Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

አቡጊዳ –የአንድነት ፓርቲ በነ ዶር በየነ ከመድረክ ታገደ

$
0
0

የአንድነት አመራር አባላት በባህር ዳር ህዝቡን እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት፣ መድረክ የተሰኘው ስብስብ፣ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ፣ የአንድነት ፓርቲን እንዳገደ ፍኖት ዘገበ። መድረክ በአሁኑ ወቅት አራት ድርጅቶ ብቻ ያሉት ሲሆን እነርሱም፣ አንድነት፣ አረና፣ በዶር መራራ ጉዲና የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፣ በዶር በየነ ጴጥሮስ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ናቸው።

አረናዎች ጠንካራ ተቃዉሞ በማሰማታቸው እንጂ እነ ዶር መራራ እና ዶር በየነ ሙሉ ለሙሉ አንድነትን ከመድረክ ማበረር ፍላጎት እንደነበራቸው ዘገባው አክሎ ያትታል።

የዶር በየነ ሆነ የዶር መራራ ፓርቲዎች፣ እንደግፈዋለን በሚሉት ህዝብ ዘንድ በምሄድ ምንም አይነት ስብሰባዎችን ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች አድርገዉ የማያውቁ ሲሆን፣ ምን ያህል የፓርቲ አባላት እንዳላቸውም አይታወቅም።

በአንጻሩ አረና ትግራይ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በሽሬ፣ በማይጨዉ፣ በተንቤን፣ በአዲግራት፣ በሁመራ ለማድረግ የተንቀሳቀስ ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ በዛሬው ቀን በሜዳ ላይ ከሕዝብ ጋር እየሰራ እንደሆን በስፋት እየትዘገበ ነዉ።

የፍኖትን ሙሉ ዘገባ እንደሚከተለው ያገኛሉ!


ፍኖት – አንድነት ለትግል በወጣበት ቀን የመድረክ አባል ፓርቲዎች አገዱት

——————————-
“አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው” የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተክሌ በቀለ
——————-
መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ማገዳቸውን ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው የመድረኩ 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ አሳውቀዋል፡፡ በጉባኤው አንድነትን ወክለው የተሳተፉት መካከል የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ ለፍኖተ ነጻነት እንዳስታወቁት የመድረክ አባል ፓርቲ የሆኑት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና በፕ/ር በየነ የሚመራው የኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ አንድነት ከመድረክ እንዲባረር ቢጠይቁም አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ አንድነት ላልተወሰነ እንዲታገድ የሚል ሞሽን አቅርቦ በጉባኤው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

አቶ ተክሌ በቀለ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑባቸው ምክንያዎች አስገራሚ መሆናቸውን ጠቅሰው “የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑት በቅርቡ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አንድነት መድረክ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈፀም መወሰኑን፣ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮችም ውህደት እንደሚያስፈልግ በተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸውን፣ የአንድነት ፓርቲ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ድጋፍ ሰጪዎች በመድረክ ስም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ትብብር አያደርጉም በሚልና ከመድረክ ዕውቅና ውጪ መስከረም 19(ሰላማዊ ሰልፉ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ነው፡፡) በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡” የሚሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተክሌ መድረክ የራሱን ዕቅድ አውጥቶ በቁርጠኝነት የማይሰራ በመሆኑ አንድነት በተናጠልና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን መስራቱን ጠቅሰው “በተደጋጋሚ ለመድረክ በዕቅድ የተደገፉ እንቅስቃሴዎችን በማቅረብ በጋራ እንዲሰራ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አግኝቶ አያውቅም፡፡ ይልቁኑም የራሱን ጥፋት በአንድነት ላይ ለማላከክ ይሞክራል ” ብለዋል፡፡

ነገ አንድነትና መኢአድ በባህር ዳር የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የመድረክን ውሳኔ አስመልክተው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት “ መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” ካሉ በኋላ “አንድነት የታገደው ውጤታማ ስራ ስለሰራና በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ እና በተመሳሳይ ስራዎች የተቀዛቀዘውን የሰላማዊ ትግል በማነቃቃት ትግሉን ወደ ህዝብ ስላወረደ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አክለውም “መድረክ ውስጥ ካሉት ፓርቲዎች የተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አረና ብቻ ነው፤ የዛሬው ውሳኔ አረናም በቅርቡ የአንድነት እጣ እንደሚገጥመው አመልካች ነው፡፡” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ “መድረክ እንደዚህ ያለ እገዳ ከመወሰን ይልቅ አንድነትና አረና የጠየቁትን ውህደት ተቀብሎ ፖለቲካውን በአንድ ላይ ማንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስገኝ አንድነት ያምናል፡፡ ስለዚህ መድረክ የወሰነውን ውሳኔ እንደገና አጢኖ የሀገራችንን ፖሊቲካ በውህደት አብረን እንድንመራ እንዲያደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


ባህር ዳር በሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች –ፎቶዎች ይመልከቱ

$
0
0

አስደናቂ ሰልፍ ነዉ በባህር ዳር የተደረገዉ። ከቃላት ምስል የበልጠ ስለሚያስረዳ ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያዊነት ድምጹኝ ያስተጋባዉን ጀግናዉ የባህር ዳር ሕዝብ ይመልከቱ !!!!

ለዝርዝር ዘገባ
https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj ይመልከቱ

pic19

pic18

pic17

pic16

pic12

pic13

pic14

pic15

pic11

pic10

pic9

pic8

pic7

pic6

pic5

pic4

pic3

pic2

pic1

bahir_dar1

bahir6

bahir5

aeup

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ዳኛቸው ቢያድግልኝ

አቡጊዳ –ከ50 ሺሆች በላይ የሚሆን ሕዝብ ጨዋነቱን እና ሰላማዊነቱን በባህር ዳረ አረጋገጠ ( የሰልፉን አስደናቂ ቪዲዮ ይመልከቱ)

$
0
0

በባህር ዳር የተደረገው ሰላማዊ ስለፍ፣ በጣም አስደናቂና አስደሳች እንደነበረ የተለቀቁ ኦዲዮዎች፣ ቪዲዮዎች ይናገራሉ። ሰልፉ እንደተጀመረ ከ15 ሺህ በላይ እንደነበረ በሚሊዮነም ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ ገጽ የተገለጸ ቢሆንም፣ ሰልፉ በቀጠለ ቁጥር ፣ ሕዝቡ ከየአካባቢዉ ሰልፉን እየተቀላቀለ፣ ቢያንስ ከአምሳ ሺሆች በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

በፎቶዎች እና ቪዲዮዎች እንደሚታየው፣ ሰልፈኞቹ ኮከብ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እያዉለበለቡ፣ መፈክሮችን እያሰሙ፣ በደስታ ለነጻነት፣ ለመብት መከበር፣ ለሕግ የበላይነት ለአንዲት ኢትዮጵያ አንድነት ይጩሁ ነበር።

ምንም እንኳን የብአዴን የደህንነት ሰራተኞች በአለቆቻቸው ታዘዉ ረብሻና ሁከት ለመፍጠር ሙከራ ቢያደርጉም፣ አንድ ሰው ላይ ጉዳት ሳይደርስ፣ አንዲት ጠጠር ሳትወረወር፣ ሰልፉ በሰላም ተጀመሮ በሰላም ተጠናቋል። የባህር ዳር ህዝብም ጨዋነቱን፣ አስተማሪነቱን፣ ሰላም ወዳድነቱን እና አንዳንድ የሰለጠን ሕዝብ መሆኑ አረጋግጧል።

pic10

አቡጊዳ –ልጇን በጀርባ አዝላ ድምጿን ለማሰማት የወጣች ሴት

$
0
0

ልጇን በጀርባ አዝላ ድምጿን ለማሰማት የወጣች ሴትudj_lady

አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር የጠሩት ሰልፍ፣ በሶሻል ሜዶያዎች ዋን መነጋገሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን የሰማቸውን ደስታ እየገልጹ ሲሆን ፣ በባህር ዳር ሕዝብ ኩራት እንደተሰማቸው እየጻፉ ነዉ። ኢሳትን ጨመሮ በርካታ ሜዲያዎች፣ ፓልቶክ ክፍሎች፣ ድህር ገጾች ትኩረታቸው ጎጃም ሆኖ የባህር ዳሩን ታሪካዊ እንቅስቅሴ እየዘገቡም ነዉ።

አንዲት ኢትዮጵያዊት ልጇን በጨርባዋ አዝላ ፣ ለመብቷ፣ ለነጻነቷ፣ ድምጿን ለማሰማት ሰልፉን ተቀላቅላ ትታያለች። በሶሻል ሜዲያዎችም ብዙዎች ለዚች እህት አድናቆታቸውን እየገለጹ ነዉ።

እኛም ለዚች እህታችን ያለንን አክብሮትና አድናቆት እንገልጻለን። በአሥር ሚሊዮኖች ለምንቆጠር፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ለተበተንን፣ ዝምታን ለመረጥን፣ ትግል፣ አገርን መዉደድ፣ ለነጻነት መቆም ምን ማለት እንደሆነ ያስተማረችን፣ ጀግና ሴት ናት።

በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን?በከፍያለው ገብረመድኅን

$
0
0

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ስለተንሰራፋው መጥፎ የማኒጅመንትና ብሄረስብ ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ስለመኖሩ ብዙ ይነገራል። ታህሳስ 21፣ 1945 ተመሥርቶ: ረዥም ታሪክና ገና ከሥረ መሠረቱ በጥሩ የአስተዳደር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበረው የተመቻቸ ሁኔታ ለጥንካሬው ዋነኛ ምክንያት ሆኖታል።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አየር መንገዱ ሲቋቋም፡ ኢትዮጵያ በስሜንና በምሥራቅ የግዛት ክልሏ ራሱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀም ነበር – የኤርትራ ሁኒታ አለየለትም። የዛሬይቱ ኦጋዴንም ተጠቃልላ ከእንግሊዝ ጋር በተደረገ በሕግ፡ በትሪቲ: ደንብና ድፕሎማቲክ ስምምነት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር።

ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱና ኢትዮጵያ አብረው ያደጉና፡ ኢትዮጵያም ቀደም ሲል ለድህነንቷና ለግዛት አንድነቷ ታማኝነት በነበራቸው ሁለት መንግሥታት ሥር ለአየር መንገዱ የወደፊት ሕልውና እንደራሳቸው አካል ልዩ ትኩረት የሰጡት ኢንተርፕራይዝ ነበር። ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት ግን የሕወሃት የዘር ፖለቲካ አየር መንገዱንም እየተፈታተነው በመሆኑ፡ ውስጡ ያሉት ዜጎችም ሆኑ፡ ሌሎች ኢትዮጵያውንም የሚሰጉለት ድርጅት እየሆነ ነው።

ይህ ማለት ግን በእነዚህ ሁለት አሥርተ ዓመታት አየር መንገዱ አልተስፋፋም ማለት አይደለም – ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም። ብዙ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል፡ ብዙ የበረራ መስመሮች ተክፍተዋል። ነገር ግን የትኛውም ትክክለአኛ የማኔጅመንት ምሁር ሊያስረዳ እንደሚችለው፡ የአንድ ኢንተርፕራይዝ ጤንነትና አስተማማኝነት የሚለካው በዚህ ብቻ ቢሆንማ፡ ነገሮት ሁሉ ቀላል በሆኑ ነበር በዚህ በፉክክር በተወጠረ ኢንዱችትሪ ውስጥ።

እንደዚህ ቀላል ቢሆንማ፡ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ኃላፊ ወይዘሮ ትብልጽ አድገዶምና የብረታ ብረቱ ኮሮፖሬሽን አዛዥ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እንደሚያስቡት በያዓመቱ 50 አዳዲስ አውቶቡሶችን ለከተማው ማቅረብ አዲስ አበባን ገና ድሮ ከትራንስፖርት እሮሮ ባላቀቃት ነበር።

አሁን ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኒጅመንት የዘነጋው ዋናው ካፒታሉና ኢንቬስትመንቶቹ ሠራተኞቹ መሆናቸውን ነው – espirit de corps መጥፋት – እንደሌሎቹ የአገራችን ድርጅቶችና ተቋሞች ሁሉ! ድርጅቱ በዘር ፓለቲካ በመወጠሩ፡ ሕወሃት የሚመለክተው የራሱ ስዎች በአመራር ላይ መቀመጣቸውንና የዘር ፓለቲካቸውን ማራመዳቸውንና ድርጅቱን ጠቅመው እርስ በእርስ መጠቃቀማቸውን ነው። ይህ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደፊት ተስፋውን ሰባሪ ሸውራራ አስተሳስብ እንጂ ቅንጣት ለሀገር ታስቦ የሚድረግ አይደለም።
እንደዚያ ካልሆነማ ለምንድነው ነባርና አዲስ የኛ ፓይለቶች የሚወዱትንና የሚኮሩበትን ኩባንያ እየተዉ፡ በአፍሪቃ፡ በመካከለኛው ምሥራቅና እስያ ውስጥ ለመሥራት የሚገደዱት? ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠመው የማኔጅመንት ችግሮች የኢትዮጵያዊ ፓይለቶቻችን ቁጥር መመናመን (መሠረቱ በሁሉም መስክ በታጠቀ በስለላ ድርጅት የተጠናከረ ዘረኝነት ነው)። ለዚህ አይደል እንዴ: በዚህ ረገድ ራሷን ችላ የኖረች አገርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሌችም ፓይለቶችና መካኒኮች ለማሠልጠን የበቃች አገር፡ አሁን የውጭ ፓይለቶች ለመቅጥር የተገደደችው?

ዘወትር አጥሩ ዝቅተኛ በሆነበት በኩል መዝለልን ልምዳቸውና ፓለቲካቸው ያደረጉት የሕወሃት ስዎች፡ አፋቸውን አሹለው የብቃት ማንስን አንድ ጉዳይ አድርገው እንዳያነሱ፡ ደግነንቱ ዛሬም ቢሆን፡ ረዳት ካፕቴን ኃየለመድህን ስኞ ዕለት በብቃት እንዳሳየው ሁሉ፡ hኢትዮጵያውያን ፓይለቶች በሄዱበት ሁል ስመጥርና ታዋቂዎች የመሆናቸው ጉዳይ ከሕወሃትም ልደት በፊት የታሪክ ምሥክርነት አለው።

On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
እስከአሁን በምንሰማው እስከአምስት የሚደርሱ የውጭ ሃገር ፓይለቶች እንዳሉ ይነገራል። የመረጃውን እርግጠኝነት ባላጣራም፡ ቲውተር ላይ እንዳየሁት ከሆ፡ ታህሳስ 18፣ 2013 የበረራ ቁጥር ET 815 ማረፊያውን ናይሮቢን ስቶ ዳሬስላም ሣር ውስጥር ሜዳ ቆፍሮ እግሩን የቆለፈው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪም የውጭ ስው እንደነበረ ይነገራል።

ሌላው ችግርም እንዲሁ መካኒኮቻችንን ይመለከታል። እነርሱም አገር እየጣሉ እየሄዱ ነው። ባለፈው ዓመት ተኩል አገሩንና ሥራውን ጥሎ ጥገኝነት ለመጠየቅ ያለሁበት አገር የመጣ ከዩኒቨርሲቲ ክአሥርታት በፊት በማኒጅመንት ተመርቆ ሲሠራ የነበረ የቀድሞ የድርጅቱ ባልደረባ አንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ስብስብ ላይ አግኝቼው እንዳጫወተኝ፡ ባጭሩ ሁኔታው እንደሚክተለው ነው:

“በሠራተኛው እይታ፡ አየር መንገዱ የድሮ ጥላውን እንጂ የዛሬ ሪያልቲው ወንካራ ነው። ድሮ ለአየር መንገድ መሥራት ኩራት ነበር። ዛሬ ለአየር መንገዱ ለመሥራትና ታማኝ ነው ብሎ ለመታየት ሙያችንን ማሸነፋችን፡ ሃላፊነታችንን መወጣታችንና ኢትዮጵያውያነታችን በቂ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች መሆናችን እንዲታወቅ ሆን ተብሎ በሕወሃት ስዎች አያያዝና ተቀባይነት፡ ታማኝነት ልዩነቱ መሠመሩ ነው”።
“አንተ አየር መንገዱንና አገርህን ትተህ እዚህ ስትመጣ ሌላ የገፋፋህ ነገር የለም” ወይ ብዬ ስጠይቀው፡ ትክ ብሎ ተመልክቶኝ፡ “አገሪቱ ስላምና ጤና ሆና ማየትና የራሴን የወደፊት ተስፋዬን መገፈፌ ነው በተደጋጋሚ የሚሰማኝ የነበረ” አለኝ።

በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም፡ ምናልባትም ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህንን ያንገፈገፈውም ይህ ሊሆን ይችላል። አልያ ጤነነቱ የተረጋገጠ፡ በቆንጆ ገቢ ደህና ኑሮ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ይህንን ትቶ ራሱን መሥዋዕት ለማድረግ ምን ያስገድደው ነበር?

ይህ ሁኔታ እንዴት ይታረማል?

እስከዛሬ ያለውን የሕወሃትን አሠራር ስመለከት፡ ጠባቡና ጎጠኛው ቡድን ትምህርት በማግኘት የሀገራችን ሁኔታ በቀላሉ መለወጡን የሚጠራጠር ስሜት በየቀኑ ይዳስሰኛል። ስዎቹ ሥልጣን በእጃችን ወይንም ማንም አይኖርም ብለው የቆረጡ ይመስላል።

ለዚህ ነው ሁሉም ሃገራችን በስላምና በብልጽግና ለልጆቻችን የምትተላፍበትን መንገድ መቀይስ የሚያስፈልገው። 95 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባችን በሁለተኛ ድረጃ ዜግነት፡ እንዲሁም በድምሩ አምስት በመቶ የሚሆኑት የሕወሃት ደጋፊዎችና አጫፋሪዎቻቸው ከሌሎቹ ብሄረስቦች የተውጣጡትን ጭምሮ በሃገራችን ላይ የጫኑት የአፈና ቀነበር አሽቀንጥሮ መጣል አለበት።

ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን በወሰደው እርምጃ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ተከፍለዋል። አንዱ ወገን የሕወሃት ሲሆን፡ እነርሱም እንደጠላት በመፈረጅ፡ “ከሃዲ” በማለት ረዳት ካፒቴኑን በሃገር ጠላትነንት ሲፈርጁት ይሰማሉ። ቤተስቦቹንም እያስቸገሯቸው መሆናቸው ይስማል።

ሁለተኛው ወገን፡ ሁኔታውን ሀገሪቱ ካለችበት የሥልጣን ብልግናና ከላይ እንደተገለእጽው የዘረኝነት ችግር ላይ መሆኗን ተናግረው ለፓይለቱ በጎ ይመኙለታል። ለኢትዮጵያ የነፃነት ሻማ አድርገው ይመስክሩለታል።

ሶስተኛው ወገን የሚጨነቀው፡ ለፓይለቱ ወይንም ሀገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ሳይሆን፡ አየር መንገዳችን ምን ዐይነት የወደፊት ሕልውና ያጋጥመው ይሆን የሚለው ሥጋት የሚያበስለስላቸው ናቸው።

ለማንኛውም፡ ለሕውሃትም ሲሉ ሳይሆን፡ የስዊስ መንግሥት ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን ላይ የረዥም ጊዜ እሥራት እንደሚፈርድበት አልጠራጠርም። አንዳንድ ስዎች ስለኤክስትራዲሽን ሲያወሩ ይስማሉ። በኔ እምነት፡ የሞት ቅጣትን በሃገሯ የሻረች ስዊትዘርላንድ፡ የሞት ቅጣትን የሕግ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፓለቲካ መሣሪያ አድርጋ ለምትጠቀምበት ኢትዮጵያ ግለስቡን ለሞት አሳልፋ ትሰጠዋለች የሚል ቅንጣት ጥርጥር የለኝም።

ዋናው ጉዳይ ግን፡ ለረዥም ዓመታት ስዊትዘርላንድ ውስጥ እንዲታሰር መደረጉ ለኢትዮጵያውያን የታሪኩ ፋጻሜ ሊሆን አይገባም። በተለይም ይህንን እርምጃ አሁን እንደሚገመተው ፖለቲካ ከሆነ፡ እርሱን ያነሳሳው፡ ኢትዮጵያውያን የእርሱን የትግል አርማ ከፍ አድርገው ሕወሃትን ሊፋለሙትና የሃገር ጥፋት ፓለቲካውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊገድቡት ይገባል። አለዚያማ እርሱን በቃላት ብቻ ማሞካሸቱ ከሌላው ወገን እንደሚመነጨው የጥላቻና ቂም በቀል የተለየ አያደርገውም። የእነርሱ ከሳሾች የሚሉት እኮ፡ ስዎችን አደጋ ላይ ጣልክ አይደለም – ማንም አልተጎዳምና። የእነርሱ ብሽቀት አገዛዛችንን አጋለጠ፤ ሥልጣናችንን ለአደጋ አጋለጠ ነው። የቡድን ጥቅም ቧንቧችንን ሊደፍንብን ሞከረ ነው። ይህ ደግሞ እውነትና ትክክል ነው።

የስሞኑን ጫና ለመቋቋም፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የመረጠው የአየር መንገዱን የወደፊት ማስብ ሳይሆን፡ የዛሬዋን እሳት ማዳፈን ላይ ነው። ለምሳሌም ያህል ለመጥቀስ፡ አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ሻጭ ኩባንያና ከሚዲያ ጋር በመተባበር፡ ለራሱ የአይዞህ መልዕክትና ምሥጋና በማስባሰብ ላይ መሠማራቱ: ከላይ እንዳመለከቱት፡ እነዚህ ስዎች እሳቱ እስኪበላቸውና ሀገራችንንም እስኪጎዳ ድረስ እንደማይቀየሩ የሚያመላክት ነው።

ስሞኑን አየር መንገዱ ብዙ ለቅሶ ደራሽች ነበሩት

ከስሞኑ ለቅሶ ፈጥኖ ደራሽች መካከል ቦይንግ ግንባር ቀደም ነበር። ይዞ የመጣውም ፋና እንደዘገበው the 2013 “GOLD Level Boeing Performance Excellence Award” ነው።

ሌላው ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪ ነፃ ቲኬት: የፕሮቶኮል ወንበር ስጥቶና በግብዣ አምነሽንሾ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲጎበኙ ማድረግ ነበር – ጥቅሙና ግንኙነቱ ገሃድ ባይሆንም። ለማንኝውም አድረጉት። ታቦ ምቤኪም የድርጅቱን ከአቪዬሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ እና የአለም አቀፍ አየር መንገዶች አውሮፕላን የመገጣጠሚያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፡ ፕሬዝዳንት ምቤኪ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያዬት የአየር መንገዱ የማሰልጠኛ አካዳሚ አለም አቀፍ የአቪዮሽን ጥራትን ያሟላና በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆነ ተቋም ስለመሆኑ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ስሞኑን ይህንን ጋጋታ በጽሞና ላዳመጠ ሰው፡ የአየር መንገዱ ዝና እንዳይጎዳ የሚወስድ እርምጃ መሆኑን መገመት ይቻላል።

አየር መንገዱ ባይጎዳ ደስ ይለኛል። ሕይወቱና ነፍሱ ተጠብቆ ከድል ወደ ድል እንዲሄድ በኢትዮጵያዊነቴ እመኛለሁ። ይህ ምኞት ግን ፋይዳ የለውም – የሕወሃት ስዎች ነገ ተመልስው የከአፕርታይድ ሊቀመኳስ Hendrik Frensch Verwoerd Verwoerd ካደረገው ባላነሰ በዘርና ጎጥ ላይ የተመሠረተ ኋላቀር ፖለቲካቸው ነገ ተመልስው የጥቅም ገበያቸውና ሌላውን ማተራመሻቸው ያደርጉታል! የዜጎችን ስሜት ሲጎዱና የሃገርን ስላምና ደህንነት መሠሪ በሆነው ፖለቲካቸው ሲመርዙት: በእነዚህ ድርጊቶቻችው፡ የሕዝቡን ምሬትም እያከረሩ፡ የታሪክ መንገድ አይታውቅምና በጥቂት የታሪክ ተጋባዦች አማካይነት በድንገት የሚቀሰቀሰው እሳት እንዲገላገለን ሁኔታውን እራሳቸው እያመቻቹት ነው!

ሃገራችን ወደፊት እንድትራመድ ከተፈለገ: በኢትዮጵያውያን እኩለነት ላይ የተመሠረተ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሰተዳደር መፈጠር የጊዜው ጥያቄ ነው። ይህ እስካልተቻለ ድረስ፡ በውንብድና በሃገርና ወገን ከሃዲዎች የውሸትና የተንኮል አመራር ላይ የተመሠረተ የሕወሃት አስተዳደርን ዕድሜ ለማሳጠር ብዙ ነገሮች ነገ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሊፈጸሙ ይችላሉ!

ይህ ደግሞ በሚገባ ተቀነባብሮ ካልተካሄደ፡ ብሽቀቱን በቀላሉ መገላገል ካለመቻሉም በላይ፡ በየቦታው በተበታተነ መንገድ የሚደረገው የአልገዛም ባይነትም በአገር ደኅንነትና ዕድገትም ላይ ጉዳት ይኖረዋል።

ነገር ግን ክትርፍ አሳድጅ የውጭ ኩብንያዎችና የውስጥ አላዛኞች ባለፍ፡ ሌላው ዓለምም አሁን የኢትዮጵያን አፓርታይድ አገዛዝ የሃገሪቱና የቀጠናው የወደፊቱ የችግር ምንጭ መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡት ይመስላል!

The Ethiopia Observatory

አቡጊዳ –አቶ ኦባንግ፣ አቶ ፋሲል እንዲሁም ሌሎች የአንድነት/መኢአድ ሥራን አደነቁ !

$
0
0

የሶሊዳሪቲ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ አንድነትና መኢአድ ሕዝቡን በማስተባበር ያደረጉት እንቅስቃሴ እንዳስተደሳቸው ገለጹ።

“I give enormous credit to the tens of thousands of great Ethiopians who came out from their homes in the city of Bahirdar to show their support for change. Regardless of what ethnicity, religious views and political viewpoint one might hold, we should all be proud of how well they presented themselves and in doing so, represented all Ethiopians ….. The rally was carried out with great discipline, respect, civility and basic good manners towards others. There was no bloodshed or destruction. From start to finish it was peaceful. It makes Ethiopians a shining example to the world and is evidence once again that we are not people of violence, but people who seek a better future for the country we all share and love. Congratulations to the great people of Bahirdar! I am proud of you all. “

ሲሉም ለሕዝቡ ያላቸውን አድናቆን ገለጸዋል።

አቶ ኦባንግ ኢትዮጵያዉያን ነጻነታቸው ሌሎች እንዲሰጧቸው መጠበቅ እንደሌለባቸው አሳስበው በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ፣ በባህር ዳር የታየው አይነት በስፋት በአገሪቷ ክፍሎች ሁሉ እንዲስፋፋ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻዉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በቅርቡ በአንድነት አመራር ዙሪያ በግላቸው አንዳንድ መጣጥፍ ያስነበበዉን የኢሳት ባክደረባ የሆኑት አቶ ፋሲል የ ኔአም አለምም በባህር ዳሩ እንቅስቃሴ የታየው የወጣቶች ብዛት እንዳስደሰታቸው «ኢሕአዴግ በባህር ዳሩ የተሸነፈባቸው 5 ጉዳዮች» በሚል ርእስ ባቀረቡ ጽሁፍ ገልጸዋል። «መኢአድና አንድነት ሰልፉን ባህርዳር ላይ ለማድረግ መወሰናቸው የሚደነቅ ነው። ብአዴንን ዋጋ በማስከፈል ጥሩ ትርፍ አግኝተዋል» ሲሉ እነዚህ አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶ ያስገኙትን ዉጤት አስምረዉበታል።

ከአቶ ኦባንግ እና አቶ ፋሲል የኔ አለም በተጨማሪም፣ በስፋት በሶሻል ሜዲያዎች እንደምናየው በርካታ ኢትዮጵያውያን ለባህር ዳር ሕዝብ ያላቸውን ኩራት እየገለጹ ነዉ።

አቡጊዳ –የሰማያዊ ፓርቲ የድሬደዋ ስብሰባ ፎቶዎችን ይመልከቱ

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ፣ ከመኢአድ እና አንድነት ጋር የባህር ዳሩን ሰልፍ እንዲቀላቀል ከአንዳንድ ደጋፊዎቹ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም፣ የድርጅቱ አመራሮች አብሮ ያለመስራት አክርሪ አቋማቸውን በመያዝ፣ ትኩረታቸውን ከምእራብ ኢትዮጵያ ወደ ምስራቅ አዙረዉ ነበር።

የባህር ዳር ሰልፍ በሚደረገብት ቀን «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከድሬደዋ ሕዝብ ጋር ለመነጋገር» በሚል እሁድ የካቲት 16 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሳምራ ሆቴል ስብሰባም አድርገዋል።
sem2

የፓርቲዉ አሰታባበሪዎች በከተማዋ የሰልፉን ፍላየር፣ ቅዳሜ የካቲት 15 ሲበትኑ የነበረ ሲሆን ፣ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችዉ በድሬደዋ ከተማ፣ ስብሰባውን መካፈል ከነበረበት ህዝብ ጋር ሲነጻጸር፣ በሰማያዊ ስብሰባ የተገኘው ሕዝብ ብዙ ነበር ማለት እንደማይቻል የደረሰን ዜና ያመለክታል።

በሰማያዊ ስብሰባ ከተገኙ ጥቂት ኢትዮጵያዉያን መካከል ፣ አንዱ «የህግ የበላይነት በሌለበት ስርዓት ነው ያለነው፡፡ የብሄር ፖለቲካም እስካሁን አልጠቀመንም!›› ሲሉ ያለፉት የ20 አመታት የአገዛዙን የዘር ፖለቲካን አውግዘዋል። ከሃያ አመታት በፊት አክራሪ ኦነጎች እና በጀኔራል ጃራ ይመራ በነበረዉ፣ በእስላማዊ ኦርሞ ነጻ አውጭ ድርጅት ደጋፊዎች ፣ በከተማው በሚኖሩ «አማራ» የሚሏቸው ክርስቲያኖች ላይ በድረደዋ ከተማ ተነስተው በነበረ ጊዜ፣ ከተማው ለሶስት ቀናት መረበሿ፣ በዚያም ምክንያት ድሬዳዋ ልዩ አስተዳደር እንዲኖራት መደረጉም ይታወሳል።

“ኢህአዴግ በመሀከላችን ወዳጅ መስሎ ገብቶ ያጣላናል፤ እንታገላለን! ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም!”” ሲሉ የተናገሩት ሌላ የድሬደዋ ነዋሪ ደግሞ የአብሮ መስራት ጥቅም በማስረዳት፣ መከፋፈል የሚጠቅመው ለኢሕአዴግ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህ የሰማያዊ የድሬደዋ ስብሰባ፣ በጥናት በዝግጅትና በፕላን የተደረገ ሳይሆን፣ በችኮላና በእሽቅድምድሞሽ «ስለአንድነት ብቻ ለምን ይወራል? እኛም ዜናው ዉስጥ መሆን አለብን» ከሚል ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያናገራሉ።

«ሰማያዊ በጎንደር ለብቻው ሰልፍ ጠርቶ ነበር። በድሬደዋ ለብቻው ስብሰባ ጠራ። የተገኘዉ ሕዝብ ግን በባህር ዳር ከተገኘው ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር በጣም ጥቂት ነዉ። ይህ ቆም ብለው እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው ይገባል» ያሉት በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ሰማያዊ የሕዝብን ጥያቄ በማዳመጥ ከመኢአድ እና አንድነት ጋር አብሮ መስራት እንዲጀምር ያሳስባሉ። «የድሬደዋ ሕዝብ ይህ ያንስበታል። ሰማያዊ ከመኢአድ እና ከአንድነት ጋር ሆኖ ወደ ድረደዋ እንደገና መመለስ አለበት። ሕዝቡ የተዝረከረከ ሳይሆን የተደራጀ፣ አንድ የሆነ አመራር ነው የሚፈልገው» ሲሉ በባህር ዳር የታየው በድሬደዋም እንዲደገም ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

የአንድነት አመራር አባላት ፣ የፖለቲካ ፕርግራም ልዩነቶች እንደሌሉ በመገልጽ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ፣ ካልሆኑም ደግሞ በጋራ ጉዳዮች (ሰልፎችን ማዘጋጀት፣ ከዲፕሎማቶችን ጋር መነጋገር …) አብሮ ለመስራት ፋልጎት እንዳላቸው በይፋ ማሳወቃቸው የሚታወቅ ነዉ።

በሰማያዊ ፓርቲ አመራርና ደጋፊዎች መካከል፣ «ከአንድነት ጋር አብረን መስራት አለብን» የሚሉ እየበዙ እንደሆነም አንዳንድ ፍንጮች ይጠቁማሉ። የሰማያዊ አመራር «ከአቋማችን ዝንፍ አንልም» በሚሉ የጥቂቶች አምባገነናዊነት መዳፍ ዉስጥ ካልወደቀ በስተቀር፣ ዲሞክራሲያዊ አሰራር ካላ፣ በስማያዊ ፓርቲ አንዳንድ በሳል አመራር አባላት እንዲሁም ለሕዝቡ ቅርብ በሆኑ ተራ አባላት ግፊት፣ ሰማያዊ አክራሪ አቋሙን ያለዝባል የሚልም ግምት አለ።

sem11

sem13

sem12

sem10

sem9

sem7

sem6

sem5

sem4


ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሾቹ የኦሮሞ ሕዝብና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ነውን እንዴ?! በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን

$
0
0

‹‹ዕርቅና ሰላም የሕይወት ቅመም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደውለታ ቢስ ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ የሚሆን መልስ እነሆ!›› በሚል ርእስ የጻፉትን ጦማር እጅግ የማክበርዎና ኢትዮጵያዊው የምሆን ወንድምዎ ደጋግሜ አነብበኩት፡፡ ፕሮፌሰር በትክክል ተረድቼዎት ከሆነ እርስዎ በጽሑፍዎ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዋንኛ መልእክትዎ፣ አንድም ‹‹ዕርቅንና ሰላም መስበክ›› ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት ወይም ውለታ ቢስ አድርገው ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ መልስ ይሆናል በሚል እነሆ ያሉት ጦማር እንደሆነ ነው፡፡

ፕሮፌሰር ለረጅም ዓመት ካካበቱት ዕውቀትዎ፣ በትምህርት ዓለም በሥራ፣ በምርምርና ጥናትዎ ከሕይወት ተሞክሮዎና ልምድዎ በመነሳትና እንዲሁም ዕድሜዎን ሙሉ ከመረመሯቸውና በአካዳሚያው ዓለም አንቱ ከተሰኙባቸው፣ ከበሬታን ካተረፉባቸውና ጥንታዊ የኾኑ መዛግብቶቻችንን በመመርመር እስካሁን ድረስ እያካፈሉን ስላለው ሰፊ የሆነ እውቀትዎ ከምስጋና ጋር ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡ ከገለታዬ አስከትዬ ግን በተለያዩ ድረ ገጾች ከሰሞኑን ባስነበቡን ጽሑፍዎ ማዘኔን ልገልጽልዎ እወዳለሁ፡፡

ይህ ጽሑፍዎ ከዕርቅና ሰላም ይልቅ ጠብንና ኹከትን፣ ከፍቅርና አንድነት ይልቅ መለያየትን የሚዘራ መስሎ ነው የታየኝ፡፡ መቼም ለእንደ እርስዎ ዓይነት ዘመኑን ሙሉ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የሆኑ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ሲመረምር ለነበረ ሊቅ/ምሁር ስለ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ታሪከ ማስረዳት ‹‹ለቀባሪው አረዱት›› አሊያም ደግሞ ‹‹ልጅ ለአናቷ ምጥ አስተማረች›› እንዳይሆንብኝ እሠጋለሁ፡፡ ቢሆንም ግን ፕሮፌሰር በዚህ ጽሑፍዎ ለዕርቅና ሰላም ይሆናል ብለው ባቀረቧቸው መፍትሔዎች ዙሪያ ጥቂት ሙግቶችን እንዳቀርብልዎ አስገድዶኛል፡
በሙያዬ የታሪክ ተመራማሪ፣ የአርኮዮሊጂና የቅርስ ባለሙያ ነኝ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት ረገድም ጥንታዊትና ሐዋርያዊት በምትሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ካሉ ሊቃውንት አባቶቼ እግር ስር ከማያልቀው ዕውቀት ምንጫቸው እጅግ በጥቂቱ ለመጥለቅ ሞክሬያለኹ፤ እስከ ሕይወት ፍጻሜዬም ከእነዚህ አባቶቼ የማያልቀውን ሰማያዊ ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን መጥለቄን እቀጥላለኹ ብዬ አስባለኹ፡፡ እናም ክቡር ፕሮፌሰር በአንዲት ቤ/ን ጥላ ስር መገኘታችንና ሁለታችንም የኢትዮጵያን ረጅም ዘመናት ታሪክ፣ የሕዝቦቿን ገናና ሥልጣኔ፣ መንፈሳዊና ቁሳዊ ቅርሶቿን ለመመርመር ምንተጋ ከመሆናችን የተነሣ በዚህ ጦማሬ ቋንቋ ለቋንቋ፣ አሳብ ለአሳብ እንግባባለን ብዬ እገምታለኹ፡፡

ፕሮፌሰር ‹‹ዕርቅና ሰላም ለሕይወት ቅመም›› ብለው የጻፉት ጽሑፍዎ እንደሚመስለኝ መነሻ ያደረገው ባለፈው ሰሞን በአሜሪካ ሚቺጋን ስቴት የሚኖረው ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጀዋር መሐመድ፣ አንዳንድ በውጭ አገርና በኢትዮጵያ ያሉ የኦሮሞ ልሂቃንና የብሔረሰቡ ተወላጆች ዘንድ ዳግመኛ እንደ አዲስ በሰፊው መከራከሪያ ሆኖ በዘለቀው የኦሮሞ ታሪክ ትንታኔ፣ የሕዝቡ የነጻነት ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ቤ/ን ለአቢሲኒያ/ለነፍጠኛ ገዢዎች ቅኝ ግዛት ዘመቻ ዋንኛዋ አጋር ነበረች በሚሉትና በመሳሰሉት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ትኩሳቶች ዙሪያ ሲንሸራሸሩ የነበሩና አሁንም ያሉ አሳቦች ይመስሉኛል፡፡
እርስዎም በዚህ ክርክር መነሻነት ተስበው ይመስለኛል ለዕርቅና ለሰላም መፍትሔ ይሆናል ባሉት ጽሑፍዎ የኦሮሞ ሕዝብ አውዳሚ፣ አረመኔና ጨካኝ እንደሆነ የነገሩን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ‹‹ጋዳ›› የሚለው ሥርዓት አንዳንዶች እንደሚሉት አፍሪካ በቀል የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሣይሆን ሕግ አልባ፣ በጭፍን የሚጓዝ የማፊያዎች ጥርቅም እንደሆነም አስረግጠው ነገሩን፡፡ እነ ጃዋርና ተከታዮቻቸውም በሸሪያ ሕግ ሊገዙንና ሊዳኙን እያቆበቆቡ ያሉ ጠባብ ብሔርተኞች፣ የኢትዮጵዊነት/የአንድነት መንፈስ ነቀርሳና የሰይጣን መልእክተኛ ናቸው ሲሉም ፈረጇቸው፡፡
አስከትለውም የኦሮሞ ሕዝብና ኢትዮጵውያን ሙስሊሞችም አባቶቻቸው በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ቅርስና ሥልጣኔ ላይ ላደረሱት ውድመትና ጥፋት ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባቸው ለማሳሰብ ሞከሩ፡፡

ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጭካኔና አረመኔነትም ከአገር ውስጥ ካሉ ጸሐፊዎች እስከ ውጭ አገር የታሪክ ጸሐፊዎችና ተመራማሪዎች ድረስ የመሰከሩት ስለሆነ፣ ‹‹ጩኸቴን ቀሙኝ›› አሊያም ‹‹ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኻል›› እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ኦሮሞዎች በኢትዮጵያና በክርስቲያኑ ሕዝብ ላይ ላደረሱት አሰቃቂ ግፍና በደል፣ እንዲሁም ወደ አንድነትና ኅብረት እንዲመጡ ላደረጓቸው ንጉሥ ምኒልክ በሀውልታቸው ስር የይቅርታ ጉንጉን አበባ በማኖር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርዱና ለባለውለታቸው ለምድራቸው/ለአፈራቸው ልጅ ለጎበና ዳጬም ሀውልት እንዲያቆሙላቸው ምክርዎን ለግሰዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸውን ያህል ታላቅ ምሁርና ላለፉት በርካታ ዓመታት የኢትዮጵያን ታሪክ የመረመሩ ሰው እንዴት የኦሮሞ ሕዝብንና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥለው በአገሪቱ ላይ ለደረሰው ውድመትና ጥፋት ተወቃሽና ይቅርታ ጠያቂዎች እንዳደረጓቸው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ መቼም ፕሮፌሰር ኢትዮጵያ በምትባል ግዛት ይኖሩ የነበሩ የተለያዩ ሕዝቦች በተለያዩ ዘመናት ባደረጉት ጦርነትና የግዛት ማስፋፋት ወረራ የየበኩላቸውን ጥፋትና ውድመት እንዳደረሱ ይስቱታል ብዬ አልገምትም፡፡

ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ታሪካችን ዘመን፣ በታሪክ ምሁራን ዘንድ ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› ተብሎ በሚጠራው ዘመን በአማራነት ስም የሚጠሩ ገዢዎች፣ መሳፍንትና መኳንንት፣ የጎንደሩ በወሎ፣ የጎጃሙ በሸዋ፣ በትግራይ የእንደርታው፣ በአጋሜ፣ የአድዋው በአክሱም፣ በኦሮሞው ግዛትም የአርሲ፣ የባሌ፣ የሸዋና ወለጋ እያለ እርስ በርሱ እንዳልተላለቀና የአገሪቱን ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውሶች እንዳልዳረጉ ለምን የኦሮሞን ሕዝብ ብቻ ነጥለው ወራሪ፣ አውዳሚና ብቻ አድርገው እንደሳሉት በእጅጉ ግራ የሚያጋባ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዛዝብም ጭምር ነው፡፡
ፕሮፌሰር በእንዲህ ዓይነት የአንድ ወገን ብቻ የታሪክ አተያይና ትንታኔና እንዲሁም ፍረጃ ዕርቅንና ሰላምን ማውረድ ይቻላል ብለው አስበው ከሆነ ይህንን ጽሑፍ እንካችሁ ያሉት ትክክል አይመስለኝም፡፡ በእኔ እሳቤ በአብዛኛው በአገራችን ታሪክ አንድን ብሔር ወይም ሕዝብ ሆን ብሎ ለማጥፋት ወይም ለመፍጀት የተደረጉ ዘመቻዎች ነበሩ ብዬ ለመውሰድ እቸገራለኹ፡፡ አብዛኛው የታሪካችን ገጽ የሚሳየን ገዢዎች ለሥልጣን፣ በገብርልኝ አልገብርህም ሰበብ የኢኮኖሚ ጥቅምንና የፖለቲካ የበላይነትን ለመውሰድ በነበረ ውድድርና ፍጥጫ በተደረጉ ጦርነቶችና ወረራዎች ብዙዎች ምስኪኖች አምነውበትም ሆነ ሳያምኑበት ጭዳ እንደሆኑ ነው የማስበው፡፡
በተመሳሳይም በአገራችን በአብዛኛው በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ተደረጉ ጦርነቶች ውስጥም ቢሆን ሃይማኖት መሳሪያ ወይም ሽፋን እንጂ ሃይማኖትን ሰበብ አድርገው በተነሱ ተፋላሚዎች የተደረጉት ጦርነቶች ዋና ምክንያት አልነበረም፡፡ ሃይማኖት ሽፋን ነው፡፡ ጠቡና መሠረታዊው ቅራኔ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን የኅብረተሰብ ክፍሎች እንመራሃለን ወይም እናስተዳድርሃለን በሚሉት ገዢ መደቦች የሚነሳ የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ጥያቄ ነበር፣ ነውም፡፡

እናም የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ሂደት ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበጎም ሆነ በክፉ ጎኑ የሚነሳበት ታሪክ ያለው ሕዝብ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡ ፕሮፌሰር የኦሮሞ ሕዝብን ብቻ ነጥለው አውዳሚና የጥፋት ልጅ እንደሆነ በጻፉበት ብዕራቸውና ለዚህም መከራከሪያቸው ከጠቀሷቸው የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጸሐፍት መካከል ለምን እነዚሁ ጸሐፊዎች በአንጻሩ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ በተመለከተ የተዉትን ምስክርነታቸውን ለመጥቀስ/ለመጻፍ እንዳልደፈሩ ግን ግልጽ አይደለም፡፡
እስቲ ለአብነት ያህል አፅሜ ጊዮርጊስ የተባሉ ጸሐፊ ‹‹የኦሮሞ ታሪክ›› በሚል በተዉልን የታሪክ ማስታወሻቸው ዐፄ ምኒልክና ሠራዊታቸው በኦሮሚያና በደቡብ የአገራችን ክፍሎች ባደረጉት የማቅናት ዘመቻ ወቅት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ስለደረሰው በደልና ግፍ የከተቡትን በጥቂቱ እንመልከት፡፡
በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ኦሮሞ ሁሉ ተገዛ፣ በአማራ ሕግና ሥርዓት ሔደ፣ ካህናቱ አንድ ኦሮሞ አስተምረው አላጠመቁም፡፡ ይልቅስ ተፊተኛው ቂም የበለጠ ቂም በልቡ አኑረውበት መሬቱን በቀላድ ወሰዱበት፡፡ አንድ ቀላድ የቅስና አንድ ቀላድ የአወዳሽ እያሉ በዚሁ ስብከት ንጉሡን አሳመኑ፡፡ ስለ መንግሥት ያሰቡ መስለው ለንጉሡም አንድ ቀላድ፣ ለወታደር አንድ ቀላድ … መሬቱን ተካፍለው ኦሮሞን እንደ ባሪያ አድርገው ይገዙታል እንጂ የክርስቶስን መንገድ አላሳዩትም፡፡ እነርሱም የእግዝሔርን መንገድ በሚገባ አልተማሩም፣ አስተማሪም ቢመጣም ይከለክላሉ …፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው የኦሮሞ ወራሪ ኃይል በአማራውና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ዘርዝረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል ባሉበት ብዕራቸው ለምን ይህንም የኦሮሞ ሕዝብን በደል ወይም የታሪካችንን ሌላውን ገጽ ቦታ አንዳልሰጡት፣ ሊያነሡት ወይም ሊነግሩን እንዳልደፈሩ ግልጽ አይደለም፡፡ ፕሮፌሰሩ መልእክቴ በኢትዮጵያ ምድር ዕርቅና ሰላም ለማውረድ ነው ካሉን ዘንድ ሚዛናዊ በመሆን አንዱን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም የታሪካችንን ገጽ ሊያሳዩን በተገባቸው ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የአንድ ወገን ብቻ የሆነ የታሪክ ትንታኔና ዕይታ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወዴየትኛው የጥፋት መንገድ ይዞን እንደነጎደ በተግባርም ጭምር ዐይተነዋል፡፡

በሌላም በኩል እስቲ እስካሁንም ድረስ ሳስበው ግርም የሚለኝን ከዚሁ ካነሳሁት ርእሰ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አንድ ገጠመኜን እዚህ ላይ ጨምሬ ለማንሳት እወዳለኹ፡፡ ታሪኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርንበት ሰዓት የኾነ ነው፡፡ በዩኒቨርስቲው ካሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ዘንድ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጥላ ስር አብረን ያለን ጓደኛዬ በአንድ ወቅት ‹‹ራእይ ማርያም›› ከሚል የጸሎት መጽሐፍ ኮፒ የተደረገ ጽሑፍ ከአንድ ከሌላ ኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጓደኛው ጋር ይዞ በመምጣት እንዲህ አለኝ፡፡

‹‹ይቅርታ፣ ከልቤ አዝናለሁ … በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በጌታችንና በመድኃኒታችን ክቡር ደም ፈሳሽነት/ቤዛነት ሁላችንም በአንድ መንፈስ፣ ሰማያዊ ዜጋ ሆነን የእግዚአብሔርን መንግሥት እንወርሳለን ብላ በምታስተምር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሕዝቦችን የሚለያይና የሚከፋፍል መጽሐፍ መኖሩን እስከዛሬ አላውቅም ነበር፡፡›› በጓደኛዬ ንግግር ውስጥ እልክና ብርቱ የሆነ አንዳንች የቁጭት መንፈስ ነበር የሚነበብበት፡፡ ‹‹… ለመሆኑ ይህን መጽሐፍ አይተኸው ወይም አንብበኸው ታውቃለህ በማለት ‹‹የራእይ ማርያም›› መጽሐፍን አንድ ገጽ ኮፒ እንዳነበው በእጄ ሰጠኝ፡፡ እንዲህ ይላል፡-
… ከስር እስከ ጫፍ፣ ከጫፍ እስከ ስር ድረስ በአምስት ሺሕ ዓመት የማይደረስበት ትልቅ ገደል አሳየኝ፡፡ ያንዱ ነፍስ በአንዱ ላይ ሲወድቅ ዐየኹ፡፡ እኔም ምንድናቸው ብዬ ልጄን (ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስን መኾኑን ልብ ይሏል) ጠየቅኹት፡፡ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላት፡- … አራስ፣ መርገም፣ ደንቆሮ፣ ‹‹እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ›› ጋር የተኙ፣ ፈረስ፣ አህያ፣ ግመል በግብረ ስጋ የሚገናኙ፣ ወንዱም ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚዳረጉ… እነዚህ ሁሉ ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ …፡፡

በጊዜው ይህን ጉድ ካነበብኩ በኋላ እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና እርግማን የሞላበት መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያኒቱንና እውነተኞቹን የወንጌል መምህራን የሆኑትን አባቶቻችንን እንደማይወክል ባውቅም ይህ የጸሎት መጽሐፍ ተብዬ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ታትሟልና በጊዜው የመከራከሪያ አሳብም ሆነ የምሰጠው ምላሽ አልነበረኝም፡፡ ግና ስለ ስለዚሁ የጸሎት መጽሐፍ የኩነኔ ፍርድ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ያህል፤ መቼም ሌላ ስምና መልክ እስካልተሰጠው ድረስ በመንፈሳዊው ዓለም አስተምህሮ/ሕግ ካልተፈቀደልንና የእኛ ከሆነችው ሴትም ኾነ ወንድ ውጭ መሔድ ዝሙት ነው፡፡
‹‹ከጋላ›› ወይም ‹‹ከሻንቅላ›› ‹‹ከእስላም›› ወይም ‹‹ከፈላሻ›› ጋር ስለተኛን ወይም ስለዘሞትን የተለየ ነገር ሊሆንም ሊደርስም አይችልም፣ በአምስት ሺሕ ዘመንን በሚያስኬድ ገደል ውስጥም ልንጣልም አንችልም፡፡ ደግሞስ ምን ዓይነት ሕሊና ያለው ሰው ነው ሰውንና እንሰሳን በእኩል ሚዛን አስቀምጦ ፈረስም ተገናኘህ ‹‹ሻንቅላ›› ወይም ‹‹ፈላሻ›› ምንም ልዩነት የለውም ያው ነው በሚል የሚጽፍ፡፡

አንድን ጎሳና ብሔር ለይቶ ከእነርሱ ጋር ከተኛህ እንዲህ ዓይነት ቅጣት ይደርስብሃል/ያገኝሃል ብሎ እንዲህ ዓይነቱን መርገምን፣ ጥላቻንና ክፋትን የተሸከመ ድርሳን ቅድስት፣ ንፅሕትና ርትዕት በኾነች በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም አሳትሞ በማቅረብ፣ ‹‹ፈላሻነቱንም›› ኾነ ‹‹ሻንቅላነቱን›› ወዶና ፈቅዶ ባላመጣው ሰው ሕሊና ውስጥ የጥላቻ መርዝ እንዲረጭና ልቦናው ክፉኛ እንዲቆስል ምክንያት ኾኗል፡፡

ይህ ትናንትና እንደ ዘበትና ቀልድ ያየነውና በጊዜው በይቅርታ መፍትሔ ያላበጀንለት ነገር ይኸው ዛሬ ከታሪካችን ማኅደር እየተመዠረጠ የብዙዎችን ቁስል እያመረቀዘ ቤተ ክርስቲያኒቱንም ኾነ ተከታዮቿን በጥላቻ ዓይን እንዲታዩ ምክንያት ከኾነ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ታሪኮችን ዕድሉ ያጋጠመን ሁሉ ደጋግመን ሰምተናቸዋል፡፡ መፍትሔው ምን ይሁን፣ ምን መላ እንፍጠር ከማለት ይልቅ ያለፈ ታሪክን ማንሳት ምን ይጠቅማል በሚል በማድበስበስ የተውናቸው ክስተቶች እያመረቀዙ በመካከላችን መፈራራትንና ጥላቻን አነገሡብን/አባባሱብን እንጂ መፍትሔ አልሆኑንም፡፡
ብዙዎቻችንን እያከራከረን ስላለው የትናንትና ታሪካችን ርእሰ ጉዳይ ስንመለስም አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ይኸውም አብዛኛው የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ በጦርነትና በወረራ፣ በገብር አልገብርም፣ በልግዛህ አልገዛም በተደረገ ግብግብና ጭፍጨፋ በደም የቀላ ታሪክ ነው ያለን መሆኑን፡፡

አንዱ የገዢ መደብ ሌላውን፣ ክርስቲያኑ ሙስሊሙን፣ ሙስሊሙ ክርስቲያኑን ያጠቃበት የጨፈጨፈበት በርካታ ዘመናቶች የታሪካችን አካል ኾነው አብረውን አሉ፡፡ አንዱ አገር የሌላውን አገር በጦርነት በመግጠም ሀብት ንብረቱን በመዝረፍ፣ መሬቱን በመቀማት፣ በምርኮና በባርነት በማጋዝ ያሳለፍናቸው የታሪካችን ቁስሎች በፍቅር ዘይት ለስልሰውና በዕርቀ ሰላም ፈውስ አግኝተው መፍትሔ ካላገኘን አንድ ብሔርን/ሕዝብን ወይም ሃይማኖትን ብቻ ነጥሎ እንደ ጥፋተኛና አውዳሚ አድርጎ ማቅረብ ወደምንናፍቀው የዕርቅና የሰላም ምንገድ ያመጣናል ብዬ አላስብም፡፡

ደግሞስ አማራው ከኦሮሞው፣ ኦሮሞው ከትግሬ፣ ወላይታው፣ ከጉራጌው፣ ሐረሪው፣ ከአፋር በደም፣ በአጥንት በተዛመደ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በጋራ ታሪክ በተሳሰረ ሕዝብ መካከል ብሔርና ጎሳ ለይይቶ መወቃቀሱ ጥቅሙ ምንድን ነው፡፡ ትርፉስ ለማን ነው?! በእርግጥም ለእውነተኛው ዕርቀ ሰላም ቀናውን መንገድ ካላመቻቸን ላለፉት ሃያ ዓመታት ታሪክንና ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው እየተካሔዱ ያሉ የቂም በቀል ዘመቻዎች ፍፃሜያቸው እጅግ አስፈሪና አሳፋሪ እንደኾኑ ነው የታዘብነው፡፡

በሃይማኖትና በብሔርተኝነት ስም በአዲስ አበባና በሌሎች ክልል ከተሞች ቦግ እልም እያለ ያለውና ተዳፈኖ ያለው የረመጥ እሳት ሊያስከትለው የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ መፍትሔ ካላበጀንለት (ያው እስከ ዛሬ ድረስ በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በወተር፣ በቤሻንጉል ጉሙዝ፣ በጅማ … የደረሰው አሰቃቂ እልቂት፣ ጥፋትና ውድመት ሳይዘነጋ) ይህ ዓለም ሁሉ የሚያደንቀውና የምንኮራበት፣ በቋፍ ያለው ለዘመናት አብረን በፍቅርና በወዳጅነት የቆየንበት አኩሪ ታሪካችን በነበር ልናወሳ የምንገደድባቸው ጊዜያቶች ሩቅ ሊኾኑ እንደማይችሉ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ያለፈው ሰሞን የእነ ጃዋር መሐመድና የኦሮሞ ወንድሞቻችን ኦሮሞነትን ከኢትዮጵያዊነት ነጥለው ያቀረቡበት ትርክትና የትናንትና ክፉ የታሪክ ጠባሳችን፣ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸውና እያንጸባረቁት ያለው ቁጣ፣ ቅያሜና ዛቻ የነገይቱ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱስ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ብለን እንድንጠይቅ፣ እንድንሰጋ ያስገድደናል ብዬ ለማለት እደፍራለኹ፡፡
አገሪቱን እያሥተዳደረ ያለው መንግሥትም ለጉዳዩ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ያለ ቅጥ ያራገበው የብሔር ፖለቲካ ወላፈኑ እራሱንም ጭምር እየለበለበው እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ‹‹ካፈርኩ አይመልሰኝ›› በሚል ግትርነትና ዕድሜዬን ያራዝምልኛል በሚል እንዲሁ በአገም ጠቀም የተወው የጎሰኝነት/የዘረኝነት ጉዳይ ነገ መዘዙ ከየት እስከ የት ሊመዘዝ እንደሚችል መገመት የሚያዳግት አይመስለኝም፡፡ ትናንትና በሆነው በሚያኮራው ታሪካችን ተከባብረንና ተዋደን፣ አሳፋሪና ክፉ ጠባሳ የተዉብንን የታሪካችንን ምዕራፍ ደግሞ በይቅርታ ዘግተን በፍቅርና በመቀባበል መኖር ካልተቻለን የሚጠብቀን ዕድል ጥላቻ፣ መከፋፋት፣ ጠላትነት፣ መለያየት … ብቻ ነው ሚሆነው፡፡
ይህ እንዳይሆንብን፣ ይህ ክፉ ነገር እንዳይደርስብን ቆም ብለን ማሰብ ያለብን ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ያሉ የዕድሜ ባለፀጋዎችና ምሁራን፣ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራኖቻችንና የፖለቲካ መሪዎችም ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ወደ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት የሚመጡበትን ቀና የሆነ መንገድ በማመቻቸት አገሪቷን ከተደቀነባትና ካዣንበባት ጥፋት ሊታደጓት የትውልዱንም ልብ በፍቅር ዘይት አልስልሰው ለይቅርታ/ለዕርቀ ሰላም ሊያዘጋጁት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ከእኔ ይበልጥ ከእኔ ይበልጥ የፉክክር መንፈስ ወጥተው ለአገርና ለሕዝብ የሚሆን የዕርቀ ሰላም መልእክት ይዘውልን ሊመጡ ይገባቸዋል፡፡

ነገሥታትን/መንግሥታትንና ክፉ መሪዎችን በመገሠጽ፣ በሕዝቦች መካከል ፍቅርንና ሰላምን፣ በአገራችንም ብሔራዊ ዕርቅን በማስፈን ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና መንፈሳዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሊያ ግን ዕርቅንና ሰላምን ያወርዳሉ ያልናቸው አባቶቻችንም እርስ በርሳቸው ተለያይተውና ተወጋግዘው፣ ለነገ ህልውናችን በሚል ሰበብ የፖለቲከኞችን ጉያ የሚመርጡ ከሆኑ፣ ከእውነትና ከፍትሕ ጎን ለመቆም መንፈሳዊ ድፍረትና ወኔ ከተለያቸው እንዴት ባለ መንገድ ነው ፍቅርንና ዕርቅን ሰብከው አገሪቱንም ሆነ ትውልዱን ከጥፋትና ከሞት መንገድ ሊታደጉት የሚችሉት?!
በታሪካችን ለኾኑት ስህተቶች በግልፅ ይቅርታ ተጠያይቀን ዕርቅ ማውድ ካልቻልን አስቸጋሪ ነው፡፡ የሚሻለው መነጋገርና መግባባት ነው፡፡ እንደ እውነቱም ከኾነ ትናንትና ለኾነው በደል እውቅና መስጠት ሳይቻል ዕርቅ ዕርቅ የሚለው ነገር ከጉንጭ አልፋ ወሬነት የሚያልፍ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አላስብም፡፡ ዛሬ እንደገና ከበርካታ ዓመታትም በኋላ ተመልሶ እነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የምኒልክ ጦር በአያቶቻችን ላይ ያደረሰውን በደል አንረሳውም ወደሚል አዙሪት መልሶ እየከተታቸው ያለው ይኸው በይቅርታ ያልተወራረደው ታሪካችን ጥሎብን የሔደው ክፉ አበሳና ጠባሳ ይመስለኛል፡፡

እናም እንደ ፕ/ር ጌታቸው ያሉ ምሁራንና የዕድሜ ባለጠጋዎች የአንድ ወገን ታሪክን ብቻ በማጉላት ሳይሆን ሚዛናዊነት ባለው መልኩ ታሪካችንን በማቅረብ የሁላችንም የጋራ ቤታችን በሆነች ኢትዮጵያችን ተስማምተን፣ ተዋደን፣ ተፋቀርንና ተከባብረን የምንኖርባት አገር እንድትኖረን የታላቁን የሰላምና የይቅርታ አባት የኔልሰን ማንዴላን ዓይነት ሚና በመጫወት የትውልድ ባለውለታ ይሆኑ ዘንድ በእኔና በትውልዴ ስም አደራ እላለሁ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!

ትግልሽን አደነቅ በለምለም ፀጋው

ወጣቱ ትውልድ ከዓድዋ ድል የሚማረውና የሚወርሰው ምንድን ነው? (ኢሕአፓ)

ሚሊየኖች ድምጽ –ትግሉን ይቀላቀሉ ኪሚሊዮኖች አንዱ ይሁኑ ! እንዴት ካሉ የሚከተለዉን ያንብቡ

$
0
0

የባህር ዳር ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ሕዝቡ ከፍተኛ አፈናን ተቋቁሞ፣ ፍርሃትን አዉልቆ የነጻነትን ደዉል አውጇል። ሕዝብ በባህር ዳር ተናግሯል። በዚህ በባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠሩ ብቻ አይደለም ሕዝብ የተሰባሰበው። ዉስጥ ዉስጡን ከፍተኛ ድርጅታዊ ሥራ ስለተሰራ፣ ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ማንቀሳቀስ ስለተቻለ ነው። ድርጅቶች (መኢአድ፣ አድንነት እና ትብብር) በተናጥል ሳይሆን በትብብርና አብሮ በመስራት ስለመሩት ነዉ።

pic14

ይህ የባህር ዳር ሰልፍ በየቤታችን ትልቅ ደስታን እንደፈጠረ ይገባናል። ዜጎች በድፍረትና በነጻነት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ የመሰለ ደስታ የለም። ሁላችንም ተደስተናል፣ በባህር ዳር ሕዝብም ኮርተናል።

የባህር ዳሩ ሰልፍ ግን ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ መሆን የለበትም። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እየተደጋገሙ፣ በጥራትና በብቃት፣ በመቀሌ፣ በአዋሳ፣ በድሬደዋ፣ በጂማ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በመሳሰሉ ሌሎች ከተሞች መደረግ አለባቸው። የነጻነት፣ የሰላም፣ የኢትዮጵያዊነት እሳት መቀጣጠል አለበት።

አንድነት/መኢአድ በፊታቸው ከፍተኛ ሥራ አለባቸው። ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በባህር ዳር የታየዉን አይነት ሥራ ለመስራት ትልቅ ወጭ አለው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀበቶዉን እንዲታጠቅ፣ ትግሉን እንዲቀላቀል፣ የድርሻዉን እንዲወጣ ያስፈልጋል። ከአሁን በኋላ ወደ ኃላ መመለስ የለም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በባህር ዳር እንደተደረገዉ፣ በአገራችን ግዛቶች ሁሉ ሕዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፤ የግድ ነው። ይቻላልምም።

በባህር ዳር ሁኔታዎች ስለተመቻቹ አልነበረም። የፖለቲካ ምህዳሩ ስለተከፈተ አልነበረም። የመኢአድ እና አንድነት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ታስረዋል፣ ተዋክበዋል ከሥራ ተባረዋል፣ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ነዉ። ነገር ግን የተዘጋዉን በር በትግላቸው አስከፍተው ነዉ በባህር ዳር እንዳየነው ሕዝቡን ያንቀሳቀሱት።

በአገር ቤት ያለን ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች ፣ ወንዶች ፣ ወጣቶች አረጋዉያን፣ ክርስቲያኑ ፣ ሙስሊሙ፣ ትግሬው፣ አማራዉ፣ ኦሮሞዉ፣ ቅልቅሉ … ሁሉን ኢትዮጵያዊ ከአንድነት ጎን እንዲሰለፍ እንጠይቃለን። አንድነት እንደ ሌሎች ጠመንጃ የለውም። አንድነት የፈረንጆችን ጥቅም እንደሚያስጠብቁት እንደ ሌሎች የዉጭ መንግስታት ድጋፍ የለዉም። የአንድነት ኃይልና መተማመኛ ሕዝብ ብቻ ነው።

እንግዲህ

1. አገር ቤት ያለን በአካባቢያችን ወዳሉ የአንድነት ጽ/ቤቶች፣ በዉጭ ደግሞ ያለን የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች በመሄድ እንዴት መርዳትና መተባበር እንዳለብን እንጠይቅ።

2. http://www.andinet.org በመሄድ በክሬዲት ካርድ ወይንም ፔይ ፓል የገንዘብ ድጋፍ እናድርግ።

3. የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ እና የፍኖተ ነጻነት ገጽ ላይክ በማድረግ እየተሰሩ ያሉትን እንከታተል። መልእክቶችን በማስተላለፍ የቅስቀሳቅዎች አካል እንሁን::

https://www.facebook.com/FinoteNestanet https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

4. አገር ዉስጥ ላለን በአካባቢያችን የአንድነት መዋቅር ከሌለ፣ በዉጭ ደግሞ የድጋፍ ድርጅት ከሌሉ፣ ሁለት ሶስት ፣ ሆነን እራሳችንን አደራጅተን፣ ፓርቲዉን ፓርቲዉን በማሳወቅ ትግሉን እንቀላቀል። የድጋፍ ድርጅቶች ከሌሉ፣ የአገር ቤቱን ትግሉ የሚደገፉ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በነርሱ በኩል ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

5. በግለሰብ ደረጃም በጽሁፍ፣ በሃሳብ መርዳት ከፈለግን organizingethiopia@gmail.com በሚለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን።

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ወቅት እንዳለችዉ፣ ፀሐይ ለኢትዮጵያ ወጥቶላታል። ከአሁን በኋላ አይጨልምም::

አቡጊዳ –ሰልፍ በአዲስ አበባ ሊጠራ ነው – - የአድዋ በአልን ለማክበር

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ ከመኢአድ እና ትብብር ተብሎ ከሚታወቀዉ የአሥር ድርጅቶ ስብስብ ጋር በመሆን የ118 ኛውን የአድዋ ድል መታሰቦያ እንደሚያከብሩ፣ የአንድምነት ልሳን ፍኖት ነጻነት ገለጸ።

adwa_final

በአሉ የሚከበረዉ ወደ 3.7 ኪሎሜትር ከቀበና የአንድነት ጽ/ቤት እስከ ጊዮርጊስ የሚኒሊክ አደባባይ በመጓዝ ሲሆን፣ በይነቱ የመጀመሪያዉ አከባበር ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል። የፍኖትን ዘገባ እንደሚከተለው ያንብቡ
ፍኖት – 118ኛውን የአድዋ ድል በዓል 3 ፓርቲዎች ሊያከብሩት ነው
——————————–
የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ በወሰነው መሰረት የአድዋ ድል በዓልን ከሁለት ፓርቲዎች ጋር ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡
ነገ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ፓርቲዎቹ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ህዝብ ግንኙነት ክፍሉ እንደገለፀው መኢአድና ትብብር አንድነት ፓርቲ የአድዋ ድል በዓልን በጋራ በአዲስ አበባ ለማክበር ያቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው የጋራ ኮሚቴ አቋቁመው ዝግጅቶችን እያደረጉ ነው፡፡ ሶስቱ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ በወሰነው መሰረትም የበዓሉ አከባበር መነሻውን የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት አድርጎ በእግር ጉዞ የአፄ ምኒልክ ሃውልት ስር አበባ የማስቀመጥ ስነስርዓት እንደሚኖርና በመጨረሻም በመኢአድ ጽ/ቤት በዓሉን አስመልክቶ የፓናል ውይይት እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዓሉን በማስመልከትም ነገ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ፓርቲዎቹ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

አቡጊዳ –ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ስለአድዋ የገጠመው

በማተብዋ ልዳኝ –ወድቃ የተነሳችው (ከስንሻው ተገኘ)

$
0
0

ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።

“ ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ….

አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ (ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት ነበር። የሁሉም አገር – ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት። ዓይናችሁን ጨፍኑና ጊዜን አጣጥፋችሁ ወደዚያ ዘመን (1952-53) ብረሩልኝ። መጀመርያ ስለዚህ ጉዳይ ዴቪድ ሜሬዲት The first dance of freedom ን መጽሐፍ አነበብሁና (በ1985) ወዲያው እጅግ ወዳጄ ለነበሩት ለልጅ ሚካኤል እምሩ አነሳሁባቸው። በወቅቱ በእንግሊዝ አገር ስለነበሩ በግል በትኩረት የሚያውቁት መሆናቸውን አረጋገጡልኝ። ከላይ ያቀረብሁት ዘገባም የማርቲን ሜሬዲትና የልጅ ሚካኤል እምሩ ጭምቅ ሪፖርት ነው። (ልጅ ሚካኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄዱ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።)

የወቅቱ ተራማጅ ሁሉ ይህንን በጽሞና ሲከታተል ኋይት ሖል (የእንግሊዝ መንግሥት) በዚያው ሰሞን (1953) በኢትዮጵያና አንድነትዋ ላይ ትልቅ ሴራ ሲያቀጣጥል ነበር። ሊቆራርጠን። አርነስት ቤቪን የተባለው የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶማሊያ ነፃ ስትሆን የኢትዮጵያን ኦጋዴን፣ ሪዘርቭድ ኤርያና – ሐውድ እንዲሁም ጅቡቲንና የኬንያን ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት አጠቃልላ ታላቅዋን ሶማሊያ ስትመሠርት በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ከአለውሀ ባሻገር ያለው መሬት በሙሉ (ማለትም ትግራይና ኤርትራ ተዋህደው ትግራይ ትግርኝ የሚባል አገር ለመፍጠር ሽርጉድ ይዘው ነበር።) lyndon larouche የተባለውና በመደበኛው አስተሳሰብ አክራሪና የተወናበደ የፖለቲካ ነውጠኛ የአገሩን ፖለቲካ ጨረሰና ዛሬ በመላው ዓለም እየደረሰ ያለው ችግር እንግሊዝ ዘርታ ያበቀለችው አድርጐ ነው የሚያቀርበው። ይኽ አይጠረጠርም። በበኩሌ እንደማውቀው እንግሊዙ አርነስት ቤቪን የጀመረውን አይኤም ሌዊስ ካልፈጸምሁት ብሎ እነ በረከት ሀብተ ሥላሴን፣ እነ መለስ ዜናዊን ይዞ ለዓመታት ተንደፋድፎአል። (መለስ በዜግነት ሶማሊያዊ ነበር)- በነገራችን ላይ እነ በረከት ሀብተሥላሴ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ ተወልደው ያደጉባት፣ ተምረው የተሾሙባት ኢትዮጵያ፥ ዓለማቸውን ያዩባት ውብ አዲስ አበባ- ወደ ኢምንትነት እንድትመለስ ሲፍጨረጨሩ እንደ ራስ ተፈሪ ያሉ ሕዝቦች “ቤታችን መግቢያችን (ራስታ የምንላቸው)” በማለት ወደዚያች አገር መጉረፍ ይዘው ነበር።

ተመስገን ደሳለኝ ወደ ጐንደር ሄዶ ነበር አሉ። ባዶ እጁን አልተመለሰም። ወያኔ ያነወራት፣ እንደ ተስፋዬ ሐቢሶ ያሉ (በተቆላበት የሚያፈሉ) ሰነፎች የተሳለቁባት፣ በመንፈሳዊና ሕዝባዊ ክብርዋ መለስ ያሾፈባት፣….ወያኔዎች በባዶ እግራቸው የረጋገጡአትና የኮሾሮ (የአምባሻ) መያዣ ያደረጉአት….በእኔ ዕድሜ ጅማሬ ላይ “ወድቃ የተነሳችው” እየተባለች ስትጠቀስ የቆየችው ሰንደቅ ዓላማ በጐንደር ምንኛ ታላቁን ክብርዋን ይዛ – እንዳለችና እንደምትኖር የምሥራቹን ነግሮናል። ብሥራት ነውና ምሥር ብላ! ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ይኸ ወጣት ጋዜጠኛ ነው።

ኢጣሊያ የኤርትራን ደጋማ አውራጃዎች ለመያዝ የቻለችው በ1889ዓ.ም እንደ አ.አ ነው። እዚህ ላይ የንጉሠ ነገሥቱን (አጤ ዮሐንስ) አጐት ራስ ደበብንና በኋላ ጊዜ የራስ ሥዩምን ሴት ልጅ ያገቡትን ደጃዝማች ገብረሥላሴን ማውገዝ ወይስ ማወደስ ይገባ እንደሆነ አላወቅንም እንጂ በእነሱ ድጋፍና መሪነት ነው ኤርትራ የተያዘችው። ዛሬ አኪሩ ዞሮ ባንዳ የሚወደስበትና የሚቀደስበት፣ ወደል ወደል መጽሐፍም በውዳሴ መልክ የሚቀርብበት በመሆኑ ነው ግራ የተጋባነው። አዎን ዓላማዬ በማንም ዜጋ ላይ የፍትሕ ድንጊያ ለመወርወር አይደለም። የእግዜሩን መንገድ ካወቅነው ጸሎታችን “ማረን” እንጂ “አፈራርደን” መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያን የሚታደጋት የራስዋ የኢትዮጵያ ልጅ መሆን እንደሚገባው ስንነጋገርና ስንስማማ ከቆየን በኋላ ሁሉም ነገር የተለዋወጠ ሆኖአል። ኢትዮጵያውያን አገራቸውንም ራሳቸውንም ማዳን አቅቶአቸው በአገሪቱ የሚጫወቱት ወገኖች የተነሱለትን አጥፊ ዓላማ ለመፈጸም አንዳች እንቅፋት አልገጠማቸውም። በተናጠል መስዋዕትነት የሚከፍሉ ግለሰብ የፖለቲካ ተዋናያውያንና ጋዜጠኞች ደግሞ የሚሞቱለትን ሕዝብ ሊቀሰቅሱ አልቻሉም። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያሉአት ልጆች እነዚህ ብቻ ናቸውን? እስከማለት የደረሱ አሉ። “የኢትዮጵያ ልጆች በደማቸውም በአጥንታቸውም ኢትዮጵያን ከእልቂት ለማዳን ካልቻሉ ወዴት ይኬዳል? ወደ ማን ይጮኻል?” ነቢዩ ዳዊት (ልበ አምላክ የሚባለው) ለዚህ አምላክ ራሱ በጆሮው የነገረው ቁም ነገር ነበር ይላሉ መጽሐፉን የሚተረጉሙ ሰዎች። “በልጆችዋ መተማመን ያቃታት፣ ልጆችዋ በግፈኞችና በጨቋኞች ያለቁባት ኢትዮጵያ ናት፤ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው” ይሉናል። ተስፋ ከመቁረጥ የመጣ አሳብ አይደለም። የአምላኩንም ሚና እንዳንረሳ ለማሳሰብ ነው። ውዳሴ ማርያምም ባይሆን ጥቂት እግዚኦታ!

እንደ ዛሬዋ ጐንደር ሁሉ ጣልያን ኤርትራን ከያዘ በኋላ ለስድሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ነፃነት ምልክትና የክብርዋ ዘላለማዊ መግለጫ የሆነችው አረንጓዴ፣ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ቢዘን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ ስትውለበለብ ቆይታለች። እግዚአብሔር በቤቱ (ቤተክርስቲያኑ) ላይ ያዋላት ለዚህ ሕዝብ መልእክት ኖሮት ይሆናል በማለት የገዳሙ አበምኔት በ1980 ገልጠውልኛል። በዚያን ዘመን ኤርትራ በጣልያን ሥር ብትወድቅም በየበዓላቱ ሕዝቡ ይዞት የሚወጣው ሰንደቅ- አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። አንድ ኤርትራዊ ሲሞት የአስክሬኑ ሳጥን በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃል። ሠርጐች ግርማማ የሚሆኑት በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ሲንቆጠቆጡ ነው። አብያተ ክርስቲያናት ይኽ ሰንደቅ ዓላማ ተለይቶአቸው አያውቅም። ለብዙ ዓመታት ወደ ኤርትራ ስመላለስ የኖርሁ፣ ሕዝቡን የማውቅና የማከብር ስለነበርሁ ዛሬ ይኽ ወገኔ ከዚያች ከታቦት እኩል ከሚያያትና የሕልውናው ተስፋ ከነበረችው ሰንደቅ ዓላማ ሲለይ ምን ተሰማው? እያልሁ ራሴን እጠይቃለሁ። ወይስ አዲሱ የኤርትራ ትውልድ ይኽንን ቁም ነገር አያውቀውም ነበር? እዚህ ባለሁበት አገር እንደኔው በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን አረጋውያን አውቃለሁ። ለሁሉም እንደ ቀልድ “አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ የሚለመድ ነው?” እላቸዋለሁ። በሻዕቢያ ውስጥ ከአሥርና ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ መቆየታቸውን የሚነግሩኝ ብዙ ጐበዞችን በየቀኑ አገኛቸዋለሁ። ሁለቱ በአንድ ቀን የአሜሪካ ዜግነት እንዳገኙ ሲነግሩኝ እንደ ቀልድ አድርጌ “አሜሪካዊ ለመሆን ነው ሰላሳ ዓመት የወጋችሁኝ?” እላቸዋለሁ።

ኤርትራውያኑ ራሳቸው በአጸፋው “እናንተስ ሰንደቅ ዓላማውን መቸ አስከበራችሁና ነው እኛን የምታሽሟጥጡን?” ሊሉን ይችላሉ። እግዜር ይመስገን የወያኔ ሕግ በማይሰራበት በዋሽንግተን፣ በለንደን፣ በጄኔቫ…በስዊድን…የምናምንባት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደ ልብ ትውለበለባለች። ስለዚህ ለኤርትራውያን ወገኖቻችንም “የተዋችኋትን ሰንደቅ ዓላማ በምትመለሱበት ጊዜም በዚያው ሞገስ ታገኝዋታላችሁ” ለማለት ይቻላል። (የኢትዮጵያ ሕግ በማይሰራባቸው በስዊድን ወዘተ ስል እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ ትዝ ትለኛለች። ለካንስ ስቶክሐልም ላይ የተናገሩት አዲስ አበባ ላይ ያስቀጣል?)

ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያከብር የኖረው የኤርትራ ሕዝብ ነበር ስል ሌላው ሕዝብ ደንታ እንዳልነበረው መግለጤ አይደለም። ግመሎቻችን፣ በጐቻችን፣ የጋማ ከብቶቻችን፣ የቤትና የዱር እንስሶቻችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የክብር ዓርማ ያውቁታል እያሉ የሚያወጉአችሁ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ብዙ ናቸው። የአውሳው ርእሰ መኳንንት ቢተወደድ አሊሚራሕ አንፍሬ በአንድ ወቅት “እንኳን አፋሩ ሕዝባችን ግመሎቻችንም ሰንደቅ ዓላማችንን ያውቁታል” ማለታቸው ይጠቀሳል። አጋጣሚ ነገር ላንሳና ኮማንደር ለማ ጉተማ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የመሥሪያ ቤቴን ቅርንጫፍ ሥራ ለማስተባበር ወደዚያ እመላለስ ነበር። ሁለት ጊዜ ያህል የኢሳውን ባላባትና ሱልጣን ደጃዝማች ዑጋዝ ሐሰንን ተዋውቄአቸው ነበር። “ትልቁ ልጄን ትመስለኛለህ” ሲሉኝ ልዩ ፍቅር አደረብኝ። ታዲያ በ1983 አካባቢ ቢትወደድ አሊ ሚራሕ የተናገሩትን ቃል በቃል ደጃዝማች (ዑጋዝ) ሐሰን ሲናገሩት ሰምቻቸዋለሁ። ማጋነን ባይመስል ግመሎቹ ቀጥ ብለው እንደሚቆሙ ይናገራሉ። ጐበዝ! “ግመሎቻችን ለኢትዮጵያ ከእኛ የበለጠ ታማኝ ናቸው” ብል በድፍረት ትወስዱብኝ ይሆን? ግመሎቻችን ጭምር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውቁታል! እነመለስ ከዚያች ቅርጽ የለሽ እንስሳ ማነሳቸው ከተሰማችሁ አብሬአችሁ ልከሰስ እችላለሁ።

ፋሺስቶች ባላደረጉት ድፍረትና ብልግና በቀለም እኛን ይመስል የነበረው መለስ የሕገ መንግሥት ጉባዔ ሲመራ ያቺን ሰንደቅ ዓላማ እንዴት እንዳብጠለጠለ ታስታውሳላችሁ። እዚያ ጉባዔ ውስጥ በጀግንነትና በታላቅ ወኔ ይቺን ሰንደቅ ዓላማ ያወድሱ፣ የቆሙላትና ስድቡን ሁሉ የተሸከሙላት ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ (ነፍሰ ሄር) ብቻ ነበሩ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ መንጋ ወሮበሎች ፋሺስቶች ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ በመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያሰሙ ያሰማሩባቸውን ሥራ ፈቶችና ማጅራት መችዎችን አስታውሶኝ ነበር። ይችም አገር ዛሬ (በ21ኛው ክፍለ ዘመን) በዋልጌዎች፣ በጫካ አደጐች፣ በቀማኞች…እጅ እንደገባች ሁላችንም ተከሰተልን። ያን ጊዜ ከመታኝ ብራቅ እስካሁን አላገገምኩም።

እኛ ኢትዮጵያውያን – ከእኛም በፊት የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ትውልዶች- በነፃነት ተጸንሰን፣ በነፃነት ተወልደን በነፃነትም ተጠልለን ኖረናል። የሰውን ልጆች እኩልነት የምትመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝባችንን የታሪክ ቅሬቶች፣ ሐውልቶችና የነፃነት ምልክቶች–የክብርና የማዕረግ ሀብቶቻችንን ስንንከባከብ ኖረናል። አገሪቱ ትኖር ዘንድ በሰንደቅ ዓላማቸው ሥር ተንበርክከው የፈጸሙትን መሐላ ያከበሩትን ጀግኖች በፈንታችን አክብረናቸዋል። በእስዋ ተመርተን ወደ ሞት አደባባዮች ነጉደናል። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ከሁለት መቶ ሺህ ከማያንስ ሠራዊትና መሪዎቻቸው ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አድዋ ዘምታ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ድል የሆነውን ግዳይ ተወጥታለች። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ እኛ ባለቤትዋ ሆንን እንጂ የዓላም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ አለኝታ ነበረች። ያስረዳሁ ይመስለኛል።

የዚያድ በሬ ወራሪዎች ያሳደዱአት አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የክብርና የአንድነት ምልክታችን በጐዴ፣ በካራማራ፣ በጅጅጋ በገላዲ…እንደገና ስትውለበለብ አይቻለሁ። በወረራው ወቅት የሶማሊያ እብሪተኛ ኅይል ባደረሰብን ጥቃት የተቃጠለና ያለቀሰ አንጀታችን ሰንደቅ ዓላማችን ዳግመኛ ስትውለበለብ እንደገና ማልቀሳችን ትዝ ይለኛል። አልፎ አልፎ እንደዚያ ያለ ጥቃት አይጠላም። ለነፃነትህና ለአንድነትህ ዘወትር እንደ ቆቅ ተጠንቅቀህ መቆምና መሞት ግዴታ መሆኑን እንዳትረሳ ያስገነዝብሃል።
የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ሲነሣ – አሁንም ተመስገን ደሳለኝ አነሳብኝና- ከውስጤ አንድ እሳተ ጐመራ መሳይ ነገር ሊፈነዳ ይደርሳል። ትዝታዎች አሉኝና። በኤርትራ በረሃዎች፣ ቅጥልጥል የሆኑ የመስሐሊት ሸንተረሮች፣ በሰሎሞና፣ በሸኢብ…ከኢትዮጵያ የአንድነት ሠራዊት ጋር የዘመቱት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰንደቅ ዓላማዎችን ዛሬ ዓይኔን ጨፍኜ አያቸዋለሁ። እዚያው ከሰንደቅ ዓላማው አጠገብ ክንዳቸውን እየተንተራሱ እየጣሉ የወደቁትን፣ በኋላም ነጭ የሰላም ዓርማ እያውለበለቡ እንኳ በፈሪዎች (ካወርድ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ጠንካራ መልእክት አለው) የተረሸኑት ኅልቁ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ። የብዘዎቹን አዛዦች አውቃቸዋለሁ። ለወረራ የተሰማራ ኅይል የለንም። ይልቁንም የኤርትራን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ፣ እያስጠበቀም ለመሞት በሰንደቅ ዓላማው “ምሎ” የተመመ ነበር። ተሳስተን ነበር ያለቅነው? ተሳስተን ነበር እንደወጣን የቀረነው – ሬሳችን የአራዊት ሲሣይ – የሆነው- ቀባሪ ያጣው….? የኤርትራ ሕዝብ ምነው አስቀድሞ ቢነግረን ኖሮ! በአርማጌዶን እንድንገናኝ ቀጠሮ መያዝ እንችላለን።

ከጥንት ጀምሮ- ለእኔ ጥንት ከሰባ ዓመት የማይበልጠው ነው- ከዚች ሰንደቅ ዓላማ ጋር የሚያስተሳስር ታሪክ አለኝ። የራሴ ትንሽ ታሪክ! ትንሽም ትዝታ። ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ውርስ-አረፍ ልዑልአየሁ የፋሺስቶችን እርግጫና ጡጫ ታስታውሳለች። በዚህ የተነሣ ዘወትር የአገር ልብስዋ ጥለት በሙሉ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። ይኸ ብቻ አይደለም። በአሥራ አራት ዓመቴ ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ከ17 ዓመት በፊት ወደ ስደቱ ዓለም እስክዛወር ድረስ በየዓመቱ ጋቢ ፈትላ ትልክልኛለች። ሌሎች ዘመዶቼ ጋቢ አስለምደውኛል። የወይዘሮ ውርሰአረፍ ጋቢ ግን ሁልጊዜ በአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ጥለት የደመቀ ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት (በሞት ያረፈችበት ዘመን) የመጨረሻውን ጋቢ ልካልኛለች። ታዲያ ይኽንን ልማዴን ታውቅ የነበረችው ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ይታይሽ ልዑልአየሁ “እቴቴን (ሟች እህታችንን) እንድታስባት ብዬ በእስዋ ምትክ ጋቢ ልኬልሃለሁ” ብላ ወደዚህ በመጣ ሰው አደራዋን ተወጣችው። አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ። ይቺኛይቱ እህቴም ወደ ታላቅዋ ዘንድ ሄደች። አላውቅም፥ ይገናኙ አይገናኙ። ለእኔ ግን ሰንደቅ ዓላማዬ ናፍቆቴ ሆኖአል። ተከናንቤው የምተኛው ጋቢ ባላጣም። (በነገራችን ላይ ውድ ወዳጄ ጐሹ ሞገስ በዚህ ረገድ ረስቶኝ አያውቅም።)

የኢትዮጵያ ድምፅ፣ በኋላ ደግሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ከበደ አኒሳ እንደ እናቴ ልጅ የምቆጥረው ነው። በንጉሡ ዘመን በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ አራት ሰዓት ላይ ይመጣና “ና ቡና ጠጥተን እንመለስ” ይልና ይዞኝ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በኩል ይነዳል። ልክ ቤተ መንግሥቱ አጠገብ ስንደርስ እኔም እሱም አንገታችንን አውጥተን ግቢውን እንቃኛለን። ሁለት የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ የብረት ምሰሶዎች አሉ። አንደኛው አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበት ነው። ሁለተኛው (አጠር ያለው) ደግሞ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ዓርማ መሐል አንበሳ አለው። ያ የጃንሆይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን እሳቸው በከተማው ከሌሉ አይውለበለብም። የንጉሠ ነገሥቱ በከተማው መኖር አለመኖር ምልክት ያ ነበር። ስለዚህ ትንታጉ ጋዜጠኛ ከበደ አኒሣ “ዛሬ ጀንሆይ በአዲስ አበባ ስለሌሉ መንግሥት በሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” ይልና ወደ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ሶደሬ ወዘተ እንከንፋለን። ብቻ በየሳምንቱ ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሰበብ የምናደርገው የጃንሆይን ሰንደቅ ዓላማ አለመውለብለብ ይሆንና “መንግስት ከሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” እያልን እብስ ማለት እንደ ባሕል ተያዘ። በእኛ ዘመን ቡድናችን (የእግር ኳሱ-አለዚያም ጊዮርጊስ) ቢያሸንፍም በደስታ፣ ቢሸነፍም በንዴት በቢራው ማዝገም የተለመደ ነበር። ስትናደድም ትጠጣለህ፣ ሲከፋህም ትጠጣለህ።

ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረች እነ ማርከስ ጋርቪ ሦስት ሺህ ጥቁር ወታደሮች መልምለው በክተት ተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። አጤ ኅይለሥላሴ የእንግሊዝን ጦር እየመሩ በመሄዳቸው ራስ ተፈሪያውያኑ ማርከስ ጋርቪና ራስ መኰንን (ራስታ) ጃንሆይን ተቀይመው እንደነበረ በወቅቱ ሲወራ ነበር። በጽሑፍም ቆይቶናል። ይቺን አገር- ይህን ሰንደቅ ዓላማዋን- ይህን ጐላ ያለ ታሪክዋን- ወደፊትም አውስተን የማንጨርሰውን- ትዝታዋን እነዚህ ሳንቀጣቸው ያደጉ፣ በማይምነታቸው የማያፍሩ ደፋሮች ይዘን መጓዙ ራሱ ሕመም ነው። ኅብረተሰብ ይጠይቀናል። ሰላምን በሰንሰለት፣ ዳቦን በባርነት የሚሸምቱ ሰዎች ዘመን ላይ መድረሳችን ይገርመኛል። ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ የሚያውቁአትና የሞቱላት ሰንደቅ ዓላማ መደፈር እንደ እብድ አድርጐአቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ። ወዲያው ጋዜጠኞች ሰብስበው ንግግር አድርገው አንድ ብዕር በሽልማት መልክ ሰጡኝ። እኔም ለዚች ሰንደቅ ዓላማ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንሁ- የሻለቃ አድማሴን ቃልም ምን ያህል እንደጠበቅሁ አላውቅም። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ያለ ጠባቂ መሆንዋ እውነት ነው። ያለ እስዋ ነፃነታችን ባዶ መሆኑ ይሰማኛል። ባለ አምባሻዋን የመለስን ድሪቶ አደራችሁን በምትክነት አናንሳው!

የነፃነት እጦት የሚመሰክረው የሰንደቅ ዓላማ መዋረድና የአገር መደፈር ምን ማለት እንደሆነ ዘላለማዊው ሐዲስ ዓለማየሁ “ትዝታ” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጠውታል። ራስ እምሩ፣ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ…በኢጣልያ ደሴት ታስረው በቆዩበት ጊዜ የቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ የባሕር ማዶ ቅኝ ግዛት ኅላፊ ራስ እምሩን እንዲያነጋግር ታዝዞ ይሄዳል። ቆፍጣናው መስፍን በመኝታ ቤታቸው ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ሰውየው ቆሞ ሲያናግራቸው ይሉኝታ የያዛቸው የእኛ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ወደየ ክፍላቸው ሊሄዱ ሲሉ ራስ እምሩ “ወንበር ልታመጡለት እንዳይሆን፤ እንዳታደርጉት” በማለት ቅኝ ገዥውንና የሀገሩ ባለቤት የሆነውን ባለሥልጣን አቁመው አነጋገሩት። በኢትዮጵያዊ ክብርና ኩራት እየተደበቡ “ ወዳጄ እኛ ዘንድ ምን አመጣህ?” ይሉታል። እሱም እንደ ባለስልጣን ሳይሆን እንደ አሽከር ቆሞ “ ግርማዊ የኢጣልያ ንጉሥ ኢማኑኤል ሳልሳዊና የመንግስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ያለዎትን ሀብት ንብረትዎን፣ ርስትዎንና ሌሎችንም እንደ ገንዘብ ያለውን ሀብትዎን ሊመልሱልዎ ወስነዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሊረከብልዎ የሚወክሉት ሰው ካለ ይነገረውና ይረከብልዎ!” ይላቸዋል።

የራስ እምሩ ቃል ለሰውየውም እዚያ ላሉትም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርኮኞች እስደንጋጭ ሆነባቸው። ባልተጠበቀው መልሳቸው ራስ እምሩ “የእኔ ሀብትና ንብረት የቀረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በተደፈረ- አገሬ በእናንተ በተረገጠች ጊዜ ነው። አሁን ሀብትና ንብረት የለኝም። ይህን የምትጠቅበውን ሀብትና ንብረት ለምትወድደው ሰው ልትሰጠው ትችላለህ።” ይሉታል። አጭር መልስ። ዲቦኖ፣ ባዶልዩ፣ ዱካ ዳውስታ፣ ግራዚያኒ፣ ፍራንካ..ወዘተ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መርገጣቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም። ይልቁን ቀደም እንዳልሁት ይቺው ሰንደቅ ዓላማ በኤርትራ ምድር እንዲያ ስትከበር በማንም ላይ በምንም ጊዜ ስላደረሱት ጥቃት ብዙም አልሰማንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን አምባገነን ሥርዓት አወረድሁ በሚል ግለሰብ ዓርማችን ስትናቅና ስትገፋ ለማየት ችለናል። የት? በጣይቱ ከተማ- በአዲስ አበባ! ባዕድና ጠላት፣ አስገባሪና ወራሪ የተባሉትም በዚህ ነው። የበላዔ ሰብን፣ የሒትለርንና የስታሊንን፣ የቀያፋን፣ የሔሮድስንና የጲላጦስን፣ የአስቀሮቱ ይሁዳን….ኅጢአት የደመሰሰ አምላክ ይሁነውና መለስ እንደ ገና ሲያላግጥብን ትልቅዋን ዓርማችንን ቡትቱ አስመስሎ ከማምጣቱም በላይ “የነፃነት ቻምፒዮን” ሆኖ ተከሰተ። ከቶውንም የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን እንደ ማካካሻ ሰጠን። ጥሩ ተጫውቶአል። እግዜር ይመስገነው በውጭ ያለነው ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር አልተለያየንም። እንደኔማ ቢሆን ሰው ሁሉ “ወፈፌ” ወይም የጀማመረው ካላለኝ በየቦታው ለብሼ ብሔድ ደስታዬ ነበር።

ለእኔ ሰንደቅ ዓላማዬ ሁሉንም ነች። የነፃነት ብሥራት፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ በክብር የመንጐራደድ ዋስትናዬ ናት። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካ ታጋይ ኅይሎች እየተመለከቱአት ቅኝ አገዛዝን ድባቅ የመቱባት ኅይል ናት። የአፍሪካ አገሮች ወደ ፍጹም አንድነት ይመጡ ዘንድ ታሪካዊ ጥሪ ያስተላለፈች ናት። ዛሬ ደግሞ ከወደቀችበት ትነሣለች። ሰው ሁሉ ኢትዮጵያን ቢክዳት “ኢየሩሳሌም ሆይ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ” ያለው አምላክዋ ወደ ክብርዋ ይመልሳታል። እንደ ተዋረድን አንቀርም። ወደ ታሪካዊ አንድነታችን በእርግጥ እንመለሳለን። አንዳንድ ደካማ “ነፍሳት” (አዎን “ነፍሳት”) የሚያናፍሱት መፍረክረክ ከንቱ ከንቱ…ሆኖ ያልፋል። አሜን አሜን!


ከባዶ ጭንቅላት ይሻላል ባዶ እግር ከነጻነት አድማሱ

አቡጊዳ –በባህር ዳሩ ሰልፍ ከሰባ ሺህ በላይ ሕዝብ ነበር። በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደረጋል (መግለጫ ከአንድነት)

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚሆን ሕዝብ ድምጹን ለማሰማት መዉጣቱ ገልጾ፣ ለባህር ዳር ሕዝብ ያለዉን አክብሮኢትና አድናቆት የካቲት 20 ቀን 2006 ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ።

ፓርቲ የባህር ዳሩ አይነት እንቅስቅሴ በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎችን እንደሚደረጉ ያሳወቀ ሲሆን በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሰጡና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

UDJ Press release on Bahir dar mass demonstration

አቡጊዳ –የአድዋ በዓል እንዳይከበር ኢሕአዴግ መሰናክል እየፈጠረ ነው

$
0
0

አንድነት/መኢአድ እና ትብብር፣ በጋራ የአድዋ ድልን ለማክበር ከአንድነት ጽ/ቤት ጀመሮ እስከ ጊዮርጊስ የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ፣ በሚኒሊክ ሃዉልት ሥርም አበባ እንደሚያስቀምጡ በመግለጽ ፣ በሕጉ መሰረት ፖሊስ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ቢያሳዉቁም፣ ኢሕአዴግ በሚቆጣጠረዉ የአዲስ አበበ አስተዳደር አማካኝነት «በዓሉ በብሄራዊ ደረጃ ስለሚከበር ማስተናገድ አንችልም» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

addis_council

ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ የአድዋ በዓል፣ በኢሕአዴግ ዘመን፣ ከዚህ በፊት የተከበረበት ሁኔታ ብዙ እንዳለነበረ ይታወቃል። አገዛዙም አሁን በምን መልኩ በዓሉን ለማክበር እንዳቀደ ያሳወቀው አንዳች ነገር የሌለ ሲሆን፣ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ሌሎች ሲዘጋጁ፣ አብሮ ተቀላቅሎ ማክበር እንጂ ፣ መሰናክል መሆን እንዳልነበረበት ብዙዎች ይናገራሉ።

«አድዋን ለማክበር ስለፈለገ አይደለም። አገዝዙ መሰናክል እየፈጠረ ያለው» ያሉን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ፣ በአዲስ አበባ ሰልፍ መደረጉ ስለሚያስፈራው እንደሆነ ይናገራሉ። «የአንድነት ፓርቲ በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች መዋቅር አለው። በተጨማሪ መኢአድ እንዲሁም የአሥር ድርጅቶች ስብስብ የሆነው ትብብር አብረዉት አሉ። ስለዚህ አንድነት በሚጠራቸዉ ስልፎችና ስብሰባዎች ብዙዎች እንደሚገኙ የታወቀ ነዉ » ያሉት እኝህ ተንታኝ «ቢሆንም እስከአሁን በአንድነት በየቦታዉ የተደረጉ ሰልፎች ሁሉ ሰላማዊ ነበሩ። አንዲት ጠጠር አልተወረወር፣ የጠፋ ሕይወት፣ የወደመ ንብረት የለም። ሰልፈኛው በሰላም ወጥጦ ነው በሰላም የተመለሰው» ሲሉ የሕዝቡ ሰላማዊነት በማስረዳት አገዛዙ መፍራት እንደሌለበት የናገራሉ።

የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በኋላ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጥ የሚገልጽ መረጃ እስከአሁን አልደረሰንም።

የሸንጎ ድምጽ ቅጽ 3 ፣ ቁ1

አቡጊዳ –ኢቲቪ ስለባህር ዳሩ ሰልፍ የዘገበው የጅምናስቲክ ዘገባ

$
0
0

ኢቲቪ የሕዝብ ሜዲያ ነው። በሕገ መንግስቱ መሰረት ለኢሕአዴግ ሳያደላ ገለልተኛ በሆነ መንገድ እዉነትን መዘገብ ነበረበት። ነገር ግን ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚጠጋዉ ሕዝብ የተገኘበትን ታሪካዊ የባህር ዳሩን ሰልፍ አሳንሶ ለማቅረብ፣ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ፣ ሁሉም ወደ የሰፈሩ በሚሄድበት ጊዜ የተነሱ ፊልሞችን በማሳየት፣ ወደ ሰማኒያ ሺህ የሚጠጋዉን ሕዝብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል የተሞከረበት ሁኔታ ነዉ፣ በኢቲቪ የታየው። pic5

በስብሰባው የመኢአድ እና የአንድነት ሊቀመንበር ከተናገሩትም ቀንጨብ አድርገው አሰምተዋል። ኢንጂነር ግዛቸው ሰልፉን ሲጠብቁ የነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት አመስግነው ነበር: ነገር ግን ኢቲቪ ለትራፊክ ፖሊሶች የተሰጠውን ምስጋና ለአስተዳደሩ እንደተሰጠ አደርጎም ለማቅረብ ኢቲቪ ሞክሯል።

«ሕዝብ ሁሉ ያየዉን ቀይረው ይህ አይነት ዉሸትና ማጭበርበር ለማድረግ መሞከራቸው፣ ሕዝቡ ምንም የማያውቅ ደካማ አደርገው እንደቆጠሩትና እንደናቁት የሚያሳይ» ነው ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ «እራሳቸውን በ እንዲህ ሁኔታ ከሚያስገምቱ ፣ ዝም ቢሉ ይሻላቸው ነበር» ሲሉም ዘገባውን አሳዛኝ ፣ አሳፋሪና የኋላ ቀር ብለዉታል።


እስቲ የኢቲቪን የማጭበርበርና የጂምናስቲክ ዘገባ ይመልከቱ !

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>