.እስክንድር ነጋ እና አንዱዓለም አራጌ ማስታወሻቸው ተወስዶባቸዋል፤
ቃሊቲ እስር ቤት ሙሉ ፍተሻ እንደተደረገበት ዛሬ እኩለ ቀን ላይ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አቅንተው የነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አመለከቱ፡፡
ከፌደራል ወንጀል ምርመራ እንደመጡ በተነገረላቸው ሰዎች ሙሉ ቃሊቲ እስር ቤት ፍተሻ እንደተደረገበት ከእስረኞች እንደተገለጸላቸው ያመለከቱት ምንጮች እንዳሉት ፍተሻው የእያንዳንዱን የእስረኛ ክፍል ያካተተ ነበር፡፡ በዚህም ወቅት የእስረኞች ማስታወሻዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች እንደተወሰዱባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በፍተሻው ወቅት ከታዋቂዎቹ እስክንድር ነጋ እና አንዱዓለም አራጌ የእስር ክፍል የተገኙ ማስታወሻዎችና ጽሑፎች ተወስደውባቸዋል፡፡ በዚህም እስክንድር ነጋ ከ30 ገጽ በላይ ጽሑፎችን አስፈርመው የወሰዱበት ሲሆን አንዱዓለም በበኩሉ ማስታወሻዎቹ እንደተወሰዱበት ከምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡
Negere Ethiopia
↧
ቃሊቲ እስር ቤት ፍተሻ ተደረገበት –ነገረ ኢትዮጵያ
↧