Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ትንሣኤ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡ የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ትነሳለች!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሩህ አንቁ

ከለምለሞቹ ተራሮች መሃል

የጨለመባቸውን በነጻነት ጎዳና ስታጓጉዝ

የአባይ ወንዝ አናት

ኢትዮጵያ ትነሳለች!

ኢትዮጵያ የብልሆች ምድር

ኢትዮጵያ፤ የቀደምት አፍሪካ ሕግጋት ማሕደር

ለምለም የእውቀት ገበታ

የእኛ አፍሪካ የባህሏችን አለኝታ

ብልኋ ኢትዮጵያ ትነሳለች፤ ገና

ደምቃ በሙሉ ክብር

አቤት የአፍሪካ ተስፋ

መዳረሻዋ እድል

በ2011 በአፍሪካ ሕብረት ግቢውስጥ የግ ቀ.ኃ.ሥ. ሃውልት እንዲቆም ሃሳቡ ሲቀርብ፤የኢትዮጵያ ‹‹ታላቁና ባለራዕዩ መሪ›› በመቃወምና ኢትዮጵያዊነቱን በመርሳትና በመካድ ሲናገር ምንጊዜም ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ስናነሳ የሚታወሰን ክዋሚ ንኩሩማ ነው፡፡ ይህን ለመቀበል መቸገር አሳፋሪ ነው የሚሆነው›› በማለት የራሱን አሳፋሪ ክህደት ፈጸመ፡፡የከሰለ ልብ ባለቤት መሆን እንዴት ያሳፍራል! ሃፍረተ ቢስነት እንዴት ያሳፍራል! ቀደምት የአፍሪካ እንድነትን ምስረታና ተግባራዊነት ያረጋገጠን መሃንዲስ እውነታ መካድስ እንዴት ያለ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡የማይቻለውንና የማይሞከረውን የሁለት ጎራ ፍጥጫ፤ የ “ሞኖሮቪያ”ንና የ “ካዛ ብላንካን” ቡድናዊ መራራቅን አቀራርቦና አስማምቶ፤ አስታርቆና አዋህዶ የአፍሪካ አንድነትን ምስረታ እውን ስለመደረጉ ታሪክ የግርማዊ ቀ ኃ ሥን ውታ ጨርሶ የማይዘነጋው ነው፡፡ የአፍሪካ እንድነትን እውን ለማድረግ ያለመሰልቸት በትጋት ጥረዋል፡፡የአፍሪካ አንድነትን ለመመስረትም ስለ ፓን አፍሪካኖዝምም ለአፍሪካ ምሉእ ነጻነትም ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉና አሁን ለደረሰበትም ደረጃ ተጠቃሽና ባለውለታነታቸው የማይዘነጋ ነው፡፡

….የወደፊቷን የአፍሪካን ራዕይ ከነጻነት አኳያ ብቻ ሳይሆን በአንድነታችንም አኳያ ነው የምናየው፡፡ይህን አዲስ ትግል በማወቅ ካለፈው ባገኘነው ውጤት መበረታታትና ጥንካሬ ተስፋ እናደርጋለን፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ አፍሪካውያን የተለያየ ባህል ባለሃብቶች ነን፤ልዩ ተሰጥኦና ልምዶች ያሉን ነን፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች በበርካታ የሚያለያያቸው ሁኔታ ቢኖረንም በመግባባትና በመተሳሰብ አንድነት ማምጣትም እንደምንችል እንገነዘባለን፡፡… ታሪክ እንደሚያስተምረንና እንደሚያስታውሰን አንድነት ሃይል መሆኑን፤በመገንዘብ ግባችንን በማስቀደም፤ለጣምራ ግባችን የተባበረ ሃይላችንን ለዚሁ በማዋል ለዕውነተኛው የአፍሪካ ወንድማማችነት አንድነት ልንቆም ግድ ነው፡፡ …እንደ ነጻ ሰብአዊ ፍጡራን ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መቆም ይገባናል፡፡በራሳችን መተማመንን፤ግባችን በማድረግ እኩልነትን ከሌሎች በእኩልነት ላይ መሰረት ካደረጉ ጋር ሁሉ አንድ ልንሆን ተገቢ ነው………

በግንባር ቀደም የአፍሪካ አንድነት አመሰራረት ላይ የምስረታውን አባቶች በምቃኝበት ወቅት፤ ለግላቸው የመዳብ ሃውልት ይቁምላቸው በሚል ሙግት ለመግጠም አይደለም፡፡እኔን አጅግ ያሳዘነኝ፤እራሳቸውን በከለላ ውስጥ እሰገብተው፤ እራሳቸውን መሆን ስለሚቸግራቸው፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ታሪክን በማወላገድና መሰረቱን በማሳት፤ጭፍን ‹‹ራዕይ›› አለን የሚሉት በአፍሪካ መስራች አባቶች ስምና ተግባር ተከልለው፤(ይልቁንስ በራሳቸው ስምና ማንነት መቆም ባለመቻላቸው) የኢትዮጵያን የኖረና የዘመናት መታወቂያ ለማፈራረስ የቆመውንና የቆሙለትን ትልማቸውን ለማሳካት መጣራቸው ነው፡፡ ታሪክ ስለሥልጣንና ማንነት ቢሆን ኖሮ ቀ ኃ ሥን ማንም ቀድሞ አይገኝም፡፡ ቀ ኃ ሥ ከማንም የአፍሪካ መሪ የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በዘመኑ የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱት አቻ መሪዎች ‹‹የአፍሪካ አንድነት አባት›› ተብለው በ1972 ዓም በተካሄደው 9ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ በይፋ ተመርጠዋል፡፡ ቀደም ሲል በምስረታው ወቅት በ1963 ዓም የመጀመርያው የአፍሪካ አንድነት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዳግመኛም በ1966 ድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመሩ ዳግም ተመርጠው በሁለት ዘመናት በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል ፡፡ የአፍሪካን ኮሎኒያሊዝም ቅስም ለመስበርና ከአፍሪካ ምድር ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ከኋላ የመጣ አይን አወጣ እንዲሉ የማንም ጭራ ነስናሽ ጥብቅና የሚሹ አይደሉም ይሄው ጭራ ነስናሽ የራሱን ሃውልት ለማቆም የነግ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገችው ይቺ በንኩሩማህ ስም የተቸረች ሙስናዊ አካሄድ የትም አታደርስም፡፡

ታሪክ በርካታ እንቆቅልሾች አሉት፡፡ምናልባት በሃውልቱ መቆም ወቅት ንከሩማህ ወይ ሞት በማለት አጥበቀው ሲሞግቱ የነበሩ ስለፓን አፍሪካኒዝም በተነሳ ቁጥር መታወሱን ብቻ ያቀነቀኑት ንክሩማህ ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ስር የሰደደ ፍቅርና አክብሮት ቢያውቁ ኖሮ በመቃብራቸው ውስጥ መንደፋደፋቸው አይቀርም፡፡ንክሩማህ በልቡ ውስጥ ለኢትዮጵያ የተለያ ጓዳ ነበረው፡፡ምንም እንኳን ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ቀደምት ቢሆንም ኢትዮጵያን ደግሞ እንደ አፍሪካ አንጸባራቂ የጸረ ኮሎኒያሊዝም ብርሃን በመመሰል ከቅኝ ገዢዎች ጋር ሲያደርጉ በነበረው ትግል ወቅት የዚህች የነጻ ኢትዮጵያ ኮከብነት መሪያቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ከዚሁ አኳያ የኢትዮጵያን የጸረ ኮሎኒያሊዝምን ጥቃት በመታገል ነጻነቷን ጠብቃ መቆየቷ የሚያኮራ መሆኑን በማስገንዘብ፤የአፍሪካ አንድነት አሽከርካሪ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡

እርግጥ ንክሩማህ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ንቁ ተሟጋች መሆናቸው ባይካድም፤ ለፓን አፍሪካኒዝም ግን አንድም ግጥም አላበረከተም፡፡ አፍሪካ ስለአፍሪካ ብሩህ እሳቤ ያለው ቢሆንም ለአፍሪካ ግጥም አላሰፈረም፡፡ ንክሩማህ ፓን አፍሪካኒዝምንና አፍሪካ ይወድ ነበር፤ለኢትዮጵያ ግን የበረታ ፍቅር ነበረው፡፡ለዚህም ነው በምስረታው ወቅት በመዝጊያው ላይ ባደረገው ንግግሩ ላይ ስለኢትዮጵያ ግጥም ጀባ አለ፡፡ ከዓለም መሪዎች መሃል ለኢትዮጵያ ታሪካዊነትና ግንባር ቀደምትነት፤ ስለ ሕዝቦቿ መስተንግዶ የጻፈ ብቸኛ መሪ ንክሩማ ነው፡፡

ቀ ኃ ሥ ወቅቱ ሲመጣ ሃውልታቸው እንደሚገነባ አያጠራርም ምክንያቱም ‹‹እውነት በርብራብ ስር ወድቃ አትቀርም፤ ቅጥፈትም በዙፋን ላይ ተኮፍሶ አይኖርምና››::

ወደኋላ መለስ ብለን ስናስታውስ፤ ንክሩማህ የበረታ ፓን አፍሪካኒስት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ‹‹ትንቢተኛም›› ነበር፡፡ ንክሩማህ ማየት የተሳናቸው ባለራዕዮች ኢትዮጵያን ወደ ዘር ፖለቲካ አረንቋ ውስጥ ከመድፈቃቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ ገና እንደምትልቅ ያወቀ ነበር፡፡ንክሩማሕ የኢትዮጵያን ገኖ መዝለቅ ሃፍረት ለባሾች ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ …. ከማለታቸው በፊትና ከመቀላመዳቸው አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ንክሩማህ ባለጊዜ አስመሳዮች ለራሳቸው ስም ለመገንባት ጉብ ቂጥ ከማለታቸውና ‹‹ኒዮሊቤራሊዝም›› ከመዝፈናቸውና ደሟን ጨርሰው እንባዋን ከመምጠታቸው አስቀድሞ ስለማንኛውም በዝባዢና አስመሳይ ለቀስተኛ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡

በእርግጥም የንክሩማህ ግጥም ‹‹ትንቢት›› ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ትነሳለች እንደ ንጋት ጸሃይ በርታ እንደ ውድቅት ጨረቃ ደምቃ ኢትዮጵያ ትነሳለች! ከምር ገና በላይዋ ላይ ያጠላውን ጥቀርሻ ዲክታተርሺፕ አስወግዳ ት ትነሳለች፡፡ኢዮጵያ ካጠመዳት ክፉ ደዌ ተላቃ እንደገና እንደ ብርቅዬ አልማዝ ታበራለች! ከዘረኝነትና ሃይማኖት ክፍያ ትላቀቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከወረራት የመከራ ከበባ ተላቃ፤ ልጆችዋን ካስመረራቸው ክፉ አሳቢና እኩይ ምርጊት አላቃ እጆችዋን ከተበተባት የዘርና የጎሳ ፖለቲካ፤ ከችግርና ከመከራ፤ ከእልቂትና ከደዌ ነጻ አድርጋ ልጆችዋን በአንድነት ታቅፋለች፡፡ ኣምላክም መልሶ ያቅፋታል::

ንክሩማህ እውነተኛው የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡መጤዎቹ ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ቢሉም ንክሩማ ግና አስቀድሞ ሃሰት በማለት ኢትዮጵያማ የሰው ዘር መገኛ ማዕከል ነች ብሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን በፈላጭ ቆራጭነት ሊገዙና ሕዝቦቿንም ለመራና ሰቆቃ ሲዳርጉ ንክሩማ ግን አስቀድሞ ‹‹እምቢኝ! ኢትዮጵያማ የአፍሪካ አንጸባራቂ ሉል ናት፡፡ ማንጸባረቅ ማብራት አለባት! ልቀቋት ትግነንና ታብራ ብሏል፡ ንክሩማ ‹‹ ኢተዮጵያ የብልሆች ሃገር ናት፤አባይን የጦር መንስኤ ሊያደርጉ ሲዶልቱ ንክሩማ እምቢኝ! ‹‹ኢትዮጵያ የአባይ መመንጫ ናት›› አባይ ደሞ የህይወትን ስጦታ ለአፍሪካ ያድላል ብሏቸዋል፡፡ መንፈሳችንን ለማጉደፍና ለማጣጣል ሲሸርቡና ለመከራና ለስቃይ ሲያዘጋጁን፤ ንክሩማ እምቢኝ!‹‹ኢትዮጵያማ የአፍሪካ ራዕይ ተስፋ ነች›› አላቸው፡፡ ንክሩማ የጋና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ልጅ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በተስፋ አስቆራጭ ትቢያዎች ልንቆሽሽ መስሎ ሲሰማን በንክሩማ ትንቢታዊ አባባል ብርታት እናግኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ገና ትትነሳለች›› ስለዚህም በግርማዊ ቀ ኃ ሥላሴና በንክሩማ መሃል ውድድር የለም፡፡ ሁለቱም የኢትዮጵያ የተከበሩ ልጆች ናቸውና:: ንክሩማን ማክበር ማለት ቀ ኃ ሥላሴን ማክበር ነው፡፡ የሜይ 1963ቱን የንክሩማን ግጥም ሳነብ፤ ቀ ኃ ሥላሴ በኦክቶበር 1963 በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ትዝ ይለኛል፡፡ በዚያ ንግግራቸው ቀ ኃ ሥላሴ ለአፍሪካን ፓን አፍሪካኒዝም ጥብቅና ከመቆማቸውም ባሻገር የአፍሪካን ነጻነት ጠብቆና አክብሮ ለማቆየት የሚያስፈልገውን አይዲዮሎጂ በሚገባ አስገንዝበው ነበር፡፡

…አንዱን ዘር ከፍተኛ ሌላውን ዝቅተኛ አድርጎ የሚያሳየው ፍልስፍና ጨርሶ እስካልተወገደ ድረስ፤ አንደኛ ዜጋና ሁለተኛ ዜጋ የሚለው ደረጃ እስካልፈረሰ ድረስ፤ የአንድ ፍጡር ቀለም ከዓይኖቻችን ቀለም የተለየ ትርጉም እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ከዘርና ከጎሳ ከቀለም ልዩነት ባሻገር ለሁሉም እኩል እስካልሆኑ ድረስ፤ በተስፋነት ብቻ የሚታሰቡ እንጂ አንዳችም እርባና አይኖራቸውም… እኛ አፍሪካዊያን አህጉራችን ከዳር እስከዳር ሰላም እስክትሆን ድረስ አስፈላጊ ከሆነ ትግላችንን አናቆምም፡፡ ደግሞም ድልን በእጃችን እንደምናደርግ ጥርጥር የለንም፡፡ መልካምነት እኩይነትን እንደሚረታው ስለምንገነዘብ ድል እንደማይርቀን እርግጠኞች ነን፡፡

ቦብ ማረሊም እነዚህን ቃላቶች ለዜማው ‹‹ዋር›› (ጦርነት) ለሚለው የአፍሪካ የትግል ዜማ የሆነውን ሙዚቃውን አጅቦበታል፡፡(ምናለ አንድ ባለሙያስ የንክሩማን ግጥም ወደ ዜማ ቢለውጠው… ኢትዮጵያ ትትነሳለች፤ ትገናለች… ታበራለች…. ወደ ላይ ትወጣለች::)

በምትገነዋ ኢትዮጵያ አንድን ጎሳ፤ ሃይማኖት፤ቋንቋ፤ጾታ ከሌላው አብልጦ የሚያጎላ፤ ፍልስፍና አይኖርም፡፡ በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ዜጋና ሁለ፤ተኛ ደረጃ ዜጋ አይኖርም፡፡በነገዋ ገናና ኢትዮጵያ ዘር ጎሳ፤ ሃይሞኖት፤ወረዳ፤ጾታ፤ሁሉ ከዐይኖቻችን ቀለሞች መለያየት ያለፈ ትረጉም አይኖራቸውም፡፡ በምትገነዋ ኢትዮጵያ ሁሉም እኩል የሰብአዊ መበት ባለቤት ይሆናል፡፡

ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት

ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ስለ አፍሪካ አንድነት/አፍሪካ ሕብረት አስተያየት ማስፈር ልብ ሰባሪ ጉዳይ ነው፡፡ በ2013 በዓለም ካሉት 47ሃገራት እድገት ከማያሳዩት ሃገራት መሃል 36ቱ በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ በአንድ ወቅት የታንዛኒያ መሪ የነበሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ‹‹የመሪዎች የወሬ ማሕበር›› በማለት ጠቅሰውት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ‹‹የፈላጭ ቆራጭ ጋጠወጥ ራስ ወዳድ መሪዎች ክበብ›› ይሉታል፡፡ጋናዊው ታዋቂ ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴ ‹‹እባካችሁ ስለ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ማውራት ይብቃን፡፡ በአህጉራችን ካሉት ድርጅቶች ሁሉ አዘቅዝቆ የሚሄድና እርባና ቢስ የሆነ ድርጅት ነው፡፡‹‹ዴሞክራሲን›› እንኳን በሚገባ ሊተረጉም ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ የራሱ የሆነ ወጥነት ያለው ተግባር ጨርሶ የሌለው ነው›› ይለዋል፡፡

የአፍሪካ ሕበረት ዋና መስሪያ ቤት በቻይና መንግሥት ምጽዋት በ200 ሚሊዮን ዶላር ተሰራ በተባለና የቻይና ስጦታ “ለታዳጊዋ” አፍሪካ በተበረከተ ጊዜ ቅሬታዬን አስቀምጬ ነበር፡፡ የቻይና የግንባታ ኩባንያ ስራውን በአጠቃላይ ከቻይና በተገኘ ቁሳቁስና ቻይናዊያን ዜጎች ሰራተኞች ገነባው ሲባልና አስፈላጊውን ቁሳቁስ ሁሉ ያሟላውም ያው ቻይና ኩባንያ ነው ሲባልና ወንበርና ጠረጴዛም ሳይቀር ከቻይና ተጓጓዘ መባሉም ክፉኛ አሳዝኖኝእንደነበር ገልጫለሁ፡፡ በስጦታው ርክክብ ወቅትም የአፍሪካ ‹‹ሃፍረተ ቢስ መሪዎች›› ተርታ ገብተው እንደ ውሃ ወረፍተኛ ለቻይና የምስጋና ውርጅብኝ ሲያጎርፉ ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ… የአፍሪካ ሬኔሳንስ ተጀመረ ለማስቀጠልም መንገዱን አግኝተናል በማለት አሸሸ ገዳሜ ሲሉ ነበር፡፡››

አፍሪካ አልተነሳችም አልኩ፡፡ አፍሪካ ለልመና ተዳርጋለች፡፡‹‹የቻይና ትንሳኤ በአፍሪካ ተጀምሯል›› በአዲስ አበባ የተገተረው አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ግንብ የአፍሪካ የሃፈረት ግንብ እንጂ የአፍሪካ ኩራት ግንብ አይደለም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በአንድነት ለአፍሪካ ሚሆን ቋሚ ቢሮ ለመገንባት አቅሙን ካጡ፤ ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚሆነውን መስራት ከተሳናቸው ያሁኑን ግንብ ‹‹የአፍሪካ ምጽዋተኞች አንድነት አዳራሽ›› ከማለት አላልፍም:: የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት እና ሰብአዊ መብት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ሕብረት በአፍሪካ የፖለቲካ፤ የኤኮኖሚ እና የሶሻል ግንኚነቶችንና ነጻነትን ከማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ ወደ ልማት አቅጣጫውን ከማራመዱ አስቀድሞ ማከናወን ያለበት ሰብአዊ መብትን ነው፡፡ የአፍሪካን ልማት ለማከናወንም ሆነ አቅዶ ወደ ግብ ለማድረስ የሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሕዝቦች በነጋ በጠባ ለመከራና ስቃይ እየተዳረጉና የግፍ ኑሮ፤ የባርነት ቀንበር ተሸክመውጀርባቸው በተደራራቢ ችግር ጎብጦ ልማትን አመጣለሁ ብሎ ሩጫ ለመውደቅና ለከፋ መከራ ለመዳረግ መጣር ብቻ ነው፡፡

የአፍሪካ አንድነት ጸረ ኮሎኒያሊዝም፤ኒዮ ኮሎኒያሊዝም ጸረ ጸረ ጸረ ብሎ የሚደረድራቸው ማለቂያ የሌላቸው ጸረዎች በችግርና በመከራ ላሉ ሕዝቦች አንዳችም ጠቀሜታ የሌላቸው ልፈፋዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ጤት አልባ ከዚያም አልፎ ዋጋ ቢስ መሆኑን ለሰብአዊ መብት ካለው አመለካከትና ከከወነው ተግባር ነው፡፡ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ክፍሎች ጦርነት የየቀናት ክስተት ነው፡፡ሰዎች በየቦታው ሲተላለቁ የአፍሪካ አንድነት እጁን አጣጥፎ ከመመልከት ውጪ አንዳችም እርምጃ አልወሰደም፡፡ የአፍሪካ ጉልበተኛና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከውጪ ወራሪ በከፋ መልኩ ሕዝቦችን ሲጨፈጭፉ ለስደት ሲዳርጉ በግፍ ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አይኑን ጨፍኖ፤ ጆሮውን ደፍኖ፤አፉን ለጉሞ የድርጊቱ ተባባሪ መሆንን የመረጠ ነው፡፡ ለሕዝቦች እልቂት ደንታ የሌ፤ልው ድርጅት/ ሕብረት፡፡ የሩዋንዳ እልቂት በሚሊን የሚቆጠሩትን ንጹሃን ዜጎች በሞት ሲቀጥፍ የአፍሪካ አንድነት ቢሮውን ዘግቶ አርቲ ቡርቲ ከማራገብ ውጪ ምንም ያደረገው አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የአፍሪካ አንድነት ግድያውን ‹‹ጄኖሳይድ›› ለማለት እንኳን ድፍረቱና ወኔው አልነበረውም፡፡!

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ሶማልያ ለሁለት አሰርት ዓመታት በመበታተን ላይ ሳለች፤ የጎሳ መሪዎች ተቀራምተዋት ለጥፋት ሲዳርጓት እንኳን መድረስ ቀርቶ ከሩቅ ሆኖም ማስጠንቀቂያም ሆነ ማስፈራሪያ አልሰነዘረም፡፡ ለተፈጠረው ችግር ሌሎች ሃገራት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በሚያመቻቸው መንገድ ጣልቃ ገብተው ሲያማትሩ የአፍሪካ አንድነት በቂ ጦር እንኳን ለመላክና ሕዝቡን ከመከራ ለመታደግ አልሞከረም፡፡ በኮት ዲቭዋር የተፈጠረውን ችግር የፈረንሳይ ወታደሮች ገብተው ሲፈነጩበት የአፍሪካ እንደነት በስፋራው ቀርቶ በአካባቢውም አልደረሰም፡፡ በማሊም የተፈጠረውን ሽብር ለማስታገስና ስርአት ላመስያዝ የፈረንሳይ 5000 ወታደሮች ሲዘልቁ የአፍሪካ አንድነት ከጠቅላይ ቢሮው ንቅንቅም አላለም፡፡ በኢትዮጵያም የምርጫ በጠራራ ጸሃይ ሲሰረቅና ተሸናፊው አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ በዝምባብዌ፤በኬንያ፤ በዩጋንዳ ተመሳሳይ የምርጫ ውጤት ዘረፋ ሲካሄድ የአፍሪካ አንድነት በገለልተኛነት ከዳር ቆሞ ከተመልካችነት አላለፈም፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሰብአዊ መብትን ጥሰት በተመለከተ፤ ወንጀለኞችን መደገፍን ሙያ ብሎ ይዞታል፡፡ የሱዳኑ ኦማር አል በሺር በሰብአዊ መብት ጥሰትና በጦር ወንጀለኛነት በግፍ ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰው መያዣ ሰነድ ሲተላለፍባቸው ‹‹የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገራት በሮም የተፈረመውን የፍርድ ቤቱን ስምምነት አናከብርም በማለት የሱዳኑን አልበሺርን አሳልፈን አንሰጥም አቋም ያዙ›› ይህ ደግሞ ነግ በኔ በሚል ስጋትና አስቀድሞ መንገድ ለመዝጋት ሲሉ ተመሳሳይ ወንጀለኛ መሪዎች የወሰዱት አቋም ነበር፡፡ በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ተግባሩን መወጣት ባለመቻሉና ፍላጎትም በማጣቱ አይ ሲ ሲ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ጣልቃ መግባቱ አስፈላጊ ሆነ፡፡ ከ2011 አንስቶ በሰባት የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ይሄው ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርመራውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሌለው ቢሮ ያላቋቋመው የመብት ማስከበርያ ጽ/ቤት የለም ግን አንዳቸውም ለተግባር አልበቁም፡፡ የአፍረካ ሕብረት የሰብአዊ መብት ቢሮ፤ የአፍሪካ ሕብረት የልጆች መብት፤ የሴቶች መብት፤ በማለት በርካታ ኣዋጅ አውጥቷል ቢሮም አቋቁሟል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ቢሮም አለው፡፡ የዚህም ቢሮ ተግባሩ ሰብአዊ መብትን ማስከበር፤ የዴሞክራሲ ስርአትን ትግበራ ማረጋገጥ፤ምርጫዎችን በአግባቡ ተካሂደው የህዝብ ፍላጎት ማሟላት ቢሆኑም አንዱንም አላከናወነም፡፡ በአባል ሃገራት ምርጫ ወቅት ዳጎስ ያለ ወጪ በመመደብ ታዛቢዎች ቢሊክም ታዛቢዎቹ ሆቴላቸውን ሳይለቁና ምርጫ ጣቢያዎችም ቢሆን እንደነገሩ ደረስ መለስ ከማለት አልፎ አንዳችም ውጤት ያለው ትዝብት አላከናወኑም፡፡ በየሄዱበት ሃገር ያለው ገዢ ፓርቲ የሚሰጠውን መግለጫ ደግፈው ተጋብዘውና ተሸልመው ከመመለስ ውጪ ምንም አላደረጉም:: በ2010 ነፍሳቸውን በተገቢው ቦታ ያኑረውና መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲል፤በቀድሞው የቦትስዋና ፐሬዜዳንት ማሲሬ ለታዛቢነት የተሰማራው ቡድን ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ ነበር፤ የምንግስት መዋቅርን መጠቀምና ሕገ ወጥ የሆነ ሂደትም መራጩንም ማስፈራራትና መስገደድም ያልነበረበት ምርጫ ነበር በማለት ማሲሬ ቀልማዳ ትዝብቱን ተፈራረመ፡፡ ሲደመድምም ምርጫው የአፍሪካን አንድነት የምርጫ ደንብና ስርአት ያሟላ፤ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት ያካተተ፤… የአፍሪካ ሕብረት ተቃዋሚዎች ከምርጫው አስቀድሞ ያሰሙትን ቅሬታ የሚያረጋገጥ አንዳችም ሁኔታ አልታየም፡፡ ክሱን ወይም ውንጀላውን የሚረጋግጥ አንዳችም ሁኔታ አላየንም በማለት ነበር፡፡

አፍሪካ ከመቼውም በከፋ መልኩ አሁን ተበታትናለች፡፡ፓን አፍሪካኒዝም አፈር ዲቤ በልቷል፤ እድሜ ለአፍሪካሕብረት፡፡አሁን በአፍሪካ ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው አዲስ አየዲዮሎጂ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች በድፍረትናበማን አለብኝነት የዘር ብሔርተኝነትን በስልጣን ለመቆየት አመቺ ስለሆናቸው በመንዛት ላይ ናቸው፡፡ የዘርማንነት፤ የዘር ጥራት፤የዘር መኖርያ፤ በሚል ሰበብ ሕዝብን መጨፍጨፍና ከራሳቸው ከገዢዎች ውጪ ያለውን ዘር በሚልያስቀመጡትን ሁሉ ለማጥፋትና ብቸኛ ዘር ሆነው ለመኖር እየገሰገሱ ነው፡፡

በኢትዮጵያም ‹‹የብሔር ፌዴራሊዝም›› በሚል ቆንጆ መጠቅለያ የተጀቦነ ፖለቲካዊ ሂደት እየተንደረደረነው፡፡ኢትዮጵያዊያን በማንነታቸው በትውልዳቸው በቀያቸው መገለልና መገፋት መፈናቀል እየደረሰባቸው ነው፡፡በክልልተደልድለው ያለፍላጎታቸው ስም ወጥቶላቸው ለጥቃት ተዘጋጅተዋል፡፡ ጥቂት የገዢው መደብ አባላት በድሎት እንዲኖሩናያለሃሳብ እንዲንደላቀቁ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ለግፍ ተዳርጓል፡፡እንዳይናገር በሆዳም ካድሬዎችና ለጊዜው ገዢዎችእራሳቸውን በሸጡ አጎብዳጆች ተወጥሮ መከራ እየወረደበት ነው፡፡ ሆዳሙ ያዜማል ሆዳሙ ይገጥማል፤ ሆዳሙ ይጨፍራል፤ሆዳሙ ቅኔ ያፈሳል ሆዳሙ ያጨበጭባል ሆዳሙ ይደሰኩራል፤ ሆዳሙ ሆዱን ይሞላል ሕዝቡ ግን ለመከራና ስቃይተዳርጓል፡፡

ታላቁ የአፍሪካ ደራሲ ቺኒዋ አቼቤ (Things Fall Apart) ለምንድን ነው በአፍሪካ ሁሉም ነገርየሚፈራርሰው በሚል መነሾ ጻፈ፡፡የኔ መለስ አጭር ነው፡፡ባለፈው የግናሽ ምእተ አመት ነጻነት የአፍሪካን ግፈኛገዢዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ድርጅት ለመፍጠር ባለመቻሉ ነው እላለሁ፡፡ላለፉት 50 ዓመታት የአፍሪካ መሪዎችተጠያቂነትን አሻፈረን ብለዋል፡፡ የዚህ ተጠያቂ ሕዘቡ እንደሆነ ለማሳመን ጠረታቸው መጠን የለውም፡፡አፍሪካ ከቅኝገዢዎች በተተወለት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ሰበብ እየተደረገ ዘወትር በማያልቅ ጥሪ የሚጠቆመው፤ ነጮች፤ የቅኝገዢዎች ቅሪት፤ ካፒታሊዝም፤ ኢምፕሪያሊዝም፤ ኒዮ ሊቤራሊዝም፤ ግሎባላይዜሽን ነው መሸሻው፡፡ ….. የዓለምየገንዘብ ተቋም ነው፤የዓለም ባንክ ነው፤……የአህጉሩ ያለማደግና ያለመልማት ሰበቡ የመኑስናው፤ የመልካምአስተዳደር እጦት ሁሉም በመጥፎና እርኩስ መንፈስ የመጡ እንጂ የአህጉሩ አይደሉም ማለት ይዳዳቸዋል፡፡ነገሮች ሁሉ በአፍሪካ ፍርስርሳቸው የሚወጣበት ሰበብ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› የሕዝቦቻቸውን ሰብአዊ መብትባለማክበራቸው ነው፡፡የአቼቤን አባባል ለማጠናከር፤ አፍሪካ አሁን ያለችበት ሁኔታ ውስጥ ያለችበት መንስኤየአፍሪካ መሪዎች እንደመሪ ሊሆኑና ሊያደርጉ የሚገባቸውን የመሪነት ሚና መጫወት ባለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹ጥቂትየአፍሪካ መሪዎች የሕዝቦቻቸውን ክብርና ሰብአዊ መብት በአግባቡ ያከብራሉ፡፡ አፍሪካ መሪዎች ናቸው በሚባሉትገዢዎቿ እያደናቀፉ እየጣሏት እንዴትስ መነሳትና መግነን ትችላለች? ለመነሳት በሞከረች ቁጥር ያንን የመርገምትቦት ጫማቸውን ማጅራቷ ላይ አሳርፈው እንዳትነሳ፤ እንዳታድግ፤ እንዳትለማ ረግጠው ይዘዋት እንዴት ብላ ነውየምታድጋው? ያም ሆኖ ጊዜው ሲደርስ አፍሪካ ፍርስርሳቸው የወጡባት አፍሪካ ተሰባስበው አንድ የገነነች አፍሪካሆና ትነሳለች!ስለዚህም ለአፍሪካ አንድነት/ አፍሪካ ሕብረት 50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ለግ ቀ ኃ ሥላሴና ለክዋሚህንክሩማህ የማበረክተው ስንኝ

ኢትዮጵያ ከፍ በይ! የኢትዮጵያ ትንሳኤ! የአፍሪካ ትንሳኤ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንጸባራቂ ማዕድ ትነሳለች ትገናለች

ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ተላቃ

የግድበ አፍሪካ ምድር እንደሚበራው የበጋ የንጋት ፍንጣቂ

በአፍሪካ ምሽት ሰማይ እንደምትበራው የጨረቃ

ብርሃን አንቂ ኢትዮጵያ ትንሳኤዋ ያበራል ትገናለች::

ኢትዮጵያ ከራስ ደጀን ጉብታ ጫፍ ትንሳኤዋ ይታያል

እስከ ኪሊማንጃሮ ዘልቆ ይጠራል

ከፖለቲካው አረንቋ መታወቂያነት

እስከ ሀገራዊ ኩራት በልዩነት

ኢትዮጵያ አስከብራ የሁሉንም ማንነት ትነሳለች::

በአፍሪካ ምድር የነጻነት ብርሃኗን ትረጫለች

የሊቃውንት ሃገር ኢትዮጵያ ከመንደርተኛ አዋቂዎች በላይ ተንብያ

ህዝቦቿ ተሰባስበው ተዋህደው ተፋቅረውና ተግባብተው

ሰብአዊነትን ወግነው አንድነትን መቻቻልን አንግበው

ኢትዮጵያ ትነሳለች ትገናለች::

ኢትዮጵያ የነግህ የአፍሪካ ተስፋ

በትንሳኤዋ የረገጧትን የጨፈለቋትን አልፋ

ቅጥፈታቸውን ጭካኔያቸውን ሙስናቸውን

ያን ያለፈ ዘመናቸውን ከነምኞታቸው ገንዛ በብረት ሳጥን

የሕግ የበላይነትን አስከብራ፤ኢትዮጵያ እንደ ጸሃይ ታበራለች::

በምድሯም ሰላም እስከ ዘልዓለሙ እንዲሰፍን ታደርጋለች

የኢትዮጵያ ትንሳኤ በማይደፈሩት ሃቀኛ ወጣቶቿ

ከፍ ትላለች ተደግፋና ተሞሽራ በልጆቿ

ኢትዮጵያ እስከማዕዜኑ ትገናለች

ለወጣቱ ትውልድም የዘልአለም ቤቱ ትሆናለች::


የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል –ቁጥር 01 ግርማ ሞገስ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ካለምንም እንከን ተጠናቀቀ። አምባገነን መለስ ዜናዊ ከግንቦት 8 ቀን 1997 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሽብርተኛ ህጎቹ እና ተግባሮቹ የገነባው የፍርሃት ፖለቲካ ህንጻ ፈረሰ። በዚኹ እለት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ማዕከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስኮች መፈጸም አለባቸው የሚላቸውን እርማቶች በንግግሮች እና በመፈክሮች በአደባባይ አስታወቀ። እነሱም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊቀርቡ ይችላሉ፥ “መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም፣ ነፃነት እንሻለን፤ ፍትህ እንሻለን፤ አንለያይም፤ የህሊና፣ የሃይማኖት እና ሌሎች ፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ፤ በአገራችን ሰላም አጣን፤ ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ፤ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል፤ ህዝብ ማፈናቀል የዘር ማጥራት ወንጀል ነው፤ ህገ-መንግስት ይከበር፤ የሽብር፣ የነፃ ፕሬስ እና የሲቪክ ድርጅቶች ህጎች ይከለሱ ወይንም ይሰረዙ፤ ኢቲቪ ሌባ፣ ኢቲቪ ውሸት፣ ኢቲቪ ሽብር” የሚሉት ነበሩ።

መንግስት ለተጠየቀው ጥያቄዎች አዎንታዊ መልሶች መስጠት ይጠበቅበታል። ሁሉም ነገር በእጁ እና በደጁ ስለሆነ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግረው ምንም ነገር የለም። ዛሬ ብድግ ብሎ “እስከ ዛሬ ድረስ ለፈጸምኩት ጭቆና ይቅርታ ይደረግልኝ። የዜጎችን ነፃነት ከዛሬ ጀምሮ አከብራለሁ። እስረኞችን ነገ እፈታለሁ። በኢትዮጵያ በነፃ ፕሬስ ላይ የጫንኩትን ጭቆና ከዛሬ ጀምሮ አንስቻለሁ። ኢ.ቲቪ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአንድ ወር ውስጥ ከመንግስት ፖለቲካ ነፃ ሆነው እንዲደራጁ አደርጋለሁ። ህዝብ ማፈናቀል በኢትዮጵያ ዳግም አልፈጽምም። የተፈናቀሉትም ካሳ ተከፍሏቸው እና ህጋዊ ዋስትና ተስጥቷቸው ወደቀድሞ ኑሮዋቸው እንዲመለሱ በአንድ ወር ውስጥ እፈጽማለሁ። አፈናቃዮችን ፍርድ ቤት አቀርባለሁ። ሁሉም በሙስና የሚታሙ ባለስልጣኖች አዜብ መስፍን ሳትቀር ክትትል እንዲደርግባቸው አደርጋለሁ። አንድን ሙሰኛ ከሌላ ሙሰኛ ሳላበላልጥ ሁሉም ሙሰኞች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አደርጋለሁ። በዚህም በዚያም እያልኩ በየውሩ ከደሞዛችሁ እምቆርጠውን ከዚህ ወር ጀምሮ በማቆም የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችሁ እንዲያገግም አደርጋለሁ። ህገ-መንግስት አከብራለሁ።”

በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግስት ከፍ ብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ከፊሉን ያህል በማድረግ እንኳን ከአምባገነንነት ወደ ተሻለ የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ሊያደርግ ይችላል። ይኽን በማድረግ የነፃነት እና የዲሞክራሲ አድማሶች እንዲሰፋ ያደርጋል። በምላሹ የህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል። የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ማለት ደግሞ የፖለቲካ ድጋፍ ማገኘት ማለት ነው። እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ መንግስት ከተቃዋሚ ዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደርጋል ማለት ነው። ይኽን በማድረግ መንግስት የሚያጣው ነገር ቢኖር አምባገነንነትን ብቻ ነው። ምርጫው የእርሱ ነው። በታሪክ ግን አምባገነኖች ካልተገደዱ በስተቀር በፈቃዳቸው የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደረጉበት ጊዜ ስለመኖሩ ተጽፎ ያየሁት መረጃ የለኝም።

መንግስት ከፍ ብለው ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ካልሰጠ በአምባገነንነት መቀጠል መርጧል ማለት ነው። እሱም ቢሆን ችግር አይሆንም ለዲሞክራሲ ሰራዊት። የዲሞክራሲ ሰራዊት በሰላማዊ ትግሉ የዲሞክራሲ ማዕከሉን መሰረት እና አቅም ያጎለምሳል። ይኽን ማድረግ እንደሚቻል ታሪክ ትመሰክራለች። ይሁን እንጂ መንግስት አምባገነንነትን ከመረጠ ስትራተጂካዊ የፖለቲካ ስህተት መፈጸሙን ልብ ሊል ይገባል። ነፃ ምክር ነው!

ሲጠቃለል፥ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ሁለት የፖለቲካ ማዕከሎች እንዳሉ እና በመካከላቸው ሰላማዊ ትግል እንደሚካሄድ አሳይታናለች። የዲሞክራሲ ኃይሎች የሚያደርጉት የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ትግል በስልጣን ላይ ከሚገኘው አምባገነን መንግስት አንፃር የፖለቲካ መሰረታቸውን እና አቅማቸውን ሳያቋርጥ ሽቅብ ማሳደግ አለበት። በውጤቱም የፖለቲካ ኃይል ደረጃቸው ቀስ በቀስ ከበታችነት ወደ አቻነት ከዚያም ወደ በላይነት ደረጃ ይጓዛል። የበላይነት ደረጃ መያዝ ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ ማለት ነው። መንገዱ ደግሞ ምርጫ ወይንም ግብጽ ሊሆን ይችላል።

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል ሌላ ቁልፍ የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ነው። አፈጻጸሙን በስፋት ማወቅ ጠቃሚ ነው የተሳካ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ። የሽግሽግ ትግልንም ከበካዮች (Contaminants) መጠበቅ ያስፈልጋል።

Golgul/ጎልጉል በፌስ ቡካችሁም (https://www.facebook.com/goolgule) ላይ በማቅረባችሁ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። አሁንም ቀጥሉበት። ዘሃበሻም እንደዚሁ። የረጅም ጊዜ የሰላማዊ ትግል ጉዋደኛዬ አብርሃ (ኢትዮሚዲያ) ምስጋናዬን ተቀበለኝ። እንዲሁም ቋጠሮ፣ ኢትዮጵያ ዛሬ፣ አቡጊዳ፣ አሲምባ፣ ECADFORM እና ያላየሁዋችሁ ድረገጾች በሙሉ ለምትለግሱኝ ትብብር ምስጋናዬ ገደብ የለውም። ትግሉ የጋራ ቢሆንም!

እኛ ያልነው ለፉገራ…ክንፉ አሰፋ

$
0
0

በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፈሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ ብርጭቆ ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ። በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው ተቀብለው በደስታ ጨለጡት።

በረከት ለጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጆሯቸው እንዲህ ነበር ያላቸው። “ብርጭቆ ውስጥ ያለው መለስ የጀመረው ወይን ነው።”

አሁን አሁን መቀለጃ እየሆኑ የመጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ መለስ የጀመረውን ሁሉ፤ ፉገራም ቢሆን – ያንን ለመጨረስ ነው የተቀመጥኩት ይሉናል። እየደጋገሙ!

***

ብርኖ በምትባል የቼክ ሪፐብሊክ ትንሽ ከተማ ከነበርኩበት ሆቴል ውሰጥ የተሰቀለ ቲቪ ካለወትሮው የ’ሕዳሴውን’ ግድብ የሚያሳይ ምስል ይዞ ብቅ አለ። የምሽት ዜና ትንተና መሆኑ ነው። በቼክ ቋንቋ ይተላለፍ የነበረው የዜና ትንተና ባይገባኝም ከምስሉ የመልእክቱን ይዘት ለመረዳት አላስቸገርኝም።

ግን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?

የቲቪውን ጣቢያ መቀያየር ጀመርኩ። ሲ.ኤን.ኤን፣ ቢ.ቢ.ሲ.፣ አል ጃዚራ…ቪ.ኦ.ኤ.። የኳታሩ አል ጃዚራ ጉዳዩን በስፋት ይዞታል። Death on the Nile (በአባይ ላይ ግድያ) በሚለው አምዱ ምሁራንን እና ባለስልጣናትን እያቀረበ ስለ ‘ሕዳሴው’ ግድብ ያወያያል። በአሜሪካን መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግብጹ ሱኒ ‘አል ጋማ አል ኢስላሚያ’ ድርጅት ደግሞ ኢትዮጵያን በጦር ለመውጋት ዝግጁ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ አውጇል።

ሂደቱ እንደገና ሌላ ጥያቄ አጫረብኝ። የግድቡ ወሬም ሆነ ስራ ከተጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው ነው። ዓለም አቀፉ ሜዲያና ዘራፍ ማለት የጀመሩት ቡድኖች ዛሬ ያባነናቸው ምስጢር ምንድነው? አመቱን ሙሉ የት ነበሩ? መልሱን የምናውቀው እኛ ባለቤቶቹ ብቻ ነን። በእርግጥ አቶ መለስ የአባይ ካርድን ይዘው ይጫወቱት የነበረውን ጨዋታ ግብጾች ጠንቅቀው ያውቁት ኖሮ የ’ሕዳሴው’ን ሽርጉድ ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር።

ከሁሉም ነገር እንግዳ የሚሆነው፣ በየመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አስተየት የሚሰጡ የፈረንጅ ‘ምሁራን’ ጉዳይ ብቻ ነው። እነዚህ ተመራማሪዎች ስለ አባይ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ…ወዘተ ሊቅ ሆነው የተሳሳተ ግምታቸውን እያቀረቡ ሌላውንም ግራ ያጋቡታል። ስለ ግድቡ በአልጃዚራ አስተያየት ትሰጥ የነበረችዋ ኤክስፐርትም ሂደቱን ‘ብቀላ’ እንደሆነ ገልጻዋለች። ሌላውም እንዲሁ ‘የሕዳሴው ግድብ’ ጦርነት እንደሆነ ገልጿል። የአካባቢ ጥበቃ፣ ኤኮሎጂ… ወዘተ ችግር ያስከትላል የሚሉም አሉ። ሁሉም አስተያየቶች ግን ከኛ ከሃገሬው አመለካከት የራቁና ከመላምት ያለፉ አይደሉም። እውነታው ሌላ ነው። ፉገራ እና ፉከራ!

በደርግ ጊዜ ነው። መንገድ ላይ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ‘የሚቀፍል’ አንድ ወጣት ነበር። በዚህ ሰው የፖለቲካ ‘ፉገራ’ ፈገግ የሚሉም ሳንቲም ጣል ያደርጉለታል። አነድ ቀን ‘ኢሰፓኮ፣ ባዶ ባኮ! ‘ እያለ ሲቀልድ ካድሬዎች አይን ውስጥ እንደገባ ነቃና ማምለጫ ዘዴ ፈጠረ። መንጌን ማወደስ። ‘የሰው ጥራቱ፣ እንደ መንግስቱ!…’ እያለ ከተማውን አቀለጠው። ይህ ዘዴው ከተደገሰለት ሞት ቢያስተርፈውም፣ ከእስር ግን አላስመለጠውም። የማታ ማታ በሚሊሽያዎች ተይዞ ታሰረ። እዚያው ሆኖ እነዲህ አለ። ‘እኛ ያልነው ለፉገራ እነሱ ግን ለመግደል ሙከራ።’

የነጻ ትግል ስፖርት የሚሰሩ አትሌቶች ተመልካቾቻቸውን አልፎ አልፎ ‘Be smart. Don’t try this at home’ ሲሉ ይመክራሉ። ‘አስተውሉ! ይህንን ነገር እቤታችሁ አትሞክሩ።’ እንደማለት ነው። በቦክስ ሪንግ ውስጥ የሚያደረገው መዝለል፣ መውደቅ እና መነሳት ሁሉ ቀድመው ተለማምደው የሰሩት አክሽን መሆኑን ነው የሚናገሩት። እነዚህ አትሌቶች ለመኖር ሲሉ የሚሰሩት ድራማ እንጂ፣ የሚታየው ድብድብ ሁሉ የ’ፉገራ’ መሆኑን ነው በማስታወቂያቸው የሚናገሩት። በግልጽ ባይሉትም። እንዲህ አይነቱ ጨዋታ ጥበብን ስለሚጠይቅ ማየት እንጂ መሞከሩ አደጋ ያመጣል።

አቶ መለስ ‘Be smart. Don’t try this at home.’ ሳይሉ ማለፋቸው ይመስላል እነ ሃይለማርያም ዛሬ ማኖ እየነኩ ያሉት። ‘መለስ የጀመረውን ለመጨረስ ቃል ገብቻለሁ።’ አይደል እያሉን ያሉት?

ባለፈው ማክሰኞ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ መቀልበስ ስራ በኢቲቪ የቀጥታ ስርጭት መታየት ሲጀምር ነው ጫጫታው በዓለም አቀፍ ሜዲያ የተከተለው። እስከዚህች ቀን ድረስ ግን ኢቲቪ ይቀርበው የነበረው ፕሮፓጋንዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰልቸት ያለፈ የሜዲያ ትኩረት አልሳበም ነበር። ዜጎችን በፕሮፓጋንዳ በማሰልቸት ኢቲቪ በእውነቱ የሂትለሩን ጆሴፍ ጎብልስ ሚና በደንብ ነው የተጫወተው። ጆሴፍ ጎብልስ እንዲህ ብሎ ነበር። “ውሸትን እየደጋገምክ ተናገር። በመጨረሻ ሕዝቡ እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል።”

የቅልበሳው ትእይንት ማክሰኞ እስከታየበት ቀን ድረስ የ’ሕዳሴው’ ግድብ ተረት-ተረት እንደሆነ ነበር እነ ግብጽ የሚያውቁት ለማለት የሚያሰቸል ክስተት ነው ያየነው። የግበጽና ሱዳን ጩኸት፣ የሌሎች ቡድኖች ማስፈራሪያ ዛቻና የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ማግኘት የጀመረውም ከዚያ በሗላ ነው። “እኛ የመሰለን ፉገራ …።” እንደማለት ነው።

ነብሳቸውን ይማረውና አቶ መለስም በህይወት ቢኖሩ ኖሮ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጠርተው፡ “እኛ ያልነው ለፉገራ፤ እናንተ ለመገደብ ሙከራ!” ይሏቸው ነበር።

ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ከ80 እጅ በላይ ድርሻ አላት። ይህንን ያህል ለአባይ እየገበርን እሰካሁን በአባይ ወንዝ ተጠቃሚ ያለመሆናችን የሚያንገበግብ ጉዳይ ነው። አባይ ተገድቦ ለኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ቢውል የማይደሰት ሰው ቢኖር የኢትዮጵያ ጠላት በቻ ነው።

አሁን በተያዘው መልኩ አባይ ተገድቦ ስራ ላይ ይውላል ብሎ የሚያስብ ካለ ግን ልጅ ውይንም ጅል መሆን አለበት። ‘አባይ ይገደባል’ ብለው የሚከራከሩኝ ወዳጆቼ ለሃገራችን እድገት ካላቸው በጎ ምኞት ያለፈ ሌላ እውነታ እንደሌለው ነው ማስረዳቸው።

የ’ሕዳሴው’ ግድብ፤ የቱኒዥያውን ቤን አሊ፣ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክ፣ እንዲሁም የሊቢያውን ጋዳፊ የጠራረገው የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ ማእበል የወለደው ሃሳብ ነው። ለችግር ጊዜ ተቀምጦ የነበረ ጆከር ነው የሳቡት። ይህ ደግሞ የወጣቱን አንደበት ከያዘው የኮብል ስቶን ፕሮጀከት ጋር በመታገዝ እነ መለስን ከማዕበሉ ጠብቋቸዋል።

የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም። እንደ እንጉዳይ ተክል ከመቅጽበት ብቅ ያለ ነገርም አይደለም። ለዘላቂ ሳይሆን ይልቁንም ላጭር ጊዜ እንደሚወሰድ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት አይነት ነው። አቶ መለስ ዜናዊ የግድቡን መሰረት ሲጥሉ 6ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨቱ ጉዳይ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችልም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዚህም አንደኛው ምክንያት በ1993 (እ.ኤ.አ.) አቶ መለስ ዜናዊ ከግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ነው። (የሁለቱን መሪዎች ፊርማ የያዘውን ይህንን ሚስጥራዊ ስምምነት በወቅቱ ለህትመት በማብቃቴ ለማእከላዊ እስር ተዳርጌ ነበር።) በዚህ ሁለትዮሽ ውል በአንቀጽ አምስት ላይ ‘አንዱ ሃገር ሌላውን ሃገር በሚጎዳ መልኩ ውሃውን መጠቀም አይችልም።’ በማለት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ መብት የሚገፍ ሃረግ ተቀምጧል። ይህ ዲፕሎማሲዊ አንቀጽ በህግ ቋንቋ ሲገለጽ ‘ኢትዮጵያ አነዲት ማንኪያ ውሃ ከአባይ ላይ ብትቀዳ፡ የግብጽን ተፋሰስ ሰለሚቀንስ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ አለባት።’ እንደማለት ነው። ከኛ አልፎ ግብፅ ምድር ላይ የሚንፏለለውን ውሃ ካይሮ ተጠቀመች አልተጠቀመች እኛ ምን አገባን?

በአለም አቀፍ ህግ፣ ሁለት ሃገሮች ተስማመተው የሚያጸድቁት ሰነድ ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው እስካላፈረሱት ድረስ ሀጋዊ ሰነድ ሆኖ ይቆያል።

አቶ በረከት ስምዖን አልጃዚራ ላይ ባለፈው አርብ ቀርበው፤ በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ሰነድ ሲያነሱ፤ የራሳቸው ስርዓት በ1993 ያፀደቀውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን የተፈጥሮ እና ሀጋዊ መብት አሳልፎ የሰጠውን ውል እንደዋዛ አልፈውታል። ይህ ሰነድ በቅኝ ግዛት ዘመን ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የከፋና ለክርክር እንኳን የማያመች ነው።

በአባይ ወንዝ 84 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያን ያላሳተፉ እነዚያን የቅኝ ግዛት ውሎች ሁሉ ውድቅ ለማድረግ የህግም ሆነ የሞራል የበላይነት አለን ብዬ አምናለሁ። ግና የ1993ቱ ምስጢራዊ ሰነድ እንዴት ነው ሊፈርስ የሚችለው? ይህ ውል ሳይፈርስ እንዴትስ ነው አባይ ሊገደብ የሚችለው? ለዚህ ጥያቄ እነበረከት በእርግጠኝነት መልስ ሊስጡን አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ ማየት ያለብን አባይ ዓለም አቀፍ ወንዝ መሆኑን ነው። ዓለም አቀፍ ወንዝ ደግሞ በአንድ ሃገር አዋጅ ሳይሆን፤ በዓለም አቀፍ ህግ ነው የሚመራው። የአባይ ወንዝ ለመጠቀም የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች ሁሉ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ህጉ ያስገድዳል።

በሶስተኛ ደረጃ አባይን ከምር መገደብ ካስፈለገ፤ አባይን መገደቢያ ገንዘብ አይጠፋም። የህወሃቱ ኢፈረት ብቻውን አንድ አይደለም፤ አራት አባይን መገደብ የሚያስችል ገንዘብ አለው። ገዢው ፓርቲ እርግጥ ለኢትዮጵያ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ስኬት ካሰበ በፓርቲው ስም ያከማቸውን ገንዘብ አውጥቶ ለግድቡ ተግባር ማዋል ይችላል። የኢፈርት ህለቀመሳፍርት ገንዘብ ቢያጓጓው እንኳ በአክሲዎን ሽያጭ ገንዝብ መሰብሰብ ይችል ነበር። ለግድቡ ያስፈልጋል የሚሉን 80 ቢሊየን ብር ነው። እስካሁን ከህዝብ በውዴታም ሆነ በግዴታ ተገኘ የተባለው ደግሞ 7 ቢሊየን ብር። 73 ቢሊየኑን ታዲያ ማን ሊሞላው ይሆን? ወይንስ እንዳሁኑ አይነት ያልተጠበቁ ችግሮች ሲገጥሙ ስራውን ለማቆም እንደምክንያት ሊቀርብ?

ከውስጥ ሰዎች እንደምንሰማው ከሆነ ደግሞ እነ መሶበ ሲሚንቶ እንዲሁም የህወሃት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች የግድቡን መሰረት በመጣል ስም ከህዝብ የተሰበሰበውን 7 ቢሊየን እየተቋደሷት ይገኛሉ። በአንድ ወንጭፍ ሁለት ወፍ .. እንዲሉ። 7 ቢሊየን ቀላል ገንዘብ አይደለም። በቅጡ ቢያዝ ኢትዮጵያን ጸብ ውስጥ የማይጨምራት እጅግ ብዙ የሚተገበር የልማት ስራ ላይ ሊውል ይችል ነበር። ኢትዮጵያ ሃይል ሊያመነጩ የሚችሉ በርካታ ትናንሽ ወንዞችም አሏት።

የ’ሕዳሴው ግድብ’ በዚህ ሂደት ተግባራዊ ይሆናል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ለገዢው ፓርቲ ግዜ መግዣነት ስለማገልገሉ ግን ቅጥ ያጣው የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ምስክር ነው። ጫወታው ሳይገባቸው በሃገር ፍቅር ስሜት ብቻ የተሸውዱ እንዳሉ ሁሉ ሕዝቡን ባልተጨበጠ ነገር የሚያሞኙት ልማታዊ ጋዜጠኞች እና ልማታዊ አርቲስቶች ነገ ትዝብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

በአንድ ጽሁፌ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት በኡጋንዳ – ጂንጃ የነጭ አባይ ምንጭ የሆነው የቡጃጋሊ ግድብ ስራ ተጠናቋል። ኡጋንዳ የነጭ አባይ ምንጭ ነች። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ የሃገሪቱን የሃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የነጭ አባይ ፕሮጀክት ዘርግተው ተግባራዊም አድርገዋል። ለዚያውም በአለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እርዳታ! ነጭ አባይ የሃገሪቱን የሃይል ምንጭ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል።

ይህ ግድብ ሲታቀድም ሆነ ሲሰራ ታዲያ በጩኸት እና በመፈክር አልነበረም። የሃገሪቱ አርቲስቶች አልዘፈኑለትም። ሕዝቡ ስለፕሮጀክቱ እንዲጮህለትም ሆነ እንዲጮህበት አልተደረገም። እነደ”ህዳሴ”ው መዋጮ ሁሉ የዜጎች ኪስ አልተበረበረም፤ ከወር ደመወዙ የተቆረጠ ነገር የለም። ቡጋጃሊ ሲገደብ ቦንድ አልተሸጠም፤ ወታደራዊ ማርሽም አልተሰማም። ሙሴቬኒ አንባገነን ቢሆኑም ለሃገራቸው እድገት ብልሃት በተሞላበት መንገድ ሄደዋል። ‘Think global, act local’ ነው ጫወታቸው። ‘ሞያ በልብ ነው’ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።
አባይን በፕሮፓጋንዳና በጩኸት ለመገደብ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ታዲያ ይህንን እያዩ እንኳን አልተማሩም። አባይ ሲቀለበስ በላይቭ ቲቪ ማሳየት ከፕሮፓጋንዳነቱ ባሻገር ምንድነው ጥቅሙ? ድርጊቱ ህልውናው በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ ሕዝብን ለጦርነት መጋበዝ ይመስላል። ውግዘቱና ጫናው ሲበዛ ጉዳዩን ለማቆም ምክንያት ለመፍጠርም ያመቻል።
አለም አቀፉ ህብረተሰብ በ’ሕዳሴው ግድብ’ ጉዳይ ላይ ዝምታን ነው የመረጠው። ለዚህም ምክንያት አለው። ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ሆና ሌሎች ሃብትዋን ያላግባብ ሲጠቀሙ፤ ድልድሉ ትክክል እነዳልሆነ አለም ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም። የመለስና ሙባረክ ፊርማ ሳይቀደድ የተጀመረው የአንድዮሽ ውሳኔም የት ተጀምሮ የት ላይ እንደሚያልቅ ያውቁታል። ለዚህም ይመስላል ለግድቡ የገንዘብም ሆነ የሞራል ድጋፋቸውን ሊነፍጉ የቻሉት። የግድቡ ጅማሮ አንደኛ አመት ሲከበር የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶ ነበር። ዲፕሎማቶቹ ግን በስፍራው ሳይገኙ ቀሩ። ለ’ሕዳሴው’ ግድብ እውቅና በመስጠት የፖለቲካ ስህተት ላለመስራት የመከሩ ይመስላል።

አርዐያ ተስፋማርያም ሰሜናዊው ኮከብ ቴድሮስ ሃይሌ

የሕዝብ ድሎች ሲመዘገቡ-ሲጣጣሙ፤

መነገር ያለበት ቁጥር 6 በልጅግ ዓሊ

የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን! ግርማ ሞገስ

ትውልድ ያናወጠ ጦርነት የመጸሃፍ ግምገማ በአቶ አበራ ለማ

$
0
0

”ትውልድ ያጫረሰ ጦርነት” የሚለውን የሻለቃ ንጋቱ ቦጋለን መጽሃፍ (nigebogo@yahoo.com) ከሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን መደብሮችና ከአገር ቤት ማግኘት ሲችሉ፤ ”የጀግና ወሮታ” የተባለውን ሰለሞን ለማ ገመቹ ያጠናቀረውን መጽሐፍ ደሞ ካዲስ አበባ (ስልክ ቁ. 0911791931) ማግኘት እንደሚችሉ ኣሳስባለሁ፡፡

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ስደት ድህነት ነው ድህነት የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው በግሩም ተ/ሀይማኖት

$
0
0

በጨለማ ውስጥ የምትዳክረው የየመኗ ዋና ከተማ ሰነዓ ሆኜ ስንቱን ጉድ አየሁ፡፡ ስንቱ ስደተኛ ላይ የደረሰውን እያየሁ አለቀስኩ፡፡ ኡኡኡ….ድረሱ አልኩ፡፡ኢትዮጵያን እንወዳለን የምትሉ ሰዎች ህዝቡን ሳይሆን ባዶ መሬቱን ድንጋይ አፈሩን ነው እንዴ የምትወዱት ወገን አለቀ ድረሱ…ብያለሁ፡፡ ተመስገን ዛሬ ከስንት ሺዎች እልቂት በኋላ የሚደርስ ባይሆንም ሰሚ መገኘቱ ደስ ይላል፡፡ ለወሬም ቢሆን ተሰምተናል፡፡ ባይሆን ፕሮግራሙን ያየ እንኳን ሊማርበት ይችላል እና ብራቮ ኢቲቪ….ተመስገን ስለተረፍኩ ዛሬ ለስንቱ እልቂት ምስክር ሆኛለሁ፡፡ ሰነዓ መብራት ችግር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ኩራዝ ለኩሳ በጀኔሬተር ጩኸት (ባንድ) የምትታጀብ ጭል..ጭል በሚል ደብዛዛ ብርሃን ያላት ሰፊ ናይት ክለብ ትመስላለች፡፡ ብቅ ጥልቅ የምትለው መብራት ተራዋ ለእኛ ሆነና እውነት ባይኖር እንኳን ዘፈን አይጠፋም፡፡ አንዳንዴም ምን ዋሹ የሚለውን ለማየት ኢቲቪ ከፈትኩ፡፡ ከዜና በኋላ ስለስደት ለየት ያለዝግጅት እንደሚያቀርቡ ማስታወቂያውን ሰምቼ ጠበኩ፡፡ ዘ-ይገርም ነው፡፡ ግን ሁሌ ከቀብር በኋላ ማሸርገዳችን..ልታይ ልታይ ማለታችን እስከመቼ ይሆን የሚቀጥለው?

ፕሮግራሙ ሲጀምር ግን ይሄ ሁሉ ተቆርቋሪ መስሎ መታየት ፈላጊ እስከዛሬ የት ነበር? ብያለሁ፡፡
ሌሎችንም የት ነበሩ አስብሏል፡፡ እውነት ለህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በፊት ኧረ!…የወገን ያለህ ይህን ያህል ዜጋ አለቀ ስንል ምነው ምላሽ የሚሰጠን ጠፋ? አንድ በሉ፡፡ ይህን ያህል ዜጋ ታፍኗል፣ 14 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሀረጥ የሚባለው ካምፕ ውስጥ ታጉረው ወደሀገር የሚመልሰን ጠፋ ሀገራችን መልሱን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወጡ ድረስ በርሃብ ሲቆሉ…ሲረግፉ መልስ መቼ ሰጡ? ሁለት በሉ፡፡ በስንት ሺህዎች በየጎዳናው እስኪረግፉ ቀባሪ አጥተው በየመንገዱ ወደቁ ኧረ የሰሚህ ያለህ ስንል ዝምታው ለምን ነበር?

አሁንም ይሄ ሁሉ አታሞ ድሰቃ እውነት ለስደተኛው ሊሰራ ታስቦ ከሆነ አልረፈደም፡፡ ግን ከልብ አለመለቀሱ እነሱ ውይይት ብለው በተቀመጡበት ቀን እዚህ የመን ውስጥ ስንቶች በአፋኞች መከራቸውን እየበሉ ነው? ስንቶች ተደብድበው አካላቸውን አጥተዋል? እውነት ድንበሩ ከተዘጋ በዚህ ሳምንት ብቻ ወደ የመን የተሻገረው ህዝብ ብዛት በሺህዎች መሆኑ እና የIOM (ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት) ሰራተኞች ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆኑን ማሳወቃቸው ምን ያሳያል፡፡ ዛሬም እየተዋሸ ፖለቲካዊ ድስኮራ መሆኑን አያሳይም? ተሰብስቦ ከማውራት ወደ ተግባር መሸጋገር ነው የሚያስፈልገው፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ጭርስ አንዳንዶች ዛሬም የሚያወሩትን የሚያውቁ ሆነው አልታዩም፡፡ ስለቻይና እድገት ባልተያያዘ መልኩ የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ብዙ አወሩ፡፡ ባለ ሁለት ዲጂት ተከታታይ እድገት አስመዘገበች በተባለው ኢትዮጵያ ድህነት የለም ለማለት ሞከሩ፡፡ በድህነት አይደለም የሚሰደዱት አሉንም፡፡ እግዚአብሄር ይስጣቸው አንባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሆዳቸው ብለው የአይጥ ምስክር…ያስባሉንን እውነቱን ነገሯቸው፡፡ ሁለቱን ነጣጥለን አንመልከት ድህነት አይደለም ያሰደዳቸው ማለት ስህተት ነው አሉም፡፡ የውይይት አቅጣጫውን ግንዛቤ በማነስ ስደት እንደሚወጣ ለማድረግ የሞከሩ ሰዎች በዝተው መታየታቸውና እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ መሆናቸው መናገራቸው ደግሞ ድራማውን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ጥናት ቢያደርጉ እውነት ይሄን ነበር የሚናገሩት? ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ቢያገላብጡ የውጭ መገናኛ ብዙሀንን ቢከታተሉ እንኳን ችግሩ ገብቷቸው ይናገሩ ነበር፡፡ ግን ባልሰሩት፣ ባላዩት ጥናት አቅራቢ ሆነው ለተከራከሩት ሰዎች አንድ እውነት አስረግጬ ልነግራቸው ወደድኩ፡፡

እህቷ ሞታ በተሰጣቸው ገንዘብ ሌላኛዋ እህቷ ሄደችበት ብሎ ግንዛቤ ማጣት ነው ያለው ጥናት አቅራቢ በምን አስቦት ነው፡፡ ሲዋሽስ በልክ ቢኮን ምን አለበት ከአረብ ሀገር ሞተው ሬሳ ሲገባ ወይም መቀበራቸው ሲነገር ገንዘብ የሚሰጠው ማነው መንግስት፣ አረቦቹ ወይስ ራሱ ከኪሱ ሰጣቸው..ይሄ ራሱ የግንዛቤ ማጣት ነው፡፡ ቢያውቅ እንዲህ አይነት ውሸት አይዋሽም ነበር፡፡ ሊቢያ በጋዳፊ ቤተሰቦች እንደዛ ለሆነችው መሰረት..ሉብናን በአደባባይ ከቆንስላው በር ላይ ተወስዳ ለሞት የተዳረገችው አለም ደቻሳ መገናኛ ብዙሀን የዘገቡላት እንኳን ቢሳቤስቲን አላገኙም፡፡

እሺ ጥናት አድርጌያለሁ ባዩ እንዳለው ይሁን (ውሸቱን እውነት እንበለው)እና የሟች እህት ግንዛቤማ በደንብ አገኘች በእህቷ ሞት ተማረች፡፡ ግን ችግር ሲፎክታት መጻኢው ጨለማ ሲሆንባት ርሃብ ሲዘምትባት ብሞትም ልሙት ያስባላት ችግር፣ ረሀብ መሆኑን እንዴት አይታሰብም? ‹‹ረሀብ ስንት ቀን ይሰጣል..›› የሚለውን የሎሬየት ፀጋዬ ግጥም ማሰብም ያስፈልጋል፡፡

ግንዛቤ ማጣትም ሆነ ገንዘብ ማጣት ሁለቱም ደህነት ነው፡፡ ስደት በየትም አልነው በየትም አሽሞነሞነው ስደት ድህነት ነው፡፡ ድህነት ደግሞ የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው፡፡ ሰላም አጥቶ መብቱ ተረግጦ የሚሰደደው ኪሱ የዳለበውም ቢሆን የሰላም ደሀ ሆኖ ነው፡፡ ሌላ ታፔላ መለጠፉም ሆነ ማሽሞንሞኑ ስደትን አያጠቁረውም አያቀላውም፡፡ ጥናት አጥንተናል ባዮችም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ነውና ይልቅ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቡ…ህገ-ወጥ ደላሎች ያላቸውን ተዋረድ እና ሰንሰለት መናገሩ ብቻ ምን ፋይዳ አለው፡፡ እዚህ የመን ያለ ኤምባሲ ስንት የሚያዙትን ህገ-ወጥ ደላሎች ሲፈቱ ዝም ከማለት ውጭ ምን አደረገ? አሁን በቅርቡ ያየነው እንኳን ስልሳ ኢትዮጵያዊያንን አፍኖ የተያዘ ሰው ሲፈታ ዝም አይደል ያሉት ያውም ከነደበደባቸው 60 ልጆች ተይዞ እሱ ወጥቶ ልጆቹ ታስረው ቀርተዋል፡፡ አሁንስ ቢሆን በየመን ህገ-ወጥ አጓጓዦች ከኤምባሲው ምን ደረሰባቸው ገብተው ይወጣሉ፡፡ እጅና ጓንት ናቸው፡፡

ብቻ ሁሉ የይምሰል ነው፡፡ እውነቱን አሁንም ያለውን በተከታታይ ለማሳየት እሞክራልሁ፡፡እዚሁ ፌስ ብክ ላይ ይህን በተመለከተ ሰፍሮ ያገኘሁትን ሁልተ ፅሁፍ እነሆ…

1…. “ጩኸቴን ቀሙኝ”

ሰሞኑን ETV ሰለስደት ፕሮግራም ማስተላለፉን ተያይዞታል በቃ የኛ መንግስት ሁሉ ነገር ለፓለቲካ ጥቅም እንጂ ለሀገር:ለህዝብ ተብሎ የሚሰራው ነገር የለም ማለት ነው ?
የተለያዩ ሰዎች የኢትዮጵያዊያንን የስደት ስቃይ በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ሰሚ አጥተው እንደውም ያን በመግለጻቸው የመንግስት ተቃዋሚ እየተባሉ በየመንግስት ባለስልጣኖች ማስፈራሪያ ሁሉ ይደረግባቸው ነበር ታዲያ ዛሬ ምን ተገኘና ነው መንግስት የህዝብን ጩኅት መልሶ ለህዝብ የሚያሰማው ?

ይህ ነገር ችግሮቹ ብዙ ቢሆንም የችግሮቹ መንሴዎችን የአንበሳ ድርሻውን የሚወስደው ያው የራሱን እንጂ የህዝቡን ድምጽ አልሰማም ብሎ ያስቸገረው መንግስት ነው :: ሁሉን ነገር ያበላሹ እና ሲበቃቸው ይሁን ወይም ለፓለቲካ ፍጆታ ለማዋል ሲሉ ያው የተለመደው በETV ሰዎቹን ሰብስቦ ለቅሶ ይቀመጣል:;ይህ ከዚህ በፊት ለሞተው ለተሰቃየው ምን ይጠቅመዋል ? መንግስታችን ከዚህ በፊት ሰዎች ሲጮሁ ለምን ለመስማት አልፈለገም? አሁንስ እውነት እርምጃ ለመውሰድ ነው ወይስ ያው እንደተለመደው ለፓለቲካ ፍጆታ ለማዋል ብቻ ? ለምን በህዝብ ይሾፋል ግን ? እያንዳዳቸው መሪ ቦታ ላይ ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስተሩ (ነኝ ካሉ) ጀምሮ ይህን ችግር ከዚህ አራት እና አመስት አመት በፊት ያውቁታል መፍትሄ ለመፈለግ አይደለም ችግራችንን (የስደተኞችን) ሰምተው ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር ለ ETV ሲሆን ግን ዶክመንተሪ ሰርተው ለቀቁልን ? ልክ ዘፋኞቻችን ነጠላ ዘፈን እንደሚለቁት ማለት ነው :: የተውሰነ ቀን ይሰማ እና ይረሳል ! እስቲ ሌላው ቢቀር በየሀገሩ ያሉ ኤምባሲዎች የመንግስትን ተቃዋሚ ከሚያሳድዱበት ጊዜ በጣም ትንሹን 3/4 እንኳን የዜጋቸውን መብት የሚከበርበትን ሆኔታ ያመቻቹ ነገሮች በ ETV ሰለቀረበ ተቀረፈ ማለት አይደለም እውነት ችግሩን ለመቅረፍ ታሥቦ ከሆነ በየሀገሮቹ ካሉት ዜጎች ጋር የሚወያይ ልዕኳን ያስፈልጋል ለገንዘብ መሰብሰብ ሲሆን ልዕኳን ሳይሆን ልዕኳኖች ነው የሚላከው :: ይቅርታ በንዴት መንፈስ ነው የጻፍኩት ከዚህ በላይ ብጽፍ መጥፎ ስለሆነ እዚሁ ላይ ላብቃ ከተረጋጋሁ እቀጥላልሁ ለማንኛውም ግን ዘግይቶም ሆነ ለፓለቲካ ፍጆታ ETV ይህንን ዝግጅት በማቅረቡ መንግስታችን ባይማር እንኳን ህዝቡ የሚማረው ነገር ሊኖር ይችላል እና እናመሰግናለን ::

2………ማፈሪያ የሆነው ETV ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚል ዶክመንተሪ የሚመስል ነገር አሳይቶናል፤በጣም የሚያሳዝን ነው።ስለ ወገንም የማያዝን ልብ የለንም።ነገርግን ይህ ስርሃት አልበኛ መንግስት ያወጣው ወገንን የመፍጀት ስትራቴጂ አንዱ አካል ይመስለኛል፤ለወገን ተቆርቓሪም ሆኖ አይደለም ይህንን ዶክመንተሪ ያሳየን።
ወገኖቻችን ለምንድነው ለዚህ አደጋ ራሳቸውን የሚያጋልጡት?
ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለምን ይህን አደጋ ይጋፈጣሉ?አማራጭ ማጣት ነው።
ህዝቡ ተስፋ እንደቆረጠ ያሳያል፤እንጂ ወያኔዎች እንዳሰቡት ምንም ትርፍ አያመጣም።
ምነው በየአረብ አገራቱ ከደረሱ በኇላ እንኯን ቆንስላ ፅ/ቤት ሄደው አቤቱታቸውን እያሰሙ ለ3ናለ4 ቀናት በየቆንስላው በር ላይ ተቀምጠው የሲሚንቶ ቅዝቃዜና ውርጭ ሲፈራረቅባቸው እያዩ አላየንም ነበር ሊሉን አስበው ይሆን?
ታዲያ አሁን አዝነናል ለማለት በምን ሞራል ነው የሚነፋረቁት?

የሰባአዊ መብት ድርጅቶች፡ የሃይማኖት አባቶች፡ ምሁራን እና የካናዳ ፓርላማ አባላት የተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች የፖልሲ አማራጮች አቀረበ (ሽንጎ)

ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ

ኢትዮጲያ የማን ናት? ከኤደን መስፍን(ኖረዌይ)

$
0
0

እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጾ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደትቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ከህብረተሰብ ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆኑ፣ በሕዝብ ይሁንታ ስልጣን የያዙ መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በቤሔራዊ ስሜት የታነፀ በሃገሩ ጉዳይ የማያመነታ ህብረተሰብ ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን መሪዎች ግን እንኳን የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የሕዝብን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ መብቱን ገፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አርገዋታል፡፡

በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊ የሆነ የመብት ጥሰትን የተቃወመ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ ሃገር ሲቸበቸብ ኢትዮጲያ የኢትዮጲያዊያን ነች ብለው የተቃወሙትን፣ የእምነት ነፃነታቸውን አናስነካም ብለው በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁና በሌላም ሃገራው ጉዳይ ላይ እንደ ዜጋ ይመለከተናል ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ የተማረውን ክፍል ስም እያወጡ በየማጎሪያው በእስር በማሰቃየትና ገሚሱንም በማሳደድ ኢትዮጲያ የምንላትን የሁላችን የሆነች ታላቅ ሃገር በሞኖፖል በመቆጣጠር የአንድ ግለኛ ቡድን የግል ሃብት አረገዋታል፡፡

ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ለሃገርና ለሕዝብ የተሻለ ሃሳብ አለን የሚሉትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችን ጨምሮ የሞያ ስነምግባራቸውን ጠብቀው አምባገነኑ ስርዓት በሕዝብና በሃገር ላይ የሚፈፅመውን ግፍና በደል በብእራቸው ያጋለጡ ጋዜጠኞችን በጅምላ ለሱ የሚመቸውን ስም እያወጣለቸው በየማጎሪያ ካምፑ የወረወራቸው እጅግ ብዙ የህሊና እስረኞች አሉ፡፡ ከህፃን ልጁ ተለይቶ በእስር የሚማቅቀው እስክንድር ነጋ፣ እውነት በመፃፏ ከነህመሟ በእስር የምትማቅቀው እርዮት አለሙ፣ በዘረኛው ቡድን ላይ የሰላ ሂስ በማቅረቡ በአሸባሪነት ተፈርጆ በእስር የሚሰቃየው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ እንዲሁም በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳን ጨምሮ ብዙ ምርጥ የሃገር ልጆች በዚህ ዘረኛ ቡድን ግፍ እየተፈፀመባችው ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ በተለይ በሃገር ቤት ያለው የበደሉ ገፈት ቀማሽ የሆነው ወገን ለለውጥ ጥግ ድረስ ለትግል አልተዋቀረም፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚተው አይደለም የልቁኑም ወያኔን ለመታገል ቆርጠው ከሚሰሩ የህዝብ ሃይሎችን በመቀላቀል ትግሉ የሚጠይቀንን ሁሉ የምንሆንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡

ኢትዮጲያ የነማን፣ የማን እንደሆነች ማወቅ የሚቸግርበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ጥቂት ዘረኛ ቡድኖችና ሆድ አደሮች የነገሱባትና ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የቅንጦት ኑሮ የሚኖሩባት፣ ብዙሃኑ ለሃገርና ለዳር ድንበሩ መከበር ከጥንት ጀምሮ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍስሶ ባቆያት ሃገር ላይ የበይ ተመልካች ሆኖ በርሃብና በእርዛት በሚኖርባት ሃገር ናት፡፡

እናም ይህ ዘረኛ የወያኔ ስርዓት እንዲያበቃለትና ዘመን እንዳይሻገር እነሱ እንደሚሉን ጥቂቶች(ኢምንቶች) ሳንሆን እልፍ አእላፍ ሆነን ለነፃነታችን፣ ለሃገራችን አንድነትና ለወደቀው ክብራችን ብለን በአንድነት እንነሳ፡፡ ኢትዮጲያ የኛ የብዙሃን እንጂ የጥቂት ዘረኛ ቡድን መፈንጫ አትሁን!!!!!!!!!!
ኢትዮጲያን እግዚሀብሔር የባርክ!!!!

የአባይ ወንዝ ህዳሴ ግድብ ትርፎች፤ ቦንድ፣ ዕዳ፣ አፈር መዛቅ፣ የጦር ዛቻ በዘውገ ፋንታ

አባ ማትያስ : “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም” – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ « ..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል…የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል…ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።
..
አቶ ጌታቸው በቅርቡ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ወ/ስላሴ ከአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ በማድረግ እንደተበቀሏቸው ማወቅ ተችሏል። በጎንደር ተወልደው ያደጉትና በሰባዎቹ መጀመሪያ አመታት ሕወሐትን የተቀላቀሉት አቶ ጌታቸው በአብዛኛው አመራር « ጥሩ ሰው ነው፣ ላመነበት ነገር ወደኋላ የማያፈገፍግ..» ተብሎ እንደሚነገርላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። በሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ተተክተው በ1994ዓ.ም ወደስልጣን የመጡት ጌታቸው በተጨባጭ ሙስና ፈፅመዋል የሚል መረጃ እንደሌለ ያመለከቱት ምንጮቹ ነገር ግን በአብዛኛው ባለስልጣናት የሚፈፀመው መጠነ ሰፊ ዘረፋና ሙስና በተመለከተ በርካታ መረጃና ማስረጃ በጌታቸው እጅ እንደሚገኝ አያይዘው ገለፀዋል። በሌላም በኩል በ1994ዓ.ም በደህንነት ቢሮ የበታች ሹማምንት ሆነው በአቶ መለስ ከተመደቡት መካከል ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስና ወ/ስላሴ እንደሚገኙበት ያስታወሱት ምንጮቹ፣ አክለውም ሁለቱ የሕወሐት አባላት ከስር ሆነው ፈላጭ ቆራጭ አመራር ይሰጡ እንደነበረና በዚህ ተግባራቸው ከጌታቸው ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸውን አስታውቀዋል። ኢሳያስ ከአቶ መለስና ስብሃት ጋር ስጋ ዝምድና እንዳለው ማወቅ ተችሏል። በተለይም በዚህ ጣልቃ ገብ አሰራር ተማረው የቆዩት አቶ ጌታቸው ከቅርብ አመት ወዲህ ከአቶ መለስ ጋር ጭምር አለመግባባት ፈጥረው እንደነበረ ሲታወቅ፣ አቶ መለስ የጤና ችግር ተፈጥሮቦቻው እንጂ በዛው ወቅት ከስልጣን ሊያነሷቸው ከወሰኑት ባለስልጣናት አንዱ ጌታቸው እንደነበሩና ከመለስ ህልፈት በኋላ የደህንነቱ ሹም የታቀደባቸውን እንደደረሱበት ምንጮቹ አስታውቀዋል። የጠ/ሚ/ሩን ህልፈት ተከትሎም አቶ ጌታቸው ስልጣናቸውን በማደላደል ጎልተው መውጣቸውንና በወ/ስላሴ ላይ የወሰዱት እርምጃ ማስረጃ እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአቶ ጌታቸው ወንድም ዳንኤል አሰፋ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል ተደርጎ ባለፈው ጉባኤ መመረጡ ሲታወቅ፣ የዳንኤል ባለቤት የስብሃት ነጋ ዘመድ እንደሆነች ተጠቁሞዋል።

ከስልጣን የተነሳው ወ/ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን እንደሚታወቅ ያስታወሱት የቅርብ ምንጮቹ « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው ብለዋል። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር – እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አስታውሰዋል። ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አዜብ መስፍን በቅርቡ ቨርጂኒያ መጥተው እንደነበረ ምንጮች ገለፁ። ድምፃቸውን አጥፍተው የመጡት አዜብ በተጠቀሰው ከተማ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ የገዙት መኖሪያ ቪላ ውስጥ ለጥቂት ቀናት እንደቆዩና ወደአገር ቤት እንደተመለሱ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ከቪላው ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎች እየተጠናከሩ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።


“ሕልምና ቅዥት” ክፍል ፪. የጐንቻው!

ጎንደርና ደሴ ተነሱ –መግለጫ ከአንድነት ፓርቲ

$
0
0

ሐምሌ 7 በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፉ!!

ድምፃችሁንም በአደባባይ አሰሙ!!
————————————————————–
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት)
የተሰጠ መግለጫ
————————————————————–

ፓርቲያችን አንድነት ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፓርቲ በመሆኑ የሚያደርጋቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ኃላፊነት በተሞላበት ህጋዊ አግባብ ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት/Millions of voices for freedom” በሚል መሪ ቃል የጀመረውም ህዝባዊ ንቅናቄ የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ያነገበ ነው፡፡

የአንድነት ፓርቲ ህዝባዊ ንቅናቄ አካል የሆኑ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በሚካሄዱባቸው ከተሞችም ስለሰልፉ ማወቅ ለሚገባቸው መንግስታዊ አካላት ህጉ በሚጠይቀው መሰረት በወቅቱ አስፈላጊው የማሳወቅ ኃላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል፡፡ የኢህአዴግን መንግስት አንድነት ፓርቲ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ማግኘቱ አስደንግጦታል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በየክልሉ ያሉ የመንግስት መዋቅሮችን በተለይም የፀጥታውን ዘርፍ በመጠቀም ህዝባዊ ንቅናቄያችንን በህገወጥ መንገድ ለማደናቀፍ መንቀሳቀሱ ነው፡፡

ፓርቲያችን ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማደረግ ቢያቅድም መንግስት የሰልፉ ቀን እንዲተላለፍለት አሳማኝ ጥያቄ በማቅረቡና ይህንንም ህግ ስለሚፈቅድለት ሰልፉን ለሐምሌ 7 , 2005 ዓ.ም አስተላልፏል፡፡ ኢህአዴግ ግን በአንፃሩ በጎንደር ከተማና በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ 9 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን በህገወጥ መንገድ እንዲታሰሩ አድርጓል፤እነዚህ አባላት እስከ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ወደ ሐምሌ 7 የተላለፈውን ሰልፍም ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡

አንድነት የሰጣቸውን የቅስቀሳ ተልዕኮ በመወጣት ላይ ያሉ አመራሮችንና አባላትን የማዋከብና የማገት ተግባር ተፈፅሟል፡፡ በተለይም አርብ ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በመክበብ በርካታ አባላት የታገቱ ሲሆን ፖሊሶችም ከህግ አስከባሪ አካል በማይጠበቅ ሁኔታ ከፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረባ ላይ ካሜራ ነጥቀዋል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሰራተኞች የጎንደር ነዋሪ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዳይሳተፍ ቤት ለቤት በመዞር ቀስቅሰዋል፡፡

በደሴና በሀይቅ ከተሞችም የአንድነት አመራሮች በተደጋጋሚ እገታ የፈተፀመባቸው ሲሆን የትራፊክ ፖሊሶችም መደበኛ ስራቸውን በማቆም በመኪና የሚደረገውን ቅስቀሳ በተደጋጋሚ አደናቅፈዋል፡፡

የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሰራተኞች የደሴ ነዋሪ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዳይሳተፍ ቤት ለቤት በመዞር ቀስቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም በድንገት የስፖርት ዝግጅት እንዳለ በማወጅ ወጣቶችና የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ላይ እንዳይሳተፉ ለማከላከል እየተሞከረ ይገኛል፡፡ በደሴ ከተማ የተለጠፉ ፖስተሮችን የመቅደድና በጭቃ የማበላሸት ድርጊትም ተፈፅሟል፡፡

ኢህአዴግ በጎንደርና በደሴ የሚደረገውን የቅስቀሳ ስራ በማደናቀፍ ሰልፉ እንዳይካሄድ ቢሞክርም የከተሞቹ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች ከአንድነት አመራሮችና አባሎቸ ጎን በመቆም ቆራጥነታቸውን ማሳየታቸውን እናደንቃለን፡፡

አንድነት ይህን ሁሉ የኢህአዴግን ህገወጥ እርምጃ ተቋቁሞ በነገው እለት በጎንደርና በደሴ ከተሞች የጠራቸውን ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በቆራጥነት ለማካሄድ በያዘው አቋም ፀንቷል ፡፡ በመሆኑም መላው የጎንደርና የአካባቢው እንዲሁም የደሴና የአካባቢው ነዋሪዎች እስከአሁን እያሳዩ ባሉት ቆራጥ ፀንተው በነገው እለት በሚደረጉት ሰልፎች ላይ እንዲሳተፉ አንድነት ፓርቲ በድጋሚ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ በሁለቱም ከተሞች ለሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ ነዋሪዎች አበባና ሌሎች ወዳጅነትን የሚያንፀባርቁ ስጦታዎችን በየመንገዱ ለሚያገኟቸው ፖሊሶችና የፀጥታ አስከባሪዎች እንዲያበረከረቱና ወዳጃዊ ሰላምታ እንዲሰጡ እንጠይቃለን፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአገዛዙ ካድሬዎች የወረደ ተግባርን ይመልከቱ !

$
0
0

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም

የአገዛዙ ካድሬዎች ላለፉት በርካታ ሳምንታት የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለዉን ሰላማዊና ሕዝባዊ ቅስቃሳ ከግቡ እንዳይደርስ ለማድረግ፣ በአለቆቻቸው ታዘው የተለያዩ የአፈና እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበረ በሰፊት ተዘግቧል። በርካታ ታሰረዋል፤ ወከባና እንግልትም ደርሶባቸዋል።

ነገር ግን የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች እንደዉም ሕዝቡ እግዚአብሄር የሰጣቸውን የዜግነት መብት ለማረጋገጥ ቀርተዉ የተነሱ ይመስላል። አፈናዉ የበለጠ እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሕዝቡን ድጋፍና መነሳሳትም ወደ ላይ ሄደ እንጂ አልቀነሰም።

ሕዝቡ እያሳየ ባለው ታላቅ ተነሳሽነት ተስፋ የቆረጡ የአገዛዙ ካድሬዎች የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች የሚለጥፋቸውን ፖስተሮችና መፈክሮች በማንሳትና በመቀዳደድ ጸረ-ዴሞክራሲያዊና ጸረ-ሕዝብነታቸውን እያሳዩ ነዉ። አንዳንድ ፖስተሮች አልቀደድ ሲላቸው ደግሞ፣ በላዩ ላይ ጭካ እስከመቀባት የደረሱበት ሁኔታም አለ።

በኢሕአዴግ ካድሬዎች ጭካ የተቀባ የአንድነት ፖሶተር ይመልከቱ !

dirty_work_of_cadresjpg

መመሪያ ለጎንደር እና ደሴ ከተማ ነዋሪዎች –የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል(አንድነት)

$
0
0

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም

“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የሚል መሪ ቃል በማንገብ ዕሁድ በሚካሄደዉ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ ሁሉም ተሳታፊ የሚከተሉትን ተግባራት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

to_dessie_and_donder_people

1. ሰልፉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ፡፡ የተለያዩ ትንኮሳዎች ቢፈታተኑንም እንኳን ሰልፉ ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ እና ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ማካሄድ ይገባል፡፡ አንድ ጠጠር እንኳን ፍፁም መወርወር የለበትም፡፡

2. የተመረጡ መፈክሮችን ብቻ ማሰማት

3. በሰልፉ ወቅት አላስፈላጊ ተግባር የሚፈፅሙ ካሉ ማጋለጥ

4. ስድብን እና አላስፈላጊ ቃላትን ከመጠቀም መቆጠብ

5. የቻልን አበባ (ይህ የበለጠ ይመረጣል) ያልቻልን አረንጓዴ ቅጠል ይዞ ከቤት መዉጣት ፤ በሰልፉ ላይ ከፍ አድርጎ ማዉለብለብ፡፡ ሰልፉ ሲጠናቀቅ የያዝነዉን አበባ ወንድሞቻችን ለሆኑት የፀጥታ አስከባሪዎች/ፖሊሶች የፍቅራችን መግለጫ እንዲሆን በገፀ-በረከትነት ማበርከት፡፡

6. የሚቻል ከሆነ ነጭ ልብስ መልበስ

7. አንድ እጅን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ሦስት እጣቶችን ማሳየት

8. በማንኛዉም አካል አላስፈላጊ/አፍራሽ ተግባራት ሲፈፀሙ ስናይ ለመረጃ እንዲሆን ፎቶ ማንሳት እንዲሁን በቪዲዮ መልክ መቅረፅ

9. ሰልፉ ሲጠናቀቅ በሰላም ወደ ቤት መመለስ

ፍኖተ ነጻነት –የደሴ ትራንስፖርት ህዝብ እንዳያመላልስ ተደረገ

$
0
0

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም

በደሴ አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች(ከወረባቡና ሐይቅ)፣ በነገው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ወደ ከተማይቱ ለመምጣት ትራንስፖርት ያስፈልጋቸው የነበሩ ዜጎች፣ በከተማው አስተዳደር ስውር ትዕዛዝ መሰረት፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የትራንስፖርት መኪኖቹ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መታዘዛቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሰልፉ አዘጋጆች በመደወል እየገለጹ ነው፡፡

ሁኔታው ያሳዘናቸው ሰዎች በቻሉት መንገድ ሁሉ ወደ ሰልፉ በመምጣት ድምጻቸውን እንደሚያሰሙና መሰናክሉን እንደሚያልፉት አስታውቀዋል፡፡

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>