Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

የማለዳ ወግ …ጉዞ ወደ ዓድዋ ! “ዓድዋ –ይከበር፣ ይዘከር –ለዘላለም !”ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ብቻ ነው አልልም ። ዓድዋ ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት ምንጭ ስለመሆኑ የታሪክ መዛግብትም ሆኑ ባእዳን የታሪክ ልሂቃን ሳይቀር የሚመሰክሩት ሃቅ ነውና ። በዓድዋ የጥቁር ዘር አትንኩኝ ባይበት ሲረጋገጥ የጥቁር ዘር ለነጻነቱ ቀናኢ መሆኑን ለአለም የታየበት መሆኑም የሚታበል አይደለም !

የዚህ ታላቅ ድል ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናችን አልፋና ኦሜጋ ሲያኮራን ይኖራል። የዓድዋን ታሪካዊ የድል በአል በመላ አለም በሚንገኝ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አመት በመጣ ባሰለሰ ቁጥር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በአሉ ሃበሾች በነጭ እብሪተኞች ላይ የተቀዳጀነው የዓድዋ ድል ነውና ቀጣዩ ትውልድ ታሪኩን አክብሮና ጠብቆ እንዲኖር እገዛ ስለሚያደርግ የበአሉ መከበር ታሪክን ከማወራረስ አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ። የዘንድሮው 118ኛ የዓድዋ ድል በአል ለማክበር በአገርና በቀረው አለም በምንገኝ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰፋ ያለ የመታሰቢያ ማዘከሪያ ዝግጅትን በማድረግ ላይ መሆናችን እውነት ነው ።

በአረቡ አለም በተለይም ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአሉን አድምቀን እንድናስበው ስለማይደረግ እድሜ ለቴክኖሎጅ በአሉን በማህበራዊ ገጾቻችን ለማክበር ተፍ ተፍ በማለት ላይ እንገኛለን። በሪያድ ኢንባሲና በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎቻችን የዓድዋን ታላቅ ሃገር አቀፍ በአል በአዳራሾቻቸው ተሰባስበን እንድናከብረው ቢያደርጉን ምንኛ በኮራን ነበር ! ዳሩ ግና የኢንባሲና የቆንስል ሃላፊዎቻችን እንዲህ አስበው አናውቃቸውም እና እንደ ልማዳችን እናዝናለን ። ቢያንስ የገዥው ፖለቲካ ድርጅቶች እና በጎጥ ለተመሰረቱት የልማት ማህብራት የሚሰጡትን ያህል ለቱባው ኢትዮጵያዊነት ክብር ሰጥተው ዓድዋን ሻማ አብርተን የጀግኖቻችን ታሪክ ላንድ አፍታ እያነሳሳን እንድናዘክር ፣ እንድንማማርና ጀግኖቻችን እንድናመሰግን አያደርጉም ። እውነቱ ይህ ሆነና የስደት ፍሬ የሆኑ በአረብ ሃገር ተወልደው የሚያድጉ ልጆቻችን በሚማሩበት እየሰበሰቡ የብሔር ብሔረሰብ የድርጅት በአላትን ሲያከብሩ ማድምቂያ ያደርጓቸዋል። የዓድዋንና የመሳሰሉ ሃገር አቀፍ በአላት ሲከበር ግን ትምህርት ከመዝጋት ባለፈ ስለበአሉ ምንነት ገላጭ የሆነ ትምህርት በብጣቂ ወረቀት ግንዛቤ እንዲሰጠቸው አይደረግም። ዛሬ በአረቡ አለም የተወለዱ ታዳጊዎች ሊኮሩበት ከሚገባው የሃገራቸው ታሪክ ይልቅ ስላደጉበት አገር በአላት የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው እየገፋናቸው በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ። የበአሉን አከባበር ካነሳሁ አይቀር ቀልቤን ወደሳበው እና መነሻየ ወደ ሆነው በስድስት ትንታግ ጎልማሶች እየተደረገ ስላለው የዓድዋ ታሪካዊ የእግር ጉዞ ላምራ …

በፍላጎት የተሰባሰቡ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስድስት ጎልማሶች በአሉን በክብር ለማዘከር ወደ ዓድዋ በእግራቸው ተጉዘዋል…

1ኛ / ጋዜጠኛና የፊልም ባላሙያው ብርሃኔ ንጉሴ
2ኛ/ ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ዓለሙ ከኢትዮጲካሊንክ
3ኛ/ መሐመድ ካሣ (ኬር ኤቨንትስ ኤንድ ኮሙኒኬሽን – የባህልና የኪነ ጥበብ ፕሮሞተር)
4ኛ/ ሙሉጌታ መገርሣ (ደብሊው) (የፊልም ባለሙያ)
5ኛ/ አለምዘውድ ካሳሁን (የካሜራ ባለሙያ)
6ኛ/ ያሬድ ሹመቴ (የፊልም ባለሙያ)

ጎልማሶች ወርቅ ጊዜያቸውን ሰውተው በአንድ ውለው በአንድ አስበው ለታሪካዊው 118 የዓድዋ ድል መታሰቢያ ልዩ ዝግጅት አቅደው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴው አመሩ። ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 በግምት ወደ 40 ቀን የሚወስደውን ረጅሙን ወደ ዓድዋ የሚያደርጉትን የ1,006 ኪሎ ሜትር ርቀት ጉዞ ከአዲስ አበባ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አደባባይ በአንድ እርምጃ ጀምረው ዛሬ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበዋል።

ታላቁን የዓድዋ ድል ለማዘከር “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም” የሚል መፈክርን ቀዳሚ መመሪያ አድርገው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድግበው እያውለበለቡ ይህን ጉዞ ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋና አላማ 118ኛ የዓድዋን ድል ቀን በዓድዋ ለማዘከር እንደሆነም ሰምተናል። ትንታግ ጎልማሳ ወንድሞቻችን በትጋት የጀመሩትን ጉዞ ሊያጠናቅቁ የቀራቸው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው።

አራዳ ጊዮርጊስ ከአጤ ምኒልክ አደባባይ የተጀመረውን ጉዞውን ቀደምት አባቶቻችን የዓድዋ ድል ከ118 አመት ለማስገኘት እየተሰባሰቡ የዘመቱባቸውን ከተሞች ተከትሎ የሚከወን መሆኑ ታሪካዊውን የሃገር ወዳድ ወንድሞች ጉዞ ልዩ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው በማውለብለብ ጉዟቸውነወ በመከወን ላይ የሚገኙት ተጓዦች በየደረሱባቸው ታሪካዊ ከተሞች ሞቅና ደመቅ ያለ አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን ያን ሰሞን ተጓዦች መረጃውን አድርሰውናል።

እኒህ የብርታት ተምሳሌት የሚሆኑን ትንታግ ወንድም ተጓዦች ቃል አቀባይ ተጓዦች ያን ሰሞን ኮንቦልቻ እንደደረሱ በሰጠው ማብራሪያ እንዲህ በማለት ያስረዳል “… ማለዳ በአድዋ ድልድይ ተሻገሩ፡፡ ለገጣፎ – ለገዳዲ – ሰንዳፋ – በኪ – አለልቱ – ፍቼ – ሐሙስ ገበያ – ሸኖ – ሰምቦ – ጥያኪ – ጫጫ – ጠባሴ – ጅሁር መገንጠያ – ደብረ ብርሃን – አንኮበር መገንጠያ – ቀይት – ጉዳ በረት – ጣርማ በር – ደብረ ሲና – ጭራ ሜዳ – አስፋቸው – ሸዋ ሮቢት – አጣዬ – ከሚሴ – ሃርቡ – ፎንተኒና – አልፈው ኮምቦልቻ ደርሰዋል፡፡ በመንገድ ላይ አጤ ምኒልክ እና ሠራዊቱ (የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች) ለአገርና ለሕዝብ ዘብ የቆሙ ወታደሮች የደረሰባቸውን መከራ ይዘክራሉ፡፡ የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ድል ነው፡፡ በዚህ ድል አፍሪካዊያን ይኮራሉ፡፡ የዚህ ድል ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በዚህ የታሪክ ሰንሰለት ተምሳሌቱን ዳግም ለዓለም ለማወጅ ታሪካዊ ጉዞ እያደረጉ ናቸው፡፡ ተጓዦቹ – ሰንቃጣ ወይንም (ስንቅ አጣን) ሲደርሱ የታሪካዊ ጉዞ ፈተና ይቀምሳሉ፡፡ (ይራባሉ – ይጠማሉ፡፡) የስድስቱ ተጓዦች ለመራብ – ለመጠማት መዘጋጀታቸው ልዪ የሚያደርገው ስንቅ እያላቸው መሆኑ ነው፡፡ ስድስቱ የእግር ተጓዦች የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም አድዋ ይደርሳሉ፡፡ 118ኛ የዓድዋ ድልን በአድዋ ተራራ ያከብራሉ፡፡ በርካታ ታሪካዊ መዘክሮችን አዘጋጅተዋል፡፡ ለምሳሌ ሶሎዳ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ በክብር ለማቆም አቅደዋል፡፡ የአድዋ ክብረ በዓል ላይ የበዓሉን ማብሰሪያም መድፍ ይተኮሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጓዦቹ – ‹‹በየደረስንበት የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገልን ነው፡፡ !›› ብሏል ! ጉዞው አሁንም ቀጥሏል … እኒህ ወንድሞች ትጋትና ቁርጠኝነትን በትጋት እና በተግባት ለማሳየት ፣ የአባቶቻችን ታሪካዊ ተጋድሎ በክብር ለማስታወስ “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !” ሲሉ የእግር ጉዞ አኩርቶኛል! በእርግጥም እኒህ ወንድሞቻችን ለአባቶች ተጋድሎ ተድበስብሶ እንዳይቀር እና አንጸባራቂውን ድል ለቀጣዩ ትውልድ በክብር ለማውረስ ስራ በመስራታቸው ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል! ይህን መሰል ፋና ወጊ ታሪክ ለመስራት መታደል በእርግጥም መታደል ነው !

አዎ ! እኔም በአድዋ ድል እኮራለሁና “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !” እላለሁ !
የዓድዋን ድል በክብር እዘክራለሁ ! እናዘክራለን !

ክብር ለደሙ ለቆሰሉና በክብር ለሞቱ ሰማዕታት ! ክብር ለጀግኖቻች አርበኞቻችን !

ከሰብር ለእምየ ምኒሊክ ! ክብር ለእቴጌ ጣይቱ !

ክብር ለኢትዮጵያ !

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ


በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ የካናዳ የፓርላማ አባላትና እውቅ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦታዋ ተደረገ

$
0
0

Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል።

በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ካናዳውያን እንዲሁም ከበርካታ አፍሪካ ሀገራት የመጡና በአህጉሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ይመለከተናል የሚሉ ትውልደ አፍሪካ ምሁራንን ጭምር ያካተተ ነው። በዚህ ድርጅት ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የሚሳተፉበት ሲሆን ከመስራች አባላት አንዱ ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው።
የስብሰባው ዓላማ ድርጅቱን ከፓርላማ አባላትና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉና አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ካናዳውያን ጋር ማስተዋወቅ ሲሆን። በዋነኛነትም ይህ ህገወጥ የመሬት ነጠቃና ቅርምት በሚደረግባቸው አገሮች ውስጥ የካናዳ ግብር ከፋይ ሕዝብ ገንዘብ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳርያ በመሆን ለአምባገነን መንግስታት እንዳይውል ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ማሰባሰብያም ነበር።

ስብሰባውን በንግግር የከፈቱቱ የፓርላማ አባል የተከበሩ ሄለን ላቫንዴር ሲሆኑ ለስብሰባው ዝግጅትና ስኬትም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው። እርሳቸውም የጉዳዩን አሳሳቢነት አጽንኦት ሰጥተው ከተናገሩ በሁዋላ መድረኩን ለመስራችና የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆኑት ለፕሮፌሰር ሮይ ኩልፔፐር አስተላልፈዋል። ሮይም የስብሰባውን ተካፋዮች አመስግነው በበኩላቸው ይህ ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስፈልጉባቸውን ጉዳዮች በመዘርዘር የድርጅቱ ማለትም የ CELADA ዓላማና ግብም በመላው አፍሪካ እየተከናወነ ባለው የመሬት ነጠቃና ቅርምት ዙርያ ያጠነጠነ መሆኑን አስረድተው ለእለቱ ተናጋሪዎች እድል ሰጥተዋል።

የመጀመርያው ተናጋሪ እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የተከበሩ ኦቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ ከንግግራቸው ቀደም ሲልም ጥቂት ደቂቃዎች የሚፈጅ በሊቢያ አማካይነት በማሊ ውስጥ የተደረገው የመሬት ቅርምት የሚያደርሰውን አፍራሽ ተጽእኖ፣ የሕዝቡን ቁጣና ተቃውሞ የሚያመለክት ፊልም እንደ መግቢያ ካሳዩ በሁዋላ የችግሩን ጥልቀትና ውስብስብነት በማስረዳት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ያለውንም ነገር በመጥቀስ ካናዳ ልትወስድ የሚገባትን አቋም፣ ሊኖራት የሚገባውን ፖሊሲ በማሳሰብ ንግግራቸውን አብቅተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋምም የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያመለክት በመሆኑ ካናዳም የምትለግሰውን እርዳታ በዚሁ መነጽር ትመለከተው ዘንድ አሳስበዋል።

የማዳጋስካር ተወላጅዋ የ CELADA አባል የሆኑት ማጊ ራዛፊምህኒ ለበርካታ አመታት ለUNICEF ያገለገሉ ሲሆኑ በማዳጋስካር እየሆነ ያለውን የሀገሪቱ ፖሊሲ አገም ጠቀም የሆኑ እርምጃዎችን ቢወስድም አደጋው የከፋ መሆኑን በመግለጽ እርሳቸውም ተመሳሳይ ጥሪ ለካናዳ ሕዝብና መንግስት አቅርበዋል።

በመሬት ቅርምት ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ በተለያየ መስክ ስኬትን ያገኘው የኦክሰፋም ካናዳ ዳይሬክተር የሆኑት ሮበርት ፎክስ በበኩላቸውም የሁኔታውን አሳሳቢነትና አደገኛነት በመግለጽ መሬትም እንደማንኛውም ሸቀጥ ሊሸጥ ሊለወጥ ይችላል በሚል መርህ ሕዝቡን ማፈናቀልና ሀብት ማጋበስ በሚፈልጉ ሰዎች የገንዘብ ፈሰስና ለሀገራቸው ሕዝብ ደንታም በማይሰጣቸው ባለስልጣኖች ግፍ እየተፈጸመ መሆኑንና አብራርተው ምንም እንኳ ችግሩ ዛሬ የአፍሪካ ቢሆንም ነገ ግን ሁላችንንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ብለዋል። በመቀጠልም መሬትን እንደ ተቀማጭ ሀብት የሚያዩት ከበርቴዎች ትላልቅ የእርሻ መሬቶችን በልማት ስም በመግዛት አጥረው ካለምንም ልማት በመያዝ የመሬት ዋጋ የሚያሻቅብበትንና ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱበትን ጊዜ እየጠበቁ ነው በማለት በአፍሪካ ድሀ ገበሬዎች ላይ የሚሰራውን ግፍ ተናግረዋል። ለዚህም ምሳሌያቸው ሞዛምቢክ ነበር። ሞዛምቢክ ውስጥ ለውጭ ባለሃብቶች ከተሰጠው መሬት ውስጥ 70% የሚሆነው ታጥሮ የመሬት ዋጋ ውድ የሚሆንበትን ጊዜ የሚጠብቅ ሸቀጥ ሆኗል ብለው ነበር። በዚህም ምክንያት መልማት ያለበት መሬት በከበርቴዎች ተይዞ ሳለ ሚሊየኖች ግን በረሃብ ያልቃሉ የሚል አንድምታ ያለውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንደ ደቡብ ሱዳን ያለ ገና የጸና መንግስትና ፖሊሲ የሌለበት ሃገር ውስጥ በሀገሪቱ ውስጥ መልማት ካለበት መሬት ውስጥ 10% በውጭ ኢንቨስተሮች ተይዟል። ይህ እጅግ በጣም ሰፊ መሬት ነው። ኢትዮጵያን እንደምሳሌ በጠቀሱበት ንግግራቸውም የ140 የእግርኳስ ሜዳን የሚያህል ስፋት ያለው የአበባ እርሻ ልማት ውስጥ በርካታ ወጣት ሴቶች በቀን ሰራተኛነት ተቀጥረው በአለም ላይ ያሉ ኬሚካሎችን ሄርቢሳይድ፣ ፈንጂሳይ፣ ኢንሴክቲሳይድ፣ ባክቴሪሳይድ ወዘተ በቆዳቸው በሳንባቸው እየሳቡ ያለ እድሜአቸው የሚረግፉ እንዲሆኑ መገደዳቸውን በመግለጽ የመሬት ቅርምቱ በተለይም በሴቶች ላይ ያስከተለውን አደገኛ ተጽእኖ ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ተጋንኖ የሚነገረው የእርሻው ኢንቨስትመንት የስራ እድል ይፈጥራል፣ የምግብ ምርት ያሳድጋል ለማህበራዊ አገልግሎቶች አመቺ እድል ይሰጣል የሚባሉት መደለያዎች ፈጽሞ ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ሲገልጹ በመሰረቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሰራተኛ ቁጥርን በመቀነሱ እንጂ በስራ እድል ፈጣሪነቱ አይታወቅም ብለዋል። ኢንቨስተሮችም የሀገሬውን ህዝብ የመቀለብም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚሸጥ ምግብ የማምረት ግዴታም የሌለባቸውና እንዲያውም የእርሻ መሬትን በአብዛኛው ለምግብ የሚሆን ሳይሆን ለስኳርና የነዳጅ ዘይት ለማምረቻ የሚጠቀሙበት መሆኑን ገልጸዋል። ኮካኮላ የስኳር ምርቱን በዚህ ጉዳይ ከሚጠቀሱ አምራቾች ባለመግዛት የጥፋቱ ተካፋይ ላለመሆን የወሰደው እርምጃ አበረታች መሆኑንም ለተሰብሳቢው ገልጸው የመሬት ቅርምቱ ለአጭርጊዜም ይሁን ለረጅም ጊዜ ሕዝባዊ ጠቀሜታ እንደሌለው አክለዋል። በመጨረሻም ካናዳም ሆነች የበለጸጉ ሀገሮች በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወስዱት አቋም ወቅታዊም አስፈላጊም መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።

ሌላው ተናጋሪ ብሩስ ሙር ሲሆኑ የ Canadian Hunger Foundation (CHF) ዳይሬክተር የነበሩና በተለያዩ አንጋፋ ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ አባልነት በዳይሬክተርነት ያገለገሉና በአሁኑ ወቅት የ ‘North South Institute’ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የ Forum of Democratic Global Governance (FIM) የቦርድ አባል እንዲሁም የ ‘Transparency International’ አባል ናቸው። ብሩስ ሙር በአስከፊው የኢትዮጵያ ድርቅ ወቅት ለውጪ ሰዎች መጓጓዝ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ እስከ ኮረም ድረስ ዘልቀው የችግሩን ስፋትና ክብደት ከተመለከቱ በሁዋላ ለካናዳ መንግስትና ለዐለምም የችግሩን መጠን ያሳወቁ በዚህም ሳቢያ ከፍተኛ እርዳታ ለኢትዮጵያ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ያደረጉት ሲሆኑ በዚሁ የመሬት ቅርምትና የለጋሽ አገሮች ሚና በተለይም ካናዳ ሊኖራት ስለሚገባው ፖሊሲ አጠር ያለ ግን ጥልቅና ጠበቅ ያለ አስተያየት ሰንዝረዋል። እንደ እርሳቸው አባባልም የከተማዎች የከፋ ድህነት የገጠሩ ጉዳይ ችላ መባሉን አመልካች ነው በማለት ተናግረዋል። በማከልም ከ 2000 -2010 ዓ ም በሰነድ የሚታወቅ የመሬት ይዞታ ዝውውር 200 ሚሊየን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 134 ሚሊየኑ በአፍሪካ ውስጥ ነው። ይህም ጉዳዩ ለ አፍሪካ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ያመለክታል። የምግብ እጥረት ከተከሰተ በሗላ ሳውድአረብያ ከ ኢትዮጵያ ብዙ መሬት ገዝታ ነበር በጣም የሚገርመው በ2009 ዓም ሳውዲ የመጀመርያ ምርቷን ከኢትዮጵያ በወሰደችበትና ሕዝብዋን በመገበችበት ወቅት ወርል ፉድ ፕሮግራም አምስት ሚሊየን የ ኢትዮጵያ ረሃብተኞችን መግቦ ነበር። ይህ የሚናገረው ትልቅ እውነት አለ፣ ይህ የሚያመለክተው ትልቅ ክፍተት አለ በማለት የተሰማቸውን ገልጸዋል።

ሌሎች ተሰብሳቢዎችም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ ጥልቅና ውስብስብ ጉዳይ ለፓርላማ አባላት ቀርቦ ካናዳ ልትወስድ ስለሚገባት አቋም በቂ ግንዛቤ ማስጨበጡ እንደ አማራጭ ቀርቧል። በተለይም የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለሕዝብ መፈናቀል ተጨማሪ መሳርያ እንዳይሆን ካናዳውያን ኢንቨስተሮችም ይህንን በመረዳት እንደዚህ ያሉ አገሮች ውስጥ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የሚያስከትለውን ተጽዕኖና የሚያመጣውንም አደጋ ልብ እንዲሉ እንዲደረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲያደርግ በየአቅጣጫው መረባረብ አስፈላጊነቱን ጠቅሰዋል።

በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ የ CELADA ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮይ በዚህ የመሬት ቅርምት ዙርያ በዚህ ጉባዔ ላይ የተገኛችሁ በጉዳዩም ላይ በቂ እውቀት ያላችሁ ጠበብቶች አላችሁና የኤክስፐርት ምስክርነታችሁን ለፓርላማ አባላት በማቅረብ ይህንን ውስብስብ የሆነ ነገር በማስረዳት እንደምትተባሩ አምናለሁ። በየአቅጣጫው በያዝነው ስራ እንበርታ ለዚህ አንገብጋቢ ችግር መፍትሄ ለማስገኘት የየበኩላችንን እናድርግ በማለት ተሰብሳቢዎቹንና ለዚህ ስብሰባ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው የእለቱ መርሃግብር በዚሁ ተጠናቋል።

የአድዋ ድል እና የአጼ ምኒልክ ሃውልት ትዝታችን!ዳዊት ከበደ ወየሳ –አትላንታ

አያስቅም! አጭር ወግ ክንፉ አሰፋ

$
0
0

በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው – ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ፣ ጾም በኩዳዴ» ይባል ነበር። ይህ አባባል አሁን መኖ በዘዴ በሚል ተቀይሯል። መቼም ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው።

ጋዜጠኛ አቤል አለማየሁ በቅርቡ ባሳተመው “የአዲስ አበባ ጉዶች” የሚል መጽሃፉ ላይ ስለዚህች ታሪካዊ ምግብ ቤትም ትንሽ ብሏል። የምግብ ቤትዋ ባለቤት “ገሊላ ምግብ ቤት” የሚለው ጽሁፍ በከፊል አጥፍተውታል። አሁን ምግብ ቤት የሚለው ተነስቶ “ገሊላ” የሚለው ብቻ ነው የቀረው። ጉዳዩ በህግ እንዳያስጠይቃቸውም ይመስላል ጽሁፉ ላይ ነጭ ቀለም ነው የደፉበት። የምግብ ቤቷ ትራንስፎርሜሽን መሆኑ ነው። የዚህ ትራንስፎርሜሽን ትርጉም የገባቸውም ሆነ ያልገባቸው ተስተናጋጆች ወደ ገሊላ (ምግብ ቤት) ጎራ ማለታቸው አልቀረም። የዚህች ቤት አዲሶቹ ደንበኞች በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ወጣቶች ናቸው። እዚያ ሲገቡ ሰልፍ ይጠብቃቸዋል። ይህች ስፍራ ስፋትዋ ለምግብ ቤት በቂ ነበር። ለቀን አልጋ አገልግሎት ግን ትንሽ ስለጠበበች ነው ሰልፍ ሊከሰት ያቻለው። ተራ የደረሳቸው በመጀመርያ ሜኑ ይቀርብላቸዋል። የቀድሞው የምግብ ሜኑ በወይዛዝርት ፎቶ ተቀይሯል።….
ይህ ዘርፍ አሁን ከኮብልስቶንም የበለጠ አዋጭ እየሆነ በመምጣቱ፤ ምግብ ቤቶች የአገልግሎት አይነታቸውንና የሜኑ ደብተራቸውን እየቀየሩት መሆናቸው እውነት ነው።

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ወሬ መሰማት ከተጀመረ ትንሽ ዘገየ። ይህ አዋጅ ከተሰማ በኋላ የእርሻ፣ የኢንዱስትሪና የሃይል አቅርቦቶች በሙሉ በአስር እጥፍ ነው ያደጉት። እድገታቸው ታዲያ ወደላይ ሳይሆን እንደባህር ዛፍ ወደታች ነው። በእርግጥ የለውጥ ምልክቶች በሀገሪቱ እየታዩ ነው ከተባለ የዝሙት ኢንደስትሪው በደንብ ለመጠቀስ ይችላል። ይህ ዘርፍ በተለይ ከአረብ ሃገር የበርካታ ቱሪስቶች መስህብ ሆኗል። በዚያን ሰሞን አንድ በአዲስ አበባ የሚታተም ጋዜጣ ድንግልና በአስር ሺህ ብር እንደሚሸጥ አስነብቦን ነበር። አንዲት ደናግል ለዚህ ጸያፍ ነገር ስትዳረግ ድህነትን ብቻ አይደለም የምትሰናበተው። የማንነትዋ መግለጫ የሆነው የሞራል ጉዳይም አብሮ ይሄዳል።

የአገልግሎት ክፍያው የሚከናወነው በዶላር መሆኑ ደግሞ በዚህ ዘርፍ ላይ የግሽበት ችግር አይደርስበትም። ኢንደስትሪው ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ምንጭም ስለሆነ ይመስላል ከመንግስት በኩል እየተበረታታ የመጣው። የውጭ ምንዛሪ በማስገኘቱም «ልማታዊ» ተግባር ተብሏል። መንግስት ከዚህ ሴክተር ምን ያህል እንደሚጠቀም በውል ባይታወቅም አገልግሎት ሰጭዎቹ (ደላሎቹ) ግን ሃብታም እንደሆኑ ይነገራል።

ወደ ጎተራ አካባቢ በተሰራው የኮንዶሚንየም መንደር ደግሞ ሌላ ታሪክ አለ። ይህ ኮንዶ «ፌስቡክ» የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ለምን ፌስቡክ እንደተባለ ለማወቅ ብዙም ግዜ አይፈጅም። የቆነጃጅት ኮረዳዎች ሁሉ መሰብሰቢያ ነው። ትምህርት አቋርጠው ወይንም ከቤተሰብ ተኮራርፈው የተሰወሩ የቤት ልጆችን ለማግኘት ወላጆች ወደ ፖሊስ ጣብያ መሄድ አቁመዋል። ወደ ጎተራው «ፌስቡክ» ብቅ ካሉ የጠፉትን ሁሉ እዚያ ያገኙዋቸዋል። ባለሃብቶች እና ባለግዜዎች ወጣት ሴቶችን እየወሰዱ እዚያ እንደ እቃ ያስቀምጧቸዋል። ይህን የሚያጫውቱኝ ወዳጆቼ እየሳቁ ነበር የነገሩኝ። ነገሩ ያሳዝናል እንጂ አያስቅም!
በዚህ ልማታዊ «ቢዝነስ» ውስጥ ጨቅላዋ ማሪቱም ገብታበታለች። የማሪቱን ነገር ማንሳቱ ብቻ ሁኔታውን በደንብ ይገልጸዋል።

ይህች ጨቅላ ጉብል በወግና በማዕረግ ያደገችበትን ቀዬ ለቃ ከወጣች አመታት አልፈዋል። በሃገሬው ሹሩባ ተጎንጉኖ የነበረው ያ ዞማ ጸጉርዋ በፈረስ ጸጉር ተተክቷል። እንደምንጭ ውሃ ጥርት ብለው የነበሩት አይኖችዋ በህብረቀለማት ኩል ተበርዘዋል። በአረንጓዴ ካኪ የተሰፋላት ሽንሽን ቀሚሷ ካላይዋ ላይ ተጥሎ በዘመናዊ ሚኒ-ስከርት ተቀይሯል። ኮንጎ ጫማዋም በሂል ተለውጦ ምቾትዋን ወስዶባታል። ማሪቱ አሁን አዲስ ዓለም ውስጥ ናት። እንደ አሻንጉሊት ሁለመናዋ ሰው-ሰራሽ ሆናለች። ስምዋም ተቀይሯል። አሁን ሜሪ ናት። ማሪቱን ሜሪ ለማድረግ ደላሎቹ ችግር የለባቸውም። ዘመናዊ ልብስ እንጂ ዘመናዊ ስም ወጪ አያስወጣም። ለማሪቱ ከሜሪ ይልቅ ማርታ ወይንም መስከረም ይቀርብ ነበር። እነዚህን ሁለት እርከኖች ዘልሎ ፈረንጅኛው ላይ መሄዱ፣ ምን ያህል ፈጣን የእድገት ጎዳና ላይ መሆናችንን ያሳየናል።

እርግጥ ነው። ማሪቱ በትምህርቷ ገፍታ ሰዎች የደረሱበት ለመድረስ ችሎታውና ፍላጎቱ እንጂ አቅሙ አልነበራትም። እድሜዋ ለአቅመ ሄዋን እንደደረሰ እንደከተሜ እኩዮችዋ ለኮሌጅ ትምህርት አልታደለችም። ወላጆችዋ ብዙም ቅሪት የላቸውም። ለችግር ግዜ አስቀምጠዋት የነበረችውን ገንዘብ ለ«ህዳሴው ግድብ» መዋጮና ቦንድ መግዣ አውለዋት በተስፋ መኖር ጀምረዋል። አዎ ተስፋቸውን ሁሉ በህዳሴው ላይ አድርገዋል። ግና ተስፋ የእለት ጉርስ አይሆንም።
ሜሪ ድህነትን ለማሸነፍ ስትል የማትወደውን ስራ የመስራት ውሳኔ ላይ ደርሳለች። በውሳኔዋ እንዳትጸጸት የሚያጽናናት ነገርም አለ። «ትምህርት ምን ያደርጋል? የተማረ የት ደረሰ?» የሚለው የወላጆችዋ አባባል በእምሮዋ ውስጥ ያቃጭል ነበር። ይህንን አባባል እንደ ጥቅስ እቤትዋ ላይ ሰቅላዋለች። ከህሊና ወቀሳ ለመሸሽ ስትፈልግ ቀና እያለች ይህንን ጥቅስ ታነብና ትጽናናለች። ታላቅ ወንድምዋ የኢንጅነሪንግ ምሩቅ ነው። የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ከልጅነቱ ጀምሮ ይመኝ የነበረውን ስራ ሊያገኝ አልቻለም። ይህም፣ ወላጆቹ በትምህርት እና በእውቀት ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸው ነበር። የኋላ-ኋላ ግን የስራ አጡን ጎራ ለማምለጥ አዲስ ስልት ቀየሰ። የኢህአዴግ አባልነት ፎርም ሞልቶ በጥርነፋ መያዙ ግድ ሆነበት። ከዚያም በ«አነስተኛና ጥቃቅን» ዘርፍ ተደራጅቶ ኮብልስቶን ላይ ተሰማራ። ድንጋይ ሲፈልጥና ሲሸከም ለመዋል መስፈርቱ መብዛቱ ሜሪን አምርሯታል። በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ መሆን፣ ከዚያ የአባልነት ፎርም መሙላት፣ ከዚያ በአነስተኛና ጥቃቅን መደራጀት፣ ከዚያ መጠርነፍ…።

በደርግ ግዜ ኑሮ መሯቸው በሱዳን ድንበር ሊጠፉ የነበሩ ወጣቶች፤ ጠረፍ ላይ ሲደርሱ አንድ መፈክር አዩ። “ትግላችን መራራ፣ ጉዟችን እሩቅ፤ ግባችን ረጅም ነው!” የሚል መፈክር። ወጣቶቹ ተስፋ ቆርጠው ጉዟቸውን አቋረጡ። ከዚያም ጫካ ገቡ ይባላል። ያሁኑ ዘመን ጫካ «ቼቺንያ» የሚባለው መንደር ነው። ሜሪም ወንድሟ ያለፈበትን ረጅም መንገድና አስቸጋሪ መስፈርቶች ማሟላት ስለሚሳናት አጭሩን መንገድ መምረጥ ነበረባት።
በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅር የሚመጡ ቱሪስቶች፣ አየር ባየር ነጋዴዎችና ባለስልጣናትም ጎራ እያሉ የሚዝናኑባቸው ማሳጅ ቤቶች እንደአሸን ነው የፈሉት። ከታይላንድ የዝሙት እንደስትሪ የተወረሱ “ሃፒ እንዲንግ” ተግባራት የሞራል ውድቀታችን ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። እንደዚህ አይነቶቹ ነውር ነገሮች ሁሉ ገቢ እስካስገኙ ድረስ አዋጭ ስራዎች ናቸው። በልማታዊው መንግስታችንም ይበረታታሉ።
ሁሉን ነገር ተነጠቀን የቀረችን አንዲት ነገር ሞራል ብቻ ነበረች። የሞራል እሴቶቻን ግን እንዴት ነው እንዲህ የራቁን? መልካም ስነ-ምግባር፣ ጨዋነት፣ ግብረ-ገብነት እና ፈሪሃ እግዚአብሄር የጠፋበት ህብረተሰብ መጨረሻው ምን ሊሆን ይችላል? ሃገር ማለት መሬት ብቻ አይደለም። ሃገር ማለት ሕዝብና አንድ ሉዓላዊ አካል ብቻም አይደለም። መልካም ስርዓት እና የሞራል እሴት የሌለው ሃገር ከማፍያ ጉረኖ የተሻለ አይሆንም።
ሌት ተቀን የምንደኖቅርበት እድገትና ትራንስፎርሜሽም የሚመጣው በመጀመርያ ሃገር ስትኖር መሆኑን መገንዘብ ይበጃል። …. የሃይማኖት አባቶችስ ይህንን እያዩ ለምን ዝም አሉ? ስራቸው ፍትሃት ማድረግ እና እና ግብር መሰብሰብ ብቻ መሆን ነበረበት? ወይንስ እነሱንም ይኸው ልማታዊ አስተሳሰብ ተጸናወታቸው?

አንድነት –አንድነት በአሜሪካ ካሉ ደጋፊዎቹ ጋር መከረ !

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል።

«በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ። ኢትዮጵያን በልቡ ይዞ የሚኖር ነው» ያሉት ኢንጂነር ግዛቸው፣ በዉጭ ያለው ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ሰላም፣ ዲሞክራሲ ፣ ለዉጥ እንዲኖር እያበረከተ ስላለው ትልቅ አስተዋጽ አመስግነዋል። በባህር ዳር የተደረገው በሌሎች ከተሞች በተጠናከረ መንገድ ለማድረግ ፓርቲው እቅድና አላማ እንዳለው የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው፣ በቅርቡ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት አይነት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ እና የሚሊዮኖች ድምጽ ለላንድ ሪፎርም በሚል ፣ አገር ሰፊ እንቅስቃሴዎች እንደሚደረጉ አሳዉቀዋል። ይህ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄዎች፣ በአዲስ አበባ ተጀምሮ፣ አዋንሳ፣ መቀሌን፣ ደሴን፣ ደብረ ታቦርን፣ አዳማን፣ አሶሳን፣ ቁጫን ፣ ድሬደዋን፣ ጂንካን በአጠቃላይ ወደ 12 የሚሆኑ ከተሞችን የሚያዳርስ ሊሆን እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፣ የእንቅስቃሴው ማጠቃለያው እንደገና በአዲስ አበባ እንደሚሆን ከኢንጂነር ግዛቸው ማብራሪ ለማወቅ ተችሏል።

በነዚህ ሁሉ ከተሞች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ የገንዘብ አቀም እንደሚጠይቁ ያስረዱት የአንድነት ሊቀመንበር፣ በዉጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም አሳስበዋል። የሚሊዮኖች ንቅናቄ፣ አንድነት ፓርቲ ቢጠራዉም፣ «የሕዝብና የሚሊዮኖች ንቅናቄ» ያሉት ኢንጂነር ግዛቸው በዉጭ ያለው ማህበረሰብ ትኩረት ሰጥቶት፣ ሙሉ ድጋፉን እንዲያበረክት ፣ ያሉ የድጋፍ ድርጅቶችም ቀበቷቸውን ታጥቀዉ አክቲቭ እንዲሆኑ፣ በዉጭ ያሉ ሌሎች የሲቪክ ማህበራምት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ተማጽኖ አቅርበዋል።

በስብሰባዉ የነበሩ የድጋፍ ድርጅት መሪዎችና ደጋፊዎች፣ በተደጋጋሚ የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ላለው እንቅስቅሴዎች ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ሲሆን፣ በተለይም በባህር ዳር የተደረገው፣ ከልብ እንዳስደሰታቸው ተናገረዋል። ተሰብሳቢዎቹ በርካታ ጥይቄዎችን በተለያዩ ጉዳዮች ያቀረቡ ሲሆን፣ ኢንጂነር ግዛቸውም ጊዜ ወስደው ሰፋ ያለ መልስ ሰጥተዉበታል።

አቡጊዳ –እስክንደር የጻፈው ለነጻነት ነው፤ የሞራል ድፍረት ያለው ነው –ጆን ኬሪ

$
0
0

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ሽብርተኛ ነህ በሚል መስረት የሌለዉ ክስ ተከሶ የ18 አመት እስራት ፣ በፖለቲካ ዉሳኔ እንደተፈረደበት ይታወቃል። የአሜሪካው የዊጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄን ይቃወማሉ። ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን፣ ለነጻነቱ የጻፈ ሲሉ፣ ከሌሎች አንጋፋ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እኩል አስቀምተዉታል።1394241_527514827333456_269824761_n

የጆን ኬሪ ይፋዊ ዘለፋ፣ የጋዜጠኛ እስክንደር ሆነ የሌሎች በርካታ ጋዜጠኞችና የሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መታሰር፣ ኢሕአዴግ በአገሩ ካሉ ዜጎቹ ጋር ብቻ ሳይሆን ከበርካታ የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር እንዲጋጭ እያደረገዉ እንዳለ የሚያመላክት ነው።

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ዋና ደጋፊ እንደሆነች ይታወቃል። በርካታ የአገዛዙ ቱባ ቱባ ባለስልጣናር በአሜሪካ ቤት ያላቸው፣ በአሜሪካ ባንኮች ገንዘብ የሚያሰቀምጡ እንደሆነ ይነገራል። በአመት ከ370 ሚሊዮን ዶር እርዳታም አሜሪካ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ይታወቃል።

በአምባሳደሯ ወይም በስቴት ዲፓርትመንት በአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊ ደረጃ ሳይሆን፣ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደረጃ የነ እስክንደር ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት፣ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጆን ኬሪ፣ በአደባባይ እስክንደርን መጥቀሳቸው፣ ምን ያህል በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከላይ ያሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት እያሳሰበ እንዳለ የሚያሳይ ነው።

ጆን ኬሪ የሚከተለውን ነበር ያሉት፡

“The truth is that some of the greatest accomplishments in expanding the cause of human rights have come not because of legislative decree or judicial fiat, but they came through the awesomely courageous acts of individuals, whether it is Xu Zhiyong fighting the government transparency that he desires to see in China, or Ales Byalyatski, who is demanding justice and transparency and accountability in Belarus, whether it is Angel Yunier Remon Arzuaga, who is rapping for greater political freedom in Cuba, or Eskinder Nega, who is writing for freedom of expression in Ethiopia, every single one of these people are demonstrating a brand of moral courage that we need now more than ever.”

ሙሉዉን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑና ወደ 12፡30 ፎርወርድ ያደርጉ !

ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ ገለታው ዘለቀ

$
0
0

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።

በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣ እንደገና መልሰን የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን። እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው።

የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን። በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው። ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው። “ኢትዮጵያዊያን በህግ ፊት እኩል ናቸው” ይላል። ከሁሉ በላይ ደግሞ የ1995ቱን ስናይ “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው” ብሎ እጅግ ኣጠንክሮ ለዜጎች መብት መቆሙን ይደነግጋል። በውነቱ ይህ ኣንቀጽ ብቻውን ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዋስትና ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ተግባራዊው እውነት ደግሞ ለብቻው በተቃራኒው ተንሰራፍቶ ይታያል። ይህ ለምን ሆነ? እንዴት እንዲህ ሊሖን ይችላል? ብለን ነው መጠየቅ ያለብን። እንዲህ ስንጠይቅ የችግሩ ዋና ጉዳይም የስርዓት እጦት ሳይሆን ሌላ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። በርግጥ ለወደፊቱዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ስርዓት ማምጣት ያስፈልጋል። በተለይም ብዙህነቱዋን ተንከባክቦ የሚይዝ ማህበራዊ የፖለቲካ ስርዓት ያሻናል። ያ ማለት ግን ከችግራችን እንድንወጣ ብቻውን ዋስትና ነው ማለት ኣይደለም። የቱንም ያህል ጥሩ ስርዓት ዘርግተን ከችግራችን ሳንወጣ ልንቆይ እንችላለን። ርግጥ ነው የማንነት ፖለቲካ ማህበራዊ ቀውስን ያመጣ ችግሮች የበለጠ እንዲነዱ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ መንግስት ውድቀት በሁዋላ ከዚህ የፖለቲካ መዋቅር መውጣታችን ለመፍትሄ ትልቅ በር ኣለው። ይሁን እንጂ ኣሁንም ቢሆን የቱንም ያህል ቆንጆ ስርዓት እናምጣ ኢትዮጵያን ከመከራና ከርሃብ የሚያወጣት እሱ ብቻውን ኣይደለም። ታዲያ ምንድነው? የሚል ጥያቄ መምጣት ኣለበት። ኣዎ፣ ዋናው የሃገራችን ችግር ያለው የፖለቲከኖች ስብእና ተክለሰውነት ወይም ፐርሰናሊቲ ጋር የተገናኘ ነው።

ሃገራችን ከችግር እንድትወጣ ከተፈለገ የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። የችግሮቻችን ቁንጮም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እጦት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስንል ኣንድ ፓርቲ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የፍርድ ቤቱን ልጓም ለቀን መልሶ ከበላንም ይብላን፣ በራሳችን ላይ ይፍረድብን፣ ብሎ በራስ ላይ የመወሰን ኣቋም ነው። ወታደሩን ኣገርህን ጠብቅ የፓርቲ ጠባቂ ኣይደለህም ኣንተ ኣገር ጠባቂ ነህ ለማለት የፖለቲካ ሰዎችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ፖሊሱን፣ ባንኩን፣ ሚዲያውን ሁሉ ልጓሙን ለቆ በሙያህ ኣገልግል ብሎ መወሰን ሲቻል ነው ከገባንበት ኣረንቋ የምንወጣው። የናፈቀንን ዴሞክራሲ በህይወት የምናየው። ጥያቄው ይህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዴት ሊመጣ ይችላል ነው። የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ከራስ ጥቅምና ዝና በላይ የህብረተሰብን ዝናና ጥቅም በተጠሙ ሰዎች ሊነቃነቅ ይችላል። ኣንድ ቁርጠኛ መሪ ኣገር ሊለውጥ ይችላል። በታሪክ የታዩ ኣንዳንድ ቁርጠኛ መሪዎች በየሃገሩ ተነስተው ጥሩ መሰረት እየጣሉ ኣልፈዋል። በሃገራችንም የተጠማነው ይህንን ነው።

በኣሁኑ ጊዜ ተቃዋሚው ክፍል መንግስትን ኣጥብቆ ማውገዙ ትክክል ነው። የህዝቡም ልብ ነጸብራቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መንግስት በማንኛውም መንገድ ሲወድቅ ስልጣን ይዞ ጥሩ ስርዓት መዘርጋቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ቁርጠኝነት (political commitment) ያላቸውን ሰዎች ይዘዋል ወይ? ብለን እንድናስብ ያደርገናል። በዚህ ረገድ ተቃዋሚው ጥቃቅን በሆኑ ፖሊሲዎች ከመከፋፈል ይልቅ ወደ ጋራ እያመሩ ከሁሉ በላይ የፖለቲከኞችን ስብእና የመገንባቱ ላይ ማተኮር ለነገይቱ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። ይህን ስብእና ወይም ተክለሰውነት የመገንባት ስራ ፓርቲዎችን ቢዚ የሚያደርግ ወቅታዊ ስራ መሆን ኣለበት። ኢትዮጵያ በኣሁኑ ደረጃዋ ጥቃቅን ፖሊሲዎችን በማነጻጸር የምታማርጥበት ጊዜ ላይ ኣይደለችም። መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ያጣች በመሆኑዋ የስካንዲኒቪያው ኣይነት ዴሞክራሲ ይሻልሻል የኣሜሪካው ኣይነት? ማለቱ ያልበላትን የማከክ ያህል ነው። ሁሉቱም ሆኖላትስ ነው?
ዋናው በኣሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጉዳይ ፓርቲዎች እኔ እሻላለሁ ለማለት ዋናው መመዘኛቸው የተሰባሰቡት በተለይም ኣመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች የፖለቲካ ቁጠኝነት ኣላቸው ወይ? ቁርጠኝነት በሞላቸው ሰዎች ቁጥር የትኛው ፓርቲ ያይላል? የሚል ልብ ያለው ድጋፍ ነው በተግባር የሚታየው ወይም መታየት ያለብት።

በቲየሪ ደረጃ በኣሁኑዋ ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ ኣይገባም። ይሁን እንጂ በተግባር ይገባል። ይገባል ብቻም ሳይሆን ፍርድ ቤት የፖለቲካ መሳሪያ ነው። ኣሁን እዚህ ጋር የጎዳን የስርዓቱ ወይም የኣሰራሩ ጉዳይ ሳይሆን መከራ ውስጥ የከተተን ጉዳይ የግለሰቦች ስብእና ጉዳይ ሆኖ ነው የምናየው። ለምን እነዚህ ግለሰቦች ስርዓቱን ይጥሳሉ፣ ህጉ ለምን ኣቅም ያጣል? ካልን የፖለቲከኞቹ ላእላይ ስብስብ በተለያየ የግል ጥቅማጥቅም የተተበተበ በመሆኑ ነው። ድህነታችንም ኣንዱ ኣስተዋጾ ያደረገ ይመስላል። የተሻለ ስራ ለማግኝነት፣ ከድህነት ለመላቀቅ፣ ፖለቲካን መሳሪያ ማድረጉ የተለመደ መሆኑና ወደዚያ ጠጋ ያሉ ሃላፊዎች በዚህ ሞቲቭ የተሞሉ ስለበዙበት ስርዓቱ በቁሙ እንዲሞት ኣድርጎታል።

ባለፈው ጊዜ ኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋታል የሚል ኣንድ ኣርቲክል ጽፌ ነበር። በርግጥም በኣሁኑ የነጻነት ትግል ኣሰላለፍ በኩል ጎድሎ የታየው ይሄ ነውና ይህንን ማቋቋም ተገቢ ነው። ይህ ኮሚሽን ፓርቲዎችን እያበራታታ ይህን ተፈላጊ ስብእና በመገንባቱ ረገድ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ፣ የመፍትሄ ኣሳቦችን በማጠናቀር ረገድ፣ ለኣዲሲቱዋ ኢትዮጵያ የሚሆነውን ኣዲስ ሰውነት በመጠቆሙ ረገድ ከባድ ሚና ሊጫወት ይችላል። ከዚያ በተረፈ ደግሞ እኛ ተራ ዜጎች መሪዎቻችንን የማጎልበትና ወደ ህብረት የመግፋት እንዲሁም ስብእናቸውን የመገንባት ሃላፊነት ኣለብን።

የብዙ ኣፍሪካ ሃገሮች ችግር ይሄ ይመስለኛል። ታግለን በብዙ መስዋእትነት ኣንድ ኣምባገነን ከጣልን በኋላ መልሰን በሌላ ኣምባ ገነን እንተካለን። ሌላው ኣለም እየተሻሻለ ሲሄድ ይሄኛው ክፍለ ኣለም ወደ ኋላ የቀረበት ትልቁ ምክንያት የነጻነት ታጋዮች ራሳቸው በሚገባ ለኣመራር የሚበቃ ስብእና ሳያዳብሩ ወደ ስልጣን ስለሚመጡ ነው።ደቡብ ሱዳን ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ለብዙ ኣመታት የነጻነት ትግል ታግለው፣ ብዙ ደም በመፍሰሱ ዓለም ሁሉ እነዚህ ሰዎች ቢገነጠሉ ይሻላል ብሎ ፈርዶላቸው ተገነጠሉ። የዳርፉሩን እልቂት የማያውቅ፣ ያልሰማ ያለም ክፍል የለም። ያ ሁሉ ሆኖ ኣዲስ ኣገር ከመሰረቱ በኋላ ገና ኣንድ ጊዜ እንኳን ምርጫ ሳያካሂዱ፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይመሰርቱ፣ ከሁለት ዓመት ያልዘለለ እድሜ ያላትን ኣገር በጎሳ ከፋፍለው ማመስ ጀመሩ።

ያለ መታደል ሆኖብን በኣንዳንድ ኣፍሪካ ሃገራት የሚነሱ መሪዎች ስልጣን ላይ ከመጡ በሁዋላ ሁለት ነገር በጣም ይወዳሉ። ኣንደኛው ዝና ሲሆን ሁለተኛው ገንዘብ ነው። ሁለቱም እጆቻቸው ይዘዋል። ባንዱ ስልጣን በሌላው ገንዘብ። ዝናውን ወደው ገንዘቡን ችላ የሚሉ ቢሆኑ ትንሽ ይሻል ነበር። ነገር ግን ሁለቱንም በሃይል ስለሚወዱና ለዚህ የተሰጠ ስብእናቸው በውስጣቸው ስላልሞተ ክብ በሆነ ችግር ውስጥ እንድንወድቅ ኣድርጎናል።ኢትዮጵያዊያን በዚህ ላይ ልንነቃ ይገባናል። በተለይ የፖለቲካ ሰው መሆን የፈለጉ ወገኖቻችን፣ መሪ መሆን የሚሹ ወገኖቻችን በየጊዜው የባህርይ ለውጥ እያሳዩ በኣመለካከትና በሃላፊነት ስሜት እያደጉልን እንዲሄዱ እንሻለን። ከፍ ሲል እንዳልኩት እኛ ተራ ዜጎች ከውጭ ሆነን መፍረድ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻችንን መንከባከብና ፍቅርን ክብርን ማሳየት ለፖለቲካ ቁርጠኝነታቸው ሃይል ይሰጣል።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

geletawzeleke@gmail.com
ገለታው ዘለቀ

የሰማያዊ አመራር አባላት በሶስት መስመር ወደ ተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ተጓዙ

$
0
0

ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር እንዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር ገምግሞ መፍትሄ መስጠትም አንዱ ሌላው የጉዞ አላማው ነው፡፡
የመስክ ጉበኝቱ በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡

ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ


የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ አንዱ ዓለም ተፈራ

የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ነዉ በሚለው ላይ የቀረበ አስተያየት –አብርሃ ደስታ

$
0
0

እስቲ በግልፅ እንነጋገር:
ለተጋሩ
==============

አንዳንድ ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በህወሓት ዘመን የተለየ ጥቅም እንዳገኘ አስመስለው ሲያቀርቡ እንወቅሳቸዋለን። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ በህወሓት ዘመን እንደተጠቀመ ሳይሆን እንደተጎዳ ጠንቅቀን እናውቃለንና። በሌላ በኩል ህወሓት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንደሆኑ ይሰብካል። ህዝብና ገዢ ፓርቲ በምንም ስሌት አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ ግልፅ ነው። ፓርቲና ህዝብ አንድ አድርጎ የማሰብን ያህል ድንቁርና የለም። ግን ይሁን ብለን እንቀበለው። የህወሓት መሪዎች ስልጣናቸው በመጠቀም የኢትዮጵያን ሃብት እየመዘበሩ የራሳቸው ስርዓት ተጠቃሚ መሆናቸው ግልፅ ነው (ለዚህም ነው ስልጣን መልቀቅ የማይፈልጉ፤ ስልጣን ላለመልቀቅም ህዝብና ፓርቲ አንድ እንደሆኑ አድርገው ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩ)።

እሺ:

ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ከሆኑ፣
ህወሓቶች በስርዓታቸው ተጠቃሚ ከሆኑ፣
የትግራይ ህዝብ የስርዓቱ ተጠቃሚ ነው ቢባል ለምን ይደንቀናል?

ምክንያቱም ህወሓቶች ተጠቃሚ መሆናቸው እናውቃለን። የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው ካልን የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነው ልንል ነው ማለት ነው።

ስለዚህ የትግራይን ህዝብ ሁኔታ በቂ መረጃ የሌላቸው ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በተለየ የስርዓቱ ተጠቃሚ ነው ብለው ቢደመድሙ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም መረጃው የሚያገኙት ከህወሓት ነው። ህወሓት የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል። ታድያ ተቃዋሚዎች የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነው ቢሉ ችግሩ ምንድነው? ችግሩ ያለውኮ ህወሓቶች ጋ ነው። ህዝብና ፓርቲ አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ እየታወቀ አንድ ናቸው ይላል። ህወሓት “የኢትዮጵያ ሃብት እየዘረፍክ ነው!” ሲባል “አይ እኔ ብቻ አይደለሁም የምዘርፈው፣ የትግራይ ህዝብም አብሮኝ እየዘረፈ ነው፣ ከትግራይ ህዝብ ነጥላቹ አትዩኝ፣ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው …” ይለናል (የራሴ አገላለፅ መሆኑ ነው)። የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ከሆኑ ታድያ ህወሓቶች በተጠቀሙት ቁጥር የትግራይ ህዝብም ተጠቃሚ ነው ማለት ነው።

እኛ ተጋሩ ህዝብና ፓርቲ አንድ የሚያደርገውን ህወሓት የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳውን እንዲያስተካክል ማድረግ አለብን። የትግራይ ህዝብ በህወሓት ዘመን ተጠቃሚ ሳይሆን ተጎጂ መሆኑ ማስረዳት አለብን። ህዝብና ፓርቲ በየትኛውም መለክያ አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ ልናስረዳቸው ይገባል። የትግራይን ህዝብ ችግር በቅርበት የምናውቀው እኛ የትግራይ ሰዎች እስከሆንን ድረስ ችግሩን ማጋለጥ ይኖርብናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሓት የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ በሚሰጠው የተሳሳተ መረጃ እንዳይታለል የበኩላችን ሚና መጫወት አለብን።

የትግራይን ህዝብ ድምፅ ማሰማት አለብን። ህዝብን ለመጨቆን ገዢዎችን መተባበር ሳይሆን ህዝብን ለመርዳት የሚደርስበትን ዓፈናና በደል ማጋለጥ ይኖርብናል። ህዝብ ለሚበድሉ ገዢዎችን መተባበር ከወላጆቻችን የወረስነው ባህላችን አይደለም። ባህላችን ለህዝብ ነፃነት ሲባል ጨቋኝ ገዢዎችን መታገል ነው። አሁንም ጠቃሚ ባህላችንን እንተግብር።

አቡጊዳ –ግንቦት ሰባት በባህር ዳር የታየዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ማደራጀትና መምራት ትልቅ ነገር ነው አለ።

$
0
0

የግንቦት ሰባት በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገዉ የሳምንቱ ርእስ አንቀጽ፡ በመኢአድ እና አንድነት ፓርቲ ለተጠራዉ የባህር ዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ያለዉን አድናቆት ገለጸ።

«ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የማደግ እድል አላቸው። ስለሆነም ግንቦት 7 ለባህርዳሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደራጆችና ተሳታፉዎች “እንኳን ደስ ያላችሁ”» ሲል የግንቦት ሰባት ርእስ አንቀጽ ያተተ ሲሆን በባህር ዳር ለታየው አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴም ያለዉን አጋርነት በይፋ አስቀምጧል።

ግንቦት ሰባት «ኢሕአዴግ ሰላም የሚያውቅ አይደለም» በሚል በሰላማዊ ትግል ለዉጥ ማምጣት አይቻልም በሚል ድምዳሜ፣ የትጥቅ ትግል አማራጭ ይዤ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ድርጅት እንደሆነም ይታወቃል።

የግንቦት ሰባትን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

የህወሓት ታጋዮች ቅሬታቸው ገለፁ –አብርሃ ደስታ

$
0
0

ባሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የዉኃና አፈር ጥበቃ (Water and Soil Conservation, ማይን ሓመድን ዕቀባ) ተግባራት የሚከናወኑበት ግዜ ነው። ህዝብ ስራው ትቶ ተገዶ በፕሮግራሙ ይሳተፋል። ለፖለቲካ ሲባል ህዝብ በፍላጎቱ ተሳተፈ ተብሎ ሪፖርት ይቀርባል። እውነታው ግን ሌላ ነው። በየዓመቱ ህዝብ ሳያምንበት ተገዶ ይሰራል። በግዜው ያልሰራ እስከ ሦስት መቶ (300) ብር ተቀጥቶ ይሰራል። በዚሁ ምክንያት ብዙ ሌሎች የግል ሥራዎች ይቆማሉ። ዜጎች ብዙ ኪሳራ ይደርስባቸዋል።

የዉኃና አፈር ጥበቃ ሥራ የጉልበት ስራ ነው። መስራት የሚችል ይሰራል፣ ወይ እንዲሰራ ይገደዳል። በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ጣብያ ሩባ ፈለግ ግን ለየት ያለ ጉዳይ ተከስቷል። የዓፅቢ ወንበርታ ህዝብ በህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ንቁ ተሳታፊ የመኖሩ ያህል ባከባቢው ብዙ አካል ጉዳተኞች (የቀድሞ ታጋዮች) አሉ። በጉልበት ስራ መሰማራት አይችሉም። ምክንያቱም አካላቸው ጎድሏል። እናም በጡረታ ገንዘብ በገጠር ህይወት ነው የሚኖሩ። የአካል ጉዳተኞች መሆናቸው ታውቆ ላለፉት ሃያ ሦስት (23) ዓመታት በዉሃና አፈር ጥበቃ ሥራ ተሳትፈው አያውቁም። ምክንያቱም አካላዊ ቁመናቸው አይፈቅድላቸውም፤ ግማሾቹ ዓይናቸው የጠፋ ግማሾቹ እግራቸው የተቆረጠ ወዘተ ናቸው።

አሁን ግን ለመጀመርያ ግዜ በተለየ ሁኔታ አካላቸው የጎደሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች በዉኃና አፈር ጥበቃ ፕሮግራሙ እንዲሳተፉ በመንግስት አካላት እየተገደዱ ይገኛሉ። ለምን አሁን እነሱን ማስገደድ ተጀመረ? የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በመንግስት አካላት ላይ ተቃውሞ አስነስቶ ነበረ። ህወሓቶች የቀድሞ ታጋዮቹ ዒላማ አድርገው በዉኃና አፈር ጥበቃ እንዲሳተፉ ያስገደዱበት ምክንያትም ህዝብ ፀረመንግስት ሲነሳ የቀድሞ ታጋዮቹ ከመንግስት ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝቡን ጥያቄ በመደገፋቸው ነው። ታጋዮቹ ዓፈና በዝቷል፤ ለዚህ አይደለም መስዋእት የከፈልነው፣ ፍትሕ ጠፍቷል ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በማንሳታቸው ነው።

አሁን የድሮ ታጋዮቹ በግዝያቸው በፕሮግራሙ ባለመሳተፋቸው የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸው ለብቻቸው እንዲሳተፉ ይደረጋል። የገንዘብ ቅጣቱ እስከ ሦስት መቶ ብር ይደርሳል። ሦስት መቶ ብር ደግሞ መክፈል አይችሉም፤ ግድቡም መገደብ አይችሉም። ምክንያቱም ታጋዮቹ የሚተዳደሩት በጥሮታ ገንዘብ ነው። የጥሮታ ገንዘቡ ደግሞ ከሦስት መቶ ብር በላይ አይደለም። ታድያ ሦስት መቶ ብር (የጥሮታ) ለመንግስት ከፍለው በምን ሊተዳደሩ? ምን በልተው ሊገድቡ? በግድቡ ለመሳተፍም ይከብዳቸዋል። ምክንያቱም ግድብ የጉልበት ስራ ስለሆነ። አካላቸው አይፈቅድላቸውም፤ ምክንያቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው።

በዚሁ ምክንያት በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሩባፈለግ ጣብያ ከባድ ዉጥረት ነግሷል። በጣብያው (ንኡስ ወረዳ) እስካሁን ድረስ 963 ዜጎች በፕሮግራሙ ባለመሳተፋቸው ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክስ ከተመሰረተባቸው ዜጎች ከ100-150 የሚደርሱ ሰዎች ተቀጥተዋል። ሌሎችም ቅጣታቸው እየተጠባበቁ ነው። የአከባቢው ህዝብ የካቲት 13, 2006 ዓም ይህ የመንግስት ካድሬዎች ተግባር በመቃወም “ሰሚ የለም ወይ?!” በማለት በጭኾት ተቃውሞውን አሰምቶ ነበረ።

የቀድሞ ታጋዮቹ ግን መንግስትን ክፉኛ እየወቀሱ ነው። አካላቸው በመጉደሉ ምክንያት ምንም ዓይነት የጉልበት ስራ መስራት የማይችሉ የመንግስት ተግባር ስለተቃወሙ ብቻ አሁን በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ እየተገደዱ ካሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ፍቃደኛ ከሆኑ (1) አምሳአለቃ ሃይለማርያም ገብረእግዚኣብሄር፣ (2) አምሳአለቃ አታኽልቲ ገብረኪሮስና (3) አስራአለቃ ወልደአብርሃ ገብረመድህን ይገኙባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደርግ ከወደቀ ከ1983 ዓም ጀምሮ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በምንም ዓይነት የመንግስት የጉልበት ስራ ተሳትፈው አያውቁም። አሁን መቃወም በመጀመራቸው ግን እየተገደዱ ይገኛሉ። አሁንም ቢሆን በጉልበት ሊገድቡ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። የመንግስት ጥረት ግን ታጋዮቹ መንግስትን መቃወም እንደማያዋጣቸው ተገንዝበው ተቃውሞአቸውን እንዲያቆሙ ለማስገደድ ብቻ ነው። መንግስትን ከደገፉ ግን ነፃ ይሆናሉ። አይገደዱም። እንዲህ ነው የህወሓት ተቃውሞን የማፈን ስትራተጂ።

ቀደም ሲል የህወሓት ካድሬነታቸው በማቆማቸው ምክንያት መሳርያቸውን (ጠመንጃቸውን) በመንግስት አካላት ተነጥቀዋል። በአካላዊ ጉዳት ምክንያት ከህወሓት ዉትድርና ቢወጡም ጠመንጃቸው ግን ይዘውት ነበር የሚኖሩ። ጠመንጃቸው ይፈልጉታል። ምክንያቱም (አንድ) ራሳቸው የሚከላከሉበት ነው። ለብዙ ዓምታት ከነሱ ጋር የኖረ ስለሆነ ማንነታቸው አድርገውታል። እናም ጠመንጃቸውን ሲነጠቁ insecurity ይሰማቸዋል። ትልቅ የሞራል ውድቀት ይሰማቸዋል። የሞራል ኪሳራ ይደርስባቸዋል። ህወሓትም ይህን ያውቃል። እናም ነጠቃቸው። (ሁለት) ጠመንጃቸው በትንንሽ ከተሞች የሚገኙ ሃብታም የህወሓት ካድሬዎች የቤት ዘበኞች በመሆን ስራ የሚያገኙበት ነው። ጠመንጃ ከሌላቸው በዘበኝነት የመቀጠር ዕድል አያገኙም። ስለዚህ ስራ እንዳያገኙ ስለተፈለገ ነው። ስራ ካላገኙ በመንግስት ጥገኛ ይሆናሉ። ጥገኛ ከሆኑ ደግሞ መንግስትን ይደግፋሉ እንጂ አይቃወሙም። መንግስትን ካልተቃወሙ ደግሞ ህወሓት የፈለገውን ዓፈና የማድረስ መብት አገኘ ማለት ነው። ስለዚህ የዚህ ሁሉ ዓላማ ተቃውሞውን በማዳከም ህዝብን መጨቆን የሚቻልበት መንገድ ማመቻቸት ነው።

በብዙ የትግራይ አከባቢዎች የዉኃና አፈር ጥበቃ ፕሮግራም እየተሰራበት ያለ ሲሆን ባከባቢው ተገኝቶ በፕሮግራሙ ያልተሳተፈ ገበሬ መሬቱ እየተነጠቀ ይገኛል (እንደ ቅጣት መሆኑ ነው)። ነገሩ እንዲህ ነው። የህወሓት ካድሬዎች ማዳበርያ ለመሸጥ ሲባል ገበሬውን በአስገዳጅ እንዲገዛ ያደርጋሉ። ማዳበርያ ካልገዛ ይታሰራል፣ የመንግስት አገልግሎት አያገኝም፣ መሬቱም ይነጠቃል። ገብሬውም እነዚህ ሁሉ ቅጣቶች መሸከም ስለማይችል የማዳበርያ ዕዳ ይገባል። ማዳበርያውን ለመግዛት ገንዘብ ከተለያየ ተቋማት ይበደራል። ብድሩ ለመመለስ በከተሞች አከባቢ ወይ ሌላ ራቅ ያለ ቦታ በመሄድ ተጨማሪ ስራ ይፈልጋል። ዕዳውን ለመክፈል ስራ ፍለጋ ከቀዩ ይርቃል። ካድሬዎች ደግሞ “ባከባቢው እያለማ አይደለም” በሚል ምክንያት መሬቱ ተወስዶ ለሌላ ካድሬ ይሰጣል። ገበሬው ለዘላለሙ ከቀዩ ይፈናቀላል። ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነው። መሬት የኔ ነው ብሎ ፍርድቤት ሂዶ መከራከር አይችልም። ሁሉም ነገር በሕግ ሳይሆን በመመርያ ነው የሚሰራው። እናም ህዝብ ችግር ላይ ወድቋል።

የታጋዮቹ ጉዳይ ግን አሳሳቢ ነው። ታጋዮቹ አካላቸው ጎድሏል። እኛን ከጨቋኞች ነፃ ለማስወጣት ሲሉ መስዋእት ከፈሉ። ለኛ ሲሉ አካላቸው ጎደለ። አሁን መስራት አይችሉም። መቃወምም እንዳይችሉ እየተደረጉ ነው። እነሱ የቤት ስራቸው ጨርሰዋል። ለኛ ሲሉ አካላቸው የጎደሉ ወገኖች አሁን እኛ ልንተባበራቸው ይገባል። እኛ ልንታገልላቸው ይገባል። እኛ ነፃ ልናወጣቸው ይገባል። ምክንያቱም እነሱ ዓቅሙ የላቸውም፤ እንደ ድሮ ሩጠው ጫካ መግባት አይችሉም። ከዚሁ ዓፋኝ ስርዓት እንገላግላቸው።

ፍኖት –ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ

$
0
0

ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡

ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች «750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት» በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡

አስተያየት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” ላይ ፈቃደ ሸዋቀና

$
0
0

የሻምበል ፍቅረ ስላሴን ባለ 440 ገጽ መጽሐፍ ላነብ ስነሳ ጸሐፊው በሃያ ዓመታት የእስር ቤት ቆይታቸው በስልጣንና የሃላፊነት ዘመናቸው የነበሩትን ብዙ ክንዋኔዎች ፣ ውሳኔዎችና ተዋናዮችን አስመልክቶ የነበራቸውን እይታ እንደገና ለማጤንና ለማሰላሰል እድል አግኝተው የጻፉት ሊሆን ስለሚችል ሚዛናዊ የሆነ ዕውቀት፤ እንዲሁም የመንግስታቸውን የውስጥ ለውስጥ ሥራዎች ከሩቅ እናይ የነበርን ተራ ዜጎች ሳናውቃቸው የቀሩ ነግሮችን የምናገኝበት ይሆናል የሚል ጉጉት ነበረኝ። በተጨማሪም በመግቢያው ሊተርኩልን ቃል የገቡትን የደርግን የግዛት ዘመን ዋና ዋና ቁም ነገሮችና ክንዋኔዎች እንደወረደ አቅርበውልን አንባቢዎች የሁሉንም ነገር ፋይዳ የራሳችንን ሚዛን ተጠቅመን እንድንረዳው ይተውልናል ብዬ አስቤም ነበር። ይህ ከንቱ ምኞት መሆኑን ወደ ገጾቹ ውስጥ ርቄ ሳልሄድ ነው ያረጋገጥኩት። በሁሉም የደርግ የግዛት ዘመን ክንዋኔዎችና የፖለቲካ ተዋናዮች ላይ የራሳቸውን ዳኝነቶች አመለካክቶችና ግለ-አይታዎች (bias) ጨምረውበታል።

ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ከእስር በወጡ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜያቸውን ወስደው ይህን መጽሀፍ በመጻፋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። ወደፊትም ሌሎች መጽሐፎች እንደሚጽፉ ቃል ገብተዋል። የሚቀጥሉት ላይ በበለጠ የሃላፊነት ስሜት እንዲጽፉ ለማሰቢያ የሚረዳ ነገር ካስተያየቴ ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። እውነት በመናገርና በሀቅ በመመስከር ከሚገኘው ብዙ ጥቅም ውስጥ አንዱ ለተናጋሪው የህሊና ፈውስ የሚያስገኝ መሆኑ ነው። ለሻምበል ፍቅረስላሴና ለቤተሰባቸው መልካሙን ነገር ሁሉ እመኝላቸዋለሁ። መጽሀፋቸው ላይ በማቀርበው አስተያየት ላይ ግን ርህራሄ የለኝም። የምንሟገትበት ጉዳይና ታሪክ ከያንዳንዳችን ስብዕና በላይ ስለሆነ።

የዚህን ጽሁፍ ርዕስ ግምገማ (Review) ከማለት ይልቅ አስተያየት(Observation) ያልኩት እውቄ ነው። መጽሀፉ እንደመጽሀፍ የሚገመገም ባህርይ የለውም። ብዙው የደራሲው ነጻ እይታ ዘገባ ነው። ትልልቅ ድምዳሜዎች ላይ የደረሱባቸውን ነጥቦችና በፖለቲካ ባላንጦቻቸው ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ተዓማኒ የሚያደርግ ወይም የሚያረጋግጥ ወይም ደርግን ከክስ የሚያነፁበት ማስረጃ የሚሆን የግረጌ ማስታወሻም (Footnote) የዋቢ ዝርዘርም (Reference list) የለበትም። መጽሀፉ ባቀራረቡ ከሞላ ጎደል የደርግ በተለይም የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ገድል ነው። ለበርካታ ደርግ ላይ ለሚቀርቡ ወንጀሎችና ጥፋቶች ሁሉ የተገቢነት ማረጋግጫ (justification) ለመስጠት ደራሲው ሙከራ ሲያደርጉ ይታያል። ስለዚህ ግምገማ የሚገባው መጽሀፍ ነው ማለት ለመጽሀፉ የማይገባውን ነገር ማድረግ መስሎ ታይኝ። ማድረግ የሞከርኩት ፈጣን ወፍ በረር ቅኝት ብቻ ነው። ምሳሌ የሚሆኑ ነገሮችን አሳይቼ ብዙውን ነገር ትቼዋለሁ።

በደርግ የግዛት ዘመን ከደረሰው የጥፋት ከምር ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎችና ተራ ዜጎች የሚወስዱት የተለያየ መጠን ያለው ድርሻ እንዳለ ብዙ የሚያከራክር አይመስለኝም። ከዚህ የጥፋት ከምር ላይ እያንዳንዱ የደርግ አባልና በተለይ በከፍተኛ ሀላፊነት ላይ የነበሩ ደራሲውን የመሰሉ መሪዎች የሚያነሱት ትልቅ ድርሻ አለ። በሚያሳዝን ሁኔታ ሻምበል ፍቅረስላሴ ለይሉኝታ ያህል ብለው እንኳን በግልም ይሁን በጋራ ምንም ሀላፊነት አይወስዱም። የመንግስታቸውን ጥፋት ሁሉ በሌላ ያመካኛሉ። ኢህአፓን አጥብቆ በመወንጀል የደርግን ለመሸፈን ይቻላል በሚል ሀሳብ ይመስላል ኢህአፓ ገደላቸው የሚሏቸውን 271 ሰዎች ዝርዝር ከምጽሀፉ 21 ገጾች ሰጥተው አስፍረዋል። (ከገጽ 275 – 296). ዝርዝሩ ደርግ ራሱ እየገደለ ኢህአፓ ገደላቸው የሚባሉ ሰዎች ስም ሁሉ ይዟል። ለምሳሌ ዶክተር መኮንን ጆቴን የገደላቸው ራሱ ደርግ መሆኑን እንደሚያምኑ የመኢሶን አባላት የነበሩ ጓደኞቼ ነግረውኛል። በአጸፋው ኢህአፓ ብለው የፈጁትን ሰው ዝርዝር ይቅርና ጠቅላላ ቁጥር እንኩዋን ሊነግሩን ፈቃደኛ አይደሉም። ተራ ተመልካች ካለችግር የተረዳውንና ብሎ ብሎ የጨረሰውን የኮሎኔል መንግስቱንና የደርግ መንግስት ጥፋቶችና ሀገርን አደጋ ላይ የጣለ ግትርና እምባገነናዊ አመራር በጨረፍታ እንኩዋን ለመተቸት አለመሞከራቸው ወይ ቀጥተኛ ክህደት ፣ ወይም የውሻ አይነት ቅድመ-ሁኔታ አልባ ታማኝነት ፣ ከዚህ ከዘለለ ደግሞ “በምኒልክ ጊዜ የደነቆረ ምኒልክ ይሙት እንዳለ ይኖራል” የሚባለው አይነት ነገር አስመስሎባቸዋል።

በመከረኛይቱ ሀገራችን ላይ ብዙ መታከም የሚገባው ትልልቅ ቁስል አለ። የሚሻለው ወደማከሙ መዞር እንጂ ቁስሉ ላይ ጨው መነስነስ አይደለም። ሻምበል በመጽሀፋቸው ብዙ ቦታ ይህንን ጨው ቁስላችን ላይ ካለሀሳብ ነስንሰውታል። በህይወት የሌሉና ሊከራከሯቸው የማይችሉ ሰዎችን ሳይቀር በስልጣን ዘመናቸው ጊዜ እንደሚደረገው አሁንም በመደዳው ይወነጅሏቸዋል። ይህ አጻጻፍ በውድቀታቸው ላገኛቸው ለራሳቸው ቁስል ፈውስ ይሆነኛል ብለው አስበው ከሆነም ተሳስተዋል። ንጹህ ራስን እንደገና ማግኘት (redemption) የሚቻለው ለዕውነት ክብር በመስጠት ብቻ መሆኑን የተረዱት አልመሰለኝም። ዛሬ የሚገዙንን ገዥዎች እካሄድና አገዛዝ ስለጠላን የደርግን ዘመን ግፍ እንዳለ የረሳነው መስሏቸው ከሆነም በጀጉ ተሳስተዋል። የወጋ እንጂ የተወጋ አይረሳም። ደጉ፣ ቸሩና አስተዋዩ የአትዮጵያ ህዝብ በወደቀ እንጨት ምሳር ማብዛት አይገባም ብሎ ስለተወውና እነሻምበል ፍቅረስላሴ ትተውለት በሄዱት ምስቅልቀል ላይ በመጠመዱ እንጂ የደረሰበትን ግፍ ረስቷል ማለት አይደለም። ወዳጅ ዘመድ በግፍ የሞተበት ፣ ጧሪ ልጃቸውን ያጡ እናት አባቶች ፣ ቤቱ የፈረሰበት ቤተሰብ ፣ ከነጠባሳው የሚኖር ዜጋ፣ ከገበያ ላይ ሳይቀር ካለፈቃዱ ታፍሶ ጦር ሜዳ የተማገደው ማገዶ ትራፊ አሁንም አለ እኮ!

በመጽሀፉ ላይ የምሰጠው አስተያየት ርሳቸው የሚወነጅሏቸውን ድርጀቶች ወይም ሰለባዎች ወይም ግለሰቦች ወክዬ ለመሟገት አይደለም። ከሻምበል ፍቅረስላሴ መጽሀፍ ጋር ያጣላኝ አንዳንዱ ነገር በቅርብ በምናውቀው ታሪክ ላይ ያሳዩት ይሉኝታ የሌለው አጻጻፋቸው ነው። በጊዜው ያልተወለደውና ለዕውቀት ያልደረሰው ትውልድ የተሳሳት ግንዛቤ እንዲወስድ ሲጋበዝ ዝም ብሎ ማየትም ተገቢ አልመሰለኝም። ስለዚህ በዚህ መጽሀፍ ላይ የምሰጠው አስተያየት ጨከን ያለ መስሎ ታይቷችሁ ከሆነ ከዚህ አቅጣጫ እዩልኝ። ሌላ የግል ወይም የቡድን ሂሳብ የማወራርደው የለኝም። የኛ ሀገር ሰው እንደሚለው ከጅብ የሚያጣላ ጓሮዬ ያሰርኩት አህያ የለኝም።

እኔ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ተፈንቅሎ ደርግ ስልጣን ሲወስድ 19 ሊሞላኝ ጥቂት ወራት የቀሩትኝ የአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርኩ። በደርግ ዘመን ለነበረው ሁሉ እንግዳ አይደለሁም ማለት ነው። እንደብዙ ወጣቶች ኢህአፓ አካባቢ ልሳተፍ እንጂ ያደረኩት ተሳትፎ ብዙ አልነበረም። ካስተዳደጌ ይሁን ከሌላ በልጅነቴ ጀምሮ አንዳንድ ገዜ አስተማሪና ጉዋደኛ እስቲጠላብኝ ድረስ ጨቅጫቃ ተማሪ ነበርኩ። አንድ ነገር እስኪገባኝ ድረስ ሰው አስቸግር ነበር። በ1968 ዓም መጀመሪያ ኣካባቢ አንድ የኢህአፓ የጥናት ክበብ ላይ ስሳተፍ ደርግ የወዛደሩ ፣ ኢህአፓ ደግሞ የላብ አደሩ እምባገነንነትን እናሰፍናለን በሚሉት ነገር ላይ ችግር ነበረብኝ። ለካርል ማርክስ ጭንቅላት እስከዛሬ ድረስ ትልቅ አድናቆት ቢኖረኝም የሶሻሊዝም ሳይንስነትም አይገባኝም ነበር። የጥናት ቀጠሯችን ዕለት በኢትዮጵያ ያለውን የላባደር ቁጥር ፈልጌ ጠቅላላ ከ45ሺ እንደማይበልጥ አረጋግጬ መጣሁ። አዲስ አበባና አቃቂ አካባቢ ያለው ብቻ 20 ሺ አይሞላም ነበር። 35 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት አገር ላይ ሀምሳ ሺ ለማይሞላ ሰው ሺ ጊዜ ተበዝባዥ ሲሆን ቢውል አምባገነን እንዲሆን የምንታገልበት ምክንያት እልገባ ብሎ አስጨንቆኝ ነበር። ይህን ነገር ሳነሳ ሰብሳቢያችን የነበረው ልጅ ሳቀብኝ። ከማርክስ እየጠቀስ ሊያስርዳኝ ሲሞክር ይበልጥ አዞረብኝ። ማርክስ የሚያወራው አይነት ላባደርማ ጭራሹኑ እዚህ አገር የለም ብዬ ድርቅ እልኩ።

የኛ አገር ላባደር ማርክስ እንደሚናገርለት እንዳውሮፓው ሳይሆን እንዴውም የተፈናቀለ (depeasantised) ገበሬ ነው ብዬ ተከራከርኩ። ሰብሳቢያችን ስደብ አዘል ሽሙጥ አሽሟጠጠኝና ተጣላን። ከዚያ ሴል ውስጥም ወጣሁ። እዚያ ሴል ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ልጆች የነበራቸውን የህዝብና ሀገር ፍቅር በፍጹም አልጠረጥርም። እኔ የህዝብና ያገር ፍቅራቸውን እንደሆን እንጂ በጀግንነትና በመስዋዕትነት ስሜት አልወዳደራቸውም። እነሱ ለህዝብ ሲሉ ለመግደልም ሆነ ለመሞት ዝግጁ ነበሩ። እኔ የሚያገዳድል ነገር ባለበት አካባቢ መገኘት አልወድም። ሰው የሚገድል ሰው ምን አይነት ህሊና እንዳለው እስከዛሬ አይገባኝም። ሁሉም ማለት ይቻላል በኋላ አልቀው ተገደሉ። ብዙ ሊሞቱ የማይገባቸውና በህይወት ቢኖሩ ትላልቅ ሳይንቲስት የሚወጣቸው የቅርብ ጉዋደኞቼ በደርግ ተገለዋል። እኔ ቀጭኑን የቀይ ሽብር ዘመን አስተማሪ ሆኜ ገጠር ውስጥ አለፍኩት። መጨረሻ ላይ የቀይ ሽብሩ ዶፍ ሊያባራ አካባቢ ያበዱ ካድሬዎችና ባለስልጣኖች ርዝራዥ ኢህአፓ ብለው እኔንና ጥቂት ጉዋደኞቼን ሊበሉን የምኖርበት ወረዳ አብዮት ኮሚቴ ውስጥ መዶለታቸውን ሰማሁ። አምልጬ ባንድ ትልቅም ባይሆን ጠቃሚ ስልጣን በነበረው አጎቴ ርዳታ ተረፍኩ። አጎቴ ለኔና ለታናሽ ወንድሜ ብቻ ሳይሆን ለጓደኞቼም መዳን ረዳ። ከሁሉ በላይ አብዱል ቃድር የሚባል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የደሴ ልጅ፣ አሁንም በህይወት አዲስ አበባ የሚኖር የጓደኛዬ ጓደኛ ባጎቴ ርዳታ ሞት ከሚጠብቅበት እስር ቤት ለማውጣት ስለቻልኩ እስከዛሬ ደስ ይለኛል። ከዚያ በኋላ ያለውን የደርግ ዘመን አጎንብሼና ትምህርት ላይ አተኩሬ የሆዴን በሆዴ ይዤ ባድርባይነት ነው ያሳለፍኩት። ስለዚህ የብዙ ሰው ያህል ቂም የለኝም። እነሻምበል ፍቅረስላሴ ላይ አሁን ከደረሰባቸው በላይ እንዲደርስባቸው አልፈልግም። ጉዳያቸውን ያየው ዳኛ እኔ ብሆን ኖሮ የሀያ ዓመት ቀርቶ የሁለት ወር እስራትም እልፈርድባቸውም ነበር። ሰው ሲዋረድና ሲሰቃይ ማየት አልወድም። የሰሩትን ስራ አልቅሼ ነግሬና ወቅሼ ንስሀ እንዲገቡ መክሬ ነበር የምለቃቸው። ግፈኛን በደግነት እንጂ በግፍ በመቅጣት ርካታ የሚገኝ አይመስለኝም።

ሻምበል በመጽሀፋቸው ሊሰጡን የሚሞክሩትን የማህበራዊ ሳይንስ ትንታኔ ቢተውት ይሻል ነበር። ኮሎኔል መንግስቱም መጽሀፋቸው መጀመሪያ ላይ እንዲህ አይነት የምሁር ተግባር ውስጥ ሲንጠራሩ ተመልክቼ ነው ሳላነብላቸው የወረወርኩት። ሻምበል ፍቅረስላሴ ሊቃውንት ተንታኞችን ሊጠይቅ የሚችለውን ማህበራዊ ሳይንስ ቀርቶ በተመክሮ እንኳን ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮችን ስተዋቸዋል። ለምሳሌ በጊዜው ተነስቶ ስለነበረው ስለጊዚያዊ ህዝባዊ መንግስት ጥያቄ አንስተው በተቹበት ክፍል ውስጥ ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስት ሊመሰርቱ ይገባል ተብለው የተጠቀሱትን የህብረተሰብ ክፍሎች በየተራ እያነሱ እንዴት እንደማይችሉ ያስረዳሉ። የገበሬውን ተሳትፎ በተመለከተ፣
“ገበሬው ንቃቱ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የመንግስትን አወቃቀርና አሰራር ማወቅ ቀርቶ የሚኖርበትን አካባቢ እንኩዋን እንዴት እንደሚተዳደር ለይቶ ለማወቅ ችሎታ የሌለው መደብ ነበር” ይሉናል። (ገጽ 226)።

ተማሪዎችን አስመልክቶ ሲናገሩ ደግሞ፥

“ተማሪዎች የስራም ሆነ የኑሮ ልምድ የላቸውም። ቤተሰብ ማስተዳደር እንኩዋን በቅጡ አያውቁም። . . . . . . . መንግስት ስልጣን ውስጥ ተካፋይ መሆን አለባቸው የሚል ሀሳብ ማቅረብ ከግዴለሽነት ወይም ግራ ከመጋባት የመነጨ ይመስላል” ይላሉ። (ገጽ226)”.
ይህን የሚጽፉት ሻምበል ፍቅረሰላሴ ከስልጣን አባሮ እስር ቤት ያጎራቸው ተማሪዎች የነበሩ ልጆች አደራጅተው ያሰማሩት የገበሬ ሰራዊት መሆኑን ፈጽሞ ረስተውታል። በታሪካችን ውስጥ ትንሽ ወደኋላ መለስ ብለው ቢያዩ ሀገሪቱን ለየዘመናቸው እንዲመች አድርገው አደራጅተው ፣ ሕግ አውጥተው ፣ ዳኝነት አይተው ፣ ገበያ አቋቁመው፣ ሲያስፈልግ የጎበዝ አለቃ መርጠው ፣ ጦርነት ተዋግተው ያቆዩልን አባቶቻችን ገበሬዎች መሆናቸውን መገንዘብ ይችሉ ነበር። የገዳን ስርዓት የሚያክል አስደናቂ የመንግስት ዘይቤ የፈጠሩት ያገራችን ከብት አርቢዎች እንደነበሩ ሻምበል የሚያውቁ አልመሰለኝም። ደርግን ከመሰረቱትና ሻምበል በመጽሀፉ እንደሚነግሩን አህያ የከበቡ የጅቦች ስብስብ በሚመስል ጉብዔ ላይ 60 ሰዎች ላይ እጅ እያወጡ ካለፍርድ ይገደሉ ብሎ ከሚወስን ወታደር የተሻለ ፍርድ ሊሰጡ የሚችሉ ብዙ ያገሬ ገበሬዎች እንዳሉ አውቃለሁ።

በደርግ የግዛት ዘመን ብዙ ሰው ከሀገር የሚሰደደው ደርግ ሀገሪቱን ለልጆችዋ የሲዖል ጎሬ ያደረጋት በመሆኑ መሆኑን ከሀያ አመት በሁዋላ እንኩዋን ማየት አለመቻላቸው ገርሞኛል። ገጽ 440 ላይ ሻምበል እንዲህ ይላሉ።
የኛን መንግስት ለማዳከም ታዋቂና የተማሩ ግለሰቦችን ጠላቶቻችን አስከድተዋል። የአሜሪካ መንግስት የስለላ ድርጀት (ሲ አይ ኤ) ከፍተኛ በጀት በመመደብ የመንግስት ባለስልጣናትን ፣ ይዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ፣ ታዋቂ ስፖርተኞችን በብዛት አስኮብልሏል”።

ሻምበል ስደቱን ነው ኩብለላ የሚሉት። አሜሪካ ተሰዶ መኖር ለግል ኑሮ የሚጠቅም መሆኑ ከደርግ በፊት የማይታወቅ ነገር አስመሰሉት። በደርግ ጊዜ የነበረውን አንድ ከስደት ጋር የተያያዘ ቀልድ ሻምበል አልሰሙም መሰለኝ። ቀልዱ እንዲህ ነው። አንድ ቀን ቦሌ አይሮፕላን ጣቢያ የሚጀምር ብዙ ሺ ህዝብ ተሰልፎ ኮሎኔል መንግስቱ አዩና “ይህ ሁሉ ህዝብ ምንድነው” ብለው ጠየቁ አሉ። “ጓድ መንግስቱ ከሀገር ሊወጣ የተሰለፈ ህዝብ ነው” ብሎ አንድ ባለሙዋል ይነግራቸዋል። ታዲያ ይህ ሁሉ ሰው ከወጣ እኛስ ምን እንሰራለን ብለው ከኋላ ተሰለፉ አሉ። ሰልፈኛው ቅድሚያ እየሰጠ ስላሳለፋቸው መጨረሻ ላይ ከፊት አንደኛ ሆነው ተሰለፉ አሉ። ያን ጊዜ ያ ሁሉ እልፍ ሰው ሰልፉን ትቶ የበተናል። ኮሎኔል ግራ ገብቷቸው “ምን ሆኖ ነው ሰልፈኛው የሚበተነው” ብለው ባለሙዋሉን ሲጠይቁት “አይ እርሶ መጀመሪያ ከተሳፈሩና ከሄዱማ ለምን እንሄዳለን ብለው ነው” አላቸው ይባላል። ከደርግ በፊት ውጭ ሀገር ትምህርታቸውን የጨረሱ ምሁራን ዲግሪያቸውን እስከሚረከቡበት ድረስ ላለመዘግየት በፖስታ እንዲላክላቸው ጠይቀው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ እንደነበር የማናውቅ አስመሰሉት።

ሻምበል መጽሀፉ ውስጥ የነበረውን የኢኮኖሚ ችግር በሙሉ እንዱን እንኳን እኛ ስለተሳሳትን የተፈጠረ ነው እይሉም። በራሳቸው የፖሊሲና የማኔጅሜንት ችግር በጊዜው በነበሩት የመንግስት እርሻዎችና ሌሎች የኢኮኖሚ ተቋሞች ላይ የደረሰውን ውድቀትና ኪሳራ ሁሉ በኢህአፓ ላይ ለጥፈውታል። በጊዜው ኮሎኔል መንግስቱና ተራው የደርግ አባል ሁሉ የኤክስፐርት ቦታ ተክተው ካልሰራን ሲሉ እንደነበር እዚህ ጊዜና ቦታ የለኝም እንጂ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ እችል ነበር። አንዲት እንኳን ምስሌ ሳይሰጡን በደፈናው ኢህአፓ “በተለያዩ የተንኮል ዘዴዎች የማምረቻ መሳሪያዎች በማበላሸት ወይም በማቃጠል የምርት እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ አድርጓል”። ይሉናል። (ገጽ 253)
ሻምበል ከ1967 ዓም ጀምሮ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያመጹባቸውንና የደመሰሷቸውን ሰዎች ሁሉ ጨፍልቀው መሬታቸው የተወረሰባቸው የመሬት ከበርቴዎች ይሏቸዋል። ያመጹ ባለመሬቶች መኖራቸው እውነት ነው። ታሪኩ ግን ይህ ብቻ አይደለም። ጠመንጃቸውን እንደጌጥ የሚወዱ በርካታ ድሀ ገበሬዎች መሳሪያ አስረክቡ ሲባሉ እንደውርደት ቆጥረው ለወንድ ልጅነት ክብራቸው ሲሉ የሸፈቱ ብዙ ነበሩ። እኔ በግል ጅባትና ሜጫ አውራጃ ውስጥ ጀልዱ በሚባል አካባቢ አስተማሪ በነበርኩበት ቦታ የሆነውን አውቃለሁ። አማራና ኦሮሞ ገበሬዎችና አነስተኛ ነጋዴዎች ናቸው። መሳሪያችንን ተውልን ብለው ለምነው ሲያቅታቸው የሸፈቱ ሰዎች በስም የማውቃቸው ነበሩባቸው። የተወሰነ ጊዜ ቢሆንም ተዋግተው የሞቱት ሞቱ። የመሬት ከበርቴ በሌለበት ሰሜን ሸዋም ተመሳሳይ ነገር መሆኑን አውቃለሁ።

ደርግ ገበሬዎችን መሳሪያ ሲገፍ ትልቅ ጠቃሚ የህብረተሰብ ባህሪ እየቀየረ መሆኑ አልገባውም። በየጥምቀቱና በየበአላቱ በዘፈን ላይ “ምንሽሬ ፣ ቤልጅጌ” የሚባሉ ዘፈኖችና “መራዥ ተኳሹ” የሚባሉት የጀግንነት ፉከራዎች ቆሙ። የጀግንነት መንፈስም አብሮ ተሰበረ። እሱ ዱሮ ቀረ ተባለ። የወያኔ ጦር ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ ኮሎኔል መንግስቱ ደብረ ብርሃን ሄደው “ጀግናው የመንዝ የመራቤቴና የቡልጋ ህዝብ ሲዘምት እንጂ ሲዘመትበት አይተን አናውቅምና ተነስ” የሚል ሰበካ ካካሄዱ በሁዋላ አንድ ዘመዴ ገበሬ ያለኝን አልረሳውም። “ይቺ ሰውዬ” ፣ አለ መንገስቱን። ፊቱ ላይ የንቀትና የጥላቻ ገጽታ አይበት ነበር። “ያኔ መሳሪያችንን ገፍፋ ሴት አድርጋን ስታበቃ ዛሬ ባንድ አዳር ወንድ ልታደርገን ፈለገች አይደል? እንግዲህ እንደፎከረች ራሷ ትቻለው። እኛማ አንድ ጊዜ ቁጭ ብለን ሸንተናል” ነበር ያለኝ። ትንሽ ማሰብ የሚችል አንጎል ያለው ሀገር እመራለሁ ፣ አገር እወዳለሁ የሚል ሰው አንድ ሶሺዎሎጂስት ወይም ከባላገሮቹ መሀል ሽማግሌዎች ጠርቶ የሚሰራው ስራ ምን እንደሚያስከትል ይጠይቅ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ብዙ ዓመታት ከደርግ ቀደም ብለው ሀገራችንን የመሩት አፄ ምኒልክ ቢሆኑ ኖሮ አዋቂ ሳያማክሩ እንዲህ አይነት ነገር አይሞክሩም ነበር። ሕዝቡን ቢፈሩት እንኳን እንደማትነካኝ ማልልኝ ብለው መሳሪያውን ይተውለት ነበር።

ደርግ በችሎታ ማነስና በማያውቀው ነገር ገብቶ ሳይሳካለት የቀረውን ነገር ሁሉ ሻምበል ፍቅረስላሴ በተለይ በኢህአፓ ላይ ብዙ ጊዜም ከተጠቀሙባቸው በሁዋላ በፈጁዋቸው መኢሶንን በመሳሰሉ ደርጅቶችና መሪዎቻቸው ላይ እየወስዱ የለጠፉት ነገር አስተዛዛቢ ነው። ለምሳሌ በሶማሊያ ወረራ ጊዜ ደርጉ ውስጥ የነበረውን ያመራር መዝረክረክና የሰራዊት ሽሸት ሁሉ በኢህአፓ ያመካኛሉ።እንዲህ ይላሉ፤
“የኢትዮጵያ ጦር የያዘውን ቦታ እየለቀቀ እንዲያፈገፍግ የተደረገው በሶማሊያ ጥንካሬና ግፊት ብቻ ሳይሆን በጦሩ ውስጥ የተሰገሰጉት የኢህአፓ አባላት ጦሩን በማሸበራቸውና እንዲሸሽ ቅስቀሳ በማካሄዳቸው ጭምር ነው። ………………የኢህአፓ አባላት በጦሩ ውስጥ ሽብር ነዙ።….. ከዚህም አልፈው በግርግርና በተኩስ መሀል መሪዎችን ከጀርባቸው እየተኮሱ ገደሉ” (ገጽ 364)
በመጽሀፉ ውስጥ ብዙ ቦታ እንደሚያደርጉት ይህን ከባድ ክስ ያስቀምጡና ክሱን የሚያስረዳላቸው አንዲት መረጃ ወይም ምሳሌ አይሰጡም። ነገሩን በደርግ ዘመንም ሰምተነዋል። ይህ የተደረገበት ልዩ ምሳሌ (specific case) በጊዜ ፣ በቦታ ፣ በስም ተለይቶ ሲሰጥ ሰምተን እናውቅም። የሻምበል አይነት ስልጣን የነበረው ሰው ደግሞ ለመረጃ ቅርብ ስለሚሆን ማስረጃ ማቅረብ ሊቸገር አይገባም።

ሻምበል ፍቅረ ስላሴ በስልጣን ዘመናቸው የደረሰውን ታሪካችን የማይረሳውን ግፍ ሁሉ እንዳለ በኢሕፓና ትግሉን እናግዛለን ብለው ከውጭ ሳይቀር በረው ሀገር ገብተው ሂሳዊ ድጋፍ በመስጠት ትግሉን ለመምራት በተሳተፉ ወግኖቻችን ላይ ካለምንም ይሉኝታ ለመደፍደፍ ያደረጉት ሙከራ በጣም ያሳዝናል። ተገኘ የተባለ ጥሩ ነገር ሁሉ የደርግና የመንግስቱ ኃይለማሪያም ይሆንና የተበላሸ ነገር ሁሉ ደግሞ በነዚህ ሀይሎች ላይ ይላከካል። ሐላፊነት መውሰድ ብሎ ነገር የለም። ሌላው ቀርቶ ደርግ ከውስጥ ኢህአፓ ከውጭ አጣብቀው መከራቸውን በሚያሳዩዋቸው የመኢሶንና የሌሎች ደጋፊዎቻቸው ድርጀት መሪዎችንም ካለይሉኝታ ይከሷቸዋል። መንግስቱና ደራሲው ራሳቸውን ሳይቀር የሚመጻደቁበትን የሶሻሊዝም ሀሁ እጃቸውን ይዘው ያስቆጠሩዋቸውን ደርጅቶች መሪዎች እነ ኃይሌ ፊዳን ስልጣን ባቁዋራጭ ሊይዙ ሲሉ ደርሰው እንደገደሏቸው እያማረሩ ይነግሩናል። ካለፍርድ የተገደሉበትን ሁኔታ ሁሉ ተገቢ አስመስለው ያቀርቡታል። ከአምቦ ከተማ አለፍ ብሎ ቶኬ ከምትባል ቦታ ተደብቀው የተያዙትን የመኢሶን መሪዎች እስር ቤት እንኩዋን ሳያደርሷቸው ሜዳ ላይ እንዳረዷቸው በዚያው አካባቢ እኖር ስለነበር እየተሸማቀኩ ሰምቻለሁ። የደርግ ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ ጥሩ ይሆኑና በነጻነት ለመንቀሳቀስ የዜግነት መብታቸውን የተጠቀሙ ዕለት ርኩስ ይሆኑባቸዋል ለሻምበል።

ሻምበል ፍቅረስላሴ ደርግ በጥይት የፈጀውን ሠራተኛና ወጣት ሁሉ ኢህአፓ አስገደላቸው ይላሉ እንጂ እኛ ገደልናቸው አይሉም። ያየር መንገድ ሰራተኞች መንግስት ያገተባቸውን የስራተኛ ማህበር መሪ ይለቀቅልን ብለው በተነሳ ግርግር ላይ 6 ሰራተኞች በመንግስት መገደላቸውን ይነግሩንና ይህም ስለሆነ “ኢህአፓ ድል አድራጊ ሆኖ ወጣ” ብለው ያሽሟጥጣሉ። እንዴውም ግርግር ላይ “የመጀመሪያውን ተኩስ የተኮሱት የአህአፓ አባላት እንደነበሩ በተደርገ ማጣራት ተረጋግጧል” ይሉናል (ገጽ 251) ። የተጣራበትን መንገድም ይሁን ሰነድ ላንባቢው ዋቢ ለመስጠት አይጨነቁም። ደርጎቹ ከስዎቹ መሀል የተወስኑ ሰዎች አስረው ዘቅዝቀው እየገረፉና ጥፍር እያወለቁ የመረመሩዋቸው ሰዎች እንደሚኖሩ የምንገምት ሰዎች አለን። ከዚያ ያገኙትን ማስረጃ ይሆን ወይ ብዬ ለማሰብ እንድገደድ አደረጉኝ። ሻምበል ፈቅረስላሴን አወዛጋቢና አከራካሪ ሊሆን የሚችል መጽሀፍ መጻፍ ያማከራቸው ሰው ዋቢ መጥቀስና ማስቀመጥ ተገቢ መሆኑን የነገራቸው አልመሰለኝም።

ደርግ የገደላቸውን የመኢሶን አባላትም በራሱ በመኢሶን ያመካኛሉ። ለምሳሌ እንዲህ ይላሉ።

“የመኢሶን መሪዎች ከኮበለሉ ብኋላ በርካታ አባሎቻቸው ላይ የመጉላላት ፣ የመታሰርና ከሥራ መባረር በሎም የመገደል አደጋ ደርሶባቸዋል። ይህ የመኢሶን የስልጣን ጉጉትና የአመራር ድክመት ውጤት መሆኑ ነው”። (ገጽ 342)

የመሪዎቹ መኮብለል በምን ተአምር ነው ደርግ ካለፍርድ ተራ አባሎቹን እንዲፈጅ ምክንያት የሚሆነው? መሪህ ስለኮበለለ ተብሎ ተከታይ የሆነ ያገር ዜጋ ካለፍርድ ይፈጃል እንዴ? ሻምበል አንዳንዱ ሎጂካቸው የተዘቀዘቀ ነው። የደርግን ወንጀል በዚህ አይነት የተውገረገረ ዘዴ ለመሸፈን መጣር በታሪክ ላይ ትልቅ የሽፍትነት ስራ መሆኑ ሻምበል የገባቸው አልመሰለኝም።

ሌላ አንድ ልጨምር። የጄነራል ተፈሪ በንቲ፣ የሻምበል ሞገስ ወልደሚካኤልና መቶ አለቃ አለማየሁ ሀይሌ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የተፈጸመባቸውን ዘግናኝ አገዳደል ድራማ ይተርኩልንና መደምደሚያ ላይ እንዲህ ይላሉ።

“የኢህአፓ መሪዎች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የመወሰንና የማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን መንግሥት በመለመሏቸው ጥቂት የደርግ አባላት አማካይነት አንበርክከው ስልጣን ለመያዝ ይቻላል ብለው በቀየሱት ከጀብደኝነት የመነጨ ስልት ምክንያት የደርግ አባላትን ለእሳት ዳረጉ” ይሉናል(ገጽ 127)።

በራሱ በደርግ አሰራር ተመርጠው ሀላፊንት ላይ የተቀመጡትን የደርግ መሪዎች በግል ውሳኔ ከደርግ ውጭ አሲረው የገድሉዋቸውን ኮሎኔል መንግስቱን አረዷቸው እንደማለት ኢህአፓ ለሳት ዳረጋቸው ሲሉ ትንሽ አያፍሩም። የሚገርም ነው። የቀድሞ የጃንሆይ የመኪና ማቆሚያ ጋራጅ ውስጥ ከታሰሩ በሁዋላ ድምጽ በማያወጣ ጠመንጃ አስቀድመው አዘጋጅተው የረሸኗቸውን መንግስቱን ነፃ አውጥቶ ሌላ የሚከስ ሰው ምን አይነት ህሊና እንዳለው ለመገመት ይከብዳል። ጄኔራል ተፈሪ ፣ መቶ አለቃ አለማየሁና የሻምበል ሞገስን በጊዜው የነበረውን የርስበርስ መጨፋጨፍ ለማስቆም መላ ያሰቡና በስልጣን ጥም ያበዱትን ኮሎኔል መንግስቱን ገለል ለማድረግ ህልም የነበራቸው ቅን ሰዎች ነበሩ፣ ሆኖላቸው ቢሆን ኖሮ የተሻለ የሰላምና የእርቅ አቅጣጫ ሊመጣ ይችል ነበር፣ ብለን የምናስብ ብዙ ኢትዮጵያዊያን መኖራችንን እንዳይገምቱ ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ህሊና ላይ አንዳች የሚያህል መርግ የተቀመጠበት ይመስላል። ለነገሩ ሶስቱንም የደርግ አባሎች የኢህአፓ ስርጎ ገቦች ይሉዋቸዋል እንጂ ለመሆናቸው ወይም ያደረጉትን ያደረጉት ከኢህአፓ በተሰጠ ትዕዛዝ ስለመሆኑ ምንም የቀረበ መረጃ የለም። ሙዋቾቹ የደርግ አባሎች በጊዜው የያዙትን ስልጣን ያገኙት ግን በዚያ ጨለማ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ በምትመስል የምርጫ አካሄድ መሆኑን ደራሲው ራሳቸው አልደበቁም። ሙዋቾቹ የሰሩት ነገር ጥፋት ነው ብለን ብንስማማስ እንኩዋን በዚያ ሁኔታ ከሚታረዱ ለምን ታስረው ቃላቸውን ሰጥተው ለፍርድ መቅረብ ነበረባቸው ብሎ የሚከራክር ህሊና አጡ። ያን ጊዜ ህሊናው ባይኖራቸው አይገርመኝም። ዛሬ ከብዙ ዘመን በኋላ ይህን ማሰብ አለመቻላቸው ግን ይገርማል።

ሻምበል ሁሉንም የደርግ መንግሥት ክንዋኔ በዚህ መጽሀፍ ላይ ማጠቃለል እንደማይቻል መጽሀፉ መጨረሻ ላይ ነግረውናል። ሳይነግሩን የቀሩት ነገሮች ግን ሊያልፉዋቸው የማይገቡና እዚህ መጽሀፍ ላይ የደርግ ጥሩ ተግባራት አድርገው ከነገሩን ስራዎች ጋር የሚነጻጸሩ ትልልቅ ነገሮች ናቸው። በደርጉ የመጨረሻ እድሜ አካባቢ ተነስቶ የነበረውን የከሸፈ መፈንቅለ መንግስት በተመለከተ ምንም አልነገሩንም። በጃንሆይ ጊዜ ስለደረሰው ችጋር በሰፊው ተርከዋል። በ1977 ዓ.ም ስለደረሰው ዘግናኝ የችጋር እልቂት ትንፍሽ አላሉም። የሚያመካኙባቸውን ሁሉ ጨርሰው ስለፈጁ የሚለጥፉበት አካል ስላጡ አስመሰለባቸው። አከራካሪ ስለነበረው ቤተሰብን መተከልና ጋምቤላ እስከመክፈል ስለደረስው ቅጥ ያጣ የሰፈራ ፕሮግራም ምንም አላሉም። ስለዚያ በጅጉ በድንቁርና ላይ ስለተጀመረ መንደር ምስረታ ስለሚባል የዕብደት ስራ ምንም አላሉም። እኔ ከገበሬዎች እንደተማርኩት ገበሬዎች ዳገታማና ጭንጫማ ጥግ እየፈለጉ መኖሪያ ቤት የሚሰሩት መሬቱ ጭንጫማ ስለሚሆንና ተፋሰስም ስለሚኖረው በክረምት ከብቶቻቸው አረንቋ እንዳይገቡ ፣ የማይታረስ መሬትም ላይ ስለሚሰፍሩ የርሻ መሬት ለማትረፍ ፣ ለጥ ያለው ሜዳ ደግሞ ውሀ ስለሚተኛበት ለሳርና ለግጦሽ እንጂ ተፋሰስ ስለሌለው ለቤት መስሪያና ለከብት በረት ስለማይሆን ነው። ይህን ነገር አቅርበው መንደር ምስረታውን ስለሞገቱ የታሰሩ ገበሬዎች አጋጥመውኛል። ደራሲው የደርግን ጥፋቶች ላለመንካት ሲሉ ብዙ ትንንሽ ነገሮችን እንድናስታውስ የሚወተውቱተን ያህል እነዚህን ትልልቅ የጥፋት ተግባራት ወደጎን የገፏቸው ይመስላል።

የፖለቲካ አመራር በውሱን አቅም ውስጥ ማድረግ የሚቻለውን ነገር ባግባቡ የማድረግና በተለይም አስቸጋሪ ቅራኔን የመፍታትና ስምምነት የመፍጠር (compromise) ጥበብ ነው። ይህንን የማያውቁ ፣ አንዴ እንዲቀናቸው የጠቀማቸው ዘዴ ለሁሉም ችግር መፍቻ የሚጠቅም የሚመስላቸው የፖለቲካ መሪዎችና ሀይሎች ከውድቀት አያመልጡም። ብዙ የፖለቲካ መሪዎች የሚፈልጉትን ነገር ወይም ለፕሮፓጋንዳ ብለው የሚያወሩትን ነገር ራሳቸው ደጋግመው ይሰሙና እንደውነት ያምኑታል። ያን ጊዜ ነገር ይበላሻል። ማስተዋል ሁሉ ቦታውን ለዕብሪት ይለቃል። በደርግም ላይ ሆነ በሌሎች አምባገነኖች ላይ የሆነው ይህ ነው። የደርግ ታሪክ ባጭሩ ሲጠቃለል ይኸው ነው። ሌተና ኮሎኔል መንግስቱን ሀገር ወዳድ እያሉ ሊሸጡልን የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ሻምበልም ሊሸጡልን እንደሚሞክሩት ኮሎኔል መንግስቱ ከስልጣናቸው በላይ ሀገራቸውን የሚወዱ ሰው አልነበሩም። በግትር አምባገነንነትና ራስ ወዳድነት ሀገርና ህዝብ ክፉኛ የጎዱ አምባገነን ናቸው። በተግባር ያየነው ይህንን ነው።

ስላለፈ ነገር መጻፍ ጥሩ የሚሆነው መማሪያና ማስተማሪያ የሆነ እንደሆን ነው። ሻምበል ስለደርግ ይኖራቸዋል ብለን የገመትነውን የሚያክል ከደርግ ጥፋትና ልማት የምንማርበት መማሪያ ነገር በዚህ መጽሀፍ ላይ አልሰጡንም። ወደፊት ይክሱን ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ።

Fekadeshewakena@yahoo.com

አድዋ ለኔ አንዱ ዓለም ተፈራ

$
0
0

እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው። በአሜሪካ ሆኜ የአድዋን በዓል አከበርኩ። የኢትዮጵያዊያን ድረገፆችን እየተመላለስኩ ቃኘኋቸው። ሬዲዮኖችን አዳመጥኳቸው። የስልከ ልውውጦችንና የእንግዶችን ሃሳቦች ተከታተልኩ። ስደሰት፣ ሳዝን፣ በጣም ስደሰትና በጣም ሳዝን ዋልኩ። ሲመሽና የምኝታ ሰዓቴ ቀርቦ ባልጋዬ ላይ ስጋደም፤ እንቅልፍ ቶሎ አልወስድህ አለኝ። መገለባበጡ ለውጥ አላመጣ ሲል በሃሳብ መዋተቱን ተያያዝኩት። አድዋ ለኔ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከዕለቱ ወደላይና ወደታች መዋዠቅ ጋር ተዛምዶ አፋጠጠኝ። እውነት አድዋ ለኔ ምንድን ነው?

አድዋ ከመቶ ዓመት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ነው። በዚያ ጊዜ የተካፈሉትና የነበሩት አሁን የሉም። አድዋ በአንድ የሀገራችን አካባቢ የተፈፀመ ጉዳይ ነው። ታዲያ ለኔ ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ ላለሁት ምኔ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ ስመላለስበት እኩለ ሌሊት ሆነ። ለካስ እንዲያው በቀላሉ በጃችን የያዝነውን ነገር ጠፍረቅ አድርገን ስንይዘው፤ ያሙለጨልጫል። በልጅነቴ ገና አንድ ወር ሲቀረው ላከብር እንደፋደፍ የነበርኩት ወጣት፤ አሁን ለምን አንደማከብረው ራሴን ስጠይቀው፤ መልሱ ጊዜ ወሰደብኝ። ስደተኛ ስለሆንኩ ነው? ወይንስ ይኼም በናንተ ቤት አለ?

ዓያችሁ፤ አዲስ አበባ ተወልዶ አሜሪካዊ ነኝ የሚል የፈረንጅ ልጅ አለ። ዋሺንግተን ዲ. ሲ. ተወልዶ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የሀገሬ ልጅ አለ። ከወላጆቻቸው የወረሱት ስለሆነ ነው። ይኼ በልብ ውስጥ ገብቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚያስብለው ኢትዮጵያዊነት የበቀለውና የለመለመው የትና እንዴት ነው? ኢትዮጵያዊነት ከመወለጃ ቦታ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ከሆነ፤ ታዲያ የት መጣ? ማነው ባለቤቱ?
ይኼ ኢትዮጵያዊነት የበቀለው፤ ፋሺስት ጦሩን ከቶ ሀገራችንን ሊወር ሲመጣ፤ ባንዳዎች በጣሊያን፤ ሹምባሽ ቁልባሽ የሚል ተለጣፊ ሹመት ተቀብለው፣ ለፋሽስቱ ሰግደው፣ አብረውት ተሰልፈው፣ አንዳንዶቹ መስቀላቸውን በአክሱም ቤተክርስትያን ይዘው ፋሽስቱን ጣሊያን ገዥያችን ብለው ውዳሴ ሲገቡ፤ አንዳንዶቹ ከጣሊያን ፋሽስት መሣሪያና ገንዘብ ተቀብለው ከፋሽስቱ ጋር በማበር በትግራይ ምድር የሚዋጉትን በመርዝ ጢስና በመንገዳቸው የጠርሙስ ስብርባሪ በመበተን በዱርና በገደሉ በመከታተል ሲወጓቸው፤ በባዶ እግራቸው፣ በስስ ስንቅ (ያለበቂ ስንቅ) ዘምተው፤ ወደ ቤታቸው ባልተመለሱት አርበኞቻችን ሕይወት ነው። በኤርትራ የነበሩ ወገኖቻችን፤ ጣሊያን ያስታጠቃቸውን መሣሪያ አንግበው፤ ያንተ አስካሪስ አልሆንም በማለትና ወደ መሐል ኢትዮጵያ በመምጣት፤ ከወገኖቻቸው ጋር ሲዋጉ በወደቁት ኢትዮጵያዊያን ደም ነው። ኢትዮጵያዊነት የለመለመው በአድዋና በመሰል አኩሪ አባቶቻችን ባደረጉዋቸው ተጋድሎዎች ነው። አድዋ የተፈጠረችውና ያበበችው፤ በኢትዮጵያዊነት በኢትዮጵያዊያን ደም ነው።

ይህ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ያደገው፤ ከድርቡሽ ጋር በተደጋጋሚ በጎንደርና በመተማ በተዋደቁት አባቶቻችን ቆራጥነት ነው። በግብፅና በቱርክ፣ በጣሊያንና በእንግሊዝ ድጋፍ በሱዳን በተደጋጋሚ በኤርትራ ምድር፤ እምቢ ለሀገሬ ብለው በተሰው አባቶቻችን ደም ነው። በቅርብና በሩቁ ታሪካችን፤ በሀገራዊ አንድነት፤ ጠላትን በመመከት፣ የመሬታችንን ጭብጥ አፈር አላስነካም ባሉ አያቶቻችን ነው። ደህነቱን እና ጥጋቡን፣ ደስታውን እና ሐዘኑን፣ ልጅ መውለዱን እና መዳሩን፣ ጎጆ መስራቱን እና አውድማ መጣሉን አብረው በሠሩበት ሀቅ ነው። አብረው የግጦሽ ከብቶቻቸውን ባዋሉባቸው ሽንተረሮች ነው። ወንዞችንና ተራሮችን ተባብረውና ተጋርተው ኣቆዩልን እውነታ ነው።
በሶማሊያ ወረራ፤ እብሪተኛው ሰይድ ባሬ ጦሩን ከቶ፤ ያጎረሰውን እጅ ነካሽ የሆነው ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሚጠራው ቡድን ከሶማሌ ጋር ወግኖ ሲዋጋን፤ እምቢ ለሀገሬ ብለው በቆራጥነት በወደቁት ኢትዮጵያዊያን ደም ነው። የሰው በላው የመንግሥቱ ኃይለማርያም ደርግ፤ መንግሥቱ ኃይለማርያምን በሥልጣን ለማቆየት ከአንድ ትውልድ በላይ በጨረሳቸው ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ነው። ኢትዮጵያዊነት የቆየው፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም ሀገራችንን እንድትበታተን ሀገር አውዳሚ የአስተዳደር መመሪያውን በተግባር ሲያውለው፤ ከመንግሥቱ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጥብኛለች ብለው ሕይወታቸውን በሠጡ ኢትዮጵያዊያን ደም ነው። ባድሜ ላይ በቀሩት ወጣት ኢትዮጵያዊያን ደም ነው። ዛሬም ይኼ ፀረ-ኢትዮጵያ ገዢ ቡድን በየእስር ቤቱ በአጎራቸው ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን ጀግንነት ነው። ዛሬም ሀገራቸውን ባገኙት መንገድ ለቀው በምድረ በረሃና በስደት እየረገፉ ባሉት ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ነው። ኢትዮጵያዊ ያደረገን ይኼ ነው። ዛሬ ሀገራችንን ለመበታተን ይኼ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት የሚተገብረውን ፀረ-ኢትዮጵያ አካሂያድ እምቢ ብለው በቆሙ ጀግኖች ሕይወት ነው። አድዋ ይኼ ነው፤ የማንነቴ ምሰሶ። ማቸነፋቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ባንድ ላይ ሀገራዊ ተግባር ማድረጋቸው ነው። ያ ነው አድዋ!

አድዋን የማከብረው ደም ስለተዘራበት ሳይሆን፤ ኢትዮጵያዊነትን ስላጎለበተልኝ ነው። ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ስለተነሱበትና ደማቸውን ስላፈሰሱበት ነው። ሴት ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ነጋዴ አርሶ አደር፣ ቄስ ወታደር ባንድ ላይ ሀገሬ ስላለበት ነው። ለወራሪ የሀገሬን አፈር አላስቀምስም ብለው፤ ቤታቸውን ጥለው፣ በወጡበት ሳይመለሱ ስለቀሩበት ነው። እህል ባገልግል፣ ስንቅ ባህያ፣ እግርን ያለጫማ፤ በጎራዴና በጦር ስለዘመቱበት ነው። አድዋን እነሱ በሕይወታቸው የኔ ኢትዮጵያ ስላደረጉልኝ፣ ቢቸፉም ኖሮ ስላቸነፉም፤ አድዋ የኔ ናት። ስላቸነፉም፤ አድዋ ኢትዮጵያዊነቴን በልቤ ሞልቼ ደረቴን እንድነፋ አድርጎኛል። አድዋ የኔ ናት። አድዋ የኔ ናት። አድዋ የኔ ናት።
በኢትዮጵያዊነት አቸናፊነቱ እኮ፤ አድዋ ኢትዮጵያዊነት አልበቃው ብሎ፤ ለዓለም ጥቁሮች ሰንደቅ ሆኗል! ጥቁርን እንደሰው አልቀበልም ያለውን የነጭ እብሪት፤ ሆን፣ እንደሰው ብቻ ሳይሆን፣ እንደእኩል ብቻ ሳይሆን፣ እንዳቸነፈው እንዲቀበል እንደኮሶ እየመረረው እንዲጋት አድርጎታል። ታዲያ አድዋ በኔ መከበር ይነሰው! አድዋ ኢትዮጵያዊነት ይነሰው! ኢትዮጵያዊነታችን ለመቅደላ፣ ለመተማ፣ ለዶጋሊ ይነሳቸው? አሁን የኛ ተራ ነው። አሁን ለኛ ኢትዮጵያዊነታችን የሚለመልመው፤ ለም መሬታችን ለባዕድ አይሠጥም ብለን ስንታገል ነው። አሁን ለኛ ኢትዮጵያዊነታችን የሚለመልመው፤ የሀገሬን ደንበር አላስነካም ብለን ስንቆም ነው። ኢትዮጵያዊነታችን የሚፈካው፤ ዘረኝነትን፣ መከፋፈልን፣ አድልዎንና ሙስናን ወጊዱ ብለን ስንመነጥራቸው ነው።

ኢትዮጵያዊነታችን ሕያው የሚሆነው አንዳችን ለአንዳችን ስንቆም ነው። ኢትዮጵያዊነታችን የሚኖረው ኢትዮጵያ ስትኖር ነው። አድዋ ይከበራል። ኢትዮጵያ እስካለች አድዋ አለ፤ አድዋ ኢትዮጵያ ናትና! ለዚህ ነው የማከብራት። በሕይወት እስካለሁ ድረስ አድዋን አከብራታለሁ።


የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስና የሲቪል ማኅበረሰብ ሕጎቹ ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል -ዘሪሁን ሙሉጌታ

$
0
0

“መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን አንነጉድም” አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል አቀባይ
የ2013 የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት መውጣትን ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት የፀረ-ሽብር፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የበጎ አድራጎትና ማኅበራት (የሲቪል ማኅበረሰብ) ሕጎች ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ላይ በሕጎቹ የሀገሪቱን ሕዝቦች ስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ጫና እንደሚያደርጉ ሲጠቅስ መቆየቱ ይታወሳል። መንግስት በበኩሉ የፀረ-ሽብር ሕጉ በሀገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሽብር አደጋ ለመግታት አስፈላጊ መሆኑን፣ የፕሬስና ሕጉም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን ለማስፋት እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ አዋጁም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለመግታትና ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራትን ለማበረታታት መሆኑን ሲገለፅ ቆይቷል።

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጎች የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያሽመደመደና የፖለቲካ ዓላማ ያዘሉ፣ የገዢውን ፓርቲ የስልጣን ዘመን የሚያረዝሙ በማለት ሲቃወሙ ቆይተዋል።

ከሰሞኑንም ይሄው ጉዳይ እንደ አዲስ ተነስቶ እያወዛገበ ነው። በመንግስት በኩል ሕጎቹን የማሻሻል ሁኔታ በራሱ መንገድ የሚያየው መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።

“በእኛ እምነት ሕጎቹን መቀየር የሚያስፈልግ ከሆነ በሂደት ከታለመላቸው ዓላማ አንፃር ያመጡት ስኬት ተመዝኖ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ መንገድ (Organic Process) መልሶ የሚያያቸው ይሆናል” ያሉት አቶ ጌታቸው ከዚህ ውጪ ሕጎቹን በደፈናው ከመቃወም በስተቀር በዝርዝር የመጣ ጉዳይ የለም ብለዋል። ከዚህ ይልቅ ሕጎቹን ለማስቀየር መፈክር ማሰማቱ እንደማይጠቅም ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው “መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን የምንነጉድበት ምክንያት የለም” ብለዋል።

በአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው ፓርቲያቸው ገዢው ፓርቲ በሕጎቹ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር ፈቃደኛ ከሆኑ በደስታ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ፓርቲያቸው ለስርዓት ለውጥ የሚታገል ቢሆንም፤ ኢህአዴግን ጨምሮ በውጪ ሀገር በሚገኙ በሕግ ካልተከለከሉ በስተቀር ከማንኛውም የዴሞክራሲ ኃይል ጋር ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ገንቢ ውይይት ማድረግ እንፈልጋለን። ኢህአዴግም በማንኛውም የሕግና የፖሊሲ የሀሳብ የበላይነት ለማግኘት ፍረጃውን በመተው፣ ፓርቲዎችን በማናናቅና ሕዝባዊ መሠረታቸውን ሳይክድ እስከመጣ ድረስ በሕጎቹ ላይ ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለመነጋገር እንዲያመችም ሕጎቹን በጅምላ ከመቃወም ባለፈ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገርም እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ሕጎቹን በጅምላ የሚቃወሙትም አዋጆቹ የወጡበትን መሰረታዊ ፍላጎት (Intention) ዴሞክራሲንና ሕገ-መንግስቱን የሚጥሱ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ –አንድነት

$
0
0

የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተፈፀሙ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ተመልክተነዋል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት የመብት ጥሰቶች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በተደጋጋሚ ያጋለጣቸው እና ከፍተኛ ትግል እያደረግንባቸው የሚገኙ አስከፊ ተግባራት እንደሆኑ ቢታወቅም የቆምንለት ዓላማ እና እየታገልነው ያለው ስርዓት በሌሎች ዘንድም ድርጊቱ የታወቀ መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው፡፡ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ ያካተታቸው እንደተጠበቁ፣ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከዚያም የላቁ እንደሆኑ አንድነት በተጨባጭ ያውቃል፡፡

የኢህአዴግ መንግሥት ዜጎችን በማፈን፣ ሚዲያዎችን በመዝጋት፤ ለህግ የበላይነት ቁብ በማጣት፤ ድብቅ በሆኑ እስር ቤቶች ዜጎችን በማጎር፤ በጥርጣሬ ያዝኳቸው የሚላቸውን ዜጎች በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ በማስገደድ፤ በማሰቃየት፤ በማስፈራራት፤ በመግደልና አስገድዶ ከሀገር በማሰደድ የተመሰከረለት ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገዥው የኢህአዴግ መንግሥት የተለየ አመለካከት ያላቸውና ስርዓቱን የሚተቹ ዜጎች የመከራ ገፈት የሚጋቱባት ሀገር እንደሆነች መቀጠሏም ከዜጎቿም ሆነ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የተሰወረ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል በግፍ ታስረው ከሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌ እና ናትናኤል መኮንንን ከመሳሰሉ ብርቱ ሰላማዊ ታጋዬቻችን በኋላ እንኳን በቅርቡ የፓርቲያችን የቀድሞ ዋና ፀሐፊና የአሁኑ የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ሃሳባቸውን በመጽሔት ጽፈዋል ተብለው ለእስር መዳረጋቸው የስርዓቱ አፋኝነት መቋጫ ያጣ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሌላኛው አባላችን አቶ አለማየሁ ለፌቦ ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ጀምሮ ወደ ደቡብ ክልል ሲመለሱ የፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለ27 ቀናት መታሰራቸው፤ በኦሮሚያ በደቡብ እና በሰሜናዊት ኢትዮጵያ በተለየ ሁኔታ አባሎቻችን በአመለካከታቸው ብቻ ከስራ እየተፈናቀሉ መሆኑ፤ ጋዜጠኞች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ዛሬም በእስር ላይ መሆናቸው፤ ከዚህ በተጨማሪ ሙስና፤ የመሬት ቅርምት፤ የዜጎች መፈናቀል እና ህገ ውጥ አሰራር በበኩሉ ከስርዓቱ ጋር የተገነባ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡

በሪፖርቱ የተዘረዘሩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መድገም ባያስፈልግም በዚህች ሀገር የተንሰራፋው ህገ ወጥነት ይቀየር ዘንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የሲቪክ ተቋማት፤ ድፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እና የሚመለከተቸው አካላት ህጋዊ በሆነ ሁኔታ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይህ ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ባለበት ‹‹ጤነኛ እንደሆነ መንግሥት ›› ራሱን ለመቁጠር እንደሚያስቸግረው እንረዳለን፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ ምህዳሩን ለሁሉም እኩል በማድረግ፤ የፀረ ሽብር፤ የፕሬስ፤ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ማደራጃ፤ ህጎችን በመቀየር፤ የሊዝ አዋጁን እና በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ የተካተተውን የፕሬስ ነጻነት የሚገፋ አንቀጽ በመሰረዝ፤ ከዴሞክራሲና የፍትሕ ተቋማት ላይ እጁን በማንሳት ከሚመጣበት የህዝብ ቁጣም ሆነ የታሪክ ተወቃሽነት ቢያመልጥ መልካም ነው እንላለን፡፡ አንድነት፣ በሀገራችን ያሉትን የፖለቲክ ችግሮች በዉይይት ለመፍታት በኢሕአዴግ እና በተቃዋሚዎች መካከል ሁሉም አሸናፊ የሆኑበትና ቅንነት ያለበት ውይይት እንዲደረግ፣ ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ በገለጸው መሰረት፣ ኢሕአዴግ ወደ መሃል ሜዳ መጥቶ ለዉይይት እንዲዘጋጅም እንጠይቃለን።

በሪፖርቱ የተዘረዘሩ እና ሎችም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በሚመለከት ግን በተለይ የተወካዮች ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽንና የእንባ ጠባቂ ተቋማት ከፓርቲ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ መርምረውና አጣርተው የመብት ጥሰት የፈጸሙትን የመንግስት አካላት ለፍትህ ማቅረብ ግዴታቸው መሆኑን አንድነት ፓርቲ ያሳውቃል፡፡

ከሁሉም በላይ ዋነኛ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆናችሁ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ መላው የሀገራችን ዜጎች ሰፊው ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት እንጂ ከጥቂት አምባገነን መሪዎች መብት የሚለምን አለመሆኑን በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስርዓቱን ለመታገል በአንድ ድምጽ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአሜሪካ መንግሥትም ቢሆን አንዲህ ዓይነቱን ከአሜሪካ ባህልና እሴት ጋር የሚቃረኑ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተደጋጋሚ በየዓመቱ ሪፖርት ከማውጣት ባሻገር ትርጉም ያለው ጫና በማሳደር ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ለዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት መከበር ሊቆም ይገባል ብለን እናምናለን፡፡

ዘለዓለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባUDJ

ከፍተኛ የመንግስት ፕሮቶኮል ሹም ከስልጣን ተነሱ(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ከፍተኛ የፕሮቶኮል ዋና ሹም ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ በላይ ግርማይ ከስልጣን መነሳታቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባል የሆኑትና ከ1990ዓ.ም ጀምሮ የጠ/ሚ/ሩ እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ፕሮቶኮል ሹም ሆነው በአቶ መለስ ዜናዊ ተሾመው ሲያገልግሉ መቆየታቸውን ያስታወቁት ምንጮች የአቶ በላይ ቢሮ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ውስጥ እንደነበረ ጠቁመዋል። የቀድሞ ፕ/ት ነጋሶ ጊዳዳ፣ የጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንዲሁም የፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የፕሮቶኮል ሹም ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ፣የውጭ አገር ባለስልጣናት፣ አምባሳደራትና ሌሎች አካላት ወደ ጠ/ሚ/ሩም ሆነ ፕሬዝዳንቱ ከመግባታቸው በፊት ጉዳያቸው በአቶ በላይ ግርማይ በኩል ያልፍ እንደነበር አያይዘው ገልፀዋል።

ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለ14 አመት በከፍተኛ ፕሮቶኮል ሹምነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ በላይ ለአቶ መለስ ከነበራቸው ታማኝነትና ቀረቤታ አንፃር ከጠ/ሚ/ሩ ሞት በኋላ በነበራቸው ስልጣን ብዙም ደስተኛ እንዳልነበሩ የጠቆሙት ምንጮች አክለውም በሕወሐት ውስጥ ተፈጥሮ ከቆየው የቡድን ልዩነት ጋር በተያያዘ አቶ በላይ ግርማይ ከሃላፊነት እንዲነሱ በነደብረፂዮን መወሰኑን አስታውቀዋል።

በሌላም በኩል ለአቶ በላይ ግርማይ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ይጠቁማሉ። የአቶ መለስና የወ/ሮ አዜብ ታማኝ ከሚባሉት የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ከስልጣን ተነስተው በሙስና እስር ቤት መወርወራቸውን፣ እንዲሁም የቤተመንግስት የደህንነትና ጥበቃ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈሪ ቀጥሎ ከስልጣን የተነሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አቶ በላይ ግርማይ እንደሆኑ ምንጮቹ ገልፀዋል። አቶ በላይ ግርማይ የጋዜጠኛ ብርቱካን ሃረገወይን ባለቤት ሲሆኑ፣ ጋዜጠኛ ብርቱካን በኢትዮጲያ ራዲዮና ቴሌቪዥን በሃላፊነት ተመድባ የምትሰራና አቶ መለስ ዜናዊን ብዙ ጊዜ ለብቻዋ ቃለምልልስ ታደርግ እንደነበረ፣ እንዲሁም ከጠ/ሚ/ሩ ጋር ወደ ተለያዩ አገራት አብራ ትጓዝ እንደነበረ ምንጮቹ አመልክተዋል።

ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤

አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤

ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ ዓላማዎችና ዘዴዎች ላይ መከራከርና ሀሳብን ማጥራት አስፈላጊ ነው፤ በሰላማዊ ትግል ተግባር አለ ቢባልም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ ወይም የተቃውሞ አቅዋሞችን ከማሳየት አያልፍም፤ አገዛዞች ጃዝ! ብለው ውሻና ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ሲለቁ የጉልበት ጥርስና ዱላ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያርፋል፤ ጉዳት ይደርሳል፤ ሰላም ይቃወሳል፤ በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል ቂም ይጀመራል።

ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤ ‹የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ።

አራት፣ ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት!

በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም።

አምስት፣ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፤የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፤ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፤ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው።

የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡ በሰውነት ደረጃ ሕዝቡ መብቶቹን ሁሉ እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣

በዜግነት ደረጃ ሕዝቡ ለሥልጣን የሚያበቃውን የዜግነትና የፖሊቲካ መብቶች እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣ ሕዝቡ የሰውነትና የዜግነት መብቶቹን ተገንዝቦ በአገዛዝ ስር አልተዳደርም የማለት መንፈሳዊ እምቢተኛነት እንዲያድርበት ማድረግ፣ በግልጽ ጭቆናን የሚጠላና ለመብቶቹና ለነጻነቱ በቆራጥነት የሚቆም ሕዝብ እንዲፈጠር ማበረታታት፣ መብቶቹንና የሥልጣን ባለቤትነቱን የተረዳና ከጭቆና ጋር የተጣላ ሕዝብ በፖሊቲካ መስመር ቡድኖችን እየፈጠረ እንዲደራጅ ማድረግ፣ ያወቀና የነቃ፣ በፖሊቲካ መስመር የተደራጀና ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና የሚጠላ ሕዝብ ለማንም ጉልበተኛ የማይንበረከክ ሕዝባዊ ኃይል እንዲሆን መጣር፣

የትጥቅ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ በሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አውርዶ ወንበሩን ለራሱ ለመውሰድ ነው፤ ይህንን ሲያደርግ ሕዝቡን ወደጎን ትቶ ወይም ዘልሎ ነው፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በጠመንጃ ሥልጣን የሚይዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥልጣኑን ለሕዝብ እናስረክባለን፤ ትክክለኛ ምርጫ እናካሂዳለን በማለት ሕዝቡን በተስፋና በጠመንጃ ይዞ ነው፤ ነገር ግን ሥልጣንን ሕዝብ ለፈቀደው አስረክበው ከቤተ መንግሥት ሲወጡ አናይም፤ ሲሸሹ ወይም ሬሳቸው ሲወጣ እንጂ።

ብዙውን ጊዜ የማይታሰብ ወይም ብዙዎች የሚዘነጉት የሁለቱ ትግሎች የገንዘብ ወጪ በጣም ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ነው፤ ሰላማዊ ትግል በሕይወትም፣ በንብረትም፣ በመሣሪያም በዝግጅትም የሚያስከፍለው ዋጋ ከትጥቅ ትግል ጋር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ ነው።

ስለዚህም በሁለቱ በተለያዩ ስልቶች አራማጆች መሀከል የሚደረግ ክርክር ምን ዓይነት ነው? የሰላማዊው የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ የትጥቅ ትግል የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የወያኔ አገዛዝ ነው፤ በሌላ አነጋገር በሰላማዊ ትግል ሕዝቡ በሰላማዊ ትግል ትንሽም ቢሆን የነጻነትን አድማስ ለማስፋት እንዲችል ድፍረትን በማስተማር በኩል የማይናቅ አስተዋጽኦ ቢያደርግም አገዛዙን የመነቅነቅ ኃይል ገና አላዳበረም፤ አንድም ውጤት አላሳየም፤ የትጥቅ ትግሉ ከፉከራና ከሽለላ እስካሁንም አልወጣም፤ የሰላማዊ ትግል ዓላማ ሕዝቡ መብቶቹን እንዲያውቅ ለማንቃትና ለመብቶቹ እንዲታገል የሚያስችለውን ብቃት ለማስጨበጥ ነው፤ ስለዚህም ዘዴው በሕዝቡ ላይ ነው፤ የትጥቅ ትግሉ ዘዴ አገዛዙን በጉልበት ገልብጦ በዚያው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ ሌላ አገዛዝ ለመመሥረት ነው።

በኢትዮጵያ ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ሁሉ የቆሙበትንና የቆሙለትን ዓላማና ዘዴ በግልጽ ተገንዝበው ካልተሰለፉ በተንፈራጠጠ አስተሳሰብ የተባበረ ተግባር ሊገኝ አይችልም።

አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ አደረገ!! –አንድነት

$
0
0

ህዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው 17 ከተሞችም ተለይተው ታውቀዋል፤
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር በተከታታይ ሊካሂዳባቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት”(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብሩ በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊት ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት ነው፡፡ ህዝባዊ ንቅናቄው ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ አንድነት የመሬትን ጉዳይ በአጀንዳነት በመምረጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግ የመረጠባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ በሚደረግ ትዕይንተ ህዝብ እንደሚጀመር የሚጠበቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” ህዝባዊ ንቅናቅ 14 ከተሞች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና ሶስት ከተሞችም በተጓዳኝ ለህዝባዊ ንቅናቄው መመረጣቸው ታውቋል፡፡ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባ፣ ደሴ፣ አዋሳ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ መቀሌ፣ ደብረታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ለገጣፎ፣ አዲስ አበባ ሲሆኑ ተጓዳኝ ከተሞቹ ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ) እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንድነት ፓርቲ ባለፈው ዓመት(2005ዓ.ም) ለሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ስክታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል፡፡993754_546619252089680_666940779_n

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>