት ቋሚ መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚል ነው። ከዚያ ባሻገር ግን የመንግስትና ሀይማኖትን መለያየት በተመለከተ የቅንጦት የሚመስል ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ ውይይት ለመጫር ነው ጽሁፉ ሙከራ ያደረገው።

6.የተሰጡትን ምላሾች ሁሉ ለማንበብ ግዜ አላገኘሁም፤ የተወሰኑትን ግን አለፍ አለፍ ብዬ ተመልክቻቸዋለሁ። አብዛኞቹ ስድቦች ናቸው። ብዙዎቹ አስተያየቶች ደግሞ አስፈግገውኛል። ከጨዋዎቹ ተቺዎቼ ውስጥ አባዛኞቹ ያተኮሩት “ይሄንን አደባባይ ይዘህ ባትወጣ ይሻል ነበር” የሚል ሲሆን፤ በጣም ጥቂት ጨዋዎች ደግሞ “እንዴት ኢሳትን ትነካለህ? ትደፍራለህስ?” የሚሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። እንደትልቅ ድፍረት፤ ራስን ከገደል ጫፍ እንደመወርወር፤ ራስን እንደማጥፋትም የቆጠሩትም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ግጭት የተፈጠረ፤ “የከዳሁ” ሁሉ የመሰላቸው አሉ።

7.ካለፈው የፖለቲካ ልምዳችን እንደምናውቀው፤ ሰው ካልተቀየመ ወይንም ካላኮረፈ ወይንም ካልከዳ ራሱንና የራሴ የሚለውን ስለማይተች፤ የበሰሉ፤ የተማሩ፤ በዚህ በምእራቡ ዓለም ለረጅም ግዜ ኖረው የሀሳብን በነጻነትና ያለፍርሀት መግለጽ ፋይዳ ተረድተዋል የተባሉት ሁሉ ያልጠበቅኩትን ተግሳጽ ሰንዝረዋል። በእውነቱ አንድን ጽሁፍ ብቻ መሰረት አድርገን፤ እዚህ ሁሉ ስጋትና ተግሳጽ ውስጥ መግባታችን የሚያሳየው፤ “ጸረ-ኢህአዴጉም ጎራ (የኛ ጎራ ማለት ነው)፤ መንግስት በሚማቅቅበት፤ “ከመንጋው የተለየ ሀሳብን የማስተናገድ ባህል እጦት እንደሚሰቃይ ነው።” ይሄ አደገኛ ነው። እነሆ ቃና ቀይሬ እንደ ንጉስ ላስረዳ ነው።
የትችት ትችት ትችት

8.ባለፈው ሰሞን ወዳጃችን ልጅ ተከሌ ማለፊያ ግሩም ጽሁፍ አንደጻፈ ሰማን። ጽሁፉም ተነበበልን። አሰላሰልነውም። አንዳንድ ሰዎች ለጽሁፉና ለጸሀፊው የሰጡት ምላሽ አላስደሰተንም። ቢሆንም አልገረመንም። ያንዳንዶቹ የተጻፈም ያልተጻፈም ምላሽ ግን አሳስቦናል። የልጅ ተክሌን ሀሳብ ከመተቸትና ከመበለት ይልቅ፤ ልጅ ተክሌን ወደመንቀፍና ወደማጠየፍ አዘንብለዋል። የጽሁፉን ፍሬ ነገር ሳይሆን የጸሀፊው ቁመትና ውፍረት ወርድና ክብደት ላይ የሚወያይ መብዛቱ አጅግ አሳስቦናል። ሀሳቡን ተችተው አስተያየት ለመስጠት የፈቀዱትም ቢሆኑ፤ ያተኮሩት፤ “የራስ ተቋም በአደባባይ አይተችም፤ ለጠላት ደስ ይለዋል፤ ንፋስም ይገባልና” የሚል አይነት ስሜት ይጎላበታል። አንዳንዶች ከቶም የጸሀፊውን ነገር የተገነዘቡ አይመስልም።

9.ቀድሞ ነገር፤ ልጅ ተክሌ የአገራችንንና የህዝባችንን ጥቅም የሚነካ ጽፉህ ይጽፋል፤ አገራችንን የሚጎዳ መንገድ ይሄዳል ብለን አንሰጋም። ይሄ እምነታችን ጥንትም ነበረ፤ አሁንም አለ። በርግጥ ልጅ ተክሌ ብዙም ባልተለመደ መልኩ አፈሙዙን፤ ወደወገን/ወደራሱ ማዞሩ ለብዙዎች ግርታን ቢፈጥር አይደንቀንም። ይሁን እንጂ፤ አንደኛ ልጅ ተክሌ ይሄን ሲያደርጉ የመጀመሪያው አይደለም። ሁለተኛ፤ የኛ የሆነውንና በኛ ምድር ላይ የተተከለውን ልጅ ተክሌ ከሀሳቡ አልፈን እሱን መጠራጠራችን በጎ ሆኖ አላገኘነውም። ስህተትም ነው። ይሄ ጽኑ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ደዌም ነው። እስከመቼ የተለየ ሀሳብን እንሸሻለን? እስከመቼስ በራሳችን ድጋፍና ሰልፍ ጫጫታ ተውጠን እንኖራለን የሚል ጥያቄም ፈጥሮብናል? አንዳንዴ ወጣ ብሎ ማየት ያሻል።

የሀሳብ ነውር የለውም፡ የድርጊት እንጂ

10.የተለየ ሀሳብን መፍራት የለብንም። መጋፈጥ እንጂ። ሰው ነፍስ ካወቀ፤ የሀሳብ ነውር የለውም። የሀሳብ ጸያፍም የለውም። የሀሳብ ወንጀልም የለውም። ስለማይናገረው እንጂ ማንስ በጭንቅላቱ የሚያስበውን፤ በልቡም የሚመኘውን እንደምን እናውቀዋለን? ማንም ሰው፤ እንወያይበት፤ እናስበበት፤ እናድግበትም ዘንድ፤ ስህተትም ከሆነ እንዲታረምና እንዳይደገምም ብሎ ባደባባይ በስሙ በጻፈው ጽሁፍ ሲሆን ሲሆን ሊሸለም እንጂ ሊጎሸም አይገባውም። በርግጥ ልጅ ተክሌ ሲጎሸምና ሲዘለዘል የኖረ ወዳጃችን ስለሆነ፤ በአመታት ትችትና ነቀፋ የደነደነው ቆዳው በዚህ ይሰነጠቃል ብለን ከቶም አንሰጋም። የሰዎቻችን ከተለመደው የተለየ ሀሳብን ለማስተናገድ የመፍራትና የመቅፈፍ ነገር ግን ረብሾናል።

11.ደግሞስ በዚህ በምእራብ የነጻነት አጥቢያ የምንኖር ሰዎች ስለምን ትችትን እንፈራለን። ስንት ነገርስ እንፍራ? ስንት ነገርስ ያሸብረን? ኤደን ባህረሰላጤንና ሳህል በረሀን፤ አባይንና ጎጀብን ተሻግረን ተሰደን፤ በንጽጽርም ቢሆን የተሻለ ነጻነት ካለበት ዓለም መጥተንም፤ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ሰቀቀን ይከተለን? እንግዲያውስ እላችሁዋለሁ፤ ነጻነታችንና ዴሞክራሲያችን በአለት ላይ እንጂ በአሸዋ ላይ መገንባት እንደሌለበት ህዝባችን ሊያውቀው ይገባዋል። “ይሄን ሀሳብ አንሸራሽር፤ ይሄንን ሀሳብ ግን ከቶም አታንሳው” የሚል ማእቀብና ምክር፤ በአገራችን እንዲሰፍን የምንመኘው ዴሞክራሲና ነጻነት ጸር ነው። ይሄ እስክንድር የታሰረለት፤ ርእዮትም የታጎረችበት፤ ሲሳይም የተሰደደበት ራእይ አይደለም። ደግሞስ፤ ይሄንን የሚፈቅደውስ ማነው? ህሊናችን አይደለምን? ከህሊናችን በላይ የተሻለ ከልካይስ፤ ፈቃጅስ ከወዴት ይገኛል?

12.ለዚህ ነው እኛ ሰው ህሊና ይስጥህ ሲባል እንጂ ልቡና ይስጥህ ሲባል የማይረዳኝ። ህሊና ያለው ሰው ደግሞ ህሊናው የፈቀደውን እንዲናገር፤ ህሊናውን የደረሰበትን ግኝት እንዲመሰክር ልናበረታታው ይገባል እንጂ፤ ልናከላክለው አይገባም። ካልሆነም ደግሞ የጸሀፊውን ሰብእናውን ሳይሆን ሀሳቡን ልንመትረው፤ እይታውን ልንተቸው፤ አመለካከቱን ልንተረክከው እንችላለን። እንጂ የጸሀፊውን ሰብእና ለማጥቃትና ጸሀፊውን ትልቅ ሀጢያት እንደፈጸመ በማነጣጠር የምንናገረውም የምንጽፈውም እኛ የታገልንለትንና ለህዝባችን ልናወርሰው የምንምለውንና የኛን ህልም የሚያንጸባርቅ አይደለም።
የማይጠየቅ ተቋም፤ የማይተች እውቅና

13.ወዳጃችን ልጅ ተክሌ ከዚህ ቀደምም ብዙዎቻችን የምንሸሻቸውን ሀሳቦች ለመናገር የሚጀግን፤ ብዞዎቻችን የምናፍራቸውን ሀሳቦች ለመጻፍ የሚተጋ የስደት ወዳጃችን ነው። ባለፈው ጽሁፍ ያነሳውም ሀሳብ፤ ምንም የሚጣል የለበትም ብለን ባንመሰክርም፤ በራሱ የሚተማመንንና በአለት ላይ የተገነባ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚተጋን ቡድን የሚያስደነግጥ ነገር አላገኘንበትም። ያለበለዚያማ በሚጻፈውና በሚወራው ጠላታችን መደንገጡ፤ የሚናገሩና የሚጽፉትንም ወደእስር ማጋዙ ስህተት አይደለም ማለት ነው። እኛ መንግስትነትን አጥተን በተለዩ ሀሳቦች መንሸራሸር ይሄን ያህል ከበረገግን፤ የመንግስትነትን ስልጣን የያዘው አካል በተቺ ሀሳቦች መንሸራሸር ቢጨነቅና መንገደኛውን ሁሉ ቢያስር ምን ያስደንቃል?

14.በርግጥ፤ ወዳጃችን ልጅ ተክሌ በሰዎች ዘንድ ታምኖ የተነገረውን ምስጢር ያባከነ፤ ወይንም እሱ ለድርጅቶች ባለው ቀረቤታ ያገኘውን መረጃ የተጠቀመ ባሪያችን ቢሆን እኛም ይከፋን ነበር። አንለቀውምም። ለጥፋቱ እንቀጣው ነበር። ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ የተጠቀመው መረጃ ሁሉ አደባባይ በህዝብ ዘንድ በግልጽ ያለ እንጂ፤ የተተቸው ተቋም ጋር በሚሰራበት ግዜ ያገኘው መረጃ አይደለም። ደግሞስ የማይተች እውቅና፤ የማይጠየቅ ተቋም ለመመስረት ነው እንዴ የምንታገለው? እንግዲያውስ ያለፉትን አስር አመታት ብቻ ብንገመግም፤ ትልቁ የጎዳንና እንዳናንሰራራ ቀስፎ የያዘን ጥፋት የምንክባቸውን ለመተቸት፤ የምንቆልላቸውን ለመጠየቅ አለመድፈራችን፤ “ዝም በሉ፡ ጠላት እንዳይሰማ፡ በቃ ይሁንላቸው ይደረግላቸው” የሚለው የተለማማጭነትና የሰቀቀን ባህርይ ነው።
አደባባይ ወይስ ወደጓዳ?

15.በልጅ ተክሌ ላይ ከተሰነዘሩት ትችቶች መካከል፤ “ትችቱ ለምን በአደባባይ ሆነ? ውስጥ ለውስጥ አይሻልም ነበር ወይ” የሚሉት ጥያቄ-ተኮር ትችቶች መልካም እንደሆኑ ይሰማናል። የኛም ሀሳብ ይኸው ነው። ይሁን እንጂ፤ ያ አንድ መንገድ ነው። ብቸኛው መንገድ አይደለም። ልጅ ተክሌም የተከተለውን መንገድ ለመከተሉ ጥሩ ምክንያት ይኖረዋል። ልጅ ተክሌ እንዲህ ያለውን ትችት ይዞ ወደአምባ ሲወጣ፤ ግራ ቀኙን አላየም፤ በቅጡም አላሰላም ለማለት አንደፍርም። መጠየቅ ያለብንን በአደባባይ ባለመጠየቃችን፤ መናገር ያለብን በአደባባይ በግዜ ባለመናገራችን ምክንያት እነሆ ቅንጅት እንደብጉንጅ ውስጥ ውስጡን አብጦ፤ በመጨረሻ አይፈርጡ አፈራረጥ ፈረጠ። ከቅንጅት ቁስል እስካሁንም አላገገምንም። እንደልደቱ አያሌው ያሉ እስካሁንም ያልተካናቸውን ትንታግ ፖለቲከኞች አጣን። (በዚህ ሀሳብ ብቻ የምንበሳጭ እንኖራለን፤ ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ “ልደቱ ናፈቀኝ” የሚል ጽሁፍ እየጻፈ እንደሆነ ጠቁሞናልና ከዚህ ለሰላውም ትችት እንዘጋጅ)።

16.በመሰረቱ በአደባባይ የሚነሱና ውስጥ ለውስጥ የሚነገሩ ሀሳቦች ውጤታቸው አንድ አይደለም። በአደባባይ የሚነገር ነገር ትኩረት ይሰጠዋል። ሰዎች ይወያዩበታል። ተወቃሾችና ተከሳሾች ካሉም ለወደፊቱ ያርሙታል። ተጠያቂ አካልም ወደፊት እጋለጣለሁ ሲል አግባብ ካልሆነ ስራ ይታቀባል። ውስጥ ለውስጥ የሚደረጉ አስተያየቶችና እርማቶች ከስራ ላይ ይልቅ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት እንደሚዶሉ የልጅ ተክሌ ምስክርነት አያሻንም። እንጂ፤ የጋዜጠኞቹ ትጋትና ፍጋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በየአካባቢው የሚገኙ የኢሳት ደጋፊዎች አስተዳደራዊ ምሬትና ስሞታ ቢጻፍ፤ “ይሄ ድርጅት እስካሁንስ እንደምን ቆመ?” ያሰኛል። “ወደፊትስ ይቆማልን?” የሚለውም ጥያቄ የሰይጣን ጆሮ አይስማው በማለት ብቻ የሚጠፋ አይደለም። እንደ ኢሳት ያለ ህዝባዊና ተስፋ የተጣለበት ተቋም እንዲያድግ የአደባባይ ውይይት፤ የግንባር ትችት፤ የፊት ለፊት እርማት ያስፈልገዋል። የምንፈልገው ተቋም በአደይና በጸደይ (የሰዎች ስም ናቸው) ላይ የቆመ ሳይሆን በአለት ላይ የተተከለ መሆን ነው ያለበት። እስካሁንም ሰዎች መካብ እንጂ ድርጅቶች/ተቋማት መገንባት አልቻልንምና።
በአደባባይ የሚሰራ በአደባባይ ይጠየቃል

17.ደግሞስ ኢሳት በአደባባይ የሚሰራ የአደባባይ መገናኛ ብዙሀን እንጂ የህቡእ ጋዜጣ አይደለም። ሰለዚህ ኢሳት ለሚሰራው የአደባባይ ስራ በአደባባይ መጠየቅ አለበት። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት “የእንወያይ፡” ዝግጅታቸው ላይ ወዳጃችን ፋሲል የኔዓለምና አፈቀወርቅ አግደው ያንጸባረቁትን ሀሳብ በአደባባይ እንጂ በውስጥ ተቹ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም እነሱ ስህተት ቢሆንም ባይሆንም ሀሳባቸውን በአደባባይ የማንጸባረቅ እድል ሲያገኙ፤ የነሱን ሀሳብ የሚቃወመው ሰው ግን በውስጣዊ አስተያየት ብቻ መወሰኑ፤ የነፋሲልን ሀሳብ የሰሙት ሰዎች፤ የተለየውን ሀሳብ እንዳያዳምጡ እድል መንፈግ ነው። ይሄ ኢሳት የቆመለት ኢሳት የቆመበትም መሰረት አይደለም።

18.የሰማያዊ ፓርቲ በመጪው የአፍሪካ አንድነት/ህብረት 50ኛ አመት ምስረታ በዓል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። ከአገራችን ያላግባብ የተነቀልን ተቃዋሚዎች ነን የምንል ሰዎችም ድርጅቶችም፤ እንዲህ ያለውን ሰልፍ፤ ጠሪዎቹ ለምንም ዓላማ ይጥሩት “በርቱ ግፉበት፤ ብቻ እንዲህ ብታደርጉት መልካም ነው፤ ይሄንንም ብታክሉበት ሸጋ ነው” ማለት ነው ያለብን። እንጂ ዓላማቸውን ሙሉ በሙሉ ማራከስ፤ አግባብ አይደለም። ልጅ ፋሲል ግን የሰዎቹ የሰልፍ ጥሪ ሀቀኛ መሆኑን እንደሚጠራጠርና እንዲያውም ትኩረት ለማግኘት ያደረጉት አይነት ጥሪ እንደሆነ ነው የተናገረው። ያ ብቻም አይደለም፤ ይሄ አይነቱ ሰልፍ ቢደረግም እንኳን፤ ስርአቱን በምእራባዊያን ዘንድ ሰልፍና ተቃውሞ ፈቃጅ ሊያስመስለወም ይችላል የሚል ፍራቻ አንጸባርቋል። በርግጥ ልጅ ፋሲል ሀሳቡን የሰጠው በግሉ እንደሆነ ቢናገርም፤ እሱ የኢሳት ዋና ማኔጂንግ ኤዲተር እንደመሆኑ መጠን አንድን ነገር ተናግሮ በግሌ ነው የተናገርኩት በማለት ብቻ ሊያመልጥ፤ ኢሳትንም ነጻ ሊያደርገው አይችልም።

19.በሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ ይሄንን በግሌ ነው ያልኩት የድርጅቱ አቋም አይደለም የሚል ብልሀት ይጠቀማሉ። ልጅ ፋሲል በአስተያየቱ ላይ ከዚህ ቀደም ኢሳት የሰራቸውን ተመሳሳይ የሰልፍ ጥሪ ዘገባዎች እንደምሳሌ አቅርቧል። ከተቀመጠበት የሀላፊነት ወንበር አንጻርም የሚሰነዝረው እያንዳንዱ ሀሳብ የኢሳት ሊመስል፤ ሊሆንም እንደሚችል መረዳት አለበት። እንዲህ ያለውን በአደባባይ የተነገረ ሀሳብ መተቸት ያለብን፤ ኢሳት አንዳንዴ ፈንገጥ ያለ ሀሳብ አይመቸውም እንጂ ሲሆን ሲሆን በራሱ በኢሳት ላይ፤ ያለበለዚያ ግን በተገኘው መድረክ ነው። የለም እንቶኔን አትንኩ የሚለው አስተያየት፤ ለራሱ ለእንቶኔም አይበጅም።
ለነገሩ የኛ ችግር፡

20.ለነገሩ በስደት የምንገኝ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ግለሰቦች፤ በአገር ቤት የኛን ስደትና ሚና የሚቀንስ፤ የኛን መኖር ምክንያት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ የሚጀምር ሲመስለን፤ ያንን እንቅስቃሴ ለማጣጣልና ለማራከስ እንፈጥናለን። ይሄ እኛም በስደት ወደኬንያ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ላለፉት 12 አመታት በኢህአፓም በመኢሶንም፤ በቅርቡ ደግሞ በነግንቦት ሰባትም በነከበደም በነገመቹም ላይ ያስተዋልነው በሽታ ነው። ልክ የዛሬ አስራሁለት አመት ተሰደን ወደናይሮቢ ስንገባ የተቀበሉን ደግ ድርጅቶች ከነገሩንና እስካሁንም ከትውስታችን ካልወጣው ነጥብ አንዱና ዋንኛው “አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መኖር፤ በምእራባዊያን ዘንድ፤ አገር ቤት ዴሞክራሲ ያለ ያስመስላል” የሚል ነጥብ ነው። እነሆ ታሪክ ራሱን እንዳይደግምና፤ እኛ ከአመታት በፊት እንከሰሰስበት የነበርነውን፤ ማለትም የአገርቤቱ እንዲህ ነው የሚለውን ክስ፤ እኛም በተራችን እንዳንደግም መጠንቀቅ አለብን። ከፖለቲካ ወንጀሎች ሁሉ የከፋው ሌሎችን የከሰስንበትን ጥፋት ወይም በሌሎች በስህተት የተከሰስንበትን ጥፋት እኛ ስንፈጽም ነው።

21.ይቀጥላል።
እኛው ነን፤ ግንቦት ልደታ፤ 2005፤ ተረንቶ፤ ከናዳ

የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም

በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ

$
0
0

የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?

አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።

በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።

አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።

አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።

ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።

ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።

አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።

ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።

_ _ _ _ _ _
ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 76


ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ አባ መላ! ከሎሚ ተራተራ፦ ከሎሚ ተራተራ፦

$
0
0

እነደምን ከርማችሁ ወዳጆች ? እኔ አምላክ ይክበር ይመሰገን ደህና ነኝ። ሰሞኑን ከወደ ትውልድ አገር የመጡን አዛውንት እንኳን ደህና መጡ፤ የሰሜን አሚሪካ አየርሰ እንዴት ተቀበሎት ለማለት ወደ ጎረቤት ቤት፤ ጎራ ብዪ ነበርና፤ አረፍ እንዳልኩ አንድ ቀደም ብሎ ባለሁበት ከተማ ለጥቂት ወራት በርቀት ዝቅ ብለው እጅ በመንሳት የሃገሬን ተናፋቂ ባህል የሚያሰታውሱኝና እጀግም የማከብራቸውን አባት ድምጥ ሰማሁ።

እንድምነ ዋላችሁ አሉ አቶ በልሁ፤ ድምጣቸውን ያለወትሮዎቸው ለዘብ አድረገው፤ ;;’’’’’ እግዚአብሒር ይመሰገን”’ እንደምን ዋልክ በልሁ ግባ፣ ምነው ? ምን አዲሰ ነገር ሰማህ ደግሞ ድምጥህ ያለወትሮው ለዘብ ብሏል አሉ አቶ ታከለ፤ የዛሪን አያረገወና ልጆቻቸውን ለማየት ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጡ ወዲህ ቀረ እንጂ ድሮማ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው “ አልሞ ተኳሸ” እያለ ነበር አሉ።

አቶ በልሁና አቶ ታከለ ለረጅም ግዜ ወዳጆች ከመሆናቸውም ሌላ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ ዘወትር በቁጭት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ካላቸው ሃገራዊ ፍቀር በመነሳት መደረግ ሰለሚገባው የሃገር ጉዳይ ፤ በተለይም እንዴት አንድነታቸንን መገንባት እንደሚገባን አበክረው ከሚናገሩት የአካባቢያቸን የሰሜን አሜሪካ አዛውንቷች ዋናዎቹ ናቸው።

ወዲያዉ እግራቸው እንደገባ ወንበርም ላይ ሳይቀመጡ አዬ…; ተወኝ እባክህ…..ሲሉ የሰሙትን ለማጫወት ጀመሩ።, እኔም ኖር;……. በዪ እጅ ከነሳሁ በሗላ ጆሮዪን ሰጥቼ ማዳመጥ ቀጠልኩ፣…… ይገርምሃል ሰሞኑን በዚህ በ “ቡል” ቶክ…ነው.. ”ፓል”ቶክ,,….የሚባል…. የመወያያ መደረክ…..አዪ……ለነገሩ እኔ ይሔንን የመወያያ መድረክ ሳይሆን….”የወሬ ቋት” ነው የምለው። አሉና… ቀጠሉ.. አንድ “አባ…መላ….የሚባል….የ..ወያኔዎቹ አፈቀላጤ.. ሚሰጥር አጋለጠ።……የወያኔን..የግፍ ሰራ መደበቅ (መሸፈን) ደከመኝ..ብሎ ተቃውሞ ሲያሰማ ዋለ። ብዙም ሚሰጥር የማወቀው አለ ብሏል..’…. እያለልሕ …..አዳሜ ተሰበሰቦ ….”ውይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ እያለልህ” ከበሮ፤ ይደልቃል።

ሲሉ ከልቤ ሳቅኩና፤ ፈጠን በዪ ማጋለጡ፣ መልካም አይደለምወይ ብዪ ? ጠየቀኳቸው? ሲመልሱ….እሱማ..መልካም..ነው። አሰገራሚዉ ነገር እኮ አራት ቀን ሙሉ..እንደውም አምሰተኛው ቀን ይኸው መጣ ተሰበሰቦ ማዳነቅ ምን ይሰራል? የተገኝወን መረጃ ሰበሰቦ ተግባራዊ ሰራ ላይ ማተኮር ነው የሚበጀው።

ብለው ሲሉ. በዚሁ ቃላቸው ተሰማምቼ እቸኩል ሰለነበር የሚጣፍጠውን ጫዋታ ገና በእፍታው፤ ትቼ በሉ ደህና ይዋሉ ብዪ ተሰናብቼ ወጣሁና፤ እቤቴ እሰክደርሰ” ወይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ” አሉ አቶ በልሁ፤ እያልኩ እያሰላሰልኩ እቤቴ ደርሰኩና ይቺን ለመጫጫር በቃሁ እላችኸላሁ።

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው “ወይ መላ ነሸ አሉ፣ ወይ መላ አባ መላ” እያሉ ከበሮ መደልቅ; አባታችን አቶ በልሁ እንዳሉት አይጠቅመንምና መላው ዳይሰፖራውን ይታሰብበት እያለኩ፤ ከዚህ የሚከተለውን ይበጀናል ያልኩትን ብትጠቀምም ባትጠቅምም መፍትሄ ነው። ብዪ ሰለማምን ጀባ እላለሁ።

ዳይሰፖራው ማተኮር የሚገባው፦

1ኘ.በተገኝው ማንኛውም ይጠቅማል የተባሉትን ኢንፎረሜሸኖች በማሰባሰብና በማጠናከር ላልሰማውና ላልተረዳው፣ የህበረተሰብ ክፈል እነዲደርሰ ማደረግና ለውጤቱም ተግቶ መሰራት።

2ኛ፤ ማንኛወም አይነት የጥላቻና የ መጎነታተል ወይም የመናናቅ የ ትግል ሰልት መራቅና ወቅታዊና አንገብጋቢው በሆነው የሃገራችን ቸግርላይ በማተኮር ሳንሰልችና ሳንታክት እያንዳንዳችን የድርሻችንን በቅንነትና በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ማበርከት።

3ኛ.በወቅታዊው የሃገራቸን የፖሎቲካ፣ የ ኢኮኖሚም ሆነ የመሃበራዊ ችግሮቻችንን እና መፍትሄዎቻቸውንም ጭምር ባለሞያ ወንድሞቻችንንም ሆነ እህቷቻችንን በመጋበዝ ህብረተሰባችን ሰለወቀታዊው የሃገር ችግርና መፍትሄው ማወያየት።

4ኛ.የፖሎቲካ ድረጀቶችም የኔ የፖሎቲካ ፐሮገራም ነው ለወቀታዊው የሃገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄ የሚሆንው። ከሚል አሰተሳሰብ ወጥተን የጋራ የሆነወን የገጠመንን የሃገር ችግር በጋራ አፋጣኝ መፍትሄ ለማምጣት በመቻቻል፤ ተግቶ በጋራ በመሰራት አገር ወሰጥ ላሉት ለፖሎቲካ ድረጅቶች መልካም ኢትዮጲያዊ ሰሜትን በሁሉም መሰክ በመተግበር አጋርንትን በተገበር ማሳየት።

5ኛ.ከሁሉም በላይ ለምናልመውና ለማይቀረው የህዝብ የሃግር ባለቤትነት እያነዳንዱ ዜጋ ድርሻዪ ምንድነው ? በማለትና ለተግባራዊነቱም እውቀቱንም፤ ጉልበቱንም፤ ገንዘቡንም ህይወቱንም ሳይቅር ለመሰዋት የተዘጋጀ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ ነው።

ይህንን ካልተረዳና ለተግባራዊነቱም ካልተዘጋጀን በሰተቀር ቀደም ብዪ በመግቢያዪ ላይ እንደገለጥኩተ ትርፉ አቶ በልሁ እናዳሉት”………..

ሆይ…….መላ…….ነሸ…….አሉ……..ሆይ,,……..መላ………አባ…….መላ…

ነውና…… እነዲህ አይነቱን …ባዶ…ከበሮ…..ከመደለቅ…ያውጣን ! አሜን !!!

በተመሳሳይ መጣጥፍ እሰክንገናኛ ደህና ሁኑ በቸር ይግጠመን ! ችርም ያሰማን !

ከሎሚ ተራ ተራ. Wednesday, May-22-13

አሰተያየትዎን / ነቀፊታዎንም ቢሆን : mwl200825 @yahoo.com

የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያን የዜጎችን መፈናቀል አወገዙ፤

$
0
0

ብሄርን መሰረት ያደረጉ መፈናቀሎችንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረጉ ሰብአዊ ግፎችን ለመዋጋትም ቃል ገቡ

በቶሮንቶና አካባቢዋ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያ በተለያየ ስፍራ የሚደረገውን ብሄርን መሰረት ያደረገ መፈናቀልና ሀይማኖትን የዘመረኮዘ የሰብአዊ መብት ገፈፋ በጽኑእ አወገዙ።

ባለፈው እሁድ ሜይ 19 ቀን ብሉር መንገድ ላይ በሚገኘው በትሪኒቲ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ፤ በሁለቱ ዋና ዋና ሀይማኖት መሪዎች አስተባባሪነት በተደረገው ስብሰባ ላይ፤ ተሰብሳቢዎቹ በያዝነው ግንቦት ወር ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግና ጉዳዩን ለአለም መንግስታት ለማሳወቅም ወስነዋል።

በዚህ፤ ከአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በሕዝብ እንደራሴነትና በተለያዩ ሀላፊነት ኢትዮጵያን ሲያገለግሉ የቆዩት ሀጂ መሀመድ ሰይድ በምክትል ሊቀመንበርነት፤ እንዲሁም በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ቃል አቀባይ፤ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ፤ በሊ/መንበርነት የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮችን የያዘው ስብስብ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ የስብስቡ ምክትል ሊ/መ ሀጂ መሀመድ ከህመማቸው እንዲፈወሱ ጸሎት በማድረግ ተጀምሮ፤ ሶስት ሰዓታት ያህል በመምከር፤ በወቅቱ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳቦችን አሳልፏል።
የስብሰባው ሊቀመንበር ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር፤ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም የሚሉ ሰዎች ሰዎች መሆናቸውን እንደሚጠራጠሩ፤ ክርስትናም ከፖለቲካ ጋር ተቃርኖ እንደሌለው፤ እንዲያውም፤ ክርስቶስም ይሁን ነቢያትና ሀዋርያት ነጻነትን እንደሰበኩና፤ የዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ነጻነታቸውን ለማስከበር ከመታገል ወደሁዋላ ማለት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

ሊቀ ካህናት ጨምረውም፤ ቤተክርስቲያን የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ እንደማትታገል፤ እንዲሁም ማናቸውንም የፖለቲካ ቡድኖች ወይንም ፓርቲዎች ለይታ እንደማትደገፍ፤ ይሁን እንጂ ለነጻነት የሚደረግን ትግል የመምራት የሞራል ግዴታ እንዳለባት፤ ለነጻነት ትግል የሀይማኖት ተቋማትና ተከታዮቻቸው ቀዳሚ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ወደወቅታዊው አንገብጋቢ የአገር ጉዳይና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ሲናገሩም፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር የሚቀረፈው የስርአት ለውጥ ሲመጣ እንደሆነና ሁላችንም ለዚያ ዓላማ መሳካት በትጋት መስራት እንዳለብን አሳስበው፤ እስከዚያው ግን ይሄንን የመከራ ግዜ በድርጅትና በሀይማኖት በብሄርና በግል ጸብ ሳንለያይ በአንድነት መጋፈጥ አለብን ሲሉ መክረዋል።
ከረጅም ውይይት በሁዋላም ከክርስቲያኖችና ከሙስሊሞች፤ ከሴቶች እንዲሁም ከፖለቲካ ድርጅቶች የተወጣጡ 13 አባላት ያሉበት የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያንን የሚያስተባብር ግብረ ሀይል ተቋቁሟል።

ተሰብሳቢው ህዝብ፤ ይህ ግብረ ሀይል፤ በቀጣዩ አንድ ወር ውስጥ፤ ሶስት አበይት ስራዎችን እንዲያከናውን ሀላፊነት ሰጥቶታል። አንደኛ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ የሚካሄድ የተቃውሞ ስልፍ እንዲያዘጋጅ፤ ሁለተኛ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለካናዳ መንግስት የሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያሰናዳ፤ ሶስተኛም ለተጎዱት ወገኖች የገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረግበት መንግድ እንዲጠና ወስኗል።

ከአፋር እስከቤኒሻንጉል፤ ከጅጅጋ እስከ ጉራፈርዳ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን መፈናቀልና ሰቆቃ በጽኑ ያወገዘው ስብሰባ፤ በሜይ 25 በኢትዮጵያ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ጥቁር ልብስ በመልበስ አጋርነቱን ለማሳየትም መግባባት ላይ ደርሷል።

ከቶሮንቶ ካናዳ ለተጠናከረው ዘገባ፤ ሀብታሙ ስለሺ

ሥር ነቀል ወይሰ ሰር በቀል ለውጥ ? ከሎሚ ተራ ተራ…….

$
0
0

“ለመብቀል ለመብቀል፤ ሰንዴውም ይበቅላል።
ለመብቀል ለመብቀል ቦቆሎም ይበቅላል።
ለመብቀል ለመብቀል አረሙም ይበቅላል።
ቦቆሎው ከአረሙ ሰንዴም፤ ከእንክረዳዱ በተግባር ይለያል።”

ክቡራን አንባቢያን ሆይ ለመሆኑ ወያኔ አገር በቀል፤ አጥፊና ላለፉት 22 ዓመታት ሕዝብን የገደለ፤ ያፈነ ያሰደደ፤ ያሰረና ያፈናቀለ፤ አሁንም ድረሰ በመግደልና በማፈን እንዲሁም በዝርፊያላይ የተስማራ ክፉ፤አገር በቀል ሰረአት ለመሆኑ ምሥክር መቁጠር ያሰፈልጋል ትላላችሁ?
“ወችው ጉድ፤ አሉ ብላታ;፤…………..፤ መቼም ጆሮ አልሰማ አይልምና: በተቃዋሚው ጎራ ዘወትር አሰደንጋጭና አሰገራሚ ውይይቶችን መሰማት የቀን ከቀን ክሰተት ቢሆንም ቅሉ፤ እኔን በእጅጉ ያሰገረመኝ ግን የወያኔን ሰርአት በሰመ “ሪፎርሜሸን (reformation) “ጠግነን ጠጋግነን መልሰን እናሰቀምጥ የሚለው ተቃዋሚነኝ ተብዬው ጎራ ነው። መጠርጠር አሁን ነው አለ ,፣ያገሬሰው”
“ ጠርጥር፣ ጠርጥር ፤ ገንፎ ለሥልሦ ቢገባም
አያጣም ሥንጥር” አትሉኝም፤-“

ከዛ በፊት ግን ሪፎርሜሽን (Reformation) (ማሻሻያ) ማለት ምን ማለት ነው?። መልሱን እናንተው መልሱ። እኔ ግን ይህቺን አንድ ምሳሌ ጣል ላድርግና ወደሌላኛው ልለፍ።

አሁን በአዐምሮችሁ አንድ ቆንጆ ቤት ሳሉ፤ ይኸ ቤት መሰረቱ በባለሞያ መሀንዲሰ በደንብ የተገነባ ነው። ይኸ ማለት ቤቱ በምን ያህል ካሬሜትር ቦታ ላይ እንደሚሰራ፤ ምን የህል ሲሚንቶ ምን ያህል አሸዋና ሌሎችም ሌሎችም፤ ብቻ አንድ ቤትን ጥሩ ቤት ነው ሊያሰኙ የሚችሉትን ያሟላ ነው።

ከጥቂት አመታት በኸላ ግን ባለቤቱ መሰኮቱ ጥሩ ጸሃይ አላሰገባ አለ በሩም በደንብ አልከፈት አለ፤ በሚል ሁኔታ ሁለቱንም መቀየር ፈለገና በዙ መድከም ሣያሰፈልገው ባለሞያ አናጢ አማክሮ አሮጌውን (ጸሃይ) አላሰገባ ያለውን መሰኮትና በደንብ አልከፈት ያለውን በረ አሰቀየረውና ጽሃዩም በደንብ ይገባ ጀመር በሩም ወለል ብሎ ይከፈት ጀመር እላችሁ አለሁ።

የፖሎቲካ ማህደሩ በሰነሰርአቱ ከተዘረጋ ከላይ እንደተመለከታችሁት ቤት አልመችና አልሰራ ያለውን ያለ ብዙ ችግርና ውጣ ውረድ ማሻሻልና መቀየር ይቻላል። ቸግሩ ግን

ግን ቀድሞውኑ ባልተመሰረተ ነገር ሰለማሻ ሻያ፤ (ሪፎረሜሸን) ( Reformation) ትንታኔ ለመሰጠት መንደርደሩ አይመሰላችሁም ?

ከዛ በፊት ግን አሁንም እሰቲ በቅድሚያ መኖር ሰለሚገባው ነገር እንጠይቅ ? ፖሎቲካል ኢኒሰቲቲዩሽን (political Institution) ማለት ምን ማለት ነው? ብለን እንጠይቅና መልሰ እናግኛ፤ አለ እንዴ ግን ? መች አጣችሁት፤

ፖሎቲካል ኢኒሰቲቲዩሸን ማለት፤-(political Institution) :- በህግ የበላይነት የሚያምን ፤ ሁሉን ያማከለ ህግን መተዳደሪያው ያደረገና መንግሰታዊ መሰተዳድሮችን፤ የመሀበራዊ መሰተዳድርን ለህብረተሰቡ በመፍጠር ምሳሌ በመሆን ሌሎች የፖሎቲካ ድርጅቶች ያለምንም ጫና እንዲመሰረቱ የሚያመቻች፤ የንግድ ተቋማት በአግባቡ እንዲመሰረቱና ያለችግር መንቀሳቀሰ እንዲችሉ የሚፈጥርና የሚያመቻች፤ ሁሉም እኩል የሚዳኝበት ፍርድቤት ያለውና የሰልጣን ሳይሆን የህግ የበላይነትን በማራመድ በዚሁ አላማ የመምረጥና የመመረጥን መብት ያከበረና የሚያሰከብር ተጠያቂነትም እንዳለ አምኖ የሚመሰረት የፖሎቲካ ድርጀት ማለት ነው።

ከላይ በዝርዝር ለመመልከት የሞከርናቸው ግን እንኳን መመሰረትና በሀሳብ ደረጃም እንደሌሉ ግን አፋኙ ወያኔ (TPLF) ላለፉት 22 አመታት ለሕዝብም ሆነ ላለማቅፉ ሕብረተሰብ አረጋግጠውልናል። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው የእደሳ ወይም ማሻሻያ (Reformation) የሚታሰበው? የሌለና ያልተመሰረተ ነገርሰ እንዴት ይታደሳል? መልሱን እናንተው መልሱ።

ለመሆኑ በአንድ አገር የሰረአት ማሻሻያ ለውጥ ለማምጣት አሰፈላጊ ናቸው፤ ለውጦቹንም ውጤታማ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፤ ከሚበሉት ዋና ዋናዎቹ ምንድናቸው ትላላችሁ? የኔን በከፊል እንደሚከተለው ጠቆም ጠቆም ላድርግና የናንተን ደግሞ እናንተ ጨምሩበት፡፡
ሪፎርሜሽን ሲታሰብ ፤ለተግባራዊነቱ፤ በቅድሚያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በሃገሩውሰጥ መኖራቸውን ማረጋገጥ በጣም አሰፈላጊ ነው።

1ኛ) በሃገሩ ውሰጥ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት መኖሩንና የዲሞክራሲ ሰርአት ቢያንስ ቢያንሰ ጭላንጭሉ እንኳን ያልጠፋ ለመሆኑ ማረጋገጥ ሲቻል።
2ኛ) መንግሰት ነኝ ተብዩው የህግ የበላይነትን የተረዳና አክባሪነቱም ባለማቀፉ ታዛቢዎች ዘንድ የተረጋገጠ መሆን ሲቻል።
3ኛ) በማንም እና በምንም አይነት ሁኔታ ጫና የማይደረግበት ለሕዝብ ግልጥ የሆነ ሚዲያ መኖሩን ማረጋገጥ ሲቻል።
4ኛ) ከፖሎቲካ ነጻ የሆኑ መሃበራት (Institution) ለምሳሌ የትምህርት፤ የመምህራን ማህበር፤ ባንክ ፤እነዲሁም ሌሎች መሃበራዊ ተቆማት ያለምንም ተጽዕኖ መንቀሳቀሰ መቻላቸውን ማረጋገጥ።
5ኛ ከሁሉም በላይ የሰበአዊ መብት እረገጣ አለመኖሩ ባለማቀፉ የሰባዊ መብት ተቆርቆሪ ድርጅቶች ማረጋገጥ ሲቻል።

እነግዲህ ባለማቀፍ መሰፈርት ከላይ የተዘረዘሩት አንዱም እንኳን በማይታዩበት እንዴት አይነት ጥገና ለማደረግ እነደሚታሰብ አላውቅምና፤ ሰንወያይ ይህንን ሁሉ ግምት ውሰጥ እያሰገባን ቢሆን መልካም ነው እላለሁ።
ሥለዚህ የሚያሰፈልገን ያለጥርጥር ሥርነቀል ለውጥ ነው። የተነቃነቀም ጥርሰ ሣይነቀል አይድንም፤ ነውና ተባብረን እንንቀለው እያልኩ መጣጥፌን ለጊዜው እዚህ ላይ ላብቃና፣ ውሃ ፉት ልበል።

በቸር ይግጠመን፤ አሰተያየትዎን/ ነቀፌታዎንም

ሎሚ ተራ ተራ ፡= Mwl200825@yahoo.com Friday, May-24-13

ግንቦት ሃያ ሲመጣ…በዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)

$
0
0

ግንቦት 20 በየአመቱ ሲመጣ፤ በብዙዎች ህሊና ውስጥ የተለያዩ ስሜቶች ይመላለሳሉ – ለሚያስደስተው ደስታ፤ ለሚያዝነውም ሃዘን። ሁሉም በየራሱ መንገድ ግንቦት ሃያን ሊያስታውሰው ይችላል። ግንቦት ሃያን በተለየ መንገድ ከሚያስቡት አንዱ የሆነው፤ የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ ማሽን ኢቲቪ ይህንን ቀን የሚገርም ውሸት እና ቅጥፈት በማስተላለፍ ያሳልፈዋል።

ግንቦት 20 ሲመጣ የኢቲቪ ትግርኛ ፕሮግራም የሚያስተላልፋቸውን ዘፈኖች ልብ በሉ። ከሰላሳ አመት በፊት የተዘፈነው፤ “እምበር ተጋዳላይ” ዛሬም የጭፈራ ማድመቂያቸው ነው። በዚህ ዘፈን የኢትዮጵያ ሰራዊትን የሚሳደቡና የሚያንቋሽሹ ግጥሞች ሲያሰሙን ውለው ያድራሉ። ዋናው ኢቲቪም የነሱን ፈለግ በመከተል፤ የህወሃት ዝፈኖችን ሲያሰማን ይሰነብታል። በትግሉ ውስጥ የተሳተፉት የትግራይ ታጋዮች ብቻ እንደሆኑ ተደርጎ፤ የኢህዴን/ብአዴን ትግል ተፍቆ… በቴሌቪዥኑ ስክሪን ላይ የህወሃት ታጋዮች አዳፍኔ ይዘው ተራራ ሲወጡና ሲወርዱ ይታያሉ። ይህንን የተመለከተ የአሁን ትውልድ ወጣት በ’ርግጥም ትግሉም ድሉም ህወሃት ያመጣው ገጸ በረከት አድርጎ፤ እነመለስ ዜናዊን ቢያመልክባቸው ሊገርመን አይገባም።

ከምንም በላይ የሚያሳዝንና የሚያሳፍረው ድርጊት ግን ከዚህ የተለየ ነው። በኢቲቪ ውስጥ እርጥባን የሚጣልላቸው የህወሃት እና የኢህአዴግ ግልገል ካድሬዎች፤ ምላስ አንደበታቸውን ሳያነቅፋቸው… የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትን… የ“ጠላት ጦር” እያሉ ሲጠሯቸው መስማት እጅግ ያሳዝናል። “የአሞራውንም ሆነ የቀሽ ገብሩን ዶክመንተሪ” የተመለከተ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለዚህ ምስክር ነው። በትረካቸው መሃል “የጠላት ወታደር፣ የጠላት ሰራዊት” እያሉ መጥራትን ተክነውበታል። በሚገርም ሁኔታ የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ወይም ሳሞራ የኑስ “የጠላት ወታደር” ከማለት ይልቅ… ቢያንስ አፋቸውን አርመው “የደርግ ወታደር” ሲሉ፤ የኢቲቪ ካድሬዎች ግን የጠላት ጦር እያሉ ጆሯችንን ብቻ ሳይሆን ህሊናችንን ያሳምሙታል።

የዚያ ትውልድ ሰዎች ብንሆንም/ባንሆንም፤ በውትድርና መስመር ውስጥ ብንሳተፍም/ባንሳተፍም “ጠላት” የሚለውን ቃል በትግርኛ ቲቪም ይሁን በአማርኛ መስማት ለህሊና የሚቀፍ ነው። ከዚያ በላይ ግን አባባሉ አንድ ሌላ እውነት ያስጨብጠናል። ይህ አባባሉ ህወሃት ኢትዮጵያዊ የሆነና ለኢትዮጵያ ብሎ የቆመን አካል “ጠላት” ብሎ የመፈረጅ ባህል እንዳለው፤ ጥርት አድርጎ ያሳያል። “ህወሃቶች ጨካኝ እና አረመኔ” ብለው የሚጠሯቸ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም እንኳን፤ “ወንበዴዎች” ከማለት ያለፈ ሌላ ቃል በወያኔዎች ላይ ሲሰነዝሩ ሰምተን አናውቅም። ታዲያ እራሳቸውን ንጹህ እና ቅዱስ የሚያደርጉት የኢቲቪ ካድሬዎች፤ “ከመምህሩ ደቀ-መዝሙሩ” እንደሚባለው ከህወሃት በላይ ህወሃት ሆነው፤ በኢትዮጵያዊነት ጎራ የተሰለፈን አካል በጠላትነት ፈርጀው፤ “ጠላት” ብለው ሲጠሯቸው… ትክክል እንዳልሆኑ፤ ቢያንስ ግንቦት ሃያ ሲመጣ ልንነግራቸው ይገባል።

በክምር ስንዴ ውስጥ ጥቂት እንክርዳድ እንደማይጠፋው ሁሉ በቀድሞ ሰራዊት ውስጥ፤ ቀዩን መስመር አልፈው ግፍ እና በደልን የፈጸሙ ሰዎች ሊኖሩ ይቻላሉ። ከዚያ በተረፈ ግን የኢትዮጵያ ሰራዊት ማለት… በየብስ ተጉዞ፣ በባህር ተንሳፎ፣ በአየር አንዣብቦ፤ ድንበር አልፈው የመጡ ተስፋፊዎችን፤ አገር ገንጣይና አስገንጣዮችን አከርካሪ ሲሰብር የነበረ፤ ክብር እና ምስጋና ሊሰጠው የሚገባ ጀግኖች የነበሩበት፤ ጀግኖችን ያፈራ የኢትዮጵያ ጋሻ እና መከታ የነበረ ነው። ይህ ሰራዊት የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የግል ወይም የደርግ የወል ሰራዊት አልነበረም። የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች የተሰዉበትና የተሰዉለት መከላከያ ሰራዊት ለመሆኑ፤ ከጥቂት የህወሃቶች በቀር አብላጫው ህዝብ ይስማማበታል። ይህንን በአንደበታችን ብንክደው እንኳን፤ ታሪክ እና ትውልድ የማይፍቀው ሃቅ ነው።

ግንቦት ሃያ በመጣ ቁጥር፤ የቀድሞ ሰራዊትን በመሳደብ እና “ጠላት” በማለት የበአል ማዳመቂያ ማድረግን አንድ ቦታ ማቆም ያስፈልጋል። ዛሬ የምንመጻደቅበት መከላከያ ሰራዊት ልናይ የቻለው ከዚያ ቀድሞ በነበረው ወታደራዊ ስነ-ስርአት ላይ በመገንባቱ ነው። ከወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ጀምሮ የጦር ካምፕ እና መሳሪያዎቻችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የቀድሞ ሰራዊት ውርስ እና ቅርሶች ናቸው። አጼ ምኒልክ አድዋ ላይ የተዋጉበት፤ እነባልቻ አባ ነፍሶ የተኮሱት መድፎች እንደቅርስ ተቀምጠው በታሪክ እንደሚጎበኙት ሁሉ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ከምስራቅ እስከ ሰሜን ጫፍ ለመሰለው የአገር አንድነት የተዋጋባቸው ጠመንጃ እና ጀበርና ጭምር ለታሪክ መቀመጥ አለባቸው እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ቅርስን “ጠላት” የሚል ቅጽል ሰጥተን፤ ቅጥፈትን ለትውልድ ማውረስ የለብንም።

አሜሪካኖች በየአመቱ ለአገራቸው ለተሰዉ ወታደሮች ከፍተኛ ክብር ለመስጠት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ Memorial Day በማለት፤ በርስ በርስ ጦርነት ወቅት በሁለቱም ወገን የወደቁትን ወገኖቻቸውን ያስባሉ እንጂ፤ አንዱ ሌላውን እያረከሰ እና እያኮሰሰ ወገኑን “ጠላት” የሚልበትን አጋጣሚ አይተንም ሰምተን አናውቅም። ስለሆነም ግንቦት ሃያ ሲመጣ… ከሰለጠኑት ህዝቦች ቢያንስ አንድ ነገር እንማር።

ስስታምም አንሁን። ትግሉን እና ድሉን የህወሃት ብቻ የምናደርገውን የታሪክ ስስት አንድ ቦታ እናብቃው። ለኢትዮጵያዊነት የተሰዉትንም ሆነ፤ አሁን የቆሙትን “ጠላት” ብሎ ማለት ይብቃ። ተራራውን በመትረየስ ሲያሸብሩ ኖረው፤ እነሱን በብዕር እና በቃል እያንቀጠቀጡ ሲአያሸብሯቸው፤ ወገንን በ“ጠላት”ነት ፈርጀው “አሸባሪ” ብለው ማሰርን ያቁሙልን። እናም ግንቦት ሃያን በመሰላቸው መንገድ ሲያከብሩት… የህዝብንም ቅርስ እና ሃብት ያክብሩ። በአንድ በኩል የቀድሞውን ሻለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የአገሪቱን ፕሬዘዳንት አድርጎ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞውን ጦር ጠላት ብሎ መጥራት ተጻራሪ እና አሳፋሪ ተግባር በመሆኑ፤ ቢያንስ የፕሮፓጋንዳ ምህዋር፤ በአዲስ ዜማ ሊቀየር ይገባዋል – የግንቦት ሃያ መልዕክታችን ነው!!w

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ? ዛሬ ካልወጡሰ መቼ?በሎሚ ተራ

$
0
0

ዝነኛውና የማይጠገበው ድምጻዊ (ዶ/ር) ጥላሁን ገሠሠ፤ ሲያንጎራጉር፤ እንዲህ ብሎ ነበር፤
“ጩኸቴን ብትሰሙኝ ፤ ይኸው አቤት አቤት እላለሁ በደል ደርሦብኝ እጮሃለሁ ብያለሁ”

እያለ ያንጎራጎረውን እኔም አቤት አቤት የ ( የመሪ ያለህ!!! ) በዪ እኔም እጮሀለሁ። ምንም እንኳን ሰለኮነሬል ጎሹም ሆነ ሰለ ዶክተር ታዬ ታላቅ ሰራና አገር ወዳድነታቸው አገር የሚያወቀው ያደባባይ ሚሰጥር ቢሆንም ቅሉ፤ ሰሞኑን ግን የተለያዩ የሀገርኛ ጉዳይን የሚያሳዩ ቪዲዩዎችን ሰመለከት ድንገት የኮነሬል ጎሹን ብዙዎችን ያሰደነቀና ያኮራ ሃገር አቀፍ የጥብቅና ንግግር (On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) አየሁና በቁጭት ምን ተብሎ፤ ማን አሰከፍቶት ይሆን ኮነሬሉ ጥግ የያዙት ? ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትሰ ? የት ገቡ ? በማለት በቁጭት ለመጠየቅ ብዕሬን አነሳሁ።
መቼም እንዲህ ያለውን አንገብጋቢ ሃገራዊ ጥያቄ የሚጠይቁ በርካታዎች እንደሚሆኑ ባምንም ጥቂቶች ደግሞ የ ምርጫ 97 ቱን ምሳሌ በማድረግ የሞተ ዘመድ የለውም ወይ? ይኸ ሰው ምን ነካው የሚሉ እንደማይጠፉም አምናለሁ። መልሴ ግን የሞቱ ዘመዶች በርካቷች አሉኛ፤ ተሰፋዪ ግን አይሞትም።ተሰፋ ላንድም ሰከንድ አጥቼ አላውቅም ነው ።

እንዲህ አይነቱ ጥያቄ አገራችን የምትገኝበትን የፖሎቲካ ሂደትና ቀውሰ በሰፊው እንድንጠይቅና ከሰኸተታችንም ታርመን ይቅርም ተባብለን፤ በሃገር ጉዳይ እኔ ማን ነኝ ? ምንሰ ማድረግ ይጠበቅብኛል ? የሚለውን ጥያቄ በቅንነት በመጠየቅ አንተ ትብሰ፤ አንቺ ትብሸ በመባባል እንደገና እጅ ለእጅ ተያይዝን አገራችን እንድትገባበት ከተቆፈረላት ጥልቁ ጉድጓድ የማውጣት አገራዊ ግዴታ አለብን በዬ አምናለሁ።

ከገጠመን እና ከተጋረጠብን የፖሎቲካ ውጥንቅጥ አኳያሰ እባክህ፤ እባክሽ ያሰፈልጋል ወይ ? ብቃት ያላቸው የፖሎቲካ መሪዎችሰ እባካችሁ እሰኪባሉ መጠበቅ አለባችው ወይ ? በሚል የተለያዩ እሣት የሚተፉ እንጉርጉሮዎች ከየጎራው ሊነሱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ከተጋረጠብን ከፍተኛ አደጋ ባሻገር ምንሰ ብናደርግ አገር ትዳን እንጂ ነው መልሴ።
ሥለዚህ ሰለጠንካራ የፖሎቲካ አመራር ብቃታቸውና፤ ሰራቸው በርካታ አገር ወዳዶች የሚመሰክሩላቸውን ጠንካራ መሪዎች ዳግም ወደ ፈጠጠው የትግል ጎዳና እንዲመጡ የማይደረግበት ምክነያት ምንም ሊኖር አይችልም። እነ ኮነሬል ጎሹንም እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትንም ሌሎችም አሉ የሚባሉትን ከየ አካባቢያችን ውጡ፤ አገራችን ኢትዮጲያ ትጮሃለች፣ የመሪ የለኸ እያለችም ትጣራለች ብለን የማውጣት ሃገራዊ ግዴታ አለበን። እከሌ ከከሌ ሳንል ጩኸታችንን እናሰማና አገራችንን ተባብረን ከውድቀት እናድን።

“ይሄ – መሪ ትግሉ ይወልዳል የሚለውም ባዶ ጩኸታችን ለ 22 አመት ወልዶ አላሳየንም እና ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ፡
የሚዲያ ክፍሎችም በሙሉ፤- እነ ቪ. ኦ. ኤም፣ ዶቼ ቬሌም ፤ እሣትም፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ካሜራችሁን ወደ አራቱም ማዕዘናት አዟዙሩት ፤ምክነያታቸውንም አሰሙን እያልኩ ጩኸቴን ብትሰሙኛ እላለሁ። በቸር ይግጠመን!!

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live