ለሰሚም ግራ ሆነ አማርኛ ይመስላል-አይደል…ነገሩ ግን ወዲህ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በ2006 ሚያዚያ 5 በቶኩማ ሆቴል ከአዳማ ዩኒቨርሲቴ ተማሪዎችና ከከተማው ደጋፊዎቹ ጋር ውይይትና በእለቱም አዲሳባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን በመጋበዝ በፖለተካዊ ፍልስፍና ላይ በጥያቄና መልስየዳበረ ፓናል ተካሂዶ ነበር፡፡በፕሮግራሙ ላይ ከዋናው ቢሮ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እናተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ያፓርቲው ሕ/ግ ሃላፊ ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ፓርቲው የአዳማ አስተባባሪዎች በየወሩ የሚያደርጉትን “የስነጥበብ ለለውጥ”-art for change- ዝግጅት ለጋዜጠኛዋና መምህሯ ርዕዮት አለሙ መታሰቢያ በማድረግ ልዩ የስነ ፅሁፍ ዝግጅት አቅርበዋል፡፡ የርእዮት ቤተሰቦችም በቦታው በመገኘት ስለርዕዮት የናዝሬት ልጅ መሆን በመግለፃቸው ዕለቱ ያልታሰበ ደስታን ፈጥሮ ውሏል፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ሙሉ ወጪ ለመሸፈን የታቀደው ፕሮግራም ወጪው ከአቅም በላይ በመሆኑ ቀሪ ክፍያ ሳፈጸም የቀረ ቢሆንም ወጪውን ለመሸፈን ለዋናው ቢሮ በቃልና በቃለ-ጉባዔ በማሳወቅ ስድስት ወራት ጊዜ አለፈ፡፡ሆቴሉ ካደረገው ትብብር አኳያ የሚያሰመሰግነው ሆኖ ሳለ ፤ክፍያው ሊፈፀምለት ይችል ዘንድ ማረጋገጫ እንኳን በማጣቱ ፤ ፓርቲውንና ከፓርቲው ጋር በመተባበር የስነ ጥበብ ፕሮግራሙን ያከናወነውን ሊያ የተሰኘ ማሰልጠኛ ለመክሰስ እንደሚገደድ አሳውቋል፡፡
ይህን ዘገባ እስክንሰራ ድረስ የአዳማው ቢሮ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ለሁለት ወራት ተዘግቶ ዕቃዎቹም እንደተዘጋባቸው የታወቀ ነው፡፡በተደጋጋሚ ወደዋናው ቢሮ ያደረግነው መመላለስም ሆነ የተላላክናቸው ደብዳቤዎች ምንም ውጤት አላመጡም፡፡ በመሆኑም የአዳማው የፓርቲው ሐላፊዎች ይከሰሱ ዘንድ ፤ መልካም በሰሩና የፓርቲውን እንቅስቃሴ ባቀላጠፉ በሽልማትና ምስጋና ፋንታ ቢሮአቸው ተዘግቶ ሳለ ለተጨማሪ ተጠያቂነት ተገፍተዋል፡፡ሁላችንም ይህንን በጸጋ የምንቀበለው የትግሉ አንድ አካል አድርገን መሆኑን፤ ሁሉም የአንድነት ደጋፊ እንዲያውቅልን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ተስፋዬ ዋቅቶላ
የአዳማ አንድነት ሕ/ግ ተጠሪ