Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ-አንድ በሉ! –ከተክሌ በቀለ

$
0
0

በዛሬዉ እለት የህዝብ ታዛቢ በመሆን ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰዎችን ለማስመረጥ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት/አካላት፤አመራሮችም ጭምር በተለያዩ የምርጫ ጣብያዎች እንደተገኙ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡የታዘቡትን እያካፈሉን ሲሆን እኔም ያየሁትን ላካፍል ወደድኩ፡፡የታዘብኩት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ ዘጠኝን ነዉ፡፡መቐለ ከተማ ወረዳ ሓዉልቲ ያለሁ ነበር የመሰለኝ፡፡አስተባበሪዎቹ፤የወረዳዉ ካድሬዎች፤የአንድ ላምስት አስተባባሪዎች፤በሰፈሩ የማዉቃቸዉ ደህንነት ነን ባዮች ወዘተ ከተጠራዉ ህዝብ በቁጥር አያንሱም፡፡የሚሉትን በሙሉ እኔና ታዛቢ አድርጌ የወሰድኩት የማይጨዉ ሰዉ እንሰማለን፡፡አደራጅተዋቸዉ ለቀሩባቸዉ ስልክ ይደዉላሉ፤ግርግር በሌለበት ይጨነቃሉ፤የላኩዋቸዉን ለማስደስት መልእክቱንም በሸፍጥ ለመፈጸም ሽልጉድ ይላሉ፤ከዉጭ ሆነዉ ይሰልላሉ፤የማያዉቁትን ያሰተዉላሉ…..
ኢህኣዴግን ምርጫ እያስጨነቀዉ መሆኑንና ምርጫ ቦርድም ከጭንቀቱ ሊገላግለዉ ከልኡካኖቹ አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ታዝቧል፡፡እኛም መኢኣድና አንድነት እንዳይዋሃዱ ብቻ ሳይሆን እንደፓርቲ እንዳይቀጥሉ የሚያደርገዉን ጸረ ዲሞክራሲና ፍፁም በታሪክና በህግ የሚያስጠይቅ ድርጊት እየታገልን ሂደቱንም እየታዘብን እንገኛለን፡፡በመላ አገሪቱ የተመረጡቱ የዛሬዎቹ የህዝብ ታዛቢዎች ሁሉም በኢህኣድግ ደም የሚሰሩ ፍጡራን ናቸዉ በማለት መደምደም በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ በምርጫዉ ሰበብ ብቻ ህዝቡን ለማደራጀት የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎችና እድሎች አሉን፡፡እንጠቀምባቸዉ፡፡እድሎችን በጋራ ለማጎልበትና ለመጠቀም ግን የፓርቲ ጥላና ማህተም ሳያስጨንቀን ለትግሉ ዉህደትና አንድነት ከልብ እንትጋ፡፡አንድነት ፓርቲ እንደነግብጹ…በህግ እስከማግድ ቢደረስም የአንደነት ምርጥ ልጆች አንድነታቸዉን በማጽናት በሌሎች የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ቤት በመግባት አላያም አመራሬ በሚያስቀምጠዉ አፋጣን ሰላማዊ የትግል ስልት በመሰለፍ ትግሉን በጽናት እንደሚወጡት አልጠራጠርም፡፡አሁንም የፓርቲ ስምና አርማ ሳይበግረን፤የስልጣን ሃይሎችን በመግፋት ለዉህደትና(አንድ አይነት ፕሮግራም ያለን) ለትብበር ተግባራዊ እንቅስቃሴ እናድርግ፡፡መንገዳችንን በተቻለ መጠን እናስተካከል እንጂ የመጨረሻዉ ግባችን ላይ ባጭር ጊዜና በትንሽ መስዋእት እንደርሳለን፡10153833_587630041337455_4078181881316786241_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>