Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? ፈቃደ ሸዋቀና

$
0
0

ሀገራችን መሬት ላይ እንድ ሌላ ግዙፍ የርሀብና የችጋር ዳመና እያንዣበበ ነው። አንዳንድ ቦታም ግዳይ መጣል መጀመሩን እየሰማን ነው። ይህ ችግር በሰብዓዊ ዕውቀትና ሀይል የሚፈታ ሆኖ ለምንድነው እንዲህ እየተመላለሰ የሚጎበኘን? ሌሎች ሀገሮች ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ችግር እየገጠማቸው እንደኛ ለአዋራጅ ጉስቁልናና ልመና አልተዳረጉም። እኛ ጋ ምን የተሰወረብን ነገር አለ? የአፍሪካ የውሀ ሰገነት የምትባልና ከማንም የማይተናነስ የተፈጥሮ ጸጋ ያላት ሀገር ይዘን ለምን እንደዚህ አይነት ሕዝብ ሆንን? በጅጉ የሚደንቅ ነገር ብቻ ሳይሆን በንዴት የሚያቃጥል ነገር ነው። እንደሚመስለኝ ችግሩን የልፈታንበት አንዱ ምክንያት ተገቢና የበሰለ ውይይት የማናካሂድ ህዝብ መሆናችንና ይህንንም ለማድረግ የመወያያና መፍትሄ ፍለጋ ሁኔታ እንዳይፈጠር መንግስታቱ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲሉ የሚፈጥሩት እንቅፋትነት ይመስለኛል። እስከመቼ በዚህ ውርደት እንደምንቀጥል ባሰብኩ ቁጥር የሚያመኝን ህመም ችዬ ነው ይህን ለውይይት የሚሆን ጽሁፍ የጻፍኩት።

ከላይ በርዕሱ ላይ ያነሳኋቸውን ቃላት ብዙ ሰዎች በተለዋዋጭነት ሲጠቀሙባቸው መስማት ያልተለመደ ነገር አይደለም። ችጋርን ወይም ሰፊ መጠን ያለውን የሀገራችንን ርሀብ ድርቅ እያሉ የሚጠሩ ሰዎች ብዙ ናቸው። ርሀብና ችጋርንም እንደዚሁ የሚያደበላልቁ ሰዎች ብዙ ናቸው። ዝቅ ብዬ ለማሳየት እንደምሞክረው ድርቅ የምንለው የአየር ባህርይ ርሀብና ችጋር ብለን ከምንጠራቸው ነገሮች ጋር በመሰረቱ የመንስዔና የውጤትም ሆነ ሌላ የተፈጥሮ (structural) ተዛምዶ የለውም። ይህንን በቅጡ ለመረዳት የቃሎቹን ቀጥተኛና ቴክኒካል ትርጉም የያዙትንም ጽንሰ ሀሳብ በቅጡ መለየት ያስፈልጋል። በዚህ ላይ ይህን የሚያረጋግጡ በርካታ የአለማችንን ተመክሮ መመልከት ይጠቅማል።

ድርቅ (Drought) ባንድ አካባቢና ባንድ ወቅት ባልተለመደ ሁኔታ የሚደርስን የዝናብ መጥፋት ወይም መጠን መዛባት የሚገልጽ ቃል ነው። ከሰው ቁጥጥር ውጭ የሆነ የአየር ሁኔታንና የአየር ሁኔታን ብቻ የሚገልጽ ሀሳብ ነው ማለት ነው። ርሀብ (Hunger) በምግብ አለመብቃት ምክንያት ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸው ሳይሟላ ቀርቶ ውሎ ለማደር ብቻ ምግብ የሚያገኙበት አልፎ አልፎም በምግብ ችግር ምክንያት ለሞት የሚዳረጉበት ሁኔታ ነው። ችጋር (Famine) ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ ምግብና ውሀ በማጣት አካላቸው እያለቀ ሄዶ በብዙ ቁጥር (mass) ለዕልቂት የሚዳረጉበት ሁኔታ ነው። ድርቅ በመሰረቱ ከርሀብም ሆነ ከችጋር ጋር ተፈጥሮአዊ ዝምድና የለውም ብያለሁ። በሌላ አነጋገር ድርቅ የርሀብም የችጋርም የተፈጥሮ ምክንያት አይደለም። በምግብ ራስን ለመቻልና በችጋርም ሆነ በርሀብ ላለመጠቃት የግድ እህል አምራች ሀገር መሆንም ላያስፈልግ ይችላል። ሌላ ነገር ሰርተው ምግባቸውን ከውጭ ገዝተው የሚኖሩ ሀገሮች እሉ። ስለዚህ ድርቅና ኤል ኒኖ የርሀብ ምንጭ ነው የሚለው ልፈፋ ሌላ የጎላ ስሕተትና የችግሩን ዕውነተኛ መንስዔ መሸፈኛ ሆኖ እያገለገለ ነው። እንዲያ ቢሆን ኤል ኒኖና ድርቅ አገር እየመረጡ ችጋርና ርሀብ አያመጡም ነበር።

ድርቅ የተፈጥሮ ሁኔታ ስለሆነ ለመከላከልም አይቻልም። ችጋርና ርሀብ ሰው በጥረቱ ሊከላከላቸውና ሊያጠፋቸው የሚችሉ ነገሮች ናቸው። ብዙ ሀገሮች ይህን በማድረጋቸው ከኛ የበለጠ ድርቅ እየመታቸው እንኳን ችጋርም ርሀብም አይነካቸውም። እድግመዋለሁ ድርቅ የርሀብና የችጋር የተፈጥሮ ምክንያት አይደለም። ይህን የሚሉ ሰዎች ወይ አውቀው እውነተኛውን ችግር መሸፈን የሚፈልጉ ወይ አገላብጦ ማየት የተሳናቸው የዋሆች ናቸው። አንድ ሰው ናላው እስኪዞር ድረስ አልኮል ጠጥቶ ሰክሮ መኪና ሲነዳ ተጋጭቶ ወይም ገደል ገብቶ ቢሞት የሞቱን ምክንያት በደፈናው የመኪና አድጋ ነው ብሎ መሸፋፈን እውነት እንዳልሆነ ሁሉ በኛም ሀገር እየተደጋገመ የሚደርሰውን ርሀብና ችጋር በኤል ኒኖና በድርቅ ማመካኘት ዕውነት አይደለም። ሌላው ቀርቶ ችጋርንና አደገኛ ርሀብን በጊዜ በመለመን ማስቀረት ይቻላል። በሀገራችን የስከዛሬዎቹን ችጋሮች ጥፋት መቀነስ ወይም ማስወገድ ያልተቻለው መንግስታቱ ክብራቸው ወይም ሊፈጥሩ የፈለጉት ገጽታ የተበላሸ እየመሰላቸው ችግሩን በመደበቃቸውም ነው። ባሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች ለርዳታ ሰጭዎች የሚያቀርቡትን አንዴ ራሳችንን ስለቻልን ራሳችን እንወጣዋለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ርዳታ ስጡን የሚሉ የተምታቱ መልዕክቶችን አሁን ሀገሪቱ ውስጥ ግዳይ መጣል ከጀመረው ርሀብ ጋር ስናስተያየው ከዚሁ በባዶ ቤት የአክብሩኝ ባይነት የመግደርደርና የመደባበቅ ተግባር ብዙ አለመራቃችንን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሹማምንት ነጋ ጠባ በሚቲዮር ፍጥነት ኢኮኖሚ አሳደግን ሲሉን የነበረው ፕሮፓጋንዳና ኢኮኖሚው አንድ የድርቅ ወቅት የሚያሻግር አቅም የሌለው ሆኖ መገኘት እንዳሳፈራቸው በግልጽ ይታያል። ይህ እንዳይሆን ቀድሞ ነበር ስታቲስቲክሱን አልሞ መደቆስ የነበረባቸው። ለመሆኑ አንድ አስርት ሙሉ በሚያስጎመጅና አለም እይቶት በማያውቅ መጠን ሲያድግ የነበረ ግብርና እንዴት ያንድ በልግና መኸር ዝናብ ችግር መሻገር ኣቃተው? አለም ለዚህ ጥያቄ መልስ እየፈለገ ይመስለኛል። እስካሁን ለዚህ ጥያቄ መልስ የሰጠ ሹም ግን አላየሁም።

ችጋር በድርቅ ሳይሆን ሰዎች በተለይም መንግስታት አስበው መስራት ያለባቸውን ስራ በዕውቀትና በትጋት ባለመስራታቸው ወይም በተለያየ ምክንያት ትክክለኛ ፖሊሲ ለመከተል ባለመፈለጋቸው የሚመጣ አደጋ ነው። እዚህ ላይ ከባህል ጋር የተያያዙ ሌሎች ሊለወጡ የሚገባቸውና የሚችሉ ምክንያቶችን መጨመር ይቻል ይሆናል። በአለም ዙሪያ በብዙ መጠንና በተደጋጋሚ ማየት እንደምንችለው ሰዎች ምግባቸውን ባግባቡ የማያሟሉባቸው ሀገሮች የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚገፉ ወይም አፈናና አድሎ የበዛባቸው ፣ ማናለብኝነትና አምባገነናዊ ፖለቲካ ስርዓት የሰፈነባቸው ፣ ማህበራዊ ግጭቶችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ መጨፍለቅ በሚያበዙ ወይም ሙስና በሚፈጥረው ቀውስና ብልሹ አስተዳደር የተበከሉ የህግ ልዕልና የሌለባቸው ናቸው። እውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ብዙ ጊዜ ትልልቅ ድርቅ ይከሰት እንጂ ሰው ተርቦ ሞተ ሲባል የማንሰማው ዴሞክራሲያዊና ግልጽነት የሰፈነበት ስርዓት ስላላቸውና መንግስት ልሒቃኑና ተቋማቱ ከነፖለቲካ ልዩነታቸው ካለምንም ይሉኝታና መፎጋገር ስለመጭው ዘመን ተጨንቀው ስለሚያስቡ ስለሚወያዩና ስለሚያቅዱ ነው።

የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የቀድሞዎቹም ያሁኖችም ድርቅን የርሀብና የችጋር ምክንያት አድርገው ራሳቸውን ነጻ ለማድረግ በሚያደርጉት ሀሰተኛ ጥረት በጣም ይመሳሰላሉ። የቀድሞዎቹን መንግስታት ህዝብ በማስራብና ለችጋር በመዳረግ የሚከሱት የዛሬዎቹ መሪዎች አሁን ሀገሪቱን የገጠማትን የርሃብና የችጋር አደጋ ልክ እንደቀድሞዎቹ በድርቅ በተለይ በፈረደበት ኤል ኒኖ ማመካኘቱን ተያይዘውታል። ኤል ኒኖ ከችጋር ጋር ዝምድና ያለው ስራቸውን ባግባቡ ባልሰሩ ሀገሮች እንደሆነ እንድናውቅ አይፈልጉም። በነሱ ቤት አንድም የፖሊሲም ሆነ የሀገር አስተዳደር ምክንያት የለበትም። የችግሩ መንስዔ የግብርና ፖሊሲ ፣ ያጠቃላይ የኢኮኖሚ ወይም የመሬት ይዞታ ፖሊሲ ወይስ የዴሞክራሲ ችግር ብሎ ሰው እንዲጠይቅና መልስ እንዲፈልግ አይፈልጉም።

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ አንድ የዲያስፖራዎች (ይህ ዲያስፖራ የሚል ቃል ሲያስጠላኝ) ነው በተባለ ስብሰባ ላይ በድርቅ ምክንያት ካሊፎርኒያና አውስትራሊያም እየተሰቃዩ ነው ሲሉ ወዶ አይስቁ ሳቅ እየሳኩ ስምቻቸዋለሁ። እኛ ሀገር ላይ የተለየ ነገር አልመጣም እያሉ መዋሸታቸው ነበር። እኝህ ሰውዬ እንዴት ምስክር አይኖርም ብለው እንደገመቱ በጣም ነው የገረመኝ። እኔ ራሴ ድርቁ በገነነበት ባለፈው ስፕሪንግ ካሊፎርኒያ ሳን ፍራንሲስኮ ኦክላንድና ሳን ሆዜ አካባቢ ነበርኩ። ጆግራፈር ስለሆንኩ ለንደዚህ አይነት ጆግራፊያዊ ክስተት መመልከቻ ትልቅ አይን አለኝ። ሁኔታውን ስራዬ ብዬ ነበር ለማየት የሞከርኩት። ብዙ የደረቀ ሳርና ቅጠል ብዙ ቦታ አይቻለሁ። አፈሩም ብዙ ርጥበት እንዳልነበረው አይቻለሁ። አቶ ሀይለማሪያም የሚያወሩት ስቃይ ግን በቦታው አልነበረም። ለመኪና ማጠቢያ ውሀ አራርቆ መጠቀምን ፥ የጓሮ አትከልት ዉሀ ቆጥቦ ማጠጣትን ፥ ቧንቧ የሚያወርደው ውሀ ቀጠን እንዲል ማድረግንና ሌሎች የውሀ ቁጠባ ስራዎችን ሰቃይ ነው ካላሉ በስተቀር ስቃይ አልነበረም። ብዙ ያካበቢው ነዋሪ ድርቅ መኖሩን እንኩዋን የማያውቅ አለ። ካለኝ መረጃ አውስትራሊያም ስቃይ ሊባል የሚችል ነገር አልነበረም። በነገራችን ላይ አቶ ሀይለማሪያም ስለ ካሊፎርኒያና አውስትራሊያም በድርቅ መሰቃየት ሲናገሩ ያጨበጨቡት ዲያስፖራዎች በጅጉ አስገርመውኛል። ጭብጨባቸውን ስሰማ አቅለሽልሾኝ ነበር ብዬ ዕውነቱን ልናገር መሰለኝ። ቪዲዮውን ያላያችሁ እዩትና የገባችሁ ካላችሁ የጭብጨባውን ትርጉም ንገሩኝ። የድርቅ ስቃያችን ከካሊፎርኒያና ከአውስትራሊያ ጋር ይመሳሰላል ስለተባለ ሀገራችን እኩል ሆነች ብለው መደሰታቸው ይሆን? ቁጥሩ ይህን የሚያህል ገልቱ ዲያስፖራ ያለ አይመስለኝም ነበር።

ወደተነሳሁበት ነገር ልመለስ። ድርቅ የምክንያት ርሀብና ችጋር የውጤት ግንኙነት እንዳላቸው እያደረግን የምንለፍፈው ወሬ ከደረቅ ውሸትነቱ አለፎ ለስንፍና የሚዳርግ አደገኛ ነገርም ነው። ተፈጥሮን (ድርቅን) መቆጣጠር ስለማንችል ድርቅ በመጣ ቁጥር ለሚመጣው ርሐብና ችጋር እጅ እየሰጠንና እየለመንን ከመኖር ሌላ ምርጫ የለንም ወደሚል አደገኛ ድምዳሜ ይወስደናል። ለሀገሩ የሚቆረቆር ማንኛውም ቅን ኢትዮጵያዊ የሀገራችን የርሀብ ምንጭ ድርቅና ኤል ኒኖ ነው የሚለውን ሀሰት የማታለያ ፕሮፓጋንዳ መቀበል ቀርቶ ለመስማት ፈቃደኛ ሊሆን አይገባም። ባለስልጣናትም ይህን ውሸት በመደጋገም ካለባቸው ሀላፊነት እንዲሸሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። ይህ የችግሩ መፍቻ የመጀመሪያ ርማጃ ይመስላኛል።

ግጥጥ ያለው ዕውነት ግን እንዲህ ነው። የኖቤል ሎሬቱን አመርትያ ሴንን የመሳሰሉ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ዴሞክራሲ ባለበት ቦታ ሁሉ ርሀብና ችጋር የለም። ችጋርና ሰፊ ህዝብ የሚሸፍን ርሀብ በአንድ ሀገር ውስጥ የዴሞክራሲና ነጻ ማህበረሰብ አለመኖር ውጤት ናቸው። ዴሞክራሲ ባለበት ሀገር እንደልብ በሚካሄድ ክርክር የሀሳብ አማራጮች ይፈልቃሉ። አምባገነኖች ህዝብ የሚጠቅምና ርሀብ ጭራሽ የሚያስወግድም ቢሆን እንኳን ስልጣናቸውን የሚፈታተን ከሆነ ርሃብና ችጋሩን ይመርጣሉ። ነጻ ውይይትና ክርክር ስልጣንና ፖሊሲ የሚጠይቅ ስለሆነ ይህንን እንድንወያይ አይፈልጉም። በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታን ፖሊሲ ህዝብ አይከራከርበትም። ሀገሬውን የመንግስት ጭሰኛ ያደረገ ፖሊሲ በኔ እምነት ርሀብተኛ ሀገር ለመሆናችን አንድ ምክንያት ይመስለኛል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይህ ነገር ከተቀየረ የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው ነበር ያሉት። የገበሬው የይዞታ ባለቤትነት ርግጠኝነት አለመኖር ፣ የግለሰብ ይዞታዎች ከጊዜ ጊዜ እየተቆራረሱ ማነስ ፣ በርሻ መሬት ላይ ያለውን የሰው ብዛትና ግፊት ለመቀነስ የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ባግባቡ አለመዘርጋት ከብዙ ጥቂቶቹ የሀገራችን የርሀብና የችጋር ምክንያቶች ይመስሉኛል። ተገቢና ስራ ላይ ባግባቡ መዋል የነበረበትን የብሔረሰቦች የእኩልነት ጥያቄ ወደ በለጠ ልዩነትና ሰዎችና ካፒታል ብሄረሰብ ሳይመርጡ እንዳይዘዋወሩ የሚያደርገው ፖለቲካ ሁኔታ ችጋር ይፈለፍል እንደሆነ እንጂ ብልጽግና አያመጣም። አነስተኛ ገበሬዎችን በገፍ እያፈናቀሉ ለውጭ ሀገር ቱጃር መሬት መሸንሸን ችግርና ርሀብ ያፈላ እንደሆን እንጂ የማንንም ችግር ሲያስወግድ አልታየም። ሀገርን ለዜጎቿ ሳይሆን ለባዕዳን መስሕብ በማድረግ የዳበረና ችግር ያስወገደ ሀገር የለም። ይህን ማረም የማይችል መንግስት ርሃባችንን በኤል ኒኖ ሲያመካኝ ማፈር አለበት። በነዚህና እነዚህን በመሳሰሉ ማነቆዎች ላይ በግልጽና በቅንነት ተወያይተን መፍትሄ ካላበጀን ርሀብና ችጋር በየጊዜው የሚጎበኙን የውርደት ሀገር ሆነን መኖራችን ይቀጥላል።

የሀገራችንን ባለስልጣኖች አስመልክቶ በጣም የሚያስተዛዝበው የርሀቡ ደረጃ ለምን ባደባባይ ተዘገበ በማለት ባለማቀፍ ሚዲያዎች ላይ የሚያካሂዱት ቡራ ከረዩ ነው። የሚዲያው የርሀቡን አስከፊነት በስፋት መዘገብ ልመና ለማቀላጠፍ ይረዳ እንደሆን እንጂ ጉዳት የለውም። ቡራ ከረዩው ሀገርና ህዝብ ተጎዳ በሚል ሳይሆን በብዙ ቅባት ያሳመርነው ገጽታ ለምን ይነካል ነው። ሰሞኑን ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ አስመልክቶ የመንግስት ሹሞችና ደጋፊዎች የሚያደርጉት ያዙኝ ልቀቁኝ በጣም አስገራሚም አስተዛዛቢም ነው። በካሜራ ላይ ሰለባዎች እየተናገሩ ያካሄዱትን ዘገባ በምን ምክንያት ነው የምናወግዘው? ለንደን ያለው ኤምባሲ የሚለው ቢያጣ የርሀቡን አስከፊነት አስመልክቶ ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ላይ በሰጠው የተቃውሞ መልስ ቢቢሲ ርሀቡን ያመጣው ኤል ኒኖ ነው የሚለውን የመንግስት ውሸት ደግሞ ባለማለቱ አጥብቆ ይከሳል። እንዲህ ይላል። “The report also failed to give perspective on the drought situation currently unfolding in Ethiopia and around the world and how it is triggered by the El Nino phenomenon”. የዚች አረፍተ ነገር ቁም ነገር ችግሩን ያመጣብን ኤል ኔኖ ስለሆነ ምንግስታችን አይጠየቅም የምትል ነች። ተጠያቂነትን ማምለጫ ብልጠት መሆኗ ነው። ኤል ኒኖ ሀገር እየለየ ነው እንዴ ጥቃት የሚያደርሰው? አስር ዐመት ሙሉ ግብርና ከሁለት ዲጂት በላይ ያደገባትን ሀገር ከቀርፋፋዎቹ እንዴት እድርጎ እንደመረጣት ግራ የገባው ታዛቢ ታዲያ ምን ይበል?
በኔ አመለካከት ከዚህ በአለም ፊት በተደጋጋሚ ካዋረደንና እያዋረደን ካለ ርሀብና ችጋር መገላገል የምንችለው በችግሩ ዙሪያ በግልጽ በመወያየት ነው። የስካሁኑን ተመክሯችንና መረጃዎቻችንን ይዘን በግልጽ እንወያይ። ይህ የወገንተኛ ፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። የህልውና ጉዳይ ነው። ወደ ዝርዝር ምክንያቱ እንግባ ካልን በመንግስት ላይ ብቻ በማመካኘት የምንገላገለውም አይደለም። እንደ ህዝብ ያሉብንም ባህላችን ውስጥ የተዋቀሩና ለችግሩ የዳረጉን ብዙ ችግሮች አሉ። በሀገራችን ይህን ሁላችንም የምንወያይበት ዴሞክራሲያዊ መድረክ ያስፈልገናል። ለመፍትሄውም ፍለጋ ሆነ ያገኘነውን የመፍትሔ ሀሳብ ስራ ላይ ለማዋል ዲሞክራሲ የግድ እንደሚያስፈልገን ግን ብዙ መከራከር ያለብን አይመስለኝም። ይህን ማድረግ ካልቻልን የሚቀጥለው ቸነፈር ጊዜም ይህንኑ እያወራን በውርደታችን ለመቀጠል ተስማምተናል ማለት ነው።


የቀበሮዎች ስብሰባ በዛምብራ በበላይነህ አባተ

ካሳ ከበደና የሻእቢያ ኮሶ ! ከጋዘጠኛ ደምስ በለጠ

$
0
0

በቅርቡ ፤ በኢትዮጵያና በኤርትራ ህዝብ ስም ፤ ዋሽንግቶን ዲሲ ውስጥ ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባል ድርጅትና ኢሳት/ግንቦት 7 ያዘጋጁት ፤ አንድ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር ። በአጠቃላይ ዋሽንግተን ዲሲንና የአበሻ ፖለቲካ ተዋንያኑን (ኤርትራን ጨምሮ ማለቴ ነው የሃበሻ ስል) የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ፤ ስብሰባው አዳራሽ ውስጥ የነበሩትን በኢንተርኔት መስኮት ሲመለከት ፤ ዋሽንግቶን ውስጥ ስብሰባ ከተደረገ በፍፁም የማይቀሩ ግለሰቦችን ፤ ጋዜጠኞችን ፤ ጥቂት የግንቦት ሰባት ደጋፊዎችን እና የሻእቢያ የሰሜን አሜሪካ ተወካዮችንና ተራ የሻእቢያ አባላትን በቀላሉ በስም እየለዬ ፤ መጥራት ይችላል ።

ውድ አንባቢዎቼ ፤ በተለይ የዋሽንግተን ነዋሪ የሆናችሁ ፤ በረጅም ጊዜ ልምድ እንደምታውቁት ፤ ስብሰባ በተጠራበት ቦታ ሁሉ የማይቀሩና ፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እጃቸውን እያወጡ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ፤ ንግግር ወይም አስተያየት የሚሰጡ ሰዎችን ታውቋቸዋላችሁ ብየ እገምታለሁ ። እነዚህ ሰዎች የአዘጋጆቹን ፍላጎት፤ በተለያየ መንገድ አስቀድመው ይረዳሉ ። ከዚያም ስብሰባው ላይ እሳተ-ነበልባል የሆነ ንግግር ያደርጋሉ ። የስብሰባውን አዳራሽ ፤ በተለይ የሰብሳቢዎቹ እጅ ፤ እስኪቃጠል ድረስም ያስጨበጭባሉ ። አዘጋጆቹን አስደስተው ፤ ራሳቸውም የሚፈልጉትን ትኩረትና የሚወዱትን ጭብጨባ ጠጥተው ፤ ደስ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ ። ታዲያ ለትግሉ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ፤ ከዚህ ከፍም ዝቅም አይልም ። እንደዚሁ ሁሉ ፤ ሆይ ሆይታ በሞቀበት ፤ ጭብጨባና ከንቱ ውዳሴ በበዛበት ቦታ ፤ ማንም ያዘጋጀው ማ ፤ ጉዳዩን ሳይመዝኑ ፤ አይምሮአቸውን ለተፈላጊው ጉዳይ አዘጋጅተው ፤ ታጥበውና ታጥነው የጠሯቸው የፖለቲካ መድረክ ላይ ሁሉ ፤ የፕሬዚዲየሙን ወንበር ለማሞቅ የሚገኙ ምሁራን ሰዎችንስ አስተውላችኋል ?

በዚህ የሻእቢያና የግንቦት ስብሰባ ላይ ፤ የውጪ እንግዶቹንና አንዳንድ ያልገባቸው ወገኖችን ትቼ ፤ በኔ በኩል ያስተዋልኩት እንዲህ አይነቶቹን ሰዎች ነው ። “ቪዥን ኢትዮጵያ” የሚባለው ቡድን ፤ በዚህ ስብሰባ ላይ ፤ የቶሎ ቶሎ ስም ወጥቶለት ለሻእቢያ ተልእኮ የስጦታ መጠቅለያ ወረቀት ሆኖ የቀረበ ድርጅት ነው ። በግንቦትና በኢሳት ፊታውራሪነት ፤ ራሱን እንዲያቀርብ የተዘጋጀው ይህ ድርጅት ውስጥ ፤ በሃገርና በህዝብ ላይ የተሰራውን የሸፍጥ ተግባር ደግሞ ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አይኑን አፍጥጦ አይቶታል ። በተለይ ሻእቢያን ወክሎ የመጣው ግለ-ሰብ እዚያው እፊታቸው ፤ ሻቢያን ለመንካት ያሰበ ቢኖር “ራሽያን ሮሌት” እንደመጫወት ይቆጠራል ፤ እወቁት ብሎችኋል ። እደግመዋለሁ እያለም ያንኑ አባባሉን ደግሞ ነግሯችኋል ። ኢትዮጵያውያን ናችሁና ባዘጋጃችሁት መድረክ ላይ የሻእቢያን መልእክት ፤ አገጫችሁን ከፍ አድርጎ ይዞ ፤ የሚፈልገውን ሁሉ እንደኮሶ ግቷችሁ ሄዷል ። እናንተም የሻእቢያ ፕሮፓጋንዳና ጉድፍ ማስተላለፊያ ቱቦ ሆናችሁ አገልግላችኋል ። ህሊናቸሁ ምን እየተደረገባችሁ እንደሆነ ካልገለፀላችሁ ፤ ጊዜ ይገልፅላችዋል ። ከንቱ ውዳሴና ሙገሳ እንደ ጤዛ ብልጭ ብለው የሚጠፉ ነገሮች ናቸውና ።

“…….በመንፈሳዊው አለም ሰው የለ ፤ በፖለቲካው አለም ሰው የለ ፤ በሽምግልናው አለም ሰው የለ ፤ እንዴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ የሰው ምድረ-በዳ ሆነች ? እያልኩ አወጣለሁ አወርዳለሁ…… እንደኔው የሚጨነቁ ሰዎችም ያሉ ይመስለኛል ።”
ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር አገር ነች ፤
ልጆቹዋ ግን ሰይጣን አድሮባቸዋል ።……
ኢትዮጵያ ግን የምታደላላቸው ልጆች የሏትም ፤
የሚያሳዝኗት ግን ሞልተዋል ፤……
ኢትዮጵያ የወላድ አገር ነች ፤
ግን የሰው ምድረ-በዳ ሆናለች ።

የላይኛው ቃልም ሆነ ቅኔ ፤ እዚያው ስብሰባው ላይ እንግዳ ከነበሩት መስፍን ወ/ማርያም ፤ የክህደት ቁልቁለት ከተሰኘው መፅሃፍ የወሰድኩት ነው ።

የዛሬው ርእሴ “ቪዥን ኢትዮጵያ” የተባለው ድርጅት አይደለም ። ምንም ስላልሆነና ከስጦታ መጠቅለያ ወረቀትነት ባሻገር ህልውና ስለማይኖረው ። እዚያው እነሱ ከኢሳት ጋር የጠሩት ስብሰባ ላይ የጋበዟቸው እንግዳ ናቸው የዛሬው ዋናው ርእሴ ። ዶ/ር ካሳ ከበደ ። ሳስበው ውዬ ሳስበው ባድር ፤ የካሳ ከበደ የኢሳኢያስ አፈወርቂ ሽንጥ ገትሮ ተከራካሪነት አልገባህ ብሎኝ ከረምኩ ።

ዶ/ር ካሳ እኮ የደርጉ ዘመን አንቱ የተባሉ ባለስልጣን ናቸው ። ስጋ ሜዳ በኋላ ላይ ታጠቅ ጦር ሰፈር የተባለውን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ለማስገንባት በጊዜው የሃገሪቱ መሪ በነበሩት ፤ በኮለኔል መንግስቱ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው የነበሩ ሰው ናቸው ። የሃገሪቱን አንድነት ከገንጣይና ከሶማሊያ ወራሪ ለመከላከል ፤ በዚሁ በታጠቅ ጦር ሰፈር 3 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ የገበሬ ልጅ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶበታል ። ይህ የገበሬ ወታደር ከሶስት ወራት ስልጠና በኋላ ፤ በሰሜንም በምስራቅም ያለክፍያ የሐገሪቱን አንድነት ትጠብቃለህ ተብሎ ተማግዷል ። ለዚህ ለአንድነት የፈሰሰ ደም ፤ በተለይ ደግሞ ከሻእቢያ ጋር እየተዋጋ መስዋእትነት ለከፈለው ህዝባዊ ሚሊሺያ ፤ ካሳ ከበደ ፤ እንደ ደርግ ባለስልጣን ሃላፊነት መውሰድ ይኖርባቸዋል ። በሰሜን የተደረገው ጦርነት ደግሞ የተካሔደው ፤ ኢሳኢያስ አፈወርቂ ከመራው ፤ ከሻእቢያ ጦር ጋር ነው ። እንዴት ሆኖ ነው ዛሬ ካሳ ከበደ ፤ ለሻእቢያው ቁንጮ ፤ ኢሳኢያስ አፈወርቂ ሽንጣቸውን ገትረው ተከራካሪ ሆነው የተገኙት ?

ከዚህ ሌላ ፤ ካሳ ከበደ በተባበሩት መንግስታት ፅ/ቤት የዚያን ጊዜው መንግስት ፤ ማለትም የደርግ መንግስት የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ ፤ አምባሳደር በመሆንም ሰርተዋል ። በጊዜው ኢትዮጵያን በመወከል ፤ የሐገራችንን በጎም ሆነ መልካም ገፅታ የመወከል አደራ ፤ በኢትዮጵያ እና በህዝቧ ተሰጥቷቸው የነበሩ ሰው ናቸው ። (የደርግ ድንቁርና እንዳለ ሆኖ) በተሰጣቸው አገራዊ አደራ የተነሳም ፤ ላገለገሉት መንግስት መርሕ ቆመው መስራት ተገቢ ነበር ። የገንጣዮችን የነሻእቢያን ደባም ፤ አቅማቸው በፈቀደ በማክሸፍ ጥረት ላይ መንግስታቸውን ወክለው ሰርተዋል ብዬ እገምታለሁ ። ታዲያ እንዴት ተደርጎ ነው የዚያ መንግስት ፓርቲና የኢሠፓ የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የውጪ ግንኙነት ሃላፊ ፤ ዛሬ ለገንጣዩ ኢሳኢያስ አፈወርቂ ሽንጥ ገታሪ ሆነው የተገኙት ?

ወይስ ዶ/ር ካሳ ከበደ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ስርዓት ግፍና በደል ደርሶበታል ብለው አስበው ይሆን ? ከሆነስ የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃነት ፤ በኢሳኢያስ አፈወርቂ በኩል ላመጣው እችላለሁ ብለው ገምተው ነው ? ለኢሳኢያስ አፈወርቂ ሽንጥ ገታሪ ለመሆን የቆረጡት ። እንዴትስ ተደርጎ ቢታሰብ ነው ፤ የገንጣዩ የሻእቢያ መሪ ኢሳኢያ አፈወርቂ ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል አላማ የለውም ተብሎ በኢሳኢያስ አፈወርቂ ተነግሮ ፤ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ፤ በካሳ ከበደ በኩል የሚነገረን ።

በዚህም ብዬ በዚያ ባስበው ፤ ባወጣው ባወርደው ፤ ምክንያቱ በፍፁም አልመጣልህ አለኝ ። በነገራችን ላይ ፤ ካሳ ከበደ ፤ ከወንድምዎ ከኮለኔል መንግስቱ ጋር በመሩት የመንግስት ስርዓት ውስጥ እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ ደልቶት አልኖረም ። ወንድምዎ ስል ግን ፤ ያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ይታማ የነበረውና በኋላ ላይ “የአጥፍቶ መጥፋት” ደራሲ ፤ የፃፈውን መፅሐፍ ተመርኩዤ እንዳልሆነ በቅድሚያ ይታወቅልኝ ። ዛሬ እትሙን ባላስታውሰውም እርስዎ ራስዎ እዚህ አሜሪካ ከመጡ በኋላ በጦቢያ መፅሄት ላይ ፤ አንድ ቃለ መጠይቅ አድርገው ማንበቤ ግን ትዝ ይለኛል ። በዚያ ቃለ መጠይቅ ላይ ኮለኔል መንግስቱ በስጋ ባይወለዱኝም የርእዮተ-አለም ወንድሜ ናቸው ማለትዎን ግን በደንብ አስታውሳለሁና ነው ።

ስለዚህ ካሳ ከበደ ሆይ ፤ ሰው ምክንያታዊ ነውና እኔም ካሳ ከበደና ኢሳኢያስ አፈወርቂ ምን አገናኛቸው ለሚለው ጥያቄ መልስ ፍለጋ ወደኋላ ተጓዝኩና ፍተሻ ገባሁ ። አቧራ ከለበሱት መረጃዎቼ ውስጥ አንድ ነገር አገኘሁና መልሱ ይህ ይሆን እንዴ ? ስል ጠረጠርኩ ። ጥርጣሬየን እርስዎ ደህና አድርገው ያውቁታል ። ከአንባቢዎቼ ጋር ግን ልካፈለው ወደድኩ ። ምንም ቢሆን ፤ በአንድ ዘመን ላይ የትከናወነ ታሪክ ፤ ምናልባት በጊዜ ምክንያት ይደበዝዝ ይሆናል እንጂ ፤ ጨርሶ ሊጠፋ ግን አይችልም ።

ዶ/ር ካሳ የዛሬን አይድርገውና በስራ ምክንያትም ሆነ በግል በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲወጡም ሆነ ሲገቡ ፤ መጡ መጡ ተብለው ፤ ተፈርተው ፤ ታፍረው ተከብረው ሁሉም ሰው ሽር ጉድ ይልልዎ እንደነበር አይዘነጋዎትም ። መጨርሻ ላይ ግን ኢትዮጵያንና ህዝቧን እንዴት አድርገው ነው በዚያው በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል ጥለዋቸው የወጡት ?

ቃሬዛውና የሂልተን ሆቴል ብርድ ልብስ !

ከዛሬ ሃያ አራት አመታት በፊት የሆነ ታሪክ ነው ። የመጨረሻውን “ኦፕሬሽን ሰለሞን ” የተሰኘውን ተልእኮ በመሪነት ይወጣ ዘንድ ፤ የእስራኤል መንግስት ፤ ኡሪ ሊብራኒን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ፤ ልዩ ወኪል በማድረግ ሾሞታል ።

“ኦፕሬሽን ሰለሞን” የመጨረሻው ሰአት ላይ ከመድረሱ ሶስት አመታት በፊት ፤ ይላል ስቴፓን ስፔክል ፤ የአሜሪካ አይሁዶች ማሕበር ሰዎች ፤ ጌሊ ኩሊንክና ናትሻፕረን ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ካሳ ከበደን አግኝተው ሲወያዩ “አንተ ሕልውናህ ከዚህ ከምትሰራው ተልእኮ ጋር የተያያዘ ነው ። የተፈለገው ግብ ላይ እንድንደርስ ከተባበርከን ፤ በአስፈላጊው ሰአት ልንደርስልህ እንደምንችል ፤ እርግጠኛ ሁን ። ብለውት ነበር ።

የእስራኤሉ “ኦፕሬሽን ሰለሞን” ሹመኛም ፤ ስለ ካሳ ከበደ ማንነት የራሱን ግምት የሰጠው እንዲህ በማለት ነበር ። “ገና መጀመሪያ ላይ ከካሳ ጋር ፤ እንደተገናኘን ለኔ የሚስማማኝ የራሴ ሰው እንደሆነ አወቅኩኝ ።………..ለዚህ አለም ኑሮ የተስተካከለ ስብእና ያለው ፤ ነገር ግን ንቁና ተጠራጣሪ ቀበሮ ፤ ጨካኝና ግትር መሆኑን ካላወቅህ ይጎዳሃል።” ነበር ያለው ፤ ይላል መፅሐፉ ።

ኡሪ ሉብራኒ የሰጠው አስተያየት እንዳለ ይቀመጥና ፤ ፈላሻዎቹን ከኢትዮጵያ የማውጣቱ ተግባር “በኦፕሬሽን ሰለሞን ዘመቻ” እየተጠናቀቀ ባለበት ወቅት ፤ የመጨርሻው ሰአት ላይ ፤ ኡሪ ሉብራኒ ሁለት መኪናዎች አስከትሎ ፤ የመጨረሻዎቹን ተጓዦች እያሳፈረ የነበረው ሲ 130 ሄርኩለስ አውሮፕላን ውስጥ ሁለት በቃሬዛ ላይ የተኙ ፤ ህሙማንን ለማሳፈር ዝግጅቱን አጠናቀቀ ።እነዚህ በሽተኛ ተጓዦች ከሂልተህ ሆቴል በተወሰደ ብርድ ልብስ ተጠቅልለዋል ።

ህሙማኑ ሲጫኑ ያዩ የሞሳድ አባላት ኡሪ ሉብራኒን ፤ “እነዚህ ሰዎች እንዲህ በጠና ከታመሙ ለምን እናጓጉዛቸዋለን ? ከህመማቸው ሲያገግሙ ቢመጡ አይሻልም ? ብለው ይጠይቁታል ። ማን ያውቃል ፤ ከሞት ተርፈው ፤ እንነሱም በስትሬቸር ወደ እስራኤል ገባን ፤ ብለው ለማውራት ያስችላቸው ብዬ ነው የፈቀድኩት ፤ ሲል ተናገረ ።……….እነዚህ ሁለቱ ከሂልተን ሆቴል በቃሬዛ ብርድ ልብስ ለብሰው የተጓዙት ህሙማን ከኢትዮጵያ ፀጥታ ሃይሎች እይታ እንዲያመልጡ ፤ በስራኤል የፀጥታ ሰራተኞች በጥንቃቄ በተቀነባባረ ዘዴ ፤ ወደአውሮፕላኑ የተሳፈሩት ሰዎች ናቸው ። ኡሪ ሉብራኒ አውሮፕላኑ ህሙማኑን እንደያዘ በፉሪ ተራራ አናት ላይ እያዘገመ ፤ ከአይናቸው እስኪሰወር ሲያዩ ከቆዩ በኋላ አብረውት ለነበሩት ባልደረቦቹ “ ካሳ ከበደ እንደፈለገው በቃሬዛ (ስትሬቸር) ላይ እንደተኛ ወደ እስራኤል ሊገባ ነው” አለ ፤ እየሳቀ ይላል ፤ መፅሐፉ ። እነዚህ በሂልተን ሆቴል ብርድ ልብስ ተጠቅልለው የነበሩት ህሙማን ፤ ካሳ ከበደና የኢትዮጵያ ደህንነት ም/ሚንስትሩ መርሻ ቀፀላ ነበሩ ።

ዶ/ር ካሳ ከበደ ስንትና ስንት ጊዜ በክብርና በአጃቢ ከተሸኙበት የቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ፤ እንዲህ በብርድ ልብስ ተጠቅልለው ነው ከኢትዮጵያ የወጡት ። በሰሜን አቅጣጫ ፤ በእስራኤሎቹ ሄርኩለስ አውሮፕላን ወደ ቴልአቪቭ ሲነጉዱ ፤ ለአንድ ሳምንት ብቻ የቆየው የሃገሪቱ ጊዜያዊ መንግስት አባላት ለስብሰባ ቤተ-መንግስቱ ካፊቴርያ ውስጥ ካሳ ከበደን ፤ ለስብሰባ እየጠበቋቸው ነበር ። ይህ ከመሁኑ ከአንድ ሳምንት በፊትም ፤ ኮለኔል መንግስቱ በደቡብ ኢትዮጵያ በኩል ፤ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ዚምቧቡዌ ሸምጥጠው ነበር ።

እዚህ ላይ የፍቅሬ ቶለሳ አንድ ቅኝት ትዝ አለኝ ።

“ሞኝ ዋርካ ሊተክል
ግንዱን ተሸክሞ ያምጣል።
ብልጥ ዋርካውን ኪሱ ከቶ
ፈጠን ፤ ቀልጠፍ ብሎ ይራመዳል ።”

እንግዲህ ፤ ከላይ ያቀረብኳቸውን መረጃዎች ያገኘሁዋቸው ስቴፓን ስፔክል ከተባለ ደራሲ መፅሓፍ ላይ ነው ። “ ኦፕሬሽን ሰለሞን ያልተነገሩ ምስጢሮች” ይላል የመፅሐፉ ርእስ ። ደራሲው ስቴፓን ስፔክል ፤ በዚህ መፅሃፉ ላይ ፤ ከፈላሻዎቹ ጋር በተያያዘ የነበሩትን ጉዳዮች ፤ ከዋሽንግተን እስከሞስኮ ፤ ከአዲስ አበባ እስከ ቴልአቪቭ ፤ የነማን እጅ እንዳለበትና እነማን ምን ሚና እንደነበራቸው በሚገባ ገልፆበታል ። ስለዚህም በአሜሪካዊው ኸርማን ኮህንና በእስራኤላዊው ኡሪ ሉብራኒ መካከል በሚደረጉ የንግግር ልውውጦች ፤ ካሳ ከበደን “ዘ ብሮከር ፤ መንግስቱ ኃ/ማርያምን ደግሞ “ኮካኮላ” የሚል የሚስጥር ስምም ሰጥተዋቸው ነበር ። ይህ ቅፅል ስም የወጣላቸው ፤ ካሳ ከበደ ፈላሻዎቹን ከማስለቀቅ ጋር ባላቸው ሚና ፤ መንግስቱ ኃ/ማርያምን ደግሞ በጥቁረታቸው የተነሳ ከኮካኮላ ቀለም ጋር አያይዘውት ይሆናል ብየ እገምታለሁ ። የፈላሻዎቹ ጉዳይ ፤ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሃቅ ሻሚር ፤ እስከ ከፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ የደረሰ ጉዳይም ነበር ።

“አሜሪካውያኑም ሆኑ እስራኤሎቹ ፤የካሳ ከበደ መፃኢ እጣ ፈንታ አደጋ ውስጥ እንዲወድቅና ለጉዳት እንዲጋለጥ አይፈልጉም ። ቦብ ፍሬዘር በጉዳዩ ላይ ሲናገር ‘የኋላ ኋላ የካሳ ከበደ ማረፊያው የተደላደለና ከላባ የተሰራ ምቹ ፍራሽ እንዲሆን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብሏል ።’

በጉዳዩ ዙሪያ በአዲስ አበባ ፤ በዋሽንግቶንም ሆነ በቴል አቪቭ ሁሉም የየራሱን የካርታ ጨዋታ መቀመር ይዟል ። የዛሬው ርእሴ መሪ ተዋናይ ዶ/ር ካሳ ከበደም የራሳቸውን ጆከር ካርታ መዝዘዋል ።

ደላላው የጠየቀው ክፍያ ስንት ነው?

ለኢትዮጵያ መንግስት የሚከፈለውን ገንዘብ ካሳ ከበደ ሲደራደሩ ፤ ለራሳቸውም የሚገባውን ድርሻ እንዴት እንዳስቀመጡ ፤ ስቴፓን ስፔክል እንዲህ ሲል ዘግቦታል ።

“አርብ እለት ይላል “ኦፕሬሽን ሰለሞን ያልተነገረው ሚስጥር’ መፅሃፍ ደራሲ ፤ አርብ እለት ፤ ከኡሪ ሉብራኒ ጋር ተገናኝቶ ፤ በገንዘቡ መጠን ዙሪያ የጀመረውን ውይይት በመቀጠል ፤ ፈላሻዎቹን በአየር ትራንስፖርት ለማጓጓዝ ፤ የሚያስፈልገውን ዋጋ በማውጣት በአጠቃላይ 60 ሚሊዎን ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት እንደፋይናንስ ድጋፍ እንዲከፈልና ለራሱም የልፋቱ ዋጋ እንዲታከልለት ካሳ ከበደ ጥያቄ አቀረበ ።” ይላል ።

አዎ ፤ የካሳ ከበደ ጆከር ካርታ ፤ የልፋታቸውን ዋጋ ከእስራኤላውያኑ መጠየቅ ነበር ። ከአመታት በፊት ለሌላ ተልእኮ ወደአሜሪካ ጎራ ብለው የነበሩት ካሳ ከበደ “American “Association for Ethiopian Jews” ከሚባል ድርጅት ጋር ግንኑነት አድርገው ፤ ለልፋታቸው ዋጋ ጠይቀው ፤ ቃል ተገብቶላቸው ነበር ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ፤ እንደ እስቴፓን ስፔክል መፅሃፍ ። ለመሆኑ ካሳ ከበደ ፈላሻ የሆኑትን ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ለማጓጓዝ ፤ የልፋታቸው ዋጋ ስንት ነበር ?

መፅሐፉ የገንዘቡን መጠን ፍንጭ ሲሰጥ …….. “የአይሁድ አጀንሲው ፕሬዚደንትም ሆኑ ገንዘብ ያዡ ፤ የቀረበውን የክፍያ መጠን ግዙፍነት ቢሰሙ ፤ ብዙ የተገፋበትን ጥረት በድንጋጤ ፤ ወደ ቀድሞው ስፍራው ሊመልሱት ይችላሉ ።” ካለ በኋላ ፤ በመቀጠል ፤ “በተለይ ካሳ ከበደ ጉዳዩን እንዲያቀላጠፍና እንዲያሳካ ላደረገበት $3.4 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ለመክፈል እንደተስማሙ ቢሰሙ ፤ በጉዳዩ ላይ የሚያደርጉት መንቀርፈፍና የሚፈጥሩት ማነቆ ፤ ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት ፤ ለጊዜው ዩሪ ሊብራኒ ፤ በጉዳዩ ላይ ከነሱ ጋር አለመነጋገርን መረጠ” ይላል ።

በመጨረሻም ! መርጃዎቼን ካገኝሁበት ከስቴፓን ስፔክል መፅሐፍ ላይ የሚቀጥለውን ርእስ ልዋስ ነው ።

ካሳ ከበደ “የመክፈቻ ቁልፍ” መሆኑ አብቅቷል

ዶ/ር ካሳ ከበደ ፤
1ኛ) የኢትዮጵያን ህዝብ ፤ በቀውጢው ሰአት ፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት እርስዎ ፤ በብርድ ልብስ ተጠቅልለው ፤ ሜዳ ላይ ጥለውት ነው እኮ እንደ ኮለኔል መንግስቱ የፈረጠጡት ።
2ኛ) ከስጋ ሜዳው ማሰልጠኛ ወጥተው በኤርትራ በረሃና ተራሮች ላይ ፤ የትም ወድቀው የቀሩት ኢትዮጵያውያን የገበሬ ልጆች ደም እኮ ፤ እስካሁን ድረስ አልደረቀም ።
3ኛ) ፈላሻዎቹን ኢትዮጵያውያን ወደሌላ አገር ለማስተላለፍ ፤ የልፋቴ ዋጋ ይከፈለኝ ብለው ዋጋ የጠየቁ ሰው ነዎት እንደ መፅሃፉ መረጃ ።
አሁን ምን ተገኝቶ ነው ኢሳኢያስ አፈወርቂ በኔ ይሁንብህ ካሳ ! እኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እቅድ የለኝም ብሎ ለእርስዎ የሚነግርዎ ? እሺ ፤ እርስዎ እንዳሉት ፤ ነገረዎ ብለን እንውሰድልዎ ። ከስቴፓን ስፔክል መረጃ ተነስተን ፤ ያለፉትን ሁኔታዎች ሁሉ ስንገመግም ፤ እርስዎ ዛሬ ማን ስለሆኑ ነው የእርስዎን ቃል የምናምነው ? ወይስ ገንጣዩ ኢሳኢያስ አፈወርቂ ፤ ለእርስዎ ከነገረዎት ቃል ጀርባ ፤ እንደ መጨረሻዋ ሰአት ሁሉ ፤ አንድ የተደበቀ ነገር አለ ?

ዶ/ር ካሳ ከበደ ፤ መቼም ኢሳኢያስ አፈወርቂ ገንዘብ ከፍሎዎታል ብዬም አልጠረጥርም ፤ ለራሱም በአረቦች ድጎማ የቆመ ፤ መናጢ ድኻ መንግስት ነውና ። ኢሳኢያስን በከንቱ ውዳሴ መደለል ፈልገው ከሆነ ደግሞ ፤ እሱ መንግስቱ ኃ/ማርያም አይደለምና አይሸነግሉትም ። እርሱ ራሱ ከልጅነቱ ጀምሮ በዚህ ተግባር ጥርሱን ነቅሎ አድጎበታል ።

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ፤ ዶ/ር ካሳ ከበደ የእርስዎ መክፈቻ ቁልፍነት አክትሟል ። የሚያመጡት ለውጥም የለም ። እውነትም ይሁን ሐሰት የተናገሩት ሁሉ የሚደመጥበት ፤ ያዘዙት ሁሉ የሚፈፀምበት ፤ የረገጡት መሬት የሚንቀጠቀጥበት ፤ ዘመን “Gone with the wind” ። የኮለኔል መንግስቱ ፀኃይ የጠለቀች ጊዜ የርስዎም አብራ ጠልቃለች ።

በተረፈ ቸር ይግጠመን እላለሁ ።
በዚህ አጋጣሚም ፤ ለነፃነት ዘለቀ ሰላምታዬን ያቅርቡልኝ አደራ ።

በፅሁፉ ላይ አስተያየትም ሆነ ፤ ትችት ካላችሁ ፤ እነሆ ኢሜል አድራሻዬ anbesawyibra@gmasil.com .

ላስ ቬጋስ ኒቫዳ
ኖቬምበር 22/ 2015

የባለ 11% እድገታችንና ብቃት የለሽ አስተዳደር ያስከተለው ረሃብ በሜሮን አየለ

$
0
0

ሀገራችን ላለፉት ሃያ አራትት አመታት ስለልማቷ፣ ስለእድገቷ ብዙ ተብሏል፥ እየተባለም ይገኛል። ሆኖም ግን አደገች፣ በለጸገች እየተባለ ይነገረን እንጂ ሕዝቧ/ዜጎቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኑሯችን እያሽቆለቆለ፣ ፍትህ እየተዛባ፥ መብት እየተረገጠ አስከፊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን። የሀገራችን እድገት ምስክሮች እኛውና የኛው ኑሮ መሆኑ ቀርቶ ሌሎች አውሮፓውያኖችና ለጋሽ መንግስታት ‘ለመንግስታችን’ እየመሠከሩለት፣ ወያኔም ምሥክርነታቸውን እንዳረጋገጡለት ለኛ መልሶ በቴሌቪዥንና በሬድዮ ቀንና ማታ ያደነቁረናል።

ሃገራችን ችግር ላይ ነች ብለን ስንል የታየንንና የተረዳነውን ገሃድ አውጥቶ መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ ለህዝብና ለሃገር በማሰብ እንጂ እንደወያኔ በአግድም ወይንም የተገላቢጦሽ አተረጓጎም በሃገርና በህዝብ ላይ ችግር መፍጠር ወይንም ህዝብን ለአመጽና ለብጥብጥ ማነሳሳት ወይንም መጋበዝ ማለት አይደለም።
መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው ስብስብ የተሞላው በራስ ወዳዶች፣ ብልጣ ብልጦች፣ አስመሳዮችና የህዝብ ችግርና ሰቆቃ በማይሰማቸው ግለሰቦች ነው። ይህንን የሃገራችንን ችግር ከነችግር ፈጣሪዎቹ ልቅምቅም አድርጎ ማስወገድ የማናችንም ሃገር ወዳድ ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ ነው።

በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የኋሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ወያኔ ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ አስተሳሰብና የሃይል አምባገነናዊ አገዛዝ ተሸብቦ ያላስነባው ህዝብ፤ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፤ ያላፈረሰው አንድነት፤ ያላዋረደው የህዝብ ስብዕና፤ ያልገባበት የእምነት ተቋም፤ ያልበተነው የሞያ ማህበራት፤ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም::

ባለፉት አመታት በወያኔ አገዛዝ በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገውን ትግል ለማኮላሸት እርስ በርሱ የሚቃረኑ ህጎችና መመርያዎችን አርቅቆ እያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ አንገላቷል፤ ገድሏል፤ ለማምለጥ የታደሉትንም ከአገር በግፍ እንዲሰደዱ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት በሃገራችን በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ለሚገኘው ረሃብና ድርቅ ዋና መንስዔዎች የተፈጥሮ አየር መዛባት ብቻ ሳይሆን በዋናነት የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፡፡ የችግሩ መንስዔ አንኳር ችግር በየደረጃው የሚገኘው የመንግስት አካላት ሃገርንና ህዝብን በሰለጠነ መንገድ ለማስተዳደር ብቃት የለሽነት እና ብልሹ አስተዳደር እንጂ ባለስልጣናቱ እንደሚደሰኩሩት አካባቢያዊ ነገሮች አይደሉም፡፡
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እስከዛሬ እየተከሰተ ያለው ረሃብ ከተፈጥሯዊነቱ ይልቅ ሰው ሰራሽነቱ ነው የሚያመዝነው፡፡ ይህም ማለት ለረሃቡ መንስዔ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደር፣ የሙያ እና የአስተዳደር ብቃት የለሽነት እና በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ችግር ለማስወገድ የሚያስችል የፖለቲካ ፈቃደኝነት እና ፍላጎት የሌለው አምባገነን እና ጨካኝ ዘረኛ መንግስት በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ ተንጠልጥለው የሚገኙት ቡድኖች ትክክለኛ ለሆነ ዕቅድ እና ለህዝቦች ደህንነት ጠቀሜታ ያላቸውን ፖሊሲዎች ለመንደፍ የማይችሉ፣ ህዝብን በዘርና በቋንቋ በማበጣበጥ እድሜያቸውን ለማራዘም የሚፈልጉ ጠባቦች፣ ሀሳበ ግትር እና ለተሻለ ለውጥ በምንም ዓይነት መልኩ ዝግጁ ያልሆኑ የጫካ ወሮበላ የአስተሳሰብ አድማስን የተላበሱ ፍጡሮች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ሃገራችን ሀሳብን በነፃነት ያለፍርሀት መግለፅ የማይቻልባት፤ የዜጎች የኑሮ ደረጃ ከዕለት ዕለት እየተባባስ የሚሄድባት፤ ዘመናዊ የመረጃ መገናኛዎች ሆን ተብለው የታገዱባት፤ የህዝቦቿን ጥንታዊና ብርቅዬ የሆነውን መከባበርና አንድነት በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ለመከፋፈል አገዛዙ የሚጥርበት፤ ዜጎች አለአግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰደዱባት፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ መንግሥት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ ነፃ ሚዲያ የሌለባት፤ ዜጎች ለሀብት ንብረታቸው ዋስትና የማያገኙባት፤ ህዝባዊ መንግሥት የሚናፍቅ ህዝብ ያለባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ቤቶች በቁመታቸው ማደጋቸው እንደዕድገት የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለች። ስለሆነም ኢትዮጵያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማድረግ ለነፃነት፣ ለፍትህ እና ለእኩልነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡

ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የአንድነት ሃይሎች በመተባበር፣ በመጣመርና በመዋሃድ ሃይልን፣ እውቀትን፣ ህብረትን እንዲሁም ገንዘብን በማቀናጀት የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብር ለአንዴና ለመጨረሻ አሸቀንጥሮ ወርውሮ ሃገርንና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርዓቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የበኩሌን ሃሳብ ለማቅረብ እወዳለሁ::

የማለዳ ወግ …የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* “በኢትዮጵያ በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !” ባለሃብቱ!
* ” ቅሬታ ውንጀላው መሰረት ቢስ ነው ” የኢትዮጵያ ዲፕሎማት

ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ ባለስላጣኖች መሬታቸውን እየተቀሙ በደልና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ሞሀመድ አልሸህሪ የተባሉ ባለሃብት ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል። እኒሁ ባለሃብቶችን መርተው ወደ አፍሪካና ወደ ኢትዮጵያ ከአመታት በፊት ወደ የዘለቁት ባለሃብት አንዳንድ የመንግስት ኃላፊዎች በኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ሀገሪቱ ያስገቡትን ንብረቶች ለመውረስ በእርሳቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የወንጀል ክስ አንደተመሰረተባቸው ማስታወቃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል ። ቅሬታ አቅራቢው ሳውዲ ባለሃብት ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ሙስናው የከፋ እየሆነ መምጣቱን በመጠቆምሳውዲ ባለሃብቶች በማመሳሰል ( Forgery) ወንጀል ሳይቀር ተወንጅለው ለስራ ያስገቧቸውን እቃዎች መመለስ እንዳልቻሉ አስረድተዋል ።

ከስድስት አመት በፊት ጀምሮ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሳውዲ ባለሃብቶች በመንግስት የተገባላቸው ቃል በተግባር ባለመፈጸሙ 50 % እጅ ያህሉ ባለሃብት ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣታቸውን እኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ሳውዲ ባለሃብት ተናግረዋል ። በደረሰባቸው በደል ተማረው ሀገሪቱን ለቀዋል ስላሏቸው ባለሃብቶች ሲያስረዱም ያቻሉት ሸጠው መውጣታቸውን አልደበቁም። መሸጥ ያልቻሉትና ያልቻሉት እቃቸውን ትተው የወጡት ግን ተመልሰው እቃቸውን ቢጠይቁ ” በማናውቀው ወንጀል እንያዛለን !” በሚል ስጋት ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ላይ ወረታቸውን በትነው መቅረታቸውን ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል ።

ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማይታወቀውን የሳውዲ ባለሃብቶች ቅሬታና ብሶት ለታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ ለአረብ ኒውስ በአደባባይ ያጋለጡት ባለሃብቱ ሞሃመድ አልሻህሪ ቅሬታቸውን ለሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቢያቀርቡም እስካሁን ምነም አይነት ምልሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል !

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜናውን ማስፈንጠሪያ በፊስ ቡል የፊት ገጼ ላይ እንደለጠፍኩ ” እንዴት ይህን ያልተጨበጠ መረጃ ሊንክ Link ይዘህ ትለጥፋለህ? ” በማለት የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማት ቆንስል ሸሪፍ በስልክ ቅሬታቸውን ግልጸውልኛል ። ለሚሊዮኖች በአለም ዙሪያ የተሰራጨውን መረጃ ማስተላለፊን በአግራሞት የተመለከቱትና በጅዳ ቆንስል የኢኮኖሚ ኋላፊ አቶ ሸሪፍ ኼሪ በዜናው ዙሪያ ዘርዘር ባለ መልኩ አነጋግረውኛል ። እኔም ያቀረብኩት መረጃ ከአረብ ኒውስ ማግኘቴን ደግሜ በማስረዳት ማሰተባበያ ማቅረብ እንጅ የወጣውን መረጃ አታሰራጩ ፣ አለያም አትለጥፉ ማለት እንደ ሚከብድ አሳውቄቸዋለሁ !

ቆንስል ሸሪፍ በመጨረሻም ” አረብ ኒውስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣው መረጃ የተዛባ በመሆኑ አስፈላጊው ሁሉ እርምጃ ይወሰዳል ” በማለት “ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው ! ” ላሉትን የተሰራጨ መረጃ ምላሽ ለመስጠት በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸውልኛል !

ቸር ያሰማን !

ጀግንነት ወይስ ውርደት? መኩሪያ ለዓለም

ኤሊኖ ወይስ አውሮቦሮሶች ነጋ አባተ ከእስራኤል

$
0
0

ሰሞኑን ድኅረ- ገፆቻችንን ያጥለቀለቀው ዓቢይ ጉዳይ “ርሃብ” በሚባል ጨካኝ ምጣድ ላይ ተዘርግፈው እየተቆሉ ላሉ ወገኖቻችን የእንድረስ ጩኽትን የሚያስተጋባ የፌስ ቡክ “የክፉ ቀን”
ዘመቻ ይመስለኛል። ምንም እንኳን ዕንቅስቃሴአችን ከጩኽት መዝለሉን እርግጠኛ ባልሆንም እኔም በጓደኞቼ አማካኝነት ተሳታፊ ሆኛለሁ። ቆይ ግን ጎበዝ! ቆም እንበል በእውነት ክፉ ቀን ወይስ
ክፉ ጠላት? ኤሊኖ ወይስ አውሮቦሮሶች?። “አህያውን ሲፈሩ መደላድሉን” እንዳይሆን ብየ ነው።

የፌስ ቡኩን ዘመቻ የከፈቱት ወገኖቼ በንጉስ በአጤ ምኒልክ ዘመነ- መንግስት ከ1880-1884 የተከሰተውንና ወገናችንን በመሮ ጥርሱ አድቅቆ በትውልድ መካከል የማይደብስ ጠባሳ ጥሎብን ያለፈውን እነኝያ “ክፉ ቀን” በመባል የሚታወቁትን ድርብርብ አሰቃቂና ማቅ-ለበስ ዐመታት ስያሜ በመውሰድ የተጀመረ ዕንቅስቃሴ ይመስለኛል። አዎ! ከባድ ዓመታት ነበሩ ክፉ ቀን የሚል መጠሪያ ይዘውም በታሪክ መዝገብ ከነግሳንግሳቸው ሰፍረዋል። ሌላው ሳይቀር ወራሪው የጣሊያን ጦርም ስለርሃቡ መረጃው ስለነበረው ይህንን ክፉ አጋጣሚ ተጠቅሞበታል ይባላል። ግን ወዴት ወዴት“ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል ይባል የለ” ያ ክፉ ቀን ወዴት የአሁኑ (?) ወዴት።

በዚያ ክፉ ቀን ህዝቡ በሞት የተሸነፉ ዘመዶቹን እየቀበረም እየጣለም እሱም ከሞት ጋር ግብግብ እየገጠመና በነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እየተጣደፈ ከአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ወደ ንጉሱ ዓጤ ምኒልክ ቤተ-መንግስት በጥቁር እንግዳነት ከአሸለቱ ቁመናዎቹ ጋር የተገጠገጠው ችግረኛ ቁጥር እንዲህ ቀላል የሚባል አልነበረም። በዘመኑ ይህንን የሰቆቃ ትዕይንት በዓጤ ምኒልክ ቦታ ሆኖ ላየው ይጨንቃል አቅል ይሰውራል። ይሁን እንጅ ንጉሱ ከእውነቱ ዘወር አላሉም ይልቁኑም በተሰበረ ልብ እንዳመጣጡ ተቀበሉት እንጅ። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ምንድነው ህዝብ የሚያምነው መሪ ሲያገኝ የአባት ያክል ያምነዋል። ህመሙን ፤ ጭንቀቱን፤ የሆዱን ብሶት ሊያካፍለው ይፈልጋል።

ከእግዚአብሄር ቀጥሎ ህዝብ ልቡን የሚጥለው በእርሱ ላይ ነዋ!። ዓጤ ምኒልክ ይህ ግርማ ሞገስ በህዝባቸው ላይ ነበራቸው እምየ የሚለውን ስም ያገኙትም በነኚህ የጭንቀት ቀናት ነው ይላሉ ብዙዎቹ። ለሩህሩህነታቸውና ለደግነታቸው ከህዝብ የተሰጠ የፍቅር ስጦታ!። ደጉ ንጉስ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ከባድማው የተሰደደውን መፃተኛ እንደዛሬዎቹ ጅቦችና ዘግቶ በላዎች፤ ሲቀጥልም የዘመናችን ኦውሮቦሮሶች፤ ክቡሩን የሰውን ልጅ በስቃይ ጅራፍ እይነረተ እመሬት ላይ ስለሚደባልቀው፤ ብሎም እነርሱ ራሳቸው ጎትተው ስላነገሱት የችጋር ጭራቅ መስማት እንደማይፈልጉት የአፍ ጉልበተኞች የመስቃን ቃል አልተናገሩም ፈሪሃ እግዚአብሄር አላ!። በእኔ የንግስና ዘመን ? የምን ርሃብ? ብለው የአካኪ ዘራፍ ምላስ አልወነጨፉም። ከዚህ ይልቅ በቅርባቸው ለነበሩት የሃይማኖት አባቶች እግዚአብሄር ምህረቱን ይልክ ዘንድ አጥብቀው እንዲለምኑ አሳስበዋቸው እሳቸው ግን ከዙፋናቸው ወርደው በእጃቸው የተገኘውን ያድሉ ገቡ። በአካልም በአስተሳሰብም የሸመገሉት ንጉስ ምኒልክ ያደረጉት ይህንን ነው።

የእኛዎቹ የዘመናችን አውሮቦሮሶች ግን በመለኮት እቅድ ምክኒያት ግንዘተ-ልቦና ሆኖባቸዋልና ክፉ ዘርን ይዘሩ ዘንድ በመርዝ በተሞሉ አለብላቢት ምላሶች ላይ በመቆማቸው፤ መልካም ዜና ከነርሱ ዘንድ ላይሰማ እነርሱ ለጸባዖት የራቁትን ያህል ለእነርሱም የራቀ ነው። ከዚያ ይልቅ በደደቢቱ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተው፤ ነገር ግን ጠረጴዛ ላይ ተፈትኖ ለመውጣት በምሁራን መካከል ለመገኘት የሚቅለሰለሰውንና የዓይን-ዐፋሩን የኢኮኖሚክስ ስሌታቸው የ”ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ድምር በሁለት አሃዝ ተመንድገናል እያሉ እንደልጅ ይቧርቃሉ። ወደ ጉልምስና የማይመጣ የተፈጥሮ ህግጋትን የናደ ውበት አልባው ልጅነት! ድንክየነት! ይሏል እንግዲህ ይህ ነው። ለዚህ ነው ታላቁ መጽሓፍ መጽሓፍ ቅዱስ “ንጉሶቿ ህጻናት ለሆኑ ለዚያች ሃገር ወዮላት” የሚለን በልጅነት አዕምሮ መጡ በልጅነት አዕምሮ አረጁ በልጅነት አዕምሮ ወደ መቃብር መውረዱን ተያይዘውታል። የሸመገለና የተፈታ ልብማ እርቅ እርቅ ይሸተዋል፤ ሁሉን የሚሸከምበት ሰፊ የፍቅር ቋት ይኖረዋል፤ ማንም ያለጭንቀት የሚያርፍበት የመንፈስ ጥላ ይኖረዋል።

ምድራችን ለቁጥር የሚታክቱ ለስልጣናቸው የሚንሰፈሰፉ ነገስታትንና አምባገነኖችን አስተናግዳለች ይሁን እንጅ የህዝባቸውንና የሃገራቸውን ክብር የሚነካ ጉዳይ ሲገጥማቸው ግን ሁሉም ማለት ይቻላል ግንባር ቀደም ሆነው ዘብ በመቆም አያስነኬዎች ናቸው። ከእነዚህም መካከል አንዱ አጤ ምኒሊክ ናቸው። ንጉሱ ስልጣን ይገባኛል ብለው ታግለዋል ተራራ ወጥተው ወርደዋል። በህዝብ ላይ ርሃብ በመጣ ጊዜ ግን ህዝቤ፤ ድሆቼ ብለው ከልብ በተሰበረ መንፈስ አነቡ አንጅ የተሟገገውን ገላ አይተው ጎሽ የኔ ልጅ በእኔ የንግስና ዘመን ጠግበኸልኛል ብለው የሳሳውን ገላውን በፕሮፐጋንዳ ሳማ አልገሸለጡትም።

እንደ ወንጭት የተጠረበውን ባቱን አይተው እንዲያ እንጅ ጠብደሃል በል በሚል የግፍ ቃል አንገቱን አስደፍተው ባይተዋር አላደረጉትም። እዚህ ላይ እንደ ዋቢ የምጠቅሰውና “እውነት” የሚለው ክቡር ቃል ይገልጠዋል ብየ የማስበው የሶፎክለሱ ንጉስ ኤዲፕስ ትዝ አለኝ። በእርሱ ዘመን የአቴናን ምድር ያንቀጠቀጠ አንዳች የመቅሰፈት ምች ከተማዋን ያደቅቃት ያልማት ጀምሯል ። ህዝቡም በደረሰበት አደጋ ተደናግጦ፤ ተጎሳቁሎና እንደሞት ሰራዊት በአስፈሪ ድባብ ታጅቦ ወደ ቤተ መንግስቱ ይተም ይዟል። ይህን የተረዳው እውነተኛውና አስተዋዩ ንጉስም ህዝቡን ለመቀበል ከነሞገሱ ወደ ሰገነቱ ይወጣል። በሚያየው ነገር ግን ልቡ ይናጥ ይደማ ጀምሯል። አይን-ስውሩን ነቢይ የዚህ መቅሰፍት መንስኤና መፍትሄው ምን እንደሆነ እንዲነግረው አጥብቆ ይጠይቀዋል። ከብዙ የዙሪያ ንግግርና ከሽማግሌዎቹ መዘምራን ምክር
በኋላ ንጉሱ እውነቱ ካልወጣ መፍትሄ የለም በሚል እሳቤና ፤ እውነትንና ፍትህን በአደባባይ ለማቆም ቆርጦ በመነሳቱ ምክኒያት አውጫጭኙ ከሯል። ሁሉም ክርክሩ በፈጠረው ግለት በፍርሃት እየተለበለበ
ጥግጥጉን ይዟል ይባስ ብሎም ንጉሱ ችግሩና መፍትሄው ካልተገኘ ደግሞ በየደረጃው ያሉትን ሃላፊዎችን ተገቢውን ቅጣት እንደሚያከናንባቸው ዛተ። የነገሩ ስር ከግራ ከቀኝ እየተቧካ በስተመጨረሻው
ፍርጥርጡ ወጣና ንጉሱ የመርገሙ ምክኒያት ሆኖ ተገኘ። እዚህ ላይ ነው የኤዲፐስ ማንነት የሚታየው ከተጠያቂነት ለመዳን ልሸፍን ላዳፍን፤ ስልጣኔን ንግስናየን ላስጠብቅ አላለም በራሱ ላይ አስቃቂውን
እርምጃ በመውሰድ ስልጣኑን ለቆ ከምቹው ቤተ-መንግስት በመውጣት የእውነትንና የፍትህን ጫፍ አሳየ። እዚህ ላይ ከንጉሱ አስገራሚ ባህሪዎች ሁለት ዋና ዋና ቁምነገሮችን ልናይ እንችላለን በመጀመሪያ ከኔ የተሻለ ዕውቀት ሌሎች ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብና ሌላው ደግሞ እውነት እንዳትዳፈን መድከሙ ናቸው። የአቀባበላቸው ዳኝነት እውነት መሆኑ ደግሞ ሁለቱን ንጉሶችን አመሳሰለብኝ።

የመጣጥፌ ዋና ዓላማ የዘመናችንን አውሮቦሮሶች ጥላሸት በመቀባት የፖለቲካ ትርፍ በማግኘት በጭንቅ ውስጥ ባሉ ወገኖቼ ህይወት ላይ ቁማር ለመጫወት እንዳልሆነና ሰውን ያክል ክቡር ፍጥረት እንደሰው በስፍራችን መገኘት አቅቶን በነገር ዘባተሎ እየተጠላለፍን በወደቅንበት በዚያ ቁመናውም ልኩም በማይታወቅ የውዝግባችን ቅርቃር በመሸንቆር ያስተሳሰብ ብልግና ውስጥ ራሴን ለመጣል በመፈለግም አይደለም።
ጥያቄየ ግን እውነቱ ወዴት ነው ? ነው። የርሃባችን አቢይ ምክኒያት ብዙዎቻችን እንዳልነው የቀኑ ክፋት ወይስ የገዥዎቻችን ክፋት ? ወይስ እነሱ እንዳሉት ኤሊኖ?። ኤሊኖ! አይ ቅጥፈት! ነገ ደግሞ
የሆነ ችግር ቢፈጠር የዚህ ችግር ዋና ምክኒያት የህዳሴው ግንባታ ያመጣብን ጣጣ ነው ሊሉን ይችላሉ ምን ችግር አለው? ባፈጠጠ የህሊና ጥሰት ለሚኖር እጓለ ምዑት ሰፈር እኮ ውሸት አንድ ሙዚቃ ነው።
ምነው ገዥዎቻችን ራሱን እንደሚበላ አውሬ አረመኔነቱን አጦዙትሳ? የዚህ በለየለት የህዝብ የጠላትነት ጫፍ ላይ መቆም ጉዳይስ የሂሳብ አወራረዱን ምን ያስመስለው ይሆን?። ደግሞስ በዚሀ በሰለጠነ ዘመን ሰለ ርሃብ ማውራት አይቀፍም ወይ?። ለገባውማ ይቀፋል ይጎፈንናል እንጅ! ለደደቢት ምሩቃን ግን ይህ የመርህ ጉዳይ ነውና እንደ ታላቅ ስኬት ይቆጠራል።

በአጤ ምኒልክ ዘመን ከደረሰብን ርሃብ አርባ ዓመት ቀደም ብሎ በድንች ላይ ጥገኛ በነበረው የአየርላንድ ህዝብ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ርሃብ አየርላንዶቹ ታሪካቸውን በሃዘን የሚገልጡት ምዕራፋቸው ነው። “ The great famine” ተብሎ በተሰየመው በዚህ ርሃብ “The potato blight” የሚባል የድንች በሺታ ተከስቶ በሚሊዮን የሚቆጠር የአየር ላንድን ህዝብ አርግፏል አሰድዷል። ለዚያ ርሃብ በህዝቡ በኩል የቀረበው ምክኒያት በጊዜው በነበረው የአስተዳደር ብልሹነት ነው ሲል በሹሞቹ በኩል ግን የለም በጊዜው የተከሰተውን የድንች በሺታ ነው በሚል የተነሳው ውዝግብ ቀጥሎ ግን ሳይቋጭ ደተንጠለጠለ የቀረ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጅ ያ የርሃብ ምች እንደኛ እያሰለሰ አዚም ላይሆን ዳግመኛም ተከሰቶ የአየርላንድን ህዝብ ላይቀጥፍ አሸልቦ በአየርላንዳዊያን ግብዓ- ተመሬቱ ተፈጽሟል። የእኛ የርሃብ አዙሪት ግን እኛኑ ሊቀብረን እየሰለለን ይመስላል እውነተኛውን መንሰኤውንና መፍትሄውን ገና አላገኘነውማ!።

በዚህ በምኖርበት በእስራኤል ሃገር እስራኤላውያኖቹ የሚሉት እኔንም የሚገርመኝ ነገር አለ። ይኸውም መሬታቸው በአብዛኛው አሽዋማ ነው ግን ይሰሩበታል፤ የተስተካከለ የዝናብ ወቅት የላቸውም
እነርሱ በዚያም ጥገኛ አይደሉም፤ የመሬታቸው የቆዳ ስፋት ትንሽ ነው ግን ከሚበላው የሚደፋው ይበልጣል። እነርሱም በኩራት የሚናገሩት እዚህ ላይ ነው። “በካርታ ላይ እስራኤል ብሎ ለመጻፍ ቦታ
እንደሌለ ሁሉ መሬታችንም ጠባብ ናት ግን እስራኤል ሃገር ርሃብ የለም።” ይላሉ። ስለአንዱ የገጠር መሬታቸው ትንሽ ልንገራችሁ ትንሿ ገጠር יוטבטה’’ (ዮትባታ) ትባላለች በሃገሪቱ ደቡብ ምስራቃዊ
ክፍል ትገኛለች። የዚህች መንደር መሬት አሽዋ ነው የመንደሯ ነዋሪዎች አርሰው ለማምረት ሲፈልጉ መጀመሪያ መሬቱን አጥበው ጨውን ማስወገድ አለባቸው ከዚያ በኋላ ነው ዘር የሚዘሩት ታዲያ የዚህች ትንሽ የገጠር መንደር ገበሬዎች በመላ እስራኤል የእርሻ ምርታቸውንና የወተት ተዋጾዖቻቸውን በማቅረብ ይታወቃሉ። እስኪ በስራኤል ዓይነት የእኛን ሁኔታ እንመልከት።

ወደ ጉዳያችን ስመለስ የዘንድሮው ጠኔ ገድ አልባ ሆኖና እንደ ቀላዋጭ እንግዳ ተሰልችቶ ነው ብቅ ያለው። በም ዕራባውያን በኩል ከሰራተኛው ህዝብ ከሚሰበሰበው ግብር እየተቆረሰ የሚላከው ገንዘብ
የገዥዎቻችን የብልግና ጡንቻ ማፋፊያ እንደሆነና አውሮቦሮሶችም መናጢ ደፍቶ በላ ትዝቢዎች መሆናቸውን ከተገንዘቡ ውለው አድረዋል። እናም የሚራራው ልባቸው ተዘግቷል። እዚህ ላይ አንድ ገጠመኜን በምሳሌነት ላንሳ በስደት ከሃገሬ ከመውጣቴ በፊት በሙያየ ለአንድ መያድ (NGO) የ 30 ደቂቃ አጭር ተውኔት እንዳዘጋጅላቸው እየተነጋገርን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍው የኖርዌይ ልዑካን ቡድን ለግምገማ ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡበት ወቅት ነበር። ልዑኩ የስራ ምገማውን ከጨረሰ በኋላ የደርሰበት ድምዳሜ ከሚንቀሳቀሱት ጣቢያዎች መካከል ሰባቱን መዝጋት መወሰኑን አሳወቀ ምክኒያቱስ ተብሎ ሲጠየቅ ልዑኩ የሰጠው አጭር መልስ “ የሃገራችሁ ባለጠጎች የሚይዟቸውን መኪኖች ስንመለከት በእኛ ሃገር በብዙ ሰዎች የማይያዙ ንብረቶች ናቸው እኛ ይህንን የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስናንቀሳቅስ ከድሆች እየለመንን ነው። በእኛ ግንዛቤ እነዚህ

ባለጠጎቻችሁን በታግባቧቸው ይህን ፕሮጀክት ሊያንቀሳቅሱ ይችላሉ ብለን እናምናለን።” በማለት

ውሳኔአቸውን አጸኑ።

አስተውሉ እነዚህ የኖርዌይ ሰዎች እየተናገሩ ያሉት ሰው ስለሚባለው ሰው ነው። ወገኖቹ በርሃብ

ሲያልቁ ከአልጋው ወርዶ መሬት በመተኛት ያለውን ስለሚያካፍለው ሰው!። ከሚያማርጠው ውስኪ

ወጣ ብሎ ለወገኖቹ አንድ ጣሳ ውሃ ማቅረብ ስለሚችል ሰው!። ልቦናውን እንደተሰረቀውና እንደ

አለሌ የሜዳ አህያ ከሚፋንንበት ርቆና ከህሊናው ጋር ታርቆ ስለሚኖረው ሰው!። በነርሱ ሃገር የህሊና

ግዴታ የሚባል ነገር አላ!። ይህማ ባይሆን ከሃገራቸው ኢትዮጵያ ድረስ ምን አንከራተታቸው?። እነዚህ

እንግዶች የኢትዮጵያ ባለጠጎች ይሳተፉ ማለታቸው በሰው ውስጥ ሊኖር የሚገባውን ህሊና መሰረት

አድርገው ነው። ህሊናውን በጣለ የወዲኒ መንጋ መካከል መኖራቸውን አላወቁም ነበር።

የወደቅንበትን እናስተውል የማዕድ በጀት አልባ ሆኖ በቆሻሻ ገንዳ ከውሻ እና ከአሞሮች ጋር እየተናጠቀ

ጉሮሮውን ዘግቶ በሚያድርባት ሃገር ሌላው የሁለት ሚሊዮን ብር ይዞ ሲንፈላሰስ የህሊና ህግ ስለተጣሰ

አይጠየቅም!። የፋራ ነው!። ውሃ ባአግባቡ ማቅረብ ባልቻለች ሃገር ውስጥ ጥቂቶች ውስኪ እንደ

ውሃ የሚራጩባት የጉድ ሃገር መሆንዋን ስናይ የሰው ያለህ ብለን በባይተዋርነት እንንገደገዳለን። ምንጩ

ሲመረመር ደግሞ አይን ያወጣ ሌብነት በሃገሪቱ በመንሰራፋቱ ነው። የወረድንበት የዝቅጠት ልክ

ሲለካ አራዊትን እንኳን አልመጠነም ቀልለን ተገኜን። ምን ማለቴ ነው በቡድን የሚጓዝ የአራዊት

መንጋ ዞጉን አይነካም ነውር ነው ህገ-አራዊት ወሰናይ አላቸውና! ቢጣሉ እንኳን አይገዳደሉም ።

ኃይላቸውን ለሌላው ባላንጣቸው ይጠብቁታል እርስ በርሳቸው ቢገዳደሉ ለነገ የመኖር ዋስትና

እንደሌላቸው ያውቁታል ይህ ዕውቀት አላቸው። ያደኑትን ተካፍለው ይበላሉ ከመሃከላቸው አውራ

የተባለው እንኳን ኃላፊነት ተሰምቶት ከርሱ ለሚያንሱት ትቶላቸው ዘወር ይላል። ሃገራችን ግን

በአውሮቦሮሶች ተውርራለች።

በግሪካውያን ጥንተ-እምነት ጥናት መሰረት አውሮቦሮስ የሚባል የድራጎን አይነት ነበር። ፕሌቶ ስለዚህ

ዝርያ ሲናገር “ዝርያው ዓይን ስለሌለው አድኖ የሚበላውን አያይም ፤ ጆሮም ስለሌለው አዳምጦ

የሚጎመርበት ፍጥረት የለም አፈርና ውኃ ሲልስ አድጎ በመጨረሻ ከጅራቱ በመጀመር ራሱን እየበላ

ወደ ግብዓ- ተመሬቱ ያዘግማል። እናም ፕሌቶ ስለዚህ አሳዛኝ አውሬ ሲደመድም ራሱን የሚበላ ፍጥረት

በዚህች ምድር ህልውና የለውም።’’ ይህን የድራጎን ዘር ከእኛዎቹ ወዲኒዎች ጋር ያመሳሰልኩበት

ምክኒያትም የሚሰሙበት ጆሮ የሚያዩበት ዓይን ስለሌላቸው ነው። ያላቸው አፍ ብቻ ነው። ያ ነው

ጉልበታቸው። ያንም ህዝባቸውን ለመብላት እየተጠቀሙበት ነው ሌላውን ለማሸነፍ አፍ ብቻውን

ጉልበት አይሆንም ። ግን ርቀቱ እስከየት ነው?። ህዝብ በስደት ውኃና በርሃ እየበላው አንድ ወፍ የሞተ

ያክል እንኳን የዚያን ህዝብ ዕልቂት ከቁብ አይቆጥሩትም የዕልቂቱ ምክኒያትም እነርሱ መሆናቸውን

ባለመቀበል በክህደት ይደመድሙታል። ከዚህ በላይ የራስን ህዝብ ራስንም ከመብላት የበለጠ

አረመኔነት በየትኛው ፍጥረት ይታያል?። 15 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ ውሸት ነው ብለው በፕሮፐጋንዳቸው

ለማፈን ተሯሯጡ በርሃብ እየተጠበሰ ካለው ህዝብ ይልቅ የእንቧይ ካብ ስልጣናቸው በልጦባቸው

በተራበው ህዝብ ላይ ቀለዱ። ይባስ ብለው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመበጀት ህወሐትና

ብአዴን (EPRDF) ለአስረሽ ምቺውና ለሴሰኝነታቸው ማስገሪያ እየበተኑ ነው።

የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ በሚል ፈሊጥም ፊታቸውን በአሞሌ ታጥበው ለአንድ ሰው 25 ሚሊዮን ብር

ግምት ያለው ቤት እየሰሩ እንደሆነ ነግረውናል። እነዚህ ሰዎች የህዝብን ገንዘብ ሰርቀው የግላቸው

ሲያደርጉ ኢሞራላውነትና ኢሰብዓዊነትን እያነገሱ ነው ይህንም ሲያደርጉ ህዝብንም ትውልድንም እየበሉ

እንደሆነ አላወቁም ትውልድን ሲበሉ ራሳቸውን እየበሉ መሆኑንም ገና አልተገለጠላቸውም ። ከዚህ

በላይ በህዝብ ላይ ንቀትና ጥላቻስ በምን ይገለጣል?። የናረ የህዝብ ጠላትነት!። ግን አንድ ነገር

እመኛለሁ ደብቶ ከያዘን ከዚህ አዚም ስንወጣ! ያኔ ለጠላቶቻችን ዕድሜ የሰጠናቸው እኛ መሆናችን

ሲገባን ራሳችንን እንወቅሳለን።

The enemy of the people (የህዝብ ጠላት) ከሚለው የኢብሰን ተውኔት ትንሽ ማለት ፈለግሁ።

በኢብሰን ተውኔት ውስጥ ከህዝብ ጎን በቆመው ሃኪም እና በህዝብ ጠላትነት በቆመው የከተማዋ

ከንቲባ ገጸ፟-ባህሪያት መካከል ያለውን ፍትጊያ በአጭሩ ስናይ ሃኪሙ የከተማዋን ነዋሪ እያረገፈው

ያለውን ሞት ምክኒያት ለማወቅ ሲወድቅ ሲነሳ ይቆይና ምክኒያቱን ያገኘዋል ያም የከተማዋ ህዝብ

የሚጠቀምበት ውኃ በመመረዙ ነው። ሃኪሙ መንስኤውን በማግኘቱ ትንሽ ተደስቶ ወደ መፍትሄው

ሲዞር ደግሞ መፍትሄ ብሎ ያገኘው የከተማዋን ህዝብ ወደ ሌላ ስፍራ ማዞር ነው ይህንንም ለከተማዋ

ከንቲባ ያማክረዋል። የከተማዋ ከንቲባም ለሃኪሙ ምክኒያቱንም መፍትሄውንም እንዳይናገር

ይከለክለዋል ይባስ ብሎ በከተማዋ ከሚገኘው ታዋቂ የጋዜጣ ኤዲተር ጋር በመመሳጠር

የፕሮፕጋንዳውን ስራ ያጧጡፉታል። ለህዝቡ ሞት ደንታ ያልሰጠው ከንቲባ የሃኪሙንም የመናገር

መብቱን ከለከለው። የከንቲባው ዋና ዓላማ ህዝብ አይደለም ስልጣንን ማስጠበቅ ነው ለዚህም

የፕሮፕጋንዳውን ስራ ማጧጧፍ ነው። ትንቅንቁ ይቀጥላል። የህዝብ ጠላት የሆኑ ሹሞች ጉዳያቸው

ከስልጣናቸው ጋር እንጅ ከህዝብ ጋር አይደለም ይህ ስራቸው ደግሞ በህዝብ ጠላትነት ጎራ

ያስፈርጃቸዋል። ቸር ያገናኘን።

በደልን መላመድ ባርነት ነው ! አሥራዳው (ከፈረንሳይ)


የተቆለፈበት ቁልፍ ! ትችት! በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

$
0
0

ከዶ/ር ምህረት ከበደ፣ የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት፣ እ.አ በ2005 ዓ.ም የተጻፈ መጽሀፍ፣ 438 ገጽ
ትችት! በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፣ የስልጣኔ ተመራማሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያ !

ይህን መጽሀፍ አግኝቴ ለማንበብ እድል ያጋጠመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ባለቤቴ ወደ ኢትዮጵያ ሄዳ ስትመለስ ይዛልኝ ከመጣች በኋላ ነው። በዶ/ር ምህረት ከበደ የተጻፉ ሁለት ወፈፍራም መጽሀፎች ሲሆኑ፣ አንደኛው መጽሀፍና በቅርብ የወጣውን የሽፋኑ ሰዕል ደስ ስላለኝ እንደ አጋጣሚ አንስቼ ካገላበጥኩኝ በኋላ፣ እስቲ ብዬ ደግሞ ሌላውን ሳገላብጥ አቀራረቡ ደስ ስላለኝ ሃሳቡን ይበልጥ ለመረዳትና ለመገምገም ሆነ ወይም ለመተቸት እንዲያመቸኝ በሚል በመጀመሪያ ያገላበጥኩትን በመተው ቀደም ብሎ የታተመውን ማንበብ ጀመርኩኝ። እንደ ዕውነቱ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ የሚመጡ በአማርኛ ቁንቋ የተጻፉ መጽሀፎችን ትንሽ ካገላበጥኩኝ በኋላ ምንም ስለማይጥሙኝና አብዛኛዎችም ዝም ብሎ ትረካና የህብረተሰባችንን ህሊናዊ አወቃቀርና በዚያም አማካይነት በመሬት ላይ የሚታየውን ህያው በሆነ መልክ ለመተንተንና እንድንረዳው የሚያደርጉ ስላይደሉ በንባቤ አልገፋባቸውም። የስነ-ጽሁፍም ዋና ዓላማው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን አስቀያሚም ሆነ ቆንጆ ነገሮች ስዕላዊ በሆነ መልክ መግለጽ ሲችሉና አንባቢውን በልዩ ሃሳብ ውስጥ ተመስጦ እንዲዋኝ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው። ከዚህ አኳያ የዶ/ር ምህረት ከበደ መጽሀፍ ልዩና አንባቢዉን በሃሳብ ባህር ውስጥ ገብቶ እንዲዋኝ የሚያደርግና፣ የአገራችንን ነባራዊም ሆነ የህዝባችንን ህሊናዊ አወቃቀር ግሩም በሆነ መልክ የሚያቀርብ በታሪካችን ውስጥ በመጀመሪያ ጊዜ በልዩ አቀራረብ የተዘጋጀና የተጻፈ ትምህርታዊ መጽሀፍ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። የመጽሀፉ አርዕስትም ካለምክንያት የተመረጠ ሳይሆን፣ ለአንድ የተቆለፈበት ነገር መፍትሄው በአዕምሮ ውስጥ ያለ ቁልፍና፣ ለአንድ ህብረተሰብ መዘበራረቅና ስነ-ምግባር መበላሸት ደግሞ የጭንቅላት መቆለፍ ወይንም የአዕምሮን የማሰብና የመፍጠር ኃይል ለመገንዘብ ካለመረዳት ጋር የተያያዘ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። ጸሀፊው የኖይሮ ባዮሎጂ ሊቅ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሙያ ባልሰለጠነ ከማንኛውም ምሁር የሚበልጥ ግንዛቤ ስላለው፣ የአዕምሮን ልዩ ልዩ ባህሪዎች የበለጠ የተገነዘበና በመጽሀፉ ውስጥ ደረጃ በደረጃ ቲያትራዊ በሆነ መልክ ያቀረበ ነው። በመጽሀፉ ውስጥ የተዘረዘሩት ልበ-ወለድ ስሞች ባህርይና ድርጊት በእርግጥም የማንኛውም ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆኑ፣ የጠቅላላው የዓለም ህዝብ ባህርይ ሲሆኑ፣ በሌላ ወገን ግን ባደገና በሰለጠነው የካፒታሊስት ህብረተሰብ ውስጥ የሚኖረው ግለሰብም ሆነ ህዝብ ከማቴሪያላዊ ዕድገት ጋር በተያያዘ አስተሳሰቡና ድርጊቱ ለየት ያለ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ደራሲው በሁለት በተለያዩ አገሮች የሚኖርና ሙያዊን ተግባራዊ የሚያደርግ በመሆኑ፣ በሁለት አገሮች ያለውን የዕድገት ልዩነት በንጽጽራዊ መልክ በማወዳደር ማቅረቡ አጠቃላይ የሆነ ማቴርያላዊ ዕድገትም ሆነ ዕድገት በቀጨጨበት ዓለም ውስጥ የሚኖር ህዝብ ስለሰው ልጅም ሆነ ስለተፈጥሮ የተለያየ አስተሳሰብና ግንዛቤ እንዳላቸው ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጣል። ወደ መጽሀፉ መሰረታዊ ሃሳብና የአሰራር ስልት ላይ ደረጃ በደረጃ ልምጣበት።

የትዕይንቱ ዋና ተዋንያን መላኩና ሰሎሜ ሲሆኑ፣ ሁለቱም ለየት ያለ የማህበረሰብ መሰረት(Social Background) ያላቸውና፣ በአስተሳሰብም የሚራራቁ አይደሉም። ከሁለቱ ተዋንያን ባሻጋር፣ በመጽሀፉ ውስጥ ልዩ ልዩ ባህርይ ያላቸው ስዎች ተካተውበታል። ጥሩ አመለካካት ያላትና መላኩን እንደታናሽ ወንድሟ አድርጋ ያሳደገችውና ለቁም ነገር እንዲደርስ የረዳችው፣ የህሊና ስፔሻሊስት የሆነችው ዶ/ር ሳራ፣ የስሜቱ ተገዥና የሚያደርገውን በትክክል የማያውቀው ምንተስኖት የሚባለው የዶ/ር ሳራ ባል፣ ቀና አመለካከት ያለው፣ ራሱን ከተንኮል ያፀዳውና በራሱ ጥረት ከታች በመነሳት ከፍተኛ ቦታ የደረሰው ማርቆስ የሚባለው የመላኩ የቅርብ ጓደኛ፣ የስሜቷ ተገዢ የሆነችና፣ የራሷን ጥቅም ለማግኘት ስትል ምንም ነገር ከማድረግ የማትመለሰውና በተንኮል የተካነችው ስንክሳር የምትባል ሴት፣ ሰፋና ጠለቅ ያለ ዕውቀት ያላቸውና ብዙ ነገሮችን ማገናዘብ የሚችሉት የሰሎሜን አባትና እናት፣ አቶ ኦላንና ባለቤታቸው፣ መንፈሱ ቆንጆ የሆነውና በልጅነቱ የበሰለ አስተሳሰብን ያዳበረው የሶሎሜ ወንድም፣ ሶለን የሚባለው፣ በልጅነቷ ብዙ ስቃይን ያሳለፈችውና በእናቷ ግሪክ፣ በአባቷ ደግሞ ጥቁር አሜሪካዊት የሆነችው መንፈሷ ቆንጆ የሆነና የሰዕል ስጦታ ያላት ሶፊያ፣ የኩላሊት በሽታ ስፔሺያሊስት የሆነውና፣ የኩላሊትን በሽታ ከማከም በስተቀር በጭንቅላቱ ውስጥ ሌላም ብዙ ዕውቀት የሌለውና፣ ለመኖር ብቻ የሚኖረው፣ ክብሮም የሚባለው፣ እነዚህ ሁሉ እንደየባህርያቸው በመጽሀፉ ውስጥ በመካተት ለመጽሀፉ የንባብ ጣዕም የሰጡት ናቸው ማለት ይቻላል። ደራሲው እንደዚህ ዐይነት የተለያየና የተዘበራረቀ አመለካከት ያላቸውን ስዎች በልበ-ወለዱ ውስጥ ማካተቱና መቃኘቱ የሚያመለክተው የቱን ያህል የህብረተሰብአችንን የተበላሸ ማቴሪያላዊ መሰረትና የህዝባችን የተዘበራረቀ የህሊና አወቃቀር እንደገባው ነው። ወደ ዋናው ተዋንያን ወደ መላኩና ሰሎሜ ጋ፣ እንዲሁም የሰሎሜ ቤተሰቦች ጋ በመምጣት የደራሲውን አመለካከትና፣ ስለሰው ልጅ ያለውን ግንዛቤና፣ እንዲሁም ይህ ጉዳይ ስለ አንድ ህብረተሰብ ዕድገትም ሆነ ፀረ-ዕድገት ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖና አስተዋጽዖ ጠጋ ብለን እንመልከት።

መላኩ በአባቱ የአፋር ሰው ሲሆን፣ አባቱን ፈጽሞ አያውቀውም። ስለሆነም መላኩ አባቱ በሌለበት መቂ ከተማ አክስቱ ቤት የተወለደ ሲሆን፣ በእናቱና በአክስቱ አለመግባባት የተነሳ እናቱ አዲስ አበባ መጥታ አስር ዐመት እስኪሞላው ድረስ አሳድጋው በድንገት በመኪና አደጋ ሞተች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኑሮው ስቃይና ትምህርቱን በስርዓት ይከታተል አይከታተል የሚቆጣጠረው ዘመድ አልነበረውም። አጠገቡ ያለውም አጎቱ ሊረዳው የሚችል አልነበረም። መላኩም በኑሮው የተጎሳቆለ ስለነበር የትምህርት ቤት ጓደኞቹ ይስቁበት፣ ይሳለቁበት ነበር። እናቱ ተቀጥራ ትሰራ የነበረበት መስሪያቤት አለቃ የነበሩት ወይዘሮ የትናየት የሚባሉት እንዳጋጣሚ በመንገድ ላይ ሲሄዱ፣ መላኩ አንድ ቀን ውሃ በባልዲ ተሸክሞ ሲሄድ አሳዝኗቸው እያዩት ጠጋ ብለው በመጠየቅ የማን ልጅ እንደሆነ ለማረጋጋጥ ይችላሉ። የሚኖርበትን ሁኔታም እስከቤቱ ድረስ ሄደው በማየት ወስደው እሳቸው ጋር እየኖረ ያስተምሩት ዘንድ አጎቱን ይጠይቁታል። በስነ-ስርዓት መላኩን መከታተልና ማሳደግ ያልቻሉት የመላኩ አጎትና ባለቤቱ፣ እንዲያውም ጎርምሶ እስቸግሮናል በመላት በመሄዱ መስማማታቸውን ለወይዘሮ የትናየት ይነግሯቸዋል። መላኩም ወይዘሮ የትናየት ቤት በሳቸው የመጨረሻ ልጅ ሳራ በምትባለው እየታገዘ ትምህርቱን በመከታተል ጎበዝ እየሆነ መጣ። ማትሪክንም አልፎ የህክምና ትምህርት በመከታተል ላይ ሳለ ደስ ስላላው ለሳራ ሌላ ዐይነት ትምህርት ለመማር እንደሚፈልግ ይነግራታል። እንደ ወንድም የረዳቸውና ያሳደግችው ሳራም እንግሊዝ አገር የመማር ዕድል አገኘችለት። እንግዝሊም የኢኮኖሚከስ ትምህርቱን በመከታተል ላይ እንዳለ ይበልጥ ያደላ የነበረው ፍልስፍና፣ ታሪክና የስነ-ልቦና መጽሀፎችን በማንበብ ነበር። የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን እንደዋና አይመለከተውም ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ አንድ ካናዳዊ ዝንባሌውን በማየት ረድቶት፣ ካናዳ፣ ቶረንቶ ሄዶ እዚያ ትምህርቱን የመከታተል ዕድል አገኝለት። መላኩም የማስተር ትምህርቱን በጥሩ ውጤት ካጠናቀቀ በኋለ ዶክትሬቱን ለመስራት ዕድል ቢያገኝም አገሬ ውስጥ ብዙ ያልተሰራ ነገር አለ በማለት በመመለስ አገሩን ለመርዳት ቆርጦ ተነሳ። እንደተመለሰ ተቀጥሮ የመስራት ዕድል ያገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መስሪያቤት ውስጥ ነው። እዚያም አንድ አራት ዐመት ያህል ከሰራ በኋላ መስሪያቤቱ የሰውና የገንዘብ ጠር ነው፣ ጥቂቶችን የሚያደልብና ድህነትን የሚያጠናክር ነው በማለት በግልጽ የሚታይ አነስ ያለ መስሪያቤት ውስጥ ተቀጥሬ ብሰራ ይሻላል በማለት ብዙ ገንዝብ የሚያገኝበትን መስሪያቤት ጥሎ በመውጣት ሌላ ቦታ ተቀጥሮ መስራት ይጀምራል። እንዳጋጣሚ ወይዘሮ የትናየት ቤት ማደጉና፣ እንደ እህትም እየተከታተለች ታስረዳውና ታስተምረው የነበረችው ሳራና፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለፍልስፍና፡ ለታሪክና ለህሊና ሳይንስ የነበረው ዝንባሌና፣ የተፈጥሮን ምንነት ጠጋ ብሎ ለመገንዝብ የነበረው ጉጉት ባህርይውንና ስለሰው ልጅ ያለውን አስተሳሰብና፣ ስለ አጠቃላይም ህብረተስብአዊ ዕድገት ያለውን አመለካከት መቅረጻቸው የማይካድ ለመሆኑ የልበ-ወለዱን አቀራረብ ለተመለከተ ሊገነዘበው ይችላል።

ሁለተኛዋና እንደሱው ዋናው ተዋናይ የሆነችው ሰሎሜ ደግሞ የተሻለ የህብረተሰብ መሰረት ካላቸው ቤተሰብ ውስጥ የተወለደች ስትሆን፣ ከአስራአንድ ዐመቷ ጀምሮ ከቤተሰቦቿ ጋር አሜሪካን አገር በመሄድ ትምህርቷን እዚያ የተከታተለችና፣ በጥሩ ቤተሰብአዊ አስተዳደግ በፍቅር ያደገችና፣ ስለሰውም ልጅ ያላት ዝንባሌ ከመላኩ ጋር የሚመሳሰል ነው። ሰሎሜ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ እንደዚሁ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትንና ሴተኛ አዳሪዎችን መልሶ የማቋቋም፣ በውጭ ሰዎች የሚደጎም የገብረ-ሰናይ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ መስራት ጀመረች። እዚያ ተቀጥራ መስራት ከጀመረች ወዲህ፣ ይህ ዐይነቱ በህፃናት ላይ የሚደርሰው ግፍና፣ ካለ አሳዳጊ ጎዳና ላይ ተጥሎ ለማኝ መሆንና፣ በትንሹ በትልቁ እንደ ቆሻሻ ዕቃ መታየትና፣ በሴተኛ አዳሪዎችም ላይ የሚደርስባቸው ግፍ እየከነከናት በፍጹም ልትቀበለው የማትችለውና፣ እንደ ህብረተሰብአዊና እንደ ተፈጥሮ ህግ ሆኖ መታየት እንደሌለበት መገንዘብና፣ ይህንንም መዋጋት እንዳለባት ቆርጣ ተነሳች። ደራሲው ቁልጭ አድርጎ እንደሚተነትነው፣ ሶሎሜ እየደጋገመች የምታነሳው ጥያቄና መልስም ለማግኘት የሚያስጨንቃት፣ የሰው ልጅ ለምን ደሃ እንደሚሆን ነው። ለድህነት መንስዔ የሚሆነው ምክንያት ምንድነው ? ድህነት ከህብረተሰቡ የአኗኗር አወቃቀርና አስተሳሰብ ጋር የተያያዘ ወይስ ዋናው ምክንያት ሌላ ነገር ነው? የሚለው ጥያቄ ያብሰለስላታል። እንደደራሲው አተናተን፣ “ …. አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃን ወይም ሴተኛ አዳሪ ችግራቸውም ሆነ ማንነታቸው ከህብረተሰቡ ሁኔታ ተነጥሎ የሚታይ ሳይሆን፣ የተሳሰረና የተጠላላፈ ነው፣“ የሚለው መደምደሚያ ላይ እንደደረሰች ደራሲው በግሩም ብዕሩ ያረጋግጣል። ሰሎሜ ጥያቄን በመጠየቅና መልስም ለማግኘት የምትጨነቅ ብቻ አይደለቸም። ለሰው ልጅ ሁሉ ፍቅር አላት። ደሃ፣ ሀብታም፣ ቆሻሻ ልብስ የለበሰ፣ ወይም የዘነጠ፣ ለአንዳንዶች አስቀያሚ የሆነ ወይም የአካል ጉድለት የደረሰበት፣ ለሷ የሰው ልጅ ሁሉ አንድ ነው። አንዱ ከሌላው እንደማይበልጥ ነው የምትገምተው። አንዳንዶች፣ አንዱን ሰው ቆንጆ ነው፣ ሌላውን ሰው ደግሞ አስቀያሚ ነው ሲሉ ግራ ይገባታል። የሰውንም ልጅ የምትለካው በለበሰው ልብስ ወይም „መልኩ በማማሩ“ ሳይሆን፣ በመንፈሱ ቁንጅናነትና፣ ስለሰው ልጅ ባለው አመለካከት ብቻ ነው። ለሷ የሰው ልጅ ሁሉ ሰው ነው። አንዱ ከሌላው የሚበልጥበት ወይም የሚያንስበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ዕምነቷ ነው። አንድ ቀን ከመላኩ ጋር ተቀጣጠረው እሱን ለመጠበቅ ስትል አንድ ቡና ቤት ውጭው ላይ ትቀመጣላች። አንድ በፍጥነት የሚበር ታክሲ በአካባቢው ቆመው የሚለምኑ ሽማግሌ ገጭቶ ከወደቁበት ሳያነሳቸው ዝም ብሎ እየነዳ በፍጥነት ያመልጣል። የሽማግሌውን መውደቅና የደረሰባቸውን መጠነኛ ጉዳት የተመለከተችው ሰሎሜ በፍጥነት በመሄድ ከወደቁበት አንስታና ደግፋ በመውሰድ ቡና ቤቱ በራፍ ላይ ያለው የቡና ቤት መቀመጫ ላይ እንዲቀመጡ ታደርጋለች። ይህንን የተመለከተችው የቡና ቤቱ አሳላፊ ወደ ሰሎሜ ጋ በመምጣት ቡና ቤቱ እንደዚህ ዐይነት ቆሻሻ ልብስ የለበሱና የተጨራመቱ ስዎችን ማስተናገድ እንደማይችልና፣ እንደነዚህ ዐይነት ሰዎችም ደንበኞቿን እንደሚያባርሩባት ቦታውን ለቀው እንዲሄዱ ታመናጭቃቸዋልች። ሶሎሜም በአሳላፊዋ አነጋገር በመገረምና በመናደድ፣ ለምን እንደዚህ እንደምታስብና፣ ይህም ሊሆን እንደማይችል፣ የቡና ቤቱ ባለቤት መጥቶ እንዲያነጋግራት ለአሳላፊዋ ትነግራታለች። ይህ ሊሆን እንደማይችልና፣ እሷ ራሷ እንደምትወስን በመጨቃጨቅ ላይ እንዳሉ የቡና ቤቱ ባለቤት ውስጥ ሆኖ ይመለከታቸው ስለነበር ውጭ ወጥቶ ጉዳዩን ለማጣራት ከሰሎሜ ጋር ይነጋገራል። ሰሎሜም ነገሩን ካስረዳችው በኋላ ሁለቱም ብዙም ሰው የሌለበት ቦታ ቡና ቤቱ ውስጥ ገብተው እንዲቀመጡ ቦታ ይሰጣቸዋል። ሰሎሜም በመኪና አደጋ የተጎዱትንና በድህነት የተጎሳቆሉትን ሽማግሌ ምግብ አዛላቸው ከተመገቡ በኋላ በህይወት ዘመናቸው አግኝተው የማያውቁትን ብዙ ገንዘብ አሽክማ ትሸኛቸዋለች። ደራሲው እዚህ ላይ ለማመልከት የሞከረውና በትክክልም እንዳስቀመጠው አብዛኛው ህዝብና፣ በተለይም ደግሞ በትንሽ ዕውቀት ጭንቅላቱ ለብ ለብ ያለው ስለደሃና ቆሻሻ ልብስ የለበሰ ሰው ላይ ያለውን የተዛባ አመለካከት ነው። የደራሲው አገላለጽ በአገራችን ውስጥ በተለይም ኤሊት ነኝ የሚለው ጭንቅላቱ ውስጥ የተንሰራፋውን የተወላገደና፣ ለህብረተሰብ ዕድገት ጠንቅና፣ በአጠቃላይ ሲታይ ደግሞ ስለሰው ልጅ ያለንን የተዛባ አመለካከት ለማሳየት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ አንድ ቀን መላኩና ሰሎሜ በመኪና ወደ ቦሌ አቅጣጫ እየነዱ ሲሄዱ የትራፊክ መብዛት በፍጹም አላንቀሳቅስም ይላቸዋል። ሰሎሜም በመገረም መላኩን ትጠይቀው የነበረው፣ ለመሆኑ አዲስ አበባ ማለት ቦሌ ብቻ ናት ወይ ? ለመሆኑ ለምን እዚህ አካባቢ ብቻ መኪናና ሰው በአንድ ላይ እየተጋፉ ይሄዳሉ ? እያለች ትጠይቀው ነበር። በተለይም ትላልቅ የቤት መኪና ይዞ የሚነዳውን ጎልማሳ ስትመለክት ስለሰው ልጅ ደንታ የሌለው ብቻ ሳይሆን መንገዱ ሁሉ ለሱ ብቻ የተሰራ ይመስል መንገዱን ሲያስጨንቅና በሰው ላይ ለመጋለብ ስታይ በጣም ያበሳጫታል። በተለይም የመንገድ አሰራሩ በደንብ ታቅዶና ለሰው ልጅ ታስቦ ባለተሰራበትና፣ የእግረኛ መሄጃ፣ መኪና ነጂዎች ልጆች ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ተብሎ ልዩ መሄጃ መንገድ ባልተሰረባትና፣ የቢስኪሌትና የአውቶብሶች መሄጃ ልዩ መስመርና መንገድ በሌለበት ከተማ ውስጥ በሰው ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ደራሲው በደንብ በመገንዘብ በጥሩ ብዕሩ ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጣል።

ሰሎሜ በስራዋ ላይ እያለችና ከመላኩ ጋር ያላቸውን ግን ደግሞ በግልጽ ወጥቶ ያልተመነዘረውን ፍቅርና ግኑኝነታቸውን በማውጣትና በማውረድ ላይ እያሉ፣ አባቱና እናቷ፣ እንዲሁም የሰሎሜ ሁለት ወንድሞች የሚኖሩበት ከቺካጎ ከተማ ከሷ በሁለት ዐመት ከፍ የሚለው ታላቅ ወንድሟ ሶለን ላይ ሽጉጥ ተተኩሶበት ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበትና ሆስፒታልም ገብቶ በመታከም ላይ እንደሚገኝ፣ በፍጥነት ወደ ቺካጎ መምጣት እንዳለባት በስልክ ይነገራታል። ጉዞዋን ወደ አሜሪካ ከማቀናቷ በፊት ግን ከመላኩ ጋር በመገናኘት፣ እሷ የምታሳድጋቸውን የሷ አክስት ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሁለት፣ ገና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆችን መላኩ እንዲከታተላቸውና በማንኛውም ነገር እንዲረዳቸው አደራ ብላ ጉዞዋን ወደ አሜሪካ ታቃናለች። የሷ ወደ አሜሪካን መሄድና በመላኩና በሰሎሜ መሀከል ያለው መፈላለግና ውስጣዊ ፍቅር ሳይወጣ ሁለቱም እንደሚዋደዱና እንደሚፋቀሩ ስሜታቸውን ሳይገልጹ መሄዱ ልበ-ወለዱን በጉጉት እንድናነበው ይጋብዘናል። በሌላ ወገን ግን የልበ-ወለዱ ዋና መልዕክት፣ ይህ በሁለት ሰዎች ያለውን በጾታ ላይ የተመሰረተ ፍቅር ለማሳየት ሳይሆን፣ ዋና ዓላማው ሁለት በአስተሳሰብ የሚገጣጠሙ ፍቅረኞች ስለህበረተሰብአቸው ኋላ-መቅረትና አገራዊ መዝረክረክና የሰው ልጅም ኑሮ በዚህ መልክ መሄድና መታየት እንደሌለበት የግዴታ በአዲስ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ሁለገብና አጠቃላይ ለውጥ መምጣት እንዳለበት ለማመልከት ብቻ ነው።

ሶሎሜ ሁለት ታላላቅ ወንድሞች ሲኖራት፣ በተለይም የሁለት ዐመት ዕድሜ ከሚበልጣት ሶለን ከሚባለው ታላቅ ወንድሟ ጋር በጣም ይዋደዳሉ። ቤተሰቦቿ የዲቪ ዕድል አግኝተው አሜሪካን በመሄድ ኑሮአቸውን እዚያ የመሰረቱ ናቸው። የሰሎሜ አባትና እናት የሚከባበሩና ልጆቻቸውንም በስነስራዓት ያሳደጉ ሲሆኑ፣ የስሎሜ አባት የጊዜንና የገንዘብን አጠቃቀምን በደንብ የተገነዘቡና፣ ካለምክንያት የሚባክን ገንዘብና ጊዜን በስርዓት አለመጠቀም ያበሳጫቸዋል። „ገንዘብ የጊዜ ምንዛሬ ነው፤ ጊዜም ያልተመነዘረ ገንዘብ ነው“ የሚል ፍልስፍና አላቸው በማለት ደራሲው የኑሮ ፍልስፍናቸውን ያስረዳናል። ፍልስፍናቸው ከዚህ ርቆ በመሄድ በአጠቃላይ ስለ አንድ ህበረተሰብ ዕድገት ያላቸውን አመለካከት፣ ልጃቸው ለአደጋ ከመጋለጡ በፊት፣ ከልጃቸው ከሶለን ጋር ክርክር ወይም ውይይት በሚያደርጉበት ጊዜ ጣል ጣል የሚያደርጉትን አስተሳሰብ ለተመለከተ የአገራቸው ኋላ-ቀርነት የሚያስጨንቃቸው እንደሆነ ከልበ-ወለዱ መገንዘብ ይቻላል። እንደዚሁም ሶለን የአባቱን ፈለግ በመከተል ስለሰው ልጅ ያለው አመለካከት በወጣትነት ጊዜው የዶክትሬትና የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከያዙትና በዕድሜም ወደ ስድሳና ወደ ሰባ ዐመት ከሚጠጉት ጋር ሲወዳደር ልቆ የሄደ መሆኑን ደራሲው በግሩም መልክ ያሰቀምጣል። በተጨማሪም የጥቁር አሜሪካንን የጭቆናና የስቃይ ትግል ታሪክ ያነበበና የእነ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን ስራና የትግል እንቅስቃሴ ጠንቅቆ ያወቀ ስለነበር፣ አብዛኛውን ጊዜውን የሚያሳልፈው ከጥቁሮች ጋር ነው። ጥሩና ትችታዊ አመለካከት ያዳበረው ሶለን በተለይም አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች ራሳቸው ጥቁር ሆነው ጥቁር እንዳይደሉ፣ ጥቁር አሜሪካውያንን እነዚያ ጥቁሮች እያሏቸው ሲጠሩቸው በጣም ይገርመው ነበር፤ ይበሳጭም ነበር። ይህም የሚያረጋግጠው የሶለንን የስባዊነት ባህርይና በዕውቀት የዳበረ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ተማርን፣ ረቀቅን ብለው ሌላውን ወንድማቸውን የሚንቁትን፣ የዶክትሬትና የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የያዙትን ስንትና ስንት እርምጃ እንደሚበልጣቸው ነው። በተጨማሪም ህብረተሰብአዊ ባህርይንና ሰብአዊነትን ያላካተተ፣ እንዲሁም ደግሞ ትችታዊ አመለካከት የሌለውና ስልጣኔ አጋዥ ያልሆነ የዶክትሬትነትና የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚበልጥ ከስነ-ጽሁፉ መረዳት እንችላለን።

ሰሎሜም ወንድሟን ለመጠየቅ ወደ ሆስፒታሉ ከሄደችና ወንድሟን ማጽናናት ስትጀምር፣ በመሀከሉ ብልጭ ያለባት ወንድሟ የተኛበትን ሆስፒታል እኛ አገር ካለው ጋር ስታወዳድር በጣም ነው የገረማትም፤ ያዘነችውም። ሁለም በሃሳብ ላይ እያሉ መጠየቅ የጀመረችው እንደዚህ በማለት ነበር: „አንድ እንኳ እንደዚህ ዐይነት ሆስፒታል አገራችን ቢኖር ስንት ሰው ከሞት ይተርፍ ነበር ?“ እያለች ነው የህዝባችን መበደልና የአገራችንን ኋላ-ቀርነት የሚያብከነክናት። ሰለሆነም፣ ጥሩ ነገር ስታይ ይህም ነገር እኛም አገር ቢኖር ኑሮ በማለት ነው ምሬቷንና ብስጭቷን እንዲሁም ምኞቷን የምትገልጸው። ስለ ዕድገት ያላትን የልጃቸውን አገላለጽና አስተያየት ጠጋ ብለው የሚያዳምጡት አባቷ አቶ ኦላን፣ ይህ ዐይነቱ በጥሩ መልክና ቆንጆ አካባቢ የተሰራ ሆስፒታል ከሌሎች ነገሮች ጋር ተነጥለው መታየት እንደሌለባቸው ለማስረዳት ይሞክራሉ። በሳቸውም ዕምነት፣ ይህ ዐይነቱ ሆስፒታል በአጠቃላይ ሲታይ ህዝቡ ወይም መንግስት ስለሰው ልጅ ያላቸው አመለካከት ለየት ያለና፣ ባህሉም የላቀ ስለሆነ የሰው ልጅ እንደ ዕቃ የሚጣል ሳይሆን የሚከበርም መሆኑን የሚያመለክት ነው በማለት ለልጃቸው ቀስ ብለው ያስረዷታል። እሷም የሳቸውን ነገር ሙሉ በሙሉ ሳትቀበል ይህ የግዴታ ከባህል ጋር ብቻ የሚያያዝ አለመሆኑን፣ ዱባይና ሪያድ ያሉትን በንጽህናና በአያያዝም የማይተናነሱትን ሆስፒታሎች እየተጠቀሰች ከኛው ጋር በማወዳደር „ደሃ ሁልጊዜም ደሃ ነው፤ አያልፍለትም“ እያለች ትነግራቸዋለች። ድህነት ተፈጥሮአዊ አለመሆኑ ስትናገር የነበረችው ሰሎሜ እዚህ ላይ ደግሞ ብዙም ሳታስብ ድህነትን እንደ ተፈጥሮአዊ እንደሆነና፣ ከባህል ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ ለማስረዳት ትሞክራለች። አቶ ኦላን ንግግሯን በደንብ ካዳመጡ በኋላ፣ የአረቦቹ ዕደገት ከጭንቅላት ተሃድሶና ከዕውነተኛ ስልጣኔ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከዘይት ሽያጭ የተገኘና፣ አንድ ቀን ዘይቱም ሲያልቅ የዶላርም እጥረት እንደሚኖርና፣ በድሮ ሁኔታቸውና የአኗኗር ስልታቸው ሊገፉበት እንደማይችሉ በሰከነና በጠለቀ መንፈሳቸው ረጋ ባለ መልክ ልጃቸውን ያስረዷታል። በሌላ አነጋገር፣ ዋናው የስልጣኔ ምንጭ በገንዘብ መደለብና መትረፍፈፍ ሳይሆን በጭንቅላት መዳበርና፣ ዕውቀትና ስልጣኔም ከጭንቅላት የሚፈልቁ መሆናቸውን ደራሲው በሚገርም ነገር ፕላቶናዊና ሶክራትሲያዊ በሆነ መንገድ ያስተምረናል። አቶ ኦላናም በመቀጠል፣ የጃፓኑንና የኮሪያውን ስልጣኔ ከአረቦቹ ጋር በማወዳደር ንጹህ በንጽሁ በአስተሳሰብና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ብዙ የአፍሪካ አገሮች የተትረፈረፈ የጥሬ-ሀብትና፣ ጥሩ አካባቢና አየር እያላቸው ባለማወቃቸውና መሪዎችም ስግብግቦችና የደነቆሩ ስለሆኑ ህዝቡ ደህ እንዲሆን አድርገውታል በማለት ያስረዷታል።

ሰሎሜም የአባቷን ግሩም አገላለጽ ከአዳመጠችና በመደነቅ፣ እንደኛ ያለው ህዝብ ታዲያ ድህነትን ለማስወገድ ከየት መጀመር አለበት ብላ? አባቷን በጥያቄ ታፋጥጣቸዋለች። በመቀጥልም፣ በልመና መኖር ስልችቶኛል፣ እስከመቼ ነው በልመና የምንኖረው? እያለች የምሬቷን ትናግራለች። በመሀከሉ ስልክ በመወደሉ የሰሎሜ እናት፣ እንደመሰላቸት በማለት እስቲ ወደ ስልኩ ጋ ልሂድ፣ የአንድ ሺህ ዐመት ችግር በአንድ ቀን ክርክር አይፈታም በማለት ለባለቤታቸውና ለልጃቸው ይነግሯቸዋል። አቶ አላናም ፣ „ የአንድ ሺህ ማይል ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀመራል“ በማለት ቀልዳቸውን ጣል ያደርጋሉ። አቶ ኦላናም አፋቸውን ከጠራርጉ በኋላ ከየት እንጀምር ብለው ጥያቄ በማቅረብ፣ እዚያው ካለንበት ነው መነሳት ያለብን በማለት ለልጃቸው ያስረዷታል። በመቀጠልም ችግራችንን ለመቅረፍና ስልጣኔንም ለማምጣት የግዴታ ያለንበትን ሁኔታ በሚገባ ማወቅ እንደሚያስፈልግና፣ ያለፈውን ትውልድም እንደተጠያቂ ማድረግ እንደማይቻል ደራሲው እንደ አቶ ኦላን በመመስል ልቆ በሄደው አስተሳሰቡ እጅግ በሚያሰደንቅ አገላለጹ ዕድገት ከየት መጀመር እንዳለበትና፣ ምንስ መመስልና ወዴትስ መጓዝ እንዳለበት ያስተምረናል። ስለዚህም ይላል ደራሲው፣ በአቶ ኦላና በመመሰልና ኋላ-ቀርነትና የጎታች ባህልን የዕድገት ጠንቅነት እያመለከተ፣ „ በየትኛውም ሥልጣኔ ውስጥ ፈር ቀዳጅና ፋና ወጊ ተብለው ለውጥ ያመጡ ሰዎች መጀመሪያ ወንጀለኛ፣ ከዚያም አሳሳች ተብለው መፈረጃቸው የተለመደ ነው። በእርግጥም እነዚህ ጥቂት ብርቅዬ ከዋክብት ከህብረተሰቡ በሰላሳና በአርባ ዐመት ቀድመው ወደፊት የሄዱ ስለሆነ ከሰው አይገጥሙም፤ ሰው አንድም ባለበት ስለሚረግጥ አንድም የኋልዮሽ እንጽርት ጨዋታ ላይ ስለሚባትል እነሱን ይፈራቸዋል፤ ስለዚህም ይጠላቸዋል። ምንም እንኳ እንደ ዕውነት ፀርና አሳች መሲህ ቢታዩም በሚቀጥለው ትውልድ ግን ሁሌም ብሩህ ከዋክብት ተብለው ይሞገሳሉ፤ የመታሰቢያ ሐውልትም ይሰራላቸዋል።“ በማለት አቶ ኦላን ከልጃቸው ጋር ያደረጉትን የሃሳብ መለዋወጥ ይነግረናል። ይህ አገላለጹ በሶፊስቶች በውሸት ተወንጅሎ መርዝ እንዲጠጣና እንዲሞት የተፈረደበት ሶክራትስን፣ ወደ እስር ቤት የተወረወረውን ጋሊሌዮንና፣ እንዲቃጠል የተደረገውን ታላቁን የሬናሳንስ ምሁር ጊዮርዳኖ ብሮኖን ሁኔታ ያመለክተናል። ሁልጊዜም ለዕውነት የሚታገል በመጀመሪያ አሳሳቸ በመባል የውሸት ወሬ እንደሚነዛበትና እንዲጠላ የሚደረገውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ደራሲው ያስረዳናል። ስለዚህም ይላል ደራሲው፣ የስልጣኔ ፈር ወዳጆች ጥቂቶች ሲሆኑ የሚቀጥለው ትውልድ ተግባር ያንን በመመርኮዝ፣ በማስፋፋትና በማዳበር ዕምርታ በመሰጠት ህብረተሰብአዊ ለውጥ መምጣት እንደሚችል ነው። ለዕውነተኛ ስልጣኔ የሚታገል በምንም ዐይነት በስም አጥፊዎችና ሰውን በሀሰት በሚከሱ መደናገጥና የስልጣኔውን መንገድ ለቆ መውጣት እንደሌለበት ደራሲው ያመለክታል። ዕውነት ለጊዜው ብትዳፈንም አንድ ቀን ግን ባሸናፊነት በመውጣት ውሽት ነዢዎችን እርቃናቸውን እንዲቀሩ ማድረጓ በታሪክ የተረጋገረጠ ነው። ዛሬ በቴክኖሎጂ የተራቀቁና ዓለምን የሚቆጣጠሩ አብዛኛዎቹ የምዕራብ አውሮፓ የካፒታሊስት አገሮች እዚህ ዐይነቱ የተወሳሰበና የአደገ ሁኔታ ላይ ሊደርሱ የቻሉት የአሰተሳሰብ ለውጥ በማድረጋቸው ሲሆን፣ የጭንቅላት ተሃድሶ ለማግኘትና የተፈጥሮን ህግ ለመረዳትና የነበሩበትን የጨለማ ሁኔታ ለመለወጥ ሶስት መንፈስን የሚያድስ መንገድ እንደተጓዙ ደራሲው ቁልጭ ባለ መልክ ያስተምረናል። በእሱም አገላለጽ፣ ሬናሳንስ ወይም የግሪኮችን ዕውቀት መልሶ ማግኘትና በሱ ላይ በመመርኮዝ የስልጣኔውን ፈር መቅደድ፣ ሬፎርሜሽን ወይም በሃይማኖት አካባቢ የተደረገው የአስተሳሰብ ለውጥና ይህም ለካፒታሊዝም መነሳትና ማደግ አንደኛው መንገድ መሆኑና፣ ከዚህም ባሻገር ኢንላየትሜንንት በመባል የሚታወቀው ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ፣ እነዚህ ሶስቱ ደረጃ በደረጃ ለአውሮፓ ህዝብ ዕድገት መንገዱን ያሳዩት እንደሆኑ ደራሲው በደንብ ያስቀምጣል። ከዚህ ስንነሳ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶች የገበያ ኢኮኖሚ አማራጭ የሌለው የዕድገት ትክክለኛው መሳሪያ ነው የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት መሆኑን ዶ/ር ምሀረት በግሩም ብዕሩ ሳይንሳዊ በሆነ አቀራረብ ያስተምረናል።

ሰሎሜ ወንድሟን ለማስታመምና የጤንነቱን ሁኔታ ለመከታተል ወደ አሜሪካ ተመልሳ ከሄደች በኋላ እዚያው ለረጅም ጊዜ ትቆያለች። በመጀመሪዎች ሳምንታትና ወር በየጊዜው ኢ-ሜይልም ሆነ ስልክ ከመላኩ ጋር ይጻጻፉና ይደዋወሉ ነበር። መላኩም ስንክሳር ልምትባለው የሰሎሜ ጓደኛ ወደ አሜሪካ ስትሄድ ለሰሎሜ ቆሎና ደብዳቤም ይልክላታል። ይሁንና ግን ስንክሳር የደብዳቤውን ምስጢር ለማወቅ ስትል ቺካጎ ከደረሰች በኋላ ለራሷ በማስቀረት እንደጠፋባት ለመላኩ ትነግረዋለች። በአንድ በኩል ሰሎሜ አንድም በወንድሟ በሞትና በሽረት ላይ መገኝትና በደረሰበትም ከፍተኛ አደጋ በሀዘን ላይ በመውደቋ፣ በሌላ ወገን ደግሞ እንደ ቤተሰብ እዚያው ቤታቸው ውስጥ ጉድ ጉድ ከሚለው ክብሮም የሚባለው የኩላሊት ሀኪሙ ጋር ግልጽ የሌለው ግኑኝነት ይጀምራሉ። አልፎ አልፎም ለብቻቸው እየተገናኙ ይገባበዛሉ። እንደገና ቺካጎ ከተማ ውስጥ ለረጅም ወራት እንድትኖር የተገደደችው ሰሎሜ በመላኩና በክብሮም መሀከል መዋለል ትጀምራለች። በአንድ በኩል መላኩን ከልቧ ትወደዋለች፤ በሌላ ወገን ደግሞ በጠባዩ ቀለስለስ የሚለውን ክብሮምንም ላለማስቀየም ትሞክራለች። መላኩ ሰሎሜ ወደ ቺካጎ ከሄደችና እዚያም ለረጅም ጊዜያት እንድትኖር ከተገደደች ወዲህ በአስተሳሰቡ ብዙም ተለውጧል። በሃሳብ ከመዳበሩና ከመደንደኑ የተነሳ የመጀመሪያ ፍቅረኛው ልባዊ ፍቅር ማሳየት ስላልቻለ ወደ ካናዳ ጥላው ከሄደች በኋላ ግራ የተጋባው መላኩ ራሱን መልሶ መላልሶ የሚጠይቀው የመጀመሪያው ጓደኛው ለምን ጥላው እንደሄደች ነው። እሷንም በክርክክርና በሙጉት ለማሳመን ያደረገው ሙከራ ሁሉ የባሰውን እንዳራቃትና፣ ሌላ ሰው እንድትወድ እንደተገደደች ደራሲው ይነግረናል። ይህ በእንደዚህ እያለና በመላኩና በሰሎሜ መሀከል የነበረው የጠበቀ ግኑኝነት ወደ መላላቱ በማምራቱ፣ የቤተሰቦቹና በተለይም የአባቱ ሁኔታ የሚከነክነው መላኩ ከስራ ፈቃድ በመውሰድ ለመፈለግ ሲል ወደ መቂ ከተማ ያመራል። ወደ መቂ ከሄደ በኋላ አንድ ሆቴል ቤት ውስጥ ካረፈ በኋላ አንደ ሆቴል ቤቱ ውስጥ በሚሰሩ ሴት አማካይነት ሁኔታውን ካጣራ በኋላ አብረው ያፈላልጉታል። የመጨረሻ መጨረሻም አክስቱንና የእህቱን ልጆች ሁሉ ያገኛቸዋል። የሚኖሩበትንም ሁኔታ ሲያይ በጣም ያዝናል። እንደ አጋጣሚ ከቤተሰቦቹ ጋር የተገናኘው የበዓል ዕለት ስለነበር አንዱን ልጅ ወደ ገበያ ይዞ በመሄድ በግ ገዝቶ አምጥቶና አሳርዶ ያሽመነምናቸዋል። በረሃብና በችግር ሲሰቃዩ የኖሩትን ቤተሰቦቹን ደስታ በደስታ ያደርጋቸዋል። መላኩም ቀኑ ከመሸ በኋላ እዚያው ቤት ሲያድር ቁንጫና ትኋን በሰውነቱ ላይ እየደነሱበትና ደሙን እየመጠጡበት እንቅልፍ ያሳጡታል። አስተዋዩና አርቆ አሳቢው መላኩ በዘመዶቹ ላይ የሚደረሰውን፣ ከሃሳብ ድህነት የመነጨ ድህነትና ጉስቁልና እንዲሁም እጅግ አስቀያሚ ኑሮ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ጋር በማገናኘት ይከነክነዋል። ጥቂት ቀናት እዚያ ከቆየ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ይወስናል። በመጀመሪያ ግን መኪናውን ወዳቆመበት ወደ ሆቴል ቤቱ ጋ ከአክስቱ ትልቋ ልጃቸው ከመዐዛ ጋር ተያይዘው ይሄዳሉ። ከመሄዱ በፊት እዚያ ተቀምጠው አንዳንድ ነገር አዘው በመጠጣት ላይ እያሉ መዐዛ አንድም በደስታ በመዋጧ፣ በሌላ ወገን ደግሞ መላኩ እስኪመጣ ድረስ እሷና ልጆቿ እንዲሁም እናቷ በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀው እንደነበርና፣ ልጆቿንም መመገብ ባለመቻሉ የመጨረሻ መጨረሻ የአይጥ መርዝ ጠጥታ ለመሞት መርዙን ገዝታ በመወሰንና ባለመወሰን ላይ እንዳለች መላኩ እንደደረሰላቸው ስቅቅ ብላ ታለቅሳለች። ቀደም ብሎ ግን መላኩ ለአክስቱም ሆነ ለመዐዛ ልጆች ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ታሪኳን ከመናገሯም በፊት አምስት ሺህ ብር ያህል ይሰጣታል። እሱን ከሸኘች በኋላ ወደ ቤት በመመለስ ከእንግዲህ ወዲያ መላኩን በማስጨነቅ መኖር እንደሌለባቸው በመረዳት ገንዘቡን ሁሉ በመሰብስብ ንግድ ለመጀመር ቆርጣ ትነሳለች፤ በዕቅዷም በመግፋት ስኬታማ ትሆናልች። በየጊዜው በዕርዳታ መኖር እንደሌለባትና በትንሽም ገንዘብ ራሷን መለወጥ እንዳለባት በመረዳት የማሰብ ኃይል እንዳላት ታረጋግጣለች። መላኩም በአንድ በኩል ዘመዶቹን ለመርዳት በመቻሉና ከድህነት የሚወጡበትንም ሁኔታ በማመቻቱ ደስ ሲለው፣ በሌላ ወገን ደግሞ እናቱ እሱን አክስቱ ጋ ጥላ ብትሄድ ኖሮ ሊደርስበት የሚችለውን ሁኔታ ማውጣትና ማውረድን ተያያዘው። ብዙ አሰበ። ምናልባትም የኤይድስ ሰለባ ሆኖ ዕድሜው በለጋ ወጣትነቱ ይቀጭ እንደነበር ቁልጭ ብሎ ታያው። ካሊያም ሹፌር በመሆንና ትልቅ መኪና በመንዳትና ቤተሰብ በመመስረት ብዙ ልጆች ወልዶ አስቸጋሪ ኑሮም እንደሚኖር ታየው። እንድ አጋጣሚ የዶ/ር ሳራ እናት ባያገኙትና ባያስተምሩት ኖሮ ይህንን ያህል ደረጃ ላይ መድረስ እንደማይችል መገንዘብ ቻለ። ይህም በመሆኑና ጥሩ መንፈስም ስላለውና ጭንቅላቱም በፍልስፍና የተገነባ ስለሆነ ቤተሰቦችን ሳይረሳና ሳይንቅ ለመፈለግ መሄዱና እነሱንም መርዳት መቻሉ እያንዳንዱ የተማረ እንደሱ ማሰብ ቢችል የቱን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ታየው። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ የደራሲውን የላቀ የጭንቅላት መዳበርና ለአገርና ለህዝብ ማሰብ የሚያመለክት ነው። በዚህ መልክ እያንዳንዱ ዕውቀቱን ቢያገናኝና የማሰብ ኃይሉንም ካዳበረና ለወገኑ የሚያስብ ከሆነ ለውጥ በውጭ ዕርዳታ ሳይሆን ከውስጥ በራስ የማሰብ ኃይል ብቻ ሊመጣ እንደሚችል የኖይሮ-ባዮሎጂው ምሁርና ሃኪም፣ እንዲሁም በታሪክና በፍልስፍና ጭንቅላቱ የዳበረው ታላቅ ምሁር ድ/ር ምሀረት ከበደ ስለድህነት ዋናው ምክንያትና እንዴትም መፈታትና በአራት እግር መቆም እንደሚቻል በሚገባ ያስተምረናል።

የመላኩና የሰሎሜ ግኑኝነት ያልተቋጨ ፍቅር በነበረበት ሁኒታ ውስጥና፣ በመሀከላቸው የነበረውን መፈላለግ ለማፍረስ ተንኮል የምትሸርበው ስንክሳር አመቺ ጊዜን በምትጠባበቅበት ወቅት የስሎሜን ወንድምም ሶለን ከአደጋው ለመትረፍ ባለመቻሉ ከዚህ ዓለም በሞት ይለያል። ይህ በእንደዚህ እንዳለ እንደ እናት ሆነው ያሳደጓት ልጅ ዶ/ር ሳራ ከባሏና ከሶስት ልጆቿ ጋር የባሏን ቤተሰቦች ለመጠየቅ ለእረፍት ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ። ዶ/ር ሳራም በጣም ስለደከማት ያንኑ ዕለት የባለቤቷ ቤተሰቦች ጋር መሄድና ማረፍ ባለመፈለጓ ለጊዜው ሆቴል ቤት ውስጥ አረፉ። የዶ/ር ሳራ ባል በራሱ ስሜት የሚነዳ ስለነበር ለባለቤቱና ለልጆቹ ደንታ ሳይሰጥ አብዛኛውን ጊዜውን ከድሮ ጓደኞቹ ጋር ነው የሚያሳልፈው። በሁለቱም መሀከል የነበረው ፍቅር የሻከረ ስለነበር ደራሲው እንደሚለን የመባለጊያ የወረቀት ፈቃድ የሰጠቺው ይመስል የትም እያደረ ነው የሚመጣው። ስለሆነም የህሊና ሳይንስ ሃኪም የሆነችው ዶ/ር ሳራ አብዛኛውን ጊዜዋን ከልጆቿና ከመላኩ ጋር ነው የምታስልፈው። አንደኛው ልጃቸውም ኦቲዝም(Autism) በሚባል የአዕምሮ መሰናክል የሚሰቃይ ስለሆነና፣ ከፍተኛ ክትትልም ስለሚያስፈልገው ዶ/ር ሳራ ከልጇ በፍጹም አትለይም። ጊዜዋን በተለይም ከአንድ ልጇ ጋር የምታሳልፈው ዶ/ር ሳራ ከመላኩም ሆነ ከመላኩ ጓደኛ ማርቆስ ጋር እየተዘዋወሩ በከተማ ውስጥም የተሰሩትን አዳዲስ ህንፃዎችና የአማኑኤልንም ሆስፒታል መጎብኘት ደስ ይላታል። በተለይም የአማኑኤልን ሆስፒታል ስትጎበኝ የምታነፃፅረው አሜሪካን ካሉ ካማሩና በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ከመቶዎች በላይ የሚገኙበት ሃኪሞችና ነርሶች እንዲሁም ድሬሰሮች ጋር ነው። በተለይም የአማኑኤል ሆስፒታል መርካቶ ውስጥ መሆኑ ነገሩ ይከነክናታል። እንደዚህ ዐይነት ሆስፒታል እንደዚህ ዐይነት ቦታ መሰራት ያለበት ሳይሆን ወጣ ያለና፣ አካባቢውም ሆነ ግቢው በአማሩ ዛፎችና አበባዎች፣ እንዲሁም የሰውን ጭንቅላት በሚያድሱ መናፈሻዎችና መቀመጫዎች ማማርና መሰራት የነበረበት እንደነበር ለማስረዳት ትሞክራለች። ስለሆነም ሃሳቧ ስለዚህ ሁኔታና ስለጭንቅላት ህመምና በተለይም ደግሞ ስለ ኦቲዝም ምንነት በዩኒቨርስቲው የነርብ ህክምናና የህፃናት ክፍልና ሆስፒታል ውስጥ ሰሚናር ለመስጠት አቀደች። በቴሌቪዝንም ተጠይቃ ስለኦቲዝም ሰፊ ማብራሪያ ሰጠች። ቃለ-መጠይቁንና ገለጻዋን በተሌቪዝን የተመለከተው ባላቤቷ ይዘዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጀመረ። ባለቤቷ ወያኔን የሚጣላ በመሆኑና እሷም በአባቷ ትግሬ ስለሆነች የባሰውኑ ወያኔን ሆንሽ አይደለም ብሎ ጮኸባት። ምንተስኖት አሜሪካን አገር በኢንተርናሽናል ዴቬሎፕሜንት የሰለጠነ ቢሆንም ይህንን ያህልም የዳበረ ጭንቅላት የለውም። በራሱ ስሜት የሚመራና አርቆ የማሰብ ኃይሉ ውስን ነው። ስለሆነም የነገሮችን ሄደት ሳያጤን ቶሎ ብሎ ወደ ጠብ ያመራል። ከሱ ዕምነት ውጭ ያለውን እንደ ጴንጤ ቆንጤ የመሰለውን ሃይማኖት ፈረንጆች ሆን ብለው የሰውን ጭንቅላት ለማደንዘዝና የጥቁርንም ህዝብ ተገዢ ለማደረግ የፈጠሩት ሃይማኖት ነው ብሎ ስለሚያምን ከመላኩ ጋር፣ መላኩ የጴንጤ ቆንጤን መዝሙር ሲያዳምጥ ሲሰማ በመብገን ግጭት ውስጥ ሊገባ ቻለ። መላኩም ረጋ ባለ መልክ መዝሙሩ የጴንጤ ቆንጤ በመሆኑ ወይስ ጠቡ ከሃይማኖት ጋር ነው? ብሎ በመጠየቅ፣ የኦርቶዶክስም ሃይማኖት እንደዚሁ የራሱ መዝሙር እንዳለውና በአጠቃላይ ሲታይ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በታሪክ ሂደት ውስጥ ብቅ ያለና የጥንት አባቶቻችንም ተገደው የተቀበሉትና እንደ ዕምነትም የወሰዱት እንደሆነ በጥሞና ያስረዳዋል። የመላኩን የበሰለና ረጋ ያለ ክርክር ያዳመጠው ምንተስኖትም በመገረም ወደ ጠብ ሳያመራ በውይይት ብቻ በመሀከላቸው ያለውን ልዩነት ለማብረድ እንደቻሉ ደራሲው ግሩም በሆነ መልክ ያስረዳዋል።

ይህ በእንደዚህ እንዳለ መላኩ ወደ ዱባይ ለስብሰባ ከመሄዱ በፊት ከሳራና ከቤተሰቦቿ ጋር በየጊዜው እየተገናኙ ከተማውን ያሳያታል። በተለይም በአገራችን ውስጥ ያለውን ጭንቅላት ላይ የሚከሰት በሽታ ሁኔታ ለማከም አንድ ማዕከል ለማቋቋም እንዳሰበች ለመላኩ ታስረዳዋለች። እንደ ኦቲዝም የመሳሰሉት የጭንቅላት መዛባቶች ቢኖሩም ችግሩ በደንብ የታወቀና በዚህም መስክ ስፔሽያላይዝ ያደረገ እንደሌለና፣ ህክምናም እንደማይሰጥ ደርሳበታለች። በመሆኑም ዕቅዷን በዝርዝር ለመላኩ ትነግረዋለች። መላኩም የሷን ቀና አስተሳሰብ በደንብ ካዳመጠ በኋላ ስለ ኦቲዝም ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድታስረዳው ይጠይቃታል። ዶ/ር ሳራም የመላኩን ጥያቄ ካዳመጠች በኋላ በጥሞና ጥያቄውን በሚከተለው መልክ ታስረዳዋለች። „ ኦቲዝም አንድ በሽታ ነው ማለት አይቻልም። በአጠቃላይ ተመሳሳይ መግለጫ ያላቸው ከአዕምሮ ዕድገት መዛባት ጋር የተያያዙ ችግሮች የጋራ ስም ነው። ኦቲዝም የሚለው ስም `አውቶ´ ማለትም የአንድ ሰው እኔነት (ራስ ) ከሚለው ቃል የወጣ ሲሆን፣ ኦቲዝም የተባለበት ምክንያት ይህ ችግር ያጋጠማቸው ሕፃናት አብዛኛው ዓለማቸው በራሳቸው ውስጥ ስለሚሽከረከር ነው። አሁን አየህ አዕምሮው በትክክል የሚሠራ ሰው ውስጣዊውንና ውጫዊውን ዓለም አመጣጥኖ ነው የሚኖረው። ኦቲዝም ያለባቸው ሕፃናት ግን ልክ ሳጥን ውስጥ እንዳለ ሰው ብዙውን ጊዜ የሚያሳልፉት በራሳቸው ጭንቅላት ውስጥ ነው። ከዚህም የተነሳ ለሰው ግራ የሚያጋባና ለመረዳት አስቸጋሪ የባህርይ፣ የቋንቋና የማህበራዊ ግኑኝነት ጉድለቶች ይታዩባቸዋል። ደግሞም በአብዛኞቹ ላይ የአዕምሮ ዝግመት ይከሰታል። እንደባቢዬ(ልጇ) በጣም የከፋ የአዕምሮ ዝግመት ያለባቸው ከሆነ፣ ህመሙን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል። ሁሉም ልጆች በሁሉም አቅጣጫ በተመሳሳይ ደረጃ ጉድለት ስለማይኖራቸው፣ ኦቲዝም ያለበት እያንዳንዱ ልጅ አንድ ሊሆን አይችልም።“ በማለት በሚገባ ታስረዳዋላች። የሷን ልጅም አድራጎትና ከአንድ አሻንጉሊት ጋር ብቻ መጫወት የተመለከተው መላኩ ለምን ከአንድ ነገር ጋር ብቻ አንደሚጫወት፣ ለምን ሌላም ነገር እንደማያሳኘው አጥብቆ ይጠይቃታል። የሷም መልስ፣ በአጠቃላይ ሲታይ ኦቲዝም ያለባቸው ህፃናት በራሳቸው ዓለም ወስጥ ስለሚኖሩ ለውጥ እንደማይፈልጉና፣ ለየት ያለ ነገር ሁሉ እንደሚረብሻቸው በጥሞና ታስረዳዋለች። ለምሳሌ ብርሃንና ለየት ያለ ድምጽ ይረብሻቸዋል በማለት ኦቲዝም ያለባቸው ህጻናትን ችግር ነገረችው። በመቀጠልም ዶ/ር ሳራ ስለ ኦቲዝም ምንንነትና በሚያድጉና በያዛቸው ህፃናት ላይ ያለውን ዘለዓለማዊ ጠንቅነትና፣ ራስን ችሎ አለመኖር ያደረገለችነትን ገለጻ ካዳመጠ በኋላ ወደ ቤቱ መኪናውን እየነዳ ሲሄድ የህብረተሰቡ ኋላ-ቀርነትና በምድር ላይ የሚታየው መዝረክረክ የሚቆጨውና ግራ የገባው መላኩ፣ በህፃናትም ላይ የሚታየው ኦቲዝም በህብረተሰቡ ላይ እንደሚታይ መላምት ነገር ታየው። የህብረተሰቡን በስነስራዓት አለመደራጀትና የከተማውን ዕቅድ-የለሽ አሰራርና ቆሻሻነት አጥብቆ የተመለከተውና ሁሌም የሚቆጨው መላኩ ዶ/ር ሳራ ያስረዳቸው ሁሉ ፊቱ ላይ በመደቀን፣ በኦቲዝም የሚሰቃዩና ዘለዓለማዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት አንድን ወደ ኋላ የሚጎተት ህብረተሰብ መግላጫ ምላ ምት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገነዘበ። አንድ ጭንቅላቱ በደንብ ያልዳበረ፣ ሎጂካዊ አስተሳሰብ የሌለውና በተወሳሰበ መልክም ማሰብ የማይችል ሰውና ህብረተሰብ ልክ ኦቲዝም እንደያዘው ህፃን ነው ብሎ ገመተ። ስለሆነም አንድ ህብረተሰብም ሆነ ግለሰብ በበቂው በሰለጠኑና ፍልስፋናዊ አመለካከት ባላቸው አዋቂዎች ካልተደገፈና ቴራፒም ካላገኘ ዘለዓለሙን ደሃና ተመጽዋች ሆኖ እንደሚኖር ተሰማው። መላኩም የአገራችንና የሌሎች የአፍሪካ አገሮችን ችግር ከኦቲዝም ጋር በማመሳሰል እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል። „በእርግጥ በአፍሪካውያን ድምር አስተሳሰብም ላይ ኦቲዝም ያልተለየ ዝብርቅርቅ ያለ ዕድገትና የአስተሳሰብ መዛባት ያለ መሆኑ አይካድም። አኗኗራችንም የኦቲዝም አዕምሮ ከሚፈጥረው አኗኗር ብዙም ርቆ አልታየም። በእርግጥ ኦቲዝም ያለበት ልጅ ችግሩን ማወቅም ማመንም እንደማይችል፣ የኛም ማህበረሰብ ለዚህ ከኦቲዝም እጅግ ለማይለየው የአስተሳሰባችን በሽታ የነቃ አይመስልም።የህዝብ አስተሳሰብና አመለካከት በትክክል ካልዳበረና ካልተቃኘ ማህበራዊ ኦቲዝም ሊከሰት እንደሚችል ገመተ„፤ በማለት የኖይሮ ባይሎጂ አዋቂና የፍልስፍና ተመራማሪው ምሁር ዶ/ር ምህረት ከበደ በመላኩ በመመሰል የህብረተሰባችንን ውስን የማሰብ ኃይልና፣ ችግሩንም ለመቅረፍና ውበትና መልክ ለመስጠት አለመቻል በሚገባ መልክ ከኦቲዝም ዐይነቱ የአዕምሮ መዛባት ጋር ሊመሳሰል እንደሚችል ያስተምረናል። ይህ የአዕምሮ መዛባትና ራስን ለማወቅ አለመቻል በተማረውም ሆነ ባልተማረው፣ እንዲሁም ስልጣንን በጨበጡና ባልጨበጡ መሀከል ያለ አጠቃላይ ህብረተሰብአዊ ክስተት መሆኑን ደራሲው በሚገባ ያብራራል። መላኩም ስለኦቲዝም ምርምርና መፍትሄም ለማግኘት የሚደረገው ርብርቦሽ በብዙ ውስብስብ ችግሮች የሚሰቃየው ህብረተሰባችንም እንደዚሁ እንደ ኦቲዝም ሰፊ ጥናት ማካሄድ የሚችሉና የህብረተሰብም ዕድገት ምን መምሰል እንዳለበት ምርምር ባደረጉና በሚያደርጉ የሰለጠኑ ምሁራን መመርመርና መፍትሄ ማግኘት እንዳለበትና፣ ይህም እንደሞዴል እንደሚያገልገል አሰበ።

መላኩም ለሰሚናር ወደ ተባበሩት ኤምሬትስ በመሄድ እዚያ በቆየበት ጥቂት ቀናት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዕድገትና ንጽህና ይመለከታል። ይሁንና የነሱ ዕድገት ከዘይት ሀብት ጋር የተያያዘ ቢሆንም ገንዘባቸውን በስነ-ስራዓት ስለሚጠቀሙበት ከምዕራቡ ቴክኖሎጂን በመግዛት ዕድገትን ሊቀዳጁና ለአገሮቻቸውም ውብትን ለመስጠት እንደበቁ መላኩ በሚገባ ይመለከታል። መላኩ ይህንን ሁሉ ከተመለከተና፣ የማሰብ ኃይላቸውም ወደፊት ቀስ በቀስ በመለወጥ ከአውሮፓ አገሮች ጋር በጊዜ ሊደረሱ እንደሚችል በማውጠንጠን የሌሎችን የአፍሪካን አገሮችንና የኛን ህብረተሰብ ችግር ግራ መጋባት በዚህ መልክ ይገልጸዋል። „ የሥልጣኔ ትልቁ መለኪያ ገንዘብ ሳይሆን ለሰው ልጅ ያለን ክብርና እውነተኛ ሰብአዊነት ነው። አፍሪካውያን ግን ገና የራሳችንንም ህዝብ ያላከበርን፣ ዓለማችን ኪሳችን፣ መለኪያችን ድሎታችን የሆንን ስለሆነ፣ ብዙ መንገድ መሄድ ሳይኖርብን አይቀርም። መሪዎቻችንም የኛው ውጤት ስለሆኑ ምርጫውን አሸንፈው እስከ ቤተ መንግስት ቢደርሱም ራሳቸውን ማሸነፍ ሳይችሉ በሌላ ይተካሉ። ከራሳቸው በላይ ህዝባቸውን፣ ከምቾታቸውም በላይ መጭውን ትውልድ ማስበለጥ እስኪችኩ ያለወታደር አደባባይ መውጣት የማይችሉ እንደባነኑ የተኙ፣ እንደ ተጆሩ የመስከኑ ነገሥታት ሆነው ይቀራሉ„። በማለት የአፍሪካውያን መሬዎችን አስተሳሰብ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
መላኩም ዱባይ ሆኖ ተንኮለኛዋ ስንክሳር ከደወለችለትና፣ ሰሎሜ ከክብሮም ጋር ያላትን ወደ ዕውነተኛ ፍቅርና ግኑኝነት ያልተመነዘረ የውሸት ወሬ ከነገረችው ጀምሮ ህልሙ ወደ ቅዠትነት ተለውጧል። ይህ በእንደዚህ እንዳለና አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ እንደገና መቂ ያሉትን ቤተሰቦቹን ለማየት ወደዚያው ከቀርብ ጓደኛው ማርቆስና ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አንድ ፈረንጆች ባቋቋሙት የፌስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ገብታ መስራት የጀመረችው የሶለን ጓደኛ ከነበረችው ከሶፊያ ጋር ሆነው ወደዚያ ያመራሉ። መቂ ከደረሱና ጥቂት ቀናት በቆዩበት ጊዜያት ውስጥ በመላኩ ርዳታ የአክስቱ ልጅ መዐዛና ቤተሰቦቿ የቱን ያህል ለውጥ እንዳመጡ ይገነዘባል። መላኩም ሆነ ማርቆስ በመዐዛ አርቆ አሳቢነትና ታታሪነት፣ እንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ንግድ ጀምራ መሳካቱንና ሌሎች ሰዎችንም ቀጥራ ማሰራት በመቻሏ በብልሀነቷ ይደነቃል።

መላኩ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ወደ አሜሪካን አገር ስልጠና ከመሄዱ በፊት የአባቱ ነገር እረፍት አልሰጠው ስላለ ወደ አፋር ለመሄድና ለመፈለግ ጉዞውን ይጀምራል።፡ ከአንድ ሹፌር ጋር በመሆን ወደ አፋር ያመራል። ደብረዘይት ደርሰው ምሳ ከበላሉ በኋላ ጉዞአቸውን በመቀጠል ወደ አፋር ከመድረሳቸው በፊት አዋሽ ወርደው ፓርኩን ያያሉ፤ አዋሽም ለማደር ይወስናሉ። ከአዋሽ ስባት ይልቅ፣ አዋሽ አርባ ለማደርና ትንሽም ለመዝናናት ሰለመረጡ ወደዚያ ሲነዱ አንድ በጨአት የመረቀ ሊፍት ጠይቆአቸው ይወስዱታል። በመንዳት ላይ እያሉ ሰውየው ዐይኖችቹ በጨአት መቃም የተመረዙና የሚቆጣም ፊት ያለው ስለሚያስመስለው መላኩ ሊጠይቀው ፈልጎ ነገሩን ሳብ ያደርጋል። ይህንን ሲመለከትና በአካባቢው ዝም ብሎ የሚንገላወተውን ሰው ሲመለከት ካለመስራት ሊመጣ የሚችለውን የጭንቅላት መቦዝና አጠቃላይ ስንፍና ማውጣት ማወረድ ይጀምራል። ጨአትም በህሊና ላይ ያለውን ከፍተኛ አሉታዊ ነገር ማሰላሰል ይጀምራል። በተከታታይ ጫት የሚቅም ሰው በውስጡ ባሉ ካቲኖንና ካቲኖል በሚባሉ ኬሚካሎች ጭንቅላቱ ስለሚመረዙና ሱሰኛም ስለሚሆን ቃሚው ጨአት ካላገኘ በስተቀር በፍጹም የማሰብ ኃይሉ እንደሚዳክምና ለስራ ያለውም ፍላጎት በጣም እንደሚቀዘቅዝ ይረዳል። በአዋሽ ያየውንና የተገነዘበውን ከጠቅላላው ከአገሪቱ ሁኔታ ጋር ያገናዝባል። አንዳንድ ቡና ቤቶችም ወደ ጨአት መቃሚያነት የተለወጡበትንና፣ ሴቱም ሆነ ወንዱ የጨአት ሰለባ በመሆን ከፍተኛ የህሊና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ይረዳል። የደረሰበትም ድምደማ ይህ ጉዳይ ታስቦበት ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትና መከልከልም እንዳለበት ማውጣት ማውረድ ይጀምራል። በዚህ መልክ የአገሪቱ ችግሮች የተወሳሰቡና ልዩ ልዩ ገጾች ሲኖራቸው፣ ይህም በነቃና ሀብረተሰብአዊ ኃላፊነት በሚሰማው መንግስት መፈታት እንደሚችልና፣ እንደዚህ ዐይነቱ ትንሹንም ሆነ ትልቁን፣ ሴቱንም ሆነ ወንዱን ሰለባና ቁራኛ ያደረገ ዕፅ በህግ ካልተከለከለና ህብረተሰብአዊ መፍትሄ ካልተገኘለት የአገሪቱና የመጪው ትውልድ ዕጣ ምን እንደሚሆን ታየው። ካረፈበት ሆቴል ወጣ ብሎ ትንሽ ለመዝናናት ሲል በአካባቢው የቆመውን የትላልቅ መኪና ጉድ ይመለከታል። እነዚህ የኤይድስ በሽታ ምንጮች መሆናቸውንና፣ በዚህ መልክ ስንት ወጣት ሴቶች ህይወታቸው እንደተበከለና እንደተበላሸ ያወጣል ያወርዳል። በነጋታውም ጉዞአቸውን ወደ አፋር በመቀጠል ሲሄዱ አንዱ የአፋር መንገደኛ ሊፍት ሲጠይቃቸው ሹፌሩ አለመስማማተቻውን ይገጻልሉ። ምክንያቱም በዚያ ያለ ሰው ዝም ብሎ መኪና ሴሄድ ሊፍት የሚጠይቅና የሚሄድበትን ስለማያወቅ ዝም ብሎ የሚሳፈር ነው ብለው ሹፌሩ አለመስማማታቸውን ይነግሩታል። አንዳንዱም ሊፍት ከተሰጠው በኋላ የሚሄድብትን ስለማያውቅ ውረድ በሚባልበት ጊዜ ጠብ እንደሚፈጥር ሹፌሩ ያጋጠማቸውን ችግርና የቀሰሙትን ልምድ ለመላኩ ይነግሩታል። መላኩም በሹፌሩ ሃሳብ በመስማማት መንዳታቸውን ይገፉበታል። ጎዞአቸውንም በመቀጠልም የመኪናውን ጋጋታና የመንገዱን መበላሸት ይመለከታል። መንገዶቹ በቅርብ ጊዜ የተሰሩም ቢሆንም፣ ከመኪናዎች ክብደት ጋር እየተመጣጠኑ ባለመሰራታቸው ወዲያውኑ በመበላሸት ለመንዳት የሚያሰችግሩና ለአደጋም የሚያጋልጡ ሆነው ያያቸዋል።

መላኩ ከሹፌሩ ጋር ሆኖ ጉዘውን በመቀጠል በህይወቱ ዘመን ያላየውን በዕቅድ ያልተሰሩና ዝም ብለው ብቻ መንገድ ላይ ቁጥጥ ያሉትን ቤቶች ይመለከታል። ሰውም ሆነ ከተማዎች የሰውነትና የከተማነት ዕድል ሳያገኙ በዚያው ይሞታሉም፤ ያረጃሉም። ይህ ሁኔታ የጠቅላላው የአገራችንን ሁኔታና፣ እንደ ባህል የተወሰደወን ኋላ የቀረ የቤት አሰራረና የአኗኗ ስልት የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈና መፍትሄ ሊያገኝ ያልቻለ ትልቁ የማሰብ ኃይላችን ድክመት ውጤት ነው። የሰው ልጅ ለእንደዚህ ዐይነቱ የተዝረከረከና የጨለመ አኗኗር ሁኔታ የተፈጠረ ይመስል። መላኩ ከሹፌሩ ጋር ጉዞውን በመቀጠልና አካባቢውን በመቃኘት የቤቶችን አሰራር ሲመለከት የሰው ልጅ እንዴት በእንደዚህ ዐይነት ጎጆዎች ውስጥ መኖር እንደሚችል ግራ ይገባዋል። ለልጆችና በዕድሜ ለገፉ ተብሎ ተከልሎ ያለተሰራ ቤትና፣ ሁሉም ነገር እዚያው በዚያው የሚካሄድበትን ቤት ሲመለክት የአገሩን ኋላ-ቀርነት ጥልቀትነቱንና ውስብስብነቱን ይገነዘባል። በመንገድ ላይ እያሉና በረሃውን እያቋረጡ ሲሄዱ ዛፍ የሚመስል ነገርና ፍሬ ያዘለውን፣ ከብቶች ተንጠልጥለው ፍሬውን ሲበሉ ይመለከታል። በአካባቢው ሌላም ዛፍ አይታይም። ይህ ዛፍ በጥቂት ውሃ ወይም በትንሽ ዝናብ ሊበቅልና በርሃንም የሚቋቋም ነው ተብሎ ስለታመነበት በደርግ ዘመን ከሌላ ቦታ መጥቶ የተተከለ ነው። ስሩ ወደ ታች ሃምሳ ሜትር ያህል ስለሚደርስ የመሬት ውስጥ ውሃን የመምጠጥ ኃይሉ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በአካባቢው ያሉትን ሌሎች ዛፎችና አትክልቶች ሁሉ እያወደመ ለብቻው በአሸናፊነት የወጣ የአትክልቶችና የዛፎች ጠንቅ ነው። ፍሬውም በየቦታው ስለሚበተን በራሱ ውስጣዊ ኃይል በመብቀልና በመራባት አካባቢውን አዳርሶታል ማለት ይቻላል። በአሸናፊነት የወጣውን ኢምፔሪያሊስታዊ ኃይል የሚመስልና የሚቀናቀኑትን ሁሉ የሚደመስስ ልዩ የአፅዋት ዘር ነው። ስሙም ፕሮስፒስ ይባላል። የመጨረሻም የሄደበትን የአባቱን የመፈለግ ዓላማ ሳያሳካ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል። መላኩ እግረ መንገዱን ወደ አፋር ሲሄድና ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ የተመለከተው ነገር፣ ከጂቡቲ የሚመጡ ትላልቅ መኪናዎች ዕቃ ጥቅጥቅ አድርገው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ፣ እንደገና ደግሞ ወደ ጅቡቲ ሲሄዱ ምንም ነገር ይዘው የሚሄዱት ነገር ስለሌለ ለመኪናዎች የሚፈሰው የነዳጅ ወጪና የሾፌሮችም የቀን አበል የቱን ያህል እንደሆነ ይገምታል። በዚያውም እኛ ኢኮኖሚክስ ተማርን የምንለውን ሁሉ በመቅደምና አርቆ በማሰብ፣ በጥሬ ሀብት ማውጣትና በመሸጥ ላይ የሰለጠነ እንደኛ ያለ አገር ከውጭ አገር ጋር በሚያደርገው የንግድ ልውውጥ የቱን ያህል ለኪሳራ የሚዳረግ መሆኑን ያመለክታል። በመቀጠልም ተጨማሪ ውጤትና(value-added- በቴክኖሎጂ ምጥቀት ላይ የተመሰረተ የምርት ክንዋኔ)ዕውነተኛ ህብረተሰብአዊ ሀብት(National Wealth) ከጭንቅላት እንደሚመነጭ በመገንዘብ በአገራችን የሰፈነውን ከማሰብ ጉድለት የሚደርሰውን መረን የለቀቀ ድህነት ዋናው ምክንያት ሌላ ሳይሆን የሃሳብ ድህነት መሆኑን ያመለክተናል።

መላኩ አዲስ አበባ ከመድረሱ በፊት ሰሎሜ የፕሮጀክት ስራ ለማካሄድ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ የመላኩን ዐይን ላለማየት ስትል በቀጥታ ወደ መቀሌ ትሄዳለች። በመሀከሉ ማርቆስ በሰሎሜና በመላኩ መሀከል የደረሰውን መቃቃርና ኩርፊያ ምክንያቱን በመፈላለግ ለዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት ስንክሳር ልትሆን እንደምትችል ገመተ። ስንክሳርም ወደ አገር ቤት መጥታ በአንድ በኩል በሰሎሜና በመላኩ መሀከል ያለውን መሻከር የባሰውኑ ለማባባስ የሆነ ያልሆነ ነገር ትቆፍራልች። በሌላ ወገን ደግሞ ክብሮም ወደ መቀሌ መጥቶ ከሰሎሜ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት አንድ መቋጠሪያ እንዲኖረው እንደዚሁ ዘዴ ትፈላልጋለች። ይሁንና ግን እሷ ባለሰበችው ወቀት ደግሞ መላኩ ወደ አሜሪካን እንደሚሄድ ትሰማለች። ሰሎሜም ሳተሰማ ክብሮም ወደ አዲስ አበባ ይመጣል። አመጣጡም ወደ መቀሌ ለመሄድና ከሰሎሜ ጋር ለመገናኘት ነበር። ይህም ውጥን የስንክሳር ሲሆን፣ በመላኩና በሰሎሜ መሀከል ያለውን መቃቃር የባሰውኑ ለማፋፋምና ምዕራፉ እንዲዘጋ ለማድረግና፣ እሷም መላኩን ጠቅልላ የራሷ ለማድረግ ነው ይህ ሁሉ እቅዷ። ክብሮምም አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ስንክሳርም ለሰሎሜ ስልክ በመደወል እንዴት አድርጋ እንደምትነግራት ማውጠንጠን ጀመረች። ስልክ ደውላላትም ስርፕራይዝ እንደምታደርጋት ነገረቻት። ሰሎሜም ጭንቀት ውስጥ ገብታ በነበረችበት ጊዜ ክብሮም ባደረገው ስህተት ይቅርታ ሊጠይቃት እንደመጣ ታስረዳታለች። ይህም አሰፈላጊ እንዳልሆነና ችክ ያለ ተግባር ነው ስትል የምሯን ገለጸችላት። ሰሎሜም ምንም ማድረግ እንደማትችልና የስንክሳርም ተንኮል እንዳለበት በመገመት ነገሩን ተቀበለችው። ክብሮምም ከስንክሳር ጋር አብረው መቀሌ ከሄዱና ከሰሎሜ ጋር ከተገናኙ በኋላ፣ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ዘመድ ልጠይቅ ብላ ብቻቸውን ጥላቸው ወጣች። ክብሮም በነገሩ የተፀፅተ በመምስል ሰሎሜንን ይቅርታ ጠየቃት። አብረውም አንዳንድ ቦታዎችን ከጎበኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ አብረው መጥተው የሰሎሜ አክስት ቤት አረፉ። ሰሎሜና አክስቷ ብቻቸውን ሲሆኑ በክብሮምና በሷ መሀከል የሆነውን ነገር ሁሉ ነገረቻቸው። እሳቸውም ፍቅር የያዘው ሰው እውር ነው በማለት ለክብሮም ማድላታቸውን በተዘዋዋሪ ይነግሯታል። እሷም መላኩን ትወደው እንደነበረና፣ አሁን ግን በሱ ላይ መጥፎ ነገር ሰለሰማች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባት ትነግራቸዋለች። መላኩንም የምትወደው በመልኩ ሳይሆን ልክ እንደ ወንድሟ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ስላለው እንደሆነ ትነግራቸዋለች። ይሁንና ግን የሱ አሜሪካን መሄድና መቆየት፣ በሌላ ወገን ደግሞ የሶፊያ ወደ አዲስ በባ መጥቶ ከሶፊያ ጋር መገናኘትና፣ አንዳንዴ አንዳንድ ነገሮችን ለማየት አብሮ መውጣት በመሀከላቸው ፍቅር ያለ ይመሰል ስንካሳር በማስወራቷ ሰሎሜ ማረጋገጫ በሌለው ወሬ በመናደድና ተስፋ በመቁረጥ ከእንግዲህ ወዲያ ከመላኩ ጋር ምንም ግኑኝነት እንደማይኖራቸው ወሰነች። ከጥቂት ቀናት በኋላ ክብሮም ወደ አሜሪካ ሲመለስ፣ ሰሎሜ ደግሞ እንደገና ወደ መቀሌ ተመለሰች።፡ ግራ የገባው ማርቆስም የዚህን ዐይነቱን የተንኮል ምንጭ አፍላቂውን ማን እንደሆነ በማውጣት በማውረድ ላይ እንዳለ፣ ከስንክሳር በስተቀር ሌላ ሰው ሊያደርግ እንደማይችል ለሰሎሜ አክስት ይነግራቸዋል። ማራቆስ ራሱ በቅርብ የሚያውቀው ነገርና ከሱም ምንም የተሰወረ ነገር የሌለ መሆኑን ሰለሚያውቀው፣ በመላኩና በሶፊያ መሀከል ምንም ዐይነት ግኑኝነት እንደሌለና፣ ሊኖርም እንደማይችል፣ ሶፊያም አዲስ አበባ ከመጣች ጀምሮ ልክ እንደ እህቱ በማየት ያስተናግዳትና፣ የምትሰራበትንም ሆስፒታል በመሄድ የሚጎበኝ እንደነበር ሁኔታውን በጥብቅ የተከታተለ ነው። መላኩም በዚህ አጋጣሚም በፈረንጆች የተሰራውንና የሚተዳደረውን የፊስቱላ ሆስፒታል ከሌሎች አገሪቱ ውስጥ ካሉ ሆስፒታሎች ጋር ሲያወዳድር የሰማይና የምድር ሆኖ ይታየዋል። ግቢውም ሆነ የሰራተኖቹ አያያዝና ለአደጋው የተጋለጡትን ወጣት ሴቶች እንክብካቤ ለየት ያለ መሆኑንም ይገነዘባል። በሌሎች ሆስፒታሎች ውስጥ ያለው መግማማትና የአሰራር ሁኔታ ከቫይረስ በሽታ እንደሚብስና፣ ከበሽታው ይልቅ ግቢው፣ የሆስፒታሎቹና የሰራተኞቹ ሁኔታ ታማሚውን በሽታውን የባሰውኑ እንደሚያብሱበት ይገነዘባል።

መላኩም ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ተቆልሎ የሚጠብቀውን ስራ መልክ ካሲያዘ በኋላ እሱም በበኩሉ የሰሎሜንን ዐይን ላለማየት ለስልጠና ወደ አሜሪካ ለመሄድ ይዘጋጃል። በዝግጅት ላይ እያለ ግን ከአሜሪካ የዶ/ር ሳራ እናት ስልክ ደውለው በጣም አስደንጋጭ ወሬ ይነግሩታል። ስልክ የተደወለው በእኩሌሊት ላይ ስለነበር ስልኩን ስያነሳ የሳራ እናት መሆናቸውን ይገነዘባል። እሳቸውም እየጮሁ ይናገሩ ስለነበር ምን አደገኛ ነገር ተፈጠረ ብሎ ይጠይቃቻዋል። በሳራና በባሏ ምንተስኖት መሀከል ጠብ ተፈጥሮ እንደነበርና፣ ባልየውም ሳራን ሲመታት ትልቁ ልጃቸው በ911 ስልክ ይደውልና ለፖሊሶች ሲነግራቸው፣ ፖሊሶች ምንተስኖትን ወስደው አስራ ቀን ያህል ካሰሩት በኋላ በማስጠንቀቂያ ፈቱት ብለው ይነግሩታል። ይሁንና ግን ደም ፍላቱ ያልበረደለት ምንተስኖት በሰተነጋታው እንደገና ጭቅጭቅ በመፍጠር ትንሽ ከተጨቃጨቁ በኋላ ትልቁንና ትንሹን ልጅ ገድሎ ባለቤቱንም በብዙ ጥይት ካቆሰላት በኋላ ራሱን ገደለ ብለው የሆነውን ሁኔታ ያስረዱታል። መላኩም በበኩሉ ራሱን ይዞ ከጮኸና ካለቀሰ በኋላ የሳራን ሁኔታ ይጠይቃቸዋል። በጣም ተጎድታ ሆስፒታል እንደገባችና አንድ ትንሽ ልጃቸውም ተደብቆ እንደተረፈ ይነግሩታል። መላኩም ድርጊቱን የሰማው አርብ ሲሆን እንደምንም ብሎ ቪዛውን ሰኞ ካገኘ በኋላ ማታውኑ ወደ አሜሪካን ለመብረር ወሰነ። እዚህ ላይ የደራሲው ገለጻ አንድ አርቆ አሳቢ ሰው ባህርዩ ካልገራና የማሰብ ኃይሉም ደካማ ከሆነ ሰው ጋር የጋብቻም ሆነ ወይም አንዳች ግኑኝነት ቢፈጥሩ ምን ዐይነት ስቃይ ውስጥ እንደሚወድቅ ነው። በሌላው ወግን ደግሞ ፍቅር የአጋጣሚ ነገር ስለሆነነ፣ የሚፈላለገውም አንዱ በሌላው ጭንቅላት ውስጥ ገብቶ ምን ዐይነት ሰው መሆኑን መመርመር የሚያስችል መሳሪያም ሆነ ችሎታ ስለሌለው፣ መጀመሪያ ላይ ቅልስልስ ብሎ የገባው የኋላ ኋላ ዕውነተኛ ጸባዩን በማውጣትና ማንነቱን በማሳየት ሌላውን ሰው ስቃይ ውስጥ እንደሚከተው ከደራሲው ግሩም አቀራረብ መረዳት እንችላለን።

መላኩ አሜሪካን በቆየበት ጊዜ ታስተናግደው የነበረችው ተንኮለኛዋና፣ መላኩን ለማጠመድ የምትፈልገው ስንክሳር ነች። ስንክሳር እንደምንም ብላ መላኩን ጓደኛውና ምናልባትም የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ ማድረግ ነበር ዋና ዓላማዋ። ቀስ በቀስ እያለች እሱን ለመጠጋት ያደረገችው ሙከራ በከፊል ቢሳካም አሁንም ቢሆን መላኩና እሷ ልብ ለልብ ሊገናኙ አልቻሉም። መላኩም ስለሰሎሜ ያለው ፍቅር ተሟጦ ያለቀ አየደለም። ስለሆነም መላኩም በትክክል ወዴት እንደሚያደላ ግራ ገብቶታል። ይህ በእንደዚህ እንዳለ መላኩ አሜሪካን በቆየበት ጊዜም በሰሎሜና በክብሮም መሀከል ያለውን ግኑኝነት ዕውነት አስመስላ በመንገር ሃሞቱን እንዲቆርጥና እንዲረሳት ለማድረግ ትጥራለች። ክብሮም ሰሎሜን ጋብዟት በመርከብ ላይ እንዳሉና ተነስተው በመደነስ ላይ እንዳሉ ሰሎሜ ሳታስበው ቀለበት ጣቷ ላይ እንዳደረገላት፣ እንደሳማትና አብረው የተነሱትንም ፎቶ ታሳየዋልች። መላኩም በዚህ ይናደዳል። ይሁንና ግን ሰሎሜ ፈልጋው ያደረገችው ሳትሆን ባላሰበችውና ባልጠበቀችው ሰዓት ማርቆስ ጣቷ ላይ የሰካላት ነው። ማርቆስም ይህንን ሁሉ ከተከታተለና መረጃም ከሰበሰበ በኋላ፣ በአንድ በኩል በሶፊያናና በመላኩ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በሰሎሜና በክብሮም መሀከል አለ የሚባለው ግኑኝነት መሰረት የሌለውና፣ መላኩንና ሰሎሜንን የግዴታ ማስታረቅ እንዳለበት ስትራጂ ይቀይሳል። ሰሎሜ ወደ መቀሌ ከሄደችና ጥቂት ሳምንታት እዚያ ከቆየች በኋላ እሷ ሳታስበው ማርቆስ መቀሌ በአውርቶፕላን ይሄድና አንድ ሆቴልቤት ውስጥ ከአረፈ በኋላ ስልክ ይደውልላታል። መቀሌም እንዳለና ሊያገኛትም እንደሚፈልጋት ይነግራታል። በተቀጣጠሩበት ሰዓት ወደ ሆቴል ቤቱ ከመጣች በኋላና አንዳንድ ነገሮች አዘው በመጫወት ላይ እያሉ ቀስ በቀስ በሶፊያና በመላኩ መሀከል ያለው ግኑኝነት ውሽት መሆኑና፣ ከእሱም ምንም ነገር የተደበቀ ነገር እንደሌለና፣ ይህንንም ያደረገቸው ተንኮለኛዋ ስንክሳር እንደሆነች ያረጋግጥላታል። በመቀጠልም ችካጎ ድረስ ክብሮም ጋ ስልክ በመደወል የሰራውን ቲያትር አንድ በአንድ በመዘርዘር የግዴታ ካሳ መክፈል እንዳለበት ያስረዳዋል። ሰሎሜን የማርቆስን ጥበብና ለዕውነት የቆመ ሰው መሆኑን በመገንዘብ በድርጊቱ በጣም ትደሰታልች። ከእንግዲህ ወዲያ ከመላኩ ጋር የነበራትን ግኑኝነቷን እንዴት እንደገና እንደምትጠግንና መልክም እንደምታስይዘው ታስባለች። የሚገኛኙበትንም ጊዜ በናፍቆት ነበር የምትጠባበቀው። ማርቆስ ስሎሜንን ካሳመነና እሷም አምና ከተቀበለችው በኋላ፣ አሁን ደግሞ መላኩን ማሳመን ነው የቀረው ስራው። መላኩ እስኪመጣ ድረስ ግን ጥቂት ቀናቶች መጠበቅ ነበረበት።

መላኩም ከሁለት ወር ስልጠና በኋላ ከአሜሪካ ጉዞው ይመለሳል። ይሁንና ትንሽ ብልጭታን ያገኘው በመላኩና በስንክሳር መሀከል የተጀመረው ግኑኝነት ዕረፍት አልሰጠው ብሏል። ስንክሳርም ወደ አገርቤት እንደምትመለስ ስለነገረችው በምን መንገድ ግኑኝነታቸውን እንደሚያጠንክሩ ያሰላስል ገባ። መላኩ ከአሜሪካ በተመለሰ ዕለት ማርቆስ ቤት ነበር ያረፈው። መላኩም ጸሎቱን ካደረገ በኋላ ማርቆስ ያዘጋጀለትን ቁርስ መብላት ሲጀምሩ፣ መላኩ በማርቆስና በሶፊያ መሀከል ሊኖር ስለሚችለው የወደፊት ግኑኝነት ሲያወራለትና በነገሩም እንዲገፋበት ሲያበረታታው፣ ማርቆስ ደግሞ ስንክሳር የወጠነችውን ተንኮል ውሸት እንደሆነ እንዴት አድርጎ እንደሚነግረው ማውጣት ማውረድ ጀመረ። ቀስ ቀስ እያለ በጣም አስፈላጊ ዜና እንደሚያሰማው ይነግረዋል። መላኩም ደንገጥ በማለት ምን እንደሚያመጣ በመጠባበቅ ላይ እንዳለ፣ ሰሎሜም ሆነ መላኩ ያሰቡት ነገር ትክክል እንዳይደለና፣ ስንክሳርም ያቀነባበረችው ተንኮል እንደሆነና፣ በእሱና በሶፊያ መሀከል የጦፈ ፍቅር እንዳለ አድርጋ ለሰሎሜ እንደነገረቻት ማርቆስ ለመላኩ ረጋ ባለ መልክ ይነግረዋል። መላኩም በስንክሳር በኩል ለሰሎሜ የላከው ደብዳቤ ስንክሳር እንዳለቸው የጠፋ ሳይሆን በመሀከላቸው ያለውን ግኑኝነት ለመበጠስ ስትል ነው ደብዳቤውን የደበቀችው ብሎ ማርቆስ እቅጩን ይነግረዋል። መላኩ ግን ይህንን ባለማመን ይህ ሁሉ የፈጠራ ስራ ነው፤ ታዲያ ቀለበት ሲያደርግላት የተነሱት ፎቶ ከየት መጣ ብሎ ይነግረዋል። ማርቆስም ለመላኩ የሆነውን ድራማ ሁሉ እየዘረዘረ ሲነግረው የባሰውኑ ግራ ይጋባል። በመቀጠልም ማርቆስ ከክብሮም ጋር በስልክ ያደረገውን ንግግርና በቴፕ የቀዳውን አንድ በአንድ ያሰማዋል። መላኩ ይህ ሁሉ ቲያትር ግራ ቢያጋባውምና ለማመንም ቢሳነው፣ ሳንዲያጎ በቆየበት ጊዜ ስንክሳር ያደረገችውንና የተጫወተችበትን ሁኔታ ፊቱ ላይ ድንቅር አለ። ጠረቤዛውንም በመምታትና በመጮህ ሳንዲያጎ በነበረበት ወቅት የተጫውተችበትን ነገር ሁሉ ዘርዘሮ ነገረው። በመጨረሻም የማርቆስ ድርጊት ሁሉ እየገረመውና ነገሩን ለማውጣጣት የወሰደውን እርምጃ ሲያስበው፣ ለማርቆስ አንተም ልክ እንደተንኮለኛዋ ስንክሳር ሆነሃል አይደለም አንዴ ብሎ ይነግረዋል። ማርቆሰም ሰሎሜ ከመላኩ ጋር ለመገናኝተ በጉጉት እንደምትጠባበቅና ምግብ ሁሉ እንደተዘጋጀና ሶፊያም እዚያ ላይ እንደምትገኝ ያበስርለታል። በማርቆስ ልባዊ ቀናነትና ዕውነትን ለማግኝት ሳይታግቱ መስራት በሁለት ፍቅረኞች መሀከል የነበረውን መሻከርና ወደ ዕልክነት መሸጋገር እንደገና ሊጠገንና ወደ ጤናማ ሁኔታ እንደሚመለስ ደራሲው ሰዕላዊ በሆነ መልክ ይገልጸዋል። ደራሲው እንደሚለው በተንኮሎኞት የውሸት ወሬ የተነሳ በሁለት ሰዎች መሀከል ያለው ግኑኝነት መሻከሩና ወደ ጠብ ማብራቱ ብቻ ሳይሆን፣ እንደዚህ ዐይነቱ የጥቂት ተንኮለኞች ስራዎችና የውሽት ወሬዎች ስንትና ስንት ስልጣኔዎችን እንዳፈራረሱና፣ በመቶ ሺሆች ለሚቆጠሩ ስዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት እንደሆኑ ደራሲው በደንብ ያብራራል። ቢያንስ ባለፉት አስርና አስራ ዓምስት ዓመታት በኢራክ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሊቢያ፣ና ዛሬ ደግሞ በሶሪያ የደረሰውንና የሚደረሰውን የህዝብ እልቂትና የስልጣኔ ውድመት ስንመለከት ጥቂት ሰዎች በተሳሳተ ኢንፎርሜሽን በሚነዙት ወሬና በሚጭሩት እሳት የስንት ሰው ህይወት እንደሚያልቅ የምንመለከተውና በዐይናችን በየቀኑ የሚተላለፍ ሀቅ ነው። ሲአይኤ የሚባል እጅግ አሳሳች የሆነ ወሬ አምራችና ጠብ ጫሪ፣ እንዲሁም ሞሳድና ሌሎች የምዕራቡ ዓለም የስለላ ድርጅቶች በሚነዙት የተሳሳተ ወሬ በቂ ዕውቀት የሌላቸው ሰዎች ጥቂት መሳሪያና የገንዘብ ዕርዳታ በማግኘት የራሳቸውን ስልጣኔ እንደሚያፈርሱ በገሃድ የሚንመለከተው ጉዳይ ነው። ሰለጠንኩኝ የሚለውም የምዕራቡ ዓለም የሚሊታሪ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነቱን ተገን በማድረግና የውሸት ፕሮፖጋንዳዎችን በማስፋፋትና ጥቂት የዋሆችን መሳሪያ በማድረግ፣ በሃይማኖትና በጎሳ በማሳበብ አንድን ህዝብ እርስ በርሱ በማበላላት ፍዳውን እንደሚያሳየውና፣ ከእንግዲህ ወዲያም እንደገና እንዳያንሰራራ ሁኔታውን ሁሉ እንደሚያጨልምበት የውሸት ወሬ የትኛውን ያህል አሳሳችና አገርና ስልጣኔ አውዳሚ እንደሆነ መረዳት እንችላለን። በአገራችንም ምድር በአለፉት አርባ ዓመታት የደረሰው እልቂትና አገር መበታተን ከተሳሳተ ኢንፎርሚሽንና ዕውቀት በመነሳት በጥቂት ግለሰቦች በተጫረ እሳትና በቀላሉ ሊበርድ ባልቻለ መቀጣጠል የተነሳ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ጭንቅላት እስካልዳበረና ማመዛዘን እስካልቻለ ድረስ ለስልጣን የሚስገበገቡ ጥቂት ኃይሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብን ገደል ውስጥ መክተት እንደሚችሉ በታሪክ ውስጥ የተረጋገጠ ነው።

መላኩና ሰሎሚ እንደገና ከታረቁና ከተጋቡ በኋላ ጫጉላቸውን ለማሳለፍ ለሽርሽር ወደ ደቡብ አፍሪካ ይሄዳሉ። መጀመሪያ ያረፉት ጆሃንስበርግ ሲሆን፣ በተነጋታው በአውቶቡስ የተወሰነ ቦታዎችን ካዩ ባኋላ አውቶቡስ ቀይረው ስዌቶን ዞር ዞር ብለው ያያሉ። ጆሃንስበርግም እዚያው በዚያው ደሃና ሀብታም፣ የወዳደቁና ቪላቤቶችን ያቀፈች ከተማ ስለሆነች በቅራኔ የተሞላችና ብዙ ወንጀልም የሚፈጽምባት ከተማ ነች። በተለይም ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጉብኝት ለመጣ ሰውና፣ መግቢያውንና መውጫውን ለማያውቀው እንደልብ ተዝናንቶ የሚንሸራሸሩባት ከተማ አይደለችም። መላኩና ሰሎሜም የተቀራቸውን አራት ቀናት በኬፕ ታውን አካባቢ ለማሳለፍ አቅደው ስለነበር ወደዚያ ያቀናሉ። አካባቢውን ዞር ዞር ብለው በሳፋሪ ካዩ በኋላ ኔልሰን ማንዴላ የታሰሩበትን የሮቢን ደሴትን ለማይት በተነጋታው ወደዚያ ያመራሉ። ደሴቱም ለእስር የተመረጠበት ምክንያት በቀላሉ እስረኛው ለማምለጥ የማይችል መሆኑን ይደርሱበታል። እነመላኩም ፕሬዚደንት ማንዴላ የታሰሩበትን ክፍል ከጎበኙ በኋላ የገረማቸው ነገር ሰውየው ለአስራስምንት ዐመታት ከታሰሩ በኋላ ሲፈቱ ቂምበቀል በልባቸው ሳይቋጥሩ በደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የቀይ ደመና ትብብር እንዲፈጠር መስመሩን መቅደዳቸውና ሁሉም የደቡብ አፍሪካዊ ህዝብ ለጊዜውም ቢሆን በስምምነት ሊኖር የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠራቸው ነው። በሌላ ወገን የኔልሰን ማንዴላ ልብ በፍቅር የተሞላ ቢሆንም፣ ነፃነትን ተቀዳጀ የተባለው ጥቁሩ ደቡብ አፍሪካዊ ከቀድሞ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር ከድህነት ያመለጠ ሳይሆን እንዲያውም በባሰ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ እነመላኩን የሁኔታው አለመቀየር ግራ ያጋባቸዋል። ስለሆነም አፓርታይድ „በመወገዱ“ የጥቁሩ ህዝብ ኑሮ ይህን ያህልም ያልተለወጠ መሆኑን የተገነዘበችው ሰሎሜ፣ መላኩን እንደዚህ በማለት ትጠይቀዋለች። „ግን ያልገባኝ እሺ በማንዴላ ጉዳይ ምንም ጥያቄ የለኝም እንዳወራነው ነው። እኔ የሚገርመኝ አፓርታይድ ከወደቀ፣ ኃይልም(ስልጣንም) ለጥቁሮች ከተሰጠ ታዲያ በተለይ ስዌቶና ጆሃንስበርግ፣ እዚህም ኬፕታውን የሚታየው የጥቁርና ነጭ ልዩነት ምንድነው? እኔ ግን አሁንም የማንዴላ ሥራ ፍሬ አልታየኝም። ማለቴ አስገራሚ ሰው ናቸው፤ ግን በቃ ለውጥ ማለት ይሄ ነው?„ ብላ ጥያቄ ታቀርብለታለች። መላኩም የማንዴላ ትግል ፍሬያማ እንደሆነና ህግም እንደተለወጠ፣ ትግሉ የመጨረሻ መጨረሻ ፍሬያማ እንዲሆን ከተፈለገ የእያንዳንዱ ዜጋ አዕምሮው መከፈትና ነፃ መውጣት እንዳለበትና፣ የታሪክም አደራ በመጭው ትውልድ ላይ እንደተጫነና፣ የሱም ተግባር እንደሆነ ለማስረዳት ይሞክራል። እዚህ ላይ ግን ከደራሲው ጋር ሙሉ በሙሉ መስማማት አይቻልም ይሆናል። የህግ መለወጥ በራሱ የመንግስቱን ምንነት መቀይርና ተግባሩም ምን መሆን እንዳለበት አይገልጽልንም። በደቡብ አፍሪካም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የተካሄዱትን የነፃነት ትግሎች ስንመለከት ስልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉት አዲሱ ኃይሎች ያለውንና የፈረጠመውን የመንግስት መኪና ለራሳቸው በማድረግና ከህዝብ በመራቅ ወደ መጨቆኛ መሳሪያነት ይለውጡታል። የመንግስት ምንነት ግልጽ እስካልሆነና፣ ዲሞክራሲያዊ የሆነ የህዝብ ተሳትፎና የአስተዳደር አወቃቀር እስካለተመሰረተ ድረስ አዳዲስ ኤሊቶች ኢንተርናሽናል ኮሙኒቲ ከሚባለው ጋር በመቆላለፍ አገዛዙን የባሰ ጨቋኝ በማድረግ ዕውነተኛ ነፃነትን ብቻ ሳይሆን፣ ዕውነተኛ ዕድገትም እንዳይመጣ ጠንቅ ይሆናል። ስለሆነም የመንግስትም ሆነ የዲሞክራሲና የነፃነት ጉዳይ እንደገና በአዲስ መልክ መጠናት ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው። የዲሞክራሲ፣ የነፃነትና የስልጣኔ ጉዳይ በምንም ዐይነት ጥቂት ኢሊት ነን፣ ሁሉንም ነገር እናውቃለን ለሚሉ መተው ያለበት ጉዳይ አይመስለኝም። በተለይም ምሁራዊ እንቅስቃሴና ትችታዊ አመለካከት ባልዳበረባቸው እንደኛ በመሳሰሉ አገሮች አምባገነናዊ አገዛዝ እየተመላለሰ መከሰቱና የድህነቱን ዘመን እንደሚያራዝመው መታወቅ አለበት። ፕሬዚደንት ማንዴላና ፓርቲያቸው ስልጣን ሲይዙ፣ በአንድ በኩል የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲ የሚባለው የግዴታ የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክ ፖሊሲን ተግባራዊ እንዲያደር ግፊት አደረገ፣ በሌላ ወገን ደግሞ የመሬት ጥያቄና ሊሎችም የሀብት ይዞታ ጥያቄዎች መነሳት እንደሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጠው። በዚህም ምክንያት አብዛኛው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ የኢኮኖሚ ዕድገት ተጠቃሚ እንዳይሆንና በውሳኔ ውስጥም እንዳይካተት ማዕቀብ ተጣለበት።

መላኩና ስሎሜ አሁንም ደቡብ ከኬፕ ታውን ሳይወጡ እዚያው ሰለመጭው ዕቅዳቻው ሃሳብ ለሃሳብ ሲለዋወጡ፣ አዲስ አበባ ደግሞ ማርቆስና ሶፊያ ቢፈላለጉም፣ መፈላለጋቸውን ግን በግልጽ አውጥተው መናገር አልቻሉም። ሶፊያ ሆስፒታል ውስጥ ስራዋን እየሰራች፣ በተጨማሪ ደግሞ የስዕል ኤግዢቪሽን ለማሳየት ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና ትላለች። በመጨረሻም አባቷ በልጅነቷ ሲያጫውታት ፈገግ ይል የነበረውን ገጽታውን ለመሳል ያቅታታል። በጭንቅላቷ ውስጥ እየመላለሰ የሚታያት ግን አሁንም ተስፋ የቆረጠና የተጨማደደ ፊቱ ነው። በመጨረሻም አባቷ ወደ ላይ እየወረወራት ሲቀበላትና ስትስቅ፣ እሱም ፍልቅልቅ ሲል የተነሱትን ስዕል በትልቁ ትሰራለች። ይህ በእንደዚህ እንዳለ ሳታስበው ማርቆስ ከቸች ይላል። አንድ ቦታ ተቀምጠው የአባቷን ሰዕል እያየች ያለፈችበትን ውጣ ውረድ ትዝ ብሏት ቀስ ቀስ እያለች የህይወት ታሪኳን ታጫውታዋለች። በሷ ምክንያት አባቷና የምትወደው ጓደኛዋ ሶለን ህይወታቸው እንደጠፋ ትነግረዋለች። በተጨማሪም ያላጬሰችው አንዳችም ዕፅ እንደሌለና፣ ሙሉ በሙሉ ተስፋዋ ተሟጦ እንደነበረ ትዘረዝረታለች። እሱም በጥሞና ካዳመጠ በኋላ፣ በሷ የጨለመ ታሪክ ሳይሳቀቅና ተስፋ ሳይቆርጥ እሱም በበኩሉ ያለፈበትን አስቸጋሪ ጉዞና፣ ብዙ ሰዎችም በድለውት እንደነበርና፣ ይህንን ሁሉ ከመጤፍ ሳይቆጥር ይቅርታ በማድረግ፣ ስንክሳር ደግሞ በሰሎሜና በመላኩ ላይ በደል እንዳትፈጽም በማለት ምን ዐይነት የብልህነት ስራ እንደሰራ ታሪኩን ይነግራታል። እሷም በሱ ስራ በመደነቅና ግሩም ሰው መሆኑን በመረዳት ሁለቱም ቀስ በቀስ በፍቅር እንደተጠመዱና፣ በሃሳብና በልብም እንደሚገናኙ ፍላጎታቸውን ይገልጻሉ።

መላኩና ሰሎሜ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት ወተር ፍሮንት በሚባለው መዝናኛ ባለበት አካባቢ ተቀምጠው ሳለ ሁለቱም በሃሳብ ማዕበል ይዋጣሉ። ስሎሜም መላኩ ምን ያስብ እንደነበር ትጠይቀዋለች። እሱም የሚጽፈው መጽሀፍ እንዳለው ነገር ግን ሃሳቡ ቶሎ አልመጣ እንዳለውና ግራ እንደገባውና በጭንቀት ዓለም ውስጥ እንደሚገኝ ይነግራታል። ለመሆኑ የመጽሀፉ አርዕስት ምንድንነው ብላ ትጠይቀዋለች። እሱም ርዕሱን እንደሚያውቀውና፣ ያልተጻፈና አልጻፍ ያለ መሆኑን ይነግራታል። ታዲያ ማወቅ ይቻላል ብላ እንደገና ትጠይቀዋለች። ቀና ብሎ እያያት „የተቆለፈበት ቁልፍ“ ነው ብሎ ይነግራታል። እሷም በበኩሏ፣ የምትጽፈው ስለተቆለፈበት ቁልፍ ከሆነ ቁልፉን ካገኘህ ሃሳቡም ይመጣልሃል ስትለው፣ ምን ትቀልጂያለሽ በማለት፣ ምናልባት በመጀመሪያ አርዕስቱን በመምረጤ ሳይሆን አይቀርም ሃሳቤን የቆላለፈው ይላታል። እንደዚህ እያሉ ሃሳብ ለሃሳብ ሲለዋወጡ የድሮው ትዝታቸው ብልጭ አለባቸውና ወደ ሌላ ዓለም ውስጥ ገቡ። መላኩም አሷ አሜሪካ በነበረችበት ወራቶች እኛ መኪና ግጭቷቸው ሳለ አንስታ የጋበዘቻቸውና ገንዘብም የሰጠቻቸው አባባ አራጋው የሚባሉት ሽማግሌ እንደሞቱ ይነግራታል። እሷም በጣም በማዘን አገሯ ምን ዐይነት አገር እንደሆነና፣ ሽማግሌና ህፃናትን የሚንከባከብና የሚረዳቸው እንደሌለ፣ ህብረተሰቡም ርስበርሱ የሚተጋገዝ እንዳልሆነ ያበሳጫታል። እሱም ህብረተሰብ ማለት ምን ማለት ነው? ውል የሌለው ነገርና ዝም ብሎ የተሰበጣጠረ መሆኑና፣ እሱም በታሪክ አጋጣሚ ሰው የመሆን ዕድል እንዳጋጠመው ይነግራታል። ይህ ዐይነቱ አገላለጽ ምንድነው የሚያመለክተው? ከሞላ ጎደል አንድ ህብረተሰብ በዕውቅ ካልተደራጀና፣ በተለይም ደግሞ ታዳጊው ትውልድ በሚገባ ታንጾ የታሪክ ባለቤት እንዲሆና ታሪክን እንዲሰራ ከተፈለገ ህብረተሰብአዊና ሰብአዊ ባህርይ ያለው አገዛዝና ኢንስትቱሽኖች መኖር አለባቸው። አንድ አገር በየአካባቢው ህዝቡን የሚንከባከብና፣ እያንዳንዱም ግለሰብ እንደየችሎታው የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ የታሪክ ባላደራ እንዲሆን ከተፈለገ የግዴታ በዕውቅና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ አገዛዝ ያስፈልገዋል። ይህ በሌለበት አገር የየግለሰቡ ጉዞና አኗኗር ዓላማ-ቢስ ይሆናል። አገርና ህብረተሰብም ትርጉም አይኖራቸውም።

በአጠቃላይ ሲታይ የዶ/ር ምህረት ከበደ መጽሀፍ በዐይነትም ሆነ በአቀራረቡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሀፍ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ደራሲው በኖይሮ ባይሎጂ ዕውቀት የዳበረ ሰው ብቻ ሳይሆን የስልጣኔንም ትርጉም የገባውና ሰብአዊ ባህርይ ያለው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው ልል እችላለሁ። ስለህብረተሰብ ትርጉምና ስለህዝብ አኗኗር የጻፈው፣ ከዚህም በመነሳት ስለህበረተሳበችን ኋላቀርነት ያቀረበው ትንተና የምናየው ቢሆንም፣ ልንረዳውና ሊከንክነን ያልቻለ ነው። የዶ/ር ምህረት ከበደ አቀራረብ ሶክራሲያዊና ፕላቶናዊ ነው። ስለዚህም ፍልስፍናዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ህሊናዊ የሆነ የአንድን ህብረተሰብ ዕድገትም ሆነ ውድቀት ከጭንቅላት መዳበርና አለመዳበር ጋራ ያያዘ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሉ ከሚባሉት ስነ-ጽሁፎች ውስጥ ሊካተት የሚችል መጽሀፍ ነው ብል እንደመድፈር አይቆጠርብኝም። የደራሲው አቀራረብ የዳንቴ የአምላኮች ኮሜዲንንም የሚያስታውሰን ሲሆን፣ የአንድን ህብረተሰብ በጨለማ ዓለም ውስጥ መኖርና፣ የሆነውን ያልሆነውን በማድረግ በብልግና ዓለም ውስጥ መዝፈቅና፣ ከእንደዚህ ዐይነቱ ኋላቀር አኗኗር እንዴት መውጣት እንደሚቻል ብርሃኑን የሚያንፀባርቅልን ነው። የደራሲው አቀራረብ ሺለሪያዊም ነው። የሰላሳ ዓመት ጦርነትን ታሪክ ያጠናው ፍሪድርሽ ሽለር እንደሚለን፣ ከአሪስቶተለስ ጀምሮ ስለዴሞክራሲ ሰምተናል። አሁንም ቢሆን ከአረመኔነት ባህርያችን አልተላቀቅንም ይላል ሺለር። በሱ እምነትም፣ የዚህ ሁሉ ችግር አዕምሮና ልብ አንድ ላይ ለመገናኘት ባለመቻላቸውና፣ ስራቸውንም ለማቀነባበር ስላልቻሉ ነው ይለናል። የኖይሮ ባዮሎጂስቱ አዋቂና ፈላስፋው ዶ/ር ምህረት ከበደም ይህንን መሰረት በማድረግ ነው የሚያስተምረን። በእሱ ዕምነት ብቻ ሳይሆን፣ በእኔም ዕምነት፣ ዛሬ በዓለም ደረጃም ሆነ በአገራችን ምድር በሃይማኖትና በጎሳ ስም ተሳቦ የሚካሄደው ቅጥ ያጣ ግድያ፣ ህዝቦችን አፈናቅሎ አገርን ወደ አጠቃላይ ድህነትና ረሃብ እንድታመራ ማድረግ ዋናው ምክንያት የጭንቅላት በደንብ አለመዳበርና ዘመናዊነት በሚባል አጉል ፈሊጥ፣ ነገር ግን ደግሞ ከስልጣኔ ጋር ምንም ነገር የሚያገናኘው የሌለ ጥቂት ኤሊት ነን በሚሉና ከውጭው ኃይል ጋር በተቆላለፉ ኃይሎች የሚካሄድ ዘመናዊ አረመኔያዊ ተግባር ነው።
የዶ/ር ምህረት ከበደ መጽሀፍ በአገራችን ታሪክ ውስጥ በዐይነትም ሆነ በአቀራረብ የመጀመሪያው ስለሆነ ለወደፊት ምርምራችንና ዕድገታችን እንደመመሪያ ሊያገለግል የሚችል መጽሀፍ ነው። ማንኛውም ለአገሬ አስተዋጽዖ አደርጋለሁ ወይም እታገላለሁ የሚል ከዚህ መጽሀፍ ወጭ ትግል ሊያደርግ አይችልም። ደራሲው እንዳለው ሁላችንም በኦቲዝም ትይዘን የምንሰቃይ ስለሆነ፣ አገራችንን ከማጥፋታችን በፊት እስቲ ባለንበት ቦታ ሁሉ በመቀመጥም ሆነ በመቆም እናስብ። በዚህ አማካይነት ራሳችንን ማግኘት ስንችልና ማንነታችንን ስንረዳ በእርግጥም ታሪክን ለመስራት ዝግጁ ነን ማለት ነው። በተረፈ ለዶ/ር ምህረት ከበደ ክቡራዊ መልዕክቴ ይድረሰው። ጤንነትህን እንዲጠብቅልህ ለእግዚአብሄር እጸልይልሃለሁ። ታላቅ ደራሲና ታላቅ ጽሀፍ !!

ፈቃዱ በቀለ !!
fekadubekele@gmx.de

መንደሪ ነው አገሪ! ለምለም ፀጋው

ልማታዊ ዲያስፖሮ፡- ስጡ የቀመሰ ዶሮ በበላይነህ አባተ

ዐይናችን ተከፍቷል ህሊናችን ነቅቷል ከአንተነህ መርዕድ

$
0
0

የመጀመርያው የኬንያ ፕሬዝደንትና የነፃነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብዙ ጊዜ የሚጠቀስላቸው፣ ስለ ቅኝ ገዥዎች የተናገሩት እውነት ይህን ይመስል ነበር። “ሚሲዮኖች ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መጽሃፍ ቅዱስ፤ እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ዐይናችንን ጨፍነን እንዴት እንደምንጸልይ አስተማሩን። ዐይናችንን ስንገልጠው ግን እነሱ መሬታችንን እኛ መጽሃፍ ቅዱሱን ታቅፈናል” አሉ። “When the Missionaries arrived, the Africans had the land and the Missionaries had the Bible. They taught how to pray with our eyes closed. When we opened them, they had the land and we had the Bible”.

ኬንያም ሆነ ሌላውን የአፍሪካ አገር በሚሲዮንነት ቆይቶም ለቅኝ ግዛት ወርረው የያዙት፣ ለአገሩ ባዳ ለሰው እንግዳ የሆኑ ነጮች ነበሩ።በመሆኑም አገሬው ባለው አቅሙ እየተባበረ ታግሏቸው ነፃ ወጥቷል። ሌሎች አፍሪካውያን ያዩትን የውጭ አገዛዝ እኛ ልጆቻቸው እንዳናየው ከመላ ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ አባቶቻችን ዘርና ቋንቋ ሳይለያቸው ተደራርበው ድንበሯ ላይ በመውደቅ ነፃነታትንን ከማስጠበቃቸውም በላይ ለመላው ቅኝ ተገዥ ኩራትና የነፃነት ቀንዲል ሆነው አልፈዋል። እኛ ግን አሁን አባቶቻችንን ከገጠመው የተለዬ የአገርና የህዝብ ጠላት ገጥሞናል። ከሃያአምስት ዓመት በፊት የመጡት ወራሪ ወንድሞቻችን ወያኔዎች አገሪቷን ሲቆጣጠሩ አንገታቸው ላይ ኩሺታ(መቀበርያቸው ጨርቅ) ምላሳቸው ላይ የዘረኝነት ከፋፋይ መርዝ ይዘው መጡ። “ሁላችንም በጎጥ እንደራጅ፣ በማንነታችንና በቋንቋችን ላይ እናተኩር” ብለው ሰበኩን።

በተቀነበበልን የጎጥ አጥር ተጨፍነን ገባንላቸው፣ ያለፈ አስቀያሚ ታሪካችንንና አፅም እየቆፈርን የምንበቃቀልበትን ስልት እያዘጋጁ ሲሰጡን ሳንመረምር ተቀበልን። ካለፈ ታሪካችን ስህተት በባሰ ስህተት ውስጥ ገብተን መሳርያ ሆንን። አሁን ባንነን ዐይናችንን ስንገልጥና ልቦናችንን ስናቀና እነ አቦይ ስብሃት፣ እነ አቦይ ፀሃይ፣ እነ ሳሞራ የኑስን የመሳሰሉ ወያኔዎች መሬታችን፣ቀሪውን ሃብታችን፣አጠቃላዩን ህልውናችን በእጃቸው ውስጥ ሆኖ ሲሳሳቁና ሲዘባበቱብን አገኘናቸው። ከእኛ እጅ የቀረው ክፍፍልን፣ ለብሄረሰብ መብታችን በየዓመቱ ተሰባስቦ መጨፈርና በርሃብ ማለቅ ሆነ።

አባቶቻችን አይደለም መጽሃፍ ቅዱስ፣ መድፍና መትረየስ ይዘው የመጡ የውጭ ጠላቶችን እጃቸውን እየሰበሩ መልሰዋቸዋል። የኤይድስ ቫይረስ ከሌላ የሰውነት ህዋሳት ጋር ተመሳስሎ በማጥቃቱ መከላከል እንደሚያስቸግረው ሁሉ የእኛ ደም፣ ቀለምና ቋንቋ የተካኑ የባንዳ ልጆች ለይቶ ማጥቃት ስላልተቻለን አሁን አለንበት አዘቅት ውስጥ ተገኝተናል። የህወሃቶች ብቸኛው ሃይላቸው ህዝበን የመከፋፈል ክህሎታቸው፣ የብዙሃኑ ህዝብ ድክመትም በአንድነት ቆሞ የጋራ ጠላቶቹን መታገል አለመቻሉ ነው። ከብዙ ልፋትና መከራ በኋላ ዐይኑን መግለጥ የጀመረው ኢትዮጵያዊ የተከሰተለት እውነት ቢኖር ይኸው ነው።

አንገታቸው ላይ ኩሺት ብቻ ጠቅልለው የመጡ ወያኔዎች በአንድ ጀንበር ሚሊዬነር፣ የብዙ ፎቆች ባለቤቶች፣ ሰፋፊ የከተማና የእርሻ መሬት ከበርቴዎች፣ በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና በቻይና የብዙ ካምፓኒዎች ባለቤትና ባለድርሻ ሲሆኑ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ የከተማ መሬቱን ተነጥቆ ዘበኛቸው፤ እርሻው ተነጥቆ የቀን ሠራተኛቸው፤ መብራቱ ጠፍቶበት ሻማ ይዞ እነሱን እራት የሚያበላቸው፤ መድረሻ ካጣም በስደት የእየአገሩን እስር ቤት የሚሞላና ኩላሊት ገባሪ ሆኗል።
ዛሬ የወላጆቻችን መሬት ሊነጠቅ አይገባውም ብለው የተነሱ የኦሮምያ፣ የጋምቤላ፣ የጎንደር ልጆችን የሚጨፈጭፉት ህወሃቶች አገዛዛቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ ህዝቡ በገባርነት እንዲኖር የትምህርት ስርዓቱን ሲገድሉት፤ የእነሱ ልጆች በስዩም መስፍን ተቆጣጣሪነት በቻይናና በምዕራቡ ዓለም ትልልቅ ዩኒቨርስቲዎች ተምረው አሁን ያሉትንና ወደፊትም የሚፈጠሩትን ይህወሃት ካምፓኒዎች እንዲመሩ፤ እያረጁ ከፖለቲካው የሚገለሉትን አባቶቻቸውን የሚተኩ መሳፍንት እንዲሆኑ እየተዘጋጁ ነው። አገር ውስጥም ልጆቻቸው አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ ወላይትኛ እንዲማሩ ተመቻችቶላቸው በመላ አገሪቱ እንዲሰማሩ ሲደረግ፤ ሌላው ህዝብ ከራሱ ቋንቋ ውጭ ሌላውን በጥላቻ እንዲያይና ወንዝ እንዳይሻገር ሆኖ በመንደሩ ታውሮና ደህይቶ እንዲኖር ፈርደውበታል።

የግፍ ጽዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። እኩይ ዓላማቸው የገባው ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር ተንቀሳቅሷል። ዐይኑን ገልጧል። በቆየም ቁጥር አጥርቶ ያያል። በተለይም ሁለቱን ታላላቅ ህዝብ አማራንና ኦሮሞን ለመለያየት ብዙ የደከሙበት ቢሆንም የቋጠሩት መተት መፈታት ጀምሯል። የተረጨው መርዝና የተፈጠረው ክፍተት ብዙ በመሆኑ ከሁሉም ወገን የሰከነ እንቅስቃሴን ይጠይቃል። እንደህወሃቶች የእንግሊዞች መርዝ ያንገበገባቸው ጆሞ ኬንያታ ለወገኖቻቸው የሰጡት ምክር የቆየ ቢሆንም ለእኛ ዛሬ ላለነው ሁኔታ ስለሚጠቅም ላካፍላችሁ። “የነበረው የዘር ጥላቻ ማብቃት አለበት። የቆየው የጎሳ ጥቃት መቆም አለበት። ባሳለፍነው መራራ ታሪካችን ውስጥ ስንቆዝም አንኑር። ያለፉትን የከፉ ታሪኮቻችንን ከማስብ የወደፊቷን አዲሲቷን ኬንያ ማለም እመርጣለሁ። ይህንን ዓይነት ብሄራዊ ስሜትና ማንነት ከፈጠርን የኢኮኖሚ ችግራችንን ለመፍታት ረጅሙን ጉዞ መሄድ እንችላለን” ብለዋል። (Where there has been racial hatred, it must be ended. Where there has been tribal animosity, it will be finished. Let us not dwell upon the bitterness of the past. I would rather look to the future, to the new Kenya, not the bad old days. If we can create this sense of national direction and identity, we shall have gone a long way to solving out economic problems).

ባለፈው ታሪካችን አባቶቻችን ሉአላዊነታችንን ለማስጠበቅ የከፈሉትን ጉልህ አኩሪ መስዋዕትነት ያህል ብዙ አስከፊና አሳፋሪ ታሪክ አለን። ያንን አስከፊ ታሪካችንን የሚክዱትም ሆኑ ዘወትር የሚቆፍሩት ሁሉ በትናንት የሚኖሩ ኋላቀሮችና ዛሬን የማያዩ ጨለምተኞች ናቸው። ከሁሉም በላይ ሳያውቁት የህወሃት መሳርያዎች ናቸው። የኢትዮጵያ አፈር ትናንት በደርቡሾች፣ በግብፆች፣ በጣልያኖች ጥይት ተደራርበው ከወደቁ ኦሮሞዎች፣ አማሮች፣ ትግሬዎች፣ ወላይታዎች፣ ሶማሌዎች፣ ሲዳማዎች፣… ደምና አጥንት ውህደት የተቀመመ ነው። ዛሬም የወያኔ አጋዚ ጥይትና ዱላ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በአምቦ፣ በወለጋ፣ በጎንደር የሚወድቁ ወጣቶች እየታደሰ ያለ አፈር ነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር አፈር! ሰሞኑን ገዛሃኝ ኦሊጋ፣ጉቱ አበራ ዴሬሳ፣ ካራሳ ጫላ፣ ደበላ ታፋ ቢሮ፣ ደጀኔ ሰርቤሳ፣ ሚፍታህ ጁነዲ ቡሽራ፣ ሙራድ አብዲ ኢብራሂም፣ በቀለ ሰይፉ፣ በቀለ ሰቦቃ ሁንዴ፣ ኢብሳ መብራቱ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በግፍ ተገድለዋል፤ በጎንደር ደግሞ ሽመልስ አቡሃይና ከሰላሳ በላይ እስረኞች ተገድለው በእሳት እንዲነዱ ሆኖ የግፍ መስዋዕቱ ደም ጨሶ ሰባቱን ሰማያት አዳርሷል። ወያኔዎች ይህንን ሁሉ ሥራቸውን የሚከፍሉበት ሰዓት ተቃርቦ እያቃጨለ ነው። አምባገነኖች እስከመጨረሻዋ ሰዓት አይባንኑም። ሩቅ ሳንሄድ የደርግ ባለስልጣናት አዲስ አበባ በወያኔ መድፍ ስር ሆና የቤታቸውን ቀለም ያስቀቡ ነበር። ወያኔዎች ገንዘብ አሽሽተናል፣ እናመልጣለን ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ኢትዮጵያዊ የሌለበት ዓለም የለም። እንደናዚ ወንጀለኞች ተለቅመው ፍርድ ያገኛሉ። እንደባተቱም ይኖራሉ።

ዛሬ ባከማቹት ጦር መሳርያና በሰራዊቱ ይመፃደቁ ይሆናል። ከአመራሮች በቀር ጦሩ የህዝብ ልጅ ነው። የተመኩበትን መሳርያ ያዞርባቸዋል። ደርግም መላ አፍሪካን የሚያስርድ ሰራዊትና መሳርያ ነበረው። በታላቁ የኬንያ መሪ ጥቅስ የጀመርሁትን በተከታዩ መሪ ጥቅስ ልዝጋ። ይቃወሙኛል ያላቸውን የህዝቡን ልጆች ጨፍጭፎ በምስራቁም ድል ተኩራርቶ የሶሻሊስቶችን መሳርያ እስከ አፍንጫው የታጠቀው ደርግ። እብሪቱ ከፍ አለ። የሚደፍረኝ የለኝም፤ ዘላለማዊ ነኝ ብሎ ፏለለ። ይህንንም ዓለም በተለይም አፍሪካውያን መሪዎች እንዲያዩለት በአስረኛው የአብዮት በዓል በብዙ ሚሊዮን ዶላር ደገሰ (እንደ አሁኑ በተመሳሳይ ወቅት ብዙ ሚሊዮኖች በርሃብ እየረገፉ እንዳይነገር ታፍኗል) አብዮት አደባባይ ላይ የሰራዊት፣ የሚሳይል፣ የታንክ፣ የአየር ሃይል ትርኢት አሳዬ። ከእንግዶቹ መካከል የዚያን ጊዜ የኬንያ መሪ አራፕ ሞይ ነበሩ። ያዩት መሳርያና ሰራዊት ብዛት አስደነገጣቸው። ጎረቤት ናቸውና። አገራቸው ሲመለሱ በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ “የምን ኢምፔርያሊዝም፣ የምን ቅኝ ገዥ ያስፈራችኋል። የሚፈራስ ጎረቤታችን ሆኗል” ካሉ በኋላ በርሃብ እየተጥናፈረች ላለችው አገር መሳርያ ሳይሆን ሰላምና ምግብ መሆኑን አፅንዖ ሰጥተው ንግግራቸውን ሲዘጉ “ኩላ ቻኩላ፣ ሲታ ማዚዋ፣ ላላ ሰላማ” ብለዋል። (የስዋሂሊ ትርጉሙ “ስጋችሁን ብሉ፣ ወተታችሁን ጠጡና በሰላም ተኙ” ነው) ወያኔዎች ሆይ የሚበላው እህል የራበው፣ ፍትህ የጠማውና ግፋችሁ የጎመዘዘው ህዝብ ከድግምታችሁ ነቅቶ ሊበላችሁ እያዛጋ ነው። ካልነቃችሁ መልካም እንቅልፍ! ላላ ሰላማ!!

Amerid2000@gmail.com

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዲያስቦራ ምዕመናን ግራ መጋባት እስከ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን ማቋቋም መኩሪያ ለዓለም

ኦሮሞው ኢትዮጵያዊ ያነሳውን የትግል ችቦ ሌላው ኢትዮጵያዊም ተቀብሎ ያበራል! ገለታው ዘለቀ

$
0
0

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከዚህች ከኣዲስ ኣበባዋ የመሬት ነጠቃ ጥያቄ በጅጉ ገዝፎ የሄደ ነው። ከፍተኛው ጥያቄ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ህወሃት ይህን ዘረኛ ፖለቲካውን ተሸክሞ ኣዲስ ኣበባ ከገባ በሁዋላ በተለይ ኦሮሞንና ኣማራን ጸጥ ኣድርጎ ለመግዛት የተጠቀመው ዘዴ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ከታች እስከ ላይ ያሉትን ባለ ስልጣናት በኣልተማሩና የማስተዳደር ችሎታ በሌላቸው ነገር ግን ታዛዥ ብቻ በሆኑ ሰዎች መሙላት ነበር። ወያኔዎች ይህን ያደረጉበት ምክንያት ህወሃት ይዞት የተነሳው ጥያቄ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የዴሞክራሲ ጥያቄ ባለመሆኑና ዋናው ዓላማው የሆነ የራሱን ክብ ለመጥቀም በመሆኑ እነዚህን ክልሎች ኣፍኖ የሚይዝለት ኣስተዳደራዊ መዋቅር ስላስፈለገው ነው። ህወሃት ያሻውን ያደርግ ዘንድ “የራሴ” የሚለውን ክብ ለመጥቀም ይችል ዘንድ በየክልሉ የራሱን መጠቀሚያዎች መፈለግ ስለነበረበት ነው። በነዚህ ክልሎች ሰው በባትሪ ተፈልጎ የሚሾመው ህወሃት የኣሳቡ እስኪሞላ ድረስ ፈረስ የሚሆኑትን ሰዎች በማግኘት ላይ የተመሰረተ ነበር። የማይጠይቅ፣ የሚፈራ፣ ለጥቅም የሚንበረከክ፣ እውቀት የሌለው፣ በባትሪ እየተፈለገ የሚሾመው ህወሃት ቀድሞ ላሰበው የግል ጥቅም ስራው ኣንድ ራሱን የቻለ ስትራተጂ ኣድርጎ ስለወሰደው ነው። ውሎ ሲያድር ይህ ስትራተጂ ምን ኣመጣ? ከባድ የመልካም ኣስተዳደር ችግር በተለይ በኦሮምያና ኣማራ ክልሎች ኣመጣ። የበቁ የነቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ወይ በኦነግ ወይ በተቃዋሚ እየተፈረጁ ተወገዱ። የኦሮሞ ህዝብ ልቡ ኣዘነ። የተማሩ ልጆች እያሉኝ፣ ጥሩ ጥሩ ማስተዳደር የሚችሉ ልጆች እያሉኝ ለምን እንዲህ ኣደራጋችሁኝ? እያለ ኣነባ። ኣማራው ኣካባቢም እንደዚሁ ታዛዡን እየፈለጉ ሲሾሙ በክልሉ ቀልጣፋ ኣገልግሎት ጠፋ፣ ህዝቡ ወደ ወረዳ ወደ ክልል ወደ ዞን ሲሄድ የሚያገኛቸው ባለስልጣናት ችግሩን የማይረዱ ኣንዳንዴም በሚያሳፍር መልኩ ህዝቡ የሚለው እንኳን የማይገባቸው ሆነው ተገኙ። ተራው ሰው የበለጣቸው መሪዎች በየቦታው በመኖራቸው ህዝቡ ከኣመራር ኣካላቱ የሚጠብቀው ነገር ጠፋ። በተለይ የነዚህ የሁለቱ ክልሎች ትልቅ ችግር ይሄ ነው። ህወሃት እነዚህን ክልሎች ከቀጣበት መንገድ ሁሉ በጣም ኣስከፊው ቅጣት ይሄ ነው። በራሳቸው ልጆች በጃዙር ቀጣቸው። በርግጥም ልጆች እያሏቸው የተማሩትን የተሻሉትን እያባረረ በማይሆኑ ሰዎች እንዲተዳደሩ መደረጉ ትልቅ ቀውስን ኣምጥቷል። ህወሃት እነዚህ ሰዎች መሳሪያው ስለሆኑና እላይ ቆልለውት እየሰገዱለት ስለሚኖር ደስ ብሎታል። የመጣው ማህበራዊ ቀውስ ግን ልክ የለውም። ይህ ችግር በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ቢታይም በኦሮምያና በኣማራ ግን የከፋ የከፋ ሆኖ ይታያል። በኣንዳንድ ቦታዎች ህወሃት ስልጣን ሲይዝ የወረዳ ሊቀመንበር የሆኑት ህወሃት ከመምጣቱ በፊት ችሎታ የሌላቸው ጥሩ ምግባር ያልነበራቸው ወዘተ ነበሩ። እነዚህን ሰዎች እየሰበሰበ የቀበሌ ምክር ቤት፣ የወረዳ ምክር ቤት፣ የክልል ምክር ቤት እያለ ነው ይሾም የነበረው። ህዝቡ ለጊዜው ይስቅ ነበር። ይሁን እንጂ መራራው እውነት ግን እነዚህ ሰዎች የዚህን ህዝብ እጣ ፈንታ የሚወስኑ ስለነበር ሳቁ ወደ ኣዘን በፍጥነት ተቀየረ። ኣንዳንድ ለምልክት ከየብሄሩ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎችን ደግሞ ህወሃት በኣጃቢ ስም የቁም እስር ኣስሯቸው የህወሃትን ፍላጎት እያስፈጸሙ እንዲኖሩ ተደርገዋል።ይህ ችግር ለብዙ ኣመታት ሲቆይ የመልካም ኣስተዳደር ብሶቱን ኣበዛና እነሆ ዛሬ ህዝቡን በእንባ ኣራጨ።

ኣንዱ የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የሚያስተዳድሩትን ህዝብ ጥለው ህወሃትን ቆመው የሚያበሉ የክልሉን ኣስተዳዳሪዎች ማውገዝ፣ ህወሃት የፈጠረው ይህ ራስ ወዳድና ስግብግብ ፖለቲካ እንዳስቆጣቸው ለመግለጽ፣ ለውጥን ለመሻት ነው። ሌላው ጉዳይ ደግሞ ከመልካም ኣስተዳደሩ ችግር በተጨማሪ ኣጠቃላይ የፖለቲካው ኣወቃቀር ህዝቡን ግራ ግብት ኣደረገው። በተፈጥሮ ሃብት፣ በባህል፣ በፖለቲካ ተሳትፎዎች ግልጽ የሆነ ስምምነት የለም። ይሄ ጉዳይ ከፍተኛ ማህበራዊ ምስቅልቅል ኣመጣ። ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመን ስትኖር ኣንዳንድ ክፉ ትውስታዎች(memories) ነበሯት፣ ብዙ መልካም ትዝታዎችም(good memories) ነበሯት። የህወሃት ፖለቲካ የቆመው ግን መጥፎዎቹን ትዝታዎች(bad memories) እየመረጠ በነዚያ ላይ ነው ቤቱን የሰራው። ነገር ግን ፖለቲካ ዓላማው በጎ ለውጥን ማምጣት በመሆኑ ለማህበረሰብ ለውጥ እንደ ኤነርጂ ኣድርጎ ሊጠቀምባቸው የሚገባው ጥሩ ጥሩ ትዝታዎችን በማጉላት ነበር። የኛ ፖለቲካ ግን በተቃራኒው መጥፎ ትዝታዎችን በማጉላት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠረው ኤነርጂ ኔጌቲቭ እንዲሆን እየታገለ ነው።ታዲያ ፖለቲካ በመጥፎ ትዝታዎች ላይ ሲቆም ኣንዱ ውጤት ይህ ነው። ቡድኖችን ማጋጨት፣ ብሄራዊ ማንነትን ማኮሰስ ፣ ኣገርን ማስጠላት ስደትን ማብዛት ነው። ይህ ጉዳይ ህዝቡን ውስጡን ጎድቶታል። ፖለቲካ በመልካም ትዝታዎች ላይ ቆሞ እነሱን እያራገበ መጥፎዎቹን ሊያርምና ሊክስ ነበር የሚገባው። ኣለመታደል ሆነብንና የህወሃት ፖለቲካ መጥፎዎቹን እያራገበ፣ ማራገብ ብቻ ሳይሆን ማጣፈጫ ጨው ጨመር እያደረገ የውሸት ታሪክ እየጻፈ ኣበላሸው። ይህ ጉዳይ በጣም ጎድቶናል። ትልቅ ብሄራዊ ስብራትም ኣመጣ።

ኣሁን የህዝቡ ጥያቄ የለውጥ ጥያቄ ነው። ድሃው ህዝብ በቃል የሚገልጻቸውና የማይገልጻቸውን ውስብስብ ችግሮቹን በማስተር ፕላኑ ለመግለጽ ይሞክር እንጂ ብሶቱ የትየለሌ ነው። ትልቁ ብሶት የተበላሸውን የሶሺዮ ፖለቲካ ስርዓት እንዲለወጥ ከመፈለግ ነው። ህዝቡ ለውጥ ያለ ልክ ተርቧል። ጥያቄው ይሄ ነው።ወለጋ ውስጥ ያለውን ኦሮሞ፣ ምእራብ ሃረርጌ ያለውን ኦሮሞ ወዘተ…. ገንፍሎ እንዲነሳ ያደረገው ጉዳይ የመልካም ኣስተዳደር እጦትና ይህን ተከትሎ የመጣው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግፎች ናቸው።

ታዲያ የህዝቡ ጥያቄ የለውጥ ይሁን እንጂ በዚህ የለውጥ ወራት ጊዜ የትግላችንን ፍሬ ሊለቅሙ ከሚጣደፉ ወያኔዎች መጠንቀቅ ኣስፈላጊ ነው። በሃገራችን የሚመጣው ለውጥ ግዙፍ ለውጥ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን እንደገና ኣፍርሶ የሚሰራ መሆን የለበትም። ኢትዮጵያን እንደገና የሚያንጽ ስራ ነው የሚያስፈልገው። ስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ኣንድነት ኪዳን ውስጥ ልንገባ ይገባል። ይህ ማለት ኢትዮጵያን በመገንጠል ሪፈረንደም ወይም በሌላ መንገድ ኣፍርሰን እንደገና እንስራ ወይም እንገነጣጠል ማለት ኣይደለም። ኢትዮጵያን እንደዚህ ለማሳብ ኣይቻልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግልጽ የሆነ የቡድኖች የድንበር ክልልም የለም። እነዚህ ኣሁን ያሉት ዘጠኝ ክልሎች ትናንት ወያኔ የፈጠራቸው፣ እንዳሻው የሰራቸው ናቸው። ኢትዮጵያ ስትፈጠር ዘጠኝ ክልል ነበረች የሚል ታሪክ የለም። ወያኔ በፈጠረው ኮራብትድ ክልል የመገንጠል ሪፈረንደም ኣይሰራም። ኣገራችን ኣንድ ናት። የተቀየጠው ህዝብ ብዛት ከብሄሮች ቁጥር በልጧል። ወያኔ እንደሚለው ሳይሆን የጋራ ግዙፍ ታሪኮች ኣሉን። የጋራ ሃብት ኣለን። ወንዞቻችን የተፈጥሮ ሃብቶቻችን የጋራ ናቸው።ኣንዳንድ የወያኔ ኣባላት ከዚህ በፊት ጥለውት የነበረውን የመገንጠል ጥያቄ ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ሲነሳባቸው ሊያነሱ ይችላሉ። ኣምነውበት ባይሆንም ለጊዜው መሸሸጊያ ይሆነናል ከሚል ትግራይን ለመገንጠል ያስቡ ይሆናል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ በቀጥታ ኣይደለም። እንዲህ ኣይነት የህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ይህንን ትግል ሃይጃክ በማድረግ ሊሆን ይችላል። በመጀመሪያ ኣገሪቱን ኣፍርሰው፣ በተለይ ኣማራውንና ኦሮሞውን ኣባልተው ነው የሚሄዱት። የመገንጠል ጥያቄው ከሌላ ብሄር እንደመጣ ኣድርገው ሌላውን ብሄር በየቤትህ እደር ኣይነት ከበተኑ በሁዋላ የሚያስቡትን ለማድረግ ይሞክሩ ይሆናል። ከዚህ በፊት ኣንስተውት ጥለውት የነበረ ጥያቄ ቢሆንም ወያኔ ኣይታመንምና ይህን ብንገምት ኣይፈረድም። ሃያ ኣምስት ዓመት ሲዘርፉ ቆይተው ኣሁን የመገንጠል ነገር ቢያመጡ ፍጻሜው ምን ይሆናል? የሚለውን ጥያቄ እናዘግየውና እንደዚህ ሊያስቡ ስለሚችሉ ለዚህ ፍላጎታቸው የኦሮሞም ህዝብ ሆነ የኣማራ ወይም የደቡብ እንዲሁም ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመች ኣይሆንም። የኦሮሞ ጥያቄም ሆነ የሌላው ህዝብ ጥያቄ የለውጥ፣ የመልካም ኣስተዳደርና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው።

የለውጡ ጥያቄ ኢትዮጵያን እንደገና የማነጽ ስራ ነው። ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ ማለት እኛ በቋንቋ የተለያየን ቡድኖች ኣብረን ስንኖር የኣንድ ቡድን የበላይነት ሳይኖር እንዴት ኣብረን በእኩልነት እንኑር? እንዴት ኣድርገን ያለንን ባህል በኣንድ በኩል ወደ ላይ እያሳደግን በሌላ በኩል ወደ ጎን እየተማማርን እንኑር? የቋንቋ ሃብቶቻችንን እንዴት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንጠቀም? እንዴት ኣድርገን የተሻለ ብሄራዊ ማንነት እንገንባ? በኣካባቢያችን ያለውን የተፈጥሮ ሃብት እንዴት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንጠቀም? ፖለቲካዊ ኣሰላለፋችን እንዴት እናድርገው? በሚሉ ጉዳይች ዙሪያ የመግባቢያ ኣሳብ ማምጣትና በዚህ ስምምነት ላይ መተዳደር ማለት ነው መስማማት ማለት:: ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ ማለት ወደፊት ለቡድኖች ሁሉ እኩልነትን የሚያመጣ ኣሳብ ማመንጨትና በዚያ ላይ ኣቋም ይዞ ኣዲሲቷን ኢትዮጵያን መገንባት ነው። በመሆኑም የለውጡ ጥያቄ ሰፊ ነው። ኢትዮጵያውያን ለውጥ ሲያነሱ ኣገራቸውን ለማፍረስ ኣይደለም። ኢትዮጵያ ማለት ኦሮሞ ነው። ኦሮሞ ማለት ኢትዮጵያ ናት። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ጥያቄ እንደግፋለን። ለውጥ ይምጣና የተሻለ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ማእቀፍ ውስጥ እንግባ። ሁላችን የኦሮሞ ወንድሞቻችንን ጥያቄ ደግፈን ለመልካም ኣስተዳደርና ለዴሞክራሲ እንታገል። በትግላችን ላይም ሆነ በውጤቱ ላይ በኣንድም በሌላም መንገድ ለወያኔ መሰሪ ዓላማ እድል ፈንታ ኣንሰጥም።ኦሮሞው ኢትዮጵያዊ ያነሳውን የትግል ችቦ ሌላው
ኢትዮጵያዊም ተቀብሎ ያበራል!

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያችንን ይባርክ

ገለታው ዘለቀ
geletawzeleke@gmail.com

የኢትዮጵያና ኤርትራ ቅራኔዎች ከሚንጋ ነጋሽ


ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል ዘዴ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል- የመጨረሻ መጨረሻም አገርን ያወድማል! በፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር

$
0
0

ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ።

በእርግጥ ለአንድ አገር ስርዓት ባለው መልክ መተዳደርና፣ ህብረተሰቡም በዕቅድና በዓላማ እንዲመራ ከተፈለገ በዚያ የሰፈነው አገዛዝ ህብረተሰቡን በማደራጀት ረገድ የሚጫወተው ሚና አለ። ጥያቄው ግን አንድ ህብረተሰብ ዓላማ ባለው መልክ እንዳይደራጅና ቆንጆ ቆንጆ ስራዎችን እንዳይሰራ የሚያግዱት ነገሮች ምን ምን ናቸው? በስነ-ስርዓት እንዲደራጅስ ከተፈለገ መሪዎችም ሆነ ህብረተሰቡ መከተል የሚገባቸው ኖርሞች፣ ፍልስፍና፣ ሞራልና ስነ-ምግባር አሉ ወይ? ምንስ ይመስላሉ ? ወይስ አንድ ህዝብ እየተዋከበና ርስ በርሱ እየተፋጠጠ መኖሩ ተፈጥሮአዊ ግዴታ ነው ወይ ? አንድ ህብረተሰብስ በምን መልክ ነው መታየት ያለበት? በሌላ አነጋገር፣ ለመብላትና ለመጠጣት ብቻ የሚኖርበት ? ወይስ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ስነ-ምግባራዊ፣ ጥበባዊና ኢኮኖሚዊ፣ እንዲሁም ሌሎችም ነገሮች ተደራጅተው ህብረተሰቡ እንደሰውነታችን በብዙ ነርቮች ተሳስሮ፣ ልክ እንደደም ዝውውር ሳያቋርጥ፣ በተለይም ኢኮኖሚው አንድኛው መስክ ከሌላው ጋር በመያያዝ ውስጠ-ኃይሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እየተጠናከረ የሚጓዝበት መድረክ ነው ወይ ? የሚሉትን ጥያቄዎች ጠጋ ብሎ መመልከትና መመርመር የሚያስፈልግ ይመስለኛል። በተለይም በአሁኑ ዘመን የግሎባል ካፒታሊዝም አይሎ መውጣትና፣ የብዙ ህብረተሰቦችን ህይወት ወሳኝ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲያመሩ ማስገደድና ማዘበራረቅ፣ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ፈራቸውን እየሳቱና በቀላሉ የማይመለሱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት ይቻላል። በተለይም የየመንግስታቱ መኪና በከፍተኛ ደረጃ ሚሊታራይዝድ መሆንና ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የጦር ስልት ውስጥ እንዲካተት መደረጉ፣ በዚህም ላይ የስለላው ድርጅት መጠናከርና ህዝብን አላላውስም ማለት፣ ብዙ የአፍሪካ መንግስታት አንድ መንግስት ለአገሩና ለህዝቡ ምን መስራት እንዳለበት እንዳይገነዘቡና አትኩሮአቸውንም በሀገር ግንባታ ላይ እንዳያደርጉ አግዷቸዋል ማለት ይቻላል። የየመንግስታቱትም ሚና ህብረተሰቡን ከማደራጀት፣ ህብረ-ብሄርን ከመገንባት፣ በሳይንስና በቲክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ የውስጥ ኢኮኖሚ ላይ ከመረባረብ ይልቅ፣ ራስን ወደ ማጠናከሪያና ሀብት ዘራፊነት ተለውጧል። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታትና አገዛዞች የህዝቦቻቸው ተጠሪዎች ሳይሆኑ፣ በውጭ ኃይሎች የሚታዘዙና፣ በተለይም ጦርነትንና ህዝባዊ ሀብትን ሊፈጥር የማይችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚያደርጉ ናቸው።

ከዚህ ስንነሳ በፍጹም ልናልፈው የማንችለው ጥያቄ ከፊታችን ተደቅኖ ይገኛል።ይኸውም ብዙ የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮች ከሞላ ጎደል ስርዓት ባለው መልክ ተደራጅተው ሲጓዙና፣ የብዙ ሚሊያርድን ህዝቦች ዕድል ወሳኝ መሆን ሲችሉ፣ እንደኛ ያለውንስ ህዝብ ስነ-ስርዓት ያለው አደረጃጀት ለምን ተሳነው? ስነ-ስርዓትስ ባለው መልክ ለመደራጀት የሚጎድሉን ነገሮች ምንድናቸው? ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊ፣ ህብረተሰብአዊ ? ወይስ የፖለቲካ ፍልስፍና እጦትና መሪዎች የሚመሩበት አንዳች ፍልስፍና አለመኖር ?

ለአንድ ህብረተሰብ በስነ-ስርዓት መደራጀትን አስመልክቶ ከጥንት የግሪክ ስልጣኔ ጀምሮም ሆነ ከዚያም በፊት ህግና ስርዓት አስፈላጊ መሆናቸውን በብዙ ምርምር የተደረሰበትና በኢምፔሪካል ደረጃም የተረጋገጠ ነው። ይሁንና ግን በተለይም ፍልስፍናን ከፖለቲካ ጋር ማያያዝና፣ አንድም ህብረተሰብ ሚዛናዊ በሆነ መልክና በስነ-ስርዓት የማደራጀትን አስፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ ውይይት የተካሄደበት ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ ነው ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ የተነሱና ብዙም ምርምር የተካሄደባቸው የፖለቲካ ፍልስፍናዎች፣ ህብረተሰብን በአንድ ስርዓት ባለው መልክ ማደራጀት፣ በግሪኩ የተለያዩ ፍልስፍናዎች ላይ ተመርኩዞ ነው። እዚህ ላይ ሌላው የሚነሳው ጥያቄ፣ የተለያዩ የግሪክ ፈላስፋዎች አትኩሯቸውን ለምን በፍልስፍና ላይ፣ በተለይም በፖለቲካ ፍልስፍና ላይ አደረጉ ? የሚለው ከባድ ጥያቄ መመለስ ያለበት ይመስለኛል። እንደሚታወቀው የሰው ልጅ ለህይወቱ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያና ራሱንም ለመከላከል መሳሪያዎች ቢያስፈልጉትም፣ ከዚህ ዘልቆ በመሄድ የማሰብ ኃይሉን በማዳበርና ራሱንም በማደራጀት ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ ደረጃ በመሸጋገር የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤትም መሆን እንደሚችል የታወቀ ጉዳይ ነው። ከዚህ ስንነሳ ከላይ የተጠቀሱት መሰረታዊ ጉዳዮች በየጊዜው ሊሻሻሉና በቁጥር እየጨመረ ከሚሄደው ህዝብ ጋር ሊጣጣሙ የሚችሉት የሳይንስና የቴኮኖሎጂ ሚናነት በግልጽ ከተቀመጡና፣ በነዚህ ላይ ከፍተኛ ርብርቦሽ ከተደረገ ብቻ ነው።፡ይሁንና አንድ ህዝብ የማሰብ ኃይሉን እንዳያዳብር፣ አዳዲስ መሳሪዎችን በመፍጠር ከዝቅተኛ ህብረተሰብ ወደ ከፍተኛ እንዳይሸጋገር፣ ከቁም ነገር ስራ ይልቅ በሆነ ባልሆነው ነገር በመያዝ ወይም በጦርነት በመጠመድ ዝብርቅርቅ ኑሮ እንዲኖርና፣ በዚያው እንዲገፋበት የሚያደርጉትና፣ ይህ ዐይነቱም ኑሮ እንደ ባህልና እንደ ልማድ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ። ይህንን ሁኔታ ጠጋ ብለው የተመራመሩት የግሪክ ፈላስፎች የሰው ልጅ ከእንስሳ የተለየ ከሆነና፣ ራሱንም ማደራጀትና በሰላም መኖር የሚችል ከሆነ ለምንድን ነው ወደ ጦርነት የሚያመራው? ለምንድን ነው የተዘበራረቀ ኑሮ የሚኖረው? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ነበረባቸው።

ሶክራተስና ፕላቶ ብቅ ከማለታቸው በፊት በስድስተኛው ክፍለ-ዘመንና ከዚያ በፊት የግሪክ ህዝብ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኝ ነበር። የርስ በርስ መተላለቅ፣ መጠን የሌለው ብዝበዛና ድህነት፣ የተፈጥሮ አደጋዎች መደጋገምና ሌሎችም የግሪክን ህዝቦች ኑሮ ያመሰቃቀሉና፣ ዕረፍትና ሰላም አንሰጥም ያሉ ሁኔታዎች የህዝቡ ዕጣዎች ነበሩ። እነዚህን የመሳሰሉ የኑሮን ትርጉም ያሳጡ ሁኔታዎች በእነ ሆሜርና በሄሲዮድም ሆነ በግሪክ ህዝብ ዕምነት የአምላኮች ድርጊት እንደነበሩና፣ ባስፈለጋቸው ጊዜ ህዝቡን ለመቅጣት ሲሉ የሚልኩት ውርጅብኝ እንደነበርና፣ ህዝቡም ካለ አምላኮች ፈቃድ በራሱ አነሳሽነት ምንም ሊያደረገው የሚችለው ነገር እንደሌለና፣ የነሱንም ትዕዛዝ መጠበቅ እንደነበረበት የታመነበት ጉዳይ ነበር። ከሶክራተስና ከፕላቶ በፊት የነበሩ የመጀመሪያዎቹ የተፈጥሮ ፈላስፎች ይህንን አስተሳሰብ ትክክል እንዳልሆነና፣ በተፈጥሮ ውስጥ ይከሰቱ የነበሩ አደጋዎች፣ ለምሳሌ እንደ ብልጭታና የመሬት መንቀጥቀጥም ሆነ ሌላ ነገሮች የአምላኮች ተልዕኮዎች ሳይሆኑ የተፈጥሮ ህግጋት እንደሆኑና፣ ማንኛውም ነገር ካለምክንያት እንደማይከሰት ለማመልከት ቻሉ። ይህ የመጀመሪያው የተፈጥሮ ፍልስፍናና፣ በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን በታላቁ የግሪክ መሪ በሶሎን ተግባራዊ የሆኑት የመጀመሪያው የፖለቲካ ሪፎርሞች በግሪክ ህዝብ አስተሳሰብ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አስከተሉ። ህዝቡ ከማንኛውም የባርነት ማነቆዎች እንዲላቀቅ መደረጉ፣ የነበረበትን ዕዳ እንዳይከፍል መሰረዝና፣ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እንደነፃ ዜጋ እንዲታይ መደረጉ ከፍተኛ የአስተሳሰብ ለውጥን ሊያመጣ ችሏል። ከፍተኛ የባህል ለውጥ የታየበትና ልዩ ልዩ የፍልስፍና አስተሳሰቦችና፣ የሂሳብ ምርምሮችና ሳይንሳዊ አስተሳሰብም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው በተለይም የግሪክን ምሁር ጭንቅላት መያዝ የጀመሩትና ዕውነተኛ ዕድገት የታየበት። በፒታኩስና በሶሎን የአገዛዝ ዘመን የግሪክ ህዝብ ከጦርነት ተላቆና በአጉል ጀግንነት ላይ የተመሰረተን ዝናን ጥሎ ራሱን በማግኘት ዕውነተኛ የሲቪክ አገዛዝን የተቀዳጀበት ዘመን ነበር። የማቴሪያል ደስተኛነት ብቻ ሳይሆን የመንፈስንንም ነፃትና ደስተኛነት በመቀዳጀት የመፍጠር ችሎታውን ያዳበረበት ዘመን ነበር። ከፒታኩስና ከሶሎን አገዛዝ በፊት የግሪክ ህዝብ በጦርነት የተጠመደና ይህንን እንደሙያው አድርጎ በመያዝ የሚዝናናበት ዘመነ ነበር። ይሁንና ግን የፒታኩስና የሶሎን የፖለቲካ ሪፎርሞች በግሪክ ህዝብ ላይ መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ቢያመጡም ይሁ ሁኔታ ግን በዚያው ሊገፋበት አልተቻለም። በመሆኑም የስልጣን ሽግግር ሲካሄድና የኃይል አሰላልፍ ሲቀየር፣ የፖለቲካ ፍልስፍናና አደረጃጀት እነሶሎን በቀደዱት መልክ ሊጓዝ አልቻለም። በተለይም የስልጣንን ምንነት ከራሳቸው ዝናና ጥቅም አንፃር መተርጎምና ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት አንዳንድ የግሪክ መሪዎች የፖለቲካውን አቅጣጫ ይቀይራሉ። ህብረተሰብአዊ ስምምነትን የሚያጠነክር ፖለቲካዊ አካሄድ ሳይሆን ውዝግብነትን የሚፈጥር፣ የህዝቡን መንፈስ የሚረብሽና የጥቂት ኦሊጋርኪዎችንና ቡድኖችንም ሆነ ግለሰቦችን ጥቅም የሚያስቀድም ፖሊሲ መቀየስ ይጀምራሉ። በመሆኑም የኦሊጋርኪዎችን አመለካከት የሚያስተጋቡና ይህም ትክክል ነው ብለው የሚያስተምሩ ፈላስፋዎች፣ ሶፊስቶች ተብለው የሚጠሩ፣ የፖለቲካውን መድረክ እየተቆጣጠሩና ብዙ ወጣቶችንም በማሳሳት የበላይነትን እየተቀዳጁ በመምጣት በስምምነት የተመሰረተውና ለከፍተኛ ስልጣኔ የሚያመቸውን የእነሶሎን የፖለቲካ ፍልስፍናን ከመከተል ይልቅ ስግብግብነትንና ዝናነትን በማስቀደም ህብረተሰባዊ መዛባት እንዲፈጠር ያደርጋሉ። በተለይም የአቴን የበላይነትን መቀዳጀትና ከሌሎች ደሴቶች ጋር ሲወዳደር በስልጣኔ ቀድሞ መሄድ የግሪኩን የመጀመሪያውን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እየደመሰሰው ሊመጣ ቻለ። የመንፈስን የበላይነት፣ ጥበብና ህብረተሰብአዊ ስምምነትን የሚቀናቀነው የሶፊስቶች አመለካከት በመስፋፋት አገዛዙን ይበልጥ ለጦርነት የሚገፋፋና፣ የህዝቡን ሰላም የሚነሳ ስርዓት በመሆን በስንትና ስንት ጥረት የተገነባው ስልጣኔ በተሳሳተ ፍልስፍና መፈራረስ ይጀምራል።

በወቅቱ የተለያዩ የግሪክ ግዛቶች፣ በአንድ በኩል በራሳቸው ውስጥ በሚደረግ ሽኩቻ የተወጠሩ ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ የፐርሺያ አገዛዝ አቴንና ሌሎችንም ግዛቶች በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ተደጋጋሚ ጦርነት ይከፍትባቸዋል። በፐሪክለስ የሚመራው አገዛዝ ሌሎችንም በማስተባበር ከፐርሺያ ወራሪ ጦር በኩል የተከፈተበትን ጦርነት መክቶ ይመልሳል። ይሁንና ግን እነ ፐሪክለስ ሌሎችን ግዛቶች በማስተባበር በፐርሽያ ጦርነት ላይ ድል ከተቀዳጁ በኋላ የጥጋብ ጥጋብ ይሰማቸዋል። ቀደም ብሎ የተደረሰበትን የእኩልነትና ስምምነት ውል በማፍረስ በሌሎች የግሪክ ግዛቶች ላይ ወረራ ያደርጋሉ። እጅ አልሰጥም ያሏቸውን ግዛቶች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በማካሄድ በተለይም ወንድ ወንዱን በመጨረስ ሴቶችንና ህፃናትን ገባር ያደርጓቸዋል። ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ነበር። የግሪክን ህዝብ ትርምስ ውስጥ የከተተ ነበር። ይሁንና ይህ የአቴን ጥጋብና ግፍ በስፓርታ የገዢ መደብ ሊከሽፍና ሊገታ ቻለ። በዚህ ድርጊቱ ፐሪክለስ አቴን ለሌሎች ግዛቶች በስልጣኔዋ ምሳሌ ትሆናለች ብሎ እንዳለተመጻደቀ ሁሉ፣ በተግባር ያሳየው ግን በኃይሉ በመመካት ወረራንና ጭፍጨፋን ነበር ያረጋገጠው።

እነ ሶክራተስና ፕላቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻና፣ በአራተኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ብቅ ሲሉ ይህንን የወንድማማቾችን ርስ በርስ መተላለቅና፣ ህዝቡን ሰላም ማሳጣትና ኑሮውም ትርጉም እንዳይኖረው ማድረግ የተረጎሙት ከተሳሳተ ፍልስፍና ጋር የተያያዘ ስልጣን መሆኑን በማመልከትና፣ በአንድ ግለሰብ ላይ ብቻ የሚሳበብ ሳይሆን፣ ጠቅላላውን የፖለቲካ አወቃቀርና አገዛዙ የሚመራበትን ፍልስፍና በመመርመር ነበር። በሶክራተስ ዕምነትና አመለካከት፣ በጊዜው ፐሪክለስ ታላቅ መሪ ቢሆንም በሱ ዘመን አቴን ወደ ኢምፔርያሊስትነት የተለወጠችና፣ የአገዛዙም ፖሊሲ ዝናን በማስቀደም ኃይልንና ስግብግብነትን(Power and Greed) ዋና ፍልስፍናው አድርጎ የተነሳ አገዛዝ መሆኑን በማመልከት ነበር። በመሆኑም ይላል ሶክራተስ፣ በፐሪክለስ ዘመን ወጣቱ ሰነፍ፣ ለፍላፊና አጭበርባሪ የሆነበት ዘመንና፣ አሳሳች አስተሳሰብ በማበብ በተለይም የወጣቱን ጭንቅላት በመያዝ ወደ ማይሆን አቅጣጫ እንዲያመራ የተደረገበት ሁኔታ ነበር። ባህላዊ ኖሮሞችና መከባበር የጠፋበት፣ ሽማግሌ የማይከበርበትና፣ ህዝቡም ይዞ የሚጓዘው አንድ ዕምነት አልነበረውም። አስተሳሰቡ ሁሉ የተዛበራረቀበት ነበር።

በጊዜው የነበረው ትግል ይህንን አቅጣጫ የሌለውን ጉዞና በስልጣን መባለግ አስመልክቶ በሶክራተስና በፕላቶ በአንድ ወገን፣ በሌላ ወገን ደግሞ በሶፊስቶች መሀከል የጦፈ ትግል ይካሄድ ነበር ። ሶፊስቶች የእነ ፐሪክለስን የአገዛዝ ፍልስፍናን ሲደግፉ፣ መሰረተ-ሃሳባቸውም በጊዜው የነበረውን ሁኔታ መቀበልና ይህም ትክክል መሆንኑ ማስተማር ነበር። ሶፊስቶች በአነሳሳቸው ተራማጅ ቢሆኑም፣ ፍልስፍናቸው በቀጥታ በሚታይ ነገር ላይ ተመርኩዞ ትንተና መስጠትና፣ በጣፈጠ ግን ደግሞ በተሳሳተ አቀራረብና አነጋገር የሰውን ልብ መማረክ ነበር። ስለዚህም በሶፊስቶች ዕምነት ስልጣን ላይ ያለው የገዢ መደብ የሚያወጣውን ህግ አምኖ መቀበልና፣ ከዚህ ሌላ አማራጭ ነገር እንደሌለ ሲከራከሩና ለማሳመን ሲጥሩ፣ እነሶክራተስና ፕላቶ ደግሞ፣ በተለይም ፕላቶ በሶክራተስ በመመሰል ይሉት የነበረው የጠቅላላውን የፖለቲካ አወቃቀር ለመረዳት ከነበረው ሁኔታ አልፎ(Trnascedental) መሄድና መመርመር እንደሚያስፈልግ ያመለክቱ ነበር። በሌላ አነጋገር፣ ሶፊስቶች ኃይልንና ለስልጣን መስገብገብን ትክክል ነው ብለው ሲሰብኩ፣ እነሶክራተስና ፕላቶ ደግሞ እንደዚህ ዐይነቱ ጉዞ እጅግ አደገኛ እንደሆነና፣ የመጨረሻ መጨረሻም አንድ ህብረተሰብ ሊወጣ የማይችልበት ማጥ ውስጥ የሚከተው ነው ብለው በጥብቅ ያሳስቡ ነበር። ካሊክለስ የሚባለው አንደኛው የሶፊስቶች መሪ የእነሶክራተሰን በአርቆ አስተዋይነትና በሚዛናዊነት ላይ የተመረኮዘ የፖለቲካ ፍልስፍናን ሞኞች ብቻ ናቸው የሚከተሉት ብሎ በመስበክና በማንቋሸሽ፣ ፖለቲካ በስምምነት ላይ ሳይሆን በአሽናፊና በተሽናፊነት ላይ የተመረኮዘና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ኃይል ያለው ብቻ ነው ሊገዛ የሚችለው በማለት ሽንጡን ገትሮ ይከራከር ነበር። በተጨማሪም በሶፊስቶች ዕምነት አንድ ሁሉንም ሊያሰተባብርና፣ ሁሉም ሰው ሊቀበለው የሚችለው ዕውነት ነገር የለም። ሁሉም ሰው አንድን ነገር እንደፈለገው ሊተረጉምና ሊረዳ ይችላል። ፕሮታጎራስ የሚባለው የሶፊቶች ሌላው መሪ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ የዕውነት መለኪያ አለው፤ (Man is the Measure of Everything) አንድ ሁሉንም ሊያሰተባብርና ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባው ዕውነት የለም በማለት የሶፊስቶችን የተሙለጨለጨ አመለካከት ያስተጋባ ነበር።

በሶክራተስና በፕላቶ የፍልስፍና ዕምነት ግን ማንም ሰው ዓላማና ተግባር ሲኖረው፣ በመጀመሪያ ከትክክለኛ ዕውቀት ጋር ነው የሚፈጠረው። ይሁናን ግን እያንዳንዱ ግለሰብ በዚህች ዓለም ላይ ሲወረወር እንደየህብረተሰቡ ሁኔታ ከተፈጠረበት ዕውቀት ጋር እየራቀ ይሄዳል። በአንድ ወቅት ነገሮች ርስ በራሳቸው እንደተያያዙና የተወሳሰቡ መሆናቸውን ይገነዘብ የነበረው ጭንቅላት፣ የተያያዙ ነገሮችን እየበጣጠሰ መመልከት ይጀምራል። ነገሮች ሁሉ ብዥ ይሉበታል። ዕውነትን ከውሽትን ለመለየት ይቸገራል። ከዚህም በላይ ለአንድ ችግር መነሻ የሆነውን ዋና ምክንያት ለመረዳት ችግር ውስጥ ይወድቃል። በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት ወደ ጥንቱ ሁኔታ ለመመለስ ማንኛውም ሰው ሀቀኛውን መንገድ ለመፈለግ የማያቋርጥ ትግል ማድረግ አለበት። እየመላለሰ ራሱን መጠየቅ አለበት። በቀላሉ በሚታዩ ነገሮች ላይ መማረክና እነሱን ትክክል ናቸው ብሎ መቀበል የለበትም። ስለሆነም፣ በሁለቱ ዕምነት የሰው ልጅ ሁሉ ጠላት ከመንፈስ ተነጥሎ የሚታየው አካል ነው። ሰዎች ራሳቸውን ለማጎልመስ ሲሉ በሆነው ባልሆነው ነገር ይታለላሉ። አስተሳሰባቸው በማቴርያል ነገር ላይ ሲጠመድ ስግብግብነትንና አብጦ መገኘትን፣ ሌላውን ሰው ደግሞ ማንቋሸሽና መናቅን እንደ ዋና የኑሮ ፍልስፍናቸው አድርገው ይመለከታሉ። ይህ ዐይነቱ አመለካከትና ከቆንጆ ስራ እየራቁ መሄድና በራስ ዓለም ውስጥ መኖርና መሽከርከር ለጦርነትና ለአንድ ህብረተሰብ መመሰቃቀል ምክንያት ነው ብለው ያስተምሩናል። በሌላ አነጋገር የሰዎች ንቃተ-ህሊና ዝቅ እያለ ሲሄድ፣ ወይንም ደግሞ በተሳሳተ ኢንፎርሜሽንና ዕውቀት በሚመስል ነገር በሚጠመድበት ጊዜ እያንዳንዱ ግለሰብ የህብረተሰቡ አካል መሆኑን ይዘነጋል። እንደዛሬው ባለው ሁኔታ ደግሞ ሃይማኖትንና ጎሳነትን በማሰቀደም እያንዳንዱ ግለሰብ የእኔ ሃይማኖት ወይም ጎሳ ከሌላው ይበልጣል በማለት ሰብአዊነትን ከማስቀደም ይልቅ ወደ አለመተማመንና እንዲያም ሲል ወደ ርስ በርስ መጨራረስ ያመራል። ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ብልጥ ነን ለሚሉና ለስልጣንና ለገንዘብ በሚሽቀዳደሙ ጥቂት ኃይሎች እንደመሳሪያነት በማገልገል አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖርና፣ ድህነትና ረሃብ እጣው እንዲሆን ይደረጋል።

በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር የማሰብ ኃይል ችግር ወይም የዕውቀት ችግር ነው። ዕውነተኛ ዕውቀትን የምንጎናጸፈው ትምህርት ቤት በምንማረው ወይም እንደ ዳዊት ሸምድደን በምንደግመው ዐይነት የሚገለጽ አይደለም። በሁለቱም ዕምነት ሆነ ኋላ ብቅ ላሉት የአውሮፓ ፈላስፋዎችና ተመራማሪዎች፣ ዕውነተኛ ዕውቀት ማለት ራሳችንን እንድናውቅ የሚያደርገን፣ ወደ ውስጥ ራሳችንን ለመመልከት እንድንችል ግፊት የሚያደርግብን፣ የበለጠ ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚያስችለን፣ የተፈጥሮን ህግጋት ጠለቅ ብለን እንድንረዳ የሚያስችለንና፣ በጥንቃቄም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በማውጣትና ቅርጻቸውን በመለወጥ እንድንጠቀምባቸው የሚያግዘን፣ ህብረተሰብን በስነ-ስርዓትና መልክ ባለው ሁኔታ እንድናደራጅ የሚረዳን፣ ከሰውነታችን ፍላጎት ይልቅ የመንፈስን የበላይነት በማረጋገጥ በመንፈስ ኃይል በመመራት ከሌላው ተመሳሳይ ወንድማችን ጋር ተሳስቦ መኖር መቻል፣ በፍጹም የራስን ጥቅም በማስቀደም ዓላማ አለመመራት…ወዘተ. ናቸው። ለተንኮልና ለምቀኝነት ተገዢ አለመሆንና ወደ ብጥብጥ አለማምራትና፣ ህብረተሰብአዊ ምስቅልቅልነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን አለማዘጋጀት፣ የማንኛውም የሰው ልጅ ፍጡር ጥረት አርቆ በማሰብ ኃይል በመመራት ወደ እግዚአብሄር ለመጠጋት መጣር ነው። በፕላቶ ዕምነት ሌላው ለአንድ ህብረተሰብ ምስቅልቅል ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ወይም ለጦርነት ምክንያት የሚሆኑ ከሰብአዊነትና ከወንድማማችነት ይልቅ የብሄረ-ሰብ/ጎሳ አድልዎነት(Ethnic Solidarity) ምልክት የሆኑ ቅስቀሳዎች ቦታ ከተሰጣቸው ነው። በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ለሚከሰት ችግር ዋናው ምክንያት የተለያዩ ብሄረሰቦች በመኖራቸው፣ ወይም አንደኛው ብሄረሰብ በሌላው ላይ ጫና ስለሚያደርግ ሳይሆን፣ በስልጣን ላይ ያሉ ኃይሎች ራሳቸው በሚፈጥሩት ልዩነትና ስልጣን ላይ ለመቆየትና ህዝቡን አደንቁረው ለዘለዓለም ለመግዛት እንዲችሉ የብሄረሰብን ጥያቄንና ሃይማኖትን የፖለቲካ መሳሪያ አድርገው ሳይንሳዊውንና የስልጣኔውን ፈር ያሳስታሉ። ስለዚህም ለአንድ ህብረተሰብ ችግር ዋናው መፍትሄ እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌላው የማይበልጥ መሆኑን ሲረዳና፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የተለያዩ ብሄረሰቦች መኖር የታሪካዊ ግዴታ እንጂ እንደክፋት መታየት የሌለባቸው መሆኑን ሲገነዘብ ነው። የእያንዳንዱም ግለሰብ ግንዛቤ የሰውን ልጅ ሁኔታ ልክ እንደተፈጥሮ ህግ መረዳት ሲሆን፣ ተፈጥሮ ውስጥ የተለያዩ ነገሮች፣ ለምሳሌ የተለያዩ አበባዎች፣ የተለያዩ ዛፎችና የተለያዩ ከብቶች መኖር የተፈጥሮን ውበት እንደሚያመለክቱና፣ የተፈጥሮም ግዴታ የሆኑትን ያህል፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥም የተለያዩ ብሄረሰቦች፣ ጥቁርና ቀይ መልክ ያለው ሰው፣ ረዥምና አጭር ሰው… ወዘተ. መኖር እንደ ውበት መታየት ያለባቸው ነገሮች እንጂ መበላለጥን የሚያረጋግጡ አይደሉም። ስለሆነም ልዩ ልዩ ነገርችና አንድነት(unity in muliplicity) እዚያው በዚያው መኖር የተፈጥሮ ህግጋት መሆናቸውን በመረዳት ልዩነት ለጠብ ምክንያት ሊሆን እንደማይችል እንደመሰረተ ሃሳብ መወሰድ ያለበት መመሪያ ነው። ስለዚህም በአንድ ህብረተስብ ውስጥ የሚከሰቱ ብጥብጦች የተፈጥሮን ውስብስብነትና ውበት ለመረዳት ካለመቻልና ጠለቅ ብሎ ለማየት ካለመፈለግ የተነሳ ወይም በተሳሳተ ዕውቀት በመመራት አንድን ህብረተሰብ ለመግዛት መቻኮል ነው። ለዚሁ ሁሉ መፍትሄው ይላል ፕላቶ፣ ማንኛውም ግለሰብ አርቆ አሳቢነትን በማስቀደም በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ ለመግንባት መጣር አለበት። ማንኛውም ግለሰብ ይህንን የዩኒቨርስ ህግ ሲረዳና ስምምነትንና ስርዓትን(Harmony and Order) በጭንቅላቱ ውስጥ ሲቀርጽ በምድር ላይ ዕውነተኛውን ገነት ይመሰርታል ይላል።

ወደድንም ጠላንም ከብዙ ሺህ ዐመታት ጀምሮ በዓለም ላይ የተከሰቱ የርስ በርስ መተላለቆች፣ በአገሮች መሀከል የተካሄዱ ጦርነቶች፣ ረሀብና የወረርሽኝ በሽታዎች፣ በዘመነ-ሳይንስ እሰካዛሬም ድረስ ዘልቆ ብዙ የሶስተኛውን ዓለም አገሮች የሚያምሰውና፣ የአንድ አገር ህዝብ እየተሰደደ እንዲኖር የሚያደርግ፣ ጊዜ ያመጣላቸው ኃይሎች ድንበር እየጣሱ የሌላውን አገር የሚወሩ፣ እነ ሶክራተስና ፕላቶ ከፈለሰፉት የሰብአዊነት(Rational Humanism) ይልቅ ሳይንሳዊ „አርቆ-አሳቢነትን“(Scientific Rationalism) በማስቀደምና በበላይነት በመመካት ነው። ለምሳሌ ሜስትሮቪክ „The Barbarian Temperament“ በሚለው እጅግ ግሩም መጽሀፉ ውስጥ የሚያረጋግጠው፣ በሃያኛውና በሃያአንደኛው ክፍለ ዘመን የምዕራቡ ዓለም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ቢራቀቀም፣ እንዲሁም ደግሞ የሊበራል ዲሞክራሲን አስፍኛለሁ ቢልም የተወሳሰቡ የጦር መሳሪያዎችን፣ የኬሚካልና የባዮሎጂ መርዞችን በመስራት በሚያስፈልገው ጊዜ ጠላቴ ነው በሚለው ላይ እንደሚበትንና፣ ብዙ ሺህ ህዝቦችን መጨረስ እንደሚችል ነው። ይህ ዐይነቱ ዕልቂት በፋሺዝም ዘመን በጉልህ የታየና የተረጋገጠ ነው። እንደዚህ ዐይነቱ ድርጊት እንደገና ሊከሰት የሚችልበትም ሁኔታ አለ። በኢራቅ ህዝብ ላይ የደረሰው ግፍ፣ በየቀኑ በአፍጋኒስታን ህዝብ ላይ የሚደርሰው ዕልቂት፣ ከአራት ዐመት በፊት ደግሞ አንድን አምባገነን ገዢ አዳክማለሁ ወይም ጥላለሁ ብሎ በዚያውም አሳቦ በሊቢያ ህዝብ ላይ የወረደው የቦንብ ናዳ የምዕራቡን ዕውነተኛ ገጽታ የሚያሳየን ነው። እንደዚሁም ከአራት ዐመት ጀምሮ በውጭ ኃይሎች በተጠነሰሰ ሴራና በገንዘብና በመሳሪያ በመደገፍ በሶሪያ ህዝብ ላይ የደረሰውና የሚደርሰው ዕልቂትና የታሪክ ቅርስ መፈራረስ በዘይት ሀብትና በመሳሪያ እንዲሁም በስልጣን በተመኩና ስልጣንን መባለጊያ ባደረጉ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች አማካይነት ነው። በአሜሪካ የኒዎ-ኮም(Neo-Com) አራማጆችም ሆነ በጠቅላላው የአሜሪካ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሚሊታሪና የኢንተለጀንስ ኤሊት ዘንድ ያለው ስምምነት ዓለምን ለመግዛት ከተፈለገና፣ የሶስተኛው ዓለም አገሮችም በቴክኖሎጂና በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ ህብረተሰብ እንዳይገነቡ ከተፈለገ የተለያዩ ሰበቦችን በመፈለግ እርስ በርሳቸው ማጫረስ ነው የሚል ነው። ይህንንም በገሃድ ይናገራሉ። ከዚህም ስንነሳ ጠቅላላው የአሜሪካ የፖለቲካ ኤሊት ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ቢኖረው ኖሮና፣ ስልጣኔንም ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ የፖለቲካ ስሌቱ የተለየ መሆን ነበረበት። በኢራቅ፣ በሊቢያና በሶሪያ አገሮች አምባገነን አገዛዞች ቢኖሩም፣ የእነዚህን አገዛዞች አስተሳሰብ መቀየርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን የሚቻለው ጥቂት ኃይሎች እንዲያምጹ እነሱን በመርዳት ሳይሆን የፖለቲካ ውይይት እንዲካሄድ በማድረግ ብቻ ነበር። በሌላ አነጋገር መሆን የነበረበት የፖለቲካ ስሌት እነዚህ አምባገነን አገዛዞች የሰለጠነ ፖለቲካ እንዲያራምዱ ማስተማር ነበር። በሌላ ወገን ደግሞ በአንድ ሀብረተሰብ ውስጥ አምባገነናዊ አገዛዝ አለ ከተባለ ከውስጥ በሚደረግ ምሁራዊና ሳይንሳዊ ግፊት ብቻ ነው ሁኔታዎችን መለወጥ የሚቻለው። እንደምናየው የውጭ አገሮች ጣልቃገብነት በሶስቱም አገሮች የነበረውን ሁኔታ የበለጠውን አዘበራረቀው እንጂ መሻሻልን በማምጣት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍን አላደረገም። ስለሆነም በእንደዚህ ዐይነቱ ቅጥ ያጣ የቦምብ ውርጅብኝ እነዚህ አገሮች እንደገና በእግራቸው ሊቆሙ ወደማይችሉብት ሁኔታ ወስጥ መወርወር ቻሉ። ሃምሳና ስድሳ ዐመታት ያህል የሰሯቸው ስራዎች፣ የገነቧቸው ከተማዎችና የመሰረቷቸው ህብረተሰቦች ከፈራረሱና ከተመሰቃቀሉ በኋላ እንደገና እነሱን መልሶ ለመገንባት እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል። የህዝቡም አቅም የሚፈቅድና አስተሳሰቡም የተዳከመ ስለሆነ ህልሙ ከቀን ተቀን ችግር አልፎ ህብረተሰብአዊ ግንባታ ላይ ሊያተኩር አይችልም።፡ በሌላ ወገን ደግሞ የሰለጠንኩኝ ነኝ የሚለውን የምዕራቡን የካፒታሊስት የገዢ መደቦችና ጠቅላላውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖኢና የሚሊታሪ ኤሊት ተንኮል የማይረዱ የሶስተኛው ዓለም አገዛዞችና መንግስታት የማያስፈልግ ቀዳዳ በመስጠት ሁኔታውን ያባብሱታል። የኢራቅ፣ የሊቢያና የሶሪያ አገዛዞቹ ብልሆች ቢሆኑ ኖር ከውስጥ ተቃውሞ ሲነሳ ነገሩ እንዳይባባስ በውይይትና በስምምነት መፍታት በቻሉ ነበር። በፖለቲካ ጥበብ ያልተካኑት እነዚህ መሪዎች ግን ነገሩን ረገብ ለማድረግ ከመሯሯጥ ይልቅ የእልክ ፖለቲካ በመከተላቸው አገራቸው እንዲፈራርስና የብዙ መቶ ሺህ ሰው ህይወት እንዲጠፋ ለማድረግ በቁ። በዚህም የተነሳ አንዳንድ ነፃ አውጭ ነኝ የሚሉ ድርጅቶች የማያስፈልግ እሳት እየጫሩ መጨረሻ ላይ ማቆም የማይቻል እሳት እየሆነ በመምጣት ታሪክን አውዳሚና ህዝብን ጨራሽ ለመሆን በቅቷል።

የዚህ ሁሉ ችግር ዋናው ምንጭ ምንድነው? ቢያንስ ባለፉት 70 ዐመታት የዓለምን ፖለቲካ የሚቆጣጠረው የምዕራቡ ዓለም ስለዲሞክራሲ ይዘትና አመለካከት ያለው አካሄድና ግንዛቤ ለየት ያለ መሆኑን ነው። የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ቢኖራቸውም ዕድገታቸውና ተቀባይነታቸው እንደየአገሮቹ ታሪክ፣ ህብረተሰብ አወቃቀርና የማቴሪያል ሁኔታና እንዲሁም ንቃት-ህሊና የሚወሰን ነው። ዲሞክራሲን ከላይ ወደ ታች ወይም በጠብመንጃ ኃይል የሚተከል ሳይሆን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከንቃተ-ህሊና ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው። ችግሩ ግን የምዕራቡ የካፒታሊስት ዓለም አካሄድ ዲሞክራሲን በየአገሮች ውስጥ ለማስፈን ሳይሆን እንዴት አድርጌ አገሮችን አተረማምሳለሁ የሚል ነው። የዕድገት ሂደታቸውን አዛባለሁ የሚል ነው አካሄዱና የፖለቲካ ስሌቱ። የዚህ ሁሉ ችግር ታላቁ ሺለር እንደሚለን፣ የሰው ልጅ ከአርስቲቶለስ ጀምሮ ዲሞክራሲ የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ ሰምቷል፤ ሆኖም ግን በመሰረቱ ከአረመኔ ባህርዩ አልተላቀቀም። ፍሪድርሽ ሺለር፣ „ታሪክ ማለት ምን ማለት ነው፣ ለምንስ ዓላማ የዓለምን ታሪክ ማጥናት አለብን“ በሚለው እጅግ ግሩም ስራው ውሰጥ የሰውን ልጅ እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ ከመረመርና፣ የግሪክን ስልጣኔና የአውሮፓን የህብረተሰብ ታሪክ ካጠና በኋላ የደረሰበት ድምዳሜ፣ የሰው ልጅ ህብረተሰብአዊ ባህርይ እንዲኖረውና ታሪክን እንዲሰራ ከፈለገ የግዴታ ውጣ ውረድን ማሳለፍና ከፍተኛ የጭንቅላት ስራ መስራት እንዳለበት በጥብቅ ያሳስባል። ይሁንና ግን የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ ሰብአዊነትን ሊጎናፀፍ የሚችለው መንፈሱን ከልቡ ጋር ያገናኘ እንደሆነ ብቻ ነው ይላል። ሺለር እንደዚህ ዐይነቱ ድምደማ ላይ የደረሰው በአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን በአውሮፓ ምድር ውስጥ በፕሮቴስታንትና በካቶሊክ ሃይማኖት መሪዎች የተለኮሰውንና፣ ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ምክንያት የሆነውን ሰላሳ ዐመት ያህል የፈጀውን ጦርነት በሰፊው ከመረመረና፣ የመሪዎችን የተሳሳተ ፖለቲካ በጥልቀት ካጠና በኋላ ነው። በአስራአራተኛው ክፍለ-ዘመንም በጣሊያን ሰፍኖ የነበረውም ሁኔታ የሚያረጋግጠው የአሪስቶክራሲውንና የቀሳውስቱን ቅጥ ያጣ ፖለቲካና፣ ህዝቡም ራሱን በራሱ ማግኘት አቅቶት የሆነ ያልሆነውን የሚሰራበት ወቅት ነበር። አንድ ህዝቡን የሚያግባባ ቋንቋ ባለመኖሩም ለስራና ለሃሳብ ልውውጥ የማያመችና ለስልጣኔ እንቅፋት የሆነበት ወቅት ነበር። በዚህም ምክንያት የተነሳና በገዢ መደቦች ቅጥ ያጣ ኑሮ ህዝቡ በረሃብ፣ በድህነትና በልዩ ልዩ በሽታዎች ይሰቃይና ህይወቱ ይቀሰፍ ነበር። ይህንን በጥብቅ የተከታተለው ዳንቴ በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ህዝቡን የሚያግባባ ቋንቋ ይፈጥራል። ቀጥሎም የአምላኮች ኮሜዲ በመባል የሚታወቀውን ትልቁን የሌትሬቸር ስራ በመጻፍ፣ አንድ ህዝብ እንዴት አድርጎ ከጨለማ ኑሮው ተላቆ የብርሃኑን ዓለም እንደሚጎናጸፍ ያመለክታል። ዳንቴ በዚህ ስራው ለተከታዩ ትውልድ መነሻ የሚሆን ትልቅ ስራ ሰርቶ ያልፋል። በመሆኑም ሬናሳንስ የሚባለው የግሪኩን ዕውቀት እንደገና ማግኘትና ከጊዜው ሁኔታ ጋር ማቀናጀት የተጀመረው እነዳንቴ በቀደዱት የብርሃን መንገድ አማካይነት ነው ማለት ይቻላል። ይህም ማለት ጭንቅላትን ለማደስና፣ ከኋላ ቀር አስተሳሰቦች ለመላቀቅ፣ ፍልስፍናን፣ ሳይንስን፣ ጥበብን፣ ግጥምንና አርክቴክቸርን የጭንቅላት ተሃድሶ መመሪያ ማድረግ ለአንድ ህዝብ ስልጣኔን መስራትና ተስማምቶ መኖር አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር የዳንቴ ስራዎችና በሬናሳንስ ዘመን ተግባራዊ የሆነው ስልጣኔ ያረጋግጣል። ስለዚህም አንድ ግለሰብም ሆነ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለውና፣ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስም ተፈጥሮን በመቆጣጠር፣ ተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ለራሱ መጠቀሚያ በማድረግ ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊሽጋገር የሚችለው፣ የሬናሳንስ ወይም የግሪኩን ፍልስፍናና፣ በኋላ ደግሞ የጀርመን አይዲያሊስቶች፣ማለትም ሺለር፣ ጎተ፣ኸርደር፣ ዊንክልማንና፣ በተጨማሪም ላይብኒዝና ካንት ያዳበሩትን ፍልስፍናና የሳይንስ መሰረት መመሪያ ማድረግ የተቻለ እንደሆን ብቻ ነው።

ከዚህ ስንነሳ ማቅረብ ያለብን ጥያቄ፣ በተለይም አገርን አስተዳድራለሁ የሚል አንድ መሪ ወይም አገዛዝ እንዴት አድርጎ ነው ጭንቅላቱን በአዲስ ዕውቀት በማነፅ ህብረተሰብአዊ ስምምነትና ስርዓት እንዲፈጠር የሚያደርገው? እንዴትስ አድርጎ ነው ቆንጆ አስተሳሰብን ከጭንቅላቱ ጋር በማዋሃድ የራሱን ጥቅም ሳያስቀድምና አድልዎን የፖለቲካ ዘይቤው ሳያደርግ፣ እንዲሁም ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም ሰለባ ሳይሆን አገር ማስተዳደር የሚችለው? እንዴትስ ለስልጣኔና ለቆንጆ ስራዎች ታጥቆ ሊነሳ ይችላል? የሚሉትን ጥያቄዎች በዝርዝር እንመልከት።

በብዙዎቻችን ዕምነት ትምህርት ቤት የተማረና ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ኢኮኖሚክስም ሆነ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት አጠናቆ በማስትሬት ወይም በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀ አገርን በስነስርዓት ማስተዳደርና፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በማድረግ ሚዛናዊ ዕድገት በማምጣት በስልጣኔ እንድትታወቅና ህዝቦቿም በደስታና በስምምነት እንዲኖሩ ሊያደርግ የሚችል ይመስለን ይሆናል። የሶክራተስን፣ የፕላቶንና፣ እንዲሁም በኋላ የተነሱትን፣ ሃይማኖትን ከፍልስፍና ጋር በማጣመር በአውሮፓ ምድር ስልጣኔ እንደገና እንዲያንሰራራ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉትን የታላላቅ ቀሳውስት ስራዎች ስንመለከት፣ እንዲሁም ከአስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን በኋላ ብቅ ብቅ ያሉትን ሳይንቲስቶችንና ለሰው ልጅ ያስተላለፉትን ዕውቀት ስንመረምር፣ በግጥምና በቲያትር እንዲሁም የፖለቲካ ተዋንያንን አእምሮ በፍልስፍና ለመቅረጽ የታገሉትን እንደ ሺለር፣ ላይብኒዝና ካንት እንዲሁም ጎተን ስራዎች ስንመለከት እኛ ትምህርት ቤት ገብተን የተማርነው ትምህርት፣ ከነዚህ ጠቢባን ጋር በፍጹም የሚጣጣሙ አይደሉም። ከነዚህ የፍልስፍና ምሁራንና ሳይንቲስቶች ጽሁፎች መገንዘብና መማር የምንችለው በአንድ አገር ውስጥ ስልጣኔ ማምጣት ከተፈለገና ህዝቡም በስምምነት እንዲኖር ከተፈለገ የግዴታ የማያቋርጥ ትግል ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ነው። ስለዚህም ልክ እንደ ግሪክ ፈላስፋዎች ኋላ ላይ ብቅ ያሉት የአውሮፓ ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች ለሌላ ነገር ሳይሆን ለአዕምሮና መንፈስ ከፍተኛ ቦታ በመስጠት ምርምራቸውን አካሄዱ።

በአጠቃላይ ሲታይ የሰው ልጅ አዕምሮ/መንፈስ ጥሩ ወይም መጥፎ አስተሳሰብ ይዞ ሊቀረጽ ይችላል። ጥሩ አስተዳደግ ካለውና አዕምሮው በጥሩ ዕውቀት የተገነባ ከሆነ ሰብአዊ ባህርይ ሊኖረውና ታሪክንም ሊሰራ ይችላል። በአንፃሩ ደግሞ አንድ ሰው በልጅነቱ በጥሩ ሁኔታ ካልተያዘና ጭንቅላቱ በጥሩ ዕውቀት ካልተገራ ሃሳቡና ተግባሩ ተንኮልን ማውጠንጠንና የታሪክን ሂደት ማጣመም ይሆናል። ይሁንና ግን አንድ ሰው ራሱን በራሱ ለማግኘት ከፈለገ ጭንቅላቱ በጥሩ ዕውቀት የተገራውም ሆነ የተዛባ አስተሳሰብ ያዳበረው በየጊዜው የጭንቅላት ጂምናስቲክ መስራት አለባቸው። የሰው ልጅ አስተሳሰብ የሚለዋወጥ በመሆኑ አርቆ አሳቢ የሆነውም ቢሆን አልፎ አልፎ ኢራሽናል ስለሚሆን ወደ መጥፎ ተግባር እንዳያመራ ከፈለገ ሰውነቱ ጂምናስቲክ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ጭንቅላቱም በስራ መወጠር አለበት። ስለዚህም አንድ ግለሰብም ሆነ የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ታሪክን ይሰሩ ዘንድ ራሳቸውን ከጥሩ ነገር ጋር ማገናኘት መቻል አለባቸው። ከአንድ አካባቢ የሚመጡ ግፊቶችን ለመቋቋም የሚችሉና በክርክር ለማሳመንና ቆንጆ ቆንጆ ነገሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ የማያቋርጥ ትግል ማድረግ አለባቸው። ለዚህም ደግሞ በተከታታይ ደቀ-መዝሙራንን ማስለጠን በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የተለመደ አሰራር ነበር። እንደኛ አገር ያለው ጋ ስንመጣ ተከታታይነት ያለው ሃሳብ ማዳበር ያለመቻልና ደቀ-መዝሙሮችንም አለማሰልጠንና ዝግጁም አለመሆን ነው። ከዚህ ስንነሳ በዛሬው የግሎባል ካፒታሊዝም ዘመን አንድ ሰው ቀና አስተሳሰብ ቢኖረውምና ለስልጣኔ የቆመ ቢሆንም ባለው የላላና የሳሳ ምሁራዊ ኃይል ምክንያት ከውጭ የሚመጣውን ግፊት ሊቋቋም የማይችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። በአካባቢውም ተንሸራታች ኃይሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሳይወድ በግድ ስልጣኔን የሚቀናቀነውን ሬል ፖለቲካ የሚባለውን እንዲቀበልና እንዲያራምድ ይገደዳል። ይህም ማለት ዕውነተኛ ዕውቀትና ሀቀኝነት በራሳቸው የሚበቁ መመዘኛዎች አይደሉም። ከውጭ የሚመጣውን ግፊት ለመቋቋም ዋናው መፍትሄ በራስ መተማመንና ለውጭ ኃይል መግቢያ ቀዳዳ አለመስጠት ነው። ስልጣንን የሚይዙ ኃይሎች የሚሰሩትን የሚያውቁና ለአንድ ዓላማ የተሰለፉና በአንድ ራዕይ የሚመሩ መሆን አለባቸው። ከዚህ በሻገር በአገር ውስጥ በተለያየ ዘርፍ ሊንቀሳቀስ የሚችል ሰፋ ያለ ምሁራዊ ኃይል እንዲሰለጥን አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ትችታዊ አመለካከት በዳበረበት አገርና፣ ምሁሩም ለውጭ ኃይል ሳይሆን ለአገሩ ህዝብ ብቻ ጥብቅና የቆመ መሆኑን በሚያረጋግጥበት አገርና ህዝቡንም የሚያስተምር ከሆነ የውጭ ኃይሎች እንደፈለጋቸው እየገቡ ሊያሳስቱና በአገዛዛዙ ላይ ግፊት ሊያደርጉ አይችሉም።

በሌላ ወገን ግን ዛሬ በሁላችንም ዘንድ ያለው ትልቁ ችግር ሁላችንን ሊያስማማንና እንደመመሪያ ሊሆነን የሚችል ፍልስፍናና ራዕይ አለመኖሩ ነው። የፖለቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትም ሆነ ለመጽሄትም ሆነ ለድህረ-ገጾች በየጊዜው በተለያዩ አርዕስቶች ላይ የሚጽፉ ምሁራን እንደፈለጋቸው የሚጽፉ እንጂ ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ መለኪያን እንደመመርኮዢያ በማድረግ አይደለም ሃሳባቸውን ለመግለጽ የሚሞክሩት። ስለሆነም በየጊዜው የሚቀርቡት ጽሁፎች ከምን ተነስተው እንደሚጻፉ አይታወቅም። አቀራረቦችም በጣም ተደጋጋሚ ከመሆናቸው የተነሳ በአገራችን ምድር ያለውን የህዝባችንን የቀን ተቀን ኑሮ የሚዳስሱና የችግሮችንንም ዋና ምክንያቶች እንድንረዳና መፍትሄም እንድንፈልግ የሚጋብዙን አይደሉም። ሁሉም የፈለገውን የሚጽፍ ከሆነና ራሱን እንደመለኪያ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ ደግሞ ይህ ዐይነቱ አካሄድ ሶፊስታዊ ነው የሚሆነው። ስለዚህም ነው ሶክረተስና ፕላቶ እንደዚህ ዐይነቱን አመለካከትና አካሄድ አጥብቀው የታገሉት። ምክንያቱም እያንዳንዱ ምሁር ራሱን እንደዋና መለኪያ የሚቆጥርና፣ ከሌላውም የተለየ መሆኑን ለማረጋግጥ የሚጥር ከሆነ አንድን ህዝብም ሆነ ታዳጊ ወጣት ሃሳቡን ሊሰበስብለትና እንደመመሪያም አድርጎ ሊወስደው የሚችለው ሳይንሳዊ ፈለግ አይኖረውም ማለት ነው። ስለሆነም ለአንድ አገርና ህዝብ እታገላለሁ የሚል ምሁር ኃላፊነቱ ተጨባጩን ሁኔታ በጥልቀትም ሆነ በስፋት መረዳት ብቻ ሳይሆን ችግሩ ሊቀረፍ የሚችልበትን ዘዴ መጠቆም ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ የሚመራበት ግልጽ ፍልስፍናና ሳይንሳዊ የአሰራር ዘዴ እንዲኖረው ያስፈልጋል። እኔ እስከማውቀው ድረስም በአውሮፓ የህብረተሰብ ትግል ታሪክ ውስጥ እያንዳንዱ ምሁር፣ ምሁር ነኝ ብሎ ዝም ብሎ ይታገል የነበረ ሳይሆን በምን ዐይነት ፍልስፍናና ነው በጊዜው የነበረውን ችግር መረዳትና መፍትሄስ ማግኘት የሚቻለው ብሎ ነበር ራሱን ያስጭንቅ የነበረው። በዚህም ምክንያት ነው በአውሮፓ ምድር ውስጥ ፍልስፍናዊ አመለካከት ስር ሊሰድ የቻለውና፣ አገሮችም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የተወሳሰበ፣ የጠራና ግልጽ የሆነ ህብረተሰብ መገንባት የቻሉት።

ሌላው በአገራችንም ሆነ ውጭ አገር በኢትዮጵያዊ ኮሙኒቲ ዘንድ ያለው ትልቁ ችግር አካዳሚክ ዕውቀትን ሰፋ ካለው ምሁራዊ ዕውቅት ነጥሎ ለማየት አለመቻል ነው። ሁሉም ሰው ትምህርትን ለመቅሰም የሚያስችለው ውስጣዊ ኢንተለጀንስ ቢኖረውም፣ ምሁራዊነትንና(Intellectualism)ሎጂካዊ አስተሳሰብን ሊጎናጸፍ የሚችለው ስርዓት ያለው ጥናት(systematic reading)ሲያካሂድና፣ በምድር ላይ የሚታየውን ነገር ለመረዳት ራሱን ሲያስጨንቅ ነው። ለዚህ ነው አብዛኛውን ጊዜ በንጹህ አካዳሚ ትምህርት የሰለጠኑ ሰዎች በምድር ላይ ያለውን ነገር በሚገባ ማንበብ የማይችሉትና የችግሩንም ዋና ምንጭ ለመረዳት የሚያስችል መሳሪያ የማይኖራቸው። ስለሆነም አንድ ሰው በትምህርት ጎበዝ ቢሆን እንኳ የስልጣኔ ትርጉምን እስካልተረዳ ድረስና፣ ለስልጣኔና ለእኩልነትም ሽንጡን ገትሮ ሊታገል እስካልቻለ ድረስ ለህብረተሰብ ግንባታ የሚያደርገው አስትዋፅዖ ከቁጥር ውስጥ የሚገባ አይሆንም። አንድ ወጥ አስተሳሰብ ይዞ ያደገ በመሆኑም የአንድን ነገር ሂደት ከሁሉም አቅጣጫ የመመርመርና የማመዛዘን ኃይል ሊኖረው በፍጹም አይችልም። እንደዚህ ዐይነቱ ሰው ከራሱ ጥቅም ተሻግሮ የዕውነት ጠበቃ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ስለሆነም አንድ ሰው በዚህ ወይም በዚያኛው ርዕዮተ-ዓለም እመራለሁ ቢልም እንኳ ይህ ማለት ግን ቀናና ጥሩ ሰው፣ ወይም ደግሞ ምሁራዊ ኃይል ያለውና ከተንኮል የጸዳ ነው ማለት አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ ርዕዮተ-ዓለም ሽፋን እንጂ የአንድን ሰው ምንነት መግልጫ አይደለም። አንድ ሰው ማርክሲስት ነኝ ወይም ሊበራል ነኝ ወይም ደግሞ ይህንኛውን ወይም ያኛውን የፖለቲካ ዕምነትና ሃይማኖት እከተላለሁ ቢልም እነዚህ ሽፋኖች ድብቅ ዓላማውን የሚገልጹ ወይም ማንነቱን የሚያሳዩ አይደሉም። ወይም አንድ ሰው ሊበራል ነኝ ስላለ የተቀደሰ ዓላማ፣ ማርክሲስት ነኝ የሚለው ደግሞ የሰይጣን ዓላማ አለው ማለት አይደለም። እነዚህ ዐይነቱ ግለሰቦች በተናጠልም ሆነ በፓርቲ ደረጃ ተደራጅተው ለዚህ ወይም ለዚያኛው ርዕዮተ-ዓለም እንታገላለን ቢሉም የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ የሚታገሉባቸው መሳሪያዎች እንጂ በራሳቸው ዕውነተኛ ስልጣኔ አጎናጻፊ አይደሉም። እንዲያውም የዕውነተኛውን የስልጣኔ መንገድ የሚያደናቅፉና ወደ ሌላ ውዝግብ ውስጥ የሚከቱን ናቸው። ዛሬ በንጹህ የካፒታሊዝም ሊበራል ስርዓት ውስጥ እያለን እንኳ ዓለም ወደ ሰላም እያመራች አይደለችም፤ እንደምናየው የዓለም ህዝብም ብልጽግናን እያየ አይደለም። ጦርነትና ድህነት በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ የሀብት ዘረፋና በጥቂት ሰዎች እጅ የሀብት ክምችት የሰው ልጅ እጣ ሆነዋል። በየአገሮችም ውስጥ ህብረተሰብአዊ ውዝግብ የመከሰቱ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ የየመንግስታቱ ሚና ጦርነትን ዓለም አቀፋዊ ማድረግና ህዝብን ማሳሳትና አትኩሮውን ወደ ውጭ ማድረግ ነው።

እዚህ ላይ መቅረብ ያለበት ጥያቄ የምዕራቡ ካፒታሊዝም በአሸናፊነት ከወጣ በኋላ ለምንድነው አሁንም ቢሆን የሰው ልጅ ዕጣ ጦርነትና መፈናቀል፣ እንዲሁም መበዝበዝ የሆነው? ካፒታሊዝም ከፊዩዳሊዝም ጋር ሲወዳደር ተራማጅ ስርዓት ቢሆንምና የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምጥቀት ቢታይበትም፣ ከ17ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ቀስ በቀስ እያለ የበላይነትን እየተቀዳጀ የመጣው ኢምፔሪሲስታዊ ወይም ሶፊስታዊ አስተሳሰብ የየመንግስታቱ መመሪያ ሆነ። በመሆኑም ከ13ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ሰብአዊነትን ሙሉ በሙሉ ለማስፈን የተደረገውን ትግልና አስተሳሰብ በመደምሰስ በነፃ ገበያ ስም የሚመራን፣ የአንድን ህዝብ አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ወደ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ የሚቀይር ርዕዮተ-ዓለም በማዳበርና በማስፋፋት ካፒታሊዝም የበላይነትን ተቀዳጀ። የሰው ልጅም ኑሮ ንጹህ በንጹህ ኢኮኖሚያዊ ነው የሚለውን በማስፋፋት፣ የኑሮው ፍልስፍናም ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ሞራላዊና ስነ-ምግባራዊ እንዳይሆን ለማድረግ በቃ። በዚህ ምክንያት በሰብአዊነት ፈንታ የብዝበዛ ስርዓት ሊፈጠር ቻለ። ይህ ሁኔታ ከሰላሳኛው ዐመት ጦርነት በኋላ በ1648 ዓ.ም በዌስት ፋልያ ላይ የየአገሮችን ነፃነት የሚያውቅ ስምምነት ሲደረስበትና ተቀባይነትን ሲያገኝ፣ በብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ውስጥ የብሄረተኝነት ስሜት ማየል ጀመረ። ከውስጥ የአገርን ኢኮኖሚ በሰፊ መሰረት መገንባትና ወደ ውጭ ደግሞ ያላደጉ አገሮችን የጥሬ ሃብት አምራች አገሮችና አቅራቢዎች የሚሆኑበትን ሁኔታ ታለመ። በተለያዩ አውሮፓ አገሮች መሀከል እሽቅድምደም በመጀመር የሶስተኛው ዓለም አገሮች በካፒታሊዝም ሎጂክ ውስጥ ሊገቡና እጣቸውም በዚያው የሚወሰን እንዲሆን ተደረገ።

ከዚህ አጭር ትንተናና በመነሳት ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በአሽናፊነት የወጣውንና እየተወሳሰበ የመጣውን ካፒታሊዝም በተለይም በአፍሪካ አህጉር ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖና እስካሁን ድረስም አላላቅቅ ያለንን የጭቆና፣ የብዝበዛና እንዲሁም የምስቅልቅል ሁኔታ የፈጠረብንን ስርዓት ጠጋ ብለን እንመልከት። ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ካፒታሊዝም የበላይነትን እየተቀዳጀ ሲመጣ የስልጣኔው ፕሮጀክት እየተደመሰሰና የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ፣ በተለይም የአፍሪካ ሁኔታ እየተበላሽና እየተዘበራረቀ ይመጣል። የካፒታሊዝም ተልዕኮ በዓለምአቀፍ ደረጃ ስልጣኔን ማስፋፋት ሳይሆን በጉልበት ላይና በስግብግብነት እንዲሁም በማጭበርበር ላይ በመመርኮዝ በተለይም የአፍሪካን አህጉር ንጹህ የጥሬ ሀብት አምራችና አቅራቢ ማድረግ ነበር ዋናው ፕሮጀክቱ። በመጀመሪያ በ15ኛው ክፍለ-ዘመን የባርያን ንግድ ማስፋፋት፣ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ደግሞ የቅኝ ግዛት አስተዳደር በመመስረት ከውስጥ ቀስ በቀስ እያለ የሚያድግ ስርዓት እንዳይፈጠር ሁኔታውን ያዘባራርቃል። በተለይም በቅኝ ግዛት ዘመን የተቋቋሙት አስተዳደሮች ከቅኝ ገዢዎች አገሮች ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ወደ ውስጥ የስራ ክፍፍል እንዳይዳብርና የውስጥ ገበያም እንዳይስፋፋ እንቅፋት ይፈጥራል። ወደ ቅኝ ግዛትነት የተለወጡ አገሮችም የተወሰኑ የጥሬ-ሀብትና የእርሻ ምርት ማውጣትና ማምረት፣ እንዲሁም ውጤቱንም ወደ ውጭ መላክ ስለነበረባቸው በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የስራ ክፍፍል በማዳበር ወደ ውስጥ ሰፋ ያለ ገበያ ለመገንባት እንዳይችሉ ታገዱ። ይህ ሁኔታ በራሱ መንደሮችን፣ ትናንሽና ትላልቅ ከተማዎችን በስነስርዓት በመገንባት ወደ ህብረተሰብ እንዳይለወጡ እንቅፋት ሆነባቸው። የተተከሉትም የባቡር ሃዲዶች የጥሬ-ሀብት የሚወጣባቸውን ቦታዎች ከወደብ ጋር ማገናኘት ሰለነበር ወደ ውስጥ ህዝቡን የሚያስተሳስር የመመላለሻ መንገድና የባቡር ሃዲድ እንዳይሰራ ታገደ። በዚህም ምክንያት ህብረተሰብዊ ውህደት እንዳይፈጠር መሰረት በመጣል፣ በአንድ አገር ውስጥ ጎሳዎች በጎሳ ደረጃ ሊደራጁ የሚችሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታና፣ ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ እንቅፋት የሆነን እንደ ስርዓት ሊቆጠር የማይችል ሁኔታን በመፍጠር የሰዎች አትኩሮ ጠባብ እንዲሆን ለማድረግ በቃ።

ከፖለቲካ ነፃነት „መቀዳጀት“ ከ50ኛዎቹ ዐመታት መጨረሻና ከ60ሳዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ የብዙ አፍሪካ አገሮች ዕድል በሌላና በረቀቀ መልክ ህብረተሰብአዊ ዝብርቅርቅነት የሚኖርበትና ብዝበዛው የሚቀጥልበት ሁኔታ በመፍጠር በየጊዜው የሚነሱ አገዛዞች አስተሳሰብ በትናንሽ ነገሮች እንዲጠመዱ ተገደዱ። አስተሳሰባቸው ብሄራዊ አጀንዳ እንዳይኖረው ተቆለፈ። የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውና ወደ ህብረ-ብሄር ግንባታ እንሸጋገራለን ያሉትን ደግሞ በመንግስት ግልበጣ አማካይነት በመጣል የአገዛዝ አለመረጋጋትና አለመተማመን ሊፈጠር ቻለ። ስልጣን ላይ የሚወጣው መሪ ከዚህ ወይም ከዚያኛው የምዕራብ አገር መንግስታት ጋር በማበርና ታዛዥ በመሆን አገሩን ሊገነባ እንዳይችል ተደረገ። በዚህ ላይ ደግሞ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠሩት ኢንስቲቱሽኖችና፣ በአዲስ መልክ የተከሰተው የኃይል አሰላለፍ የብዙ አፍሪካ አገሮችን የወደፊት ዕድል የሚወስኑ ነበሩ። ከ1945 ዓ.ም በኋላ ሁለት ዐይነት የኃይል አሰላለፎች ቢከሰቱም፣ በመሰረቱ ግን በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የሚመራው የካፒታሊስቱ ጎራ ነበር/ነውም ዓለምአቀፍ ኢንስቲቱሹኖችን በመቆጣጠር የአብዛኛዎቹን የሶስተኛው ዓለም አገሮችን፣ በተለይም ደግሞ የአፍሪካን ህዝብ ዕድል ይወስን የነበረውና ዛሬም የሚወስነው። በዚህ ላይ ደግሞ ዶላር ዋናው ዓለምአቀፋዊ የንግድ መገበያያና የሀብት ማከማቻ ገንዝብ በመሆኑ አብዛኛዎቹ አገሮች የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት ሲሉ የግዴታ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸውን በተወሰነ መስክ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ተገደዱ። በዚህም ምክንያት የአገር ውስጥ ገበያን ማዳበር ባለመቻላቸው በገንዘብና በምርት፣ እንዲሁም በገንዘብ አማካይነት የሚካሄደው የንግድ ልውውጥ ውስን በመሆኑ፣ የየአገሮቹ የገንዘብ ኃይል ሊዳከም በቃ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ተወዳዳሪ ሊሆንና ተቀባይነትም ሊያገኝ የማይችል ሆነ። በሌላ አነጋገር፣ የአንድ አገር የገንዘብ ጥንካሬ ሊወሰን የሚችለው ወደ ውስጥ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ ሲዳብርና፣ በየኢኮኖሚ መስኮችም መሀከል የንግድ ልውውጥ ሲኖርና፣ በዚህም አማካይነት በኢኮኖሚው ውስጥ የሚሽከረከረው ገንዘብ ፍጥነቱ ሲጨምር ነው። ከዚህም በላይ አንድ አገር ገንዘቧ ጠንካራና ዓለምአቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው ከተፈለገ ወደ ውጭ የምትልከው ምርት በፋብሪካ የተፈበረከና ያለቀለት ምርት መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር፣ አንድ አገር ለዓለም ገበያ የምታቀርበው ምርት የእርሻ ምርት ውጤት ወይም ያልተፈበረከ የጥሬ ሀብት ብቻ ከሆነ ገንዘቧ ደካማ ይሆናል፤ ተቀባይነትም አያገኝም። ከዚህ አጭር ትንተና ስንነሳ የካፒታሊዝም ውስጣዊ ሎጂክና እንቅስቃሴን መገንዘቡ ከባድ አይሆንም። ወደ ሌሎች ነገሮችም ስንመጣ አካሄዱ ለየት ያለ ቢመስልም ዋናው ባህርዩ ግን የበላይነትን(Dominanz) መቀዳጀት ነው። ይህም ማለት እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ኢትዮጵያንም ጨምሮ እንደ ነፃ አገር መታየት የለባቸውም። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠንካርና በራሱ የሚተማመን ህብረተሰብ መገንባት የለባቸውም። ይህ ዐይነቱ አካሄድ ወደ ውስጥ ህብረተሰብአዊ ስምምነትና ውህደትን ስለሚያመቻችና ብሄራዊ ስሜትን ስለሚያጠናክር የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠርና ግፊት በማድረግ የየመንግስታቱ አጀንዳ አትኮሮአቸው በትናንሽ ነገር ላይ መጠመድ አለበት። እንዲያም ሲል ወደ ጦርነት እንዲያመራ ይደረጋል።

በተለይም ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት መፈጸሚያ በኋላ ሙሉ በሙሉ በአሽናፊነት የወጣው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተልዕኮው ህብረተሰቦችን ማዘበራረቅና፣ በህብረተሰቦች ውስጥ ግጭት እንዲፈጠር ሁኔታውን ማመቻቸት ሆነ ተግባሩ። ለዚህ ደግሞ የትምህርት መስኩ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል። የአንድን ሰው አእምሮ ስትቆጣጠረውና በገንዘብ ስትገዛው የህብረተሰቡንም አቅጣጫ ታዛንፋለህ። የስልጣኔውን መንገድ ሁሉ ታጨልምበታለህ። አብዛኛው ህዝብ የማሰብ ኃይሉ ሲዳከም በቀላሉ ወደ ባርነት ይለወጣል፤ በራሱ ላይ ዕምነት አይኖረውም። የዓለም ገበያና የዓለም ንግድ እንዲሁም ለዚህ እንዲያመች ተብሎ የረቀቀው የኢኮኖሚክስ ትምህርት ዋናው ዓላማቸው የብዙ አፍሪካ ህዝቦችን ዕድል በዚህ ዐይነት የካፒታሊስት ሎጂክ ውስጥ እንዲሽከረከሩ በማድረግ ለዝንተዓለም ባርያ አድርጎ ማስቀረት ነው። ለምሳሌ ለትምህርት ቤትና ለዩኒቨርሲቲ ተብሎ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተዘጋጀውን የኢኮኖሚክስ መማሪያ መጽሀፎችን ለተመለከተ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ተቀባይነት ያገኘ(Conventionalism or normative positivism) የመማሪያ መጽሀፍ በራሱ አርቀን እንዳናስብና የዕውነተኛውን ስልጣኔን ትርጉም እንዳንረዳ ሊያደርገን የቻለ ነው። ዕድገትንና ስልጣኔን ከህብረተሰብ አወቃቀርና ከታሪክ አንፃር፣ እንዲሁም የተለያዩ አገሮችን ልምድ መሰረት አድርጎ እንደመነሻና እንደመማሪያ ከመወሰድ ይልቅ፣ ርዕዮተ-ዓለምንና የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል ጥቅሞችን የሚያንፀባርቅ ትምህርት በመማር የታሪክ ወንጀል ተሰራ፤ እየተሰራም ነው። የሳይንስና የቴክኖሎጂን ዕድገት ስንመለከት ግን ንፁህ የምርምርና የጭንቅላት ውጤት መሆናቸውን መገንዘብ እንችላለን። ኢኮኖሚክስ ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው ከፊዚክስ፣ ከኬሚስትሪና ከባዮሎጂ ጋር ሲያያዝ ብቻ ነው። ይህንን መሰረተ-ሃሳብ ያላካተተ የኢኮኖሚክስ ትምህርት የመጨረሻ መጨረሻ አገሮችን መቀመቅ ውስጥ ነው የሚከታቸው። ለምሳሌ በኢኮኖሚክስ ታሪክ ውስጥ መርካንትሊዝም፣ ፊዚዮክራሲ፣ በእነ አዳም ስሚዝና ፔቲ ኢንዲሁም ሪካርዶ የሚወከለው ክላሲካል ኢኮኖሚክስ፣ ይህንን እያረመ ወይም እያስተካከለ የወጣው የማርክሲስት ኢኮኖሚክስ፣ ከዚያ በኋላ ማርክሲዝምን በመቃወም የወጣው የማርጂናሊስት ወይም የኒዎ-ክላሲክል፣ ዛሬ ደግሞ ኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክስ ተብሎ የሚታወቀው፣ በእነ ሹምፔተር የሚወከለው ኢቮሉሺናሪ ኢኮኖሚክስ፣ በቬብለን ቶርስታይን የሚወከለው የኢንስቲቱሽን ኢኮኖሚክስ፣ ብዙ የምዕራብ አውሮፓ ኢኮኖሚዎች የተገነቡበት፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ፊዚካል ኢኮኖሚክስ እየተባለ የሚታወቀው በጣም ጠቃሚ ዕውቀት፣ እነዚህ ሁሉ የኢኮኖሚክስ ዘርፎች ናቸው። ተማሪው ይህንን ሁሉ እንዳያውቅና፣ በተለይም ምዕራብ አውሮፓ የአደገበትን ምስጢር እንዳይገነዘብ በሃያኛው ክፍል-ዘመን በእነሳሙኤልሰንና በሌሎች የተደረሱት እንደ መመሪያ በመውሰድና እነሱን በመሸምደድ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአፍሪካ ምሁራን ሊሳሳቱና ለየአገራቾቻው መቆርቆዝና ድህነት እንደ ዋና ምክንያት ሊሆኑ በቅተዋል። ዛሬ በአፍሪካ ውስጥ ለሚታየው መዝረክረክና ድህነት ዋናው ምክንያት ፖሊሲ አውጭዎቹ ሳይሆኑ በመሰረቱ በርዕዮተ-ዓለም ላይ የተመሰረተው ለምዕራቡ የካፒታሊስት ዓለም የሚያመቸው የኢኮኖሚክስ ትምህርት እንደመመሪያ በመወሰዱ ነው። ከዚህም በላይ በየአገሮቹ የሰፈነው መንግስታዊ አወቃቀርና የፖለቲካ ኤሊት ለዕድገትና ለስልጣኔ ሽንጡን ገትሮ እንዳይታገል በመኮላሸቱ በቀላሉ የዕድገትን ፈለግ ማጣመም ተቻለ። ኒዎ-ሊበራሎች የበላይነትን በመቀዳጀት ከዩኒቨርሲቲ አልፈው ኢንስቲቱሽኖችን ሁሉ በመቆጣጠር አብዛኛው ተማሪ ዐይኑን እንዳይከፍትና፣ የዕውነተኛ ዕድገትንና ስልጣኔን ትርጉም እንዳይረዳ ሊደረግ በቃ። ለዚህም ነው ሶክራተስ፣ ፕላቶና የእነሱን ፈለግ ይዘው የተነሱት ምሁራን ተቀባይነት ያገኘን ዕውቀት መሳይ ነገር አጥብቀው የታገሉት። ምክንያቱም ተቀባይነት ያገኘ ነገር ሁሉ ካለንበት ቦታ ርቀን እንዳንሄድ ያደርገናል። በማሰብ ኃይልና በኮመን ሴንስ ልንፈታ የምንችላቸውን ችግሮች እንዳንፈታ መንገዱን ሁሉ ይዘጋብናልና።

ዛሬ አገራችንና የሌሎች አፍሪካ አገሮችን ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳትና ምክንያቱንም ለመገንዘብ የምንፈልግ ከሆነ ከሞላ ጎደል የላይኛውን ትንተና ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለብን ይመስለኛል። ሌላው ችግራችን ደግሞ የኛንም ሆነ የሌሎች አፍሪካ አገሮችን የተወሳሰበ ችግር ለመረዳት በሚሞከርበት ጊዜ አውሮፓውያን እስከ አስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተጓዙበትን የምሁር ውይይትና ክርክር እንደልምድና ትምህርት አድርገን ለመውሰድ አንቃጣም። ያም ሆነ ይህ በአውሮፓ የህብረተሰህብ አወቃቀርና በአፍሪካ አገሮች የህብረተሰብ ሂደት መሀከል ያለውን ልዩነት ትንሽም ቢሆን ጠጋ ብለን እንመልከት። ይህ ዐይነቱ ግምገማ ከሞላ ጎደል ዛሬ ብዙ አፍሪካ አገሮች ለምን በዚህ ዐይነቱ የተመሰቃቀለና ደካማ የሆነ የኢኮኖሚ ክንዋኔ ውስጥ ለመገኘት እንደተገደዱ የተወሰነ ግንዛቤ ሊሰጥን የሚችል ይመስለኛል። አንደኛ፣ የብዙ አፍሪካ አገሮች ህብረተሰብ አወቃቀር ከብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ጋር ሲነፃፀር ይለያል። አበዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በፊዩዳሊዝም ስርዓት ያላለፉ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አወሮፓው ህብረተሰብ የርዕዮተ-ዓለም ግጭት አልተካሄደባቸውም። ሁለተኛ፣ ብዙ የአፍሪካ ህብረተሰቦች ከሌላው ዓለም ጋር የነበራቸው በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት እጅግ የላላ ነበር። ለምሳሌ የግሪክ ስልጣኔ በአረቦችና በአይሁዲዎች አማካይነት ከግሪክ ቋንቋ ወደ ላቲን እየተተረጎመ ወደ አውሮፓ ሲገባና ሲስፋፋ፣ ብዙ አፍሪካ አገሮች ይህ ዕድል አላጋጠማቸውም። ሶሰተኛ፣ የብዙ ምዕራብ አውሮፓ የህብረተሰብ አወቃቀር በሩቅ ንግድ አማካይነት ሲበለጽግና ውስጠ-ኃይል በማግኘት ወደ ተሻለ የህብረተሰብ አወቃቃር ሲሸጋገር፣ አብዛኛዎቹ አፍሪካ አገሮች ይህ ዐይነቱ ዕድል አላጋጠማቸውም። አራተኛ፣ በአስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን በባርያ ንግድና፣ በአስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ደግሞ በቅኝ አገዛዝ አማካይነት ህብረተሰብአዊ አወቃቀራቸው ይበላሻል። በማበብ ላይ የነበረው የስራ ክፍፍል ይኮላሻል። አብዛኛዎቹ አፍሪካ አገሮች ለምዕራብ አውሮፓ ጥሬ-ሀብት አቅራቢ ብቻ እንዲሆኑ ይፈረድባቸዋል። ለዚህም የየመንግስታቱ አወቃቀር ወደ ውስጥ ዕድገትንና ስልጣኔን እንዳያመጣ ሆኖ ይዘጋጃል። አምስተኛ፣ ከቅኝ አገዛዝ መላቀቅ በኋላ በዓለም አቀፍ ላይ አዲስ የተፈጠረው የኃይል አሰላለፍ የአፍሪካን ዕድገት የሚጻረር ነበር። ስደስተኛ፣ ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓው ምድር ፍጻሜ ያገኘው ጦርነት ወደ አፍሪካና ወደ ሌሎች የሶስተኛው ዓለም አገሮች ይሸጋገራል። አንጎላንንና ሞዛቢክን፣ ከብዙ ዐመታት ጀምሮ በኮንጎ/ዛየርና በማዕከለኛው አፍሪካ የሚካሄደውን ጦርነት ስንመረመር፣ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ምድር ውስጥ ጦርነት ፍጻሜን ሲያገኝና የተደላደለ ህብረተሰብ ሲመሰርቱ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ግን በጦርነት መድማት ነበረባቸው፤ አለባቸውም። አውሮፓውያን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ሲበለጽጉ አፍሪካ በጦርነት መድማት አለባት፤ ህዝቦቿም የሰከነና የሰለጠነ ኑሮ መኖር የለባቸውም፤ መዋከብና መበዝበዝ ዕጣቸው መሆን አለብት። ሰባተኛ፣ ለዚህ ደግሞ ፍልስፍና አልባ የሆኑ መሪዎች እንደ አሻንጉሊት በየቦታው መቀመጥ ቻሉ። በተዋቀራላቸው የስለላ መሳሪያ፣ በሰለጠነላቸው ወታደርና የፖሊስ ሰራዊት አማካይነት ማንኛውንም ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ማፈንና ብልጽግና እንዳይመጣ ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጠረላቸው። በአገራችንና በሌሎች አፍሪካ አገሮች የተቋቋሙት የወታደር ተቋሞች፣ የስለላ መዋቅሮችና የፖሊስ ሰራዊት በመሰረቱ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረውን ኃይል አሰላለፍ የሚያንፀባርቁና፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘረጋውን የአገዛዝ ሰንሰለት አጋዦችና ታዛዦች እንጂ ከየህብረተሰቦቻቸው ፍላጎት አንፃር ከታች ወደ ላይ ቀስ በቀስ እየተደራጁና ሲቪክ የሆነ ባህርይ እንዲኖራቸው ሆነው የሰለጠኑ አይደሉም። በዚህም ምክንያት በብዙ የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያንም ጨምሮ የሲቪልና የወታደሩ ቢሮክራቶች እጅግ አረመኔና ህብረተሰብአቸውን ለውጭ ኃይሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የተዘጋጁ ናቸው ማለት ይቻላል።

በዘመነ-ግሎባላይዜሽን ሁኔታው ምስቅልቅልና ለብዙ ምሁራንና የፖለቲካ ተዋናዮች ግልጽ ያልሆነ ሁኔታ የተፈጠረበት ዘመንን እንመለከታለን። በተለይም ከ1989 ዓ.ም በኋላ የተፈጠረው አዲስ ሁኔታ ካፒታሊዝም ለጊዜውም ቢሆን በአሸናፊነት እንዲወጣና ሁሉም አገሮች ቢያንስ በመርህ ደረጃ የነጻ የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲን እንዲከተሉ አስገደዳቸው። አብዛኛዎቹ አገሮች ወደ ውስጥ ከማተኮር ይልቅ ይበልጥ ወደ ውጭ በማተኮር በማኑፋክቱር ላይ የተመረኮዘ ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ እንዳይገነቡና እንዳያስፋፉ አገዳቸው። አብዛኛዎች አገሮች በተለይም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተልና ተግባራዊ በማድረግ ከአገርና ከህብረተሰብ ግንባታ ይልቅ የአገልግሎት መስኩ እንዲስፋፋ ሁኔታዎችን አመቻቹ። ስለሆነም ከዚህ ጋር ተያይዞ የውጭ ኤክስፐርቶች በየአገሩ በመሰማራትና በየመንግስታቱ ላይ ግፊት በማድረግ የተዛባና ሀብት ሊፈጥር የማይችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ አደረጉ። ይህ ዐይነቱ አካሄድ በአንድ አገር ውስጥ ያልተመጣጠነ ዕድገትና የሀብት ፍሰት በማስከተል በየአገሮች እየተሰፋፋ ለመጣው ድህነት ዋና ምክንያት ሆነ። በዚህ መልክ ግሎባል ካፒታሊዝም በልዩ ልዩ መስኮች በመሰማራትና በየመንግስታቱ ላይ ግፊት በማድረግ መንግስታቶችን የበለጠ ከህዝቦቻቸው እንዲርቁና ወደ ጨቋኝነት እንዲለወጡ ሁኔታው ገፋፋቸው። በዚህም መሰረት አገር፣ ህብረ-ብሄር(Nation-State)፣ ብሄራዊ ኢኮኖሚና ብሄራዊ ነፃነት፣ እንዲሁም የመንግስት ትርጉምና ሚና በአንድ አገር ዕድገት ውስጥ የሚኖረው መሰረታዊ ተግባር፣ ህብረተሰብአዊ እሴትና ህብረተሰቡን ሊያቅፍና የመፍጠር ኃይሉን ሊያዳብር የሚችል ብሄራዊ ባህል፣ የግለሰብ ነፃነትና ሚና፣ የሚያድጉ ልጆች ሁኔታና እንክብካቤ፣ እንዲሁም ጤናማ የሆነ የቤተሰብ ምስረታና፣ ይህም የአንድ አገር ምሰሶ መሆን… ወዘተ… ወዘተ. ቦታና ትርጉም እንዳይኖራቸው ተደረገ። አንድ አገር ማንም እየመጣ የሚፈነጭበትና ከየመንግስታቱ ጋር በመቆላለፍና በመባልግ ሀብት የሚዘርፍና ህብረተሰባዊ እሴቶች የሚበጣጠሱበት መድረክ ሆነ። ይህ ሁኔታ በየአገሮች ውስጥ የሴተኛ አዳሪዎችን መስፋፋት፣ ህጻናትን ማባለግና ከሰው ልጅ ጤናማና ተፈጥሮአዊ ኖርም የራቁ ግኑኝነነቶች በመፍጠርና በማስፋፋት ህዝቡ ስለ ህብረተሰብ ትርጉም ደንታ እንዳይኖረው ተደረገ። ስለሆነም በብዙ የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያንም ጨምሮ፣ እነዚህ አገሮች እንደ አገሮች ቢታዩም፣ ህዝቦች ግን ህበረተሰብአዊ ንቃተ-ህሊና(Social Consciousness) እንዳይኖራቸው ተደረጉ።

ዛሬ በብዙ የአፍሪካ አገሮች አምባገነንነት ሰፍኗል፤ ዲሞክራሲ የለም እየተባለ የሚለፈፈውና የሚወደሰው ይህንን ውስብስቡን የዓለም ሁኔታ ለመመርመር ካለመቻል የተነሳ ይመስለኛል። የብዙ የአፍሪካ አገሮች ችግር ፕላቶ እንደሚለን ዕውነትን ከውሸት ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ለመስፋፋት አለመቻሉና፣ ዕውነተኛ ሁለ-ገብ የሆነ ምሁራዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩ ነው። ሰፋ ያለ የዳበረ ምሁራዊ እንቅስቃሴና፣ በሁሉም አቅጣጫ የሚገለጽ ብሄራዊ ባህርይ ያለው ምሁራዊ እንቅስቃሴ በሌለበት አገር የውጭ ኃይሎች ከውስጡ ኃይል ጋር በማበር የጨለማውን ዘመን ያራዝማሉ። የጭቆና መሳሪያዎችን እየላኩና እያስታጠቁ የጸጥታ ኃይል በሚሉት አማካይነት አንድ ህብረተሰብ ተዋክቦ እንዲኖር ያደርጋሉ። ህብረተሰቦች ታሪክ የሚሰራባቸው፣ ህዝብ ተረጋግቶ እንዲኖር ነገሮች በስነስርዓት ከሚዘጋጅባቸው ይልቅ ወደጦርነት አውድማ እንዲቀየሩ ይገደዳሉ። ዕውነተኛ ህብረተሰብአዊ ሀብትን በማይፈጥር በተራ ሸቀጣ ሸቀጥ አማካይነት ህብረተሰብን ማዋከቡ በከፍተኛ ፍጥነት መካሄድ አለበት። እንደ አገራችን ባሉት ደግሞ ከሌሎች ነገሮች ጋር ተደምሮ የኮሞዲቲ ገበያ የሚባል በማቋቋም ሰፊው ገበሬ አመለካከቱን ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያዞር በማድረግ ለዓለም ገበያ የቡናና የሰሊጥ ምርት አቅራቢ፣ ለውስጥ ገዢዎች ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እንዲሆን ተደርጓል። ከውጭ ሰልጥነው የገቡትና ዝናን ያገኙት አዲሶቹ ኤሊቶች ዋና ተግባር ህዝባችንን ወደ ባርነት መለወጥ ነው። ይህ በግሎባልይዜሽን ዘመን ንቃተ-ህሊናቸው የደከሙ ህብረተሰቦችንና፣ በኒዎ-ሊበራል ርዕዮተ-ዓለም የሰለጠኑ ተውረግራጊዎችን እየፈለጉና እያሰለጠኑ በአንድ በኩል ህብረተሰቦች ርካሽና የቆሻሻ ፍጆታ ዕቃ መጣያ ሆነዋል፤ በሌላ ወገን ደግሞ አብዛኛው ህዝብ ብዙ ቀናትና ወራት የለፋበትን የቡናም ሆነ የሰሊጥ ምርት በርካሽ ዋጋ እንዲሸጥ በመገደድ ወደ ባርነት እንዲለወጥ ተደርጓል። በዚህ መልክ ባለፈው ሃያ አራት ዐመታት በህብረተሰብአችን ውስጥ አዲስ ድህነትን ፈልፋይና የአገራችንን አቅጣጫና ዕድገቷን ያጣመመ እጅግ አደገኛ የህብረተሰብ ክፍል ብቅ ሊል ችሏል። ይህ የህብረተሰብ ክፍል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዋቀረው የፊናንስ ሰንሰልት ውስጥ በመካተት በካፒታሊስት አገሮች የሚካሂደውን የሀብት ክምችት(Capital Accumulation) አጋዥ ሆኗል። ወደ ውስጥ ደግሞ የህብረተሰቡን ሀብት በመምጠጥና የተንደላቀቀ ኑሮ በመኖር ለከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ምክንያት ሆኗል። በራሱ ዓለም ውስጥ የሚኖር፣ ዐይን ያወጣና ህብረተሰቡም ወደ ጥፋት መንገድ ሲያመራ ማየት የማይችልና፣ ማየት ቢችል እንኳ ደንታ የሌለው የህብረተሰብ ክፍል ሊሆን በቅቷል። ፍልስፍና አልባ የሆነና ህብረተሰብአዊ ኖርሞችን መከተል የማይችል፣ ወይም ህብረተሰቡ በተወሰኑ ኖርሞች ላይ እንዲተዳደር ማድረግ የማይችል ከሰፊው ኢትዮጵያ ህዝብ ተነጥሎ የሚኖር፣ የራሱ መዝናኛና ልዩ የመገበያያ ቦታ(Shoping Center) ያለው ኃይል ብቅ ብሏል። በዚህ መልክ ብቻ ነው የዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም ብዙ የሶስተኛውን ዓለም አገሮችን የሚቆጣጠረውና ለመቆጣጠር የሚችለው።

ዛሬ በአገራችን ምድር የሰፈነውን ፍልስፍና አልባ ፖለቲካና ህዝብን ማዋከብ ከዚህ ቀላል ሁኔታ በመነሳት ነው መመርመር መቻል ያለብን። በቀላል የሊበራል ዲሞክራሲና የነፃ ገበያ ፎርሙላ፣ ወይም በአምባገነን ስርዓት መስፈንና በዲሞክራሲ እጦት የህብረተሰብአችንን የተወሳሰበ ችግር ለመገንዘብ አንችልም። የአገዛዙ ችግር የፖለቲካ ፍልስፍና አልባነት ችግር ነው ስል ምን ማለቴ ነው? በመጀመሪያ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አለ። ይኸውም ወያኔ/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ውስጥ የፈለቀና የፊዩዳሊዝምና እጅግ የተዘበራረቀው ካፒታሊዝም ውጤት አገዛዝ ነው። በተለይም በአርባዎቹ መጨረሻና በሃምሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የተተከሉት በፍጆታ ምርትና አጠቃቀም ላይ የተመሰረቱት፣ ግን ደግሞ የውስጥ ገበያን ማስፋፋትና ማዳበር የማይችሉት ኢንዱስትሪዎች ለዛሬው አገዛዝም ሆነ ቀደም ብለው ለነበሩት ቢሮክራሲያዊ መዋቅሮች የባህርይና የአሰራር መሰረቶች ሆነዋል። ከአዋቂነትና ከብልህነት፣ ከጥበብና ከቆንጆ ቆንጆ ስራዎች ይልቅ ተንኮለኛ፣ ዳተኛና አራዳ እንዲሁም አገር ከፋፋይ ሆነው ብቅ ሊሉ የቻሉት አርቆ ባለማሰብ በተዋቀረው በተቆራረጠና ህብረተሰብአዊ መተሳሰርን በማያጠናክር የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካይነት ነው። የዛሬውን የወያኔ አገዛዝ ከተቀሩት ለየት የሚያደርገው የብሄረሰብን ወይም የጎሰኝነትን ጥያቄ አንግቦ በመነሳቱና፣ የተለየም መሆኑን ለማረጋገጥ መሞከሩ ብቻ ነው። የጎሰኝነትን ወይም የብሄረሰብ ፖለቲካንም የሚጠቀመ ለከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እንጂ ለየብሄረሰቦቹ ነፃ መውጣት በማሰብ አይደለም። ይህ ዐይነቱ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በምዕራቡ የካፒታሊስት ዓለም የሚደገፍ ሲሆን፣ በተለይም እንግሊዝና ሌሎች የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮች ደጋፊዎች ናቸው። ስለሆነም ከራሱ ባሻገር ማሰብ የማይችለው አገዛዝ ለስልጣንና ለሀብት ክምችት በማለት ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር የዘጠና ሚሊዮንን ህዝብ ዕድል ማጨለም ችሏል። የባርነቱንና የድህነቱን፣ እንዲሁም የጥገኝነቱን ዘመን ለብዙ መቶ ዐመታት ማራዘም ችሏል። ሁኔታው የባሰ እንዲመሰቃቀልና መጠገኛና መፍቻ መንገድም እንዳይገኝ ማድረግ ችሏል። በተለይም የአገዛዙ መሪዎች ያደጉበት ሁኔታና ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ለመቀላቀል አለመቻል የተለዩ መሆናቸውን በማስመሰል በእንደዚህ ዐይነት አገርን ከውስጥ የሚያስቦረቡርና ለውጭ ጠላት ደግሞ ካለምንም መከላከል ትጥቅን ፈቶ እጅ የሚያሰጥ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል።
ከዚህም ስንነሳ በአስተሳሰባቸው አንድ ወጥና ድርቅ ማለት፣ በምንም ዐይነት ለሰው ልጅ አለማሰብ፣ ወይም ህብረተሰብአዊ ፍቅር አለመኖር፣ አሁንም ቢሆን ጦርነትንና ድንፋታን ማስቀደም፣ ሶክራተስና ፓላቶ እንዳሉት ከህዝባዊ ስነ-ምግባርነት(Civic Virtue) ይልቅ፣ ህብረተሰቡን ማመሰቃቀል፣ ታዳጊው ትውልድ ኃላፊነት እንዳይኖረው ማድረግና ቀማኛ እንዲሆን ሁኔታውን ማመቻቸት፣ ከፋፋይነትና ለውጭ ኃይሎች ሰጥ ለጥ ብሎ መገዛትና፣ ይህንን እንደትልቅ ፈሊጥ አድርጎ መያዝ ዋናው የፖለቲካ „ፍልስፍናቸው“ በመሆን አገራችንን ከሁሉም አቅጣጫ ለማዳከም ችለዋል። ይህ ዐይነት የፖለቲካ ዘይቤ ከሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሲወዳደሩ ልዩ ሊያስመስላቸው ይችል ይሆናል፤ ነውም። በአንዳንድ ነገሮች ከቀደመው የኃይለስላሴና የደርግ አገዛዝ ቢሮክራቶች የሚመመሳሰሉበትም ሁኔታ አለ። ይኸውም ብሄራዊ ባህርይ ማጣት፣ በተለይም ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ሰጥ ለጥ ብሎ ማጎብደድ፣ ወይም አሜሪካንን እንደ አምላክ ማየትና አገርን መካድና የአገርን ምስጢር አሳልፎ መስጠት፣ ሰፊውን ህዝብ መናቅና ተንኮሎኝነት፣ በዚህ የሚመሳሰሉ ናቸው። ይህንን በጭንቅላታችን ውስጥ ስንቋጥር ነው የነገሮችን ሂደት መገንዘብ የምንችለው። ዝም ብሎ ግን አገዛዙ ለኢትዮጵያ አጀንዳ የለውም፤ ማርክሲስት ነው፤ የአልባንያውን ዐይነት ሶሻሊዝም ነው የሚያካሂደው፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲን ነው የሚያራምደው፤ ህገ-መንግስቱ ስታሊኒስታዊ ነው፤ የሚሉት አነጋገሮች የህብረተሰብአችንና የአገዛዙን የህሊና አወቃቀር፣ እንዲሁም ደግሞ የታሪክን ሂደት እንዳንረዳ የሚያደርገን አይደለም። በተጨማሪም የተበላሹ ማቴሪያላዊ(Socio-economic formation) አወቃቀሮች በሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የሚኖራቸውን ተጽዕኖ ባለመገንዘብ የሚሰነዘሩ መንፈሰ ሀተታዎች እንጂ ሀቁን የሚነግሩን አይደሉም። ስለዚህም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ተንታኝ ከራሱ ስሜት በመነሳት እንጂ አንዳች ፍልስፍናንና ስልትን(Methodology) በመከተል አይደለም የዛሬውን አገዛዝ ባህርይና ፖለቲካ የሚባለውን ፈሊጥ ለመተንተን የሚሞክረው። እንደዚህ ዐይነቱ በአንዳች ፍልስፍናና ስልት ላይ ያለተደገፈ አቀራርብ ደግሞ የችግሩን ዋና ምንጭ እንዳንረዳ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ ፍቱንና ህብረተሰብአችንን ሊያረጋጋና ወደስልጣኔ ሊያመራው የሚያስችል መፍትሄ እንዳንሰጥ ያግደናል። ለመጻፍ ተብሎ የሚጻፍ፣ ወይም ደግሞ ቁጭትን ለመወጣት ተብሎ የሚጻፍ ነገር የለም። ስለሆነም የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታም ሆነ አጠቃላዩን የህዝባችንንና የአገዛዙን የህሊና አወቃቀር ለመረዳት፣ በፍልስፍና፣ በህሊና ሳይንስ፣ በህብረተሰብ ሳይንስና እንዲሁም በተነፃፃሪ የታሪክ ምርምር(Comparative studies) የሚደገፍ ጥናት ቢካሄድ ተቀራራቢ መልስና መፍትሄ ማግኘት የሚቻል ይመስለኛል።

ያም ሆነ ይህ የዛሬው የወያኔ/የኢህአዴግ አገዛዝ የፖለቲካ ስልጣንን ሲጨብጥ ሜዳው ክፍት ነበረለት። የሚጋፈጠውን ሲያጣ ፍቅርና ሰላምን ከማስቀደም ይልቅ እንደልቤ መፈንጫ አገኘሁ በማለት ህብረተሰቡን ማዋከብ የፖለቲካው ዘይቤው አድርጎ ተያያዘው። የህብረተሰቡን ሀብት በመንጠቅና ጥቂቶችንም በማባለግ እያበጠ መምጣት ጀመረ። ከኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ዕርዳታ ሲፈስለት እኔ ነኝ ብቸኛው ኃይል በማለት በግሎባላይዜሽን ጉያ ስር በመውደቅና በመታሸት የህብረተሰቡን ችግር ውስብስብ አደረገ። ለዚህም ደግሞ መለሰ ወዳጃችን ነው፤ በአካባቢውም ሰላምንና መረጋጋትን የሚያመጣ ነው እየተባለ መወደስ ቻለ። በሌላ ወገን ግን የምዕራቡ ዓለም የተከተለውና ዛሬም የሚከተለው ፖለቲካ ከአጭር ስሌት አንፃር የተተለመ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ጋር የቆመና እሱንም የደገፈ፣ ራሱም እንደ ዋና ጠላት መታየቱ በፍጹም አልገባውም። ስለሆነም መለስ ከመሞቱ በፊትና ስልጣን ላይ 20 ዐመታት ያህል በቆየበት ዘመን፣ ልክ ሶክራተስ ፐሪክለስን እንደወነጀለው፣ ሰነፍ፣ ለፍላፊ፣ አጭበርባሪ፣ አገር ሻጭና ከሃዲ፣ በዝሙት ዓለም ውስጥ የሚዋኝ፣ ዕውነትን ከመፈለግ ይልቅ ለውሸት ጠበቃ የቆመ ትውልድ፣ በግልጽ የሚታዩ ነገሮችን የሚክድና፣ ተቀባይ ሲያጣ ደግሞ ቃታ የሚሰነዝር ትውልድ ለማፍራት በቅቷል። ይሁንና ግን መለስ ከፐሪክለስ ጋር ሊወዳደር የሚችል መሪ አልነበረም። ፐሪክለስ በሌሎች የግሪክ ግዛቶች ላይ የአቴንን የበላይነት ለማስፈን የታገለና በአቴን ስልጣኔ የሚኮራ ነበር። በመለስ ይመራ የነበረው የወያኔ አገዛዝና የዛሪው ወያኔ ግን „ከአሜሪካን ጋር እየተመካከርን ነው የምንሰራው“ በማለት የበታችነቱን ያረጋገጠንና የሚያረጋግጥ፣ ለስልጣኔ ጠንቅ የሆነ አገዛዝ ነበር፤ ነውም። ብሄራዊ አጀንዳ የሌለውና ኢትዮጵያችንን ከውስጥ በማዳከም የሚደሰት ነበር፤ ነውም። የዓለም የገንዘብ ድርጅትንና የዓለም ባንክን የኒዎ-ሊበራል አንጀት አጥብቅኝ የሞኔተሪ ፖሊሲ በመከተልና በዚህ በመዝናናት ድህነትን የፈለፈለ ነው። የዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት ደግሞ በስልጣን መታወርና የማንአለብኝ ብሎ እየተመጻደቁ መኖር ነው። በዚህ ዐይነት በውሸት ላይ በተመሰረተ አገዛዝ ግን ደግሞ ነገ እንደዱቄት የሚበን፣ አገዛዙ መግቢያና መውጫ የሚያጣበት ቀን መምጣቱ አይቀሬ ነው። በታሪክ ውስጥ አንድ ጨቋኝ አገዛዝ ለብዙ ዘመናት የቆየበት ጊዜ የለም። በሌላ ወገን ግን በህዝባችንና በአገራችን ላይ ያደረሰው አደጋ በቀላሉ ተገልጾ የሚያልቅ እይመስለኝም። ብዙ ጥናትንና ምርምርን የሚጠይቅ ነው። በአጭሩ ግን አገዛዙ ህዝባችንን በሀዘን ዓለም ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል፤ ግራ የገባው፣ ለምን እንደሚኖርና ወዴት እንደሚጓዝ የሚያውቅ አይመስልም። ለማኝ እንዲሆን ተደርጓል። በራሱ ላይ ዕምነት እንዲያጣ ሆኗል። ተፈጥሮአዊ ነፃነቱ ተገፏል። ወጣት ልጆቹን ለውጭ ከበርቴዎች ካለ ዕድሜያቸው ለጋሽ እንዲሆን ተደርጓል። ብሄራዊ ነፃነታችን ተገፏል። በአንድ በኩል አሽረሽ ምችው፣ በሌላው ወገን ደግሞ ተስፋ መቁረጥና መዘናጋት የህብረተሰብአችን ልዩ ባህርይ ሆነዋል።

በዛሬው ወቅት ወደ አስራ አራት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን የሚያሰቃየው ረሃብ ከአገዛዙ ባህርይ፣ አወቃቀር፣ ብሄራዊ ባህርይ ማጣትና በዘረፋ ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። በተጨማሪም የረሃቡና የድህነቱ መስፋፋት የሚያመለክተው አገራችን የቱን ያህል በውጭ ኃይሎች መዳፍ ቁጥጥር ስር እንደወደቀች ነው። የአገዛዙ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከውጭ የመጣና በውጭ ኃይሎች የተደነገገ በመሆኑ ወደ ውስጥ፣ በተለይም ሰፊውን አምራች ገበሬ ሊያግዝ የሚችል የማምረቻ መሳሪያና ማዳበሪያ እንዲመረት ማድረግ የሚያስችልና፣ ቀስ በቀስ ደግሞ ህብረተሰብአዊ ሀብት እንዲፈጠር የሚያደርግ ባለመሆኑ ሰፊው ህዝባችን የግዴታ እንደገና ለረሃብና ለድህነት ተጋልጧል። የአገዛዙ የሃሳብ ድህነትና ህዝብን መናቅ ህዝባችን ሊወጣው የማይችለው ፍዳ ውስጥ ከቶታል። ይህ በብዙ ድሮች የተቆላለፈው ችግርና የህብረተሰቡና የገዢው መደብ አስተሳሰብ በከፍተኛ ደረጃ መዳከም፣ 70% በመቶ የሚሆነው የአገራችን ምድር ለእርሻ የሚያገልግል ቢሆንምና፣ አገራችንም በውሃ ብዛት ክምችት በዓለም አቀፍ ደረጃ አምስተኛ ቦታን ብትይዝም፣ አሁንም ቢሆን በረሃብ የምትታወቅና ህዝባችንም በልመና እንዲኖር የተገደደ ነው። በአገራችን ምድር ውስጥ እየተደጋገመ ረሃብ መከሰት በዛሬው አገዛዝ ብቻ የሚሳበብ አይደለም። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በአገራችን ምድር የተከሰተውን ህብረተሰብአዊ አወቃቀር ለተከታተለና ላጠና፣ አዲስ የተፈጠረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ኤሊት ብሄራዊ ባህርይ የነበረውና ያለው አልነበረም። በመሆኑም እንደዚህ ዐይነቱ ኤሊት ከሰፊው ህዝብ ርቆና ተገልሎ የሚኖርና፣ ፈጣሪም ባለመሆኑ በየጊዜው በአገራችን ምድር ረሃብ እንዲከሰት አድርጓል። ይህ ሁኔታ እንደባህል በመወሰዱና እስከዛሬ ድረስ በመዝለቁ በሰፊው ህዝብና በየጊዜው ብቅ በሚለው አዳዲስ ኤሊት መሀከል ምንም ዐይነት ግኑኝነት እንዳይፈጠር ተደርጓል። አዲስ አበባ የተቀመጠው ኤሊትና የገዢው መደብ ገበሬው በስንትና ስንት ልፋት በብርድና በጠራራ በባዶ ሆዱና ካለጫማ እያረሰ እንደሚያቀርብለት የገባው አይመስልም። ስለሆነም የአስተሳሰብ ለውጥ እስካልተደረገ ድረስና፣ ሃላፊነትን ሊቀበልና ብሄራዊ ስሜት ሊኖረው የሚችል አዲስ የህብረተሰብ ኃይል እስካልተፈጠረ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ለሚቀጥሉት ሰላሳና ሃምሳ ዐመታት ድህነትና ረሃብ ይሆናል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።

የወያኔን አገዛዝ የተበላሸና ህዝብን ለዝንተዓለም የሚያወዛግብ ፖለቲካን ስንመለከት በጣም የሚያሳዝኑና የሚያስቁ ሁኔታዎችን እንመለከታለን። ወያኔ ለዘለዓለም ስልጣን ላይ ለመቆየት ባለው ፍላጎት መሰረት ከውስጥ የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ገንዘብ ከኢኮኖሚው ዕድገት ሁኔታ ጋር እየተመጣጠነ እንዲታተም ከማድረግ ይልቅ፣ በብዛት እንዲታተም በማድረግና የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ በማድረግ ሊያደልብ ችሏል፤ አባልጓልም። ይህ አዲሱ መጤ የህብረተሰብ ክፍል አምራችና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመትከል የስራ መስክ የሚፈጥር ሳይሆን፣ በተለይም በአገልግሎት መስክ ላይ በመረባረብ በከፍተኛ ደረጃ የፍጆታ ዕቃ ተጠቃሚና የህብረተሰቡን ሀብት የሚመጥ ሊሆን ችሏል። ይህ በራሱ አገራችን ውስጥ መረን በለቀቀ መልክ ለተስፋፋው ድህነትና ድብቅ ረሃብ እንደ አንድ ዋና ምክንያት ሊቆጠር የሚችል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ራሱ የሚቆጣጠረው የኢንዱስትሪ መስክና አዳዲስ የሚተከሉት ኢንዱስትሪዎች በመሰረቱ ወደ ውስጥ ህዝባዊ ሀብትን(National and Social Wealth) ለመፍጠር የሚያስችሉና የስራ መስክ ለመከፍት የሚበቁ አይደሉም። በዚህም ምክንያት የውስጥ ገበያው ሊስፋፋና ሊዳብር የቻለበትን ሁኔታ አንመለከትም። በየቦታው ያሉ የቢሮክራሲው ማነቆዎች ደግሞ ህዝቡን የሚያሰሩና ወደ ውስጥ የጥሬ-ሀብት እንዲወጣና ሰፊው ህዝብ ወደ ስራ ዓለም እንዲሰማራ ለማድረግ የሚያስችሉ አይደሉም። በዚህም ምክንያት አገዛዙና ቢሮክራሲያዊ ማነቆዎች፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሚኒስትሪዎች የሰፊው ህዝብ ተጠሪዎች ሳይሆኑ የህዝብን ሀብት የሚዘርፉና ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት ችግሩን እንዳይቀርፍ ትልቅ እንቅፋት ለመሆን የቻሉ ናቸው። የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ ሚኒስተሮችን ዋና ተግባር በምንመረምርበት ጊዜ በመሰረቱ በየክፍለ ሀገራት ወይም በየክልሉ እየተዘዋወሩ የየአካባቢውን የኢኮኖሚና የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ማጥናትና፣ ከዚህ በመነሳት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የሚገባቸው ነበሩ። ሁኔታውን ስንመረምር ግን ሁሉም ሚኒስተሮች ማለት ይቻላል፣ ከህዝቡ ርቀው የሚኖሩና በየክፍላተ ሀገራት ምን ምን የስራ ክፍፍል እንዳለና፣ የገበያውም ሁኔታ በምን መልክ የተደራጀ መሆኑን ለመቃኘት የሚጥሩ አይደሉም፤ ፍላጎትም የላቸውም። ይህ እንግዲህ የአገዛዙን ፖሊሲ ሲመለከት፣ በሌላ ወገን ደግሞ አገዛዙ ለረጅም ዘመናት በስልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ፍላጎት የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ ባሉት ኢንስቲቱሽኖችና እስከመጠጥ ቤት ድረስ ሰርጎ በመግባት ህዝቡን ፍዳ እያሳየ ነው። ምንም የፖለቲካ ዕውቀት የሌላቸውን ሁሉ ደጋፊዎች በማድረግ ፖለቲካን ወደ ርካሽነት የለወጠ አገዛዝ ነው ማለት ይቻላል። ይሁ ጉዳይ እስከውጭ ድረስ በመዝለቅና አንዳንድ በኢትዮጵያውያን የሚተዳደሩ ቡና ቤቶችን በማቀፍ በውጭ አገር ያለው ኢትዮጵያዊ እንዲቃቃርና እንዳይቀራረብ እያደረገ ነው። በተለይም በብዛት ለትምህርት እየተባሉ የሚላኩ ምንም ነገር የማይገባቸው ልጆች በካድሬነት በመመልመል የማይሆን ነገር እየሰሩ ነው። ስለሆነም እነዚህ ወጣት ትግሬዎች/ኢትዮጵያውያን በማያውቁት ነገር ውስጥ በመግባት በሌላው ወያኔን በሚጠላው ኢትዮጵያዊ እንደጠላትነት እየታዩ ነው። አገዛዙ ህብረተሰቡን በመከፋፈልና የተወሰነውን ህብረተሰብ ክፍል በጥቅም በመደለል የሚያካሂደው ፍልስፍናዊ አልባ ፖለቲካ በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ማጥ ውስጥ እየከተተን ማለት ነው። ኢትዮጵያን እንደ አገርና እንደ ህብረ-ብሄር በጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረተ ላይ የመገንባቱ ሁኔታ ለብዙ መቶ ዐመታት እንዲተላለፍ እየሆነ በመምጣት ላይ ነው። ይህ ዐይነቱ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ለራሱ ለአገዛዙ ብቻ ሳይሆን ለትግሬ ብሄረሰብም የሚያመች አይሆንም። ወያኔ ቢወድቅ እንኳ የተቀሩት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ እንዲሁም አባቶቻችንና እናቶቻችን የሆኑት የትግሬ ብሄረሰብ ተወላጆች በጥርጣሬ እየታዩ ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚገለሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። ስለዚህ የዚህን የተወሳሰበና አደገኛ ሁኔታ በመረዳት አዲስ የትግል አቅጣጫ መቀየስ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ከዚህ ስንነሳ የተቃዋሚውን ኃይል የትግል ስትራቴጂ ወይም ፍልስፍና በጥቂቱም ቢሆን መቃኘቱ አስፈላጊ ይመስለኛል።

አጠቃላዩንና የተወሳሰበውን የአገራችንን ሁኔታ ስንመረመር ተቃዋሚ ነኝ በሚለው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ይህንን የተወሳሰበ ሁኔታ ለመረዳት የሚያስችል ትንታኔ ሲሰጥ አይታይም። በብዙዎቻችን ዕምነት የዛሬው የወያኔ አገዛዝ ብቻውን የሚጓዝና፣ የተከተላቸውና የሚከተላቸውም ፖሊሲዎች ከውጭው ዓለም ጋር በተለይም፣ ኢንተርናሽናል ኮሙኒቲ ከሚባለው ጋር የሚያያዙ አይደሉም። የዓለም አቀፍ የገንዘብ ደርጅት(IMF)፣ የዓለም ባንክ፣ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የአውሮፓ አንድነት በአገራችን የኢኮኖሚ ፖሊስና ተግባራዊ መሆን ላይ ምንም ዐይነት ተፅዕኖ የላቸውም። ስለዚህም ትግሉ ከወያኔ ጋር ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ በሳይንስና በቲዎሪ እንዲሁም በፍልስፍና ደረጃ ዓለም አቀፍ ኮሙኒቲ የሚባለውን መጋፈጥ አያስፈልግም። የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ አገዛዝ ከተላቀቀ ሁሉ ነገር ይሰተካከላል የሚል ከዓለምና ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም አመለካከት በተቃዋሚው ኃይል ጭንቅላት ውስጥ የተቋጣረ ይመስላል።፣ ይህ ዐይነቱ አመለካከትና የትግል ስትራቴጂ ከታሪክ ልምድና በሳይንስና በፍልስፍና መነፅር የሚደገፍ አይደለም።

እኔ እስከተከታተልኩትና እስካጠናሁት ድረስ 1ኛ¬) ተቃዋሚው ነኝ የሚለው ኃይል ብሄራዊ አጀንዳ ያለው አይመስለኝም። አገር ወዳድነቱና ብሄራዊ ስሜቱም ያጠራጥራል። ምክንያቱም ሳይንቲስቱ ላይብኒዝ እንደሚለው አንድ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ህዝብ ወዳድና ለአገሩ የሚቆረቆረው በሳይንስና በፍልስፍና ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ብቻ ነው። 2ኛ) ፍልስፍናዊ መሰረት የለውም ወይም ደግሞ በምን ዐይነት ፍልስፍና እንደሚመራ ግልጽ አይደለም። 3ኛ)ባለፉት 24 ዐመታት በአገራችን ምድር የተፈጠረውን እጅግ አስቸጋሪ የኢኮኖሚ፣ የህብረተሰብና የማህበራዊ እሴቶች መበጣጠስና፣ የህዝባችንንም ኑሮ የመረመረና ለነዚህም ዋናው ምክንያት ምን እንደሆነ ጠጋ ብሎ ለመገንዘብ የቃጣና፣ የሚቃጣ አይደለም። በየጊዜው ንግግር ለማድረግ ተጋብዘው እዚህ አውሮፓ የሚመጡትን የተቃዋሚ ተጠሪዎች ንግግር ለተመለከተ በምድር ላይ ያለውን ሁኔታ በቅጡ የተገነዘቡ አይመስሉም። አነጋገራቸው በነፃነት እጦት፣ በዲሞክራሲ አለመኖርና ምርጫ በስነ-ስራዓት አለመካሄድ አኳያ የሚደረጉ ንግግሮች እንጂ፣ ሰፊና ጠለቅ ያሉ ትንተናዎችን ሲሰጡ አይታዩም። ውጭ አገር ያለውም ችግሩን በምርጫና በህገ-መንግስት ዙሪያ ከማየት አልፎ በህብረተሰብአችን ውስጥ የቱን ያህል የአዕምሮ መዛባት(Austim) እንደሰፈነና፣ ለዚህም ደግሞ ልዩ ጥናትትና መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ጥናት ሲያቀርብ አይታይም። 4ኛ) በአጠቃላይ ሲታይ የተቃዋሚው ኃይል ነኝ የሚለው በአገራችን ውስጥ የምዕራቡን ዓለም፣ በተለይም ደግሞ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምን ጣልቃ-ገብነት ከምንም አይቆጥረውም፤ ወይም ደግሞ ከፖለቲካ ስሌቱ ውስጥ የለም። አንዳንዶች ይህንን ጉዳይ ሲያነሱ አይ ግራ ቀደም ተብለው ይወነጀላሉ፤ ከወዳጃችን ከአሜሪካን ጋር አታጣሉን ይባላሉ። እነዚህ ሰዎች ወደ ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ እንኳ ውይይት እንዳይካሄድ በሩን በመዝጋት ምሁራዊና ሳይንሳዊ ክርክር እንዳይደረግ ለማድረግ በቅተዋል። 5ኛ)ሌላው ትልቁ ችግር የብሄረሰብ ነፃ አውጭ ነኝ የሚባሉት ምሁራዊ ሁኔታና፣ የአንዳንዶችም በየጊዜው የመለዋወጥ አስተሳሰብና አካሄድ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ እየፈጠረ መጥቷል ማለት ይቻላል። በመሰረቱ በአገራችን ያለው ችግር የብሄረሰብ ችግር ወይም ጭቆና አይደለም። የንቃተ-ህሊና ጉድለትና የታሪክንና የህብረተሰብን ዕድገትና ሂደት ያለመረዳት ጉዳይ ነው። ከዚህ ስንነሳ እዚህና እዚያ እንቀሳቀሳልን የሚሉት የነፃ አውጭ ድርጅቶች ነን ባዮች ፍልስፍናቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም። ተበድሏል የሚሉትን ወገናቸውን እንዴትስና በምን መንገድ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የጥበብና የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤትና ተጠቃሚ ለማድረግና ቆንጆ ኑሮ ሊኖር የሚችልበትን መንገዱን ሲያሳዩን አንመለከትም። የዲሞክራሲና የነፃነት እጦት መፈክሮች ብቻ የትም አያደርሱትም። ከሌሎች አገሮች ልምድ እንደምናየው፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የአንጎላና የሞዛምቢክ፣ እንዲሁም የዚምባብዌ ህዝቦች የነፃነት ትግሉ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ በፍጹም አልቻሉም። በድሮው አገዛዝ አዲስ የገዢ መደቦች በመቀመጥና ከውጭው ዓለም ጋር በመቆላለፍ ሀብት ዘራፊዎችና አቆርቋዦች ሆኑ እንጂ ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ ሊያደርጉ አልቻሉም። እንደምናየው በእነዚህ አገሮች ሁሉ በተለይም ወጣቱ ስራ አጥ በመሆንና የማስለጠኛ ቦታ በማጣቱ ተፈጥሮአዊ ችሎታውን ተግባራዊ እንዳያደርግ ተገዷል። ስለሆነም በዚህም ሆነ በዚያ መስክ ብሄረሰባችንን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ቡድኖች በመሰረቱ ከነዚህ የሚለዩ አይሆኑም። ምናልባትም እንደጆከር በመቀመጥ ማስፈራሪያ የሚሆኑና፣ የድህነቱንም ዘመን የሚያራዝሙ ይሆናሉ። ከዚህ ስንነሳ ከፍልስፍና፣ ከሳይንስ፣ ከቲዎሪና ከጥበብ፣ እንዲሁም ከህብረተሰብ ሳይንስ ውጭ በነፃነት ስም ብቻ የሚካሄዱ ትግሎች የትም አያደርሱም። የዛሬው አገዛዝ ቢወድቅ እንኳ ምናልባት የደቡብ ሱዳን ዐይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ስለሆነም እያንዳዱ የነፃ አውጭ ድርጅት ነኝ የሚል እዚህና እዚያ ከመሯሯጡና ከምዕራቡም ምክር ከመጠየቅ ይልቅ እስቲ በአንድነት ተቀምጠን በየአንዳንዱ ጥያቄ ላይ ክርክርና ውይይት እናድርግ። እስከምረዳው ደረስ የአንደን አገር ችግር፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ህብረተሰብአዊና ማህበራዊ፣ እንዲሁም ባህላዊ ችግሮች በፖለቲካ ዲስኮርስና በዲሞክራሲያዊ ውይይት ብቻ ነው መፍታት የሚቻለው። ስለሆነም ለስልጣን ከመቻኮል ይልቅ የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታና የዓለም አቀፍ የፖለቲካን፣ የሚሊታሪ፣ የርዕዮተ-ዓለምና የኢኮኖሚ አወቃቀር ጠጋ ብለን እንመርምር፤ አብረን ተቀምጠንም እናጥና። ለዚህም ደግሞ ድፍረቱ ይኑረን። ለብቻችን መሯሯጥና ለአውሮፓው አንድነትም ሆነ ለአሜሪካ መንግስት ተጠሪዎች እሮሮ ማሰማቱ ትክክለኛው የትግል ዘዴ አይደለም። እንዲያውም ራስን አለመቻልና የነፃነቱንም መንገድ ውስብስብ የሚያደርገው ነው። የአውሮፓንና የአሜሪካንን መንግስታት በዲፕሎማሲ ማሳመን አይቻልም። የአሜሪካም ሆነ የምዕራብ አውሮፓ መንግስታቶች ተቃዋሚውን ኃይል እንዲደግፉ ከተፈለገ ተቃዋሚው ኃይል ከወያኔ የተሻለ የሚሰራ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ይህም ማለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይሰፍንና ጠንካራ ህብረተሰብ እንዳይመሰረት ጠንክሮ መስራት አለበት።

ከዚህ አጭር ሀተታ ስነሳ፣ ከዚህ ዐይነቱ የተወሳሰበና አገርን ለማውደም ከተቃረበ ችግር እንዴት እንወጣለን ? የሚለው ነው ዋናው ጥያቄያችንና መመለስ ያለብን ጉዳይ። በተራ የነፃ ገበያና የሊበራል ዲሞክራሲ ፎርሙላ ወይስ አስቸጋሪ በሆነው ግን ደግሞ ፍቱን በሆነው በሬናሳንስ ፍልስፍና አማካይነት ነው የተወሳሰበውን የህብረተሰብአችንን ችግር ልንፈታ የምንችለው። በእኔ ዕምነት ተራ የሊበራል ዲሞክራሲና የነፃ ገበያ ፎርሙላዎች ለኛ ብቻ ሳይሆኑ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ችግር በፍጹም መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ አይደሉም። መፍትሄው የመንፈስን የበላይነት የሚያስቀድመውን የሬናሳንስን ሁለ-ገብ የህብረተሰብን ችግር መፍቻ ስልት የተከተለን እንደሆን ብቻ ነው። እኛ ብቻ ሳንሆን ዛሬ የተቀረው የዓለም ህዝብ የሚመኘው የመንፈስን የበላይነት የሚያስቀድምና የኑሮን ትርጉም እንድንረዳ የሚያደርገንን መንገድ ነው። በእርግጥ ይህ አካሄድ ከአገራችን ሁኔታ ጋር የሚጣጣምበትን ዘዴ መፈለግ የሚያሻ ይመስለኛል። ለማንኛውም ከየት እንደመጣን፣ በዚህ ዓለም ላይ ለምን እንደምንኖርና፣ ምንስ ማድረግ እንዳለብንና ወዴትስ እንደምናመራ የተገነዘብን እንደሆን ብቻ ተቀራራቢ መፍትሄ ማግኘት የምንችል ይመስለኛል። ለዚህ ሁሉ መፍትሄውም የፒታጎራስን፣ የሶክራተስንና የፕላቶንን ወንድማዊ ወይም የእህትማማች ፍቅር እንደመመሪያ አድርገን የወሰድን እንደሆን ብቻ ነው። ይህ ፍቅር ግን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ምሁራዊ ፍቅር ማለት ነው። ዕውነትን ለመፈለግ የሚረዳንና ሶፊስታዊውን የመሙለጭለጭ መንገድ አሽቀንጥረን የሚያስጥለን መሆን አለበት። በሃሳብና በልብ እንድንገናኝ የሚያደርገንና፣ ራሳችንን አውቀንና ለውጠን ህብረተሰብአችንን ከገባበት ማጥ ውስጥ እንዲወጣ የሚያስችለው ፍልስፍናና መመሪያ መሆን አለበት።
ፈቃዱ በቀለ
fekadubekele@gmx.de

የወያኔ/ኢሕአዴግ የግፍ ቀንበር መሰበር አለበት፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመታደግ በመተባበር ልንነሳ ይገባል። የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር

እናት ገዳዮችን ምን ቛንቛ ይግለጻቸው በበላይነህ አባተ

አገር እንደዋዛ፤ ስትደርቅ እንደጤዛ አቢቹ ነጋ

$
0
0

ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተሰደው ይገኛሉ። የስደታቸው ምክንያት ብዙና የተለያየ ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልግም። ሁሉንም አንድ የሚአደርግ ነገር ግን አለ። ስደትን ደስ ብሎት የተቀበለ የለም። አንድ ቀን ወደ ሃገር ተመልሶ ሃገሩንና ሕዝቡን መርዳት ሁሉም ይፈለጋል።

ኢትዮጵያዊያኖች በየቀኑ በሚባል ደረጃ ይገናኛሉ። የግንኙነታቸው አድማስ በምንገድና በገበያ አዳራሽ ብቻ የተወሰን ሳይሆን በጸሎት ቤት፤ በድግስ፤ በበዓላት፤ በሐዘን፤ በግልና በመሳሰለው ይገናኛሉ። በምንም መድረክ ይገናኙ ስለሃገራቸው፤ ስለወገናቸው፤ ስለታሪካቸው፤ ባሕላቸው፤ ቀያቸው፤ የሃገራቸው መልካ ምድር፤ ሃይማኖታቸው፤ ኑሯቸው፤ የሃገር ናፍቆታቸው፤ ፖለቲካቸው መነጋገርን ያዘወትራሉ።

አንዳንዴ ብዙ ውይይቶች ጫፍ ደርሰው ሊበጠሱ የደረሱ እስኪመስል ድረስ ይጨቃጨቃሉ። ሁሉም ተወያይ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ባለሙያ መስሎ ይታያል። ውይይታቸው ፊት ለፊት ብቻ ሳይወሰን ዘመኑ በወለደው የመገናኛ ብዙሃን፤ ማህበራዊ ድረ ገጾች፤ ቴሌ ኮንፈረንሶችን በመጠቀም ይደረጋል። አንዱ ሌላውን ግልሰበ ሲአብጠለጥል፤ አንዱ ቡድን ሌላውን ሲኮንንና ሲአወግዝ መስማትና ማየት ልምድና በሐሪ ሆኗል። ብዙውን ጊዜ እነዚህ ውይይቶችና ክርክሮች ለችግሩ መፍቴሄ ሳይሰጡ ጥፋትን፤ ስህተትንና ውግዘትን አጉልተው ይቋጫሉ።

ብዙዎች ይህ የኢትዮጵያዊያን መገለጫ የሆነውን ባሕሪ ያወግዛሉ። እንደዚህ ጸሐፊ እይታ ከሆነ እርር ትክን ያለ፤ እስከ መጣላት የሚአደርስ ውይይት የሚአደርጉት ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን ከመውደዳቸው የተነሳ ብቻ ሳይሆን ጤናማና አዋቂነትም ነው ይላል። ሃገርን ከማፍቀር የተነሳ ለሕዝቧ ይበጃል የሚሉትን ሐሳብ መሰንዘራቸው ሊአስወግዛቸው አይገባም። አለመንጋገርና አለመወያየት ግን የጤናማ በሐሪ ምልክት አይደለም ሊሆንም አይችልም። መነጋገርና መወያየት ካለ ለችግሮች መፍትሔ ማግኘት ይቻላል።

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃውም በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ኢትዮጵያ እየታመሰች ትገኛለች። በሃገር ቤት በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ልባቸው ተሰብሯል፤ ደንግጠዋል፤ ተጨንቀዋል፤ ሱባኤ ገብተዋል። አምላክ በቅዱስ እጁ ሃገራቸውን እንዲባርካትና እንዲቃኛት ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል። ምክንያቱ ግልጽ ነው-ቀውሱ ከቀጠለ የሚወዷት ሃገራችው ልትፈርስና ብትንትንዋ ሊወጣ በመሆኑ ሰግተዋል። ብዙዎችም የሚፈራው እንዳይሆን ምንመደረግ አለበት ብለው ሌት ተቀን ሲለፉ ይታያል። አገሪቱ ከፈረሰች መግቢያ ሊጠፋ ነው። በሶማሊያ፤ በሶሪያ፤ በአፈግሃኒስታን፤ በኢራክ፤ በሩዋንዳ፤ በሊቢያ፤ በማሊ ወዘት ከወደቁት አገሮች (Failed States) ጎራ ልትመደብ ነው የሚል ስጋት አላቸው። ይህ ከሆነ ደግሞ ባለሶስት ቀለሙ፤ ባለ ወርካው ፣ ባለመዶሻው ፣ የአማራው፣ የኦጋዴኑ፣ የደቡቡ፣ የጉራጌው፣ የቤንሻንጉሉ፣ የጋሞው፣ የቅማንቱ (ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል) ባንዲራ የሚውለበለብበት መሬትና ወጋግራ አይኖርም። ያለ ሃገር የጎሳ ጥያቄ አይኖርም። ማፍረስና ማውደም ለሁሉም ቀላል ስራ ሲሆን መልሶ መግጠም ግን ይቸግራል። በዛ ጊዜ ቄሱም፤ ሸሁም፤ ፓስተሩም ዝም መጽሃፉም ጎሳውም ዝም ይሆናል።

ሁል ጊዜ እናቶቻችን እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ-አይሆንምን ትቶ ይሆናልን ማሰብ ይላሉ። ይህም የቅድሚያ ዝግጅት (Contingency Planning) ያስፈልጋል እንደማለት ይሆናል። ዕውነት አላቸው- ማሰባቸው ተገቢ የመስላል።

የኢትዮጵያዊያን ስጋትም እንዲሁ በአየር ላይ የተፈበረከ፤ መሰረተቢስ፤ ተራ መላምትና የናፋቂነት አስተሳሰብ አይደለም። የኢትዮጵያን ፖለቲካያዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማሕበራዊ፤ አስተዳደራዊ፤ ሕጋዊ መስፈርቶች (Indicators) ለሚከታተልና ሰክን ብሎ ለሚአስብ ሰው ብዙ ጉዳዮች ዓይናቸውን ያፈጠጡ እውነታዎች ናቸው። ከወደቁት አገሮች ጋር ሊአስመድባት ወይም ወደዚያ እያንደረደሯት ያሉ ምልክቶች በገሃድ ይታያሉ። አሁን እዚህ ደረጃ አልደረስንም። ጉዞው ግን ፈጥኗል። እሩቅ አይደለም። ስለሆነም ለብዙዎቻችን ሁሉም ነገር ጨልሟል።

ጨለማውን ወደ ብርሃን መቀየር ይቻላል። አዎ እንችላለን (YES WE CAN) ብለን በአንድነት ከተነሳን ይቻላል። መፍትሔው በየአንዳንዳችን ቤትና ቡድን እጅ ይገኛል። ሩቅ መሄድ አይኖርብንም። ለብዙ ዓመታት ብዙ ተከራክረናል። ክርክሩ ይብቃ። መፍትሄው ላይ እንስራ። በእጃችን የሚገኝ መፍትሔ አለ። መፍትሔው ከየአንዳንዳችን የሚጠበቅበት ጊዜ ትላንት ወይም ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። በየለቅሶ ቤቱ፤ ጸሎት ቤቱ፤ በግብዣው፣ በአደባባይና በመንገድ ስናወጣና ስናወርዳት የነበረችውን ኢትዮጵያ በተግባር የምንታደግበት አስራ አንደኛው ስዓት ላይ ደርሰናል። ወደድንም ጠላንም የመጣንበት ጎሳ ሳይሆን የመጣንበት ሃገር ገላጫችን እንደሆነ አንዘንጋ።

ከሰሞኑ የሚታየው የሕዝብ እንቅስቃሴ ሁሉን አቀፍ መሆኑ ያስደስታል። ቀድሞ ነጻ አውጪ ነን እያሉ ይሰብኩ የነበሩት እንደ ሌንጮ ለታ ዓይነቶች በኢትዮጵያ ጥላ ስር ለመስራትና ለእርቀ ሰላም ጥሪ ሲአቀርቡ ማየትና መስማትን የመሰለ ትልቅ ተስፍ ሰጪ ነገር የለም። በእጃችን ያለው መፍትሔ የሚባለው ምሳሌም ይህ ነው። ሌሎችም ይህን ፈለግ ሊከተሉ ይገባል። በስልጣን ላይ ያለው መንግሥትም ከሕዝብ ጋር ለመነጋገር ዝግጁነቱን በአስቸኳይ ለሕዝብ ማብሰር አለበት። ይህን ካላደረገ ኪሳራው ይበልጥ የሚጎዳው እራሱን ነው።

በየስርቻወ ነጻ አውጪ እየመሰረቱ መናቆር ለማንም የሚበጅ አይሆንም። መገንጠልና ነፃነት መፍትሔ ቢሆን ኖሮ በኤርትራ፤ በደቡብ ሱዳን፤ በፓኪስታን ወዘተ ያለው ሁኔታ ባልታየ። ይህን የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ይኖርላ ብሎ ለማመን ይቸግራል። ካለም የሚወክለው ጥፋትን ነው ። ስለዚህ ዓማራ፤ ኦረሞ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ደቡብ ሕዝቦች፤ ኦጋዴን፤ አፋር፤ ቤንሻንጉል፤ ጉራጌ ወዘት ሳይባል መነሳት ያስፈልጋል። ለነገሩ ብዙዎቻችን የነጻ አውጪ መሪዎችን ጨምሮ የጎሶችን ክልል እንኳን ጠንቅቀን አናውቅም።

ይሀን ካላደረግን አገር አንደዋዛ ትጠፋና መጨረሻችን እንደ ጤዛ ተኖ በወጡበት መቅረት ይሆናል። በአገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ መንቃት አለበት። ቢረፍድም አልዘገየምና አገራችንን ከውድመት እንታደጋት። ሳይኖራት አስተምራ፤ አብልታና አጠጥታ አሳድጋናለች። ዓማረ አረጋዊ ‘መንግሥት እራሱን ይፈትሽ’፤ የሻቢያው ተስፋዬ ገብረአብ ‘ጎዳናው የት ያደርሳል’ ብለው ያስነበቡን መጣጥፎች’ ምክሮች ለሁላችንም የሚመቹ ናቸው። እናዳምጣቸው። አንዳንዴ ከምናምኑም የርግብ እንቁላል መጠበቅ ክፋት የለውም። መርዝም መድሐኒት ይሆናልና። መሬቱ ሰፊ አየሩ ምቹና ለሁላችንም በቂ ስለሆነ እንወቅበት። አመሰግናለሁ።

አቢቹ ነጋ (aneganega2013@gmail.com)

ታሕሳስ 12, 2008

ህገ-መንግስቱ ይከበር፤ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በአብራሃም ለቤዛ

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>