በኦሮሚያ ክልል መቱ ዞን የአንድነት ፓርቲ የድ/ጉ/ኃላፊ የሆኑት አቶ ታመነ መንገሻ ጳጉሜ 4 ቀን ታስረው እንደነበረና ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በዋስ እንደተለቀቁ በመለቃቸውም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ካድሬዎች ለምን ተለቀቁ መታሰር አለባቸው በማለታቸው በድጋሚ መታሰራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ አይዘነጋም፡፡ አቶ ታመነ መንገሻ የታሰሩት አማራ ይውጣ ብለሃል በሚል ሰበብ እንደሆነ ይህን ተናገሩ በተባለበት ወቅትም ታመው አልጋ ላይ እንደነበሩ፣ ፖሊስ በሳቸው ላይ እንዲመሰክር በፖሊስ ጣቢያ ለምስክርነት ያቀረበው ግለሰብም እሳቸው ሁልጊዜ ሲናገሩ የምሰማው “ዓላማችን መለያየት ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት እንዲቀጥል ነው” ብለው በማለታቸው መስካሪውም እንዲታሰሩ ተደርገው በዋስ ተለቀዋል፡፡ አማራ ይውጣ ብለሃል በተባሉበት ቀን ታመው በህክምና ላይ እንደነበሩ በህክምና ማስረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው ቢረጋገጥም መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፖሊስ ሀሰተኛ ምስክሮች አስመስክሮ 2 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ፈርዶባቸዋል፡፡
↧
በመቱ ዞን የአንድነት ፓርቲ የድ/ጉዳይ ኃላፊ 2 ዓመት ተፈረደባቸው
↧