Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ሰበር ዜና አንድነትና መኢአድ መጋቢት 11 የቅድመ ውህደት ፊርማ ሊያደርጉ ነው

$
0
0

የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትእና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የሁለቱ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ መመሪያ ያስተላለፉት ሁለቱን ፓርቲዎች ፓርቲዎች ለማዋሀድ እያሸማገሉ የሚገኙ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች የተካተቱበት ኮሚቴ ያቀረባቸው የማስማሚያ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ እና የሁለቱም ፓርቲዎች ፕሬዘዳንቶችና የውህደት ኮሚቴ አባላት ውህደቱ የዘገየበትን ምክንያት ከዘረዘሩ እንዲሁም የሁለቱ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይትና የመፍትሔ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡ የቅድመ ውህደት ፊርማው በሚፈረምበት ዕለት ሁለቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ሂደት የሚያመቻቹ ወኪሎቻቸውን እንደሚያሳውቁም የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘግቧል፡፡


አቡጊዳ –የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ሊዋሃዱ ነው

$
0
0

በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ጠንካራ ፓርቲ ይባሉ የነበሩት መኢአድ እና ኤዴፓ ነበር። ሁለቱን ፓርቲዎች የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት እና የመኢአድ ላዕላይ ምክር አባላት ቤት መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ፣ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ፍኖት ነጻነት ዘገበ።

በምርጫ ዘጠና ሰባት ከመደረጉ በፊት የፓርቲዎች ዉህደት ተፈጽሞ እንዳልበረ ይታወቃል። ምርጫዉ ከመደረጉ ከስድስት ወራት በፊት ብቻ ፣ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ ሸምጋይነት በወቅቱ ጠንካራ የነበሩት መኢአድ እና ኤዴፓ ፣ ዉህደት ሳይሆን ለምርጫዉ ዘመቻ ወቅት እንዲቀናጁ መደረጉ ይታወሳል። ቅንጅቱንም ከምርጫ በኋላም ወደ ዉህደት ለማሸጋገር የተሞከረው ሙከራም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱ የሚታወቅ ነው።

አሁን በመኢአድ እና በአንድነት ሊደረግ ያለው ዉህደት፣ ከሁለት አመታት በላይ ፣ በርጋታና በጥንቃቄ ሰፊ ዉይይቶች እንደተደረገበት የገለጹት ያነጋገርናቸው የአንድነት አመራር አባላት፣ የዉህደቱ እንቅስቃሴ ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ እንደሆነ ይናገራሉ። «በቅንጅት ጊዜ ከላይ ወደ ታች ነበር ዉህደቱን ለማድረግ የተሞከረው። አሁን ግን ካለፉት ስህተቶች በመማር መቀራረብኑና የዉህደት እንቅሳሴ የተጀመረዉ በወረዳ ደረጃ ነው» ያሉት የአመራር አባላቱ፣ ለዚህ ቀን መደረሱ በዋናነት ምክንያት የሆኑት ከታች ያሉ የመኢአድ እና የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደሆኑም ለማሳየት ሞክረዋል።

የአንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ሌላ ለሰማያዊ፣ ለአረና፣ ለኢዴፓም ሳይቀር አብሮ የዉህደት አሊያም የትብብር ጥሪ ማቅረቡ በስፋት የተዘገበ ነው። የአረና ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ጋር የመዋሃድ ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ በዉህደቱም ረገድ ዉይይቶች እየተደረጉ እንደሆነም ይታወቃል። የሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ በፊት የነበሩ ተምክሮዎችን ከግምት በማስገባት፣ ነገሮችን በርጋታ ለማየትና ለጥንቃቄ ሲሉ፣ ለጊዜዉ በተናጥል መንቀሳቀሱን የመረጡ ቢመስልም. የአመራር አባላቱ ሰማያዊ ፓርቲ የአገርን ጥቅም ከሁሉም በላይ እንደሚያስቀድምና፣ ተባብሮ በመስራት እንደሚያምን ይናገራሉ።

ሌላው በተወሰኑ ክፍሎች የአገዛዙ ተለጣፊ ተደረጎ የሚቆጠረው ኢዴፓ አመራርም ፣ በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ያደረጋቸው የፖለቲካ ፕሮግራሞቹና አቋሞቹ በብዛት ከአንድነት ፣ መኢአድ ካሉ ጋር እንደሚቀራረብ በመገልጽ፣ የኢሕአዴግ የዘር ፖለቲካን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣን፣ ሙስናን የመሳሰሉት አጥብቆ ሲቃወሙ እንደነበረና እንደሚቃወሙም ይናገራሉ። በቅርቡ በሰንደ ጋዜጣ ላይ እንደተዘገበው የኢዴፓን የኢዴፓን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ወጣት ኤርሚያስን ፣ ፓርቲያቸው በቅርቡ ጉባኤ አድርጎ አዲስ አመራር በመረጠበት ወቅት ጉባኤው ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በ1997ቱ ምርጫ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረምና ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለአዴፓ የፖለቲካ እውቅና የሚሰጡ ከሆነ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁነት መኖሩን አስታውቀዋል።

የሚሊዮኖች ድምጽ –ቃሌ እና ደብተራው ቁጫንና ድሬደዋን ስፖንሰር አደረጉ !

$
0
0

በደቡብ ክልል፣ በጋሙ ጎፋ ዞን የምትገኝ ወረዳ ናት። ወደ 150 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ አላት። በዚያ ያሉ ገበሬዎች ከሚያርሱበት ቦታ በግድ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉ በተጨማሪ፣ ብዙዎች ያታሰሩባት ወረዳ ናት። የቁጭ ወረዳ ትባላለች። dire_kucha

በአንድነት ፓርቲ አነሳሽነት ለሕዝብ የፋ የሆነው የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ትኩረት ከሰጠባቸው ወደ አሥራ የሚሆኑ አካባቢዎች አንዷ ቁጫ ናት። በቁጫ ሊደረግ የታሰበዉን ትእይነተ ሕዝብ በመደገፍ፣ በዚያም ለሚኖረው የተገፋዉ ሕዝብ ሶሊዳሪቲ በማሳየት የቃሌ ፓልቶክ ክፍል ፣ የቁጫን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ እንደሚሸፍን እና ስፖንሰር እንደሚያደርግ ይፋ አደርጓል።

ሌላዋ የሚሊይን ድምጽ ዘመቻ የሚደረግባት ከተማ፣ የኢትዮዮጵያ ሁለተኛ ከተማ የሆነችዋ አንጋፋዉ ድሬዳዋ ናት። የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍል ፣ ድረደዋን ስፖንሰር እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።

የቃሌ እና የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍሎች ከአለም ዙሪያ ሁሉ የተሰባሰቡ ፣ በኢንተርኔት ፓልቶክ አፕሊኬሽን ፣ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ዘወተር የሚመካከሩ፣ የአገራቸው ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት ክፍሎች ነው።

በኢትዮጵያ የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል፣ ስለተመኘንና ስላወራን ብቻ ዉጤት የሚያመጣ አይደለም። አገዛዙ ዘወትር ስለሚፈጽማቸው ግፎች ማዉራት አንድ ነገር ነው። እነዚህ ግፎች እንዲያቆሙና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ ማድረግ ሌላ ነገር ነው።

የቃሌና የደብተራው ታዳሚዎች ፣ ከዉይይት አልፈው፣ አገር ወዳድነታቸውን በተግባር በማሳየት፣ በሜዳ ፊት ለፊት አምባገነንነትን እየተጋፈጡ ያሉ ጀግኖችን በቁጫና በድሬደዋ በመደገፍ የሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ነው።

የቃሌና የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍሎች ለወሰዱት አኩሪና አገር ወዳድ አቋም ያለንን አድናቆት እየገለጽን፣ የተቀረነዉ በየአካባቢያችን እየተሰባሰብን ትግሉን እንድንቀላቀል፣ከሚሊዮኖች አንዱ እንሆን ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

ትግሉን ለመርዳት፣ ለመደገፍ፣ ከሚሊዮኖች አንዱ ለመሆን የምንፈልግ ካለን በሚከተለው አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
millionsforethiopia@gmail.com

አቡጊዳ –የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል –ግርማ ሰይፉ

$
0
0

በአንድነት እና መኢአድ የዉህደት እንቅስቃሴ ላይ አስተያይተ የሰጡት የፓርላማ እና የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ምክር ቤቶቹ ይሄን ታሪካዊ ዉሳኔ ባሳለፉበት ወቅት የሚከተለውን ብለዋል፡

«ዛሬ በመኢህአድ ፅ/ቤት የመኢህአድ እና የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት የጋራ ስብሰባ አድርገው አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህውም ለቀጣይ ሐሙስ መጋቢት 11/2004 ዓ/ም የቅድመ ውህደት ሰምምነት እንዲደረግ እስከ አሁን ውህደቱን ለማዘግየት የተወሰደው ጊዜ ከበቂ በላይ በመሆኑ አጅግ አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ይህን ጉዳይ አጠናቆ የጋራ ጉባዔውን የሚያመቻች ኮሚቴም በእለቱ ይፋ እንዲደረግ ከስምምነት ተደርሶዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ውህድ በሚሆኑበት ወቅት ፈታኝ ይሆናሉ የተባሉ የፕሮገራም እና የደንብ ልዮነቶች የሚባሉት ውሕዱን ፓርቲ የተሻለ ደንብና ፕሮግራም እንዲኖረው ከማድረግ የዘለለ ውህደቱን ለማዘግየት ምክንያት እንዳይደሉ መግባባት ላይ ተደርሶዋል፡፡ የውህዱን ፓርቲ ስያሜ በተመለከተም ተሳታፊዎቹ በአዲስ መሆን እንዳለበት እና ይህም ተጠንቶ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ የሚወሰን እንደሆነ ግንዛቤ ተይዞዋል፡፡ ትልቁ ነጥብ የነበረው በሁለቱም ፓርቲዎች በኩል አመራሮች በምንም ሁኔታ ውህደቱን ለማዘግየት ቢሞክሩ አባላት ተዋሕደው አመራሮች ተንጠልጥለው እንደሚቀሩ በተደጋጋሚ የገለፁ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ጭብጨባ ድጋፍ አግኝቶዋል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ይህ ጉዳይ ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ እውን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል፡፡ ቸር ወሬ ያሰማን፡፡ የመጋቢት 11 ሰው ይበለን፡፡»

አቡጊዳ –በኑሮ ዉድነት ላይ በአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰልፍ ሊጠራ ነው !

$
0
0

የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው እንደሆነ የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ። «በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ መንግስት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለመጠየቅ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በማነቃነቅ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ መወሰኑን የዞኑ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ» ሲል ነው ፍኖት የዘገበው።

ይህ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ምክር ቤት የሚጠራዉ ሰልፍ፣ የአንድነት ፓርቲ ይፋ ካደረገው የአሥራ አራት ከተሞች የሚሊየንም እንቅስቃሴ የተለየና በተጨማሪ የሚደረግ ሲሆን፣ የሚሊየነም እንቅስቃሴ በመሬት ባለቤትነትና በፍትህ ላይ ያተኮረ እንደሆነ በስፋት የተዘገበ ነው።

የአዲስ አባበ የአንድነት ምክር ቤት፣ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎች መቃቅር ያለው ሲሆን፣ ከማእከላዊ ፓርቲ ዉጭ፣ በራሱ በርካታ እንቅስቃሴዎች የሚያደርግ ምክር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። ፓርቲዉ አባላትን በአዲስ አበባ እንዳደረጉት በራሳቸው አነሳሽነት ሰላማዊን ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እንደሆነ ብዙ ጊዜ አመራር አባላቱ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

አቡጊዳ –የ«ጥይቱ ልጆች» ከየካቲት 30 እስከ ዛሬ መጋቢት 9 የነበሩበት ሁኔታ

$
0
0

እመቤት ግርማ ( 18 አመት ወጣት)፣ ንግስት ወንዳፍራዉ፣ መታሰቢያ ስዩም፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ምኞት መኮንን በሩጫ ወቅት ሁከት ፈጥራችሁላ ተብለው ከታሰሩ «የጣይቱ ልጆች» መካከል የሚገኙ ናቸው።

የካቲት 30 2006 ዓ.ም
እሑድ ቀን ነው። በተዘጋጀው የሴቶች የ500 ሩጫ በርካታዎች ይሮጣሉ። ቢጫ ኬኔቴራ ለብሰዋል። ሩጫዉ እንደተጀመረ ድምጾች መሰማት ጀመሩ። የስድብ፣ የክፉ አይደለም። «የጣይቱ ልጆችን ነን፤ የሚኒሊክ ልጆች ነን፣ ለነጻነት ነው የምንሮጠዉ፣ እርቦናል፣ መብታችን ይከበር፣ የታስሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ …» የሚሉ ድምጾች። በሌሎች ሯጮች ላይ ጠጠር አልተወረወረም። የወደመ ንብረት የለም። መንገዶች አልተዘጉም። ሩጫዉ አልተስተጓጎለም። በሰላም ተጀመሮ በሰላም ነው ያለው።

run_women2

run_women1

ከመነሻው የእህቶቻችንን የነጻነት ድምጽ እያዳመጡ ሲክታተሏቸው የነበሩት የደህንነት ኃይሎች ሩጫውን እንዳለቀ በርካታ ሴቶችን አፍሰው ወደ ሾላ የካ ፖሊሰ መምሪያ ወህኒ ቤት ይወስዷቸዋል። ወንጀላቸው ምንድን ነው ? በአገራቸው ድምጻቸው ከፍ አደርገዉ የነጻነትን ድምጽ ማሰማታቸው።

ከታሳሪዎቹ መካከል ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ሲሆን ሌሎች ደግሞ የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው። ከሴትቹ ጋር አብረው የነበሩ ፣ ሴቶች ታፍሰው ሲወሰዱ ለምንድን ነው የምትወስዷቸው ያሉ ወንዶችም፣ «ለምን? » ብለው በመጠየቃቸውም አብረው ለእስር ተዳርገዋል።

መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም፡
እስረኞቹ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። መርማሪዎ ፖሊስ ኮማንደ ርየማታ ይባላሉ። « የተከሰሱበት ምክንያት እሁድ የካቲት 30 ቀን በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ላይ ተመሳስሎ በመግባት፣ “የጣይቱ ልጆች ነን ፣ የምኒልክ ልጆች ነን ፣ ኑሮ መረረን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ” በሚል ሁከትን ለማነሳሳት ቀስቅሰዋል። መረጃ አሰባስቤ ስላልጨረስኩ፣ መረጃዎቼን እንዳያጠፉብኝ፣ ሰዎችም እንዳይመሰክሩ እንዳያስፈራሩ፣ በተጨማሪም ብዙዎቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ስለሆነ፣ መረጃ እስካሰባስብ የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ» ይላል። ፍርድ ቤቱ ግን «አራት ቀን ይበቃቹሃል» በማለት ለመጋቢት 5 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጣል።

መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም፡
የሰማያዊ ወጣቶች የፍርድ ቤት ውሎ (ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው)

ባሳለፍነው ሳምንት ታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የሴቶች ውድድር ላይ በመሳተፍ ተቃውሞ በማሰማታቸው ለእስር የተዳረጉት ሰባት ሴቶችና ተባባሪ ተደርገው የታሰሩ ሶስት ወንዶች ዛሬ በነበራቸው ቀጠሮ መሰረት ቀበና በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡

ታሳሪዎቹ በአንድ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ የከረሙ ቢሆንም ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ያመጣው ወንዶቹን ነበር፡፡ሴቶቹ ለሰዓታት ዘግይተው በሩጫው ወቅት ለብሰውት የነበረውን ባለ ሙሉ ቢጫ ቀለም ቲ ሸርት እንደለበሱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ዳኛው ከተሰየሙ በኋላ ከሳሽን በመወከል የቀረቡ ሁለት ፖሊሶች ‹‹ምርመራችንን ባለማጠናቀቃችን ተጨማሪ የሰባት ቀን የምርመራ ግዜ ይፈቀድልን››በማለት ጠይቀዋል፡፡የተከሳሾች ጠበቃ(የጋዜጠኛ ርዕዮት ወላጅ አባት አቶ አለሙ ጎቤቦ) ፖሊስ ደምበኞቼን በእስር ለማቆየት ካለው ፍላጎት እንጂ ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለው በአደባባይ በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልገውም ስለዚህ ደምበኞቼ ጉዳያቸውን በውጪ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ያክብርልኝ››በማለት ተከራክረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመናገር እድል እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሲፈቀድላቸው ‹‹ሲቪል የለበሱ ሰዎች እየመጡ በሌሊት ጭምር ከታሰሩበት ቤት እንዲወጡ በማድረግ እንገድላችኋለን፣ከአሸባሪዎች ጋር መስራታችሁን አቁማችሁ አብራችሁን ስሩ፣በመጥረጊያ አናትሽን ብልሽ የሚደርስልሽ አይኖርም››የሚሉ ማስፈራሪያዎችን እንዳደረሱባቸው በመግለጽ ዋስትና ይሰጠን ሲሉ አቤት ብለዋል፡፡

ፖሊሶቹ በተከሳሾች የቀረበው ሐሰት መሆኑን በመግለጽ ‹‹ሴቶቹ ለምሳሌ ወደዚህ ለመምጣት የቆዮት የለበሱትን ቲሸርት እንዲለውጡ ሲነገራቸው እምቢ በማለታቸው ነው፡፡በመኪና ላይ ይጨፍሩ ነበር፡፡እስር ቤት ውስጥም ሌሎች እስረኞችን ያነሳሳሉ ››ብለዋል፡፡

ቲሸርቱ በፍርድ ቤት እንዳይለበስ ያልታገደ በመሆኑ መልበስ መብታቸው ነው ያሉት አቶ አለሙ ‹‹ደምበኞቼን ፖሊስ በፈለገው ጊዜ ሊያገኛቸው የሚችል በመሆኑ በእስር መቆየታቸው ተገቢ አይደለም››ብለዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጡት ዳኛው ‹‹ፖሊስ የእስረኞቹን መብት ማክበር ግዴታው ነው ስለዚህ የተባለው ነገር እንዳይደገም በማለት የዋስትና መብታቸውን ሳይጠብቁ ለፖሊስ ተጨማሪ አራት ቀን በመፍቀድ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ፖሊስ ጣብያ እንዲመለሱ አዘዋል፡፡

እስረኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ፖሊስ አሁንም ‹‹ምርምራውን አልጨረስኩም፣ ተጨማሪ የምይዛቸው ሰዎች አሉ፣ የተያዙትም ቢለቀቁ ሌላ ወንጀል ይሰራሉ›› በሚል ሰባት ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ይጠይቃል።

በአንጻሩ የታሳሪዎቹ ጠበቃ ሆነው የቀረቡት የጋዜጠኛ ርዕት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌደቦ በበኩላቸው ፖሊስ ተሰጥቶት የነበሩት ሰባት ቀናት መረጃ ለማሰባሰብም ሆነ ሌሎች የምይዛቸው ተጨማሪ ሰዎች አሉ ያላቸውን ቢኖሩ ኖሮ ለመያዝ በቂ እንደነበር አያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም ታሳሪዎቹ በኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሰሩና ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን መከታተል ስለሚችሉ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ይከርከራሉ።

ፍርድ ቤቱ እንደገና ለስረኞች የዋስትና መብት ከልክሎ መጋቢት 9 ቀን ፖሊስ ሁኡን ናገር አጠናኽሮ እንዲቀርብ ያዛል። እንደገና ተጨማሪ አራት ቀናት ለፖልሲ ተሰጠ።

መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም
እስረኞች እንደገና ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ፖሊስ ምንም መከራከሪያ ማቅረብ አልቻለም። እንደገና 14 ቀናት ይስጠኝ ብሎ ይጠይቃል። በፍር ድቤቱ ቁጥሩ እጅግ በርካታ ሰው አለ። መቀመጫዎቹ ሁሉ ሞልተው የቆሙ ብዙ ናቸዉ። በዉጭም በብዛት አሉ። የተለያዩ ዬምባሲ ተወካዮች፣ ጋዜጠኞችም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በቦታው አሉ። እስረኞቹ መጋቢት 1፣ መጋቢት 5 ቀን ቀርበው ፣ ፖሊስ ዝግጁ አይደለሁም በሚል ለመጋቢት 9 ተላልፎ ነበር። በመጋቢት 9 ፖሊሲ ስራዉን አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ መመሪያ ሰጥቶ ነበር። ነገር ግን መጋቢት 9 ቀን፣ አሁንም ፍርድ ቤቱ ሌላ ሰበብ በመስጠት ቀኑን አራዘመ። ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ ሲል ቀጠሮዉን ለነገ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም አስተላለፈ።

የነገዉን የፍርድ ቤቱ ዉሎ ዘገባው እንደደረሰን የምናቀርብ መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።

አቡጊዳ –ሰባቱ የጣይቱ ሴቶች እና ሶስቱ ወንዶች ከ11 ቀናት እሥር በኋላ ተፈቱ

$
0
0

ሰባቱ የጣይቱ ሴቶች እና ሶስቱ ወንዶች ከአራ አንድ ቀናት በዋስትና መፈታታቸውን ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ ዘገበ።
TAItu7
«በመደበኛ ፍርድ ቤት ክሴን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ በማለት ቀበና ለሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትናንት ጥያቄ አቅርቦ የነበረው ፖሊስ ዛሬ ማለዳ አስሩን ተጠርጣሪዎች ቀበና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡» ሲል የዘገበው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን «በወጣቶቹ ላይ ክስ ለመመስረት የሚበቃ ወንጀል አለመገኘቱን በመጥቀስ ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁ አቃቤ ህግ ለፖሊስ ምክር መስጠቱን የሰሙት ጠበቃ አቶ አለሙ ጎቤቦ ደምበኞቻቸው ያለ ዋስትና እንዲለቀቁና መዝገቡ እንዲዘጋ ቢከራከሩም ፖሊስ ክሴን እመሰርታለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው 1300 ብር እንዲሁም የአዲስ አበባ ቀበሌ መታወቂያ ያለው ሰው በማቅረብ በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል» ሲል በፌስቡክ ዘግቧል።

የጣይቱ ሰባቱ ሴቶች ተብለው የሚታወቁት ሰባቱ ኢትዮጵያዉያን እና ሴቶቹ በፖሊስ ሲያዙ ለምን ብለው የጠየቁት ሶስት ወንዶች፣ ከየካቲት 30 ጀምሮ በአጠቃላይ ለአሥራ አንድ ቀናት የታሰሩ ሲሆን በእሥር ቤት በነበሩም ጊዜ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ይናገራሉ።

ፍኖት –የአዳማ/ናዝሬት ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ

$
0
0

በአዳማ/ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ምርቱ ጉታ፣ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ገደማ በተለምዶ ዝቋላ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ መታሰሩን፣ የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡ WETAT_GUTTO

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፀው ዝቋላ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ የገበያ ስፍራው እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲያሰሙ የነበረውን ብሶት እንደዜጋ ለማዳመጥ ከሞከሩ የአንድነት አባላት መካከል ወጣት ምርቱ ጉታን አስረውታል፡፡

ወጣት ምርቱ ጉታ በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ 4 ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን፣ በአዳማ ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ለማሰራጨት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀትና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪቃል፣ በአዳማ የአንድነት ጽ/ቤት በወሩ መጨረሻ ለሚዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የፖስተር ንድፍ፣ በእጁ ይዞ በመገኘቱ፣ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ታውቋል፡፡

የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል በጽ/ቤቱ በወሩ መጨረሻ የሚያደርገውን የኪነጥበብ ምሽት የከተማው ተወላጅ ለሆነችውና በህገወጥ እስር ለምትገኘው ለርዕዮት አለሙ መታሰቢያ እንደተሰየመ የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ጨምሮ ገልጧል፡፡


ዘላለም እሼቴና አለምነው መኮንን ምንና ምን ናቸው? ታረቀኝ ሙጬ

$
0
0

“ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ” ይባላል፡፡ ዶክተር ዘላለም እሼቴ በተባለ ሰውዬ በአማሮች ላይ ተጻፈ በተባለ አንድ አጭር ደብዳቤ ላይ ተመሥርቶ አድማሱ በላይ የሚባል ሌላ አቃቂረኛ የሰጠውን ተገቢና ወቅታዊ ግብረ-መልስ በአቡጊዳ ድረ ገፅ ላይ አነበብኩና እኔም በማውቀው ቋንቋ በአማርኛ ትንሽ መናገር አሰኘኝ፡፡ የዶክተሩን ጽሑፍ ያነበብኩት የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት አጠገቤ አስቀምጬ ከአንዴም ሁለቴና ሦስቴ ደጋግሜ ነው፤ አጭር በመሆኑም ጊዜ የሚወስድ አልነበረም፡፡ መዝገበ ቃላት ያላገኘሁለት ነገር የዶክተሩን ማንነት ለማወቅ የነበረኝን ጉጉት አዘል ጥያቄ የሚመልስልኝ ነው፤ ሰውዬው የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ የማያውቅ ምናልባትም ጨረቃ ላይ የሚኖር ዓለመኛ ዜጋ መስሎኛለ፡፡ እነሱ የተወራከቡት በፈረንጅ አፍ ነው፡፡ የዶክተር ተብዬውን ጽሑፍ ከአድማሱ ጽሑፍ ውስጥ በተወነጨፈ ማያያዣ አማካይነት በኢትዮሚዲያ ድረገፅ ላይ ነው ያነበብኩት – በከፍተኛ እልህ፡፡ የለም፣ ግዴላችሁም ይሄን አማራ የሚባል መከረኛ ሕዝብ ለማጥቃት ያሰፈሰፈው በዝቶኣለ፡፡ ከድረ ገፅ አንስቶ እስከቴሌቪዥኑ እየተረባረቡበት ናቸው፡፡ ምን አር’ጓቸው ይሆን ከ23 ዓመታትም በኋላ ሊበርድላቸው ያልቻለው? ለመሆኑ የአማራ ኮከብ ምን ሆኖ ይሆን እንዲህ ጠላት የበዛበት? በእውኑ በጣም ይገርመኛል፡፡ ተኝቶም የማያርፉለት የሲዖል ትሎች ተላኩበት፡፡

ዘላለም ባለው ነገር ላይ ባልስማማም ያለውን ነገር ለማለት መብቱ እንደሆነ አምናለሁ፤ አማራ ስሙ ሲነሳ ራሱ የሚቀፋቸው የሚመስሉኝ የሚዲያ አካላትም በዚህ ዘውግ ላይ የሚሰነዘርን ዝባዝንኬ ሁሉ እውነትነቱን አንዳችም ለማጣራት ሳይሞክሩ እንዳለ ማስተናገዳቸው የነሱን ማንነት ከመግለጡ ውጪ ሌላ ጉዳት የለውምና ብዙም ቅር አይለኝም – በዚያ ላይ የርሱን የመናገር መብት እንደጠበቁ የኔንም ቢጠብቁ ጥሩ ዳኞች ባሰኛቸው ነበር፤ ግን ይሞቷታል እንጂ ይህን አያደርጉም፡፡ ምክንያቱም ከአቋማቸው ውልፊት የሚልን ነገር ማስተናገድ ይቅርና ማየትም አይፈልጉምና – ተበላልተን ጨርሰናል፤ አራዶች “ተነቃቅተናል!” ይሏታል ይቺን አካሄድ – እንአካሄድ፡፡ አለበለዚያ ፊታውራሪ አደፍርስ ደቻሳ ሻሌሞ ወይም ደጃች አስደግድግ ግደይ ቢራቱ ወይም ባላምባራስ ውቤ ጉልማ ሙክታርና ራስ ገመቹ ሐጎስ ደስታ በተናጠልም ሆነ በቡድን አማርኛን እየተናገሩ የዛሬ ስንት አሠርትና ምዕተ ዓመታት በፊት ባጠፉት ጥፋት ዛሬ ላይ ሆኖ አማራነቱን እንኳን በቅጡ የማያውቅ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋና የጎንደር ምሥኪን ገበሬ በወያኔ የቻምበር ጋዝ የዕልቂት ወረፋ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት ንስሃ እንዲገባና በጸጸት ዕንባ እየታጠበ አድራሻቸውና ማንነታቸው በውል ያልተገለጸ ሌሎች ወገኖችን ይቅርታ እንዲጠይቅ የሚጋብዝን የወያኔን ተልእኮ ያነገበ መርዘኛ “ምሁራዊ ጥናት” ለማስተናገድ ድፍረት የሚያገኝ አንድም ሚዲያ ባልተገኘ ነበር፡፡ ይህ ዐረፍተ ነገር ቢረዝምም ደግማችሁ እንድታነቡልኝ በትህትና ብጋብዛችሁ ደስ ይለኛል፡፡ በእውነቱ አለመታደል ነው፡፡ በርግጥም ባቢሎን ሆነናል፡፡ ይህ ግብዣ እውነት የሚሆነው መላዋን ኢትዮጵያ እንደ አንበጣ ወርረው ሀገሪቷንና ሕዝቡን እንደመዥገር እየቦጠቦጡ ለሚገኙት ከትግሬው አብራክ ለተገኙ የገዢ መደብ አባላት ቢሆን ነበር – ነገሩ “ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ” ዓይነት ነው፡፡ ለወያኔ ወረራ የሽፋን ተኩስ የሚሰጠው አካል መብዛቱን ስመለከት “ወርቅ የጫነች አህያ የማትደረምሰው ምሽግ የለም” የሚለው የፈረንጆች ብሂል ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል፡፡ በመሠረቱ ይህ ዘላለም የተባለ ሰው አማራ ነኝ ማለቱን በጭራሽ አልቀበለውም፡፡ ለምን ቢባል አማራን አያውቀውምና፡፡ እንደእውነቱ አማራነትን ማንም ለማንም የሚሰጠው የችሮታ ጉዳይ አይደለም – ሰውዬው አማራ ቢሆንም ግድ የለኝም ለማለት ነው፡፡ በትንሹ አማርኛን መናገር ወያኔው በልካችን ሰፍቶ የሰጠንን የአማራነት ማንነት ለማግኘት በቂ ነው፡፡ ስለሆነም እንኳንስ አማርኛን ለመናገር የሚጸየፉ አንዳንድ ደናቁርት የኢትዮጵያ ምድር ሰዎች ይቅርና ስንትና ስንት ፈረንጅና ጥቁር አፍሪካዊያን አማርኛን ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ባልተናነሰ ወግ ሲጠርቁበትና በሀበሻነት የድራቦሽ ማንነትም ሲኮሩበት እያስተዋልን የኖርንበት ሁኔታ ሞልቷል፡፡ እናም እንኳንስ አማርኛን የሚናገረው የአማራው ንስሃ አባት ዶክተር ዘላለም ሲልቪያ ፓንክረስትም አማራ ነኝ ብትል ይቻላት ነበር – አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር መጣበቅ ካለበትም ነበረች ማለትም እንችላለን፡፡

በነገራችን ላይ አማራን የሚጠሉ ወገኖች አንዱና ትልቁ ችግራቸው አማራ በጎጥና በቋንቋ እየተኮማተረና እየጠበበ ወርዶ እንደነሱ ሸጥ ውስጥ ለመወተፍ የሚያበቃው ግለሰባዊና ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ልክፍት የሌለው መሆኑ ነው፤ ይህ የአማራ ኮስሞፖሊታዊ ባሕርይ የሚያበሳጫቸው ይመስለኛል፡፡ ፀረ-ኢትዮጵያውያን – የውስጦቹም የውጪዎቹም – በጣም የሚቋምጡለት ነገር ቢኖር አማራን ቢችሉ ማጥፋት ባይችሉ አስተሳሰቡን ማክሰም ነው – የሚፈሩት አማራዊ አስተሳሰብም “እኔ ሰው እንጂ፣ እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ፣ እኔ አፍሪካዊ እንጂ እኔ የዚህች ዓለም አንድ አካል እንጂ በዘርና በጎጥ መከፋፈል የማምን፣ እንደውሻ አጥንትና ደም የማነፈንፍ ጎሰኛና ዘረኛ ልሆን የማልፈልግና የማልችልም ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል ነው – በዚህ ምክንያት ነው የዕልቂት ዐዋጅ የታወጀበት፤ ሌላ ይቅርታ የሚያስጠይቅና ጸጸትና ንስሃ ውስጥ የሚያስገባ ወንጀልም ሆነ ኃጢኣት የለበትም፤ ይህንንም ስል እንደማንኛውም ሕዝብ አንዳንድ አባላቱ በራሱም ሆነ በሌሎች ላይ ጥፋት የማይፈጽሙ ቅዱሣንና ብፁዓን ናቸው የማለት ወያኔያዊ ድፍረት የሌለኝ መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ጥፋትና ልማት ሰብኣዊ እንዲ ብሔረሰባዊ አይደለም – አማራን በአጥፊነት ሌላን በአልሚነት የመመደብ አዝማሚያ ካለ ዕብደት ነው፡፡ ቀፎው ዘላለም ይህን ይረዳልኝ፡፡ አማራ ቢወቅጡት ቢፈጩት ከእንግዲህ ወደሸጥና ፈፋ ወርዶ የሚወተፍላቸው አይደለምና ጠላቶቹ ቁርጣቸውን ቢያውቁ ደስ ይለኛል – እንደግል አመለካከቴና እንደአካሄድም፡፡ በመሠረቱ ዘላለም አማራ ነኝ ማለቱ እውነትም ሀሰትም ሊሆን ይችላል፤ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሠ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታምራት ላይኔና ሌሎችም አማራ ነን ብለው ድርቅ ካሉ ደግሞ ማንም መሆን የማይችልበት ምክንያትም የለም፡፡ አሜሪካዊው ጆን ኬሪስ አማራ ነኝ ቢል መቀበል እንጂ ምን ምርጫ ይኖረናል? ሆ! አማራ አናት ላይ ፊጥ ያላችሁ ኧረ እባካችሁን ውረዱለትና ይረፍበት!

የአስተሳሰብ ጓደኛው አለምነው መኮንንም አማራ ነኝ ብሎ ሲያበቃ በስድብ አጥረግርጎን የለም በዚያን ሰሞን? አማራ እንኳንስ ለስድብ አንገቱን ለካራ አመቻችቶ ከሰጠ ሩብ ምዕተ ዓመት ሊሆነው ነው – ዕድሜ በስሙ ሀገር እየገዙ ለዚህ ሰቆቃ ለዳረጉት ኢትዮጵያውያን መኳንንትና መሣፍንት፡፡ ራሱ ልጋጉን ሳይጠርግ ልጋጋም የሚል አማራ ነኝ ባይ የወያኔ አፋዳሽና ሆዳም ባንዳ አማራን በተሳደበ ማግሥት ይሄ ዘላለም እሚሉት ሰው በለሰለሰ አንደበትና በጨዋ ቋንቋ ከአለምነው ያልተለዬ መልእክት በኢትዮሚዲያ ማስተላለፉን ስረዳ በርግጥም በዚህ የተገፋ ሕዝብ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ ከውስጥም ከውጪም እንደተከፈተበት መገንዘብ አላቃተኝም፡፡ ግን ለምን? ግፍ ሲበዛ ወደራስስ ይዞር የለምን? ለምን እየተስተዋለ አይሆንም?

የዘላለም ጽሑፍ ዋነኛ መልእክት አማራው ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ስላሰቃዬና ስለበደለ አሁን ያሉት አማሮች በነቂስ ወጥተው የበደሉትን ይቅርታ ይጠይቁ ነው፡፡ የኛ ማንዴላና የኛ ማዘር ተሬዛ ዶፍተር ዘላለም በዘወርዋራ መንገድ የሚለን ያለ አማሮች እግዚኦ በሉና ከኦሮሞና ከጉራጌ፣ ከሲዳማና ከዳዋሮ፣ ከጀምጀምና ከኮንሶ፣ ከወላይታና ከሃዲያ፣ ከጠምባሮና ከከምባታ፣ … ታረቁ አለበለዚያ የአባቶቻችሁና የአያት ቅድመ አያቶቻችሁ ኃጢኣት በእናንተ ላይ መፍረዱን እንደቀጠለ ይቀራል በማለት እያስፈራራን ነው፡፡ የሰውዬው አባባል እውነትነት ቢኖረው ኖሮ አነሳሱ የሚጠላ አይደለም፤ እንደዚህ ዓይነት ክስተቶች በአርመኖችና በቱርኮች እንዲሁም በሌሎች የቅኝ ገዢና ተገዢ ሀገሮች መካከል ታይተዋል፡፡ ይሁንና ይህ ሰው አንድም ሞኝ ነው(foolish or naïve at best)፤ አንድም የኢትዮጵያን ታሪክ ፈጽሞውን አያውቅም፤ አንድም አእምሮው ያልበሰለ ጮርቃ ነው፤ አንድም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ አናፍሎት የሚሠራውን ስላሳጣው ሳይታወቀው የወያኔን ወንጀል በተበዳዩ በአማራው ላይ ደፍድፎታል፤ አንድም እንደነአለምነውና እንደሙሉጌታ አሥራት፣ እንደነገነት ግርማና ክፍሌ ወዳጆ፣ እንደነ አሰፋ ብሩና እንደተቀዳ ዓለሙ፣ … ሰውነቱን ለወያኔ ያከራዬ አጋሰስና ገልቱ ዜጋ ነው (ሰለጠነ በሚባለው ዓለም ችግረኛ ሴቶች ማኅፀናቸውን ለሀብታሞች እያከራዩ ገንዘብ ያገኛሉ ይባላል፤ የነዘላለምም የነአለምነውም የነብርሃኑ ዳምጤም እንደዚያው ነው – ሰውነትን፣ አንደበትን፣ ምንን ምናምንን – የሚነገርንም የማይነገርንም የሰውነት አካል ባወጣ ማከራየትና ጃዝ ሲባሉ እንደውሻ መጮኽና እንደአህያ ማናፋት፤ ተናገሩ ወይ ጻፉ ሲባሉ ሼክስፒርን በሚያስንቅ የቋንቋ ምጥቀት የጅሎችን ጭንቅላት በአሰስ ገሰስ ቱሪናፋ ማሾር – ከዚያም ወያኔን በዕድሜ ማራዘሚያነት ማገልገል(ARV – antiretroviral)፤ ከዚያም ሆድን በቆሻሻ መኖና በቆሻሻ አልኮል መቆዘር፤ ከዚያም በሥነ ልቦና ቀውስ መቆዘምና መዋተት፣ ከዚያም ጥቁር ታሪክ ጥሎ ዘር ማንዘርን ማዋረድ – ከዚያም … ከዚህ በላይ ምን ከዚያም አለና ዳሩ)፡፡ አዬ መማር! ትምህርት እንዲህ እንደዋዛ ገደል ይግባ?

እንዲያ ባይሆን ኖሮ አማራው ባለፈ ታሪኩ ጥፋት እንኳን ቢኖበት በአሁኑ ወቅት እንደዐይጥ በተገኘበት እየተጨፈጨፈ በሚገኝበት ሁኔታ፣ መንግሥታዊ ጄኖሳይድ ታውጆበት ከዐርባጉጉና በደኖ ጀምሮ ያለዕረፍት በጥይትና በርሀብ፣ በመፈናቀልና ሆን ተብሎ በሚሰራጭ በሽታና የኤድስ ቫይረስ፣ ሆን ተብሎ በመርፌ በሚሰጥ ዘር አምካኝ መርዝ ትውልድ እንዲከስምና አማራ እሚባል ከናካቴው እንዲጠፋ እየተደገረበት ባለበት ሁኔታ እንዲህ ያለ የግፍ ግፍ ሊጻፍ ባልተሞከረ ነበር፡፡ ስለዚህ እላለሁ – ስለዚህ ዘላለም የሚባለው ደደብ ሰውዬ የሸንጎ ፍርድ የሚገባው የመጨረሻ ገልቱና የአማራ ጠላቶች ተላላኪ ነው – እዚህች ላይ የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ባህል ባይገድበኝ ኖሮ “የውሻ ልጅ!” ብዬ ብሰድበው ምንኛ እልኼን በተወጣሁ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው – ባህላችንም መጽሐፉም አትሰዳደቡ አትነቃቀፉም ይላላ! ጅል ሰው አያጋጥማችሁ ወንድሞቼ፡፡ ደደብነቱ አስገድዶኝ እንዲህ ስናገረው ስለርሱ ሞኝነትም ስለኔ የመረረ ስሜትም በደምሳሳው ስለሁለታችንም በጣም አዝናለሁ [ይቅርታና ‹ደደብ› ስል ሌላ ቃል ከማጣት አንጻር ቀለል ባለ የፈረንጅኛው አገላለጽ idiot ወይም moron ለማለት እንጂ stupid ለማለት ፈልጌ እንዳልሆነ በትህትና ልግለጥ]፡፡ ይህ ሰው የይቅርታን ቃል ምንነት በፍጹም አያውቀውም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ኢትዮሚዲያም የይቅርታን ምንነት ሊያስረዳው አልቻለም ወይም አልፈለገም፡፡ የወደቀ ግንድ ምሣር ይበዛበታልና ግዴለም ሁሉም በዚህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ ያለውን ሽብልቅ ሁሉ እያነሳ ይቀርቅብ – “እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳም” ይላሉ አሉ ወዳጆቻችን ዐረቦች፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን ለሁሉም ጊዜ ያለው በመሆኑ እንዲህ በግልጽና በአደባባይ በአማራው ላይ ያላገጡና ያሾፉ ሁሉ የውሻን ደም በከንቱ የማያስቀረው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሥራቸውን እንደሚሰጣቸው መረዳት የሚገባን መሆኑን አለመዘንጋት ነው፡ አሁን ዘመኑ የነሱ ነው፤ ዘመነ ዕቡያን ወዕኩያን፡፡ እነአያ ምንተስኗቸው አሁን ቢፈልጉና ሲፈልጉ ሟችን ለገዳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሊያደርጉት ይችላሉ – ዘላለምም ሆነ ወንድሙ አለምነው እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው – በጌቶቻቸው ወያኔዎች ጃዝ ባይነትና ድርጎ ከፋይነት፤ የሆድ ነገር አያድርስ፡፡ ማን ነበር “ሆድ እንኳንስ ከኋላችን አልሆነ፤ ቢሆን ኖሮ ገፍትሮ ገደል ይከተን ነበር” ያለው? ጥሩ ብሏል፤ እንኳንስ ከፊት ለፊታችን ሆነ – ባይሆን ከፊታችን ተንጠልጥሎ ይጎትተን፡፡

በመሠረቱ የሞተ ሰው ማንንም ይቅርታ አይጠይቅም፤ እንዲጠይቅ መፈለግም ቂልነት ነው፡፡ ሣሞራ የኑስ “አማራን አርቀን ቀብረነዋል” ሲል፣ የእንጨት ሽበቱ አቦይ ስብሃት ነጋ “ኦርቶዶክስንና አማራን አርቀን ቀብረናል” ሲል፣ የፈራረሰው መለስ ዜናዊ “አማራን ገድለን ቀብረናል” ሲል፣ ድምፂ ወያኔ “አማራ አህያ ነው፤ ቦቅቧቃም ነው፤ እያሳደድክ ጀርባ ጀርባውን በለው” ሲል፣ አማራው በአርሲ፣ በማጀቴ፣ በጉራፈርዳ፣ በቤንሻንጉል፣ በሐረር፣ በሶማሌ፣ በጅማ፣ በአዲስ አበባ፣ በክልሉ፣ ወዘተ. ሕጻን ዐዋቂው አንገቱ በሠይፍ እየተቀላና ደረቱ በጥይት እየተቦተረፈ ሲረፈረፍና ከኖረበት ቀየ ባዶ እጁን ሲባረር … ይህንና መሰል ውርጅብኝ በአማራው ላይ በሥነ ልቦናም በአካልም ሲደርስበት በዳዮች ይቅርታ እንዲጠይቁት ሃሳብ ያቀረበ አንድ እንኳን ዘላለም እሼቴ ነበረ ወይ? ወይንስ አማራው ከውሻ ያነሰ ነፍስ ያለውና ግፍና በደሉ ሊታይለት የማይገባው እዚህ ግባ የማይባል ፍጡር ይሆን? ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘና ነው ለዚያውም አማራ ነኝ በሚል – አማራ መሆኑ ግን በሚያጠራጥር ሰው አማራው ይቅርታ እንዲጠይቅ በተቅለሰለሰ በእግረ መንገድም ለሹመት ይሁን ለሽልማት የሚቅመደመድ በሚመስል አንደበት የሚጠየቀው? ምንድን ነው እየሰማን ያለነው? አእምሮ ወዴት ተሸሸገ? ማሰብን ምን በላው? ለመሆኑ ዘላለም ማነህ? ምንድንስ ነህ? በሕይወት ካለህ እስኪ አናግረኝ፡፡ ይህን ዕውቀት ከየት አባህ ማለቴ ከየት አገኘኸው? “ወይ መዓልቲ!” አለ ትግሬ – እንደኔ ቢጨንቀው፡፡ እኚህ ወያኔዎች በየወሩ አዳዲስ አወዛጋቢ አጀንዳዎችን እየቀረፁ ቅንጭላታችንን ሥራ ያስፈቱ ያዙ እኮ፡፡ እኒህ ሸረኞች፡፡ ደግሞም የተባባሪወቻቸው ኆልቁ መሣፍርት ማጣት፡፡

ጎበዝ፣ ባይቆጭ ያንገበግብ ይባላል፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ ማጽናናት ሲገባ እንዲህ ያለ የበደል በደል፣ እንዲህ ያለ የግፍ ግፍ ከወያኔ መንደር ካልሆነ በስተቀር ከማንም ሊፈልቅ አይችልም፡፡ አድማሱ በላይ በጥሩ አነጋገር ጥሩ መልስ ሰጥተሃልና የአማራው ውቃቢ ይጠብቅህ ልጄ፡፡ ሌሎችም ባንተ መጣጥፍ ሥር እንደኔው የተናደደ መልስ ሰጥተዋልና የበለጥሻቸው አድባር በሄዱበት ትከተላቸው፡፡ ጥቂቶቹን ከዚሁ ከአቡጊዳ ድረገፅ ላይ ጨልፌ እንዳሉ ከዚህ በታች ላስቀምጥና የንዴትና ቁጭት ብዕሬን ለአሁኑ ልስቀል፡፡ ከተናግሮ አናጋሪ ግን ይሠውራችሁ ወገኖቼ – ቀንድ ነው ጭራ እምትሉትን አስበቀለኝ እኮ፡፡ ደግሞ ምንም ኤዲት ሳላደርግ እንዲሁ እንዳለች ነው እምልካት፡፡ ሰውን ግን ምንድን ነው እንዲህ እያጀዘበው ያለው? የአብዬን ወደ እምዬ አሉ? ማንም የሁሉም ዘር ጥጋበኛ በአማራ ስም እየተነሣ አዳሜን እየቀጠቀጠ ገዛና ሁሉም ያለፈ የታሪክ ሰምበርና ጠባሳ በዚህ ምሥኪን ሕዝብ መሳበብ አለበት? ግን ግን ዶፍተሩ እንደተባለው የአለምነው መኮንን ወንድም ይሆን? ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር፡፡

1.Ethioman – Well said mr Admasu! The politics of anger and hate should end
We are one people against a system of division and dictatorship

2.ታው – ምን አልባት ዶ/ር ዘልአለም የአለምነው ዘመድ ይሆን? ጎበዝ! የዚህ ሁሉ ችግር ምንች ወያኒ ብቻ የሚነግረንን ታሪክ መስማታችን ነው;; ጆሮአችንን ለታሪክ ሰዎች ቅድሚያ እንስት;; ፖለቲከኖችን በተለይ ጎሳን መሰረት ያደረጉትን አንከተል;;የህዝብ ልጅ መሆን ይሻላል;;

3.Anonymous – One of our serious handcap of present day Ethiopians is our blind affinity to worship those who have/or say they have a PhD. It is not surprizing because education is highly valued in Ethiopia. Zelalem Eshete is a remarkably foolhardy idiot no matter what his cousin says about his narrow and artificial ‘scholastic apptitude’ Anyone with an elementary common sense would recoil with the idea or a suggestion of an Amhara collective guilt let alone offer apologies. We know that the extremly naive and foolhardy Welloye, Wallelign Mekonen, was manipulated by his Tigrean and Eritrean handlers and was idiot enough to publish what they wrote for him in his name. Once their purpose was achieved they informed about his hijacking of a plane to the Ethiopian authorities and his group was killed just after they left Bole airport.Better to get rid of the fool FAST. That is the Wallelign of the Tigreans and their “hero” Maybe his follower Zelalem may not even be aware of this and is expecting some reward from TPLF. But they know a fool inside out and know how to deal with his type. They will make him roll in their mud for some time first. We will soon see.

4.Saaby – This guy called zelalem is not even using his real name. The guy is a Tplf cadre pretending to be amhara and doing the job which Tplf started in Dedebit 40 years ago to annihilate the amhara population. It is a campaign of genocide and persecution on the amhara population which is an openly known agenda of TpLF.
The dead psychopath and fascist meles zenawi let the cat out of the bag when he said in 2005 that interahawme is coming to Ethiopia. He was reiterating his agenda of evicting, dispossessing, massacring, and persecuting the amhara.
Make no doubt about it the fascist woyane are preparing the ground for more genocide and [ersection of amharas and we should not sit and watch from the side lines. Any one who has seen what the fascist Tplf can do and has done has to take heed.

5.Derba Gochu –
“No, Revolutionaries” must repent In truth, it is the so called “revolutionaries” who should repent. They have grossly misrepresented the politics and aspirations of Ethiopian people for the last fourty to fifty odd years. Their analyses have largely been wrong. Their conclusions were as bad or even worse. They picked up a complex ethnic issue took it through a complicated thought process, when they hit the walls they come up with a very simplistic solution in the form of secession. To justify this fix they cut and paste f’..up Stalin’s gibberish or references from the man from the far corner of the world (Mao). You don’t need to have a PhD to work out that Ethiopia has very little resemblance to those countries conditions. Poor Ethiopia somehow was put on a par with the industrialized nations of Europe as a colonizing power who came in search of Labor and raw materials for their industries. How sillier and ridiculous could it get? No one ethnic group is immuned from dominating act and ill doing to other ethnic groups, in the past and even today. To paint a bad and good guy scenario was wrong and as we all know that only happens in Hollywood. The honest thing to do is to acknowledge our problems and formulate solutions to solve them with honesty and in fairness in a collaborative manner and move forward. No point exaggerating the problems beyond what they already are and run for cover in the form of simplistic cope out exercise (secession). Simply, the analysis we have been fed for so long lacked originality massively and totally ignored the aspirations of the Ethiopian people. It reads like this. “I have read it and it worked elsewhere. Accept it.” One should not dictate while championing Democracy. Because of this Ethiopia endured incalculable Human and economic cost. Thanks for the resilience of the Ethiopian people. In the face of all the hate propaganda, a call to rise up to send them at one another’s throat and divisions thrown at them they managed to stick together and have been riding the storm as best as they could. What one should do is help them to stick together and face the challenges in life as one and not disharmonize them

In the past year, a couple of prominent contributors, have put up separate apologies and thought that was a good beginning and hoped the different organizations will do the same but it is disappointing to see none following suit. The quest for repentance should be taken up by the “Revolutionaries” and not by any Ethiopian ethnic group. The writer should be commended for highlighting this fallacy.(ሠረዝ የተጨመረ)

ሰንደቅ –ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ የሥነምግባር ደንብ ላይ አልፈርምም አለ

$
0
0

በ2002ቱ ጠቅላላ ምርጫ መቃረቢያ ላይ ከ60 ያላነሱ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፓርቲዎችም እንገዛበታለን ብለው ከፈረሙበት በኋላም ሕግ ሆኖ የወጣው የስነ-ምግባር ደንብ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደማይፈርም አስታወቀ። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሰንደቅ እንደተናገሩት፤ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ በሀገሪቱ ፓርላማ ሕግ ሆኖ እስከወጣ ድረስ ፓርቲው እንደገና የሚፈርምበት ምክንያት የለም ብለዋል።

ኢህአዴግን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመግባት እንደ ቅድመ ሁኔታ እየቀረበ ያለው የምርጫ የስነ-ምግባር ደንብ በቅድሚያ ፈረሙ የሚባለውን “እኛ እንደቁምነገር አንቆጥረውም” ሲሉ የመለሱት ኢንጂነሩ ከኢህአዴግም ጋር የሚደረግ ማናቸውም ውይይት በቅድመ ሁኔታ ላይ መመስረት እንደሌለበት ገልፀዋል። በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ውይይትም ሆነ የጋራ ምክር ቤት የምክር ቤቱን ነፃነት ጥያቄ ላይ የሚጥል ስለሆነ ለመነጋገርና ለመወያየት የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ ፊርማ እንደቅድመ ሁኔታ መቅረብ የለበትም ብለዋል።

“አሁን ተቋቁሟል የሚባለው የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በራሱ ብዙ ችግር ያለበት፣ ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ተሰብስበው የሚቀልዱበት እንጂ ሐቀኛ ሆኖ በነፃነት ውይይት የሚደረግበት ም/ቤት አይደለም” ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ተናግረዋል። ስለሆነም ፓርቲያቸው ለጊዜው በፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የመሳተፍ ፍላጎት የለውም ብለዋል።

ከኢህአዴግ ጋር ለመነጋገርም ሆነ ተቀራርቦ ለመወያየት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት ኢንጂነሩ ሕጋዊ ፓርቲዎች ሆነን በምርጫውም እንደምንሳተፍ ሰለሚታወቅ ሌላ የተለየ ቅድመ ሁኔታ አያስፈልግም፣ ወደፊርማ የሚያስገባ ሕጋዊ መሠረት የለም ብለዋል።

ኢንጂነር ይልቃል ወደፊርማ የሚያስገባ ሕጋዊ መሠረት የለም ቢሉም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነ-ምግባር ለመደንገግ በወጣው አዋጅ 662/2002 ዓ.ም አንቀጽ 21(6) እና (7) ላይ አዋጁ እንዲወጣ ተስማምተው በፈረሙ ፓርቲዎች እንደሚቋቋምና የስነ ምግባር ደንቡ ሲቀርፅ በልዩ ልዩ ምክንያት ያልተሳተፉ ሌሎች ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤቱ የሚያወጣውን የስምምነት ሰነድ መፈረም እንዳለባቸው ያስገድዳል።

ይሁን እንጂ፤ “የምንፈርመው ነገር የለም” ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲያቸው በዚህ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው አረጋግጠዋል። በምርጫውም የሚኖራቸው ተሳትፎም ደንቡን በመፈረምና አለመፈረም ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በአጠቃላይ ገዢው ፓርቲ የፖለቲካውን መድረክ ጨምድዶ በያዘበት ሁኔታ ነው ብለዋል። አሁን ባለው ሁኔታም ምርጫው ፍትሐዊ ይሆናል ብለው እንደማያስቡ ነገር ግን መብቱን የማስከበር የሕዝቡ እንጂ የኢህአዴግ መልካም ፈቃድ አይደለም ሲሉ አስረድተዋል።

በቅርቡ ኢህአዴግ በመወከል ወደ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አባልነት የተዛወሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ አስፋው በበኩላቸው ማንኛውም ፓርቲ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ለመግባት በማመልከቻ መጠየቅ እንዳለበት ሀገር አቀፍ ፓርቲ መሆንና በጥር ወር 2002 ዓ.ም የወጣውን የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነ-ምግባር ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 662/2002 ዓ.ም መፈረም አለበት ብለዋል። ፓርቲዎቹ ወደ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሲመጡ የስነ-ምግባር ደንቡን እንዲፈርሙ የሚያስገድደው በፓርቲዎች ስምምነት ሕግ ሆኖ የወጣው አዋጅ እንጂ ኢህአዴግ
አለመሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል።

ሰንደቅ –አራት ምሁራን አንድነት እና መኢአድን እንዲዋሃዲ እያሸማገሉ ነው !

$
0
0

በመኢአድ ጽ/ቤት እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በእነ ዶክተር ያእቆም ኃይለማሪያም፣ በዶክተር ዳኛቸው አሰፋ አደራዳሪነት የተጀመረው የቅድመ የፓርቲዎች ውህደት ድርድር ውጪ የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይሎች የቀመሩት አይደለም ሲሉ ከአደራዳሪዎቹ አንዱ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።

ስማቸው አይጠቀስ ያሉ ዶክተር አሁን የያዙትን ኃላፊነት በምን መልኩ እንዳገኙት ለሰንደቅ እንደገለፁት፤ “እኛ ይህን ኃላፊነት የወሰድነው በራሳችን ተነሳሽነት እና በአንዳንድ ሰዎች ድርድሩን በሽምግልና ለምን አትገቡበትም የሚል ጥያቄዎች ስለቀረበልን ነው። በምርጫ አሸንፎ ለመውጣት በጋራ መስራት ተገቢ ነው ብለንም ስለምናምንም ጭምር ነው። ከዚህ ውጪ እኛ በራሳችን ተነስተን በእነሱ ላይ የምንጭነው ነገር የለም።”

“በውጭ ሀገር የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይሎችን ተልዕኮ ይዛችሁ በድርድሩ ላይ እንዲሁም ከፕሮፌሰር አስራት እስከ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ድረስ የነበረውን መኢአድ ቅርጽና ይዘት ለመለወጥ እንደምትሰሩ አንዳንድ ወገኖች እየገለፁ ነው። በዚህ ላይ የእርሶ አስተያየት ምንድን ነው” ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “እኔ የምዋሽበት አንድም ሁኔታ የለም። በተለይ ከውጭ ኃይሎች ጋር ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ ከማናቸውም ጋር ግንኙነት የለኝም። እኛ የተነሳነው በሀገራችን ሰላም ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የአንድ አምባገነን ፓርቲ የበላይነት እንዲጠፋ፣ ተቃዋሚዎች በትብብር ሆነው ወይም በምርጫ ብቻቸውን ተሳትፈው ይህን ስርዓት እንዲለውጡ ወይም እንዲያስወግዱት ነው። በራሳቸው በፓርቲዎቹና በአንዳንድ ወገኖች ጥያቄ እንጂ ውጪ ይገኛሉ ከሚባለው ኃይሎች ጋር በፍፁም ግንኙነት የለንም። ዳኛቸውም ሆነ አቶ ይልማም ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት የላቸውም” ሲሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ ተከላክለዋል።

“ፖለቲካ ፓርቲዎች የያዙትን የፖለቲካ ኢኮኖሚ መስመር በሽምግልና መፍታት ይቻል ይሆን?” ብለን ላቀረብነው ጥያቄ ዶክተሩ የሰጡን ምላሽ፣ ፓርቲዎቹ በፕሮግራማቸው ተመሳሳይ ናቸው። በአባሎቻቸው ተመሳሳይ ናቸው። ሁለት ሆነው የሚኖሩበት በቂ ምክንያት የለም። በሁሉም ነገር ይመሳሰላሉ። በርዕዮተዓለም ሆነ በአስተሳሰብ አንድ ናቸው። በተናጠል መኖራቸው ለእኔ ትርጉም አልባ ነው” ብለዋል።

በመኢአድ ፓርቲ ፕሬዚዳንት በአቶ አበባው መሐሪ በኩል ውህደቱ ጥልቅ ውይይት አድርገን ብንፈጽመውና የተወሰነ ጊዜ ብንወስድ የተሻለ ነው። ሐሙስ የጥድፊያ እንዳይሆን የሚል ሃሳብ ቢሰነዝሩም፤ በዶክተሮቹ በተደረገ ጫና የግድ ከሐሙስ ማለፍ የለበትም በሚል ለሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቀን ተቆርጧል ሲሉ በስበሳባ ውስጥ የተካፈሉ አባላት ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ እንዴት ታለፈ ብለን ለዶክተሩ ጥያቄ አቅርበንላቸው፤ “እንደዚህ አይነት ቅሬታ አሁን ከእናንተ ነው የሰማሁት” ብለውናል።

በዚህ ነጥብ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን የመኢአድ ፕሬዝደነት የሆኑት አቶ አበባው መሐሪን ደውለን አግኝተናቸው ነበር። ሆኖም እሳቸው፤ “በዚህ የውህደት ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ገልጸውልናል። በዚህ ድርድር ላይ ፓርቲያቸውን
ወክሎ የሚደራደረውን ሰው ስልክ ቁጥር ደውለው እንደሚያገናኙን ቃል ገብተው ተለያየን። ሆኖም ደግመን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም።

የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲዎች እንዲዋሃዱ በተካሄደው የድርድር ሂደት ላይ በአደራዳሪነት እየተሳተፉ የሚገኙት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም፣ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አለማየሁ ረዳ እና አቶ ይልማ ይፍሩ ናቸው። ነገ ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በፓርቲዎቹ መካከል የቅድመ ፓርቲ ውህደት ፊርማ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

ፍኖት –አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ አደረጃጀቱን ሊዘረጋነው

$
0
0

አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ አደረጃጀቱን ሊዘረጋ መሆኑንና ይህንኑ በተመለከተም ከፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት፣ከወረዳ ሰብሳቢዎችና ከወረዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ያሬድ አማረ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡

ግንኙነት ኃላፊው ወጣት ያሬድ እንዳስታወቁት ቅዳሜ መጋቢት13 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው ስብሰባ አንድነት አሁን ባሉት የምርጫ ጣቢያዎች ልክ አደረጃጀት ለመዘርጋትና የ2007ን ምርጫን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በቀጣይ የአዲስ አበባ አደረጃጀት ምን መሆን አለበት የሚል የጋራ ምክክር ለማድረግ እና የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ታቅዷል፡፡ በተጨማሪም ፓርቲው መዋቅሩን በክፍለ ከተሞች ለማጠናከር በወሰነው መሰረት የክፍለከተማ አደራጆችን ይፋ ያደርጋል፡፡ በእለቱ የአንድነትን አደረጃጀት በተመለከተ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የመወያያ ፅሁፍ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

ኢጋመ- በጋዜጠኞች ላይ ያለ ማስረጃ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን!

$
0
0

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ)
ETHIOPIAN JOURNALISTS FORUM (EJF)
በጋዜጠኞች ላይ ያለ ማስረጃ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን!ejf

ማህበራችን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዶ የምዝገባ ሰርተፊኬት ለማግኘት የጀመረው እንቅስቀሴ በቅርቡ ከመንግስት አወንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ በማድረግ የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅና የመናገር ነፃነትን ከማበረታታት ባለፈም ከአህጉራችን አፍሪቃ ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር የመላው አፍሪቃ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቅና የመናገር ነፃነትን የሚያበረታታ አህጉራዊ ተቋም ለመመስረት ተነሳሽነትን ወስዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡም የምስራቅ አፍሪቃ ጋዜጠኞችን በማስተባበር አህጉር አቀፍ እንቅስቃሴያችንን ለማስጀመር ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተግባር ጋዜጠኛውን ሳይወክሉ የጋዜጠኛውን ስም የያዙት የኢጋማ፣ የኢነጋማና የኢብጋህ አመራሮች ነን የሚሉት ግለሰቦች በመቀናጀት በየሚዲያው እየቀረቡ ጋዜጠኞችንና የሚዲያ ተቋማትን ለማሸማቀቅ ያለመ ውንጀላና አሉባልታ የመንዛት ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ቀርበው በጋዜጠኞች ላይ ከሽብር ፈጠራ እስከ ሀገር ማተራመስ የደረሰ የውንጀላ መዓት ቢደረድሩም አንዳችም ማስረጃ አላቀረቡም፡፡

ለምሳሌ የካቲት 22 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ (ቅጽ13 ቁጥር 737) ላይ ስማቸውን ደብቀው ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ጋዜጠኞች ሀገር ለማተራመስና ሽብር ለመፍጠር እየተዘጋጁ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ “ምን ማስረጃ አላችሁ” ለሚለው የጋዜጠኛዋ ጥያቄ የመለሱት “እኛ እና እነሱ እንተዋወቃለን፡፡” የሚል አስገራሚ መልስ ነው፡፡ ይህ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅ የተወረወረ በመሆኑ የኢጋማ፣የኢነጋማና የኢብጋህ አመራሮች ነን የሚሉት ግለሰቦች ጋዜጠኞችን እና የሚዲያ ተቋማትን ያለ ማስረጃ መወንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲያቆሙ ይጠይቀል፡፡

በመቀጠልም በሪፖርተር ጋዜጣ (የዕሁድ እትም ቅፅ 19 ቁጥር 1446) የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም “ኢጋማ በምስረታ ላይ ያለውን የጋዜጠኞች መድረክ አስጠነቀቀ” የሚል ዜና ተመልክተናል፡፡ ሆኖም በጋዜጠኞች ስም ተሰባስበው ጋዜጠኛውን የሚጠቅም አንዳች እንቅስቃሴ ሳያደርጉ ከመተኛታቸው ብዛት አልጋቸው ለረገበ ማህበራት ማስጠንቀቂያ ምላሽ በመስጠት ጊዜ በመሆኑም ምለሻችን በዝምታ መስራት ነው፡፡ የግለሰቦቹ የውንጀላ ንግግር የሚያስረዳው ከህግ፣ ከሞራል እና ከሙያዊ ስነምግባርም በላይ ራሳቸውን ለመሾም የሚፍጨረጨሩ መሆኑን ነው፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ ጊዜያት መንግስት የፕሬስ ተቋማት ላይና ጋዜጠኞች ላይ የወሰዳቸውን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃዎች እንደ ጋዜጠኛ ማህበር መሪ ከመኮነን ይልቅ የመንግስትን እርምጃ ሲያወድሱ ተስተውለዋል፡፡ በተጨማሪም በእስር ላይ ሆነው ህክምና በመከልከላቸው ለከፋ ስቃይ ስለተዳረጉ ጋዜጠኞችም ትንፍሽ ሲሉ አልታየም፡፡ እነዚህ የጋዜጠኛ ማህበራት መሪዎች ነን ያሉት ግለሰቦች እንደማህበር መሪ ሳይሆን እንደ ስለላ ተቋም ጋዜጠኞች እና አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ሃገር ለማተራመስና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው በይፋ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም

1ኛ. የሶስቱ ማህበራት መሪዎች አለን የሚሉትን መረጃ ለመንግስት በአፋጣኝ ሳይሰጡ መቆየታቸው በሀገራችን ህግ መሰረት ሊጠየቁው እንደሚገባ እንዲሁም
2ኛ. የሶስቱ ማህበራት መሪዎች በጋዜጠኞች እየተቀነባበረ ነው ካሉት የሽብርና ሀገር የማተራመስ እንቅስቃሴ ጀርባ እንዳሉ የጠቀሷቸውን ኤምባሲዎች በግልፅ ጠቅሰው ለመንግስት እና ለህዝብ እንዲያስታውቁ እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ)
መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር (ከሰንደቅ ጋዜጣ የተወሰደ)

$
0
0

በአዲስአበባ በተለይም በስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓታት የሚታየው የትራንስፖርት ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ ብቻም ሳይሆን ሠራተኞች በሰዓት ወደስራ ገበታቸው እንዳይገቡ በማድረግ በምርታማነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ እንዲሁም አብዛኛውን ሠራተኞች ላልተፈለገ ወጪ በመዳረግ የኑሮ ውድነትን በማባባስ ረገድ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ የሚታወቅ ነው። yetaxi-werefa

ከታክሲ የዞን ስምሪት አንስቶ ተጨማሪ አውቶብሶችን ወደመስመር በማስገባት በመንግስት በኩል የተደረጉ ጥረቶች
ቢኖሩም ችግሩን በአስተማማኝ መልኩ ለመፍታት ያስቻሉ አልነበሩም። በተለይ በአዲስ አበባ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ አንዳንድ የታክሲ መስመሮች በመዘጋታቸውና በተለዋጭ መንገድ እንዲሄዱ በመገደዳቸው ብዙዎች ባለንብረቶች የራሳቸውን የታሪፍ ማሻሻያ በማድረግ ሕብረተሰቡን ላይ ተጨማሪ ወጪ አስከትለውበታል።

ከንቲባ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባን ትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የቀላል ባቡር እና የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ማስፋፋት በቁልፍ ተግባርነት አስተዳደራቸው ይዞ እየሰራበት መሆኑን ያስረዳሉ። “ከባቡሩ መሠረተ ልማት በተጨማሪ የአንበሳ አውቶቡስ አቅም ለማሳደግና ሌሎች የከተማን የትራንስፖርት አቅርቦት አማራጮች ለማስፋፋት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ከዓለም ባንክ በተገኘ የሙያ ድጋፍ በመታገዝ የተለያዩ ጥናቶች መካሄዳቸውን ጠቅሰዋል።

በጥናቱም መሠረት አቅርቦትን ማሻሻል ብቻም ሳይሆን ከትራንስፖርት ጋር ተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮችን ለመፍታት የትራንስፖርት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተቋቁመው የተለያዩና ተስፋ ሰጪ የሚባሉ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል። ከነዚህ መፍትሔዎች መካከል ጥቂቶቹ ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት በግል ኩባንያዎች በኩል ማስፋፋት፣ ዘመናዊ የትራፊክ ኮርፖሬሽን ማዕከል መገንባት ፣የትራፊክ መብራት መትከልና ዘመናዊ ከተማ የትራንስፖርት አመራር አቅም ለመገንባት እንዲሁም ከመንገድ
ውጪ የፓርኪንግ አገልግሎት ማስፋፋት ወዘተ ሥራዎችን ለመስራት እየተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ የዉሃ ችግር (ከሰንደቅ ጋዜጣ የተወሰደ)

$
0
0

የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በተመለከተ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ውሃ በፈረቃ የሚያገኙበት ያልታወጀ አሰራር እየተስተዋለ ነው። ብዙ አካባቢዎች ከ24 ሰዓታት በላይ የመጠጥ ውሃ በተደጋጋሚ በመጥፋቱ ነዋሪዎች መደበኛ ሥራዎቻቸውን ጭምር በመተው ጄሪካን ይዘው ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ የሚንከራተቱበት ትይዕንት አዲስነቱ እየቀረ የመጣ ይመስላል።

አቶ ድሪባ ኩማ ግን በያዝነው በጀት ኣመት ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ የውሃ ምርትን መጨመር መሆኑን ይናገራሉ። “በበጀት ዓመቱ በአቃቂ ዋልፊልድ የ19 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና ተያያዥ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ከእነዚህ
ጉድጓዶች 70ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማምረት ታቅዶ 80ሜትር ኪዩብ ማምረት ተችሎአል። በቅርቡ የውሃ ማሰባሰቢያ ሪዘርባየር ሥራው እንደተጠናቀቀ ምርቱ ወደ ሥርጭት ይገባል።

ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲ ዊልፊልድ የ11 ጉድጓዶች ሲጠናቀቅ እስከ 40ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት ያስችለናል። እንዲሁም የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን በማስፋትና የድሬ ግድብን በማሻሻል የማጣሪያ ጣቢያውን የማምረት አቅም ወደ 195ሺ ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰራ ነው። የድሬ ግድብ ሲጠናቀቅ 30ሺ ሜትር ኪዩብ የውሃ ምርት የምናገኝበት ሲሆን ይህ የማስፋፊያ ግንባታ በ2007 ዓ.ም ክረምት ውሃ መያዝ ጀምሯል። እንዲሁም 70ሺ ሜትር ኪዩብ ማምረት የሚያስችል የ24 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ የሲቪል ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በዚህ ፕሮጀክት
እስካሁን ድረስ ከተጠናቀቁ 16 ጉድጓዶች ብቻ 94ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማግኘት ተችሏል።

ይህም ከፕሮጀክቱ ከሚጠበቀው 70ሺ ሜትር ኪዩብ በላይ ነው። ስለሆነም የተጀመሩ የሲቪልና መካኒካል ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ምርቱ ወደሥርጭት ይገባል። በአጠቃላይ ወደ 260ሺ ሜትር ኪዩብ የሚጠጋ ውሃ ማምረት የሚያስችል ሥራ እተሰራ ነው። ይህ ማለት እስከአሁን በቀን በአማካኝ የውሃ ምርታችን 359ሺ ሜትር ኪዩብ ሲሆን አሁን ያገኘነው 260ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደስርጭት ሲገባ የከተማዋ ውሃ አቅርቦት ችግር ይፈታል፤ የውሃ ምርታችንም ወደ610ሺ ሜትር ኪዩብ ያድጋል ብለዋል።

የውሃ አቅርቦት እጥረት ባለባቸው ዳገታማ አካባቢዎች ጊዜ የማይሰጡ አጣዳፊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ እስከ30ሺ
ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዙ 50 ትላልቅ የውሃ ታንከሮችና 20 ቦቴዎችን የማቅረብ ሥራ ተጀምሯል። በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች የውሃ ጉድጓዶች በስፋት በመቆፈር ውሃን ማምረት እንዲቻል 5 ዘመናዊ ሪጎች ከኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ የፌዴራል መንግስት ገዝተው ለከተማ አስተዳደር ድጋፍ አድርጓል።

ከረዥም ጊዜ አኳያ የውሃ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የገርቢ ግድብ ጥናት ተጠናቆ ለግንባታ ሚሆን ፋይናንስ
እየተፈለገ ሲሆን በቅርቡ ወደግንባታ ይገባል። የአዲስ አበባ ውሃ አቅርቦትን ከ25-30 ዓመት ድረስ የሚቃለልበት ሌሎች ተጨማሪ ግድቦችን ለመሥራት ጥናቶች መጀመራቸውን ከንቲባው በመግለጽ መጪው ጊዜ ብሩህ መሆኑን
በንግግራቸው አመላክተዋል።


በቦስተን እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የውደሳ እና የምስጋና ቀን በቦስተን

$
0
0

imagesበቦስተን እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የውደሳ እና የምስጋና ቀን በቦስተን

እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2006 / Sunday, March 30, 2014
ከቀኑ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ/From 2:00 PM to 6:00 PM
በካምብሪጅ፤ ዋልደን የኮሚኒቲ አዳራሽ፣ 21 ዋልደን ስኩዬር ሮድ፤ ካምብሪጅ፤ ማሳቹሴትስ 02140፣
(Walden Square Community Rm, 21 Walden Sq. Rd., Cambridge, MA 02140)

በእለቱ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር እና በወቅቱ ላለፉት 30 ወራቶች በእስር የሚማቅቀውን የሰብአዊ መብት ታጋይ፤ የፖለቲካ መሪ እንዲሁም የሕሊና እስረኛ የሆነውን የአንዱአለም አራጌን የውደሳ እና የምስጋና ቀን በካምብሪጅ፤ ዋልደን የኮሚኒቲ አዳራሽ፣ 21 ዋልደን ስኩዬር ሮድ፤ ካምብሪጅ፤ ማሳቹሴትስ 02140፣ (Walden Square Community Rm, 21 Walden Sq. Rd., Cambridge, MA 02140) ተዘጋጅቷል፤
በእለቱ

• የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የሕይወት ታሪክ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር በሚደረገው የሰላማዊ ትግል ያደረገውን አስተዋጻኦ በተመለከተ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ይቀርባል፤
• የአንዱአለም አራጌ “ያልተኬደበት መንገድ” በሚል ርዕስ በእስር ቤት የጻፈው እና በጉጉት የሚጠበቀው መጽሀፍ በቦስተን አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በይፋ ይመረቃል፤ ይሸጣል፤ የመጽሀፉ ሽያጭ ገቢም፤ ሙሉ በሙሉ በችግር ላይ ላሉት ለአንዱአለም አራጌ ቤተሰብ መርጃ ይውላል፤
• በእለቱ ሌሎች የሕሊና እስረኞችም ይዘከራሉ፤ ይታወሳሉ፤ ይወደሳሉ፤

በእለቱ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ለማስወገድ እና የሰው ልጅ መብት እንዲከበር እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመከባበር የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው የሰላማዊ ትግል የአንድ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት በመሆኑ በቦስተን አክባቢ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት አንዱአለም አራጌን እና መሰል የሕሊና እስረኞችን በማወደስ ኢትዮጵያዊ ግደታችንን እንድንወጣ በክብር ተጠርተዋል!!

አይርሱ ያስታውሱ!! የአገርዎ ጉዳይ ለግለስቦች ወይም ለፓርቲዎች የሚተው አይደለም፤ ተባብረን ዲሞክራስያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ትግል የበኩሉዎትን ድርሻ ለመወጣት ለራስዎ ቃል ይግቡ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
በቦስተን የአንድነት ድጋፍ ድርጅት
ቦስተንimages AndwalemFlyer

ፍኖተ –መኢአድ የቅድመ ውህደት ፊርማውን አደናቀፈ (መግለጫ ከአንድነት)

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የውህደት ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሰሞን ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ነው፡፡ የዚሁ አካል የሆነ እንቅስቃሴ በመኢአድና አንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባላት በእጅጉ እያሳዘነ ነው፡፡

በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀውን ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በሰጠነው የደብዳቤ መልስ ላይ እንደገለጽነው በአንድነት ፓርቲ እይታ አመራሩ የፊት ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብሰባ ሠፊ የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡
በዚሁም መሠረት፡-
የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈፅማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መሠረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር፣ የፊርማው ስነ ሥርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር፡፡
በከፍተኛ አመራሮችና በሁለቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ መሠረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንቶች ተስማምተው፣ የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈራርመን፤ ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል የዕውቅና ሠነድ አግኝተን የመጨረሻ የስነ-ስርዓቱን መርሃ-ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት በኩል በቁጥር መ/ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በእለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንዳማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ከደብዳቤው እንደተረዳነው መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ የሚቀለብስ፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተስማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግባቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ በማንሳትና በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል፡፡ ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ ምክንያቱ የመኢአድ ፕሬዚንት ሲሆኑ ይህን ሁኔታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎች፣ በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሁለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለሕዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ ኃላፊነቱን የሚወስዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይም ፕሬዝደቱ መሆናቸውን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓርቲያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም

በዘመነ ኢሕአዲግ ኑሮ ከድጡ ወደማጡ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

$
0
0

የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ መምጣት ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን ጥላቻ እንዲከር እያደረገው ነው<

የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ እና እየወረደ በመምጣቱ ሕዝቡ ከምቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት ኑሮን መቋቋም በማይችልበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ መኖር ከባድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የችግሩ ሰለባና ተጠቂ የሆኑት ሰዎች በየጊዜው ከሚያሰሙት ሮሮና ጩኸት መረዳት ይቻላል::ይህንንም እየተባባሰ እና እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ እንደሆነ ታውቋል:: የአንድነት ፓርቲ ሊጠራ ባሰበውና በታቀደው ሰላማዊ ሰልፉም ላይ በስርዓቱ እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በምሬት የታመቀ የብሶት ድምጻቸውን በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ላይ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል:: በአሁኑ ወቅት ጥቂት የስርአቱ ደጋፊዎች እና የወያኔ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር በኑሮ ውድነቱን የተነሳ ተጎጂ ያልሆነና ሕዝቡ ኑሮን መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ስርዓቱን የማያማርር የህብረተሰብ ክፍል የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም ::

የወያኔ መንግስት የሚያራምደው ፖሊሲ የመላው ኢትዮጵያን ሕዝቡ ፍላጎት እና ጥቅም ማዕከል ያላደረገ ሲሆን የተወሰኑን የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል :: መላውን የኢትዮያ ህዝብ እና ክልል ተጠቃሚ ያላደረገው የመንግስት የልማት ስትራቴጂ ፖሊሲ እና በመላው ሀገሪቱ ላይ በስፋት ተንሰራፍቶ ያለው ሙሰኝነት ከእለት ወደ እለት የሕዝቡ የአኖኖር ሁኔታ እያሽቆለቆለ እና እየወረደ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለኑሮ ውድነቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂው መሆን ያለበት ሀገሪቱን እየመራው እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት እያሳደገ እንዳለ የሚያወራው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ነው:: በነገራችን ላይ የኢህአዲግ መንግስት በየጊዜው ስለ ሀገሪቷ ኢኮኖሚ እድገት የለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ይለፍልፍ እንጂ ይህን በፍጥነት እያደገ ነው ብሎ ወያኔ የሚያወራለትን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት በተመለከተ የተባለው እድገት ከወረቀት ኣልፎ መሬት ላይ የሚታይ ነገር የለም የሚሉ ሰዎች በብዛት የሚገኙ ሲሆን ይህም ሀሳብ እኔንም ጨምሮ ብዙዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው::

ታስታውሱ እንደሆነ የወያኔ ቁንጮ የነበረው ሟቹ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት በአሥር አመት ዉስጥ «ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ትችላለች። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርጋለን» ብለው ነበር ነገር ግን ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር የውሃ ላይ ሽታ ሆኖ ቀረ :: በአንጻሩ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርገዋለን ያሉለት ኢህአዲግ ኢትዮጵያን በብቸኝነት በሀይል መግዛት ከጀመረ ወደ 23 አመታት እየተጠጋ ሲሆን በእነዚህ አመታቶች ውስጥ ምንም የተለወጠ ነገር የለም:: የወያኔ መንግስት በተቆጣጠረው በመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈልፉት የኢትዮጵያ ኢኮነሚው ዕድገቱ በፍጥነት ሽቅብ እየገሰገሰ ሳይሆን ወደታች እያሽቆለቆለ ይገኛል:: ምናልባት የኢኮኖሚ እድገቱ በወረቀት ስሌት ላይ ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ የሰዉ የአኖኖር ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።በአሁኑ ሰአት ሕዝቡን የውሃ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የኔት ዎርክ ችግር፣ የትራንስፖርት እንደሚፈልገው አለማግኛት በአጠቃላይ ችግሩ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል:: በይበልጥ የአዲስ አበባን ነዋሪ ክፉኛ ምሪት ውስጥ አስገብቶታል::

በመላው አገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በአገሪቷ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት እየታየ ሲሆን በሀገሪቱ ላይ በደረሰው በኢኮኖሚ ችግር የተነሳ ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ነገሮች እየከረሩ በማንኛውም ጊዜና ሰሀት ግባታዊ ሕዝባዊ አመጽ ሊነሳና ትልቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸዉ።

በአሁኑ ሰአት እንደሚታየው እና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል ህዝቡ ሀገሪቱን እየመራ ባለው የወያኔ መንግስት ለመመራት ፍቃደኛ አይደለም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሮሮ በማሰማት ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ ከየቦታው የሚሰማው እና የሚታያው የሰበዓዊ መብት ረገጣው አፈናና ግድያው ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሶ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ በየቀኑ እያሸቀበ የመጣው የኑሮው ውድነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ሲሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የሕዝቡ ንዴትና ቁጣ በከፍተኛ ሁኔታ በመፋፋም ላይ ይገኛል::

ከዚህም የተነሳ መንግስት በየቀበሌው፣በየመስሪያ ቤቱ በሚጠራቸው ማንኛውም ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኛት ሕዝቡ ፍቃደኛ እና ደስተኛ አይደለም:: ስለዚህም የሕዝቡ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆን የወያኔን መንግስት ክፉኛ ጭንቀት ውስጥ የከተተው ጉዳይ ሲሆን በመሆኑም ለመጪው 2007 ለሚደረገው ምርጫ የሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለው ጥላቻ እየጨመረ መምጣት እራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ይገመታል::

የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ባለስልጣኖች በሚቀጥለው አመት ምርጫ የሕዝቡን ድምጽ እንደማያገኙ በሚገባ ቢረዱትም ነገር ግን የለመዱትን የማጭበርበር እና የሌብነት ልምዳቸውን በመጠቀም ለቀጠይም አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበላይ በመሆን ሕዝብን እየጨቆኑና እየረገጡ ለመኖር የሚያስችላቸውን ስትራቲጂ በመንደፍ እነሱ እንደሚሉት የጀመሩትን የልማት ዕቅድ ለመተግበር ሳይሆን ኢትዮጵያን የማፈራረስና ኢትዮጵያውነትን የመጥፋት ዘመቻቸውን ለማስቀጠል የሚያረዳቸውን ማንኛውንም እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ ወደ ኋላ አንደማይሉ የተረጋገጠ ነው::

እንደ እኔ አስተሳሰብ የወያኔ ኢሕአዲግ መንግስት በምንም ታአምር በምርጫ ተሸንፉ ስልጣኑን በቀላሉ ይለቃል ወይም ስልጣኑን ለተቃዋሚዎች ያጋራል የሚል እምነቱም የለኝም::በአሁኑ ሰአት እንደምናየው እንዲሁ በቀላሉ የኢሕአዲግ መንግስት ስልጣኑን ይለቃል ወይም ለተቃዋሚዎች ያጋራል ብሎ ማሰብ የዋህነትና የማይታሰብ ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ወያኔና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆድና ጀርባ እንደሆኑ ለብዙ ጊዜ እንደማይቀጥል በምሪት እና በህልእ የተሞላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ ዳግም እንዳያንሰራራ ወደ መቃብር ይወስደዋል ብዬ አምናለው:: ስለዚህ የወያኔ መሰሪ አካሂድ ተስፋ ሳያስቆርጠን የወያኔን መንግስት በተገኛው መንገድ ሁሉ በመታገል እና በመቃወም የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ለማረጋገጥ ትግላችንን ማቀጣጣል ይጠበቅብናል::ኢትዮጵያ በቆራጥ ታጋይ ልጆቿ ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ትወጣለች!!!

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

gezapower@gmail.com

ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!! የእሪታ ቀን ሰልፍ በአዲስ አበባ ይጠራል (የአንድነት መግለጫ)

$
0
0

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ዛሬ በጽ/ቤቱ መግለጫ ሰጠ ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!

ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!

ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡

ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን”በሚል ስያሜ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ወሰነ!! ከአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!

$
0
0

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!
ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡

ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡

የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ1920578_827198673963262_1874916504_n

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>