Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬዎች ጋጋታና ሽብር አይገታውም በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ደጋፊዎች


አረና –አረና በሕወሃት የሽብር ተግባር አያትጠፍም (መግለጫ)

$
0
0

ዓረና ትግራይ ራኢዩን የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ በማድረግ ወደፊት ይገሰግሳል እንጂ በህወሓት የሽብር ተግባር አይታጠፍም !!! (ከዓረና ትግራይ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

የዓረና ትግራይ 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ ከተሞች ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች በማካሄድ በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር ምንጩና መፍትሄው፣ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፖለቲካ ራኢና ኣማራጭ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የማስቀረት ብቃት ለማሣየት አስመልክቶ ከህዝብ ለመምከርና በትግራይ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ከመጀመርያው የጥቅምት ወር 2006 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ተጀመረ። ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባው በቅደም ተከተላቸው በውቕሮ፣ በማይጨው፣ በዓብይ ዓዲ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ሲካሄዱ ህዝብ ወደ ስብሰባው እንዳይመጣ የማደናቀፍ ተግባር በገዢ ፓርቲው የአከባቢ ካድሬዎች የታየ ቢሆንም ህዝቡ የማዳመጥ ፣አስተያየት የመስጠት መብቱን ለመጠቀም ባሳየው ፍላጎት በስብሰባው አዳራሽ በመገኘቱ ውጤታማ የህዝብ ስብሰባዎች ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በሽረ ከተማ የህዝብ ስብሰባ ለማካሄድ ህዝቡ ወደ ስብሰባ ኣዳራሽ እንዲመጣ በሚገባ ከተቀሰቀሰ ህዝቡም ጥሪውን ኣክብሮ ወደ ኣዳራሹ በጥዋቱ እንደመጣ የከተማው ኣስተዳደርና በፓርቲው መዋቅር በተደራጀ ረብሻ የህዝብ ስብሰባው ሳይካሄድ መቅረቱን ይታወሳል፡፡ በዕቅዱ መሰረት ፓርቲያችን በምስራቃዊ ዞን ዋና በዓዲግራት ከተማ ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባ ለማካሄድ ኣዳራሽ እንዲሰጠን ለከተማው ኣስተዳደር ተጠይቆ ኣዳራሽ ተይዞኧል ኣይቻልም የሚል መልስ በመስጠታቸው እንግዲያው ስብሰባው በኣደባባይ እናደርገዋለን ሲባሉ ተመልሰው ኣዳራሽ ተፈቅዶላችኃል የሚል ምላሽ ተስጥቶን በስብሰባው ቀን ህዝቡ ተገኝቶ ዓረና ባዘጋጀው ኣጀንዳ እንዲመክር ለማስቻል የዓረና ከፍተኛ ወጣት ኣመራሮችና ኣባሎች በዓዲግራት ከተማና ኣከባቢዋ ተሰማርተው በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ ሃሳብነ በነፃ የመግለፅና የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንቀሳቀሰ ነፃነት የሚያረጋግጡ መብቶች በመጠቀም በህዝባዊ ስብሰባው የሚመክርባቸው ኣጀንዳዎችና የስብሰባው ቀን፣ ስዓትና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ በማደል ተሰማርተዋል፡፡

ለህዝቡ የሚታደለው ፅሑፍ የሚፈነዳ ቦንብ ኣልነበረም ወደ ህዝቡ ህሊና ዘልቆ የሚገባ ሓሳብ ብቻ ነበር፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ዓረና ትግራይ የመሬት ባለቤትነት የመንግስት መሆኑ ቀርቶ የህዝብ/ዜጎች እንዲሆን የመሬት ሊዝ ኣዋጅ እንዲሻር፣ ዜጎች ለመኖርያ የሚስፈልጋቸው ቦታ በሕገ መንግስቱ መሰረት ያለ ሊዝ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ ለወጣት ሴቶችና ወንዶች በግፍ ለስደት መዳረግ ምክንያት የሆነው ብልሹ ኣስተዳደር በማስወገድ በሃገራቸው ሥራ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ የሙያ ብቃት መስፈርት መሰረት ባደረገ መርህና የሙያና የኣካዳሚ ነፃነት በማረጋገጥ የመመህራንና የመንግስት ሠራተኞች ችግር ለማስወገድ እንደምንሰራ፣ በኣስገዳጅ የማዳበርያ ግዢ ለገዢው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብዝበዛ የተጋለጡና በእዳ ተጭነው ለጎስቋላ ኑሮ የተዳረጉት የትግራይ ገበሬዎች ችግር ለማስወገድ የማደባርያ ግዢ በውዴታ እንደሚሆንና ግብርናውና ገበሬው ለመደገፍ ለገበሬው ድጎማ ማድረግ እንደማያስፈልግ፣ ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ እንደሚሆኑ ዋና ስራቸው የፓርቲ ኣባል ምልመላና በትምህርት ቤቶች ለሚነሱ የመብት ጥያቂዎች ማኮላሸት የሆነ የህ.ወ.ሓ.ት (ኢህኣደግ) የ 1-5 የትምህርት ኔትወርክ እንደሚቀር፣ በትግራይ ህዝብ ደምና ኣጥንት የተገኘው ሙሉ በሙሉ የትግራይ ህዝብ ሃብትና ንብረት የሆነው ት.እ.ም.ት ከህወሓት መንጋጋ ኣውጥቶ ተጠሪነቱ ለክልሉ መንግስት በሆነ በነፃ የባለሙያ ቦርድ እንዲተዳደር በማድረግ የክልሉን ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እነዲውል የማደረግ መሆኑ፣ በት.እ.ም.ት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሠርተው የሚያገኙት ትርፍ በትግሉ ለተጎዱ ታጋዮችና ሲቭል ኣርበኞች እንዲሁ የሻዕብያን ወራራ ለመመከትና ሃገራቸውን ለመጠበቅ ለጉዳት የተዳረጉ ኣርበኞችና ቤተሰባቸውን ለመደገፍ እንደሚውል፣በሕገ-መንግስቱ እንደተደነገገው ገዢው ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲያቆም የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ እነዚህ የአማራጭ ፖለቲካዊ ፕሮግራም ኣጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ሓሰቦች እንጂ የሚፈነዱ ፈንጂዎች ኣልነበሩም ! እነዚህ በጠራራው ፀሃይ ለህዝቡና ለህ.ወ.ሓ.ት ኣባላትና ደጋፊዎች ጭምር የቀረቡ ኣጀንዳዎች ነበሩ፡፡

እነዚህ ለህዝቡ የቀረቡ የአማራጭ ፖሊሲ ኣጀንዳዎች በሳዕሲዕ ፃዕዳ እንባ ወረዳ ዋና ከተማ ዕዳጋ ሓሙስ ለህዝቡ ሲታደሉ አንዲት ወረቀት ሳትቀደድ ኣንድ ሰው እንኳን ኣልቀበልም ሳይል ሁሉም በደስታ ተቀብሎ ለወጣት ኣመራሮቹ በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ሙሩቕና የዓረና የሥራ ኣስፈፃሚ ኣባልና የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴና መም/ ሃይለ ገብረፃዲቕ ያሳየው አክብሮት የሚደነቅ እንደነበረ ይመሰክሩለታል፡፡ በሻዕብያ የወደመችው የጎሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ የነበረችው ውብዋ ዛላንበሳን በመተካት የከተመችው የፋፃ ከተማ ነዋሪዎችና የኣካባቢው ገበሬዎች የስብሰባው ኣጀንዳ፣ ጊዜና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ ሲታደላቸው ህዝቡ በሰላም ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ” ቀድመን መመጣታችሁ ብናውቅ ኖሮ ሻይ ቁርስ ኣዘጋጅተን እነቆይ ነበር” በማለት በኣክብሮት እንደተቀበላቸው በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅና የዓረና ትግራይ የድርጅት ጉዳይና የፅሕፈት ቤት ሓላፊ የሆኑት ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ ና ኣቶ ሃይለኪሮስ ተፈሪ የህዝቡ ጨዋነት እንግዳ ተቀባይነትና ለኣማራጭ ሓሳብ ያለው ጥማት ይመሰክሩለታል፡፡ የዓዲግራት ከተማ ህዝብ ኣቀባበልም ተመሣሣይ ነበር፡፡

የህዝቡን የልብ ትርታ ያለማራቸው የዘኑ የገዢው ፓርቲ ኣስተዳዳሪዎች ዓረናና ህዝቡ የማይገናኙበት፣ የህዝቡ ስብሰባ የማካሄድበትና የዓረና ወጣት ኣመራሮች ሞራላቸው ተጎድቶ የሚያርፍበት እኩይ ብልሃት መዘየድ ጀመሩ፡፡ በዕዳጋ ሓሙስ የህ.ወ.ሓ.ት መታወቅያቸውን በማሣየት ለህዝቡ የስብሰባ ጥሪ የሚያድሉ የዓረና ኣባላትን ማቆም ጀመሩ፤ በፓርቲ መታወቅያ የመንግስት ሥራ መስራት ኣትችሉም ሲባሉ ሁሉም በእጃቸው ሁሉም በደጃቸው የሆነላቸው የህወሓት አባላቱ ወድያው ፖሊስ ጠርተው የዓረና ኣባላትን ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴንና መም/ሃይለ ገ/ፃድቅን ወደ ፖሊስ ጣብያ በእስር ወሰዱ፡፡ አባላቶቻችን መታወቅያቸውን እንዲያሳዩ ተጠየቁ ኣሳዩ፡፡
(1) መመ/ሃይለ ገ/ፃድቅ የዓረና መታወቅያ ስለሌህ የዓረና ፅሑፍ ማደል ኣትችልም ተባለ
(2) የሚታደሉት ፅሑፍ የዓረና ማህተም ስለሌለው ለህዝብ መሰጠት ኣትችሉም ተባሉ
(3) ፅሑፍ እያደላችሁ የመኪና መንገድ ትዘጋላችሁ ኣሉ የህወሓት ካድሬዎቹ በድፍረት !

በስንት ንትርክ ለሚያጋጥማቹሁ አደጋ በራሳችሁ ሓላፊነት ተብለው ሥራቸውን ቀጠሉ፡፡ በራሳችሁ ሓላፊነት? ሲባል ብትደበደቡ ብትዋረዱ ብትገደሉ የሕግ ከላላ ኣንሰጥም ማለት ነበር፡፡ ያለምንም እንከን ህዝቡ በሰጣቸው ሞራል ስራቸውን በሚገባ ፈፅመው በደስታ ወደ ዓዲግራት ተመለሱ። ይህ የሆነው ዕለት ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም ነበር፡፡ በዓዲግራት ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና ኣቶ ኣብርሃ ደስታ እንዲሁም መም/ፍፁም ግሩምና መመ/ገዛኢ ንጉሰ ኢሉ፡፡ ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም የስብሰባ ጥሪ የሚገልፀው ፅሑፍ በዓዲግራት ማደል ማደል ተጀምረዋል፡፡ ዕለተ ዓርብ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም የዓዲግራት ከተማ ሰፊ በመሆኑ ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ፣ ኣቶ ሃይለኪሮስ፣ መም/ገዛኢ ንጉሰ፣ መመ/ፍፁም ግሩም በቀበሌ 01 ሲንቀሳቀሱ ህዝቡ ምግብና ውሃ እየሰጠ የስብሰባው ጥሪ እየተቀበለ በክብር እንዳስተናገዳቸው ይመሰክራሉ።

ይህንኑ እውነት እየተከታተሉ ይታዘቡ የነበሩ የጥፋት መልእክተኞች የዓረና መመራርና ኣባላት ለማወክ ተዘጋጅተው ኖረው የስብሰባው ጥሪ ለህዝቡ የሚያድሉ ወደ ሆስፒታል ኣከባቢ ሲደርሱ የቀበሌ ካድረ የሆኑ ሴቶች ወረቀቱን ተቀብለው መቅደድ ጀመሩ፡፡ ዕድሜኣቸው ከ12-16 ዓመት እንደሆኑ የሚገመቱ ህፃናትም መሰብሰብ ጀመሩ ሆ! እያሉ መረበሽ ጀመሩ፣ ሴቶቹ መብታቸው በማለት አደፋፈሩ። የማወክ መብት? ህፃናቱ የተላኩ እንጂ የራሳቸው ኣጀንዳ የሌላቸው መሆኑ በተግባር ለመፈተን የወዳደቁ የስኳርና የቡና መጠቃለያ የደብተርና የጋዜጣ ፅሑፎች ሲሰጣቸው የዓረና ፅሑፍ መስሎአቸው ሳያዩት ተቀብለው ወድያው ይቀዱታል ልክ የስብሰባው መጥሪያ ፅሑፍ ተቀብለው እንደቀደዱት፡፡ ለህፃናቱ መብታችሁ ነው እያሉ የሚያጅቡ ትላልቅ ወንዶችና ሴቶችም ነበሩበት ። ህፃናቱ ሁሉም ሊባል በሚችል ሲጋራ ያጤሳሉ ፣ ስትቀርባቸው መጠጥ መውሰዳቸው የሚሳውቅባቸው በእጅጉ ጠጅ ይሸቱ ነበር። የአከባቢው ሰዎች በሰጡት መረጃ መሰረት የተለያየ ሱስ ተጠቃሚዎች ለመሆናቸው በከተማው ፖሊስ የሚታወቁ ናቸው።በዚህ የውንብድና ተግባር በዓረና ከፍተኛ ወጣት አመራሮችና አባሎች የአካልና የሞራል ጉዳት ተፈፅሞአል ፣ የቀበሌ ሴቶች በፌስታል አፈር እያቀበሉ ህፃናቱ በአዓረና አባላት በላያቸው ላይ አፈር በማፍሰስና እክታ በመትፋት አሳፋሪ ወንጀል ሲፈፀም በዓዲግራት ከተማ የሚገኙት የከተማው አስተዳደርና ፖሊስ የዞኑ አስተዳደርና ፖሊስ መብታቸው ነው እያሉ ያሳዩት የወንጀል መተባበር አሳፈፋሪ ተግባርና መንግስታዊ ውንብድና የሚያሰኝ ነው።

በዛው ጨዋ ህዝብ ፊት እነደዚህ ያለ የውንብድና ተግባር ተፈፀመ፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ተግባሩ የተቀነባበረው በዞኑ በከተማው መስተዳድር ስለመሆኑ ኣስተዳዳሪዎች፣ ፖሊስ ያሳዩት ተግባራቸው ይመሰክርላቸዋል፡፡

በነዚህ ጥቂት ቀናት የዞኑ መስተዳድር የፀጥታ ኣደጋነቱን በተግባር ሲያስመሰክር ህዝቡ ደግሞ የሕግ ኣስከባሪነት ሚናው መወጣቱን በገሃዱ ዓለም ቁጭ ብሎ ታይቶኣል፡፡ መስተዳደሩ በራሳችሁ ሃላፊነት የህግ ከለላ ኣንሰጣችሁም ሲል በዓረና ኣመራሮችና ኣባላቶች ሊያወርዱት የከጅሉት ወንጀል ጠቋሚ ነበር። የህዝብ ስብሰባው እንዳይካሄድ የተፈጠረው ውንብድና የመስተዳድሩ እጅ እንዳለበት የሚያሳየው -የዞኑና የከተማው መስተዳደርና ፖሊሲ በኣባሎቻችን የተፈፀመውን በዓይናቸው ያዩት ወንጀል ማጠራትና ማስቆም ሲገባቸው ፍርደ ገምድል እንዲሉ በሞባይል ስልክና፣በካሜራ ቀርፃችሁናል ህፃናቱም ቀርፃችሁኣል ትፈተሻላችሁ ብለው የሁሉም አባሎቻችን ሞቫይልና ካሜራ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ መቦርበራቸው፣ በተደራጀና በህፃናት ከለላ የተደበቀ የወንብድና ተግባር ሲፈፀም መስተዳደሩና ፖሊሱ እያዩ በጠራራ ፀሃይ በኣባላቶቻችን ላይ ኣሰቃቂ ግፍ እነዲፈፅሙ ሙሉ ፍቃድ ማሳየታቸው የሚያስቆጥራቸው በመሆኑ ፣በሕግ የተቋቋመ ፓርቲ የቆመለትን ራኢና ፖሊሲ ለህዝቡ ለማስተዋወቅና በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የሚገራበት መንገድ ከህዝቡ ለመምከር ያደረግነው ጥሪ እንዳይሳካ ለማወክ የተላኩ ህፃናት መብታቸው ነው እያሉ የሕገ-ወጥ ተግባር ከለላ መስጠታቸውና ለባሰ ጥፋት እንዲዘጋጁ ማበረታታቸው የወንጀሉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸው መሆኑንየከተማ ፖሊስ የኣረና ኣባላት ባረፉበት ሆቴል ማታ አልጋ በያዙበት ሆቴል ከምሽቱ 4፣00 ሰዓት ተገኝቶ እሁድ ለሚካሄደው ስብሰባ የእግር ኳስ፣ የብስከሌታ ውድድር ስላለ በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለቱ ስብሰባው እንዳይካሄድ በማደናቀፍ ምክንያት መሆኑን በተደራጀ ወንብድና የኣካል ጉዳት የደረሰባቸው የኣረና ኣባላት በከተማው ጤና ጣብያ ተመርምረው የራጀ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸውና ሆስፒታል እንዲወሰዱ በሃኪም የተሰጠ ትእዛዝ በፖሊስ ኣለመፈፀሙን፣ የተፈፀመው የወንብድና ተግባር ለማድበስበስ በሃሰት ክስ፣ በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና መም/ፍፁም ግሩም የተቀነባበረው ወንጀላ እየተፈፀመ መሆኑን ነው ።

ህ.ወ.ሓ.ትና መስተዳድሩ ወደዚህ የፖለቲካ ቅሌት የሚገፋፋቸው ያለው በዓረና የኣማራጭ ፖሊሲ ልዕልና መርበትበቱንና ወደ እራቆቱ የወጣ በጠራራ ፀሃይ የኣማራጭ ፓርቲ ወጣት መሪዎችን በማፈን ማንበርከክ መምረጡንና የትግራይ ህዝብና ወጣት ልጆቹ የከፈሉት መስዋእትነት ጭራሽ ከምድረ ትግራይ ጠራርጎ ለማጥፋት መቑረጡን የሚያሳይ እኩይ ተግባር በመሆኑ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የተቃውሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለትግራይ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሰማል፡፡ ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ የከፈለው የ17 ዓመታት የትግል ዘመን ብህ.ወ.ሓ.ት ተቀብሮ እንዳይቀር በማደስ የተነሳ ፓርቲ እንደመሆኑ በህ.ወ.ሓ.ት የሽብር ተግባር የማይታጠፍ መሆኑን በማረጋገጥ በህዝባችን ፊት የሚከፈለውን ሁሉ መስዋእትነት እየከፈልን ብፅናት የምንቀጥልበት መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል፡፡

የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች የተደረጁ ኣሸባሪ ወንጀለኞችን በመመከት የኣባለቶቻችን ህይወት ለመታደግ ያሳየው ድፍረት እንዲሁም የዕዳጋ ሓሙስ ከተማ ነዋሪዎችና የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች ዓረና ለህዝቡ የቀረበው ጥሪ በማክበር ያሳያችሁት ኣክብሮትና ፍላጎት ኣክብሮታችን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ዓረና ትግራይ ፓርቲ በዚሁ የወንብድና ተግባር ሳይንበረከክ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ህዝብ በኣጠቃላይና በዓዲግራትና ኣከባቢዋ የህዝብ ስብሰባ በመጥራት ከህዝቡ መምከር በፅናት እንደንቀጥልበት በእርግጠኝነት ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም
መቐለ

ጌዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? ቁጥር ሁለት በአለማየሁ መሰለ

ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ በሴቢሴ ሬድዮ ያደረጉት ቃለ ምልልስ

አቡጊዳ –ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ የጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ !

$
0
0

በከፍተኛ ወከባ ዉስጥ ቢኮንም፣ የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር መስቀል አደበባይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ዘገባዎች ገለጹ። የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ የተጠራው ሰልፍ ፣ ከበላይ በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት፣ ፖሊሶች መንገዶችን እየዘጉ ሕዝብ እንዳይቀላቀል ቢያደርጉም፣ በርካታ ሕዝብ፣ የነበሩ መሰናክሎችን ሁሉ እያለፈ፣ በሰልፉ ተገኝቷል።

«ተከበርሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም ፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይወደም» እያሉ ሰልፈኞች በመዘፈን በአገር ዳር ድንበር ጉዳይ ቀልድ እንደሌላ ያሳወቁት።

ይህ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ ሰልፍ በጎንደር ሁለተኛው ሰልፍ መሆኑ ነዉ። ከአራት ወራት በፊት በሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ ዘመቻ ወቅት፣ የአንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ከ40 ሺሆች በላይ መስቀል አደባባይን ማጥለቅለቃቸው የሚታወቅ ነዉ።

ሚኒሊክ ሳልሳዊ በስፋት የዘገበዉን ለማንበብ እዚህ ጋር ይጫኑ !

የአቶ አለምነው መኮነን ጭንቅላት ወይንም ጭንቅላት አልባነት ! አንዱ ዓለም ተፈራ

$
0
0

በዕርግጥ የአንድን የሀገራችን ክፍል ነዋሪዎች ጉዳይ አንስቶ በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ መንገድ መነጋገር፤ ወደድንም ጠላንም፤ ያለንበት ዘመን ግዴታ ሆኗል። ትናንት አኝዋኮች ተረሸኑ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን ተከበው ተሰቃዩ፣ ኦሮሞዎች በእስር ቤት ታጎሩ እያልን እንደጮህን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በአማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደል አንስተን መነጋገር ግዴታችን ሆኗል። የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲህ ሆኑ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲያ ሆኑ ስንል ብዙ ዓመታት ቆጠርን።በማይዘነጋ መንገድ ደግሞ እያንዳንዱን ለይተን እያነሳን፤ ይኼኛውን ብቻ የሚያደርጉ የዚህኛው ክፍል ብቻ ተወላጆችና ለዚያ ክፍል ብቻ ተቆርቋሪዎች ተደርጎ ስለሚወሰድ፤ እያንዳንዱን ጉዳይ “ለሌሎች” መተውና ጠቅላላ ኢትዮጵያዊንን በሚነኩ ጉዳዮች ላይ ብቻ መቆም፤ የታጋይነት ምልክት ተደርጎ የተወሰደ ፈሊጥ ሆኗል። እኔ ይኼን ትክክል ብዬ አልወስደውም። ለእያንዳንዱ ጉዳይ ቆሜ እቆጠራለሁ።

በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራና በዚያ ብቻ ሀገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎዬን የምለካ ስለሆነ፤ ይህ ጉዳይ ከአእምሮዪ ውጪ ነው። አማራው አማራ በመሆኑ ብቻ ለሚደርስበት በደል መቆርቆር፤ የግድ ከአማራ መወለድ አለበት የሚል ካለ፤ ዘረኛ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ አያምንም። ለአማራው የሚቆረቆረውን ሁሉ ደግሞ ትምክህተኛ አማራ የሚል ሁሉ፤ ዘረኛ ነው። አማራን ይጠላል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰውን በደል የኔ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ ነኝ ባይ፤ ባይ እንጂ ኢትዮጵያዊ ታጋይ ነኝ ሊል አይገባውም። በአኝዋኩ ወገናችን፣ በኦሮሞው ወገናችን፣ በአማራው ወገናችን፣ በኦጋዴኑ ወገናችን የሚደርሰው በደል፤ የእያንዳንዳችን በደል ነው ብለን መውሰድ ካልቻልንና፤ የአንዱን ወገን በደል ብቻ ይዘን የምናቅራራ ከሆነ፤ ውሸታምና ዘረኛ ለመሆናችን ሌላ መረጃ አያስፈልግም። በዚህ ጽሑፍ፤ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት እና የብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የተናገሩት፤ ምን ያህል ፀረ-ኢትዮጵያና፤ ውሃው የተቀዳበት ምንጭ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ፓርቲና መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ እንደሆነ አሰምራለሁ። እናም ደግሞ ይህ አደገኛ መርዝ፤ ጠንከኛነቱን አሳያለሁ።

በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ገዢ ቡድን የፖለቲካ ስሌት፥ አማራውን ማጥቃት፤ ከሥር መሠረቱ ሲፈጠር ምሰሶዬ ብሎ የያዘው የትግል ምሰሶው ነው። ቀጥሎም የመንግትነቱን ካባ ካጠለቀ ወዲህ፤ ከራሱ አልፎ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሥልጣን መቆናጠጫ ዋና መሰላሉ፤ ይኼን መቀበልና መተግበር ሆኗል። ይህ ደግሞ ከአማራው ወገን ተወለድን ለሚሉትም ሆነ ከአማራው ወገን አልተወለድንም ለሚሉት ሁሉ የሚሠራ መለኪያ ሚዛን ነው። አንድ ጭንቅላት ብቻ ነው ያለው፤ የገዢው ቡድን ጭንቅላት። ስለዚህ አቶ አለምነው መኮነን ተናገሩት ወይንም አቶ ደሳለኝ ሀይለ ማርያም ተናገሩት ለውጥ የለውም። ሁሉም አፋቸው እንጂ ጭንቅላታቸው የነሱ አይደለምና! እናም የግለሰቡን የአቶ አለምነውን ሰውነት ሳይሆን፤ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት ነው ማስመዘን የምፈልገው። ቀደም አድርጎ ግን አቶ አለምነው ጭንቅላት አላቸው ወይ? ወይንስ ጭንቅላት የላቸውም? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው። በዕርግጥ በዚህ ወራሪ በመሰለ አስተዳደር ለመዘፈቅ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ማንነትን ሽጦ መቆም ግዴታ ነው። ይህ በአእምሯቸው ሳይሆን በሆዳቸው የሚመሩ ሰዎች ብቻ የሚሰበሰቡበት አስተዳደር ለመሆኑ ማስረጃ፤ የራሳቸውን ነፃነት አለማግኘታቸው ነው። ወይንም በትክክለኛው አነጋገር፤ ራሳቸውን መሸጣቸው ነው። አእምሮ ማጣታቸው ማለቱ ይቀላል።

ወንጀል ከተፈፀመ፤ እከሌ ወይንም እከሌና እከሌ ይኼን ሠሩ ወይንም ያንን ሳይሠሩ ቀሩ ብሎ አንድን ወይንም የተወሰኑ ግለሰቦችን መወንጀል፤ ተገቢ ነው። በአንድ ሀገር ያሉትን የአንድ የኅብረተሰብ ክፍል አባላትን ግን ለይቶ ይኼን አደረጉ በተለይም እንዲህ ናቸው ብሎ መወንጀል፤ ከግልብነቱ በላይ የኅብረተሰብን ምንነት አለማወቅን የሚያሳይ አጉሊ መነፅር ነው። ከዚህ ተነስቼ ነው የአቶ አለምነው መኮነንን ንግግር የምረዳው። እስኪ ከአቶ አለምነው መኮነን ንግግር ጠቀስ አድርጌ፤ ጭንቅላት አላቸው ወይንስ የላቸውም? ያስባለኝን ላሳያችሁ፤

፩ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት። ”
፪ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል። ”
፫ኛ፤ “ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም። ”
፬ኛ፤ “ ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት። ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ”
፭ኛ፤ “ ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው። ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብ እየተመገበ ያቅራራል። ”

እዚህ ላይ አቶ አለምነው መኮነን ሁለት መልዕክት ባንድ ላይ አስተላልፈዋል። የመጀመሪያው፤ የአማራውን ጠባየ ቢስነት አመልክቶ፤ አማራውን መኮነን ሲሆን፤ በሥር አስደግፎ ደግሞ፤ አማራው ከሌሎች ቦታዎች በተሰደደበት ምክንያት መንግሥታዊ አካላት ተጠያቂ አይደሉም ብሎ ለማሳመን የተቀመመ መርዝ ነው። ለመሆኑ አቶ አለምነው መኮነን ኢሕአዴግ ራሱ፤ የአማራውን ከሌሎች መፈናቀል ትክክል አልነበረም ሲል፤ የት ነበሩ? መንግሥት በየደረጃው፤ “ደን ስለጨፈጨፉ ነው” ሲል፤ የት ነበሩ? ይኼ የናንተ ቦታ አይደለም ሲባሉ፤ የት ነበሩ? ወይንስ ኢሕአዴግ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት በመጠቀም፤ ያመነበትን ባደባባይ ተናግሮ በጓሮ በር ራሱን ነፃ ለማውጣት የለከካት መልዕክት ናት? የተፈናቀሉት በትምክህተኛነታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ነው። ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አዛውነት፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ደሃዎች፣ ባለፀጎች፣ ሁሉም ታታሪ ሠራተኞች ተባረዋል። ያካባቢው ሰዎች በተቻላቸውና መንግሥታዊ መዋቅሩ በማያውቀው መንገድ ድጋፍና ሐዘኔታ ሠጥተዋቸዋል። ይህ መንግሥታዊ ተግባር ትክክል ስላልሆነ ወደ መጡበት ይመለሱ ሲል ኢሕአዴግ ራሱ ወስኗል። አቶ አለምነው መኮነን! በኢሕአዴግኛ አነጋገር ወንጀለኛው እርስዎና እንደርስዎ ያሉት አፈናቃዮች ናቸው። ተራዎ ደርሶ፤ እርስዎም መጠቀሚያነትዎ አብቅቶ፤ እስኪባረሩ ወይንም ዘብጥያ እስኪወረወሩ ድረስ፤ ከወገብዎ በደንብ ልምጥ ይበሉ!

አማራው እንዲህ ነው ብሎ መጮህ፤ አማራውን ሌሎች እንዲበድሉት ፍቃድ ፈርሞና ታርጋ ለጥፎ መሥጠት ብቻ ሳይሆን፤ አማራው በተፈጥሮ ጎደሎ ስላለበት፤ ከአማራ የተገኘ ሁሉ፤ አብሮ ለመኖር አይመችምና፤ ከያለበት አባሩት ማለት ነው፤ ከኢትዮጵያዊነትም! ይህ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ሰብዓዊነት ነው። ለነገሩ በዚህ ሹመት ከተመደበ በሆዱ ተንፏቆ በሆዱ ከሚያድር ሹም ሌላ ምን ይጠበቃል? አቶ አለምነው መኮነን ከአማራው ወገን ተወላጅ መሆናቸው ዋጋ የለውም። የአቶ በረከት ስምዖንም የአማራው ተወላጅነትና ተወካይነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ! እንዲህ ነው በአማራው ላይ መሾም ማለት!

በሌላ በኩል ስለ አንቀጽ 39 ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። እስኪ ለምን ቀረበላቸው የሚለውን እናጢን! አንቀጽ 39 አማራውን ለብቻው እንደ አማራነቱ የሚጎዳው ነው ወይ? አማራውን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ ነው ወይ? የአማራ ክልል ሰዎች እንዲጠይቁ የተገደዱት? ጥያቄውን ማንሳታቸው የሚያመለክተው፤ አንድም አማራን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ፤ ወይንም የኢትዮጵያን አንድነት አማራው አጥብቆ ስለያዘ ነው። ከዚህ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም። ታዲያ አማራው የሚጠቃበት መንገድ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ነው ማለት ነው። በተለይም ኢትዮጵያዊነትን ስላጠበቀና በመላ ኢትዮጵያ ተበትኖ ስለኖረ። እናም አንቀጽ 39፤ “ኢትዮጵያን ለመጉዳት የታሰበ ወይንም አማራን ከማጥቃት ጋር የተያያዘ ነው።” ብለው ቢያንስ በአማራው ክልል ያሉት የራሱ የገዥው ካድሬዎች ያምናሉ ማለት ነው። ይኼ ራሱን ችሎ የሚታይ በመሆኑ እዚህ ላይ አስተያየት አልሠጥበትም። ለዚህ ጥያቄ የአቶ አለምነው መኮነን መልስ ደግሞ፤

፮ኛ፤ “ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ ታይቷል። ”

በዚህ መልስ የምረዳው፤ አቶ አለምነው መኮነን እንደ አቶ ደሳለኝ ሀይለማርያም የራሳቸውን ጭንቅላት ተጠቅመው የሚሠሩ ሳይሆን፤ በሟቹ “ባለራዕይ” መሪያቸው የሚጎተት መሆኑን ነው። ሟቹ ቢኖሩ ከዚህ የተለዬ እንደማይናገሩ ስለምናውቅ፤ አቶ አለምነው መኮነን ማስተላለፊያ ቀፎ መሆናቸውን ተረዳሁ። ታዲያ የአቶ መለስ ዜናዊን ቀሚስ ለምን አያጠልቁም? አዎ አምባገነኖች ከነሱ ሌላ በራሱ ጭንቅላት አስቦ የሚሠራ እንዲኖር አይፈልጉም። ታሪክም ይኼንኑ ነው የሚያስረዳን።

እንግዲህ አንደኛ፤ አቶ አለምነው መኮነን የራሳቸው ጭንቅላት የላቸውም ወይንም አከላቱ እንደ ግንድ በድኖ ከራሳቸው ውስጥ ቢኖርም፤ የገደል ማሚቶ ሆኖ ከማስተጋባት ሌላ ሙያ የለውም ማለት ነው። ሁለተኛ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነን ተግባር፤ በአማራው ትምክህነት ማመካኘት፤ አደገኛና ለወደፊቱ የአማራውን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን፤ የአማራውን የኅብረተሰብ አካልነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ መርዝ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ልጠቁም የምፈልገው፤ ራሱ ኢሕአዴግ ሳይወድ ተገዶ ያመነበትን የአማራውን የማፈናቀል ወንጀል፤ ከኢሕአዴግ አሳልፎ በአማራው ላይ ለመለከክ የተደረገ የብልጠት ቅሌት ነው። ማሳረጊያው ግን፤ ይኼን መዘርዘሩ ሳይሆን፤ ይኼን ማውገዙ ሳይሆን፤ ይህ እንዳይደገም ሆነ ለዚህ ተጠያቂዎችን በሕግ ፊት ለማቅረብ፤ የታጋዩ ወገን ምን እያደረገ ነው? ነው። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ራዕይ ኖሮን በአንድ ድርጅት ተሰባስበን የምንነሳበት ትግል ነው። ይህ የአማራው ብቻ እንጂ፣ የትግሬው፣ የኦሮሞው፣ የደቡቡ፣ የኦጋዴኑ፣ የአኙዋኩ የግል ጉዳይ ያልሆነ አይደለም። የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን በአንድነት እስካልተነሳን ደረስ፤ መፍትሔው የውሃ ውቀጥ መፍትሔ ነው፤ ውሃን ቢወቅጡት መልሶ እምቦጭ ነውና! ከነአቶ አለምነው መኮነን ሆነ ከአሽከርካሪዎቻቸው ተወግዘውም ሆነ ተለምነው መፍትሔ እንዲሠጡን መጠበቅ፤ ላም አለኝ በሰማይ ነው።

አንድነት ከባድ ተግዳራት ይገጥመዋል፤ታደለ መኩሪያ

$
0
0

የሀገራችንን የፖለቲካ አካሄድ ለአርባ ዓመታት ተከታትያለሁ። ሀገሪቱን የሚመሩት ሆኑ ተቃዋሚዎች በውል የሕዝቡን ችግር የተረዱት አይመስሉም። የሕዝብን ይውንታ ያላገኙ በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም ቢሆኑ፣ እሽ አትበሉን የንጉሥ ዶ ሮ ነን ባዮች ናቸው። ሕዝቡም የቅኝ ገዥዎችን እየተከላከለ ነፃነቱን አስከብሮ የኖረ ነወ። በዚህም ይኩራራል፣ ግን የራሱን ነፃነት እርሱን ከሆነ ሰው ይጠብቃል። በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም በመሣሪያ ኃይል አንገቱን አስደፍተውት አብሮት የተፈጠረውን ነፃነት ቀምተውት እንደወር ቀለብ ሰጪና ነሺ ሆነው ሲያላግጡ ይታያሉ። በቅርቡም አንድ የወያኔ ባለሥልጣን በገሃድ በመገናኛ ብዙሃን እንደገለጸው የገበሬውን ሕብረተሰብ ተኛ ስንለው ይተኛል፣ ተነስ ስንለው ይነሣል፣ ብሎ በድፍረት ተናግሯል።ይህ ሁኔታ በግላጭ ለዩኒቭርሲቲ መምህሩ፣ ለተማሪው፣ለጅንራሉ ፣ ለተራ ወታደሩ፣ ለባንክ ማኔጀሩ ፣ ለተቃዋሚ የፓለቲካ መሪው ፣ ለአባላቱ አይሰራም ማለቱ ይቻል ይሆን? ግመልን ለመጫን እንዲተኛ ይደረጋል ውሻም ጌታው ላይ መጠላጥሉንና ጭራውን መቁላቱን እንዲያቆም እንዲተኛ ይደረጋል። የወያኔው ባለሥልጣንም የነገሩን ይህንኑ ነበር። ከዚህ ሰው መሆናችንን ካልተቀበለ መንግሥት ፍትህን መጠየት እንዴት ይቻላል? ፍትህ የሰው ተፈጥሮ መገለጫው ነው።ሰው በሰውነቱ ነፃነት የተላበሰ ከሆነ የፍትህ ሕሊናና ሰሜትም ተላብሶ የሚመጣ ፍጥረት ነው። ከዚህ ውጪ ሰውን ማሰብ አይቻልም።

በታህሣሥ 20፡ 2006 ዓ ም የአንድነት ፓርቲ የሥራ አስካጅ አባላቱን ለመምረጥ የተገኘው ተሰብሳቢ ፍትህ!፣ ፍትህ! እያለ በቁጣ እጆቹን ሲያወናጭፍና በእንባ ሲራጭ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቲቪ (ኢሳት) ተመልክቻለሁ። በቤገምድር ክፍለ ሃገር በዳባት ወረዳ በድድቅ ጭለማ የወያኔ ታጣቂዎች ከአርሶ አደሩ ቤት ገብተው አባወራውን ገለው፣በዕቅልፍ ላይ ያለቸውን ሕፃን ቀኝ እጇን በጥይት ክፉኛ አቁስለዋት ስለነበር የተቆረጠውን እጇን ለታዳሚው አሣየችው፤ እንደመብረቅ ጮህ፣ ቁጣውን ገለጸ፣ እንባውን አዘራ፤ ቤተሰብም ይህቺን ሕፃን ይዙ ፍትህ ፍለጋ ነው፤ በሀገሩቱ ፍትህ እንደሌለ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ለማሳየት ነው፤ ተሰብሳቢውስ ቢሆን ፍትህ ፈላጊ ነው።
በሀገራቸን ፍትህ ቀስ በቀሰ እየጠፋ ከመጣ ዓመታት ተቆጠሩ። በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ ንግሥ በዘመድ በጋብቻ በጉቦ ሚዛናዊ ፍርድ ይዛባ እንጂ ፍትህ ከሕዝቡ አዕምሮ አሟጦ አልጠፋም። ስለዚህ ሕግ ተጥሷል ብለው ዜጎች ሲያስቡ እስከ ንጉሠ ነገሥቱ ችሎት ድረስ ዶሲያቸውን አንግበው ይሄዱ ነበር። ከ1966 ዓ ም ለውጥ በኋላ ሰዎች ያለ ፍርድ ሲገደሉ ፍትህ ፍቺውን እያጣ መምጣቱን ለመረዳት ሕዝቡ ጊዜ አልወሰደበትም።

በ1967 ዓ ም ነበር፤ከአራቱም ማዕዘናት ሕዝቡ ለገበያ መጥቶ ይገበያያል፤ የደርግ አባል የሆነ የለውጥ ሐዋሪያ ስለአብዮቱ መግለጫ ይሰጣሉና ስብሰብ ብላችሁ አዳምጡ ተባለ፤ ሕዝቡ ተሰበሰበ፤ ስለአብዮቱ ተደሰኮረ፤ የለውጥ ሐዋሪያው መፈክር አሰሙ፤ ኢዲዮ ይውደም፣ አቆርቋዠ ይውደም፤ ኢህአፓ ይውደም፣ አዳሃሪ ይውደም፤ሕዝቡ ተዳከመ። አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ገበያተኛ፣ የእርግምን ጋጋታው ምንድነው በማለት አርጎመጎመ፤ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ‘ጃኖሆይ አልጋ ቡሰኒ ትውደሚ ኢረ ካየኒ’ ጃኖሆይን አውርደው ትውደምን በዙፋናቸው ላይ አስቀመጧት ብለው ጠየቁ። ደርግም በተግባር ካለሕግ የበላይነት ማውደሙን ቀጠለ። ብዙ ሳይቆይ በአካባቢው አንድ ወጣት ተማሪ በፓሊስ ተገደለ፤ መምህራንና ተማሪዎች ሥራ አቆሙ፤ ገዳዩ ለፍርድ ይቅረብ አሉ፤ የመምህራኑ መሪ በታጣቂዎች ተገደለ፤ ልክ እንደቤገምድሩ ቤተሰቦች የአስተማሪውን አስክሬን በመኪና ተጭኖ የሁለት ወር ሕፃኑን ባለቤቱ ታቅፋ ጓደኞቱ 400 ኪሎ ሜትር ተጉዘው አስከሬኑን ለወላጆቹ አዲስ አበባ አሰረከቡ፤ ለምርመራ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወሰደ። አስከሬኑን አጅበው የሄዱ መምህራን፣ ጉዳዩን ከአስራ አራቱም ክፍለሃገር የመጡ የመምህራን ተወካዮች በስድስት ኪሎው ጽፈት ቤቱ በሰብሰባ ላይ ነበሩና ስለ መምህሩ ግድያ አስረዱ።
ወደያውኑ በሀገራችን ፋሽሽታዊ ተግባር እየነገሰ መምጣቱን አስመረውበት፣ በጅማው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይቀርባል በማለት ውሳኔ ተሰጥቶት አለፈ። ለመምህሩ ቅብር ተወካዮቹ በሙሉ በቀጨኔ መድኃኒዓለም ተገኙ። ዛሬ እነዚያ የመምህራን መሪዎች በሕይወት የሉም፤ ለፍትህ መስዋዕትነትን እየከፈሉ አለፉ።የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበርም ከጅማው ስብሰባ በኋላ በእግሩ ሊቆም አልቻለም።

በአንዲት ሀገር ሕዝቡ ፍትህ የለም ብሎ ካመነ የሀገር ፍቅሩ ይቀንሳል። ስው አይደለህም ተብሎ በሕገ አራዊት መዳኛትን አይፈቅድም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት የከፈለውን ዋጋ ከራሱ አልፎ የዓለም ሕዝብ ያውቅለታል። ነገር ግን ስለራሱ አበሮት ስለተፈጠረው ነፃነቱ ያለው ግንዛቤ አናሳ ሆኖ ይታያል። በሕግ አራዊት የሚተደደር ሕዝብ መሆኑ አልተገለጠለትም። ዛሬ ሥልጣን ላይ የወጡት ወያኔዎች ቢሆኑም ፍትህ ጠፋ ብለው ለነፃነታቸው ዱር የገቡ እንደሆነ ይነገር ነበር፣ ሆኖም በቅርቡ ከመሥራች መሪዎች በመነገር ያለው ሌላ ነው። የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ለመሰዋዕትነት የገበረው ለፍትህ ሳይሆን የአማራውን ሕዝበና የኦርቶዶክ ሃይማኖትን ለማጥፋት የድርጅቱ መሥራች አባት አቦ ስባት ነጋ በተዘዋዋሪ ይነግሩናል። ‘የአማራውን አከርካሪው ሰብረናል የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አጥፍተናል በማለት በኢፋ ተናግረዋል። ለግራኝ ሙሐመድም ለዩዲትም አልሆነላቸውም፤ የቤቶ ሞሶሎኒን ግን አሳክተዋል፤ የተከበሩ የፓርላማ ተመራጩ የአዋሺ ባንክ መሥራች አቶ ቡልቻ ደመቅሣን ተከታይ አፍርተዋል፣በኦሮመኛ እንዲህ ይተረታል ‘ማንጉዶን ገልገላ መሪቴ፤ ኢጆሌን ገነማን አላን ባቴ፤ አዛውቱ ማታ የመከሩትን ከጠዋቱ ልጆቹ አደባባይ አወጡት ማለት ነው። የአቶ ቡልቻን ምኒሊክን ማውገዝ ተከትሎ በነፃነት እንድንኖር ያደረጉን ንጉሥ ስም በየፓል ቶኩ ሲብጠረጠር እሰማለን፤ ስለምኒሊክ የተዘፈኑ ዘፈኖችም አዳይደመጡ እየተባለ ነው፤ ከአዋሽ ባንክ ገንዘባችሁን አውጥታችሁ ከወጋገን ባንክ አስቀምጡ የሚል ጨዋ ሰው የለም፤፤ አቶ ቡልቻ ግን የሚሉት ያንን ነው። አቶ ስባት ነጋና ስብስባቸው ወያኔ ሩዋንዳ ውስጥ በሁቱና በቱትሲው መካከል የተፈጠረውን የእርስ በእርስ መጫረስ በኦሮሞና በአማርኛ ተናጋሪው መካከል ሊፈጥሩት ያቀዱት አልተሳካም። የቤቶ ሞሶሎኒ እቅድ ከከሸፈ ሰንበት ብሏል፤ ከዘር፣ ከፓለቲካ ፓርቲ፣ ከሃይማኖት፡ ከዜግነት በፊት ሰው ነኝ፣ ማለት ከተጀመረ ቆይቷል፤

ስለዚህ የወያኔን የሕግ አራዊት አራማጅ ቡድን በሕጋዊነት ሕጋዊ ለማድረግ የሚደረገው ሰላማዊ ትግል የሰውን ረቂቅነትና ታላቅነት የሚጠይቅ ነው፤ የሰውነት ሕልውናውን የተገፈፈን ሕዝብ ክብሩን ለማስመለስ ለሚደረግው ትንንቅ ብቃትና ቆራጥነትን የተላበሰ መሪ ግድ ይላል፤ሆኖም በሥልጣን ላይ ያለውን ስብስብ ከአቅም ማነስ ተነስቶ የሚታየውን ሐቅ ደፍጥጦ ሕጋዊ ከማድረግ በፊት ዘለቄታዊ ጥቅሙ መታየት ይኖርበታል። የአንድነት ፓርቲ ከግንቦቱ 97 ዓ ም ምርጫ ይህንን ግንዛቤ ሳያገኝ አይቀርም። ደግም ደጋግሞ አንድን ነገር መሥራት ውጤት እንደማያመጣ ማወቁ ክብደት እንደሌለው ግልጽ ነው፤ ‘ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ’ የሚለውን የግንቦት 1997ዓ ም አበባል ከአዲሱ የአንድነት ሊቀመበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ሰለሰማሁት ነው። ከስብሰባው እንደተረዳሁት ‘የፍትህ’ ጥያቄ ነው። ይህ የስውነት ጥያቄ የተቃዋሚዎች በቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ ፍትህ የተቀማው ሕዝብ ጥያቄ ነው። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ፍትህ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በ እሥር ይማቅቃሉ፣ እንዲታሰሩ ማን ትዕዛዙን እንደሰጠ አይታወቅም፤ በጠራራ ፀሐይ ሰዎች ይገደላሉ ትዕዛዙን ማን እንደሰጠ አይነገርም፣ አንድ የተቃዋሚ ድርጅት በመንገድ ላይ ወይም በቤቱ ይደበደባል ማን ትዕዛዙን እንደሰጠ ሃላፊነት የሚወስድ የለም፤ የወያኔ ጅንራል በሞባይል ስልኪ በቁባቱ ባት ላይ ተቀምጦ ሠራዊቱን ለሞት ወደ ጦር ሜዳ ይልካል፤ በስልክ ወይም በብጣሽ ወረቀት ትዕዛዝ ፍርድ ይዛባል፤ ዜጋ ሲገደል ሲታሰር ይታያል፤ ትዕዛዙን የሰጠውን አልጠየቅንም፤ የሕግ አራዊቱን ሞተር አቀሳቃሹ ማነው? ተጠያነት በሌለው መንግሥት መመራት ራስንም አስጠያቂ ያደርጋል። ዛሬ ባይሆን የልጅ ልጆቻችን ይጠይቁናል። ያም ሆነ ይህ እንደሃገር ነፃነት ለራሳቸው ነፃነት የቆሙ ኢትዮጵያውያን አሉ። በዕርግጥ በተናጠል የሚከፈለው መሰዋዕትነት ፍጣን ውጤት ባያስገኝም ወደ ነፃነቱ በሚወስደው ጎዳና ላይ ናቸው። ይህ የያንዳንዱ ሃላፊነት ለራሱ መብትና ነፃነት መቆም ሲሆን፤ የፓለቲካ መሪዎችም ተግባር ይህን አሰባስቦ በቆራጥነት መምራት ነው፤ የኢትዮጵያ ዕስልምና ተከታይ ወገኖቻችን የፍትህ ጥያቄ አቅጣጫ ወደ ቀድሞው የሃገር ነፃነት አሁን ደግሞ’ የሰው ነኝ’ ነፃነት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው።

የአንድነት ፓርቲ መሪውንና የሥራ አስካጅ ኮሚቴውን በመረጠበት ዕለት የቀረበለት ሰቆቃ ነበር፤ የትግሉን መራራነት ጠቋሚ ነው። አባላቱም የዛችን ሕፃን የተቆረጠ እጇን ሲያይ ስሜቱን መቆጣጠር ተሳነው ‘እኔም ሰው እኮ ነኝ፣ ሕመሟ ተሰማኝ፣ በማለት ነበር ፍትህ! ፍትህ! በማለት ስሜቱን የገለጸው፤ መሪዎቹም ወደፊት የሚገጥማቸው ተግዳራት እንደቀድሞው ወያኔን በማውገዝ፣ ለኢንባሲዎች ደብዳቤ በመጻፍ ወይም በራቸውን በማኳኳት እንዳልሆነ ፍትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ወደ ሕዝቡ ተጠግቶ ነፃነቱን እንዲያስከብር ማስተባበር መሆኑን አመልካች ነው።ይህም ቢሆን እስከ ሕይወት መሰዋዕትነት የሚጠይቅ ይሆናል።ፍትህ በሌለበት ሕብረተሰብ ሕግ አራዊት በነገሰበት መራጭም ተመራጭም አይኖርም።
በኢትዮጵያ ፍትህ ይንገሥ!
ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca

ሌንጮ ለታ –ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…? ክንፉ አሰፋ

$
0
0

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።” ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። “ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።
በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል።

“ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።” የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን በደንብ ጠረግ ጠረግ አደረግኩና እንደገና አነበብኩት።
“ታሪክ እንሰራለን” የሚለው ሃረግ በስህተት የሰፈረ ነበር የመሰለኝ። ሌንጮ ለማለት የፈለጉት “ታሪክ እናነባለን” ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ደጋግሜ ያየሁት። ያነበብኩት ነገር ትክክል ነው። ይህንኑ ቃል ከራሳቸው አንደበትም ሠማሁ። በስህተት የሰፈረ ዜና አልነበረም። ታሪክን ማንበቡም ሆነ መስራቱ ቀርቶ “ሃገር ቤት ገብተን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን።” የሚል ቢሆን እንኳን ግርታውን ይቀንሰው ነበር።

በፍትህ ሳይሆን ይልቁንም በአዋጅ በምትተዳደር ኢትዮጵያ፤ እጅና እግራቸውን ብቻ ይዘው በመግባት ታሪክ መስራት የሚችሉ ከሆነ በምትሃት አልያም በመለኮታዊ ሃይል ብቻ መሆን አለበት። ሌንጮ ሃገር ቤት ገብተው ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰናቸው ላይ ምንም ችግር የለብኝም። የዚህ ውሳኔ ትክክለኝነት የሚዳኘው አስቀድመው በሚተቹ እና በሚተነብዩ የፖለቲካ ነብያት አይደለም። ፍርድ የሚሰጠው ሂደቱ በተግባር ሲፈተን ብቻ ይሆናል። ይህን ለማየት ደግሞ ብዙም ሩቅ አይሆንም። በጎረበጠ የፖለቲካ መንገድ ላይ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት መወሰናቸው ግን አስመራ ላይ፤ በሻእቢያ ከታገቱት የኦነግ መሪዎች የተሻለ ውሳኔ ይመስላል። ታሪክ ለመስራት አስመራ የመሸጉት እነ ዳውድ ኢብሳ ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።

ችግሩ ያለው “ታሪክ እንሰራለን” ማለቱ ላይ ነው። እንደዚህ አይነት የፖለቲካ ትግል ውሳኔ ላይ መድረስ ቀላል ነገር አይደለም። ከመቅጽበት የመጣው ይህ ውሳኔ ልክ እንደ ኦሎምፒክ ውድድር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አትሌት ይመስላል። አትሌቲክስም ቢሆን የአካል ብቃትና በቂ ዝግጅትን ይጠይቃል። ፖለቲካ ደግሞ ዘው ብለው ገብተው ታሪክ የሚሰሩበት በኦሎምፒክ የውድድር መድረክ አይደለም። እነ ሌንጮ እየነገሩን ያሉት አዲስ አበባ ገብተው በባላገሩ አይደል ላይ ለመወዳደር አይደለም። በባላገሩ የጫወታ ደንብ ጥሩ ስራ የሰራም፤ አስቀያሚ ስራ የሰራም ይሸለማል። ሌንጮ ታሪክ እንሰራለን የሚሉት “ስልጣን ወይንም ሞት!” የሚል መፈክር አንግቦ እስካፍንጫው የታጠቀ ሃይልን በመጋፈጥ ነው።

ታሪክን ለመስራት ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጠፍተው አያውቁም። ከኦሮሞ ድርጅቶችም ቢሆን እነ ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ እና ፕ/ር መረራ ጉዲና አሉ። የኦሮሞን ህዝብ አደራጅተው በምርጫም፣ በፓርላማም፣ በሰልፍም፣ በእርግማንም፣ በጸሎትና ምልጃም፣ በወረቀትም … ብዙ ተጉዘዋል። የእነዚህ ድርጅቶች አባላት እንደጥጃ እየተለቀሙ እስር ቤቱን ከማጨናነቃቸው በቀር ታሪክ ሲሰሩ አላየንም። አንድ እርምጃ ወደፊት፤ አስር እርምጃ ወደኋላ እየተጓዙ ሄደው…ሄደው በመጨረሻ ራሳቸውም ታሪክ ከመሆን አላለፉም። ይህ ለአቶ ሌንጮ ለታ እንግዳ ነገር አይደለም። አቶ ሌንጮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በከባድ ሚዛን ደረጃ የሚመደቡ ናቸው።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ታግሎ ታሪክ ከመስራት ይልቅ ነድጅ ቆፍሮ ታሪክ መስራት እንደሚቀል ለሌንጮም አዲስ ነገር አይደለም። እርግጥ ነው። የታሪክ ትርጉም አሰጣጣችን ላይ እንለያይ ይሆናል። የገዥው ፓርቲ የታሪክ ትርጉምም ከልማት ጋር ይያያዛል። በዘመናችን ብዙ ታሪኮችን እየሰማን ነው። ልማታዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ሁሉ ዛሬ ታሪክ ሰሪ ይባላል። ታሪክ ሰርተው የሚሸለሙ የልማት አርበኞችን በቴሌቭዥን እናያለን። በአነስተኛና ጥቃቅን እየተደራጁ የኮብል-ስቶን ድንጋይን እያናገሩ ያሉ ወጣት ምሁራንም በታሪክ መዝገብ ላይ እየሰፈሩ ይገኛል።

ኦቦ ሌንጮ ታሪክ የሚሉን እንዲህ አይነቱን ድራማ እንደማይሆን እርግጠኞች አይደለንም። እኝህ የፖለቲካ መሪ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው ግዜው አሁን አይደለም። በሽግግሩ ዘመን 20 ሺህ ጦር እና 20 መቀመጫ ይዘው በነበሩበት ጊዜ ለዚህ እድሉ ነበራቸው። ያንን እድል ይዘው ታሪክ ከመስራት ይልቅ ድርጅታቸው ጥቁር ነጥብ ጥሎ ነበር ያለፈው። አቶ ሌንጮ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው በሽግግሩ መንግስት የኢትዮጵያ መሪ ሆነው በተመረጡ ግዜ ነበር። በወቅቱ ምን ነበር ያሉት? “በዚህ ላይ አልተዘጋጀሁበትም።” ሲሉ የእድሉን በር ራሳቸው ዘጉት። በርግጥ ያን ጊዜ ከኦሮሚያ የመገንጠል አዙሪት ውስጥ አልወጡም ነበር። ትልቅ ህዝብን ይዘናል እያሉ፤ የመገንጠል ጥያቄን ሲያነሱ በአለም ላይ የመጀመሪያዎቹ ብቻ አይደሉም። የኦሮሞን ህዝብ በፖለቲካ አናሳ ማድረጋቸው የታያቸውም ከ40 አመታት በኋላ መሆኑ ነው። በዚያን ወቅት ኢትዮጵያን መምራት እንችላለን ለማለት በራስ መተማመን አልነበራቸውም። አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚል መርህ ምርጫ አድርገው ከመጓዝ ይልቅ፤ እንደ አናሳ ጎሳ “መገንጠል አለብን” የሚል ያታሪክ ስህተት ውስጥ ነበሩ።

ከኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ወጥተው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባርን መመስረታቸው ከታሪክ ተወቃጭሽነት ሊያድናቸው ይችላል ። ይህንን በማድረጋቸው የሰማይና የምድርን ያህል ርቆ የነበረውን የፖለቲካ መስመር ሊያጠበው እንደሚችል ግልጽ ነው። ዛሬ የመገንጠልን ጥያቄውን ውድቅ አድርገው ለዲሞክራሲና ለፍትህ መታገል መምረጣቸው ታሪክ ሰሪ ሊያደርጋቸው አይችልም። ይህ ሊሆን የሚችለው ለውጥ አምጥተው ፍትሃዊ ስርዓት ማስፈን ሲችሉ ብቻ ነው።

ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ በመግባት ታሪክ እሰራለሁ ሲሉ ይህ የመጀመርያቸውም አይደለም። እ.ኤ.አ. 1993 የስራ ባልደረባቸውን ከከርቸሌ ለማስፈታት አዲስ አበባ ዘው ብለው ገብተው ነበር። እኝህ ሰው ሲገቡ ቦሌ ላይ ልዩ አቀባበል ተደረገላቸው። በብረት ተጠፍረውም ከርችሌ ተወረወሩ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዶ በነበረው የግዮኑ የሰላም እና እርቅ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሲገቡ የታሰሩ ልኡካንን እዚያው ተቀላቀሉ።

ሌንጮ በዚያ ሰዓት ታሪክ ይሰራሉ ብለን ጠብቀን ነበር። ግን ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ለመውጣት አንድ ሳምንትም አልፈጀባቸውም። በወቅቱ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ረጅም ቃለ-መጠይቅ አድርጌ ይህንን ታሪክ በማሳትመው ጋዜጣ ላይ ለህዝብ ይፋ አድርጌዋለሁ። እርግጥ ነው። የሌንጮ ለታ ፖለቲካ እውቀት የሚደነቅ ነው። በፖለቲካ ብስለታቸውና ትንተናቸው ከማደንቃቸው የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ናቸው። ፖለቲካ ማወቅ እና ህዝብን መምራት ግን በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ብዙውን ግዜ የሰዎችን የፖለቲካ ብቃት የምንለካው በንግግር ችሎታው ብቻ ነው። ጥሩ የፖለቲካ መሪ አስተዋይም መሆን አለበት። የመሪ አስተዋይ አለመሆን ደግሞ ችግር የመፍታት ብቃታ ማጣቱን ነው የሚያሳየን። ኦነግ ከ40 አመታት በላይ በትግል ላይ እንደሆነ ይነገረን እንጂ ድርጅቱ ድል አድርጎ አይተን አናውቅም። የሽግግሩን መንግስት ላይም ቢሆን የተገኘው በድል አድራጊነት ሳይሆን ከህወሃት እና ከሻእቢያ ጥሪ ተደርጎለት ነበር።

በአሁኑ የአዲስ አበባ ጉዞ ሌንጮ እንደቀድሞው ልዩ አቀባበል ላይገጥማቸው ይችላል። በእርግጠኝነት ለመናገር ከጉዞው በፊት አንዳች ቅድመ ሁኔታዎች ወይንም ስምምነቶች ይኖራሉ። ይህ ካልሆነ ግን እኝህን ሰው በቀይ መስመር ላይ ማስቆም ወይንም ደግሞ ማኖ ማስነካቱ አይቀሬ ነው። እሳቸውን ቀይ መስመር ላይ ለማቆስም በጣም ቀላል ነው። የበደኖው፣ የዋተሩና የአርባጉጉ ፋይሎች እየተመዘዙ ማውጣት ብቻ ይበቃል። አልያም ቦሌ ላይ እነ ዋልታ ብቅ ብለው በካሜራ ይቀበሏቸዋል። ልማቱን እንዲያደንቁ ይጠየቃሉ። በእስር ያሉ ወገኖችና “ሽብርተኞች”ን ማውገዛቸውም የግድ ነው። በዚህ መስመር ላይ ከሄዱ “አባ ጸበል ይርጩን” ብለው እንደገቡት እንደነ ስም አይጠሬ ተዋርደው ይመለሱና የፖለቲካ ሞትን ዳግም ይቀምሷታል።

ለእንደዚህ አይነቱ “ልማታዊ” የተቃውሞ አስተሳሰብ ሳይገዙ ታሪክ መስራት ከተቻለ ግን ተአምር ይሆናል። ለማንኛውም መልካም ጉዞ…


ሕወሃት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሮአል በነጻነት አድማሱ

የአማራውን ሕዝብ ክብር የደፈሩና ያዋረዱ አምባገነን ገዥዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!! (አንድነት)

$
0
0

‹ጉድ ሳይሰማ…›› እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ስርዓቱን ከነችግሩ መሸከሙ አልበቃ ብሎ መሪ ነን በሚሉት እየተበሻቀጠና ለውርደት እየተዳረገ ይገኛል፡፡

ፓርቲያችን በትኩረት እየተከታተለው ያለውና ሰሞኑን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይና በኢሳት ይፋ የተደረገው የአማራ ክልል ም/ ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በአደባባይ መሳደባቸውንና ማዋረዳቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መለቀቃቸውና የክልሉ መንግስት ለማስተባበል እንኳ ዝግጁ አለመሆኑ የሚያሳየው ንቀትንና ጥላቻን ብቻ ሳይሆን እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ትከሻ ላይ ተቀምጠው ፀረ ህዝብ አቋም እንደሚያራምዱ ነው፡፡ ፓርቲያችን የብአዴን/ኢህአዴግ ባለስልጣን በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን ክብር የሚነካ አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ ሊመለከተው እንደማይችል አስረግጦ ለመናገር ይወዳል፡፡ ፀረ ህዝብ አቋም የሚያራምዱ አምባገነኖችንም ከህዝብ ትክሻ ለማውረድ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡ አንድነት በቅርቡ በጉራ ፈርዳና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዜጎች ላይ የተወሰደው የማፈናቀል ተግባር ስርዓቱና የስርዓቱ መሪዎች የፈጠሩት ችግር እንጅ የአካባቢው ሕዝብ የፈጠረው እንዳልሆነ ያምናል፡፡

አቶ አለምነው መኮንን የተባሉት ባለስልጣን የአለቆቻቸውን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ህዝብ ‹‹ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፣ ትምክህተኝነቱን ያልተወ፣ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ›› ካሉ በኋላ ‹‹የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት›› በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ለዚች ሀገር ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣትና የሌሎች ጠላት አድርጎ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡

ፓርቲያችንም ይህንን አሳፋሪና የዜጎችን ክብር የደፈረ የባለስልጣኑ አባባል በቸልታ የሚታይ ሆኖ አላገኘውም፡፡

ስለዚህ፡-

1.ግለሰቡ በዚህ የተዛባ አመለካከቱ ለአማራ ህዝብ መሪ ሊሆን ስለማይችል በአስቸኳይ ከፓርቲና ከመንግስት ኃላፊነቱ እንዲነሳና ለህዝቡ ይፋ እንዲደረግ፤
2.ህዝቡን ያዋረደው ባለስልጣን ላይ ርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ግን የግለሰቡ አመለካከት የብአዴንና የክልሉ መንግስት አቋም አድርገን የምንወስድ መሆኑ እንዲታወቅ፤
3.አንድነት ፓርቲ ፀረ-ህዝብ አቋም ያለው ግለሰብ ባደረገው የህዝብ ጥላቻ ንግግር (Hate speech) ተነስቶ ለሕግ የሚያቀርብ መሆኑ እንዲታወቅ፤
4.ፓርቲያችን ህዝቡን በማስተባበር በባህርዳር ከተማ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ድርጊቱን የማውገዝና እንዲቆም የማድረግ ርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ስለዚህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የክልሉን ህዝብ እየመራው ያለው ብአዴን/ኢህአዴግ ለህዝብ ክብር የሌለው ድርጅት መሆኑን አውቆ ከፓቲያችን ጎን በመቆም እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የማይታረቁ ወገኖች የማይታረቅ ኀሳብ ይዘው ሲፋጩ የዋሉበት መድረክ በዘሪሁን ሙሉጌታ

$
0
0

ባለፈው ቅዳሜ (ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም) በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን የድህረምረቃ ተማሪዎች የኢትዮጵያን የፕሬስ ሁኔታ በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚኖረውን ሚና በተመለከተ የአንድ ቀን የውይይት መድረክ አዘጋጅተው ነበር።

መድረኩ ዘግየት ብሎ ቢጀመርም የተጠናቀቀውን ግን ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው። የውይይቱ ሙቀትና ግለት በፈጠረው ስሜት የሻይና ቡና እረፍትን ያስፈለገው አልነበረም። በውይይቱ ላይ በርካታ ርዕዮተ ዓለማዊ መፋጨቶችና ጉንተላዎች የታዩበት ነው። ውይይቱ በዋናነት ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው “ልማታዊ ዴሞክራሲ” አስተሳሰብ ውስጥ የፕሬሱ ሚና ምን እንደሆነ ለማየት ቢፈለግም፤ ውይይቱ ግን ኢህአዴግና አንድነት ፓርቲ የሚሟገቱበት እንዲሁም ዶ/ር ዳኛቸውና አሰፋና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በኀሳብ የተጎሻሸሙበት፣ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው የፓርቲያቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሞከሩበት፤ አቦይ ስብሃትና አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው የኢህአዴግን ጥቅም ላለማስነካት የተፋለሙበት፤ ሁሉም ተፃራሪ ኃይሎች በአንድ ቦታ ተገኝተው የሃሳብ ፍልሚያ ያደረጉበት መድረክ ነበር ለማለት ይቻላል። ውይይቱ የተቃራኒ አስተሳሰብ ባላቸው ወገኖች የሚደረግ ቢሆንም፤ ዶ/ር ዘነበ በየነ መድረኩን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርተውታል።

በውይይት መድረኩ የተገኙ፣ ጥናት ያቀረቡ ወገኖች የአሰላለፍ መስመራቸው ከወደ ገዢው ፓርቲ የሚያደሉ ቢመስሉም፤ ከተሳታፊዎች ተነስተው የነበሩ ኀሳቦችም ሚዛናቸው ከፍተኛ ስለነበር ውይይቱ ውጥረት ይታይበት ነበር። በመጠኑም ቢሆን የምርጫ 97 የምርጫ ክርክር የሚያስታውስ ይመስል ነበር። በምርጫ 97 ወቅት የኢህአዴግ ተከራካሪዎች በኀሳብ እጥረት ቢበለጡም በእሁድ ዕለቱ ውይይት ላይ ግን ለኢትዮጵያ የሚበጀው መንግስታዊ ስርዓት “ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ” ነው ሲሉ ተሟግተዋል። በአንፃሩ “ልማታዊ ብሎ ዴሞክራሲ” የለም በሚል ከፍተኛ የሆነ የኀሳብ ትንቅንቅ የታየበት ነበር።
የዕለቱ ዋነኛው መከራከሪያ በልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የሚዲያው ሚና ምን መሆን እንዳለበትና በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ እንዲያተኩር ቢፈለግም ፖለቲካዊ ክርክሩ የጎላበት ነበር።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ ለመወያያ ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ የልማታዊ መንግስት አስተሳሰብ ከሩቅ ምስራቅ ሀገራት ማለትም ከደቡብ ኮሪያ፣ ከታይዋንና ከጃፓን የሚቀዳ አስተሳሰብ መሆኑን በመጠቆም የአስተሳሰቡን ተግዳሮቶች ወገናዊ ባልሆነ (Neutral) መንገድ አቅርበውታል። “የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ” የሚለውንም የኢህአዴግ መስመር ብዥታ ያለበት አካሄድ መሆኑንም በስሱ ገልፀውታል። ከሁሉም በላይ ልማታዊም ተባለ ዴሞክራሲያዊ ቢያንስ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ሊያግባባ የሚችል፣ ሀገራዊ መግባባት (National Consensus) አስፈላጊነትን ደጋግመው ገልፀዋል። ዶ/ር አብዲሳ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ከ400 በላይ ሰዎች ታስረዋል በሚባልበት ሀገር ይሄንን ገዢ ሀሳብ ወገናዊ ባልሆነ መንገድ ማንፀባረቃቸው በተወያዮች ዘንድ በበጎ እንዲታይላቸው አድርጓል። ይሁን እንጂ ዶ/ር አብዲሳ ለብሔራዊ መግባባት “የታሰሩ ይፈቱ፣ በውጪ የተሰደዱም ይመለሱ፣ መንግስትና ተቃዋሚዎች ያለቅድመ ሁኔታ ይደራደሩ” በሚል መጠን (Tone) ቢናገሩት የተሻለ እንደነበረም መገመት ይቻላል። ለዚህም ይመስላል የዶ/ር አብዲሳን የመወያያ ጽሁፍ አፍቃሬ የገዢው ፓርቲ ተወያዮችንና ተቀዋሚዎችን ያላጠገበው።

የፋና ብሮድካሰት ኮርፖሬት አክሲዮን ማኅበር ሥራአስኪያጅ በዕለቱ የመወያያ ጽሁፍ ካቀረቡ አንዱ ነበሩ። ስራ አስኪያጁ አቶ ወልዱ ይምሰል ሚዲያው በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ በሚፈጠረው ፖለቲካል ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ተሳትፎ ከሌለው በቀር ሚናውን መወጣት እንደማይችል በመግለፅ አሁን ያለውን ሚዲያ ተችተዋል። በተለይ የግል ሚዲያውን አነሳስና አመጣጥ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ገልፀውታል። አቶ ወልዱ ሚዲያው በዴቨሎፕመንታል ዴሞክራሲ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን የፋና ብሮድካስትን ሞዴል የሚመስል ነገር ተናግረዋል። በዕለቱ በስብሰባው ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የተገኙት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአሁኑ ወቅት ያለው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣን ወይም ኃይል (Political Power) ነው በማለት የአቶ ወልዱን ጥናት በአጭር ቃል መትተውታል።

ዶ/ሩ በዕለቱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከመሰረቱ (Public) የሕዝብ ቢሆንም የግል (Private) ሆኖ ከመቆየት መጥቶ አሁን ሕዝባዊ የበላይነት ይዞ በመጣበት ጊዜ ውይይቱ መካሄዱን አወድሰዋል። ነገር ግን በውይይቱ ላይ ሁሉም አካላት አለመጋበዛቸው ወይም ግብዣው ያላረካቸው መሆኑን ሳይናገሩ አላለፉም። በውይይቱ የተሳተፉ አካላት ሚዛናዊ አለመሆኑንም ለመጥቀስ የገብረክርስቶስ አባትን ተረት የአለቃ ደስታ ነገዎ የመጀመሪያው የአፄ ኃይለስላሴ ፓርላማ ሲቋቋም አፄ ኃይለስላሴ የፓርላማው ተሰብሳቢዎችን ከአንድ ወገን መሆናቸውን በማየት (እነዚህ ሰዎች የሚመክሩ ወይስ የሚመከርባቸው) በማለት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሚዛናዊ አለመሆን ጠቅሰዋል። ከዚሁ የተሳታፊዎችና አቅራቢዎች ሚዛናዊ አለመሆን ጋር በተያያዘም “አንዳንድ ሚኒስትር ዲኤታዎችን በማይበት ጊዜ” በማለት የአቶ ሽመልስ ከማልን በውይይቱ ላይ መገኘት ጥያቄ እንዳጫረባቸው ጠቅሰዋል።
የዶ/ር አብዲሳን የማወያያ ጽሁፍን ዶ/ር ዳኛቸው ሲያሄሱም በልማታዊ መንግስትነትና በዴሞክራሲያዊ መንግስት መካከል ውጥረት (Tension) አለ ማለታቸውን እንደሚስማሙበት ገልፀዋል። በደርግ ጊዜም እኩልነት ከነፃነት (Equality Vs Liberty) የተፋጠጡበት በመሆኑ ደርግ የዜጎችን ነፃነት ጨፍልቆ እኩልነት ሊያመጣ ፈለገ ብለዋል። በእሳቸው አገላለፅ “አሁን የመጣብን ጉድ” ያሉት ልማትን በበላይነት ይወስድና ነፃነትን (Liberty) ይጨፈልቃል። ኢህአዴግ አሁን የሚመራበት “ልማታዊና ዴሞክራሲ የፈለጋችሁትን ያህል ብትባባሉት አይታረቅም ብለዋል።

በመቀጠል የተናገሩት አቦይ ስብሃት ነበሩ። የአቦይ ስብሃት ምላሽ ለዶ/ር ዳኛቸው መልስ የሚመስል ነበር። በአቦይ ስብሃት እምነት ልማት እንደ አይዲዎሎጂ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው። የመኖር ወይም ያለመኖር ነው። በአቦይ እምነት ልማት የዴሞክራሲ መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ኃይሎች የሚባሉ ባለሃብቱና ላብ አደሩ ናቸው። ሌሎቹ የደጋፊነት ሚና ሊኖራቸው ይችላል። ልማት የእንጀራና የቤት ጉዳይ ሳይሆን የፀጥታ ጉዳይ ነው። ልማት ያለ ዴሞክራሲ አይሄድም። ቢያንስ ባለው ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መፈቀድ ስላለባቸው። ኢህአዴግ በሕገመንግስቱ እነዚህን መብቶች አስቀምጧል። እነዚህም የመነጋገር የመፃፍና የብሔር እኩልነት ናቸው ብለዋል።

“ልማትና ዴሞክራሲ አይነጣጠሉም” የሚለውን ደግሞ አቶ ስብሃት ሲያስረዱ “አንዱ ያለ ሌላው ሊኖር አይችልም” ብለዋል። በኢትዮጵያ ልማት ከሌለ ዴሞክራሲ የለም። ሁለቱም ተባብረው መሄድ አለባቸው ብለዋል። እንደ አቦይ ሰብሃት ገለፃ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ መገለጫዎች አንዱ የነፃ ገበያ ስርዓት ነው። ነገር ግን የነፃ ገበያ አስተሳሰብና ኢህአዴግ የተዋወቁት በድንገት ነው። አቦይ ስብሃት የተገናኙበትንም አጋጣሚ ሲገልፁ፤ “መጀመሪያ የነበርነው ሶሻሊዝም ነበር። ነገር ግን ወደ ካፒታሊዝም እንዙር ተብሎ ነገሩ ሲጠና ሰዎች ወደ ውጪ ልከን፣ መፃህፍት ከውጪ አምጥተን ነበር። ይሄ ካፒታሊዝም የሚባል ነገር ምን እንደሆነ በሀገሪቱም ሆነ እኛም እንደ ድርጅት አናውቀውም። ነፃ የኢኮኖሚ ባዕዳዊ እንሰሳ በመሆኑ ይሄንን ባዕድ እንሰሳ ለማጥናት ብዙ ጊዜ ወስዶብናል። በደርግም ቢሆን የነፃ ገበያ አስተሳሰብ ብዙ ሰው አስገድሏል። ኢህአዴግም ነፃ ገበያን ለማጥናት በአራቱም አቅጣጫ ሰው ልኮ በታላቅ እሩጫ አስጠንቷል” ብለዋል። ከዚያም ወደ ዴቨሎፕመንታል መንግስት ማምራቱንና በእሳቸው ቃል በቃል አገላለፅ “የመንግስት እጅ ያለበት ነፃ የኢኮኖሚ ስርዓት” መመስረቱን አስረድተዋል። ስለሆነም መንግስት በጥንቃቄ በተመረጡ ጉዳዮች ገበያው ሊፈፅማቸው በማይችል መስኮች እጁን ያስገባል። ልማታዊ ዴሞክራሲ መንግስት ማለት ይሄው ነው ብለዋል። መንግስት እጁን ያላስገባበት ካፒታሊዝም እንደሌለ በመናገር የእንግሊዝም ሆነ የአሜሪካ መንግስታት ልማታዊ መንግስታት እንደነበሩም ተናግረዋል።
በመቀጠል መነጋገሪያው ወደ አንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው ነበር። አቶ ሃብታሙ አገዛዙ በልማታዊ መንግስት ባህሪይ ስም እንቅፋት ናቸው ያላቸውን በማጥፋት የተመሠረተ በመሆኑ ለዴሞክራሲያዊ ሂደት መፈናፈኛ የማይሰጥ ስርዓት ነው ብሎታል። እስካሁንም ድረስ አንዱን ከአንዱ ከማምታታት ባለፈ ኢህአዴግ ስለልማታዊ መንግስት ግልፅ አለመሆኑን ጠቅሷል። በተለይ ከ1993 ዓ.ም “ተሃድሶ” በኋላ የመጣው የኢህአዴግ ባህሪ ልማታዊ አስተሳሰብን እያቀነቀኑ በስልጣን ላይ በመቆየት ገዢ የመሆን ፍላጎት መኖሩን፣ ልማት የሕዝቡና የሀገር ሳይሆን የገዢው ፓርቲ ህልውና ተደርጎ መታየቱን ከግምት የሚያስገባ እንደሆነና በዙሪያው ደግሞ እንቅፋት ይሆናሉ ብሎ የሚያስባቸውን ገለል በማድረግ፣ አስቀድሞ ይዞት በመጣው የፖለቲካ ባህሪው የሚነሳውን ማንነቱን በጉልበት እያሰፈነ የሚሄድ ስርዓት ነው ብሎታል።

ይሄ ስርዓት ደግሞ የቱንም ያህል ተሻግሮ ተሻሽሎ ቢመጣ ልማታዊ ባህሪውን ይዞ ለስልጣኑ እንቅፋት የሚሆኑትን በጠላትነት ፈርጆ መንቀሳቀሱን የጠቀሰው አቶ ሀብታሙ በዚህ ረገድ የግል ሴክተሩን ከማቀጨጭ ባለፈ ምሁራንን በጥርጣሬ እንደሚያይና የግል ሴክተሩን በፖለቲካ ካድሬ ከመምራት ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ ዳር ማግለሉን ጠቅሷል። ኢህአዴግ ሁሉንም አገልግሎ እያለ የተለየ ኀሳብ መስተናገድ ባልቻለበት ሁኔታ ዴሞክራሲ እንዴት ሊኖር ይችላል ሲልም ጠይቋል።

“ኢህአዴግ ከእኔ የተለየ አስተሳሰብ የያዘ በሙሉ መጥፋት አለበት ብሎ የሚያምን ስርዓት እንዴት አድርጎ ዴሞክራሲያዊ ግን ደግሞ ልማታዊ የሚሆነው” የሚለው አቶ ሀብታሙ አሁንም በልማትም ሆነ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ያስፈልጋል ብሏል።
የግል ሚዲያውን በተመለከተ የሬዲዮ ፋና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዱ እና አቦይ ስብሃት የሰጡትን አሉታዊ አስተያየት በተመለከተም አቶ ሃብታሙ ምላሽ ሲሰጥ የሚሚ ስብሃቱን ሬዲዮ ጨምሮ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የሕዝብ የመገናኛ ብዙሃን ፍርድ ቤት ባልወሰነበት ሁኔታ በሕግ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች “አሸባሪ ናቸው” እንደሚሉ በመግለፅ ከግሉ ሚዲያ በላይ መወቀስ ያለባቸው መሆኑን ጠቅሷል። በጥቅሉ በሂደት ይመጣል የተባለው ዴሞክራሲ ሂደቱ እየተደናቀፈ በሂደት ይመጣል ማለት ዘበት ነው። በርካታ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን እስር ቤት ወርውሮ ለብቻው እየፈረጠመ ያለ መንግስት ልማታዊ ባህሪ የለውም፣ የግሉ ሴክተር ከጠቅላላው የሀገሪቱ ሀብት ጂ.ዲ.ፒ 5.6 በመቶ በያዘበት አሳፋሪ ሁኔታ ፈጣን ልማት ሊረጋገጥ አይችልም። በኢትዮጵያ የግል ዘርፍ እድገት የልማት ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ጉዳይ ነው። የግል ዘርፉ በቀጨጨበትም ልማት አይመጣም። የግል ዘርፉን የሚያቀጭጭ፣ ምሁሩን የሚጠራጠርና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን “አሸባሪ” የሚል ስርዓት ልማታዊ ሊሆን አይችልም ብሏል። የፖለቲካ አለመረጋጋት ከመፈጠሩም በፊት ኢህአዴግ ከዚህ ባህሪው መውጣት እንዳለበትም ገልጿል። ለዴሞክራሲ ማበብ ወሳኝ የሆኑ ተቋማት ነፃነታቸው ማረጋገጥና ሚዲያውም መሀል ላይ ቆሞ ኅብረተሰብ የሚያገለግል መሆን አለበትም ሲል አስረድቷል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለውይይት የሚሆን ጽሁፍ ከማቅረባቸው ባሻገር ልማታዊነትና ዴሞክራሲያዊነት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ለማስረዳት ብዙ ብለዋል። አቶ ዛዲግ እምብዛም በሕዝብ የማይታወቁ (public personality) ባይኖራቸው በየጥናታዊ መድረኩ የኢህአዴግን አቋም ከሌሎች በተሻለ የሚያቀርቡ ወጣት ፖለቲከኛ ናቸው። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ናቸው።

ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የሚለውን የገዢው ፓርቲ አስተሳሰብ ለማስረዳት “የማይታረቅ ነው” የሚለውን የዶ/ር ዳኛቸውን፣ የዶ/ር ነጋሶን፣ የዶ/ር ያዕቆብን የአቶ ሀብታሙንና እንዲሁም የዶ/ር አብዲሳን የጥርጣሬ አቋም “የሚታረቅ ነው” በሚል የኮሪያና የታይዋንን ልምድ በማንሳት ለማስረዳት ጥረት አድርገዋል። ኮሪያና ታይዋን ልማታዊ መንግስታት ቢሆኑም ዴሞክራሲያዊ አለመሆናቸውን፣ ለዚህም ምክንያቱ የመጀመሪያው ደሞክራሲያዊ ላለመሆን ማስቻያ ምክንያት (enabling environment) መኖሩ ነው። ይኸውም በደቡብ ኮሪያም ሆነ በታይዋን ብዝሃነት አለመኖሩ፣ ሁለተኛው አርሦ አደሩ እርስ በርስም ሆነ ከገበያ ጋር የተገናኘ commercialized ስላልነበር መንግስትን የመቃወም ችሎታ አልነበረውም። እንዲሁም በወቅቱ ያሉት የደቡብ ኮሪያና የታይዋን መንግስታት ዴሞክራሲያዊ ያለ መሆን ፍላጎት (will) ነበረባቸው። ዴሞክራሲያዊ ያለመሆን ፍላጎታቸው የመጣው ደግሞ አክራሪ የቀኝ ኃይል (far right movement) በመሆናቸው፣ ሕዝባቸውን የሚጠራጠሩ መንግስታት ስለነበሩና ለአርሶ አደሩ መሬት አከፋፍለውትም ቢሆን አያምኑትም። እንዲሁም የሚፈሩት ሌላ ውጫዊ ጠላት የቻይና እና የሰሜን ኮርያ መንግስት ነበር። በእነዚህ ምክንያቶች ልማታዊ ቢሆኑም ዴሞክራሲያዊ አልነበሩም። ነገር ግን በሂደት ወደ ዴሞክሪሲ የተቀየሩት ተበትኖ የነበረው አርሶ አደር ምርት እየጨመረ ሲሄድ Commercialized ሲሆን፤ እርስ በርሱ በመገናኘቱ ለጭቆና የማያመች መሆኑ፤ በሌላ በኩል የመንግስታቱ ዴሞክራሲያዊ ያለመሆን ባህሪ የሶቪየት ኅብረት መፍረሱን ተከትሎ የሚፈሩት ጠላት ስላልነበረና የfar right movement ወደ መሀል መምጣቱን ተከትሎ ወደ ሶሻል ዴሞክራሲ መምጣት በመጀመራቸው ነው ይላሉ።

አቶ ዛዲግ ወደ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሲመጡ በመጀመሪያ ፖለቲካ ኢኮኖሚው በገበያ ያልተሳሰረ አርሦ አደር በመኖሩ ዴሞክራሲያዊ ላልሆነ አስተዳደር ሊመች ቢችልም በሀገሪቱ ከፍተኛ ብዝሐነት አለ ብለዋል። በሀገሪቱ የብሔር የሃይማኖተና የጾታም ብዝሃነት በመኖሩ። ይሄንን አቻችሎ ለመምራት ዴሞክራሲያዊ መሆን አስፈላጊ ነው ብለዋል። በእሳቸው አባባለ ብዝሀነትን ማስተናገድ ባለመቻላችን ከመፍረስ ጫፍ ደርሰን ተመልሰናል ብለዋል። ከዚህ አንፃር አሁን ያለው ስርዓት Undemocratic አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል አሁን ያለው መንግስት ፀረ-ዴሞክራሲ የመሆን ፍላጎት (will) የለውም ብለዋል። ለዚህ ኀሳባቸው ደግሞ እንደ መከራከሪያ ያቀረቡት ታጋዮች ለልማት፣ ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ትምርታቸውን አቋርጠው በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ለሞት ገብረው ያመጡት ስርዓት ነው ብለዋል። “ኢህአዴግ አክራሪ የቀኝ ኃይል አይደለም። ኢህአዴግ ሕዝቡን የሚጠራጠርና አርሶ አደሩን የሚፈራ አይደለም። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳሉት አርሶ አደሩ በሸካራ እጁ እቅፍ ድገፎ ያደርሰው አርሶ አደሩ ነው። እና ኢህአዴግ በአርሶ አደሩ ተፈጥሮ በአርሶ አደሩ እዚህ የደረሰ ሰርዓት ነው” ብለዋል። እንደታይዋንና ኮርያም የሚፈራው ሊውጠው የተዘጋጀ የጎረቤት መንግስት የጦርነት ስጋት ስለሌለበት በማንኛውም መመዘኛ ኢህአዴግ ፀረ-ዴሞክራሲያዊ የሚሆንበት ዕድል የለውም።
በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ከላይ የተጠቀሱት ተናጋሪዎች ኀሳብ ተጨምቆ ሲታይ ሁለቱ አስተሳሰቦች የሚታረቁበት መስመር ቁልጭ ብሎ የወጣ አይመስልም። ኢህአዴግ ልማት ቢልም እየተካሄደ ያለው ልማት በዋናነት በቻይና መንግስት ብድርና እርዳታ የሚካሄድ መሆኑና ከኅብረተሰቡ የልማት ጥያቄ አንፃር አርኪም በቂም አለመሆኑ በሌላ ወገን ደግሞ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በተመለከተ በሕዝቡም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገሪቱ ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አስጊ መሆኑ የኢሕአዴግን “ልማታዊ ዴሞክራሲ” ብዥታዊነት ይበልጥ ያንፀባረቀ የሚመስል ነው። ኢህአዴግ በንድፈ ኀሳብ የደቦና የመብትን ጥያቄ ሳይነጣጠሉ አስኬዳለሁ ሲል ተቃዋሚዎቹ ደግሞ መብት ይረጋገጥና ከዛ ደቦው (ልማቱ) ይከተላል የሚል ኀሳብ እያንፀባረቁ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በዚያኑ ዕለት አንድ ወጣት የዩኒቨርስቲ ተማሪ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳቦ ወይስ ነፃነት ቢሉት ነፃነትን ይመርጣል” ማለታቸውን በማስታወስ ግራ መጋባቱንም ገልጿል።

በዕለቱ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ተቀራራቢነት ያለው የውይይት ኀሳብ ያቀረቡት አቶ ሞሼ ሰሙና የፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታምራት ገ/ጊዮርጊስ ነበሩ። ሁለቱንም አቅራቢዎች በልማታዊ ደሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የፕሬሱን ፈተና ዘርዝረዋል። በተለይ የአቶ ሞሼ ሰሙ ኀሳብ የፕሬሱ የአነሳስ ችግርና የመንግስትን ጫና በማያወላዳ ሁኔታ ጠቅሰውታል። ብዙዎቹ ተሳታፊዎች የአቶ ሙሼን ኀሳብ ዓይንን በማይስብ ማሸጊያ እንደታሸገ ግን ደግሞ ይዘቱ እንደሚጥም ብስኩት የመሰሉትም ነበሩ። የአቶ ሞሼን የጥናት ሃሳብ በሌላ ጊዜ የምንጠቃቅሰው ይሆናል።

ጋዜጠኛ ታምራትም ለጋዜጠኝነት ሙያ ሉአላዊነት ተሟግቷል። ሙያውን ፖለቲከኞች በራሳቸው አሰላለፍ ለማካተት የሚሄዱበተን ጥረት ትክክል እንዳልሆነ ገልጿል። የጥናት ኀሳቡ ከሕገ-መንግስቱ አንፃር በመሆኑ ሕገ-መንግስቱ የነፃነት ሰነድ (Liberal Document) እንደሆነ አስገንዝቧል። ምንም እንኳ በሕገ-መንግስቱ የመልማት መብትንና የብሔር ብሔረሰብ የቡድን መብትን በመጥቀስ ወደ ልማታዊ ሕገ-መንግስት የሳቡት ቢኖሩም ታምራት ግን ሕገ-መንግስቱ መሠረታዊ የመናገር፣ የመፃፍና ሌሎች የግለሰብ መብቶችን በበቂ ሁኔታ ያካተተ በመሆኑ የነፃነት ሰነድ በማለት ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ከልብ ወደማይወዱት ሊብራሊዝም ስቧቸዋል።

ጋዜጠኛ ታምራት በስራ ላይ ያለውን ሕገ-መንግሰት በውስጡ የተካተቱትን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማስላት፣ የመገንጠልና የቡድን መብት ጥያቄዎችን እንደሌሉ በመቁጠር `Liberal Document` ነው በማለቱ ተቃውሞ የቀረበበት ከኢህአዴግ ወገን ብቻም አልነበረም። ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ “አንተ ለሀብታም ስለምትፅፍ ነው” በሚል ኃይለቃል ፖለቲካ ቢፅፍ ኖሮ የችግሩን ገፈት ይቀምስ እንደነበር በገደምዳሜም ቢሆን አስተያየት ሰጥተውታል። ዶ/ር ዳኛቸው ታምራት ሕገ-መንግስቱ “የነፃነት ሰነድ ነው” ያለበት አገላለፅ የፖለቲካ ጉዳዮችን ፅፎ ቢሆን ኖሮ ይሄንን ቃል በሙሉ ልብ አይጠቀምም ከሚል መነሻ ሊሆን ይችላል። ያም ሆኖ በጋዜጠኛ ታምራት እምነት ሕገ-መንግስቱ የነፃነት ሰነድ ቢሆንም በአስፈፃሚው የሚወጡ ሕጎች ግን ሕገ-መንግስቱን የዘነጉ መሆኑንም ሳይጠቅስ አላለፈም።

በመጨረሻ የተናገሩት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ለዶ/ር ዳኛቸው መልስ የሰጡበት ነበር። አቶ ሽመልስ ዶ/ር ዳኛቸው ነፃ ፕሬስ የለም ማለታቸውን “ደፋር” በሚል አገላለፅ ከመቱት በኋላ “ኀሳባችንን የምንገልፅበት መድረክ አጣን” የሚለውን የዶ/ሩን ቅሬታ ከእኛ በላይ የመጽሔትና የጋዜጣ ፊት በየዕለቱ እየወጡ እንደልባቸው የሚያጨናንቁ ሰዎች ኀሳባችንን መግለፅ አልቻልንም ማለታቸው ቅጥፈት መሆኑን በመግለፅ ሚኒስትር ዴኤታው በሀገሪቱ ነፃ ፕሬስና ኀሳበን የመግለጫ መሳሪያ ችግር እንደሌለ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የውይይት መድረኩ የተሟሟቀ ነበር ማለት ይቻላል። በርካታ ሃሳቦችም ተፋጭተዋል። በጥቅሉ ፕሮፌሰር አብይፎርድ በመጨረሻ እንዳሉት የዴሞክራሲ ተራራ እየወጣን ነው ብለዋል። ተራራው ትክክል መሆኑን ማመን አለብን። አልፎ አልፎ ግን በውይይት ወቅት ሻካራ ስሜት ሊፈጠር፣ ሊኮሰኩስም ይችላል። ስለዚህ ዴሞክራሲያዊም ሆነ ልማታዊ ስንል ብዙ ጣጣ አለው። እነዚህን ችግሮች ክፍት በሆነ ውይይት ማስኬድ ነው። በመጨረሻም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መርህ የሚደረግ ውይይት በፈላጭ ቆራጭ ቋንቋ መሆን የለበትም ብለዋል

ፍኖት –ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ በባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የክብር መግለጫ ተበረከተላቸው

$
0
0

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ትላንት ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መከበር ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት በቅርቡ 93ኛ ዓመታቸውን ላከበሩት ሌተናል ጀነራል ጃገማ ኬሎ የክብር መግለጫ ምስክር ወረቀት እንዳበረከተላቸው የማህበሩ ምክትል ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

jagama_kello

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ም/ጸሀፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ለፍኖተ ነፃነት የሚከተለውን ብሏል “ሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ታላቅ ተጋድሎ የፈፀሙ ናቸው፤ ማህበራችንም በኢትዮጵያ አንድነት ዙሪያ ስለሚሰራ እንደነዚህ አይነት ጀግኖችን ክብር ይሰጣል፡፡ ለዚህም ነው ለሌተናል ጀረናል ጃገማ የክብር ምስክር ወረቀት የሰጠናቸው፡፡ ” አያይዞም “የብሔር ግጭቶች እንዳይፈጠሩና ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ እንዲያተኩሩ የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡” ሲል ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ ስለተሰጠው የክብር መግለጫ አብራርቷል፡፡

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመራሮችና አባላት ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ በመኖሪያ ቤት በመገኘት የክብር መግለጫ ምስክር ወረቀት ሲያበረክቱላቸው የአካላቸውን መድከም ተቋቁመው በሙሉ ወኔ ወጣቱ ትውልድ በዘር መከፋፈሉን ትቶ ኢትዮጵያን እንደቀድሞው አንድ ለማድረግ እንዲታገል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ወጣት ጥላዬ ተናግሯል፡፡

አቡጊዳ –ከሳኡዲ የተለመሱ ተቃዉሞ ሊኦያሰሙ ሲሉ በፖሊስ ተበተኑ !

$
0
0

በሳዉዲ መንግስት በግፍና ጭካኔ ተባረው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ፣ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ፣ «መንግስት ትኩረት አልሰጠንም» በሚል ድምጻቸውን ለማሰማት የተሰባሰቡ ወደ 400 መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን በፖሊሲ እንዲበተኑ መደረጉን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ።

«ቦሌ አካባቢ ከሚገኘው ጊዜያዊ ማረፊያቸው፣ ከ400 በላይ ሆነው ቅሬታቸውን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማሰማት ያቀዱትን ቅሬታ አቅራቢዎች ፖሊስ በትኗቸዋል፡፡ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መሀከል ከ20 የማይበልጡት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አቅራቢያ ቢሰባሰቡም ፖሊሶች አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እያስገዷቸው መሆኑን በስፍራው ያለው የፍኖተ ነፃነት ሪፖርተር ዘግቧል» ሲል ነበር ፍኖት የዘገበዉ።

የሳዉዲ ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰው በነበረ ጊዜ፣ ባለስልጣናቱ ከነርሱ ጋር ፎቶ በመነሳት፣ ለስደተኞች የሚያስፈልገው እንክብካቤ እንደሚደረግ ሲገጽሉ እንደነበረ ይታወቃል። ኢቲቪ ስደተኞችን በአይሮፕላን ማረፊያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ ብነስደተንጮ የተሰጡ የምስጋና መልእክቶችን በማስተላለፍ፣ የስደተኞችን ጉዳይ ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርጎት እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነዉ።

በባህር ዳር ሰልፍ በአድዋና አዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅቶች ይኖራሉ –አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው። በአድዋ እና በአዲስ አበባ ከሌሎች ደርጅቶ ጋር በጋራ በመሆን (ሚአድ፣ አረና፣ ትብርር፣ መድረክ..) ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቡ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በማሰብ ትልቅ አከባባር ለማድረግ ነው የታቀደው። በአድዋና በአዲስ አበባ ባሉ ብዙ ህዝብ ሊይዙ በሚችሉ አደባባዮች አከባበሩ ሊደረግ እንደሚችል ግምት ቢኖርም ፣ የአንድነት ፓርቲ የአከባበሩ ይዘት፣ ሰዓትና ቦታን ገና ይፋ አላደረገም።

በባህር ዳር የሚደረገዉ ግን ከአድዋና ከአዲስ አበባዉ የተለየ ነዉ የሚሆነው። በቅርቡ የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው፣ በክልሉ የሚኖረው ሕዝብ ላይ የሰነዘሩት ጸያፍና ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አባባሎችን በመቃወም የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ጉዳዩ አንድ ሰው የተናገሩት ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ እንደዚህ አይነት ሕዝብን የናቀና ያዋረደ አስተያየት የሰጡ ባለስልጣን ከሃላፊነታቸው ወዲያዉኑ እንዲነሱ አለማድረጉ፣ በሕግም አለመጠየቁ፣ ችግሩ ከግለሰብ አልፎ ድርጅታዊ መሆኑንም የሚያመላክትበትም ሁኔታም አለ።

«የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል»፣ «አማራዉ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው»፣ «የአማራዉ ሕዝብ የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት» …. የመሳሰሉ አስተያየቶችን ነበር ባለስልጣኑ የሰነዘሩት።

ሰልፍ መጥራት በራሱ ለዉጥ አያመጣም። በባህር ዳር፣ አድዋ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ የሚደረጉ ሰልፎችና ዝግጅቶች በማይሻማ መልኩ ፖለቲካዉን እንዲያናጉት፣ የማያሻማና የሚያስተጋባ መልእክት እንዲያስተላለፉ ከተፈለገ፣ ሕዝብ በነቂስ መዉጣት አለበት። ለዚህም ትልቅ ድርጅታዊና የቅስቀሳ ሥራ መስራቱ የግድ ነዉ። በየወረዳው፣ በየመንደሩ ፣ ቅስቀሳዎች መደረግ አለባችው። በራሪ ወረቀቶች፣ ፓምፍሌቶች በስፋት መዘጋጀትና መበተን ይኖርባቸዋል።

አንድ ነገር አንርሳ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ካልደገፍናቸው፣ ከጎናቸው ካልቆምን ፓርቲዎቹ ብቻቸውን በራሳቸው ምንም ሊያመጡ አይችሉም። ገዢው ፓርቲ የሚተማመነው በያዘው ጠመንጃ፣ ባሰማራቸው ሰላዮቹና ካድሬዎችቹ ነዉ። አንድነቶች ግን የሚተማመኑት በሕዝብ ጉልበት ብቻ ነው። እያንዳንዳችን የድርሻችንን ከተወጣን፣ በአዲስ አበባ፣ በአድዋና ባህር ዳር የምንኖር የሚደረጉ ሰልፎችን እና ዝግጅቶችን ከተቀላቀልን፣ ነጋሪና ቀሳቅሽ ሳንፈልግ፣ በኛዉ አነሳሽነት ቅስቀሳ ካደረግን፣ ተዓምር የማንሰራበት ምንም ምክንያት የለም።

በሰልፉ ለመገኘት የማንችል ደግሞ፣ በተለይም በዉጭ አገር ያለን፣ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከማሳወቁ በተጨማሪ፣ በገንዘባችን ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል።

አንድነት –አንድነት በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙ 34 ዞኖች ተጨማሪ ቢሮ ለመክፈት እንቅስቃሴ ጀመረ


ጉራማይሌ ፖለቲካ ክፍል 1 ( ጎንደር እና ጥምቀት) –ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡

የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው ቦታዎች የሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ፣ ሰማያዊውን ፅድቅ ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊው አከባበርም በእጅጉ ስለሚማርክ ጭምር ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በወዳጆቼ ጋባዥነት የዛሬ አስራ አምስት ቀን በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝቼ ነበር፤ በወቅቱም የታዘብኩት ጉዳይ ከሺህ ዓመታት በፊት የተፈፀመ አንድ ክስተትን እንዳስታውስ ገፊ-ምክንያት ሆኖኛል፤ ይኸውም በዘመነ ኦሪት የምድረ ባቢሎን ሰዎች አምላካቸውን ከመንበረ ሥልጣኑ ለመገልበጥ አሲረው ወደ ሰማይ የሚያወጣቸውን ታላቅ ግንብ መገንባት የጀመሩ ጊዜ አምላክ በድርጊታቸው ተቆጥቶ ቋንቋቸውን በማደበላለቁ ውጥናቸው በአጭር እንደተቀጨባቸው በመፅሀፉ የተተረከ ነው፡፡ …እነሆም ይህ በሆነ ከሺህ ዓመታት በኋላም የጎንደር ሕዝብ እና መንግስት በአንድ አደባባይ፣ በአንድ ድግስ ላይ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የመግባባት መንፈስ ርቆባቸው፣ ጉራማይሌነታቸው ደምቆ አስተውያለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ኢህአዴግ መራሹ-መንግስት ከበረሃ ‹የብሔር ፖለቲካ› የተሰኘ መርዝ ቀምሞ መምጣቱ ሳያንስ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን (ባንዲራችን) ላይም ኮከብ ይሉት ዲሪቶ ለጥፎ ‹ጨው ቢጠቀለልበት፣ ስኳር ቢቋጠርበት… ምንድን ነው? ያው ጨርቅ ነው!› ማለቱ ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ እጅግ አስቆጥቶት ነበር፡፡ በነዚህና መሰል ድርጊቶቹም የተነሳ ግንባሩ በሀገር ጉዳይ ላይ ዛሬም ድረስ መናፍቅ ተደርጎ ተቆጥሯል፤ ደግሞም ነው! ምክንያቱም ያቺ ልባችንን በደስታ የምትሞላው ባንዲራ እስከ ደርግ ውድቀት ጧትና ማታ በክብር ስትሰቀልና በክብር ስትወርድ ነው የኖረችው፡፡ ያን ጊዜ በየመንገዱ መኪና ውስጥ ያለው ከመኪናው ወርዶ፣ እግረኛውም የደረሰበት ቦታ ላይ ቀጥ ብሎ ቆሞ፣ ጠዋት ከፍ አድርጎ ሲያውለበልባት፣ አመሻሻ ላይ ደግሞ በዝማሬ አውርዶ በክብር አጣጥፎ ሲያስቀምጣት ማየት በእውነቱ ልብን በከፍተኛ ሃሴት ይሞላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ግና! ዛሬ ዘመን ተቀይሮ፣ ታሪክ ተሽሮ ስንት የደም መስዋዕትነት የተከፈለባት ውድ ባንዲራችን በተሰቀለችበት ዞር ብሎ የሚያያት ጠፍቶ ተበጫጭቃ ሰርግ ቤት የተጎዘጎዘ ወረቀት መስላ መታየቷ በቁጭት አንገብግቦ፣ በሀዘን ልብ ይሰብራል፡፡ እናም ብዙሃኑ ባንዲራ የሚያውለበልብበት አጋጣሚ በተፈጠረ ቁጥር ከፍ የሚያደርጋት ያችኑ ንፅኋን (የድሮዋን) ሰንደቅ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ይሁንና ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ድንገት ከእንቅልፉ የባነነው ኢህአዴግ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሁሉ መውለብለብ ያለበት ኮከብ የታተመበት ባንዲራ ብቻ እንዲሆን በአዋጅ እስከመደንገግ ደርሷል፡፡ ይህንንም አዋጅ ተከትሎ በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች ባንዲራን በተመለከተ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡

ሰሞኑን በጎንደር ከተማ ያያሁት ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፤ ባንዲራችን የባህላዊም ሆነ ኃይማኖታዊ በዓላት ዋነኛ አድማቂ መሆኗ ነባር ልማድ ነው፤ እናም ጎንደር ላይ ዘንድሮ የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት በታቦታቱ ዙሪያ በተለያየ መልኩ የተዘጋጀውም ሆነ ሕዝቡ ያነገበው ሰንደቅ፣ አገዛዙ ‹‹ከዚህ ውጪ…›› ብሎ ለእስር እንደሚዳርግ በአዋጅ የለፈፈለትን ባለ ኮከቡን አይደለም፤ ይልቁንም በብዙሃኑ የሀገሬ ሕዝብ ልብ ላይ የታተመችውን ያችን ንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ ብቻ ነበር፡፡ …ኩነቱም የፓርቲ ‹ፖለቲካዊ ፍቺ› ሰጥቶ ሰንደቁን ላዥጎረጎረው ኢህአዴግ ‹‹እመራዋለሁ›› ከሚለው ሕዝብ ያለውን ዕርቀት አመላካች ሆኖ አልፏል፡፡

ሌላው የዕለቱ ጉራማይሌ ክስተት በተለያየ ቅርፅ የተሰሩ፣ የኢትዮጵያን መልከዓ-ምድር የሚያሳዩ ሶስት ግዙፍ ካርታዎች በመኪኖች ላይ ተጭነው ለዕይታ አደባባይ መቅረባቸው ነው፤ እነዚህ ካርታዎች የሚያመላክቱት የሀገራችን ሰሜናዊ ድንበር መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ ትግራይ ላይ ተገድቦ እንዲቀር ከሻዕቢያ ጋር የተዋዋሉበትን አይደለም፤ ስመ-ጥሩው ጀግና አሉላ አባነጋ ጦሩን ሰብቆ ‹ቼ ፈረሴ› ብሎ እስከጋለበበት ቀይ ባህር ድረስ የሚዘረጋውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ይዞታ ያካተተ እንጂ፡፡

ይህ መሳጭ ትዕይንትም ሕዝብና መንግስት ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት መደማመጥ የማይችሉ (ቋንቋቸው የተደበላለቀባቸው) ሆነው እዚህ እንደደረሱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጉራማይሌ ግንኙነት ገፊ-ምክንያት ደግሞ የጎንደር ሕዝብ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አልነበረም፤ ገዥው ፓርቲ ይቺን ሀገር ለመመስረት እልፍ አእላፍ ቀደምት አባቶች የሞቱላትን፣ ታሪክ የተሰራባትን ባንዲራ በማን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አህሎኝነት ያሻውን የለጠፈባት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ያላስከበረ የሀገር ግንጠላ ላይ መሳተፉ የፈጠረው ቁጭት ነው፡፡…መቼም የዕለቱን ኩነት ቋራ ሆቴል በረንዳ ላይ ከእኛ በጥቂት ሜትሮች ዕርቀት ተቀምጦ ቁልቁል ሲከታተል የነበረው በረከት ስምዖንየተጠናወተው የእብሪት ፖለቲካ አይነ-ልቦናውን ካልጋረደበት በቀር ይህ ጉዳይ የሚያስተላልፍለት አንዳች አገራዊ ምስጢር ያለው መሆኑ አይጠፋውም፡፡

ጉራማይሌ ፖለቲካ ክፍል 2 ዛሬም መሬት ማስወሰዱ ቀጥሏልን? –ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

ከእነዚህ ክስተቶች በተጨማሪ በአካባቢው የተመለከትኩት ከባድ ውጥረት አለ፤ ይኸውም ‹ለሱዳን ሊሰጥ ነው› እየተባለ የሚነገርለት የመሬት ጉዳይ ካመጣው ጣጣ ጋር የሚጋመድ ነው፤ በርግጥ በአንዳንዶች ዘንድ መሬቱ ወደ ውስጥ ስልሳ (60)፣ ወደ ጎን ደግሞ አንድ ሺህ (1000) ኪሎ ሜትር ድረስ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡ ይሁንና በግሌ ይህ ክስ ማረጋገጫ የሚቀርብበት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡

በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ ለመሆንም በዚህ በተጠቀሰው የመሬት ስፋት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ከተሞችን መመልከቱ የተሻለ በመሆኑ፣ በቀጥታ ከሱዳን ጋር ከሚዋሰኑ ሁለት ከተሞች አንስተን እናስላው፤ እናም ከመተማ ከተነሳን ሸህዲን፣ ወህኒ፣ ነጋዴ ባሕር እያልን ጭልጋን እናገኛለን፡፡ መነሻችን ከሌላኛው የወሰን ከተማ ተሂ ከሆነ ደግሞ ምንጁግጁግ፣ ወዲ በርዚን፣ ኩሊት፣ ሸንፋ፣ ማሕበረ-ስላሴ ገዳምን አልፈን ደንገል እንደርሳለን፡፡ እንግዲህ የሰማነው ወሬ እውነት ከሆነ እነዚህ መሬቶች ሁሉ ለሱዳን ተሰጥተዋል ማለት ነው፡፡ ግን ለምን? ኢህአዴግ እንዲህ ሙጭጭ ብሎ የያዘውን ሥልጣን ሊያሳጣው የሚችል ውሳኔ ላይ ለመድረስ (ከተሞቹን ለሱዳን ለመስጠት) የተገደደበት ምን ምክንያት አለ? በነገራችን ላይ ይህ አስተያየት ስርዓቱ ለሀገር ጥቅም ይቆረቆራል እንደማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ክፉ ቀን ሥልጣኑን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ሁኔታ ከገጠመው ሀገር ከመበታተንና ከማፈራረስ የሚመለስ አለመሆኑን የቀድሞው ተሞክሮዎቹ ይነግሩናል፡፡

የሆነው ሆኖ ሊተኮርበት የሚገባው ኢህአዴግ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሳይሰጥ ያደፈጠበት አንዳች የሸሸገው ሚስጥር ቢኖር ነው የሚለው ይመስለኛል፤ የዚህ መነሻ ምክንያታችን ደግሞ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በድብቅ ለሱዳን የሰጣቸው (ዛሬ ተወሰዱ ከሚባሉት ውስጥ የማይካተቱ) መሬቶች የመኖራቸው እውነታ ነው፤ ይኸውም ብአዴን የመሰረተው ‹‹ዘለቀ እርሻ›› የተሰኘው ድርጅት በአንድ ወቅት ያስተዳድራቸው የነበሩት አብደረግ እና ደሎል (ሽመል ጋራ እና ምዕራብ አርማጭሆ) ውስጥ በቁጥር ከአንድ እስከ ስምንት የተሰየሙ ግዙፍ የእርሻ መሬቶች ነበሩ፤ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ከቁጥር ሁለት እስከ ስምንት ያሉትን (በድምሩ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ሄክታር የሚደርሱ) መሬቶችን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይህንንም ተከትሎ ‹‹ዘለቀ እርሻ›› እንቅስቃሴ አልባ ሆኗል፡፡ በርግጥ ‹ቆራጦቹ› የብአዴን አመራሮችም ቢሆኑ እንዲህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ አይክዱም፤ ይልቁንም ‹ቀድሞውንም ግማሹ ይዞታ የእነርሱ ነበር› ብለው ያስተባብላሉ እንጂ፡፡ …ግና! ማን ነበር ‹‹ከሱዳን ነጥቀን የወሰድነው መሬት አለ!›› ያለው? መለስ ዜናዊ ይሆን?

እንዲሁም ‹‹ስናር›› የተባለው ከፊል ቦታ ለሱዳኖች መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ሰምቻለሁ፤ ርግጥ ስናርን ሱዳኖች እንዲቆጣጠሩት በር የተከፈተላቸው የደርግ መንግስት በወደቀበት ማግስት (በ1983 ዓ.ም መጨረሻ) ነው፤ የዚህ ስጦታ መግፍኤ በትግሉ ዘመን ሱዳን ኢህአዴግን ‹አቅፋና ደግፋ› ለድል እንዲበቃ ያበረከተችው ውለታን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ይነገራል፡፡ እናም ሱዳኖች እንደ መና የወረደላቸውን ያልታሰበ ገፀ-በረከት ለመጠበቅ ወደ አስራ ሁለት ገደማ የሚደርሱ ወታደራዊ ካምፖችን መስርተው እስከ 1988 ዓ.ም ድረስ የምድሪቱን በረከት ሲቀራመቱ መቆየታቸው እውነት ነው፡፡ ይሁንና በ1988 ዓ.ም በወቅቱ የሱዳን መንግስት አፈ-ጉባኤ የነበረው ሃሰን አል-ቱራቢ እጅ እንዳለበት የተጠረጠረውን በአዲስ አበባ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንነት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ ኢትዮጵያና ሱዳን (በተለይም ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠትና ባለመስጠት ጉዳይ) ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህን ጊዜም ኢህአዴግ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ‹‹መሬታችሁን አስመልሱ›› በሚል ቀስቅሶ በሱዳናውያን ላይ ያዘምታቸውና ድል ያደርጋሉ፤ ስናርም ተመልሳ በኢትዮጵያውያን ይዞታ ለመጠቃለል በቃች፡፡ ግና! አሁንም እንቆቅልሽ በሆነ ሁኔታ (ከ1999 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ) እንደገና ወደ ሱዳን ተላልፋ ተሰጠች፤ በነገራችን ላይ ስናር በሃያ ስድስት ‹‹ኮርድኔት›› የተከፋፈለች ስትሆን፣ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ይዞታ ሊባል የሚችለው ‹‹ኮርድኔት 24›› በተሰኘው ውስጥ ባለፈው ዓመት ህይወታቸው ያለፈውና በርካታ ታጣቂዎችን ማስከተሉ የሰመረላቸው ባሻ ጥበቡ እና አስመሮም መኮንን የተባሉ ግለሰቦች ለሱዳናውያን ሳያስረክቡ፣ በራሳቸው ኃይል ተገዳድረው ያቆዩት መሬት ነው፡፡ በተቀረ በአካባቢው የምናገኛቸው ኢትዮጵያውያን ከሱዳናውያን ላይ በአረብኛና እንግሊዘኛ በተፃፈ ውል በተከራዩት መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡

በአናቱም በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ሊሰጡ ነው እየተባለ የሚነገረው እንደ መተማ-ዮሀንስ፣ ዳፋ፣ ሽመል ጋራ፣ ፎርኹመር፣ አብዱራፊ፣ ነፍስ ገብያ፣ አለቃሽ (በረሃማ አካባቢ ነው)… የመሳሰሉ ከተሞች ስማቸው ተደጋግሞ በመነሳቱ፣ አካባቢውን ውጥረት ውስጥ ከትቶታል፡፡ በርግጥም ከአገዛዙ ያደረ ታሪክ አኳያ መሬቶቹን አይሰጥም ተብሎ አይታሰብም፤ በተለይም ጉዳዩን ለጥጠን የሰሜን አፍሪካ አብዮት በፈጠረበት ስጋት፣ በድንገቴ ውሳኔ እየገነባ ካለው የ‹‹ህዳሴ ግድብ›› ጋር አነፃፅረን ካየነው፣ የሱዳንን ድጋፍ ለማግኘት መሬቶቹን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል ወደሚል ጠርዝ እንገፋለን፡፡ …ግና! ይህ አይነቱ ኢህአዲጋዊ ድፍረት ‹‹አባትየው ቢሞት የለም ወይ ልጅየው?›› በሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ ‹‹ተሰጡ›› ወይም ‹‹ሊሰጡ›› ነው ብለን የምንጫጫባቸው መሬቶች‹‹የይገባኛል›› ጥያቄ ያልቀረበባቸው በመሆኑ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ ‹በባሌ ሲጠብቁን፣ በቦሌ ገባን› እንዲል፣ ስርዓቱ ሆነ ብሎ ከእውነታውአርቆ ለማደናገር የሚጠቀምባቸው አጀንዳዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መጠርጠሩ አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ጉራማይሌ ፖለቲካ ማለት ይህ ነው፡፡

ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ኢህአዴግ በእነዚህ አካባቢዎች እያደረገ ያለው የሚከተለው መሆኑ ነው፡- ከኩሊት እስከ ቋራ ድንበር ድረስ ከወሎ፣ ከጎጃም እና ከጎንደር ነዋሪዎች አሰባስቦ የመልሶ ማስፈር ስራ ሰርቷል፤ የሰፈራው ዋነኛ አላማም ለም መሬት ይዘው እያረሱ ቤተሰብ መስርተው እንዲቀመጡ ያማቻቸላቸውን ሰፋሪዎች መሳሪያ በማስታጠቅ በአካባቢው በኩል ሊመጡ የሚችሉ የኃይል አማራጭን የሚከተሉ ተቃዋሚዎችን እንዲከላከሉ እና ከአቅማቸው በላይ ሲሆን ደግሞ አስቀድመው መሬት ለሰጣቸው መንግስት እንዲያሳውቁ ማድረግን ያሰላ ነው፡፡ በዚህም ለሥልጣኑ አስጊ የሆነውን ቀዳዳ ለመድፈን እየሞከረ እንደሆነ መረዳት ይቻላል (በነገራችን ላይ ከጎንደር ተቆርሶ ለትግራይ መሬት ተሰጥቷል የሚል አደገኛ ቅስቀሳም እየተካሄደ ነው፤ በግሌ ይህ ጉዳይ የሚያወዛግብ አይመስለኝም፤ ስርዓቱ ያነበረውን ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም የማንደግፈው እስከሆነ ድረስ መሬቱ ወደ የትኛውም የሀገሪቱ ክልል ቢሄድ ለውጥ አይኖረውም፤ ምክንያቱም በኢህአዴግ ግብዓተ-መሬት ላይ የሚያብበው መልከዓ-ምድራዊ ፌደራሊዝም (Geographical Federalism) እነዚህን አጨቃጫቂ መሬቶች ለአስተዳደር አመች በሆነ መልኩ ማዋቀሩ አይቀሬ ነውና)

ጉራማይሌ ፖለቲካ ክፍል 3 (አያሌው ጎበዜና ባሕር ዳር) –ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

አቶ አያሌው ጎበዜ ድርጅቱን የተቀላቀለው አስተማሪ ሆኖ እየሰራ በነበረበት አዲስ ዘመን ከተማ በ1984 ዓ.ም ቢሆንም በተፋጠነ ሂደት የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈፃሚ አባል መሆን ችሎ ነበር፤ ከ1987-1992 ዓ.ም የክልሉ አስተዳዳሪ አዲሱ ለገሰ ምክትል ሆኖ ተሹሟል፤ በዮሴፍ ረታ የአስተዳደር ዘመን (ከ1992-97 ዓ.ም) ደግሞ መጀመሪያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ኃላፊ፣ ቀጥሎ አፈ-ጉባኤ ሆኖ ሰርቷል፡፡

ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት ሰሜን ሸዋ በቅንጅት እጩ ሲሸነፍ፣ አያሌው ደግሞ በማርቆስ ከተማ በባሶ ሊበን ወረዳ ሊያሸንፍ ችሏል (አሸናፊነቱ ምንም እንኳ እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ተወዳዳሪዎች በድርጅታዊ የድምፅ ስርቆት የተገኘ ቢሆንም) ከ1998 ዓ.ም አንስቶ እስከያዝነው አመት መጀመሪያ ወራት ድረስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ የቆየው አያሌው ጎበዜ ‹‹ለሱዳን ተሰጠ›› ወይም ‹‹ሊሰጥ ነው›› ከተባለ መሬት ጋር ተያይዞ የማጀገኑና የማንፃቱ ቅስቀሳ የኑፋቄን መንገድ የተከተለ ይመስለኛል (የጉዳዩ ስሁትነት የኛይቷን ‹ፋክት› መፅሄትንም ይጨምራል) በደፈናው ከዚህ ቀደም ‹አያሌው ለሱዳን በሚሰጥ መሬት ላይ አልፈርምም በማለቱ፣ ደመቀ መኮንን ፈረመ› የሚባል ምንጩ የማይታወቅ ወሬ ሁላችንም ጋ ደርሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከብአዴን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት፣ አያሌው ያውም ርህራሄ አልባ የነበረውን የጉልበታሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ውሳኔ ተቃውሞ ‹ፈርም›፣ ‹አልፈርምም› አይነት አንጃ ግራንጃ የሚፈጥር ደፋር ልብ ያሌለው መሆኑን ነው፡፡

በግልባጩ ፖለቲካችን ጉራማይሌ ነውና ለብአዴን ፍቅር በሌላት ባሕር ዳር አያሌው ተወዳጅ እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ የተወዳጅነቱ ሚስጥር ግን ከድርጅቱ ይልቅ ‹‹መረጠኝ›› ለሚለው ሕዝብ ታማኝ በመሆኑ እና በሀገር ጥቅም ከእነ ‹ኦቦ› አዲሱ ለገሰ ተሽሎ ሳይሆን፣ ከራሱ የግል ባህሪና ሰብዕና ጋር ስለሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ካሉ ነዋሪዎች እና አብረውት ከሚሰሩ የበታች ሰራተኞች ጋር የመሰረተው ማሕበራዊ ግንኙነት ዋነኛው ነው፤ በርግጥም የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው ሲሞት ቀብር ላይ ይገኛል፤ ማታም እዝን ይዞ በመሄድ ሲያፅናና ያመሻል፤ ሰርግን በመሳሰሉ የደስታ ዝግጅቶችም ላይ እንዲሁ ይሳተፋል፤ እነበረከት ስምዖን ለሚያቀነቅኑት ግራ ዘመም ፖለቲካም ሩቅ በመሆኑ፣ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ባህሪይ ይስተዋልበታል፤ ለአብነት እምነቱ የሚያዝዘውን (ከመፆም ጀምሮ በቤተ-ክርስቲያን ተገኝቶ እስከ ማስቀደስ ያሉ ጉዳዮችን) እንደ ባለሥልጣን ግብዝ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተራ አማኝ ዕለት ተዕለት ሲፈፅም ይታያል፡፡ በቤተሰብ አስተዳደርም ቢሆን አራት ልጆቹን መንግስት ትምህርት ቤት ከማስተማር አልፎ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ስነ-ምግባር ማሳደጉን፣ ብልሹ አድርገው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ካሉ ከአንዳንድ ኃላፊነት ከማይሰማቸው ባለሥልጣናት ጋር አነፃፅረው የሚያመሰግኑት የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በህክምና በማዕረግ የተመረቀችውን ብቸኛና የመጀመሪያ ሴት ልጁንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡

በአናቱም የትኛውም ባለ ጉዳይ ቢሮው ሲመጣ ያለ ቢሮክራሲ ማስተናገዱም ሆነ ለሚቀርብለት አቤቱታም ጥያቄ ‹አይሆንም› አለማለቱን እንደ በጎ ተግባር የቆጠሩለት ሰዎች ለሰውየው ገፅታ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተቀረ ኢህአዴግ እንደ አሰባሰባቸው በርካታ ባለስልጣናት እርሱም አለቆቹን አብዝቶ የሚፈራ ሽቁጥቁጥ ሰው መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በተለይም የብአዴን ካድሬዎች ‹‹ሽማግሌው›› እያሉ በሹክሹክታ የሚጠሩትን አዲሱ ለገሰን እና ሞገደኛውን በረከት ስምዖንን የ‹መለአኩ ገብርኤል› ያህል እንደሚፈራቸው ሰምቻለሁ፡፡

ይህ ፍራቻውም በፍትሕ እና በሙስና ቢሮዎች አካባቢ ከብቃት ይልቅ ‹‹የራሴ›› የሚላቸውን የትውልድ መንደሩን ሰዎች በመሾሙ ‹‹እመራዋለሁ›› የሚለውን ሕዝብ ለከፋ ብሶትና መከራ አጋልጦ ነው ከሥልጣኑ የተሰናበተው፡፡ ይህም ሆኖ ከኃላፊነቱ ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረበ ከአንድ አመት በኋላ ነው ፓርቲው ያፃደቀለት፤ ያለፈውን ሙሉ ዓመትም በቢሮው ከመገኘቱ እና በትላልቅ ጉዳዮች ላይ ከመሳተፉ ባለፈ፣ ሁሉንም ሥራ ሲሰራ የነበረው ዛሬ በምትኩ የተሾመው የዋድላ ደላንታው ገዱ አንዳርጋቸው ነው፤ ገዱ ድርጅቱን የተቀላቀለው ከአያሌው አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ዋድላ ደላንታን ኢህአዴግ ከደርግ መዳፍ በኃይል ነጥቆ በወሰደበት ወቅት ነበር፤ ያን ጊዜ የገበሬ ማሕበር ሕብረት ሱቅ ሠራተኛ የነበረው ገዱ ዛሬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለመሆን ችሏል፤ በርግጥ ይህ ሰው ጠንካራ ሠራተኛ እና የበላይአመራሮችን ተጋፋጭ እንደሆነ ይነገርለታል፤ እንዲሁም እንደ አያሌው ከሙስና ጋር ብዙም ንክኪ የለውም (በነገራችን ላይ የብአዴን ዋነኛአመራሮች ለሙስና ሩቅ እንደሆኑ በወሬ ደረጃ ይሰማል፤ ግና! ይህንን እንደምን ማመን ይቻላል? …በርግጥ በክልሉ በተዘዋዋሪ መንገድ የጀነራል አበባው ታደሰ ነው ከሚባለው ባለ አራት ፎቁ ‹‹አልዋቅ›› ሆቴል ሌላ በወሬ ደረጃ የአመራር አባላቱ ንብረት የሆነ አላጋጠመኝም፤ ነገር ግን እኔን አላጋጠመኝም ማለት ሰዎቹ ንፁሃን ናቸው እንደ ማለት አይደለም)

የሆነው ሆኖ ብአዴን በበረከት ስምዖን፣ በአዲሱ ለገሰ፣ በካሳ ተክለብርሃን፣ በታደሰ ጥንቅሹ እና በከበደ ጫኔ ስም የመሰረተው ‹‹ጥረት›› የተሰኘው ኮርፕሬሽን ዳሽን ቢራ፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ ዘለቀ እርሻ፣ አምባሰል አስመጪና ላኪ፣ ጣና ሞባይል እና ጣና ፍሎራ የተሰኙ የንግድ ድርጅቶችን ያስተዳድራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አትራፊ የሚባለው ዳሽን 49 ፐርሰንቱን እንግሊዝ አገር ለሚገኝ አንድ ቢራ አምራች ድርጅት ሲሸጥ፤ ጣና ሞባይልም በአሜሪካን ሀገር የታወቀው የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው ወልደሉዑል ካሳን ጨምሮ ለአራት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻን አስተላልፏል፡፡ ይህ ሁኔታም ድርጅቶቹ ትርፍና ኪሳራቸውን በውጪ ኦዲተር እንዲያስመረምሩ የሚያስገድድ መደላድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አሰራር የእነ አዜብ መስፍን መቀለጃ ከሆነው ‹‹ኤፈርት›› በተሻለ መልኩ ለዘረፋ እንዳይጋለጥ መታደጉ አከራካሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንግሊዛዊው ድርጅት የዳሽን ቢራ 49 ፐርሰንት ድርሻን ገዝቶ ሲያበቃ፣ ወጪና ገቢውን አይከታተልም ማለቱ ሩቅ ነውና፡፡

በትግራይ ሕዝብ ስም እየነገደ፣ ለህወሓት አመራር አባላትና ቤተሰቦች ብቻ መምነሽነሺያ የሆነው ‹‹ኤፈርት››ም በእንዲህ አይነት መልኩ ለውጭ ድርጅቶች ድርሻ እንዲሸጥ ካልተገደደ በቀር ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው፤ ይህ ሁኔታም የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠ ሁሉ የቻለውን የሚዘግንለት ከመሆን የሚተርፍበትን እድል ያመቻችለታል (በነገራችን ላይ እንደሚወራው የብአዴን አመራሮች ወደ ሙስና አለመግባታቸው እውነት ከሆነ፣ ምክንያቱ ጠፍጥፎ የሰራቸውን ህወሓት በመፍራት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በግልባጩ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚፈራው የለምና እንዲህ እንደቀለደ በሚቀጥለው ወር የተመሰረተበትን 39 ዓመት ለማክበር ሽር-ጉዱን ከወዲሁ ተያይዞታል)

ሌላው የብአዴን አመራሮች አስገራሚ ታሪክ ከዋነኞቹ መካከል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሕላዊ ዮሴፍን… የመሳሰሉት የትዳር አጋራቸውን ያጩላቸው አንዲት ሴት መሆናቸው ነው፡፡ እኚህ የዋግ ኡምራ ተወላጅ በታጋዮች ዘንድ ‹‹ማዘር›› እየተባሉ ሲጠሩ፣ ኢህአዴግ ውስጥ ባሉ አንዳንድ አሽሟጣጮች ደግሞ ‹‹ጣይቱ›› በሚል ቅፅል ስም ይታወቃሉ፤ ይህ ስያሜ የአጼ ምንሊክ ባለቤት የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ታላላቅ መኳንቶችን እየመረጡ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር ያጋቡ ነበር ከሚለው ትርክት የሚነሳ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ኩነት ጉራማይሌ የሚያደርገው የ1993ቱን የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ የብአዴን መሪዎች ‹‹ቦና-ፓርቲዝም››ን በአደባባይ ሲያወግዙና ሲተቹ መስማታችን ነው፡፡

(ቀሪውን ጉራማይሌ የፖለቲካ ወጋችንን በሚቀጥለው ሳምንት እመለስበታለሁ)

የእኛ ታሪክና የፖለቲካ ውጥንቅጥ፡- ጥቂት አሳቦች በሞገደኛው ተክሌ ወሥርጉተ ሥላሴ ጽሑፎች ላይ (ክፍል-፩-) በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ የተባሉ ጸሐፊ በተለያዩ ጊዜያት የሚጽፏቸውን በአብዛኛው ታሪካዊ የሆኑ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርስ አዘል፣ በኃይለኛው አገራዊ/ኢትዮጵያዊ ዘዬ፣ ትውፊትና ባህል የተጫነው የሚመስለውንና፤ (ይህን ለማረጋገጥ የሚወድ ጸሐፊዋ ‹‹ኢትዮጵያዊነት የሚነበብ መንፈስ ነው›› በሚል ርእስ ያስነበቡትንና ‹‹የኢትዮጵያዊነትህን መንፈስ በቅጡ ካልተረዳኸውና ካልተቀበልከው ‘ጉግ ማንጉግ’ የኾነ አንካሳ መንፈስ ይጨፍርብኻል፡፡›› እስከ ማለት የደረሱበትን፣ በኢትዮጵያዊነት ወኔ፣ ስሜትና ረቂቅ መንፈስ ፈጽሞ የሰከረውን መጣጥፋቸውን ማየቱ የሚበቃው መስለኛል፡፡) እንዲሁም ምክርና ትችት ዘመም የኾኑ፣ እንዲያም ሲል ‹‹የኢትዮጵያዊነት ወኔና ስሜት›› በእጅጉ ጎልቶ የወጣበትንና ያየለበትን መጣጥፎቻቸውን ለማንበብ ዕድሉ ገጥሞኛል፡፡

ይህችን ‹‹ዘመም›› የምትል አብዮተኛ ቃል ያለ ምክንያት አይደለም እዚህ ጋር የሰነቀርኳት፡፡ የትናንትናው ትንታግና አብዮተኛው ያ ‹‹ሩቅ አላሚ ቅርብ አዳሪ›› የኾነው ትውልድ ‹‹ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም!›› ብሎ ያቀጣጠለው የለውጥ አብዮት፣ ወደ ለየለት አሰቃቂና አስፈሪ ነውጥና ፍጅት ተለውጦ፣ በሂደትም ‹‹አብዮት የገዛ ልጆቿን እንኳን ሳይቀር ትበላለች!›› ወደሚል አስፈሪ ፃረ ሞትነት ተቀይሮ ‹‹በግራና ቀኝ ዘመም›› በሚል ምድሪቱን ‹‹አኬል ዳማ/የደም ምድር›› እንድትሆን ያደረገበትን ያን የእምዬ ኢትዮጵያን የጨለማና የሰቆቃ ዘመንዋን እግር መንገዴን ለማዘከር ጭምር ነው፡፡

ያችን በማኅፀንዋ አብራክ ክፋይ፣ በገዛ ልጆቿ የአብዮት ደም ጅረት ታጥባና ተነክራ፣ በኀዘንና በብርቱ ሰቆቃ መንፈሷ ደቆና ቅስሟ ተሰብሮ፣ የኀዘን ከል ለብሳ፣ ከዘመን የተኳረፈችውን ኢትዮጵያን፣ የዛን ጊዜው የቀ.ኃ.ሥ የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩት አንጋፋው ምሁርና ዛሬም እንኳን በእርጅናቸው ዘመን፣ በአብዛኛው የጥላቻና የመለያየት ነጋሪት ከሚጎሰምበት ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ለመፋታት አልሆንልህ ያላቸው፣ ጉምቱው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪነታቸው ዘመን በቋጠሯት ግጥማቸው/ስንኛቸው የዛን ዘመኗን እምዬ ኢትዮጵያን እንዲህ ነበር የገለጽዋት፡
-
ይኽው ትታያለች ለሕዝብ በይፋ፣
ጥቁር ተከናንባ ጥቁር ተጎናጽፋ፡፡
እኔስ መስሎኝ ነበር ዘመድ የሞተባት፣
የእናት ሞት የአባት ሞት፣
የልጅ ሞት ያጠቃት፣
ለካ እሷስ ኖራለች ዘመን የሞተባት፡፡

ውድ አንባቢዎቼ ያው እንግዲህ ዘንድሮ አብዮቱ ዐርባ ዘመንም እየሞላውም አይደል እንዴ?! እስከ ጥፋቱና ልማቱም ቢሆን የዚህ የዛሬው ትውልድ አባል የኾንኩ እኔ፣ ያ ትውልድ ለውድ እናት አገሩና ለወገኑ ከነበረው ፍቅርና መቆርቆር የተነሣ በእንባው፣ በላቡና በደሙ የከፈለውን ያን ግዙፍና ታላቅ መሥዋዕትነት የማደንቅ ብቻ ሳልሆን የውለታው ባለ ዕዳ ነኝም ብዬ ነው የማስበው፡፡ እናም እንዲህ እግር መንገዴንም ቢሆን ያን ትንግረተኛ ትውልድ ላነሳሳው፣ ልዘክረው ወደድኹ፡፡

በነገራችን ላይ እናንተ በዲያስፖራ የምትገኙ የዛ ትውልድና የታሪኩ ባለቤቶች የዛን ትንታግ ትውልድ የለውጥ እንቅስቃሴውን ለመዘከር አንዳንች ነገር አላሰባችሁም እንዴ! እስቲ ከጥላቻ ፖለቲካው፣ ከመለያየቱ፣ በጎሪጥ ከመተያየቱና ከመፈራረዱ ለአፍታ ወጣ በሉና እነዛን ደማቸውን ለሕዝቦችህ ፍትሕና ዕኩልነት፣ ለሰው ልጆች መብትና ክብር መስፈን፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕውን መሆን ሲሉ በየጎዳናው፣ በየጋራ ሸንተረሩና ተራራው ያፈሰሱትን የትውልዳችሁን/የጓዶቻችሁን ታሪክና ውለታ ለእኔና ለትውልዴ በፍቅር፣ በቅንነትና በበጎነት መንፈስ ልታስተላልፉን/ልታሳውቁን ሞክሩ፣ እሹም፡፡

‹‹ንግባኤከ ኀበ ቅድመ ነገር/ወደቀደመው ነገር እንመለስ›› እንዲል መጽሐፉ፡፡ ለዚህ ለዛሬው መጣጥፌ ዐብይ ምክንያት የኾኑኝ በኢትዮጵያዊነት ሕያው መንፈስና ቅናት እየነደዱና እየተቃጠሉ ያሉት ጸሐፊዋ ሥርጉተ ሥላሴ፣ የትናንትናው ወይም የዛሬው የእኔው ትውልድ አባል ይሁን አይሁኑ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ስለ ጉምቱ ብዕረኛው አቶ ተክለ ሚካኤልም ቢሆን እንዲሁ፡፡’

ለማንኛውም ግን ዋና አነሳሴ እነዚህን ብዕርተኞች በትናንትናውም ሆነ በዛሬው የትውልድ ተርታ ለማሰለፍ አይደለም፡፡ በተጨማሪም ታሪኩን በደሙ የጻፈውንና ያጻፈውን የትናንትናውን ትውልድ የትግል እንቅስቃሴውን ለመዘከርና ውለታውንም ለማሰብ ወይም ለማሳሰብ አይደለም፡፡ ግና በዚህ ጽሑፌ ሥርጉተ ሥላሴና አቶ ተክለ ሚካኤል በተለያዩ ጊዜያት ያስነበቧቸው መጣጥፎቻቸው አንዳንች የቅናት ስሜትን ስላጫረብኝ እኔም የበኩሌን ዕዳ ለመወጣት በማለት ነው ብዕሬን በድፍረት ያነሣሁት፡፡

የቀድሞው የኢሳት ቴሌቪዥን ባልደረባ የነበሩት ሞገደኛው አቶ ተክሌ በተለያዩ አገራዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎችና ክርክሮች ዙሪያ የሚያንሸርሽሯቸውን ጽሑፎች እከታተላለሁ፣ አደንቃለሁም፡፡ አቶ ተክሌ ከሰሞኑን ባስነበቡን መጣጥፋቸው በወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጀዋር መሐመድና ደጋፊዎቹ የተነሳውን የሰሞኑን ሚጢጢዬ አብዮት አስመልክቶ ኢህአዴግ ከሚያራምደው የብሔር ፖለቲካ አንፃርና በተቃራኒው ከአንድነት ኃይሎች አቋም ጋር በማዛመድ ‹‹ተወደደም ተጠላ የአንድነት ኃይሎች ለብሔር ፖለቲካ ሰፊ የመጫወቻ ሜዳ ለመስጠት ባለመቻላቸው በኢህአዴግ ተበልጠዋል፡፡

እናም እነ ጃዋርም ኾነ ለረጅም ዓመታት የኦሮሞን የመገንጠል ጥያቄ በብርቱ ሲያቀነቀኑ የነበሩ የኦሮሞ ብሔርተኞች፣ አንጋፋውን የኦነግ ታጋይ እነ ሌንጮን እንኳን ሳይቀሩ ቢያንስ ቢያንስ በመርህ ደረጃ ያን መብታቸውን በሚያከብርላቸውና በራሳቸው ቋንቋ የሚያስተዳድሩትን ክልል በሰጣቸው በኢህአዴግ ጉያ ውስጥ ለመወሸቅ እያኮበኮቡ ነው፡፡›› የሚል አንድምታ ያለው ጽሑፍን አስነብበውናል፡፡
የዲያስፖራውን ፖለቲካ በአለፍ ገደም በመተቸትና የሰሞኑን የኦሮሞ ብሔርተኞች ፀረ-ምኒልክ ዘመቻ አስመልክቶ በአንድነትና በብሔር ፖለቲካ አቀንቃኞች መካከል የተነሣውን፣ በአዲስ አበባውያኑ አራዳዎች የፌስ ቡክ አድማቂዎች ዘንድ ‹‹አቧራው ጨሰ›› የተተረተበትን የሰሞኑን ክስተት በማስመልከት አቶ ተክሌ ያሰፈሩትን አሳብ እህታችን ሥርጉተ ሥላሴ የሚመች ብቻ ሳይሆን የማይቀበሉትም እንደኾነ በሰፊው አትተው ጽፈዋል፣ ተጨባጭ ያሏቸውን ምክንያቶችንም በመደርደር ለመከራከር ሞክረዋል ፡፡

የእነዚህ ብዕረኞች ፍቅር፣ ቅንነትና ጨዋነት የተሞላው የአሳብ ልውውጣቸውና በምክንያት የተደገፈ ክርክራቸውም ይበል ሚያሰኝና አልፎ አልፎ በየድረ ገጹ፣ ጋዜጣውና መጽሔቶች ላይ ባልተገራ ብዕራቸውና ሰብእናቸው ብቅ እያሉ አሳብን በአሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ስድብና ጥላቻ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ፣ ፉከራና ቀረርቶ ለሚቀናቸውና፣ እንዲያም ሲል የስም ማጥፋት ዘመቻ (character assassination) ውስጥ ለሚዶሉ ጸሐፍቶቻችን ጥሩ ምሳሌና አርዓያዎች ናቸው ብዬ አስባለኹ፡፡

በመሠረቱ የእነዚህ ክቡራን ጸሐፊዎች የወንድማችን የአቶ ተክሌና የእህታችን የሥርጉተ ሥላሴ የሰሞኑን የአሳብ ልውውጥና ሙግት በአብዛኛው ትኩረቱን ያደረገው የብሔር ፖለቲካን በሚያራግቡና በተቃራኒው ደግሞ አንድነትን በሚያራምዱ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞቻችን ዘንድ ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ርቀት ለማሳየት፣ ለመገምገምና ለመተንተን የሞከረ ነው፡፡ ለዚህ የአሳብ ሙግት ዋና መነሻና ማድመቂያ የሆነው ደግሞ ከሰሞኑን ወጣቱ ከያኒ ቴዲ አፍሮ የዓፄ ምኒልክን የግዛት ማስፋፋት ወረራ አስመልክቶ በአንድ በአገር ውስጥ በሚታተም መጽሔት ሰጠው የተባለው ቃለ መጠይቅ በበርካታ የኦሮሞ ተወላጆች/ኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ የቀሰቀሰው ብርቱ ቁጣ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም የካናዳው ተክሌ ‹‹የኛ ነገር፡- የተሸነፈ ርእዮተ አገርና ገፊ ፖለቲካ›› በሚል ርእስ ባስነበቡት ጽሑፋቸው የአንድነት ኃይሉ ከተቸከለበት የአንዲት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ወጥቶ ብሔርተኝነትን ለሚያቀነቅኑ ብሔርተኛ ፖለቲከኞች ዕድል የሚሰጥ የፖለቲካ አጀንዳን በመቅረፅ ምቹ የመጫወቻ ሜዳ ለማዘጋጀት እስካልቻሉና እስካልደፈሩ ድረስ መጪው ጊዜ ለአንድነት አቀንቃኞች ከአሁን በበለጠ አዳጋችና ፈታኝ እንደሚሆንባቸው ምሳሌዎችን ጭምር በመጥቀስ ለመተንተን ሞክሯል፡፡

በአንፃሩም ሥርጉተ ሥላሴ ‹‹የማረተ ማጭድ ሸክም በሐቅ ጭብጥ ይረታል›› በሚል ርእስ ያስነበቡን ጽሑፋቸውን፣ በእነደ አቶ ተክሌ ያሉ ‹‹ኢትዮጵያዊነትንና የብሔር ፖለቲካን በተመለከተ›› የሚያራምዷቸው ጠንጋራ አመለካከቶች ውለው አድረው የትውልዱን ጤናማ መንፈስ እንዳይበክሉት ቀድሞ መከላከል ይገባል በሚል ጽኑና ቅን መንፈስ ተነሳስተው እንደጻፉት ይነግሩናል፡፡

ጸሐፊዋ ‹‹ኢትዮጵያዊነት የሚነበብ መንፈስ ነው›› በሚለው ጽሑፋቸውም ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ጸንቶ፣ አብርቶና ደምቆ የሚቆይ ረቂቅና ሕያው መንፈስ መሆኑን ለማስረዳት ረጅም ርቀት በመጓዝ የብሔር ፖለቲካ ያደረሰብንን ስብራትና ለወደፊቱም የተሸከመውን ክፉ አደጋ ለማሳየት ደክመዋል፡፡

ጸሐፊዋ በዚህ ስሜትም ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያዊነትን ከሚዋጋ ስሜት ያድነን!›› ዘንድም ተማፅነውልናል፡፡ በዚህ መካከል ደግሞ ኢትዮጵያዊነት የዘላላም ቅርሳችንና ቃል ኪዳናችን ነው፡፡ በሚሉና በተቃራኒው ደግሞ፣ ኢትዮጵያዊነት ሳንወደውና ሳንፈቅደው እንደ ኮሶ ተበጥብጦ በግድ እያነገፈገፈን የተጋትነው፣ እየቀፈፈንና እንደ አባ ጨጓሬ እየኮሰኮሰን የተደረበብን ማንነት ብለው በሚሉ ሰዎች ዘንድ እየተካሔደ ያለው አስጥ አገባ ከሰሞኑን ዳግም በአዲስ ኃይልና ጉልበት ተጠናክሮ የኢትዮጵያንና የዲያስፖራን የፖለቲካ ሰማይ ክፉኛ እያወደው፣ እያጠነውና እየናጠው ይገኛል፡፡

የባለፈው ሰሞን በእነ ጀዋርና ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ብለው በሚያቀነቅንቱ መካከል በማኅበራዊ ድረ ገጾች፣ በመጽሔቶችና በጋዜጦች፣ በየድረ ገጾቹ፣ በየፓል ቶኩ የሰማነው ጉድ፣ የጦር አውርድ ቀረርቶና ሽለላ፣ ስድብና ዛቻ፣ ጽንፈኝነት፣ መራር የሆነ ጥላቻና ቂም የሞላባቸው ሰቅጣጭ ሙግቶች የነገይቱን ኢትዮጵያ ህልውና እንደ ሕዝብም ደግሞ በሰላምና በመቀባበል ለመኖር ተስፋችን የደበዘዘ መስሎ እንዲታየኝ ነው ያደረገኝ፡፡

ቢቻለን፣ ብንወድና ብንፈቅድ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በአንድነት ለመኖር ካልሆነም ደግሞ ተለያይተንም ቢሆን በመልካም ጉርብትና ለመቀጠል የሚያስችለን ፍቅር፣ ቅንነትና በጎነት ምን ያህል እየራቁን እንደሔዱ እንዳስተውል አስችሎኛል፡፡

የረጅም ዘመናት ታሪካችን እንደሚነግረን ትናንትናም ሆነ ዛሬ ኢትዮጵያ ተብላ በምትጠራው ግዛት ውስጥ ያሉ ሕዝቦች የሚያስተሳስሯቸው ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እውነታዎች በርካታ ናቸው፡፡

እስቲ ኤርትራ ሂዱ ማነው ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከጉራጌ ሕዝብ ያልተዋለደ፣ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም ፣ ወደ ምስራቅም ወደ ምዕራብም ተጓዙ ይሄ ሕዝብ በደምና በአጥንት የተሳሰረ ሕዝብ ነው፡፡ እስቲ ወሎን ተመልከቱ ሃይማኖቱ ሳይገድበው ተዋዶና ተዋልዶ የሚኖር ታላቅ ሕዝብ ያለበት አገር/ምድር ነው፤ ወይስ የነበረበት ልበል ይሆን እንዴ!? ‹‹መሐመድ ኤልያስ፣ ትዕግሥት ሁሴን›› ተብለው የሚጠሩ አያሌ ሰዎች ዛሬም ድረስ ያጋጥማችኋል፡፡ የሃይማኖት ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ግና ፍቅር የተባለ አንዳንች ኃያልና ጽኑ አሸናፊ መንፈስ ሰንሰለት ሆኖ ያስተሳሰራቸው ሕዝቦች!!

በቅርቡ በሀገረ አሜሪካ አገር ሕይወታቸው ያለፈው ዕውቁ የታሪክ ምሁር ፕ/ር ታደሰ ታምራት ለዶክትሬት ድግሪ ድርሳናቸው የሚሆናቸውን ጥናትና ምርምር ለማድረግ ከሚማሩበት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተነስተው የውቦች አገር ወሎ ውስጥ ተገኝተው ነበር፡፡

ፕ/ር ታደሰ ለዚሁ ጥናታቸው ወደምታስፈልጋቸው አንዲት ጥንታዊት የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ለመጎብኘት እንደተዘጋጁ በዛች የገጠር ቤ/ን የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠባቂ የሆነ አንድ ግለሰብ የቤተ ክርስቲያኒቱን በር ከከፈተላቸው በኋላ፣ እኔ ሙሰሊም ነኝ እርስዎ ግን መግባት ይችላሉ ብሎ ወደ ውስጥ ይገቡ ዘንድ እንደፈቀደላቸው ተማሪያቸው የኾኑትና በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ታሪክ መምህሬ የሆኑት የአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲው ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ይህን የአስተማሪያቸውን አስደናቂና ልብ የሚነካ ገጠመኝ ሲናገሩ ሰምቼቸዋለኹ፡፡
እንዲህ ዓይነቱን ፍቅር፣ እንዲህ ዓይነቱን መተማመን፣ እንዲህ ዓይነቱን በጎነትና ቅንነት፣ እንዲህ ዓይነቱን ዓለም ሁሉ ምሳሌ ያደረገውን አብሮነት፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እስከ ቅዱስ ቁርአን፣ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ነቢዮ መሐመድ፣ ከግሪክ ጸሐፊዎችና ፈላስፎች እስከ አውሮጳ አሳሾችና ተጓዦች በውብ ቀለም የከተቡለትንና የተናገሩለትን ይህን ውብ የሆነውን አንድነታችንና ውብ ፍቅራችን ዛሬ በነበር ልንዘክረው በቋፍ ላይ ያለን ነው የምንመስለው፡፡

እዚህም ቤት እዛም ቤት የሚሰማው ድምፅ ደግ አይመስልም፣ የበቀል ሰይፎች በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተመዘው እያፏጩ ያሉ ነው የሚመስለው፡፡ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ አንድነትና አብሮነት የሚሰብኩንና ወደ ዕርቅ መንገድ ይዘውን የሚጓዙ የዘመኑ ነቢያትም አድራሻቸው ወዴት እንደሆነ ጠፍቶብናል፡፡

የሕዝብ እንባ፣ ብሶት፣ ዋይታና እሮሮ እንቅልፍ፣ ዕረፍት የሚነሳቸው፣ ለፍትሕና ለእውነት ጥብቅና የቆሙ፣ በሕዝባቸው ፍቅር ፈፅመው የነደዱ፣ ‹‹ይህን ሕዝብ በምድረ በዳ በከንቱ ከምታጠፋው እኔ ከሕይወት መዝገብ እስከ ዘላለሙ ደምስሰኝ!›› የሚሉ በነፍሳቸው የተወራረዱ የዘመናችን ሙሴዎች፣ ፍቅርንና ዕርቅን የሚሰብኩ ፖለቲከኞቻችን፣ መሪዎቻችን አድራሻቸው ወዴየት ይሆን!?

የትናንትናም ሆነ ዛሬው መንገዳችን በአያሌው ፍቅርን የተራበ፣ ይቅርታን የተራቆተ፣ አንድ መሆንን የገፋና የተጠየፈ ነው፡፡ ይህ ዛሬ የደረስንበት የአገራችን የፖለቲካ የታሪክ ሒደት ውጥንቅጥና ቀውስ በአብዛኛው የትናንትና ውጤት ነው፡፡ እናም የኢትዮጵያችን የዘመናዊ ፖለቲካ ጅማሮ መንገዱ በደም የተመረቀ፣ በደም የጨቀየ፣ በደም የተፈፀመ፣ የደም መንገድ፣ የደም ጎዳና ነው፡፡ የብዙዎች ወገኖቻችን ደም እንደ ጅረት የጎረፈበትና፡-

‹‹የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፣
ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ፡፡›› ተብሎ አሰቃቂ ሙሾ የተወረደበትን የታሪካችንን አብዛኛውን ምዕራፍ በደም ያስዋበ፣ በደም ያወየበ የፖለቲካ ታሪክ ነው ያለን፡፡ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራም ሆነ በወያኔ በኩል፣ በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር፣ በኢሀአፓና በመኢሶን፣ በኢህአዴግና በተቃዋሚው ስም ጎራ ለይቶ የተላለቀው ሕዝብ የአንድ ምድር ልጆች እንደሆኑ ነው የማስበው፡፡

የትናንትናው እንዳይበቃን ዛሬም ደግሞ አስፈሪውና አስደንጋጩ ነገር ደግሞ እዚህም ቤት እዛም ቤት የሚጎሰመው ነጋሪት፣ የሚነፋው መለከት ሞትን የሚያውጅ፣ ጥፋትን የደገሰ መሆኑ ነው፡፡ ዛሬም በትናንትና ታሪካችን ላይ ተቸክለን ለቂም በቀል የምንፈላለግ፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከአንድነትና ኅብረት ይልቅ መለያየት፣ ከሰላም ድምፅ ይልቅ የጦርነት ነጋሪት ወኔያችን የሚያሞቀው፣ የሚቀሰቅሰው ሕዝቦች የመሆናችን ምሥጢር ነው፡፡

አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግሥትም፣ በአገራችንም ሆነ በውጭ ያሉት የሚበዙት በተቃዋሚ ስም የተደራጁ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና የፖለቲከኞቻችን መንፈስ ገና ወደ ዕርቅ መንገድ ወደ ፍቅር የልዕልና ከፍታ ሊወጣ፣ ሊያድግና ሊመነደግ እንዳልተቻለው ደግመን ደጋግመን ዐይተናል፣ ታዝበናል፡፡

ከሰሞኑን በአፍቃሪ ምኒልከና በፀረ ምኒልካውያኑ መካከል የነበረው ስድብ፣ ውርጅብኝና የጦር አውርድ ዘመቻና የቃላት ጦርነት ገና በትናንትና ታሪካችን የሆኑትን መልካም ክስተቶች በምስጋና ተቀብለን፣ በአንፃሩ ደግሞ በታሪካችን የሆኑትን ስህተቶች አምነን ተቀብለን ይቅርታ ለመጠየቅ የሚሸነፍ ቅን መንፈስ እንደሌለን ያሳየን ነው ማለት ይቻላል፡፡ እናም ገና ወደ አንድነት፣ ወደ ዕርቅና ፍቅር መንገድ ለመድረስ ረጅም መንገድ በፊታችን ተዘርግቶ ይጠብቀናል፡፡ ይህን መንገድ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ተጉዘው ሊያሳዩን የሚችሉ ባለ ራእይና ቁርጠኛ የሆኑ ፖለቲከኞች፣ ከልባቸው የትግል ሰዎች የሆኑ፣ ሰው የሆኑ ሰዎች፣ የእውነትና የፍትሕ ጠበቃዎች በዚህ ዘመን የግድ ያስፈልጉናል፡፡
በቅርቡ በሞት የተለዩን የአፍሪካ ብርቅዬ ልጅ፣ የፀረ አፓርታይድ ታጋይና ነፃነት አርበኛ፣ የሰላምና የፍትሕ ጠበቃ፣ የይቅርታ ጀግና የሆኑት ኔልሰን ሮሂላላ ማንዴላ/ማዲባ እ.ኤ.አ በ1990 በአይርላንድ ፓርላማ አባላት መካከል ተገኝተው ባደረጉት ንግግራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፡-

‹‹We are in struggle because we value LIFE and LOVE all humanity!›› ያው ፍቅር ለሚገባቸው፣ ፍቅር ለሚያግባባቸው የማዲባ መልእክት ግልፅ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ፍቅር … ሰላም … ካላግባባን፣ ካላቀራረበን እንግዲህ ምን ያግባባን እንደሆነ እኔጃ፡፡ ግን … ግን … እናንተዬ በሰላማዊም መንገድ ይሁን ነፍጥ አንስተን እንታገላለን የምንል ሰዎች የትግላችን የመጨረሻ ግቡ ምንድን ይሆን?!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

nikodimos.wise7@gmail.com

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ –ግርማ ካሳ

$
0
0

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።

በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡

“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»

እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።

ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።

«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።

ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።

ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡

“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”

ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።

«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።

አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?

በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።

እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።

አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>