Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥለሴ ትንግርታዊ ዝቅጠት (አብርሃም አየለ)

$
0
0

በቅርቡ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥለሴ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ የሰጠው ቃለ መጠይቅ በዚህም ‹ዲሞክራሲ ለአፍሪካ አያስፈልጋትም! ለአፍሪካ የሚያስፈልጋት መልካም አስተዳደር ነው› ብሎ የተናገረው ‹ድንቅ› አባባል የመገናኛ ብዙሀን መነጋገሪያ ለመሆን መብቃቱ ይታወቃል፡፡ ኃይሌ ሊነግረን ያልቻለው በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር መካከል ያለውን ተዛምዶና ልዩነት ነው፡፡

‹ትንሽ እውቀት አደገኛ ነው› የሚባል አባባል አለ፡፡ ትንሽ እውቀትም ሳይኖር አዋቂ ነኝ ብሎ በማያውቁት ጉዳይ ላይ መናገር ደግሞ ከአደገኝነት ባለፈ ፈገግ የሚያሰኝበትም ጊዜ አለ፡፡ የኃይሌን የተጠቀሰውን አባባልም ከዚህ አያልፍም፡፡

ከሁሉ በፊት የሚገርመው ኃይሌን ስለ ሩጫ፣ በሩጫም አማካኝነት ስለአገኘው ሀብትና በዚህ ስለሰራቸው ሆቴሎች ስለገነባቸው ህንጻዎች ጋዜጠኛው ቢጠይቀው መልካም በሆነ ነበር፡፡ ‹ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ› እንደሚባለው፤ ጋዜጠኛው ይህን የመሰለ ዐብይ ጉዳይ የጠየቀው ማንነቱን ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን፤ ስለአፍሪካዊያን አመለካከት በዚህ መልኩ በማቅረብ አንባቢዎቹንና አድማጮቹን ፈገግ ለማሰኘት ይሆናል ብሎ መገመት ያስኬዳል፡፡

ከዚህ ጉዳይም አልፎ መንገድ በስሙ ሰይመን ከፍተኛ ቦታ ስለሰጠነው ኃይሌ ብዙ መናገር ይቻላል፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና እስቲ አንድ ሁለት የሚሆኑ ጉዳዮችን እናንሳ፡፡

በዓለም እውቅና ያገኙ አትሌቶች፤ በሩጫም ሆነ በኳሱ እንዲሁም በሌላ ያገኙትን ሀብት ወገናቸው የሚራደበትን ተቋማትና ሌላም አስተዋጽኦ ሲያደርጉ በብዛት ሰምተናል፡፡ በዚህም መልካም ምግባራቸው ከልብ ያደነቅናቸውም አሉ፡፡ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል – አፍሪካዊ የሆነው የአይቮሪኮስቱ ተወላጅ ድሮግባን እንመልከት፡፡ በ38 ዓመት እድሜ ላይ የሚገኘው ይህ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋች ድሮግባ በአገሩ ለአገሩ ሕዝብ በሰራቸው አንጸባሪቂ ስራዎቹ ፍቅርና አክብሮትን ከወገኖቹ ለማግኘት ችሏል፡፡ ከአደረጋቸው ተግባራትም መካከል ለአብነት ያህል የሚከተሉት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ለአምስት ዓመታት በዘለቀውና በሁለት ተጻራሪ ቡድኖች መካከል በአገሩ የተደረገውን ደም አፋሳሽ የእርስበርስ ጦርነት ያለውን ተደማጭነት በመጠቀም እንዲቆም አድርጓል፡፡ ለአንድ ድርጅት ለሰራው ማስታወቂያ የተከፈለውን ሶስት ሚልዮን ፓውንድ እንዳለ ወገኑ የሚጠቀምበትን ሆስፒታል አሰርቶበታል፡፡ ለምሳሌ ያህል እነዚህ ተጠቀሱ እንጂ ድሮግባ በለሌች የማኅበራዊ ዘርፎችም እንዲሁ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሰው ነው፡፡ የእኛው ኃይሌና ጓደኞቹ ሆቴል ከመስራት፣ ህንጻ ከመገንባት ባለፈ ይሄ ነው የሚባል ለወገናቸው ያደረጉት ምን አለ? መልሱን ለአንባቢ ልተወው፡፡

ማናቸውም ሰው በይበልጥም በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅናን ያገኘ በሚዘዋወርበት አገር፣ በሚሰራቸውና በሚናገራቸው ሁሉ ሀገሩን በማስከበር፣ የሀገሩን ባህልና እሴት በመጠበቅ በኩል እንደ አምባሳደር ይቆጠራል፡፡ ይህም ምንም እንኳን ይህን አድርጉ ተብሎ የተጻፈ ህግ ባይኖርም እያንዳንዱ ዜጋ ሊከተለው የሚገባ አመለካከት ነው፡፡ እንግዲህ ኃይሌ በሚዘዋወርባቸው ቦታዎች ከውጭ ጋዜጦች ጋር በሚያደርጋቸው ቃለምልልሶች ሀሳቡን በእንግሊዝኛ ለመግለጽ የሚያደርገውን መፍጨርጨር እየተመለከትንም እየሰማንም ነው፡፡ ምናልባት በራሱ ቋንቋ በአስተርጓሚ ቢናገር ሊያስተላልፍ የፈለገውን በሙሉ ስሜት ለመግለጽ በቻለ ነበር፡፡ አሁን አሁንማ በሕዝባዊ ስብሰባዎች በጉርማያሌ ቋንቋ የሚሰነዝረው አስተያየት በእሱና በአድማጩ መካከል አስተርጓሚ ሳይስፈልግ አይቀርም የሚለውን እሳቤ እንድንወስድ አድርጓናል፡፡

ይህን የመሰለው ዝቅተኛ አመለካከት – ‹ትንሽ እውቀት..› በእሱ ላይ ቢቀር መልካም በሆነ፡፡ ከእሱም አልፎ ልጆቹን በአገራቸው ቋንቋ እንዳይናገሩና እውቀቱም እንዳይኖራቸው ‹አማርኛ ካካ፣ ኦሮሚኛ ካካ› በሚለው ጨቅላ አስተሳሰቡ በክሏቸው ይገኛል፡፡ ይህም ያለውን ግንዛቤና አስተሳሰብ ምን ያህል የወረደ መሆኑን ለማሳየት ጥሩ መስተዋት ነው፡፡

በመጨረሻም ከዙሁ አትሌት ጋር በተገናኘ ለአንባቢዎች ለማስተላለፍ የምፈልገው መልክት አለ፡፡ አሉታዊ አመለካከቶች ‹አይቻልም፣ ክልክል ነው› በተንሰራፉበት ህብረተሰባችን ይህን በአዎንታዊ አመለካከት ለመቀይር ከጥቂት አመታት በፊት ጥረት ተደርጓል፡፡ ‹ይቻላል!› የሚለውና በህብረተሱ ዘንድ እንደ መሪ መፈክር የተወሳደው ቃል ተግባራዊ እንዲሆን ያደረገው፤ ብዙዎች እንዳመኑበት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ሳይሆን፤ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት የነበረው አቶ ክቡር ገና መሆኑ እንዲታወቅና ስራውም ለባለቤቱ እንዲሰጥ አስገነዝባለሁ፡፡

Abrehamayele2008@gmail.com


ኢትዮጵያ፤ ሙስናና በእምቢተኝነት ቅሬታ የሚያሰሙት ንብረት ማቃጠላቸው። ድርጊቱን እናውግዝ ወይንስ ይበል እንበል? ተጠያቂው ማነው? በፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን፣

$
0
0

መግቢያ

ትርጉም ከማይሠጠው በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን ለማሰማት በተነሳሱት ላይ የገዥው ፓርቲ ከፈጸማቸው ግድያዎች በተጨማሪ፤ አሁን በቅርብ የወጡት ቁንፅል የቪዲዮ ቅንብሮችና የዜና ዘገባዎች፤ እኒሁ በኦሮሚያ አካባቢ በእምቢታ ቅሬታቸውን ለማሰማት የተነሱት፤ ንብረትና ተቋሞችን ወደ ማጥፋት/ማቃጠል እንዳመሩ ያመለክታል። በዚህ ቀውስ ዙሪያ፤ በውጪ ሀገራትና በሀገር ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል፤ የጎደራ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው። በውጪ ሀገር በሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን መካከል የሚገኙ ጥቂቶቹ፤ የማቃጠሉን/ማውደሙን ተግባር፤ በገዥው ፓርቲ ከሚፈጸሙት ጽንፍ የለሽ አረመኔያዊ ምግባርና ሥር ከሰደደው ሙስናቸው ጋር (በዚህ ረገድ በትክክል) ያዛምዱታል። ለኒህ በውጪ ላሉት ኢትዮጵያዊያን፤ ተግባሩን ይበል ለማለታቸው መሠረት የሚመስለው፤ አያሌዎቹ የወደሙት ንብረቶች፤ ባለቤቶቻቸው በሥልጣናቸው የባለጉ ልሂቆችና የውጪ ሀገር ኩባንያዎች መሆናቸው ነው። የኒህ ንብረቶችና ሕንፃዎች ባለቤቶች፤ የዘሩትን ነው እያጨዱ ያሉ በማለት አቋማቸውን ያቀርባሉ። ይሄን ግንዛቤ የሚያስተጋቡ ወገኖች፤ በእምቢተኝነት ቅሬታን ለማሰማት መነሳሳት፤ ለለከት የለሽ ምዝበራና ግድ ብሎ የመጣ አደገኛ ክፋት፤ ማሻሪያ ነው ብለው ይወስዱታል። ሌሎች፤ በተለይም ራሳቸውን የሰላማዊ ትግሉ ዘበኛ ብለው የሚቆጥሩ፤ በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን በማሰማት የተሳተፉትንና ዝግጅቱን ያቀናበሩትን የሚያካትት ክፍል፤ የንብረት ማቃጠሉንና ማውደሙን በመቃወም ይከራከራሉ። የታየው ውድመትና ቃጠሎ፤ የሰላማዊ ትግሉና በሰላማዊ ታጋዮች ላይ የገዥው ፓርቲ እያደረሰ ላለው አጥር ዘለል አረመኔያዊ ተግባር የተከተለውን አጸፋ በማይወዱ ተንኮለኛ ጠምጣሚዎች፤ የተከናወነ ነው ይላሉ። ውድመቱና ቃጠሎው ቁጥራቸው በዛ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን፤ አወዛጋቢና የከረረ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው ይመስላል። ምርጫ የለሽ አረንቋ ውስጥ የገቡ በሚመስል ሁኔታ ተጠምደዋል – (ማለትም ጥፋቱን ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በማይችሉበት ወጥመድ ውስጥ መገኘታቸው)።

እንደ የሰላማዊ እምቢተኝነት ዘበኝነቴ አግባብ ደግሞ፤ የተስተዋለውን ቃጠሎና ውድመት ይበል አልልም። ከምኞታችን በተጻራሪ ግን፤ በጣም የከፋ ቃጠሎና ውድመት ተግባራዊ የመሆን ችሎታ አይቀሬ ሀቁን፤ አውቃለሁ፤ አሳስቦኛልም። እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ይህ ቀውስ እንደሚከተል ቀደም አድርጌ፤ ተገንዝቤ ነበር። እናም፤ ከጓደኞቼ ከነፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ፣ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደና ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግሥቱ ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ሙስና ከንካኝ ባህሪ ባነሳንባቸው ወቅቶች ሁሉ፤ የዚህ መከሰት ችሎታ እንዳለ ጠቁሜያለሁ። በኢትዮጵያ ያለውን የሙስና ክፋትና ክብደት ስንወያይ፤ ሚዛኑ ይኼ ነው በማይባል ደረጃ ሊከተል የሚችለውን ጥልቀቱ የማይደረስበት ጥፋት በማሰብ፤ ልክ ጭንቅላቶቻችን የተውገረገሩ፣ ድምፆቻችን የተሽመደመዱ መሰሉ። ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊያን በመንግሥት የተደገፉ መዋዕለ ተቋማትና ንብረቶች፤ የነሱ ያልሆኑና በተቃራኒው “የውጭ” ዕሴቶችና አልፎ ተርፎም የመበዝበዣና የመጨቆኛ መሳሪያዎች አድርገው የሚወስዷቸው?

እንግዲህ፤ ለምን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ (ውቀመን) ብልጽግናን እንደሚያስከትል በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን ለማሰማት የተነሳሱት ሊረዱት እንዳልቻሉ፣ ነገር ግን በግልባጩ እነሱ ከዚያ አልፎ “የሀገር በቀል” (ማለትም በፖለቲካ ፓርቲና በልሂቃን ባለቤትነት የተያዙት) “መዋዕለ ንዋይ” እንኳ የማይጨበጥ/የውጭ ባለቤትነት ያለው ንብረት ብለው መወሰዳቸው፣ ለምን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ (ውቀመን) “የስርቆት ማንቆለጳጰሻ ቃል” እና የከፋ በዝባዥና ለመጥፎ ምግባር አባሪ በር ከፋች ተደርጎ እንደተወሰደ . . . ወዘተ. እናም እነሱ እኒህን ሁሉ ለማውደም ለምን እንዳቀኑ መረዳት ከፈለጉ፣ ንባብዎን እንዲቀጥሉ አበረታታዎታለሁ። በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ሙስና ሁለተናዊ ባህሪ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት፣ እንዴት የሀገሪቱን ተቋማዊ መስተሳሰሮች ተመልሶ በማይጠገን ሁኔታ እየጎዳ እንደነበርና አሁንም እንደቀጠለ መረዳት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ ይህን ተግባር ለመዋጋት ዕቅድ ለማውጣት ማሰብ በዕውነት የምትፈልጉ ከሆነና ልክ የለሽ የማጥፋት አደጋውን ለማዘግየት በዕውነት የምትሹ ከሆነ፤ እባክዎን ለማብራራት ይፍቀዱልኝ።

ይህ ሐተታ የተሰናዳው፤ እርስዎ (አንባቢው) በኢትዮጵያ የነገሰውን ሙስና አልገታ ባይ ባህሪይ ተረድተው፤ ከዚያ በኋላ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉ “መፍትሔዎችን” እንዲያስቡባቸው ለመማጸን ነው። ይህ እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት፤ ዕቅዶችን መቀየስና “መፍትሔዎችን” መሻት፤ በታሰበበት ሀገር፤ እዚህ ላይ ኢትዮጵያ፤ የሚገኘውን ሙስና ዓይነትና ምንነት በደንብ አድርጎ መረዳት ስለሚጠይቅ ነው።

የገዥዎች ንጥቂያ፤ የታላቅ ሙስና ቅርጽ የያዘው የችግሩ መሠረታዊ መንስዔነቱ

ከዚህ በፊት በተለያዩ ወቅቶች እንዳሳየሁት፤ በኢትዮጵያ ነግሦ እየተገነዘብን ያለነው፤ የገዥዎች ንጥቂያ ተብሎ የሚታወቅ፤ ከሙስናዎች ሁሉ በጣም ሰርሳሪና የማይገታ ዓይነቱ ነው። የዚህ ዓይነቱ ሙስና፤ በሙስና ስነ-ጽሑፍ ውስጥ የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ – ቢሮክራሲያዊ) ሙስና ከሚባለው ተለይቶ መታወቅ አለበት። የገዥዎች ንጥቂያ፤ በተለምዶ ሁኔታ፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ሀገሮች፤ ድኅረ-ኮምኒስት (የሽግግር) ሀገሮችን በመተው፤ የተመዘገበውና የተስተዋለበት ዓይነት ሙስና ነው። አስተዳዳራዊ (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና በተለይ፤ ጉቦ ከፋዩ፤ በሀገሩ ያሉ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ እና መተዳደሪያዎችን በመለጠጥ፤ ለራሱ ሚዛናቸው እንዲደፋ በማድረግ ማካሄድ ነው። ባጠቃላይ የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና፤ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች መዋቅራዊ ውጣ ውረድ ተግባራዊ ሂደቱ ላይ የሚፈጸም ሲሆን፤ የፖለቲካ ( ታላቁ ) ሙስናው የሚካሄደው፤ ከፍተኛውን መንግሥታዊ ሥልጣን በያዙት ደረጃ ነው። የተለያዩ የአስተዳደራዊ ሙስና ምሳሌዎች ሊሆኑ ከሚችሉት መካከል ለመጥቀስ፤ የተወሰነ ብያኔን እንዳይተገበር የማደናቀፍ፣ መዝገቦችን የማጥፋት፣ ወይንም መዝገቦችን አስመስሎ የመቅዳት ተግባር ተባባሪ መሆን፤ በከፍተኛ ደረጃ ሕጋዊ የሆኑ (እንዲተገበሩ የተመሩትን) የማስተጓጎል ወይንም/እናም እንዲዘገዩ የማድረግ፣ የተመደቡበትን የመሥሪያ ቤት የሥራ ሰዓት ለግል ጥቅም ማከናወኛ ሰዓት የማድረግ፣ ያልያዙትን ሥልጣን እንደያዙ በማስመሰል የመቅረብ፣ ጣልቃ የመግባትና ለዘመድ ጥቅምን የማስገኘት (የሥልጣን ብልግና)፣ የሕዝብን ንብረት ያላግባብ የመጠቀም፣ ከሥራ ምድብ ቦታ ያለመገኘት፣ ለልማት ከሚውሉ የአገልግሎት ዝግጅቶች መላሾ መውሰድ ላይ የመጠመድ፣ የሕግ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ድጋፍ ለመሥጠት ገንዘብ የመቀበል፣ የሕዝብን ንብረት ወደ ግል መጠቀሚያነት የመምራት፣ ሕገ-ወጥ የሆኑ ተግባራትን እንዳላዩ ዓይቶ የማለፍ፣ ተራ ሌብነትና ንብረት የማባከን፣ ከዋጋ በላይ የመጫን፣ ሕልውና የሌላቸውን የሥራ ዝግጅቶች የማካሄድ፣ ቀረጥ የመሰብሰብ፣ የቀረጥ ፍተሻ ማወናበጃ የማድረግ፣ …ወዘተ።

ምንም እንኳ ከሥሩ መንግሎ ማጥፋት ባይቻልም፤ ደግነቱ፤ መንግሥታት የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና የሚያደርሰውን ጉዳት፤ መንግሥታዊ ተግባራትን በታወቀ ይፋ መዋቅራዊ ሂደት፣ በተጠያቂነት እና በግልጽነት ሊያሳንሱት ይችላሉ። ይህ የሚሆነው፤ ለምሳሌ የሚከተሉትን በማድረግ፤

ሀ) ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጪ ሥልጣን ያለው አካል በማቋቋም
ለ) ነፃ የምርጫ ቦርዶችን በማቋቋምና ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመፍቀድና በማሳደግ
ሐ) ነፃ የዜና ሥርጭት ተቋማትን በመጠቀም፣ ይህ ደግሞ በተራው ተቆርቋሪ ቡድኖችን፣ የኅብረተሰቡ የትብብር ማኅበሮችን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና፣ … ወዘተ እየረዳ
መ) የፓርላማውን የምርመራ ሥልጣን በመጠቀም
ሠ) ነፃ የሆኑ ፀረ-ሙስና ቦርዶችን እና የተልዕኮ አካሎችን መፍጠር
ረ) ነፃ የሆነውን የፍትህ ሥርዓት በመጠቀም

ይሁንና፤ በኢትዮጵያ የተገነዘብነው የገዥዎች ነጠቃ በመባል የሚታወቀው፣ በሽግግር ባሉ (በፊት ሶሺያሊስት የነበሩ) ሀገሮች የተከሰተው ነው። ይህ፤ ጉልበተኛ ቡድኖች፤ ተቋሞችና መመሪያዎች፣ ሕጎችና ማዘዣዎች በሚያመቻቸው መንገድ እንዲገነቡላቸው ተገቢ ያልሆነና የተበላሽ ተጽዕኗቸውን በመጫን፤ ለሕዝቡ በጎ ተግባር ከማዋል ይልቅ፤ ለራሳቸው ጥቅም የሚያስጠብቁበት ክስተት ነው። የገዥዎች ነጠቃ በተለያየ መንገድ ሊነሳና ሊተገበር ይችላል፤ ማለትም ጉልበተኛ ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይንም የጥቅም ትስስር ያላቸው ስብስቦች፤ ባንድ በኩል ሚስጢራዊ የሆኑ መንገዶችን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕጋዊና ተገቢ መዋቅሮችን በመጠቀም፤ ተፎካካሪዎቻቸው በኃላፊነት የተቀመጡትን ባለሥልጣኖችን እንዳይገናኙና የአገልግሎት በሮች እንዳይከፈቱላቸው በማገድ የሚከሰት ነው። የተለዩ ቡድኖችና የመንግሥት ባለሥልጣናት፤ “የመንግሥት ባለሥልጣናትን የፖለቲካ ኃላፊነትና የግል የንግድ ፍላጎት የደበዘዘ መለያያ አጥር” በመለጠጥ አሸዋረው፤ ከኅብረተሰቡ ይልቅ ለራሳቸው የጋራ ጥቅም በማዋላቸው ሊነሳ ይችላል (ከሄልማን፤ 1998፡3 የተወሰደ አስተሳሰብ)። እንደ የብሮድማን እና ሬካናቲኒ (2001) አስተሳሰብ)፤ የገዥዎች ነጠቃ፤ ለተለዩ ቡድኖችና የንግድ ጥቅሞች የሚረዱ መመሪያዎችና ደንቦች ማስፈጸሚያ በመቀየስ፤ ጠቅላላ የፖለቲካ ሂደቱን ድምጥማጡን የሚያጠፋ ጎጂ ሙስና ነው።

የገዥዎች ንጥቂያ ከሀገር ሀገር ሊለያይ ይችላል። በአንዳንድ ሀገሮች፤ የገዥዎች ንጥቂያ፤ በብልግና የላሸቀ ምግባር ተብሎ በሚታወቀው ስር የሰደደ መሰሪ ካፒታሊስታዊ ግዛት፤ አንድ ገጹ ሆኖ ሊታይ ይችላል። በዚህ ክት፤ ጉልበተኛ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና በጣት የሚቆጠሩ ገዥዎች ባሉበት ሀገር፤ እኒሁ ገዥዎች አዳዲስ መንግሥታዊ መመሪያዎች ሲወጡ፤ ሆን ብለው በመጠምዘዝና ቅርጹን በማሳመር “የጨዋታ ሕጎችን” ለራሳቸው እንዲያጋድል የሚያደርጉበት ነው። ይህን፤ በኃላፊነት የተቀመጡ ባለሥልጣናት፤ የተደራጁ የንግድ ቡድኖች፣ ጥቂቶቹ ገዥዎች ወይንም ጉልበተኛ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ፤ ድንጋጌዎችን ሲያውጁ እና/ወይም በሚወጡ ሕጎች ላይ ድምጻቸውን ሲሠጡ መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪ ደግሞ ግዙፍ የሆነ “የምጣኔ ሀብት ሥምሪትና የፖለቲካ ሥልጣን በአንድነት በአንድ ክፍል መያዝ” እና ጥቅም አሳዳጆች በሀገሪቱ የግዛት ልጓምና በሀገሪቱ ሀብት የበላይነቱን መጨበጥ በሚከተለው የሀብት አለመመጣጠን ይታያል። የገዥዎች ንጥቂያ ክስተት፤ በኃይለኛ መሪዎች (ማለትም የአካባቢ ወይንም የሀገር አቀፍ የሆኑ)፣ ሚኒስትሮች፣ ሕግ መወሰኛና የፍትኅ ሚኒስትር ሥራ አስኪያጆች፣ የመንግሥታዊ ተቋማትና/ትልልቅ ድርጅቶች፣ የገዥው ፓርቲ ባለቤትነት ያለባቸው ኩባንያዎች ሥራ አስኪያጆች በሚያደርጉት ድብቅ ሻጥር ሊታይ ይችላል። በአንዳንድ በኩል የገዥዎች ንጥቂያ፤ የሕጋዊና የፖለቲካ ተቋማት መዳከም ውጤት ነው። በሌሎች አንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ፤ ነጣቂዎቹ፤ ለንጥቂያቸውና ለብዝበዛቸው እንዲያመችላቸው የሀገሪቱን ሕጋዊና ፖለቲካዊ ተቋማት ሆን ብለው ያዳክሟቸዋል። በተጨማሪም፤ በምጣኔ ሀብት ሥምሪቱ እደሳ መክሸፍ እና ጉልበተኛ ግለሰቦች ወይንም የተደራጁ ቡድኖች፤ ከ“መንግሥት ይዞታ ወደ ግለሰብ ባለቤትነት” የሚደረገውን የሽግግር ሂደት በመጠቀም፤ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለውን የሕዝብ ንብረት፤ በመመንተፋቸው ይከሰታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች የገዥዎች ንጥቂያ፤ የተደራጁ ቡድኖች፤ እነሱ የፈለጉትን ያደርጉ ዘንድ፤ ግዛታዊ መዋቅሩን፣ ፍርድ ቤቶችን፣ መረጃ ክፍሉን፣ ጦር ሰራዊቱን፣ ሕዝብ መገናኛ መስመሮችን ጭምር፤ ተጽዕኖ ለማድረግ በሚስጥር፤ በግዛቱ ውስጥ የድብቅ ግዛት (“ጎድናዊ ግዛት”) ሲፈጥሩ ሊታይ ይችላል። የገዥዎች ንጥቂያ በነገሰባቸው አንዳንድ ሀገሮች፤ የመንግሥት በሆነውና የግለሰብ በሆነው፣ ይፋ በሆነውና ይፋ ባልሆነው፤ የግዛት ክፍልና የገበያ ክፍል በሆነው መካከል ያለው የመለያያ መስመር አካቶ ድብዝዟል። ከላይ በተሠጠው ገለጻ እንደምትረዱት፤ በገዥዎች ንጥቂያ ሥር፤ የአንድ ሀገር ሕጎች፣ ደንቦች፣ ሕጋዊነቶች እናም በመጨረሻም አጠቃሎ ተቋማቱ እንዳሉ የሙስናው አካል ናቸው። እኒህን የመሰሉ የሙስና ገጾች፤ ቀደም ብሎ ከላይ ከተገለጸው አስተዳደራዊ/መዋቅራዊ ውጣ ውረድ ሙስና ፍጹም የተለዩ ናቸው።

በአንዳንድ ኢትዮጵያን በመሰሉ ሀገሮች፤ (ሃሰን፤ 2013) (በተወሰነ ደረጃ ደግሞ፤ እንደ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ የመሳሰሉ ሀገሮች) ጠቅላላ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት ሥምሪቱ፣ ሕጋዊና ወታደራዊ መዋቅሮች በሙሉ እንዳሉ በጉልበተኛ የተቧደኑ ክፍሎች ወይንም በትውልድ ሐረግ የተሰባሰቡ ቡድኖች እጅ ገብቷል። ይኼን የመሰለው ሙስና፤ አደገኛና መርዛማ ነው። ምክንያቱም፤ እኒሁ የተዋቀሩ ቡድኖች፤ ከታላላቅ ድርጅቶች ባለቤቶች እና/ወይም በጣት የሚቆጠሩ ገዥዎች ጋር በመተባበር፤ የሁሉም ተቋማትን ወሳኝ የሆነ የደም ሥር (የምጣኔ ሀብት ሥምሪት፣ የኅብረተሰቡ ትስስር፣ የጦር ሰራዊት) እየተቆጣጠሩ በመገኘታቸው ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ እንደ ሩስያ በ1990ዎቹ እና በአንዳንድ የአፍሪቃ ሀገሮች፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደታየው፤ የንጥቂያው ተግባራዊነት፤ በጣም የተደራጀና ዘሎ ገባ ገፋፊ ነው። ነጣቂዎቹ፤ አመጽና ማስፈራራት፤ ከሌሎች መገልገያ መሣሪያዎቻቸው መካከል እንደተጠቀሙ ታውቀዋል። የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ሥርዓት ወሳኝ የደም ሥር በበላይነት ለመቆጣጠር፤ የራሳቸውን ሁሉን ከላይ አንቆ ያዥ የንግድ ተቋም (ሞኖፖሊ/ ኦሊጋርኪ) እና ወሳኝ የተጣመረ የንግድ ቡድን (ካርቴል) በማቋቋም፤ እግረ መንገዳቸውን በሥራ ላይ እየዋለ ያለውን የገበያ ማሻሻያ ሂደት ባንድ በኩል በማሰናከል ታውቀዋል። ባጭሩ፤ ይኼን የመሰለው ሙስና፤ የአዲሱ ዘመናችን የተደራጀ የወንጀል ምግባር ይመስላል።

የያንዳንዱ ሀገር ልዩ የሆነ የሙስና ባህርያት

የነጣቂዎች ብልሹ ተግባራት በሁሉም ዘንድ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ናቸው። ነገር ግን፤ ከሀገር ሀገር ወይም የንጥቂያው አጀማመር እና የነጣቂዎች ዓይነት ሊለያይ ይችላል። በድኅረ-ኮምኒስት ሀገሮች፤ ሄልማን እና ተባባሪዎቹ እንዳሉት፤ (2003) በየግል “ነጣቂ ድርጅቶች (ማለትም ለባለሥልጣናት የጨዋታውን ሕግ እንዲመቻችለት የግል ክፍያ የሚያካሂድ) እና በተደማጭ ድርጅቶች (ማለትም ለባለሥልጣናት ክፍያ ሳይቸገር፤ በሕጎቹ ላይ ተደማጭነት ያላቸው ድርጅቶች)” መካከል ልዩነት ያደርጋሉ። በጥቅሉ ነጣቂዎቹ፤ ስርዎ ስሙ የተሠጠው (ኖሜንክላቱራ)፤ በቀድሞው የሶቪየት ሥርዓትና የምሥራቅ አውሮፓ ፈርጅ ሀገሮች ሥር፤ መንግሥት ይቆጣጠራቸው በነበሩት የምርትና የንግድ ድርጅቶች፤ የቀድሞ ሥራ አስኪያጆችና በመዋቅሩ ተሰግስገው የነበሩ ኃላፊዎች ቡድን፣ (ቁጥራቸው በግምት ከሕዝቡ ከመቶ አንድ ነጥብ አምስት የሚሆኑ) ናቸው። እኒህ “ከሌሎች በተለየ የተከበሩ ባለመብት ሆነው፤ ፍጹማዊ የሥልጣን ልጓሙን ጨብጠው፤ እርስ በርሳቸው የማያልቅ የፖለቲካ ቁማር በመጫወት ተጠምደው” ነበር። በተጨማሪም “የተሠጣቸውን የኃላፊነት ቦታ በመጠቀም፤ የንግድ ተቋሞችን ነጣቂ” ባለሥልጣናት ሊሆኑ ይችላሉ። አለያም የተሰባሰቡ የፓርላማ አባላት፣ ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ ሚኒስትሮች፣ ዳኞች በመተባበር ሊሆኑ ይችላሉ (የራሱ የገዥው ፓርቲ መሪዎች፣ ከሳሽ፣ ዳኛና ጠበቃ በመሆን)። የገዥዎች ንጥቂያ በሁሉም ቦታ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ሆኖ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ውስጥ፤ በድኅረ-ኮምኒስት ካሉት ሀገሮች በአንዳንድ ወሳኝ ጉዳዮች ይለያያሉ።

አንድ ሲሉ፤ እኒህ የኢትዮጵያ ነጣቂዎች፤ እንደ ሩሲያዊያን እና የምሥራቅ አውሮፓ አጓዳኞቻቸው ስርዎ ስሙ በተሠጠው (ኖሜንክላቱራ)(የኮምኒስት ፓርቲው ከፍተኛ ባለሥልጣናት) አባል አይደሉም። ከኒህ ከኛዎቹ፤ ብዙው አባሎቻቸው ሥልጣን ለመውሰድና ራሳቸውን ለማበልጸግ ብጥስጣሽ ልብሶቻቸውን ጣጥፈው ለብሰው ከበርሃ የመጡ ሽምቅ ተዋጊዎች ነበሩና።

ሁለተኛ ደግሞ፤ እንደ ኢትዮጵያ በመሰሉ ሀገሮች፤ የገዥዎች ንጥቂያ ክስተት፤ በተፈጥሮው በጣም ውስን ነው (ባላባታዊ አስተዳደር ቀመስ እና በጎሳ ትስስር የተያዘ)። አለመታደል ሆኖ፤ በትስስር ተቀፍድዶ የተያዘው የኢትዮጵያ ሙስና፤ ለቅናትና መቻቻል አመቺ ይሆናል። ሙስናው የረዳቸው የአንድ ወገን ሊሂቃን ሀብታቸውን ሲያበዙ፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ያሉት ቅናት ይይዛቸዋል። በተገላቢጦሹ፤ በገዥው ቡድን ወገኖች በኩል፤ ይኼን መርዛማ ተግባር ችላ ብሎ የማለፉ አቀቤታ ሊከሰት ይችላል። ይህ ዝንባሌ የኬንያን ኅብረተሰብ ሠርጾ መግባቱ ታውቋል (የሚሸላ ሮንግን,የ 2009. “አሁን መብላቱ የኛ ተራ ነው።” የሚለውን መጽሐፍ ይመልከቱ።) የመጨረሻው ውጤት፤ እያንዳንዱ (በአብዛኛው ኃይለኛ) የጎሳ ቡድን ተራቸውን እየተቀባበሉ ሌሎችን በመጠቅጠቅ ራሳቸውን በሀብት የሚያደልቡበት እሾካማ ተናካሽ የሙስና እሽክርክሪት ነው። በነዚህ ሀገሮች (በተለይም ኢትዮጵያ) አንድ ሽንጡን ገትሮ የሚያደባ ጠንካራ መዘዝ እንዳለ ይታዘቧል – ይሄውም ለሙስና የደንበኝነት እና የዘመናዊ – ወራሽነት ባህሪ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ፤ የቀድሞ አንቆ ያዥ ገዥዎች ከፖለቲካ ሥልጣናቸው ከተወገዱበት ከአንዳንድ የድኅረ-ኮምኒስት ሀገሮች፤ ለምሳሌ እንደ ምሥራቅ አውሮፓ በተጻራሪነት መልኩ፤ የኢትዮጵያ ነጣቂዎች የፖለቲካውንም የምጣኔ ሀብት ሥርጭቱንም ጠቅልለው ይዘውታል። የሩስያ እፍኝ ገዥ ባለጸጎች፤ ሀብት ያግበሰበሱት፤ ከዚያም ከዚህም በማምታታት እና ሁሉንም ዓይነት የሀብት ማጠራቀም ወንጀሎችን በማካሄድ፤ የሀገራቸውን ንብረት በጣም በርካሽ ዋጋ በማግበስበስ ጭምር ነበር (የኢትዮጵያ አጓዳኞቻቸውም ይሄኑ ተግብረዋል)። አቶ ፑቲን ታዲያ የአንዳንዶቹን የሥልጣን ጥመኝነት አልወደደውም ነበርና የመንጥር ዘመቻውን አካሄደና አንዳንዶቹን ወደ ዘብጥያ አወረደ። አንዳንዶቹን ደግሞ ለስደት ዳረጋቸው። ይሄን ሲያደርግ በጎን ንብረታቸውን ጋፍፎ ባዶ አስቀርቶ ነው (ለሱ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ለመሆን ያልቃጣቸውን ትቶ)። የምሥራቅና የመካከለኛው አውሮፓ ነጣቂዎች፤ በከፊል እነዚህ ሀገሮች የአውሮፓ ኅብረትን መቀላቀል ስለፈለጉና ስለጣሩ፤ እናም የአውሮፓው ኅብረት ያስቀመጠውን ቅድመ-ሁኔታ ማሟላት ስለነበረባቸው፤ ኅብረቱም የገዥዎችን ነጣቃ በመታገልና በማጥፋት ስለረዳቸው፤ ቀስ በቀስ የፖለቲካ ተደማጭነታቸውን አጡ።

በአራተኛ ደረጃ፤ ኢትዮጵያን በመሰሉ ሀገሮች፤ የገዥዎች ነጠቃ አቻ የለውም፤ ማለትም በሌሎች ሀገሮች ከሚገኘው በተለየ መንገድ ጠንካራ ነው። ይህም፤ ሁሉን የፖለቲካ ሂደቱን ማከናወኛ መስሪያ ቤቶችና የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ቁንጮ ያጠቃለለ መሆኑ ነው። እዚህ ላይ ንጥቂያው የጦር ሠራዊቱን፣ የጸጥታ ክፍሉን፣ የውጭ ጉዳይ መመሪያውን፣ እና የፍትኅ ሥርዓቱን አልፎ ተርፎም የሕዝብ ግንኙነት መስመሮችን በሙሉ ያካትታል። በኢትዮጵያ፤ የጉልበተኛ ዘራፊዎቹ የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ቁንጮ አንቀው መያዛቸው፣ የሀብት ምንጩን ያላግባብ መውሰድ፣ በዘረጉት የፖለቲካ ሥልጣን ትስስር ተጠቅመው ሀብት ማካበት አልጠግብ ባይነት፤ በደሃና በሀብታሞች መካከል ያለውን የአጥር ልዩነት ከመቼውም በላይ እያሰፋ፤ አሁንም ያለምንም ገደብ እየጎደራ ነው። የልሂቃኑ ዝርፊያ እንዲያው በደፈናው፤ ራሱን መንግሥታዊ ሥርዓቱን በወንጀል የተጨማለቀ ስላደረገው፤ አልፎ አልፎ የተደራጀ ወንጀለኛ ቡድን (ማፊያ) የሚያከናውናቸው ድርጊቶች ብቅ ይላሉ። የገዥዎች ንጥቂያ በኢትዮጵያ ሌላው የተለየ መገለጫው፤ በጣም የከፋ የአንድ ጎሳ ወገንተኝነት ተፈጥሮው ነው። በዚህም የተነሳ፤ የመንግሥት የሚባለውና የግል የሚባለው፤ መለያ መስመራቸው ደብዝዟል፤ ፓርቲው ከመንግሥቱ ተለይቶ የማይታይ አካል ሆኗል። ለዚህም ነው ብዙዎቹ፤ የኢትዮጵያን የሙስና ቅንብር፤ በጣም የጋለ ዝርፊያ ነው ወደ ማለት የተፈታተኑት። እኒሁ ወገኖች፤ በዚህ የተነሳ፤ ይህ የተነጠቀ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት በክፉ አዟሪት ውስጥ በመጠመዱ፤ ማንኛውም የአስተዳደሩን ሂደት ለማሻሻል የተወጠነ መመሪያ፤ ከወዲሁ ለውድቀት ተዳርጓል ይላሉ። ከመንግሥት አካል ውጪ ሆነው በሚንቀሳቀሱት እና በመንግሥቱ ውስጥ ባሉ ጉልበተኛ ቡድኖች መካከል የማያቋርጥ ፍጥጫና ግጭትን ያያሉ።

በኢትዮጵያ ምን ተፈጠረ?

በኢትዮጵያ የተከሰተው ከሀገሪቱ የንግድ ማከናወኛ ደንብ በተጻራሪ፤ የባዶ ቀፎ ኩባንያዎች መቋቋም ነው። እነዚህ ባዶ ቀፎ ኩባንያዎች የተቋቋሙት፤ ከሁለት እስከ አምስት የሚሆኑ “የአክሲዮኑ ተቋሯጮች”፤ እኒህ “የአክሲዮኑ ተቋሯጮች” የፖርቲ መሪዎች ሆነው፤ በመሰየም ነው። ገነት መርሻ እንደገለጹት፤ የፖለቲካ ፓርቲ የሆኑ የንግድ ክፍሎች በሀገሪቱ የንግድ ሥምሪት ሂደት ጎን ለጎን መሰለፍ፤ ለ ሀ) “የጥሬ ገንዘብ ተጋፎ ወደ ውጪ በመንጎዱ የሀገሪቱ የብልጽግና ምንጭ ሊሆን የሚችለው መንጠፉ፤ ለ) የፍቃድ አሠጣጡን እና ማምታታቱ ሐ) የመንገድ ሥራን፣ የሕንፃዎች መቆምን፣ እና ሌሎች የእነፃ ተቋራጭነትን በሚመለከት ለሚወጡ የመንግሥት ጨረታዎች፤ የውስጥ መረጃን በሚመለከት የቅድሚያ ጥቆማን ማግኘት፤ መ) የተወዳዳሪዎች እጥረት እና የመጨረሻው ደግሞ ሠ) የንግድ ሥምሪቱንና ባለሙያተኞችን በሰላ የአድልዖ ዘዴ የማግለል መንገድ ከፍቷል።
የታዘብነው፤ “የመንግሥት ንብረት የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን ለግለሰቦች ለመሸጥ በተቋቋሙ አስፈጻሚ ክፍሎች፤ አድልዖና በጥቅም የተቆራኙ ቡድኖች ፈጠራ ሲፋፋም ነው (ሚንጋ ነጋሽ)። የኢትዮጵያ ሕዝብ የታዘበው፤ የመንግሥት ንብረት የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን፤ ለግለሰቦች ለመሸጥ የተደረገው ሂደት፤ በትክክል አለመካሄዱ ነበር ((የገነት መርሻን፤ 2010)፣ የያንግን (1998)፣ የቬስታልን (2009)፣ እና የሚንጋ ነጋሽን (2010) ጥናቶችና ጽሑፎች ይመልከቱ)። ኢትዮጵያዊያን የታዘቡት፤ ፈጥርቀው በሚይዙ የፖለቲካ ፓርቲ ኩባንያዎች (“የችሮታ ተቋሞች”) እንደ የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ችሮታ – ትመማች (ኢፈርት – በእንግሊዝኛ፤ ትእምት – በትግርኛ ) እና በሥሩ በተጠቃለሉ ከመጠን በላይ የበዙ ኩባንያዎች፤ ከአጥናፍ አጥናፍ ተዘርግቶ የተዋቀረ የገዥዎች ንጥቂያ ነበር። የተረዳነው፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን አባላት፤ የሽምቅ ተዋጊዎች በነበሩበት ወቅት የዘረፉትን የሀገር ሀብት ለመመለስ፤ እምቢተኝነታቸው ነው። የምናውቀው፤ “በፓርቲያቸውና በመንግሥት የንግድ ድርጅቶች፤ ባንኮችን ጨምሮ፤” አጥር ዘለል የፓርቲ አባሎቻቸው “በከፍተኛ ደረጃ ባሉ ቦርዶች በበላይነት” መቀመጣቸውና፤ በአካባቢያቸው ላሉ የፓርቲ ኩባንያዎች፤ በቀላሉ የባንክ ብድር ማንዶልዶላቸው ነው። የሥራ ተቋራጭ ጨረታውን፤ “ሌሎች” የተባሉ ኢትዮጵያዊያንን በማግለል፤ ከፓርቲው ጋር ትስስር ላላቸው መሥጠቱና ውድድር ማምከኑ፤ ልክ በሕንጻ ግንባታ ውስጥ በጣም አይሎ እንዳለው፤ ወገንተኝነቱ፤ (የዓለም ባንክ ሙስናን በኢትዮጵያ ምርመራ፤ ምዕራፍ 6ን ይመልከቱ) ተቀጣጠለ። ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና አሁንም በመቀጠል፤ ዕለት ተዕለት እየታዘብን ያለነው፤ ለኒሁ ግዙፍ የተጠራቀሙ የንግድ ድርጅቶች ኅብረቶችና ካድሬዎቻቸው ለያዟቸውና የሚወዷቸው ኩባንያዎች ውለታ ማመቻቸቱ ነው። የዚህ ውጤት፤ የውድድር ሂደቱን ማምታታትና የውድድር የገበያ ሁኔታውን ባዶ ማስቀረት ሆኗል። የታዘብነው፤ ልክ በሶቪየት ኅብረት ጥላ ሥር እንደነበሩት ሀገሮች፤ የገንዘብ ነክ ጉዳይ በሙሉ፤ በተወሰነ ቡድን መያዙና በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው። በኢትዮጵያ እየታዘብን ያለነው፤ አዲስ የዜና ማሰራጨትን እና ፀረ-ሽብር በሚባሉ የይስሙላ ሕጎች ታንቆ መያዝን ነው። በኢትዮጵያ የተመከትነው፤ የአዳዲስ ሕጎች – ልክ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከውጪ ሀገሮች እርዳታ እንዳያገኙ የሚያግደው ሕግ ዓይነት፤ በዚያኑ ወቅት የገዥው ፓርቲ በሕጉ ሳይታሰር፤ ከውጪ በሚያገኘው እርዳታ ያለ ልክ በመጠቀም ላይ እያለ፤ – መረቀቃቸውና መታወጃቸው ነው። ያደገው፤ ጀሯችን ዳባ ይልበስ ያሉ ጉልበተኛ መሪዎች “አጉል ግትር፣ እብሪተኛና ከሀቁ የራቁ” የዜሮ ድምር አስተሳሰብ ባህላቸው ነው። ኢትዮጵያዊያን የታዘቡት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በማያቋርጥ ሁኔታ ሲጨፈጨፉና ድራሻቸው ሲጠፋ፣ የሀገሪቱ ተቋማትን፤ ነፃ የኅብረተሰቡ ማህበራትን በመበጣጠስም ሆነ የትምህርቱን ጥራት በማላሸቅ፣ በየጊዜው ራሳቸው ያወጧቸውን ሕጎችን በመጣስ፤ … ወዘተ. ሲያዳክሟቸው ነው። እየተገነዘበ ያለው፤ የውጪ እርዳታ ሠጪ መንግሥታትን ለመሸወድ፤ (ድርጅቱ እራሱ በሙስና የተነከረ መሆኑ የሚታማው) የተኮላሸ የፀረ-ሙስና መርማሪ ኮሚሽን መቋቋሙና፤ ይኼንኑ ሙስናን ለመዋጋት የሚደረግ ጥረት፤ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት እስከመጠቀም ድረስ መጥለፋቸው ነው። ልክ እንደ ሩስያና ሌሎች ቦታዎች፤ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የሕግ አውጪውን፣ ሕግ አስፈጻሚውን፣ የፍትኅና ሁሉን የሕግ ማውጫና ማስከበሪያ መንግሥታዊ ክፍሎችን ነጥቆ ይዟል። እኒህ፤ “ለዝርፊያ መቀራመት የተመራ (ለኪራይ ሰብሳቢነት)” ከሁሉም በላይ በጣም የከፋው ሙስና፤ የገዥዎች ንጥቂያ ሙሉ ገጸ-ባህሪ ማሳያ ምስሎች ናቸው።

እኒህ ጥቂቶቹ ናቸው፤
የተከተለው ውጤት፤

የገዥዎች ንጥቂያ (የማፊያን ተግባር ዓይነቱ) እና ወንጀለኛው ገዢ ቡድን፣ ከማይታመን እብሪትና ጭቆና ጋር ተዳብሎ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የጠለቀ ጨለምተኝነትን፣ ሁሉም ለራሱ ብቻ የሚስገበገብበትና፣ ጥግ ጥጉን ይዞ ተከፋፍሎ የተፋጠጠበትን ሀቅ አስከትሏል። ይህም በአንድ ምሽት፤ በፈጠራ ችሎታቸውም ሆነ ይኼ ነው በሚባል ጥሩ ነገር የማይታወቁ የትናንት ቁምጣ ለባሽ የሽምቅ ተዋጊዎችና ደሃ ታክሲ ነጅዎች፤ በማይታሰብ ደረጃ የተለጠጡ ቱጃሮች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ፤ ያገሬው ትንንሽ ባለሀብቶች፤ የጥፋቱን አቦል የተቋደሱበት የንብረትን መጋየት አስከትሏል። ግብታዊ መነሳሳት ግብታዊ አይደለም – ማለትም፤ ያለ ምክንያት ከመሬት ተነስቶ የሚካሄድ አይደለም። ምክንያቶቹ፤ በገዥው ፓርቲ በኩል ያለው የሚያቅለሸልሸው ስግብግብነት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ባለሀገር ነዋሪዎቹ፤ ለዘመናት ቀደምቶቻቸው ከኖሩበት ባድማቸው መፈናቀላቸውና፣ ይሄ ነው በማይባል ወይንም ያለምንም ማካካሻ፤ እኒሁ የተነጠቁ መሬቶች፤ የገዥው ፓርቲ ንብረት ለሆኑት ኩባንያዎች፣ ለገዥው ፓርቲ ልሂቃንና፣ ለውጪ ሀገር ሰዎች፤ ባለቤትነታቸው መዘዋወሩና መሠጠታቸው ነው። የግብታዊ መነሳሳቶች ምክንያቶች፤ ያለምንም ጥርጥር፤ የገዥው ክፍል መሪዎች ጭፍን ወገንተኝነትና በዚሁ ክፍል ልሂቃን በኩል የተደራጀ የቡድን ወንጀል መፈጸሙ ናቸው። ሙስና የጋለበበት የመሬት ልውውጡ፤ የሀገሪቱን የብልጽግና ምንጮች ባለቤትነት፤ ከተራው ሕዝብ ወደ በጣም ጥቂት ግለሰቦች እንዲዛወር አድርጓል። መሬታቸው በግዳጅ ተነጥቆ የተፈናቀሉትና የተጨቆኑት፤ ግፉ መጋቱ በቃን ያሉበት ሁኔታ ታየ። እንደ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ባለሙያነቴ፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን ያልተገራ ቁንጠጣ (አስገድዶ ማፈናቀል፣) እብሪት፣ የማይረካ ስግብግብነት፣ አፍኖ ያዡ ሙስና ) የማያባራ የሚነቅዝ ቁርሾ ትቶ ማለፉ ይታየኛል። ለገዥው ያልተገራ ቁንጠጣና ለፓርቲው ልሂቃን ወንጀለኛ ተግባር ምስጋና ይግባውና፤ አሁን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ፤ ለማጭበርበርና ለምዝበራ የጌጥ ስም ሆኖ ተወስዷል። በርግጥ፤ ሕዝብን ማዕከል የሚያደረጉና በትክክል ድጎማቸው የሚካሄዱ የከተማ ልማት ውጥኖች፤ ሁሉንም ባለጉዳዮች በአቸናፊነት የሚያስቀምጡ በሆኑ ነበር። መሬት ቀመስ ለሆነው ለከት አልባ ሙስና ምስጋና ይግባውና፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን የገማ ተንኮል ሽረባ፤ የወደፊት ሕጋዊ የልማት ውጥኖችን የመካሄድ ዕድልን ሽርሽሮታል። ያለ ጥርጥር እኒህ ያልተገሩ የገዥው ሤረኛ ቡድን ቁንጠጣዎች፤ ለወደፊት ልማት ከፍተኛ ደንቃራ ይሆናሉ።

በሻጥር የገማውንና በዝርፊያ የተለወሰውን፤ ብዙ አለመረጋጋቶችን ያቀጣጠለውን የመሬት ነጠቃ ትንሽ ጨምሬ እንዳብራራ ይፍቀዱልኝ። ልክ እንደ ቻይናና ሰሜን ኮርያ፤ መሬት የኢትዮጵያ መንግሥት ንብረት ነው። ይህ በተራው፤ መሬትን ያለምንም ማካካሻ ለመንጠቅ ሩጫን፣ ባገኙበት ለማግበስበስና ለአድልዎ የተመቸ ሁኔታን ፈጠረ። ከሚሽጎደጎደው የማያልቅ የመሬት አዋጆች ጥቂቶቹን መገልገያ መሣሪያቸው አድርገው በመጠቀም፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና መሬት ነጣቂዎች፤ የቻይናን አስገድዶ መሬትን መውረሱን ቀድተውት ይሆናል። የኢትዮጵያ መሬት ነጣቂዎች፤ ከእንዲህ ዓይነቱ ተግባር ጋር የተያያዙትን ችግሮች መረዳት የተሳናቸው ይመስላል።
አንደኛ፤ በማስገደድ ማፈናቀሉ፤ የሰብዓዊ መብቶችን ረገጣና ቻይና የፈረመችውን አስገድዶ ከመሬት የማፈናቀል ዓለም አቀፍ ውልን ድፍረቶች ማስከተል ብቻ ሳይሆን፤ የተንኮል ጥንሰሳው፤ እያደገ ለመጣው የገቢ ልዩነት ማሻቀብ አስተዋጽዖ አድርጓል። እያደገ የሚሄድ የኑሮ ልዩነት የሚያስከትለው ጣጣ እንዳለ፤ የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ገዥዎች መረዳት ነበረባቸው።

ሁለተኛ፤ በቻይና፤ አብዛኛው የመፈናቀሉ ተግባር የተፈጸመው፤ ከማዕከላዊው መንግሥት ፍላጎት ውጪ፤ በአብላጫው በአካባቢው ባሉ የክልል ባለሥልጣናት ነበር። በኢትዮጵያ፤ ሁለቱም መሬት የማካለሉ እቅድና በሥራ ላይ መዋል የተከናወኑት፤ በማዕከላዊው መንግሥት ባለሥልጣናት ዕዝና መመሪያዎች ነው። ይህም ላደጉት ቁርሾዎች አስተዋፅዖ አድርጓል።

ሶስተኛ፤ ሁለቱም የቻይና ማዕከላዊና የአካባቢ መንግሥታዊ አካሎች፤ ለብዙኀን የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በር የከፈተ የፋብሪካ የሥራ ቦታዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም በተዘዋዋሪ መንገድ ንብረታቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ሰዎች፤ የፋብሪካ ሥራው፤ ከፊል ማካካሻ እንዲሆንላቸው አድርጓል።

አራተኛ፤ በኢትዮጵያ በስፋት ከተስተዋለው በተጻራሪ፤ ምንም እንኳ የተሠጣቸው ማካካሻ መሬታቸው በወቅቱ ሊያስገኝ ከሚችለው ዋጋ ፍጹም የማይስተካከል ቢሆንም፤ የቻይና የአካባቢ ባለሥልጣናትና አልሚዎቹ፤ የተፈናቀሉትን የካሷቸው ይመስላል።

አምስተኛ፤ በኢትዮጵያው ሁኔታ፤ ከመሬት ጋር የተያያዘው ሙስና ተጠቃሚዎቹ (በማስገደድ ማፈናቀሉንና የንብረት መውደሙን በሚያካትተው) የገዥው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሆነው ተገኝተዋል።
ስድስተኛ፤ ከቻይናው በተለየ ሁኔታ፤ የራሱ የገዥው መመሪያዎች ክፍፍሉን እያባባሱት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ በጎሳ መስመሮች የተከፋፈለ ነው። በዚህም የተለሳ፤ ዘውገ-ነኩ የሙስና ነቀዛው ግጭቱንና ብጥብጡን ያባብሰዋል።

በመጨረሻም፤ ከኢትዮጵያ መሬት ነጣቂዎች በተለየ መልክ፤ የቻይና በለሥልጣናት፤ መሬታቸው ያለአግባብ በተነጠቁ ሰላማዊ ተቃውሞ አሰሚዎች ላይ የጥይት ውርጅብኝ አላሰፈሩም። ለዚህ ይሆናል ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ጎሳዎች፤ በተለይም ኦሮሞዎች፤ የፌዴራል ፖሊሱን (በተደጋጋሚ ተማሪዎችን አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲደበድብ የተስተዋለው) እና የጦር ሠራዊቱን፤ ንብረትነቱና መጠቀሚያነቱ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አጥፊ ጦር-ቀመስ የታጠቀ የሕዝብ መጨፍጨፊያ ቡድን አድርገው የሚወስዱት። የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ገዥው ፓርቲ ለፈጸማቸው ግፎች ተጠያቂነት እንደሌለው፤ በተደጋጋሚ አስተውለዋል። በጥቂቱ ለመጠቆም፤ በ 1995፣ 2005/6፣ 2014፣ አና አሁን 2015/6 ገዥው ክፍል እያደረሰ ያለውን ስቃይ፣ ግለስቦችን ከምድረ-ገጽ መሰወሩን፣ ጋፎ ማሰሩን፣ እና መጨፍጨፉን፤ በ2003 በአኝዎክ ወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን የሕዝብ ዕልቂት፣ በ2001 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መግደሉን ያስተውሏል። የኢትዮጵያን ሕዝብ የማያልቀው ግፍ አንገሽግሾታል። እኒህና ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሌሎች ስቃዮች ናቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ በሥልጣን ላይ ያለው የነሱ መንግሥት እንዳልሆነ እንዲያስቡ ያደረጋቸው። የሕዝብ ብልጽግና ምንጮቹን ጥቂቶቹ መቀራመታቸውና የኒህ ጥቂቶች ለከት የለሽ የሙስና ተግባር ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ ንብረቶቹና መዋዕለ ንዋዮቹ ከነሱ የማይወግነው የመዥገሩ ቡድን ናቸው፤ ብሎ እንዲያስብ ያደረገው። እናም ከዚህ ተከትሎ፣ “ከሌሎች” የሚመነጨውን ሙስና መገመቱ ከባድ አይደለም (በብዙዎች እንደወራሪ የተወሰዱ) በብዙ ሁኔታዎች ላይም፤ አንድን ጎሳ እንወክላለን በሚሉት እየተራገበ – በከፍተኛ ቅናትና ቁጣ እየተስተዋለ እያደረገ፤ ብሎም ተከፋፍሎ፤ ሁሉም ወደ ጥጉ መፈርጠጡን እያከረረው ሄደ።

የገዥዎች ንጥቂያ፤ ከጭቆናው፣ ከእብሪቱና፣ ከአረመኔ ተግባሩ ጋር ተዳምሮ፤ ሀገሪቱን እየተመነደገ ለሄደ የኅብረተሰብ-የፖለቲካ-የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ምስቅልቅል በሩን ፍንትው አድርጎ ከፍቶ፤ ለወደፊቱ የጎሳ/የጠባብ ወገንተኝነት ግጭቶች መካሄድ በማመቻቸት፤ እየበሰበሰ የመጣው ሥርዓት ወደ የሚጋለጥበትና የሚፍረከረክበት ሁኔታ አምርቷል። አለመታደል ሆኖ፤ እየሟሸሸ በመሄድ ላይ ያለው ሥርዓት፤ የአጓዳኝና የንጹኀን ሰለባዎች ይኖሩታል።
“መፍትሔዎች”፤ አሁን ካለንበት ወዴት እንሄዳለን?

ከላይ እንዳመለከትኩት፤ ለገዥዎች ንጥቂያ፤ መሻሻል ማድረግ ዕርሙ ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ በየጊዜው፤ በሕግ የመተዳደር ሥርዓት፤ በከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዳሻቸው ሲለሚሽከረከር፤ የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር ነፃ የሆነ የፍትኅ ሥርዓትን አስከባሪ አካል የለም። በተለያዩት የመንግሥት አካሎችም ምንም ዓይነት የሥልጣን ድርሻ ክፍፍል፣ መከባበርና መጠባበቅ የለም። ያለን ነገር ቢኖር፤ የተሽመደመደ ፋይዳ ቢስ ፓርላማ ነው። አለን ብለን የምንቆጥረው፤ በአጥንት የለሽነትና ደካማነት ታስሮ የተያዘ፤ ሥልጣን አልባው የፀረ-ሙስናው ድርጅት ነው። ከሞላ ጎደል ሁሉም የነፃና በግል ባለቤትነት የተያዙ ጋዜጦች ተገደው ድምጥማጣቸው ጠፍቷል፤ ብዙዎቹ ጋዜጠኞችም ታስረዋል፤ አለያም ተሰደዋል። እኒህ አረመኔያዊ እርምጃዎች፤ ሀገሪቱ (ራሱ የገዥው ሤረኛ ቡድንም) ነፃ የዜና አገልግሎትን በመጠቀም፤ ሥር የሰደደውን ሙስና የማጋለጥ ችሎታውን ነፍጓታል። በሀገሪቱ ያሉ የኅብረተሰቡ ድርጅቶች፤ አንድም ድርሻቸው ጠፍቷል አልያም የገዥዎቹ መገልገያ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ያለን፤ የመርማሪ መሥሪያ ቤቱ ሙስናን እና የቢሊየን ብሮች መሰወርን ሲያጋልጥ፤ የምርመራ ሹሞቹን አሽቀንጥሮ የሚያባርር የሀገራችን ዋና የሥራ አስኪያጅ አካል ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ እያንዳንዱ የቁጥጥር ድርጅት፤ አልፎ ተርፎ መሥራች፣ አቋቋሚ ፈትፋቹና አሁን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ቁንጮው ላይ በክብር የተቀመጡት አቶ ስብሃት ነጋ፤ በድፍረትና ያለዕፍረት፤ ሙስና በኢትዮጵያ ቅጥ አጥቶ ከመስፋፋቱ የተነሳ፤ የሃይማኖት ተቋማትን ሳይቀር ሰርፆ ገብቶባቸዋል እስኪሉ ድረስ፤ የገዥዎቹ ሤረኛ ቡድን መገልገያ ነው። የኢትዮጵያ ሤረኛ ገዥ ቡድን፤ የፀረ-ሙስና አለቃ ሆኖ የማይስተካከል ሥልጣኑንና ማኪያቬሊያዊ ስልቱን በመጠቀም፤ የሚያስቸግሩትን ለማጥመድና ጭጭ ለማሰኘትና ከተቻለም የሤራ ግዛታቸውን ሕይወት ለማርዘም የሚያገለግል ቭላድሚር ፑትንን (ማለትም መለስ ዜናዊን) የመሰለ አጥቷል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎችና ግብረ አበሮቻቸው፤ (ወይም ባጠቃላይ መላ ሀገሪቱ) (የአሜሪካን ዘራፊ ባላባቶችን የተቋቋመ) ስግብግብ የሤረኛ ገዥ ቡድኑን የሚገታ ወይም የሚያፈራርስ፤ ቴዎድሮስ ሮዝቬልት የላቸውም፤ የኢትዮጵያ ሤረኛ ገዥ ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት ተለይቶ መታየት አይችልምና። ሄዶ ሄዶ፤ በኦሮሞዎች ላይ የሤረኛ ገዥ ቡድን የተወሰዳቸው የድንብርብርና አይምሬ የጭካኔ እርምጃዎች በግልጽ የሚያመለክቱት፤ የገዥው ክፍል አንድ ፈላጭ ቆራጭ ቁንጮ መሪ ማጣቱን ብቻ ሳይሆን፤ ሀገር አቀፍ ማዕከላዊ ዕዝና ቁጥጥር እንዳነስው ጭምር ያመለክታል።

የቀሩልን፤ ሶስት በንፅፅር ሲታዩ ጠናካራ የሚባሉ ቡድኖች ሲሆኑ፤ እኒህ ቡድኖች፤ ሀገሪቱን ሁሉ ያበሻቀጠው ሙስና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ስቆቃ ሊያረግቡት ሲችሉ፤ የሚወስዷቸውት እርምጃዎች፤ እግረ መንገዳቸውን፤ ያልተገራ ዘራፊውን ገዥ መንግሥት ዕድሜ የማርዘም ዕድል አላቸው። ምንም እንኳ እኒህ ሶስት ቡድኖች የሤረኛ ቡድኑን መንግሥት የፖለቲካ ሕልውና ማርዘም ቢችሉም፤ በዚህ ደረጃ ያለ ሙስና በባለቤቶቹ ሊድን ስለማይችል፤ ከአይቀሬው ውድቀቱ ሊያተርፉት አይችሉም። እኔ በማቅማማት ላይ ያለሁት፤ ሀ) አህጉራት አቀፍ ተቋማት፤ ለማሳሌ እንደ አይ. ኤም. ኤፍ፣ የዓለም ባንክ፣ እና ሌሎችም፤ ለ) ዕርዳታ ሠጪ ሀገሮች፤ ዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት (በተለይም እንግሊዝ) እና ሐ) የገዥው አካል የሆኑና ከገዥው አካል ጋር ቅርበት ያላቸው ጉዳዩ የሚያገባቸው፤ ማለትም፤ “ላለው ሥርዓት ጥብቅና ቆመው የሚጠብቁት”ን (ብርሃኑ መንግሥቱ, 2016 – “ለፖለቲካ ሠፈሩ ምልጃ . . .”) በማጤን ነው። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ፤ በመንግሥቱ ላይ ከባድ ጫና ማድረግ የሚችል ፈርጠም ያለ ጉልበት አላቸው። እኒህ ተቋማትና ዕርዳታ ሠጪ ሀገሮች፤ ይህ መንግሥት ምን ያህል የዕርዳታ ጥገኛ – ዕልም ብሎ የዕርዳታ ጥገኛነቱ “[ልክ] በሕመም ማስተገሻ ከኒና እንደተለከፈ በሺተኛ፣” እንደሆነ ያውቃሉ። በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገሮች፣ ዩናይትድ ኪንግደም፤ ከርዳታ ሠጪ ተቋሞች ጋር በመሆን፤ የሚሠጡት ዕርዳታ፤ ገዥዎቹ ለኒሁ ክፍያ የሚያደርጉላቸው፣ በግዳጅ ሰውን ወደ አንድ አካባቢ የሚያሰፍሩበት ወይንም በሌሎች መንገዶች የሚያፈሱት፤ የሙስናው ምንጫቸው መሆኑን ግጥም አድርገው ያውቃሉ። ሌሎች ቦታዎች ላይ እንዳሳየሁት፤ ዕርዳታ ሠጪ መንግሥታት፤ የፓርቲው ስብስብ የተዋቀሩ ግዙፍ የንግድ ድርጅቶች መነሻ ገንዘባቸው፤ የሚሠጡት ዕርዳታ መሆኑን ያውቃሉ። እኒህ ዕርዳታ ሠጪ መንግሥታት ከፈለጉ፤ የትግሬዎች ነጫ አውጪ ግንባር መሪዎችን፤ ከውጪ የተሠጠን ዕርዳታ ማባከንና ገንዘቡን ያለአግባብ ወዳልተገባ ቦታ ማዛወር በሚል ክስ መስርተው፤ አንገታቸውን ሊያስደፏቸው ይችላሉ። ሶስተኛውን ቡድን በተመለከተ፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግሥቱ (2016) እንዳቀረበው፤ “ላለው ሥርዓት ጥብቅና ቆመው የሚጠብቁት” የሚሳካላቸው፤ “ከመካከላቸው ጥቂት አክራሪ የሆኑ ባለጉዳዮችን”፤ ለውጡ ለነሱ ዘላቂ ፍላጎት በጣም ጠቅሚነቱን በማግባባትና፤ ለውጡንም ተቀብለው በመምራትም ነው። እዚህ ላይ ትክክለኛ ጥያቄ ማስቀመጥ ይቻላል። እኒህ የሥርዓቱ ዘብ ቋሚዎች፤ ከላይ እስከታች ሁሉም የፓርቲ አባላት በሚገማ መልኩ ሙስኞች ሆነው፤ የራሳቸውን ስግብግብነትና ግለኝነት መቆጣጠር ይችላሉ ወይ? የሚለውን ነው። ታዲያማ ይኼን ካላደረጉ፤ እስካሁን ያካበቱትን ሁሉ ያጣሏ!
እሺ፤ ታዲያ በእምቢተኝነት ተቃውሟቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማሰማት የተነሱት ኦሮሞዎች ንብረቶችን እና የመዋዕለ ንዋይ ሕንጻዎችን ለምን አቃጠሉ? ይኼማ ባንድ ሌሊት እልም ያሉ ቱጃሮች ያደረጋቸውን የራሳቸው ያልሆነን መሬት፤ እንዳሻቸው በሚዘርፉ ሁሉን ለኔ የፓርቲ ልሂቃን ላይ፤ ሥር የሰደደው ምሬት ያስከተለው ነው። ሕዝቡ ያየው፤ ጥሮ ግሮ ሀብት ማግኘት፤ ወይንም በአያት የቅድመ አያት ባድማ ላይ ለማረስ ቅድሚያን ማግኘት ሳይሆን፤ ሀብት ማካበቱ፤ ቅጥ ያጣ ሙስናን፤ አፍቃሪ ፓርቲ መሆንን፣ የደም ትስስርን ተከትሎ ሲነጉድ ነው። በእምቢተኝነት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት የተነሱት፤ ከትውልድ ቦታቸው ላይ በአስገዳጅ መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሥራ የላቸውም፤ ገንዘብ የላቸውም፣ ተስፋውም እንኳ የላቸውም። የኒህ ተነሳሺዎች የተለዩ ይዞታዎችን እየለዩ ማጥቃቱ እንደሚያመለከተው፤ ማቃጠሉ/ ማውደሙ እና የእምቢታ ዕቀባው ያተኮረ የሚመስለው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና የደጋፊዎቹ በሆኑት ላይ ነው። አለመታደል ሆኖ፤ እኒህን የመሰሉ ቅሬታዎች፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች ዘንድ ተረግዟል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ብዙ የሚቃጠልና የሚጠፋ የሀብት ምንጭ ባይኖራትም፤ በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊት ሊደገም ይችላል።

አለመታደል ሆኖ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የምጣኔ ሀብት ሥምሪት አጉራ ዘለል ጉልበተኝነት እና መንግሥት የሚመራው የስቃይ ናዳ፤ አንጀቱ ቆስሏል። ያንጀት መቁሰል ወደ ተስፋብሲነት፣ አክራሪ ቁጠኝነት፣ እና የዛለ መንፈስ መያዝ ያመራል። ከዚያም በላይ ራስን ጎጂ እስከመሆን ያደርሳል። ስለዚህ፤ የንብረት ቃጠሎዎች፤ ኦሮሞዎች ከደረሰባቸው በደል የተነሳ ያንጀታቸው መቁሰል ተከታይ ውጤቶች ናቸው። አንድ ቀን እኒህን የመሰሉ ጥፋቶች፤ ምንአልባትም በከፋ ሁኔታ፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ይደገሙ ይሆናል የሚል የሚቀነቅን ፍርሃት አለኝ። በላያችን ያንዣበበውን አደጋ እንዳይከሰት የሚያደርጉ ተገቢ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለን ፀሎትና ተስፋ እናደርግ።

ጸሐፊው፣ ሰዒድ ሃሰን፣ በመሪ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት (ኢኮኖሚክስ) ፕሮፌሰር ናቸው። ሊያገኟቸው ከፈለጉ፤የኢሜል አድራሻቸው፤ shassan@murraystate.edu ነው።

ለዲ/ን ኒቆዲሞስ፦ በውቀቱ ስዩም፣ ጓደኛው ተመስገንን “ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር …” እንዳለበት አልመከረም! ውሸት ነው! አሊ ጓንጉል

$
0
0

ዲ/ን ኒቆዲሞስ፣ በውቀቱ ጓደኛው ተመስገንን “..ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር …” እንዳለበት መክሯል የሚሉትን ከየትኛው ገጽ ላይ እንዳገኘኸው አላውቅም። “አንሶላ”፣ “ሲጋፈፍ” እና “ማደር” የሚሉት፣ እንኳን ቃላቶቹ ራሳቸው፣ የግስ እርባታቸውም በምዕራፉ ውስጥ የለም። ለነገሩ ግን “መጽሃፉም” እንኳን ቢሆን፣ “ብዙ ተባዙ” ሲል አንሶላ ሳይጋፈፉ መባዛት የለም። በውቀቱ ያለው “አለምን መቅጨት…” ማለት ደግሞ፣ እንዳለ በጽሁፋዊ (Literal) ትርጉሙ በየትኛው መ/ቃላት “አንሶላ መጋፈፍ..” ማለት እንደሆነ ዲ/ን እና ዲ/ን ኒቆዲሞስ ብቻ መሆን አለበት የሚያውቀው። ስለዚህ ዲያቆኑ ዋሽቷል።

ለመሆኑ ፍሮዳይኒዝም “…የሚያስተምረው ራስን ያለ ልክ መውደድን ነው። ሃይማኖትን አለመከተል፣ እግዚአብሔርን አለመቀበል፣ ባህልን አለመጠበቅ፣ ወሲብን ለእርካታ ብቻ መጠቀም፣ የገዛ እናትን ለወሲብ መመኘት የገዛ ወላጅ አባት እንዲሞት በጥልቅ መሻት የመሳሰሉት እሳቤዎች የፍሮይድ አስተምህሮ የማዕዘን ድንጋይ ናቸው። ለፍሮዳዊያን ወሲብ እንቅልፍ ማምጫ እንጂ ከአብሮ መቆየት፣ ከቅዱስነት፣ ዘርን ከማስቀጠል፣ ሓላፊነት ከመውሰድ ጋር ፈፅሞ አይገናኝም…” ያልከው ከየትኛው መጽሃፍ ላይ ነው ያገኘኸው? ለምን መጽሃፉን ከነገጹ ጠቅሰህ አትነግረንም? እኔ “ሲግመንድ የሚታወቅባቸው ነገሮች” ብየ ጎግል አድርጌ፣ በጎግል የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ያገኘሁት ይኸን ነው፦ “… Freud has been influential in two related, but distinct ways. He simultaneously developed a theory of the human mind and human behavior, and a clinical technique for helping unhappy (i.e. neurotic) people. በግርድፉ እንዲህ ይተረጎማል፦
ሲግመንድ ፍሪውድ በተለያየ መንገድም ቢሆን በሁለት [እርስ በርስ] በተገናኙ ጉዳዩች ለውጥ አምጪ ሆኗል–ደስታ ቢስ የሆኑ ስዎችን መርዳት የሚያስችል የህክምና ቴክኒክ ፈጥሯል፣ የሰው ልጅን ባህርይ (behavior) እና አይምሮ (mind) በተመለከተም ቲዩሪ ነድፏል።
ሲግመንድ በስራዎቹ ውስጥ ስለወሲብ እና ውስብና መጻፉ እርግጥ ነው። እግዚአብሄርን አለመቀበል ደግሞ ከሶቅራጢስ ጀምሮ ያለ፣ በዚህ ዘመንም ትልቅ ሃይማኖት እየሆነ ነው። ነገር ግን ታላቅ የክ/ዘመኑ ሊቅ ከሆነው ከሲግመንድ ፍሩይድ ታላላቅ ስራዎች ውስጥ “ወሲብ፣ ባህልን አለመጠበቅ፣ ወዘተ…” የመሳሰሉትን ኢምንት የሆኑትን ጉዳዩች ብቻ በመጥቀስ፣ እንዲህ በሙያው የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጠውን ሳይንቲስት “ሰይጣን” አድርጎ መቀባት፣ የራስን “ቅዱስነት ለማጉላት” [ምናልባትም ምንም ቅዱስ ነገር ሳይሰሩ] ካልሆነ ምን ይባላል?
መግቢያየ ላይ እንደጠቀስኩት ዲ/ን ኒቆዲሞስ ያልተባለውን “ተብሏል” ብሏልና ዋሽቷል። “ከአንድ የሃይማኖት ሰባኪ እንደዚህ ያለ ውሸት አይጠበቅም…” እንዳልል፣ በውቀቱ ካሁን ቀደም “…የዲሲ ቄስ በበኩሉ ሙዳየ ምጽዋት አፍሶ፤… የንስሃ ልጁን ጡት ተንተርሶ፤ በቴስታ ተከሳክሶ ይኖራል የሚል ሀሜት አለ…” እንዳለው፣ የአብዛኛውን የሃይማኖት መሪዎችን በሞራል የመዝቀጥ ነገር ሳስበው “በርካታ እውነት የሚናገሩ የሃይማኖት መሪዎች አሉ” የሚል እንድምታ ያስከትልብኛል። እናም በደፈናው ዲ/ን ኒቆዲሞስ እንዲህ ያለተጻፈ ነገር እንደተጻፈ አስመስሎ የመጻፉ ነገር ብዙም አይገርመኝም።

እኔ ዲ/ን ኒቆዲሞስን ብሆን ኖሮ፣ ብዕሬን የማነጣጥረው፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ እስተ ሎንዶን ከተሞች ሳይቀር የምዕራቡን አለም ከተሞች እስኪቀውጥ ድረስ በኡኡታ አገር ሲያምሱ እና ሲያተራምሱ፤ “በቴስታ ሲከሳከሱ…” የሚውሉትን እና በቅርቤ ያሉትን ሰዎች መተቸት እና መፍትሄ መፈለግ ላይ ነበር የምሰራው። “እሱ ብሎ ቄስ፣ እሱ ብሎ ጳጳስ፣ ዲያቆን ማንትስ ይኼን ያህል ገንዘብ አጎደለ፣ የወያኔ ተላላኪ ነው…ወዘተ…” የሚል ጽሁፍ እና የቪዲዩ ንትርክ ሳናይ ውለን የምናድርበት ቀን አለ እንዴ?

አንድ በአገሪቱ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ አንቱ የተባለ ያገሬን ሰው “ለኢትዮጵያ ምን ትመኛለህ” ብለው “…ላንድ ሰከንድ የነብይነት ስልጣን ባገኝ፣ ኢትዮጵያዊ እንዳይዋሽ አደርገው ነበር” ያለኝን ሳስታውስ፣ እና እንዲህ ከሃይማኖት መሪዎች የሚታየው ማስመሰል፣ ቅጥፈት እና ሸፍጥ፣ ኢ-ሞራላዊ መሆን…ወዘተ ያመጣብን ይሆን? እላለሁ።

ስለ ዲሲ ቄስ “ሙዳየ ምጽዋት ማፈስ”፦ አንዲት በጣም የምግባባት እና በሰዓት $7.00 እያገኘች፣ ተሰኞ እስተ ሰኞ ያለ እረፍት እየሰራች፣ ሜሪላንድ የምትኖር ያገሬ ሴት “… የስለቴን ለቤተስኪያን $1000.00 አገባሁ…” ብትለኝ “አብደሻል እንዴ! አሊቤርጎ የመሰለ ቤት ተከራይቶ ለሚሰብክ አጭበርባሪ ሁላ እንዴት እንዲህ የደከምሽበትን ገንዘብ ትስጫለሽ?” ስላት “…በቃ! ደስ ያለኝን ነገር ስላገኘሁ፣ ደስ ያለኝን ነገር አደረግሁ” ካለችኝ ወዲህ፣ እውነትም የያንዳንዳችን የደስታ ማግኛችን መንገድ የተለያየ ነው። ይቺም እህቴ፣ ደስታ እስተሰጣት ድረስ፣ ገንዘቧን ወንዝ ውስጥ ብትበትነውስ ምን አገባኝ?” ከዚያ ወዲህ አንስቼባት አላውቅም።

ስለ ዲሲ ቄስ “የንስሃ ልጁን ጡት ተንተርሶ ማደር”፦ በውቀቱ “ ሃሜት አለ…” ነው ያለው። እኔ ደግሞ በእርግጥ የሆነውን እና የግለሰቧን ማንነት ማውጣት ባይሆንብኝ ኖሮ፣ ለንስሃ አባቷ ሃጥያቷን ልትናዘዝ የሄደች ሴት እንዴት በአባቷ ልትደፈር እንደነበር ከነቤተስኪያኑ እና ከነቄሱ እዚህ በተናገርኩ ነበር። ምን ላተርፍ? የጉዳዩ ባለቤት የሆነችውን ሴት ራሷን፣ ዛሬም እየሄደች የአባቷን ስብከት እንደምትሰማ ስትነግረኝ “እኔ አንቺን ብሆን ኖሮ አንደኛ አጋልጠው ነበር፣ ሁለተኛ እሱ ያለበት ቦታ ድርሽ አልልም ነበር…” ስላት “… እሳቸውን ለመስማት ብዬ ብቻ አይደለም የምሄደው፣ ለቦታው ነው…” ታለችኝ ወዲህ፣ እንዲህ ያለ ክርክር አቆምሁ። እኔ የማውቀው፣ ሲጀምር ቦታውን (መስበኪያውን ቦታ/ቤተስኪያኑን) ያቆሙት እሳቸው (አባቷ) እና አባቷን መሰሎቹ ተጥራርተው ነው። እዚሃር/ሚካየል ራሱ ወርዶ ጎልላት ሲሰቅል አላየሁም።

አሁን አሁንማ በየፈረንጅ አገሩ ያለ ያበሻ ቄስ ሁላ “እልል በቅምጤ ” ሆኖለታል። የፈረንጅ ቸርች ሁላ ምእመን እያጣ እየተዘጋ ነው። ያበሻ ቄስ እና ደብተራው ሁላ እየተጠራራ ይገዛዋል። አንድ ወቅት፣ እንዲያው ለቤተሰብ ብዬ (እድሜ ለ66ቱ አብዩት፣ እኔም ተሃይማኖት ተተፋታሁ 35 ዓመት አለፈኝ) አንድ አዲስ የተከፈተ ቤተስኪያን “ግራንድ ኦፐኒንግ” (በውቀቱ “ሙዳየ መጽዋቱን እያፈሰ” አለ? ቀላል ቢዝነስ ነው እንዴ!) ላይ ተገኝቼ ነበር። ጸሎተ ቡራኬ ተሰጥቶ እንዲያው ታ’ቀረቀርኩበት ቀና ተ’ማለቴ ቀድሞ ያላየሁት አንድ ፈረንጅ ታ’ጠገቤ ቆሟል። መቸም ኢትዬጵያ የኖረ፣ ቅባ ቅዱስ አግኝቶ፣ ከርስትና የተነሳ፣ የተጠመቀም ይሆናል … እያልኩ ሳስብ፣ ራሱ ወሬ ጀመረኝ–በሹክሹክታ፦

“…ኢትዮጵያዊ ነህ፣ አይደል?”
“አዎን”
“አይ ኖው”
“ኧረ! እንዴት አወቅህ በል?”
“ዌል…ይኼ ቤተስኪያን የኛ ነበር፣ የሸጥነው ለኢትዮጵያዊያን ነው እና…”
ጆሮዬ ቆመ። “እናንት እነማን ናችሁ? ማለቴ የማን ቤተስኪያን?”
“የግሪክ…” አለና ፈገግ ብሎ ቀጠለ “…የማስተዳደሪያ ገንዘብ (በሙዳየ ምጽዋት የሚገኘው) መግባት አቆመ፣ ምዕመኑ ተመናመነ። ሳር ማሳጨጃ እና ማጽጃ ባጀት ሁሉ ጠፋ። እናም ተዘጋ፤ ይኼው እናንተ ገዛችሁት” አለኝ።

ለነገሩ የዲ/ን ኒቆዲሞስ ትኩረት በመሰረቱ፣ በንግስት ሣባ ርዕሰ ጉዳይ አስታኮ፣ የበውቀቱን በአደባባይ “ከሃይማኖት ጋር መፋታት…” (ኢ-አማኒነት) ለማጋለጥ እና ኢ-አማኒነትን ለመዋጋት ያደረገው ይመስለኛል። ኢ-ሃይማኖተኛነት እየገነነ/እየገዘፈ የመጣ “ሃይማኖት” እንደሆነ ዲ/ን ኒቆዲሞስ ሳያውቁ ቀርተው አይመስለኝም። ያ ብቻ’ማይደል፣ እንዲህ “ኩላሊት እያወጡ ይወስዳሉ፤ አሳ ነባሪ በላቸው፣ አይሲስ አረዳቸው…” እየተባልን ሁሉ እንዲህ አይናችንን እየጨፈንን የምንመጣበት የምዕራባዊያኑ አገር፣ ስለ እዝጌሩም ሆነ ሰይጣኑ፣ ስለ ሳባም ሆነ ሰለሞን፣ ስለ ወሲብም ሆነ “አንሶላ መጋፈፍ” ወዘተ… በነጻነት ለመወያየት፣ ለመጻፍ፣ ለመናገር ወዘተ የሚያስችል ዲሞክራሲያዊ መብት ያላቸው በመሆኑ ያቆሙት እና እንዲህ ያደረጁት/ያለሙት አገር መሆኑን ዲ/ን ረስቶት አይመስለኝም። የእሱም የንጀራ ነገር ቢሆንበት ይመስለኛል።

የምዕራባዊያኑ በነጻነት የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመናገር፣ የመጻፍ ወዘተ ሲፈቅድ፣ ኢ-አማኒያኑንም የሚሞግት ነጻነትንም ያካተተ ነውና፣ ዲ/ን ኒሞዲቆስ መከራከር መብቱ ነው። ግንሳ መዋሸት ባልተገባ ነበር። ደሞ’ስ የደራሲ በውቀቱ ጽሁፍ መጥፎ መሆኑን የታየውን ያህል፣ እንዲያውም መጽሃፉ ውስጥ የሌለውን እና “… እግረ ሙቅ ለሚጠብቀው ወዳጁ እንደ መልካም ወዳጅ በደጁ ከሚጠብቀው መከራ… ያንዣበበበትን የመከራ መርግ ለጊዜውም “…አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር…” ብሎ ስለመምከሩ በምናብም ቢሆን የታየውን ያህል፤ የተመስገን ደሳለኝ መልካም ሰብዕና፣ እና “… እንደምታሰር …ሰምቻለሁ… ልጆቹን ይዤ የመጣሁት ለዛ ነው። ከምሳ በኋላ እነሱን ሳዝናና ለመዋል አስቤያለሁ። የዛሬው ቀን የነሱ ነው…” (ገጽ 78)፣ የማለቱ እና ተመስገን ያለችውን ግማሽ ቀን፣ በጉዲፈቻ የሚያሳድጋቸው ልጆቹን ለማዝናናት የማሰቡ እና የማድረጉ መልካም ሰብዕና ለምን አልታየህም? ምነው የበውቀቱ አጉል/መጥፎ ሰብእና ብቻ ታየህ? የሌላውን ሰው መጥፎ ስራ (አንዳንዴ የሌለ ጥፋትን በመፍጠር፣ እና ምንም አይነት መልካም ስራ ሳንሰራ) አጎልቶ በማውጣት፣ የራስን መልካምነት ለማሳየት ከመሞከር የምንወጣው መቼ ነው?

‹‹… ወዳጄ እንግዲህ የፈራኸው የመከራ ቀን ኮተተት እያለ እየመጣ እንደሆነ ሳይገለጽልህ እንዳልቀረ እገምታለኹ እናም አብዮተኛው ወንድሜ …” የሚል ጽሁፍ ያለው የትኛው ገጽ ላይ ነው? መጀመሪያ ነገር እያንዳንዱን በመጽሃፉ ውስጥ ተጻፈ ያልከውን ነገር አንድም ቦታ ላይ ገጽ በመጥቀስ ያሳየኸው ነገር የለም። ሲመስለኝ እንዲሁ አድበስብሶ እና አስመስሎ ደራሲውን ለማስጠቆር የተጻፈ ነው የሚመስል።

“… በጠራራ ፀሐይ ወሲብ እንደ ሸቀጥ በሚቸረቸርባት በአሜሪካዋ በላስቬጋስ ከተማ ቆይታው በኋላ ይህችን ከተማ ‹‹አትጠገብም፣ ትጣፍጣለች›› በሚሉ ውብ ቃላት ነው ሊገልጽልን የሞከረው። እንዲህ ዓይነቱ ከሃይማኖታችን፣ ከኢትዮጵያዊ ባህላችንና ትውፊታችን ያፈነገጠ የበዕውቀቱ ለወሲብ ያለው ይሄ አፈንጋጭ አመለካከቱ እንዴት በልቡ ሊሰርጽ እንደቻለም እንዲህ ሲል ያወጋናል…” በሚልም በዕውቀቱን ሊተቸው ይሞክራል። ለመሆኑ የትኛው ባህላችን? ይኼ የ10 እና 11 አመት ህጻናት በቦሌ እና መርካቶ፣ በሃገሪቱ ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች… በየአደባባዩ ተኮልኩለው፣ ይበሉ ይቀምሱት አጥተው እያየን፣ ት/ቤት በመሄጃ እድሜያቸው ገላቸውን ሸጠው የሚኖሩ ህጻናት የፈሉበትን ኢትዮጵያዊ ባህላችንን፣ ትውፊታችንን እና ሃይማኖታችንን ነው?

ባንድ ወቅት አገር-ቤት ሆኜ፣ ለኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ፕሮጄክት ለመስራት፣ እየዞርኩ ቃለ መጠይቅ አደርግ ነበር። መርካቶ ውስጥ፣ በጎዳና/ሴትኛ አዳሪነት የምታድር አንዲት የ13 አመት ልጅ “…ኮንዶም ትጠቀሚያለሽ?” ስል ጠየቅኋት። “…እሞክራለሁ። ካልፈለጉ ግን አላስገድዳቸውም” አለችኝ። “…ኮንዶም አለመጠቀም፣ ለኤድስ እና አባለዘር በሽታ ያጋልጣል…” ከማለቴ “ተወኝ ባክህ! ኤድስም፣ አባለዘርም በሽታ ነው። ቀን ይሰጣል። አንተ ምግብ ሳትበላ ስንት ቀን መቆየት ትችላለህ? በሽተኛ እናቴ እና ሁለት ታናናሽ ውንድሞቼ የሚጠብቁት የኔን እጅ ነው። ጊዜ የለኝም..” ብላ፣ እዚያው ትታኝ፣ የመርካቶ ጽልመት ውስጥ ገባች።

እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ ጠቅላላ አሜሪካ፣ ቬጋስም ሆነ ሎስ አንጀለስ፣ 18 አመት ያልሞላቸው ልጆች፣ ለወሲብ ባደባባይ የማይታዩበት እና በዚህ እድሜ ክልል ካሉ ልጆች ጋር ወሲብ መፈጸም፣ በህግም ሆነ በሞራል የሚያስጠይቅበት አገር መሆኑን ነው! ሃያ አንድ አመት ያልሞላው ሰው መጠጥ ገዝቶ የማይጠጣበት፣ ሲጠጣ ቢገኝ፣ ሻጩም ጭምር የሚቀጣበት ህግ እና የሞራል መሰረት ያለው አገር እና ህዝብ መሆኑን ነው የማውቀው።

የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች ክንፉ አሰፋ

$
0
0

መገናኛ ብዙሃንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር ተቀብሎ በዜሮ የሚሸኝ ጀግና ነው። በዚህ ተግባሩ አድናቂው ነኝ። “እኔ-ነኝ” ያለ የዲሲ ፖለቲከኛን ሳይቀር ከአንዴም ሁለቴ እንደማስቲካ እያኘከ መትፋቱን እንመሰክራለን። የጡት አባቱ የሆነው ኦነግንም ቢሆን ‘A Critical Assessment of the Oromo Liberation Front” በሚለው መጣጥፉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ የጠረበ ፍጡር ነው። ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ የ”ነፍጠኛውን ሜድያ” ለመጠቀም የማይሞክርበት ምክንያትም የለም።

ጃዋር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ብቅ ያለው በቅርቡ ነው። በመጀመርያም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተማረባቸው ዱሙጋም እና ጭላሎ፣ አዳማም ሆን ሲንጋፖር ሆኖ ድምጹ አልተሰማም። የፖለቲካ ሂሳቡን ሰርቶ ሲያበቃ የበግ ለምድ ለብሶ ብቅ አለ። በሚኖሶታ ያለመውን ቅዠት ይዞ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ሲደርስ ባነነ። እዚያው ላይ ፈነዳ። ከዚያ በፊት ስሙም ተሰምቶ አያውቅም። እስከ ዲሲ ጉዞ ድረስ የኦሮሞ ህመም አይሰማውም ነበር። “ትንሽ ቆሉ ይዞ ወደ አሻሮው… “ እንዲሉ የኦሮሞነት ጆከሩን ይዞ ፖለቲከኞችን እና መገናኘ ብዙሃኑን መቅረብ ነበረበት። እነሱም ከሚገባው በላይ አስተዋወቁት። በደንብ አድርጎ ቦነሳቸው። ምሁር በሃገር የጠፋ እስኪመስል ድረስ መድረኩን እሱ በቻ ተቆጣጠረው። ቪ.ኦ.ኤ.፣ አልጃዚራ፣ ሲ.ኤን. ኤን፣ እና ዶች ቬለ ላይ ሳይቀር እየወጣ የኛን እጣ ፈንታ እስኪበቃን ነገረን። “ወጣቱ ምሁር” አንቱ የተባለ የኢትዮጵያ ጉዳይ ተንታኝ ሆኖ ከረመ። ድምሩን ካወራረድ በኋላ ፊቱን አዞረ። አዟዟሩ አደገኛ ነው። የፍሬቻ ምልክት ሳያሳይ እንደሚታጠፍ መኪና አይነት። “ይህ ሰው በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የጫነው ዲግሪ ነው ወይንስ ድንጋይ?” እስኪያስብል ድረስ በዘርና በሃይማኖት በፖለቲካ ፈነዳ።

ባጣ ቆዩን ትግል ሲቀላቀል ለአፍ ሟሟሻው አጼ ምኒሊክን አነሳ። የእምዬ ምኒሊክ አጽም እና ሃውልት ላይ ክተት አወጀ። ግዜ የሰጠው ቅል… እንዲሉ እንጂ የመላው ጥቁር ሕዝብ ማንነት መነሻ የሆኑት ምኒሊክ በሱ አፍ የሚጠሩ እንኳን አልነበሩም። ዳሩ መነሻውን የማያቅ መድረሻ የለውም። ሁለት አይን ያለው፤ ከሁለት አቅጣጫ ይመለከታል። ሁለት ጆሮ ያለውም ሁሉንም አመዛዝኖ ይሰማል። አንገት ያለው ደግሞ አዙሮ ያለፈውን ይመለከታል። ያለፈው ከሌለ የወደፊቱ ከምን ሊነሳ? ጃዋር በአምሳሉ የፈጠራቸውን ምስለኔዎችን በሱ የፖለቲካ ዜማ ቃኝቶ ሲያበቃ በፓልቶክ ክፍሎች አሰማራቸው።

ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ገና ነብስ ያላወቁ ሕጻናትን ፎቶ በማህበራዊ ድረ-ገጾች እየበተኑ ለራሳቸው የፖለቲካ ግብ መጠቀም መሞከራቸው ነው። በሞራልም፣ በስነ-ምግባርም ሆነ በባህል ፍጹም ነውር የሆኑ ነገሮችን እያሰሙን አብረን ከረምን። በቃ! የጃዋር ፖለቲካ ይኸው ነው። ይህ ነው የሱ ጀግነነት። ምኞቱ ጀግና መሆን ከሆነ ደግሞ ቦታው ሚነሶታ አልነበረም። ስለ አመጽ የሚሰብክ ወንድ ልጅ መኖርያው ልክ እንደ አንበሳ ከወደ በረሃው ነው።

ይህ ሰው በፌስቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረውን አንድ ጽሁፍ ካነበብኩ በኋላ፤ ለዚያ አሳፋሪ ጽሁፍ ምላሽ በመስጠት እና ባለመስጠት ላይ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነበር። በጃዋር ገጽ ላይ የሰፈረው በዚያ አስጸያፊ ጽሁፍ ያልቆሰለ ቢኖር ጉዳዩ ያልገባው ብቻ መሆን አለበት። በእርግጥ ሌሎች እንዳደረጉት ነገሩን ንቆ መተው ይቻላል። ታድይ የሰው ዝምታ እንደስምምነት የተወሰደ ይመስል የሰውዬው ሙቀት እየጨመረ ሄደ። በተቀረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ላይ የጥላቻ ዘመቻውን ገፋበት። በዓድዋ እና የአጼ ምኒሊክን ቅኝት በአዲስ ዜማ ይዞ ዳግም ብቅ አለ። እንደራሴውን በስውር እየሰበሰበ በባንድራችንና በኢትዮጵያዊነት ላይ ዘመቻ አቀደ። ይህንን በሰፊው እመለስበታለሁ።

በፌስቡክ ገጹ ላይ የሰፈረው የጃዋር መልእክት እንዲህ ይነበባል፤
…Enjoy the show, the bill is on us… ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ “(የኦሮሞ አመጽ) ትዕይንቱን እያያችሁ ተዝናኑ። ሂሳቡን በኛ ተውት።” እንደማለት ነው።

አሳዛኙን የኦሮሞ ወገኖቻችን እልቂት ነው ተዝናኑበት እያለን ያለው። ይህንን አሰቃቂ ድራማ ከሚነሶታ ሆኖ ሲመለከተው አስቂኝ ነው የሆነበት። እሱ ምን አለበት? እሳቱ ውስጥ አልገባ። ወላፈኑም ፈጽሞ አይነካው። ምሰቆቃውን እንደ ሆሊውድ ፊልም ቁጭ ብሎ መመልከቱ ሳይንሰው ሌሎችንም በራሱ ወጪ ለመጋበዝ የሚዳዳው ደፋር። ይህ ስላቅ ነው ወይስ ፌዝ? ከሞቀ ቤቱ መሽጎ በሰው ልጅ ሰቆቃ መቀለዱ አንድ ነገር ነው። ከሁሉም የሚያስገርመው ደግሞ በዚህ ጽሁፍ ስር ድጋፋቸውን የሚገልጹ እንደራሴዎቹ ብዛት ነው። ሰው በዘር ፖለቲካ ሰክሮ ማሰብና ማገናዘብ ተስኖታልም ያሰኛል። ጽሁፉ በግልጽ እንደሚያስረዳው እየተካሀደ ያለው እልቂት ላይ ጃዋር ማፌዙ አልገባቸው ይሆን? በዚያው የፌስ ቡክ ገጽ ላይ የሚወጡ ዘግናኝ ፎቶዎችን እየተመለከተ የሚዝናና ሰው ካለ ይህ ጤነኛ አይደለም። የአእምሮ ችግር ያለበስ ሰው እንኳን በዚህ አይነቱ የሰዎች ሰቆቃ የሚዝናና አይመስለኝም። ግን የዚህ ሰው ፍላጎት ምን ይሆን?
በዚያ ሰሞን ወዳጄ ሄኖክ የሺጥላ የለቀቀው ጽሁፍ ጃዋርን በደንብ አድርጎ ይገልጸዋል።

“እንጀራውን” በተገፉ እና በተከፉ ሰዎች ታሪክ ላይ ያደረገ ሰው ፣ ህይወቱን በሰዎች መከራ ላይ የገነባ ፣ ኑሮውን ባጋጣሚ ለድምጽ አልባ እና አቅም አልባ ወገኖቹ ለታይታ የሚቆጭ…. ራሱን ትልቅ ለማድረግ፣ ከፊት ሆኖ ለመታየት እና ለመግነን ማናቸውንም አይነት ክፋት ከመፈጸም ልቡ ተው የማይለው ሰው። ሲል ሄኖክ ይገልጸዋል። እኔም ጃዋርን ከዚህ በተሻለ አልገልጸውም።

ሲጀመር እየተካሄድ ባለው የኦሮሞ ወንድሞቻችን የመብት ትግል ውስጥ የእነ ጃዋር እጅ መግባቱ አብዛኞችን ጥርጣሬ ውስጥ ከትቷል። ምክንያቱም ግልጽ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች እና ገበሬዎች ስለ መብት ሲሟገቱ የእነ ጃዋር አጀንዳ ደግሞ ሌላ በመሆኑ።

የኦሮሞ ተማሪዎችና ገበሬዎች ይዘውት የተነሱት ጥያቄ አግባብ ያለውና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደገፍ የሚገባው ጉዳይ ሆኖ ሳለ ሌላው ወገን ዳር ቆሞ የመመልከቱ ምስጢር ግልጽ ይመስላል። እነዚህ ወገኖች መብታቸውን ለማስከበር የማያባራ ትግል እያደረጉ ባሉበት ወቅት እነጃዋር በረጅሙ ምላሳቸው ሌላውን ወገን የሚያስበረግጉ መፈክሮችን ይዘው ብቅ አሉ። “ኦሮሚያ ለኦሮሞ!” እና “የክርስትያኑን አንገት መቁረጥ!” መፈክር!

እርግጥ ነው። ጃዋር ረጅም ምላስ አለው። ወገን የሚሻው ደግሞ ረጅም ምላስ ሳይሆን ረጅም ጭንቅላት ነበር። የሁለቱ ልዩነት የትየለሌ ነው። ረጅም ጭንቅላት አርቆ ሲያስብ ረጅም ምላስ ደግሞ ከሩቅ ይስባል። እንደ አለመታደል ሆኖ ባለ ረጅም ምላሶች የህዝብን የመብት ጥያቄው እየነጠቁ በራሳቸው አጀንዳ ይተኩታል። እናም የዚህ ትግል ውስጥ ሌላው ወገን ተመልካች ብቻ እንዲሆን ያደረጉት ጃዋር እና በሱ የፖለቲካ ቅኝት ውስጥ ያሉት ደቀ መዛሙርቱ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ይዘውት የተነሱት መፈክር ሌላውን ወገን ባያስበረግግ ነበር የሚገርመው። አንዳንድ ቦታዎች የጃዋርን መፈክር የያዙ ሰልፈኞችን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ማሰማራታቸውን ማስተዋሉ ለዚህ ማስረጃ ይሆናል።

በአንድ ወቅት በጃዋር የሚመራ ይህ ቡደን ዋሽንግተን ዲሲ ስቴት ዲፓርትመንት በር ላይ ቆሞ፣ “Ethiopia out of Oromia”! “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ጥውጣ!” እያለ ፈረንጆችን ይማጸን የነበረበትን ማስረጃ ከዩቱብ ላይ መመልካት ይቻላል። (https://www.youtube.com/watch?v=uXah_qtW8sg)

በሌላ ግዜ ደግሞ “…እኔ በምኖርበት አካባቢ ቀና የሚል ክርሲያን ከተገኘ አንገቱን በሜንጫ ቆርጠን እንጥላለን::”(https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8) ሲል የአይሲስን አንገት ቆረጣ በአደባባይ ያበሰረ ሰው ነው። እዚህ ላይ ልብ በሉ። ወንጀል የሰራን ክርስትያንን ሳይሆን “ቀና የሚል” ከተገኘ ነው እናርዳለን ያለው። ልቡ ያሰበውን እና አእምሮው የሚትያሰላስለውን ነው ያፈነዳው። የተናገረው በስህተት እንኳን ቢሆን ንግግሩን ባስተባበለው ነበር።

ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር አንድ ምሽት በአምስተርዳም ስንጫወት፣ “በእርግጥ ጃዋር መሃመድ የክርስቲያን አንገት እቆርጣለሁ ብሎ ተናግሯል?” ሲል ጠየቀኝ። አብሮን የነበረው ገረሱ ቱፋም “ንግግሩን ከኮንቴክስት መረዳት አለብን…” እያለ ሲያስረዳ ሞከረ። ገረሱ ቱፋ በዩኒቨርሲቲ ለኦሮሞ መብት ሲታገል ቆይቶ በኋላም በአስመራ በኩል ሞክሮ ሲያበቃ በሆላንድ በስደት የሚኖር ወጣት ነው። ኮንቴክስቱ ባይገለጽልንም ከዩትዩብ ላይ ያወጣሁት ቪድዮ አንገት በሜንጫ ስለመቁረጥ በግልጽ አማርኛ አስቀምጦታል። በዚያ እለት ነበር የኦሮሞ ሕዝብ በብዛት የሚኖረው በሸዋ እንድሆነና ይህም የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኑን ዶ/ር መረራ ያስረዳን።

በእነ ማልኮሜክስና በእነ ማርቲን ሉተር ምድር ቁጭ ብሎ አይሲስን አንገት መቅላት ወንጀል መናገሩ አይደለም የሚገርመው። ይህንን በአደባባይ በኩራት ሲናገር ህግ ባለበት ሃገር ዝም መባሉ እንጂ።

አል ጃዚራ ላይ ወጥቶ ኢትዮጵያዊነት በላዩ ላይ እንደተጫነበትም ደስኩሯል። ይህንን ዲስኩር ከሱ ውጭ ከሌሎች የኦሮሞ ልሂቃን አልሰማንም። በማንነት ቀውስ ውስጥ ካለ ሰው ይህንን መስማቱም ሊደንቀን አይገባም። ይልቁንም ይህንን ከነ በቀለ ገርባ ፣ ከዶ/ር መረራ፣ ከበአሉ ግርማ ፣ ከሎረት ጸጋዬ ገ/መድህን፣ ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ወይንም ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ አንደበት ብንሰማው እበር የሚከብደን። በእንደዚህ አይነት የጥላቻና የዘረኝነት እምሮው የታወረ ሰው እመራዋለው የሚለው አመጽ ላይ ለማበር የኢትዮጵያ ህዝብ ፈቃደኛ ባይሆን ሊደንቀን አይገባም። ከየትኞቹም የኦሮሞ ልሂቃን እንዲህ አይነት የኦሮሞ ሕዝብን ክብር የሚነካ ንግግር ሰምተን አናውቅም። “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ” “የክርስትያኑን አንገት በሜንጫ እንቆርጣለን” ሲል የትኛው የኦሮሞ ወገን ወይንም የትኛው የሙስሊም ህብረተሰብ ጃዋርን እንደወከለው አናውቅም። ልቡን ሞልቶ ሲናገር ግን የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ወገን ነጥሎ ለማስመታት የታቀደ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ግልጽ ነው።

የፖለቲካውን ምህዳር ጠቆጣጥረው ዘረኝነትን እና ጥላቻን ሲሰብኩ ምን እናደርጋለን? ንቆ መተው ወይንስ ቀይ መብራት ማሳየት? ቤንጃሚን ፍራንክሊን፣ ስለጥቃቅን ነገሮች ሲናገር፣ “በጥቃቅን ነገር ተጠንቀቅ፤ ትንሽ ፍሳሽ – ትልቅ መርከብን ታሰምጣለች።” ብሎ ነበር። በእርግጥ መርከቡ ሊሰምጥ የሚችለው ውሃ መርከብ ውስጥ እንዲገባ ስንፈቅድላት ብቻ ነው።

የጃዋርን አካሄድ ሳሰላስለው ቦካሳ ይታወሰኛል። የትም አይደርስም የተባው የማእከላዊ አፍሪካው አስር አለቃ ቦካሳ፣ ሁለቱም ተመሳሳይ አመጣጥ አላቸው። ሁለቱም በማንነታቸው የሚያፍሩበት የበታችነስ ስሜት ውስጥ የኖሩ ናቸው። ሁለቱም የማንነት ቀውስ ውስጥ የነበሩ ናቸው። ጃዋር በአንደበቱ እንደነገረን የአማራ እና የኦሮሞ፣ የክርስትያን እና የሙስሊም ቅልቅል ነው። እንደዚህ የተበሳተሩ ብዙ አሉ። አብዛኞቹ ታዲያ በማንነታቸው ይኮራሉ። እንደ ጃዋር ያሉ ጥቂቶች ግን የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ቢገቡ አይደንቅም። አባት እና እናቱን የማያውቀው ቦካሳ ከ 12 አመቱ ጀምሮ የማንነት ጥያቄ ሲያንገላታው የነበረ ሰው ነው። የም ሆኖ የትም አይደርስም እየተባለና የተናቀ ወታደር ነበር። የሃገሪቱ ርእሰ ብሄር ይሆናል ብሎ ያሰበ አልነበረም። አስር አለቃ ቦካሳ በለስ ቀንቶት እ.ኤ አ. 1966 በመፈንቅለ መንግሰ ስልጣን ይዞ ሲያበቃ የማእከላዊ አፍሪካን ህዝብ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ፈጀ ሀገሪቱን እንዳልነበረች አደረጋት።

ሰዎች ለአዶልፍ ሂትለርም የነበራቸው አመለካከት ከዚህ የተለየ ልነበረም። አንድ የጀርመን ታሪክ ተመራማሪ ሁኔታውን ሲገልጸው “They all had one thing in common – they underestimated Hitler” ነበር ያለው። ሁሉም የሚጋሩት አንድ ነገር ነበር። ሁሉም ሂትለርን ንቀውት ነበር። በመጨረሻ ሂትለር የጀርመን አዲሱ ቻንስለር ሆኖ ብቅ ሲል የናዚ ፓርቲ አባላት በደስታ እና በእንባ ተቀበሉት። በሀገሪቱ ህግ ሳይሆን በሂትለር አምላኪ ሆኑ። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የጃዋር አምላኪዎች እያደረጉ እንዳሉት ማለት ነው። ጃዋር “የእልቂቱን ትእይንት በኔ ሂሳብ እያያችሁ ተዝናኑበት” ያለውን አጢነው አይመስለኝም። በደፈናው ስለሚያመልኩት እንጂ።

ቦካሳም ሆነ ሂትለር በጥላቻ የመጡ ስለነበሩ ከምደር-ገጽ ጠፍተው ታሪክ ሆነው አልፈዋል። ጥለውት የሄዱት አሻራ ግን እስካሁን አለ።

ያገር ያለህ ወይም የዳኛ ያለህ!!! /ለውይይት የቀረበ/

ማ ማ በ ሰ ማ ይ ከተንሳይት በቃና

የሃገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተግዳሮቶች ገለታው ዘለቀ

$
0
0

በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ለማንሳት ስነሳ በ1994 ዓ.ም የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት ውስጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ሲወያዩ አንድ ምሁር የተናገረው ነገር ትውስ አለኝ። ትዝይላችሁ እንደሆነ የዚህ ምሁር ንግግር ብዙዎችን ኣስደምሞ ነበር። ለማስታወስ ያህል ይህ ምሁር ለራሳቸው ጠቅላይ ሚንስትር ለነበሩት ለአቶ መለስ እንዲህ ነበር ያለው።

“እዚህ አገር ሌላ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ተመስርቶ፣ ገበሬው ውስጥ ገብቶ ፋይዳ ያለው ለውጥ አይኖርም እርስዎ እያሉ። አይኖርም። ምክንያቱም እርስዎ እንዳይኖር ያደርጉታልና ነው። እስካሁን በዚህ ተሳክቶልዎታል በሚቀጥሉት ሃያ ኣመታትም ይህንኑ ያደርጋሉ።”

የሚገርመው ይህ ምሁር ምንም ውስብስብ ነገር አልተናገረም። ብዙ ምጡቅ አሳቦች በዚህ ስብሰባ ላይ ተነስተው ነበር። ይሁን እንጂ በተለይ የዚህ ምሁር ንግግር ግን ከተማሪው እስከ ምሁሩ፣ ከነጋዴው እስከ ሰራተኛውና ገበሬው ድረስ ኣስደንቆ ነበር። ለምን ብየ ጠይቄ አውቃለሁ። ሰው ሁሉ ይህን ምሁር ያደነቀበት ዋና ነገር ሁሉም በልቡ ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዲህ ነበር የሚያውቃቸውና ነው። እሳቸው እያሉ መድብለ ፓርቲ አይኖርም የሚል እምነት በዚህ ሁሉ ሰው ልብ ውስጥ ስለነበር ነው። አሁን ይህ ምሁር በሃቀኝነት ይህን ስሜት መግለጽ ሲችል ሁሉም እዎ! አገኘኸው ኣይነት ነው የተደመመው። አንዳንዴ የውስጥን ስሜት በቅንነት የሚገልጽ ሰው ሲገኝ ደስ እንደሚለን ነው ነገሩ። ምሁሩ እንዳለው አቶ መልስ ቅንነት የጎደላቸው ናቸው ብሎ ህዝብ ያዝን ስለነበርም ነው። በርግጥ ከዚህ ምሁር የወጣው ይህ ቃል ቅንነትንና እውነትን ይዞ ስለነበር የብዙዎችን ስሜት በቀላሉ መግዛት ችሎ ነበር።

ያ ምሁር “እርስዎ እያሉ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አይኖርም” አለ። አሁን አቶ መለስ ከዚህ ዓለም የሉም። ይሁን እንጂ ኣሳባቸውና ያፈሯቸው ደቀመዛሙርት ልክ እንደሳቸው ስለሆኑ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላም እነሆ ዛሬ ድረስ የዚህ የመድብለ ፓርቲ ጉዳይ እክሎች በዝተውበት ይኖራል። አቶ መለስ በኣካል ባይኖሩም አሉ ማለት ነው።

ያ ምሁርም ሆነ ብዙው ኢትዮጵያዊ በዚህች አገር በዚህ መንግስት ስር መድብለ ፓርቲ አድጎ ነጻ ምርጫ ተካሂዶ በውነት ያሸነፈው ስልጣን ይይዛል የሚለው እምነት በብዙዎች ዘንድ የወረደ ቢሆንም ግን ያሉትን ፓርቲዎች ወይ ተቀናጅተው ወይ አንድ የተሻለ ፓርቲ ጠንክሮ ወጥቶ ለመብታቸው እንዲያታግላቸው ይፈልጋሉ። እናም ዛሬ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሆነው ጉዳይ ለምን አንድ ጠንካራ ድርጅት አይኖርም….? ለምን ተቃዋሚዎች ይበታተናሉ….? ለምን ህብረት አቃተን……? የሚል ነው። እንዴውም በአንድ ወቅት ህዝቡ ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ እያለ ብስጭት የተሞላበት ስሜትም አንጸባርቆ ነበር። በርግጥም መቶ የሚሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች የቀፈቀፍን እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን በረከት አንለውም። ወደዚያ እሚታጠፈው ታጥፎ የሚከስመው ከስሞ የተወሰኑ ፓርቲዎች ይበቁናል። መቶ ፓርቲ ስሙንም ሸምድደን አንዘልቀው።

ከዚህ ከብዛቱም በላይ ግን የኢትዮጵያ መድብለ ፓርቲ ስዓት ጉዳይ ከፍ ያሉ ችግሮች አሉበት። በዚህች በዛሬዋ ጽሁፌም የገጠሙንን ለእኔ የታዩኝን ኣራት ጉዳዮች አንስቼ ችግሮቻችንን ለመዳሰስ እፈልጋለሁ።

ከዚያ በፊት ግን የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ሃይላት ደካማዎች ናቸው ይላል። ለምን? ሲባል አንዱ ኣዘውትሮ የሚያነሳው ጉዳይ አማራጭ ፖሊሲ የላቸውም የሚል ነው። ሌሎች አንዳንድ ሰዎችም በርግጥ ይህን አሳብ ይጋራሉ። እውነቱን ለመናገር መንግስት ግን ይህን አዘውትሮ የሚገልጸው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይመስለኝም። ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ለዲፕሎማቶች ነው። መንግስት ተቃዋሚዎች ኣማራጭ ፖሊሲ የላቸውም ብሎ ለህዝቡ ቢናገር ህዝቡ ጥያቄው የአማራጭ ኣሳብ ጉዳይ እንዳልሆነ ያውቃል። ኣማራጭ ኣሳብ የሚባለው ነገር በመጀመሪያ እውነተኛ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ይጠይቃል። እውነተኛ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ባለበት ኣገር ኣማራጭ ኣሳቦች ህዝብ ጋር ወርደው በሃሳብ የበላይነት የያዘው የህዝብን ቀልብ ስቦ ተመራጭ ይሆናል። የህዝብን ቀልብ ስቦና ኣስደምሞ ስልጣን በማይያዝበት ኣገር ጥያቄው የህግን የበላይነት የማያከብሩ ስብስቦች ይውረዱና ለውጥ ይምጣና ደሞ ሌላውን እንሞክረው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ራሱ በሚያወጣቸው ህጎች ስለማይገዛ፣ ህግን ስለማያከብር፣ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ የሰባዊ መብቶችን ራሱ መንግስት እንደፈለገ ስለሚጥስ ለውጥ እንፈልጋለን የሚል ነው። በመሆኑም ተቃዋሚዎች በነጻነት በማይንቀሳቀሱበት ኣገር ኣማራጭ ኣሳብ የላቸውም የሚለው ክስ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ሳይሆን ከፍ ሲል እንዳልኩት ለውጭው ዓለም ይሆናል።

ለነገሩ እኮ ኣንዳንዶቹ የተጠናከረ ባይሆንም ኣማራጭ ኣሳቦች ኣሏቸው።አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ጥሩ አማራጭ ኣሳቦች አሏቸው። መንግስትን በመሬት ፖሊሲ ዙሪያ ሲቃወሙና መሬት በመንግስትም በህዝብም በግልም መያዝ ኣለበት ሲሉ ኣማራጭ ኣሳብ ማለት ይሄ ነው።

በኣስራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ምርጫ ወቅት ቅንጅት ያን ያህል ህዝባዊ ተቀባይነት ያገኘው ህዝቡ የቅንጅትን ማኒፌስቶ ኣንብቦ ስለጨረሰ ኣይደለም። በዚያች ስድስት ወር ውስጥ ቅንጅት ሰፊ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ስለሰራም ኣይደለም። ህዝቡ በሃይል ለውጥ ፈልጎ ነበር። በኣንዳንድ ቦታዎች በቅንጅት ተወካይና በኢህዓዴግ ተወካይ መካከል ምርጫ ሲካሄድ ህዝቡ ለመመረጥ ኢህዓደግ ኣለመሆን ብቻውን በቂ ነው ይል ነበር። ይሄ የሚያሳየው ለውጥን በጣም ከመሻት የመጣ ምርጫም ነበር። አንደኛው ይሄ ነው። ሌላው ደግሞ የለሂቁ ክፍፍል መቀነስና ዘግይቶ የታየው ህብረት ነበር የኢትዮጵያን ህዝብ በተስፋ ባህር ላይ እንዲያ ያንሳፈፈው።

ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንቅፋቶች እንመለስና ርግጥ ነው ተቃዋሚዎች ብዙ መሰናክል ኣለባቸው። ጥንካሬና ህብረት ተስኗቸዋል። አቶ መለስ ቢሞቱም የመድብለ ፓርቲ ጉዳይ እያደር ቁልቁል ሆኗልና ለዚህ መሰረታዊ ችግሮች ናቸው ያልኳቸውን ዝቅ ሲል እኔም ላቀብል።

1. የህወሃት የጠለፋ የትግል ስልት
ህወሃት (ኢሃዴግ) ተቃዋሚዎችን የሚያጠቃበት ስልት በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ የመድብለ ፓርቲ የማሰናከያ ድንጋይ ነው። ህወሃት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ደርግን ለመጣል ይጠቀም ከነበረባቸው ዘዴዎች መካከል ሰርጎ መግባት፣ ማታለል፣ መደለል፣ የስነ-ልቡና ጦርነቶችን ማድረግ ዋና ዋና ዘዴዎቹ ነበሩ። እነዚህን ስልቶች ዛሬም መድብለ ፓርቲ ስርዓት መስርቻለሁ በሚልበት ስርዓት ውስጥ ይጠቀምባቸዋል። ህወሃት ኣዲስ ኣበባን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ሌላ ቀዝቃዛ ጦርነት ከፍቶ ነው የሚኖረው። ዋናው ኣንዱ ችግሩ ህወሃት ራሱን እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን የሚያየው እንደ ዘውግ ተቆርቋሪ ማህበር በመሆኑና ለኢትዮጵያ የሚበቃ ወይም ኢትዮጵያን የሚሸፍን ዓላማ ስለሌለው በመድብለ ፓርቲ ውስጥ የውነት መጫወት ኣይችልም። ብሸነፍም ልሸነፍ ብሎ ለመወሰን ቢያንስ ኣገራዊ ድርጅት መሆንን ይጠይቃል። የሌሎቹ “የኢህዓዴግ” ኣባል ፓርቲዎችም ለህወሃት ተገዢ ከመሆን ባሻገር እንደዚሁ ተመሳሳይ ተፈጥሮ ነው ያላቸው። ለዚህ ነው እነዚህ ድርጅቶች የህይወት ታሪክ ውስጥ ጥርት ያለ ርእዮት የማይታየው።

በመሆኑም ኣውራው ፓርቲ ህወሃት ፖለቲካን ከማህበራዊ ማንነቱ ጋር ኣጣብቆ ስለያዘ በቀላሉ ለሃሳብ ፍጭት እጅ ስለማይሰጥ ተቃዋሚ የሚባሉትን ሁሉ በጠላትነት ያያቸዋል። እናም በደርግ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረውን ስልት ተግባራዊ እያደረገ ተቃዋሚዎች እንዳያድጉ ያደርጋል። ከተራ ኣባል እስከ ኣመራር ድረስ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ዘንድ ሰላይ እየሰገሰገ ህብረት እንዳያድግ፣ ህዝባዊ ሰላማዊ ትግሎችን እንዳይመሩ እያደረገ ያሸመደምዳቸኣል። ህወሃት ለብዙ ዓመት የዳበረ የጠለፋና ቆረጣ ልምድ ስላለው ተቃዋሚውን በቀላሉ ይጠልፈዋል። ኣንዱና ትልቁ ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች ኣለመጠንከር ምክንያት ይሄ ነው። በነገራችን ላይ ህወሃት እንዳይጠነክሩ የሚያደርገው ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ብቻ ኣይደለም። ኣጋር ድርጅቶቹንም ነው። እነ ብዓዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴግ ጠንካራና በራስ የሚተማመኑ እንዲሆኑ ኣይፈልግም። ይህን ቢያደርግ የሃገሪቱ የፖለቲካ ኣቅጣጫ እስካሁን ይቀየር ነበር። ነገር ግን እነዚህን ኣጋር ድርጅቶቹንም ጠልፎ ይዟቸዋል። ኢሃዴግ የተባለው ድርጅት እውነተኛ ማንነቱ ይታይ ቢባል ህወሃት ነው። ኢሃዴግ የህወሃት የፌደራል ስም ነው። ይሄ ማለት የኦህዴድ የደህዴግና የብአዴን ኣባላት ጨዋዎች ናቸው ማለት ኣይደለም። እነሱ ለግል እድሎች (Opportunities) መስፋት ሲሉ የህወሃትን የበላይነት ተቀብለው በሃገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳያድግ እያደረጉ ያሉ ናቸው። ተራው ኣባል ግራ ቢጋባም ከላይ ያሉት ግን በተለያየ ስልት የተያዙና ለህወሃት የበላይነት የሚሰሩ ናቸው። በኣጠቃላይ ህወሃት በስልጣን ለመቆየት ኣሳብን ወይም በኣሳብ በልጦ መገኘትን መሰረት ኣድርጎ ኣይኖርም። ዋናው እምነቱ ጠለፋ ነው። ኣጋር ድርጅቶችን መጥለፍና በራሱ እዝ ስር ማድረግ፣ ፕሬሱን መጥለፍ፣ ሰላማዊ ትግሉን መጥለፍ፣ ውጭ ያለውን ተቃዋሚ መጥለፍ…..ሁሉንም መጥለፍ…. ነው አዋጭ የትግል ስልት አድርጎ የሚኖረው። ስለዚህ በሃገራችን መድብለ ፓርቲ ስርዓት ኣድጎ እንዳናይ የሚያደርገን ይሄ የጠለፋ ጉዳይ ነው። ኢሃዴግ “ንብ” ነኝ ሲል የንብን የህብረት ስራ ያስታውሰናል። ኣውራው ኣለ። ሌሎች ደግሞ ውሃ ቀጂና ዘበኞች ናቸው መሰለኝ። ኣውራው ህወሃት ቢሆን እነ ኦህዴድ ብአዴንና ደህዴግ ዘበኞችና ውሃ ቀጂዎች ሆነው ይኖራሉ። ይሄ መለወጥ ኣለበት። በዚያች ድሃ ኣገር፣ ሁላችን ድሆች ሆነን እንዲህ ያለ ጅማሮ የትም ኣያደርሰንም።በህብረተሰቡም ውስጥ ይህ ነገር የተለየ ኤነርጂን እየፈጠረ ወደአልሆነ አቅጣጫ ስለሚመራን ቶሎ መቆም አለበት።

2. የፖለቲካ ውቅር (Political setup)

ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ የፖለቲካው ውቅር ነው። በመሰረቱ ኢትዮጵያ በብሄር ላይ የተመስረተ ፖለቲካ ካማራት በኮንፌደራል የመንግስት ውቅር ነው መተዳደር ያለባት። በርግጥ ይህ ጥያቄ የማንም እንዳይደለ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በብሄር ላይ የፖለቲካ ቤትን ኣቁም እንደገና መድብለ ፓርቲ ስርዓትን ኣራምዳለሁ ማለት ኣንዱን በሬ ወዲህ ኣንዱን በሬ ወዲያ ኣጣምዶ እርሻ ልጀምር እንደማለት ይቆጠራል። መድብለ ፓርቲ ስርዓትና የብሄር ፖለቲካ ኣብረው ኣይሄዱም። የብሄር ፖለቲካ ባለኣንድ ፓርቲ ገዢነትን የሚያበራታት ስሜት ያለው ነው። ሰማኒያ የሚሆኑ ብሄሮች ሰማኒያ የፖለቲካ ድርጅት ኣቋቋሙ ማለት መድብለ ፓርቲ ስርዓት እውን ሆነ ማለት ኣይደለም። መድብለ ፓርቲ ስርዓት ማለት በኣንድ ብሄራዊ የፖለቲካ ማንነት ስር የተሰባብሰቡና የጋራ ትልቅ ግብ ያላቸው ነገር ግን በፖሊሲና በኣይዲዮሎጂ የሚለያዩ ድርጅቶች ኣሳብ እያፋጩ በፖሊሲ ብልጫ እየተመረጡ የጋራ ኣገር የሚያሳድጉበት ስርዓት ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሁን የለም። ብሄራዊ ማንነት በኣካባቢ የፖለቲካ ማንነት እንዲዋጥ ስለሚደረግ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ኣይኖርም። መንግስት ለኣንዳንድ የህብረ ብሄር ድርጅቶች ፈቃድ ሰጥቶና እድገታቸውን አየከረከመ የሚያኖራቸው ኣንዱ በስልጣን ላይ ያቆየኛል የሚለው እምነቱ ስለሆነ ነው። ብዙሃኑን ለመያዝ፣ ግጭቶችን ለመቀነስ ነው። ከዚህ ውጭ ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰዓት መድብለ ፓርቲን የሚያስተናግድ ሲስተም ኣልቀረጸችም። ብሄራዊ ድርጅቶች የቆሙት ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ ስላላቸው እንጂ ሲስተሙ እየጠለፈ የሚጥል ነው።

3. የፖለቲካ ባህላችን

በእኔ እምነት ይህም የተወሰነ ተጽእኖ የፈጠረ ቢመስለኝም እንደ ዋና ችግር ግን ኣላየውም። በርግጥ ነው በተለይ ቀደም ያለው ትውልድ እስካሁን የግራው የፖለቲካ ተመክሮ ተጽእኖ ፈጥሮበት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የተለወጡና በኣዲስ መንፈስ የተነሱ ደግሞ አሉ። ያልተለወጡትና ዛሬም በድሮ በሬ ለማረስ የሚሹቱ አነሱ በርግጥ እርስ በርስ ሲጠላለፉ ይታያል። ይሄ መቀረፍ ያለበት ችግር ነው። ለኢትዮጵያ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መሽመድመድ ግን እንደ ዋና ምክንያት ኣይታይም። ያም ሆኖ ግን የፖለቲካ ባህላችን ሊያድግ የሚገባው ብዙ ነገር ኣለውና በመድብለ ፓርቲው ስርዓት እድገት ላይ የተወሰነ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል። ከዚያ ውጭ መንግስት ራሱ ተቃዋሚውን የፖለቲካ ባህላችን ደካማ ነው እያለ ቅስማቸውን ለመስበር እንደሚሰራ ይታወቃልና ፓርቲዎች ባህላችን ጥሩ ኣይደለም እያሉ ራሳቸውን ማፍረስ ለመንግስት እድሜን ከመጨመር ሌላ ኣይጠቅምም።እሚስተካከለውን ማስተካከል መድብለ ፓርቲን የሚሸከም ልብና ትከሻን ማዳበር ያስፈልጋል።

4. የግል ዝንባሌዎች

ኣንዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ኣለመጠናከር አስተዋጾ ያደረገው ጉዳይ ደግሞ ፖለቲካ በሃገራችን ውስጥ ሙሰኛ ስለሆነ ነው። ከፍተኛ የሚባሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድሎችን ሁሉ ዘርፎ ይዟል። በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የትምህርት እድልን ሳይቀር ዘርፎ የወሰደ በመሆኑ ፖለቲካው ሙሰኛነቱ ጫፍ ረግጧል። ስኮላርሺፕ ለማግኘት፣ በስራ ላይ እድገት ለማግኘት፣ የተሻለ ኑሮ ለመኖርና በተሰብንና ዘመድን ለመርዳት፣ ወደ ፖለቲካ ጠጋ ማለት ኣዋጭ ነው። ፖለቲካው እነዚህን ኦፖርቹኒቲዎች መዝረፉና ሙሰኛ መሆኑ ያመጣው ኣንዱ ችግር እድሎች በጠበቡበት ድሃ ኣገር የሚኖሩ ዜጎችን እድል ፍለጋ ሳያምኑበትም ቢሆን ወደ ፖለቲካ እንዲሳቡ ያደርጋል። ከመንግስት ጋር ኣጎብድደው እየሰሩ የተሻለ ትምህርት ለማግኘት ይጥራሉ። ኣንዳንዶች ደግሞ ገዢው ፓርቲ ደመወዝ እየቆረጠላቸው በተቃዋሚ ስም መንግስትን የሚደግፉም ይኖራሉ። ይህ ችግር በሰፊው በአገር ደረጃ ሲታይ ፖለቲካችን ጥሪ ባላቸው ኣስተዳዳሪዎች ብቻ ሳይሆን በብዙ እድል ፈላጊዎች የተጠቀጠቀ ሰሚያደርገው ኣጠቃላይ ፖለቲካችንን ጨዋታውን ኣበላሽቶብናል ይመስለኛል። ፖለቲካው ከመንግስትም በላይ ሆኖ ፓርቲ መንግስትን ሳይቀር ውጦ በሚኖርበት ኣገር፣ ፖለቲካው እንዲህ በሰፊው እድሎችን ሁሉ ከየሲቪል ሰርቪሱ ሰርቆ በሚኖርበት ኣገር፣ መድብለ ፓርቲ ኣፈር ይበላል። ፖለቲካም ኣያድግም።

ማጠቃላያ
እነዚህ ከላይ የጠቃቀስኳቸው ችግሮች ለሃገራችን መድብለ ፓርቲ ስርዓትና ለፖለቲካችን እንቅፋቶች ናቸው ብለናል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ብዙዎቻችን ጠንካራ ፓርቲ ባለመኖሩ በጣም እናዝናለን። ለምንድነው ጠንካራ ፓርቲ የፈለግነው? በአሁኑ ሰዓት ለምን ጠንካራ ፓርቲ ፈለግን? ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲስ ማለት ምን ማለት ነው?። መድብለ ፓርቲ ስርዓት በጠፋበት ኣገር ጠንካራ ፓርቲ ስንል በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ጽህፈት ቤት እየከፈተ የጦፈ የቢሮ ስራ የሚሰራ፣ ብዙ ኣባላት የመዘገበ ወዘተ ከሆነ ስህተት ነው። ላም በሌለበት ኩበት ለቀማ ማሰብ ነው። እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ የሚያስፈልገው መድብለ ፓርቲ ስርዓት ባለበት ምህዳሩ ባለበት ኣገር ነው። የኣሁኑ ትግል ከዚህ ይለያል። ትግሉ የነጻነት ትግል ነው። መድብለ ፓርቲ ስርዓትን ከምር ለመጀመር ነው ትግሉ። ለዚህ ደግሞ ብዙ ኣባል የመዘገበ ብዙ ቢሮ ያለው ድርጅት ሳይሆን የሚያስፈልገን ኣንድ ሰውም ሊበቃን ይችላል። ትግልን የሚመራ ኣንድ የነጻነት ታጋይ ሊበቃ ይችላል። በአሁኑ ሰዓት የተነሳውን የኦሮምያ ኣመጽ የትኛው ጠንካራ ፓርቲ ነው የቀሰቀሰው? ማንም ፓርቲ ኣይመራውም። ህዝብ ነው ያስነሳው።

አሁን እኛ ጠንካራ ፓርቲ የምንለው በምርጫ ያሸንፍልናል ሳይሆን ሰላማዊ ትግልን ይመራል ብለን ኣስበን ከሆነ ትክክል ነው። ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው ከድርጅታዊ ጥንካሬው በላይ የጥቂት ኣመራሮቹ ቁርጠኝነት ይበልጥብናል። እነዚህ ድርጅቶች ኣባላት ምዝገባ ላይ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም። ሁሉም በልቡ ኣባላቸው ነው። ለዚህ ነው ኣንድ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ሲጠራ ያን ያህል ሰው የወጣው። በልቡ ኣባል ሆኖ የጨረሰውን ሰው ፎርም ካላስሞላን ብሎ ጊዜ ማጥፋቱ ዋጋ የለውም። ይልቅ ህዝቡን በሰላማዊ መንገድ ለመብቱ እንዲታገል ማድረግ ነው። ይህን ግፍ የጠገበ ህዝብ ስለነጻነት ልናስተምረው፣ ስለለውጥ ጥቅም ልናስተምረው ኣያሻም። የሚያስፈልገው ትግልን የሚመሩ የነጻነት ታጋዮችን ማፍራት ነው።

ጠንካራ ፓርቲ ቢኖረን መልካም በሆነ። ነገር ግን በተለይ በሃገር ቤት ይህን ኣይነት ፓርቲ በኣሁኑ ሰዓት መጠበቅ ችግር ኣለው። ዋናው ማወቅ ያለብን ነገር ተቃዋሚዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ኣላቸው። ባይመዘግቡትም፣ የድርጅት ኣባል ኣድርገው መታወቂያ ባይሰጡትም ህዝቡ ኣባል ሆኖ ጨርሷል። በመሆኑም ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁኑ ፈጣን ምልሽ የሚሰጠው ሰፊ ህዝብ ኣለ። ህዝባዊ ተቃውሞዎችን መምራት የሚችል የተሰጡ መሪዎች ያሻናል። በዚህ ጊዜም ጠንካራ ፓርቲ ስንል የላይኛውን መሪዎች የመስዋእትነትና የቆራጥነት መንፈስ የሚመለከት ነው። ጠንካራ መሪዎች ብቅ ሲሉና ተቃውሞዎችን ሲመሩ ህዝቡን ለመብቱ ሲያታግሉት ያን ጊዜ ብዙዎችን ውጦ ጠንካራ ፓርቲ ወጣ ይባላል። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን ማድረግ ያለብን መልካም ራእይ ያላቸውን ፓርቲዎች ውጤት ተኮር እንዲሆኑ መከታተል ጠቃሚ ነው። መቼም ጠንካራ ፓርቲ ሁሌም እንሻለን። ይሁን እንጂ የአሁኑ አንገብጋቢ ጥያቄያችን የህዝቡን መብት የሚያስመልሱ ቆራጥ የነጻነት ትግል መሪዎችን ነው። ስለዚህ ህዝቡ መረዳት ያለበት ነገር ጣንካራ ፓርቲ መጠበቁ ጊዜ ይወስዳል። የፓርቲውም ቁጥር ገና ሊጨምር ይችላል። አሁን የሚያስፈልገው ዜጎች ለነጻታቸው፣ ለመብታቸው በራሳቸው መቆምን ነው። ህዝባዊ እምቢተኝነቶች መሪዎችን ያፈራል። ታላቁ መሪ ማርቲን ሉተር ኪንግ የነጻነት ትግል ውጤት ነው፣ ከህዝብ ትግል መሃል የወጣ ነው። ማርቲን ሉተር ሳይሆን ትግሉን ያፈራው ትግሉ ነው ማርቲን ሉተርን ያፈራው። ኔልሰን ማንዴላ በራሳቸው አንደበት እኔ የደቡብ አፍሪካዉያን የትግል ውጤት ነኝ ብለዋል። መሪ የሚያፈራ ትግል ማድረግ አለብን። ኢትዮጵያን በተሻለ አቅጣጫ መምራት የሚችሉ ብዙ ልጆች አሉ። ጭቆና ተጭኗቸው ይሆናልና እነዚህን መሪዎች የህዝብ ትግል ያወጣቸዋል። በሌላ በኩል ፓርቲዎችም በቆራጥነት ትግሉን ምሩ፣ ህዝቡን ለመብቱ አታግሉት። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

አስተያየት ካለዎት በዚህ ኢሜየል ይጻፉልኝ
geletawzeleke@gmail.com

ኦሮምያና “ልማታዊ ሙስናዎቿ”ከሚክያስ ግዛው

$
0
0

እኔ እንኳን ወያኔ በፈጠራቸው ዘረኛ የክልል ስሞች አካባቢዎችን መጥራት አልፈልግም ነበር። በዘር፣ ነገድ፣ ጎሳና ጎጥ የሚወሰን የማንነት ግንባታ (identity empowerment) አፍራሽ ይመስለኛል። ብቻ ይሁን እስቲ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ወዘተ ማለቱን ትቼ እንደው እንደዘበት “ኦሮምያ” ልበል። ኦሮምያ ውስጥ ሙስና (corruption) እንደ አንድ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ዘርፍ (political economic sector) ተቆጥሮ ዋልጌዎች ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ እየተገበሩት ይገኛሉ። ይህ በደጋግና ጀግኖች ሕብረተሰብ ማህል የተደነቀረው የክፋት ገጽታ የመልካም አስተዳደር መርሆችን (good governance principles)፣ ባህላዊ ትሥሥሮችንና ሥነ-ምግባርን በማጨለሙ ሕዝቡን ለድህነት ዳርጓል። እስቲ እኔ ከታዘብኩት ውስጥ ጥቂቱን ላካፍላችሁ።

እውነት (Truth)፣ እውነት እምነት ነች። ሰዎች ስለአካባቢያቸውም ሆነ የዓለም ዙርያ እንቅስቃሴና ክንውኖች እውነቱን የማወቅ መብት አላቸው። ሰዎች እውነትን ሲረዱ ወደፊት ሊተገብሩ ስላቀዱት ዓላማ ግንዛቤ ይጨብጣሉ። በኦሮምያ የስልጣኑ ባሌቤት ኦሕዴድ ቀድሞውም ቢሆን በእብለት መሠረት ላይ የታነጸ በመሆኑ እውነት ማንጸባረቅ አይችልም። ድርጅቱ ባለቀልም የዋርካ ሥዕል ያለበት ባንዲራ እያውለበለበ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ከመንጎድ ውጭ ፋይዳው አይታይም። በአሮምያ ክንውኖች ሁሉ ህፀፅዊ(fallacious) ወደ መሆን ደርሰዋል። በየስብሰባው ውሃ የመይቋጥሩ አረፍተሃሳቦች (fallacious arguments) ይወረወራሉ። ባለስልጣናት ሕዝቡን በመናቅ አደናጋሪና አሳሳች (deceptive, misleading ; fallacious testimony) መረጃዎችን ይበትናሉ። የውስጡ መሠረታዊ ችግር ሳይመረመር ላይ ላዩን የተድበሰበሰ (disappointing; delusive) መፍትሄ መሰል ሃሳብ ቀርቦ ስብሰባው በተዳፈነ ሠላም (fallacious peace) ይጠናቀቃል። በእርግጥ ሁሉንም በአንድ ላይ መጨፍለቅ (generalization) ተገቢ አይደለም። የለበሱትን ሕዝባዊ አደራ በንፃት የሚጠብቁ ቢኖሩም የሙሰኞቹ ጥቁር ሥራ ግን በጎ ክንውኖችን ማጉደፉ አልቀረም። እውነት – ኦሮምያ ምድር ሞታ ልትቀበር ትንሽ ቀርቷታል።
መሬት (Land)፣ መሬት በሕዝባዊ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስትውል ልማት ባግባቡ ይፋጠናል። በሃገራችን የመሬት ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ አልፋና ኦሜጋ ነው። የተፈጥሮ ኃብት (Natural resources) ከጉልበትና ዓዕምሮ (labour and mental) ጋር ሲዋሃድ ምርትን (production) ያስገኛል። መሬት የተፈጥሮ ኃብት ዋነኛ መፍለቅያ ምንጭ ነች። ማንም ሠላምንና ጸጥታን፣ ልማትንና እድገትን የሚፈልግ ስብስብ የመሬትን ጉዳይ ፍትሃዊ (justify) ለማድረግ ሲል ጠቃሚ መሠረታዊ ህጎችን (system of rules)በቅጡ ይቀርጻል። ይህ ጉዳይ ፈጽሞ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ ጥቁር ገበያዎች (black markets) እንደ አሸን ይፈላሉ። ጥቁር ገበያ በሙስና (Corruption) የሚመራ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ፍዳና ዕዳ ነው። መሬት የመንግሥት ኃብት እንዲሆን ፈላስፎችና የምጣኔ ኃብታዊ ሊቆች እጅግ ሠፊ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሠጥተዋል። “መሬት ላራሹ” በኢትዮጵያ ተራማጆች ዙርያ ዘወትር ሲነሳ የቆየ ታሪካዊ መፈክር ነበር። የተጨቋኖችና አጋሮቻቸው እምቅ አስተሳሰብ የወለደው ይህ ታሪካዊ መፈክር ተንቆ ይባስኑ የኦሮምያ መሬት የቀማኞችና ሙሰኞች መገልገያ ሆኗል። በኦሮምያ መሬት አሞሌ ጨው ተሸክሞ ለመጣ ሁሉ በቀላሉ እንደምትቸረቸር ኮማሪት ተንቃለች። መሬት “በሶስተኛ ደላሎች” ስም እንደዋዛ የምትለወጥ ጉቦኛ ባለሥልጣናትና መዝባሪው ነጋዴ የሚሻሟት አሳዳሪ የራቃት ባለቤት አልባ ሆናለች። መሬት በኦሮምያ ምን ያልሆነችው አለ? አሜሪካ የተፈጠረችው በቀይ ሕንዶች ደም ላይ ነው። አሜሪካ የተገነባችው በአፍሪካውያን ባርያዎች ግፍና ሰቆቃ ነው። ይህን ግፍ የዲሞክራሲ ቋሚ ምሰሶ ወይም ዓምድ አይደለም። ገዥው መንግሥት ሰዎችን በፌደራል ፖሊስ ጥይት ካስገደለ በኋላ “ለዲሞክራሲው ግንባታ ገና ነን፤ አሜሪካ እስከ ስድሳዎቹ መባቻ ድረስ ሰዎች ይገደሉ ነበር” ብሎ ያወራል። አገዛዙ ልማቱን እየዘረፈ፣ ሰዎችን እንደ ቀይ ሕንዶች ከቀዪአቸው እያፈናቀለ፣ ጥሬ ሃብቱን ለባዕድ እየቸረቸረና “መሬቴን አትንኩ” ያሉትን ነዋሪዎች እያሽመደመደ “ዲሞክራሲው ገና አልጎለበትም” ብሎ ያሾፋል። ይህን ትምህርት የቀሰሙት ከሱዛብን ራይስ ከሆነ ያሳዝናል። መልካሞቹን የዲሞክራሲ እሴቶችና የመልካም አስተዳደር መርህን ካደጉት ሃገሮች ተሞክሮ እየቀሰሙ ማዳበር ሲቻል መሬትን ለመቀራመት ብሎ ተወላጁን፣ አገር በቀሉን (indigenous) መግደል የዲሞክራሲ ባህሉም ወጉም አይደለም።

ኢንቨስትሜንት፣ (investment) እኔ ራሴ investment, establishment, department, እንደው ምናለፋችሁ «ment» ያለበት እንግሊዘኛ ሲነገር እፈራ ነበር። ግናስ የሠፈራችን አንድ አጉራ ዘለል “ኢንቬስተር” ተብሎ ከውጭ ሲመጣ ቃሉን ተለማመድኩኝ። ምን ሊቨሰትር ነው? ብዬ ስጠብቅ አቀባባይ ረድፈኞችን በእንግሊዘኛ ደልሎ አስደልሎ መሬት ጨመደደ። መሬቱን ደግሞ ሸጦ ገንዘቡን መሬቱን ከሰጡት ከባለስልጣናት ጋር ተካፈላው ሲባል ሰማሁ። በኦሮምያ ብዙ ኢንቬስተሮች ይስተናገዳሉ። ከባለሱቁ አንስቶ እስከትላልቅ ሳሙና፣ ዘይትና ብስኩት ፋብሪካ ድረስ በሙስናው ማህደር ተመዝግቦ በጉቦኛው ማህተም ይለፍ የተመታለት የንግድ ተቋም ሁሉ “እንቬስትሜንት” ተብሎ ይወደሳል። ባንዳንድ አካባቢዎች የኢንቬስትሜንቱ ባለቤቶች (clandestine wealth) “የማይታዩት ባለስልጣኖች” ወይንም ተባባሪዎቻቸው ሲሆኑ የንግድ ፈቃዱ የተመዘገበው ባንድ ጭቁን የኢንቬስተሩ ሎሌ ነው። ይህ ዘመናዊ የሎሌነት ሥራ የተቀዳው በቅኝ ግዛት ሥር ከነበሩት የአፍሪካ ሃገሮች ነው።

ስብሰባ (session)፣ አስተማሪያችን “ስብሰባ ሎጂክ (logic) መጠቀምያ ጠቃሚ ጊዜ ነው” ሲሉ እሰማ ነበር። የፍርድ ሸንጎ ሠብሳቢ የነበረው አጎቴ ደግሞ “የስብሰባ አዳራሽ ዝም ብሎ ተሰባስቦ እንቅልፍና ራስ ምታት መሸመችያ ቦታ አይደለም” ይል ነበር። ሰው ከተሰበሰበ ንድፈ ሃሳብ አፍልቆ፣ እልባት ያለው ውሳኔ ሸክኖ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ አለበት (Theory + practice = Praxis)። ኦሮምያ ስብሰባ ታበዛለች። በሃያ አምስት ዓመታት ኦሮምያ ያስተናገደችው ስብሰባ በሜትር ሲለካ የዓለም ሊግና የተባበሩት የዓለም መንግሥታት ማህበር ካደረጉት ስብሰባ በሶስት እጥፍ ይበልጣል። ምን ንድፈ ሃሳብ ተወረወረ? ምን ተወሰነ? ምን ተፈየደ? ምንም። በእርግጥ እድሜ ለሙስና ሠማይ ጠቅስ ሕንጻዎች ቆመዋል፣ ጥሬ ኃብቱንና ምርቱን ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ መንግሥት ዘመናዊ መንገድ አንጥፏል። የሕዝቡ ኑሮ ግን አልተሻሻለም። የሕዝቡ ባህልና እሴቶች ተደፍጥጠዋል። ተሰብሳቢዎች የሙስናንና ጉቦ መርሆችን በሰምና (wax) ወርቅ (gold) አሽሞንሙነው ይለያያሉ። ሰሙ “ሙስና ይጥፋ” ሲሆን ወርቁ ደግሞ”ሙስና እጥፍ ይሁን” ነው። የመናገር ችሎታ፣ በእጅ የመሄድ አክሮባትና ድፍረት መለማመጃ የሆነው የኦሮምያው ሙስና ወለድ ስብሰባ ብዙ ገንዘቦች አባካኝ ጎጂ ባህል እየሆነ መጥቷል። ሃቀኛ ነጋዴዎች የመንግሥት ገቢ ለመክፈል ማለዳ ወደ አገር ውስጥ ገቢ ሲሄዱ “ፋይሉ አልተገኘም” ተብለው በኪራይ ሰብሳቢዎች ይባረራሉ። ችግሩን ለማን አቤት ይባላል። አለቆች ስብሰባ ላይ ናቸው። ሃቀኞች ዓመታዊውን ግብርና መንግሥት የደነገገውን ቫት ለመክፈል እንኳን ተቸግረዋል። የመንግሥትን ገቢ ለማስገባት ሙስና ለምን አስፈለገ? ፋይሉ ጠፍቷል በመባሉ ምክንያት ግብር የተቆለለበት ሃቀኛ ነጋዴ ሲጉላላ ማየቱ አሳዛኝ ነው። ይህ ክፋት ኬንያና ናይጄርያም እንኳን አልተከሰተም። በኦሮምያ “ስብሰባ” ሙስናን ማጠናከርያና ኪራይ ሰብሳቢዎችን ማሰልጠኛ ሠንበቴ ከሆነች ሰነበተች።

ፍትህ (justice)፣ በኦሮምያ ፍትህ ደብዝዛለች። ደብዳቢውና ተደብዳቢው ፖሊስ ጣብያ ቢሄዱ ተደብዳቢው ይታሠራል። ዘራፊና ተዘራፊ ሸንጎ ፊት ቢቀርቡ ተዘራፊው ተሸማቆ ከእልፍኙ በአፋጣኝ እንዲወጣ ይደረጋል። ዳኛና ጠበቃ የጥቅም ትሥሥር አድርገዋል። ፍርደ ገምድል ዳኛው የባለጉዳዩን ሳይሆን የጠበቃውን እጆች ያያል። ደህና ጉቦ ሰጪ ጠበቃ ዝናን ያተርፋል፣ በርካታ ደንበኞች ያፈራል። ለፍትህ የቆሙ ጠበቆች ደግሞ ሥራ ፈተዋል። “ፍትህ ይስፈን” እያሉ ሲጮኹ ሙሰኛው ዳኛና መሠሪው ጠበቃ ይሳለቁባቸዋል። ፍትህ በኦሮምያ እጅግ ተረግጣለች። ታድያ በአቋራጭ ለመክበር ኢፍትሃዊ ነገሮችን ሳይፈሩ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። በኢፍትሃዊ አሠራሮች ልምድን የቀሰሙት ደላሎችና አቀባባዮች የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። እነርሱ ለዳኞችና ጠበቆች ሐሰትን አደልቦ እንደምን ማሸነፍ እንደሚቻል ህግን ሳይፈሩ፣ ሰውን ሳያፍሩ ምክር ያካፍሏሉ። ክፉዎች የምክር አገልግሎት በሚሰጡባቸው ቢሯቸው ውስጥ የፍትሃብሄር ህግና መጽሃፍ ቅዱስ ሁለቱም ጠረቤዛው ላይ ተቀምጠዋል። እግርግዳው ላይ ደግሞ “እግዚአብሄር ያያል” የሚል በእንግሊዘኛና ኦሮምኛ የተጻፈ ጥቅስ ተሰቅሏል። አይ ዘመን!

አቀባባይ ረድፈኛ ሚና (liaison role between the corruptor and corruptors of public officials) አቀባባይ ረድፈኛ (እንደ ራሴ አተረጓጎም) በሙያው ደላላ ያልሆነ ስልታዊ ደላላ ነው። ከደላሎች የሚለየው ነገር ቢኖር ባለስልጣኖችን በጥቅም አሳውሮ መቅረብ መቻሉ ነው (dangerous liaison)። የመናገርና የማሳመን ፣ የማዘበራረቅና የማዛባት ችሎታ የተላበሱት አቀባባይ ረድፈኞች አገዛዙ ባመቻቸው የሙስና መሠላሎች ወደ ላይ የወጡ የዘመኑ አራዶች ናቸው። እነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች ጉቦ ሰጪንና ጉበኛን፣ ሠነፍ ተማሪንና ቦዘኔ አስተማሪን፣ ባለስልጣንንና አራጣ አበዳሪውን፣ ፍርደገምድል ዳኛውንና ቆቁን ጠበቃ፣ ወዘተ፣ አገናኝ ናቸው። ካለነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች እገዛ ውጭ ባለስልጣን ሊመዘብርና ሙስና ሊቀበል ያዳግተዋል። መሥሪያ ቤቶችን ሁሉ የሙስናና ምዝበራ አርማ ተሸካሚ ያደረጉት እነዚህ በስልታዊ ብረዛ ሳይንስ የተካኑት አቀባባይ ረድፈኞች ዋዛ አይደሉም። ህግና ፍትህ ሚኒስቴር – ሙስናና አድልዎ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር – የምዝበራ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር – መሃይምነት ማስፋፍያ ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር – የጨረታና መሬት ሽሚያ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር – የዋጋ ንረት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – ኢንቬስትሜንትና ሃዋላ ሚኒስቴር፣ የእርሻ ሚኒስቴር – እንጀራና በርበሬ ላኪ ሚኒስቴር፣ ወዘተ፣ እንዲሆን ሚናውን የተጫወቱት መለኞች ከአስመጭና ላኪዎቹ ወይም ሕንጻ አከራዮቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ላፍታም ቢሆን የማይርቁ የሙስናና ዝርፍያው ተቋም (kleptocracy) ባለውለታዎች ናቸው።
ቋንቋ (mother tongue)፣ በኦሮምያ ኦሮሚፋ ብቻ ነው የሥራ ቋንቋ። ልጆቿ ሌላ ክልል ሄደው መሥራት አይችሉም። እሷም ከትግራይ ወይም አማራ አልያም ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ ወይም ደቡብ ክልሎች የሚመጡትን ልጆች አታስተናግድም። አትድረሱብኝ – አልደርስባችሁም – ብላለች። ኦሮምያ አማርኛ ቋንቋን እንደ መጨቀኞ መሣርያ ያህል በመጥላትዋ ሳብያ አፈሯን ፈጭተው፣ ውሃዋን ጠጥተው ያደጉትን ኦሮምኛ የማይችሉትን አንጡራ ልጆቿን እንኳን የጉዲፈቻ ዜግነት ከልክላቸዋለች። ኦሮምያ – አማርኛ የነፍጠኞች ቋንቋ መሰላት እንጂ የጋራ መግቢያብያ ቋንቋ ልማትን እንደሚያፋጥን ቴክኖሎጂንም እንደሚያስፋፋ አላጤነችም። አማርኛ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ ለብዙ ዓመት ማገልገሉ ማንንም ባልጎዳ ነበር። የሆነስ ሆነና የኢትዮጵያ ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ መሆኑስ ይታወቃል? ኦሮምያ ይህን የልማት እንቅፋት ሽራ ይልቅስ ብዝህነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጠናከር ቀዳሚ ሚናዋ ሊሆን ይገባል።

ባጠቅላይ ሃቀኝነት፣ ደግነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሙስናንና ጉቦን መጸየፍ – እነዚህ የሕዝቡ የመልካም ባህርይ መገለጫ የሆኑት እሴቶች በኦሮምያ ውስጥ ወደ ጉሮኖ ተወርውረዋል። እነዚህን እሴቶች ዳግም ሊያንጸባርቅ የሞከረ ሁሉ መሳለቅያ ይሆናል። ኬንያና ናይጄርያ በሙስናና ጉቦ ጫፍ ላይ የደረሱ ሃገሮች እየተባሉ ሲነገር ቆይቷል። ኦሮምያ ደግሞ በጥቂት ዓመታት ክብረወሰኑን አልፋ የሙስናና ጉቦ ፍልስፍና የተሃድሶ ምድር እንዳትሆን ያሰጋል። ይህን የመሳሰሉት ግፎች ናቸው ዛሬ ሕዝቡን ለአመጽ ያነሳሱት። የፍትህ መዛባት፣ እስር፣ ግድያና የምጣኔ ኃብቱ ይዞታ ልዩነት ካልተገደቡ በቀር ሕዝቡን ለመብቱ ከመታገል የሚያቆመው አንዳች ኃይል የለም። የፌደራል መንግሥቱ እጆች “አመድ አፋሽ” ወይም የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ እንዳሉት”የኢትዮጵያ ሕዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለት…”ሆኖ አይደለም ይህ ሁሉ አመጽ የበረከተው። ሙስናው፣ የአስተዳደር በደሉ – ኑሮውን አናግተውበት – በድህነትና ሰቆቃ ጅራፍ መገረፉ፣ በአምባገነኖች (tyranny, timocracy, oligarchy, plutocracy) ውሳኔ ብቻ መነዳቱ አልበቃ ብሎ ቀማኞች መሬቱንና የመሬቱን የተፈጥሮ ገጸበረከት በጠመንጃ አስገድደው (military command) በጠራራ ፀሃይ ስለሚዘርፉት እንጂ። የእርምቱ እርምጃ ከሰላው ጫፍ ይጀመር።
ጥቂቶቹ የትግራይ ሕወሓት መሪዎች ለም የሆኑትን የጎንደርና ወሎ አጎራባች መሬቶች በማናለብኝነት ተነሳስተው ወደ ትግራይ ክልል መደባለቃቸው ያስከተለውን አደጋና የህዝብ ቁጣ በሚቀጥለው ጊዜ እዘግባለሁ።
እግዚአብሄር ቸር ዘመን ያምጣልን፣ አሜን


ሲኖ ትራክ (Sino Truck) ሲኖ ጭራቅ፣ ቀይ ሽብር ከ ሚኪያስ ግዛው

$
0
0

እነዚያ ቀያዮቹን የቻይኖች መኪኖች ገና ከሩቅ ሲያዩ ጭራቅ የመጣባቸው ያህል ልጆች ይርበደበዳሉ። ገና የሲኖ ትራኩን ድምጽ ሲሰሙ የከለላና መከታ አያያዝ ስልትን ያልተማሩት እነዚያ ጨቅሎች የሚደበቁበትን ቦታ ለመምረጥ ሲባዝኑ ይታያሉ። “ሲኖ ትራክን ገና ከሩቁ ስታዩ…” እያሉ ወላጆቻቸው ጠዋት ጠዋት የሚነግሯቸው የጥንቃቄ አወሳሰድ ምክር ትምህርቱን አስረስቷቸዋል። ይህንኑ አደገኛ ቀይ መኪና ወላጆች በዘመናቸው ካዩት ዘግናኝ ድርጊት ጋር በማመሳሰል “ቀይ ሽብር” ብለውታል።

ሃገራችን ኢትዮጵያን አንገቷን ካስደፋት ትላልቆቹ ክፋቶች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስግብግብነትና የኅሊና መሸርሸሩ እጅግ አሳዛኞቹ ናቸው። ሃገር የቱንም ያህል ለማች፣ በሰማይ ጥቀስ ሕንጻዎች አሸበረቀችም ሆነ ዘመናዊ መንገዶች ተነጠፉላት ሥነ-ምግባርና ግብረገብነት ከተሸረሸሩ “ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ” ነው።

በንጉሡም ይሁን በደርግ ዘመን ሙስናና ጉቦ ቢኖርም እንዲህ እንዳሁን ሕዝቡን አላንገሸገሸም ነበር። አብዛኛው ሰው ፈሪሃ እግዚአብሄርነት በውስጡ ስላደረ በኅሊናው ይተዳደር ነበር። በደርግ ዘመን “መንጃ ፍቃድ በጉቦ አውጣ”፣ “መንጃ ፈቃድ ቤቱ ድረስ መጣለት”፣ ሲባል ሰው ወሬውን እንደ ጉድ ተገረሞ ያዳምጥ ነበር። ሰውንም ራስንም አደጋ ውስጥ የሚከት መርዝን በጉቦ መሸጥ የቴክንሽያኑን ኅሊና ቢስነት ደረጃ መገመቻ ነበር። መንጃ ፈቃድ በጉቦ መስጠት የሞት ፍርድ ያህል ነበር። ዛሬ እፍረት መሆኑ ቀርቶ ሁሉም ነገር ሙስናና ጉቦ ሆኗል። ሙስና ሞትንም ትሸጣለች። መሬት በጉቦ ይቸረቸራል። ባለገንዘብ መሬት ገዝቶ ጭሰኞች ይቀጥራል። የሠማይ ስባሪን ያህል ሹመት ተሸካሚ ግለሠብ ሕንጻ አከራይ ሁኗል። የሕዝብ አደራ የተሸከመው አገልጋይ አስመጭና ላኪ ነጋዴ ሆኗል። አለማየሁ እሼቴ ምናልባት በስድሳዎቹ መግቢያ ላይ ነው መሰለኝ፣ ባማረ ድምጹ – “ማን ይሁን ትልቅ ሰው” – በሚለው ዘፈኑ ላይ – “እባክህ አምላኬ ደጉን ዘመን አምጣ” – ሲል ለእግዚአብሄር ምልጃውን አቅርቦ ነበር። የየኔውን ዘመን ገምቶ አምላኩን የተማጸነው ከያኒ ዛሬስ ምን ታዝቧል? ምናልባት አለማየሁ እሼቴ እንደገና ቢያንጎራጉር “እባክህ አምላኬ ያን ዘመን መልሰው” ይል ይሆን? በእርግጥ የዘንድሮው ከተሻለ ያምናው ታሪክ ነበር። አለመታደል ሆኖ እንጂ “ከዘመን ዘመን አሸጋግረን” ማለት ከኋለኛው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን በላቀ መንፈሳዊ ጽናት፣ በተሻለ ሠላምና ብልጽግና አሸጋግረን ማለት ነው። “ልማታዊው መንግሥት” ሥነ-ምግባሩንና ግብረገብነቱን ሸርሽሮ ሁሉንም ደረመሰው።

ሲኖ ትራክ ምንም አላጠፋም። ሲኖ ትራክ በቻይና የተፈረበከ ፈጣን ጉልበታማ መኪና ነው። ጥፋቱ የሹፌሩ ነው። ጥፋቱ የአሽከርካሪው ነው። በእርግጥ ጥፋቱ የአሽከርካሪው አይደለም። ጥፋቱ የሥርዓቱ ነው። ጥፋቱ በእድሜው ለጋ ለሆነው ወጣት ወይም ሱሰኛ ካለችሎታው አራተኛና አምስተኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ የሚሰጠው የየክልሉ መሥሪያ ቤት ነው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ በትምህርት ዲግሬ ከማግኘት ያላነሰ ፈተናና ውጣ ውረድ ነበረው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ከሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ፣ ከሶስተኛ ወደ አራተኛ፣ ከአራተኛ ወደ አምስተኛ፣ ለመዝለል እጅግ ከፍተኛ ልምድንና ብስለትን ይጠይቅ ነበር። ዛሬ መንጃ ፈቃድ በጉቦ መያዝ ከጉልት በቆሎ የመሸመትን ያህል እንኳን አይከብዱም። ዛሬ ሹፌሮችንና ረዳቶችን ለይቶ ማየት አይቻልም። ሹፌሩ አራራ ይዞት ጫት ለመቃም አንዱ ሥርቻ ጎራ ሲል ረዳቱ መኪናውን ያሽከረክራል። የታክሲው አሽከርካሪ ዕቃ ለመግዛት ሱቅ ሲገባ ወያላው ሁለት ቢያጆ ሰርቶ ይጠብቀዋል። የታክሲው ባለቤት ይህን ሁሉ ጉድ አያውቁም። ቢያውቁም፣ ታክሲው የዕለቱን ገቢ ይዞላቸው እስከመጣ ድረስ ለተሽከርካሪው ደህንነትም ሆነ ለተሳፋሪዎቹ ነፍስ፣ ቅጠል ተሸክማ አስፋልቱን ለምትሻገረዋ ባልቴትም ሆነ ወደ ቄስ ትምህርት ቤት ለሚጓዙት ጨቅሎች አይጨነቁም። እሳቸውስ ቢሆን ምን ያድርጉ – ለሾፌራቸውና ረዳቱ መንጃ ፈቃዱን የሠጠው መሥሪያ ቤትን የሕዝብ ጉዳይ ካልቆረቆረው።

ሥርዓቱ መንጃ ፈቃድ አስጣጡም ላይ ሆነ የበሰለ ልምድ ያላቸው የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን በአግባቡ እንዲሰማሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ነበረበት። ይህ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የሚታየው የበርካታ ሰዎች ውድ ሕይወጥ መጥፋትም ሆነ የንብረት መውደም ባልተከሰተ ነበር። ሥርዓቱ ዘመናዊ መንገድን ማንጠፍ ብቻ ሳይሆን አነዳድን፣ በርጋታ መቅደምንም ሆነ በመስመሮቹ ማህል ረግቶ የመንዳትን ሥነ-ጥበብ ቀርጾ ትምህርቱን ማሰራጨት ነበረበት። ፈጣን መንገድን ሥልጣኔ ለጎደለው አሽከርካሪ”ፈንጭበት” ብሎ መልቀቅ ራሱ “ቀይ ሽብርን” ማፋፋም ነው። ሲኖ ትራኮች “ቀይ ሽብር” የተባሉት ለዚህ ነው። ከአዲስ አበባ አዳማ የተዘረጋው አውራ ጎዳና (motor way) ላይ መንዳት ከተክለ ኃይማኖት መርካቶ እየተሽለኮለኩ የመንዳትን ችሎታ ማሳያ መንገድ አይደለም። በፈጣን መንገድ ላይ ፍሬቻ ሳያበሩ መታጠፍ ወደ ሽንኩርት ተራው ተጋፍቶ እንደመግባት ቀላል አይደለም። በዘመናዊው መንገድ መንዳት “ሥልጣኔን” እንጂ “አራዳነትን” አይጠይቅም። የመንገዶቹን መስመሮች ማህል (driving field)ጠብቆ መንዳት፣ ወደ ሌላ መሥመር ለመግባት ፍሬቻ ማሳየት (turn signal)፣ እስር የተወተፈ መኪና ወይም ሞተር ሳይክል መኖር አለመኖሩን (blind spot) ማረጋገጥ፣ በጥንቃቄ የመቅደም ስልትን (take over) እንዲሁም ፍጥነትን መቆጣጠርና (speed control) ከፊት ካለው ተሽከርካሪ እርቀትን መጠበቅ (safe gap) ወዘተ፣ የመንዳት ችሎታ ብቻ ሳይሆን ሥልጣኔና (civilization) ለነፍሳት ሁሉ የመጠንቀቅ ሠብዓዊነት (humanity) ነው። በከተማ ውስጥ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ከሁሉም በላይ አስተዋይነት ነው። ምናልባት መኪና ማሽከርከር ፈቃድ ያላቸውን ዲያስፖራዎችን አሰባስቦ በአውራጎዳና ላይ አነዳድን በኤግዚቢት መንገድ የማሳየት ወርክ ሾፕ ቢዘጋጅ ጠቃሚ ይመስለኛል። ይህን ስል ካገራችን በቂ ችሎታ ያላቸው አስተዋይ አሽከርካሪዎች ጠፍተዋል ማለቴ ሳይሆን የውስጡንም የውጭውንም ልምድ መለዋወጡ ትምህርትን ከመቅሰምያ ዘዴዎች አንደኛው ነው ማሌቴ ነው። አምላክ ሀገራችንን፣ ወገናችንን ይጠብቀን፣ አሜን።

ኢትዮጵያ ወዴት? ግርማ ሞገስ

$
0
0

የዛሬው ያረጀ አምባገነናዊ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት እንደ ትናንቱ ታላቅ ወንድሙ የደርግ መንግስት የኢትዮጵያችንን የነገ ተረካቢዎች ህጻናት እና ወጣቶች እያሰረ እና በጥይት እየገደለ የስልጣን ዘመኑን ማራዘም ብልህነት አድርጎ ተያይዞታል። 100% መርጦኛል የምትለውን ህዝብ እየገደልክ በስልጣን ላይ መቆየት አትችልም። ያረጀው ወጣቱን እየበላ የሚኖርበት ዘመን በኢትዮጵያችን ማክተም አለበት። ወጣቱ አገሩን ካረጀው ህወሃት/ኢህአዴግ መንጋጋ ፈልቅቆ በመውሰድ ማስተዳደር መጀመር አለበት። ሰላማዊው ትግል ገና መጀመሩ ነው። እገሌ ከገሌ ሳንል በአገር ውስጥ እና በውጭ የምንኖር የአገር ሽማግሌዎችም ሆነን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የወጣቱ ምኞት ይሳካ ዘንድ ተገቢ የአጋዥነት ሚናችንን ልንጫውት ይገባል። ለማንኛውም ይህቺ አጭር ጽሑፍ ባለፉት አራት ወሮች በኢትዮጵያችን ሰላማዊ አቤቱታ በማሰማታቸው እና ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ በኦሮሚያ ክልል በጥይት ሕይወታቸውን ለተነጠቁ ህጻናት እና ወጣቶች ማስታወሻ/መታሰቢያ ትሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።!

ኢትዮጵያ ወዴት? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ውይይት እንድከፍት ያነሳሳኝ ኢትዮጵያችን ባለፉት አራት ወሮች ያደረገችው የለውጥ እንቅስቃሴ፣ እንቅስቃሴውን በመምራት ላይ ያሉት ወጣቶች የምር ስራ ላይ መሆናቸው እና የህዝባችን ብስለት ተደማምረው ነው። በሰፊው እንደሚታወቀው ባለፉት አራት ወሮች የኦሮሚያ ወጣት ሳይገድል እየሞተ የለውጥ አስፈላጊነትን በሰላማዊ ተቃውሞ መፈክሮቹ ሲያሰማን ቆይቷል። ዛሬ በህይወት የሊሉትም የለውጥ ጥሪ ድምጻቸው ይሰማናል። እንግዲህ በአንድ አገር ባለፉት አራት ወሮች ያስተዋልነው አይነት በአይን የሚታይ፣ በጆሮ የሚሰማ፣ በእጅ የሚዳሰስ አልፎም በህልም ሳይቀር የሚመጣ የለውጥ እንቅስቃሴ ሲፈጠር ማንኛውም አገሩን እና ህዝቡን የሚወድ ዜጋ በጭንቅላቱ እና በህሊናው “ወዴት እየሄድን ነው?” የሚለው ጥያቄ መመላለሱ የማይቀር ነው። የዚህ ጽሑፍ ግብም በዚህ ጥያቄ ዙሪያ የኢትዮጵያን የቀድሞዎቹን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በአጭሩ በማስታወስ እና የዛሬውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመመርመር “ወዴት እየሄድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ አንባቢን ሊያወያይ የሚችል መልስ መስጠት ነው። በተጨማሪ ይህ ጽሑፍ በመኪያሄድ ላይ የሚገኘውን የሰላማዊ ትግል አቅም ውቂያኖስነት ያመላክታል። የሰላማዊ ትግሉን ደህንነት እና ቀጣይነት ዘላቂ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥቂት ምክሮችንም ይሰነዝራል።

ኢትዮጵያ ባለፈው በ20ኛው እና አሁን በያዝነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለለውጥ በርካታ እንቅስቃሴዎች አድርጋለች። በኢትዮጵያችን በግልጽ የሚታይ እና የሚጨበት የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት እንቅስቃሴ የተጀመረው በ1950ዎቹ በመንግስቱ ንዋይ በተመራው መፈንቅለ መንግስት እና መፈንቅለ መንግስቱን ደግፎ እና ዘውዳዊውን አገዛዝ ተቃውሞ በአዲስ አበባ መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ነበር ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መሬት ለአራሹ፣ የብሔር እኩልነት፣ ህዝባዊ መንግስት፣ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ ወ.ዘ.ተ. መብቶች የሚሉትን የመብት መከበር ጥያቄዎች መፈክር ቀርጾ ቀደም ብለው የነበሩትን ጭቆናዎች ተከታታይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በማድረግ ለህዝብ አስተዋወቀ። ይህን በማድረጉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በርካታ አባላቱን ለዘውዳዊው አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች ጥይት ከፍሏል። የዚሁ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውጤት የሆኑት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ አንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአፓ እና መኢሶንም የዴሞክራሲ ሽግግርን ጥያቄ አንስተው አንድ ትውልድ ከፍለዋል። ሻቢያ፣ ኦሌፍ እና ህወሃትም ይኸው የተማሪዎች እንቅስቃሴ የወለዳቸው ተቃዋሚ ድርጅቶች ናቸው። ያም ሆነ ይኽ ዘውዳዊውን አገዛዝ የገረሰሰው ህዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድል ፍሬ በአውሬው ወታደራዊ ደርግ ተሰረቀ። በዚህ አይነት እስከዚህ ድረስ የተደረጉት እንቅስቃሴዎች የተፈለገውን የፖለቲካ ለውጥ አላመጡም። ከዚያ ከደርግ ወደ ህወሃት/ኢህአዴግ የተደረገው የመንግስት ስልጣን ሽግግር ወደ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ሽግግር ያመራል የሚል ተስፋ በብዙ ወጣቶች ዘንድ ፈጥሮ ነበር። እሱም ሳይሆን ቀርቷል። በቅርቡ ደግሞ በምርጫ 97 ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ሽግግር ቢሞከረም በአንድ በኩል በህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን ጥመኛነት እና በሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚው መካከል ህብረት አለመኖር፣ የድል ሰብሳቢነት ልምድ አልባነት እና የሰላማዊ ትግል ቀጣይነት ባህል ማጣት ተደማምረው የተገኘው መለስተኛ ድል ሳይቀር ባክኖ በምትኩ በቆሻሻው መለስ ዜናዊ የሚመራ ፍጹም አምባገነንነት ሌባ መንግስት በኢትዮጵያ ነግሷል። እነዚህ ሁሉ በወጣቶች የተመሩ እንቅስቃሴዎች የፖለቲካ ምኞታቸውን (ግባቸውን) ተፈጻሚ ማድረግ ባይችሉም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ብሩህ ወጣቶችን በመስዋትነት ከፍለው ሄደዋል።

በየዘመኑ በስልጣን ላይ የነበሩት አምባገነኖች የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲሉ የለውጥ ጥያቄ ያነሳውን ወጣት ቢፈጁም በሚያፈቅሩት ስልጣን ላይ ብዙም ሳይቆዩ እነሱም ጠፍተዋል። ካለፈው ስህተታቸው መማር አለመቻል የአምባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህሪያቸው መሆኑን ታሪክ ደግማ ደጋግማ ታስተምራለች። እነሱም ደግመው ደጋግመው አይማሩም። ስለዚህ ዛሬም በስልጣን ላይ የሚገኘው አምባገነናዊ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት እንደ ቀድሞው በመንግስቱ ኃይለማሪያም ሲመራ እንደነበረው አምባገነኑ ደርግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ ባለፉት 22 አመቶች ግድም ውስጥ ቀደም ሲል በፍጹም አምባገነኑ ሟቹ መለስ ዜናዊ መሪነት አሁን ደግሞ በቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መሪነት ሰላማዊ አቤቱታ እና ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው ብቻ በየአደባባዩ በጥይት አንደበታቸውን የተነጠቁ (የተገደሉ) ወጣቶች ቁጥር ጥቂት አይደለም። ጥቂት ልጥቀስ። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም. የኤርትራ ሬፌረንደም በሰላማዊ መንገድ በመቃወማቸው ወጣቶች በህወሃት/ኢህአዴግ ጥይት ተደብደበዋል። በ2001 ዓ.ም. ድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የተደረገውን ስምምነት በመቃወማቸው ወጣቶች በህወሃት/ኢህአዴግ ተደብድበዋል። የ2005 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1997) ምርጫን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ የህዝብ ድምጽ ይከበር በማለታቸው ብቻ ሰላማዊ አቤቱታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው በህወሃት/ኢህአዴግ ጥይት ወጣቶች በግንባራቸው ሳይቀር በጥይት ተደብድበዋል። በየአደባባዩ የተረሸኑት ወጣቶች አይረሱንም። በ2014 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በህዳር ወር 2008) ዓ.ም. ጀመሮ የኦሮሚያ ወጣቶች ማስተር ፕላኑን በመቃወማቸው፣ የኦሮምኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ ይሁን በሚል በጀመሩት ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ የአምባገነኖችን ጥይት በግንባር፣ በአንገት፣ በደረት እና በቀረ አካላቸው እየተቀበሉ እንዲወድቁ መደረጋቸው ትኩስ ሐዘናችን ነው። የኢትዮጵያን ወጣት የነፃነት እና የዴሞክራሲ ጥም በግድያ ማቆም እንደማይቻል የማይማሩት አምባገነኖች ብቻ ናቸው።

በነፃነት እና በዴሞክራሲ መኖር የአሜሪካኖች ወይንም የእንግሊዞች ወይንም የአውሮፓውያን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር ሁሉ ምኞት እና ፍላጎት ነው። አለም አቀፋዊ መስፈርትን የሚያሟሉት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ መሪዎችን የመምረጥ ነፃነቶች በኢትዮጵያ የሉም።! ልብ በሉ! እነዚህ ነፃነቶች “ለሶስት ሺ አመት ‘ነፃነቷ’ ተከበሮ የኖረች ኢትዮጵያ” የምንለው አይነት “ነፃነት” አይደሉም። እነዚህ ነፃነቶች ጎረቤት ኤርትራን የሚያስተዳድረው ሻቢያ የሚለፍፈው አይነት “ነፃነትም” እንዳልሆኑ ልብ በሉ። እነዚህ ነፃነቶች የመናገር፣ የመቃወም፣ የመደራጀት፣ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተሰብስቦ ተቃውሞ ማሰማትን፣ ወ.ዘ.ተ. የመሳሰሉትን ያካትታል። ለነዚህ ነፃነቶች መኖር ደግሞ ዴሞክራሲ የግድ መኖር አለበት። ዴሞክራሲ ከሌለ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ መሪዎችን የመምረጥ ነፃነቶች አይኖሩም። እነዚህ ነፃነቶች እና ዴሞክራሲ አይነጣጠሉም። ስለዚህ በነፃነት እና በዴሞክራሲ ስርዓት መተዳደር የኢትዮጵያውያንም ምኞት እና ፍላጎት በመሆኑ ላለፉት አርባ እና ሃምሳ አመታት በተከታታይ የመጣ የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ እነዚህን ጥያቄዎች አንስቷል።

በኦሮሚያ ክልልም ወጣቶች ያነሷቸው ጥያቄዎችም የተለዩ አይደሉም። የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ይከበር፣ የዜጎቿን ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፣ የዜጎች የመናገር፣ የመቃወም፣ የመምረጥ፣ የዴሞክራሲ መብቶች ይከበሩ የሚሉ ናቸው። ኢትዮጵያ የህግ-በላይነት የሚከበርባት እና የዜጎቿን መብት የምታከብር አገር እንድትሆን የሚጠይቁ ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች ኢትዮጵያችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ሳይሆኑ ወደፊት፣ ወደ ስልጣኔ የሚገፉ ናቸው። ባለፉት አራት ወሮች እንዳስተዋልነው ከሆነ ለእዚነህ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሽግግር ጥያቄዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወጣት ያልተመጣጠነ መስዋዕት ከፍሏል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዳር ቆሞ በመመልከት የምናግዘው የአምባገነኖች የገዢነት ዘመን መሆኑን የምር ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ ነው። አምባገነኖች ችግሩን ይበልጥ አወሳስበው ኢትዮጵያችንን ይበልጥ ወደ ተወሳሰበ እና ልንፈታው ወደ ማንችለው ችግር ውስጥ ሊከቷት እንደሚችሉ አገር ወዳዶች በሙሉ ከወዲሁ ልናስብበት የማይገባ አብይ ጉዳይ ነው። ዛሬ አምባገነኖች ኦሮሚያን በወታደራዊ እዝ እናስተዳድራልን ማለት ጀምረዋል። ይኽ እርምጃቸው ችግሩን ይበልጥ ማወሳሰብ ነው። አምባገነኖች በተቀነባበረ ህዝባዊ እምቢተኛነት ተገደው ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ እስካልተደረጉ ድረስ ወይንም እንዲሄዱ እስካልተደረጉ ድረስ ቀዳሚ ግባቸው ለሆነው ስልጣን ሲሉ ችግሩን ይበልጥ ማወሳሰባቸው የማይቀር ነው። በኦሮሚያ የተነሳው መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነገ በአማራው ወይንም በደቡብ ክልል ቢነሳ የአምባገነኖች መፍትሄ እነዚህንም ክልልሎች በወታደራዊ እዝ ማስተዳደር እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል። ሁልሽም ተራሽን ጠብቂ መሆኑ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምንል አገር ወዳዶች በሙሉ በቻልነው መንገድ እና ባለን አቅም ሁሉ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ልንተባበር ይገባል። ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ህዳር ሁለት 2 ቀን በኦሮሚያ ጊንጪ ከተማ ተጀምሮ ባለፊት አራት ወሮች ውስጥ ወደ ቀረው ኦሮሚያ በመዝመት በወለጋ፣ በአንቦ፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በቦረና፣ በባሌ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተቀጣጠለው ሰላማዊ ተቃውሞ ቀጣይነት ሊኖረው እና ወደ ቀረው ኢትዮጵያ እንድ ሰደድ እሳት መቀጣጠል አለበት። ማለትም ሰላማዊው ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ይበልጥ ሊሰፋ፣ ይበልጥ ሊቀናበር እና አመትም ይፍጅ ከዚያ በላይ ቀጣይነቱን እንዳያጣ ማድረግ አለብን።

ቀደም ሲል መንግስት በኦሮሚያ የተፈጠረው ተቃውሞ መንስዔው የመልካም አስተዳደር እጦት ነው ሲለን ነበር። ለመሆኑ መልካም አስተዳደር ምንድን ነው? የፖለቲካ መልካም አስተዳደር አለመኖር ህጋዊ በሆነበት አገር ህዝብን በማጭበርበር ጊዜ እያባከኑ የስልጣን ዘመንን ለማራዘም እስካልሆነ ድረስ እንዴት ስለኢኮኖሚ እና ስለ ማህበራዊ ጉዳዮች መልካም አስተዳደር ማውራት ይቻላል። ህወሃት/ኢህአዴግ በተደረጉ ምርጫዎች በሙሉ ስልጣን ላይ መቆየት የቻለው በፖለቲካ ሙስና ድምጽ በመስረቅ ነው። ይህ ደግሞ እራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ይሁን ብሎ ህጋዊ ያደረገው የፖለቲካ መልካም አስተዳደር አልባነት ነው። በዚህ የፖለቲካ ሙስናው ተባብረው በኦሮሚያ በ100% እንዲያሸንፍ ያገዙትን የኦፕዲኦ የፖለቲካ ሹሞች እና ካድሬዎች ዛሬ ዞሮ በመልካም አስተዳደር ማጉደል ቢከሳቸው ኩምክና ከመሆን ያለፈ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ አይሆንም። በዚህ የፖለቲካ ሙስና ተግባሩ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይደረግ በየክልሉ የሚተራመሱ ፀረ-ነፃነት እና ፀር-ዴሞክራሲ ካድሬዎቹን በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎች ተቃዋሚዎችን በማዋከብ፣ በማሰር እና ድምጽ በመዝረፍ የፖለቲካ ሙስና ተግባር እንዲተባበሩት ደሞዝ እየከፈላቸው አይዟችሁ ሲላቸው ከርሞ ዛሬ የህዝብ ተቃውሞ ሲፈጠር ተጠያቂዎቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም ማለቱ የንቀቱን መጠን ያሳየናል።

ዐርብ ቀን መጋቢት አንድ 2008 (March 10/2016) ደግሞ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በኦሮሚያ እና በቀሩት የሃገሪቱ ክልሎች ውስጥ ለተፈጠረው የህዝብ ቅሬታ መንግስታቸው እና ፓርቲያቸው ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ አስታወቁን። ይህ ኃላፊነትን የመቀበል እርምጃ ቀደም ብሎ መደረግ የነበረበት ትክክለኛ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ዘግይቶ በመምጣቱም አንቀበልም ባንልም ቃላቸውን በተግባር መደገፍ አለባቸው። ስለዚህ ፓለቲካዊ ኃላፊነትን በመውሰድ በአገሪቱ ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ የፖለቲካ ሹሞችን ከስልጣን ማባረር አለባቸው። ህጋዊ ኃላፊነትም መውሰድ አለባቸው። ስለዚህ ግድያ የፈጸሙ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ፣ ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው ብቻ ለተገደሉ ወጣቶች ቤተሰቦች ካሳ መክፈል፣ እነ በቀለ ገርባን፣ እነ በቀለ ገና እና የመሳሰሉትን የኦፌኮ መሪዎች፣ አባላት፣ እና ደጋፊዎች እንዲሁም ጉዳዩን በመዘገባቸው የታሰሩ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን በፍጥነት መልቀቅን ያካትታል። ችግሩ ግን “ይቅርታ መጠየቅ” እና “ስህተቴን ተቀብያለሁ” ማለት የህወሃት የቅርብ ጊዜ ማጭበርበሪያ ፈሊጥ እየሆነ መምጣቱን ካወቅን ውለን አድረናል። የህወሃት ይቅርታ ማለት አንተም ተቃውሞ አቁም እኔም ወደ ቀድሞ ገዢነት ስራዬ ልመለስ ማለት ነው። በአንድ በኩል ኦሮሚያን በወታደራዊ እዝ አስተዳደር ስር ለማድረግ ሽር ጉድ እያለ በሌላ በኩል “ይቅርታ” ማለት ቅንነትን አያሳይም። ይኽ ሁሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ግራ እና ቀኝ እስክስታ የሚያሳየን የተነሳውን ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ በራሱ አነሳሽነነት ፈቅዶ (ሳይገደድ) በሰላማዊ መንገድ መፍታት ፍጹም ባህሪው እንዳልሆነ ነው። በጫካ ተወልዶ እና ተቃዋሚዎችን በመግደል አድጎ ስልጣን ላይ ከወጣ ወታደራዊ ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ጸባዮችን መጠበቅ የለብንም። ላብራራ።

እንደሚታወቀው ህወሃት ወታደራዊ ድርጅት ነው። በጦር ሜዳዎች የገጠሙትን ተመሳሳይ ወታደራዊ ድርጅቶችን TLF (የትግራይ ተወላጆች ድርጅት), EDU, EPRA/EPRP, DERG በጦር ሜዳ ደመሰሰ። የህወሃት መሪዎች እና የTLF (የትግራይ ተወላጆች ድርጅት) መሪዎች አብረው ለመስራት ህብረት ፈጥረናል ተባብለው እራት ከበሉ በኋላ በእምነት በህውሃት ካምፕ በተኙበት በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት። አረመኔው ህወሃት መንግስት ሊሆን አካባቢ ደግሞ የመንግስት መዋቅር (ዛሬ ፈደሬሽን የሚለንን) እንደሚከተለው አቋቋመ። በህዝብ ቁጥራቸው የሚፈራቸውን ኦሮሞዎችን፣ አማሮችን እና የደቡብ ህዝቦች በሞግዚትነት (በጠባቂነት) የሚገዙለትን (1) ኦፒዲዎ ፣ (2) ቀደም ሲል ከኢህአፓ ተገንጥሎ እራሱን EPDM ብሎ ሲጠራ የነበረው እና በስተኋላ ለTPLF የገበረውን ድርጅት (ብአዴን መሰለኝ የአሁኑ ስሙ?)፣ (3) የደቡብ ህዝቦችን የሚገዛለት (ዛሬ በኃይለ ማሪያም ደሳለኝ የሚመራው) ድርጅት ፈጥሮ እና (4) ህወሃትን ጨምሮ፣ አራቱን ያካተተ ኢህአዴግ የተሰኘ ቡድን ፈጠረ። በተጨማሪ (5) በህዝባቸው ቁጥር የማይፈራቸውን እንደ እነ ቤንሻንጉል፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ እና የመሳሰሉትን ህዝቦችን ደግሞ አፍነው የሚገዙለት እንደ አስፈላጊነቱ የሚያነጋግራቸውን ድርጅቶች ደግሞ “አጋር ድርጅቶች” ብሎ ሰየማቸው። በዚህ አይነት ፌዴሬሽን ፈጠርኩላችሁ ብሎ ህወሃት ኢትዮጵያን ጠቅሎ በመግዛት ላይ ይገኛል።

የፈደሬሽን የሚለው አወቃቀር ትርጉም ከሞላ ጎደል አገርን በጋራ ማስተዳደርን አካባቢን ደግሞ ህዝቦች በግላቸው እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ዴሞክራሲን ከላይ ወደ ታች የሚያደርስ የፖለቲካ አወቃቀር ነው። በሃቀኛ ፈዴሬሽን የፌዴራል መንግስት በየመንደሩ በካድሬዎች አማካኝነት ህዝብን የሚያሰቃይበት ምክንያት አይኖርም። የህወሃት ፌዴሬሽን ግን በዘር ከፋፍሎ የመግዣ መዋቅር ሲሆን በዚህ ላይ በ 1 ለ 5 የተሰኘው ጠርናፊ መዋቅር ጨምሮበት ህወሃት እስከ ቤተሰብ ድረስ ፖለቲካዊ ቁጥጥር ማድረግ ችሏል። ደርግ እስከ ቀበሌ ድረስ ብቻ ነበር ህዝብን የሚቆጣጠረው። ህወሃት ግን ከደርግ ዘመን የከፋ አምባገነናዊ የፖለቲካ ማዕከላዊ አገዛዝ ስርዓት በኢትዮጵያ አስፍኖ ኢትዮጵያን ህዝብ እስከ ቤተሰብ ደረጃ ወርዶ አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል። ስለዚህ የህወሃት/ኢህአዴግ ፈዴሬሽን መለወጥ አለበት። 1 ለ 5 የሚለውም ጠርናፊ መዋቅር መፍረስ አለበት።

ከፍ ብለን እንዳነበብነው ህወሃት ስልጣን ላይ የወጣው በምርጫ ሳይሆን በጠበመንጃ ነው። ምርጫ የሚባለው ጣጣ ውስጥ የገባውም ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው። ከሶቪየት ህብረት ውድቀት በኋላ ምዕራቡ (አሜሪካ እና ምዕራብ አውሮፓ) ነፃ ፉክክር እና ምርጫ አዲሱ የአለም ስርዓት ነው በማለታቸው እርዳታቸው እና ድጎማቸው እንዳይለየው ሲል የማይተዋወቀውን እና የማያምንበትን የብዙሃን ፓርቲ እና የምርጫ ፖለቲካ ስርዓት ተቀብያለሁ አለ። ከዚያ በምርጫ ህዝቡ ከስልጣን እንዳያወርደው ህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን ላለመልቀቅ ሙሉ በሙሉ በፖለቲካ ሙስና ተሰማራ። ነፃ ምርጫ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን ሶስቱን የመንግስት ቅርንጫፎች ጠቅሎ ያዘ፣ ነፃ ፕሬስ እንዲዳከም ወይንም እንዳይኖር አደረገ፣ የምርጫ ቦርድ ፈጣሪም እሱ ሆነ። ስለዚህ ህወሃት/ኢህአዴግ በየአምስት አመት በግንቦት ወር በኢትዮጵያ የሚደረገውን ምርጫ እንደ ጦር ሜዳ ወሰደው። በዚህ ላይ የቃዋሚ ህብረት የለም። በምርጫ ከተሳተፈ በኋላ ዛሬ በኦሮሚያ እንደምናየው ህዝባዊ እንቢተኛነት በመቀስቅስ “ድምጽ ማስከበር” የሚችል ህዝብ መፍጠር ባለመቻላችንም ታግዞ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ያገኙቱን ድምጽ በኃይል እየዘረፈ በምርጫ 2002 ዕ.ም. በ99.7% በቅርቡ በምርጫ 2007 ዓም ደግሞ በ100% አሸነፍኩ አለን። በጠብ መንጃ አዲስ አበባን ሲይዝ አንተ ማነህ? ያለው እንደሌለ ሁሉ ድምጽ ማስከበር የሚችል ህዝብም ሆነ ተቃዋሚ ፓርት ባለመኖሩ ከምርጫዎች በኋላም አንተ ማነህ? ሳንለው ይኸው እስከ ዛሬ ስልጣን እንደጨበጠ ይገኛል። የተቃዋሚዎች ህብረት ቢኖር እና ዛሬ በኦሮሚያ የሚገኙት ወጣቶች ከሚያደርጉት ጋር ተመሳሳይ ህዝባዊ እምቢተኛነት በማድረግ “ድምጽ ይከበር” የሚል ህዝባዊ እንቅስቃሴ በመፍጠር ድምጹን ማስከበር የሚችል ህዝብ ቢኖር ኖሮ ሁኔታውን ለመቀየር ይሞከር ነበር። ዛሬ በኦሮሚያ መሚኪያሄድ ላይ የሚገኘው ህዝባዊ እምቢተኛነት እግረ መንገዱን ከምርጫም በኋላ ድምጹን የሚያስከብር ህዝብ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ። የምርጫ 2007 ዓ.ም. ምርጫ 100% አሸናፊነት የኢትዮጵያን ወጣቶች አስመርሯል። በቃን አሰኝቷል። አውቀው ሲታለሉለት ከከረሙት ለጋሾቹ (ሸሪኮቹ) ምዕራባውያን ውስጥ እንኳን አንዳንዶቹ አሁንስ አበዛኸው ብለዋል። እውነት ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ በስብሷል። መሄድ አለበት። በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በሙሉ ያካተተ ሁሉን አቀፍ ህብረት መፈጠር ያስፈልጋል። ቢቻል ኢህአዴግን እና ህወሃት/ኢህአዴግ “አጋር” የሚላቸውን ድርጅቶችም ያካተተ። ካልሆነም ከህወሃት/ኢህአዴግም ሆነ ከአጋር ድርጅቶቹ ውስጥ ተራማጅ የሆኑቱን ግለሰቦች ያካተተ። ይኽን ማድረግ ሽግግሩን ሊያቀል ይችላል። የገዢው ፓርቲ አባላት በሽግግሩ ወቅትም ሆነ እና ከሽግግሩ በኋላ በሰላም በአገራቸው መኖር እንደሚችሉ እንዲሰማቸው ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ገዢው ፓርቲም ሆነ የወቅቱ ባለስልጣኖች ያላቸው የተሻለ አማራጭ ከተቃሚው የሽግግር ህብረት ጋር መተባበር ብቻ መሆኑን በውይይት እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል።

እርግጥ ነው ለሁሉም አገር የሚሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት መፍጠሪያ አንድ አይነት ቀመር (ፎርሙላ) የለም። ከታሪካችንም እንደምንረዳው የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት እና ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር መውሰድ እና ማስፈጸም የሚያስችል ህብረት መፍጠር እጅግ ፈታኝም አስሸጋሪም ጉዳይ ነው። የዴሞክራሲ ሽግግር የከሸፈባቸውም ሆነ የተሳካ ሽግግር ያደረጉ አገሮች ታሪክም የሚያስተምረን ህብረት መፍጠር ቀላል እንዳልሆነ ነው። ህብረት ለመፍጠር የዴሞክራሲ ሽግግር መሪዎች በትንሹ፥ አርቆ አስተዋይነትን፣ ብዙ ውጣ ውረድን፣ የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ መሆኑን መረዳትን፣ ረዘም ያለ እና ቀጣይነት ያለው ጥረት ማድረግን፣ የድርድር ክህሎት አቅም መገንባትን፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ መመራትን እና የመሳሰሉትን እልህ አስጨራሽ ስራዎች ይጠይቃል። በዚህ አይነት የሚደረስ ስምምነት እና የሚፈጠር ህብረት (coalition) እያንዳንዱ ድርጅት ትንሽ ሰጥቶ እና ትንሽ አግኝቶ የሚፈጠር ህብረት ይሆናል። በዘውዳዊው፣ በደርግ እና በህውሃት/ኢህአዴግ እንዲሁም በምርጫ 97 የተፈጠሩ ጥሩ የለውጥ እና የዴሞክራሲ ሽግግር አጋጣሚዎች ባክነዋል። አሁን የተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ እንቅስቃሴ እንደቀድሞዎቹ አጋጣሚዎች ሳይባክን ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር እንዴት መግባት እንደሚቻል ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል። ወጣቶቹን ማዘዝ ሳይሆን ልንተባበራቸው እና ልናግዛቸው ይገባል።

ህብረት (coalition) ሲባል የፓርቲዎች ውህደት ሳይሆን በተያዘው የለውጥ እንቅስቃሴ ብሎውም በዴሞክራሲ ሽግግር ዙሪያ በሚቀረጽ የጋራ አጀንዳ ዙሪያ ብቻ ተባብሮ አብሮ ለመስራት የሚፈጠር ቡድን ነው። ውህደት ለረጅም ጊዜ በትናንሽ ጉዳዮች ላይ ተጋግዞ በመስራት የሚፈጠር ትውውቅን እና መተማመንን ቅድሚያ ይላል። በጋራ መስራት የሚቻሉ ነገሮችን ለይቶ አውጥቶ በእነሱ ዙሪያ ተሰባስቦ ተጋግዞ አብሮ የመስራት ባህልን መገንባት ቅድሚያ ይላል።

በመጨረሻ የሰላማዊ ትግሉን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ጥቂት ምክሮችን በመለገስ ጭቅጭቄን ላብቃ፡፡
(1) በስልጣን ላይ የሚገኘው አምባገነን ቡድን የተቃዋሚ መሪዎችን እና ብሩህ ለውጥ ተመኚ ወጣቶችን የሚገድለው እና የሚያስረው የሰላማዊውን ትግል ጭንቅላት በመቁረጥ ትግል ለመግደል እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም። ገዢው ቡድን ያሰበው እንዳይሳካለት ለማድረግ አንደኛው መድሃኒት የሰላማዊ ትግል እውቀት በማስፋፋት አዳዳሲ መሪዎች እና የሰላም ትግሉ ሰራዊት እንዲያድገ ማድረግ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች የሰላማዊ ትግል እውቀት በቀጣይነት እንዲቀስሙ ማድረግ ከቻልን በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ቡድን ፈተናውን እናበዛበታለን ማለት ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ትግልን አለማወቁ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው በሚሊዮኖች የሚፈጠሩ ወጣቶችን ማሰር አይችልም። ስለዚህ ሰላማዊው ትግል ቀጣይነት ይኖረዋል። ሁለተኛው መድሃኒት ደግሞ የታሰሩት የሰላማዊ ትግል መሪዎች እና ታጋዮች በፍጥነት እንዲፈቱ ጥያቄያችን ማቋረጥ የለብንም። በዚህ ረገድ በተለይ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት ሸሪኮች እና ለጋሽ የምዕራቡ መንግስታት ከተሞች ሰልፎች በመውጣት የዲፕሎማሲ ጫና ማድረግ እንችላለን።
(2) ጥሩ የሰላማዊ ትግል እውቀት ያላቸው እና በየጊዜው በምድር ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች በፍጥነት መልስ እየሰጡ ሰላማዊ ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ የሚችሉ መሪዎች ሊኖሩ ይገባል።
(3) ዛሬ ቴክኖሎጂ የዴሞክራሲ ሽግግርን በከፍተኛ ደረጃ እየረዳ ነው። በእጅ ስልክ በሚሰራጩ አምባገነናዊ ጭፍጨዎች ብቻ የአለምን ህብረተሰብ ሃሳብ ማስቀየር እና በአገር ውስጥ እና በለጋሽ አገሮች መዲናዎች ትላልቅ ሰላማዊ ተቃውሞች መቀስቀስ ይቻላል። የሰላማዊ ትግል ሰራዊት የእጅ ስልኩን በመጠቀም ዜና ዘጋቢም ሊሆን ይችላል ማለት ነው። ስልጠና መስጠት ሊያስፈልግ ይችላል። እርግጥ ቴክኖሎጂ ብቻውን ህያው ሰዎችን አይተካም። ዜናዎቹን ለማብራራትም፣ ለድርድርም፣ ተቋሞችን ለመመስረት እና ለመገንባት እና ለበርካታ ጠቃሚ ተግባሮች በሰላም ትግል የሰለጠኑ ታታሪ መሪዎች ያስፈልጋሉ። አጀንዳዎች እና መፈክሮች መቅረጽ፣ ፓርቲ መገንባት፣ ህብረት (coalition) መፍጠር፣ ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች ለመቅረጽ ብሎም ለማሰራጨት፣ ህዝብ በዴሞክራሲ ሽግግር እንዲያምን እና ተሳታፊ ለማድረግ እና ለመሳሰሉት ወሳኝ ስራዎች በሙሉ ብቃት ያላቸው የሰላማዊ ትግል መሪዎች ያስፈልጋሉ።

(4) ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ፍርሃትን ማስወገድ ወይንም ፍርሃትን መቆጣጠር መቻል የመጀመሪያ ጉዳይ ነው። በሰላማዊ ትግሉ መሳተፍ ሊያስከትል የሚችለውን ስቃይ እና መከራ በማሰብ ከትግሉ እራስን ማግለል ስርዓቱ የሚፈጽመው ስቃይ የተሻለ አድርጎ መቀበልን ሊያስከትል ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ የሰላም ትግሉ ሰራዊት ፍርሃትን ማስወገድ ወይንም መቆጣጠር አለበት ስንል የሰላማዊ ትግሉ ሰራዊት (በዘር፣ በቁንቋ፣ በይማኖት፣ በጾታ፣ በሃይማኖት፣ በአይዶሎጂ፣ ወ.ዘ.ተ.) እሱን ያለመሰሉትን ወይንም የመንግስት ባለስልጣናትን፣ የገዢውን ፓርቲ አባላት እና ተከታዮች በሆነ ባልሆነው ማስበርገግ የለበትም። የመንግስት ባለስልጣኖች፣ የገዢው ፓርቲ አባላት እና ተከታዮች በሽግግር ወቅት እና ከሽግግር በኋላ ስቃይ እና በቀል ይፈጸምብናል በሚል ስጋት እንዲናወጡ ካደረግን ሽግግሩን የተራዘመ እና የተወሳሰበ የማድረግ ችግር ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ስለዚህ ፍርሃት ስለማስወገድ ስናስብ ግባችን እኛን ታጋዮችን ከፍርሃት ነፃ ማውጥት ብቻ ሳይሆን እኛን በማይመስሉ ወይንም በፖለቲካ ባላንጣዎቻችንም ዘንድ እንዳይፈሩን ማድረግንም ያካትታል።

(5) ሰላማዊ ትግሉን ከጥላቻ ነፃ እንዲሆን ማድረግ ይገባል። ጥላቻ ንጹህ በሆነ አዕምሮ እና ህሊና እንዳናስብ ያደርገናል። አዕምሮዋችን በጥላቻ ከተመረዘ የምንሰጠው ዳኝነትም ፍትሃዊ አይሆንም። በጥላቻ ከተመርዘን ወንጀል ወደ መፈጸም ልንሸራተት እንችላለን። ነገ እኝንም ሆነ እንወክለዋለን የምንለውን ወገን ሊያሳፍር የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን። የምንቃወመው ገዢውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ስርዓት እንጂ እኛን የማይመስለውን ወይንም ተቃዋሚዎቻችን መሆን የለበትም። የሰላም ትግል ሰራዊት ከጥላቻ ነፃ የመሆን አቅም ሊኖረው ይገባል። ስለዚህ ከጥላቻ ነፃ የመሆን አቅም የመገንባት ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል። እርግጥ የፖለቲካ ባላንጣዎቻችንንም ማፍቀር አለብን ማለቴ አይደለም። ከጥላቻ ነፃ መሆን የሰላማዊ ትግሉን ማራኪነት፣ ተአማኒነት፣ አስማኝነት እና ስኪታማነት አቅሞች ከፍ ያደርጋል ማለቴ ነው።

(6) ሰላማዊ ትግል ከጉልበትም ነፃ መሆን አለበት። ጉልበት፣ ግድያ፣ ሽብር እና የመሳሰሉት ዘዴዎች የአምባገነኖች መንገዶች ናቸው። በዚህ አይነቱ መንገድ አምባገነኖች ይበልጡናል። እኛም ጉልበት እና ግድያ መጠቀም ከጀመርን አምባገነኖች የረጅም ጊዜ ልምድ እና ቁጥር ስፍር በሌለው ለረጅም ጊዜ ባከማቹት ህይወት ማጥፊያ አቅማቸው እንዲገጥሙን እድል እንሰጣቸዋለን ማለት ነው። ባለፉት አራት ወሮች ብቻ እንኳን ምዕራቡ በኦሮሚያ ለሚካሄደው ሰላማዊ ትግል በፍጥነት ድጋፍ መግለጹን እናስታውሳለን። እኛ በሰላማዊ ትግሉ ላይ ግድያን እና ሽብርን ከቀላቀልን ግን ምዕራቡ ደንታ አይኖረውም። እንዲያውም የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደራዊ አቅም ከፍ እስካለ ድረስ ምዕራቡ ከቀድሞ ወዳጁ ከህወሃት/ኢህአዴግ ጎን ነው የሚለጠፈው። የሚካሄደውን ሰላማዊ ትግሉም የአገር ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ በማስመሰል ህዝብን አደናግሮ ለማስተባበር እና ሰላማዊው ትግል ቶሎ እንዳይንሰራራ አድርጎ ለመምታት እንዲችል ቀዳዳ ይከፍትለታል። ስለዚህ ሰላማዊ ትግላችንን ከብክለት (Contamination) በንቃት መጠበቅ አለብን። ይኽን ማድረግ ለሰላማዊ ትግላችን ቀጣይነት እና ድል አድራጊነት የምንፈጽመው የደህንነት (የጸጥታ) ስራ አድርገን መውሰድ አለብን። ጀብዱኛ ግለሰቦች ወይንም ሌሎች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅለው ጥይት የሚተኩሱም ከሆነ የሶሪያ አይነት ሁኔታ በኢትዮጵያችን ለፈጠር የማይችልበት ምክንያት አይኖርም። ሰላማዊ ትግሉ በፕላን የሚመራ እና በድስፕሊን እየታነጸ መሆን አለበት። ሰላማዊ ሰልፈኞችን ተቀላቅሎ በፖሊስ ላይ ድንጊያ መወርወርም ጉዳቱ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ፖሊሶች በድንጋይ ከመገደላችን በፊት እራሳችንን ለመከላከል ነው ግድያ የፈጸምነው ሊሉ ይችላሉ። ፖሊሶች እንዲፈሩን ማድረግ የለብንም። እንዲያውም የተወሰኑት እንዲቀላቀሉን ማድረግ አለብን። ብዙ የክልልም ሆነ የፌዴራል ፖሊሶችም ይህን መንግስት ከልብ በፍቅር የሚወዱት አይመስለኝም።

(7) ስለማዊ ትግላችን ከግብታዊነት ነፃ መሆን አለበት። ግብታዊ ሰላማዊ ትግል በትግላችን ሂደት ውስጥ ለምንወስዳቸው እርምጃዎች አምባገነኖች ሊሰጡ የሚችሉትን አረመኔያዊ ምላሽ በቅድሚያ የመገመት እና የመዘጋጀት እድል ስለማይሰጠን ግብታዊነትን በትግላችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ግብታዊ ሰላማዊ ትግል ሊገጥሙት የሚችሉትን ወሳኝነት ያላቸው እንቅፋቶች በቅድሚያ አንስቶ ተመራምሮ ተገቢ ፕላን ስለማያሰላ ውጤቱ ውድመት ሊሆን ስለሚችል ግብታዊነት ሊወገድ ይገባል። ግብታዊ ሰላማዊ ትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን አምባገነን መንግስት ማውረድ ቢችልም ቀደም ብሎ የተሰላ ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚያደርግ የዴሞክራሲ ሽሽግር ፕላን ስለማይኖረው የሰላማዊው ትግል ፍሬ በሽግግር ወቅት ሊከሰት በሚችል በመፈንቅለ መንግስት ወይንም በራሱ ከስልጣን በወረደው ቡድን ሊነጠቅ ይችላል። ግብታዊትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን መንግስት ማውረድ ቢችልም ግባታዊው ትግል ቅልበሳን የሚከላከል ፕላን ስላማይኖረው አገሪቱን ወደ ነፃ ምርጫ እና ወደ ዲሞክራሲ ማሸጋገር ሊሳነው ይችላል። ህዝብን የድል ባለቤት ማድረግ አይችልም። አዲስ አምባገነን ወይንም ነባሩ አምባገነን ቡድን የድል ፍሬ ሰብሳቢ ሊሆን ይችላል።

(8) የሰላማዊ ትግላችን መሪዎች ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል የሚለው አባባል በፖለቲካም እንደሚሰራ ማስተዋል አለባቸው። ስለዚህ ሰላማዊ ትግሉን ከፍ በማድረግ በአገር ውስጥ ከንብረት ባለቤትነት፣ ከመሬት ባለቤትነት፣ ከንግድ፣ ከሰራተኛ ደሞዝ የሚያሰባስበውን ግብር እና በኢትዮጵያ ስም ከለጋሾች የሚፈስለትን የገንዘብ መጠን ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል። ይህ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግ የሚባለው ነው። ሰላማዊ ትግሉን ከፍ በማድረግ ከጅቡቲ፣ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሸቀጦችን ማቆም ይቻላል። መንገዶችን በተለያዩ ከተሞች ላይ በመዝጋት ከውጭ ወደ አዲስ አበባ እና ሊሎች ከተሞች የሚገባ ነዳጅ እና በርካታ ሸቀጦችን ማስተጓጎል ይቻላል። በዚህ አይነት የመንግስትን ኪስ መዳበስ ይቻላል። የኪሱ እብጠት ሲቀንስ እንደቀድሞው ደሞዝ የመክፈል አቅሙ ስለሚዳከም ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ ህጻናትንን እና ወጣቶችን እንዲገድሉ የሚያዛቸውን ደህንነቶች እና ፖሊሶች እንደልቡ ማዘዝ ይሳነዋል። ሰራዊቱም ሰለማይከፈለው በተቃዋሚው ሁሉን አቀፍ ህብረት ለሚደረግለት “ለህገ-መንግስተ ተገዛ” እና “ሰላማዊውን ለውጥ ተቀላቀል” ጥሪ የሚሰጠው ምላሽ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዎንታዊ እየሆነ እንደሚሄድ መጠራጠር የለብንም።

(9) የህዝቡ ጥያቄ በቅርቡ፥ “በ100% አሸናፊነት የተፈጠሩት መሳቂያ የፌዲራል እና የክልል ፓርላሞች ይፍረሱ፣ ጊዚያዊ መንግስት ይቋቋም፣ አዲስ ምርጫ ይደረግ” ከሚል ደረጃ እንደሚደርስ ጥርጥር የለኝም። ስለዚህ አርጅቶ በመበስበስ ላይ የሚገኘው የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት አንዴ “ስለ ይቅርታ” ሌላ ጊዜ “ስለመልካም አስተዳደር እጦት” በስውር ደግሞ “ስለ ወታደራዊ ዕዝ አስተዳደር“ ማውራቱን አቁሞ ከህዝብ ቢታረቅ እና የተጀመረውን የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ብሎም የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት ቢቀላቀል የሚሻለው ይመስለኛ። ቢያንስ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ የሚገኙ ተራማጅ ሰዎች ይህን አይነት እርምጃ ቢወስዱ ለራሳቸውም ለአገሪቱም ጠቃሚ ይመስለኛል። የአገር ሽማግሊዎች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሁሉን አቀፍ ጉባኤ መጥራት የሚያስችል ስራ መስራት መጀመር ያለባችሁ ይመስለኛል። እርግጥ ለውጥ ነገ ይመጣል ማለት አይደለም። ስራው ግን ቢጀመር ጥሩ ነው።

ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ በማንሳታቸው ብቻ ወጣት ልጆቿን የምትገድል፣ የምታስር፣ የምታዋክብ ኢትዮጵያ ማብቃት አለባት። ዜጎቿን በነፃነት እና በዴሞክራሲ ማስተዳደር ወደ ምትችል ኢትዮጵያ መሸጋገር አለብን። የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ተገቢውን ትብብር ካገኘ እንደሚሳካ ጥርጥር የለኝም።!

ከሰላምታ ጋር
ግርማ ሞገስ

ልሳቅ ወይስ ላልቅስ በለምለም ጸጋው

በርሀብ የሚገድል መንግሥት እንዴት በሥልጣን ላይ ይቆይ? ገለታው ዘለቀ

$
0
0

ታላላቅ ረሀቦች ተብለው በዓለም ታሪክ ከሚዘከሩት ውስጥ የቻይናውያን ረሀብ ኣይዘነጋም። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1958-1961 ድረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ረሀብ ተከስቶ ወደ ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ ረግፏል። ብዙ ምሁራን እንደሚሉት ለዚህ አስከፊና ቻይናውያን ሊረሱት ለማይችሉት ረሀብ አንደኛ ተጠያቂ ማዖ ዚዳንግን ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ መሪ የነበረው ማዖ ዚዳንግ በሶቪየት ህብረት በነጆሴፍ ስታሊን አብዩት ፍቅር የከነፈ ሲሆን ቻይናን በአምስት ዓመታት ውስጥ ከሁዋላ ቀር ግብርና አውጥቼ ወደ ኢንዱስትሪ እለውጣታለሁ በማለት Great Leap Forward ታላቁ የግስጋሴ ርምጃ የተሰኘ የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ነድፎ አመጣ። እቅዱ የግል የመሬት ባለቤትነትን የሚጻረርና የወል እርሻን የሚያራምድ ነበር። በዚሁ እቅድ መሰረት ቻይናውያን በፍጥነት እየተደራጁ የወል እርሻ ሥራን ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ እቅዱ እንደተቋመጠለት ሳይሳካ ቀርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገላቢጦሽ ችግር አመጣና ቻይናውያንን አስርቦ ቁጭ አለ። ዛሬ ላይ ያን ረሀብ የ Great Leap Forward ረሀብ ይሉታል።

በማዖ ዚዳንግ ጊዜ ቻይናውያን በጋራ እርሻ ከጀመርን ነው የምናድገው ተብለው የግል እርሻ በሰፊው ማካሄድ ተከልክሎ ስለነበር አልፎ አልፎ ጓሮ አካባቢ ትንሽ አትልክት ቢጤ ከማሳደግ ውጭ መሬት ሁሉ የጋራ ሆኖ በጋራ ማረስ ተጀመረ። ከፍተኛ የሰው ኃይል ደግሞ ከግብርናው ተቀንሶ ወደ ብረት ማቅለጥ ሥራ እንዲሄድ ታዞ የብረት ማቅለጥ ሥራ ተጀምሮ ነበር። ይሁን እንጂ እቅዱ ቀቢጸ ተስፋ የሞላውና የግል መብቶችን የጣሰና የግል ንብረት ባለቤትነትን የሰበረ በመሆኑ ከፍተኛ ሶሺዮ ኢኮኖሚክ ኪሳራን አመጣና ወዲያው ከሸፈ። እንደታሰበው ምርታማነትን ሳያሳድግ ቀርቶና በተቃራኒው ሄዶ ብዙ ሰው ጨረሰባቸው። ታዲያ ቻይናውያን እድለኛ ሆነው የድህረ ማዖ መሪዎች ለዛች ኣገር የኢኮኖሚ እድገት የተሻለ ፖሊሲ አምጥተው ማደግ ችለዋል። እነሆ ዛሬ ቻይና ድህነትን ለመቀነስ ባደረገችው ጥረት ከዓለም አንደኛ ናት። በዓለማችን ታሪክ ውስጥ መጠናቸው ይብዛም ይነስም ከፓሊሲና ከመልካም ኣስተዳደር ብልሹነት የተነሳ ሰዎች በረሀብ አልቀዋል።

ዩክሬን ውስጥ ከ 1932-1933 ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በርሀብ ያለቁት ጆሴፍ ስታሊን ባወጣው የኣምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደሆነ ብዙ ምሁራን ይስማማሉ። ከ 1932-1933 ጊዜ ውስጥ፣ በዚህች ኣጭር ጊዜ ወደ ኣስር ሚሊዮን የሚጠጉ ዮክሬናውያን በረሀብ ኣልቀዋል። ህጻናት ዋይ ዋይ እያሉ፣ አረጋውያን እያቃሰቱ በሳይቤሪያ በረሀ ሳይቀር በየሜዳ የቀሩበትን ይህን ክፉ ጊዜ ዮክሬናውያን በቋንቋቸው ሆሎዶሞር (Holodomor) ሲሉ ይዘክሩታል። በአማርኛ በረሀብ መግደል ወይም ሰውን በችጋር መጨረስ እንደ ማለት ነው። ረሀቡ ሰው ሰራሽ ነው፣ የስታሊን የአምስት ዓመት ትራስንስፎርሜሽን እቅድ ውጤት ነው ብለው የዩክሬን ሰዎች ኣምርረው ኮንነውታል። በርግጥም ዮክሬናውያን ይህን ለማለት ይገባቸዋል። በጣም የከፋው ነገር ደግሞ ከፖሊሲው መክሸፍ ባሻገር ረሀብ በተከሰተበት ወቅት ስታሊን የውጭ ርዳታ እንኳን እንዳያገኙ በተለያየ መንገድ ተጽእኖ ፈጥሮ ነበር። ረሀብ ያለባቸው አካባቢዎችም ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ እንዳይዘዋወሩ በመከልከሉ የጉዳቱን መጠን ኣስፍቶታል።

በርግጥ ይህ አሁን የምናወራው ረሀብ ከብዙ ዓመታት በፊት ያለ ነው። ዛሬ የሰው ልጅ አይራብም። ቢያንስ እጅግ ብዙው ዓለም በምግብ ኣይቸገረም። ወደኛው ቤት ስንመለስ ግን በሃያ ኣንደኛው ክፍለ ዘመን እንደነ ስታሊንና ማዖ ዚዳንግ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣው የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተባለው በመጨረሻ ይሄውና ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ለረሀብ ኣጋልጦ ቁጭ ብሏል። ዩክሬናውያን ስታሊን በችጋር ገደለን ሲሉ ሆሎዶሞር እንዳሉት እኛም የመንግሥት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኢትዮጵያውያንን ኣስርቦ እየገደለብን ነው።

ለዚህ ረሀብ ምክንያቱ ምንድን ነው? ሲባል የኢትዮጵያ መንግሥት ሮጦ ድርቅ እኮ ኣውስትራሊናያ ካሊፎርኒያም ገባ….. አልሰማችሁም እንዴ?….. ይላል። የውቅያኖስ ውኃ ሙቀት መጨመርን ተከትሎ የመጣ የኣየር ንብረት ችግር ኤሊኖ የተባለ የአየር መዛባት ያመጣው ችግር ነው ብለው ያብራሩልናል። ኤሊኖ ሆኖብን ነው እንጂ የኣምስቱ ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅዳችን ኣገራችንን ትራንስፎርም ኣድርጓል ይሉናል። ብንራብም በጥንድ ቁጥር እያደግን ነው ሲሉን ደግሞ ግራ የተጋባው ዜጋ እነዚህ ሰዎች የሚያወሩት ስለ ሌላ ሀገር ይሆን? እያለ ይደመማል። ወይስ እኔ የምኖርባትን ይህቺን ኢትዮጵያን የሚመለከት ነው? እያለ ይገረማል።

ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ረሀብ ላይ ወድቆ ስናይ ማንን ነው የምንወቅሰው? ተፈጥሮን ነው? በርግጥ ኢትዮጵያ አፈርና ውኃ የላትም ወይ? የሚል ጥያቄ እናነሳለን። በመሰረቱ የአገራችን ረሀብ መቶ እጅ ከፖሊሲ ችግር የመጣ ነው። ከአመራር ችግር የመጣ ነው። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ ከምሥራቅ ኣፍሪካ ሀገራት የውኃ ገንዳ የምትባል አገር ናት። ውኃ ሞልቷታል እየተባለች በሌሎች ኣፍሪቃ ሀገራት ይቀናባታል። በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ከሀገሪቱ ሆድ ሞልቶ የሚተርፍ ነገር ማምረት የሚያስችል ለም መሬትም አላት። ይሁን እንጂ ድሮም ቢሆን የብዙ ገበሬዎችን ህይወት ካበላሸው የመሬት ፖሊሲ ጀምሮ ያለንን የከርሰ ምድር ውኃና ወንዞች በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላችን እነሆ ዝናብ ጸጥ ሲል ለረሀብ ተጋልጠን ቁጭ እንላለን። አፈርና ውኃ እያለን መራባችንን ስናይ በርግጥ የኛ ሀገር ረሀብ ከአመራር ችግር ጋር ብቻ መያያዙን በሚገባ ያሳየናል።

አሁን ያለንበት ዘመን የሰው ልጅ የሚራብበት ዘመን አይደለም። ቴክኖሎጂ አድጎ ረሀብን ጉልበቱን ሰብሮታል። የከርሰ ምድርን ውኃን አየሳቡ፣ መስኖ እያለሙ፣ የተለያዩ የእርሻ ግብዓቶችን እየተጠቀሙ አገሮች የምግብ ዋስትናቸው ከቶ ኣሳሳቢ የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ኣሁን ይህ ዘመን ስለ ምግብ ሳይሆን ስለ ቴክኖሎጂ፣ ስለ የተሻለ ህይወት፣ ስለሌሎች ፕላኔቶች የሚታሰብበት ዘመን ነው። በዚህ ዘመን የሚራብ ህዝብ መንግሥት የሌለውና በጦርነት ምክንያት ህዝቡ ማምረት ካቆመ ነው። መንግሥት ያለበት አገር አይራብም። ለምሳሌ ያህል ሶርያን ብናይ ፕሬዚደንት ኣሳድ ወደ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ክፍል መቆጣጠር ኣልቻለም ነበር። ይህ ሰፊ የሀገሪቱ ክፍል ከኣሳድ እዝ ውጭ ቢሆንም ኣሳድ ደማስቆ ላይ ቁጭ ብሎ ግድ የለውም። ኣንዳንድ ከተሞች እርዳታ እንኳን እንዳይደርስላቸው የጦርነት ቀጣና ሆነው ብዙ ሰው በአጥንቱ እስኪቀር ተርቧል። ኣሳድ ሰማኒያ በመቶ የሶሪያን ግዛት ኣጥቶ፣ በሶሪያውያን ስደት በተባበሩት መንግሥታትት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት ፣ ኣውሮፓውያን፣ ዓለም ባጠቃላይ ተጨንቀው ስደተኛውን ምን እናድርገው? እያሉ ኣስሬ ስብሰባ ሲጠሩ፣ ዓለም በሶሪያ ስደት ስትናወጥ ኣሳድ ደማስቆ ቤተመንግሥቱ ቁጭ ብሏል። ይገርማል። ዲክቴተርስ ምን ያህል ግድ የለሽ እንደሆኑ ከግል ጥቅም ባሻገር ለብዙሀኑ እንደማያስቡ ያሳይል።

ወደ ሀገራችን ስንመለስ ያለፈው ትራንስፎርሜሽን እቅድ በአገሪቱ ውስጥ በመስኖ ሊለማ ከሚችለው ኣምስት በመቶ እንኳን ሳያለማ ገበሬውን እንደ ጥንታዊ ዘመኑ የዝናብ ጥገኛ ኣድርጎ ለኪሳራ መዳረጉ ሳይበቃው እንደገና ሁለተኛ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብሎ መጣ። እቅዱ የገበረውን የመሬት ችግር የማይፈታ ሆኖ ይታያል። የኣምስቱ ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ልክ እነስታሊን የወደቁበትን ይመስል በኢትዮጵያም በውጤቱ ኣገሪቱን ወደ ተሻለ ህይወት ከመምራት ወደ ርሀብ ሲወስዳት ይታያል። ረሀቡ ደግሞ የእለት እንጀራ ብቻ ሳይሆን የሚጠጣ ውኃንም ይጨምራል። የከርሰ ምድር ውኃችንን ለእርሻ ልማት መጠቀም አለመቻላችን ብቻ ሳይሆን እቅዱ የመጠጥ ውኃ እንኳን ኣሳጣን። ይሄ ተሀድሶ ሊባል አይችለም። ዛሬ አንዳንድ ቦታዎች የሚታየው የጀሪካን ሰልፍ መንግሥትን ኣያሳፍረውም። ይህ ረሀብና በምግብ ራስን አለመቻል የተከሰተው ከመንግሥት የፖሊሲ ችግር ጋር የተያያዘ ነው የሚያስብለን ዋነኛ ምክንያት ኣንደኛ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ገበሬ ውስጥ ወደ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ገበሬ ከፍ ያሉ ቦታዎች የሚኖር ሲሆን ይህ ገበሬ የመሬት ባለቤትነት የሌለው ከመሆኑም ባሻገር የበሬ ግንባር የምታክልን መሬት እያረሰ ይኖራል። በአማካይ አንድ ሄክታር መሬት ነው የሚያርሰው። መንግሥት ይህንን ሰፊ ህዝብ በዚህ መልኩ እንዳይንቀሳቀስ ኣፍኖ ይዞ በሌላ በኩል ደግሞ በዝቅታ ቦታዎች አካባቢ ያለውን ለም መሬት ለመሬት ቅርምት ዳርጓል። እነዚህ ሁለት መሰረታዊ የግብርናው ችግሮች ያለንን ሪሶርስ ተጠቅመን ረሀብን እንዳናሸንፍ ኣድርጎናል። ለረሀብ ኣጋልጦናል። በሌላ በኩል መንግሥት የምከተለው የእድገት ኣቅጣጫ ግብርና መር ነው ይበል እንጂ በተግባር ግን በብልጭልጭ (glitz economy) እድገት የተለከፈ ነው። ለታይታ የሚሆኑ ነገሮችን ሰርቶ “በጥንድ እያደግን ነው” አጨብጭቡ ማለት ለስልጣን እድሜ ይቀጥላልድ ክመትን ይሸፍናል ብሎ ያምናል።
በመሰረቱ አገሮች ሁሉ የዝናብ ሁኔታ ስለተመቻቸላቸው ኣይደለም ከርሀብ ያረፉትና ዜጎቻቸውን ያላሥራቡት። ለምሳሌ ግብጽን ብንወስድ ይህቺ ኣገር በዝናብ ኣትደገፍም። የሷ ድጋፍ መስኖ ነው። ከሀገሪቱ መሬት ዘጠና እጅ የሚሆነው በረሀ ነው። ለምንም ኣይሆንም። ለእርሻ ከሚሆነው ጥቂት መሬቷ ውስጥ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆነው በመስኖ የሚለማ መስኖን የተደገፈ ነው። በመሆኑም በየዓመቱ አንጋጣ የምትጠብቀው የለምና ያለ ኣሳብ ከመስኖ ልማቶቿ ቀለቧን ታፍሳለች። ራሷን ከመቻል ኣልፋም እነሆ ዛሬ ለእኛ ለርሀብ ማስታገሻ የሚሆን ወደ ኣንድ ሚሊዮን ዶላር ለገሰች።

የኢትዮጵያ መንግሥት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው ግብርና መር ፖሊሲ ኣለኝ በሚል ነው። ግብርናን ተገን ኣድርገን ነው ወደ ኢንዱስትሪ የምናድገውና ጥርመሳ ውስጥ የምንገባው ይሉናል። በመርህ ደረጀ ብዙ ሰው ይስማማል። በርግጥም በኛ ሁኔታ ግብርና መር የልማት ስትራተጂ ነው የሚያስፈልገን። ታዲያ በተግባር ግብርና መር ማለት ቢያንስ ቢያንስ በዚህ ሩብ ምእተ ዓመት የስልጣን ዘመን በመስኖ ሊለማ የሚችለውን መሬት ጥርግ ኣርጎ መጠቀም ሲቻል ነበር። እስካሁን የለማው ኣምስት በመቶ ኣለመሙላቱ የሚያሳየው ግብርናው ላይ ትኩረት ኣለመደረጉ ነው። ወሎ ውስጥ በመስኖ ሊለማ የሚችል በብዙ ሺህ ሄክታር የሚለካ መሬት እያለ ዝናብ ሲጠፋ ረሀብ ከተፍ ኣለ። በጣም በቂ የሆነ የከርሰ ምድር ውኃ እያለን ያንን እየጎተቱ ኣውጥቶ ኣካባቢን ኣረንጓዴ ማድረግና ቢያንስ ረሀብን ማጥፋት ሲቻል ግብርናው መር መንግሥት ኣልሞከረውም። ውኃ ያዘለ መሬት ላይ ቆመን በውኃ ጥምና በርሀብ አለቅን::

በጣም የሚገርመው ደግሞ በተለይ በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ይህ ሁሉ ሕዝብ በፖሊሲ ችግር ተርቦ እያለ መንግሥት ኣለመደንገጡ ነው። ይሄ ኣሳዝኖኛል:: ልክ ስታሊን የዩክሬንን ህዝብ ኣፍኖ እንደጨረሰው መንግሥትም የቁጥር ጨዋታ ይዟል። ረሀቡን ለመሸፈን ይሞክራል። ኣንዳንዴም ረሀቡ በቁጥጥሬ ስር ነው ይላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ኣሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ ረሀቡ ኣሳሰበን የሚለገሰው እርዳታም በቂ ኣይደለም እያሉ ኣሳብ ይዟቸዋል። እንዴውም በቅርቡ የተባበረችው ኣሜሪካ ድርቁ ለሰኪዩሪቲዋ ኣሳስቦኛል ብላለች። በርግጥ ኣርቆ ኣሳቢ መሪዎች ስላሉ ነው። ድርቅና ረሀብ ኣገርን ሊፈታ ይችላል። እየተባባሰ የመጣው ሥራ ኣጥነትና ስደት ሲደመር ርሀብ የአገርን ሉዓላዊነት የሚደፍሩ ኣገርን የሚያፈርሱ እምቅ ችግሮች ናቸው። ይህንን ጦማር እየጻፍኩ ባለሁበት ሰዓት እንኳን ሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ መሪዎች ማለተም ፕሬዚደንት ኦባማና የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ አሜሪካ ውስጥ በተሰበሰቡበት ወቅት ፕሬዚደንት ኦባማ እንዲህ አሉ፣ “ከሀምሳ ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የሚባለው ድርቅ በኢትዮጵያ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመርዳት አስቸካይ ርምጃ ወስደናል::”
በዚህ ደረጃ ትኩረት ያገኘና ዓለምን ያሳሰበ ድርቅ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ኣሳሳቢ ኣይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብርና መር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኣለኝ የሚለው መንግሥት በሁለተኛው ዙር ላይ ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ሲያስርብ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምን እንደሚያደርጉ ኣላውቅም። ለህዝባዊ ተቃውሞ ኣንዱ ትልቁ መነሻ የድህነት መጨመር ሲሆን በተለይ በረሀብ ሰዎች ከተጎዱ ደግሞ ከበድ ያለ የለውጥ ትግል መኖር ኣለበት። ኣሜሪካም ሆነች ካናዳና እንግሊሊዝ፣ ስዊድን፣ አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ፣ ጀርመንና ሌሎች ለጋሽ አገሮች ድርቁና ረሀቡ ያሳሰባቸውን ያህል እንዴት የኛው መንግሥት ኣላሳሰበውም የሚለው ነገር እንደገና እጅግ ገራሚ ነው።
ለማናቸውም ዋናው የአገራችን ረሀብ ችግር ያለንን ውኃ ስቦ እያወጡ ማልማት ኣለመቻል ጋር የተያያዘ ነው። የተራብነውም ውኃ ወይ ከመሬት ውስጥ ወይ ከወንዞቻችን ስበን ማልማት ባለመቻላችን መሬታችንን ለመሬት ነጣቂ በማስረከባችን፣ የመሬት ላራሹ ጥያቄ ባለመመለሱ ሲሆን ይህም በቀጥታ የመንግሥት ችግር ነው። ከፍታ ቦታዎች ላይ ያለው ድሀ ገበሬ መሬቱን በከርሰ ምድርና በመስኖ ውኃ እያለማ እንዳይጠቀም ካለመታገዙም በላይ የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሀምሳ ዓመት ሙሉ ቆይቶ እነሆ ሰማኒያ በመቶ የሚሆን ገበሬ በበሬ ግንባር በምታህል መሬት ላይ ታስሮ ይገኛል። ኢትዮጵያ ታሪካዊ ኣገር እንደመሆኑዋ ለጋሽ ኣገራት በቀና ልብ እርዳታውን ቢያጎርፉትም ግብርናው ከጥንቱ ኑሮው ንቅንቅ ኣላለም። ገበሬው ወገናችን ዛሬም የዛሬ ሶስት ሺህ ዓመት ያርስ እንደነበረው ያርሳል፣ በሳር ቤቶች ውስጥ ይኖራል፣ ሁለ ገብ እርሻን ተጠቅሞ ኣነሰችም በዛች ያችኑ ከጓዳው እያገኘ ለመኖር ይጥራል እንጂ የገበያ ሰው ኣልሆነም፣ የዛሬ መቶ ሁለት መቶ ዓመት የነበረው ግብርና ሲስተም ዛሬም ይኖራል። በእግሩ ይሄዳል፣ በቤቱ ውስጥ የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች አያቱ ይጠቀምባችው ከነበሩት አይለይም። የታየው ለውጥ ህዝብ ብዛት ሲጨምር የመሬት ጥበት ካልሆነ ግብርናውና ገበሬው ኣልተለወጡም። ተጀምሮ የነበረ መሰረተ ትምህርት የደርግ በመሆኑ በታጋዮች ተደመሰሰና ስሙን መጻፍ ጀምሮ የነበረው ገበሬ ወደ ጥንቱ ማይምነቱ ተመለሰ።

ለዚህ ረሀብ የዳረጉን ጉዳዮች በዓጠቃላይ ኣንደኛ የመሬት ፖሊሲውና ርዳታን በአግባቡ አለመጠቀም ናቸው። በኣሥራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ ተነስቶ የነበረው የመሬት ላራሹ ጥያቄ መነሳት ኣለበት የሚያስብለን ይሄ ነው። ርሀባችን ሰው ሰራሽ በመሆኑ የመንግሥት ለውጥ የግድ ያስፈልገናል። ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ካሉ ኣገራት በእርዳታ መቀበል ከፍተኛውን ቦታ ይዛለች። ብዙ እርዳታ እናገኛለን። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ ባጀት ከሀምሳ እስከ ስልሳ በመቶ የሚሆነው ከለጋሾች በሚገኝ ርዳታ የቆመ ነው። ይህቺ ኣገር በዚህ ልክ ርዳታን ተገን ኣድርጋ የምትኖርበት ጊዜ በታሪክ ኣልነበረም። አጼ ኃይለ ሥላሴ እርዳታ ያደርጉ እንደነበር ይነገራል። ደርግ ሲመጣ በተወሰነ ደረጃ ርዳታ መቀበል የጀመርን ሲሆን ኣሁን ስልሳ በመቶ ባጀታችን በእርዳታ የቆመ ሆኖ ቁጭ ብሏል። እርዳታ ለጋሾቹ የሚረዱት ኢትዮጵያ ራሷን እንድትችል ነበር። ይህ ሁሉ እርዳታም እየተገኘ ግብርናው ፈቀቅ አለማለቱ ያሳዝናል ሳይሆን ያስቆጣል። በዚህ ያልተቆጣን በምን ልንቆጣ። ዛሬ በኦሮሚያ፣ ጋምቤላና አማራ አካባቢ ያሉ ተቃውሞዎች በርግጥ ፍትሀዊ ናቸው ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሊደገፉ ይገባል። በዚያ በድሀ ገበሬ ስም የሚመጣው እርዳታ ብዙ መስኖ ልማቶችን ሊሰራ ሲችል ተዘርፎ ይሸሻል። የኢትዮጵያ ኣንዱ ትልቅ ችግር ገንዘቡ መዘረፉ ብቻ ሳይሆን የተዘረፈው ገንዘብ መሰወሩ ነው። ዓለም ባንክ ውስጥ ከፍተኛ ኤክስፐርት የነበሩት ዶክተር አክሎግ ቢራራ ሲናገሩ ሙስና ኢንዶኔሽያም ውስጥ ነበር ይላሉ። ኢንዶኔሽያም ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ይታይ የነበር ቢሆንም ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ዘርፈው ሲያበቁ እዚያው ኣገራቸው ውስጥ የንግድ ተቋማት ነው የሚከፍቱበት የነበረው። ኣንዳንዶቹ ሆስፒታል፣ ኣንዳንዶቹ ሆቴል፣ ኣንዳንዶቹ የግብርና ሥራ ይሰሩበት ነበር ኣሉ። ይሄ መቼም ሳይሻል ኣይቀርም። የኢትዮጵያን ጉዳይ ስናይ ኣንደኛ ፖለቲካው ራሱ የብሔር በመሆኑ እነ ኤፈርት የሕዝብን ንብረት ወስደው ምን እንደሚያደርጉት ኣይታወቅም። ኦዲት ተደርጎ ለህዝብ ይፋም ኣይሆንም። የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀብትም ኣይደለም ተብሏል። ሕወሓት በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ከትግሉ ጎን ለጎን እየነገድኩ ያደለብኩት ነውና ንብረትነቱ የትግራይ ሕዝብ ነው ይላል። ይህንን ሲል አያስጠላውም። የሚገርመው ደግሞ ይሄንን የግሌ ነው ብሎ በአንድ እጁ ይዞ በጉጂ ኦሮሚያ አካባቢ ያለውን ወርቅ ደግሞ የጋራችን ነው ብሎ በሌላ እጁ ይዝቃል። ይህን ሲያደርግ አያስጠላውም። ጉጂዎች የሚጠጣ ንጹህ ውኃ እንኳን ኣያገኙም። ስለዚህ በእንዲህ ዓይነት የመንግሥት እምነቶች ግብርናው ኣያድግም። ርሀብም ይህ መንግሥት አስካለ ይቀጥላልና ድሮ መሬት ላራሹ ብለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደታገሉ የዛሬው የአለማያ የግብርና ሳይንስ ተማሪ፣ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ የጅማ፣ የዲላ፣ የጎንደር ወዘተ….. ሊነሱና የገበሬውን ኣባታቸውን የመሬት ፖሊሲ ጥያቄ ሊያስመልሱ ይገባል። ዛሬም መሬት ላርሹ ብለን ለውጥን ማምጣት አለብን። አለበለዚያ የተባበረችው አሜሪካ እንዳሳሰበችው ይህቺን አገር ረሀብና ስደት ሊፈታት ይችላል። ለለውጥ መነሳትና መታገል አለብን። ውኃና አፈር እያለን፣ እርዳታ እያገኘን ሕዝባችንን ያሥራበ መንግሥት ላይ ጥያቄ ካላነሳን በታሪክ ተጠያቂ እንሆናለን። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

የተሰደዱ እና ባገር ውስጥ በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች እና ጸሃፍትን ብዛት ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው። አሊ ጓንጉል

$
0
0

ደርጉ ሲረገምበት ከሚኖርባቸው ሌሎች ብዙ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ፣ በማንኛውም ስነ-ጽሁፍ ላይ ያደርገው የነበረው ”ሳንሱር” እና፣ ሊሾም ሊሸለም ይገባው የነበረውን በዓሉ ግርማን ያህል ታላቅ ደራሲ መግደሉ ነው። ይኼም ሆኖ ግን፣ በደርጉ ጊዜ ይታተሙ በነበሩ መጽሃፎች ዙሪያ በእነ “መጽሃፈ ሲራቅ”፣ “አቸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ”፣ ጠንክር ዘካዛንችስ፣ “ዳግላስ ጴጥሮስ” … ወዘተ በመሳሰሉት የብዕር ስሞች ይቀርቡ የነበሩት ስነ-ጽሁፋዊ ትችቶች ብስለት እና የስነ-ጽሁፉን እድገት የምታውቀው ያንዱን ትችት አንብበህ እና “ፖ!” ብለህ አድንቀህ ሳታበቃ አንዱ አዲስ አርታዒ የፊተኛውን ተችቶ ስታነብብ፣ ያን “ፖ!” ያስባለህን ጽሁፍ ታወርደዋለህ፣ እንደገና ይኼኛውን ደግሞ ሌላው ጸሃፊ ሲተች ስታነብ፣ የፊተኛው ተቺ ያላያቸውን አዳዲስ ጉዳዩች ሲያነሳልህ ታደንቃለህ። የደርጉ የሳንሱር ማነቆ እንዳለ ሆኖ፣ ይህ የስነ-ጽሁፍ እድገት መገለጫው ነው።

ዛሬ ዛሬ በሩብ ክ/ዘመን ወደ ኋላ ቀረንና፣ አለማዊ በሚሰኘው ጽሁፍ ዙሪያ ሁሉ ባብዛኛው ሲጽፉ የምናየው ዲያቆናት እና ደብተራዎች ብቻ የሆኑ ይመስላል። በቅርቡ በውቀቱ ስዩም በጻፈው “ከአሜን ባሻገር” መጽሃፍ ላይ ከወጡት አንድ አራት ትችቶች ውስጥ፣ ስሙን መጥቀስ ካልፈለገው አንድ በሳል ጸሃፊ እና ከኔው በስተቀር፣ ሁለቱ በጽሁፋቸው እንደምንረዳው እና በማእረጋቸውም ባደባባይ እንደነገሩን ዲያቆን እና የቤተ-ክህነት ሰዎች ናቸው። ዲያቆን እና ደብተራ አለማዊ ጽሁፍን አይተችም አይባልም። መተቸት የማንኛውም ሰው መብት ነው። የአርታኢነት ስነ-ምግባር እንዲኖር ግን ያስፈልጋል፤ ከተራ ስድብ እና ዘለፋ ያለፈ፣ አስተማሪ እና ሚዛናዊ ሊሆን ይገባዋል። ከቤተ-ክህነት ጋር ግንኙነት ካላቸው ታዋቂ ጸሃፊያን አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው። ሰለሱ ታች ላይ እመለስበታለሁ።

ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ “የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ የወጣውን ጽሁፍ አይቶ ያልገረመው ሰው፤ በተለይም መገናኛ ብዙሃን እና ቋንቋ አካባቢ የሰራ ወይም እየሰራ ያለ ሰው ቢኖር ይገርመኛል። ጽሁፉ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ ያገሪቱ የትምህርት ስርዐት እየሞተ መሆኑንም ነው። በርካታ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ቃላት ካንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው የመዋዋስ እና የማልመድ ነገር አዲስ አይደለም። አማርኛ ሆኖ ለምዶ የቀረ በርካታ እንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ቃላትን (እንደ “ሸሚዝ” የመሳሰሉ) በምሣሌ መጥቀስ ይቻላል። ስረ-መሰረታቸው አንድ ግዕዝ የሆነው አማርኛ እና ትግርኛም ሲወራረሱ እና አንዱ ከሌላው ጋር የመመሳሰላቸው ጉዳይ አያስገርምም። የየቋንቋዎቹን የሰዋሰው ስርዓት ማዛባት ግን ስህተት ነው። አቅሙ ካለ እንኳንስ የፌደራል የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ፣ ቋንቋዎች ሁሉ በጥናት እና ክትትል እንዲጎለብቱ ማድረግ ተገቢ ነበር። በ“የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ” ላይ በግልጽ እንደተዘረዘሩት አይነት ስህተቶች ደግሞ የቋንቋ/ው እውቀት በሌላቸው ሰዎች የሆነም ይመስለኛል።

ሳይቸግር በአማርኛ ውስጥ የትግርኛ ቃላት መሰንቀርም እየታየ ነው፣ ለዚያውም በቋንቋው ላይ በተከታታይ ጽሁፎችን እያቀረቡ ባሉ ሰዎች። ዳንኤል ክብረት የሚጽፋቸውን ጽሁፎች አነባለሁ (አንዳንዶቹን)። አንዳንድ ጊዜ የሚያነሳቸውን ጉዳዮች ያየባቸውን ማዕዘናት እወድለታለሁ። ጥቂት ቀደም ብሎ “አዳቦል” በሚል ርዕስ በለቀቀው ጽሁፍ ውስጥ “መመያየጥ/ምይይጥ” የሚለውን የትግርኛ ቃል በአማርኛ ጽሁፉ ውስጥ ሰንቅሮታል። ይኸው፦

“… ለሰው የሚገባው፣ ግልጽ የሆነና ፍሬ ያለው ነገር ለመና[ገ]ርና ለመጻፍ የቋንቋ ችሎታም ያስፈልጋል። … ሳይሰክን የተቀዳ ቡናና መግለጫ ያጣ ሐሳብ አቅራቢ አንድ ናቸው። … የቋንቋ ችሎታ ማለት ጉዳዩን እስከ ጥግ ድረስ በመናገሪያው ቋንቋ አልቆ ለመናገር መቻል ነው።… ሐሳቡን በራስህ መንገድ ማቅረብ ስለማትችል በአሰልቺ ቃላት (ጃርገን) ትሞላዋለህ። አዳቦልነት … እየበዛ በሄደ ቁጥር የመልዕክት ልውውጡ የተሰበረ፣ አንጆ አንጆ የሚል፣ ችክታ የበዛበት፤ ተግባቦት የሚያጥረውና ሐሳቡ የነጠፈ ይሆናል። ይኼ ደግሞ የዕውቀት ሽግግርን፣ የሐሳብ ምይይጥን፣ የመልእክት ዝውውርን ይጎዳል…”

“ምይይጥ” ህወሃትን ተከትሎ መሃል አገር የገባ የትግርኛ ቃል ነው–ቃሉ እንደ ትግርኛ ቋንቋ ቃል ወትሮም የነበረ ቢሆንም። እኩያ አማርኛው “ውይይት”፣ እንግሊዝኛው ደግሞ “discussion” ይመስለኛል። ዳንኤል የተጠቀመበት አውድ ይህን የትግርኛ ቃል ለመጠቀም የሚያስችልም የሚያስፈልግም አልነበረም። ዳንኤል ቃሉን የተጠቀመበት፣ የሌሎች ሰዎችን ቋንቋ ለመተቸት በጻፈው ጽሁፍ ውስጥ መሆኑ ደግሞ “ምጸት” ያደርገዋል። በጽሁፉ ወስጥ የተበላሸው አማርኛው ብቻ ሳይሆን ትግርኛውም ነው። የቋንቋው የግስ እርባታ ህግም ነው የተበላሸው።

“… የቋንቋ ችሎታ ማለት ጉዳዩን እስከ ጥግ ድረስ በመናገሪያው ቋንቋ አልቆ ለመናገር መቻል…” እንደሆነ የሚነግረን ዳንኤል ክብረት፣ ቁልጭ ያለውን እና ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ ፍቺ የማያስፈልገውን የአማርኛውን “ውይይት” በትግርኛው “ምይይጥ” ተክቶ መጠቀም እና “አሰልቺ ቃላት” የሚለውን ሃረግ፣ በእንግሊዝኛው (ለዚያውም ጨርሶ በማይመስለው) “ጃርገን” መፍታት/ማብራራቱም ራሱ ስህተት ነው የሚመስለው። ምክንያቱም አንዱ ሌላውን ሊተካ አይችልም።

… ዳንኤል ‹‹የጠቅል አሽከር›› በሚል ርዕስ በለቀቀው በሌላ ጽሁፉም ውስጥ “አነዋወር” የሚለውን ቃል የ“ኑሮ” የግስ እርባታ አንዱ አድርጎ ነው የተጠቀመበት።
“… በርግጥ ያንን ሕዝብ አንድ ሕዝብ የሚያደርጉት የጋራ ባሕል፣ ቋንቋ፣ እምነት፣ የአነዋወር ዘይቤ ይኖረዋል። … በትውልድ የዚያ ማኅበረሰብ አባል ከመሆኑ በቀር በቋንቋ፣ በእምነት፣ በባሕል ወይም በአነዋወር ዘይቤ የማይመሳሰል ሰውም አለ።…”
“አነዋወር” የሚለው ቃል በዚህ ዓ.ነገር አውድ ውስጥ “አኗኗር” ለማለት ካልሆነ ሌላ ምን ለማለት ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም።
“አነዋወር” የ“ነውር” እርባታ ይመስለኛል ሊሆን የሚችለው። [ሸፍጥ › ሸፍጠኛ › አሸፋፈጥ] ሲል እንደሚረባው ሁሉ፤ [ነውር› ነውረኛ› አነዋወር] “ ቢባል ያስኬድ ይመስለኛል። ስለዚህ “አነዋወር” ካለቦታው የገባ ይመስላል–“አነዋወር” በግዕዝ ወይም በመጽሃፍ ቅዱስ ቋንቋ/ፍቺ “አኗኗር” ማለት ነው ካልተባለ በስተቀር። ብቻ… የመጽሃፍ ቅዱስ ስነ-ጽሁፍ እንደ አብዛኛው ያገሬ ሰው ሳይገለጥልኝ እንዳልሞት።

በተረፈ ዳንኤል ክብረት የ“የበጎ ሰው ሽልማት” ድርጅት መስራች መሆኑን በቅርቡ ባንዱ ጽሁፍ ውስጥ ያየሁ ይመስለኛል። ስለ ራሳችን እርስ በርሳችን ስለ-አለመተማመናችን፣ …ወዘተ በርካታ ጸለምተኛ የሆኑ ነገሮቻችን ብቻ ጎልተው በሚወሩበት እና በሚነገሩበት በዚህ በኛ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲህ በጎ ስራ የሰሩ ሰዎችን እየመረጡ ማቅረብ እና መሸለም፣ ተተኪው ትውልድም እንዲማርበት የሚያደርግ ነውና ዳንኤል ክብረትን በመልካም ስራው እጅግ አከብረዋለሁ– አገር እንዲያድግ እና እንዲለማ ምኞት እና ፍላጎት ያለው ሁሉ ይህ የዳንኤል ጅምር እንዲቀጥል የበኩሉን እንዲያደርግ አበረታታለሁ–አንዳንድ “በበጎ ሰውነት” በተመረጡት ሰዎች ላይ ቅሬታ ቢኖረኝም።

በጥቅሉ የቋንቋው እንዲህ እየሞተ መምጣት የትም/ስርዓቱ ሞት መገለጫም ነው። ፍትህ እና ነጻነት በሌለበት ማህበረስብ ውስጥ የትምህርት ስርዓቱ ሁልጊዜም በነጻ ውድድር በችሎታቸው እየተራቀቁ እና እየመጠቁ ሊወጡ የሚችሉ ሰዎችን ወደ ኋላ እያስቀረ እና አንገት እያስደፋ፣ አድርባይ እና ለጥቅም ያደሩ ስዎችን እያቀና እና እያግበሰበሰ ይጓዛል።

የአርባ ሁለት የአ.አ.ዩ. ፕሮፌሰሮች ባንድ ጊዜ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ከስራ መባረር (ምሁራኑ ባሁኑ ጊዜ በየምዕራብ አገሩ ተበትነው፣ በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ውስጥ ከፍተኛ መምህራን ሆነው እየሰሩ ነው) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በቋንቋው ላይ ያሳደረው ጫና ቀላል አይደለም። በነጻነት እና ፍትህ ማጣት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ እና አገር ቤት ውስጥ በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች (እስክንድር ነጋ፣ እና ሌሎቹም) እና ጸሃፍትን ብዛት፣ ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው።

አማርኛ እየወረደበት ያለው መቀመቅ አስፈሪ ነው። አሁን በዚያ የአረቦች አመጽ ሰሞን፣ በጀርመን ድምጽ ሬድዬ “አረብ ስፕሪንግ” የሚለውን እንግሊዝኛ “የአረብ ጸደይ” በሚል ተተርጉሞ ሲነበብ ሰምቻለሁ። በ“Arab spring” ውስጥ ያለው “spring” የሚለው ቃል፣ አመጹ ከቱኒዚያ ተነስቶ እና ባንዴ ተስፈንጥሮ ሌሎቹን የአረብ አገሮች እንዴት እንዳዳረሰ የአመጹን በፍጥነት ወደሌሎቹ አገሮች የ“መስፈንጠሩን” ሂደት የሚገልጽ ነው፤ እንጂ ከወቅት ገላጩ “spring” (ጸደይ) ጋር የሚያመሳስለውም ሆነ የሚያገናኘው ነገር የለም። የአሜሪካ ድምጽም ይኸኑ በቅርቡ ሲደግም ሰምቻለሁ ልበል?

የትርጉም ነገር ከተነሳ አይቀር በ1996 ዓ.ም “ሳባ” በሚል ርዕስ የታተመውን የ“እንግሊዝኛ-ትግርኛ-አማርኛ” መዝገበ ቃላት (ለምሳሌ “abyss”ን “ገደል” ብሎ ተርጉሞታል) ያነበበ ሰው፣ ድሮ ድሮ በ1950ዎቹ የታተመውን “ያለ-አስተማሪ” መዝገበ ቃላት፣ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ባንድ እግሩ ቆሞ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ያጨበጭብለት ይመስለኛል። በ“አረብ ስፕሪንግ=አረብ ጸደይ” ትርጉም አኳያ ሲታይ ደግሞ ለ“ሳባ” መዝገበ ቃላት ልናጨበጭብ ይገባል።

የጀርመን ድምጽ ሬድዮ፤ አንዳንዴ አማርኛ የሚቸግረው ጣቢያ ነው። እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ የሆነ የአነባበብ ስልት (ለምሳሌ ፍስሠት፣ “ፋታ” [pause?]፣ ድምጸት [tone?] ወዘተ …) አለው። የአንዳንድ ቀኑ አነባበብ የተለመደው የአማርኛ ቋንቋ ድምጸት የለውም። ፋታ በሚያስፈልገው ቦታ ላይ (ለምሳሌ የአንድ ዓ.ነገር ማሰሪያ/ማለቂያ) ላይ ፋታ-ቢስ ሆኖ ወደ ሌላው ዓ. ነገር ፈስሦ ይወርዳል፣ አንዳንዴ ደግሞ ፋታ በማያስፈልገው ቦታ ላይ (ለምሳሌ “አበበ በሶ…..[ረጅም ፋታ ይሆንና] … በላ”) አይነት አነባበብ የተለመደ ነው የሚመስለው። አንባቢው መቸስ ከአገር ከወጣ በጣም ቆይቶ ኖሮ፣ አማርኛ ቸግሮት ነው … አይባል ነገር፣ አማርኛው የጠራ ነው፣ ማለትም “አክሰንት” የለውም። የኖረበት የባህር ማዶ አገር ቋንቋ አነባበብ ተጽእኖ አሳድሮበት ሊሆን ይችል ይሆን? እላለሁ–አንዳንዴ … እንዲያው ሳስበው ግን ራስን ላለመሆን ከራስ ጋር በሚደረግ ግብ ግብ፣ ወይም ሌላውን ለመምሰል፣ የተከሰተ ይመስለኛል። እንዴ..? አንዳንዴ’ኮ ስረ መሰረቱ ያልታወቀ ዜማ የሚያዜም እንጂ ዜና የሚያነብ አይመስልም።

እያንዳንዱ አንባቢ የራሱ የሆነ “ስታይል” (ዘዬ?) ይዞ መውጣት ይችላል፣ የቋንቋውን አነባበብ ህግ እና ደንብ መስዋዕት እስከማድረግ መድረስ ግን የለበትም። ድምጽ ለማሳመር መሟሟት ያለበት ድምጻዊ (አቀንቃኝ/ዘፋኝ)፤ የሚጫወተውን ገፀ-ባህሪ ለመምሰል መሟሟት ያለበት ደግሞ የድምጽ ተራኪ ነው። የድምጽ ጋዜጠኛ እና አንባቢ ደግሞ እንደወረደ የቋንቋውን አነባበብ ህግ እና ደንብ ተከትሎ … በተፈጥሮ ያለን ድምጽ ዝም ብሎ ማፍሰስ ነው። ለምሳሌ በኢሳቱ “ሁሌ አዲስ” ዝግጅቱ መግቢያ ላይ አንባቢው የሚያወጣው ዜማዊ ድምጽ፣ የራሱ እና እንዳለ እየወረደ ያለ ድምጽ አይመስልም። ይህ አንባቢ ራሱ ሳይዘጋጅ “እንደወረደ” እንብቦ ራሱን ቀድቶ ቢያዳምጥ፣ የራሱን ድምጽ እና በኢሳቱ የ‘ሁሌ አዲስ’ ፕሮግራም መግቢያ ላይ የሚያቀርበውን በየተራ ቢያዳምጠው፣ ልዩነቱን ራሱ መታዘብ የሚችል ይመስለኛል።

አላግባብ አንድን ቃል “መጎተት” ለምሳሌ “ዘወትር” የሚለውን ቃል “ዘ—–ወትር” በሚል አነባበብ መጎተት ወይም ከ“ዘ” ፊደል በኋላ አላግባብ ረጅም pause “ፋታ”?) ማስገባት ባላስፈለገም ነበር። በዚህ አጋጣሚ፣ የኢሳቱ ብሩክ ይባስ፣ በድምጹ ጥራት እና በአነባበብ ፍሰት፣ አይኑን ከሚያነበው ወረቀት ላይ አንስቶ ወደ ተመልካቹ ወይም ካሜራው የሚመልስበት ጊዜ መገጥጠም፣ ኢሳት ካሉት በርካታ ግሩም አንባቢዎች ውስጥ አንዱ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም ሌላው ግሩም አንባቢ እና አቀናባሪ ጋዜጠኛም ነው። የሚያወያያቸው ስዎች ከአጀንዳው ሲወጡ ወደ ጉዳዩ የሚመልስበት የጋዜጠኝነት ጥበቡ ግሩም ነው። ሰሞኑን ማንበብ የጀመረችው የኦሮምኛ ዜና አንባቢ ደግሞ፣ የተፈጥሮ ድምጿ ጥራት ጥሩ እና ዝነኛ አንባቢ እንደሚያደርጋት መገመት ይቻላል።

በሚቀጥለው ጽሁፌ፣ ከኢሳት እስከ ኢቲቪ፣ ከአዲስ አድማስ እስከ ሪፖርተር እና ሬዲዬ ፋና … ወዘተ፤ እንደ ተስቦ በሽታ በሚዛመት መልኩ እየተለመደ ያለውን የአማርኛ ሰዋሰው ግድፈት በተመለከተ ሌላ ጽሁፍ ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ።

ቸር ይግጠመን።
አሊ ጓንጉል

ኢትዮጵያውያን”ዲያስፖራዎች”ሆይ!!! ቢጫውን መተት፣በደም-ድግምት ተቋጥሮ፤ በዐይኔ፣በብሌኗ: አየሁት። አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

$
0
0

“ድግምት” ሲባል እየትደገመ ዐዚምን ለማድረግ:-በሐረጎች የሚገለጥ፣በቃላት የሚበላ፣በፊደላት የሚቋጠር፣በሰዋስው የሚታኘክ፣የሚዋጥ፣የሚሰለቀጥ፣ተመልሶም የሚተፋ፤ሲበዛም በማስታወክ የሚፈፀም ወደትፋቱ የሚያስመልስ ርኩስ ተግባር ነው፤ግብሩም ዐዘመ ይባላል።

ዐዚምን በሰው ላይ የሚያደርጉ ሰዎች እንደድንገት በአንድ ሰበብ ይጀምሩትና ለመተዳደሪያቸው ሲቀጥሉበት እንደጀመሩት ግን በቀላሉ አይላቀቁትም።እንደውም ቋሚ የገቢ ምንጫቸው እንዲሆንላቸው ሲሉ የማይቻላቸውን የሞት ቁማር ለመጀመር በግድ ሞትን ሲያስጎነጩ በመጨረሻው ሰዓታት መራራዋን ሞት ራሳቸው ድንገት በክፉ መናፍስት ተገደው ይጎነጯታል።ለእኛ የሰው ልጆች ሞት የማይቀር ዕዳችን ቢሆንም የ”ኅጢያት ድሞዝ ሞት ነውና”እንደየግፋችን አፈጻጸም እና እንደየክፍያችንም ዓይነት በምሬቱ ይለያያሉ። ይህም ልዩነት በግልጽ በአሟሟታችን(ሬሳ አሸኛኘቱ ሳይሆን)ሁኔታ ይታያል።ለዚህም ነው ኑሯችን የተጎሳቆለ ቢሆንም በማይቀረው ሞት ፊት እንኳ “እባክህ ጌታዬ አሟሟቴን አሳምርልኝ::” የሚባለው።ብታምኑም ባታምኑም በሕይወት ያለነውን እነዚያ የሞቱት ግፈኞች ዘመዶቻችን ሞተውም በቁማችን እየፈለጉን:-በመጀመሪያ ጣረ መናፍስት ሆነው በሚያገኙት አጋጣሚ ተሻምተው፣በሕይወት ያለነውን ሊገድሉን ያሳድዱናል።ይህ የፈረንጅ ልብ ወለድ አይደለም፤ባጋጣሚ ታውቋቸው የነበሩትንና ዛሬ በሕይወት የሌሉትን ሰዎች እስኪ ለአንድ አፍታ አስታውሷቸው።በነገራችን ላይ ስለሞት በጥልቀት ለማወቅ መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ዕውቀት የነበራቸውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና እንግሊዞች አግበስብሰው የወሰዱትን የደብተራ ዘነብ ኢትዮጵያዊ(ብርቲሽ ሙዚየም ዩኬ)መጽሐፍትን ማንበቡ ይረዳል።ይህ ክስተት በያንዳንዱ የግፈኛ ቤት ያለ የደም ዕዳ ታሪክ ነው።ለዚህ በምሳሌነት የሚወሱት እስራኤላውያን ናቸው፤የማይደርስ መስሏቸው “እኔ ይሄ ሰው ጥፋተኛ ሆኖ አላገኘሁበትም”ብሎ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ እጁን ሲታጠብ”እኛ ላይ እስከዘር ምንዘራችን ይተላለፍብን”ያሉት ቃል ዛሬም ድረስ እንዳስለቀሳቸውና በዓለም ላይ የቁም-ሞት እየኖሩ ይገኛሉ።

ወደ ተነሳንበት ዋና ጉዳይ ስንመጣ፣የኛዎቹ የዘመኑ ገዥዎች እረ በቅድስቲቱ የተባረከች አገራችን:-<< በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ዕርቅ ያስፈልጋል፤ካለፉት ሁለት የወደቁ መንግሥታት ታሪክ እንማር፣በቃችሁ ይበለን፤ >>ሲባሉ ማንና ማን ተጣላና፣ዕርቅ በኛ መቃብር ላይ፣እስከመጨረሻው እንጋደላለን እንጂ፤ዕርቅ አይታሰብም ብለዋል።መዘዙ ለዘር ማንዘራችን ይተላለፍ እንጂ አናደርገውም:- ሲሉ በአሁኑ ያለው ትውልድ ከገዥው ቡድን ከሰማ ሃያ አምስት አመታት አስቆጠርን።እኛ በውጭ አገር ተበታትነን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በጥንቃቄ እንመልከት።የወያኔ ቡድን ወይም ጉጅሌው ፈረንጆቹ ላይ የሚያደርገውን የሃያ አምስት አመታት ማጭበርበር ልምድ ድርጊት በግልፅ አናውቀውምን???? ድርጊቱ የማጭበርበር መሆኑ የተረጋገጠው ጉጅሌው ለግልጽ ውይይት ፈቃደኛ አለመሆኑ እና “በጉልበት ያሸነፈኝ ይቀማኝ”ብቻ የማለቱ ውሳኔ ከሕዝብ ጋር መለያየቱን እና በጣም መራራቁን አረጋግጧል።የሚያሳዝነው:-”ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ”ሆነና የኢትዮጵያውያን ነገር:- የእነሱ እና የእኛ ተብሎ ተከፈለ፤ዕውነቱ ግን የሁላችንም የኢትዮጵያውያን መሆኑ የማይታበል ሐቅ ነው።ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በጉልበት ያለውን በመንቀፍበ፤ሕግ እና በፍትህ የሚለውን ወገን በመደገፍ፤ለዕውነት እና ለግልፅነት መቆም ያለብን።

ከዚህ አንፃር የራሳችንን ጥቅም ካላስቀደምን፤እጅግ አሳፋሪ አስተዋፅዖ ማድረጋችንን በደምብ እንረዳለን።እስኪ ራሳችንን እንመርምር፣በሚሊዮኖች የምንቆጠር በተለያዩ ምክንያቶች ወጥተን:-ቢያንስ በነጻነት ስለአገራችን ለመምከር የሚያስችል የመናገር እና የመወያየት ነጻነት አለን።የየራሳችን አኗኗር ይኑረን እንጂ አብዛኝዎቻችን ግን የሩጫ ኑሮ እንግፋለን።በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው የተደላደል ኑሮ የሚኖሩት፤እናም ይህ ሩጫችን ተራ በተራ ስንሰበርና ሬሳ ተብለን በመዋጮ እስክንቆጠር ድረስ ነው:-እናም አያበቃምሳ?ይህን የቁም ሞት ቁስላችንን መሸፋፈን አለብን ወይስ በጋራ ከፍተነው ተወያይተን በሰለጠነ አዕምሮ ማከም አለብን???…ተራራቅንና አቅመቢስ ሆንን እንጂ፤ብንቀራረብ ከመውደቃችን በፊት ክንዳችንን ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ጠንካራ የማይበገር እንደሆነ ማሳየት እንችላለን።ትልቁ እና አቢይ ቁምነገሩ ጭምብል አድርገው እኛ ይህን መልካም ነገር ተገንዝበን ለማድረግ ስንቀሳቀስ:-እጃቸውን አጣጥፈው የማይቀመጡ፣የጥቅም ተገዥዎች መኖራቸውን ለአፍታም ሆነ ለሰከንድም ቢሆን አለመዘንጋት ነው።

የመጣንበትን የታሪክ ጎዳና አድቅቀን በተጨባጭ እንመልከተው እስኪ።አሁን ባለው መንግሥት ተፈናቀሉ!!!!ታሰሩ!!!!ተረሸኑ!!!!ተገደሉ!!!!ኡ!!!ኡ!!!!ኡ!!!ሲባል፤አልፎ ተርፎም በሌሎች አገሮች፣በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችሟ እና የመንግስታት ያልሆኑ ድርጅቶች፣በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፈው እያሳዩን፤እየተነገረን፤እየታወቀን፤በዝምታ ፈዘን በምን አለብኝነት እናያለን።ምንም እንዳልተፈጸመ:-ምንም ላለማድረግ ሕሊናችንን በግል ጥቅም ቆልፈን፣በምን አገባኝ ሐጢያት ተቋጥረናል።እኔ ከመጀመሪያው የስደት ዘመኔ ጀምሮ ለሦስት የሰላማዊ ሰልፎች ግዜ ወጥቼ እንደ አገር ቤቱ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰልፍ የራሴ መፈክር፣የራሴ ጥሩምባ፣የራሴ አለባበስ ከሰንደቅ ዓላማዬ ጋር ውሃና የብርድ መከላከያዎቼን ይዤ በነፃነት ያለፍርሃት በፓርላማው አካባቢ ተገኘሁ።በዚያን ጊዜ ያየሁት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ከመሆኑም በላይ እኔን እያጮለቁ የሚያዩኝ መብዛት ከቁጥራችን አናሳነት ጋር ተደምሮ ጥያቄዎችን በልቦናዬ ውስጥ አሳዝሎኝ መገኘቱንም ተውኩት፤እርግጥ አልፎ አልፎ በቤተክርስቲያን ጉዳይ፣በገዳማት መበተን በጅምላ ግድያም ሆነ በእስር ተቃውሞ ላይ አልቀረሁም።ይሁንና አልተዋጠልኝም:-ከዚህ ከ72,250 በለንደን ከተማ ብቻ የሚኖርባት ኢትዮጵያውያን:-ከዚህ ውስጥ ጉጅሌን ደጋፊ 3324 ባለኢንቨስተር1897 ባንዳ 2340 ቅጥር ነፍሰ ገዳይ 1097 ሕጻናት 5076 በፈረቃ ሥራ ምክንያ ት ሊገኙ የማይችሉ 3220 ሕመምተኞች 2454 ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት 1750 = 20158 ከወጪ ቀሪ 51092 ሰዎች በሦስት መደብ ተከፍለው በየፈረቃቸው 17030 በየትኛውም ሰልፍ ላይ (በሚንከባለል ስሌት) በትክክል መገኘት ይኖርባቸው ነበር።አሁን ባለው ተጨባጭ መረጃ ግን በአገር ጉዳይ ላይ የሚገኙት ብዛት 100-500 ሰዎች ብቻ ናቸው።መሆን ግን አለበት???…በፍጹም የለበትም!አልነበረበትም !!!…… በዚህም መሠረት ሌላ ዓይነት ስሌት መከተል አለብን፤ይኸውም ቢጫውን የተመተተ ደብተር የያዙ ሰዎች ከፓስፖርታቸው ጋር በተጨማሪ የሚጠቀሙበት ነው።በዚህም ሁኔታ ዐዚም አዙረውባቸዋልና ሒሳባችንን ያዛንፈዋል።ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን ፓውንዶችም ሆኑ ዶላሮች አሊያም የኛይቱ ብር እንኳ ሳትቀር በዐይን የማይታይ የሚሥጥር ምልክት እንዳላቸው የምናውቅ???…በአንጻሩም በእርኩስ መንፈስ የሚያምኑ ደግሞ ርኩስ ነገር ላለማድረግ ምን ይከለክላችቸዋል???መልሱን ለአንባብያን ትቼዋለሁ።

“ዝ-ሆነ ሆይኑ” አሉ ኣቦይ ጛጕ:- በትግርኛ የሆነው ሆነና ወደ ሆነው ነገር ልመልሳችሁ።ይህንንም ሁኔታ ለማጣራት ምክንያት እና ሰበቡን በጥልቀት ሳጠና ድንገት እግዚኣብሔር ሲያድለኝ ቢጫውን መተት በደም ድግምት ተቋጥሮ በባለ አምስት ኮከብ ቅርጽ የጦር ስግስግ ማህተም ተለብጦበት አየሁ።በስደት በነጻነት አገር እየኖርን አንድቀንም እንኳ ከሰባ ሁለት ሺህ ሕዝብ መካከል ቢያንስ በሺህ የሚቆጠሩ የድጋፍም ሆነ የተቃዋሚ ሰልፈኞች አግኝተን አናውቅም::ዕውነት የለንም ማለት ነው???…ጉጅሌ ነው ትክክል???በፍጹም አይደለም።ጉጅሌ:-ገዳይ፤አጭበርባሪ፤ውሸታም፤አታላይ፤አወናባጅ፤ዘራፊ፤ዘረኛ፤ደደብ፤መሆኑን ራሳቸው የጉጅሌው አባላት በግልጽ ይመሰክራሉ።ታዲያ ለምንድነው ጒደኛዬ “ሰለሞን በቀለ”የጉጅሌ ቡድንን ነቅፎ እና መልሶ የሚደግፈው?ወይም ምንም የማይቃወምበት?ምክንያት ሊገባኝ አልቻለም ነበር።አሁንማ በሚገባ አወቅኩት።ለዚህም ጥናቴ የረዳኝ የወዳጅ ጠላቴ ጒደኛዬ ሁኔታ ነው።በጣም ርቄው ሳይሆን ቀርቤው፣ተጠግቼውና መርምሬው አየሁት።እዚያ የተቀመጠውን በልጃ ስክፍተው ለብቻው የተቀመጠ ቢጫ መታወቂያ ደብተር አየሁ።ይህ ደብተር የጒደኛዬን ሙሉ ሥም፣ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አድራሻ፣መቼ እነደተዘጋጀና መቼ አገልግሎቱ እንደሚያበቃ፤የት እንደተዘጋጀ ይገልጻል።የሚገርመው ከመጨረሻው ላይ ያለው ባዶ ገፅ ነው።ከኮከብ ማህተብ በስተቀር ሌላ ሲታይ በፍጹም አንድም ነገር የሌለበት ነው። ምንም የሚነበብ የለውም፤ሚሥጥሩም እሱ ላይ ነው።የማይነበብ ጽሁፍ ያለበት ባዶው ገፅ በስውር ነባቢት እንዲህ የሚል ባለሁለት አንቀጾችን ይዟል፥

“ይህ ግለሰብ ልዩ የኮከባችን አባል ነው።ወዳጆቻችን የሆናችሁ ሁሉ፣በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ ወደኢትዮጵያ ገብቶ የፈለገውን ለማድረግ ይችላል።መሬት ለመግዛት ወይም ለመሸጥ፣የግል ንግዱን ለማስፈጸም ለመለውጥ ወይም ለመለገስ፣የፈለገውን ንብረት ይዞ ለመግባትም ሆነ ይዞ ለመውጣት፣በፈልገውም ጊዜ ለመመላለስ ሙሉ ቡሙሉ ተፈቅዶለታል።ይህን መረጃ ማገድም ሆነ መከልከል አሊያም መሰረዝ የሚችለው በየአህጉራቱ ባሉት ኤምባሲዎች የተደራጁ አካላት ብቻ ናቸው።ማሕተም ባለ አምሥት ኮከብ ማዕዘናት ቅርፅ፣የጦር ዘንግ የተሰገሰገበት፤ፊርማ የማይነበብ።”ይላል።

በእርግጥ ስለቢጫው የፓስፖርት ደብተር ስነግራት ወዲያው “አውቀዋለው!” አልችኝና “ብዙ ሰዎች’ኮ አላቸው:-” አለችኝ።”የኢሕአድግ የሚሥጥር አባልነት መታወቂያ” ተብሎ በደም የተጻፈውን’ስ አንበሺዋል???ብዬ ደግሜ ጠየቅኳት።በፍጹም አልተጻፈም አለችኝ።እንግዲያውስ አርባ አምስት ድግሪ ዘቅዝቀሽ በሰያፍ ወደላይ አድርጊና ተመልከቺው፣ኮከቡ መሓል በደቃቅ ተጽፚል አልኳት።እስኪ ቤት ስገባ የማውቃትን ልጅ ደብተር ጠይቄ እመረምረዋለሁ አለችኝ።እኔም ምን መመርመር ያስፈልጋል:- የራሷ ተግባር ይናገር የለም፣እስኪ ተመልከቻት አገር ቤት ትመላለሳለች?ወያኔ ገደለ፣አሰረ፣ረሸነ፣ገነጠለ፣ሲባል ግድ ይሰጣታል????…ፍጹም::እናም ከዚህ የበለጠ ድግምት እንዴት ሊኖር ይችላል።አዎ አለችኝ።አየሽ አፈር ድሜ ግጣ፤ጽዳትም ሆነ ሸክም ሥራ ሠርታ፤አገር ቤት ነው።አዎ አገር ቤት ይናፍቃል፤ዳሩግን እንዳትዘነጋ ድሮ ትዝ ይልሃል??አቶ ከበደ መኮንን ሲናገሩ:-”ደሞዝ ተቀብዬ ሩጥ የሚለኝ እንትናሆቴል፣ቤትና ጠጅ ቤት ነው” ሲሉ።የዛሬውን የጉጅሌን ርኩስ ካርድ ከእነሱ በምን ይለየዋል???በምንም።የተደገመብትን ቢጫ የዓለም አቀፍ ሕገወጥ መታወቂያ ጉዳይ ለጓደኛዬ አስረድቻት ግደየለም ቀዳደሽ ጣይው ብያት:-አደርገችውም፤ቢያንስ የሞራል ግዴታዋን ተወጣች።በድብቅ አገር ቤት ለመሄድ ብላ ሰልፍ አልወጣም የሚለውን አቁማ በድፍረት:-አዎ “አስራ ሥምንት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡን ላለማሳወቅ ረሃባችንን በመደበቅ:-” “ዕድገት ሞልቷልii” በማለት አንዋሽም:-በማለት በጋራ ድምጻችንን ስናሰማዋለን።ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን “ቢጫው የመተት መታወቂያ” እንዳለን ያለሕፍረት የምንናገር???…እኛዎቹ ዕውነተኛ የሕዝብ ልጆች ነን።

የአሜሪካ ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ምርጫ ሂደቶች


ነፃነት፣ ዲሞክራሲ ፣ የብሄረሰብ ጥያቄና የኢኮኖሚ ዕድገት ! -እንዴትና ለማን እንዲሁም ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገት፟ ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

$
0
0

መግቢያ

እንደምንከታተለው የአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች እጣ፣ እንደህብረተሰብና እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። አብዛኛዎች አገዛዞችና መሪዎቻቸው የአገርና የህዝቦቻቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው አይመስልም። የፖለቲካ አርቆ-አስተዋይነት የጎደላቸውና፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት የማይሰማቸው መሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከማደለብ አልፈው የአገርን ሀብት ወደ ውጭ በማሸሽ እዚያ የውጭ ባንኮችና ኢንዱስትሪ አገሮች መጠቀሚያ በማድረግና የሀብት ክምችት አመቻች በመሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ ህዝቦቻቸውን እያደኸዩ ነው። በተጨማሪም የአገሮቻቸውን የጥሬ-ሀብትና የእርሻ መሬት ለውጭ ኢንቬስተሮች፣ በመሰረቱ ዘራፊዎች አሳልፈው በመስጠት ከሀብት ዝርፊያ ባሻገር ህብረተሰብአዊ፣ ባህላዊ፣ የህሊናና የአካባቢ ቀውስ እንዲፈጠር እያደረጉ ነው። በዚያው መጠንም የአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገዛዞች የመንግስት መኪናዎች በከፍተኛ ደረጃ በጭቆና መሳሪያ በመደለብና በመጠናከር የህዝቦቻቸው አለኝታ መሆናቸው ቀርቶ የዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም ታዛዦች መሆናቸውን እያረገጋጡ ነው። በመሆኑም አገዛዞች ከህዝብ የሚነሳን ተቃዎሞን፣ የመብትና የነፃነት ጥያቄን ለማብረድ የሚፈልጉት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ሳይሆን በጠብመንጃ በመታገዝ ሰላማዊ ህዝብ ላይ በመተኮስና በመግደል ነው። ከአምስት ወራት ጀምሮ በአገራችን ምድር፣ በተለይም በአሮሞ ክልል የሚካሄዳው ተቃውሞና የወያኔ አገዛዝ ያደረገውና የሚያደርገው ጭፍጨፋ ከዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም የሀብት ምዝበራ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ብዙ ማስረጃዎችም እንደሚያረጋግጡት አግአዚ በመባል የሚታወቀው አስፈሪና ፋሺሽታዊ ጦር የሰለጠነውና የታጠቀው በአሜሪካኖች የስለላ ድርጅት በሲአይኤ(CIA) እንደሆነ ነው። ይህም ማለት የወያኔ አገዛዝ በኦሮሞ እህቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ ልጆቻችን፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ የሚያካሂደው የነፍስ ማጥፋት ዘመቻ ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ስትራቴጂያዊ ስሌት ውጭ በፍጹም ሊታይ አይችልም። የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ኮሙኒዝምን እዋጋለሁ በማለት በብራዚል፣ በቺሌና በአርጀንቲና በስድሳኛውና በሰባኛው ዐመተ ምህረት አምባገነናዊና ፋሺሽታዊ አገዛዞችን አስታጥቆ ለስልጣን እንዳበቃና የዲሞክራሲንና የነፃነት ጥያቄን እንዳኮላሸ ሁሉ፣ በአገራችን ምድር ደግሞ ከሃያ አምስት ዓመታት ጀምሮ የወያኔን አገዛዝ በማስታጠቅ አገዛዙ በህዝባችን ላይ ጦሩን እንዲመዝ የሚያሰደርገው የላይኛው አንድ አካል ነው። በሌላ ወገን በስድሳኛውና በሰባኛው ዓመተ ምህረታት በብራዚል፣ በቺሌና በአርጀንቲና በህዝብ የተመረጡ አገዛዞች በአሜሪካ ታግዘው የመንግስት ግልበጣ ሲካሄድባቸውና ፋሺሽታዊ አገዛዞች ስልጣኑን ሲወስዱ፣ በአገራችን ምድር ግን „ህጋዊ በሆነ„ መንገድ የተካሄደ ቀስ በቀስ ወደ ፋሺሽታዊ አገዛዝነት የተለወጠ የስልጣን ሽግግር ነው። ለዚህ ደግሞ የጸጥታውን መስክ ከማጠናከር በሻገር፣ በነፃ ገበያ ስም የተካሄደው ፖሊሲ አገዛዙን ሀብት አካባችና፣ በዚያው መጠንም በውጭ ኃይሎች ጉያ ስር እንዲወድቅ አድርጎታል። ስለሆነም አገዛዙ የሚያካሂዳቸው እንደ ስኳር የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችና የመሬት መቀራመት ጉዳይ፣ እንዲሁም እንደሰሊጥ የመሳሰሉትን የቅባት እህሎች በመቆጣጠርና ወደ ውጭ በማጋዝ ደካማ አገሮችን ለዝንተ-ዓለም አደኽይቶ ለማቆየት ከታቀደው ከዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝም ስትራቴጂ ውጭ በፍጹም ተነጥሎ ሊታይ አይችልም። በሌላ አነጋገር፣ የዛሬው አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀስ በቀስ አገሩን በጸና መሰረት ላይ ገንብቶ የነፃነትና የዕውነተኛ ስልጣኔ ባለቤት እንዳይሆን በምዕራቡ ካፒታሊዝም የሚደገፍና ድህነትም የባሰውን ስር እንዲሰድና አገራችንም እየተሽመደመደች እንድትኖር የሚያደርግ አገዛዝ ነው። ስለሆነም አገዛዙ የፈለገውን ያህል ህዝብ ይግደል፣ በህዝብ ነው የተመረጠ በማለት አሁምን ቢሆን ከካፒታሊስት አገሮች እርዳታውን ያገኛል።

የወያኔ አገዛዝ በህዝባችን ላይ የሚያካሂደውን የጭቆና አገዛዝና ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም የሀብት ዘረፋ በተለይም ተቃዋሚ ነኝ ከሚለውና፣ እዚህና እዚያ በተናጠልም ሆነ በቡድን ውር ውር ከሚለው በሃሳብ ደረጃ ለውይይት ቀርቦ ጥናት ሲካሄድ አይታይም። በአብዛኛዎችም ዕምነት የዲሞክራሲ፣ የነፃነትና የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዳይ ከውጭው ሁኔታ ጋር የሚያያዙ ሳይሆኑ የውስጥ ጉዳይ ብቻ ነው የሚል አመለካከትና ግንዛቤ ሰፍኗል። ችግሩ ከአገራችን የተበላሸ አገዛዝ የመነጨ እንጂ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት አገዛዙ በሚያካሄደው ጭፍጨፋና ድህነት መስፋፋት ላይ ምንም ዐይነት ተጽዕኖ የለውም፤ የኛን ችግር በውጭው ላይ ማሳበቡ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን፣ አክራሪነትም ነው ይሉናል። ስለሆነም ይላሉ፣ እነዚህ በአንድ በኩል አገዛዙን የሚጠሉና የሚታገሉ ኃይሎች፣ በሌላ ወገን ደግሞ የምዕራቡ ጣልቃ-ገብነት ሲነሳባቸው የሚያንገሸግሻቸው ለዲሞክራሲና ለነፃነት እንታገላለን ባዮች የምዕራቡን ጥቅም የማይቀናቀን አገዛዝ ስልጣን ላይ ከወጣ ዕርዳታውም ይጎርፍልናል፤ በደስታም እንድንኖር ያደርጉናል በማለት የእቅጩን ይነግሩናል። በመሆኑም ይሉናል፣ የኛ ትግል የነሱን ጥቅም የሚቀናቀን መሆን የለበትም። ጥቅማቸውን እስካልነካን ድረስ ሊረዱን ይችላሉ በማለት ከህብረተሰብ ዕድገትና ከሳይንስ ውጭ የሆነ ክርክር ያቀርባሉ። በሌላ ወገን ግን የምዕራቡ ዓለም ጥቅም ምን እንደሆን እይነግሩንም። ዕቃቸውን እንዲያራግፉና ጦርነትም እንድናካሂድላቸው፣ በዚያውም መጠንም የህዝባችንን የድህነት ዘመን እንድናራዝምላቸው ይፈልጉ አይፈልጉ እንደሆን እነዚህ ለዲሞክራሲ እንታገላለን የሚሉ እህቶቻችንና ወንድሞቻቸን በግልጽ ሊነግሩን አይችሉም። በተጨማሪም የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በማድረግ ጠንካራና የተከበረች አገር ለመገንባት ያግዙን እንደሆነ ውድ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን አያብራሩም። እንዲያውም ይሉናል እሱማ አያስፈልገንም፤ የኛ ተግባር የዛሬውን አገዛዝ ማስወገድ ብቻ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የሚመጣውን እግዚአብሄር ያውቃል በማለት ከሳይንስና ከፍልስፍና እንዲሁም ከቲዎሪ ውጭ የሆነ ክርክር ይገጥማሉ። ያም ሆነ ይህ በታሪክ እንደታየውና እንደተረጋገጠው፣ ከቀድሞው ሶቭየት ህብረት፣ ቻይናና ከጃፓን የምንማረው ሀቅ የውጭ ኃይሎች በርቀት እስካልታዩና ማንነታቸው ተገልጾ ውይይት እስካልተደረገና፣ ወደ ውስጥ ያተኮረ ሁለ-ገብ የህብረተሰብ ግንባታ እስካልተካሄደ ድረስ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ እንደማይችል ነው። በተጨማሪም ከነዚህና በመጠኑም ነፃነትን ከተቀዳጁ አገሮች የምንማረው ሀቅ አንድ ህዝብ በራሱ ኃይልና ዕውቀት ተማምኖ አገሩን ለመገንባት እስካልተነሳሳ ድረስ የዕውነተኛ ነፃነት ባለቤት ሊሆን እንደማይችል ነው። በመሆኑም የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች በማንኛውም ረገድ የህዝባችን ተቆርቋሪና የነፃነት አጋዥ ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም። ከዚህ ስነነሳ የነፃነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ጉዳይ ጠለቅ ብለን መወያየት ያለብን ይመስለኛል።
እንደሚታወቀው ክርክርና ሰፋ ያለ የጭንቅላት ስራ በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ወስጥ የተለመደውን ያህል እንደኛ ባሉ በኢኮኖሚና በህብረተሰብ አወቃቀር ወደ ኋላ በቀሩ አገሮች ውስጥ የህብረተሰብን ችግርና የወደፊት ዕድል አስመልክቶ መከራከር የተለመደ አይደለም። በተለይም ከ50ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሶስተኛውን ዓለም አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት አስመልክቶ በጣም ጥቂት ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛው ክርክር ይካሄድ የነበረው ይህንን ወይም ያንን ርዕዮተ-ዓለም እናካሄዳለን በሚሉ በአውሮፓና በአሜሪካን ምሁራን ዘንድ ነበር። ለሶስተኛው ዓለም ተቆርቋሪ ሆነው የሚታገሉ ኃይሎች አብዛኛውን ጊዜ ከካፒታሊስት አገሮች የወጡና የተገለጸላቸው ኃይሎች እንጂ፣ የዕድገትና የፀረ-ዕድገት ጉዳይ በኛ ምሁራን ዘንድ ተንስቶ ክርክርና ጥናት የተደረገበት ጊዜ አልነበረም። በመሆኑም የኢኮኖሚ ፖሊሲ በውጭ ኃይሎች ተረቆ ሲቀርብ እሱን እንደቡራኬ ከመቀበልና ተግባራዊ ከማድረግ በስተቀር ፖሊሲው ዕውነተኛ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያምጣ አያምጣ ለውይይት አይቀርብም። በሁለትና በሶስት ወራት ወይም ሳምንታት ቆይታና ከዚያ በኋላ ደግሞ ይህንን ወይም ያንን መጽሀፍም ሆነ መጽሄት እያገላበጡ ከዚያ በመነሳት ፖሊሲ አውጥቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ እንደምናየው የኛንም ሆነ የሌሎችን አፍሪካ አገሮችን ሁኔታ የባሰውኑ አባባሰው እንጂ ስርዓት ያለውና ተከታታይ ማህብረሰብ እንዲመሰርቱ አልረዳቸውም። የብዙ አፍሪካ አገሮችን ሁኔታ ስንመለከት ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በአወቅሁኝ ባይነት በራሳቸው ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በሙሉ የበሳውኑ መቀመቅ ውስጥ ነው የከተቷቸው። የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን ህብረተሰቦቻቸውን በስርዓት እንዲገነቡና እንዲያደራጁ አይደለም የረዷቸው።

ከዚህ ስንነሳ በኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከእንካስላንቲሃ በስተቀር የህብረተሰብአችንን የባህል፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን እያነሱ መከራከር የተለመደ አይደለም። እንዲያውም የህብረተሰብአችን ዕጣና የወደፊት ዕድል ለዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው እየተባለ ለሚጠራው የተጣለ ይመስላል። ሁሉም አድፍጦ ተቀምጧል ። ስልጣን ለመያዝ ጊዜን የሚጠባበቅ እንጂ ብሄራዊ ፕሮጀክት እንዳለው ሰፊ ጥናት በማቅረብ እንድንወያይ የሚያደርገን ኃይል ያለ አይመስልም። የአገርን ህልውናና በትክክለኛ ፖሊሲ መሰረተ-ሃሳብ የመገንባቱ ጉዳይ በመሰረቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ካለው ኃይል የሚጠበቅ ጉዳይ ነበር። እንደምከታተለው ከሆነ የተራማጅ ወይንም የተገለጸለት አስተሳሰብ ያለው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ስለሌለና፣ አንድ ሰሞን ተራማጅ ነኝ የሚለው ኃይል ተሟጦ ከአለቀ በኋላ በአሁኑ ወቅት የሊበራል ነፃ ገበያ እናካሂዳለን የሚሉት ዋናው ተዋናይና ግንባር ቀደም በመሆን ሜዳውን አጣቦታል። ድሮ ተራማጅ ነኝ ይል ከነበረው ኃይል ትንሽ ተሟጦ የቀረው ደግሞ ሹክክ ከማለት በስተቀር የሚፈልገውን ነገር ወደ ውጭ ወጥቶ ለመናገር የሚደፍር አይደለም። በዚህም በዚያም ብሎ ሌሎችን ተገን አድርጎ ወደ ስልጣን ሊመጣ የሚፈልግ ነው የሚመስለው እንጂ ለአገር የሚበጅ በፍልስፍና፣ በሳይንስና በቲዎሪ የተመሰረተና የተረጋገጠ ብሄራዊ ፕሮጀክት አለኝ ብሎ ወደ ውጭ ወጥቶ ሲያሰተምርና ሲከራከር አይታይም። ይህ ዐይነቱ የተድበሰበሰ አካሄድ እስካለ ድረስ፣ የፈለገውን ያህል ዲሞክራሲ እየተባለ ቢጮህም ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ በፍጹም አይችልም። ከዚህ አስቸጋሪና አደናጋሪ ሁኔታ በመነሳት ስለ ነፃነት ሊኖረን የሚገባንን ግንዛቤና መደረግ ያለበትንም ትግል እኔ በምረዳው መልክ ከታች ለመተንተን እሞክራለህ። የነፃነትና የዲሞክራሲ ትርጉሞች ግልጽ ሲሆኑ ብቻ የኢኮኖሚ ዕድገትና የህብረተሰብ ግንባታም መልክ ሊይዙ ይችላሉ የሚል ዕምነት አለኝ።

የነፃነት ትርጉምና ለነፃነት የተደረገው ትግል!

ለመሆኑ ነፃነት ማለት ምን ማለት ነው ? ኢማኑኤል ካንት የሚባለው የጀርመኑ ታላቅ ፈላስፋ „ከሩሶ ስራ ጋር ከመተዋወቄ ወይም ጽሁፎቹን ከማንበቤ በፊት አምን የነበረው በሰው ልጅ አርቆ አሳቢነትና ዕውቀት(Reason and Knowledge)ነበር። ስለዚህም ስለሰው ልጅም የነበረኝ አስተሳሰብ ለየት ያለ ነበር። ያልተማረውን ወይም ደንቆሮውን የምንቅና የተማረውን ብቻ የማከብር ነበር። ሩሶን ካነበብኩ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር በነፃ ፍላጎት (Free Will) ስር መሆናቸውን ተገነዘብኩኝ። ስለዚህም በሩሶና በአይሳቅ ኒውተን መሀከል ያለውን ልዩነት በመገንዘብ፣ የነፃነት ዓለም(The World of Freedom) ከተፈጥሮአዊ ዓለም (The World of Nature) የበለጠና ወርቃማ እንደሆነ ተማርኩኝ“ ይላል። በመቀጠልም ፣ “ሩሶ የነፃነትን የተደበቀ ምስጢር ለሰው ልጅ ሲያሰተምር፣ ኒውተን ግን የተፈጥሮን ህግ እንድንረዳ መንገዱን ከፈተልን። ሩሶ ኒውተናዊ የሰው ልጅ ሞራላዊ አባት ሲሆን፣ ውዥንብር በሰፈነበት ዘመን ስርዓት እንዲሰፍን ያደረገ ነው።“ በማለት የሰው ልጅ የግዴታ በነፃነት ዓለም ውስጥ መኖር እንዳለበት ያሳስበናል። በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ ነፃ ሆኖ የተፈጠረና በራሱ ነፃ አስተሳሰብ መገዛት አለበት። ይህን ሲገነዘብ ብቻ የራሱን ነፃነት ከማስከበር አልፎ ለሌላው ላልተገነዘበውም ጠበቃ ሆኖ ይታገላል። ነፃነት በአንድ አገዛዝ ወይም ኃይል የሚሰጥ ሳይሆን አንድ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት ማንነቱን ተገንዝቦ የሚቀዳጀው፣ ለፈጠራ ስራና ለሁለ-ገብ የአገር ግንባታ የሚያስፈልግ ቅድመ-ሁኔታ ነው። በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥም የተረጋገጠው፣ በተወሳሰበ መልክ የተካሄደውና በብዙ መልክ የሚገለጸው ነፃነት ተግባራዊ ሲሆን ብቻ ነው ቀስ በቀስ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊታይ የቻለው።

ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በካንት ዕምነት ሩሶ እንደሚለው የሰው ልጅ ህይወት ዕውነተኛ ትርጉም በነፃነት ዓለም ሲኖር ብቻ ነው። ምክንያቱም ክብርና ነፃነት ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ማንኛውም የሰው ልጅ የሌላ ሰው ፍላጎት ተገዥና በሱ እየታዘዘ መኖር የለበትም። በሌላው ፍላጎት መኖርና ማጎብደድ የራስን የኑሮ ትርጉም አለመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ ራስን እንዳልነበሩ አድርጎ መሰረዝና ማዋራድ ነው። ስለዚህም ይላል ካንት፣ “በዚህ ዓለም ላይ እጅግ የሚያስከፋው ነገር በራስ ፍላጎት አለመመራት ወይም የሌላው ተገዢ መሆን ነው“፣ በማለት ነፃ ፍላጎት የቱን ያህል የሰውን ልጅ የመኖርና ያለመኖር፣ አንድ ህብረተሰብ በስነ-ስርዓት መገንባት መቻሉንና አለመቻሉን የሚረዳን ነው ይላል። ካንት ፍሪ ዊል ወይም ነፃ ፍላጎት ሲል አናርኪ ይፈጠር ማለቱ አይደለም። ወይም አንዱ ሌላውን አያክብር ማለቱም አይደለም። ካንት ስለ ሰው ልጅ ነፃነትና ዕውነተኛ ፍላጎት ሲያስተምር የሰው ልጅ ዕውነተኛ ነፃነት ሲሰማው የመፍጠር ኃይሉም ይዳብራል። ራሱንና የሌላውን ሰው ማንነት በመረዳት የበለጠ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግኑኝነት ይገነዘባል። በካንት ዕምነት፣ ኒውተን እንደሚለው ተፈጥሮ በድን አይደለችም ወይም ህይወት የሌላት ነገር አይደለችም። የሰው ልጅም የተፈጥሮምና የማይታየው ወይም የረቀቀው መንፈስ አካል ነው። ድርጊቱ ሁሉ የተፈጥሮን ህግ በመረዳት የሚካሄድ ነው። በካንት ዕምነት የነፃነት አስተሳሰብ በብዙ ቅራኔዎች የተወጠረ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት የሰው ልጅ ጭንቅላት ውስጥ ገብተው የሚብላሉ ብዙ ነገሮች ስላሉ አስተሳሰቡ በመወሰንና ባለመወሰን፣ እንዲሁም በነፃነት መሀከል ይዋልላል። ከዚህ የአዕምሮ ጭንቀትና የአስተሳሰብ ቅራኔ ለመውጣት፣ ተግባራዊ በሚሆን የአርቆ አስትዋይነት ወይም አሳቢነት ነው የመዋለሉ ጉዳይ መስመር ሊይዝ የሚችለው። ይህም ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ ለራሱ የሚሆን የአርቆ አስተሳሰብ መመዘኛ ያወጣል። ይህ መመዘኛው ራሱን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳው መሆን አለበት። ስለሆነም ይህ ለራሱ ብሎ የደነገገው ሞራላዊ መለኪያ ለሌላውም የሚያገለግል መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር መጽሀፍ ቅዱሱ እንደሚለን፣ „በራስህ ላይ ሊደረግ የማትፈለገውን መጥፎ ድርጊት ለሌላው ሰው አትመኝ፣ ወይም አትፈፅምበት“ የሚለውንም አስተሳስበ ካንት በመቀበል የሰው ልጅ የግዴታ በአርቆ-አሳቢነት መመራት እንዳለበት ያስተምረናል። ካንት ካቴጎሪካል ኢምፔራቲቭ(Categorical Imperative) በሚለው ስለሌላው ሰው ማሰብና መሰማት በሚያስተምረው አዌርነስ(Awarness) በሚለው ብዙ መሰረተ-ሃሳቦችን በያዘው ፍልስፍናው ውስጥ ነው የሚያስተምረን። የካንት አቀራረብ የእንግሊዞቹን የሆበስ፣ ሎክንና ሁምን አመለካከት የሚጻረር ነው። በእንግሊዞች የኢምፔርሲስት ፈላስፋዎች ዕምነት የሰው ልጅ የፍላጎቱ ተገዢ ነው። አርቆ-አሳቢነቱም ከፍላጎቱ በታች የሚገኝ ነው። ስለዚህም ድርጊቱ ሁሉ አንድን ጥቅም ከማግኘት ጋር የተያያዘ ነው። በተለይም በሁም ዕምነት አርቆ-አሳቢነት የፍቅር ስሜት(Passion) ባሪያ ነች። ከዚህም በመነሳት እያንዳንዱ ግለሰብ በዚህ ሎጂክ የሚመራ ነው። በሰው ልጅ አስተሳሰብ ውስጥ ግብረ-ገብነትና(Morality) ስነ-ምግባር(Ethiccs) ቦታ የላቸውም። ግብረ-ገብነት ከአርቆ-አሳቢነት ውጭ የሚገኝና፣ በራሱ ህግ የሚተዳደር ነው። በመሆኑም በኢምፔሪሲስታዊ የሳይንስ አመለካከት ውስጥ ግብረ-ገብነትና ስነ-ምግባር ቦታ የላቸውም።

ካንት ከሩሶ የተማረው የነፃነት ዓለም በግሪኩ ስልጣኔ ዘመን ሌላ ትርጉም ነበረው። እንደሚታወቀው በግሪኩ ስልጣኔ ዘመን በእነ ሶክራተስና በፕላቶን ዕምነት የሰው ልጅ ችግር ሁሉ አርቆ አለማሰብ ወይም የዕውቀት ችግር ነው። በእነሱ ዕምነት በጊዜው ይታይ የነበረው ችግር፣ ረሃብ፣ ድህነት፣ ጦርነትና በውዥንብር ዓለም ውስጥ መኖር የዚህ ሁሉ ዋናው ምንጭ ዕውነተኛ ዕውቀት አለመኖርና አለመዳበር ሲሆን፣ የሰው ልጅም የራሱን ምንነት ለመረዳት አለመቻል ነው። ስለዚህም አርቆ አሳቢነትን ከትክክለኛ ዕውቀት ጋር በማዋሃድ የሰው ልጅ ነፃነቱን እንዲቀዳጅ ማድረግ ይቻላል ይሉናል። በጥንት የግሪክ ፈላስፋዎች በአንድ በኩልና፣ በሌላ ወገን ደግሞ በሩሶና በካንት መሀከል ተቃራኒ አስተሳሰብ ያለ ቢመስልም ሁለቱም አስተሳሰቦች የሚደጋገፉ ናቸው። ይሁንና ግን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉ የገዢ መደቦች፣ ወይም ደግሞ የተሻለ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታ ያላቸው የህበረተሰብ ክፍሎች የተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ለዘለዓለም ተገዢ ሆኖ እንዲቀርላቸው ዕውቀት የሚባለውን ነገር እነሱ በፈለጉት መልክ እየቀረጹ በማውጣትና በማስተማር ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋሉ። በመሆኑም እነሶክራተስና ፕላቶ ሶፊስቶችን ሲዋጉ ያመለክቱ የነበረው የተሳሳተ ዕውቀት የሰው ልጅ ሚናውን እንዳይረዳ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ በዕውነትና በውሸት መሀከል ያለውን ልዩነት እንዳይገነዘብ ያግደዋል። በመሆኑም የገዢ መደቦችና አፈቀላጤዎቻቸው የአንድን ህብረተሰብ ሂደትና አኗኗር ራሳቸው በፈለጉት መልክ በመተርጎምና በማጣመም ሰፊው ህዝብ ነፃ አስተሳሰብንና ዕውነተኛ ዕውቀትን እንዳይጎናፀፍ ያደርጉታል። ስልጣናቸውንም ለማራዘም ሲሉ በህብረተሰብ ውስጥ የሀብት ሽግሽግ በማድረግና ለጦርነት በመዘጋጀት አንድ ህዝብ ተስማምቶ እንዳይኖርና ታሪካዊ ስራዎችን እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆኑታል። በዚያውም መልክ እኩልነትና(justice) ጥበባዊ ስምምነት ትርጉም አጥተው ጥቂቱ የህብረተሰብ ክፍል ብቻ የሚጎናፀፋቸውና የሚደሰትባቸው ይሆናሉ። ይህ በራሱ ደግሞ የግዴታ ካንት የሚለውን ነፃ ፍላጎት(Free Will) እንዳይዳብር ያግዳል። በእኔ ዕምነትም ሆነ የካንትን ተከታታይ ስራዎች ላነበበ በትክክለኛ ዕውቀትና በነፃ ፍላጎት መሀከል ተቃራኒ አስተሳሰብ የለም። ሁለቱም የሚደጋገፉ ናቸው።

ካንት መገለጽ ማለት ምን ማለት ነው ? (What is Enlightenment ?) በሚባለው ግሩም ጽሁፉ በጊዜው የነበረውን በዲስፖቲያዊ ወይም በፊይዳላዊ አገዛዝ ይሰቃይ የነበረውን ህዝብ ችግር በማሳየት፣ አንድ ህዝብ ከተተበተበበት፣ ነፃ አስተሳሰብን ከሚያፍን ስርዓት የግዴታ መላቀቅ እንዳለበት ያመልከታል። በሱም አባባል መገለጽ ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ድክመት የተነሳ ከተተበተበት ሃሳብን ከሚያፍን ስርዓት ለመላቀቅ የሚያደርገው የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ነው። የሰው ልጅ በመሰረቱ ሰነፍ ስለሆነ የማሰብ ኃይሉን አይጠቀምም። አንድ ስርዓት ሲያሰቃየው እሱን እንደ ተፈጥሮ ህግ አድርጎ በመውሰድ የድንቁርናው ወይም የማሰብ ኃይል ድክመቱ ተገዢ በመሆን እሱን በሚመስለው በሌላ ሰው መብቱ ይረገጣል። ካንት እንደሚለን ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ የተሰጠው የማሰብ ኃይል ሲኖረው ይህንን ውስጣዊ ኃይሉን በራሱ ጥረት ከፍ ማድረግና ጥያቄዎችን በመጠየቅ ከተተበተበት የጭቆና ስንሰለት መላቀቅ አለበት። በጊዜው ዲስፖቲያዊ አገዛዝ ከሃይማኖት ጋር በመጣመር በተለይም ሰፊውን የጀርመን ህዝብ ማንነቱን እንዳያውቅና የህይወቱ ባለቤት እንዳይሆን አፍኖ ስለያዘው ካንት ብቻ ሳይሆን፣ ከካንት በፊትም የነበሩ ሌሎች ምሁራንና፣ በኋላ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ የተገለጸላቸው ምሁራን እንደ አሸን በመፍለቅና የመገለጽን ምንነት በማስፋፋት በጊዜው ከነበረው ሃሳብን አፋኝ ስርዓት ጋር መጋፈጥ ጀመሩ። በዚህ መልክ የተቀጣጠለው እሳት በመስፋፋትና አፋኙን ስርዓት መፈናፈኛ በማሳጣት ጀርመንን የገጣሚዎችና የአሳቢዎች ወይም የፈጣሪዎች አገር ማድረግ ተቻለ።

ከዚህ ስንነሳ የነፃነትን ትርጉም ለማያውቁ ወይም ደግሞ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ብለው ሌላውን አምሳያቸውን እንደፈለጋቸው ልናሽከረክረው እንችላለን ለሚሉ፣ ነፃነት የሚለው አስተሳሰብ በመጽሀፍ ቅዱስም በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ሰፍሯል። የብሉ ኪዳይ ሞሰስ ምዕራፍ ዘጠኝ ላይ፣ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በአምሳሌ ፈጠርኩት ይላል። ይህም ማለት ማንኛውም የሰው ልጅ በእግዚአብሄር ፊት እኩል ነው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር መጽሀፍ ቅዱሱ የሚለን አንደኛው ሌላውን የመግዛትና እንደፈለገው የማድረግ መብት የለውም። የሰው ልጅ የነፃነት ደረጃ ይለያይ እንጂ የመጨረሻ መጨረሻ ነፃነት የህይወት ትርጉም ነው። የነፃነት ደረጃ ስል አንድ ከእናቱ ማህፀን ያልወጣ ወይም ገና ያልተወለደ እዚያው ውስጥ ለማደግ ሙሉ በሙሉ ጥገኝነቱ በእናቱ ነው። ሲወለድና የመጀመሪያውን ብርሃን ሲያገኝ የተወሰነ ነፃነት አገኘ ማለት ነው። በመቀጠልም መዳህ ሲጀምር የተሻለ ነፃነት ያገኛል። እንደዚያ እያልን ስንሄድ አንድ ልጅ ለአቅመ-አዳም ሲደርስ ሙሉ ነፃነቱን ተቀዳጀ ማለት እንችላለን። ይህ ግን ከአካል አንጻር ስናየውና ከዚህ ቀደም ራሱ ማድረግ የማይችላቸውን መፈፀም ሲችል ነው። ይህ ዐይነቱ የአካል ነፃነት ግን ከጭንቅላት ነፃነት ጋር የማይጣጣምበት ሁኔታ አለ። የአንድ ልጅ የአእምሮ ነፃነት በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በዳበረና ስር በሰደደ ኋላ-ቀር የአኗናር ስልትና ለፈጠራ ወይንም ራስን በደንብ ለመግለጽ በማቻልበት መልክ ሊወሰን ይችላል። በሌላ አነጋገር፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ የማቴሪያልና የአስተሳሰብ ሁኔታ የአንድን ልጅ በአዕምሮ መዳበርና አለመዳበር ይወስናል። ለምሳሌ በዘልማድና በባህል በተጠመደ ህብረተሰብና በሌላ በሰለጠነ ህብረተሰብ ውስጥ ተወልዶ ባደገ ልጅ ወይም ሰው መሀከል ነፃ አስተሳሰብና ፍላጎት የዕድገት ደረጃቸው አንድ አይደሉም። በኢኮኖሚም ሆነ በባህል ወደ ኋላ በቀረ ህብረተሰብ፣ ወይም ነፃ አስተሳሰብ እንደልብ በማይሽከረከርበት ህብረተሰብ ውስጥ ተወልዶ የሚያድግ ልጅ ሳያውቀው የግዴታ በህብረተሰብ ውስጥ የተነጠፉ አስተሳሰቦችን፣ የራስን ፍላጎት ወደ ውጭ አውጥቶ አለመናገር፣ ጥያቄ አለመጠየቅ፣ ለመከራከር አለመድፈር፣ አጎድብድዶ ወይም አጎንብሶ መጥፎም ነገር ቢሆን እሺ ብሎ ተቀብሎ መሄድ እንደተፈጥሮአዊ ህግ ተደርጎ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ። በተለይም በአገራችን አሁንም ቢሆን ከላይ የተዘረዘሩ የኢትዮጵያውያን ጨዋ ባህል እየተባሉ የሚወራላቸው የሰውን አስተሳሰብ እንደወጠሩት ነው። ስለዚህም እንደዚህ ዐይነት ህብረተሰብ ውስጥ ጥቂት እናውቃለን የሚሉና ስልጣን የጨበጡ ወይም ተማርን የሚሉ ህብረተሰቡን አፉን እንደሚያሲዙትና አጎብድዶም የነሱን አሰተሳሰብ ብቻ እንዲቀበል የማድረጉ ኃይል ከፍ ያለ ነው። ከዚህም በላይ እነዚህ ኃይሎች ከውጭው ኃይል ጋር በመቆላለፍና የርዕዮተ-ዓለምና የጥቅም ሰለባ በመሆን አንድ ህዝብና ታዳጊ ወጣት አጎብዳጅ ሆነው እንዲቀሩ ያደርጋሉ። በዚያው መጠንም የድህነቱ ዘመን እየተራዘመ በመሄድ፣ አንድ ህዝብ በማቴሪያል ዕጦት ብቻ ሳይሆን ራቁቱን የሚቀረው የአስተሳሰብ ድህነትም ቁራኛ በመሆን ራሱን እንዳይችል ይደረጋል።

በመሆኑም ከጥንቱ የግሪክ ስልጣኔ ታሪክ ጀምሮ እስከ አውሮፓው የህብረተሰብ ግንባታ ድረስ ለዕውነተኛ ዕውቀትና ነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት ልማዳዊና ባህላዊ የሚባሉ አኗኗሮች የቱን ያህል የሰውን ልጅ የተፈጥሮ ተገዢ ብቻ ሳይሆኑ፣ በስልጣን ላይ የተቀመጠው ኃይል ተገዢም በመሆን እግዚአብሄር የሰጣቸውን ዕውነተኛ ነፃነት እንዳይጠቀሙና ችግራቸውን ፈቺ እንዳይሆኑ በመረዳት ነው አዕምሮን ነፃ ለማውጣት ትግል የተደረገው። የግሪኩ ስልጣኔም አነሳስ የሰውን ልጅ መሰረታዊ ቦታ በመረዳት የተደረገ እንቅስቃሴ ነው። የመጀመሪያው ታለስ የተባለው የግሪኩ ፈላስፋ 1ኛ) እግዚአብሔርን የማመሰግነው እንስሳ አድርጎኝ አለመፍጠሩ፣ 2ኛ) አረመኔ ሳልሆን የሰለጠንኩ በመሆኔ ነው ይላል። በዚያን ዘመን ግሪኮች ራሳቸውን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማወዳደር እነሱ ብቻ የሰለጠኑ መሆናቸውን ያምኑ ነበር። አንዳንድ የፍልስፍና አስተሳሰቦችን በተለይም ከግብፅም ሆነ ከህንድ ቢወስዱም፣ ለፍልስፍና መልክ የሰጡትና የዕውቀት ሁሉ አባቶች እንዲሆን ያደረጉት የግሪክ ፈላስፎች ናቸው። በተለይም ፍልስፍናን ወደ ውጭ አውጥቶ በገበያ ላይ መከራከሪያ ማድረግና ሌላውን ቻሌንጅ ማድረግ በግሪክ ፈላስፋዎች የተስፋፋና ለዕውነተኛ ዕድገትና ነፃ አስተሳሰብ መዳበር አስፈላጊ መሆኑን ግንዛቤ የተደረሰበት ነው። በተለያዩ የግሪክ ፈላስፎች የዳበሩትን ዕውቀቶች ስናገላብጥ፣ የሰው ልጅ ዕድል ቀደም ብሎ እንደሚታመንበት በአምላኮች የሚደነገግ አልነበረም። የጥፋቱም ሆነ የጥሩ ዕድሉ ወሳኝ ራሱ የሰው ልጅ ብቻ ነው። ይህም ማለት የሰው ልጅ የማሰብ ኃይሉን መጠቀም ከቻለ ኑሮውን ለማሻሻል ሲል የግዴታ መሳሪያም የሚፈጥርና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ተፈጥሮ የምታደርስበትን አደጋ በመቋቋም ወደፊት መራመድ ይችላል። ከዚያም በመቀጠልም ስርዓትና የተረጋጋ ህብረተሰብ በመፍጠር ለተከታዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይችላል። የሰውን ልጅ የስልጣኔ ታሪክ ካለብዙ ጭንቀት ስንመረምር የበለጠ ነፃ በሆነ ቁጥር የማሰብ ኃይሉ ይዳብራል። የመፍጠር ኃይሉ ይጨምራል። ስርዓትና ስምምነትን ከጭንቅላቱ ጋር በማዋሃድ የተሻለ ኑሮ ይመሰርታል። ነፃነት በሌለበት ቦታ ደግሞ የሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ ይሆናል። ለበሽታና ለረሃብ ይጋለጣል። ተፈጥሮን የመቆጣጠርና ልዩ ልዩ ነገሮችን እያመረተ ለመጠቀም ያለው ኃይል ይዳከማል። ይህ ሁኔታ በተለይም በአውሮፓ ምድር ውስጥ የካቶሊክ ሃይማኖት ባየለበት ከክርስቶ ልደት በኋላ ከሰድሰተኛው ክፍለ-ዘመን እስከ አስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የአውሮፓ ህዝብ በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል። ይህ የጨለማ ዘመን ሊደመሰስ የቻለው በሪናሳንስ እንቅስቃሴ፣ ቀጥሎ ደግሞ በሪፎርሚሽን፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ግኝት አማካይነት ነው። ያረጀውና ህብረተሰቡን ተብትቦ የያዘው ስርዓት በአዲስ ዕውቀት ሲፈተንና ግፊት ሲገጥመው ለአዲሱ ቦታውን በመልቀቅ የአውሮፓ ህዝብ፣ ዕደ-ጥበብን፣ ንግድን ማስፋፋት፣ ከተማዎችን መገንባትና ሌሎች ተዓምር የሆኑ ስራዎችን መስራት ቻለ። ይህ ሁሉ የተገኘው ከላይ በተወረወረ ወይም በገዢዎች ቡራኬ ሳይሆን የዕውነተኛ ነፃነትን ትርጉም በተረዱና ራሳቸውን ለመሰዋት በተዘጋጁ ኃይሎች አማካይነት ነው። የነፃነት ትግል አልፎ እልፎ ካልሆነ በስተቀር የተጀመረውና መስመርም መያዝ የቻለው በግለሰብ ታታሪዎች አማካይነት ነው። ይህ ዐይነቱ ትግል በተገለጸላቸው ቄሶች፣ ፈላስፎችና ሳይንቲስቶች፣ እንዲሁም የልዩ ልዩ ጥበብ አዋቂዎች የተቀነባበረ የጭንቅላት ትግልና ተግባራዊም የሆነ ነው። ስለዚህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ ለነፃነት የተደረገው ትግል ቁንጽል ሳይሆን ሁለንታዊና የሰውን ልጅ ብቁ(Perfect)እንዲሆን ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው። ካንት እንደሚለው የሰው ልጅ ማቴሪያላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው። የመንፈስ ደስታውን የሚጎናፀፈው የግዴታ በሚያገኘው ገቢ ብቻ ሳይሆን መንፈሱ የሚያድስልትን ነገርም የተጎናፀፈ እንደሆን ብቻ ነው። መንፈሳዊ ደስታዎች በልዩ ልዩ ነገሮች ነገር ግን ደግሞ በረቁቁም ሆነ በቀጥታ በሚታዩና ርካታን በሚሰጡ የሚገለጹ ናቸው። የተለያዩ ሰዎች አንድ ዐይነት ስሜት ስለማይኖራቸው የሚረኩበት የመንፈስ ደስታም ይለያያል። እንዲሁም የንቃተ-ህሊናቸው ደራጃ የመንፈስ ርካታቸውን ሁኔታ ሊወስነው ይችላል።

አብዛኛውን ጊዜ ስለነፃነት የሚጽፉ ኢትዮጵያውያንም ሆነ አንዳንድ በኒዎ-ክላሲካል የኢኮኖሚክስ ትምህርት የተካኑ የአውሮፓ ምሁራን የነፃነትን ትርጉም ከገበያ ኢኮኖሚ ጋር ነው ለማያያዝ የሚሞክሩት። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ የታሪክን ሂደት የሚያጣምም ብቻ ሳይሆን፣ ነፃነት የሚለውን ትርጉም እጅግ በጠባቡ እንድንረዳና የንግድ ሰዎች ብቻ እንድንሆን የሚያደርገን ነው። ስለዚህም ነው ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በጀርመንና በእንግሊዝ ፈላስፋዎች መሀከል የጦፈ ትግል የተካሄደው። የጀርመን ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች መንገድ የበለጠ ነገሮችን ወደ ውስጥ ጠለቅ ብሎ እንድንመረምር የሚያስችለን ሲሆን፣ የእንግሊዞቹ ደግሞ በቀጥታ በምናየው ላይ ብቻ ያተኮረና የአንድን ነገር ርስ በርሱ መያያዝና ውስጣዊ ኃይል እንዳለው እንድንገነዘብ የሚያደርገን አይደለም። ለምሳሌ የአዳም ስሚዝን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ስንወስድ በኒውተን አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነው። በኒውተን ዕምነት ተፈጥሮና ህዋ ርስ በራሳቸው የተያያዙ አይደሉም። ማንኛውም ነገር ወደ ጥቃቅን ነገር፣ ለምሳሌ እንደ አቶም ተበጣጥሶ የሚቀነሰና የሚታይ ነው። እነዚህ ተበጣጥሰውና ተሰበጣጥረው የሚገኙ ነገሮች በተፈጥሮ ውስጥ በሚገኝ ህግ የሚተዳደሩ ስለሆነ፣ እግዚአብሔር ከውጭ ሆኖ ድርጊታቸውንና እንቅስቃሴያቸውን የሚመለከት ነው። ጣልቃ አይገባም። ተፈጥሮም ስርዓት ያላትና በተወሰነ የአርቆ አስተሳሰብ ሎጂክ ስለምትዳደር፣ የሰው ልጅ ይህንን የተፈጥሮን ህግ የመረዳት ኃይል ይኖረዋል። የስው ልጅ እየረቀቀና እያሰበ ሲሂድ በማቲማቲክስ ፎርሙላ አማካይነት አንድን ነገር መረዳት ይቻላል። ልምምድና ነገሮችን ጠጋ ብሎ መመልከትና መመርመር ቦታ የላቸውም። ይህ አሰተሳሰብ ወደ ኢኮኖሚክስ ሲተረጎም በአንድ ህበረተሰብ ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ዓለም ብቻ የሚሽከረከር ነው። ለራሱ ጥቅም በሚያደርገው እሽቅድምድምና በማይታየው ወይም በረቀቀው እጁ(Invisible Hand) አማካይነት በህብረተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ መዛባቶችን ወደ ሚዛናዊነት እንዲመጡ ያደርጋቸዋል። ከፍ ብለን ስንሄድ ደግሞ በዛሬው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክስ ቲዎሪ መሰረት፣ እግዚአብሄር በፈጠረው ተፈጥሮ ላይ ጣልቃ የማይገባውን ያህል፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በሚከሰትበትና ብዙ ህዝብን በሚያሰቃይበት ጊዜ መንግስታት ጣልቃ መግባት የለባቸውም፤ በገበያው ውስጥ ያሉ ኃይሎች በራሳቸው ኃይል ቀውሱን ስለሚያርሙ መንግስታት ዝም ብለው ነው መመልከት ያለባቸው። ኢኮኖሚውን ከገባበት ቀውስ ለማውጣት ጥረት ማድረግ የለባቸውም። ወደ አዳም ስሚዙ ስንመጣ ደግሞ የሰው ልጅ ወደ ምርትና ወደ ፍጆታ(Homo Economicus) ተቀንሶ የሚታይ ነው እንጂ ሌሎች መንፈሱን የሚያድሱ ፍላጎቶች የሉትም።

ከዚህ ጋር በተያያዘና እንዲሁም ደግሞ የነፃ ንግድንም ሆነ ነፃ ገበያን በህብረተሰብ ግንባታ ውስጥ ያለውን ቦታ በሚመለከት እንደዚሁ የጦፈ ትግል ተካሂዷል። በሌላ አነጋገር፣ የጀርመን ክላሲኮች የገበያን ኢኮኖሚ ባይቃወሙም ከህብረተሰብና ከአገር ግንባታ ውጭ ተነጥሎ መታየት እንደሌለበት ያስተምራሉ፤ ያሳስባሉ። ምክንያቱም በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ዜጋ በስራ-ክፍፍል ቢለያይምና በገበያ አማካይነት የሚገናኝና የሚተሳሰር ቢሆንም፣ ይህ ዐይነቱ ግኑኝትና የስራ-ክፍፍል ጠንካራ አገርንና ህብረተሰብን ከመመስረት ተነጥሎ መታየት የለበትም። ማንኛውም ግለሰብም በመነጣጠል ሳይሆን ዕውነተኛ ነፃነቱን የሚቀዳጀውና ኢኮኖሚውንም በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው፣ በአንድ ባንዲራ ስርና ለአንድ ዓላማ የቆመ እንደሆነ ብቻ ነው። በተለይም ህብረ-ብሄሮች እየተመሰረቱና አንዳንድ አገሮች ጠንካራ ኢኮኖሚ እየገነቡ ሲመጡ፣ በብዙ መሳፍንቶች ተከፋፍላ የምትገዛውና የውጭ ወራሪዎች ሰለባ የሆነችው ጀርመን በኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ፊት መግፋት አልቻለችም። በፈላስፋዎችና በሌሎች ምሁራን ዕምነት ትናንሽ አገሮች እዚያው በዚያው ተከፋፍለው የሚኖሩ ከሆነ ህዝቦቻቸው በፍጹም ዕውነተኛ ነፃነትንና ዕድገትን እንደማጎናጸፉ፣ ስለሆነም ይህ ዐይነቱ ክልላዊ አስተዳደር ቆሞ ጀርመን በአንድ አገዛዝ ስር መተዳደር እንዳለባትና፣ የጉምሩክ ኬላዎችም መጥፋት እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ደረሱ። በዚህም አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ግለሰብአዊ ነፃነትም ቀስ በቀስ ተግባራዊ እንደሚሆን ግልጽ ነበር። ምክንያቱም ማቴሪያላዊ ዕድገት በሌለበትና፣ አንድ አገር በተለያዩ የመገናኛ መስመሮች እስካለተያያዘና፣ ህዝቡም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ እስካልቻለ ድረስ ዕውነተኛ ነፃነትን በፍጹም ሊቀዳጅ አይችልምና። በመሆኑም ግለሰብአዊና ህብረተሰብአዊ ፍላጎቶች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትና አንድም ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊጎናጸፍ የሚችለው ከክልሉ ወጣ ብሎ ማሰብ ሲችልና፣ ከሌላው ጋር በተለያዩ መልኮች ግኑኝነቱን ሲያጠናክር ብቻ ነው። በተጨማሪም ግለሰብአዊ ፍላጎቶች ሊሟሉና እያደጉ ሊሄዱ የሚችሉት አንድ አገር በቴክኖሎጂ እየመነጠቀች ስትሄድ ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ ሂደት ግለሰብአዊ ነፃነትን የሚፃረር ቢመስልም፣ ማንኛውም ግለሰብ ዕውነተኛ ፍላጎቱን ሊያረካ የሚችለው እንደ ሮቢንሰን ክሩሶ በደሴት ላይ ብቻ በመኖርና በመታገል ሳይሆን፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በተቀናጀ፣ ይሁንና ደግሞ ነፃነትን በማያፍን ህብረተሰብ ውስጥ ነው። ከዚህ አንፃር ነው እነ ላይብኒዝ ሲያስጠነቅቁ የነበረው። በኢምፔሪሲዝምና በነፃ ገበያ ስም ተሳቦ የሚሰበከው ነፃነት የመጨረሻ መጨረሻ ግለሰቦችን ወደ ርስ በርስ ጦርነት እንዲያመሩ የሚያደርግ፣ ወይም ደግሞ ዛሬ እንድምናየው ዓለም ጥቂት ኃይሎች የራሴ ጥቅም ተደፈረብን በማለት አገር የሚያተራምሱበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው በመስጋት ነው የእንግሊዝ ፈላስፎችን አስተሳሰብ አጥብቀው ይዋጉ የነበረው። የእነ አዳም ስሚዙ የነፃ ገበያ አሰተሳሰብና የነፃነት ትርጉም በጥቂት ኃይሎችና ፍላጎት በፎርማል ደረጃ የሚታይና የሚገለጽ ሲሆን፣ በመሰረቱ የሩሶንና የካንትን የነፃነት ትርጉም ወይም አስተሳሰብ የሚቃወም ነው። ምክንያቱም በግል ሀብት አማካይነት የናጠጡ ኃይሎች ከመንግስት መኪና ጋር በመቆላለፍ በነፃነት ስም ሌላውን የነሱ ተገዢና በነሱ ፈቃድ ብቻ እንዲተዳደሩ ስለሚያደርጉ ነው። እዚህ ላይ የግል ሀብትን ለመቃውም ሳይሆን፣ ቁጥጥር የማይደረግበት የሀብት ማጋፈፍ የግዴታ ስላምን ያሳጣል። በሀብት የናጠጡ ለሌላው ደንታ ስለማይኖራቸው ጦርነትን ይናፍቃሉ። መንፈሳቸው ባካበቱት ኃይል ስለሚሸፈን ጦርነት ቢቀሰቀስ እነሱ ከጦርነት የሚድኑ ይመስላቸዋል። ስለዚህም ነው የጀርመኑ ሰብአዊነት ከተደመሰሰ በኋላ በአስራስምንተኛውና በአስራዘጠናኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ብቅ ያሉት አዳዲስ የጀርመን ምሁራን የእንግሊዙን ልቅ የነፃ ገበያ ስልት በመቃወም ህብረተሰብአዊና ማህበረሰብአዊ ኃላፊነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አጥብቀው ይታገሉና ያሳስቡ የነበረው።

የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ አስተሳሰብ በአሸናፊነት ከወጣ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በዚያው መጠንም የኃይል አሰላለፍ ይለወጣል። የሀብት ቁጥጥርና ክፍፍልም ልዩ መልክ እየያዘ ይመጣል። በካፒታሊስት ህብረተሰብ ውስጥ ሁሉም በዕኩልነት ደረጃ ሀብት መቆጣጠር የማይችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። ስለዚህም ህግና የህግ የበላይነት ከዚህ አዲስ የህብረተሰብ ግኑኝነት አንፃር የሚነደፉ ሆኑ። ቀስ በቀስ የተገነባውን የኃይል አሰላለፍ የሚያረጋግጡ ናቸው ማለት ነው። የገበያ ኢኮኖሚና የነፃ ንግድ ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚሰበክባቸው መሳሪያዎች ወደ መሆን አመሩ። ማንኛውም ግለሰብ በነፃ ገበያ አማካይነት ብቻ ዕውነተኛው ነፃነቱን የሚቀዳጅ ነው በሚል በከፍተኛ ደረጃ መሰበክ ተጀመረ። ይሁንና ይህ ዐይነቱ የነፃ ገበያ በጥቂት ካፒታሊስቶች ቁጥጥር ስር ያለና፣ ማንኛውም ግለሰብ የራሱንም ቢሆን ጥቂት መጦሪያ እንኳ እንዳያዳብር የሚያግድ ነው። በተለይም የፊናንስ ካፒታሊዝም እያደገ ሲመጣ፣ ጥቂቱ ብቻ የብድር ዕድል በማግኘት አብዛኛውን የህዝብ ሀብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ መፈጠር ቻለ። እንደመሬት የመሳሰሉትም የተፈጥሮ ሀብቶች ወደ ሸቀጣ ሸቀጥነት በመለወጥ ጥቂት ግለሰቦች፣ ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚቆጣጠሩበት ሁኔታ ተመቻቸ። እንደዚህ ዐይነቱን የግል-ሀብት ዘረፋና ድህነትን የሚያስፋፋ ፖሊሲን የሚቃወም በክፉ ዐይን የሚታይና ለክፉ አደጋ የሚጋለጥ ሆነ። በዚህ መልክ የነፃነት ትርጉም በካፒታሊዝም የቴክኖሎጂና የሳይንስ ዕድገት፣ እንዲሁም የሀብት ክምችት ዘዴ በመጣመም፣ ሰፊው ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የማይችልበት ሁኔታ ተፈጠረ።

ካፒታሊዝም ለመጨረሻ ጊዜ የበላይነትን ከተቀዳጀ ከ19ኛው ክፍለዝ-ዘመን ጀምሮ በነፃ ገበያ ስም የተሰበከው ነፃነትን መቀዳጀት ተግባራዊ እንዳልሆነ በዘመኑ የተደረገውን ካፒታሊዝምን የሚጻረር ትግል መመልከቱ ይበቃል። በኢንዱስትሪ አብዮት አማካይነት ከእርሻ መሬት እየተፈናቀለ ስራ ለመፈለግ ሲል ወደ ዋና ከተማዎች እንዲፈልስ የተደረገው ጉልበቱን ከመሽጥ በስተቀር ሌላ ነፃነት እንዳልነበረው በዚህ አካባቢ የተጻፉ አያሌ መጽሀፎች ያረጋግጣሉ። ሰፊው ስራ ፈላጊ ህዝብ እንደ ቆሻሻ የሚታይና በየመንገዱ ላይ የሚያድርና፣ ከመንገድ ላይ ምግብን እየፈለገ የሚመገብ ነበር። በየፋብሪካው ተቀጥሮ የሚሰራው ሰራተኛ ደግሞ ለአሰሪው ታዛዥ ከመሆን በስተቀር በሙያ ማሀበር የመደራጀት መብት እለነበረውም። እጅግ በሚያሰለች መልክ ከማሽን ጋር እየታገለ ከማምረት በስተቀር ብሶቱንና ፍላጎቱን የመግለጽ መብት አልነበረውም። እንደዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ሰፍኖ ይገኝ የነበረው ከሶስት መቶ ዐመት በፊት የሰውን ጭንቅላት የሚያድስ የባህል አብዮት ከተካሄደና፣ በተከታዩ ደግሞ ኤላይንተሜንት የተባለው በሞናርኪዎች ፍጽም አገዛዝ ላይ የተነሳው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ብዙ የአውሮፓ አገሮችን ካዳረሰ በኋላ ነው።

በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ካፒታሊዝም በማያወላውል መልክ የበላይነትነትን ሲቀዳጅ የሰው ልጅ ነፃነት በፍጆታ ግዢና ጥቅምን ከማሳደግ አንፃር ብቻ የሚታይ ሆነ። ማንኛውም ግለሰብ በገበያ ፊት ቢያንስ በፎርማል ደረጃ ነፃ ሆኖ የሚታይ ሆነ። ይህም ማለት ነፃንቱ ሊወሰን የሚችለው ባለው የመግዛት ኃይል(Effective demand) ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር የነፃ ገበያ እዚያው በዚያው የማግለል ባህርይም አለው ማለት ነው። በዚህ መልክ ካፒታሊዝም በአገር ደረጃ መወሰኑን ሲያቆምና ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ሲወስድ በትምህርት ደረጃ የኢኮኖሚክስ ትምህርት የሰውን ልጅ የነፃነት ትርጉም በዚህ የአስተሳሰብ ክልል ብቻ እንዲወድቅ አደረገ። በንግድ አማካይነት ሁሉም አገሮች የሚተሳሰሩበት ሁኔታ ተፈጠረ። በማምረት አማካይነት ሳይሆን አንድ ህብረተሰብ የሚሻሻለው በንግድ አማካይነት ከሌላው ዓለም ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ነው የሚለው በሰፊው መሰበክ ተጀመረ።

በአስራሰባተኛውና በአስራምንተኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ያሉት የእንግሊዝ ፈላስፎችና የነፃ ገበያ አራማጆች እዚያ በዚያው የቅኝ ግዛት አራማጆች የነበሩ ያዋቀሩት እንደ ኢስት- ኢንዲያን ካምፓኒ(East Indian Company) የመሳሰሉት አዲስ በተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ ግኑኝነት ልዩ አወቃቀር በመያዝ ዛሬ የሶስተኛው ዓለም ተብለው የሚጠሩ አገሮችን ወደ ተራ ጥሬ-ሀብት አምራችነት መለወጥ ቻሉ። የነፃነት ትርጉምም በዚህ የንግድ እንቅስቃሴ ክልል ውስጥ የሚታይ ሆነ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ቀደም ብለው የተዋቀሩ የስራ-ክፍፍሎችና የህብረተሰብ አወቃቀሮች እንዲጨናገፉ በመደረግ ቀስ በቀስ እያለ በማደግ ላይ ባለው ግሎባል ካፒታሊዝም መዳፍ ስር እንዲወድቁ የተደረገው። ልክ ሩሶና ካንት እንዳስተማሩን አንድ ሰው የሌላው ጥገኛና ታዛዥ ከሆነ ነፃነቱን ተገፈፈ ማለት ነው ብለው እንዳስተማሩን፣ በግሎባል ካፒታሊዝም ስር የተዋቀረው ዓለም አቀፋዊ ንግድ በብዙ ሚሊዮን የሚጠጉ የሶስተኛውን ዓለም አገር ህዝቦች ወደ ባርነት ለወጣቸው። ይህም ማለት አንድ ሰው ወደ ተራ አምራችነት ከተለወጠ እግዚአብሔር የሰጠውን የመፍጠር ኃይል ተነጠቀ ማለት ነው። ባርያ ሆነ ማለት ነው። በማሰብ ኃይሉ ልዩ ልዩ ነገሮችን በመፍጠርና በማምረት ፍላጎቱን አሟልቶ ወደ ህብረተሰብ ኃይል ሊሸጋገር አይቸልም። ነፃ አገር ሊመሰርት አይችልም። ከዚህ በመነሳት ነው በኛና በተቀሩት የሶስተኛው ዓለም አገሮች ሊኖር የሚገባውን የነፃነት ትርጉም ምንነት መረዳት የምንችለው። በሌላ አነጋገር አገዛዞች ቢለዋወጡም አንኳ፣ ይህ ዐይነቱ ዕውነተኛ ነፃነትን የሚያፍን የስራ-ክፍፍልና የነፃ ንግድ የሚለው አስተሳሰብ እስካለተናጋና መሰረታዊ የአስተሳሰብና የአመራረት ለውጥ እስካልተካሄደና ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ፣ ነፃነት ያስፈልጋል የሚለው አባባል ለአብዛኛው ህዝብ ትርጉም አይኖረውም ማለት ነው።

ያም ሆነ ይህ ለግለሰብአዊም ሆነ ለህብረተሰብአዊ ነፃነት የተደረገው ትግል በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ከአጠቃላዩ የህብረተሰብ አወቃቀር ጋር የተያያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የተዋቀረው መንግስታዊ መኪና፣ የምርት ግኑኝነት፣ ባህላዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጉዳዮች፣ የጠቅላላው የህዝቡ አኗኗር ጉዳይ፣ መንግስትና አገዛዙ ዕድገትንና ስልጣኔን በሚመለከት ያላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ፣ … ወዘተ.፣ እነዚህና ሌሎችንም፣ ለአንድ ግለሰብም ሆነ ለጠቅላላው ህብረተሰብ ዕድገት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን የመመርመሩና እነዚህን የመታገሉ ጉዳይ የነፃነት ትግል መሰረታዊ ሃሳቦች ናቸው። በሌላ ወገን ደግሞ ለነፃነትና ለነፃ ሃሳብ እንታገላለን የሚሉ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ከአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚፈልቁ ሲሆን፣ ከነበረው ለዕድገትና ለስልጣኔ ከማያመች ሁኔታ ቀድመው የሄዱና፣ የአንድም ህብረተሰብ ዕድል በእንደዚህ ባለ የጨለማና የተዝረከረከ ኑሮ መወሰን እንደሌለበት የተረዱ ናቸው። ይህም ማለት ጭንቅላታቸውን ሙሉ በሙሉ ከፊዩዳላዊ ወይም ከኋላ-ቀር አስተሳሰብ ያጸዱ ሲሆን፣ የነፃነትን መሰረታዊ ሃሳብ በፍልስፍናና በቲዎሪ መሳሪያ በሰፊው እያብራሩ ማስተማር የሚችሉ ናቸው። በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ለግለሰብአዊና ለህብረተሰብአዊ ነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት በመጀመሪያ ደረጃ በጠብመንጃና በመጋፈጥ የተደረገ ትግል ሳይሆን በከፍተኛ የጭንቅላት ምርምር፣ አርቆ-አስተዋይነትን(Rationality)፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን(Awareness)፣ የሌላውን ሰው የኑሮ ሁኔታ መሰማትንና(Feeling) ሌሎችንም ነገሮችን ያካተተ የትግል ዘዴ ነው። እንደዚህ ዐይነቱ የትግል ዘዴ በየኤፖኩ መልኩን ይለዋውጥ እንጂ፣ የመጨረሻ መጨረሻ ዋናው ዓላማው አንድን ህብረተሰብ ወይም ህዝብ የማንም ተገዢ እንዳልሆነና፣ ማንኛውም ግለሰብ የራሱን ዕድል በራሱ መወሰን እንዳለበት ለማስጨበት ሲሆን፣ በዚህም አማካይነት ታሪክን ሰርቶ በስምምነትና በሰላም እንዲኖር ለማድረግ ነው። እንደዛሬው በጊዜው የነበረው ግንዛቤ የሰላምና የነፃነት ጠንቅ የሚሆኑ ስልጣንን የጨበጡና በሀብታቸው የሚመኩ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ኃይሎች የማሰብ ኃይላቸውን መጠቀም ስለማይችሉና ሀብት ካላቸው ጋር በጥቅም ስለሚተሳሰሩ አንድ ህዝብ ነፃነቱን እንዳያገኝ የተለያየ ዘዴ በመፍጠር ፍዳውን ያሳዩታል። በዚህም ምክንያት የተነሳ የዕድገት እንቅፋት በመሆን አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ድህነት ውስጥ እንዲኖር ያደርጋሉ። በአንድ አገር ውስጥ የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖርም እንኳ ሰፊው ህዝብ እነሱን በስነስርዓት አውጥቶ ቅርጽ በመሰጠትና በመለወጥ አዲስ ህይወት እንዳይገነባ ያግዱታል። ኑሮው ሁሉ እንዲጨልም ያደርጋሉ። ስለሆነም ነው በአውሮፓ ምድር ውስጥ በፍልስፋናና በሳይንስ አማካይነት ህብረተሰቡን ነፃ ለማውጣት እልክ ያስጨረሰ ትግል የተካሄደው። ትግሉን የጀመሩት ደግሞ ተራ ሰዎች ወይም ቃልን በመወርወር በሚዝናኑ ሰዎች ሳይሆን፣ ልክ ከእግዚአብሄር የተላኩ ይመስል የራሳቸውን ህይወት በመሰዋት አንድን ህዝብ ከጨለማ ኑሮ ማውጣት አለብን ብለው ቆርጠው በተነሱ ሰዎች ነው። ሶክራትስን እግዚአብሄር ከሰማይ ዱብ አድርጎ የላከው ፍጡር ነው ማለት ይቻላል። ሌሎችም እንደ ፕላቶንና አርስቴቶለስ፣ እንዲሁም አያሌ የግሪክ ፈላስፋዎች፣ የሳይንስና የድራማ ስዎች እንደዚሁ ልዩ ፍጡሮች ናቸው። የኋላ ኋላም ብቅ ያሉት፣ እንደ ቄስ ኩዛኑስ፣ ዳንቴ፣ ዳቪንቺ፣ ጋሊልዮ፣ ኬፕለር፣ ላይብኒዚ፣ ሺለርና ካንት፣ እንዲሁም ሌሎችም እነሱን የመሳሰሉት የጀርመን አይዲያሊስቶች ዕንቁ ጭንቅላት የነበራቸውና ከተንኮል አስተሳሰብም የጸዱ ሲሆን፣ ዕውቀታቸውም ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ያለው ነው። ስለሆነም ነው የአውሮፓ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብ በጠቅላላው ከጨለማ በመላቀቅ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እርስ በርሱ መገናኘት የቻለው።

ከዚህ ዐይነቱ የተወሳሰበና ከፍተኛ የጭንቅላት ምርምርን ከሚጠይቅ ትግል የምንገነዘበው ሀቅ፣ አንድ ሰው ነፃነት የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ ከመወርወሩ በፊት ራሱ የቱን ያህል ነፃ እንደወጣ ማሳየት መቻል አለበት። በሌላ አነጋገር ጭንቅላቱ ከማንኛውም እቡይ አስተሳሰቦች የጸዳና፣ የአንድን ህብረተሰብ አስቸጋሪ ሂደት የተረዳና፣ ይህንንም በጥሩ የቲዎሪና የፍልስፍና መነጽር መመርመር የሚችል መሆን አለበት። በበሁለተኛ ደረጃ፣ ዕውነተኛ ነፃነት በጉልበት ወይም በጠብመንጃ የማይገኝ መሆኑን የተገነዘበ መሆን አለበት። ይሁንና ግን አንድ አገዛዝ ወደ ቲራንነት ከተለወጠና ከፍተኛ በደል የሚፈጽም ከሆነ ለዚህ ጸሀፊ አመጻዊ ትግል አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባል። አንድ አገዛዝ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስዎችን ቀርቶ አንድን ሰው እንኳ የመግደል መብት የለውም። ከዚህም በላይ አንድ አገዛዝ ቆርጦ በመነሳት ዕድገትን የሚቀናቀን ከሆነ የግዴታ አመጻዊ ትግል ከፍልስፍናና ከቴዎሪ ጋር እየተጋዘ ተግባራዊ መሆን አለበት። በሶስተኛ ደረጃ፣ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የመጨረሻ መጨረሻ አንድን ህዝብ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት የሚያደርገው መሆን አለበት። በዚህም አማካይነት አንድ ህዝብ ጥበባዊ አገር ለመመስረት ወይም ለመገንባት መቻል አለበት። በሌላ አነጋገር፣ የአንድ አገር ህዝብ ኑሮ በቆንጆ ከተማዎችና፣ በቆንጆ መንደሮች የሚገለጽ መሆን አለበት። በባህላዊ ዕድገት የሚታይ መሆን አለበት። አንድ ህዝብ ከልማዳዊ ኑሮ ተላቆ ህይወቱን በአዲስ መልክ ማደራጀት መቻል አለበት። በአራተኛ ደረጃ፣ ዕውነተኛ ነፃነት አንድን ህዝብ የስልጣን ባለቤት(Empower) የሚያደርገው መሆን አለበት። ይህ ሲሆን ብቻና፣ በየጊዜው እየነቃ ሲሄድ አንድ ህዝብ በእርግጥም ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ ይችላል።

ወደ አገራችን ስንመጣ እስካሁን ድረስ ለነፃነት የተደረገው ትግል ግቡን መምታት ያልቻለው ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረተ-ሃሳቦች ማሟላት ባለመቻሉ ነው። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በአጠቃላይና፣ ብሄረሰቦች በተናጠል በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ በስዕል፣ በድራማ፣ በአርክቴከቸርና በከተማ ግንባታ፣ በዕደ-ጥበብ ሙያና በንግድ እንቅስቃሴ የሚገለጽ ምሁራዊ እንቅስቃሴ አልነበራቸውም። ህብረተሰባችንም የተገለጻለቸው ምሁሮችን የማፍራት ዕድል አልነበረውም። በዚህም ምክንያት የተነሳ አገዛዞችንና ልማዳዊ የአኗኗር ስልትን የሚጋፈጥና ሌላ የዕድገት አቅጣጫን ሊያሳይ የሚችል ወይንም አዲስ የህይወት ብርሃንን ሊያፈናጥቅ የሚችል ኃይል ሊፈጠር አልቻለም። ስለሆነም ህዝባችን የተፈጥሮን ምንነት ተገንዝቦ ወደ ተወሳሰበ የህብረተሰብ ግንባታ ለመጓዝ የሚያስችል መንፈሳዊ ኃይልን ሊቀዳጅና ኑሮውን በአዲስ መልክ ሊያደራጅ አልቻለም። የጠቅላላው ህዝብ ኑሮ ተደጋጋሚና የዘልማዳዊ ኑሮ በመሆኑ ለፈጠራ አያመችም ነበር። በዚህም ምክንያትና በሌሎች አያሌ ምክንያቶች የተነሳ የነፃነትን ትርጉም ተረድቶ በከፍተኛ እምርታ ሊታገል የሚችል ኃይል ብቅ ሊል አልቻለም። አብዛኛውን ጊዜ ባለማወቅ የተነሳ የተዋቀረው ጠቅላላው ስርዓትና ከዚህ የፈለቀው አስተሳሰብ በራሳቸው የነፃነት ተቀናቃኝ በመሆናቸው በቴክኖሎጂና በልዩ ልዩ ነገሮች ሊገለጽ የሚችል ዕድገት ሊታይ አልቻለም።

በአለፉት ሃምሳ ዐመታት ለዲሞክራሲና ለነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት፣ ይደረግ የነበረው ትግል ጠቅላላውን ህብረተሰብአዊ አወቃቀርና የህዝቡን የአስተሳሰብ መነሻ አድርጎ ከመመርመር ይልቅ በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ በማትኮር ነበር። በአገራችን የተለመደ አንድ አነጋገር አለ። ለዕድገት ጠንቅ የሆኑት አገዛዙና ስርዓቱ ናቸው የሚል ተራ አባባል አለ። በሌላ በኩል ግን ለምን አገዛዙና ስርዓቱ ለዕድገት ጠንቅ ሆኑ? ተብሎ ጥያቄ አይቀርብም። በማወቅ ወይስ ባለማወቅ ? የዕድገት እንቅፋት ሊሆኑ ቻሉ ብሎ ነገሩን ዘርዘር አድርጎ ለመጠየቅ ሙከራ አይደረገም። እንደሚታወቀው አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ ያሉ ለዕድገት ጠንቅ የሆኑ ፊዩዳላዊ ስርዓትን የመሳሰሉት የሚዋቀሩት በማወቅ አይደለም። ህብረተሰቦች በጨቅላ ዘመን በሚገኙበት ወቅት እንደዚህ ዐይነት ዕድገትንና ስልጣኔን የሚቀናቀኑ በተለያየ መልክ የሚገለጹ የአሰራርና የአመራረት ስልቶች መፈጠራቸው እንደተፈጥሮአዊ ሆነው የሚታዩ ናቸው። ጭቆናዎች ሲበዙና የህዝቡም ኑሮ ባለበት የረጋ ከሆነ ይህ ዐይነቱ ሂደት ትክክል ሆኖ የማይታያቸው ምሁራን ከመቅጽበት ፍልቅ የሚሉበት ጊዜና ቀስ በቀስም አስተሳሰባቸውን በማዳበርና በማስፋፋት ስርዓቱን የሚጋፈጡበት ጊዜ አለ። ይህ ዐይነቱ የመመራመርና የመጋፈጥ ባህል ወይም ልምድ ወይም ደግሞ ደቀ-መዝሙሮችን የማፍራት ባህል ባልተለመደበት አገር ህብረተሰቦች ባሉበት ረግጠው እንዲቀሩ ይገደዳሉ። በዚህም ምክንያት ነው የኢትዮጵያው ፊዩዳላዊ ስርዓት በተለይም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ግዛት ለስምንት መቶ ዐመታት ያህል ተንሰራፍቶ መቆየት የቻለው።

የተማሪው እንቅስቃሴ የፊዩዳሉ ስርዓት፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ከቢሮክራሲ ካፒታሊዝምና ከኢምፔሪያሊዝም ጋር በመቆላለፍ ለዕድገት ተቀናቃኝ ነው ብሎ ውሳኔ ላይ ሲደርስ፣ በእኔ ዕምነት በተለይም ስርዓቱ ለምን እንደ አውሮፓው ፊዩዳሊዝም ውስጣዊ ኃይል አግኝቶ ሊዋጋው የሚችል ውስጣዊ ኃይል ሊያፈልቅ አልቻለም? ብሎ ጠለቅ አድርጎ በመመራመር በሰፊ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሊጋፈጠው አልቻለም። ስርዓቱን ሊቀናቀን የሚችል ውስጣዊ-ኃይል ሊፈልቅና ሊዳብር የሚችለው እንደሚታወቀው እያደገ ሊሄድ የሚችል የስራ-ክፍፍልና የንግድ እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ነው። በተጨማሪም ከተማዎችና መንደሮች ሲቆረቆሩና ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ(Social Mobility) ስርዓቱን የሚቀናቁኑ የተገለጸላቸው አዳዲስ ኃይሎች ብቅ ይላሉ። እንደሚታወቀውና ማርክስም እንደሚተነትነው ካፒታሊዝም ከማደጉና የበላይነትን ከመቀዳጀቱ በፊት ቅድመ-ሁኔታዎች የተጣሉት በፊዩዳላዊ ስርዓት ውስጥ ነው። በእኔ ዕምነት የተማሪው እንቅስቃሴ ይህንን ያልተገነዘበ ብቻ ሳይሆን፣ በአውሮፓ ምድር ውስጥ በሬናሳንስ፣ በሪፍርሜሽን፣ በኢንላይተንሜንትና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ በትራንፎርሜሽን ዙሪያና በዘመናዊነት አካባቢ የተደረገውን ሰፋ ያለ ክርክር ጋር በበቂው የተለማመደ ባለመሆኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ሰፋ ያለውን የዕድገትና የስልጣኔ ጥያቄ ቀነስ አድርጎ እንዲመለከተው ተገደደ። በመሆኑም ሶስት መፈክሮች ይዞ ሲነሳ በዚህ አማካይነት ብቻ ህብረተሰብአዊ ለውጥን እንደሚያመጣ ነበር የተገነዘበው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ የተማሪው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ውጤት በመሆኑኗ፣ በተለያየ መልክ በሚገለጽ ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ጋር የተለማመደ ስላልነበር የግዴታ አመለካከቱ ውስን እንዲሆን አስገደደው። እየተከማቸ የመጣውን ችግር አገዛዙ መፍታት ሳይችልና፣ እንደመሬትና የብሄረሰብ የመሳሰሉት ጥያቄዎች እንደ መሰረታዊ አጀንዳዎች ሆነው ሲታዩ፣ በተለይም በአመራር ደረጃ ያለው የበለጠ ራዲካል እየሆነ መጣ። ይህ ኃይል የደመደመው አገዛዙን በመሳሪያ ታግዞ ከመጣል በስተቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለ ነበር ታየው። በሌላ ወገን ደግሞ የአገራችንም ሆነ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የቅኝ አገዛዝንም ሆነ ቀጥተኛ ወረራን ለመዋጋት የጦፈ ትግል ይካሄድ ስለነበር ሁኔታዎቹ ሰፋ ካለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ይልቅ ለመሳሪያ ትግል የሚጋብዙ ነበሩ። መስረታዊ ችግር ይህ ቢሆንም፣ አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ የተፈጠረው የዚህ ዐይነቱ ግልጽ ያልሆነና ተወዳዳሪ ያጣው የተማሪው እንቅስቃሴ ያስከተለው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ኃይልን አስተባብሮ በጋራ ለመታገል አንዳይቻል ሁኔታውን አበላሸው። በመሆኑም ሰፋ ባለ የጭንቅላት ተሃድሶ ጉዞ ውስጥ ማለፍ ያልቻለው ወይም ዕድል ያላገኘው የተማሪው እንቅስቃሴ እንደሶቭየት ህብረትና ቻይና፣ በኋላ ደግሞ እንደ ቬትናም ቢያንስ ኃይሉን በማስተባበርና የአስተሳሰብ ጥራት በማዳበር አዲስ አገርና ህብረተሰብ መገንባት አልቻለም። ከብሄራዊና ከስልጣኔ አጀንዳ ይልቅ ስልጣንን ለመጨበጥ በመሽቀዳደሙ አገሪቱን በቀላሉ ሊፈታ የማይችል ችግር ውስጥ ከትቶ አለፈ። የኋላ ኋላም ቶሎ ብሎ የርማት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ እልክ ውስጥ በመግባት የፖለቲካውን ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፣ ጠቅላላው የአገሪቱ ሁኔታ እንዲበላሽ የበኩሉን አስተዋፅዖ አደረገ።

ነገሩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፣ በ1917 ዓ.ም እ.አ ሶቭየትህብረት ውስጥ በቦልሺቪኮች የሚመራ ማርክሲስታዊ ሌኒናው ኃይል ስልጣንን ከመቀዳጀቱ በፊት፣ ቀደም ብሎ በታልቁ ፔተርና በታላቋ ካታሪኒ ራሺያ ውስጥ ሰፋ ያለ የዘመናዊነት ፖሊሲ ተካሂዷል። ከተማዎች ተገንብተዋል። በራሽያ ውስጥ ካፒታሊዝም ቀስ በቀስ እያለ ሊዳብር ችሏል። ይህ ዐይነቱ መጠነኛ የሆነ የኢንላይንትሜንት ክንዋኔ በራሺያ ምድር የበሰሉ፣ በተለያየ መልክ ሊገለጹ የሚችሉ ምሁራን ብቅ ሊሉ ችለዋል። እነ ቶልስቶይና ማክሲም ጎርኪ የዚህ ዐይነቱ ሰፋ ያለ የጥገና ለውጥ ውጤቶች ናቸው። በዚያን ወቅት ነው በራሺያ ውስጥ የክላሲካል ሙዚቃ መዳበር የቻለው። እነ ሌኒንና ስታሊን እንዲሁም አያሌ ጠለቅ ያለ የማርክሲስት ኢኮኖሚክስ ዕውቀት ያላቸው እንደ ቡሃሪንና ትሮትስኪ የመሳሰሉት ምሁራን የዚህ ዐይነቱ ከበርቴያዊ የጥገና ለውጥ ውጤቶች ናቸው። ስለሆነም እነ ሌኒን በ1917 ዓ.ም ስልጣን ሲጨብጡ የጀርመን ወረራ ካደረሰባቸው ኢኮኖሚያዊ መንኮታኮትና የህዝብ ዕልቂት በመላቀቅ ቀስ በቀስ ወደ ኢንዱስትሪ ፖለቲካ ለመራመድ የቻሉት የተወሰነ መሰረት ስለነበራቸው ነው። ስታሊን የሰራውን ትልቅ ወንጀል ወደ ኋላ ትተን፣ ከፍተኛ የሆነ የእንዱስትሪ ተከላና እንቅስቅቃሴ መታየት የጀመረው በ1930ዎች ገደማ ነው። ስለሆነም ሂትለር ሶቭየትህብረትን ከወረረና ብዙ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ታንኮች በማምረትና በማሰማራት የሂትለርን ወራሪ ጦር መደመሰስ ተቻለ። ይህም የሚያሳየው፣ 1ኛ፟) የዕውቀትን ሁኔታ ነው፣ 2ኛ) የአደረጃጀትን ጉዳይ ነው። 3ኛ) የዲሲፕሊን ጉዳይ ነው። 4ኛ) የመተባበርንና ለአንድ ዓላማ ቆርጦ መነሳትን ነው። እነስታሊን ከጦርነቱ በድል ከወጡ በኋላ ትላልቅ ከተሞችን መልሰው መገንባት የቻሉት ባላቸው ዕውቀትና ዲሲፕሊን የተነሳ ነው። ከዚያም በኋላ ሶቭየትህብረት የአቶም ኃይል መሆን የቻለችውና ከአሜሪካ ቀድማ ሰውን ወደ ህዋ መላክ የቻለቸው ባላት ምሁራዊ ኃይልና ቆራጥነት ነው። ወደኛ ስንመጣ ግን ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ በመሆን በአንድ አገር ውስጥ ከአስር በላይ የሚሆኑ የጦር እንቅስቃሴዎችና የከተማ የደፈጣ ተዋጊዮች በመፈጠር ህብረተሰቡን ማዋከብ ጀመሩ። ብዙ ሺህ ወጣቶችና ምሁራኖችን እንዲገደሉ አደረጉ። ይህም የሚያመለክተው በጊዜው የነበረውን የተማሪውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የማሰብ ኃይል ድክመት ነው። ሁኔታዎችን አለማጤን፣ የሃሳብ ጥራት አለማዳበር፣ በዲሲፒሊን አለመገዛት፣ ለመተባበር አለመዘጋጀት፣ ሁሉም በየፊናው በመሆን ለስልጣን መታገልና፣ የሚቀናቀነውን መግደል፣ ሰፋ ባለ ዕውቀት ላይ በመመርኮዝ ጠንካራ ድርጅትን አለመመስረት፣ ለግልጽ ዓላማ ከመታገል ይልቅ በህቡዕ በመታገል አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ዲሞክራሲያዊ ቶለራንስን ከማስቀደም ይልቅ፣ ከሚቀድመኝ በፊት ልቅደማቸው በማለት ሁኔታዎችን የባሰውኑ ማዘበራረቅ፣ … ወዘተ. እነዚህና አያሌ ምክንያቶች ተደራርበው በታሪክ ውስጥ ያልታየ የደም መፋሰስና እስከዛሬ ድረስ አልላቀቅ ያለ የቂም በቀል ቁስል በጭንቅላት ውስጥ በመተከል ህዝባችንን ፍዳውን እንዲያይ የተደረገው የህብረተሰብን ህግና በጊዜው የነበረውን አስተሳሰብ ካለመገንዘብ የተነሳ ነው። በአርቆ-አሳቢነትና በምርምር ከመመራት ይልቅ በስሜት ብቻ በመመራቱ በቀላሉ ሊፋቅ የማይችል ቁስል ተጥሎ ታለፈ። ይህንን የማትተው የተማሪውን እንቅስቃሴ ለመወንጀል ሳይሆን ምሁራዊ እንቅስቃሴን ባልለመደና የመንፈስ ተሃድሶን ባለተጎናጸፈ ህብረተሰብ ውስጥ የተፈጠረን ችግር ለማሳየት ብቻ ነው። ይሁንና ግን አሁንም ቢሆን አስቸጋሪው ጉዳያችን ይህንን ድክመታችንና የተሰራውን ከፈተኛ ስህተት አለመገንዘቡ ወደፊት እንዳንጓዝ አድርጎናል ማለት ይቻላል።

ወደ ቻይናም ስንመጣ ልክ እንደሶቭየትህብረት እንኳ ባይሆንም የኦፕየም ጦርነትና በኋላ ደግሞ በጃፓኖች በመወረር ፍዳዋን የምታይ አገር ነበርች። የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አድሃሪ ከሚላቸው ኃይሎች ጋር በመተባበር የጃፓንን ኢምፔሪያሊዝም ካባረረ በኋላ በጊዜው አምስት መቶ ሚሊዮንን የሚጠጋ ህዝብ በማደራጀት ነው ወደ አገር ግንባታ ማምራት የቻሉት። ቻይና እንደ ሶቭየትህብረት መለስተኛ የከበርቴው አብዮት የተካሄደበት አገር ባትሆንም፣ ለብዙ ሺህ ዐመታት የዳበረው ድርጅታዊና ቢሮክራሲያዊ አገዛዝ፣ እንዲሁም ደግሞ የቻይና በቴኮኖሎጂ መዳበርና ለመንፈስ መዳበር የሚያግዝ የራሷ ፍልስፍና ስለነበራት ስልጣን ከተያዘ በኋላ ህዝቡን አደራጅቶ አገር መገንባቱ ከባድ አልነበረም”። ይህም የሚያመለክተው አንድ የሚሰማና በዲሲፕሊን የታነፀና እንዲሁም ለመተባበርና ለመቻቻል ዝግጁ የሚሆን ኃይል ካለ አገር መገንባቱ ከባድ አይሆንም። ከዚህ ስንነሳ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በዚህ የታደለ አይደለም። ህብረተሰቡ ተንኮለኞችንና አመጸኞችን እንዲሁም አገር አፍራሾችን የማያመርት ነው የሚመስለው። እዚያው በዚያው ደግሞ ኩራትና አጉል ጉራ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል መለዮች እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል።

ሰለሆነም፣ ስለነፃነት በሚወራበት ጊዜ ብዙ የምናነሳቸው ነገሮች አሉ። ራሳችንንም መጥየቁ አጅግ አስፈላጊ ነው። አንዱ በሌላው ላይ ለማላከክ የሚፈልግ ከሆነና፣ በግልጽ ለመወያየት ዝግጁ እስካልተሆነ ድረስና፣ ትችትንም መሰንዘር እንደ ስድብ ተቆጠሮ የሚታይ ከሆነ በፍጹም አንድ እርምጃ እንኳ መራመድ አይቻልም። ትችት እንደ ነጹህ አየር ወይም ምግብ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። ትችት ወደ ስድብ የሚቆጥር ሳይሆን፣ ትችት ተፈጥሮአዊ ግዴታና ለአንድ ህብረተሰብ ዕድገት አስፈላጊ ሆኖ መወሰድ ያለበት ጉዳይ ነው። ስለሆነም ትችት የቲዎሪ፣ የፍልስፍናና የሳይንስ አካል ነው። በዚህም ምክንያት ነው በአውሮፓ ምድር ውስጥ ዕውቀት ሊስፋፋ የቻለው። አያሌ ሊትሬቸሮችን ላገላበጠ የሚረዳው አንደኛው ምሁር ተፈጥሮንና የተፈጥሮን ምንነት በአንድ ዐይነት ሊገልጽ ሲሞክር፣ ሌላው ደግሞ በዚህ መልክ ሊገለጽ አይችልም በማለት የሱን አሰተያየት ያዳብራል። በዚህ ዐይነት ትችታዊ አመለካከትና ነገሮችን መረዳት ህብረተሰብአዊ ዕድገት ሊመጣ ይችላል። ህብረተሰብአዊ ትችት እንደ ጦር በሚፈራበት አገርና፣ አንድ ምሁር እንደ እግዚአብሄር በሚታይበት አገር ዕድገትና ስልጣኔ በምንም ዐይነት ሊመጡ አይችሉም።
አብዮት ተካሂዱል በሚባልበት አገር አሁንም ቢሆን እንዲያውም ከፊዩዳሉ ኢትዮጵያ በባሰ ሁኔታ ዛሬ ሃሳብ እንዳይዳብር ሁሉ ነገ ተቆልፎ ተይዟል። ትችታዊ ሃሳብን ማዳበር አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። አገዛዙ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን የሚሉ ግለሰቦችም አምባገነናዊ ባህርይን ያሳያሉ። ለነሱ የመደንገግ መብት የተሰጣቸውው ይመስል አንድ አዲስ ሃሳብ ሲሰነዘር ቶሎ ብሎ ለማፈን ይሞክራል። ሌላው ደግሞ ለመማታት ይቃጣል። አንዳንዱ ደግሞ ወደ መናቅ ያመራል። እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው ማለት ነው። ከዚህ ዐይነቱ በሽታ ለመላቀቅ የግዴታ የጭንቅላት ጅምናስቲክ መስራትና ቴራፒ ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ልክ ሰውነታችንን ሲያመን ለመመርመርና ለመታከም ወደ ሃኪም ቤት እንደምንሄድ ሁሉ ጭንቅላታችንም ምርምር ያስፈልገዋል። የጭንቅላታችን በሽታ ግን ሰውነታችን ላይ እንደሚታየው ወይንም ቁርጠት ሲይዘን እንደሚያጎራብጠንና አላስቀምጠን እንደሚለው ዐይነት የሚገለጽ ሳይሆን፣ የጭንቅላት በሽታ የማይታይ፣ የማይዳሰሰና የማይጨበጥ ነው። ሊታወቅ የሚችለው ግን አንድ ህዝብም ሆነ የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ሁኔታ ማየት ሳይችል ሲቀርና ዝም ብሎ አልፎ ሲሄድ የሚገለጽ በሽታ ነው። ይህንን ውድ ወንድማችን ዶ/ር ምህረት ደበበ „የተቆለፈበት ቁልፍና ሌላ ሰው“ በሚለው ግሩም መጽሀፎቹ ውስጥ አብራርቷል። ከዚህም በላይ የጭንቅላት በሽታ በችኮነት፣ በቂም በቀልነት፣ ተንኮል በመስራት፣ የሰውን ስም በማጥፋት፣ ለትችት ዝግጁ ባለመሆን፣ ለመደባደብ በመነሳት፣ ኃላፊነትን ባለመሰማት፣ በዲሲፕሊን እጦት፣ ለሆነው ላልሆነው በመገዛት አገር ለማጥፋት መዘጋጀት፣ ለስልጣንና ለሀብት መስገብገብ፣ ወንጀል ሰርቶ አልሰራሁም ብሎ መዋሸት፣ የራስን ጥፋት በሌላ ሰው ላይ ማላከክ… ወዘተ. የሚገለጽ የረቀቀ በሽታ ነው። ይህ ሁኔታ ነው ለጦርነት መፈጠር፣ ለሰላም እጦትና ለዕድገት ጠንቅ የሚሆንና፣ ስልጣኔዎችና ታሪክ እንዲፈራርስ የሚያደርገው። ስለዚህም ነው እያንዳንዱ ሰው ራሱን ነፃ ካላወጣ ወይም የጭንቅላት ተሃድሶ(Self Emancipation) እስካላደረገ ድረስ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነትን ሊጎናጸፍና ራሱን በራሱ ማግኘት አይቻልም የሚባለው።

የብሄረሰብና የነፃነት ጥያቄ !!

በአውሮፓው የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪክ ውስጥ የሰውን ልጅ ከጨለማ አውጥቶ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ዕድል ራሱ ወሳኝ ለማድረግ ትግል ሲጀመር ፍልስፍና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ነበሩ ነፃነትን አጎናጻፊ መሳሪያዎች ሆነው የታመነባቸውና፣ እንዲዳብሩና እንዲስፋፉም ርብርቦሽ የተደረገባቸው። በፍልስፍና መሰረተ-ሃሳብ መሰረት፣ ማንኛውም ግለሰብ ከሃይማኖት ወይም ከብሄረሰብ ዕምነት ጋር በመያያዝ የሚወለድ ሳይሆን፣ እንደግለሰብና በእግዚአብሄር አምሳል የሚፈጠር ነው። በተወለደበት አካባቢ ሲያድግ በዚያ ያለውን ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ኖርሞችንና ባህሎችን በመወሰድ ሳያውቀው ይኖርበታል፣ ይለማመደዋል። ይሁንና ማንኛውም ግለሰብ በአስተሳሰቡ ሊያድግና በተወሳሰበ መልክ በማሰብ ፈጣሪ በመሆን ነፃነት የሚሰማው ከተተበተበበት የባህል ሰንሰለት ሲላቀቅ ብቻ ነው። እንደየሁኔታው ባህል ጎታችም ነው፤ ለዕድገትም የሚያመች ነው። አዳዲስ ዕውቀቶች በማይስፋፉበት፣ የስራ-ክፍፍል በማይዳብርበትና፣ አንደኛው የማህበረሰብ ክፍል ከሌላው ጋር በማይገናኝበት ቦታ ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላለፉ ባህል-ነክ ነገሮች ውስጣዊ-ኃይላቸው በጣም ደካማ ነው። የሰውን የማሰብ ኃይል በማፈን እያንዳንዱ ግለሰብ የማሰብ ኃይሉን በመጠቀም የራሱን ዕድልና ህይወት ወሳኝ እንዳይሆን ያደርጉታል። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ባህል ራሱ ውስጠ-ኃይላዊ ክንዋኔ(Dynamic Process) ነው። እስከተወሰነ ደረጃ እስካልሆነ ድረሰ ማንኛውም ማህበረሰብ የራሴን ባህል መጠበቅ አለብኝ ብሎ የሙጥኝ ብሎ እሱን ጠብቆ ሊኖር አይችልም። እንዲዚህ የሚያደረግ ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ የስልጣኔን ብርሃን ሳይጎናፀፍ ያልፋል። በሌላ ወገን ግን በአሁኑ በግሎባል ካፒታሊዝም ዘመን ቀርቶ የሰው ልጅ በስራ-ክፍፍልና በንግድ ልውውጥ አማካይነት መገናኘት ከጀመረ ጀምሮ እየተሳሰረና እየተዳቀለ መጥቷል። በተለይም በአሁኑ በግሎባል ካፒታሊዝም ዘመን ሁላችንም በቴክኖሎጂ አማካይነት በመደገፍ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመንቀሳቀስ ኑሮአችንን ሌላ አገር በመመስረት፣ የአኗኗርና የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተናል። አስተሳሰባችን ክልላዊና አገራዊ መሆኑ ቀርቶ ኮስሞፖሊታን ወይም ዓለም አቀፋዊ ሆኗል። በጋብቻም ከተለያዩ የውጭ አገር ሴቶችም ሆነ ወንዶች ጋር በመጋባት ተቀላቅለናል። ከዚህ ስንነሳ ህይወታችን በክንፈት ዓለም ውስጥ የሚኖር ነው። በአንድ በኩል በአንድ ቦታ ረግተን የምንኖር ብንመስልም ገና ያልተጠናቀቁ ወይም ተግባራዊ ያልሆኑ ህልሞች ስላሉን በሃሳብ ምናልባትም አገራችን ውስጥ ወይም ከመጣንበት ብሄረሰብ ውስጥ ገብተን በሃሳብ እንዋኛለን። ህይወታችን በቅራኔ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ነው ማለት ነው። ስለሆነም፣ በአንድ በኩል በሰለጠነ ዓለም ውስጥ እየኖርን፣ በሌላው ወገን ደግም ወደ ኋላ ስንትና ስንት ሺህ ዘመን ተመልሰን የድሮውን ባህል ለመመለስ የምንፈልግ አለን። በአሁኑ ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ የኋሊት ጉዞ የማያዋጣ ብቻ ሳይሆን፣ አደገኛም ነው።

ይህ አንደኛው ሲሆን፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በግሩፕ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንቅስቃሴ ሲኖር በዚህ አማካይነትም ሆነ፣ በየብሄረሰብ ውስጥ በሚኖረው ውሰጠ-ኃይል ብሄረሰቦች በመጀመሪያው ወቅት የነበራቸውን „የጋርዮሽ መለያ“(Collective Identity) በማጣት እየተሰበጣጠሩና እየተለያዩ(Social Differentiation) ይመጣሉ። በተለይም በአንድ ብሄረሰብ ውስጥ በሚፈጠረው የስራ-ክፍፍል አማካይነትና፣ በዚህም የተነሳ ከሌላው የብሄረሰብ ክፍል ጋር በሚደረገው ግኑኝነት የግሩፕ መለያ እየጠፋ የበለጠ የራስን ጥቅም ማሳደድ በሚለው ላይ አትኩሮ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በሚፈጠረው የስራ-ክፍፍልና ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ አንዳንድ ግለሰቦች ህይወታቸውን ለማሸነፍ ሲሉ የተወለዱበትንና ያደጉበትን አካባቢ በመተው ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ እዚያ ስራ ካገኙ ተቀጥረው በመስራት አዲስ ህይወት መገንባት ይጀምራሉ። በዚህ መልክ ባህሪያቸውና የአኗኗር ስልታቸው ይቀየራል። አንዳንዱ በፋብሪካ ወስጥ ተቀጥሮ ሲስራ፣ እዚያ ውስጥ ከመሰሉ ጋር በሚያደርገው የቀን ተቀን ግኑኝነት ቀስ በቀስ እያለ ባህርይው ይለወጣል። በዚያው መጠንም አዳዲስ የአነጋገር፣ የአረማመድ፣ የፍጆታ አጠቃቀም ባህርይ በማዳበር ገጠር ውስጥ ካለው ከተመሳሳዩ ብሄረሰብ በተለያዩ ነገሮች እየተለያየ ይመጣል። ስለሆነም ከአንድ ብሄረሰብ የተውጣጡ፣ ከፊሉ አራሽ ሆኖ ሲቀር፣ የተቀረው ደግሞ አንጠረኛ፣ የፋብሪካ ሰራተኛ፣ ነጋዴና ሀብታም፣ እንዲሁም የመንግስት ሰራተኛ በመሆን በጥንት ዘመን የነበራቸውን „ኮሌክቲቭ አይደንቲቲ“ ያጣሉ። በተለይም በህሊና አወቃቀራቸው የተለያዩ ስለሚሆኑ የማይግባቡብት ሁኔታ ይፈጠራል። እንደዚሁም አውሮፓና አሜሪካ ተሰዶ የሚኖረው ከዚህና ከዚያኛው ብሄረሰብ የተውጣጣ ግለሰብ በአስተሳሰቡ እየተለየ ይመጣል። በመሆኑም ይህንን ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ሂደተና መሰበጣጠር፣ እንዲሁም የአኗኗር ስልት ቀልብሶ አዲስ መለያ(Identity) ለመፍጥር መሞከር ብሄረሰቡን ወደ ኋላ ተጓዝ እንደማለት ይቆጠራል። አንተ ከሌላው የተለየህ ስለሆንክ እዚያው ያለህበት ቦታ በመቅረት መብትህን አስጠብቅ፣ ሀብትህንም ተቆጣጠር ማለት እድገትና መሸሻል አያስፈልግህም እንደማለት ይቆጠራል።

ይህንን ትተን ወደ ሌላ ጉዳይ ስንመጣ አንድን ብሄረሰብ በጥቅሉ ወስደን መለያይ ይህ ነው፣ በአንድነት ተነስተህ ለመብትህ ታገል ማለት አይቻልም። ለምሳሌ የኦሮሞ ብሄረሰብን ብንወሰድ በአገራችን በየቦታው ተሰብጣጥረው የሚኖሩና የህሊና አወቃቀራቸውም እንደተሰማሩበት የሙያ ሁኔታና በንግድና በተለያዩ የማህበረሰብ ነክ ጉዳዮች ላይ ባላቸው ግኑኝነት የሚለያይ ነው። የባሌው ኦሮሞ ምናልባት በቋንቋ ካልሆነ በስተቀር ከወለጋው ኦሮሞ በብዙ መንገዶች የሚለያዩበት ሁኔታ አለ። ለምሳሌ በወለጋ ውስጥ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ኦሮሞዎች የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ፣ የባሌው ኦሮሞ እስላምም የኦርቶዶክስ ክርስቲያንም ተከታይ አለ። ወደ ሸዋ ስንመጣ ደግሞ በዚያ የሚኖረው ኦሮሞ አብዛኛው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዕምነት ተከታይ ነው። ወደ ጅማና አካባቢው ስንመጣ አብዛኛው እስላም ሲሆን፣ በህሊና አወቃቀሩ ከወለጋውም ሆነ ከኢሉባቦሩ ኦሮሞ በብዙ ነገሮች ይለያል። እንደዚሁም ከባላባቱ መደብ የወጡ ኦሮሞዎች፣ በተለይም ከአባጅፋር ጋር የዘመድ ግንድ አለን የሚሉ ኦሮሞዎችና ዘመናዊ ትምህርት የቀመሱ በአኗኗራቸው ከገበሬው ወይም ከነጋዴው ኦሮሞ በብዙ መልኩ የሚለዩ ናቸው። ይህ ዐይነቱ የባህርይና የአመለካከት፣ እንዲሁም የአኗኗር ስልት ልዩነት አማራ ተብሎ በሚጠራው ብሄረሰብም ውስጥ ያለ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ጎንደርና ጎጃም አዋሳኝ ሆነው፣ ኑዋሪዎቹ በአነጋገርም ሆነ በአኗኗር ስልት ይለያያሉ። የዘፈናቸውም ቅኝታ ወይም አዘፋፈን ይለያያል። ከዚህ ስንነሳ በተላለየ አካባቢ የሚኖሩና፣ በተለያየ ሙያ እየሰሩ የሚተዳደሩ ግለሰቦችን በአንድ መለያ ለማጠቃለል መሞከር ከሶስዮሎጂ ወይም ከማህበራዊ ሳይንስ አንፃር ትክክል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ አርቲፊሻል መለያ በመፍጠር አንደኛው ብሄረሰብ በሌላው ላይ እንዲነሳ በማድረግ የስልጣኔውን በር መዝጋት ብቻ ሳይሆን፣ ዘለዓለማችንን እርስ በራሳችን እየተበጣበጥን እንድንኖር ለሚፈልጉና የኛን በዘለዓለማዊ ድህነት እንድንኖር ለሚመኙት ቀዳዳ መስጠት ነው። ስለሆነም አርቲፊሻል መለያ መፍጠርና መረጋጋት እንዳይኖር ማድረግ ራሳችንን አዳክመን የውጭ ኃይሎች መጥተው በቀላሉ እንዲወሩን መንገዱን ሁሉ አዘጋጅቶ እንደመስጠት ይቆጠራል።

በእኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው ትልቁ ችግር፣ ይህንን አስቸጋሪ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ነገሮች ከሳይንስ አኳያ እያነሳን ማጥናትና መከራከር የተለመደ ሳለልሆነ ሌሎችን ላለማስቆጣት ሲባል ብቻ አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮች ክርክር ሳይደረግባቸው ተቀብረው እንዲቀሩ ይደረጋሉ። በዚህም የተነሳ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ሁሉም በየፊናው የፖለቲካ ተዋናይ በመሆን የራሱን አጀንዳ ይዞ በመቅረብና እንደ አዋቂ በመሆን ሌላውን የዋሁን በማሳሳት የስልጣኔና የዕድገት መንገዱን ያጨልምበታል። ትግሉ ለዕውነተኛ ነፃነት መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ መነገጃና እሮሮ ማሰሚያ ይሆናል። ችግራችንን ውስጥ ለውስጥ በሳይንሳዊ መንገድ እየተወያየን ከመፍታት ይልቅ ፈረንጆች ጋ እየሄድን እሮሮ በማሰማትና ባለን መጠነኛ ቅራኔ ውስጥ ሰርገው እንዲገቡብን በማድረግ ተከፋፍለን እንድንቀር እናደርጋለን። ስለዚህም ከእንደዚህ ዐይነቱ አካሄድ ተላቀን ከዚህም ሆነ ወይም ከዚያኛው ብሄረሰብ እንደመጣን ሳይሆን እንደግለሰብ በአመለካከትና በርዕይ ደረጃ ብንቀራረብና ብንወያይ ችግሩን የበለጠ መረዳት ብቻ ሳይሆን መፍትሄም ለመፈልግ ያስችለናል። ከዚህ በመነሳት ነው የጥያቄውን አነሳስ መመርመርና፣ የተፈጠረውን ውዥንብር በመጠኑም ቢሆን መረዳት የሚቻለው።

በእኔ ዕምነት የተማሪው እንቅስቃሴ የብሄረሰብን ጥያቄ እንደ አንገብጋቢ ጥያቄ አድርጎ ሲያነሳ በጊዜው ያላያቸውና ያልተገለጹለት ነገሮች ነበሩ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ አንዳንድ ግዛቶች ወይም አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል በአንድ ማዕከላዊ ግዛት ውስጥ እንዲጠቃለሉ ሙከራ ሲደረግ ኃይል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ነው። የታሪክን ማህደር ላገላበጠ በህብረተሰብ ታሪክ ግንባታ ውስጥ ኃይል ወሳኝ ሚናን ተጫውቷል። አንዱ አገር ሌላውን ገባር ለማድረግ ሲል ባህርና ውቅያኖስን በማለፍ አንዳንድ አገሮችን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ሲያስገብራቸውና ዕድገታቸውን ሲወስን ኖሯል። የሮማውያንና የፐርሽያኖች ወረራና ግዛትን ማስፋፋት የተመዘገበና የብዙ አገሮችን ህይወትና ሂደታቸውን የወሰነ ነው። ሮማውያን ያልረገጡብት አንድም የአውሮፓ አገር የለም። በገዙበት ቦታ ሁሉ መሰረት ጥለው አልፈዋል። በባሪያ አገዛዝና በቅኝ ግዛት ዘመንም የተካሄደው አገሮችን ለማስገበርና የነሱ ቅኝ ግዛት አድርጎ ለማስቀረት ነው። ዛሬ ታላቅ የሚባለው አሜሪካንም የጥንት ኗሪ ሰዎችን በመጨረስና፣ ጥቁሩን ባሪያ አድርጎ በመዝበርና በማሰቃየት፣ እንዲሁም ደግሞ በከፍተኛ የዘርኝነት ስሜት በመወጠርና ዝቅ አድርጎ በማየት በመብዝበዝ የተገነባ አገር ነው። ዛሬም ቢሆን ኢንስቲቱሽናላይዝድ የሆነ ዘረኝነት በመስፈን ጥቁር አሜሪካኑ እንደሁለተኛ ዜጋ የሚታይበት አገር ነው። ያውም ወርቅ የመሰለ ህገ-መንግስት እያለና፣ በየአራት ዐመቱም የፕሬዚደንትና የኮንግረስ ምርጫ በሚካሄድበት አገር ዘረኝነት ሰፍኖ ሰፊው ጥቁር ህዝብ ፍዳውን ያያል። ወደ ኮሌጅና ወደ ዩኒቭርሲቲም ለመግባት የሚችለው በጣም ጥቂቱ ጥቁር ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ አካሄድ የማይደገፍ ቢሆንም በታሪክ ውስጥ የታየና አንዳንድ አገሮችም ያለፉበት ሁኔታ ነው።

ወደ አገራችን ተጨባጩ ሁኔታ ስንመጣ በኢትዮጵያዉያን ምሁራን ዘንድ ተነስቶ ያልተብላላ የጭቆና ጉዳይ አለ። ቀደም ብሎም ሆነ በኋላ በአፄ ኃለስላሴ ዘመን አጠቃላይ ጭቆናን በሚመለከት በህብረተሰቡ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ውስጥም የነበረ ነው። ጭቆናው ተጨቆኑ የሚባሉ ብሄረሰቦችን የሚመለከት ብቻ ስይሆን፣ ፊዩዳላዊ ስርዓት በሰፈነበት ህብረተሰብ ውስጥ ራሳቸው የፊዩዳል ልጆችም ይጨቆኑ እንደነበር ግልጽ ነው። የፊዩዳል ልጅ ሆኖ ካለዕድሜው ብዙ ከባድ ከባድ ስራዎችን የሚሰራና፣ ቤት ውስጥም ጭቆና የሚደርስበት ልጅ እንደነበር ይታወቃል። እነዚህ ጭቆናዎች በተለያዩ መልኮች የሚገለጹና የአንድን ልጅ ጤናማና ጤናማ ባለሆነ መልክ እንዲያድግ የሚወስኑ ሲሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜም በማወቅ የሚደረጉ አልነበሩም። ወደ አማራው ክልል ስንመጣም እስካሁንም ድረስ ለአቅመአዳም ከመድረሳቸው በፊት ልጃገረዶች እንዲያገቡ ይገደዳሉ። ከዚህ ስንነሳ በብሄረሰቦች ላይ ሰፍኗል ይባል የነበረውን ጭቆና ከአጠቃላዩ የፊዩዳላዊ አኗኗር ስልትና ከዕውቀት ማነስ ጋር ቢያይዝ ነገሩን ይበልጥ መረዳት እንችላለን። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ህብረተሰብ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ የአኗኗር ስልቶችን ይዞ የሚኖር ከሆነና፣ በሌላ በተገለጸለት አስተሳሰብ እስካለተጋፈጠ ድረስ ጠቅላላው ህብረተሰብ የዚህ ዐይነቱ የዕድገት ጠንቅ አኗኗር ሰላባ በመሆን አስተሳሰቡ ውስን መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ አኗኗሩም እንደ ተፈጥሮአዊ ተደርጎ በመወሰድ ድህነት ዘለዓለማዊ መልዮው ይሆናል። በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ የምሁራን ተግባርና ተልዕኮ ችግሩን ከሁለንታዊ አንፃር በመመርመር ሳይንሳዊ መፍትሄ መስጠት መሞከር እንጂ የማይሆኑ መፈክሮችን በማንሳት አንድ ህዝብ በቀላሉ ሊወጣው የማይችል ችግር ውስጥ መክተቱ ከፍተኛ ስህተት ነው። ይህንን አልፈን ወደ ህብረ-ብሄረ መንግስት ምስረታ ጉዳይ እንምጣ።

በአንንድ አካባቢ የሚገኙ የተሰበጣጠሩ በመሳፍንት ይተዳደሩ የነበሩ ግዛቶችን ሁኔታ ስንመለከት፣ የታሪክ ግዴታ ሆኖ ትናንሽ ግዛቶች በዚያው ሁኔታቸው ለመኖር አይችሉም ነበር። በተለይም በአስራሰባተኛውና በአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን የጠነከሩ መንግስታት ደከም ብለው ይገኙ የነበሩ እንደ ጀርመን የመሳሰሉ፣ ገና በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ጥላ ስር የማይተዳደሩ አገሮችን እየወረሩና እያጠቁ ስላስቸገሩ የግዴታ ጀርመን እንደ አንድ ማዕከላዊ አገዛዝ መዋቀር ነበረባት። በጊዜው ጠንከር ብሎና በባህል ዕድገት ተሽሎ የሚገኘው የፕረሺያው አገዛዝ አልገበርም ያሉትን በሙሉ በጦርነት በመውረርና በማጠቃለል ጀርመን አንድ ለመሆን ስትቃረብ፣ ኃይል በማግኘት ከፈራንሳይና ከአውስትሪያ የተሰነዘረባትን ጦርነት መክታ በመመለስ በ1871 ዓ.ም እ.አ የመጀመሪያው በአንድ ባንዲራ ስር የተጠቃለለ አገዛዝ ተመሰረተ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጀርመን ለዕድገት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን እንግሊዝንና ፈረንሳይን ቀድማ መሄድ ቻለች። በፕረሽያ አገዛዝ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው አጠቃላይ የትምህርት የጥገና ለውጥ የኋላ ኋላ በጀርመን ምድር ሳይንቲስቶች እንደ አሸን እንዲፈልቁ አደረገ። ለመጀመሪያ ጊዜ በሃያኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ሁለት ሶስተኛው የሚሆነው የኖቭል ሽልማት አሸናፊ የሆኑ ሳይንቲስቶች ከጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ነበሩ። ይህ ሁሉ የማዕከላዊ አገዛዝና ልዩ ዐይነት የዕውቀት ውጤት ነው። በሌላ አነጋገር ጀርመኖች ተሰበጣጥረው ቢኖሩ ኖሮ እድሜያቸውን በሙሉ በውጭ ኃይሎች በመጠቃት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባላቤት መሆን ባልቻሉ ነበር።

ወደ አገራችን ስንመጣ በተለይም አፄ ምኒልክ ወደ ደቡቡ የአገራችን ክፍል ያደረጉትን መስፋፋት አስመልክቶ ድርጊቱ ሲኮነንና፣ ጨለማን እንዳመጡ ተደርጎ ይታያል። አንዳንዶቹ እንደሚሉን ከሆነ፣ አፄ ምኒልክ ወደ ደቡብ ግዛታቸውን ከማስፋፋተቸው በፊት ህዝቡ የሰለጠነና፣ የራሱ ቴክኖሎጂና ሳይንስ የነበረው፣ እንዲሁም ደግሞ ከተማዎችን ገንብቶ በስራ-ክፍፍልና በንግድ አማካይነት በመገናኘት ተዝናንቶ ይኖር የነበረ ነው ብለው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ። ሀቁ ግን አነሰም በዛም ሁሉም ግዛቶች ተመሳሳይ ሁኔታ ነበራቸው። የአማራውም ሆነ ሌላው በኋላ በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ስር የተጠቃለለው ክፍል በስራ-ክፍፍልም ሆነ በንግድ አማካይነት የዳበሩ አልነበሩም። በመሆኑም በቴክኖሎጂ የሚገለጽ ዕድገት አልነበራቸውም። ይህ በራሱና ማዕከላዊ አገዛዙ በነበረው ውስጣዊ ድክመት የተነሳ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ እንደ አንድ ማህበረሰብ፣ ህብረተሰብና ህብረ-ብሄር በማዋቀር በሳይንስና በቴክኖሎጂ የተመሰረተ ስርዓት አጠናቆ መገንባት አልተቻለም። በሌላ አነጋገርር፣ ኢትዮጵያ በአፄ ምኒልክ ዘመን፣ የኋላ ኋላ ደግሞ በፄ ኃይለስላሴ ዘመን ወደ ማዕከላዊ መንግስትነት ብትቀየርም፣ ለአንድ አገር እንደ አገር መኖር የሚያስፈልጓት መሰረተ-ሃሳቦች ይጎድሏት ነበር፤ ዛሬም ይጎድሏታል። እነዚህም፣ 1ኛ) የዳበረና የተስፋፋ የስራ-ክፍፍል፣ 2ኛ) ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ፣ 3ኛ) በስነስርዓትና በዕቅድ የተገነቡ ከተማዎችና መንደሮች፣ 4ኛ) ብቃት ያላቸው ኢንስቲቱሽኖች፣ 5ኛ) መንገድና ድልድዮች፣ እንዲሁም የባቡር ሃዲድ፣ 6ኛ) ለአንድ አገር ዕድገትና መሻሻል የሚያስፈልጉ ሳይንስና ቴክኖሎጂዎች፣ 6ኛ) ሰፋ ያለ የዕውቀት መገብያ ኮሌጆች፣ የዕደ-ጠበባ ማሰልጠኛ ተቋሞች… ወዘተ. 7ኛ) የሳይንስ አካዳሚ፣ 8ኛ፟) የቲያትርና የሴኒማ ቤቶች፣ 9ኛ) የስፖርት ተቋሞች፣ 10ኛ) ለሲቪል ሶሳይቲ ማበብ የሚረዱ የሙያ ማህበሮች፣ እነዚህ ሁሉ በጊዜው ደረጃ በደረጃ ታስቦባቸው ለመቋቋም ስላልቻሉ በውስጣዊ ድክመት የተነሳ፣ በአንድ በኩል አገራችን እንደ አንድ ህብረተሰብና ህብረ-ብሄር ልትዋቀር አልቻለችም፤ በሌላ ወገን ደግም እንደዚህ ዐይነቱ ክፍተት የተሳሳተ አጀንዳ ላላቸውና አንድ ህዝብ ተስማምቶ ለጋራ ዓላማ እንዳይነሳ ለሚታገሉ ኃይሎች ቀዳዳ በመስጠት እስከዛሬ ድረስ ራስ ምታት ሰጥቶን ሲያሰቃየን ይኖራል። ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ምድር ዕድገት አለመታየቱ ሁሉንም ክፍለ-ሀገሮችና ብሄረሰቦች የሚመለከት እንጂ አንዱን ብሄረሰብ ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ሲባል አፄ ምኒልክም ሆነ አፄ ኃይለስላሴ በዕውቅ የወሰዱት ጎጂ ፖሊሲ አልነበረም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ-ዕድገት ዘመቻ ተካሂዷል ከተባለ ይበልጥ የተጎዳው የአማራው ግዛት ነው። ቡና ወደሚመረትባቸው ክፍለ-አገሮች ወይም በዛሬው አጠራር ክልሎች የሚሰደደውና ቡና ለቃሚ የሆነው፣ የጎንደሬው፣ የጎጃሜው፣ የወለዬውና የትግሬው ሰው ነው። ስለዚህም ስለበደልና ስለብሄረሰብ ጭቆና ሲወራ ነገሩን ካለማውቅና ሰፋ ያለ የዕድገትን አስፈላጊነት ካለመገንዘብ ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል እንጂ፣ ኢትዮጵያ የጨለመችና አስቀያሚ ታሪክ የነበራት አገር ናት እያሉ ማውራትና ማስፋፋት ኢ-ሳይንሳዊ፣ ኢ-ምሁራዊ፣ ኢ-ፍልስፍናዊና ኢ-ጥበባዊ ነው። የህብረተሰብን ዕድገት ታሪክ የሚፃረር አባባል ነው። አንድ ግለሰብም ሆን ህብዝ ሶሻላይዝድ በመሆን ራሱን በራሱ እሲኪያገኝ ድረስና ታሪክን ይሰራ ዘንድ ብዙ ውጣ ውረድ ያለባቸውን መንገዶች መጓዝ ያለበትን ሁኔታ ካለመረዳት የተነሳ ቀደም ብለው የነበሩ አገዛዞችን አረመኔዎች አድርጎ ለመሳልና አገራችንም ጨለማ እንደነበረችና፣ በተለይም ጭቁን የሚባሉት ብሄረሰቦች ከፍተኛ በደል ይደረስባቸው እንደነበር ኢ-ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ይቀርባል። አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነገሩን ለማሳመር ወይም የሰውን ልብ ለመንካት ሲሉ የሚሆን የማይሆን፣ የህብረተሰብን ህግና ሳይንስን የሚጥስ ነገር ሲናገሩ ይታያል። በተለይም በአሁኑ ዘመን ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች በጠፉበት ዘመንና፣ በተለይም የፖለቲካ ሳይንስ ትርጉም ተጣሞ በሚቀርብበት ዘመን፣ ፍልስፍና፣ ሶስዮሎጂ፣ አንትሮፖሊጂና ሳይኮሎጂ እንደመመሪያ መመርመሪያ ተደረገው በማይወሰዱበት አገር ፖለቲካ መተንተኛና ሳይንሳዊ መሳሪያ መሆኑ ቀርቶ ወደ መደንፊያነት በመለወጥ የአንድ ህዝብ ታሪክ እንዲጣመም ይደረጋል። በተለይም፣ ፖለቲካን ወደ መነገጂያና መኖሪያ የለወጡ ግለሶቦች አስቸጋሪ ሁኔታንና የታሪክ አጋጣሚን በመገጠም፣ እንዲሁም ከአንዳንድ ሚዲያዎች አላስፈላጊ ቦታ እንዲያገኙ በማድረግ በሚቀጣጠለው እሳት ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ የባሳውኑ እንዲጋይ ያደርጋሉ። እነዚህ ግለሰቦችም ሆነ ለእነዚህ ግለሰቦች ሁኔታውን የሚያመቻቹላቸው ሚዲያዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር ድርጊታቸው ፀረ-ህዝብ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ላይ እንድተሰዘነረ መረዳት አለባቸው። ወሬን ከማራገብና ሁኔታውን አመቻችቶ ከመስጠት ይልቅ ድርጊታቸውን ከሁሉም አንፃር መመርመሩ እጅግ ጠቃሚ ነው። ለዚህ ደግሞ የሚዲያና የፖለቲካ አማካሪዎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ስራቸውን ሊያቃልልላቸው ይችላል። ከስህተትም ሊቆጠቡ ይችላሉ። ስለሆነም የሚላክላቸውን ጽሁፎች በደንብ መመርመር አለባቸው። ቃለ-መጠይቅ የሚጠይቁ ሚዲያዎችም ኮታን ለማሟላት ሲሉ መጠየቅ የሌላበቸውን ሁሉ በመጠየቅ ችግራችንን የባሰውኑ ውስብስብ ማድረግ የለባቸውም። ይሁንና ግን ማንኛውም ሚዲያ የራሱ መብት ስላለው እንደፈለገው ጽሁፎችን ማስተናገድ ይችላል። ለማለት የሞከርኩት ሁላችንም ሰላምንና ብልጽግናን የምንሻ ከሆነ የባሰውኑ ውዝግብ ውስጥ የሚከተን ሁኔታ ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ አለብን ለማለት ብቻ ነው።
እንደዚህ ስል ግን በአንዳንድ ብሄረሰቦች ላይ በደል አልነበረም፤ ውይም የለምም ለማለት አይደለም። በኮሎኮንታው፣ በወላይታውና እንዲሁም በከፍቾው ብሄረሰቦች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ መባል የማይገባቸው ነገሮች ይባሉ ነበር። እነደዚህ ዐይነቱ አባባልና የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ማግለልና ለመጥፎ ነገሮች ተጠያቂ ማድረግ በተለይም በአውሮፓ ምድር ውስጥ በማዕከለኛው ዘመንና እስከ ኋለኛው ማዕከለኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተስፋፋ ነበር። በተለይም ካለምንም ምክንያት ይሁዲዎች የሚናቁና የሚጠሉ፣ እንደውሻም የሚታዩ ነበሩ። ስለሆነም ይሁዲዎች የተስቦና የኮሌራ እንዲሁም የልዩ ልዩ በሽታዎች ምንጮት ተደርገው በመቆጠር ከሌላ የህብረተሰብ ክፍል ጋር መጋባት አይፈቀድላቸውም ነበር። ይሁንና ግን ይሁዲዎች ይህንን ሁሉ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ፣ ቀስ በቀስ በመማርና በንግድ በመሰማራት የአገሬውን ሰው እየበለጡ ይሄዳሉ። ፈላስፋዎች፣ የሙዚቃና የሊትሬቸር ሊቆች፣ በኋላ ደግሞ ሳይንቲስቶችና የቴክኖሎጂ አፍላቂዎች በመሆን በተለይም ለጀርመን ዕድገት ልዩ ዕምርታን መስጠት ቻሉ። ተሰደብን፣ ተናቅን፣ ተዋረድን ብለው ወደ ጫካ በመግባትና ጠብመንጃ በማንሳት ጦርነት አላወጁም። የሚንቃቸውን በዕውቀት አማካይነት ማሸነፍ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ቻሉ። ይሁንና ግን የተሻልን ነን ብለው በመዝናናት ቂም በቀል መወጣት አልጀመሩም። ቀስ በቀስ በመጋባትና በመዋለድ እንዲሁም ዕውቀታቸውን በማስፋፋት ነው ለህብረተሰቡ ልዩ ዕምርታን መስጠት የቻሉት።

ወደ አገራችን ስንመጣ ያለው ችግር የህብረተሰብን ዕድገት ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ የራሳቸውን ብሄረሰብ የመንፈስና የማቴሪያል ዕድገት ሁኔታ በደንብ ያላጠኑ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ነገሩን ሁሉ በመጠምዘዝ የአማራው ብሄረሰብ እንደዚህ አደረገ፣ እንደዚያ ፈጠረ በማለት በየዋሁ ህዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት ስንትና ስንት ህዝብ ፈጅተዋል። ራሳቸው ማርክሲስት ነን ይሉ የነበሩ ግለሰቦች ሁሉ ሳይቀሩ አማራውን በነፍጠኝነት በመክሰስ አሳቃይተውታል፤ ገድለውታልም። ይህ ሁሉ ከታሪክ ጋር ሳይገናዘብ በተለይም ፊደል ቆጥረናል፣ ዩኒቨርሲቲም ገብተን ተምረናል በማለት በሚዝናኑ አንዳንድ ግለሰቦችና በድርጅት ደረጃ የተወሰዱ አላስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው።
ያም ተባለ ይህ ፣ ሬኔ ዴካ የሚባለው የፈረንሳዩ ፈላስፋ በአንድ ወቅት የተደረገን ድርጊት ሙሉ በሙሉ ማረጋጋጥ ስለማይቻል እንደሳይንስ ሊወሰድ አይቻልም። ሳይንስ የተፈጥሮ መነጋገሪያና መመርመሪያ፣ እንዲሁም የህብረተሰብ ማደራጃ መሳሪያ ነው። ስለዚህም የዛሬውን ችግር በታሪክ መነጽር ወይም መሳሪያ መፍታት አይቻልም። ያለፈ ነገር ያለቀለትና የደቀቀለት ነው። ስላለፈው ነገር እየደጋገሙ ማውራት፣ „ውሃ ቢውቅጡት እምቦጭ“ እንደሚሉት አባባል ነው። ስለዚህም ላይብኒዝ እንደሚለን፣ የአዲሱ ትውልድ ተግባር ዛሬ አፍጠው አገጠው የሚታዩ ችግሮችን በሳይንስና በፍልስፍና መሳሪያ መፍታትና ለመጭው ትውልድ ታሪክን ሰርቶ ማለፍ ብቻ ነው።
ከዚህ ስንነሳ የብሄረሰቦች ችግር መብታቸውን በማወቅ ብቻ ሊፈታ ይችላል ወይ ? መብትስ ሲባል ምንድ ነው ? በራስ ቋንቋ መነጋገር፣ ወይም ደግሞ የራሴ ባህል የሚሉትን መጠበቅ ? ሌላው ደግሞ ሀብትን ወይም ሬሶርስን የመቆጣጠር ጉዳይ፣ ሌሎችን አባሮ ሁሉንም የራሴ ብሎ መቆጣጠርና መዝናናት ? ለመሆኑ እነዚህ በመታወቃቸው እያንዳንዱ ብሄረሰብ ያለበትን መሰረታዊ ችግር፣ ለምሳሌ እንደ ንጹህ ውሃ ማግኘት፣ ተመጣጣኝ የሆነ ምግብ በጥራትም ሆነ በብዛት ማግኘት፣ መብራትና የምግብ መቀቀያ ጉዳይ፣ ቤትና የትምህርት ቤት ጉዳይ፣ እንዲሁም ህክምና… ወዘተ. እነዚህ መሰረታዊ የማንኛውም ሰው ፍላጎቶች የላይኛዎቹ መብቶች በመታወቅ ብቻ ሊፈቱ ይችላሉ ወይ ፟? ወይስ ዋናው ነገር የመብት ማዋቅን ጉዳይ መፍታትት ነው? ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉንም ለማለት ነው የሚፈለገው? ከዚህም ባሻገር አንድ ብሄረሰብም ሆነ ማህበረሰብ ወይም ህብረተሰብ ተከታታይነት ያለውን ጤናማ ኑሮ ለመኖር ከፈለገ የግዴታ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማዳበር ያስፈልገዋል። የቴክኖሎጂንና የሳይንስን ዕድገት የተመለከትን እንደሆን በክልል ወይም በብሄረሰብ ደረጃ ሊያድጉ ወይም ሊዳብሩ፣ ወይም ሊፈጠሩ የሚችሉ አይደሉም። በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር የተለያየ ጎሳ በጋብቻ ሲቀላቀልና፣ በስራ-ክፍፍልና በንግድ አማካይነት ግኑኝነቱን ሲያጠናክር የመፍጠር ኃይሉም ያድጋል። የቴክኖሎጂና የሳይንስ ባለቤትም ይሆናል። ይሁንና ግን በአጠቃላይ ሲታይ የቴክኖሎጂ ዕድገት ዓለም አቀፋዊ ጉኑኝነትንና፣ በዘዴ ቴክኖሎጂዎችንም መስረቀንና ማዳበርን ይሻል። በዚህ አማካይነት ብቻ ነው አንድ ህዝብም ሆነ ግለሰብ ኑሮውን ማሻሻል የሚችለው። ራሱን አገልሎ የሚኖር ማህበረሰብም ሆነ ብሄረሰብ በሃሳብ ይቀጭጫል። ዕድገትን ማየት አይችልም። ያለውንም ሬሶርሱን ወይም ሀብቱን በስነስርዓት መጠቀም አይችልም። በእኔ ዕምነት እንደዚህ ዐይነቱን ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማቋቋም ያስፈልጋል። አዲሲቱን ኢትዮጵያ ለማስተዳደር የሚችሉ ከሁሉም ብሄረሰብ በችሎታ ተመርጠው ሊስለጥኑ የሚችሉበት ሁሉኑም ዕውቀት ያካተተ ልዩ ዐይነት የኤሊቶች ዩኑቨርሲቲ ማቋቋም ያስፈልጋል። ይህ ዐይነቱ ልዩ የኤሊቶች ኢንስቲቱት በየክፍለ-ሀገሩ ወይም በየክልሉ የሚቋቋም ሲሆን፣ ፍልስፍናን፣ ታሪክን፣ ሊትሬቸርን፣ የተፈጥሮ ሳይንስን፣ ሜካኒካልና ኤልክትሮቴክኒክ ኢንጂነሪንግን፣ ጥበብና ሙዚቃን፣ የፖለቲካ ሳይንስና የሶስይሎጂ ዕውቀቶችን፣ አርክቴክቸርን… ወዘተ.፣ የሚያጠቃላል መሆን አለበት። በተጨማሪም በየክፍለ-አገሩ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ሁሉንም ዐይነት መጽሀፎች ያጠቃለሉ ቤተ-መጻህፍቶች መቋቋም አለባቸው። አገሪቱ እያደገች ስትመጣ ደግሞ በየቀበሌው የህዝብ መማሪያ ትምህርትቤቶች ቢቋቋሙ ህዝቡ የመማር ዕድልና ከዕደ-ጥበብ ሙያ ጋር የመተዋወቅ ባህልን ያዳብራል። ይህ በራሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እምርታን በማሳየት በህዝቡ ዘንደ ያለውን በማያስፈልግ መልክ የተሰራጨውን አሉባልታ በማስወገድ ህዝባችን በመከባበርና በሰላም እንዲኖር ይረዳዋል። ስለሆነም ስለነፃነትና ስለመብት በምንናገርበት ወይም በምንጽፍበት ጊዜ ነገሩን ሰፋ ባለመልክ መመልከቱ የሚጠቅም ይመስለኛል። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ዘመቻና የመብት ጥያቄ እንዲያውም የተገላቢጦሹን ነው የሚያመጣው። ድህነትን ፈላፋይ ነው የሚሆነው። የሳይንስና የቴክኖሎጂን ዕድገት አፋኝ ነው የሚሆነው። ጥበብ እንዳይስፋፋ፣ የሰዎች የመፍጠር ችሎታ እንዳይዳብር አፍኖ ይይዛል። በተጨማሪም መብት ወይም ነፃነት የሚከፈል ወይም እየተከፋፈለ የሚሰጥ ጉዳይ ሳይሆን፣ የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው። አብዛኛውን ጊዜ መብትና ነፃነት ግለሰብአዊ ባህርይ ሲኖራቸው፣ በሌላ ወገን ደግሞ ከስራና ከሙያ ጋር በተያያዘ አንድ ፈብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ወይም በሌላ የሙያ ማሀበር ተደራጅተው የጋርዮሽ ጥቅማቸው እንዲጠበቅላቸው የሚነሳ ጉዳይ እንጂ በብሄረሰብ ደረጃ የሚታይ ነገር አይደለም። ሳይንሳዊም ሊሆን አይችልም።

ዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝምና የነፃነት ትግል አስቸጋሪ ሁኔታ!

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተዋቀረው ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ስርዓት የአብዛኛዎችን የሶስተኛውን ዓለም አገሮች፣ በተለይም የአፍሪካን አገሮች፣ የኛንም ጨምሮ የዕድገታችንን አቅጣጫ ለመወሰን ችሏል። በተለይም ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ዘመናዊነት(Modernization) በመባል የሚታወቀው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በኛና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ከቅኝ ግዛትነት ከተላቀቁ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ በኛም ሆነ በነዚህ አገሮች ውስጥ አዲስ ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት፣ የፍጆታ አጠቃቀምና፣ ለየት ያለ የህሊና አወቃቀር ሊፈጠር ችሏል። ከዚህም ባሻገር የየመንግስታቱ መኪና በአዲስ መልክ በመዋቀርና በመጠናከር አዲስ የተፈጠረውን ህብረተሰአብዊ ግኑኝንት ሊያጠናክረው ችሏል።

የምትክ ኢንዱስትሪ ተከላ፣ (Import Substitution Industrialization) ወይም ደግሞ በአጠቃላይ ዘመናዊነት በመባል የሚታወቀው የኢኮኖሚ ፖሊስ በውጭ አማካሪዎች ግፊት ተግባራዊ ሲሆን፣ ዓላማው በዚህ ዐይነቱ ፖሊሲ አማካይነት ዕድገቱ ቀስ በቀስ ወደ ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችም በመዳረስ(Trickle–down) ኋላ-ቀርነት ተወግዶ ሁሉም አገሮች አነሰም በዛም የምዕራቡ የዕድገት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ የሚል ግምት ነበር። ይሁንና ግን የኢኮኖሚ ፖሊሲው ባለው ውስጣዊ ድክመት የተነሳ እንደታሰበው የእኛና የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ዕድገት ወደፊት ሊራመድ አልቻለም። በተለይም የየመንግስታቱ መኪና በመጠናከርና፣ የነበረውን ስርዓት እዚያው አፍኖ በመያዝ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊታይና የህብረተሰቡም ፈጠራ ከፍ ሊል አልቻለም። በዚህም ምክንያት የተነሳ አዲስ ውስጠ-ኃይሉ ከፍ ያለና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን ሊሸከም የሚችል የከበርቴው መደብ ብቅ ሊል አልቻለም። በሌላ ወገን ደግሞ ከታች ወደ ላይ ከኢኮኖሚው ዕድገትና ከህብረተሰቡ የማሰብ ኃይል ጋር እየተቀናጀ ያልተገነባው የመንግስት መኪና የባሰውኑ ጨቋኝ በመሆንና ከህብረተሰቡ በመራቅ ተጠሪነቱ ይበልጥ የውጭ ኃይሎች በመሆን፣ ወደ ውስጥ ደግሞ ሁለ-ገብ የሆነ የኢኮኖሚና የህብረተሰብ ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ሆነ።

በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተጠበቀውን ውጤት ሳያመጣ ሲቀር፣ እንደዚሁ በውጭ አማካሪዎች በስም የሚለያዩ፣ ይዘታቸው ግን ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ተግባራዊ በመሆን ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ዕድገትን ከማምጣት ይልቅ ሁኔታውን የባስውኑ አዘበራረቀው። በመሆኑም እርስ በርሳቸው ያልተያያዙ የኢኮኖሚ ክንዋኔዎች በመፈጠር፣ ዘመናዊ በሚባለው የኢኮኖሚ መስክና በእነዚህ ለካፒታሊዝም ዕድገት በማያመቹ የተሰበጣጠሩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መሀከል ከፍተኛ ቅራኔ መታየት ቻለ። በአንድ በኩል የዘመናዊ የኢኮኖሚ መስክ ተጠቃሚ የሆነው ክፍልና፣ በሌላ ወገን ደግሞ በተለያዩ ግን ደግሞ ጥሩ ገቢን በማያስገኙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በተሰማራው የህብረተሰብ ክፍል መሀከል „የባህል ልዩነት“ መታየት ጀመረ። በጊዜው የነበረው የአፄው አገዛዝ ይህንን ህብረተሰብአዊ ቅራኔ ለመፍታት የሚያስችል ፖሊሲ ስላልነበረው፣ እየተከማቸ በመጣው ቀውስ የተነሳ ቀስ በቀስ እያለ ከስልጣን የሚወገድበተን መንገድ አዘጋጀ። ይህ ሁኔታና፣ በጊዜው የነበረው ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ቀውስ ተደራርበው ለየካቲቱ አብዮት ምክንያት ሆኑ። አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ የተወሰዱት እርምጃዎች ከሞላ ጎደል ትክክል ቢሆኑም፣ በነበረው ትርምስ የተነሳ ግልጽ የሆነ ለካፒታል ክምችት የሚያመችና ለሰፊው ህዝብ የስራ መስክ ሊከፍት የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊስ መንደፍ አልተቻለም። የወታደሩ አገዛዝ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በውጭ ኃይሎች ግፊት ተግባራዊ የሆነው የነፃ የገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት ሳይሆን አዲስ የህብረተሰብ ኃይል በመፍጠርና በማጠናከር፣ በዚያውም መጠንም ድህነትን አስፋፍቶ ሰፊውን ህዝብ አቅመ ቢስ የሚያድርገው ሆነ።

በተለይም የግሎባል ካፒታሊዝም ባለፉት ሰለሳ ዓመታት የብዙ አፍሪካ አገሮችን ዕድል ወሳኝ በመሆኑ፣ በዚያው መጠንም የየመንግስታቱን መኪና በማጠናከርና ከሰፊው ህዝብ በመገለል፣ የየአገሮቹ መንግስታትና ህዝቦች ሆድና ጀርባ ለመሆን በቅተዋል። በዚህ መልክ የዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም በየአገሮች መንግስታት መኪና ውስጥ ሰርጎ በመግባት፣ መንግስታቶች የህዝብ አለኝታ እንዳይሆኑ ቆልፎ በመያዝ፣ በአንድ በኩል ህዝባዊ ጭቆና፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሸበርተኝነትን መዋጋት ያስፈልጋል በማለት የጎሳና የሃይማኖት ግጭት እንዲስፋፋ ተደረገ። ስለሆነም በዚህም መልክ የየመንግስታቱ ተግባር በመጨናገፍና ሀብት ያልአግባብ ምርታማ ባልሆነ ቦታ በመፍሰስ የአፍሪካ መንግስታት፣ የአገራችንም ጭምር ከውጭው ኃይል ጋር እጂና ጓንቲ በመሆን ህዝቦችን መፈናፈኛ እንዳያገኙ ለማድረግ ችለዋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በተለያዩ ዘርፎች መልክ የሚደርሱና የሚክሰቱ መዛባቶችና በደሎችን ሊዋጋ የሚችል ብቃትነት ያለው የሲቪል ህብረተሰብ ሊቋቋም አልቻለም። ይህ ሁኔታ ደግሞ በራሱ የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ለሚባሉት መስፋፋትና የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል በማበላሸት፣ የኛም ሆነ የብዙ አፍሪካ አገር ህዝቦች በራሳቸው ላይ ዕምነት እንዳይኖራቸው ሊደረጉ በቃ። በዕርዳታ ስምና ከላይ በተዘረዘረው መልክ ሰርጎ የገባው ኢምፔሪያሊዝም የህዝቦችን ነፃ ፍላጎት አኮላሸባቸው። የማሰብ ኃይላቸውን ተጠቅመው አዳዲስ መሳሪያዎችን በመፍጠር የዕድላቸው ወሳኝ እንዳይሆኑ ተደረጉ። በዚህም ምክንያት የተነሳ የኛና የተቀረው የአፍሪካ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዳይጎናፀፉና የዲሞክራሲ ስርዓት እንዳይገነባ ከሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ እንቅፋት ተደቀነበት። የአፍሪካ መንግስታትም ኢክስፐርት ነን ከሚሉት በሚሰጣቸው የተሳሰተ ኢንፎርሜሽንና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተነሳ ወደ ውስጥ ያተኮረ የኢኮኖሚ ግንባታ ማካሄድ አልተቻለም። ይበልጥ ለኤክስፖርት መስኩ አትኩሮ በመስጠትና ዕዳን ከፋይ በመሆን ለገንዘብ እንቅስቃሴና ለምርት ክንውን ይህ በራሱ እንቅፋት ሆነ። በግሎባል ካፒታሊዝም ግፊት የተነሳ የብዙ አፍሪካ አገሮች የማምረት ኃይል ሲዳከም፣ በዚያው መጠንም የቆሻሻ መጠያ ሆኑ። ሰከንድ ሃንድ ምርቶች የሚራገፉባቸው በመሆን፣ ይህ ዐይነቱ እንቅስቃሴ በተለይም የዋና ከተሞች ገጽታ ሊሆን በቃ። ይህ አጠቃላይ ሁኔታ በሰፊው ህዝብ የማሰብ ኃይል ላይ ከፈተኛ የሆነ አሉታዊ የህሊና ተፅዕኖ በማድረግ ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ይበልጥ አዘበራረቀው።

ይህንን የተወሳሰበ ዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝም በአገራችንም ሆነ በሌሎችም አፍሪካ አገሮች ሰርጎ መግባትን አስመልክቶ በተለይም ባለፉታ 25 ዓመታት በኛ ዘንድ ምንም ጥናት አልተካሄደም። በአገራችን ምድር ስልጣን የጨበጠውን ኃይል ከውጭው ዓለም ጋር ምንም ግኑኝነት የሌለው ይመሰል እስካሁን ድረስ የሚደረገው ትግል የተሟላ ሳይሆን እጅግ የሚያሳስትና ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል በማጨናገፍ ላይ። በተለይም ወጣቱ ትውልድ አስተሳሰቡ የሾለና የበሰለ እንዳይሆን እስከዛሬ ድረስ በአገራችን የደረሰው በደልና ኋላ-ቀርነት የውጭው ኃይል ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፣ እነሱንም ማስቆጣቱ ተገቢ አይደለም እየተባለ የትግሉን አቅጣጫ ለማዛነፍ ጥረት ይደረጋል። ሳይንሳዊ ጥናት እንዳይካሄድ መንገዱን በመዝጋት ለዕውነተኛ ነፃነትና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ለተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ የሚደረገው ሁለ-ገብ ነፃነት መልክ እንዳይዝ የሚሆን የማይሆን ፊዩዳላዊ አሉባልታ በማውራት የድህነቱ ዘመን እንዲራዘም እየተደረገ ነው።

በእኛ በኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ በተለይም ደግሞ ለስልጣን በሚታገሉ ኃይሎች ዘንድ ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችና፣ የኛንም ጨምሮ በግሎባል ካፒታሊዝም ወይም ይህንን በሚወክሉ መንግስታትና በኛዎች ፖለቲከኛ ነን ባዮች ዘንድ ምንም ዐይነት ግኑኝነትና የጥቅም መተሳሰር የለም። ለምሳሌ ባለፉት 25 ዐመታት በአገራችን ምድር ሲካሄድ የነበረው ፖለቲካና ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በወያኔ አገዛዝ ዕውቀትና ኃይል ብቻ የተካሄዱና የሚካሄዱ ናቸው። የውጭ ኃይሎች፣ በተለይም እንደ ቅዱስ የሚታየው ታላቁ አሜሪካን እንደ እግዚአብሔር ከውጭ ሆኖ የወያኔን አግዛዝ የሚሰራውን የሚያይ እንጂ ምንም ዐይነት ተፅዕኖ እንደማያደርግ ነው። በተጨማሪም እነ ዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ብድር ሲጠየቁ ከማበደር በሰተቀር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውስጥ ምንም ዐይነት ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ተፅዕኖ የላቸውም። ከዚህ በመነሳት የሚካሄደውም ትግል ለስልጣን የሚደረግና የወያኔን አገዛዝ የማስወገድ ትግል ብቻ ነው። የነፃነቱም ትግልና ዕውነተኛ ኢኮኖሚያው ዕድገትን የመቀዳጀቱ ጉዳይ ወያኔን ከማስወገድ ውጭ ሊታሰብ አይችልም። ወያኔ ከተወገደ በኋላ ከውጭ ኃይሎች ጋር በሚፈጠረው መልካም መቀራረብ ህዝባችን ዕውነተኛውን ነፃነት ሊቀዳጅ ይችላል የሚል አስተሳሰብ ተስፋፍቷል፤ ተቀባይነትም አግኝቷል። ይህም ማለት እስከአሁን ድረስ የወያኔ አገዛዝ ቢያንስ በኢኮኖሚ ፖሊሲና በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ ከእነ ዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ያወላገዱበትንና ያዘበራረቁትን ሁኔታ በትክክለኛው የቲዎሪ መነፅር እየተመለከትን መዋጋት የለብንም ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው በብዙ ሚሊዮን ህጎች የተበተባቸው ስምምነቶችና አገሮችን በሱ ቁጥጥር ስር የማድረጉን ልዩ ልዩ ሴራዎች ሁሉ አምነን መቀበል አለብን። ይህም ማለት ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተወሰኑ ኤሊቶች በተረጎሙትና የዓለም አቀፈ ኮሙኒቲው በሚደነግገው መልክ ብቻ የሚካሄድ ነው። በዚህም መልክ የሚተረጎም የነፃነት ትርጉም እንደገና ለውዝግብና ለሌላ የማያቋርጥ ትግል የሚጋብዘን ይሆናል። ልክ የደቡቡ አፍሪቃ ሁኔታ በኛው አገርም ይደገማል። ናኦሚ ክላይን ዘ ሾክ ዶክትሪን(The Shock Doctrine) በሚለው መጽሃፏ ውስጥ የሌሎችን አገሮች ሁኔታ ስታስረዳ እንደገለጸችውና፣ በተከበሩት ኔልሰን ማንዴላ የሚመራው አዲሱ የደቡብ አፍሪቃ መንግስትም ተገዶ ተግባራዊ እንዳደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲና ህብረተሰቡን ለድህነት የዳረገው ዐይነትም መመሪያ፣ በኛው አገርም በአዲሱ ሁኔታና በአዲሱ መንግስት ተግባራዊ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ ስንነሳ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን እንደ መጽሀፍ ቅዱስ የሚደገመውን የአማርታያ ሴንን የነፃነትንና የመንግስት አተረጓጎም ሁኔታ ጠጋ ብለን እንመልከት።

በትክክል አማርታያ ሴንን ካነበብኩትና ከተረዳሁት አንደኛውና ዋናው የነፃነት እንቅፋት የሚመነጨው ከመንግስታት የጭቆና አወቃቀር ጋር የተያያዘ ነው። የአለፉት ስድሳ ዐመታት የሶስተኛው ዓለም አገሮችን የየመንግስታቱን ኢኮኖሚ ፖሊሲና፣ እንዲሁም ደግሞ የኢንዱስትሪ አገሮችን መንግስታት ፖሊሲ ስንመለከት ሴን የሚለው ትክክል ነው። ይሁንና ግን እንደዚህ ዐይነቱ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮችና፣ በአገራችንም የተገነቡት የመጨቆኛ መሳሪያዎች የቱን ያህል ከውጭው ኃይል ጋር በጥቅም እንደተሳሰሩና እንደተዋቀሩ ከሴን መጽሀፍ ውስጥ ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም። ሴን ለማሳየት እንደሚሞክረው የሶስተኛው ዓለም መንግስታት በራሳቸው የቆሙና በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እንደሚያወጡ አድርጎ ነው። በተለይም የአፍሪካ መንግስታት እንደዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ውስጥ እንደወደቁና፣ ኃላፊነት ያለው አገዛዝ ለመመስረት እንዳልቻሉ የአፍሪካን መንግስታት አወቃቀር ችግርና የአገዛዞችን ፖሊሲ የመረመረ አይደለም። ከዚህም ባሻገር በአብዛኛዎች የአፍሪካ አገሮች የኢኮኖሚ ፖሊሲንና የማህበራዊ ሁኔታን ጉዳይ አስመልክቶ የመከራከር ልምድ አለመኖርና፣ መንግስታትም ከውጭ የሚመጣባቸውን ግፊት ለመቋቋም የሚችሉበት ምሁራዊ መሳሪያና ኃይል ይኑራቸው አይኑራቸው ሴን የመረመረ አይመስለኝም። በመሆኑ አገራችንም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በዓለም አቀፍ የግሎባል ካፒታሊዝም ሎጂክና በጭቆና ሰንሰለት ስር የተዋቀሩ መሆናቸውንና፣ ድህነትን እንደሚያስፋፉና ነፃነትንም እንዲሚገፉ ለማሳየት አልሞከረም። ከመንግስቱ ቢሮክራሲ፣ ከወታደር፣ ከጸጥታና እስከፖሊስ ኃይል ድረስ ያሉት አወቃቀሮች ቀድሞውኑ በታሰቡትና በተዋቀሩት የጎሎባል ካፒታሊዝም ሎጂክ አወቃቀር ስልት የተዋቀሩ እንጂ ከየአገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተያያዙ በመሆን የየአገሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ተብለው አይደለም የተመሰረቱትና እንዲደልቡ የተደረገው። ይህም ማለት አብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም የመንግስታት መኪናዎች ከታች ወደ ላይ ከማቴሪያላዊ ፍላጎትና ከረጂም ጊዜ የህብረተሰብ ዕድገት ጋር እየተሻሻሉ የተዋቀሩ ሳይሆን፣ በየአገሩ የሰፈኑትን ገዢዎች ጥቅም ለማሰጠብቅና ወደ ውጭ ደግሞ ታዛዥ በመሆን አገርን ማመሰቃቀል ነው። በዚያው መጠንም አገዛዞችና የመንግስት መኪናዎች በካፒታሊዝም ሎጂክ ውስጥ በመውደቅ ወደ ውስጥ አጠቃላይ የሀብት ክምችት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ሳይሆን፣ እንዲያውም ዕድገትን የሚቀናቀኑና፣ እንዲሁም ድህነትን የሚያስፋፉና የሚያጠናክሩ ናቸው። ምንም ዐይነት ጭንቅላትን የሚያድስ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በሌለበትና፣ የኃይል አሰላለፉም ውስን በሆነባቸው አገሮች ስልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉ ኃይሎች የራሳቸውን ጥቅም ከማስጠበቅና የውጭ ኃይሎችን ፍላጎት ተግባራዊ ከማድረግ በስተቀር አልፈው ሊሄዱ የሚችሉ አይደሉም። ስለሆነም አንድ አዲስ አገዛዝ ከፍተኛ ንቃተ-ህሊና እስከሌለው ድረስና፣ በዲስፕሊንና በስርዓት የታነፀ እስካልሆነ ድረስ፣ በተለይም ደግሞ የስልጣኔና የዕድገትን ትርጉም የተረዳ እስካልሆነ ድረስ፣ በዲሞክራሲና በነፃነት ስም ምሎ ተገዝቶ ስልጣን ላይ የሚወጣ ኃይል ቀድሞውን የተገነባውን የመንግስት መኪና እንደገና በማዋቀርና የመጨቆኛ መሳሪያ በማድረግና ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር የድህነቱን ዘመን እንደሚያራዝም በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች የታየ ጉዳይ ነው። በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ አገራችንንም ጨምሮ አብዮት የተካሄደበትን፣ ወይም የአስተዳደር ለውጥ የተደረገበትን ሁኔታ ስንመለከት አብዮቶች ወይም የአገዛዝ ለውጦች ተጨናግፈው የሚቀሩት ይህንን የሚቀናቀን ወይም የሚገታ ኃይል ከመጀመሪያውኑ ስለሌለ ነው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ህዝባዊ ድርጅቶች በየቦታው ተቋቋመው ነበር። ይህ ዐይነቱ ዱዋል ፓወር በጣም ጥሩ ጅምርና፣ ቢሮክራሲውን የሚተካና የሚቆጣጠር ኃይል ሆኖ የታቀደ ቢሆንም፣ የራሳቸን ጥቅም ተነካብን የሚሉ ኃይሎች ከውጭው ዓለም ጋር በመቆላለፋ፣ በተጨማሪም ውስጥ በተፈጠረው ጨቅላ አስተሳሰብና አላስፈላጊ ትግል ይህ ዐይነቱ የመጀመሪያው የዲሞክራሲ ፅንስስ በእንጭጩ እንዲቀጭ ተደረገ።። ወደ ሌሎች አገሮች ስንመጣ ደግሞ በተጨባጭ ሲታይ እንደ አውሮፓው የምሁር እንቅስቃሴ ህብረተሰብን በሚመለከቱ ማንኛውም ጥያቄዎች ላይ ውይይትና ክርክር ስለማይደረግ በአንዳች አጋጣሚ ስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች ስልጣናቸው የህዝብን ፍላጎት ማሟያና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንቢያ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸው ጥቅም መሳሪያ በማድረግ ወደ ጨቋኝነት ይለውጧቸዋል። የአንጎላንና የዚምባብዌን እንዲሁም የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ መመልከቱ ይበቃል። አንዳንድ አገዛዞች ደግሞ አሻፈረኝ ሲሉና የራሳቸውን መንገድ መከተል ሲጀምሩ እንዲገደሉ ይደረጋል። የቶማስ ሳንካራን ሙከራና አከሻሸፍ መመልከቱ ብቻ በቂ ነው። የቶማስ ሳንካራ ጓደኛ ከፈረንሳዩ የሶሻሊስት መንግስት ነኝ ባዩ የስለላ ኃይል ጋር በመመሰጣጠርና ድጋፍ በማግኘት ቶማስ ሳንካራ እንዲገደል ተደረገ። በተለይም የፈርንሳይ ፓርቲዎች፣ ሶሻሊስቶች ሆኑ ወግ-አጥባቂዎች ምንም ዐይነት ለውጥና የኑሮ መሻሻል እንዳይመጣ በድሮ ቅኝ ግዛቶቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ወንጀል በሰፊው ተመዝግቧል። ስለሆነም የካፒታሊስት አገሮች የአፍሪካ አገሮች እንዳያድጉ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ እንዳይበለጽጉ አንድ አገዛዝ ለየት ያለ መስመር የሚከተል ከሆነ የተለያየ ምክንያት በመፈልግ ብጥብጥ እንዲነሳ ወይም የመንግስት ግልበጣ እንዲካሄድ ያደርጋሉ። ምክንያቱም አገሮች ሁልጊዜ እየተዋከቡ መኖር አለባቸው። እርስ በራሳቸው ሲፋጠጡና ወደ ጦርነት ሲያመሩ ህብረተሰብአዊ መዛባት በመፈጠር የህዝቦች ዋናው ተግባር ጦርነት ይሆናል። ዕድገትና ስልጣኔ የአፍሪካ አገሮች ዋናው የትግል መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ የሰው ትግል ወደ ውንብድናነት ይቀየራል። በዚህ መልክ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በአፍሪካ ምድር ከስድሳ የማያንሱ የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎች ተካሄደው ተሳክተዋል። እነዚህ ሁሉ የመንግስት ግልበጣዎች የተካሄዱት ልዩ የክርስትናንና የሊበራሊዝም እሴት አለኝ በሚለው የምዕራቡ ካፒታሊዝም፣ በተለይም በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይና በአሜሪካን መንግስታት አማካይነት ነው። ለሶት መቶ ሺህ ምሁራን ዕልቂት ተጠያቂው የሆነው ኢዲ አሚን በእንግሊዝና በእስራኤል የስለላ ድርጅት ነው ፕሬዚደንት ሚልተን ኦቦቴን አስዎግዶ የግድያ ዘመቻውን የከፈተው።

እንደገና ወደ አገራችን ስንመጣ በደርግ ዘመን የተዋቀረው የጭቆና ስርዓት ቢፈራርስም የወያኔ አገዛዝ የአሰራር ስልቱን በመውሰድ የጭቆና ሰንሰለቱን በእዲስ መልክ መዘርጋት ችሏል። ይሁንና ደግሞ ይህንን የጭቆናና የከፋፍለህ ግዛ አጋዛዙን ለማጠናከር የምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም እንግሊዝና አሜሪካ እንደተባበሩት ግልጽ ነው። ሸበረተኝነትን መዋጋት ያስፈልጋል የሚለው ፈሊጥ ሌላው የትግል መፈክር በሆነበት ዘመን በመሀከላቸው ያለው መተሳሰርና ወደ ውስጥ ደግሞ ጭቆናን አስፍኖ ነፃነትን መግፈፍና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዳይመጣ ማድረግ ዋናው የትግል ስትራቴጂ መሆኑን የኔ ትንተና ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ጥናቶችም ያረጋግጣሉ። በተለይም እንደኛ ባለው ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ድክመት በሰፈነበትና፣ ተማርኩኝ የሚለው አንዳንዱ ዝም ብሎ ሁኔታውን በሚያይበት አገርና፣ ለስልጣን የሚሯሯጠው ደግሞ የሚታየውን ነገር ለማየትና ለመተንተን በማይፈለግበት አገር ለነፃነትና ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል እጅግ አድካሚ ይሆናል። ስለሆነም የየካቲቱ አብዮትና በኋላ ደግሞ የምርጫ 97 ውጤት ሊከስሽፉ የቻሉት በመዘናጋት፣ የውጭ ኃይሎችን በመተማመንና ለስልጣን በመስገብገብ የተነሳ ነው። ብሄራዊ አጀንዳን ከማስቀደም ይልቅ የራስን የአጭር ጊዜ ህልም ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል ነው እጅ ውስጥ ሊገባ የነበረው ስልጣን እንዲነጠቅ የተደረገውና ህዝባችንም እስከዛሬ ድረስ ፍዳውን እንዲያይ የተፈረደበት። ስለሆነም ከምርጫ 97 በኋላ በውጭ ኃይሎችና በወያኔ አገዛዝ መሀከል ያለው የእከክልኝ ልከክልህ ግኑኝነት የባሰውኑ እየተጠናከረ እንደመጣ እንመለከታለን። ለዚህ ደግሞ የአግአዚ ጦር በቂ ማረጋገጫ ነው። ይሁንና ግን አሁንም ቢሆን ይህንን ሀቅ ለመቀበል የማይፈልጉ ተቃውሚ ነን የሚሉ ኃይሎች አሉ። ታዲያ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ዐይነት የነፃነት ትግል ነው ሊካሄድ የሚችለው ? ምንስ ዐይነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት ነው ትግል የሚካሄደው ?

ታጋይ ነን የሚሉ ኃይሎች በሙሉ በርግጥም ለነፃነት እንታገላለን የሚሉ ከሆነ፣ 1ኛ) የመንግስትን መኪና አወቃቀር ከቲዎሪ አንፃር በሰፊው በማጥናትና በመገምገም ውይይት እንዲደረግበርት ማድረግ አለባቸው። የመንግስትን ምንነትና ተግባርን አስመልክቶ ከፕላቶን ጀምሮ እስከነ ሺለሩ ጥበባዊ መንግስት ድረስ ሰፊ ውይይትና ክርክር ተካሂዷል። የማርክሲስት ምሁራንም፣ በተለይም እነ ፖላንትሳስ የካፒታሊዝምን መንግስት ምንነትና የሀብት ክምችት አጋዥነት በሰፊው አጥንተው በመጽሀፍ መልክ ለንባብ አቅርበዋል። በተጨማሪም ሌሎች የሶስተኛው ዓለም አገሮችና አንዳንድ የአውሮፓ ምሁራን እንደዚሁ በሶስተኛው ዓለምና በካፒታሊስት አገሮች መሀከል ስላለው መተሳሰርና የዕድገት ማነቆነት በበቂው አትተዋል። ጆን ጋልቱን የሚባለው የስዊድሹ የሶስዮሎጂና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር፣ እንደዚሁ „ኢምፔሪያሊዝምና የኃይል አወቃቀር“(Imperialism and Structural Power) በሚለው ግሩም መጽሀፉ፣ በኢምፔሪያሊዝም አማካይነት በሶስተኛው ዓለም አገር ህዝቦች ላይ የሚደርሰውን ጭቆናና በመንግስታቱ መሀክል ያለውን የጥቅ ም መተሳሰረና የዕድገት ማነቆነት ሳይንሳዊ በሆነ መልክ አትቷል። ከዚህ በሻገር በተለይም የፋይናንስ ካፒታሊዝም አይሎ በመወጣበት ባሁኑ ወቅት የብዙ ካፒታሊስት አገሮች የመንግስት መኪና በፊናንስ ካፒታሊዝም ቁጥጥር ስር እየዋለና የስለላ መዋቅሩንም እያጠናከረ በመምጣት ነፃነትን አፋኝ እየሆነ መጥቷል። በመሆኑም ይህ ጉዳይ በሶስተኛው ዓለም አገሮች በመስፋፋት መንግስታቱን ተቀጣይና ትዕዛዝ ተቀባይ አድርጓቸዋል። በተለይም ይህ ዐይነቱ ነፃነትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማፈኑና ህዝብን መቆጣጠሩ በአሜሪካን ምድር የተስፋፋ ነው። ሳልማድ ሩድሺን ስድሳ አስምስተኛ ዕድሜውን ሲያከብር ባደረገው ንግግር የነፃነት ትርጉም በተለይም በአሜሪካ ምድር እየታፈነ እንደመጣና፣ ማን ምን ዐይነት መጽሀፍን እንደሚያነብ እንደሚመዘገብ በንግግሩ ላይ ጠቅሷል። 2ኛ) የአገራችንን የመንግስት አወቃቀር ከታሪክ አንፃር ማጥናትና፣ ለምንስና እንዴት ለኢኮኖሚ ዕድገት ጠንቅ እንደሆነ ማማልከቱ የምሁራን ተግባር ነው። ከዚህ ስንነሳ ከ40ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በአገራችን ምድር የተዋቀረው መንግስታዊ መኪና ከውጭው ኃይል ጋር የተሳሰረ እንደነበረ ማጥናትና ለውይይት ማቅረብ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ይህ ጥያቄ በሰፊው ሳይጠናና ለክርክር ሳይቀርብ ወደ ስልጣን የሚደረግ ጉዞ የመጨረሻ መጨረሻ የነፃነቱንና የዕድገቱን ዘመን ያጨልመዋል። 3ኛ) ኢትዮጵያ ከውጭው ዓለም ጋር ግኑኝነቷን ካጠናከረች በኋላ በርዕዮተ-ዓለምና በአመለካከት ደረጃ፣ እንዲሁም ደግሞ በፍጆታ አጠቃቀም ያገኘችውንም ጥቅም ሆነ የደረሰባትን ጉዳት አንስቶ መወያየቱ ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ግልጽ ያደርገዋል። በተለይም በባህል ላይ የሚደርሰው ወረራና ወጣቱን ማዘናጋቱ የቱን ያህል ራሳችንን እንዳናውቅና የነፃነቱንም ትግል አስቸጋሪ እንዳደረገው መወያየቱ ጠቃሚ ይመስለኛል። ከዚህም በመነሳት የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው የሚለፈፈውን የህግ-የበላይነትና የገበያ ወይም ነፃ ንግድ ኢኮኖሚ ውስንነት መመርመርና እኛ ከምናልመውና ከምንታገልለት ነፃነትና ዕድገት ጋር ይጣጣም ወይም አይጣጣም እንደሆን መወያዩቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። የህግ የበላይነት ዛሬ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያገኘ ኖርም ነው ብሎ ማተቱ ብቻ የሚበቃ አይመስለኝም። የህግ የበላይነት ከጥቂት ግለሰቦች በሀብት መደለብ ጋር የተያያዘና፣ ይሁንና ግን ሁሉም በህግ ፊት እኩል ነው የሚለውን የተዛባ አመለካከት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል። በተጨማሪም በዛሬው ዓለም ብዙ አገዛዞችና ኢንስቲቱሽኖች በሎቢይስቶች በሚደገፉበትና በተሰገሰጉበት ዘመን የህግ የበላይነትና ተራ ምርጫ የሚባሉት ቦታ እንደሌላቸው መረዳት ያስፈልጋል። የፈለገውን ያህል ህዝባዊ ተቃውሞ ቢደርስም በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፊርማዎች ለአገዛዞችና ለህዝብ ተጠሪዎች ቢቀርቡም፣ መንግስታት በሎቢስቶች ግፊት የተነሳ የህዝብን እርሮና ጩኸት እንደማይሰሙ እንከታተላለን። በአሜሪካንና በአውሮፓ አንድነት የሚካሄደውን የነፃ ንግድ ስምምነት(TTIP) ለተከታተለው የምንገነዘበው ድርድሩ በተዘጋ መልክ የሚካሄድና ህዝብም እንዲያውቀው የሚደረግ አይደለም። ራሳቸው የህዝብ ተጠሪዎች ነን የሚሉ ፓርሊሜንቴሪያን እንኳ የስምምነቱን ውልና አካሄድ ምስጢር ማንበብ አይፈቀድላቸውም። እስከዚህ ድረስ ነው የዘመኑ ካፒታሊዝም የህዝቦችን ነፃነት መግፈፍ የቻለው። በምንመገበው ምግብ ውስጥ ያሉትን ንጥረ-ነገሮች እንኳ የማወቅ መብት የለንም። መታወቅ ወይም በፓኬቱ ላይ በዝርዝር መቀመጥ የለባቸውም። ምክንያቱም ይህ ዐይነቱ ግልጽነት የነፃ ገበያን መሰረተ-ሃሳብ ይፃረራል የሚል ነው። ከዚህ ስንነሳ እኛ ኢትዮጵያውያን በነፃነትና በኢኮኖሚ ዕድገት መሀከል ያለውን ዲያሌክቲካዊ ግኑኝነት በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ በዓለም አቀፋዊው ካፒታሊዝምና በመንግስታችን መሀከል ያለውን መተሳሰርና መደጋገፍ፣ ከዚህም በመነሳት ይህ ዐይነቱ የእከክልኝ ልከክልህ መደጋገፍና መተሳሰር የቱን ያህል ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለነፃነት፣ እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንቅፋት እንደሚሆን መወያየቱ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ዲሞክራሲና የዲሞክራሲ ትርጉም!

በጥንታዊቱ ግሪክ ዘመን ዲሞክራሲ የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ከህዝብ አገዛዝ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ተግባራዊነቱ በሶስት ኢንስቲቱሽኖች የሚወሰን ነበር። በ507 ዓ.ም ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሌይስቴነስ የሚባለው መሪ ፖለቲካዊ የጥገና ለውጥ ያደርጋል። በጥገና ለውጡ መሰረት የውስጡን ፖለቲካና የውጭውን ፖሊሲ የሚያስተዳድር አካል ይመርጣል። ይህ አካል ህግን የሚያወጣና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ፣ ከተለያዩ የአቴን ጎሳዎች የተውጣጡ ተወካዮች የሚሳተፉበት መድረክ ይቋቋማል። በሶስተኛ ደረጃ፣ ህዝቡ ብሶቱን ወይም ቅሬታውን የሚያቀርብበት ፍርድቤት ይቋቋማል። ይህ ዐይነቱ ዲሞክራሲ ከዚህ ቀደም ብሎ በአሪስቶክራሲውና በተራው ህዝብ መሀከል የነበረውን ልዩነት ከሞላ ጎደል የሰበረ በመሆኑ፣ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ህዝቡ ከህግ ፊት እኩል ነበር። በሌላ ወገን እንደዚህ ዐይነቱ ዲሞክራሲ የተወሰነውን የአቴንን ዜጋ የሚመለከትና ሴቶችንም ያገለለ ነበር። ይሁንና ከጊዜው የህብረተሰብ ዕድገት አንፃርና በጎሳዎች መሀከል ከሚደረገው ሽኩቻ ሁኔታ ስንነሳ ይህ በአቴኑ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው የዲሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብ አንድ እርምጃና ከዚያ በኋላ ለተነሳው የአውሮፓ የዲሞክራሲ ትግልና አስተሳሰብ መሰረት የጣለ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአቴኑ ዘመን ተግባራዊ የሆነው የዲሞክራሲ አስተሳሰብ ከጎሳ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለሲቪል ሊበሪትና ለግለሰብአዊ ነፃነት በሩን የከፈተ ነው ማለት ይቻላል። እንደዚህ ከክርስቶስ ልድት በፊት በ594 ዓ.ም ስልጣንን የተረከበው ሶሎን የሚባለው መሪ አዲስና የተሻሻለ የጥገና ለውጥና ህገ-መንግስት እንዲወጣ ያደርጋል። በጥገና ለውጡም መሰረት ህዝቡ ተጠሪዎችን በመምረጥ በፖለቲካ አወቃቀሩ ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ይደረጋል። በዚህም መሰረት አዲስ የተመረጠው የህዝብ ተጠሪ ሶስት ተግባሮች እንዲኖሩት ይደረጋል። ኦርጋኑም ህግን የሚያወጣ፣ የመንስት ሰራተኞችን የሚመርጥና ጦርነት መካሄዱንና አለመካሄዱን የሚወስን ይሆናል። ይሁንና ግን በዚህ ዐይነቱ ፖለቲካዊ የጥገና ለውጥ ሴቶች፣ አገልጋዮችና የውጭ ሰዎች የመምረጥ መብት አልነበራቸውም። በህገ-መንግስቱ መሰረት፣ በእርጋኑ ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸው የመሬት ከበርቴዎች፣ ሀብታም ነጋዴዎች፣ የተለያየ ደረጃ ያላቸው አንጥረኞችና ገበሪዎች ነበሩ። በዚህ መልክ በሶሎን አማካይነት የተዋቀረው አዲሱ ዲሞክራሲያዊና ሚዛናዊ አገዛዝ በዕዳ የተተበተበውንና በባላባቱ ስር ጥገኛ የሆነውን ገበሬ ነፃ በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ያለ የስልጣኔ መሰረት ለመጣል ረዳ። በእርግጥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው ፍልስፍናም ሆነ ማቲማቲክስ፣ እንዲሁም ጥበብና አርክቴክቸር ቀጥሎም ድራማ የበለጠ በሰው የመፍጠር ኃይል ተግባራዊ ሊሆኑ የቻሉት። ሶሎን ራሱ ፈላስፋና፣ በከፍተኛ ደረጃም የተገለጸለት መሪ ስለነበር የዲሞክራሲን ሰፊ ትርጉም በመረዳት በልዩ ልዩ መልኮች ሊገለጹ የሚችሉበትን ሁኔታ ማዘጋጀት ቻለ። ይህ ሁኔታ በግሪክ ምድር ውስጥ በተለይም በአቴንና በአካባቢው ለስራ ክፍፍል መዳበርና ለንግድ ልውውጥ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። በዚህ መልክ ቀደም ብሎ በልዩ ልዩ ጎሳዎች ይደረግ የነበረው ውጊያና ፍጥጫ ቆሞ ጠቅላላው ህዝብ ለስራና ለንግድ ታጥቆ ይነሳል። ይሁንና ግን ሶሎን ስልጣኑን ከለቀቀ በኋላ ይህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ፈተና ይደርስበታል። ሶፊስቶች የመንግስቱን መኪና ወይም አገዛዙን በመክበብና ለራሳቸው መጠቀሚያ በማድረግ የጦርነት ምንጭ ያደርጉታል። የኋላ ኋላም የግሪኩ ስልጣኔ በሮማውያን ወራሪዎች ቀስ በቀስ ድምጥማጡ ይጠፋል። ታላቁ አሊክሳንደር አልገበርም ያሉትን ሁሉ ካሸነፈ በኋላ ከግብጽ፣ በሱ ስም ከተጠራው አሊክሳንደሪያ ከተማ በመነሳት በአካባቢው ስልጣኔን ለማስፋፋት ያደረገው ሙከራ በሮማውያን ወራሪዎች ይከሽፋል። ወደ ሰባት መቶ ሺህ የሚጠጉ መጽሀፎችን ሁለት ጊዜ ካቃጠሉና፣ ከግብጽም ሀብት ከዘረፉ በኋላ የግሪክ ስልጣኔ ሲደመሰስ በሱ ምትክ ወደ ሰባት መቶ ዓመታት የሚጠጋ የጨለማ ስርዓት ይዘረጋል። የሮማውያን ወረራና ሌሎችን ገባር አድርጎ መግዛት ቀስ በቀስ እየተዳከመ ይመጣል። በየቦታው የተስፋፋው የሮማውያን ኃይሉ እየተሟጠጠ ይመጣል። የመጨረሻ መጨረሻም በጀርመን ወራሪዎች በመደምሰስ ለፊዩዳሉ ስርዓት በሩን ይከፍታል። በካቶሊክ ቄሶችና በአሪስቶክራሲው የአውሮፓ ህዝብ መሰቃየት ይጀምራል። ይህ ሁኔታ ግን የኋላ ኋላ በተገለጸላቸው ኃይሎች፣ በተለይም በተፈጥሮ ሳይንስ አማካይነት መጋፈጥ ሲጀምር፣ አዳዲስ ኃይሎች በመፈጠር የድሮው አገዛዝ በአረጀው መልኩ ሊቀጥል እንደማይችል ግልጽ ይሆናል ።

ከኢንላይተሜንት ጀምሮ የተደረገውን በፍጹም ሞናርኪዎችን አገዛዝ ላይ ይካሄድ የነበረውን የተቃውሞ ትግል ስንመለከት ሪፑብሊክን መመስረትና ገበሬውን ከአርስቶክራቲውና ከፊዩዳሉ መደብ ለማላቀቅ የተደረገ ትግል ዲሞክራሲያዊ ትግል ነው ማለት ይቻላል። በተለይም በካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮችና በፕሮቴስታንት የሃይማኖት መሪዎች መሀከል የነበረው ትግል በአልተገለጸላቸውና በተገለጸላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መሀከል የተደረገ የመረረ ትግል ነበር። ሁለቱ የሃይማኖት ተከታይ መሪዎች በከፈቱት ጦርነት በአንዳንድ ቦታዎች ሁለት ሶስተኛው የሚሆነው ህዝብ እንዳለቀ የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ከዚህ ውጣ ውረድና የርስ በርስ መተላለቅ በኋላ ነው ጥቂት የተገለጸላቸው ምሁራን ጣልቃ በመግባት መረጋጋት ሊፈጥሩና፣ በፊዩዳሉ አገዛዝ የተሰቃዩ አገዛዞች በፍጹም ሞናርኪያዊ አገዛዝ በመጠቃለል ብዙ የአውሮፓ አገሮች ወደ ህብረ-ብሄር ግንባታ መሸጋገር የቻሉት። ከዚህ የምንረዳው ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚደረገው ትግል በጣም አስቸጋሪና፣ የግዴታም የተገጸላቸው፣ ሰፋና የጠለቀ ዕውቀት ያላቸው ሳይንቲስቶችና ፈላስፋዎች ጣልቃ ገብነት የቱን ያህል ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ነው። ምክንያቱም በጊዜው የነበሩት አገዛዞች በጣም አክራሪዎች ስለነበሩና፣ ህዝቡም በበሽታና በድህነት ይሰቃይ ስለነበር ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመውጣት እንዴት አድርጎ አገዛዞችን የጥቅማቸው ሳይሆን የመንፈሳቸው ተገዢዎች ማድረግ ይቻላል? የሚለው አስተሳሰብ ነበር ምሁራንን ያስጨንቃቸው የነበረው። ምክንያቱም ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ፣ የባሰ ችግር ውስጥ ላለመግባት ሲባል የተደረሰበት ውሳኔ ከፍተኛ የጭንቅላት ሰራ መስራትና የምሁራኑን መሰረት ማስፋት ነበር። ይህ ዐይነቱ አካሄድ በአውሮፓ ምድር ውስጥ በልዩ ልዩ መልክ ሊገለጽ የሚችል ምሁራዊ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋና እንዲዳብር በማድረግ የዲሞክራሲን ጥያቄና አፈታት የበለጠ እምርታና መልክ ሰጠው።

በሌላ ወገን ካፒታሊዝም እያደገ ሲመጣ የወዝ አደሩ መደብም አዳዲስ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመረ። በሙያ ማህበር መደራጀት፣ የስራ ሰዓት መቀነስና ከምርት ዕድገት ጋር ሊሄድ የሚችል ጥያቄዎች በመነሳት የከበርቴውን መደብ ማፋጠጥ ቻለ። ቀስ በቀስም የማርክስ ስራዎች ሲስፋፉ የተወሰነው የሰራተኛው መደብ ራሱን በኮሙኒስት ወይም በሶሻሊስታዊ አመለካከት ማደራጀት ቻለ። በየጊዜው ለሚነሳው የኢኮኖሚ ቀውስና ጥልቀት ያለው ብዝበዛ የካርል ማርክስና የፍሪድሪሽ ኤንግልስ ስራዎች እንደመመሪያ በመሆን አማራጭ የህብረተሰብ ማደራጃ ዘዴ ሆነ። ከካፒታሊዝም የኢኮኖሚና የህብረተሰብ አደረጃጀት ባሻገርም ሌላም ስርዓት መፍጠር እንደሚቻል ቲዎሪው እንደ አማራጭ ሆኖ ቀረበ። የማርክስ ስራዎች በጊዜው የነበረውን የካፒታሊዝም ዕድገት ነፀብራቆች ወይንም ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። የጊዜው መንፈስ(Zeitgeist) የወለደው ሲሆን፣ ዝም ብሎ ከሰማይ ዱብ ያለ ሳይሆን፣ ማርክስ ከሃያና ከሰላሳ ዐመታት ጥናትና ምርምር በኋላ ቀስ በቀስ ያዳበረው ነው። የማርክስ ስራዎችም የሚያረጋግጡት አንድን ህብረተሰብ፣ በተለይም የካፒታሊዝምን ስርዓት እነ አዳም ስሚዝና ሌሎቹ የጥንት ኢኮኖሚስቶቸ(Classical Economists) በመባል በሚታወቁት በተረጎሙት መልክ ሳይሆን በሌላ መልክም መተርጎም እንደሚቻልና፣ በማርክስ አባባል ይኸኛው ሳይንሳዊ የህብረተሰብ መተንተኛ ዘዴ መሆኑን ነው ለማሳየት የተሞከረው። በዚህ መልክ አዳዲስ ቲዎሪዎች ሲፈልቁና ሲስፋፉ የምሁሩም አስተሳሰብ በተወሰነ አመለካከት ብቻ የሚሽከረከር ሳይሆን፣ የነገሮችን ሂደት ከሌላም አኳያ መመርመር እንደሚቻል ግንዛቤ ተደረሰበት። ስለሆነም እየተስፋፋ የመጣው ቲዎሪና የሰራተኛው መደብ በሙያ ማህበሩ መደራጀት በኢንዱስትሪ ውስጥና ከዚያ ውጭ ከከበርቴው መደብ ጋር በተጠሪዎቹ አማካይነት ቁጭ ብሎ ለመደራደር የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጠረ። ይህ የሚያሳየው ምንድነው ? አንድ ህብረተሰብ መስመሩን እንዳይስት፣ ወይም ደግሞ የጥቂቶች መጨፈሪያ እንዳይሆን ከተፈለገ የግዴታ ሁሉንም አስተሳሰቦች ሊያስተናግድ የሚችል ምሁራዊና ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው።

በዘመናችን የዲሞክራሲን ትርጉምንና ተግባራዊነት ስንመለከት፣ ተግባራዊነቱ ተወካይን በመምረጥና በመመረጥ የሚገለጽ ቢሆንም፣ ይህ ዐይነቱ ሂደት ሊገለጽ የሚችለው በሶስት ኦርጋኖች መሀከል ባለው የስራ-ክፍፍል ነው። ይህም ማለት ኤክስኪዩቲቭ፣ የህግ አውጭና ህግ አስፈጻሚ። ሌሎች ዲሞክራሲያዊ ኢንስቲቱሽኖች በሙሉ በዚህ ስር ሲጠቃለሉ፣ በተለይም ከ1980ዎች ጀምሮ እያየለ የመጣው መንግስትንና ፓርላሜንትን የሚቆጣጠር ሰፋ ያለ የሲቪክ ማህበራት አለ። ስለሆነም በነፃ መደራጀት፣ ሃሳብን መግለጽ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና ህዝብንና አካባቢን የሚጎዱ ነገሮች እንዲቆሙ ማድረግ በትግል የተገኙ ብቻ ሳይሆኑ፣ የጠቅላላው የህብረተሰብ ጉዞና ዕድገት አጋዥ እንደሆኑ ማየት የተቻለው ከብዙ ውጣ ውረድና በከፍተኛ ምሁራዊ ተሳትፎ አማካይነት ነው። እዚህ ላይ አስቸጋሪ የሚሆነው የዲሞክራሲ አነሳሰና ትግል፣ የጥያቄው አቀራረብ በጣም ስፊና ውስብስብ ስለሆነ በማቲማቲካል ሞዴሎች ማቅረብ አይቻልም። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ እጅግ አሳሳች ከመሆኑም የተነሳ ወደ ማይሆን አቅጣጫ እንድናመራ በማድረግ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረግውን ትግል እንድንዘነጋ ያደርገናል። በሌላ አነጋገር፣ ዲሞክራሲ የሚጨበጥና የሚዳሰስ አይደለም፤ የምንለማመድበት፤ የምንኖርበት፣ ስሜታችንንና ቅሬታችንን የምንገልጽበት፣ የሚያሳስበንና የሚያስጨንቀንን ወደ ውጭ አውጥተን ለመወያየት የሚያስችለን መሳሪያ ነው። ስለዚህ ነው ዲሞክራሲን አታየውም፣ ትኖርበታለህ፣ ትለማመድበታለህ፣ የህይወትህ አንደኛው አካል እንዲሆን ታደርገዋለህ የሚባለው። ስለሆነም የዲሞክራሲ ምንነት በቁጥር የሚለካ ወይም በማቲማቴካል ሞዴል የሚረጋገጥ አይደለም። ከዚህ ስንነሳ የዲሞክራሲ ጥያቄ፣ ሶሻል ጀስቲስንና የኢኮኖሚ ጀስቲስን፣ እንዲሁም የፖለቲካ ጀስቲስኝ የሚያካትት ሲሆን፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ የግዴታ ዲሞክራሲያዊ ሆነው ከተዋቀሩ ኢንስቲቱሽኖች ጋር መያያዝ አለባቸው። ይሁንና ግን የካፒታሊዝም ዕድገትና መስፋፋት የሰው ጭንቅላት ከሚሸከመው በላይ በመሆኑ፣ አብዛኛው ህዝብ አቅመ-ቢስ እየሆነ እንደመጣ እንመለከታለን። በተለይም ጊዜ ወስዶ ምሁራዊ ጥናት የሚያደርገው በጣም ጥቂቱ ስለሆነ፣ ሰፊው ህዝብ በቴክኖከራቲክ ጽንሰ-ሃሳብና የአሰራር ዘዴ እየተደናበረና ግራ እየተጋባ ነው። ከዚህ በሻገር የመንግስት መኪናዎች ይበልጥ በኤክስክቲቩ የሚመሩ ስለሆነና፣ የሚሊታሪ ኢንደስትሪያል ትስስር(Military Industrail Complex) ስር እየሰደደና እየተጠናከረ በመምጣቱ፣ የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲን እያዳከመው፣ ተጠሪዎች የህዝብ ተወካዮች መሆናቸው ቀርቶ የራሳቸውን ህይወት ማራዘሚያ መድረክ አድርገውታል ማለት ይቻላል። ስለሆነም ስልጣንን የጨበጡ ፓርቲዎችና ፕሬዜደንቱ ወይም ጠቅላይ ሚኒስተሮች የአንድ አገር ተጠሪ ቢመስሉም፣ በቀጥታ የሚያንፀባርቁት የኢንዱስትሪና የሚሊተሪ ትስስርን ጥቅምና፣ በፀጥታ ኃይሎች አማካይነት የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን እየተሰጣቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነትን የሚያስፋፉና መንግስታትን የሚያወድሙ ሆነዋል። የከበርቴው የሊበራል ዲሞክራሲ እሴትና የክርስቲያን ቫልዩ የሚባለው አብዛኛው የምዕራብ አውሮፖና የአሜሪካ የሚኩራሩበት፣ በመሰረቱ ባዶ አነጋገር ነው ዛሬ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት አለው እየተባለ የሚለፈፈው። በዚህ መልክ ለሁላችንም የማይታይ ቀስ በቀስ ስር የሰደደ የመንግስት ግልበጣ ተካሂዷል ማለት ይቻላል። ያም ሆኖ ግን ይህንን የሚያጋልጡና የሚዋጉ ኃይሎችና ድርጅቶች እንደ እንጉዳይ ፈልተዋል። ስለሆነም ለዕውነተኛ ዲሞክራሲና ነፃነት የሚደረገው ትግል ያለቀለት ሳይሆን፣ ገና በአዲስ መልክ የሚቀጥል መሆኑን እንገነዘባለን።

ወደ አገራችን ስንመጣ ለዲሞክራሲ ያለን ግንዛቤ አስቸጋሪ የሚሆነው፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄን ስልጣን ላይ ያሉ ኃይሎች በቀላሉ ስልጣን ለመስጠት ወይም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለመገንዘብ ዝግጁ አለመሆናችን ነው። በዚህም ምክንያት የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ የረጅም ጊዜ ምሁራዊ ትግልን እንደሚጠይቁና፣ ለዚህ ደግሞ ከፍተኛ መስዋዕትነት መከፈል እንዳለበት አለመገንዘባችን በምን መልክ ትግሉን ማካሄድ አንዳለበን ለመወያየት ዝግጁ ባለመሆናችን ትግሉን ውስብስብ እያደረገው መጥቷል። ከዚህም በላይ የስልጣን ጥያቄ ከስልጣኔና ከዕውነተኛ የዲሞክራሲ ፕሮጀክት ጋር ሊያያዝ ባለመቻሉ ትግሉ ለስልጣን ብቻ የሚደረግ ትግል እንጂ ለመሰረታዊ ለውጥ እንዳይደለ ሁኔታዎችን ለተከታተለ ሊገነዘብ ይችላል። በሌላ ወገን ግን በአብዛኞቻቸን የተደረሰበት ድምዳሜ አንድን አገዛዝ በኃይል አስወግዶ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ይቻላል የሚለው አደገኛ ግንዛቤ ነው። ምክንያቱም እነዚህ በአጭር መንገድ፣ ይሁንና የዲሞክራሲን አፈታት የባሰውኑ የተወሳሰበና አድካሚ የሚያደርገውን ትግል የሚያካሂዱት እኛ የተሻለ የዲሞክራሲ ግንዛቤ አለን ከሚለው አስተሳሰብ የመነጨ አጉል ስሌት ነው። ይህ እንደማይሆን ደግሞ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮችና በአገራችንም ጭምር ተረጋግጧል። ምክንያቱም እነዚህ በአጭር መንገድ ስልጣን ለመያዝ የሚታገሉ ኃይሎች ራሳቸውም የዚያው ያልተገለጸለት ህብረተሰብ ውጤት በመሆናቸው አጭሩን መንገድ እንመርጣለን ብለው ሲነሱ የባሰውኑ ትግሉን ውስብስብ በማድረግ ሁላችንም በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ችግር ውስጥ ይከቱናሎ። በተጨማሪም እነዚህ የተሻለ የዲሞክራሲ ግንዛቤ አለን የሚሉ ኃይሎች ለግልጽ ውይይትና ክርክር የተዘጋጁ አይደሉም። የአገራችንን ያለፉትን አርባና ሃምሳ ዓመታት ትግል ስንመረምር፣ ለዲሞክራሲና ለመብታችን እንታገላለን ብለው የሚነሱ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ስልጣን ከጨበጡ በኋላ የባሰውኑ አፋኘና ገዳይ እንደሚሆኑ ነው። ህብረተሰብን ከማዘበራረቅና የድህነቱን ዘመን ከማራዘም በስተቀር ሌላ የሚታያቸው ነገር የለም። በዚህም የተነሳ ስንትና ስንት መቶ ዓመታት የተገነቡ እሴቶችንና ባህሎች እንዲበጣጠሱ በማድረግ ህዝቡ በውዥንብር ዓለም ውስጥ እንዲኖር ያደርጉታል። በኤርትራ ምድር የሰፈነው ፋሺሽታዊ አገዛዝና፣ ወደ ፋሽሺዝም የሚያመራው የአገራችን አመራር ከተሳሳተ የትግልና የዲሞክራሲ አስተሳሰብ የመነጨ አጉል አካሄድ ነው። ህዝቡን በዘለዓለማዊ ፍጥጫና መፈራራት ውስጥ በመክተት ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ፍዳውን እንዲያይ የተደረገው መጀመሪያውኑ የዲሞክራሲ ጥያቄ ከዕውነተኛ የጭንቅላት ወይም የመንፈስ ተሃድሶ ጋር ሊያያዝ ባለመቻሉ ነው። የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ከጭንቅላት ምርምርና ተሃድሶ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል ይገኛል ተብሎ ውሳኔ ስለተደረሰበት፣ ይህ በራሱ ከረጅም ጊዜ አንፃር ሌላ የጭቆና አገዛዝ ምንጭ ሊሆን በቃ።

በአገራችን ምድር በስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች ስለዲሞክራሲ ሲነሳ የሚያስፈራቸው ነገር የዲሞክራሲን አስፈላጊነት አለመገንዘባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ዲሞክራሲያዊ መብት ተፈጥሮአዊ መብትም መሆኑን ለመረዳት ባለመቻላቸው ነው። በዚህም የተነሳ የወታደሩ አገዛዝ ስልጣን ከጨበጠ በኋላ በዲሞራሴ ጥያቄ ላይ እንዴት እንዳንገራገረና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ የባሰውኑ ወደ አፋኝና ወደ ጨፍጫፊነት እንዳመራ እንገነዘባለን። ህዝቡ እየነቃ ሲመጣና ህዝባዊ ድርጅቶች እንደ አሸን መፍለቅ ሲጀመሩ እሱ ብቻ ሳይሆን ቢሮክራሲውም ጭምር መርበድበድ ጀመሩ። ተራማጅ ነን በሚሉ ኃይሎች ዘንድ የተደረገውን መገዳደል ትተን፣ ወርቃማ ጎኑን ስንመለከት ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝባዊ ድርጅቶች እንደ አሸን የፈለቁበትና፣ እንዲሁም የዕደ-ጥበብ ሙያዎችና የልዩ ልዩ ብሄረሰብ-ባህሎች የዳበሩበት ዘመን የዲሞክራሲ ጭላንጭል በሚታይበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር። ውስጥ ባለው የአገዛዝ ቅራኔና፣ በተለይም ደግሞ ተራማጅ ነኝ በሚለው ኃይል መሀከል ከወረቀት ትግል ይልቅ የጠብመንጃ ትግል ነው የሚያዋጣው በማለት የትግሉን አቃጣጫ ለመቀየር ሙከራ ባይደረግ ኖሮ፣ የዲሞክራሲው ጥያቄ ሌላ መስመርን ይዞ ይጓዝ ነበር። ብዙ ምክንያቶች ተደራርበው፣ በተለይም ደግሞ ተራማጅ ነኝ ይል የነበረው ኃይል ኃሉን አስተባብሮ በቀና መንፈሰ በዕውቀትና በሃሳብ ዙሪያ በመሰባሰብ ቢታገል ኖሮ የወታደሩን አገዛዝም መቆጣጠር ይቻል ነበር። ይህም ሊሆን ባለመቻሉ ቀስ በቀስ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሲወጣ የዲሞክራሲ ጥያቄ የባሰውኑ መታፈን ጀመረ። በመጀመሪያ አገርን ማዳን በሚለው ስር በተለይም አድርባዩ ሁሉ በመሰባሰብና ቢሮክራሲው ጉያ ስር በመውደቅ ከቀይ ሽብርና ከነጭ ሽብር በተረፉት ላይ ዘመቻውን በማካሄድ አገሪቱን የምሁር አልባ ለማድረግ በቃ። እዚህ ላይ ያልገባኝ ነገር፣ መኢሶን በኢህአፓ ላይ፣ ወይም ኢህአፓ በመኢሶን ላይ ሲዘምቱና ሲገዳደሉ ሰውን ብቻ ሳይሆን ዕውቀት ያለውንም ምሁራዊ ኃይል እንደገደሉ አለመገንዘባቸው ነው። ደርግም ሆነ የተቀሩት ለደርግ ያደሩ የማርክሲስት ሌኒንስት ድርጅቶች ነን ባዮች አባሎች የተረፈውን ምሁር እየጠቆሙ ሲያስገድሉ በኋላ አገሪቱ በምን ኃይል ለመገንባት እንደሚችሉ አለመረዳታቸው ነው። እነ ኮለኔል መንግስቱም ቀሪውን የተማረ ኃይልና ጂኔራሎችን ሲገድሉ ምን ታይቷቸው ነው? ለመሆኑ አንድን አገር ባልተማረ ኃይል መገንባት ይቻላል ወይ? እሲከዚህ ድረስ ምርር አድርጎ ርስ በርስ የሚያጫርስ ነገር ምንድነው ? በየትስ አገር ነው የታየው? የሚገርመውና የሚያሳዝነው ነገር ሁሉም ኃይሎች በማርክሲዝም ሌኒኒዝም እየማሉ ነበር ግድያውን ያጧጥፊት የነበረው። ያም ሆነ ይህ፣ ይህ የመረረ ሁነታ ያለፈ ቢመስልም፣ ዛሬም ቢሆን ከቂም በቀላቸው ያልተላቀቁ ኃይሎች እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል። እነዚህ ኃይሎ አብዮቱ ተቀለበሰ ከተባለ በኋላ ተቀምጠው ጊዜ ውስደው ለምን ያህ ሁሉ ጭፍጨፋ እንደተካሄደና ታሪክ እንደወደመ ጥያቄ ለመጠየቅና ግልጽ ውይይት ለማድረግ ስላልቻሉ የጭንቅላት ተሃድሶ ሊያገኙ አልቻሉም። አንዳንዶቹ አሁንም ቢሆን በድሮው ዓለም ውስጥ በመዋኘት ለቀና ውይይትና ለግልጽነት በሩን ሁሉ ዘግተዋል። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ የፈለገውን ያህል ለአገሬ ነው የምታገለው ቢባልም እያንዳንዱ ለሰራው ስራ ተጠያቂ መሆኑን እስካላመነ ድረስና፣ የመጥፎም ሆነ የጥሩ ድርጊቱ ተካፋይ መሆኑን እስካለተገነዘበ ድረሰና ራሱን ለመጠየቅ ዝግጁ እስካልሆነ ድረስ ይህ ዐይነቱ ግትርነት ሊዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ያጨናግፋል። አገርም ባላፈበት የትግል ዘዴ፣ -ትግል ካልነው፟- ሊገነባ አይችልም። ስለዚህም ዛሬ አዲስና ሌላ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የወደቅን መሆናችንን በመገንዘብና ከድሮው ህልም በመላቀቅ አስተሳሰባችንን በመለወጥ ለአዲስ ህልምና ለአዲስ ዓላማ መነሳት ያለብን ይመስለኛል። አይ ያልተወራረደ ሂሳብ ስላለብን እሱን ካላጠናቀቅን ወደፊት ማምራት አንችልም የምንል ከሆነ ትርጉም ለሌለው ለራሳችን ጥቅም ወይም ዓላማ ነው የምንታገለው ማለት ነው። ይህ ደግሞ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ላይ እንደመዝመት ይቆጠራል። ቀናውን መንገድ እንከተላለን የምንል ከሆነ ደግሞ ቂም በቀልን ብቻ ሳይሆን፣ ከገባንበት የድርጅት አምልኮ መላቀቅ አለብን። ራሳችንን ከድርጅት አምልኮ ስናላቅቅ ብቻ ነው ዕውነተኛ ነፃነትንና፣ ካንት የሚለውን ፍሪ ዊል ማዳባር የምንችለው። ይህን ካልኩኝ በኋላ ትንሽም ቢሆን ወደዛሬው አገዛዝ ልምጣ።

የወያኔ አገዛዝ ስለ ዲሞክራሲና ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው የተበላሸ ግንዛቤ ዛሬ የተከሰተ ሳይሆን ወይም አዲስ ነገር ሳይሆን፣ የድርጅቱ ባህርይ ሆኖ ተቆራኝቶት የኖረ ነው። ራሱ በብሄረሰብ ደረጃ መደራጀትና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የጥገና ለውጦች ላይ መዝመቱ የሚያረጋግጠው ወያኔ የቱን ያህል ፀረ-ዲሞክራቲክና ፀረ-ዕድገት ኃይል መሆኑን ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ከእንደዚህ ዐይነቱ በብሄረሰብ ደረጀ ከተደራጀ ቡድን ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መለመኑ ወይም መጠበቁ እጅግ የዋህነት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ድርጅቱ በምሁራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በማለፍ የዲሞክራሲን ምንነት በመረዳት ወደ ውጭ ወጥቶ ለህዝብ ያስተማረና ለጋራ ትግል እጁን የዘረጋ እልነበረም። ከሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በመተባበር ወታደራዊው አገዛዝን ሲዋጋ፣ የትግል አጋሮቹን የስልጣን መወጣጫና መጠቀሚያ ለማድረግ እንጂ በመሰረቱ እነሱን እንደ ትግል አጋሮቹ በማየት አብሮ በእኩልነት ለመግዛት አልነበረም። በመሆኑም እንደ ብሄረሰብ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ለስልጣን መወጣጫ ያገለገሉና የኋላ ኋላ ደግሞ ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች እሱ በሚፈልገው መልክ ተግባራዊ የሆኑ ናቸው። በመሆኑም የክልል አስተዳዳሪዎች ቢያንስ የራሳቸውን ውስን መብት በማግኘት አካባቢያቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ ተደርገዋል። በሌላው ወገን ደግሞ ራሳቸው የክልል ተወካዮች በምሁር ደረጃ የዳበሩና በራሳቸው የሚተማመኑ ስላይደሉ አገዛዙ ጋር በእኩል ደረጃ በመደራደር መብታቸውን በማስከበር የክልላቸውን ሀብት በማንቀሳቀስ ለየብሄረሰባቸው የኑሮ መሻሻልን ሊያመጡ አልቻሉም። የክልል አስተዳዳሪዎች በሀብት ሲደልቡና በቪላ ቤት ሲኖሩ፣ አሁንም ህዝቡ መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት አቅቶት ሲሰቃይ ይታያል። የየመንደሮችንና የከተማዎችን ሁኔታ ለተመለከተ በብሄረሰብ ነፃነት ስም አገራችን የቱን ያህል የኋሊት ጉዞ እንደምታደርግ መረዳቱ ቀላል አይደለም። ስለዚህም ከዛሬው አገዛዝ ጋር ተወዳድረን እሱን በምርጫ አሸንፈን፣ ወይንም የውጭው ኃይል ጣልቃ በመግባት አስታርቆን የስልጣን ተጋሪ በመሆን ዲሞክራሲን እናመጣለን የሚለው አካሄድ አደገኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፣ የድህነቱን ዘመን ለብዙ መቶ ዐመታት እንዲያራዝመው እንደማድረግ ይቆጠራል። የነፃነትንና የዲሞክራሲን፣ እንዲሁም የዕውነተኛው የስልጣኔ ፕሮጀክት ህልማችንን ከወያኔ አገዛዝ ባሻገር ተግባራዊ እንደሚሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። ከዚህ ስንነሳ ብሄራዊ ዕርቅ ያስፈልጋል እየተባለ የሚናፈሰው የትግል መፈክር እጅግ አሳሳችና፣ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል የሚየዘናጋና ውስብስብ የሚያደርገው ነው። ጸቡ በወያኔና ተቃዋሚ ነኝ በሚለው ኃይል መሀከል ያለ ሳይሆን፣ ያለው ችግር ስልጣኔን፣ ዕድገትን፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትንና ዕውነተኛ ነፃነትን በሚጠላው አገዛዝና፣ ዕውነተኛ ነፃነትንና ስልጣኔን በሚመኘው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መሀከል ነው። ትግሉ አገርን ከሚያፈርስ፣ ታሪክን ከሚያበላሽና ከውጭ ኃይሎች ጋር እጅና ጓንቲ በመሆን ህዝባችን በዘለዓለማዊ ጨለማ ውስጥ እንዲኖር ከሚያደርገው ኃይል ጋር የሚደረግ የነፃነት ትግል ነው። ስለሆነም፣ የብሄራዊ ዕርቅ ያስፈልጋል የሚሉ ኃይሎች የማይገባቸው ሎጂክና ሳይንስ አለ። ይኸውም የብሄራዊ ዕርቅ ከተባለ፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ ያካሄደውን የተበላሸና አገርን የመቸብቸብና፣ ለውጭ ኃይሎች የጦር ካምፕ በመስጠት ሌላ ህዝብ እንዲጨፈጨፍ የሚያደርገውንና፣ ጠቅላላውን የኒዎ-ሊበራል ፖሊሲ ፕሮጀክት በሙሉ አምኖ እንደሚቀበሉ የተገነዘቡ አይመስለኝም። ይህ ዐይነቱ አካሄድ የስልጣን ድርሻ ሲኖረን እኛም አብረን አናቦካለን፣ አገርራችንን ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ እናጠፋለን እንደማለት ሊተረጎም ይችላል። አይ ይህንን ለማለት አይደለም የምንፈልገው ከተባለ ደግሞ በሰፊውና ሎጂካዊ በሆነ መልክ ተብራርቶ መቅረብ አለበት። ይህ እስካልሆነ ድረስ የፖለቲካ መድረኩ በሚሆኑ በማይሆኑ መፈክሮችና አርዕስቶች በመያዝ ሰፊውን ህዝብ ግራ የሚያጋባ ይሆናል።

የወደፊቱ የዲሞክራሲ ፕሮጀክት ላይም ስንመጣ እንዲያው የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው የተቀበለው የህግ የበላይነት ብቻ ነው ሊሰራ የሚችለው ብለን ነገሩን አደፋፍነን መሄድ አንችልም። በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው ማን ነው? ብለን መጠየቅ አለበን። ሰባት ቢሊዮን ህዝብ፣ ይህንን እወክላለሁ የሚለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወይም ሰለጠንኩኝ የሚለው የምዕራቡ ዓለም? ይህ ጉዳይ በግልጽ መቀመጥ አለበት። በየአገሮች እንደታየው፣ በተለይም ደግሞ እንደ አገራችን ባለ በብዙ ሽህ ችግሮች በተተበተበ አገር ተራ ዲሞክራሲና ምርጫ እንዲሁም መደብለ ፓርቲ የሚባሉት ፈሊጦች አንድ እርምጃ እንኳ ፈቀቅ ሊያደርጉን አይችሉም። እነዚህ አባባሎች ወይም መፈክሮች በመሰረቱ የኢሊት መፈክሮች ወይም ህልሞች በመሆናቸው ሰፊውን ህዝብ ሙሉ በሙሉ የስልጣን ባለቤት ሊያደርጉት አይችሉም። ማንነቱን እንዲረዳና ፈጣሪ እንዲሆን አያግዙትም። ስለዚህም ህዝባችንን የስልጣን ባለቤት ወደሚያደርገው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገር መቻል አለበን። ይህ ማለት ግን ፓርሊሜንተሪ ዲሞክራሲ አይስፈልግም ለማለት ሳይሆን፣ በዛሬው ወቅት ፓርቲዎች በርዕይና በፖሊሲ ደረጃ በደንብ ተደራጅተው በማይታገሉበት አገርና፣ ከፍተኛ ምህራዊ ክፍተት በሚታይበት አገር ውስጥ የመደብለ ፓርቲን ስርዓት ለመፍጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው። በሌላ አነጋገር የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ የተሰበጣጠረውን ኃይል ሊያሰባስብ የሚችል መድረክ በመፍጠር ለሚቀጥሉት ሃምሳ ዓመታት አገሪቱን በጸና መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሁለ-ገብ ፕሮግራም መንደፍ አማራጭ የሌለው ሂደት ነው ብዬ እገምታለሁ። የተወሳሰበው ችግራችን በመደብለ ፓርቲና በምርጫ ሊፈታ የሚችል አይደለም። ወይም አንዱን ድርጅት ወይም ግለሰብ ውክልና በመስጠት ሊቀርፍ የሚችል አይደለም። የአገራችንን የተወሳሰበ ችግርና የመጭውን ትውልድ ዕድል ከራሳችን ጥቅምና ዝና ባሻገር ማየት ያለብን ይመስለኛል። ስለሆነም ሁለ-ገብና የሰፊውን ህዝብ የማሰብ ኃይሉን አዳብሮ ነፃነት እንዲሰማው የሚያደርገውን የዲሞክራሲ ስርዓት መዘርጋት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ይህ ዐይነቱ የተቀደሰ ዓላማ ወይም ህልም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ከዛሬው አገዛዝ ባሻገር ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ የሬናሳንስ እንቅስቃሴ ወይም በሁሉም መልክ የሚገለጽ ምህራዊ እንቅስቃሴ መፈጠር አለበት። በተለይም ይህ ዐይነቱ እንቅስቃሴና ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገው ትግል ለፖለቲካ ስልጣን እንታገላለን በሚሉ ኃይሎች የሚካሄድ ሳይሆን ከፖለቲካ ውጭ ያሉ በተለያዩ ሙያ በሰለጠኑ አማካይነት ብቻ ነው። በህብረተሰብ ታሪክ ግንባታም የተረጋገጠው ይህ ነው። ለፖለቲካ ስልጣን እንታገላለን የሚሉ ሰፊውን ህዝብ በቀን ተቀን የአገር ግንባታ ውስጥ ማሳተፍ የቻሉና የሚያስችሉ ስላይደለ ይህ ዐይነቱ የነሻነት ትግል መስመር ሊይዝ የሚችለው በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት ብቻ ነው። የብዙዎች አገሮች ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች የኒዎ-ሊበራል አጀንዳዎች ስለሆኑ አንድን ህዝብ የስልጣንና የስልጣኔ ባለቤት አያደርጉትም ። በረቀቀ መንገድ ነፃነትን የሚያሰገፍፉና፣ ሀብት እንዲበዘበዝ የሚያደርጉ ናቸው። ስለሆነም ከኤሊት ዲሞክራሲ ወደ ህዝብ አሳታፊ ዲሞክራሲ የምናመራበት ዘዴ ለውይይትና ለጥናት መቅረብ አለበት።

ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገትና ለማን!

ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት የተጻፉ ሊትሬቸሮች ሺህ በሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። ቁጥራቸውም ከመብዛቱ የተነሳ ትክክለኛውን ሃሳብ ለመጨበጥ በጣም ያስቸግራል። በሌላ ወገን ግን ሰለ ኢኮኖሚ ዕድገት በሚወራበት ወይም በሚጻፍበት ጊዜ ከተወሰነ ርዕዮተ-ዓለም ክልልና የኃይል አሰላለፍ ውጭ ነጥሎ ማየት አይቻልም። ምክንያቱም በአውሮፓ ህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ በየጊዜው አዳዲስ ኃይሎች ብቅ ሲሉ አዲስ ከተፈጠረው የኃይል አሰላለፍ ጋር ለማቀናጀት ሲባልና፣ አንዳንድ ምሁራን የዚህኛውን ወይም የዚያኛውን መደብ ወይም የህብረተሰብ ክፍል ጥቅም እናስጠብቃለን ብለው ስለሚታገሉ፣ ኢኮኖሚክስም በርዕዮተ-ዓለም ትግል ክልል ውስጥ በመካተቱ የአንድን ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ሁኔታ በዚህኛው ወይም በዚያኛው የቲዎሪ መነጽር ማየት አስገደደ። ስለሆነም፣ በተለይም ኢኮኖሚክስ ከሌሎች የትምህርት ዐይነቶች እየተነጠለ ሲወጣ የባሰውኑ በርዕዮተ-ዓለም መነፅር መታየት ጀመረ። ኢኮኖሚክስም ሆነ ሌሎች የሶሻል ሳይንስ ትምህርቶች እሴተ-አልባ(Value-free) መሆናችው ቀርቶ ተጣመው በመቀርብ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገው ትግል አስቸጋር እየሆነ ሊመጣ ቻለ።

በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የህብረተሰብ ግንባታንም ሆነ የኢኮኖሚ ዕድገትን ታሪክ ለተመለከተ ዕድገት የሚባለው ነገር ስልጣን ላይ ባለው ኃይልና ከሱ ጋር በጥቅም ከተቆላለፉ ኃይሎች ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው ከጥንታዊቱ የግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ ዕኩልነትና(Justice) ሚዛናዊነት ለአንድ ህብረተሰብ መረጋጋትና በሰላም መኖር አስፈላጊ ናቸው እየተባለ ትግል የተጀመረው። ምክንያቱም ስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች አብዛኛውን ጊዜ በፍልስፍናና በሳይንሳዊ ህግ ስለማይመሩ የተወሰነ የኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተልና የራሳቸውን ጥቅም ስለሚያስቀድሙ የግዴታ ለድህነት መፈልፈል በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጥቂቱ ሀብት በመቆጣጠር የጠቅላላውን ህዝብ የመኖርና ያለመኖር ዕድል እንዲወስን መንገዱን ያመቻቻሉ። የኢኮኖሚ ታሪክን መጽሀፎች ላገላበጠ በዚህ ዙሪያ የተደረገውን ዕልክ አስጨራሽ ትግል መመልከት ይቻላል።

ወደ ቲዎሪ ጥያቄ ስንመጣ ደግሞ፣ አንድ አገር ሀብት መፍጠር የምትችለው እንዴት ነው? በሚለው ዙሪያ የተለያዩ አስተሳሰቦች ይስፋፉ ነበር። በፊዚዮክራቶች፣ የመጀመሪያው የነፃ ገበያ ፍልስፍና አፍላቂዎች ወይም ላሴዝ-ፌር (Laissez faire) አሳቢዎች አመለካከት የአንድ አገር ሀብት ምንጭ እርሻ ነው የሚል ነው። ከገበሬው በስተቀር ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ምርታማ(Unproductive) ያልሆኑና፣ ከእርሻ የሚመጣው ትርፋማ ምርት(Surplus product) ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተከፋፍሎ የተቀረው እንደገና ለመዋዕለ-ነዋይ በመዋል በዚህ አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይመጣል ይሉናል። በመርከንታሊስቶች ዕምነት ደግሞ የአንድ አገር ሀብት ዋናው ምንጭ ከውጭ ንግድ የሚመጣ ወርቅና የወርቅ ክምችት ሲሆን፣ ተፈጥሮና ምድርንም ጨምሮ የሰው ጉልበት የሀብት(Wealth) ማመንጫ ዘዴዎች ናቸው ይሉናል። የሰው ጉልበት ወይም ኃይል ወይም ስራ ከተፈጥሮ ውስጥ ቆፍሮ የሚያወጣውን ንጥረ-ነገር በኃይል አማካይነት ወደ ፍጆታ ጠቀሜታ ከለወጠውና፣ የተወሰነው ደግሞ ለመዋዕለ-ነዋይ ከዋለ በዚህ አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይመጣል ይላሉ። በኋላ ብቅ ያሉት የመርከንታሊስት ኢኮኖሚስቶች ነገሩን በማስፋፋት፣ አንድ ህብረተሰብ በኢኮኖሚ ዕድገት አማካይነት እንዲተሳሰር ከተፈለገ የማኑፋክቱር አብዮት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ያረጋግጣሉ። ምክንያቱም ከእርሻ ይልቅ የማኑፋክቱር መስክ የሚስፋፋና የሚያድግ እንዲሁም የማባዛት ኃይል ስላለው ዕውነተኛ የስራ-ክፍፍልና የኢኮኖሚ ዕድገት በዚህ አማካይነት ብቻ ነው ሊፈጠር የሚችለው ብለው ይነግሩናል። በተግባርም የታየው ይህ ነው። የከተማዎች ግንባታ፣ የንግድና የዕደ-ጥበብ መስፋፋት፣ እንዲሁም የከበርቴው መደብ ማደግና ቀስ በቀስም ብሄራዊ ባህርይ እንዲወሰድ መደረጉ፣ አንድ አገር በመገናኛ መንገድ በመተሳሰር ሰፋ ያለ ገበያ መዳበር የቻለው በመርከንታሊስት የኢኮኖሚ ፍልስፍና ወይም ፖሊሲ አማካይነት ነው። ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ነው የኢኮኖሚ ዕድገት መልክ እያየዘ መምጣት የቻለውና፣ ቀስ በቀስም ህብረተሰብአዊ ሀብት(National or Social Wealth) ሊፈጠር የቻለው።

ከቲዎሪ አልፈን ተግባራዊ የሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችስ ስንመለከት፣ ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ የመጣው የመርከንታሊስቶች የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው ለካፒታሊዝም ዕድገትና መስፋፋት መንገድ የቀደደው። በጊዜው ቢያንስ ማደግ ለሚፈልጉ ኃይሎች መንገዱ ክፍት ነበር። እንደ አገራችን ሁኔታ በጎሳ የተገደበና አፋኝ አልነበረም። እንዲያውም ንቁ የሚባሉ ኃይሎችን(Active forces) በተለያየ መንገድ መርዳትና፣ የውስጥን ገበያ ደግሞ ከውጭ በሚመጣ ዕቃ እንዳይጥለቀለቅ አስፈላጊ የጉምሩክ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ የፖሊሲውና የሀብት ክምችቱ አንድ ዘዴ ነበር። ይህ ዐይነቱ በብዙዎቹ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ተግባራዊ የሆነ ፖሊሲ ነው ለካፒታሊዝም ዕድገት ዕምርታ በመስጠት ህበረተሰቡን ማስተሳሰር የተቻለውና ክልላዊና ሌሎች ገደቦችን በማስወገድ ብሄራዊ አንድነት እንዲፈጠር የተደረገው። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ነው ግለሰቦችም የመፍጠር ጭሎታቸውን ማዳበር የቻሉትና፣ አገሮችም እንደ አገር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ህብረተሰብና ነፃነት እንዳላቸው ግንዛቤ የተገባበት። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ነው ብሄራዊ ነፃነት(National Sovereignty) የሚባለው እንደ መሰረተ-ሃሳብ በመወሰድ ማንኛውም አገር በሌላኛው አገር ጣልቃ መግባት እንደማይችል የተደረሰበትና፣ አገዛዞችም የራሳቸውን ነፃነት መጠበቅና መከላከል እንዳለባቸው ስምምነት የተደረሰበት። የብሄራዊ ኢኮኖሚ ቀስ በቀስ እያለ ከተገነባና ህብረተሰብአዊ መተሳሰርና የፈጠራ ስራዎች እየተጠናከሩና እየዳበሩ ሲመጡ የእነ አዳም ስሚዙ የነፃ ገበያና ንግድ ፖሊሲ መስፋፋት ጀመሩ። የራስን ጥቅም ማሳደድ የሚለው ሃሳብ በመስፋፋት፣ ይህ ዋናኛው የሰው ልጅ ውስጣዊ ባህርይ ወይም አብሮት የተፈጠረ ነው በማለት ኢምፔሪሲስታዊ አመለካከት ያላቸው ፈላስፋዎች ይህንን ውስን አመለካከት በማስፋፋት ዋናው የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል አድርገው መስበክ ጀመሩ። ስለሆነም የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ በሃሳብና በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈለቁትና መዳበር የጀመሩት በእንግሊዝ አገር ነው። በአዲሱ የዩሊታሪያን አስተሳሰብ መሰረት ህብረተሰብአዊ ሀብትን ለመፍጠር ወይም አንድን ምርት ለማምረት ሶስት ነገሮች መጣመር አለባቸው። ይኸውም፣ የሰው ኃይል፣ ካፒታልና መሬት ናቸው። በተጨማሪም የረቀቀው የሰው እጅ (Invisible Hand) ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ አዳም ስሚዝ ያትታል። ይህ እንዳለ በመወሰድ የትምህርትቤት ኢኮኖሚክስ በዚህ መልክ ረቀቀ። ሁላችንም በዚህ መልክ ሰለጠን።

ወደ ማርክስ ቲዎሪ ስንመጣ ደግሞ፣ የመርከንታሊሲቶችን ሃሳብ በመቀበልና፣ የአዳሚ ስሚዝንም የቫልዩ ቲዎሪ በማስፋፋት፣ የስራ ኃይል ወይም የሰው ጉልበት ዋናው የዋጋና፣ ተከታታይ የካፒታሊዝም ዕድገት መሰረት እንደሆነ ያብራራል። ከዚህ ጋር በማያያዝ፣ የካፒታሊዝምን አፀናነስና ዕድገት፣ ደረጃ በደረጃ ካተተ በኋላ ውድድር(Competition) የካፒታሊዝም ዋናው የዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል መሆኑን ያመለክታል። በዚህም አማካይነት የምርት ኃይሎች ወይም የማምረቻ መሳሪያዎች በየጊዜው እየተሻሻሉ በመምጣት ለካፒታሊዝም ዕድገት ምጥቀትና መስፋፋት ይሰጡታል። የደሞዝ ዕድገትና፣ የኑሮ መሻሻል፣ እንዲሁም የፍጆታ ማምረቻ ዋጋ መቀነስ ከማምረት ወይም ከማሺኖች ምርታማነት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ መገንዘቡ ከባድ አይሆንም ። በተጨማሪም ፋይናንስ ካፒታል ወይም ብድር ለካፒታሊዝም ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል በመሆን፣ ካፒታሊዝም ከዝቅተኛ የምርት ክንዋኔ ወደ ከፍተኛና ወደ ተወሳሰበ ደረጃ መድረስ እንደቻለ እንመለከታለን። የፊናንስ ካፒታል በምርት ክንዋኔና በአዳዲስ መዋዕለ-ነዋይ ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ተጠቃሚውንም በማካተት የካፒታሊዝምን ዕድገት ማፋጠን እንደቻለ ግልጽ ነው።

ለመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ካለሳይንስና ካለቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ወይ? አብዛኛውን ጊዜ ስለሶስተኛው ዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት ችግር የሚጽፉ ኤክስፐርቶች የሚዘነጉት ነገር ሳይንስና ቲኮኖሎጂ በኢኮኖሚ ዕድገት ውስ|ጥ ያላቸውን ሚና ከቁጥር ውስጥ ባለማስገባት ነው። በተለይም የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚስቶች ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ቦታ አይሰጡትም። ለማንኛውም ብዙ ሳናወጣና ሳናወርድ፣ ወይም በትንሹ ስናሰብ የሰው ልጅ ዕድገት ከቲክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ነው። የተሻሉ የምርት መሳሪያዎች መጠቀም ሲጀምር የበለጠና በብዛት ማምረት ይችላል። ስራውንም ያቃልላል። በዚህም ምክንያት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መሆን ከጀመሩ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የምርት መሳሪያዎች መብዛት ብቻ ሳይሆን በጥራትም እየመጠቁም መምጣት ችለዋል። በዚያውም መጠንም የዛሬ ሁለት መቶ ዐመት መመረት የማይችሉ ምርቶች፣ የተለያዩ የሰብልና የፍራፍሬና እንዲሁም የቅጠላ ቅጠል ዐይነቶች ተስፋፋተው ይገኛሉ። ይህም የሚያረጋግጠው በቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የሰው ልጅም የማሰብና የማምረት ኃይል ሊያድግ እንደቻለ ነው። ከዚህ ስንነሳ ኋላ-ቀርነትና የረሃብን ምክንያት መገንዘቡ ቀላይ አይደለም። 1ኛ) ዕውነትኛ ዕውቀተ ባልተስፋፋበት አገር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሊፈጠሩና ህብረተሰብአዊ ባህርይ ሊወስዱ አይችሉም። 2ኛ) ሰፊው ህዝብ ካልተማረ ራሱ ምርትን በተለያየ ዐይነት ማምረት ብቻ ሳይሆን አንድንም ምርት በብዛት ማምረት ያቅተዋል። ኢምፔሪካል ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት የሰው ልጅ ዕድገት በቁጥር መቀነስና ረሃብና ድህነት መወገድ፣ ከሰፊው ህዝብ የመማርና የማሰብ ኃይል ጋር የተያያዙ እንደሆነ ነው። ስለሆነም ሰፋ ያለና ዕውነተኛ ዕውቀት ዋናው የስልጣኔ ቁልፎች ናቸው። በሁሉም መልክ የሚገለጽ ዕውቀትና በአንድ ክልል ብቻ ያልተገደበ ዕውቀት ነው አንድን ህዝብ ሀብት ፈጣሪ የሚያደርገውና ከድህነትና ከረሃብም ሊያላቅቀው የሚችለው።

ወደ ሌሎች ቲዎሪዎች ስንመጣ፣ የአንድ አገር ሀብት(Wealth) የሚወሰነው ወይም የሚመነጨው በሶስት ነገሮች አማካይነት ነው። 1ኛ) ኃይል(Energy)፣ 2ኛ) ቴክኖሎጂና 3ኛ) ፈጠራ፣ እነዚህ አንድ ላይ ሲጋጠሙ ወይም ሲጣመሩ አንድ አገር ተከታታይነት ያለው ሀብት መፍጠር ይችላል። በተለይም የዚህ ቲዎሪ አራማጅ የስኮቲሹ ተወላጅና በኬሚስትሪ የኖቭል ዋጋ ተሸላሚ የነበሩት ፕሮፌሰር ፍሪድሪሽ ሶዲ ናቸው። ፕሮፌሰር ሶዲ ስለ ኃይል በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያለውን ሚና በማስመር፣ ኃይልን መቆጠብና ኃይልን በመለወጥ መሀከል ያለውን ዲያሌክታዊ ግኑኝነት በማያያዝ፣ የአንድ አገር ዕድገት ሊወሰን የሚችለው በኃይል አማካይነት ብቻ እንደሆነ በግሩም መልክ ያብራራሉ። በመሆኑም ፀሀይ የኦርጋኒክና ኦርጋኒክ ያልሆኑ ነገሮች አንቀሳቃሽ ኃይልና ለዋጭ በመሆን የሰውን ልጅ ዕድገትና የተፈጥሮን ምንነት ወሳኝ ነች። በፀሀይ ኃይል ወይም ሙቀት አማካይነት ነው ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉና ፍሬ ሊያበቅሉ የማይችሉ ዛፎች ሊያድጉና ሊያብቡ፣ እንዲሁም ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉት። በምድር ውስጥ የተከማቹት እንደዲንጋይ ከሰልና ዘይት የመሳሰሉት የጥሬ ሀብቶችና ሊሎችም ንጥረ-ነገሮች የብዙ መቶ ዐመታት የፀሀይ ክምችት ውጤቶች ናቸው። ከዚህ በመነሳት የአንድ አገር ዋናው እንቅፋት ይህንን የተፈጠሮ ህግ አለመረዳት ሲሆን፣ የጭንቅላት ወይም የአዕምሮ ድህነት ያለባቸው አገሮች ፍዳቸውን የሚያዩት የተሳሳሰተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተላቸው እንደሆነ ያስተምሩናል። ምክንያቱም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ፀሀይንም ሆነ ውሃ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ንጥረ-ነገሮችን መጠቀም ያለመቻል አንድን አገር ወደ ዘለዓለማዊ ድህነት እንደሚያመራው ነው። ፕሮፊሰር እሪክ ራይነትም በሌላ መልክ ለአንድ አገር ዕድገት ጥሬ-ሀብት ተትረፍርፎ መገኘቱ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ የማሰብ ኃይልና፣ ለስራ ወይም ለስልጣኔ ያለው ፍላጎት ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ነው የሚያስተምሩን።

ከላይ አጠር ብሎ ከተዘረዘረው አስተሳሰብ ስንነሳ በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት በምናወራበት ጊዜ ግልጽ ማድረግ ያለብን ነገሮች አሉ ማለት ነው። በደፈናው የኢኮኖሚ ዕድገት ብሎ ነገር የለም። ከዚህ ጋር መያያዝ ያለበት ጉዳይ፣ ኢኮኖሚ ዕድገት ለምንና ለማን? ብለን መጠየቅ አለብን። ኢኮኖሚ ዕድገት ለዕድገት ሲባል፣ ወይስ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰውን የማቴሪያል ፍላጎት አሟልቶ በአስተሳሰብም ደረጃ እንዲያጎለምሰውና ፈጣሪም እንዲያደርገው? ይህንን በሚመለከት የትምህርትቤት ኢኮኖሚክስ የሚለው ወይም የሚሰጠን መልስ የለም። እንዲያው በደፈናው ሁሉም ነገር በገበያ አማካይነት ብቻ ሊወሰን እንደሚችል ለማረጋገጥ ይሞክራል። ለምሳሌ በትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ ማንኛውም ህብረተሰብ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ምግብ፣ ንፁህ ውሃና መጠለያ ማሟላት እንዳለበትና፣ ከዚያ በመነሳት አንድን አገር መገንባት እንዳለበት አያሰተምርም። በሁለተኛ ደረጃ፣ በትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ፣ ከተማ ምን እንደሆን አይታወቀም። የሚታወቀው ገበያ ብቻ ነው። ማለትም ገበያ ካለ ቦታና ሰዓት(Space and Time) የሚካሄድ ነው። በሶስተኛ ደረጃ፣ የትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ ህብረተሰብ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የሚተሳሰረው? እንዴትስ ነው የስራ-ክፍፍል የሚቀናጀውና የሚዳብረው? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ አያቀርብም፤ አይመልስም። ከዚህ ስንነሳ የኢኮኖሚ ዕድገት በራሱ ብቻ እንደሚጓዝ አድርገን መመልከት ከፍተኛ ስህተት ነው። ፕላቶን እንደሚያስተምረን፣ አንዱ የወረውረውን ማስተጋባት ሳይሆን፣ መመርምርና መፈተን ያስፈልጋል። ከዚያ በመነሳት የራስን ውሳኔ መስጠት ሳይንሳዊው መንገድ ነው።

እስቲ ከቲዎሪ ተላቀን ወደ ተግባራዊ ነው ወደምንለው ነገር እንመጣ። ባለፉት 25 ዐመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ የመጣ ነው ወይ? ይህንን ጥያቄ መመለስ የምንችለው፣ ከየትኛው ሁኔታ በመነሳት ነው? የምንገመግመው ወይም የምንለካው? የሚለውን ጥያቄ ካስቀመጥንና ለመመለስ የቻልን እንደሆን ብቻ ነው። ሌሎች እጅግ አብስትራክት የሆኑ የጂዲፕ አሰላልና የምርት ጭማሮና ከውጭ የመጣን ልዩ ልዩ ወደ ምርት ውስጥ የሚገቡ በግማሽ የተፈበረኩና የጥሬ-ሀብት ጉዳዮችን ትተን እንዲያው በደፈናው ስንመለከት ከተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል አንጻር፣ ምናልባት 1% ለሚጠጋው የህብረተሰብ ክፍል „የኢኮኖሚ ዕድገት“ መጥቶለታል ማለት ይቻላል። ይህ ዕድገት በትላልቅ ህንጻዎች፣ በሆቴል ቤቶች ስራና ጋጋታ፣ በመንገድ ስራ፣ የስኳርና የቢራ ፋብሪካ የሚገለጽ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከመንግስት ጋር በሺህ ድሮች የተቆላለፉ አየር በአየር ንግድ ውስጥ በመሰማራት፣ የውስጥን ጥሬ-ሀብት በመሸጥ የገቢያቸው መጠን በፍጥነት የተተኮሰ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የነዚህ ህብረተሰብ ክፍሎች የፍጆታ አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ከውጭ የሚመጣው የቅንጦት ዕቃ የማህበራዊ ስታተሳቸውን ከፍ አድርጎለታል። ይህንና ከዚህ ጋር የተቆላለፈውን ሀብት ጨራሽ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ነው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተብሎ የሚወደስልን። ይህንን ዐይነቱን የኢኮኖሚ ዕድገት በመርከንታሊስቶችም ሆነ በፕሮፌሰር ፍሪድርሽ ሶዲና ፕሮፌሰር ኢሪክ ራይነርት የኢኮኖሚ ቲዎሪ መነፅር ስንመረመረው አዲስ ሀብት የፈጠረ አይደለም። ቲክኖሎጂያዊ ምጥቀትን ያመጣ አይደለም። የውስጥ ገበያ እንዲስፋፋና እንዲዳብር ያደረገና የሚያደርግ አይደለም። ለስራ ፈላጊው ሰፊ ህዝብ የስራ መስክ የከፈተና የሚከፍት አይደለም። የባሰ ጥገኝነትንና፣ ኢኮኖሚያዊ መዝረክረክን ያስከተለና የሚያስከትል ነው። ሀብትን የሚያባክን ነው። በተፈጥሮና በሰው ልጅ ላይ ዘመቻ የከፈተ „የኢኮኖሚ ዕድገት“ ነው። ይህንን ዐይነቱን ዕድገት ጥፋት እንለዋለን። የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል በማባለግ፣ ሰፊውን ህዝብ በማድኸየት አቅመ-ቢስ ያደረገ ነው። እንደሚታወቀው አንድ አገር እንደ አገር የምትከበረው ከሁሉም አንፃር ማደግ ስትችል ነው። ግርማ ሞገስ ያላቸው ከተማዎችና የመኖሪያ ቤቶች ሲሰሩና ለሰፊው ህዝብ ሲዳረሱ ነው። ህዝቡ የመፍጠር ችሎታው ሲዳብር ነው። እንደ አንድ ዜጋ ሲታይና ጠንካራ ህብረተሰብ ለመመስረት ሲችል በእርግጥም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አለ ማለት ይቻላል። ልዩ ልዩ መናፈሻ ቦታዎችና ሲዘጋጁለትና የኬነትና ቤተ-መጻህፍቶች ሲቋቋሙለት ኢኮኖሚው ማደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ህዝቡም አዲስ አስተሳሰብ ማዳበር ይችላል። የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ አይኖርም፤ ፍቅርና ልዩ ልዩ መንፈሱን የሚያረኩ ነገሮችም ያስፈልጉታል። ከማያስፈልጉ ነገሮች እንዲቆጠብና ውድ ወንድሙን እንደሰው እንዲያይ ከተፈለገ በሳይንስ የተጠና ባህልም መዳበር ከኢኮኖሚው ዕድገት ጋር መያያዝ ያለበት ጉዳይ ነው። የዛሬው በወያኔ አገዛዝና እንዲሁም በኒዎ-ሊበራል ኤክስፐርቶችና አማካሪዎቹ ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ ማጅራት መቺዎችንና ማፊያ መሳዮችን የፈለፈለና ድህነትን ያስፋፋ ነው። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው በሪፖርተር ላይ የወጣውን ዘገባ መመልከቱ ሁኔታው የቱን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለመረዳት ያስችለናል።

ከዚህ በመነሳት እኛ ኢትዮጵያውያን ምሁር ሆን አልሆን ለምን ዐይነት ሀብረተሰብና ለምን ዐይነት አኮኖሚ ነው? የምንታገለው ብለን መከራከር አለብን። እኛን የሚያሳሰብን የዚህኛው ወይም የዚያኛው ብሄረ-ሰብ ነፃ መውጣትና አለመውጣት አይደለም። እኛን የሚያሳስበን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው የአርሞው፣ የአማራው፣ የትግሬው፣ የወላይታው፣ የጉራጌው… ወዘተ የኑሮ ሁኔታ ነው። እኛን የሚያሳስበንና አንጀታችንን የሚያቃጥለን ሺህ በሺህ ለአረብ አገሮች በመንግስት የሚሸጡት ልጆቻችንና እህቶቻችን ህይወት ነው። የሚያሳስብን በመንገድ ላይ የሚያድረው፣ ከቆሻሻ እየለቀመ የሚበላው፣ የዕፅ ሱሰኛ እንዲሆን የተገደደው ልጃችን ህይወት ነው። እኛን የሚያስጨንቀን የህዝባችን ኑሮ መጨለሙ ነው። እኛን የሚያሳስበን የአገራችን ውድመትና መቸብቸብ ነው። ህዝቡ እንደ አንድ ዜጋ እንዳይተሳሰር መደረጉ ነው። እኛን የሚያሳስበን ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዳይጎናፀፍና ዕድሉን ወሳኝ እንዳይሆን መደረጉ ነው። በዚህ ዐይነቱ ውጥቅንጡ የወጣ ስርዓት ግለሰብአዊ መብቶች መጣሳቸው ነው የሚያስጨንቀን። ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መሪ የሌለው መደረጉ ነው ሌት ከቀን እንቅልፍ የነሳን። የሚያሳስበን ያረጀ የብሄረ-ሰብ ጥያቄ ሳይሆን የዘጠና ሚሊዮኑ ህዝብ ዕድል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከ50ና ከ100 ዐመት በኋላ ኢትዮጵያችን ምን ትመስላለች የሚለው? ነው የሚያሳስበን። የዚኸኛው ወይም የዚያኛው ፓርቲ ለስልጣን መውጣትና መራወጥ አይደለም አንጀታችንን የሚያቃጥለን። ባጭሩ የአገርና የህዝብ ደህንነት፣ ከሁሉም አቅጣጫ ዕድገት አለመኖር፣ ዕድገት እንዳይኖር ከውጭ የተሸረበብን ሴራና በጣም የደከመው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነው እንቅልፍና ዕረፍት የነሳን።

የዛሬው ሁኔታ በዚህ መልክ አፍጦ አግጦ ባለበት ወቅት አንዳንድ ምሁራን ስለተከታታይነት(Sustainable Economic Growth) ስላለው የኢኮኖሚ ዕድገት ይጽፋሉ። በየጊዜው ይህንን በማስመር የሚጽፉት ምሁራን፣ 1ኛ) ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ምን እንደሆነ ለተራው ሰው ሲያስረዱ አይታዩም። 2ኛ) ባለፉት 25 ዐመታት በአገራችን ምድር ተግባራዊ የሆነውን የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትችታዊ በሆነ መልክ በመመርመርና በመጻፍ አላስተማሩንም። 3ኛ) ዛሬ አገራችን ምድር አፍጦ አግጦ ለሚታየው ድህነትና ረሃብ ዋናው ምክንያት ምን እንደሆነ አልነገሩንም። እንዲያው በደፈናው ብቻ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ያስፈልጋል እያሉ ነው የሚነግሩን። ይህንን ካላብራሩልን ደግሞ የውር ድንብራችን ነው የምንራመደው ማለት ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ከዚህ ዐይነቱ አባባል የምንረዳው ኢኮኖሚው አድጓል፣ ይሁንና ግን ተከታታይነት የለውም የሚል ድምደማ ነው። በመሰረቱ የተለያየ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም። በተለያዩ አገሮች የተለያዩ የህብረተሰብ አወቃቀሮችና አገዛዞች ቢኖሩም፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋናው አንቀሳቃሽ ሃይል ፈጠራ፣ ከዚህ የሚፈልቁት ሳይንስና ቴክኖሎጂዎች ናቸው። ከዚህም ባሻገር ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዳይ የቁጥር ብቻ ሳይሆን የዐይነትም ጭምር ነው። እነዚህ ጉዳዮች ደግሞ የግዴታ ከሰው ልጅ የኑሮ መሻሻል ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። ስለተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት በምናወራበት ጊዜ፣ ስለሪሶርስ አጠቃቀም ጉዳይ፣ ስለ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፈጠር ጉዳይ፣ ስለ አካባቢ ደህንነት ጉዳይ፣ ስለ ከተማዎችና መንደሮች በደንብ በፕላን መታቀድና መገንባት ጉዳይ፣ ስለ ፍሳሽና ስለቆሻሻ መጣያ ወይም ሪሳይክል ማድረጊያ ጉዳዮች… ወዘተ. ማተት ያስፈልጋል። በተለይም የተፈጥሮን ሀብትና ጫካንም በስነስርዓት መንከባከቡና መጠበቁ የተከታታይ ዕድገት ዋናው ዕምብርት ነው። ንጹህ አየር መተንፈስና ጤንነታችንም ሊጠበቅ የሚችለው የአካባቢያችን ሁኔታ ከሳይንስ አንፃር እየተጠና እንክብካቤ ሲደረግለት ብቻ ነው። በተጨማሪም የወንዞችንና የባህሮችን ህይወት መንከባከቡ እጅግ አስፈላጊ ነው። እንደሚባለው አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ወንዞች የተመረዙና እየደረቁ የሄዱና ህይወትም የሌላቸው ናቸው። ለዚህ ሁሉ በብዙ የስልጣኔ ተመራማሪዎችና የኳንተም ሳይንስ ምሁራን የተደረሰበት ድምዳሜ ለተከታታይ ዕድገት ዋናው ወሳኝ ኃይል ንቃተ-ህሊና( Quantum Consciousness) ነው። በሌላ አነጋገር ዝቅተኛ ንቃተ-ህሊና በሰፈነበት አገር ስለ ተራ ዕድገትም ሆነ ስለ ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማውራት አይቻልም።

ስለሆነም ተከታታይነት ስላለው የኢኮኖሚ ዕድገት በምናውራበት ጊዜ፣ 1ኛ) የመንግስትን መኪናና የሚከተለውን ፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ መመርመር ያስፈልጋል። ይህ እንቅፋት ሆኖ ከታየ ደግሞ የግዴታ ይህንን መለወጥ ያስፈልጋል። አንድ አገዛዝ እንደፈለገው በራሱ „ሎጂክ“ እየተመራ የአገርን ሀብት ሊመዘብርና ህዝብን ሊያደኸይ አይችልም። መብትም የለውም። 2ኛ) ተከታታይነት ስለሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት ሲነሳ ወይም ሲጻፍ የግዴታ ስለነፃነትና ስለዲሞክራሲ አስፈላጊነት ማንሳትና መጻፍ ያስፈልጋል። 3ኛ) ተከታታይነት የሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት የወጭ ኃይሎችን ግፊታዊ ጣልቃ-ገብነት ይቃወመል። በሌላ አነጋገር በዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው ግፊት ተግባራዊ የሚሆን ፖሊሲ አንድን አገር የግዴታ መቀመቅ ውስጥ እንደሚከታት ማስተማር ያስፈልጋል። ይህም ማለት በአገራችን ምድር ተከታታይነት የሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት ተግባራዊ ሊሆን የሚችለውና ህዝባችንም የዕውነተኛ ስልጣኔ ባለቤት የሚሆነው ከዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው መዳፍ ስር ሲላቀቅና በከፍተኛ ምሁራዊ ኃይል በግሎባል ካፒታሊዝም አማካይነት በሁሉም አቅጣጫ የሚመጣብንን ግፊት መቋቋም የቻልን እንደሆን ብቻ ነው። መልካም ንባብ !!

ፈቃዱ በቀለ
fekadubekele@gmx.de

ኢህአዴግና የመልካም አስተዳደር እጦት ብሩህ ቦጋለ ከስዊዘርላንድ

$
0
0

ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት የምትታወቅበት ነገር ህዘቦቸ አብሮ የመኖር የመተሳሰብ፣ የመከባበር እና የሠላም ተምሳሌት መግለጫ መሆናን ነው፡፡ እኛ የተለያየ ጎሳ ያለን የአትዮጵያ ልጆች ባለፈው ታሪካችን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች አሉን የዛሬ ማንነታችን ላይ አሻራ ያላቸው ማንም በቀላሉ ሊለያያቸው የማይፈቅዱለት የጋራ የሆነ ታሪክ ያለን የብዙ እምነቶችና ባህሎች ባለቤቶች ነን አንዱም ጎሳ የሌነውን ጎሳ ባህል ቋንቋውን ማንነቱን አክብሮ በሠላምና በፍቅር የኖረ ህዘብ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ /ህውሃት ስልጣኑን ከተቆናጠጠበት ከ1983 ማግስት በአጠቃላይ የአፊድሪ መንግስት ከተቋቋመበት ጀምሮ ባሉት አመታት ውስጥ ኢህኢዴግ እራሱ በመለመለቸው የህዝብ ተወካዮች አማካይነት በህግ መንግስቱ ጉባኤ ኅዳር 29 ቀን 1987 በስራ ላይ እንዲውል ብሎ ካፀደቃቸው ህጎች ውስጥ አንዱ አጨቃጫቂና አከራካሪ የነበረው አንቀፅ 39 ላይ የተቀመጠው የብሔሮች ብሔረሰቦች ሕዝቦች መብት በሚለው ስር ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሠብ ሕዝብ የራስን ዕድል በራሱ የመወሠን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው የሚለው አዋጅ ነበር፡፡

ይህን አዋጅ ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን እና ስለወደፊቷ አንዲት ኢትዮጵያ በሚጨነቁ የአትዮጵያዊነት ስሜት በሚሠማቸው የፖለቲካ አዋቂዎች በወቅቱ ህጉ ከህዝባችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በአንፃሩ ሲታይ ከአትዮጵያ የባህልና አኗኗር ጋር ይጋጫል በማለት ተቃወሙ ይሁን እንጂ ኢህዴግ/ህወሃት ጆሮ ዳባ ልበስ ከማለቱም ሌላ ይባስ ብሎ በተቆጣጠረው የመገናኛ ብዘሁን አዋጁ ለግለሠብ እና የብሔር ብሔርሰቦችን መሠረታዊ መብቶች ለማስከበር ባህሎችና ሀይማኖቶች ካላንዳች ልዮነት እንደራመድ፣ጥቅሙን፣ መብቱን ነፃነቱን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግ እንደሁም ልማትን የሚያሳልጡ ናቸው እያለ ይዘምር ነበር፡፡ዛሬም ድረስ ይህን ፕሮፓጋንዳ () ለህዝቡ በሠፊው መለፈፋን አላቆመም፡፡ ወደ እውነታው ስንመጣ ግን የተባለው፤ አሁን ዕየተባለ ያለውና ዕየሆነ ያለው ነገር ግን ፍፁም ለየቅልናቸው፡፡

ዕስኪ ስለ ዕውነት የማንናችን የብሄረሰብ ክፍል ተወላጆች ነን እንደፈለግን ከክልል ክልል ተዘዋውረን ወደ ትግራይ ወይ ወደ ሌላው ክልል ሄደን ስንቶቻችን ነን በቋቋችን ስራ ተቀጥረን መኖርስ የምንችለው?ለዚህም ነው ወትሮም የፀደቀበት አላማ የኢትዮጵያን ኅዝብ ለመከፋፈል ነው የተባለበት ምክንያት፡፡ለምሳሌም መጥቀስ በያስፈልግ ትግራይን የመገንጠል አላማ ይዞ ይንቀሳቀስ የነበረው ህወሀት ዛሬም መንግስት ከሆነ በኃላም የቀድም የጎሳ ስሙን ከለመቀየሩም በላይ ለስልጣን ያበቃቸው አጋር ድርጅቶቹም ባብዛኛው በአንድም ሆነ በሌላ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ከሚሹ ኃይላት በተገኘ ድጋፍ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ለዚህም ነው ዛሬ አህአዴግ/ህወሃት ኤትዮጵያ ከነበረችበት የአንድነትና የአብሮነት ስሜት ውስጥ ለማስወጣት ህዝቡን ወደ ማይፈልገው ጎሳዊ አስተሳሰብ ግጭት ውስጥ ለመስገባት የሚሞክረው፡፡ ይህ ጎሳዊ አስተሳስብና ግጭት ዛሬ ከአሮሚያ ከአማራው ክልል አልፎ ወደጋምቤላ ቤንሻንጉል ጉመዝ ክልል ተዛምቷል፡፡

እነኚህ ጎሳዊ ፅንፈኛ ፀብ አጫሪ ሀይሎች የሚላቸውም ከእራሱ ከአህዴግ/ህዋሀት ጋር የተለያዩ ይምሠሉ እንጂ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው እንጂ ህዝብ እንዳይደለ እንዳልሆነም ሠፊው ህዝብ በገሀድ ያውቃቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት ህዝባችን በከፍተኛ በሆነ የኑሮ ውድነት ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡ ይኸውም ገዢው ፓርቲ በሀገር ውስጥ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉት የምርት ውጤቶች ላይ ዋጋቸውን ከውጭ አገር የጉምሩክ ቀረጥ ተከፍሎባቸው ለታችኛው ተጠቃሚ በሚሸጥበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሀገር ውስጥም ምርት ዋጋ ጣራ ላይ እንዲወጣ መሰረት በመጣል፤ ከሀገር ውስጥ ምርትን ገዝተው ወደ ውጭ ሀገር ኤክስፖርት ለሚያደርጉ ግለሰቦች ገደብ የለሽ ፍቃድ በመስጠት እነዚህ ገደብ የለሽ ላኪ ነጋዴዎች በሀገር ውስጥ የሚገኘውን የሰብል ምርት በየገጠሩ በደላላ እየገቡ በውድ ዋጋ ተሸምተው እየገዙ ወደ ውጭ በሚልኩበት ጊዜ ለከተሜው ሸምቶ አደር ሕዝብ ላይ አቅርቦቱ ዝቅተኛ እየሆነ ይበልጥ ዋጋው ከእለት ወደ እለት እየናረ ይገኛል፡፡

በዚህ አካሄድ መንግስት ከላኪው ነጋዴ ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ ሲሰበስብ ነጋዴው በተመሳሳይ ከፍተኛ ተጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ መሀል አሁንም ተጎጂው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ሸምቶ አደሩ ሆኖ ይገኛል፡፡ ለኔ የሚገርመኝ ሌላው ነገር ደግሞ ይህ መንግስት በሀገር ውስጥ የሚመረቱትን የምርት ውጤቶች ለአከፋፋዮች በኮታ በተመጣጠነ ዋጋ ሽጦ ለታችኝ ህዝብ ክፍል እንዲደርስ በማድረግ ፈንታ እራሱ መንግስት እንደ አንድ የግል ነጋዴ በሞኖፓል የያዘውን ምርት ለሌላኛ አከፋፋይ በጨረታ ይሸጣል፡፡ እንደኔ እንደኔ ይህ መንግስት ይሄን የሚያደርግበት ምክንያት ብዙ ተጫራቾች በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ ተጫራቾች አንዱ ካንዱ ዋጋ አብልጦ ካልተጫረተ የማሸነፍ እድል ስለማይኖረው የግድ ለምርቱ ዋጋ መናር አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ነጋዴው በፈለገው የዋጋ እርከን አሸንፎ ቢገዛ ኪሳራ የለበትም፡፡ ለምን በገዛው ዋጋ ላይ ተተርሶ ትርፉን አክሎበት ለታችኛው ሸማች አቅርቦ አትራፊ መሆኑ አይቀሬ ነውና፡፡ በዚህ አካሄድ መንግስት የሚፈልገውን ገቢ ይሰበስባል፡፡ነጋዴውም ትርፉን ያገኛል ለዛም ነው አሁንም ተጎጂው ሰፊው ሸምቶ አደሩ ህዝብ ነው ለማለት የተገደድኩት፡፡
ከዚህም የበለጠ ልናሰምርበት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር የማናቸውም ምርት ዋጋ እንዲንር ያደረገው አከፋፋዩ ወይም የታችኛው ነጋዴ ሳይሆን አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ብቻ ነው፡፡ ይህ የማይዋጥላቸው ካሉም አንድም ወኪሎቻቸው ወይም አድር ባዮች ወይም ዝቅተኛ የንቃተ ህሊና ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የሀገራችን የእድገት ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማዕከላዊ ባልሆነ የመልካም አስተዳደር እጦት መዛባት ነው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለውጥ የማይታይባትና የህዝቡንም የፖለቲካ አመለካከት እንዳይዳብር በማድረግ ለገዥ ወደቡ ብቻ ተንበርካኪ ሆና መብትና አንድነት ጥቅሙን ማስከበር ተስኖት እንዲኖር ያደረገው፡፡

በተጨማሪም ከመንግስት ፖለቲካ ጭ በሰፊው ህዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ ከስልጣን ፈላጊነት ባሻገር በግል የሚንቀሳቀሱ የበሰሉ ኤክስፐርቶች ብሎም ኢኮኖሚስት አስተያየት ሰጪ ምሁራን ሀሳብ እና አመለካከታቸውን የመግለፅ መብት ያለመከበሩም ጉዳይ ሌላኛው ችግር ነው፡፡ ለዚህም ነው ገዢው ፓርቲ እንደፈለገ ከተቀሩት የታችኛው ህብረተሰብ ክፍል ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ በነጻ ገበያ በሚል ሽፋን በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ታክቲክና ስውር ደባ ተጠቅሞ በግብር መልክ ያላአግባብ በቢሊዮን የሚቆጠር ህጋዊ ልሆነ ገቢ እየሰበሰበ ህዝቡን ባለ ዕዳ እና አሁን ኢትዮጵያ ላለችበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት ውስጥ ተዘፍቃ እንድትቆይ ያደረጋት፡፡

ዝክረ ዲበኩሉ (1) መስፍን ማሞ ተሰማ (ከሲድኒ)

የሄነከን ቢራ ዘረፋ ምስጢር በኢትዮጵያ ሲጋለጥ ክንፉ አሰፋ

$
0
0

የሆላንድ ዜምብላ[1] ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። “መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን…”

በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ። ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። “ከአንባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም።” ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። “ይህ ካልሆነ ግን ማውደሙን እንቀጥልበታለን!” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ይህ ማስጠንቀቅያ ግዙፉ አለም አቀፍ ኩባንያ የሆነው ሄነከን ቢራንም ይመለከታል።
ባለፈው ሳምንት በሆላንድ ብሄራዊ ቴለቭዥን የተላለፈው ዜምብላ ፕሮግራም የሚሊዮኖችን ቀልብ ስቧል። ለዚህም ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ምክንያት፤ የዜምብላ ፕሮግራም በምርመራ ጋዜጠኞች የሚሰራ በመሆኑ እጅግ የሚፈራ እና በሃገሪቱ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ እየወደመ ያለው ይህ ንብረት የተቋቋመው በሆላንድ መንግስት ድጎማ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ ሆላንዳዊ ግብር ከፋይ ገንዘብ በመሆኑ ነው።

የሆላንድ የልማትና ትብብር ሚንስተር ለድሃ ሀገሮች እርዳታ ከመለገስ ይልቅ ወደ ንግድ ድጎማ ፊቱን ባዞረ ግዜ፣ 130 አትራፊ የንግድ ድርጅቶች ድጎማ እየተቀበሉ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከነዚህ ውስጥ ትልቁን የድጎማ ድርሻ የወሰደው ሄነከን ቢራ ነው። ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የሆላንድ መንግስት አንድ ቢሊየን ዩሮ ድጎማ አድርጓል። እንደ ሆላንድ መንግስት እሳቤ፣ ይህንን የልማት ትብብር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከመስጠት ይልቅ ይህንን አትራፊ ተቋም አበራትቶ ስራ በመፍጠር እና በንግድና በስራ ታክስ ሃገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒ ነው።

የዜምብላ ቴሌቭዥን ዘገባ ያጋለጠው ጉዳይ በእጅጉ ያስደምማል። እንዲህ ነው የሆነው። እ.ኤ.አ. በ 2011 ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የቢራ ስራ አዋጭ መሆኑን ስለተገነዘበ ስመ ጥሮቹን በደሌ እና ሃረር ቢራን ገዛቸው። ስራውንም በእጅጉ አስፋፋ። በአኢትዮጵያ የቢራ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ እንዳደገም ዘገባው አስምሮበታል። ትርፉም እንደዚያው አደገ።

በደሌ ቢራ ከመሸጡ በፊት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል ነበር። ሄነከን ከገዛው በኋላ ግን የከፈለው ዘጠኝ መቶ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው። አንድ ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል የነበረው ሃረር ቢራም አሁን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው ያስገባው። ትርፉ ከእጥፍ በላይ እያደገ፣ ግብሩ ከእጥፍ በላይ የመቀነሱ ምስጢር ምን ይሆን?
የግብር ማጭበርበር ጥቆማ የደረሳቸው እነዚህ ጋዜጠኞች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ንግድ ሚንስትር ሄዱ። ምኒስትሩ በዚህ የማጣራት ጉዳይ ላይ ሊተባባራቸው ፈቃደኛ አልነበረም። ከዚያም ወደ ጉምሩክ እና ቀረጥ ቢሮ አመሩ። እዚያም ምንም መረጃ እንሰጥም ይሏቸዋል። ምስጢሩን ለማውጣት የጓጉት እነዚህ ጋዜጠኖች ተስፋ አልቆረጡም። በመጨረሻ ወደ ንግድ ምክር ቤት አመሩ። የዚያ ባለስልጣን የሰጧቸው ምላሽ የሚያስቅ ነው። “የንግድና ትርፍ ዘገባ አይደርሰንም።” አሉ። ታዲያ ንግድ ምክር ቤት ይህንን ካልመዘገበ ምን ይሆን የሚሰራው?
የንግድና የስራ ግብር መቀነሱ ብቻ አይደለም። ቀድሞ በሃረር እና በበደሌ ቢራ ቋሚ ሰራተኛ የነበሩ 699 (44%) ሰራተኞችም ከሄነከን ቢራ ተቀንሰዋል። የሆላንድ መንግስት ስራ ፍጠሩ ብሎ ድጎማ ሲያደርግ፣ ይልቁንም ነባሩን ሰራተኛ ከስራው አፈናቀሉት።

በኢትዮጵያ የሄነከን ተወካይ ሆላንዳዊ ነው። የዜምብላ ጋዜጠኖች የዚህን እንቆቅልሽ ለመፍታት እሱን ማፋጠጥ ይችላሉ። ስለዚህም ወደሱ አመሩ። የገቢና ወጪ ዘገባውን እንዲሰጣቸው ጠየቁት። እንቢ እንዳይል ቸገረው። ምክንያቱም በዚያ ዘገባ የሆላንድ መንግስት የድጎማ ገንዘብ ሰላለበት። እሺ ብሎ ይፋ እንዳያደርገው ደግሞ ምስጢሩ ለህዝብ ሊወጣ ነው። እሱም አለ። “የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ለህዝብ ይፋ እንደማታደርጉት ቃል ግቡልኝ።”

ዘገባውን በእጃቸው ያስገቡት እነዚህ ጋዜጠኖች፣ ዶክመንቱን አለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም አማካሪዎች ጋ ይዘውት ሄዱ። የ አይ. ኤም. ኤፍ. ባለሙያው ወረቀቱን እንዳየ ምስጢሩን ለማወቅ ሰከንዶች አልፈጁበትም። የኢትዮጵያ ህዝብ በታክስ ተዘርፏል። ሰራተኛውም ወገን ከስራው እንዲፈናቀል ተደርጓል።

የመንግስት ባለስልጣን ሃገር ሲዘረፍ እና ወገን ከስራ ሲፈናቀል፣ ጉዳዩን ማፈን መርጠዋል። ምክንያት ቢኖራቸው እንጂ ይህን መረጃ መስጠት ሀገርን የሚጠቅም ነበር። በእርግጥ ይህ የግብር ማጭበርበር ተግባር እነሱ ሳያውቁት ሊሆን አይችልም። “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ!” ነው ነገሩ። እንዲህ እየተዘረፈ ኢኮኖሚው እንዴት ነው በ 11 በመቶ የሚያድገው?
እንግዲህ ይህ በኢትዮጵያ ከዘመቱት 130 የሆላድ የንግድ ድርጅቶች አንዱ ታሪክ ነው። ገቢውና ወጭው በግልጽ የሚታይ፣ ግዙፍ እና አለም አቀፍ ድርጅት። ሄነከን ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ይህንን ያህል ከዘረፈ የሌሎቹ – የማይታወቁት ምን ያህ ይሆን?
የቀድሞው የሆላንድ ልማትና ትብብር ሚንስቴር የነበሩት ጃን ፕሮንክ፣ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከልማት እና እደገት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለሌላቸው የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ክፉኛ ይወቅሳሉ። በተለይ መንግስታቸው በልማትና ትብብር ስም፣ በብሄራው ጥቅም ስም የስብአዊ መብት ረገጣን ችላ ማለቱን ያወግዛሉ።

በልማት ስም በሚሊዮኖች እየፈሰሰ ያለው የሆላንድ ግብር ከፋዮች ገንዘብ በኢትዮጵያ ስራ አልፈጠረም። እንደውም ሰራተኞችን አፈናቀለ። ሀገሪቱን በበለጠ የስራና የንግድ ግብር ተጠቃሚ ያደርጋል ይባል እንጂ ግብሩ በ 70 እጅ ያነሰ ሆኗል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የገበሬው መሬት እየተነጠቀ ለነዚህ ዘራፊዎች መሰጠቱ የህዝብ ቁጣን አስነስቷል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ አመጽ የገዥው ፓርቲ ችግር ብቻ ሳይሆን የሆላንድም ችግር መሆኑን በመግለጽ ዜምብላ ዘገባውን ይደመድማል።

[1] http://zembla.vara.nl/seizoenen/2016/afleveringen/23-03-2016

3 Attachments

ምክር ቢጤ ብአዴን ውስጥ ላላችሁ የአማራ ተቆርቋሪወች (ከይገርማል)

$
0
0

እንደሚታወቀው ብአዴን ከኢሕአፓ ተነጥለው ለወያኔ ባደሩ ሰዎች በወያኔ እገዛና ክትትል ከተመሰረተው ኢሕዴን የወጣ ድርጅት ነው:: ኢህዴን ህብረብሄር የነበረ ድርጅት ስለነበር እንዲህ ያለ ድርጅት በወያኔ የፖለቲካ እምነት ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም:: በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ብቸኛ አማራጭ ነው ብሎ የሚያምነው ወያኔ የህብረብሄራዊ አደረጃጀትን የሚታገስበት አቅም አልነበረውም:: በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለውን ታጋይ አሰባስቦ ከወያኔ ጎን ተሰልፎ ደርግን እንዲወጋ ተልእኮ ተሰጥቶት የነበረው ኢሕዴን ቀዳሚ ተልእኮውን ስላጠናቀቀ ደርግ ከተወገደ በኋላ ንቅናቄው እንዲፈርስና የንቅናቄው ታጋዮች ወደየጎሳ ጉረኗቸው ተሰባስበው ለሁለተኛው ዙር ተልእኮ እንዲሰለፉ አደረገ:: ይህ ሁለተኛው ዙር የጎሳ ድርጅቶች ተልእኮ ዜጎች በየጎሳ ድርጅቶቻቸው ዙሪያ ታቅፈው ጎሳዊ አመለካከታቸውን በማዳበር ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነትን ማደብዘዝና የወያኔን አላማ ማስፈጸም ነበር:: በዚህ መሰረት አማራ የሆኑት የቀድሞው ኢህዴን ታጋዮች ተሰባስበው ብአዴን የሚባል የአማራ ድርጅት እንዲመሰርቱና በዚያ ድርጅት ውስጥ እንዲካተቱ አደረገ::

ነፍጠኛ ተብሎ የተፈረጀው አማራ ከብሄሩ በላይ ኢትዮጵያን የሚወድ: ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ደሙን ለማፍሰስና አጥንቱን ለመከስከስ ወደኋላ የማይል እንደሆነ ስለሚታወቅ ብአዴንን ካለተቆጣጣሪ ብቻውን መልቀቅ ለወያኔ አላማ እንቅፋት እንደመፍጠር ተደርጎ ስለታመነ ይመስላል ድርጅቱን እንዲመሩ በቁልፍ አመራር ሰጭነት ቦታ ላይ የተቀመጡት በሙሉ ወይም በከፊል የሌላ ብሄር (ማለት የሌላ ክልል) አባል የሆኑ ሰዎች እንዲሆኑ ተደረገ:: እኒህ በድርጅቱ የአመራር ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች የህዝባቸውን ጉዳይ ትተው ወያኔ አድርጉ ያላቸውን ብቻ ተግተው በማስፈጸም አማሮች ካለአይዟችሁ ባይ ክልላቸውን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የግፍ ሰለባ እንዲሆኑ አደረጉ::

አማራን መግደል ዶሮን የማረድ ያህል ቀላል ሆነ:: እንወክለዋለን የሚሉት ህዝብ ካለታሪክ ማስረጃና ካለፍላጎቱ ወደሌላ ክልል ሲካለል: ተወልዶ ካደገበት ቀየ ያላግባብ ሲፈናቀል: ንብረቱ ሲወረስ: ሲንገላታና ሲገደል ሳት ብሎት “በአማራ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ይብቃ!” ብሎ ድምጹን ያላሰማ ድርጅት እንዴት የአማራው ወኪል ሊሆን ይችላል!
ከወያኔ አላማወች ውስጥ አንዱ አሁን የአማራ ክልል ተብሎ ከሚታወቀው ክልል ውጪ ያሉትን ክልሎች አማራ አልባ ማድረግና በክልሉ የሚኖረውን አማራ ደግሞ ቅስሙ የተሰበረ ፍጹም ተገዥ ማድረግ ነው::
የብአዴን ባለስልጣናት ይህን የወያኔን አላማ በማሳካት በኩል ዋነኛውን ድርሻ ተወጥተዋል ማለት ይቻላል:: በአቶ በረከት ስምዖን: በአቶ ታምራት ላይኔ: በአቶ አዲሱ ለገሰ: በአቶ ተፈራ ዋልዋና በሌሎችም ሲተላለፉ የነበሩት መልእክቶች መላው ኢትዮጵያውያን በየአካባቢው በሚኖረው አማራ ላይ እጁን እንዲያነሳ የሚቀሰቅሱ ነበሩ:: በሌላ በኩል በአማራው ህዝብ ላይ ተፈጸመ ተብሎ ለሚቀርበው ክስ እኒህ የብአዴን አመራሮች በሜዲያ በመቅረብ አማራ ተኮር የሆነ በደል እንዳልተፈጸመ ማስተባበያወች ሲሰጡና በአንዳንድ አካባቢወች የተፈናቀሉትም ቢሆኑ ”ዘራፊወችና ሌቦች ናቸው” በማለት ሽፋን ሲሰጡ ነበር:: በአማሮች ላይ የተፈጸመው ግፍ ምን ያህል ይሆን!
አሁን አሁን እንደምሰማው ከሆነ እኒያ በብአዴን አመራር ሰጭነት ተሰይመው በአማራው ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍ ሲያቀናብሩና ሲያስፈጽሙ የነበሩት ወንጀለኞች ከብአዴን ተገፍተው ወጥተው አመራሩ በእውነተኛ የአማራ ልጆች ተተክቷል የሚል ነገር አለ:: እየተባለ ያለው እውነት ከሆነ እንዴት ደስ ይላል!

እናንተ ብአዴን ውስጥ ያላችሁ እውነተኛ የአማራ ልጆች: ከ24 አመታ በላይ በአማራ ላይ የተፈጸመው ሰቆቃ ያበቃ ዘንድ ደም መክፈል ካለባችሁ ደም ክፈሉ:: ወያኔወች 7 ሆነው ወጥተው ለአላማቸው በጽናት መታገል በመቻላቸው ለዚህ በቅተዋል:: እናንተ እንደወያኔ የተበላሸ አላማና ግብ ይዛችሁ አይደለም የምትነሱት:: አማራን ከጥፋት መታደግና በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት: ዴሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ብላችሁ የምታደርጉት ትግል ቅዱስ ትግል ነው::
በሀይል ወረራ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ህዝቧን ቅኝ ተገዥ ባሪያ ለማድረግ የመጣውን ጣሊያንን ከኢትዮጵያ ጠራርጎ ለማስወጣት የተደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደነበረው ሁሉ የአንድ ሀገር ልጆችን በዘርና በሀይማኖት ከፋፍሎ መከራ እያወረደ ካለው ወያኔ ጋር የሚደረገው ጦርነትም ቅዱስ ጦርነት ነው:: ወደዚህ ጦርነት ለመግባት ምንም ሊያስፈራችሁ አይገባም:: አማራው ዝም ብሎ በመቀመጡ የቀረለት መከራ ስለሌለ:: ዛሬም ቢሆን አማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ በመላው ኢትዮጵያ መከራ እያዩ ነው::
ወያኔ የወልቃይትን የአማራ መሬት በሀይል ወደትግራይ ካካለለ በኋላ ባለመሬቶችን እያፈናቀለ የራሴ የሚለውን ህዝብ እንዳሰፈረበት ማንም ያውቃል:: “ኧረ እኛ አማራ ነን! ከወገኖቻችን ተለይተን በመሬታችን ላይ ሌሎች እንዲሰፍሩ ተደርጎ እኛ ለባርነት እንድንዳረግ ለምን ይሆናል::” ብለው ወልቃይቴወች ከመጮሀቸው በፊት “ወልቃይት የአማራ መሬት ነው: ወልቃይቶችም አማሮች” ብሎ ሊከራከር ይገባ የነበረው ብአዴን ነበር::
አሁንም ቢሆን ያንን ማድረግ ይቻላል:: የአማሮች መብት የሚረገጥበትን ስርአት ማገልገል ብሎም ከጠላቶቹ ጋር ተባብሮ የራሱን ቤተሰብ ማሰቃየት ተቀባይነት የለውም ብቻ ሳይሆን ህሊናንም የሚቧጥጥ የእብድ ተግባር ነው::
በአማራ ባህል ሰው የሚኖረው ለራሱ ብቻ አይደለም:: በተለይ ወንድ ልጅ ደም መላሽ: ለሀገርና ለወገን መከታ ነው ተብሎ ይታመን ስለነበር ወንድ ልጅ ሲወለድ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ጎረቤትም ደስ ይለው ነበር:: ዛሬ ላይ ከጠላት ጋር አብሮ የራሱን ቤተሰብ እንዳይፈራገጥ እጅና እግሩን ጠፍሮ ይዞ የሚያሰቃየው ከዚያው ከህብረተሰቡ አብራክ የወጣው ልጅ መሆኑ “ምን አይነት ጊዜ ላይ ደርስን!” ያሰኛል:: የወገኑ ጥቃት ሳይቆጨው ይባስ ብሎ ደግሞ ደም ከጠማቸው ወፈፌወች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የራሱን ሰው የሚያሰቃይ ሰው ምን አይነት ሰው ሊባል ይቻላል! አማራ የሚታወቀው በዚህ መልኩ አልነበርም::
በብአዴን ውስጥ ጊዜ ቦታውን ያስጨበጣችሁ አማሮች ለወገናችሁ በመቆም ይህን አጋጣሚ ልትጠቀሙበት ይገባል:: ወያኔ ሰላም ካልወደደ ምንም ማድረግ አይቻልም:: የፈለገው ቢደረግ በአንድ ወገን ትእግስት ብቻ ሰላም ሊሰፍን አይችልም:: ስለዚህ ቁረጡና ከህዝባችሁ ጎን ቁሙ:: እመኑኝ መላው አማራ ከጎናችሁ ይሰለፋል:: ይህን ስታደርጉ ብቻ ነው ህዝባችሁን ከጥፋት ልትታደጉ ራሳችሁንም ከህሊና ጸጸት ነጻ ልታወጡ የምትችሉት:: ትግላችሁን ስኬታማ ለማድረግ
1. በክልሉ በፌደራል ደህንነት ስም የሚንቀሳቀሱትን የወያኔ የደህንነትና የአፈና ቡድኖች መለየትና በስልት ማራቅ
2. በድርጅታችሁ ውስጥ ያሉትን ለወገን ደንታ የሌላቸውን አጋሰሶች: አስመሳዮች: አወናባጆች: ልፍስፍሶች: ነገር አመላላሽና እምነት የማይጣልባቸውን ሰዎች በስልት ማግለልና ድርጅታችሁን ማጽዳት
3. በሰራዊቱ: በደህንነት: በፌደራል ፖሊስና በሌሎች ወሳኝ የመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያሉትን አማሮች በተጠና መንገድ የትግሉ አጋር ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት
4. በየደረጃው ባሉት የሀላፊነት ቦታወች ላይ በሀላፊነት ሊቀመጡና አመራር ሊሰጡ የሚችሉትን ሰዎች በጥንቃቄ መምረጥ
5. በየገጠሩ ቀበሌ የሚኖሩት ወጣቶች የመሳሪያ አጠቃቀም የውትድርና ት/ ት እንዲያገኙ ማድረግ
6. በደርግ ጊዜ የነበሩትን የኢትዮጵያ ወታደሮች: ከወያኔ ጦር የተቀነሱትንና በተለያየ ምክንያት ከፖሊስና ከመከላከያ የተገለሉትን የሰራዊት አባላት አማራን በመታደግ አላማ ዙሪያ ማሰባሰብና ማስታጠቅ
7. ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖረው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ብአዴን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በማገዝ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብትና እኩልነት የሚረጋገጥባት ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሚደረገውን ትግል ደግፎ እንዲቆም ጥረት ማድረግ
8. የአማሮች እንቅስቃሴ ለሌሎች ክልሎች ስጋት እንዳይመስል የዲፕሎማሲ ስራ መስራት
9. ሕብረ ብሔር አደረጃጀት ያላቸው የተቃዋሚ ሀይሎች ወያኔንና ስርአቱን ለማስወገድ ለሚደረገው ግብግብ ጠንካራ አጋሮች መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል:: ለእኒህ ሀይሎች በአማራ ላይ የደረሰውን በደልና የወያኔን እኩይ ስራ ለመተረክ ጊዜ መውሰድ አያስፈልግም: ከማንም በፊት የተገነዘቡና ጩኸታቸውን ያሰሙ እነሱ ስለሆኑ:: አካባቢን ወይም ጎሳን እንወክላለን የሚሉት ድርጅቶች ጋርም መነጋገርና መግባባት ላይ መድረስ ተገቢ ነው
10. የትግራይ ህዝብ በአማራ ላይ የደረሰውን በደል እንዲረዳ: የወያኔን እኩይ ተግባር ገልጦ እንዲያይ: የተዋደደብንን ልጓም በማውለቅ: የተጫነብንን ጭቆና በማስወገድ: የአንድ ሀገር ልጆችን ከፋፍሎ ሆድና ጀርባ ያደረገንን ጠላት ወደታሪክነት ለመቀየር ለሚደረገው ትግል የድርሻውን እንዲያበረክት የዲፕሎማሲ ስራ መስራት:: “እኛ ካልኖርን አማራ ያጠፋሀል” የሚለውን የወያኔ ቅስቀሳ የትግራይ ሕዝብ አምኖ እንዳይቀበል በተቻለውና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማስገንዘብ
11. ከኤርትራ ጋር ለ30 አመታት የተደረገው ጦርነት ከእንግዲህ በኋላ የሚደገም አይሆንም:: ኤርትራውያን የታገሉለትንና የሞቱለትን ሀገር ማንም በሀይል ሊያሳጣቸው አይገባም:: ለነጻነት ታግለዋል በትግላቸው ነጻነታቸውን ተጎናጽፈዋል:: ኤርትራ እንደሀገር ስትታወቅ በመሬት ላይ የሰፈረ የድንበር መስመር ስላልነበረ ለሁለቱ ሀገሮች የድንበር ግጭት መነሻ መሆኑ ይታወቃል:: ከወያኔ ውድቀት በኋላ እንዲህ ያለ ነገር ሊከሰት አይገባም:: የወደብም ይሁን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ በውይይትና ሰጥቶ በመቀበል መርህ ካልሆነም በሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት ወይም በግልግል ፍርድ ቤት የሚፈታ እንጅ ጦር የሚያማዝዝ እንደማይሆን ማስረዳትና ጥርጣሬን አስወግዶ መተማመንን መገንባት ያስፈልጋል::

12. መንግስታትና አለማቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣት እንዳለበት አምነው እንዲቀበሉና እንዲደግፉ የትግሉን አላማና ግብ ማስረዳት ያስፈልጋል::
የሰው ልጅ በሀገሩ ተከብሮና በፈለገው አካባቢ ተዘዋውሮ በሰላምና በፍቅር መኖር እንዲችል የሰላም: የፍቅር: የአንድነት: የእኩልነት: የፍትህና የዴሞክራሲ አረሞች መነቀል ይኖርባቸዋል:: ብአዴኖች ልብ በሉ! የምትኖሩት ለራሳችሁ ብቻ መሆን የለበትም:: ወገኖቻችሁ በየስርቻው የጣዕር ድምጽ እያሰሙ እናንተ ደስታና ሰላም ልታገኙ አትችሉም:: ምክሬን ብትቀበሉ አማራውንና ሁሉንም ሀገር ወዳድ ሀይል ከጎናችሁ አሰልፋችሁ በታሪክ የመጨረሻውን የግፍ ስርአት አብረን እንሻገራለን:: 7 ሆነው ወጥተው ሀገር ሀገር የሚለውን ወገን እየገደሉ ለድል የበቁት ወያኔወች በድፍረት ስለገቡበት: በጽናትም ስለያዙት እንጅ አላማቸው ሕዝባዊ ስለነበረ አልነበረም:: እናንተ ለምታደርጉት ትግል በአንድ ቀን ጀምበር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ከጎናችሁ ልታሰልፉ ትችላላችሁ::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>