Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ክንፉ አሰፋ

$
0
0

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”

አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si haaeebbisu በርቺ፡፡ Jabaadhuu”

በማህበራዊ ድር-ገጾች ብዙ ፉገራዎች ከተራው ሰው ሲሰራጩ ቢታዩም፤ ነጭ ፉገራን በሚንስትር ደረጃ ስናይ ግን የመጀመርያው መሆኑ ነው።

በፌስቡክ ላይ “የጀርመን ነዋሪ ነኝ” ያለችው ልጅ ፒያሳ ባር ስታስተናግድ ተገኘች። የፌስቡክ ጓደኞችዋ በድንገት ሲያገኟት ልጅት ምንም አልመሰላት። “ለምን ዋሸሽ?” ቢሉዋት። አይኗን በጨው አጥባ መልስ ሰጠች።

“መዋሸት ብርቅ ነው እንዴ?” አለች። የሷን ፉገራ በመቶ እጅ የሚበልጡ ፉገራዎች ስለሚያጽናኗት ቅንጣት ያህል አልደነገጠችም። ጣትዋን በቴድሮስ አድሃኖም ላይ እያነጣጠረች ጓደኞችዋን አረጋጋች።

የዚህችን ወጣት ውሸት ማካበድ እንደማያስፈልግ የተረዱት ጓደኞችዋ፣ ከውቅያኖስ የጠለቀውን፣ ከባህር የሰፋውን የቴድሮስ ውሸት ከሰሙ በኋላ ነበር።

“አበስኩ ገበርኩ… የባሰ አታምጣ።” ይላሉ እናቶች።

በአጼ ምኒሊክ ግዜ ለፍርድ ሙግት የቀረበ አንድ ሰው እጁን እያወራጨ ሲናገር ብብቱ ይታይ ነበር። እብብቱ ስር ያለ ጸጉሩም አጎፍሮ ነበር። የብብቱን ጸጉር ያስተዋሉ ዳኛ፣ ችሎት በመድፈር ወንጀል 50 ጅራፍ ቀጡት። ሰውየው ቅጣቱን ሳይግደረደር ተቀበለ። ይህንን 50 ጅራፍ ለምን ሳይከላከል እንደጠቀበለ በጓደኛው ሲጠየቅ፣ ለብብቴ 50 የቀጡኝ የታችኛውን (የሃፍረተ ስጋዬን) ጎፈር ቢያዩ 100 ይሉኝ ነበር አለ።

“… የባሰ አታምጣ።” ነው ነገሩ።

ከዚህች ተራ ወጣት የባሰው ነጭ ውሸት በተጋለጠ ጊዜ፣
“የ14 አመትዋ ልጅ በአውስትራሊያ የ8ኛ ክፍል አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ ያገኘችውን 20 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ለልማት ለማዋል ወሰናለች ያልኩት ፍጹም ስህተት ነው። ስለ ጥፋቴ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

የሚል ዜና ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ እስካሁን ልንሰማ አልቻልንም። አቤ ጎርጉሮ ያወጣውን ቅሌት በፌስቡክ ከተለቀቀው የልደት ውስኪያቸው ጋር አወራርደውታል። ውሸቱ አሸማቆ፣ አሸማቆ፣ ይገድላቸዋል… ድንጋጤው ይጥላቸዋል ብሎ የገመተ ጥቂት አይደለም። ግን እንዴት አይነት ፈጣጣ ናቸው። ያንን ጉድ ይዘው ቢሮ ሲገቡ ምንም እንዳልተፈጠረ መስለው ብቻ አይደለም። ውሸታቸውን ስልቅጥ፣ዋጥ አድርገዋት ሌላ ጥፋት ደረቡበት።
“ህጻናትን ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው።” የሚለውን የክርስቶስ ጥቅስ ቀየር አድርገው የራሳቸውን ፈንጠዝያ ሊነግሩን ሞከሩ።

“…ህፃናትና ታደጊዎች የዋሆች እንደሆኑ ክፋት እንደሌላቸው ከኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። በዚህ ምክንያትም ህፃናትና ታዳጊዎች የሚነግሩኝን ማመን እመርጣለሁ። ስህተትም ቢኖራቸው ከየዋህነት ካልሆነ ከክፋት አይመነጭም። ህፃናትን ማመን ስህተት ከሆነ መሳሳትን እመርጣለሁ።…”

አይቴ ቴድሮስ በዚያ በልካቸው ባልተሰራ ወንበር ላይ ተቀምጠው ከሰሞኑ በርካታ ህጻናትን እንደሚያስተናግዱ ይጠበቃል። ከውጭም ከሃገር ውስጥም ኢቨስተር ህጻናት ወደ ቴድሮስ ቢሮ ይጎርፋሉ። በሚሊዮን እና በቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እናደርጋለን ብለው ይዋሻሉ። ቴድሮስም በፌስ ቡክ ገጻቸው ታሪኩን ይለቀልቁልናል…ውሸቱንም ይለቁልናል። እነሆ ህጻናትን ማመን ስህተት አይደለምና እንዲዋሹ ተፈቅዶላቸዋል።

አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል የሚባለው እውነት ነው። ጭንቅላት ሲገለጥ ደግሞ ገመና ይወጣል። በህወሃት መዋሸት አዲስ ነገር አይደለም። ሰዎቹ በቀን ከመቶ ግዜ በላይ ይዋሻሉ። በስነልቦና ተመራማሪዎች እነዚህን ሰዎች ፓቶሎጂካል ውሸታሞሽ ይላቸዋል። ይህ በሽታ ሰዎች ካሉበት ችግር ለማምለጥ ወይንም ከተቆራኛቸው የበታችነት ስሜት ይመጣል። ውሸት መናገር፥ አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲባል ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው። ለዚህ የስነ ልቦና ችግር ከጥቅሙ ይልቅ የረጅም ጊዜ ጉዳቱ ያመዝናል። የሚዋሸው ሰው በሰዎች ዘንድ የሚኖረውን ተቀባይነትን የሚያሳጣ ስብዕናም ያላብሳል። ችግሩ የስነልቦና ነውና መፍትሄውም የስነ-ልቦና ህክምና ነው።

አንድ አባት ልጁን ይጠራውና “ልጄ፣ ጥፋት ካጠፋህ የቤታችን ውሻ ስለሚነግረኝ ተጠንቀቅ።”ይለዋል። ልጁ ውሻ የሚሰማ እና የሚናገር ይመስለው ኖሮ ውሻውን እየቀረበ ያናግረው ነበር። ነብስ እስኪዘራ ድረስም ይህንን ውሽት አምኖ ተሸወደ።

የቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ተገላቢጦሽ ሆነብን። ነብስ እስኪዘራ ድረስ… ህዝቡን መሸወድ ተያይዞታል። በዚህ የመረጃ ዘመን ነጭ ውሸት ዋሽቶ ሲያበቃ፣ ውሸቱ ሲነቃ ሌላ ታሪክ መፍጠር ህዝቡን ዝቅ አድርጎ መመልከት አይመስልም? 20 ሚሊየን ዶላር እኮ ከ20ሺ ዶላር ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ዶላር ከ 200 ሺም ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ከ 2 ሚሊዮንም በ10 እጥፍ ይበልጣል። 20 ሚሊዮን በጣም ተጋነነ። ከአንድ ጀምረው ቀስ በቀስ እያሳደጉ ወደዚያ ቢደርሱም አንድ ነገር ነው።

ጃፓኖች እንዲህ ይላሉ። “የሚታመን ውሸት ለመዋሸት ከፈለግህ የማይታመን እውነት አትናገር።”
አይቴ ቴድሮስ በቅድሚያ ውሸትን በማንኪያ… ውሸትን በትንሹ ያለማምዱን! … ታዲያ እንደጀመሩ ይጨርሱልን።


የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል:: –‪‪‪‪‪‪ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

የአባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው ያሉ ጉዳዮች ወያኔን ውጥረት ውስጥ ጨምረውታል::ይህ የትግሉ አንድ አካል የሆነ የድል ጥርጊያ መንገድ ለፖለቲካ ድል ልንጠቀምበት ይገባል::የአባይ ግድብ ትከትሎ የመልስን መሞት አስታኮ ግለሰቡን አባይን የደፈረ መሪ በማለት እስከማላዘን ተደርሷል::የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየን ከሆነ የኢትዮጵያ የመጨረሻእ ንጉስ ሃይለስላሴ አባይን ለመገደን ይህንኑ የግድብ ዲዛይን አሰርተው ነው ዲዛይኑ በገንዘብ ኖቶች ላይ ሳይቀር ታትሟል; በጊዜው..ወያኔ ያንን ዲዛይን በዘመናዊ መሃንዲሶች አሻሻለው እንጂ አዲስ ነገር አልፈጠረም::

አሁን እየሰማንው ያለነው ደሞ አባይ የሚገደበው ሱዳን እና ግብጽ በፈለጉት መንገድ መሆኑ እየተነገረን ነው:: አስቀድመን እንደተናገርነው የህዝብ መብቶች ሳይረጋገጡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሳይገደቡ ህዝብን በግዳጅ ከጉሮሮው በቦንድ ስም እየነጠቁ ሕዝብ ያተዋጠለትን ሕዝብን ያላሳተፈ ግድብ እገነባለሁ ብሎ መነሳት ከባት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል ይህንንም ኪሳራ እያየነው ነው::ወያኔ ከሱ በላይ አዋቂ እና ከሱ በላይ ልሃገር ለህዝብ ጠበቃ የልማት ቡድን አድርጎ ቢንጠራራም ራሷን ከፍ ከፍ ያደረገች ማሽላ አንድም ለወንጭፍ አንድም ለውፍ .. የሚለውን ያስታውሰናል::

ወያኔ የሰበሰበው ቦንድ ለንግድ ድርጅቶቹ ካፒታል ማሳደጊያ ካደረገው በኋላ እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ በእኩይነት የተከበበ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ያለውን መፈረካከስ ሙስና እና የፓርቲ ካድሬዎች መበስበስ እንዲሁም የተቃዋሚው ጎራ መጠናከር በጣም ስላሰጋው በተጨማሪም የኤርትራ ጋር ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱ በአባይ ግድብ ላይ ያለው ልፍስፍስ አቋሙ የባሰ ሽባ በመሆኑ እጁን ለግብጽ እና ሱዳን እንዲሰጥ ተገዷል::ከኤርትራ ጋር ጦርነት ብንገጥም ሱዳን እና ግብጽ በተዝዋዋሪ ሊያጠቁን ይችላሉ የሚለው የወያኔ ጭንቀት እንዲሁም ለአባይ ግድብ ያሰበው ሁሉ ሳይሳካ በባዶ ስላስቀረው በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚም በባዶ ካዝና ስለቀረ መጣፊያው ያጠረው ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የአባይን ግድብ ለግብጽ እና ሱዳን አስረክቧል::አሁንም የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ከአባይ ግድብ በፊት የሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ::የሰባዊ መብት እና የህዝቦች ነጻነት ባሌለበት አገር በልማት ስም ራስን መቆለል እንደምናየው ውርደቱ በአደባባይ ያጋልጣል::ኢትዮጵያውያን ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን በወያኔ መቃብር ላይ ነጻነታችንን ማረጋገጥ አለብን::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ወገኔ›› የተሰኘውን ሙዚቃ እንዲቀሰቅስበት ፈቀደ!

$
0
0

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ በቅርቡ ‹‹ወገኔ›› በሚል ያወጣውን ዜማ ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በ2007 ዓ.ም አዲስ ላወጡት <‹ወገኔ›› የተሰኘው ነጠላ ዜማ ያለውን አክብሮት እየገለፀ፣ እርስዎ በስራዎ የገለጹትና ፓርቲውም የሚታገልላት አንድነቷ የተጠበቀላት ኢትዮጵያ እንድትኖር ለሚሰራው ስራ ይጠቀምበት ዘንድ ሙዚቃውን እንዲፈቅዱልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡›› ብሎ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት አርቲስቱ ፓርቲው ‹‹ወገኔ›› የተሰኘውን ዜማ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ገልጾአል፡፡

ወገኔ – አዲስ ዘፈን በብርሃኑ ተዘራ እና ጃኪ ጎሲ ሊያዳምጡት የሚገባ

አርቲስ ብርሃኑ ተዘራ ለሰማያዊ በፃፈው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹ወገኔ› የተሰኘውን ሙዚቃዬን ለመጠቀም የጠየቀኝን ፈቃድ በሙሉ ፍላጎቴ መፍቀዴን በፊርማዬ አረጋግጫለሁ፡፡›› ሲል ገልጾአል፡፡11016831_887283574647575_4587006491030127863_n

ምርጫውን ለህዝባዊ እንቢተኛነት እንዴት?። ዳዊት ዳባ

$
0
0

ህዘባዊ እንቢታ ማለት ዜጎች የስርአት ለውጥን ሆነ መብታቸውን ለማስከበር በብዙ ቁጥር ሆነው በጋራ አንድን ነገር ማደረግ ወይ አለማድረግ ነው። አለቀ። ብብዙ ቁጥር ተቃውሞ አደባባይ መውጣት በጋራ ልናደርጋቸው ከምንችላቸው በትንሹ ከሺ ነገሮች ውስጥ አንዱ የህዝባዊ ተቃውሞ አካል ነው። ተቃውሟችንን ለመግለፅ በጋራ ልናደርጋቸው የሚቻሉን ነገሮች ሁሌ የግድ ከባድም አጋላጭም መሆንም የለባቸውም። በይበልጥም ስንጀምረው።

ማወቅ ያለብን አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር እስከነፃነቱ እንዲሆን አልሞ ነው። ሲፈጥረው ባስፈለገው ጊዜ አፈጣጠሩን በሙሉ ነፃነቱን ማስጠበቂያ አድርጎ እንዲጠቀምበት ነው። ሀሰት የሚል ካለ ይህንን አፈጣጠሩን ነፃነቱንና መብቱን ማስከበርያ አድርጎ ሊጠቀምበት አይችልም ይበል። እኛም ኢትዬጵያዊያን ሰዎች ነን። የሰው ልጅ እንደመሆናችን ስሜታችንን ፤ አካላዊ እንቅስቅሴያችንን፤ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አካላችንን ፤ድርጊታችንን፤ አኗኗራችንን፤ የማሰብ ችሎታችንን፤ ፍላጎችንን፤ድምፃችንን ብቻ ሁለንተናዊ አፈጣጠራችንን መጠቀሙን እናውቅበታለን አናውቅበትም ነው እንጂ ጉልበታሞችን ልክ ማስገቢያ ካምላክ የተሰጠ ሀይላችን ነው።

ነፃነቱን ገፋፊው አንድ ግለሰብ ሲሆን ተገፋፊው ይሰራል ያለውን አፈጣጠሩን ተጠቅሞ በመዝጋትም ሆነ ልክልኩን በመንገር እንደሁኔታው አናቱን በድንጋይ በመበርቀስ ነፃነቱንና ክብሩን ማስመለስ ይችላል። ነፃነቱን የቀማው መንግስት ሲሆን ግን ብቻውን ሆኖ አደባባይ ላይ ወጥቶ በመጮህ ሆነ ተኩሶ እንዳሰበው ተፅኖ ፈጣሪና ውጤታማ ትግል ለማካሄድ ሁሌ የተሳካ ላይሆን ይችላል። በወረደ ምሳሌ፤- አንድ ሰው ብቻውን አገዛዝን ለመታገያና ተቃውሞውን ለመግለፅ አስቦ እደጅ ቢፀዳዳስ። ሲጀመር እስከጭራሹ ለምን እንዳደረገውም ላይታወቅ ሁሉ ይችላል። ነግር ግን ነፃነታቸውን የተነፈጉ በሙሉ አንድ ቀን ወስነው እጅ ለእጅ ተያይዘው እደጅ ቢፀዳዱስ። ይህ በቀጥታ ነቅንቅ የሆነ ተቃውሞ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ አይገባም። { አይዞን ምሳሌ ነው። ካስፈለገ ተባብሮ ማፅዳቱንም ቀጣይ የተቃውሞ አይነት ልናደርገውም እንችላለን }።

ወያኔ ምርጫውን የትላልቅ ልጆችች እንኳ ሳይሆን የሚጢጢዎች እቃቃ ጫወታ አደረገው አይደል!። የሚፈለግ ነው። ፋይዳው ይህን ያህል ነው እንጂ ስለማሳጣት ከሆነ ከዚህ በላይ ያማያሳጣ የተዘርበጠበጠ ነገር ታይቶም ተሰምቶም የሚታወቅ አይመስለኝም። ለለውጥ እየታገለ ባለው ክፍል አላማው በዋናነት ማሳጣት ስላልሆነ ግን አሁንም ወጥሮ መያዝ ነው። ይህ መዘርጠርጥ የት ሊዶል እንደሚችል ማን ያውቃል። አሳምርን እንደምናውቀው ወያኔዎች ምርጫ ተካሂዷል። በውጤቱም እንደእስካሁኑ በቃ አሸናፊ እኛ ነን ብለው ፋይሉን ሊዘጉ የሚችሉባቸው በድንብ የሚያውቋቸው ሌሎች መንገዶች ነበሩ። በዛ ላይ ተቃዋሚዎች በአፈናው ምክንያት ተዳክመው ባሉበት። ያበረና ጠንካራ ተቃዋሚ እንደሌለ እኛም እነሱም እያወቅን። ታዲያ ይህ ሁሉ ቦኩሀራማዊ(ለመረዳት አስቸጋሪ) እርምጃ ለምን? ለሚለው መልስ ለመስጠት ስንሞክር ብቻ ነው በእጅጉኑ ያሰፈራቸው ጉዳይ እንዳለ የሚገለፅልን። ከዚህ ውጪ የሆኑት ሌሎቹ መንገዶች በሙሉ አስበውበት የፈሩትን ነገር ሊያስከትል የሚችሉበት የተሻለ እድል ያላቸው ሆነው ታይቷቸዋል ማለት ነው ብለን በእርግጠኛነት እንድናምን የሚያደርገን። ታዲያ የፈሩት ምንድን ነው?።

በበዛው ዜጋ ዘንድ ከፍተኛ ምን አልባትም መጨረሻው ደረጃ የደረሰ የታመቀ ቁጣ አለ። ለብዙዎች መራብ ደረጃ የደረሰ የመረረ ችግረር አለ። መሰልቸት አለ። በውርጂብኙ በቀጥታ ተጎጂ መሆን አለ። መረን የለቀቀው አዶሎ ለሁሉም ዜጋ ሰውነት የሚያመነምን ደዌ ሆኗል። ይህንን አይነቶቹ ህዘብ እንዲያምፅ የሚያደርጉ ምክንያቶች ፈልትው ፈልተው ያሉበት ሁኔታ ማንም ቢገመግመው የሚደርስበት ተጨባጩ የአገራችን እውነታ ነው። የሰሞኑ ቦኩሀራማዊ ድርጊቶቻቸው ሁሉ ገላጭነቱ ይህንን ዜጋው እንዲያምፅ ሊያደርገው የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለክተው ደረጃውን አሳምረው ማወቅ መቻላቸውን ነው የሚያሳየን። ልናምፅ ይሆናል የሚለው ሀሳብ እጅጉኑ እንዳስፈራቸው የሚያመላክት ነው። በየትኛውም አገር ምርጫ ብዙ ዜጎች በቀጥታ ተሳትፎ የሚያደርጉበትና ፖለቲካዊ ትኩሳትና መነቃቃት የሚጨምርበት ጊዜ ስለሆነ አጋጣሚውን ተገን አድርጎ የታመቀው ቁጣችን ይፈነዳል የሚል ድምዳሜ ላይ አስረግጠው መድረሳቸውን ያሳያናል።

ያም ሆኖ በነሱ በኩልም ሆኖ ለማየት ቢሞከርም ያዋጣል ብለው ከያዙት ፈላጭቆራጭ ከሆነው መንገድ ውጪ ሌላ አይነት የተሻለ መንገድ አልነበረም ማለት ግን አይደለም። የሚያሳየን የፍራቻቸውን ጥልቀትና እውነተኛነት ነው። ባዛ ላይ የምናወራው ለጉድ ስለነገሱብን ስለወያኔዎች ነው። ከደረጃቸውና ከባህሪያቸው አኳያ ሌላው መንገድ አዋጭ ሆኖ ሊታያቸው ባይችልም አይገርምም። ስለዚህም በወሰዱት እርምጃ የምናለቅስበት መሆን የለበትም። ካወቅንበት ጠሩም ጠቃሚም ነው። በእርግጥ አዛላቂና አዋጭ እየሆናቸው ይቀጥል ወይ?። ሁላችንም በቶሎ መልስ ልንሰጥበት የሚገባ ጥያቄ ነው። ይህ የታመቀ የህዝብ ስሜት በምን መንገድ?፤ በምን ጥንካሬ?፤ በምን አይነት አብሮነት?፤ በምን አይነት አመራር? ይተገበራል በሚለው የሚወሰን ይሆናል። በይበልጥ በተሻለ ነፃነት ውስጥ በሚሰሩ ድርጅቶች ሁኔታውን መጠቀም መቻል ጋር። ለለውጥ የቆሙ ሜዲያዎች ሁሉ ህዝባዊ እንቢታውን እውን በሚያደረግ መንገድ በዋናነት መቃኘት መቻል ጋር። ትግሉ ላይ በየትኛውም መንገድ ጎልቶ የሚሰማ ተፅኖ አሳዳሪ ድምፅ ያላቸው ዜጎች ዋና ትኩረት መሆን መቻል ጋር በቀጥታ ይያዛል።

አገር ውስጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች ያለው ሁኔታ በሚፈቀደው ጥሩ ይዘዋል። አሁንም ያለው አማራጭ አበርትቶ አዳዲስ ፈጠራና ማሰብ በታከለበት መቀጠል ነው። ዛሬም የዚህ ጥረት ፋይዳ ላልታየን ግን አገር ውስጥ ሆነው፤ ለዛወም በቀጥታና በዋናነት የሚቀጠቀጡት እነሱ ሆነው ሳለ የተያያዙት ትግል መከራ ስለበዛበት ብቻ ትተን አንቀመጥም። ምርጫውንም ወጥታችሗል እስክንባል አንጫወተዋለን ማለታቸው ትክክል ናቸው። የትግሉ ሻማ እንደበራ ሲቀጥል ብቻ ብዙዎቻችንን ጨምሮ ትግሉ መሰረታዊ ባህሪውን ቀይሮ ወደ ህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚቀየር አሳምረው ስለወቁ ነው። በእርግጥ ሂደቱን ያፈጥኑ የነበሩ ጉዳዬች ገና አልተሟሉም። ህዝባዊ እንቢታው ባለቤት የለውም። ባብዛኛዎቻችን ለአፍ እንጂ ዋና ትኩረት ገና አልሆነም።

ይህም ሆኖ የምርጫውን ሂደት ትግሉን በሚጠቅም መንገድ መጠቀምን በተመለከተ በዜጎች በኩልም ልንመዛቸው የምንችላቸው ጥሩ ጥሩ ሾጥ ማድረግያ ዱላዎች አሁንም አሉት። እየመዘዝን በመጠቀም አስቸጋሪም ግራ የሚያጋባቸው፤ ተስፋ አስቆራጭ እንዲሆንባቸው ማድረግ የምንችልባቸው። ተናበን የምርጫ ካርዳችን ላይ “ እናታችሁ አፈር ትብላ “ብለን ፅፈን ወርውረንላቸው መውጣት ችለን ከነበረ አሁንም በተመሳሳይ በጋራ የምናደርገጋቸውን ነገሮቸ ማሳደግና ይህን አይነቱ በጋራ ልናደርጋቸው የምንችላቸው የተቃውሞ አይነቶች ላይ መካን ነው የሚፈልገው።

በጥቂቱ ምርጫ ውስጥ ያሉ ታቃዋሚዎች ቀን ቀጥረው ወደኛ ሁሌ እንዲመጡ አንጠብቅ። እኛ በብዙ ቁጥር በየጥያቄዎቻችንና ብሶቶቻችን ተቧድነን ወደነሱ እንሂድ። ይሄ አንድ ክፉየሆነ ሾጥ ማድረግያ ድላ ነው። ተቃዋሚዎቹም የሚቻልና ብዙ መሆናችንን ሲያዩ ለምርጫ ቅስቀሳም ብለው ይሁን ትኩሳቱን ለማታለቅ ቀጠሮ ይዛው ሊያገኙን የምርጫው ሂደት ከለላቸው ነው። ያኔ ደግሞ ግልብጥ ብለን አደባባዩ ላይ እንፈስና አስደንጋጭ እናደርገዋለን። ቀላሉ ደግሞ ምርጫ አለ እስካሉ ሁላችንም ስለቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ማውራት የተፈቀደም የምንችለው ነው። ሆን ብለን በአንመርጥህም፤ በአትመረጡም ወሬ አገሩን ከነገ ጀምረን መሙላት እንችላለን። ትግል አድርገን ከያዝነውና ሁላችንም ከተሳተፍንበት ማውራቱ ብቻ በራሱ እንኳን ለዶሮ ለለአንበሳም ፈንጋይ ነው። ስለምርጫ ማውራት አሸባሪነት ነው። በሞት ያስቀጣል የሚል አዋጅ ያወጡና ደግሞ ያኔ ሙድ እንይዝባቸዋለን። ተመስገንን በማሰብ ሁላችንም ሻርብ አንገታችን ላይ ጣል ለሳምንት ማድረግ እንችላለን። ይህን አይነት አንድ ሺ በጋራ ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ቀላል ነገሮች መዘርዘር ላሰበብት በጭራሽ ከባድ አይደለም።?።

ይህን ወይ ያንኛውን ተቀናቃኝ ከምርጫው አገደ። ይልቃልን ወይ ወይንሸት “በእጣ” ምርጫውን እትወዳደሩም አሏቸው። ይህን ስለ አንድነት ፓርቲ ወይ ሰለሰማያዊ ፓርቲ ወይ ስለወይንሸት አድርጎ የሚወስድ ካለ ኢትዬጵያዊ ሆኖ ባልተፈጠረ ይሻለን ነበር። ለክብሩም፤ ለነፃነቱም ለመብቱም ዋጋ አይሰጥምና። ጭራሹኑ እየተደረገ እየሆነ ያለው የገባውም የሚገባውም አይደለምና።

በግልፅ መታወቅ ያለበት አማራጭ አትሆኑም ብለው የከለከሏቸው ጊዜ ያኔ ስለነሱ መሆኑ ያቆማል። ስለኛ ስለዜጎች ሆኗል። ቢገባቸው ለወያኔ ደጋፊዎችም ጭምር። ያም ሆኖ አሁንም ቢሆን አገደ ወይ ከለከላቸው ማለት ምርጫዎቻችን ልናደርጋቸው እንችልም ማለት አይደለም። ሁለተኛ ዱላ በሉ። ምርጫዎቻችን መሆናቸውን ሊደበቅ በማይችል ተሸናፊም በሚያደርግ መልኩ አለም ሁሉ እንዲያውቀው ማሳየት አንችላለንና። መምረጫ ካርዳችንን ወደላይ በጃችን ይዘን። ደረታችን ላይ የተከለከሉትን ድርጅቶች ወይ ግለሰቦች ፅፈን። በነቂስ ወጥተን በየምርጫ ጣቢያው ለመምረጥ መሰለፍን ማን ነው የሚከለከልን። ወያኔ እንደተጨማለቀ የምርጫው ሂደት ይቀጥላል እስካለ ልናደርገው የሚቻለን ሌላ አሀ ብለን ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ኮሮጆ ገልብጦ አሸንፌያለው ለማለት ያቆበቆበ ባለበት ምርጫችንን በሆዳችን በድብቅ የሞኝ ነው። ድምፃችንን ለቀማኛ ያለምንም መግተርተር እንዳሻችሁ ብሎ መተው ይሆናል። በመጨረሻ የተሻለ ውጤታማ ነው ተብሎ ውሳኔ ላይ ከተደረሰበትና ከታዘዝን ደግሞ የምርጫውን ቀን በቤት ዘና ስንል የምናሳልፈው የእረፍት ቀናችን ማድረጉንስ ማን ከልክሎን?።

ይህን አይነቱ ትግል በዚህ ዘመን በየሰኮንዱ ጢዝ ስሊ መረጃ እጃችን ላይ በሚመጣበት ዘመን ማስኬድ ቀላል ነው። በጋር ሆነን የምናደርጋቸው ተግባራትና ድረጊቶች ወሳኝና ጉልበታም ናቸው። አይደለም በጋራ ሁላችንም አድርገነው ልባሞች ብቻቸውን ሆነው ጊዜ፤ ቦታና ሁኔታዎችን አመቻችተው የሚያደረጉት ትግል ምን ያህል ነቅንቅ ሊሆን እንደሚችል በተደጋጋሚ አይተናል። በዛ ላይ በጋራ ማድርግ እንደሚቻል ለማስረገጥ እርቀን ከሌሎች ተጨቋኝ ህዝቦች ተሞክሮ ማፈላለግ የለብንም። በዚሁ ዘመን እኛው አገር የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ከዚሁ ክፍል ጋር ውጤታማ በሆነ መንገድ ሲታገሉበት እያየን ነው።

ነጻነታችንን አብዝተን ተርበን ከሆነ። ማልቀሱን ትተን አንድ ነገር ልናደርግ ከወሰንን። የሁላችንንም ተሳትፎ ያለበትን ናፃነታችንን የምናውጅበትን መንገድ በዝርዝር ነግሮን ሲጨርስ ነው የታሰረው። የሚጨመር ነገር የለውም። ህዝብ ውስጥ ስላለና የብሶቱን ደረጃ በየቀኑ መለካት ስለሚችል አደባባዩን አሁኑኑ። ይህን ቁጣ ይዞ በገፍ ፍቱን መድሀኒት መሆኑን ነግሮናል። እነሱ ሊመሩት ይችላሉ ያላቸውም ክፍሎች ነበሩ። የትግሉ እራስ የት እንዳለ ባይታወቅ ይሻላል። ደግሞስ በውጪስ ቢሆን የሚለው አማራጭም በእርግጥ አለ። ይሄንኛው መንገድም የዋዛ እንዳልሆነ ታይቷቸው ለዚህ አይነቱን ትግል ላይ ሀላፊነት ለመውሰድ በሚመስል ወደፊት እየመጡ ያሉ ድርጅቶች አሉ። እሰየው ነው።

እንኳና ብዙ ሆነን በሰሞኑ የውሸቱ ሲኖዶስ መሪ ላይ ጫማ መወርወሩ ሀይለኛ ተቃውሞ ነበር። የሚያሳዝነው ከዚህ በላይ ልናጮህው እንችል ነበር። ግለሰቡ ሲደርገውም ይህን ገምቶ የነበረ ይመስለኛል። ምን ያደርጋል ከነሱ ጎጥ ስለሆኑ ሰውዬውን ፀሀይዬ አፈላልጎ ስልጣኑ ላይ እንዳስቀመጣቸው እያወቁ መንፈስ ቅዱስ ፀሃይዬ ላይ አድሮስ ቢሆን የሚሉ በቃ” የዋሆች” ብዙ ስለሆኑ ሳይካበድ ቀረ። በዛ ላይ ደግሞ ያገዛዙ ሰዎችና ጥራዝ ነጠቆች ተረባርበው ሴትን ልጅ እርጉዝ ነኝ እያለችው ሆድ ቀጥቅጦ ፅንስ ማስወረድ ባህላችን ይመስል የኛ ባህል አይደለም ጫጫታቸውን በቶሎ ጣርያ አስነኩትና ጥረቱን ገደሉት። ከዚህ በፊት ያ መናጢ የሞተ ጊዜ የምናዝንበት መንገድ እንጂ ማዘን ወይ አለማዘን የስሜት ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ባህል እንዴት እንደሆነ ባይገባንም ባህላችን አይደለም ተብሎ ስንሞገትበት እንደነበረው ማለት ነው።

ወንዱሜ አጋጣሚዉን ደግመህ ካገኘህ ሌሎቻችንም ብንሆን ጫማ አይደለም ካልሲ ጨምራችሁ ወርውሩ። ለማሸነፍ ለሚታገል የተቃውሞ ትንሽ የለውምና። እንደውም ውጤት እንዲኖረው ተደርጎ ያልተሰራ የትግል አይነትና ተቃውሞ እንጂ የማይስራ የሚባል ነገር የለም። አንዱ የትግል አይነት ከሌላው ጋር ተዛማጅ፤ ተባዥ፤ ተጋጋዥ ነው። ማሸነፍን ከፈለግን የሚጠቅመን ካልሲ መወርወር እንዴት? መቼ? በምን አይነት ሁኔታ? ቢወረወር የተሻለ ውጤታማ ይሆናል የሚለውን ሁሌም ማስላትና ነው።

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ –በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው አክሎም ‹‹የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው አክሎም ‹‹የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል›› ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው›› ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡
የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም ‹‹ህወሓት-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ብአዴን-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ኦህዴድ-ኢህአዴግ›› እና ‹‹ደኢህዴን-ኢህአዴግ›› በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡ርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል›› ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው›› ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡
የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም ‹‹ህወሓት-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ብአዴን-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ኦህዴድ-ኢህአዴግ›› እና ‹‹ደኢህዴን-ኢህአዴግ›› በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡11039154_782669048490116_1134843809282896994_n10459922_782669068490114_3327966333789706114_n

የምርጫ ቅስቀሳ እገዳ –ባንዲራ ማዉለብለብ ወንጄል ሆኗል –ግርማ ካሳ

$
0
0

የምርጫ ጊዜ ነው ይሉናል። ባለው ሕግ መሰረት፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ በመሳሰሉት ሜዲያዎች መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ማድረግ መብታቸው ነው። በዚህ መሰረት የቅስቀሳ መልእክቶቻቸው እንዲተላለፉላቸው ይጠይቃሉ። ሆኖም ሜዲያዎቹ ፣ የቀረቡት መልእክቶች ሕወሃትን እና ሕወሃት ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠራቸውን ተቋማት የሚተቹ በመሆናቸው ሊያስተናግዷቸው ፍቃደኛ አልሆኑም።
ሕወሃትን መተቸት ብቻ አይደለም፣ አረንጓደ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ያዘሉ መልክቶችም እንደ ወንጀል የተቆጠረበት ሁኔታ ነው ያለው። አይገርማችሁ ? እነ በላይ ዘለቀ የተፋለሙበት፣ እነ አጼ ዮሐንስ ደማቸውን ያፈሰሱበት ሰንደቅ የረከሰበት ዘመን ነው።
1. አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ኢትዮጵያን አይወክልም ነው ኢቢሲ እያለን ያለው።
ኢቢሲ የሰማያዊ ቅስቀሳ መልእክቶችን እንደማያስተላለፍ ከላካቸው ስድስት ደብዳቤዎች በአንዱ የሚክተለው ይገኝበታል፡
«በላካችሁት የምርጫ ቅስቀሳ መልእክት፣ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልእክታችሁ ዉስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው የሰንደቅ አላማ ምስል፣ የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክል፣ የሕግ መግስቱን አንቀጽ 3 እና የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 16 እና አንቀጽ 23 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2ን የሚጻረር ሆኖ አግኝተነዋል»
2. ግፍ በአገዛዙ ታጣቂዎች ደርሶብናል ብሎ መናገር አይቻልም
መኢአድ በቅስቀሳ መልእክቶቹ በአባላትና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርሰዉን ግፍ ለሕዝብ ለመግልጽ « የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና አመራሮች በፓርቲው መሪዎች፣ አባላቶችና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነና ግፍ የተሞላበት ድብደባ፣ መሰደድና የመታሰርና የመግደል እጣ ሲያደርሱባቸው ቆይተዋል » ይላል።
የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች ነፍሰ ጡር ሴቶች ሲደበድቡ፣ ብእር ያነሱ ሰላማዊ ኢትዮጵያዉያን መሬት አስተኝተው አጥንቶቻቸዉን ሲሰባብሩ በግልጽ በአደባባይ የተመለከትነው ነው። ሆኖም ኢቢሲ ለምን በሕዝብ ላይ ግፍና ጭካኔ የሚፈጽሙት ጨካኝ የሕውሃት ካድሬዎችና ታጣቂዎች ተነኩ በሚል ነው መሰለኝ፣ የስነ ምግባር ኮድ የሚሉትን በመጥቅስ መልክቱን ለማስተለፍ ፍቃደኛ አልሆነም።
«ይህ መልዕክት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11፣ ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ ላይ የተመለከተውን የሚጻረር ሆኖ አግኝተነዋል» የሚል ምላሽ በመስጠት ነው የፓርቲዎችን የመቀስቀስ መብት የረገጠው።
3. ምርጫ ቦርድና ፍርድ ቤት መተቸት አይቻልም
ምርጫ ቦርድ የሕወሃት ቅርንጫፍ እንደሆነና በቀጥታ ከሕወሃት በሚሰጥ መመሪያ እንደሚሰራ የታወቀ ነው። በአንድነት ፓርቲ ላይ የተወሰደው ኢ-ሕገ መንግስታዊ እርምጃ እንኳን ተራው ኢትዮጵያዊ፣ ራሳቸው የአገዛዙ ደጋፊዎችን ሁሉ ሳይቀር አፍ ያዘጋ፣ ምርጫ ቦርድን መሳቂያ ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቶችን በተመለከተ፣ በአብዛኛዉ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው። ዳኞች ለምን ፍርድ ቤቱን ተቻችሁ በሚል የሰባት ወራት እሥር የሚበይኑ፣ ከ20 ጊዜ በላይ ዜጎችን ፍርድ ቤት እየተመላለሱ የፍርድ ሂደቱና ክርክሩ እንዲቀጠል ማድረግ የተሳናቸው ፣ መጨረሻ ላይ ከሕወሃት አመራር ይሄን በይኑ የተባሉትን ወጥተው የሚያነቡ፣ ለሆዳቸው ያደሩ፣ ጥቁር ካባ የለበሱ ካድሬዎች መሆናቸውን አገር ሁሉ ያውቀዋል።
መድረክ፣ በምርጫ ቦርድና በፍርድ ቤቶች ያላቸው ችግር “ ..እስከአሁን ድረስ በታዩት የምርጫ ሙከራዎች እና ምርጫ ነክ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በሃገራችን የኢሕአዴግን ፍላጎት ከማስፈጸም ያለፈ ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አልታየም ..የዳኞች ምልመላ እና ሹመት በሕግ እወቀት፣ ልምድና ሃቀኝነት መመስረቱ ቀርቶ ለገዥው ፓርቲው ባለ ቅርበት እና የ እርሱን ፍላጎትና ተጽእኖ ለመቀበል ፈቃደኝነት ኡእተመሰረተ በመሄዱ የዳኝነት ሰርራቱ ነጻነት የለም ከሚባልበት ደረጃ ላይደርሷል ..” በማለት ነበር በቅስቀሳ መልእክቱ ያቀረበው።
ሆኖም « እነዚህ መልእክቶች በሕግ መንግስቱ የተቋቋሙ የዲሞክራሲ ተቋማትን ሕልዉና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ፣ ህዝቡ በፍትህ አካላት ላይ አመኔታ እንዲያጣና መረጋጋት እንዲጠፋ የሚያደረጉ መልእክቶች በመሆናቸውና ሕገ መንግስቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ-ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11/2 ሐንና 29/1 እንዲሁም የድርጅታችንን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚጻረር ሆነው አግንተናቸዋል » ሲል ኢቢሲ/ኢቲቪ የመድረክን መልእክት አላስተናግድም በማለት የመድረክን ሕጋዊ መብት ረግጧል።
እንግዲህ እንደምናየው ገዢው ፓርቲ መልእክት እንዳያስተላልፉ እያገደ ያለው በዋናነት ሰማያው ፓርቲን ሆኖ ፣ በተወሰነ ደረጃም መድረክ እና መኢአድ መሆኑን እያየን ነው።
ሰማያዊም ሆነ ሌሎች እንደ ኢቢሲ ያሉትን ተቋማት ባይፈትሹ ኖሮ፣ የነዚህ ተቋማት እርቃን ባልወጣ ነበር። ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ አገር ሁሉ እያወቀው ነው። እየተመዘገበ ነው። አላወቁትም እንጂ ሕወሃት እየቀለለና እየወደቀ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተተፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው። በራሳቸው እንደማይተማመኑ፣ ህዝቡን እንደሚፈሩአን እንደደነገጡ አመላካች ነው። ምናልባት አሁን የሚያደርጉትን በዚህ በዚያ አሸንፈን ካለፍነው ለማንሰራራት ይረዳናል ብለው ይሆናል።፡ሆኖም በሚያስገርም ሁኔታ ምርጫው እየጎዳቸው ነው።11033173_788905021194434_841547304513731900_n

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ተላለፈባቸው! –በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

$
0
0

᎐ተጨማሪ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል
• ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ
• ‹‹ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው›› የሺዋስ አሰፋ
• ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፣ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› ዳንኤል ሺበሽ
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እንዲሁም የዓረና ትግራይ ፓርቲዎች አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በሦስቱ አመራሮች ላይ እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡
የካቲት 26/2007 ዓ.ም ተከሳሾች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸውና ንብረትም እንደተወሰደባቸው በመግለጽ አቅርበውት ለነበረው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ሙሉ ለሙሉ በመቀበል አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ 5ኛ ተከሳሽ አቶ የሺዋስ አሰፋ በማጨብጨቡና 3ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 4ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ሳይፈቀድላቸው ‹‹ጥሩ ፍርድ፣ ጥሩ ብይን›› በማለት አቶ የሺዋስን በመደገፍ ችሎት ደፍረዋል ተብለው ጥፋተኛ መሰኘታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ተሰይሞ በአብርሃ ደስታ፣ በየሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ ላይ የሰባት ወራት እስራት በእያንዳንዳቸው ላይ ወስኗል፡፡ ሦስቱም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ድጋሜ ችሎት ውስጥ አጨብጭበዋል፡፡ በዚህም ድጋሜ ጥፋተኛ ተብለዋል፤ ከሁለት ቀናት በኋላም የቅጣት ውሳኔ ይወሰንባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሦስቱ ተከሳሾች ‹‹እድል ስጡን እንናገር፣ አቤቱታም አለን ተቀበሉን›› ቢሉም ፍርድ ቤቱ ሊሰማቸው አልፈለገም፡፡ በተለይ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹ሌላ አቤቱታ አለኝ፣ ፍርድ ቤቱ ያዳምጠኝ›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ አሁንም ችሎቱ ላይ እያፌዛችሁ ነው በሚል ጥፋተኛ ሲላቸው ሦስቱም አመራሮች ፍርድ ቤቱን ማስፈቀድ ሳያስፈልጋቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው፡፡ ‹Already› የተደፈረ ችሎት ነው›› ሲል አብርሃ ደስታ ተናግሯል፡፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ጣልቃ በመግባት፣ ‹‹የምትናገረው ነገር እንደገና ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚወስድህ ጉዳይ ነው፤ ምርመራ ይደረግበታል›› ሲሉ አብርሃ በበኩሉ ‹‹አሁንስ ቢሆን የምናገረውን ፖሊስ እየሰማ አይደለምን?›› ሲል መልሷል፡፡
አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩሉ ‹‹ከስምንት ወር በላይ ታፍነናል፡፡ በህግ አይደለም የተያዝነው፡፡ ደግሞ ማጨብጨባችን በችሎቱ ከማፌዝ ሳይሆን ከምሬት በመነጨ ነው፡፡ ህገ-መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል፡፡ እኔ ለምሳሌ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆኔ ነው የታሰርኩት፡፡›› ብሏል፡፡
አቶ ዳንኤል ሺበሽ ድግሞ ‹‹አሁንም ችሎት ደፍራችኋል ካላችሁ ቅጣቱን ጨምሩብንና ሸኙን፡፡ በእርግጥ ዳኞች ላይ ያለውን ጫና እንረዳለን፡፡›› ሲል ችሎት ውስጥ ተናግሯል፡፡
በዚህ ሁኔታ በተከሳሾችና በችሎቱ መካከል ያለው አለመግባባት ሲጨምር ዳኞቹ መጋቢት 3/2007 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ የቅጣት ውሳኔ እንደሚሰጥ በመጥቀስ ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ከችሎት እየወጡ እያሉም አቶ ዳንኤል ሺበሽ ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፤ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› እያለ ችሎቱን ለቅቆ ወጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት መውጣታቸውን ተከትሎ፣ ከዚህ ቀደም በማረሚያ ቤቱ ላይ በቀረበው አቤቱታ ዳኞች በሰጡት አስተያየት ላይ አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር በማስታወስ አቤቱታው እንዲመዘገብለት የጠየቀው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ‹‹በበኩሌ ያሉኝን መረጃዎች እያቀረብኩ ስነ-ስርዓቱን አክብሬ ክርክሩን አቀጥላለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡10653596_722906117794325_2186365328621114192_n

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው መደብደባቸውን ለቢቢኤን ሬድዩ ተናገሩ!

$
0
0

ወንበዴው መንግስት ተብየው ሽፍታ ሽፍትነቱን ቀጥሎበታል፡፡ የፍትህ ስርአትን ፍርድ ቤትን እንደ መጨቆኛ መሳሪያ የሚጠቀመው መንግስት በሚዘውረው ፍርድ ሲሞግቱት፤ ሲሸነፍ መክሸፍ ልማዱ ሁንዋል፡፡ የፍትህ ስርአቱ የደረሰበት ቁልቁለት፤የስርአቱን እብለት በማጋለጥ በኩል ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ታላቅ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች የነ አብርሃ ደስታ ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በስራቸው የተለያዩ ዛቻዎች ማስፈራሪዎች በደህንነቶች፤በፖሊሶች፤ በዳኞች ሲፈጸምባቸው ቆይተዋል፡፡ ከዚያም አልፎ ተርፎ የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም ክስ ተመሰርቶባቸዋል፡፡ የጥብቅና ፍቃድህ እንሰርዘዋለን የሚል ማስፈራሪያም ደርሶባቸዋል
እርሳቸው ግን ይህ ሁሉም ደርሶባቸው እውነትን ከማፍረጥረጥ፤ የአምባገነኑን የፍትህ ስርአት ሸፍጥ ከማጋለጥ አልቦዘኑም፡፡ በዚህ ድርጊታቸው የተበሳቸው መንግስት በዛሬው እለት ታስቦበትና ታቅዶበት በሚመስል መልኩ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶም ለቢቢኤን አስረድትዋል ቢቢኤን የዛሬ የመጋቢት 1 ፕሮግራም
ቢቢኤን High Quality like emoticon
Low Quality like emoticon http://goo.gl/UsS5lu

ይህ በርግጥም ስርአቱ በራሱ ፍርድ ቤት እየደረሰበት ያለውን ሽንፈትና ክሽፈት የሚያሳይ ነው፡፡ ወንበዴ መንግስት ይሄው ነው ሰበብ ፈልጎ ያስረሃል ያለ ስምህ ስም ይለጥፍብሃል ለማሰር አልመቸው ካልክ በዱርየ ያስደበድበሃል!11050826_535569786583084_855265809854853780_n


የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ከችሎት ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ወሰኑ -ነገረ ኢትዮጵያ

$
0
0

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት አቶ ገረመው ገ/ጻድቅ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ከችሎት ውጭ በግላቸው መወሰናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የምዕ/ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ መዋቅር ዕጩዎቻችን ያለ አግባብ ተሰርዘውብናል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ የነበር ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ የዱር ቤቴ ዕጩዎች የተሰረዙት ያለ አግባብ በመሆኑ በዕጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል፡፡

በተመሳሳይ የቀሪዎቹን ወረዳዎች ዕጩዎች ክርክርን ይዞ የነበረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ጉዳዩን እኔ አየዋለሁ በማለት ጉዳዩን ከሁለተኛ ምድብ ችሎት ከወሰዱ በኋላ የሌሎቹ ወረዳዎች ዕጩዎች በዕጩነት እንዳይቀጥሉ በግላቸው መወሰናቸው ተገልጾአል፡፡

በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተያዘ ክርክር ተመሳሳይ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባ እንደነበር ግልጽ ነው ያለው አቶ አዲሱ ‹‹ፕሬዝደንቱ ዳኞቹ ለዕጩዎቹ እንደሚወስኑ ስላወቁ ጉዳዩን ከደኞቹ ቀምተው ወስደው በግላቸው ወስነዋል፡፡›› ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል፡፡

‹‹በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ውሳኔ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ሁለተኛ ጉዳዩን መጨረስ የነበረባቸው መጀመሪያም ጉዳዩን የያዙት ዳኞች ነበሩ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ም/ፕሬዝደንቱ ብቻቸውን ማየት አልነበረባቸውም፡፡ ጉዳዩን ችሎት ሳይሰየም በራሳቸው ስለወሰኑ የዳኞች ፊርማ የለበትም፡፡ ከምንም በላይ ግን ውሳኔው ትክክልና ግልጽም ባለመሆኑ የውሳኔ ግልባጭ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡›› ሲል ም/ፕሬዝደንቱ ከህግ ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ መወሰናቸውን ገልጾአል፡:11067649_677252355733759_7267272117094212038_n

የመብት ህጎች እና ድንጋጌዎች የተቆለሉባት ግን የቤት ስራዋ የደቆሳት ሃገር –‪የምንሊክ ሳልሳዊ የሳምንቱ መልእክት

የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ!!

$
0
0

‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡
እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል››

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ ሲሆን ተወካዮቹ ወቅታዊ የምርጫ ሂደት እንቅስቃሴና የሰማያዊን የምርጫ እንቅስቃሴ፣ በምርጫው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ የፓርቲው አማራጭ ፖሊሲዎች፣ የድርጅቱን ጥንካሬ፣ የአንድነት አባላት ወደሰማያዊ መምጣታቸው ለትግሉ የሚኖረው ትርጉምና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰረዙበት፣ የፓርቲው የቅስቀሳ መልዕክቶቹ ከ6 ጊዜ በላይ በሚዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉን፣ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ፣ እስራትና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው በምርጫ ሂደት ኢህአዴግ አፋኝነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊን መቀላቀላቸው ትግሉን እንደሚያጠናክረው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድነትና መኢአድ ላይ የተፈፀመው ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እንዲሁም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በኃይል እያጠፋ ‹‹ከእኔ ውጭ አማራጭ የለም›› የሚል አቋሙን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳየት እንደሚፈልግ ለህብረቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

‹‹የአውሮፓ ህብረት ችግር የኢትዮጵያን ችግር በአውሮፓውያን ተቋማትና የስነ ልቦና ልክ ማየቱ ነው›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት ‹‹የተቃዋሚዎች አማራጭ ፖሊሲያቸው ምንድን ነው?›› በሚል የሚያነሱትን ተደጋጋሚ ጥያቄ አስታውሰው መደረጀትና መናገር ያልቻለውን የኢትዮጵያን ህዝብ በአውሮፓ ተቋም አይን አይቶ እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን ማንሳቱ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ
ሁኔታ አንጻር ብዙም እርባና እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ አገር የፖለሲ አማራጭ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ ሚዲያው በገዥው ፓርቲ የተያዘና የተቃዋሚዎችን ሀሳብ የማያስተናግድ ዝግ ሆኗል፡፡ እናንተ እንደምትገምቱት የፖሊሲ አማራጭ ለማቅረብ አመች ሁኔታዎች ቢኖሩ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ የተሻለ ምሁርራንና ሀሳብ ስላላቸው ዝርዝር ፖሊሲያቸውን ለማቅረብ አይቸገሩም ነበር፡፡›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ኢህአዴግ ‹‹ተቃዋሚዎች የተበታተኑና የተዳከሙ በመሆናቸው ለቀጠናው ሰላም አማራጩ እኔ ብቻ ነኝ›› ብሎ የአውሮፓ ህብረትን እንደሚያታልል የገለጹት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ኢትዮጵያውያን ካላቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማየት ስላልቻላችሁ ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ሲሉ አስረድተዋል።11024701_356603191190133_2206083571823058087_n

አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች ቴድሮስ አድሃኖም ውሸታቸውን እንዲያርሙ አሳሰቡ!

$
0
0

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የሚል ስያሜ አግኝተዋል!!
ጋዜጣዊ መግለጫ
ዋሽንግተን ዲሲ፤ አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች በአንድነት በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና በፌስቡክ ገጻቸው የተናገሩትን አጸያፊ እና ሃላፊነት የጎደለው ውሸት እንዲያርሙ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመገናኛ ብዙሃን ታዳጊ ወጣት በሪቱ ጃለታ የተናገሩትን የ20 ሚልዮን ዶላር የፈጠራ ታሪክ እስካሁን ባለማረማቸውና ህዝብን ይቅርታ ባለመጠየቃቸው፣ የድረገጽ አዘጋጆቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” (የፈጠራ ገጸ-ባህርይ) የሚል ስያሜ በአንድ ድምጽ ሰጥተዋቸዋል።

የአቡጊዳ፣ የአዲስ ቮይስ፣ የኢካድ ፎረም፣ የኢትዮፎረም፣ የኢትዮ ፍሪደም፣ የኢትዮ ሜድያ፣ የኢትዮጵያን ሪቪው፣ የቋጠሮ፣ የሳተናው እና የ ዘሃበሻ ድረ-ገጽ አዘጋጆች በጋራ በመሆን ይህንን አቋም የወሰዱት፣ ሚኒስትሩ በህዝብ ፊት በመቅረብ ነዋሪነትዋ በሜልቦርን ስለሆነው 14 አመት ተማሪ ብሪቱ ጃለታ በተናገሩት ፍጹም ሃላፊነት የጎደለው ቅጥፈት የተነሳ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሳምንታት በፊት ከታዳጊ ወጣትዋ ጋር በቢሮአቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤

“ነዋሪነቷ ሜልበርን ከተማ አውስትሬልያ የሆነችው የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ 20 ሚልዮን የአውስትሬልያ ዶላር ተሸላሚ ስትሆን፤ ያገኘችውን ገንዘብ በኢትዮጵያ ለልማት ለማዋል ወስናለች። በሪቱ በዚህ ዕድሜ ይህን ያህል ከፍተኛ ገንዘብ ለሃገር በማበርከት ተወዳዳሪ የሚገኝላት አይመስለኝም”

ማለታቸው የሚታወስ ነው። ይህ መግለጫ ከእውነት የራቅ ነው። የተጠቀሰው ባደን ኮሌጅ መግለጫው ሃሰት እንደሆነ ታናግሯል። የሽልማቱን ፈንድ ፈቀደ የተባለው ሮታሪ ተቋም እና የአውስትራሊያ መንግስትም መግለጫው ሃሰት እንደሆነ እና ለጉዳዩ እንግዳ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ሚኒስትሩ በአስቸኳAይ ይህንን ሃላፊነት የጎደለውን መግለጫ እንዲያስተባብሉ እና ያለምንም ማንገራገር ሕዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቁ እናሳስባለን።”

ሲሉ አስሩ የድረ-ገጽ አዘጋጆች ጠይቀዋል።

ይህ መግለጫ ፍጹም ሃስት የሆነ ታሪክ እና ፈጠራ መሆኑ በመረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ሚኒስትሩ ጥፋቱን በታዳጊዋ ህጻን ላይ ማመካኘቱን ትተው ራሳቸው ሃላፊነቱን እንዲወስዱም የደረ-ገጽ አዘጋጆቹ አሳስበዋል።beritu-and-family-1

አምስት የደህንነት አባላት ወደ ጨለማ እስር ቤት ተወረወሩ:: ‪- ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

የመከላከያ እና የደህንነት ግምገማዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ::ቀጣዩ ግምገማ ከዛቻና ማስፈራራት ወደ ልመና ሊዞር ነው::ባለፉት ሳምንታት በመከላከያ ሰራዊት በምድር ጦር እና አየር ሃይል እንዲሁም በደህንነት መምሪያ ሲደረጉ የነበሩ ግምገማዎች በስፋት ቀጥለው አባሎቻቸውን እያሰሩ እና እያስፈላሩ በመጭው ሳምንቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::
በመፍረክረክ ላይ ያለው ስርአቱ ባደረበት ከፍተኛ ስጋት እና በገባበት አጣብቂኝ ተከትሎ በመከላከያ ውስጥ እና በደህንነት ውስጥ በተከሰተው አለመተማመን የተጀመረው ግምገማ ወደባሰ ጥርስ መነካከስ መሸጋገሩን የጠቆሙት ምንጮቹ የወያኔ ባለስልጣናት በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት ሰራዊቱን እና ደህንነቱን ለመቆተጠር አለመቻላቸው ሲታወቅ ግምገማው ውጤት ባለማሳየቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምናልባትም ቀጣዩ ግምገማ ከማስፈራራት ወደ ራሳችንን እናድን ልመና ሊሸጋግር ይችላል ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::
ከምድር ጦር እና ከአየር ሃይል ተይዘው የታሰሩትን ጨምሮ በአሁን ወቅት ሌሎች አምስት የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነት ቢሮ ሰራተኞች መረጃ የጠቆመ ሲሆን በዚህም መሰረት :
1ኛ/ አቶ ተክሉ ወልደሃዋርያት .. በንፋስ ስልክ/ላፍቶእና የአቃቂ አከባቢ የስለላ ስምሪት አስተባባሪ
2ኛ/ አቶ አበራ ዋሴአንተ ….በንፋስ ስልክ/ላፍቶ እና ይዋቃቂ አከባቢ የደህንነት ሰራተኛ
3ኛ/ወይዘሪት መብራተይ ገብረአናንያ … በቅርቡ ከትግራይ መታ ቦሌ አከባቢ ካለ ቢሮ ተመድባ የነበረ
4ኛ/አቶ በክሪ አህመድ … የአፋር ክልል አከባቢ ተወላጅ እና በመርካቶ አከባቢ ተመድቦ ሲሰራ የነበረ
5ኛ/አቶ ይህደጎ (ወዲሰራዬ) …ኤርትራዊ ሆኖ ለወያኔ የሚሰራ::
እነዚህ ከላይ ስም ዝርዝራቸው የተጠቀሰው ሰዎች በተለያየ ጊዜ ከተመደቡበት ስራ ውጪ በመንቀሳቀስ በስራቸው ላይ ሆነው የተቃዋሚ ሃይላት በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ ጋሬጣ የፈጠሩ ለደምህት ድጋፋቸውን የሚሰጡ የውስጥ ቦጥቧጮች በሚል ግምገማ እና በሃላፊዎች ላይ ጥያቄ በማብዛት በስራ ላይ ሰበብ በመፍጠር የተገመገሙ እና ወደ ጨለማ እስር ቤት የተወረወሩ መሆኑ ታውቋል::በቡድን ህዝብን በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ የደህንነት አባላት ግን እንኳን ሊገመገሙ ይቅር እና በእኩይ ስራቸው ቀጥለው እንደሚገኙ ምንጮቹ ተናግረዋል::

የሚሊዮች ንቅናቄ ለሰማያዊ –አንድ ለአምሳ

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ ሕዝባዊ ትንቅንቅ ከገዢው ፓርቲ ጋር ይዟል። ሰማያዊዎች የሚያደርጉት ትግል የነጻነት ትግል ነው። የሚተማመኑት በማንም አይደለም በሕዝቡ ነው። በሕዝቡ ብቻ ! በእኛና በእናንተ ።
ገዢው ፓርቲ ሕወሃት የሰማያዊ ተወዳዳሪዎችን እያሰረ፣ ከምዝገባው እየሰረዘ፣ የቅስቀሳ መልእክቶቻቸውን ሳንሱር በማድረግ አልስተላልፍም እያለ፤ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ሲጠሩ እየከለከለ፣ ህዝቡ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሰማ ትልቅ ጫና እያሳደረ ነው። ይሳካለታል ወይ ? ያንን የምንወስነው እኛ ነን።

የሰማያዊ ፓርቲ ደግመን እንናገራለን የሕዝብ ፓርቲ ነው። ትላንት የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በሚል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በአገሪቷ ክፍል ሁሉ ያሉ አንድነቶች፣ አሁን በብዛት ሰማያዊ ሆነዋል። አሁን ሰማያዊ የምንለው ፣ ከአንድ አመት በፊት ሰማያዊ እንለው የነበረው ብቻ አይደለም። አሁን ሰማያዊ የምንለው ፣ ያኔ ሰማያዊ እንለው የነበረ፣ ያኔም አንድነት እንለው ከነበረው ጋር አብሮ የሆነ ነው። ያኔ አንድነት ሲያደረግ የነበረው የሚሊዮኖች ንቅናቄ አሁን የሰማያዊ ንቅናቄ ሆኗል።

በመሆኑም በሚሊዮን የምንጠር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ መነቃነቅ አለብን። ሰማያዊ በየወረዳው የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎችን ይፋ እንዳደረገ፣ በየወረዳው ፣ እንደ ንብ በመበተን የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ማስመረጥ አለብን።

በራዲዮና በቴሌቭዥን እገዳ ቢደረግም፣ እያንዳንዳችን በግላችን፣ ጎሮቤቶቻችን ጋር ሄደን፣ ሻይ ቡና እየጠጣን ፣ 10 ደቂቃ፣ 15 ደቂቃ አይደለም፣ ከአንድ ሰዓት በላይ በመቆየር መቀስቀስ እንችላለን። እነርሱ ከላይ ሁሉን ቢያፍኑትም እኛ ዉስጥ ዉስጡን ወደ ጎን መዘርጋት ይኖርብናል።

አንርሳ ። የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ ከገዢው ፓርቲ ጋር ሰላማዊ ፍልሚያ እያደረጉ ያሉት እነርሱ ከኛ የተለየ በደል ደርሶባቸው አይደለም። አብዛኞቹ እንደዉም የተማሩና ሥራ ያላቸው ናቸው። ሆኖም «እኔ ከተመቸኝ ስለሌላው ምን አገባኝ» ሳይሉ፣ የእያንዳንዲ ዜጋ መብት እንዲከበር ዋጋ ለመከፈል የተዘጋጁ ናቸው።

እነዚህ ወገኖች ለራሳቸው መብት በመቆማቸው ለኛ እየቆሙ እንደሆነ እያወቀን፣ እንዴት በአካባቢያችን ፣ የድርሻችንን መወጣት እንዴት ያቅተናል ?
ገዢው ፓርቲ፣ አንድ ለአምስት ይል የለም እንዴ። እነርሱ ለጥፋትና ለስለላ ፣ ለአፈና ነው። እኛ ግን ለጥሩ ነገር ተመሳሳይ ሥራ መስራት እንዴት ያቅተናል ?
ለምን አንድ ለአምሳ ብለን እንነሳም ?
እያንዳንዳችን ቢያንስ 50 ኢትዮጵያዉያንን፣ በቀበሌያችን፣ በትምህርት ቤታችን ፣ በስራችም እንዲመርጡ፣ ለሰማያዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ለምን አናደርግም ?
የምርጫው ዉጤት የፈለገዉን ይሁን። ግድ የለም። እኛ ግን እስከመጨረሻው ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርግ። ሰማያዊን እንደገፍ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !!!!!!!10858349_771934959558107_7876066551884502810_n

መድረክ “በፌዴራሊዝም ”ጉዳይ እንዳይከራከር ታገደ –ኪዳኔ

$
0
0

የኢህአዴግ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው በነገው ዕለት በቴለቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ይጀመራል፡፡ የነገው ክርክር ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ የተመለከተ ሲሆን ነገ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ተደርጎ ቀን ሙሉ ኢህአዴግ እማይጥመውን ንግግር በመቀስ ሲቆርጦው ከዋለ በኋለ ማታ ከ 2 ሰዓት ዜና በሁዋላ ይቀርባል ተብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና መድረክ በፌዴራሊዝም ላይ በሚደረግ ክርክር እናዳይከራከር ተከልክለዋል፡፡ ህዝብ ከህዝብ ጋር እያናቆረ ያለው አሸባሪው የኢሀአዴግ ፍረዳሊዝም እንዳንተቸውና አማራጭ ፌዴራሊዝማችን እንዳናቀርብ በጠበንጃ አምላኪዎች ታግደናል፡፡ በእውነቱ መጣም አሳዣኝ ነው፡፡ በዚህ ወሣኝ ርአስ ላይ እንዴት እንከለከላለን?
መድረክ እኔና ዶክተር መረራ ጉዲናን በፌዴራሊዝም ጉዳይ ላይ እንድንከራከር ወኩሎን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በኔ ሳንባ ከሚተነፍሱ ቅልብ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ነው የምከራከረው ብሎ እምቢ በማለት ህገወጥነቱን ቀጥሎበታል፡፡ ኢህአዴግ ከክርክሩ የጨረገደን በክርክሩ እንደምንዘርረው ስላወቀ ነው፡፡ አምስት አመት ሙሉ ጠብቀን ለመድረክ የተሰጠው 6 ደቂቃ ብቻ ነው ግን ኢህአዴግ 6 ደቂቃዋም በጣም ስለፈራት ከለከለን፡፡ አጃኢብ!
ለማንኛውም ነገ ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ በሚል ዶክተር መረራና የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብርሃም ሳልህ መድረክን ወክለው ይቀርባሉ፡፡


የማለዳ ወግ …መሰዊያው ያቃጠላቸው የእኛ ልጆች ! –ከነብዩ ሲራክ

$
0
0

ከእስክንድር ናፍቆት እስከ አንድነት ዘመነ፤
አይዞህ ወንድም አለም!!

…ምስላቸውን ተመልክቸ ፣ ታሪካቸውን ሰምቸ ስሜቴን ካናወጡት ጥቂት ምስሎች መካከል ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቅምጥል ከታዳጊ ናፍቆት በቅርቡ አባቱን ከታሳሪዎች መካከል ሲያፈላልግ የተነሳው የፖለቲከኛው ዘመነ ምህረት ልጅ አንድነት ዘመነ ተናጋሪ ምስልን ከሃገር ውስጥ ካየኋቸው ስሜት ኮርኳሪ ተናጋሪ ምስሎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። …

ከሃገር ወጣ ሲባል ደግሞ አስተማሪው በሞት የተነጠቀው ጥቁር ደቡበ አሜሪካዊ ማደጎ ዲያጎ አሳዳጊውን በሞት ተነጥቆ እንባ እያዘራ የሚያሳየው ምስልና ፍልስጥኤማውያኑ አባትና ልጅ አይዘነጉኝም!

ዲያጎ …

… ብራዚላዊ ወጣት ዲያጎ ከድህነትና አመጽ ነጻ ያወጡት የሙዚቃ አስማሪው በድንገት ተገድለው በቀብሩ ስነ ስርዓት ተገኝቶ ለሚወዳቸው የሙያና አባቱና ሰብአዊው ሰው ያለውን ክበር እንባውን እያዘራ ፍቅሩን ሲገልጽ የሚያሳየው ምስል ልብ በሃዘን ሰባሪ ነው …

መሀመድ አል ዱራህ …
ከሁሉም በቀዳሚነት ግን በእጎአ በ 200ዐ ዓም የሁለተኛው ፍልስጥኤማውታን አመጻ “ኢንቲፋዳ ” ወቅት ነበር ። በዚሀ ወቅት በሃገረ ፍልስጥኤም በአንድ የፍልስጥኤም አባትና ልጅ ምስል አሳዛኝ ትዕይንትና በጥይት የተደበደቡት አባትና ልጅ ህይዎቴንና እሳቤየን በብዙ መልኩ ቀይሮታል ። ..ድርጊቲ የተፈጸመው በማትረጋው ፍልስጥኤም ውስጥ ነው …በወቅቱ አመጻ ነውጥ ተነስቶ በነውጥ ሁከቱ መሀመድ አል ዱራ የተባለ አንድ ታዳጊ አባትቱን እየተከተለ በሽሽት እየሮጠ ከግርግሩ ሊያመልጥ ሲሞክር ይታያል። ብዙመ, ሳይቆይ አባትና ልጅ ከጥይቱ እርምታ ለማምለጥ በአንድ አጥር ተጠለሉ። ልጅ ከአባቱ ጀርባ ቢለጠፍም አባት የብላቴና ልጁን ህይዎት መታደግ ቀርቶ ራሱን ማዳን አልቻለም። በአጥሩ ታዛ አባት ተጎንብሶና ከጀርባው ተጣብቆ እጁን ከወደ ኋላው በመላክ በፍርሃቻ የሚርድ የሚሰፈሰፍ ልጁን ለመከላከል ሲሞክር በተንቀሳቃሽ ፊልሙ ይታያል .. ብዙም ሳይቆይ ግን አባትና ልጅ የአነጣጣሪው ወታደር የጥይት ራት ሆኑ ፣ በዚያ ፍልስጥኤማዊ አባትና በብላቴናው መሀመድ ላይ የሆነው ፈጽሞ አይረሳኝም ። በህይዎቴ ውስጥ ከባድ ለውጥ ካመጡት ምዕሎች ውስጥ መካከል ይህኛው ይጠቀሳል …

ናፍቆት እስክንድር …

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በሸብርተኝነት ተከሰው ባሉበት ናፍቆት እስክንድር በወህኒ ተወለደ ፣ አደገ ። ብዙም ሳይቆይ “በይቅርታ ምህረት ” ከአመት በኋላ ተፈታ ። ጋዜጠኛ እስክንድር ኢትዮጵያየ ብሎ መጻፉን ቀጠለ ፣ ህሳቤ ፣ አመለካከት የሃገር ህልሙን ማሰር የማይችሉት እስክንድርን ሲያጠምዱና ሲይዙ ልጁ ናፍቆትን ከት/ቤት ሲመልስ እንደነበር ሰምተናል። በመንገድ ዳር አስቆመው እስክንድርን ልጁን ናፍቆትን መንጭቀው ሲለያዩዋቸው ናፍቆት ” ከአባቴ አትለዩኝ !” ብሎ ተንሰቅስቆ ያለቅስ እንደነበር የሚያሳይ ፎቶ ባናይም ድርጊቱን ሲሰሙት ዘልቆ ያማል። ዛሬ ናፍቆትና እናቱ ሃገራቸው እልተመቻቸውምና ተሰደዋል …

ከጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች …

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ቤተሰቦች በተለይም እህቷ እስከዳር አለሙ በህገ መንግስት የተደነገገ የእስረኛ መብቷ ተገፎ ውዷንና አብሮ አደግ እህቷን ከማየት መከልከላሏን ሰምቻለሁ ። ጋዜጠኛ ተመስገንን በህገ መንግስት የተደነገገ የእስረኛ መብቱ ተፈፎ ለ40 ቀናት በዘመደ አዝማድ ፣ በሃይማኖት አባትና በሃኪም እንዳይጠየቅ የተደረገበትን ሁኔታ ተመልክተን አዝነናል ። የተመስገን እናት እንባ ፣ ምግብ ሊያቀብል ሄዶ ድንደባ የደረሰበት ወንድም የመብት ገፈፋ ተጠቃሸ ነው ።

በመሰዊያው ላይ ያሉት …
የጸሃፍቱ ፣ፖለቲከኞቹና አማኞቹ ቤተሰቦች

ኑሯቸው ወህኒ ለማድረግ የተገደዱት ፖለቲከኛው የአብዷለም ፣ የሃብታሙና የየሽዋስ አሰፋ ፣ የእስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፣ ጸሃፊ ሃያሲው አብርሃም ደስታ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በስም ያልጠቀስኳቸው ሁሉም “ወንጀላችን በህገ መንግስቱ የተሰጠንን መብት ተጠቅመን ፣ እምነታችን ባራመድን ፣ ለሃገራችን ያለንን ህልም በመናገር በመጻፋችን ነው ” ሲሉ ፍትህን አጥብቀው ይጠይቃሉ። በሰላማዊው ተቃውሞ መስመር እንጅ ጦር ሰብቀው የማናውቃቸው በመሰዊያው ላይ ያሉት ወንደም እህቶች ሁሉ ቤተሰቦች ህመም ዘልቆ ቢያምም የመሰዊያው ያቃጠላቸው ልጆቻቸው እየደረሰ ያለው ያህል የሚያም ነገር የለም ፣ ሊሰሙት ሊያዩም ይከብዳል !

እናም ” አንድነት ዘመነ ነው !” ስሙ ያሉኝ ብላቴና የአባት ስስት ፣ ጭንቅ አሳምሮ የሚያሳየው ተናጋሪ ፎቶ ነፍሴን ጨምድዷት ለህመሜ ማስታገሻ ብዕር አንስቸ ስንኝ ስቋጥር ልቤ እየደማ ነበር ። ለማዳመጥ፡ይሄንን ይጫኑ አይዞህ ወንድም አለም!!

የብላቴናው አባት ታሳሪ ማነው ?

ይህንን ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ምላሽ የሰጠኝ አንደ ወዳጀ ስለታሳሪው ሃገር ወዳድ ፖለቲከኛ እንዲህ ብሎኛል … “ዘመነ ምህረት በምርጫ ቦርድ የፈርሠው መኢአድ ሠሜን ቀጠና ሃላፊ እና በማክሠኝት 2ኛ ደረጃ ት.ቤት መምህር ነበር:: ምርጫ ቦርድ ድርጅቱን ለነ አበበው መሐሪ ሊሠጥ ጥቂት ቀናት ሢቀሩት ጎንደር ጥምቀት ላይ ችግር ልትፈጥሩ ነበር ተብለው የጥምቀት እለት በደህንነት ተይዞ ከዚያን ጊዜ ጃምሮ በማእከላዊ ይገኛል:: አሁን ላይ የሽብርተኛ ክሥ ተመሥርቶበት ቤተሠቦቹ ልጁን ይዘውት መጥተው ነው:: ልጁንያመጡት የዘመነ አባት አቶ ምህረት እና ባለቤቱ ናቸው:: ሌላው አሣዛኙ ነገር ግን ይህ ልጅ ከአሁን በሁዋላ ችግር ለይ መወደቁ.ነው ንክንያቱም የዘመነ ቤተሠቦች የሚተዳደሩት በዘመን ደመወዝ ነበር:: ለቤተሠቦቹ ገቢ ማሠባሠብ ካልተቻለ ሌላው ቀርቶ ይህ ህጻን ጎዳና ላይ ላለመውደቁ ዋሥትንና የለም። ዘመነ ቆራጥ ታጋይ መሆኑን ለማወቅ ልጁን ለምን አንድነት ብሎ እንደሠየመው ማወቅ ብቻ በቂ ነው:: ” ይላል ስለ መምህር ዘመነ ምህረትና ስለ ብላቴናው ልጁ አንድነት ዘመነ መረጃ ታቀበለኝ ወዳጀ …

ኢትዮጵያን ብለው የግንባር ስጋ የሚሆኑትና የሆኑት ወገኖች አስታወስኩና በደላቸው አልያዝህ ቢለኝ ከእነሱ አልፎ በወላጅ እናት አባት ፣ በእህት ወንድም በልጆች ፣ በዘመድ አዝማድና በጓደኞች የሚደርሰው ፈተና ዘለቆ ቢሰማኝ ” ዛሬዋ ኢትዮጵያችን እንዲህ ናት !” ነገ የመንጋቱን ተስፋ ላጽናና በሚል በውል ለማይሰማኝ ብላቴና አንድነት ጭንቅ መታሰቢያ ይዞህ ወንድም አለም ስል ይህችንም ወግ ግጥሟንም ቆጣጠርኩ …!

እስኪ ቸር ያሰማን !
መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓም10996578_778816508869952_4389730159112097685_n

የሕውሓት ገመና ሲጋለጥ! የሰብአዊ መብቶች ፍጹም የሆነ አፈና ኢትዮጵያን ወደ ከፋ አደጋ እያመራት ነው! –ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

መላው ኢትዮጵያውያን ብሶታቸውን በብር ኖቶች ላይ እየጻፉ እያሰራጩ ነው። –ፎቶዎችን ይመልከቱ

$
0
0

የኢትዮጵያ ህዝበ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎችን በመጠቀምም ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል፤ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል። ምስሎቹ በማህበራዊ መድረኮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጩ ነው።10394603_864943256875496_6179346959737954643_n (1)

10394603_864943256875496_6179346959737954643_n

10982848_864943260208829_4129492797290549939_n

11060046_664783826983814_7802953046690318802_n

11046298_864943253542163_8613024126760884882_n (1)

11046298_864943253542163_8613024126760884882_n

11062326_664783956983801_2888775592483778323_n

የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

ተከራካሪ “ፓርቲዎች”
ኢህአዴግ፤ አቶ አሰመላሽ ገ/ስላሴ እና አቶ ሬድዋን ሁሴን (ዋና ተከራካሪ ማን እንደሆነ ባይነገርም ይታወቃል)
አትፓ፤ አቶ አሰፋው ጌታቸው
መድረክ፤ ዶር መረራ ጉዲና
ሰማያዊ፤ አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ ዮናታን ተሰፋዬ
“አንድነት”፤ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ
ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግል ምልከታዬን ሲሆን፤ ሰዎች በተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በዘንድሮ ክርክር አንድ ጥሩ ነገር የውይይት ቅደም ተከተል በተራ እንዲሆን መደረጉ ሲሆን ይህ ኢህአዴግ የተሳሳተ መረጃና መደምደሚያ ሰጥቶ አድማጭ እንዳያደናገር ቢያንስ እድል ፊቷን አዙራበታለች፡፡ የመጨረሻውን መልካም እድል ያገኘው “የድንኩ አንድነት” ተወካይ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ቢሆንም በሙሉ ልብ የሚያከራክር ልዕልና ባለመያዙ ይህን ዕድል አልተጠቀመበትም፡፡ ሁለም ፓርቲዎች ከዋና ተከራካሪ በተጨማሪ አንድ አማካሪ ይዘው የገቡ ሲሆን ከሰማያዊ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ዕድል ሳያገኙ ወጥተዋል፡፡ ምክር ስለመስጠታቸውም ተመልካቾች እርግጠኞች አይደለም፡፡ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ይዞት የመጣው ግለሰብ ግን ሊመክረው እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ለዋለው ውለታ በቴሌቪዥን እንዲታይ ብቻ ይመሰለኛል፡፡ የዚህን ያህል እንደ መግቢያ ካልኩ ይበቃኛል፡፡
ኢህአዴግ ለ2007 ምርጫ ክርክር አዲስ ሀሳብ ሆነ አዲስ ሰው እንደሌለው ያረጋገጠበት መድረክ ነበር፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊ ወይም ልማታዊ ዲሞክራሲ እያለ በተለያየ ስም የሚጠራውን መስመር (ርዕዮተዓለም ሊባል ስለማይቻል) የሚያስረዱለት ዋነኛውን ሰው አቶ አስመላሽ ገብረስላሴን፤ እንደ አሰፈላጊነቱ ያለምንም ይሉኝታ ሊሳደቡ የሚችሉትን የስድብ አባት የሆኑትን አቶ ሬድዋን ሁሴንን ይዞ በክርክር መድረኩ ላይ ተሰይሞዋል፡፡ ኢህአዴግ የተሰጠውን የመጀመሪያ 15 ደቂቃ አሁንም ደርግን በጣለበት ጀግንነት ሰሜት ውስጥ ሆኖ አውቀው ይሆን ሳያውቁ 24 ዓመትን እንደ 24 ስዓት እንድንቆጥር እያደረጉ (በዕለቱ 24 ዓመት ለማለት 24 ሰዓት ይሉ ነበር፡፡) የለመድነውን በመንግሰትነት የሰሩትን ሰራ በፍፁም ከተቃዋሚዎች ጋር ሊወዳደሩበት የማይገባቸውን ተግባር እያነሱ ሲጥሉ ጨርሰውታል፡፡ ለተቃዋሚዎች ምንም እውቅና ለመስጠት ሳይዘጋጁ እውቅና በመሻት ሰሜት ውስጥ ሆነው ኦሮጌ የሆነውን የመነሻ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ የ2002 ክርክር በድጋሚ ቢቀርብ ለውጡ አቶ አሰመላሽ የተኳቸው ተከራካሪ ያለመኖር ብቻ ነው፡፡
ቀጣዩን መድረክ በቅድሚያ የተረከበው አዲስ ትውልድ ፓርቲ በመባል የሚታወቀው የአቶ አስፋው ጌታቸው የግል ፓርቲ ነው፡፡ የግላቸው መሆኑን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ የቅስቀሳ ፅሁፍ ከማንበብ ጀምሮ በማንኛውም ስብሰባ ላይ ብቸኛው ተወካይ የሆኑት እኚህ ሰው በእርግጥ ሰማቸው እንደሚለው ይህን ትውልድ አይወክሉም እንጂ፤በመጀመሪያው ዙር ለትውልድ ማፈሪያ በሚሆን ደረጃ ለክርክር ቀርበው አግኝተናቸዋል፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ከተቃዋሚ ተብዬዎቹ የመጀመሪያ በመሆናቸው ደግሞ በቀጣይ ለሚከራከሩት ሰዎች ማፈሪያ በሚሆን አጀማመር የጀመሩትን ከፍ ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠሩባቸው መረዳት ቀላል ነበር፡፡ በግልፅ ለታዘበ አቶ ይልቃል ጌትነት ከጎናቸው ሆነው ሲሸማቀቁ ላየ ሰው የአቶ አስፋው ጌታቸው የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ መንገድ በሌሎች ተከራካሪዎች ላይ ጉዳት አላደረሰም ሊባል አይችልም፡፡ ከጎን ላሉት አይደለም ቤታችን ለተቀመጥን ለእኛም ማፈሪያ የነበረ ክርክር አጀማመር ነው፡፡
አቶ አስፋው ጌታቸው ለክርክር ስለተመረጠው አጀንዳ “የመድበለ ፓርቲ ስርዓትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች” ጉዳይ አንድ ቃል ሳይተነፍሱ ስለ አረንጓዴ ቀለም ትርጉም ከረባታቸውን እና በኪሳቸው የሸጎጡትን ብጣሽ ጨርቅ እያሳዩ የተሰጣቸውን ውድ ጊዜ አጠናቀውታል፡፡ ከአረንጓዴ ትንታኔ በተጨማሪ የነገሩን ነገር ቢኖር ከኢህአዴግ ጋር ግብ ግብ ለመግጠም እንደማይፈልጉ ምለው መገዘታቸው ብቻ ነው፡፡ በእኔ እምነት አቶ አስፋው ጌታቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው እንደ ሰማቸው ይህን ትውልድ ሊወክሉ አይችሉም፡፡ አቶ አስፋው ጌታቸው በዚህ ውድ ጊዜ ውስጥ ስለ ግል የትምህርት ዝግጅትና ግላዊ ጉዳይ ለማውራት የወሰዱት ጊዜ በኢትዮጵያ ስለ አለው አስከፊ የሰብዓዊ መብታ ሁኔታ ለመናገር ድፍረት ማጣታቸው አሳዝኖኛል፡፡ ይህን አዲስ ትውልድ እወክላለሁ የሚል ፓርቲ የዞን ዘጠኝ በመባል እስር ቤት ያሉት ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም እነ ሀብታሙ አያሌው እና ሌሎች ትንታግ የዚህ ትውልድ ወኪሎች ማንሳት ነበረበት፡፡ ይህ ትውልድ ወኪል አጥቶ ሳይሆን ሁነኛ ወካዮቹ ቤታቸው በገዢው ፓርቲ ውሳኔ ወህኒ መሆኑ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ትውልድ በምንም ሁኔታ በአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና በአቶ አስፋው ጌታቸው አይወከልም፡፡
አቶ ሬድዋን እና አቶ አሰመላሽ በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ባገኙት 20 ደቂቃ በጅምላ ተቃዋሚዎችን በተለይ ሰመያዊና መድረክ ላይ ያደረጉት ውረፋ አቶ አሰፋው ጌታቸውንም ያስቆጣቸው ይመሰላል፡፡ በመጀመሪያ ካቀረቡት የመነሻ ኃሳብ በእጅጉ በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት የሌለው መሆኑ፣ ኢህአዴግ ርዕዮት ዓለም የሚባል ነገር የሌለው ብቻ ሳይሆን ከኮሚኒዝም እሰከ ነጭ ካፒታሊዝም የሚረግጥ በግለሰቦች ትርጉም የሚመራ ግንባር እንደሆነ አሰቀምጠዋል፡፡ በተለይ ድፍረት አጥተው በግልፅ አይናገሩት እንጂ በተቃዋሚዎች ውስጥ ካለው ክፍፍል በከፋ በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዮነት ለከፋ ክፍፍል የሚባቃ እንደሆነ ነገር ግን ስልጣን ላይ በመሆናቸው ግልፅ የሆነ መከፋፈል እንዳላሰዩ ገልፀዋል፡፡ በእኔ እምነት በኢህአዴግ ሰፈር ለመከፋፈል የሚሰጠው ምላሽ በጠብምንጃ የታገዘ እና ወደ ወህኒ የሚያስወረውር እንደሆነ መቀመጥ ነበረበት፡፡ ከዚህ ካመለጡ ደግሞ ሰደት ይሆናል፡፡
ዶክተር መረራ ጉዲና እሰከ ዛሬ ያለቸውን አውቀት ተጠቅመው እንደ ሁልጊዜ በተረጋጋ ሁኔታ በግልፅ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የሌለ መሆኑ በማሰቀመጥ ከርዕሱ ጋር ተዛማጅ የሆነ ጉዳይ አንስተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዶክተር መረራ በእኔ እምነት ከፖለቲካው ግንባር ቢለቁ የምመርጥ ቢሆንም ከቀረቡ ወዲህ ግን አዲስ ነገር ይዘው መመጣት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ /ዛሬም የጥብቆ እና የሚኒሊክ አልጋ ምሳሌ ቢቀር እመርጣሁ/፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊም ወይም ዲሞክራሲያዊም ያለመሆኑን ያስረዱበት መንገድ ተመችቶኛል፡፡ ዶክተር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ ሲነሳ አበክረው ሊያነሱት የሚገባ የነበረ ነገር ግን የዘነጉት ከጎናቸው ተወስደው በእስር የሚማቅቁትን አባላቶቻቸውን ነው፡፡ እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎች የኦሮሞ ልጆችን በሰም ጠርተው የሚደርሰብቻውን ግፍ ለህዝብ ማሳየት አልቻሉም፡፡ የኦሮሞ ልጆች ከምንጊዜውም በላይ እየደረሰባቸው ያለውን የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ሊያሳዩን ሙከራ አላደረጉም፡፡ በኢትዮጵያችን በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሞ ልጆች እኩል በደል የደረሰበት ያለ አይመስለኝም፡፡ ዶክተር መረራ ለፓርቲዎች ውህደት ጥያቄ ሲቀርብ ኦሮሞነታቸውን የሚያጎሉትን ያህል በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ብሔረተኝነታቸውን ሊጠቀሙበት አለመቻላቸው ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለመራጮቻቸው በዚህ ርዕስ ጉዳይ ከዚህ የተሻለ ማሰረጃ ሊሰጥዋቸው የሚችሉበት አጋጣሚ ሊያገኙ የሚችሉ አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ ህገ መንግሰታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰልፍ የወጡ የአምቦ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች በጥይት የተሰጣቸው መልስ ትክክል ያለመሆኑን ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ መብቶችን ለመጠቀም ሁል ጊዜ የሚነሳው ጉዳይ ልክ መሆን አይኖርበትም፡፡
ኢህአዴግ በሁለተኛ ክፍለ ጊዜ ባደረገው ጉንተላ እጅጉን ተበሳጭተው መስመር ከሳቱት በዋነኝነት የሚጠቀሱት ዶክተር መረራ ናቸው፡፡ ተማሪያቸው የነበረው አወያይ ጋዜጠኛ እስኪያቋርጣቸው ድረስ መስመር ጥሰው ሄደዋል፡፡ ርዕሱ “መድበለ ፓርቲ፣ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶች” ሆኖ እያለ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን አንሰተው ጊዜያቸውን ጨርሰውታል፡፡ ከውይይት ርዕሱ ጋር የማይሄዱ ነጥቦችን ኢህአዴግ አማራጭ የላቸውም አለን ብለው አድማጭ ሊይዘው በማይችለው ደረጃ ዝርዝሩን ዘርግፈውት በተገቢው ሁኔታ የወከሉትን ግንባር ምልክት እንኳን ሳያስተዋውቁ አጠናቀዋል፡፡ ለሌላ ጊዜ ለክርክር የሚቀርቡ ተከራካሪዎች በወረቀት ላይ የታተመ የምርጫ ምልክት ይዘው መግባት የሚጠቅማቸው ይመስለኛል፡፡
አቶ ይልቃል ጌትነት በአቶ አሰፋው ጌታቸው የክርክር ሂደት በግልፅ በሚታይ መልኩ የደረሰባቸውን መሸማቀቅ በዶክተር መረራ ዘና ያላ አቀራረብ ዱካኩ የተገፈፈላቸው ቢሆንም በቅድመ ክርክር ወቅት የነበረውን ነጥብ አምጥቶ ካለቸው ውድ ጊዜ ለመጠቀም መወሰናቸው እንደ ሁልጊዜውም አጋጣሚውን ለህዝብ ግንኙነት ስራ መጠቀም የፈለጉ ያስመስለዋል፡፡ ክርክሩ ላይ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ብሎ በግልፅ ያስቀመጡት አቶ ይልቃል የሰብዓዊ መብትን ለማቅረብ የሄዱበት መስመር ሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶችን ለህዝብ በሚገባው ግልፅ ምሳሌ ከማቅረብ ይልቅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያው መብቶችን በመቀላቀል ማቅረባቸው የዝግጅት እጥረት እንደነበረባቸው ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ በሰው ፊት ለንግግር ሰንቀርብ ሀምሳ ከመቶ ዝግጅት መሆኑን አቶ ይልቃል የዘነጉት ይመስላል፡፡ ከዝግጅት አንፃር ተዝረክርከው ማስታወሻውን ወደፊት ወደኋላ ሲገልፁ የነበሩትን አቶ አስፋው ጌታቸውን ማንሳት ሳያስፈልግ ነው፡፡
አቶ ይልቃል በሁለተኛውም ዙር የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ የተሰጠው ጊዜ አንሰተኛ መሆኑን በሚገልፅ ቅሬታ ጊዜ ሲያባክኑ ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር አቶ ይልቃል ያስቆጠሩት ዋነኛ ነጥብ አቶ አስመላሽ ሰለ ሰመያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉበዔ አጠራር አሰመልክቶ ያነሱት ነጥብ ነው፡፡ ይህ ነጥብ ኦቶ ይልቃል ከመረጃ እጥረት በሚል እወሰደዋለሁ ቢሉም ይህ የጠቅላላ ጉባዔ ጉዳይ ህወሃት/ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር ለሰማያዊ ፓርቲ ከተቀመሙት መርዞች አንዱ እንደሆነ ሁሉም ማወቅ አለበት፡፡ አቶ አስመላሽ የሰማያዊ ፓርቲ ደንብ ጊዜ አግኝተው ሊያነበትም ሆነ ሊያስነብቡ አይችሉም፡፡ አንብበው ፓርቲ ማፍረሻ ቀዳዳ የሚያቀብሉ በምርጫ ቦርድ የተቀመጡ ወኪሎቸ አሉ፡፡ ለዚህ ቅብብል የሚሆን ደግሞ የተዘረጋ ህጋዊ የሚመስል መስመር እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ለማነኛውም አቶ ይልቃል የነበረውን ጊዜ በርዕስ ጉዳዩ ላይ ብቻ አተኩረው በምድር ላይ ባለ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አሰደግፈው መከራከር አልቻሉም፡፡ እንደ ዶክተር መረራ በኢህአደግ ትንኮሳ መበሳጨታቸው ቢታወቅም ለመረጋጋት ያሰዩት ጥረት ጥሩ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ዘመኑን የዋጀ ፓርቲ አይደለም እራሱን የሚያወዳድረው ከንጉሶች ወይመ ከደርግ ጋር ነው፣ መሻሻል የማይፈልግ ፓርቲ ነው፡፡ በሚል ያነሱት ነጥብ በኢትዮጵያ ህዝብ ሊያዝ የሚችል አንኳር ጉዳይ ነው – በምርጫ ካርድ ይሁን በህዝባዊ አመፅ ግልፅ ሆኖ አልተቀመጠም፡፡
የመጨረሻውን እድል ያገኘው የድንኩ “አንድነት” መሪ የሆነው አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ ከሌሎቹ በተሻለ የሰብዓዊ መብት ለመርገጥ ገዢው ፓርቲ እየተጠቀመበት ያለውን “የፀረ ሽብር ህግ” አንስቶ ለመሞገት ሞክሮዋል፡፡ በምንም መልኩ ግን አስተያየት ሊሰጥበት ያልቻለው ግን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ጉዳይ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትዕግሰቱ በትክክል ያውቀዋል፡፡ በኢህአዴግ ኢትዮጵያ ይህች ያገኛትን ቦታ በአባላት ይሁንታ ሳይሆን በተደራጀ ሾኬ እንዳገኛት ስለሚያውቅ መድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ሊል አልደፈረም፤ ቢያንስ በመግቢያው ንግግር፡፡ የሚገርመው ግን አሁንም “አንድነትን” ሲጠራ አፉ ይተሳሰራል፡፡ “እንደ አንድነት ማለትም እንደ እኛ አመለካከት” ሲል ውስጡ ያለው የአንድነት መንፈስ እንዳልሆነ ያሳብቃል፡፡ ትዕግሰቱ የአንድነትን አቋም በሙሉ ልቡ ሊናገር የሚችልበት የሞራል ልዕልና ላይ እንደሌለ በሚያሳብቅበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ስለሚያቀርበው ሃሳብ ያለኝን የግል ንቀት ለመተው እየሞከርኩ ቢሆንም ለመያዝ የሞከርኩት ነጥብ የዲሞክራሲ ተቋማት የይስሙላ መሆናቸውን ገልፆ በተለይ ምርጫ ቦርድን ጠቅሶ መለወጥ እንዳለበት ሲናገር የበላበትን ወጨት ሰባሪ ቢያደርገውም እውነት መናገሩን ግን መካድ አይቻለም፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን አፍንጫህን ላስ የሚል ፓርቲ መሆኑን መግለፁም ትክክል ነው፡፡ በዚህ አስተያየቱ ኢህአዴግ ተጨማሪ እድል ባለማግኘቱ ምን እንደሚከተለው ማወቅ አይቻልም፡፡ ለማነኛውም ጌቶቹን በተለይ ምርጫ ቦርድ ታዛዥነቱን አይቶ በሰጠው ወንበር ሰሙን ጠርቶ መዝለፉ ሽርክናቻው አንድነትን ድንክ እሰከማድረግ ብቻ አስመስሎባቸዋል፡፡
የኢህአዴግ የምላሽ ወቅት ሰለባዎች እንደሚጠበቀውም ሰመያዊና መድረክ ነበሩ፡፡ የፈለገ ጠንካራ ተቃውሞ ቢያቀርቡም “አትፓ እና ድንኩ አንድነት” በኢህአዴግ አፍ ለዘለፋ አይፈለጉም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ድንኮች ምንም በማያመጣ መልኩ ተሰርተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ሂደት ዋነኛዎቹ ተዋናዮች የነበሩት ሁለቱም የኢህአዴግ ወኪሎች አንድ ጊዜ እንኳን አንድነትን ሳይዘልፉ ይልቁንም ጅምሩ ጥሩ ነው በሚል ማለፋቸው ሰራቸው ማጠናቀቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የኢህአዴግ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት መገለጫ ተብለው የቀረቡልን ምሳሌዎች ግን ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ነገር ነው፡፡ እነርሱም፤
• አሁን 75 ፓርቲዎች በሀገራችን መኖራቸው የመድበለ ፓርቲ መገለጫ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ለክርክር የቀረቡት ፓርቲዎች መኖር ዋናኛ ማሳያ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ በፓርቲ ምዝገባና ቁጥር የመድበለ ፓርቲ ቢለካ እውነት ነበር፡፡ በወረቀት የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ሳይካድ በተግባር ገን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲኖር የማይፈቅደው ኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር ያቀርባል፡፡ እምነታቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ብለው እንዲጠፉ እየሰሩ ለእርዳታ ሰጪዎች ፍጆታ የፓርቲነት ሰርተፊኬት በማደል የመድበለ ፓርቲ ስርዓት አለ ብለን እንድናምን ይፈልጋሉ፡፡ በአሜሪካን ሀገር በዋነኝነት ሁለት ፓርቲዎች መኖራቸው ዲሞክራሲ ያለመኖሩ ማሳያ ነው እንደማለት ነው፡፡ የኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር፡፡
• ለምርጫ ውድድ የቀረቡ ዕጩዎች ሌላኛው የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ አድርገው ኢህአዴጎች አቅርበዋል፡፡ ማንም እድሉን ሊሞክር ለምርጫ ዕጩ ሆኖ እራሱን ማቅረብ ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ እንዴት ሊታይ እንደሚችል አቶ አሰመላሽ እና አቶ ሬድዋን ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ ይህ በቅርቡ የመጣ የመድበለ ፓርቲ ስኬት መገለጫ ነው፡፡
• ለምርጫ ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀት ደግሞ ሌላው የመድበለ ስርዓት ስለመኖሩ ማሳያ ተድረጎ ነው የተብራራልን፡፡ አስገራሚው ነገር ከተመደበው ገንዘብ አብዛኛውን የሚወሰደው ገዢው ፓርቲ መሆኑ እየታወቀ፤ ፓርቲዎች በምርጫ ሰሞን በሚያገኙት በዚህ ገንዘብ የመድበለ ፓርቲ ስርዓትን ለማጠናከር ምን ሊያደርጉበት እንደሚችሉ ማሰረዳት አይችሉም፡፡ ተመደበ የተባለው ገንዘብ ዋነኛው ወጪ ከ45 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምርጫ አስፈፃሚዎች አበል ሲሆን፤ ለአንድ ዕጩ ተወዳዳሪ ብር 500 በማይደርሰበት ሁኔታ ይህ ገንዘብ እንዴት እንደሚጠቅም ኢህዴጎች ሊያስረዱን አይችሉም፡፡
• በጣም ያስገረመኝ አንዱ መከራከሪያ “የመድበለ ፓርቲ በሊብራል ዲሞክራሲ በሚያራምዱ ሀገሮች ለብሔር ብሔረሰቦች የማይፈቅድ ነው” የሚልው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የተለየች የብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው የተሳሳተ ነገር አሁንም ቅጥ ያጣ ይመስላል፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በሙሉ የሚኖሩባት ሀገር አሜሪካ ውስጥ በፈለጉት ቡድን ለመደረጃት አንድም ጥያቄ እንደማይቀርብ የምናውቅ አይመስላቸውም፡፡ ሊብራል ዲሞክራሲን ያለ ስሙ ሰም እየሰጡ የራሳቸውን የፖለቲካ መስመር አንዴ አብዮታዊ ሌላ ጊዜ ልማታዊ ዲሞክራሲ እያሉ ሊያደናብሩን ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የብሔርና ብሔረሰብ ፖለቲካ ጉዳይ ሲነገር የሚያስታውሰን አንድ ነገር “ለምለሚቱ ሀገሬ” የሚለው ነገር ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት ሳር የማይበቅል፣ ወተት ማር የማይገኝበት፣ ወዘተ ይመስለን የነበረው ዓይነት አሳሳች ምሳሌ ነው፡፡

በመጨረሻም በክርክሩ የነበሩ ተቃዋሚ እና “ተቃዋሚ ተብዬ” ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ውይይት ሲደረግ በቅርብ ርቀት በአንድነት ላይ የተፈፀመውን የመንግስታና ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ለማጠናከር መቆም ያለበትን ምርጫ ቦርድ ሴራ በምሳሌ አንስተው ለመሞገት ያለመሞከራቸው፤ በተለይ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ የአንድነት ድንክ መሆን እነሱን ከፍ ማድረጉን በግልፅም ባይሆን በውስጣቸው የፈጠረላቸውን ደስታ የሚያሳይ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ አንድነትን ድንክ በማድረጉ ብቻውን እንዳልተጠቀመም ማሳያ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚችለውን በመምረጥ አንፃር በጣም ተሳክቶለታል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች እግረ መንገዴን የማስታውሳቸው ዘወትር በነበሩን ስብሰባዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማስተባበር ስንደክም ከእኛ ይቅር ስንል የነበረው ለእነዚህ ፓርቲዎች መሆኑን ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲን አስመልክቶ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበረንን ልበ ሰፊነት ሳስበው በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ ለምን አደረግነው የሚል ቁጭት የለብኝም፡፡
አንድነት ፓርቲ በዚህ ክርክር ውስጥ ቢኖር ኖሮ በመጀመሪያ ከኢህአዴግ እኩል ሁሉንም ለመከራከር እድል ነበረው ፓርቲ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያቱም 450 ዕጩዎች ለፌዴራል ምክር ቤት እና 1200 የማያንሱ የክልል ምክር ቤት ዕጮዎች ስለሚያቀርብ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመከራከር ሊመጡ የሚችሉትን ትንታግ የአንድነት ወጣቶች ሳሰብ እንባ እየተናነቀኝ ነው፡፡ የዛሬ አምሰት ዓመት የዚህን ተመሳሳይ ክርክር አንድነትን ወክሎ የተከራከረው ምን አልባትም በዚህ ክርክር መነሻ ቂም ተይዞበት የነበረው፣ ዛሬ በወህኒ የሚገኘው አንዱዓለም አራጌ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ ክርክሩ ከመደረጉ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ በሚኖረው 6 ደቂቃ የመነሻ ኃሳብ ልናነሳ የምንችለውን ቢያንስ 12 ነጥብ ይዘን እንገባ ነበር፡፡ ወይም 10 ነጥብ እና በቀሪው ሁለት ደቂቃ ለህዝብ ውይይት ሊጭር የሚችል ሃሳብ የሚነሳበት ይሆን ነበር፡፡ ሁለተኛው ዙር ዘጠኝ ደቂቃ በዝርዝር ህገ መንግሰታዊ ድንጋጌዎችን አሰመልክቶ ኢህዴግ የሚሰራቸውን የክርክር ፋውሎች ለህዝብ የምናጋልጥበት ይሆን ነበር፡፡ ለዚህ ነው በ2007 ኢህአዴግ የሚችለውን መርጦዋል የምንለው፡፡
ለማጠቃለል ተቃዋሚዎች በኢህአዴግ ትንኮሳ ተገፍተው በመድበለ ፓርቲ እና በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው ለመከራከር አልቻሉም፡፡ ክርክሩን በኢህአዴግ ሜዳ ላይ ለማድረግ ማተኮር የነበረባቸው “ህገ መንግሰት” ላይ የተዘረዘሩትን መብቶች እያነበቡ በተግባር የገጠመውን ፈተና በማቅረብ ህዝቡ እነዚህን ጉዳዮች ገዢው ፓርቲ የአፈፃፀም ችግር ናቸው ቢልም በመርዕ የማያምንባቸው መሆኑን እራሱ ኢህአዴግ ከፃፋቸው የፖሊሲ፣ሰትራቴጂና የርዕዮታለም ትንተና መፅሃፉች ጋር እያጣቀሱ ማስረዳት ነበረባቸው፡፡ የህገ መንግሰቱ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል አንድ ከአንቀፅ 14 -28 የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማየት በተግባር የገጠሙትን ፈተናዎች፤ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል ሁለት ከአንቀፅ 29-44 ዲሞክራሲያዊ መብቶቸን በማየት የገጠሙትን ፈተናዎች በዝርዝር መተንተን ይቻል ነበር፡፡ በዚህ መስመር ክርክሩ ቢደረግ ኢህአዴግ ሊከራከር የሚችለው ህገመንግሰቱን ለማዘጋጀት ህይወትና ደም ተከፍሎበታል ከሚል ፉከራ ውጭ ለምን በተግባር ላይ እንደማያውላቸው ሊያስረዳ አይችልም ነበር፡፡ ምንም በቂ ምክንያት ሊኖር አይችልም የሚል እምነት አለኝ፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!udj_udj12

የሚሊዮኖች ድምጽ –መደመጥ ያለበት ክርክር በመድበለ ፓርቲ ዙሪያ –ክፍል 1 እና ክፍል 2

$
0
0

“ኢሕአዴግ አርጅቷል። የሐሳብ ድርቀት ደርሶበታል” ኢንጂነር ይልቃል
“ለኢትይጵጵያ ሕዝብ ጥልቅ ፍቅር አለን። ፣ ትልቅ አክብሮትት አለን”

ኢንጂነር ይልቃል

“ኢሕአዴግ የአሁኑ ትዉል የሚመጥን አይደለም”
አቶ ዮናታን ተስፋዬ
“በኢሕአዴግ ክራይቴሪያ ማግኘት ይሻላል፣ በአካዳሚክ ከማግኘት እየተባለ ነው “
“የካቢኔ የካድሬ ወንድምና እህቶች የጠለበ ሥራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ድንጋይ ነው የሚፈልጡት!

ዶር መራራ ጉዲና
ዶር መራራ መልእክት ለኢትዮጵይ ሕዝብ “የኢሕአደግ መሪዎች ሰበካ በቀን ሶስት ጊዜ እናበላሃለን እያሉ፣ ግን በቀን ሶስት ጊዜ እንደምታበላ አንተም ታውቃዋለህ።ኢሕአዴግ አንተን እያሳለፍኩልህ ነው እያለ ማንን እያበለጸገ እንዳለ አንተም ታውቀዋልህ። በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ጥረህ ግረህ ያስተማርካቸው ወጣቶች ዛሬ ምን እንደሚሰሩ አንተም ታውቀዋለህ። የካድሬዎችን የካቢኔዎች ልጆች ዛሬ እንዴት እንዳለፈላቸው አንተም ታወቀዋለህ። ኢሕአዴግ መንግስት ነጋዴም በሆነበት ስርዓት በየአመቱ ያለ አግባብ ግብር እየተጫነብህ፣ የማዳበሪይ እዳ እየተጫነበህ፣ እንደሚገኝ አንተም ታወቀዋለህ። ……… ታሪክ ሥራ”
ኢንጂነር ይልቃል ከዳያስፖራ ጋር አብራችሁ ትሰራላችሁ ለሚለው ክስ ሲመልሱ በዋናነት በኢትዮጵያ የፈረንጅ ጥገኛ የሆነ መንግስት እብደ ኢሕአዴግ እንደሌለ በመግለጽ ነበር። “ይሄን ያህል ብድርና እርዳት አገኝን እያሉ እንደ ትልቅ ነገር ያወሩ የለም ወይ ? “ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ኢሕአዴግ ከአዉሮፓ ሕብረትና ከመሳሰሉት የሚገኘዉን እርዳታ ባጀት ዉስጥ እስከማስገባት ድረስ የደረሰ እንደሆነም አስረድተዋል።
በውጭ የሚኖሩ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆችን እዉቀት፣ ችሎታ መጠቀም ብስለት ነው ያሉት ኢንጂነሩ በዉጭ ያሉትን ኢትዮጱዊያን “እናከብራለን፣ እንወዳቸዋለን ፡አብረናቸው እንሰራለን። ኢሕአዴግ ጥላሸት ስለቀባና ሌላ ስም ስለለጠፈባቸው ብቻ ልዩ ስም መስጠት አያስፈልግም። የአገራችን ልጆች ናቸው” ሲሉ ለነ ሬድዋን ሁሴ ክስ ድብን ያለ መልስ ሰጥተዋል።
ከኢንጂነር ይልቃል ጋር በክርክሩ ይተሳትፉት አቶ ዪናታን በበኩላቸው “ፍረጃና ውንጀላ የኢሕአዴግ ባህሪው ነው” በማለት ነበር መልሳቸዉን የጀመሩት። ኢሕአዴግ ዘመኑን የዋጀ ለዘመኑ የማይመጠን እንደሆነ የገለጺት አቶ ዮናትን ፣ አገራችን አቅራቢያ ያሉ ኬንያ፣ ታዛኒያን እንኳ የሚያክል ስርዓት የኢትዮጵያ እንደሌላት ተናግረዋል።

ክፍል 1
መድረክ እና ሰማያዊ በተሰጣቸው የመጀመሪያ ስድስት ስድስት ደቂቃዎች የተናገሩትን ይዳምጡ። ዶር መራራ እና ኢንጂነር ይልቃል የተናገሩት ለማዳመጥ 29.50 ደቂቃ ወደፊት መሄድ ይችላሉ።

ክፍል 2
ዶር መራራ፣ ኢንጂነር ይልቃል እና አቶ ዮናታን የተናገሩትን ያድምጡ። ( ወደ 9.23 ወደፊት በመሄድ እስከ 26.00 ከዚያም ለ50.00 እክሰ 58 ያገኙታል።

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>