Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ተራ ኢትዮጵያዊ መሆናችንን አንናቀው ! ግርማ ካሳ

$
0
0

አገሬን ለቅቄ ስደት የጀመርኩት በ1984 ነዉ። ኢሕአዴግ ስልጣን በጨበጠ በአንድ አመቱ። ከአስራ አራት አመታት በኋላ ለአንድ ወር ጉብኘት ቦሌን ረገጥኩ። እሑድ ቀን ፣ ግንብት ሰባት 1997 ነበር።

ከዚያ በፊት ብዙም የፖለቲካን ነገር አልከታተለም ነበር። ምርጫ እንደሚደረግ፣ ቅንጅት ሕብረት እየተባለ የምርጫዉ ዘምቻ እንደተጧጧፈ ያወኩት ትኬት ከቆረጥኩ በኋላ፣ ከምርጫዉ 15 ቀናት በፊት ነበር። በአጭሩ አባባል፣ በአገሬ ዉስጥ እየተደረገ ከነበረዉ ሁኔታ የተለየዉ፣ ዲስኮንቴክትድ የሆነ ነበርኩ ማለት ይቻላል።

በወቅቱ የነበረዊ አንጻራዊ ዴሞክራሲ አስደሰተኝ። ቅንጅት አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ አሸነፈ። ከሌሎች ቦታዎች የሚመጡም ዉጤቶች ቅንጅቶችን የሚያስደስት ነበሩ። በዚህ ጊዜ ችግሮች መፈጠር ጀመሩ። ኮሮጆ መቀየር የመሳሰሉት። አገሪቷ ወደ ቀውስ መግባት ጀመረች።በየቀኑ ጋዜጦችን እገዛለሁ። (አዲስ ዘመንን ግን ገዝቼ አላወቅም) የምወዳት ቡና ቤት ነበረች። ካፌ ማሩ ትባላለች። ቡናዬን ይዤ ጋዜጦችን አነባለሁ። አንድ ቀን እንደለመድኩት ገዝቼ ሳገላብጥ፣ ሁሉም የአንዲት ሴት ልጅን ፎቶ፣ በትልቁ አውጥተዋል። በቆምኩበት እንባ ይፈሰኝ ጀመር።

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። በኮተቤ አካባቢ በተነሳዉ ሕዝባዊ ሰላማዊ ተቃዉሞ፣ ከኢሕአዴግ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይቅ ተመታ የወደቀች። ሽብሬ ደሳለኝ ትባላለች። የዘጠና ሰባቱ ምርጫ የመጀመሪያዋ ሰላባ። ይሄን ጊዜ የ23 አመት ሴት፣ ምናልባትም የልጅ እናት ትሆን ነበር። ሽብሬን መቼም ቢሆን አልረሳትም። ስምንት አመት ቢሆነኡም፣ በርሷ ላይ የተፈጸመው፣ ትላንት እንደተፈጸመ አድርጌ ነዉ አሁን የማስበው።

ጋዜጦቹን አንብቤ እንደጨርስኩ፣ ወደ ሜክሲኮ በእግሬ አመራሁ። ሌላ አስደንጋጭና አሳዛኝ ክስተት የዚያኑ ቀን አጋጠመኝ። ነጭ መስታወት ቢጤ በፊታቸው ባደረጉ ፖሊሶች፣ የተግባረ እድ ተማሪዎች ይደበደቡ ነበር። በሰደፍ ሲመቷቸው በአይኔ በብረቱ ተመለከትኩ። ዉስጤ ተቆጣ። «እንዴት ዜጎች በአገራችዉ እንደ ከብት ይደበደባሉ ? » አልኩ። ያኔ ወሰንኩኝ።

እርግጥ ነዉ፣ እኔ ላይ የደረሰብኝ ነገር የለም። በአሜሪካን የስደት ኑሮ ጀምሬ፣ በሁሉ መስክ ደህና ሁኔታ ላይ ነዉ ያለሁት። እግዚአብሄር ይመስገን። ነገር ግን አሜሪካ እና ኢትዮጵያ አንድ ስላልሆኑ፣ በኢኮኖሚ እንደ እኔ ለምን አይሆንም ባልልም፣ እኔ እንደ ኢሚግራት በአሜሪካን አገር ያለኝን መብትና ዲግኒቲ፣ ጥቂቷን እንኳን ወገኖቼ በአገራቸው ማጣቸውን ሳሰበዉ ዉስጤ ቆሰለ። ያንንም መቀበል ከበደኝ። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊ መብት እንዲከበር ፣ ዜጎችን የመደብደብ፣ የማሰር፣ የማፈናቀል ተግብራት እንዲወገዱ፣ ዉጤት ያምጣም አያምጣም፣ ማድረግ ያለብኝ ሁኑ ለማድረግ ወንንኩ። ለራሴ ቃል ገባሁ።

በብዙ ሺሆች እንደሚቆጠሩ የቅንጅት ደግፊዎች፣ እኔም የቅንጅት ድጋፍ ማህበራትን ተቀላቀልኩ። ምርጫ ቦርድን በመጠቀም፣ የ«ቅንጅት» ሕጋዊ ስም ለነ አየለ ጫሚሶ ቡድን ፣ ገዢው ፓርቲ በመስጠቱ፣ ቅንጅቶች በቅንጅት ስም መንቀሳቀስ ስላልቻሉ «አንድነት» የሚል ስም ይዘው ትግሉን ቀጠሉ። የቅንጅት ድጋፍ ማሀብራትም ወደ አንድነት ድጋፍ ማህበራት ተቀየሩ። የቅንጅት ወራሽ የሚባለዉን አንድነትም መደገፍ ቀጠልን።

የአንድነት ፓርቲን በመደገፍ የማደርጋቸውን አንዳንድ ተግባራት የታዘበ፣ ቅንጅትን ይደገፍ የነበረ አንድ ወዳጄ «ተቃዋምዊዎች የሚረቡ አይደሉም። ለምን ጊዜህን በነርሱ ላይ ታጠፋለህ ? ያኔ ስትደክመለት የነበረዉ ቅንጅት እንኳን ፈራርሶ የለም እንዴ ? » አለኝ።

ይህ አባባል ብዙዎች የሚሉት አባባል ነዉ። ብዙ ጊዜም ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ እንዲህ አይነት አስተያየቶች አንብቢያለሁ። «ቅንጅት ፈርሷል» የሚለዉን አባባል ግን በጭራሽ አልቀበለም። የቅንጅት ስም ላይኖር ይችላል። አሁን «ቅንጅት» ላንል እንችላለን። ያኔ የቅንጅት መሪ የነበሩ፣ ያኔ በነበሩበት ሁኔታ ላይኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ያኔ ቅንጅትን ቅንጅት ያሰኘው፣ ከምርጫ ቦርድ የተገኘ ስም፣ ወይንም መሪዎቹ አለነበሩም። ሕዝቡ ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብት መከበርና ለኢትዮጵያዊነት የነበረዉን ግለትና ጥማት ማመላከቱ እንጂ። የቅንጅት ነገር፣ በዋናነተና በቀዳሚነት የተገናኘዉ ከሕዝብ ጋር ነበር። ስለዚህ «ቅንጅት ፈርሷ”» ማለት «ሕዝብ ተመችቶታል፤ ሕዝብ ደልቶታል፣ ሕዝቡ መብቱ ተከበሮለታል …. » እንደማለት ነዉ።

አሁንም የሕዝቡ ጥያቄ ያኔ የነበረዉ ጥያቄ ነዉ። አሁንም ህዝብ «የፍትህ ያለ ፣ የሰላም ያለህ፣ የሕግ በለያነት ያለህ፣ የመልካም አስተዳደር ያለህ» እያለ ነዉ። አሁን ሕዝብ «የዘር ፖለቲክ አልፈለግም፣ ኑሮ ተወደደ፣ ቀንበር በዛብኝ ፥» እያለ ነዉ።

ለምሳሌ ያኔ በቅንጅት ስም ይደረግ የነበረዉ እንቅስቃሴ አይነት፣ በሚሊዮኖች ለነጻነት ድምጽ በሚል እንቅስቃሴ ሥር ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተፋፋመ ነዉ። የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ በባህር ዳር ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። የሚሊየምም ድምጽ ለነጻነት ክፍል ሁለት በቅርቡ ይታወጃል ተብሎ ይጠበቃል። መርሳት የሌለብን ደግሞ፣ እነዚህ አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን፣ ይህን አይነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉት፣ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ ከሥራቸው እየተባረሩ ወዘተረፈ ነዉ። ፈረንጆች እንደሚሉት፣ “They are not talking the talk; they are walking the walk”::

ያኔ ቅንጅትን ስንደገፍ የነበርን፣ በጥቂት መሪዎች ስህተት፣ ተስፋ ቆርጠን ፣ ኢሕአዴግን እንደ ግዙፍና የማይነቃነቅ አድርገን ማየት የጀመርን፣ ከትግሎ ጎራ የሸሸን በጣም ብዙ ነን። ትግሉን የጎዱ፣ የሕዝቡን ኃይል አሳንሰው፣ ተስፋቸዉን በሌሎች አገሮች ላይ የጣሉ ግለሰቦችንና የፖለቲክ መሪዎች ላይ በማተኮር ወደ፣ ወደ ኋላ የተጎተትን ብዙ ነን። ነገር ግን ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን፣ እነ እስክንደር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ ናትናኤል መኮንን የመሳሉትን እናስብ እላለሁ። ተስፋ መቁረጥ፣ በቀላሉ አቅጣጫችንን መቀየር፣ ሌሎችን ደካም ማለት፣ እጅ አጣምሮ እያወሩ መቀመጥ ቀላል ነዉ። የአላማ ጽናት ኖሮ፣ የደከሙትን እያገዙ፣ የሥራ ሰው መሆን ግን ከባድ ነዉ።

እንግዲህ በቅንጅት ወቅት አኩሪና ትልቅ ሥራ እንሰራ ለነበርን፣ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፣ እንደገና ጽናቱ ይኖረን ዘንድ፣ አክብሮት የተሞላበትን ጥሪዬን አቀርባለሁ። «አንተ ምንድን ነህና ነው እንደዚህ አይነት ጥሪ የምታቀርበው ? ልትሉኝ ትችላላችሁ። አዋ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ወይንም የአንድ ድርጅት ሃላፊ አይደለሁም። እንደ ማናችሁም ፣ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ነገር ግን አንድ ነገር አውቃለሁ። እንደኔና እንዴናናት ያሉ ተራ ኢትዮጵያዉያኖች ናቸው ለኢትዮጵያ መፍትሄ የሚሆኑት። በዳያስፖራ ያሉ በሜዲያዉ የምናያቸውና የምንሰማችደው ጥቂት የታወቁ ሰዎች ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተራ ኢትዮጵያዉያን ሲንቀሳቀሱ ነው የኢትዮጵያን ትንሳኤ ማወጅ የምንችለው።

ዉድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ ወደ ቀድሞዉ ቦታችን ተመልሰን፣ ከስሜትና ከጥላቻ በጸዳ መልኩ፣ ሕዝባችን መብቱ እንዲከበር የሚያደርገዉን ትግል እንደገፍ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ ፌስቡክ ላይክ በማድረግ፣ እየተሰራ ያለዉን ነገር ይከታተሉ። የአንድነት ድህረ ገጽን በመጎብኝት የገንዘብ ፣ የሃሳብ ድጋፎዎትን ያበርክቱ።

https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

http://www.andinet.org/


የጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ቆይታ ከልማታውያን ጋዜጠኞች –አቢዩ ጌታቸው

$
0
0

ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ ነጋዴ፣ ልማታዊ መመህር፣ ልማታዊ ሃኪም፣ ልማታዊ ቄስ፣ ልማታዊ ሼክ—- ልማታዊ የሚል መዳልያ ከኢህኣዴግ የሚገኝ ትልቅ የክብር ሽልማት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ኣይነት ሽልማት የሚሰጣቸው የተወሰኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ኢህኣዴግ በህዝብ ላይ የፈለገውን አፈና ሲፈፅም ፣ የሃገር ኢኮኖሚ በሙስና ሲበዘብዝ ለምን ያማይሉ፣ ለሂሊናቸው ሶይሆን ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ለታሪክ ደንታ ቢስ የሆኑ ሁሉ በኢህኣዴግ የተዛባ ሚዛን ልማታውያን ናቸው፡፡

ሁላችን እንደ ተከታተልነው 04/06/06 ዓ/ም ከሁለት ሰዓት ዜና በኃላ ጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ እነዚህ ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ጋዜጠኞች ጠርተው የቼዝ ጭዋታ (chess play) በማካሄድ ሰዓታቸውን ኣሳልፈዋል፡፡ በዛ ጭዋታ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ስለነበሩ ሲያቀርብላቸው የነበሩ ጥያቄዎችም ልማታውያን ናቸው፡፡ ነገር ግን ኣንድ ሁለት የሚሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በተለይ ስለ መብራት ማቋረጥ፣ ወሃ እጥረት፣ የሞባይል ኔትወርክ ችግር፣ ስለነጋዴዎች ስጋት፣ ስለኢኮኖሚያዊ ሁኔታና ስለሚቀጥለው ምርጫ ዝግጅት — ወዘተ መጠየቃቸውና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ኣራባና ቆቦ የሆነ መልስ እንደ ተሰጣቸው ጆራችን ሰምተዋል፡፡

ስለሚቀጥለው ምርጫ የተነሳ ጥያቄ ሲመልሱ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በሚቀጥለው ምርጫ ወደ ፓርላማ እንዲመለሱ ምን የታሰበ ነገር ኣለ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ “የሚወዳደር ኣካል ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለበት ካልሆነ በኢህኣዴግ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች የሚሰጥ ትሩፋት ኣይኖርም” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ጥያቄው ግልፅና የማያሻማ ነበር፡፡ የጋዜጠኛዋ ጥያቄ ኣሁን ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ (በጣም ጦቦ) ወይ ደግሞ ኢህኣዴግ በራሱ ልክ የሰፋው የፖለቲካ ምህዳር ትንሽ ይሻሻል ወይም ቀዳዳ ይፈጠርለት ይሆን? እንዲሁም ተቋዋሚዎች በሄዱበት ሁሉ እየተከታተሉ ማዋከብና በፈጠራ ክስ ማሰርና ማስፈራራት ይቀንስ ይሆን ማለ~ ነው እንጂ በምርጫ ጊዜ በየትም ሃገር በገዢ ባርቲ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች እንደ ዳቦ የሚከፋፈል ትሩፋት ወይ የፓርላማ ወንበር እንደሌለና ሊኖርም እንደማይችል ጠፍቶባት ኣይደለም ጥያቄው ያቀረበችላቸው፡፡

“የሚወዳደር ፓርቲ ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለባት” ብሎዋል ጠ/ሚ ሃ/ማርያም፡፡ ጥሩ ኣባባል ነው፡፡ ነገር ግን በምን መልኩ መዘጋጀት እነደሚችሉ ቢነግ[ቸው ጥሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም፡

1/ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠቅመው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ በእርስዎና የእርስዎ ተከታዮች በተከለከሉበት ወቅት (ለምሳሌ ያኣንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ኣመራሮችና ኣባላት በክልሎችና በተለይ በኣዲስ ኣበባ ይህንን በመሞኮራቸው ስንቴ ታስረዋል ስንቴ ተደበድበዋል)፡

2/ ህዝብ በመሰብሰብ ኣላመቸውን ለማስተዋወቅ ፍቃድና መሰብሰብያ ኣዳራሽ ለጠየቁ ፓርቲዎች በእርስዎና በእርስዎ ተከታዮች ኣንዴ የሚጠብቅ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ኣንዴ ደግሞ ስራችን እያስፈታችሁን ነው በሚል ተልካሻና ኣስገራሚ ምክንያት በሚከለከሉበትና በሚታሰሩበት ይባስ ብሎም 5 ኪሎ ስንዴና ኣንድ ሌትር ዘይት ከቀበሌ በሚሰጣቸው ኑሮዋቸው በሚገፉ በኣንድ ለ5 ኔትወርክ ያታቀፉ የቀበሌ ሴቶችና ምንም ያማያውቁ ከእድሜ በታች የሆኑ ልጆች ሰብስባችሁ እንሰዲሰድብዋቸውና እንዲደበድብዋቸው እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ የዓረና ፓርቲ አመራሮችና ኣባላት በታህሳስና በጥሪ ወር በሽሬ፣ በዓዲ ግራትና በሑመራ) ፈሪውን ህ.ወ.ሓ.ት/ኢህኣዴግ ያደረገውን ኣፈና፡

3/ በሃገራችን ፖለቲካ ላቅ ያለ እውቀት ያላቸውና ለፖለቲካዊ ለውጥ ቆራጥ ኣቋም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፈጠራ ክስ የፈረዳችሁባቸውና እያስፈራራችሁባቸው ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ በዚህ ሳምንት ያአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑ ኣቶ አስራት ጣሴና ወጣት ደራሲና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ)፡

4/ የተቋዋሚ ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው በምክንያት እንዲባረሩና እንዲዋከቡ እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ፡
5/ የሃገሪቱን መገናኛ ብዙሃን 24 ሰዓት በቁጥጥራችሁ ውስጥ ኣስገብታችሁ ለግለ ሰብና ለፓርቲዎች ስም ማጥፋት ዘመቻ በምታወልበት ሃገር፡

6/ ዜጎች የፈለጉትን ሃሳብ እንዳይገልፁና የፈለጉትን የፖለቲካ አቋም እንዳይኖራቸው በ1 ለ5 የስለላ ኔትወርክ ሰርታችሁ ነፃነቱ በነጠቃችሁት ህዝብ በአጠቃላይ መንግስት የመንግስት ስራ ትቶ የፓርቲ ስራ በሚሰራበትና መንግስት መንግስትነቱን ትቶ የተራ ሽፍታ ስራ በሚሰራበት ጊዜ እንዴት ኣድርገው ነው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ራሳቸው ለውድድር መዘጋጀት የሚችሉት?

ሌላው ጠ/ሚ ደጋግመው ሲሉት የነበረ ጉዳይ ስለ ምርጫ ሂደት ነው፡፡ “ምርጫው ልክ እንደ ቅድሙ ሁሉ ነፃ፣ ፍትሓዊ፣ ዲሞክራስያዊና በህዝቡ ላይ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን እንደ መንግስት በቂ ዝግጅት እናደርጋለን” የሚል ኣስገራሚ ኣባባል ነበር፡፡
መቼ ነው ኢህኣዴጎች ከረጆ ከመስረቅ (ከመቀየር)፣ የተቋዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎ ኣስፈራርቶ ከማባረር፣ ህዝብ በነፃነት እንዳይመርጥ ከማስፈራራትና ከመደለል እንዲሁም ከማደናገር ኣልፋችሁ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄዳችሁት? መቼ ነው በህዝብ ላይ ተኣማኒነት ያተረፈ ምርጫ ከንግግር ኣልፎ በተግባር የተደረገው?
በ1997 ዓ/ም ኣንፈልጋችሁም ብሎ ድምፁ ለነፈጋችሁ የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ጥይት ያጎረሳችሁት ረስታችሁታል ማለት ነው? የወጋ ቢረሳ የተወጋ ኣይረሳምና ጠ/ሚ ሃ/ማርያም በኣጠቃላይ ኢህኣዴጎች የምትናገሩትና የምትሰሩት ፍፁም ስለማይገናኝ ይህ ኣይነት ቁማር በመጨረሻ ላይ ለናንተም ጠቃሚ ስላልደለ የኢትዮጵያ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ የፈለገውን ሃሳብ በነፃነት እንዲያራምድ፣ እንዲሰበሰብና ኣቋሙ በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልፅ ብትፈቅዱለት ጥሩ ነው፡፡ ካልሆነ ህዝብ ኣፍነህ ለመግዛት መመኮር የቱንዝያ፣ የግብፅና የሊቭያ የቀድሞ ዲክታተር መሪዎች መጨረሻ ላይ እንዳላማረባቸው ከዚህ ይማረን እያላችሁ ስትከታተሉት የነበረ የትናንት ሓቅ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ትእግስተኛና ኣስተዋይ በመሆኑ እስካሁን ትእግስቱ ኣማጥጦ በመጠቀም የታገሰ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን ትእግስት መጠን ኣለው፡፡ ስለዚ ትናንት ነገ ስለማይሆ ትእግስቱ ተማጥጦ እንዲያልቅ ባትገፋፉት ጥሩ ይመስለኛል፡፡
በሃይል ለመግዛት መሞከር የውድቀት ምልክት ነው!!

አዲስ አድማስ –ልጓም ያልተገኘለት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

$
0
0

«መንግስት የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት አለበት» (ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ)

«ባለፉት 8 ዓመታት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል»
«የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መንግስት ለዜጎቹ ግድ ማጣቱን አመላካች ነው፡፡» (የከተማዋ ነዋሪ)

የስምንት ዓመት የዋጋ ንረት
1998 2006
ቤንዚን 6.57 20.47
ነጭ ጋዝ 3.45 15.75
ታክሲ (አጭር ርቀት) 0.60ሳ 1.50
ታክሲ (ረዥም ርቀት) 1.25 3.00
አንበሳ አውቶብስ 0.50ሳ 300% ጭማሪ

አቶ መስፍን ወርቅነህ በመንግስት መ/ቤት የንብረት አስተዳደር ክፍል ውስጥ ተቀጥረው መስራት ከጀመሩ ወደ 18 ዓመት ገደማ አስቆጥረዋል፡፡ ሥራ ሲጀምሩ የወር ደመወዛቸው 720 ብር ነበር፡፡ በሥራ ዘመናቸው ለሦስት ጊዜ ያህል የደረጃ ዕድገቶችና የደመወዝ ጭማሪ ዕድሎችን አግኝተዋል፡፡ በ18 ዓመት ጊዜ ውስጥ ደሞዛቸው 1690 ብር ደርሷል፡፡

ከ15 ዓመት በፊት ትዳር የመሰረቱት በ280 ብር ከግለሰብ በተከራዩት ቤት ውስጥ ሲሆን ሦስት ልጆቻቸው የተወለዱትም እዚሁ ቤት ውስጥ ነው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አከራያቸው ድንገተኛ የሃምሳ ብር ጭማሪ ሲያደርጉባቸው ክው ብለው ደነገጡ፡፡ የከተማው ዳርቻ አካባቢ አነስተኛ የኪራይ ቤት ማሰስ ጀመሩ።

በመጨረሻም አየር ጤና የተባለው ሰፈር በ200 ብር የኪራይ ቤት አገኙና ቤተሰባቸውን ይዘው ገቡ፡፡ አቶ መስፍን ከከተማ ወጣ ብለው ቤት የተከራዩት፣ወጪያቸውን በመቀነስ የሚያገኟትን ደሞዝ አብቃቅተው ሦስቱን የአብራካቸውን ክፋዮች ሳይርባቸው ሳይጠማቸው አሳድጋለሁ በሚል ነበር፡፡ ጊዜው ግን ከእሳቸው ጋር እልህ የተጋባ መሰለ፡፡ ከዓመት ዓመት ኑሮው ወደ ላይ ይተኮስ ጀመረ ይላሉ፤ አዛውንቱ፡፡

ከአየር ጤና ካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ እሚገኘው መ/ቤታቸው ለመድረስ ሁለት አንበሳ አውቶቡሶችን መጠቀም ነበረባቸው፡፡ የአንድ ቀን የደርሶ መልስ ወጪያቸው 3 ብር ሲሆን በወር 80 ብር ገደማ ለትራንስፖርት ያወጣሉ፡፡ አንዳንዴ ከረፈደባቸው ወይ ከቸኮሉ ከ5-6 ብር ለማውጣት ይገደዳሉ – በታክሲ ለመሄድ፡፡

የቤታቸውና የመሥሪያ ቤታቸው ርቀት ለምሣ ወደቤት መሄድን ፈፅሞ የሚያሳስብ አይደለም፡፡ መ/ቤታቸው አቅራቢያ ባለች አነስተኛ ምግብ ቤት ከ8-10 ብር እያወጡ ምሳቸውን የሚመገቡት አቶ መስፍን፤ የምሳ ወርሃዊ ወጪያቸው ከ180-200 ብር ይደርስ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡

በልጆች ት/ቤት በኩል የተገላገሉ ይመስላሉ። ሁሉም በመንግስት ት/ቤት ነው የሚማሩት፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን በአመቱ መጀመሪያ ላይ ለትምህርት መሳሪያዎችና ለዩኒፎርም ማሰፊያ የሚጠየቁት ገንዘብ ወገብ ይቆርጣል። የቱንም ያህል ፈተናና ውጣ ውረድ ቢበዛባቸውም ሁሉን ተቋቁመው ወደፊት እንዲጓዙ የሚያደርጋቸው ተስፋቸው ነበር፡፡ መቼም ቢሆን የተሻለ ነገን ከማለም ቦዝነው አያውቁም፡፡ አስደንጋጩ የኑሮ ውድነት ግን ህይወታቸውን አጨለመባቸው፡፡ ህልምና ተስፋቸውን ነጠቃቸው፡፡

ለኑሮ ውድነቱ መባባስ፣ ለሸቀጦች ዋጋ መናር፣ ለትራንስፖርት ዋጋ በሁለትና ሦስት እጥፍ መጨመር፣ ለነዋሪው ኪስ መራቆት፣ ለችግርና ጉስቁል መጋለጥ፣ ወዘተ… ሰበቡ ልጓም ያጣው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ነው። ሌላው ቀርቶ መንግስት እንኳ በሰፊ እጁ ስላለቻለው “ድጎማውን ትቼ አለሁ” ብሎ በይፋ እጅ ሰጥቷል። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ የአቶ መስፍንን ህይወት ብቻ አይደለም ያናጋው፡፡ እንደሳቸው ያሉ ሚሊዮኖችን ኑሮ አቃውሷል፡፡ የሚሊዮኖችን ከእጅ ወደ አፍ ኑሮም አዛብቷል፡፡

አቶ መስፍን፤ ከ10 ብር በማይበልጥ ዋጋ ምሳቸውን ይበሉበት የነበረው ምግብ ቤት፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ዓይናቸው እያየ 40 እና 50 ብር ገባ፡፡ የዛሬው ብቻ ሳይሆን የነገው ጭምር ያሳስባቸው ጀመር፡፡ “አንዳንዴ የምንኖረው በተአምር ነው የሚመስለኝ፤ ምኑ ተምኑ ተደርጐ ከወር ሊደርስ እንደሚችል ማሰቡም ከባድ ነው፡፡ ተዉኝ እባካችሁ… ለዜጎች ግድ ያጣ መንግስት ነው ያለን፡፡ ብናልቅስ ምን ገዶት ብላችሁ!” ይላሉ አቶ መስፍን – የኑሮ ውድነቱ የወለደውን ብሶታቸውን ሲተነፍሱ፡፡

የአለማቀፉን የነዳጅ ዋጋ ውጣ ውረድ ተንተርሶ፣ የንግድ ሚኒስቴር በወሩ መጨረሻ የሚያወጣው የነዳጅ ዋጋ ክለሣ፣ በ8 አመት ውስጥ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩን ያመለክታል፡፡ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ከግንቦት 1998 ዓ.ም ጀምሮ በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የአለማቀፉ የነዳጅ ዋጋ፣ በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ተመን ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳርፏል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ የበርሜል ነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ በዚያው ዓመት በተደረገው የዋጋ ክለሣ፣ የአዲስ አበባ የተራ ቤንዚን መሸጫ ዋጋ፣ በሊትር 6 ብር ከ57 ሣንቲም ገደማ የነበረ ሲሆን ታሪፉ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደገና ተሻሽሎ በታህሳስ 1999 ዓ.ም 7 ብር ከ75 ሳንቲም ሆነ፡፡ በ8 ወር ጊዜ ውስጥ በሊትር እስከ 1ብር ከ20 ሣንቲም የሚደርስ ጭማሪ ተደርጓል ማለት ነው፡፡ በወቅቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በህብረተሰቡ የእለት ተእለት ኑሮ ላይ የጐላ ጫና አሳርፏል ለማለት ባያስደፍርም፣ ጭማሪው ቀደም ካሉት አመታት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ ነበር፡፡

ከአመት በኋላ በንግድ ሚኒስቴር በተደረገው ክለሳ፣ የነዳጅ ዋጋ ወደ 9 ብር ከ60ሣ. አድጓል፡፡ ከቀድሞው ዓመት 1 ብር ከ85 ሣንቲም ጭማሪ በማሳየት ማለት ነው። የ2001 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ ደግሞ ቀደም ካለው ዓመት 1 ብር ከ40 የሚደርስ ቅናሽ እንዳሳየ የሚኒስቴር መ/ቤቱ መረጃ ይጠቁማል፡፡ ሰኔ 2001 የተከለሰው የነዳጅ ዋጋ እንደሚያመለክተው፤ ቤንዚን በሊትር 8 ብር ከ95 ሣንቲም ገደማ ሲሆን ከሁለት ወር በኋላ በጳጉሜ 2001 በተደረገው ክለሳ፣ አዲስ አበባ ላይ በሊትር የ2 ብር ገደማ ጭማሪ በማሳየት ወደ 10 ብር ከ93 ሣንቲም ተመነደገ፡፡ ከአንድ አመት በኋላ በህዳር 2003 ዓ.ም በከፍተኛ ሁኔታ ያሻቀበው የቤንዚን ዋጋ፣ 14 ብር ከ87 ሣንቲም የደረሰ ሲሆን ከአምስት ወር በኋላ በአብዛኛው የክልል ከተሞች በሊትር ከ22 ብር በላይ ሲሸጥ፣ በአዲስ አበባ የ6 ብር ጭማሪ ተደርጐበት በሊትር 20 ብር ከ94 ሣንቲም ገባ። ይህም በ8 አመት ውስጥ በጥቂት ወራት ልዩነት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየበት ወቅት መሆኑን ያመለክታል፡፡

2004 እና 2005 ዓ.ም ከሌሎቹ አመታት በንፅፅር የነዳጅ ዋጋ የተረጋጋበት ወቅት ነበር፡፡ መጠነኛ ቅናሽም አሳይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ ከ18 ብር ከ75 ሣንቲም እስከ 19 ብር ከ45 ሣንቲም ባለው ዋጋ መካከል ሲዋልል ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ በ2006 ዓ.ም የየካቲት ወር የቤንዚን ዋጋ በሊትር 20 ብር ከ47 ሣንቲም ተተምኗል፡፡
በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል፣ እንደ እለት ተእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ነጭ ጋዝ (ላምባ)፤ በ1998 አዲስ አበባ ላይ በሊትር 3 ብር ከ45 ሲሸጥ፣ በየካቲት 2006 ዓ.ም 15 ብር ከ75 ሣንቲም እየተሸጠ ነው፤ በአምስት እጅ ጨምሮ፡፡

የንግድ ሚኒስቴር ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በየወሩ መጨረሻ ላይ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣንም የትራንስፖርት ዋጋ ማሻሻያ እያደረገ ነው፡፡ የታሪፍ ጭማሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሃይገር ባሶች፣ የከተማ አውቶቡሶችና ታክሲዎችን የሚመለከት ሲሆን አንበሳ አውቶቡሶች ከ0.50 ሳንቲም ታሪፍ ተነስተው እንደየርቀታቸው ከ300% በላይ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ በ1998 ዓ.ም የአጭር ርቀት የታክሲ ተመን 65 ሳንቲም፣ የረዥም ርቀት 1.25 ሳንቲም የነበረ ሲሆን አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ክፍያው ወደ 95ሣ. እና 1.65 ሳንቲም ከፍ ብሏል፡፡

በየጊዜው በሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ መሠረትም ታሪፉ እየጨመረ ሄዶ፣ በያዝነው የካቲት ወር የአጭር ርቀቱ 1.50 ሳንቲም፣ ረዥም ርቀቱ 3.00 ብር ሆኗል፡፡
በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ የመጣው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መምህር የሆኑት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ፤ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ በይበልጥ የሚጐዳው በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል ነው ይላሉ፡፡

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት የጠቆሙት ዶክተሩ፤ መንግስት ሌላውን ዘርፍ እየጎዳ በነዳጅ ላይ ድጎማ ያደርግ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር በሁሉም ሴክተር ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ እንደማይቀር ጠቁመው፤ በዚህ ተጎጂ የሚሆነው በተለይ በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

“በዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ እኛም መጨር አለብን በማለት መንግስት በየጊዜው በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚያደርገው ጭማሪ አያዋጣም” የሚሉት ባለሙያው፤ የነዳጅ ዋጋው በጨመረ ቁጥር የዋጋ ግሽበቱ እየጨመረ መሄዱ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ተሰብስበው እንዲመክሩበትና መፍትሄ እንዲፈልጉለት ማድረግ ተገቢ ነው” ሲሉም ይመሰክራሉ፡፡ በዋናነት የነዳጅ ዋጋን የማረጋጋት ኃላፊነት የመንግስት መሆኑንም ያሰምሩበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአብዛኛው ህብረተሰብ አቀፍ ዘርፍ በመሆኑ መንግስት ሊቆጣጠረው የሚችለው ነው ያሉት ዶክተሩ፤ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር ነጋዴው በሚሸጠው ዕቃ ላይ ዋጋ ጨምሮ በመሸጥ ጭማሪውን ሊቋቋመው እንደሚችል ጠቅሰው፣ ሸማቹ በተለይም ቋሚ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችና ጡረተኞች ግን ለጉዳት እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ሰራተኞች ሲባልም የጦር ኃይሎችና የፖሊስ አባላትን እንደሚያካትት፣ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም በዋጋ ንረቱ እንደ ሚጎዱ በመግለፅ ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊታይ ይገባዋል ብለዋል፡፡

አገሪቱ በዓመት ወደ ሶስት ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ነዳጅ እንደምታስገባ የጠቆሙት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚደረገውን ጭማሪ ለመግታት ሌላው አማራጭ የነዳጅ ፍጆታን መቀነስ እንደሆነ ጠቁመዋል። በከፍተኛ መጠን ነዳጅ የሚጠቀሙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሲሆኑ መኪኖች፣ ጄኔሬተሮች፣ ግድቦችና መሰል ነገሮች የሚሰሩት በነዳጅ በተለይም በናፍጣ በመሆኑ ይህንን ፍጆታ መቀነስ የሚቻልበት መንገድ ሊታሰብበት ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ሌላው ምሁሩ አማራጭ ነው ያሉት ጉዳይ የነዳጅ ፍለጋውን አጠናክሮ መቀጠል ሲሆን ነዳጅን እየደጎሙ መቀጠሉ አዋጪ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ሌላው ምክንያት ነው ያሉት የፍጆታ መጠን መጨመሩ ሲሆን አሁን አገሪቱ ውስጥ ባለው ሁኔታ እየተሰሩ ያሉት መሰረተ ልማቶች፤ ማሽኖችና መሳሪያዎች የሚወስዱት የነዳጅ ፍጆታ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ አገራችን በአብዛኛው ነዳጅ የምታስገባው ከኩዌት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ለመግታት መንግስት ሊያስብበት ይገባል ይላሉ። የልማት ስራዎች ሲሰሩም የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት ሳይነኩ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመው፤ “ከአቅም በላይ የሚሰራ ልማት ጫናው በህብረተሰቡ ጫንቃ ላይ ያርፍና ህብረተሰቡ ይበልጥ እየተቀየመ ከመጣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ይፈጥራል” ብለዋል፡፡ በእሳቸው ዘመን ከንጉሱ ጊዜ ተቃውሞ ለለውጡ ዋንኛ መንስኤ የነበረው የታክሲ ነጂዎች በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት ያስነሱት ተቃውሞና ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑንም ዶክተር ቆስጠንጢኖስ አስታውሰዋል፡፡

የቁጥር ጨዋታ?! –ፂዮን ግርማ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ

$
0
0

(በፋክት መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 33 የካቲት 2006 ታትሞ የወጣ)

ሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚመነጩ ናቸው። ባለፈው ሰሞን እንዲህ ብሎ በእንቆቅልሽ መልክ ጠየቀኝ። ለእኔም አጠያየቁ ልጅነቴን ስላስታወሰኝ በትዝታ ፈገግታ ታጅቤ “ምናውቅልህ” አልኩት። ”እ … ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው?” አለኝ። ጥያቄውን እኔ ከለመድኩት የልጅነት የእንቆቅልሽ መልስ ጋራ ለማዛመድ የዱር አልቀረኝ የቤት መንገድ አይሰለቻቸውም ስል ያሰብኳቸውን እንስሳት ማሰላሰል ቀጠልኩ። የመሰሉኝንም ስማቸውን ደረደርኩለት፤ አልተሳካልኝም።

እዮሲያስ አገር ስጭኝ አለና በሰጠኹት አገር ላይ ፍልስስ ብሎ፤ ”ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው … እ … ውሃ፣ መብራት እና የስልክ ኔትወርክ” ሲል ያልጠበኩትን ምላሽ ሰጥቶ በደንብ አስፈገገኝ። ዐዋቂን እንጂ ሕፃናትን የሚያሳስባቸው የማይመስለን የውሃ፣ የመብራት እና የስልክ አገልግሎት መጓደል ከማሳሰብ አልፎ በእንቆቅልሻቸው ውስጥ አስገብተው እንደ ሥነ-ቃል በየቦታው እንዲያዛምቱት እንዳስገደዳቸው ተገነዘብኩ። ቤት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚሰሙት “ውሃ ሄዳለች፣ መብራት ጠፍቷል፣ ኔትወርክ የለም” የሚለውን ነው፤ መሄድ፣ መጥፋት እና አለመኖር የሚዛመዱት ደግሞ ከመንገደኝነት ጋር ነውና ስለእንቆቅልሹ ለእዮሲያስ እና ለጓደኞቹ አጨበጨብኩላቸው።

ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ “አዲስ አበባ ውስጥ ሃያ አራት ሰዓታት ውሃ የሚያገኘው የከተማው ክፍል ሰባ አምስት በመቶ ነው” ብለው የሕፃን እዮሲያስ እንቆቅልሽ ፈገግ እንዳደረገኝ ሁሉ እርሳቸውም ፈገግ አሰኙኝ። እንደ እርሳቸው አባባል፤ ሰባ አምስት በመቶ የሚኾነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ያለመቋረጥ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሲያገኝ ሃያ አምስት በመቶ የሚኾነው ነዋሪ ደግሞ በተለያየ ደረጃ ያገኛል።አንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ ዐሥራ አምስት ቀን ቆይቶም ቢኾን ውሃ ያገኛል።

በውሃ እና በመብራት እጦት የአዲስ አበባ ሕዝብ እየተሰቃየ መኾኑን በመጥቀስ ጥያቄ ላነሱላቸው ጋዜጠኞችም ጥያቄው አጠቃላይ ስዕሉን የማያሳይ እና በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሰረተ መኾኑን በመጠቆም “አጠቃላይ ስዕሉን ካላየን በስተቀር የተሳሳተ ስዕል እንዳንሰጥ መጠንቀቅ አለብን” ሲሉ ማስጠንቀቂያ ቢጤም ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኅብረተሰቡን ችግሩ ያጡታል ብሎ ግምታዊ መላምት ማስቀመጥ ቢከብድም ምናልባት በማስታወሻ መያዣቸው ላይ የተሰጣቸውን መረጃ ሲያሰፍሩ ቁጥሩ ተገላብጦባቸው ሊኾን ይችላል ብሎ መገመት ግን ትክክለኛነት ይመስለኛል።

ምናልባት በቅርቡም “እኔ ለማለት የፈለኩት በተለይ ባለሥልጣናት በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ያሉትን ጨምሮ ሃያ አምስት በመቶ የሚኾነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሃያ አራት ሰዓት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያገኛል። ሰባ አምስት በመቶ የሚኾነው ደግሞ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ተራ ውሃ ያገኛል።” የሚል መግለጫን ይሰጡ ይኾናል ብሎ መጠበቅ ሳይሻል አይቀርም። ለነገሩ ይቺ የቁጥር ጨዋታ የገዢዎቹ የተለመደ የጋዜጣዊ መግለጫና የፓርላማ ሪፖርት ማዳመቂያ መኾን ከጀመረች ከራርማለች።

ባለፈው ጊዜ እንዲሁ የጋዜጣ ማተሚያ ቤትን በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጋዜጣን በጥራት እና በብዛት የማተም አቅም ያለው ብቸኛ ማተሚያ ቤት “ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት” ነው። እንዲሁም በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ጋዜጣ ማተም የሚችል ማሽን ያላቸው ማተሚያ ቤቶች ከሦስት አይበልጡም እነርሱም ቢሆኑ ከላይኛው አካል ፍቃድ ካላገኙ በስተቀር ለማተም ፍቃደኛ አይደሉም። ታዲያ እውነታውን ያጡታል ተብለው የማይታሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደረሰኝና የአድራሻ መያዣ ካርድ የሚያትሙትን ጥቃቅን ማተሚያ ቤቶች ሳይቀር ተደምረው ሲሰጣቸው እንደወረደ ተቀብለው አገሪቱ ላይ ወደ ሁለት መቶ ሃምሳ የሚጠጉ ማተሚያ ቤቶች እንዳሉ ጋዜጣ ማሳተም የሚፈልግ አካል ካለም ወደ እነዚህ ማተሚያ ቤቶች ሄዶ ማሳተም እንደሚችል ሲመክሩ ሰምቼ፤ ”የእነዚህ ማተሚያ ቤቶች አድራሻ የት ይኾን?” ስል ልጠይቃቸው ፈልጌ ነበር።

አሁን ደግሞ በእርሳቸው የመንግሥት አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩ ብዙኀን መገናኛ ሳይቀሩ በየጊዜው የሚያነሱትን የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ችግር በምን ስሌት እንደተሠራ በማይታወቅ መልኩ ሰባ አምስት በመቶው የከተማው ነዋሪ የተሟላ አገልግሎት እንደሚያገኝ ደምድመው ተናገሩ። እነ ሕፃን እዮሲያስ እንኳን “መንገደኛ” ያደረጉትን “ውሃ” እርሳቸው “የትም ንቅንቅ ብሎ አያውቅም” ሲሉ የቤት ልጅ አደረጉት። የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ሽፋን በመቶኛ እያደገ መሄዱንማ አገልግሎቱን የሚሰጠው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንን በየቤቱ በዘረጋው የውሃ መስመርና የቧንቧ ቆጣሪ ቁጥር ልክ ለክቶ ሁሌም በሚሰጠው መግለጫ ሲነግረን ቆይቷል። ከዛም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች የከፋ የውሃ እጥረት ሲያጋጥምም በውሃ ማከፋፈያ መኪና ውሃን ለኅብረተሰቡ የማድረስ አገልግሎት እንደሚጀምርም ጭምር ሲናገር ተሰምቶ ነበር። ጥያቄው “በየቤቱ ባሉት የውሃ ቧንቧዎች አማካኝት ሊወርድ የሚገባው ውሃ መቼ ነው ከሄደበት የሚመለሰው?” የሚለው ነው።

ነዋሪዎች በየመንደሩ ውሃ መጣ አልመጣ እያሉ፣ በርካቶች የሌሊት እንቅልፋቸውን መስዋዕት አድርገው ሲያገኙ እያጠራቀሙ ሲያጡ ደግሞ ከያለበት እያስቀዱ በሚኖሩባት ከተማ “ሰባ አምስት በመቶው በተሟላ ሁኔታ ውሃ ያገኛሉ” ማለት ተናጋሪውን ትዝብት ላይ ይጥላል። ይህን መግለጫ በየቤቱ ሆኖ የሚከታተለው “ውሃ አጥ” ነዋሪ ምናልባት በያለበት ሆኖ “ ውሃ የጠፋው እኛ አካባቢ ነው እንጂ ሌላ ቦታ ውሃ አለ ማለት ነው” በሚል ሊያስብ ስለሚችል ቁጥሩን አምኖ ይቀበላል በሚል ከኾነ ያስኬዳል። ነገር ግን እኔ እንኳን በግሌ ለማረጋገጥ ከሞከርኳቸው አዲስ አበባ ውስጥ ካሉ፤ የረር ጎሮ፣ አያት፣ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ አስኮ፣ ዊንጌት፣ ኮተቤ፣ ፈረንሳይ፣ ሽሮሜዳ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ለቡ፣ መገናኛ፣ ሃያ ሁለት፣ በአብዛኛው የኮንደምኒየም ቤቶች እና ሌሎች ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች ውሃን በየተራ እንደሚጠቀሙ ነው። እነዚህ አካባቢ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በስንት በመቶ ታስበው ይኾን? ጠቅላይ ሚኒስትር።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እንደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍ ቢያደርግለትና ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ሃያ አራት ሰዓት ውሃ ቢያገኝ፤ እንዲሁም በከፊል የሚያገኘው የኅብረተሰብ ክፍል ሃያ አምስት በመቶው ብቻ ቢኾን ኖሮ ችግርን በሂደት የመላመድ ባሕል ባለው በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ ፍጹም የውሃ እጥረት እንደ ችግር አይነሳም ነበር። ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት የአዲሱን ባቡሩን ቀለም ለመምረጥ በየቦታው እንደተቀመጡት መዝገቦች ዓይነት በየአካባቢው በማስቀመጥ መረጃን ለማሰብሰብ ቢሞክሩ የተገላበጠውን ቁጥር ያገኙታል ብዬ እገምታለሁ።
***********
በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የመደበኛ እና ኢንትርኔት አገልግሎት ተገቢ አገልግሎት አለመኖር እና ጥራት መጓደል ተጠቃሚውን እጅግ ካስመረሩት ጉዳዮች አንዱ ነው። “ኔትወርክ ተጨናንቋል፤ እባክዎትን ትንሽ ቆይተው ይደውሉ፤ የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመሩን እየተነጋገሩበት ነው፣ እባክዎትን ደግመው ይሞክሩ፤ የኔትወርክ ሽፋን የለም” የሚሉት በኢትዮ-ቴሌኮም አገልግሎት ላይ የተለመዱ ምላሾች ናቸው። ስልክ ሲደወል ከስልኩ ውስጥ ድምጽ አለመስማት፤ ስልኩ ከተነሳ በኋላ የራስን ድምጽ መልሶ መስማት፣ እያወሩ የራስን ድምጽ እንደ ገደል ማሚቱ ከሥር መስማት የተለመዱ የአገልግሎቱ አካል ናቸው። ወደ ባንክ እና በኢንተርኔት አገልግሎት ወደሚሰጡ መሰል ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲኬድም “ኮኔክሽን የለም ትንሽ ጠብቁ “የሚሉት ምላሾች እንደተገቢ ምላሽ መቆጠር ከጀመሩ ሰንብተዋል።

እነሕፃን እዮሲያስ “መንገድ የማይሰለቻቸው” ሲሉ በእንቆቅልሽ መልክ ካስቀመጧቸው ውስጥም የቴሌኮም አገልግሎትን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሲናገሩ፤ በቴሌኮም አገልግሎት ሥር ያሉት የተንቀሳቃሽ፣ የኢንተርኔት እና የመደበኛ አገልግሎት መቆራረጥ የተከሰተው አሠራሩን ዘመናዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመሳሪያ ለውጥ ሂደት አገልግሎት መዛነፍ መኖሩን ገልጸው ይህ መዛነፍ በተቀመጠለት የስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚስተካከል እርግጠኛ ሆነው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት “ከስድስት ወራት በኋላ” ሲሉ ያስቀመጡትን የጊዜ ገደብ የኢትዮ – ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ አብዱራሂም አሕመድ፤ ችግሩን ለማስወገድ መሠረተ ልማት ለመቀየር የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን እና በጥቂት ወራት ውስጥ በጣም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ለዚህ ሲባልም የቅድሚያ ቅድሚያ ተሠጥቶት ዝርጋታውን የማቀላጠፍ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ከተናገሩ ስምንት ወይም ዘጠኝ ወራት መቆጠሩን አስታውሳለሁ። ባለሥልጣናቱ በቁጥር እየተጫወቱ የሚዘልቁት እስከመቼ ይኾን?

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፤ ኢትዮጵያ የመረጠችው የቴክኖሎጂ ኩባንያ፤ ”ዴንማርክ”፣ “ኖርዌይ”፣ እና “እንግሊዝ” የሚጠቀሙበት “ሁዋዌ” የተሰኘውን ኩባንያ መሆኑን በኩራት ሲናገሩ ተሰምተዋል። ሌላውን ቁሳቁስ ቢሆን እነ “ዴንማርክ”፣ “ኖርዌይ”፣ እና “እንግሊዝ” እና የመሳሰሉት አገራት ኢትዮጵያ ከምታመጣበት “ቻይና” አይደል እንዴ የሚያስመጡት? ዋናው ጥያቄ የሚነሳው ለእነዚህ አገራት የሚገባው ዕቃ ጥራት እና ኢትዮጵያ የሚገባው ዕቃ ጥራት አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑ ላይ ነው። እነዚህ አገራት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቁጥጥር አንድ መሆን አለመሆኑ ላይ ነው። በእነዚህ አገራት ያለው ሙስና እና በኢትዮጵያ ያለው ሙስና አንድነት እና ልዩነት ላይ ነው።

ጥያቄው መሆን ያለበት “ሁዋዌ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘረዘሯቸው አገራት ካሉት አስተዳዳሪዎች ጋራ ያለው የሥራ ግንኙነት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አስተዳዳሪዎች ጋራ ያለው የሥራ ግንኙነት ምን አንድነት አለው የሚለው ላይ ነው። ሌላው ጥያቄ ደግሞ የእነዚህ አገራት ገዢዎች ለሕዝባቸው ያለባቸው ተጠያቂነት እና የኢትዮጵያ ገዢዎች ያለባቸው ተጠያቂነት ነው። የ”ዴንማርክ”፣ የ”ኖርዌይ”፣ እና የ”እንግሊዝ” ገዢዎች በየስምንት ወሩ እየመጡ “ጥቂት ወራት ታገሱ፣ ከስድስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል፣ ዕድገቱ የፈጠረው ችግር ነው” የሚሉ ምክንያቶችን እየደረደሩ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንደማይሞክሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ያጡታል ብዬ አላስብም። ለማንኛውም ስድስት ዓመት መታገስ ለለመደ ሕዝብ ስድስት ወር እሩቅ አይደለምና “ኔትወርኩ አያሰማማም፣ ኢንትርኔቱ ኮኔክሽን የለውም፣ የቤቱ እና የቢሮው ስልክ አይሠራም” እየተባባሉ ስድስት ወር መጠበቅ ብዙ የሚከብድ አይመስለኝም።
የአሁኑም የቀድሞውም ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሲሉ እንደተሰሙት፤ መንግሥት የቴሌኮምን አገልግሎት ወደ ግሉ ዘርፍ ማስተላለፍ የየማይፈልገው፤ ቴሌ ገንዘብ የሚታለብበት ተቋም በመኾኑ ነው። ምናልባት ለኅብረተሰቡ የሚከብደው ስድስት ወር መጠበቁ ብቻ ሳይሆን ባልተገኘ አገልግሎት መታለቡ ሊኾን ይችላል። በአሁኑ ወቅት ባለው አገልግሎት በአብዛኛው አንድ ሰው ወደ ሚፈልገው ሰው ስልክ ደውሎ ለማግኘት ከአምስት እና ከስድስት ጊዜ በላይ ደውሎ የራሱን ድምጽ እየሰማ ለመዝጋት የሚገደድ ሲኾን ለዚህም ቴሌ የአገልግሎት ክፍያውን ያገኛል። እንደጠቅላይ ሚኒስትሮቹ አገላላጽ፤ ቴሌ ባልሰጠው አገልግሎት ኅብረተሰቡን ያልባል ማለት ነው። ስለዚህም ከባድ የሚመስለው ስድስት ወር መጠበቁ ሳይሆን ባልበላ አንጀት መታለቡ ነው።

የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ቁጥርን በሚመለከት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ከዕቅዱ በላይ ማሳካቱን የገለጸው ኢትዮ-ቴሌኮም ለ22 ሚሊዮን ሕዝብ ተንቀሳቃሽ ስልክ በመስጠት በሞባይል አገልግሎት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ሲናገር ተሰምቷል። የተለመደው የቁጥር ጨዋታ ኾኖ ነው እንጂ፤ ደረጃው የአገልግሎት ጥራትን መሠረት አድርጎ የወጣ ቢኾን ኖሮ አገሪቷ ከአፍሪካ የመጨረሻው ተርታ ላይ ትሰለፍ ነበር።

***********
ሕፃን እዮሲያስ “ቢሄድ፣ ቢሄድ የማይሰለቸው” ካላቸው መንገደኞች ውስጥ አንዱ የመብራት አገልግሎት ነው። የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሠራተኛ የኾነ ታማኝ ምንጭ በአንድ ወቅት፤ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድርጅት ውስጥ የምትሠራ ነገር ግን ልዩ ልዩ የጥቅማ ጥቅም ድጋፍ ይደረግላት የነበረች አንዲት ጋዜጠኛ ለኮርፖሬሽኑ በርካታና አስቸኳይ የኾኑ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች እንዳለባትና ለዚህም አገልግሎት መብራት እየጠፋ ስለሚያስቸግራት የግል ትራንስፎርመር እንዲገጠምላት መጠየቋን ይነግረኛል። እርሱን ያስገረመው እርሷ ምን ዓይነት ኃላፊነት ላይ ብትኾን ለግሏ ትራንስፎርመር መጠየቋ ነበር። እኔ ደግሞ ምን ዓይነት ምላሽ እንደተሰጣት ጓጉቼ ጠየኩት። “ከአንቺ በፊት በጣም በርካታ ባለሥልጣናት ስለጠየቁ፤ ተራ ጠብቂ “ተባለች አለኝ። ምናልባት የአገሪቱ ባለሥልጣናት ለኅብረተሰቡ ችግር ቦታ ሳይሰጡ በቁጥር የሚጫወቱት፤ የውሃ፣ የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ተራ እየጠበቁ በየግላቸው ስለሚያገኙ ይኾን?

tsiongir@gmail.com

አቡጊዳ –በኢትዮጵያ ላይ እየጠነከረ የመጣዉ የግብጻዉያን ዘመቻ

$
0
0

ግብጾች ሱዳን ኢትዮጵያ እና ግብጽ እያደረጉት ከነበረው የሶስትዮች ድርድር እራሷን ማግለሏ ይታወሳል። የግብጽ ሜዲያዎች በዚህ ጉድያ ጉዳይ ላይ በስፋት እየዘገቡ ሲሆን ጸረ-ኢትዮጵያ ዘመቻና ፖሮፖጋንዳዉን በስፋት ተያይዘዉታል።

የቻይናዉ CCTV በዚህ ጉዳይ ያቀናበረዉን ለማየት እዚህ ይጫኑ።

መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት? ከበላይ ገሰሰ

ትግሉን ይቀላቀሉ ፣ ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ ይሁኑ !

$
0
0

የካቲት 16 በሚደረገዉ የባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት በጋራ የጠሩት ነዉ። ድርጅቶች እንዲህ ሲተባበሩ ያስደስታል። የተናጥል የብቻ ጉዞ የትም አይደርስምና።

ይህ ሰልፍ ምንም እንኳን የብሃአዴን አንድ አመራር አባል ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ከአንድ ግለሰብ ያለፈ መሆኑን መረዳት አለብን። ባለስልጣኑ ጸያፍና ነውረኛ አስተያየት ሰጡ የሚል ክስ ሲቀርበባቸው ፣ ገዚው ፓርቲ ፣ ግድ የለም፣ አሁኑኑ አይቅጣቸው፣ ቢያንስ ቢያንስ ግን «ጉዳዩን እመረምራለሁ። የተባለዉ እዉነት ከሆነ አስፈላጋዉን እርማት እሰጣለሁ» ማለት ሲገባው፣ ነገሩን አድበስብሶ ማለፉ፣ ገዢው ፓርቲ ምን ያህል ሕዝብ በፓርቲ ደረጃ እንደሚንቅ፣ ከሕዝብ ክብር ይልቅ የካድሬዎቹ ደህንነት የሚያሳስበው እንደሆነ ያመላከተ ነዉ።

በመሆኑም የሚሊየነም ድምጽ ፌስቡክን፣ የምንከታተል ሁላችንም፣ በኤሜል ፣ በትዊተር ፣ በእጃችን ያሉ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም ቅስቀሳዉን እንቀላቀል። ከአንድ፣ መቶ፣ ከመቶ፣ ሺህ፣ ከሺህ ሚሊዮኖች ይበልጣሉና።

በባህር ዳር ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ ያለን፣ ደዉለን ወደ ሰልፉ እንዲወጡ እናበረታታ። ለሰልፉ የሚያስፈልጉ ብዙ ወጪዎች አሉ። በገንዘባችን ድጋፍ እናድርግ። ጋዜጠኞች፣ የድህረ ገጽ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ ሜዲያዎው፣ ሰልፉን ለሕዝባችን በማስተዋወቁ ረገድ ድጋፋቸዉን ያበርክቱ። ጸሃፊያን ብእራቸውን እንዲያነሱ፣ ስለሰላም፣ ስለዴሞርካሲ፣ ስለመበት፣ ለሕግ የበላይነት እንዲጽፉ እናበረታታለን።

የቻልን በአካል ሰልፉን እንቀላቀል። ያልቻልን በመንፈስ የትግሉ አጋር እንሁን። የሁላችን የሆነቸዋን አንዲ አገር በጋራ እናድናት።1689471_680135262045226_946826287_n

አቡጊዳ –የባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ የኦዲዮ ማስታወቂያ

$
0
0

መኢአድ እና አንድነት በጋራ፣ በባህር ዳር ከተማ በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ፣ የባህር ዳርን ሕዝብ ለመቀስቀስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ከስፋራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። ፓርቲዎቹ፣ ሰልፉን የሚያስተባበር ልዩ ሎሚቴ ያዘጋጁ ሲሆን፣ የሰልፉ ማስታወቂያ ፖስተሮች በስፋት ተዘጋጅተዋል።

ከበራሪ የጽሁፍ ወረቀቶች በተጨማሪ የተዘጋጀ የቅስቀሳ ኦዲዮ በሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት፣ በፌስቡክ ተለቋል። በባር ዳር ከተማ መንገዶች፣ ይህ ኦዲዮ በላዉድ ስፒከሮች ህዝብ እንዲሰማው እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።

በባህር ዳር እና አካባቢዋ የሚኖሩ፣ በሰልፉ በመምጣት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ፣ መኢአድ እና አንድነት በቅስቀሳ ጥሪ ከማቅረባቸው በተጨማሪ፣ ከባር ዳር ርቀው የሚገኙ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፣ በባህር ዳር ያሉ ዘመድ፣ ወዳጆቻቸዉን ወደ ስለፉ እንዲመጡ በማበረታትታ፣ በገንዘብ ድጋፍ፣ በምክር፣ በሶሻል ሜዲያ ቅስቀሳዎችን ፣ በጽሁፍ ሆነ በሌሎች ችሎታዎች ትግሉን እንዲረዱ፣ ከባህር ዳር ህዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ከሚሊዮኖች አንዱ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል!


የባህር ዳር ሰልፍ ቀስቃሽ ማስታወቂያ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ !


አቡጊዳ –ባህር ዳር በቅስቀሳ ደምቃለች

$
0
0

አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል። ሕገ መንግስቱን በመጻረር ፣ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን በመገፋት የብአዴን ካድሬዎች የተለያዩ ምክንያቶ እያቀረቡ የሰልፉ አስተባባሪዎች የማገት፣ የማስፈራራት ሥራ እየሰሩ እንደነበረ የደረሰን ዜና ይጠቁማል።

bahir1

bahir2

bahir3

አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል። ሕገ መንግስቱን በመጻረር ፣ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን በመገፋት የብአዴን ካድሬዎች የተለያዩ ምክንያቶ እያቀረቡ የሰልፉ አስተባባሪዎች የማገት፣ የማስፈራራት ሥራ እየሰሩ እንደነበረ የደረሰን ዜና ይጠቁማል።

ባጃጆች (ትናንሽ ታክሲዎች)፣ በፈቃዳቸው ከጀርባቸው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ያነገቡ ፖስተሮችን ተሸክመው ባህር ዳርን እየዞሩ ይገኛሉ፡፡ የከተማይቱ ግድግዳዎች የስልክ እንጨቶች ‹‹ብአዴን/ኢህአዴግ ህዝብን የመምራት ሞራልም ብቃቱም የላቸውም››በሚሉ መፈክሮች እየተጥለቀለቁ ነው፡፡ በድምጽ ማጉያም መፈክሮች ፣ ቅስቀሳውቾ እየተሰሙ ነው።

አቡጊዳ –የአቶ አለምነህ አስተባበሉ ፤ ግን የኦዲዮ በማስረጃ አለ!

$
0
0

አቶ አልምነው መኮንን በ«አማራዉ» ላይ በተናገሩት የንቀት አባባሎች ምክንያት፣ ባለስልጣኑ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ አንድነት እና መኢአድ በመጠየቅ የክልሉ መስተዳደር በሚገኝበት በባህር ዳር ከተማ እሁድ የካቲት 16 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱ ይታወቃል።

በባህር ዳር ቅስቀሳው እየተፋፋመ ባለበት ወቅት፣ አቶ አልምነዉ መኮንን ማስተባበያ በኢቲቪ እየተላለፈ መሆኑ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡክ የሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ ፔጅ ከታች እንደተገለጸው ዘግቧል። በቀጥታ በፌስቡክ የሚሊየምን ድምጽ ለነጻነት የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴ ለመከታተል እዚህ ይጫኑ !

======================
በባህር ዳር ቅስቀሳው ተፋፍሟል። በዉጭ አገር የሚገኙ ታዋቂ ድህረ ገጾችና ሜዲያዎችም ከፍተኛ ትብብር እያደረጉ ነዉ። ዘሃበሻ፣ ኢትዮጵያን ሪቪዉ፣ ኢ.ኤም.ኤፍ፣ ኢሳት፣ አቡጊዳ በባህር ዳር በስፋት እየዘገቡት ነዉ። የብአዴን/ኢሕአዴግ አመራሮች የክልሉን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ሕዝቡን የሚያከብሩ ሳይሆን ፣ ሕዝቡን የሚንቁና ከሕዝቡ ጋር የተጣሉ መሆናቸው ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። አማርኛ ተናጋሪዎች ከሌሎች ክልሎች በግፍ ሲባረሩ፣ የክልሉ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ፣ ዝምታን የመረጡ ናቸው።

ይግረም ተብሎ፣ በገሃድ በፊት ለፊት ሕዝቡን ሲያዋርዱ፣ ሲሰድቡ እየሰማናቸው ነው። ይህ «አማራዉ» ላይ የተሰነዘረው የንቀት ንግግር፣ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው።

የብአዴኑ/ኢሕአዴግ መሪ «አማራ» በሚባለው ማህበረሰብ ላይ የሰጡትን አስተያየት ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ !

አቡጊዳ –ኢሕአዴግ ሕዝብን የሰደቡና ያዋረዱ የብአዴን አመራር አባል ጎን ቆመ !

$
0
0

ኢሕአዴግ ሕዝብን የሰደቡና ያዋረዱ የብአዴን አመራር አባል አቶ አለምነህ መኮንንን ተጠያቂ በማድረግና ከሃላፊነታቸው ከማንሳት ይቅል፣ ከጎናቸው መቆሙን አረጋገጠ።

መኢአድ እና አንድነት ፣ በአማራዉ ክልል የሚኖረው ሕዝብ ላይ ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አሳዛኝ፣ ንቀት አዘል አስተያየት የሰጡት አቶ አልምነዉ መኮንን ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወቃል። ኢሕአዴግ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ አናንቆ፣ ምንም ምልሽ ባለመስጠቱ፣ አንድነት እና መኢአድ ለየካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ መጥራታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳዉ የተጀመረ ሲሆን «ሕዝብን የሚንቁ የብአዴን መሪዎች የአመራር ብቃት የላቸውም» የሚሉ አባባሎች የያዙ ጽሁፎቸ ሲበተኑና በየቦታዉ ሲለጠፉ እንደነበረ ፍኖተ ነጻነት እና የአንድነት ሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ዘግቧል።

የባህር ዳሩ ሰልፍ ሞቅት እያየለ ሲመጣ፣ ኢሕአዴግ ነገሩ በጣም ስላሳሰበው፣ ሙሉ ሙሉ የሚቆጣጠረዉን ኢቲቪ በመጠቀም፣ አቶ አለምነው ማስተባበያ እንዲሰጡ ያደረገ ሲሆን፣ በባህር ዳርም ፣ አቶ አልምነው በኢቲቪ የተናገሩት አባባሎች ያቀፈ የማስተባበያ ወረቀት መበተን ጀምሯል።

ኢሕአዴግ አቶ አልመነዉ መኮንን በኢቲቪ ቀርበው ማስተባበያ እንዲሰጡ ማድረጉና አንድነት/መኢአድ እየበተኑ ያሉ ወረቀቶችን ለመመከት፣ የራሱ ወረቀቶችን ማሰራጨት መጀመሩ በተመለከተ አስተያየት የሰጡን አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ «እኝህን ሰዉዬ ቀስ ብለው ያነሳሉ የሚል ግምት ነበረኝ። አሁን ግን በሙሉ ኃይል ከርሳቸው ጎን ለመቆም አገዛዙ የወሰነ ይመስላል። ይሄም ጉዳዩን በኦፌሴል ከግለሰብ ወደ ፓርቲ ከፍ አድርጎታል» ሲሉም አገዛዙ ሕዝብን ከሰደቡና ካዋረዱ አንድ ግለሰብ ጋር መቆሙን እንደመርጠ ያስረዳሉ።

ኢሕአዴግ በባህር ዳር በበተናቸው ወረቀቶች ፣ መኢአድ እና አንድነትን «ጸረ-ሰላም ኃይሎች» ፣ «የትምክህትና የኪራይ ሰብሳቢ ወኪሎች» በሚል የገለጻቸው ሲሆን፣ ለሕዝብ ይፋ የሆነውን የአቶ አልመነህ ሞኮንን ንግግር የያዘዉን ኦዲዮ ፋይል ደግሞ «ተቆራርጦ የተቀጠለ» በሚል ለመካድ የመሞከር ነገር ይታያል።

አቶ አልመነህ የተናገሩትን እና ኢቲቪ ቆርጦ ቀጥል ነው ያለውን ኦዲዮ ለመስማት እዚህ ይጫኑ !

ኢሕአዴግ በባህር ዳር የበተነዉን ወረቀት ይመልከቱ፣ andm

====================================
- የአመራር ስም ማጥፋት፣ የቆርጦ ቀጥሎች ፖለቲካና የምርጫ ዋዜማ ነጠላ ዜማ ነው !
- የአማራ ሕዝብንና ትምክህትን ለያይተው መመልከት ባልቻሉ የጥፋት ፖለቲከኞች ሰፊው የአማራ ሕዝብ አይደናገርም!!
- ትምክህት የአማራ ሕዝብ ጠላት እንጂ ወዳጅ ሆኖ አያዉቅም ሊሆንም አይችልም!
- ቀጥል የጥፋት ፖለቲካ የብ አዴን ኢሕአዴግን አመራሮች ስም ማጥፋት የጸረ-ሰላም ኃይሎች የዘዉትር ተግባር ስለሆነ አዲስ ነገር አይደለም!!
- የአማራ ሕዝብ የተቀዳጃቸው የሰላም የዲሞክራሲና የልማት ጉዞ በትምህክህትና በኪራስይ ሰብሳቢ ወኪል ፓርቲዋ ፈጽሞ አይደናቀፍም !!
ብ፤አዴን የትምክህትና ኪራኡ ሰብሳቢነት አመለካከትን ሲዋጋ ኖሯል። የጸረ ትምክህትና ጸረ-ኪራስይ ሰብሳቢነት ትጉ ተጠናክሮ ይቀጥላል !
ከተማችን ባህር ዳር እያስመዘገበች የቆየችዉን ልማት በተለይ በዚህ አመት እየተካሄደ ያለዉን የተሟሟቀ የመሰረተ ልምትና የሥራ እድል ፈጠራ እንዲሁም የትልልቅ ኮንፈራንሶች ማእከል መሆኗ ያልተዋጠላቸው የጥፋት ፖለቲከኞች የሚነሱት ወሬ ከልማት ስራችን ሊያስተጓጉለን አይችልም !
======================================

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን በአቤ ቶኪቾዉ

$
0
0

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤ እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።

“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።

እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤

አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???

ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!

ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!

አቡጊዳ –ሸንጎ ለባህር ዳር ሕዝብ፣ ለመኢአድ/አንድነት አጋርነቱን ገለጸ

$
0
0

«በባህር ዳር ከተማ፣ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ ሁሉም ድጋፉን ይስጥ» ሲል የበርካታ አንጋፍ ደርጅቶች እና ሲቪክ ማህበራት ስብስብ የሆነው ሸንጎ ለመኢአድ እና አንድነት አጋርነቱን ፣ የካቲት 10 ቀን ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ።

«የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን፣ ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ ያለውን ድጋፍ ይገልጻል» ሲል ያተተው የቸንጎ መግለጫ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት በሕዝብ ላይ እያሳዩ ያለውን ንቀት አዉጓዜል።

«የሕዝባችን ትግል ውጤት እንዲያስገኝ እያንዳንዳችን ሀላፊነታችንን መወጣት የግድ ይላል። በመሆኑም በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊም በገንዘብም ሆነ በማበረታታት ይህን ሰልፍ ያዘጋጁትን በማገዝ የሕዝባችን ትግል ቀጥተኛ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን። » ሲልም በዉጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የድርቻዉን አገራዊ ግዴታ እንደዲወጣም አሳስበዋል።

የሸንጎ አባል ድርጅቶ፣ ብሩህ ኢትዮጵያ፣ መድህን፣ ትዴት (TAND) ፣ ታጠቅ፣ ኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊ፣ መኢሶን እንዲሁም SOCEPP.CA ይገኙበታል።

የሸንጎን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

የማለዳ ወግ …በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ ወዴት እየሔድን ነው ? ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል ….

” ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል … ሀበሻ የድሮወቹ የሉም … ወድ የሆነውን የሰውን ደም በከንቱ የሚጠጡ እርኩስ መንፈስ የተጠናውታቸው ውሾች ናቸው .so ሰሞኑን በ ጅዳ አካባቢ ሸር ሄራ አካባቢ የተደረገውን ግፍ ልንገርክ …በሀበሾች ጭካኔ የተገደለውን ልጅ በአካል አውቀዋለሁ አብዱ ሁሴን ይማም ይባላል … በሳንጃ ገደሉት ! ልብ በል … የሳውድ መንግስት ታዲያ እንዴት አያሳድደን ! እንደነዚህ አይነት እርኩሶች እያሉ እኛ ቤተሰብ እንዴት እንርዳ? ልጅስ እንዴት እናስተምር? ..ነብዩ ሰው እንዴት …የሰውን ነፍስ ያጠፋል? ደግሞም ሳውዲ ውስጥ ? ከተሰራ ለሚገኝ ገንዘብ እጅግ ያሳዝናል ይጎመዝዛል ! ጌታ እውነቱን ይፍረድ ለሀበሻ ጩኸት በቃኝ እኔም ሀበሻ ነኝ!!! ” ይላል !

ሰሞኑን “ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ላይ በግፍ የግድያ ወንጀል ተፈጸመ !” የሚለው ወሬ ከጓዳ እስከ አደባባይ ሲናኝ አስከፊውን ሂደት የታዘቡ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም። ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁና ከሚከታተሉ የሃገሩ ሰዎችም መልዕክቶችና አስተያየቶች ደርሰውኝ በሃፍረትም ቢሆን ለማስተናገድ ተገድጀም ነበር … የሟችን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና ስለኢትዮጵያ የሚጽፉ ፣ አንድ ከፍ ያለ ሃላፊነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያና ሃያሲ የሃገሩ ሰው አዝነውብን አግኝቻቸዋለሁ ። በቁም ነገር በቢሯች አስጠርተው ያሉኝ እንዲህ ነበር ” ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ምንድ ነው እንዲህ የመሰለ የዘቀጠ በሃበሾች ያልተለመደ ጉዳይ ተደጋገመሳ ? ሀበሾች ምን ገባባችሁ? ከአመታት በፊት በሪያድ መንፉሃ ፣ ከወራት በፊት በመዲና በአብሃ እና በዙሪያው ያን ሰሞን ደግሞ በኪሎ ተማንያ እና በዙሪያው በሃበሾች መካከል መጨካከን የተሞላበት ድርጊት ታይቷል። ከሁሉም የሚያሳዝነው የግድያ ምክንያቶቹ ጊዜያዊ ጸብን ፣ ጥቅምንና ጥቃቅን የሰው ህይዎትን በጭካኔ ሊያስጠፉ የማይገባቸው ምክንያቶች ናቸው ። ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? ” ሲሉ በጥያቄ ላፋጠጡኝ ሳውዲ ወዳጀ የሚሆን መልስ ግን አልነበረኝም ! ብቻ የሆነው አሳዝኖ ፣ አሳፍሮ አንገቴን አሰበረኝ …

እርግጥ ነው ፣ ባሳለፍናቸው አመታት በሪያድ መንፉአ አካባቢ አልፎ አልፎም በኢትዮጵያውያኑ መካከል በሚፈጠር ግጭት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዜጎች በሰላ ጩቤ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸው የመቁሰልና የመገደል አደጋ ምክንያት እንደ ነበር የአይን እማኞች አጫውተውኝ ነበር ። በጩቤ ለመወጋጋቱ ዋንኛ ምክንያትም ደግሞ ተራ ከገንዘብና ከሴት ጋር የተያያዙ እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸው ማጤንና መገንዘብ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል …በቀደሙት ጥቂት አመታት በሳውዲና የመን ድንበር ከተሞች ይህ መሰሉ ወንጀል የከፋ እንደ ነበር አውቃለሁ። በተለይም በጀዛን ፣ በአብሃና በከሚስ ምሽት በሚባሉ አካባቢዎች በዙሪያው ባሉ የከተማና የገጠር ከተሞች በከተሙ ኢትዮጵያውያን መካከል ተፈጸሞ የምንሰማው ግድያ ፍጹም ጭካኔ ያልተለየው መሆኑ ይጠቀሳል ! ወደ አብሃና ከሚስ ምሸት ለስራ ባቀናሁባቸው ቀናት በእኛ ዙሪያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የከበደ መረጃ በእጀ መድረሱን አስታውሳለሁ። በህገ ወጥ መንገድ ዜጎቻችን ከየመን ሳውዲ በሚያመላልሱ ለገንዘብ በገንዘብ እየሸጡ የሚተዳደሩ ደላሎችና አቀባባዮች በጎሳ ተቧድነውና ብሔርን ለይተው የሚከሰተውን ግጭት ከጩቤ ያለፈ እንደ ነበርም በቦታው ተገኝቸ ታዝቤያለሁ። በተለይም በአብሃ አካባቢ በግጭቱ ስለተቀጠፈው ህይዎት ፣ ፍርድን ይጠባበቁ ስለነበሩ የእኛ ገዳዮችም የፍርድ ሂደት በቅርብ እከታተል ነበር ። ከሁሉም የሚያሳዝነው የሰውን ልጅ ያህል ታላቅ ፍጡር በስለት የሚጠፋበትን ምክንያት መስማት እንደ ነበርም ትዝ ይለኛል። ከሃገር ቤት ያለ የዘር ፣ የግል ጥላቻና ጸብን መሰረት ያደረገው የደም መቃባት ፣ በገንዘብ መካካድ ” ጓደኛየን ነጠቀኝ!” ፣ “የሰማንያ ሚስቴን ደፈረ !”፣ በሚሉትና በመሳሰሉት ክሶች የሚያጠነጥነው ብቀላ በፍትህ ሳይሆን በጭካኔ ለመወጣት የሚፈጸም ያረጀ ያፈጀ ይትበሃል ሳውዲ ተከትሎን መጥቶ ስማችን ማርከሱ ደግሞ ከሁሉም በላይ ያማል !

በያዝነው አመት ከጅዳ በ400 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው በሙስሊማን ቅዱስ ከተማ በመዲናም በዜጎቻች መካከል በተፈጠረ የቨዛ ሽያጭ እና ተጓዳኝ የገንዘብ መካካድ ያስከተለው አምባጓሮ በቅዱሷ ከተማ ቅዱስ የማይባል ግድያ ለመፈጸሙ ምክንያት ነበር ። ይህም የጭካኔ ወንጀል የተፈጸመበት ኢትዮጵያዊ ፣ ወንጀል ፈጻሚው ኢትዮጵያዊው መሆኑ ደግሞ ጉድ አሰኝቶ አሳፍሮን አልፏል። ከወራት በፊትም እዚሁ ጅዳ በተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን መካከል የተነሱ አምባጓሮዎች በተመሳሳይ ጭካኔ በተሞላባቸው የግድያ ድርጊቶች የተከበቡ ወንጀሎች ምክንያት ነበሩ ማለት ይቻላል። እናም ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ….

ባሳለፍነው ሳምንት በጭካኔ የተገደለው ወንድም ወንጀል ተጠርጣሪ ፣ ተጠያቂ የቅርብ ጓደኛ ወዳጁ እንደነበረና ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሰማን ! አብዱ በማጣታቸው ትልቁ የሃዘን መርግ የወደቀባቸው፣ የሚይዙት የሚጨብጡ ያጡት ፣ ቤታቸው የጨለመባቸው አንዲት ሴት ልጂና የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ሃዘን የከበደ ነው…ስለአብዱን ቅንነት፣ ሰው አማኝ ፣ ትጉህና ታታሪነቱን የሚመሰክሩት ባልንጀሮቹም ሃዘናቸው መሪር ያደረገው የተፈጸመው የጭካኔ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ቀዳሚ ተጠርጣሪ የቅርብ ወዳኛ መሆኑ ነበር ። በዚህም ሊያምኑት በከበደ ድርጊት እርር ድብን ብለው አዝነዋል! ዛሬ የማይሰማ የማያየን አብዱ ሁሴን በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ይገኝ እንደነበር በቅርብ ጓኞቹ ጨምረው አጫውተውኛል ። የወንድም አብዱ ሁሴን ይማም የቀብር ስነ-ስርዓት ትናንት የካቲት 12 / 2006 ረቡዕ ከቀትር በኋላ በጅዳ ከተማ ተፈጽሟል ! አብዱ የሔደው ሁላችንም ወደ ማንቀርበት የላይኛው ቤት ነው ! ነፍሱን ይማረው ! ” አላህ ይርሃሙ !”

ወንጀሉን በትኩሱ ለማቅረብ በፖሊስ ክትትክ መሆኑና ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ባለመያዙ የማለዳ ወጌን እንዳዘገየው ቢያስገድደኝም መረጃውን ባሳለፍናቸው ቀናት ከበርካታ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ሞክሬ ነበር ። በዚህ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዙሪያ እየተነጋገረ የሚገኘውን አብዛኛው የጅዳ ነዋሪ ” ህጋዊ ህገ ወጥ ” ነገን ምን ይከተል ይሆን እያለ በጭንቀት በሰቀቀን እየጠበቀ ባለበት ሰአት የዚህ መሰሉ ድርጊት መፈጸም ” እንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ !” ሆኖበት ተመልክቻለሁ! ለእኔም የሆነብኝ እንዲያ ነው …

ድርጊቱ አሳዝኖኝ ለማውገዝ ያነሳሁት ብዕር መቋጫ የሚሆነው ሳውዲው ሃያሲ ወዳጀ ያጫወቱኝን ዘልቆ የሚሰማ ያልመለስኩት ጥያቄ ነው ። ሃያሲው ሃበሾች በዚህ መሰል ድርጊት እንደማንታወቅ ተናትነው ከቅርብ አመታት የሰበሰቧቸው መረጃዎች ቢያሳስቧቸው ቆጣ ብለው በንዴት ሲያጠይቁ “ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? ” ነበር ያሉኝ …እኔም ተጠርተን የማናውቅበት ወንጀል ሲደጋገም አሞኛልና ድርጊቱን አወግዘዋለሁ! ወደ መጨረሻም አሳፍሮ መልስ ያጣሁለትን የሃያሲውን ወዳጀ ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ … ግንስ … በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ እየተጠላላን ወዴት እየሔድን ነው ? ምንድን ነው እየሆነ ያለው?

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

አንድነት –በባህር ዳር የአንድነት/መኢአድ ደማቅ ቅስቀሳ

$
0
0

በዛሬው እለት 14/06/2006 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት በፍፁም ቁርጠኝነት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በቁጭት አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል።
aeup

bahir5

bahir6
በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ቢያደርግም የከተማዋ ነዋሪዎች የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን ህገወጥ ድርጊት አስቁመዋል፡፡ አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ ደምቋል፡፡ ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል፡፡ ህዝቡ ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፡፡

የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባላት ዛሬ ባህር ዳር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመኪና ከሚደረጉ ቅስቀሳዎች በተጨማሪ ፣ ሜጋፎን በመያዝ በርካታ አስተባባሪዎች በእግር ሕዝቡን እየቀሰቀሱ ሲሆን፣ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን ሕዝቡ እየተሻማ ነው እየወሰደ ያለዉ።

ኢሕአዴግ የራሱን በራሪ ወረቀቶችም እየበተነ ሲሆን፣ «ኢሕአዴግ ወረቀቶችን የመበተን፣ የሚነሳበትን ክስ የመከላከል ሙሉ መብት አለዉ» ያሉት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ፣ ሕዝቡ የሁለታችንንም ሰምቶ የመፍረድ አቅምና ችሎታ እንዳለውም ይናገራሉ። «እኛ የምንቃወመው፣ ሕገ መንግስታዊ መብታችን ተረግጦ ‘ሕዝቡን አትደርሱ፣ ሰልፍ አትዉጡ፣ ሕዝቡን አታስተምሩ …፤ ሕዝቡን ደግሞ ሰልፍ ከወጣህ እንዲህ ትሆናለን ፣ እንደዚያ ትሆናለህ .. እያሉ ሲያስፈራሩት ነዉ» ያሉት አቶ ሃብታሙ ለሕዝብ በሰላም አማራጭች ሲቀርቡለት ከማየት በላይ የሞኢአስይደስታቸው ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ።

በባህር ደር የተጀመረዉም ቅስቀሳ ከወዲሁም ከፍተኛ ዉጤቶችን አስመዝግቧል። ያለ ፍርሃት ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት መቻሉና የፍርህት ቀንበር መሰበሩ አንዱ ትልቁ ድል ነዉ። በተደረገው ቅስቀሳም ኢሕአዴግ ምላሽ እንዲሰጥ የተገደደበት ሁኔታም አለን። አቶ አልመነህ መኮንን በኢቲቪ ቀርበው እንዲታስተባብሉ መድረጉና እና ፣ ሕዝቡን ለማግባባት ወረቀቶች መበተናቸው ፣ የሕዝብ ዉስጣዊ ግፊት መጨመሩ የሚያመላክት ሌላዉ ሁለተኛ ድል ነዉ።

ቅስቀሳዉ በስፋት ዛሬ እና ነገ ይቀጥላል። የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊና ወሳኝ ነዉ። ባህር ዳር የምንገኝ ሁሉ፣ እንዉጣ፣ ድምጽችንን እናሰማ፣ ከየመንገዶቹ አረንግውዴ ቢጫ ቀይ ስንደቅ አላማችንን እያወለበለበን፣ «ተከበርሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሰ ይዉደም» እያልን ድምጻችንን አናሰማ። በባህር ዳር ርቀን ያለን፣ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ያለን፣ በሶሻል ሜዲያ ቅስቀሳ፣ በግንዘብ ድጋፍ፣ በጽፉህ፣ በምክር ድጋፋችንን እናሰማ።

የባህር ዳሩ ቅስቀሳ ተጀመረ እንጂ አላለቀም። ነገና ከነገር ወዲያ ከፍተኛ ርብርቦሾች መደረግ አለባቸው። አንድ ተብሎ ነው ወደ ሁለት የሚኬደው። የባህር ዳሩ ሰልፍ ካለፈም በኋላ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ክፍል ሁለት ይቀጥላል። ወደ ሌሎች ከተሞችም ይኬዳል። ይህ የዛሬው ትዉልድ፣ የኢትዮጵያዉያንም ትንሳኤን ያዉጃል!!!!
በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል እና ለማገዝ የሚከተሉት ይጎብኙ፡

የሚልየመን ድምጽ ለነጻነት ፌስቡክ ገጽ

https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖት ፌስ ቡክ ገጽ

https://www.facebook.com/FinoteNestanet

የአንድነት ፓርቲ ኦፊሴላዊ ድህረ ገጽ

http://www.andinet.org


አንድነት –የብአዴኑ አቶ አለምነው ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ለፍርድ መቅረብ አለበት (ብስራት ወልደሚካኤል)

$
0
0

የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን በግልፅ እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብ በመሳደቡ ያለምንም ማንገራገርና ማምታታት ይቅርታ ጠይቆ እራሱን ለፍርድ ማቅረብ አለበት፣ ማስተዋሉ ካለው፡፡ በርግጥ የኢህአዴግ መሪዎች የህዝብና የሀገር ክብር እንደሌላቸው ግልፅ ነው፡፡ ያው በትዕቢትና በጠመንጃ እንጂ አንዳቸውም ህዝባዊ ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው እንደማይመሩ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡

ነገር ግን እንደ አቶ አለምነው መኮንን በቆሸሸ አስተሳሰብ ህዝብን ያህል ነገር ባለጌ ስድብ የሚሳደብ አይደለም ህዝብን ቤተሰቡን የመምራት ብቃት አለው ብሎ ማመን ይቸግራል፤ ይበልጥ ለቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ አዘንኩላቸው፡፡

ብአዴን/ኢህአዴግም ቢሆን ምንም እንኳ ለህዝብ ክብር ኖሮት ባያውቅም አቶ አለምነው መኮንንን በአደባባይ ፍርድ በማቅረብና ከስራ በማሰናበት ተገቢውን ፍርድ ሰጥቶ ተፈፃሚ ማድረግ አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ አቶ አለምነውን እከላከላለሁ ብሎ የሚል ከሆነ እራሱ ብአዴን ህዝብን የመምራት ሞራል እንደሌለው አምኖ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ በኋላ ህዝብን የመምራት፣ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ፣….የሞራል ብቃቱ የለውም፡፡ ሰውዬው የሰደበው የአማራውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገራችንን ህዝብ ነውና፡፡ ህዝብን የሚንቅና የሚሳደብ በህገመንግስቱም ቢሆን ቅጣቱ ከባድ ነው፣ ህግ የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓት ባይኖረንም፡፡

ስለዚህ የእሁዱ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከህግም ሆነ ከማህበራዊ እሴት አንፃር ተገቢም ትክክልም ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉ የአካባቢው ሰው በሰልፉ ላይ በመታደም እንዲህ ዓይነት ትዕቢተኛ መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ የሞራል የበላይነት በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ቀጥሉበት ቢባል የሚበዛ አይሆንም፡፡

ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ግን በባህርዳር ከተማ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ምክንያቱም አቶ አለምነው መኮንን ላይ ገዥው ስርዓት እራሱ በግልፅ የእርምት እርምጃም ሆነ የይቅርታ ማስተባበያ ባለመስጠቱ ሁሉም ገዥውች ተመሳሳይ ንቀትና ትዕቢት እንዳላቸው የሚያመላክት ነውና፡፡ ህዝብን የናቀና የሚሳደብ ሰው ለሰከንድም ቢሆን ሊመራ አይገባም፣የሞራል ብቃቱም የለውም፡፡

ቦይንግ 767 –እገታ እና እንድምታው ክንፉ አሰፋ

$
0
0

አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ “ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?” ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሳምንት ዘ ሄግ ላይ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲነግሩን ጣል ያደረጓት ቀልድ ናት። የዚህች ቀልድ የፖለቲካ እንድምታ ቀላል አይደለም። መልእክትዋ ሲጠቃለል የኢትዮጵያን ህዝብ እየለቀቀ መሆኑን ትነግረናለች። እየከፋ የመጣው የኑሮውና የፖለቲካ ሁኔታ የህዝቡን አእምሮ ብቻ አይደለም እየነካው ያለው። ህዝቡ እየተገፋ ሃገርሩን ለቆ እንዲሰደድ እየተገደደም ይገኛል። በተለይ ደግሞ ሃገሪቱ በድህነት ያስተማረቻቸው ምሁሮችዋንና ባለሞያዎችዋን እንደዋዛ እያጣች ከመጣች እነሆ ሁለት አስርተ-ዓመታት ተቆጠሩ።
እለተ ሰኞ የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም.።

የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት የጣለው በኢትዮጵያዊው ፓይለት ጉዳይ ላይ ነበር። እንደዚህ አይነት ክስተት ሲፈጸም አዲስ አይደለም። ግን ይኽኛው ልዩ ነው። ይዘቱ ለየት ይበል እንጂ በ 1998 (እ.ኤ.አ.) ዩዋን ቢን በተባለ ቻይናዊ ፓይለት ከተፈጸመው ድርጊት ጋር ይመሳሰላል። የ30 አመቱ ወጣት የበረራ ቁጥር CA905 የሆነውን የቻይና አውሮፕላን በመያዝ የታይላንድን የአየር ጠረፍ ሰብሮ ገባ። የ27 አመት እድሜ ያላት ሚስቱን ይዞ ታይዋን ላይ ያረፈው ፓይለት ለዚያ አደገኛ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት የኢኮኖሚ ችግር ነበር። የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ጭማሪ፣ የመሳሰሉ ከራስ ወዳድነት ያላለፉ ጥያቄዎች በማንሳት የፓይለቱ የራሱን ክብር ዝቅ አደረገው።

በ 1995 (እ.ኤ.አ.) ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በግዳጅ ከአውስትራልያ ወደሃገሩ እንዲመለስ ተደረገ። ኢትዮጵያዊ ግን የኦሎምፒክ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ጀት ግሪክ ላይ ለመጥለፍ በመሞከሩ የአለምን ዜና ርእስ ሆኖ ነበር። ጋዜጠኛው የፕላስቲክ ቢላዋ የበረራ አስተናጋጅዋ አንገት ላይ በመደገን ወደ ሀገሩ እንዳይላክ ጥያቄ አቀረበ። በመጨረሻም ኢትዮጵያዊ ወገን ባደረገው ርብርብ የዚህ ወጣት አላማ ተሳካለት።

የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለየት የሚያደርገው ለዚህ ከባድ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት ነው። የግል ሳይሆን የሃገር፣ የራስ ሳይሆን የወገን ጉዳይ። ረዳት ፓይለቱን እብድ ያሰኘውም ይኸው ነገር ይመስለኛል። ሃይለመድህን የ40 ሺህ ብር ደሞዝተኛ ነው። በኑሮው ምንም የጎደለበት ነገር የለም። ከመካከለኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በላይ ይኖራል። የስደት ጥማት እንኳን ቢኖርበት ለመሰደድ በዚህ ሁኔታ አውሮፕላን ማገት እንደማይኖርበት ጠንቅቆ ያውቃል። ለዓለም ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልገው አንድ መልእክት ነበር። "ሜይዴይ... ሜይዴይ... የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ላይ ነው!"
ተልእኮው በሚገባ ተሳክቷል።

ሰኞ ማለዳ የመስርያቤታችን የውይይት ርእስ የነበረው ጄኔቭ ላይ ሳይታሰብ ያረፈው ቦይንግ 767 ጉዳይ ነበር። የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ታሪካዊ ውሳኔ የስራ ባልደረቦቼን ከሁለት ጫፍ ከፍሎ ለረጅም ውይይት ጋብዟቸውዋል። አንደኛው ወገን ፓይለቱ ያደረገው ጠለፋ ነው ብሎ ሲከራከር፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ድርጊቱ እንደጠለፋ መታየት የለበትም ይላል። የሁለቱን ወገን ክርክር እየሰማሁ ምንም ሳልተነፍስ ለረጅም ግዜ ቆየሁ። አእምሮዬ ግን አንድ ነገር ላይ ተጠምዶ ነበር። ክስተቱ ለፖለቲካ ደንታ የሌላቸውን እነዚህ ነጮች ማነጋገር መቻሉ እጅግ ደንቆኛል። "ወጣቱ ፓይለት ምን ያህል በደል ቢበዛበት ይሆን ለዚህ ካባድ ውሳኔ የበቃው?" የሚለው ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ይመላለስ የነበረ ጉዳይ ነው። አብዛኞቹ ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታ በደንብ እንዲረዱ ማድረጉም አልቀረም። ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል' ነውና ሁሉንም ነገር ለማስረዳት አሁን በጣም ቀላል ሆነ።

ሃይለመድህን አበራ 'እብድ ነው' የሚሉም አልጠፉም፤ ልክ እንደ አፈቀላጤው ሬድዋን። ለነጮቹ ነገሩ እንግዳ መሆኑ አልቀረም። ፓይለት ሆኖ፣ ጥሩ ኑሮ እየኖረ፣ ቤት- ንብረቱን፤ የሚወዳት ሃገሩንና ቤተሰቡን ትቶ ለእስራት፣ ለስደትና ለእንግልት ራስን ማዘጋጀት እብደት ነው ሊባል ይችላል።

በኢትዮጵያ ተመክሮም የፓይለት ሞያ ያስከብራል። በሃገራችን የፓይለቶች የኑሮ ደረጃ አንደኛውን ረድፍ ይይዛል። ይህንን የመሰለ ህይወት ጥሎ የስደትን ኑሮ መምረጥ የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ እብድ ቢያስብል የሚደንቅ አይደለም። የሚገርመው የስርዓቱ ካድሬዎች ይህንን አባባል መደጋገማቸው ነው። ከራሳቸውም አልፈው የፓይለቱ ቤተሰቦችን በማስፈራራት ይህንን እንዲመሰክሩ ሲያደርጉ ይታያል። ወትሮውን በእብዶች መሃል አንድ ጤነኛ ሰው ካለ፣ እሱ እብድ ነው። እነሱ በሰብአዊ መብት ላይ ሲቀልዱ በዚያ የማይተባበራቸው ሁሉ እብድ ነው። ለህሊናው ሳይሆን ለመኖር ሲል ሰበአዊ መብቱ ላይ የማደራደር ሁሉ ሽብርተኛ - አልያም የአእምሮ በሽተኛ ነው።

እብድ ሰው ያንን ግዙፍ አውሮፕላን በስርዓት አብርሮ፤ በስርዓት ካሳረፈ፤ በኢትዮጵያ ፓይለት ለመሆን የቅጥር መስፈርቱ እብድ መሆን ነው። ግና በአውሮፕላኑ የነበሩ 202 ተሳፋሪዎችን ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያውቁት ጄኔቭ ላይ ማረፋቸው ብቻ እነሱ የሚሉት ይጻረራል። ሃይለመድህን ዋናውን ፓይለት በሃይል አላስገደደውም። ተሳፋሪዎች እንዳይረበሹም ስለድርጊቱ አንዳች ነገር አልተነፈሰም።
ለባለስልጣናቱ ጥያቄ አለኝ። የሃይለመድህን እብድ መሆኑን እያወቁ ለምን ፓይለት አድርገው ቀጠሩት? የእሱ እብድ መሆኑ ለባለስልጣኖቹ እንዴት አሁን ታያቸው?
ያም ታባለ ይህ - የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. በስዊስ ላይ የተፈጠረው ነገር "ከሺ ቃላት... " እንደሚሉት አይነት ነው። አንዲት ትንሽ ድርጊት የአለምን ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ አነጋገረች። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት እና በአንዲት ቃል ብቻ ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ ሁሉ ለአለም አሳወቀ። ይህንን ለማድረግ ግን ራሱን መስዋዕት ማድረግ ነበረበት። ወጣቱ ሊደርስ የሚችልበትን ነገር ሁሉ አስቀድሞ ያውቀዋል። ከሃገር አመራረጥ ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች በሙሉ የተጠኑ እና በጥንቃቄ የተደረጉ መሆናቸውን ሂደቱ ራሱ ይመሰክራል።

ወጣቱ ፓይለት ሃገሩን ይወዳል። የልጅነት ህልሙን እውን ያደረገበትን የፓይለትነት ሙያም ያከብራል። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው። ራስ ወዳድ ቢሆን ኖሮ ፓይለት ሁሉ እንደሚኖረው በሃገሩ እየሰራ መኖር ይችላል። እንደ እብደት ያስቆጠረበት የዚህ ውሳኔ ምክንያቱ ግን ለህሊናው ብቻ ተገዥ መሆኑ ነው። ለሱ ቅርብ የሆኑትም ይህንኑ መስክረዋል።

በሃገራችን ሰርቶ የመኖር ዋስትና በአንባገነኖች እጅ ላይ ወድቋል። በነጻነት የመስራት፣ በነጻነት የመናገር፣ በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ...ወዘተ ዋስትና ሳይኖር የመኖር ትርጉሙ ምንድነው? ሰው ያለ ነጻነት ምንድነው? ለመኖርማ እንስሳትም እየበሉ ይተኛሉ እየተነሱም ይበላሉ - ከዛ ይተኛሉ። ከእንስሳ የሚለየን ነጻነታችን መሰለኝ። ያለ ነጻነት ህይወት ትርጉም የለውም።

በኢትዮጵያ 80 ሚሊየን ህዝብ ያለነጻነት ይኖራል። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት የዚህ ሁሉ ህዝብ ድምጽ ሆነ። የ80 ሚሊየን ህዝብ ድምጽ ሆኖ በራሱ ላይ መፍረድ መቻል ደግሞ እብደት ሳይሆን ጀግንነት ነው። አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለበት፣ ምን መናገር እንዳለበት...ወዘተ ሲወሰንት ለአንባገነኖች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ህሊናም ባርያ ይሆናል። በተለይ የራስ መተማመን እና የሙያው የተካነ ሰው ተገዥ የሚሆነው ለህሊናው ብቻ ነው። እንዲህ አይነቱ ሰው መብቱን ለድርድር አቅርቦ ራሱን በባርነት አያስገዛም። በመብቱ ላይ የሚደራደር ካለ ህሊናውን የሸጠ ሰው ብቻ ነው። ነጻነት የሚገዛ ውይንም የሚሸጥ ነገር አይደለም። ነጻነትን ሊገዛው የሚችለው ህሊናችን ብቻ ነው። ያለ እራሳችን መልካም ፈቃድ ደግሞ ማንም ሃይል ነጻነታችንን ሊደፍር አይቻለውም። ሰዎች በአካል ሊታሰሩ ይችሉ ይሆናል። የሰውን ህሊና ግን ማንም ሃይል ሊያስረው አይችልም። ኔልሰን ማንዴላ ለ27 አመታት ሲታሰር ህሊናው ነጻ ነበር። በአንጻሩ አሳሪዎቹ ነጮች የአካል ሳይሆን የህሊናቸው እስረኞች ነበሩ።
ሃይለመድህን የህዝብ ድምጽ በመሆን ከህሊናው ጋር የገጠመውን ሙግት ያሸነፈ ጀግና ነው። አላማው በውስጡ የቆሰለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ለአለም ለማሳወቅ ነበር። ይህ ባይሆን ኖሮ ችግር ውስጥ ያማያስገቡት ሌሎች ብዙ አማራጮች እና እድሎች ነበሩት። "ዘ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር" የተባለው ጋዜጣ የሃይለመድህንን ስደት መጠየቅ አስመልክቶ ባሰፈረው ዘገባ የኢህ አዴግ ስርአት ብልሹነትና የሰብአዊ መብት ረገጣው መባባሱን በስፋት ዘግቧል። ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም የሃገሪቱን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው እንዲመረምሩት አድርጓቸዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ሲነግሩን የኢአዴግ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ሃገሪቱን ወደ ጥርነፋ ፖለቲካ እና ቁምራ ኢኮኖሚ አሸጋግሯታል። ጥርነፋ እና ቁምራ አዲሶቹ ኢህአዲግኛ ቋንቋዎች ናቸው። ጥርነፋ ማለት አንድ ሰው አምስት ሰዎችን እየሰለለ በማገት ከገዥውፓርቲ አሰራር እንዳያፈነግጥ የማሰርያ ዘዴ ነው። ማንነትን የሚፈታተነው ይህ አሰራር አየር መንገድን ጨምሮ በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት ተግባራዊ እየሆነ መጥቷል።

ቁምራ ደግሞ ቁርስ፣ ምሳና ራት በአንድ ግዜ ማለት ነው። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ በአንድ ወቅት ሲጠየቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቴ በልቶ እንዲኖር ነበር ህልማቸው። እነሆ ዛሬ 70 በመቶው የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቱንም የእለት ምግብ አንድ ግዜ በቁምራ እንዲያጠቃልል አበቁት። 10ሺህ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚተዳደረው ከቦሌ አየር መንገድ እና ከሆቴሎች የሚጣል ቆሼ እየበላ ነው። በአንጻሩ ደግሞ እነ ስብሃት ነጋ ለአንዲት ጠርሙስ ሉዊስ ኮኛክ 260፣ 000 (ሁለት ሞቶ ስልሳ ሺህ ብር) ያወጣሉ። የ100 ሺህ ብር መጋረጃ ያለው፤ የ60 ሚሊየን ብር መኖርያ ቤት ውስት በሚዋኙ እጅግ ጥቂቶች እና ቆሻሻ እየተመገቡ በሚኖሩ ብዙሃን ወገኖች መሃል ያለው ክፍተት ይህ ነው አይባልም። ይህንን የኑሮ ሚዛን መዛባት የሚቃወመውን ስም ያወጡለታል። ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን ይህንን የሃብት ድልድል ለመቀበል ህሊናው የማይፈቅደውን ሁሉ "እብድ" የሚል ስም ይሰጡታል።

የ"እብዱ" ፓይለት ጉዳይ በህግ አይን ሲታይ ጠለፋ ሳይሆን እገታ ነው - የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ እንደገለፀው። እገታ እና ጠለፋ እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ድርጊቱ ጠለፋ ቢባል ኖሮ ቅጣቱም የከፋ ይሆናል። እገታም ቢሆን በስዊስ ህግ ከ3 እስክ 20 አመት ሊያስቀጣ ይችላል። የዳኝነት ስልጣኑም ያለው አውሮፕላኑ በግዛቷ ያረፈበት የስዊዘርላንድ ፌዴራል መንግስት ላይ ነው። ለግዜው ሃይለመድህን አበራን አግኝቶ ማነጋገር ስለማይቻል ወጣቱን ያቆሰለው ጉዳይ ላይ ከዚህ የበለጠ ማለት አይቻልም። የአቃቤ-ህጉ ምርመራውን እንዳበቃ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ያን ግዜ የበለጠ መረጃ ይኖራል።
ኢትዮጵያዊ ወገን በሙሉ፣ ራሱን አሳልፎ ለሰጠው ለዚህ ፓይለት ባገኘው መንገድ ሁሉ ድጋፉን መግለጽ ይጠበቅበታል።

ሰበር ዜና!! አንድነት ለትግል በወጣበት የመድረክ አባል ፓርቲዎች አገዱት- ፍኖተ ነጻነት

$
0
0

“አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው” የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተክሌ በቀለ

መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ማገዳቸውን ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው የመድረኩ 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ አሳውቀዋል፡፡ በጉባኤው አንድነትን ወክለው የተሳተፉት መካከል የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ ለፍኖተ ነጻነት እንዳስታወቁት የመድረክ አባል ፓርቲ የሆኑት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና በፕ/ር በየነ የሚመራው የኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ አንድነት ከመድረክ እንዲባረር ቢጠይቁም አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ አንድነት ላልተወሰነ እንዲታገድ የሚል ሞሽን አቅርቦ በጉባኤው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
አቶ ተክሌ በቀለ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑባቸው ምክንያዎች አስገራሚ መሆናቸውን ጠቅሰው “የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑት በቅርቡ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አንድነት መድረክ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈፀም መወሰኑን፣ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮችም ውህደት እንደሚያስፈልግ በተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸውን፣ የአንድነት ፓርቲ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ድጋፍ ሰጪዎች በመድረክ ስም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ትብብር አያደርጉም በሚልና ከመድረክ ዕውቅና ውጪ መስከረም 19(ሰላማዊ ሰልፉ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ነው፡፡) በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡” የሚሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተክሌ መድረክ የራሱን ዕቅድ አውጥቶ በቁርጠኝነት የማይሰራ በመሆኑ አንድነት በተናጠልና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን መስራቱን ጠቅሰው “በተደጋጋሚ ለመድረክ በዕቅድ የተደገፉ እንቅስቃሴዎችን በማቅረብ በጋራ እንዲሰራ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አግኝቶ አያውቅም፡፡ ይልቁኑም የራሱን ጥፋት በአንድነት ላይ ለማላከክ ይሞክራል ” ብለዋል፡፡

ነገ አንድነትና መኢአድ በባህር ዳር የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የመድረክን ውሳኔ አስመልክተው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት “ መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” ካሉ በኋላ “አንድነት የታገደው ውጤታማ ስራ ስለሰራና በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ እና በተመሳሳይ ስራዎች የተቀዛቀዘውን የሰላማዊ ትግል በማነቃቃት ትግሉን ወደ ህዝብ ስላወረደ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አክለውም “መድረክ ውስጥ ካሉት ፓርቲዎች የተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አረና ብቻ ነው፤ የዛሬው ውሳኔ አረናም በቅርቡ የአንድነት እጣ እንደሚገጥመው አመልካች ነው፡፡” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ “መድረክ እንደዚህ ያለ እገዳ ከመወሰን ይልቅ አንድነትና አረና የጠየቁትን ውህደት ተቀብሎ ፖለቲካውን በአንድ ላይ ማንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስገኝ አንድነት ያምናል፡፡ ስለዚህ መድረክ የወሰነውን ውሳኔ እንደገና አጢኖ የሀገራችንን ፖሊቲካ በውህደት አብረን እንድንመራ እንዲያደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡UDJ

አንድነት –የባህር ዳር ሰልፍን በተመለከተ የዛሬ የካቲት 15 ዉሎ

$
0
0

አንድነት – የባህር ዳር ሰልፍን በተመለከተ የዛሬ የካቲት 15 ዉሎ

- የባህር ዳር፣\ ሰልፍ ተሟሙቆ ዋለ
- የአመራር አባላትን በሆቴል ቤታቸዉ እንገድላቹሃለን እየተባሉ ነው
- ከባህር ዳር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴውን እዬትቀላቀሉ ነው
- 10 ድርጅቶች ስብስብ የሆነው የትብብር አመራሮች መኢአድ እና አንድነት ተቀላቅለው እየቀሰቀሱ ነው
bahir_dar1

bahird_Dar2

የባህር ዳር ሰልፍ ነገ የካቲኡት 16 ቀን ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀመሮ ይደረጋል። « ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል» በሚል የተዘጋጀው ፍላየር ሰልፉ የሰልፉ መነሻ፡- ግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 የሚገኘው አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሰልፉ የጉዞ መስመር፡- ከግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 ተነስቶ በድብ አንበሳ ዞሮ ወደ ክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት

በባህር ዳር አጎራባች ይልማና ዴነሳ ወረዳ፣ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢና ሁለት አመራሮች ለእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ በማስተባበራቸው ታሰሩ፤ ሌሎቹን አመራሮችም ለማሰር አሰሳ እያደረገ ነው፡፡

ነገ የካቲት 16 በባህር ዳር ከተማ ብአዴንንና አመራሮቹን በመቃወም በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የባህር ዳር አጎራባች አካባቢ ነዋሪዎችም ለመሳተፍ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፣ የአንድነት ፓርቲ የይልማና ዴንሳ ወረዳ አመራሮች ህዝቡን በማስተባበርና አስፈላጊውን መረጃ ሲያደርሱ ሰንብተዋል፡፡

ህዝቡ በብአዴን ላይ እያሳየ የመጣው ቁጣ ያሳሰባቸው የአዴትና የአካባቢው ባለስልጣናትም ሁሉም የወረዳው የአንድነት አመራሮችን በሙሉ ለማሰር እርምጃ ጀምረዋል፤ በዚሁም መሰረት የወረዳው የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ይሁኔ ዘለቀ ትላንት ማታ የታሰሩ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ አቶ ጌታቸው መስፍን እና አቶ ብሩክ ትዕዛዙ ታስረዋል፡፡

እስሩን ከምንም ያልቆጠሩት የአንድነት አመራሮችም ህዝቡን ለሰልፍ ማስተባበራቸውን ቀጥለዋል፤ የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳዎች ነዋሪዎችም ለሰልፉ መዘጋጀታቸውን እየገለፁ ነው፡፡

ወደ ባህር ዳር ከተማ ስንመለ፣ የአንድነት፣የመኢአድ እና የትብርር ለዲሞክራሲ አመራሮች ቀስቃሽ ወረቀት በመበተን ላይ ናቸው፤ ህዝቡን አጅቧቸው ቅስቀሳውን አድምቆታል፡፡

የአንድነት ፕሪዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባለት፣ በባህርዳር ጎዳናዎች ላይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን በዚያ ለበርካታ ቀናት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አባላትን እና ደጋፊዎች ጎን የቅስቀሳ ተግባራት ላት ተሰማርተዉ ነበር።

ብሕአዴን/ኢሓዴግ ግን የነገዉን ሰልፍ ለማጨናገፍ እያደረጋ ያለውን ወከባና እንግልት ግን አላቆመም። በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 በሚገኘው ሰን ራይዝ ሆቴል ያረፉት የአንድነት እና የመኢአድ የቅስቀሳ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግስት የደህንነት አባላት ወከባ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ስድስት የመንግስት ደህንነቶች የታጠቁትን መሳሪያ በማውጣት እንገላችኋለን በማለት የቅስቀሳ ቡድኑን አባላት ለማዋከብና ልከማስፈራራት ትረት አደርገዋል።

የሆቴሉን ሰራተኞችንም፣ አልጋ የያዙ ግለሰቦችን መታወቂያ አምጡ በማለት ግርግር ለማስነሳት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ለፖሊስ በመደወልም «በአንድነት አባላት ተደብድበናል፤ ፎቶም ተነስተናል» በማለት ሀይል እንዲጨመርላቸው ጠይቀዋል።

ትብብር ለዲሞክራሲ አመራሮች ከመኢአድ እና አንድነት ጋር በባህር ዳር እየቀሰቀሱ ናቸው

$
0
0

የአሥር ድርጅቶች ስብስበ የሆነው ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አመራር አባላት ከመኢአድ እና አንድነት ጋር በመሆን በባህር ዳር ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመልክታል።

የትብብሩ መስራች ድርጅቶች ዉስጥ የሐዲያ ብሔር አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፣የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፣ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የከምባታ ሕዝቦች ኮንግሬስ ፣ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት፣ የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ይገኙበታል።

የባህር ዳሩን ሰልፍ መኢአድ እና አንድነት በጋራ ከመስራታቸውም ባሻገር ፣ ሌሎች ድርጅቶችን ማሳተፋቸው ፣ በራሱ ትልቅ ዉጤት መሆኑን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። በተለይም ድርጅቶች በወረቀት ላይ ሳይሆን፣ በሥራ ትብብራቸውን ማሳየታቸዉ ሕዝብ በተቃዋሚዎች ላይ ያለዉን አመኔታ የበለጠ እንዲጨምር የሚያደርግ ነው።

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>