Quantcast
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ቅዱሳንና ብጹአንን ያያቹህ በበላይነህ አባተ


አማርኛ ተናግሪ ኢትዮጲዊያንን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!!! ሸንጎ

የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው። ገለታው ዘለቀ

የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው

ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የ ልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።

“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።

ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና።

በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ እንደሚያነክስ ሳይ እግሩ ኣርቴፊሻል መሰለኝና ኣለ ኣይደለም ኣሳዘነኝ። የሚጠጣውን እየጠጡ ኬካቸውን እየበሉ ያወካሉ። እኔና ከፊቴ ያለው ሰውየ ግን ጸጥ ብለናል። ትንሽ እንደቆየ ያቺን ጋዜጣውን በሽንጡዋ ሸመለለና ወደ ቦርሳው ከተተ። ደሞ ወዲያው ኣጨበጨበና ሂሳብ ከፈለ።

እኔም እስካሁን ባናወራም ኣብርን ለትንሽ ሰኣትም ቢሆን ባንድ ጠረንጴዛ በልተን ጠጥተናል ዝም ኣይባልም ብየ ነው መሰለኝ ቻው ለማለት ምንም ኣልቀረኝም።በመሃል ያ ያነክሳል ያልኩዋችሁ ሰውየ ድንገት ወደኛ ዞረና
“ምን ኣልክ ኣንተ? ምን ኣልክ? ድገመው እንጂ…… ልብ በሉ… ሰዎች ልብ ኣርጉ.. ምን ኣልክ ኣንተ?…” እያለ ይጮሃል።
ሁላችንም ተደናገጥን። ያ ከኔ ጋር ጠረንጴዛ ተጋርቶ የነበረው ሳምሶናይቱን እንዳንጠለጠለ
“ኸረ እኔ ምንም ኣልወጣኝም ጌታየ ምን ነካዎት” ይላል ኣስር ጊዜ። ከዚያ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየም ኣብሮ ያጫፍራል። በሁዋላ ይሄ ከኔጋር የነበረው ሰው መንጨቅ ብሎ ሲወጣ ሁለቱም ተከተሉትና ጭቅጭቁ ከውጭ ቀጠለ።

ያው መቼም ሃይ ሃይ ማለት ያገር ባህል ነውና ወደ ውጭ ወጥቼ ኸረ እሱ ምንም ኣላለም ፣ ምንም ሲል ኣልሰማሁትም ተረጋጉ እያልኩ ለመምከር መቼም ያቅሜን ሞከርኩ።

ያ የሚያነክሰው እንባው ሁሉ የመጣ ይመስላል። ይገርማል ዋሽቶ የሚያለቅስ ሰው ቢገጥማችሁ ምን ትላላችሁ?

“እንዴት ትሰድበኛለህ……” እያለ ሲሙዋገት ጓደኛውን ጠጋ ብዬ እናገላግላቸው እባክህ ምን ኣለ? ምንም ኣላልም እኮ ኣልኩት።
“የለም የለም እኔ ራሴ ሰማሁት እኮ ወራዳ ነው ሽባ ብሎ ሰደበው እኮ”
ደነገጥኩና መቼ? ብየ ጠየኩ::
ወደዚህኛው ሰውየ ዞሬ ትተዋወቃላችሁ እንዴብዬ ጠየኩ::

“በፍጹም ኣንተዋወቅም ኣለ” ግራ የተጋባው ባለ ሳምሶናይቱ ፈጠን ብሎ

“ሂሳብ ከከፈለ በሁዋላ ድምጹን ከፍ ኣርጎ እኮ ነው የሰደበው”

በውነት ግራ ግብት ኣለኝ። ሁዋላ ላይ ይሄ የሚያናግረኝ ሰው ስልኩን ኣወጣና ኣንድ ሁለት ቁጥሮችን ነካካና ወደዛ ዞር ብሎ ጥቂት ኣወራ መሰለኝ። ወዲያው እንደተመለሰ ኣንድ ፖሊስ መጣና ያንን ባለ ሳምሶናይት
“ቅደም ኣለው።”
በዚህ ጊዜ ወደ ፖሊሱ ጠጋ ብዬ ምንም እኮ ኣላለም እኔ እዚህ ነበርኩ
ምንድነው ችግሩ ለማለት ሞከርኩ። ፖሊሱ በግንባሩ ጥሩ ኣርጎ ገረፈና ኣስቆመኝ። ባለ ሳምሶናይቱ እንዲሁ “ምን ኣጠፋሁ” እንዳለ ይነዱት ጀመር። ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ባጭር ርቀት መከተል ጀመርኩ። የሚገርማችሁ ያ ቅድም ቀኝ እግሩን ይጎትት የነበረው “ሽባ” ተብየ ተሰድቢያለሁ የሚለው ሰውየ ኣሁን በግራው ማንከስ መጀመሩን ትኩር ብዬ ኣስተዋልኩና የሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ገባኝ። ብዙም ሳልርቅ ወደ ሁዋላየ ሂሳቤን ለመክፈል ተመለስኩ። ወደ ሻይ ቤቱ በር ስቃረብ ኣንዱ “ወሰዱት ኣይደል?” ኣለኝ:: ኣዎ ወሰዱት ኣልኩና ግን ምንም ኣለማጥፋቱን ኣስረግጨ ነገርኩት። ጥቂት ኣየኝና “ወንድሜ ተጠንቀቅ ከዚህ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየ የነሱ ጆሮ ነው የተለያየ ልብስ እየለበሰ ሲሰልል ነው የሚውለው ተነቅቶበታል” ኣለኝ። እኔም ወዲያው ጠርጥሬ ስለነበረ ገባኝ። እንግዲህ ያን ሰው በዚህ ርካሽ ስራቸው ኣወናጅለው የሆነ ነገር ኣርገውታል ማለት ነው።

ባለፈው ጊዜ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ከነበሩት መካከል ኣንዱ በኢሳት ቴሌቪዥን ኢንተርቪው ተደርጎለት ሲናገር ልብ ይነካል። ሲቪል እየለበሱ መገናኛ እየያዙ እንዴት የስነ ልቡና ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ገለጸ። ኑሮ ኣይደለም የምንኖረው ኣለ። ያሳዝናል። ሃሳብን መግለጽ ጥቂት ኣስተያየት መሰንዘር በስነ ልቡናና በኣካል የሚያስቀጣ ነገር የሆነባት ሃገር ናት ኢትዮጵያ።

መነሻየኮ ስለ እስክንድር ነጋ ነው። ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር፣ እስክንድርን የመሰለ ፖሊሲ የሚያመነጭ፣ የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት እንዲያስችለን ነው ።

እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ኣለም ኣውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው። ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የ እስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው። የነ ርእዮት ኣለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።

ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

ደብረ ዘይት፡- የዓለማችን ታሪክ ፍፃሜ ቅዱስ ተራራ በፍቅር ለይኩን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ቀኖና መሠረት የዓብይ ጾም ወይም የሑዳዴ ጾም አምስተኛ ሳምንት ‹‹ደብረ ዘይት›› በመባል ይጠራል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት አስተምህሮ የዓብይ ጾም ሳምንታት በሙሉ ከክርስትና ሃይማኖት አስተምህሮ፣ ሥርዓትና ታሪክ ጋር የተያያዘ የራሳቸው የሆነ ስያሜ አላቸው፡፡

የዚህ ስያሜ አመንጪም የ6ኛው መቶ ክ/ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቅና የዜማ ደራሲ የሆነው ቅዱስ ያሬድ እንደሆነ ነው የታሪክ ድርሳናት የሚመሰክሩት፡፡ ገና አውሮፓና እስያ በከፊል፣ አሜሪካና እንዲሁም የተቀረው የዓለማችን ክፍል በሙሉ ባልነበሩበትና ወንጌልን ባልሰሙበት በዛ የጥንት ዘመን ኢትዮጵያውያን ታላላቅ የሆኑና ዓለምን ዕፁብ ድንቅ ያሰኙ የሥነ ሕንጻ ጥበብና ክህሎት የተንጸባረቀባቸው ቤተ መቅደሶችን ገንብተው፣ መጽሐፍትን መርምረው፣ ዜማ ደርሰው፣ ቅኔ ፈጥረው ልዩ በሆነ መንፈሳዊ ሥርዓት ለረዥም ዘመናት አምላካቸውን ሲያመልኩ ቆይተዋል፡፡

አውሮፓ የሙዚቃ ኖታ ለመፍጠር አይደደለም ገና እንኳን ለማሰብ ባልደፈሩበት በጥንቱ ዘመን ቅዱስ ያሬድ ከሺሕ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ዜማ ከነምልክቱ ወይም ኖታው በቀመር ዛሬ ዓለም የሚደነቅበትን ሰማያዊና መንፈሳዊ ምሥጢር ያለበትን የቤተ ክርስቲያኒቱን አምልኮተ ሥርዓት መሠረት ለመጣል ችሏል፡፡
ማሕሌታዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በተጨማሪም በዓብይ ጾም ውስጥ ያሉትን ሳምንታት በሙሉ ከብሉይ መጻሕፍት፣ ከመዝሙራት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርትና ታሪክ ጋር በሚገባ አስማምቶ በመከፋፈል ቀምሮታል፡፡ በዚህም በቅዱስ ያሬድ ስያሜ አከፋፈል መሠረትም የዓብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት እሑድ ጀምሮና ሳምንቱ በሙሉ ‹‹ደብረ ዘይት›› በመባል ይታወቃል፣ ይዘከራል፡፡

እስቲ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ ጾመ እኩሌታ ወይም ደብረ ዘይት ተብሎ ስለሚከበረው በዓል ከማውራቴ በፊት በእስራኤል ምድር ስለሚገኘው የደብረ ዘይት ተራራ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ልሞክር፡፡

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል፡፡ ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡ ቦታው የሚገኘው በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከጎልጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው፡፡ በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይገኛል፡፡ በዚህም ስፍራ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ አለ፡፡

የደብረ ዘይት ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው፡፡ እንደ ወንጌሉ ጸሐፍትና የክርስትና ሃይማኖት አስተምህሮ መሠረት ከዚሁ ከደብረ ዘይት ተራራ ላይ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው፡፡ ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው፡፡

በተጨማሪም ደብረ ዘይት ተራራ ወገብ ላይ በሰፊው ተንጣሎ የሚታይ አንድ ነገር አለ፤ ይኸውም የአይሁድ መቃብር ነው፡፡ ይህን ስፍራ አይሁዳውያኑ ለመቃብርነት የመረጡበት ምክንያትም ወደፊት መሢሑ መጥቶ እስራኤልን ነፃ አውጥቶ ወደ አባቱ ያርጋልና፣ ኋላም ለፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ የሚፈርድበት ስፍራና ሙታንም የሚነሱበትና የሚሰበሰቡበት ተራራ ይህ በመሆኑ እኛ መሢሐችንን ለማግኘትና ከሙታንም ለመነሳት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን ብለው በማመናቸው ነው፡፡

አይሁድ ኢየሱስ ክርስቶስን መሢሑ እርሱ ነው ብለው አያምኑም፣ በዘመኑም አልተቀበሉትም፣ አሁንም አይቀበሉትም፡፡ መሢሕ ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ የተቀባ ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም እስራኤል ወደፊት አንድ ታላቅ መሢሕ እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው ባላቸው ተስፋ መሠረት ገና አሁንም ድረስ መሢሐችንን እንጠብቃለን ይላሉ፡፡
ስለ ደብረ ዘይት ተራራና ተራራዋን በኢየሩሳሌም ወይም በዓለማችን ካሉ ተራራዎች ሁሉ ልዩ እንድትሆን ስላደረጋት ስለ መሢሑ ይህን ያህል ካልኩ አሁን ደግሞ በመጠኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ አስተምህሮና ሥርዓት መሠረት ጾመ እኩሌታ ተብሎ ስለሚጠራው ስለ ደብረ ዘይት በዓል ምንነትና ታሪክ ከአይሁዳውያኑ ታሪክና ከክርስትና ሃይማኖት ጋር አያያዤ ጥቂት ነገሮችን ልበል፡፡

እስካሁን እንዳየነው በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት የዓብይ ጾም እኩሌታ ደብረ ዘይት በመባል ተሰይሟል፤ ይኽውም ወንጌላውያኑ እንደዘገቡት በዚሁ ሰንበት ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ለቅዱሳን ሐዋርያቱ ስለዓለም መጨረሻና ስለዳግም ምጽአቱ ምልክቱን በዝርዝር ነግሯቸዋል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ከመምህራቸውና ከጌታቸው ከኢየሱስ ጋር በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በአንድነት ተቀምጠው ሳለ፣ ደረቱን ለደብረ ዘይት ተራራ ሰጥቶ በሚያስገርም ግርማና ውበት በፊለፊታቸው የተንጣለለውን የኢየሩሳሌምን መቅደስ እያስተዋሉ፣ ጌታ ሆይ ይህን ባለ ልዩ ግርማ መቅደስና የተሠራበትን ውብ ድንጋዮች ታያዋለህን አሉት፡፡

ታሪክ ጸሐፊውና ሐኪሙ ሉቃስና ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደጻፉት ኢየሱስም መልሶ፡- ‹‹ይህን ታደናቃላችሁን እውነት እውነት እላችኋለሁ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም፡፡›› ሲል ደቀ መዛሙርቱና አይሁዳውያኑ የሚኮሩበት መቅደስና ከተማቸው ኢየሩሳሌም እንደ ጥንታዊቷ ባቢሎን የፍርስራሽ ከተማ፣ የኃጢአት፣ ያለመታዘዝ፣ የጥፋትና የውርደት ምልክት ይሆናሉ፡፡ ሲል አስቀድሞ በትንቢት መልክ በግልፅ ለተከታዮቹ ለሐዋርያቱ ነገራቸው፡፡

በኢየሩሳሌም መቅደስ አስገራሚ ውበትና ግርማ ልዩ አድናቆት ውስጥ ለገቡት ለተከታዮቹ ሐዋርያት መምህራቸው ኢየሱስ የነገራቸው ትንቢትም፣ አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ እንደዘገበው በ70 ዓ.ም. ሮማውያን ኢየሩሳሌምን በወረሩ ጊዜ ትንቢቱ ፍጻሜውን እንዳገኘ ይነግረናል፡፡

‹‹አፍሪካ ባይብል ኮመንታሪ›› እንደሚያትተው ከሆነ ይህ የኢየሩሳሌም ጥፋትና የመቅደሱ ውድመት አስቀድሞ በአይሁድ ቅዱሳን ነቢያት በሆኑት በነቢዩ ኤርምያስ፣ ዳንኤልና ሚክያስ ተገልጾ እንደነበር ይገልጻል፡፡

‹‹ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን (እስራኤል) እንደ እርሻ ትታረሳለች፡፡ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፡፡ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል፡፡›› በማለት አስቀድሞ በነቢዩ ሚክያስ አፍ መነገሩን ‹‹አፍሪካን ባይብል ኮመንታሪ›› መጽሐፍ በሰፊው ያብራራል፡፡

ሐዋርያት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆነው በሚያስገርም ውበቱና ግርማው የተመሰጡበት ቤተ መቅደሳቸውና የአባቶቻቸው የቃል ኪዳን ምድር የሆነችው ቅድስቲቱ ከተማቸው ኢየሩሳሌም በጌታ ዘንድ ለእሳት ፍርድ የተጠበቁ፣ የመጥፋትና የውርደት ምልክት መሆናቸውን አስቀድሞ የሚያውቀው አምላክ፣ የፍርድ ሰዓትን የቀጠረላቸው የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያቱ ውርንጫ ላይ ሆኖ በታላቅ ድል፣ ዝማሬና ሆታ ወደ ከተማይቱ በገባበት ሰዓት ኢየሩሳሌም በዝማሬ፣ በሆታና በሐሴት ተሞላች፡፡

በዛ ሁሉ ሆታ፣ ደስታና ሐሴት ውስጥ ተከታዮቹ ሐዋርያት፣ አይሁዳውያኑ፣ የኢየሩሳሌም ሴቶች፣ ጎበዛዝትና ሽማግሌዎች ሰማይ ሰማያትን በታላቅ ዝማሬና ሆታ በሞሉበት ቅፅበት፣ የቢታንያ ድንጋዮችና በእናቶቻቸው እቅፍ ውስጥ ያሉ ሕጻናት እንኳን ሣይቀሩ ለአይሁድ ንጉሥ የምስጋና ቅኔ በሚደረድሩበት አስደናቂ የማሕሌት ስርዓት ላይ አንድ ፈፅሞ በማንም ያልተጠበቀ እንግዳ ክስተት በኢየሩሳሌም ስለ ኢሩሳሌም ሆነ፡፡ በታላቂቱ የንጉሥ ከተማ፣ በሳሌም፣ በሰላም ከተማ በኢየሩሳሌም፡፡

ይህን በአይሁዳውያኑ ዘንድ እንግዳና ፈፅሞ ያልተጠበቀ ክስተት ወንጌላዊው ሉቃስ እንዲህ ሲል በወንጌሉ ውስጥ አስፍሮታል፡-
ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት እንዲህ እያለ፡- ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ እንኳን ብታውቂ፣ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል፡፡ ወራት ይመጣብሻልና፣ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል፣ ይከቡሻልም፣ በየበኩሉም ያስጨንቁሻል፡፡ አንቺንም በአንቺም ውስጥም የሚኖሩትን ልጆችሽን ይጥላሉ፡፡ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተውም፡፡ የመጎብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና፡፡
አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ እንደዘገበው ቅኝ ገዢዎቹ ሮማውያን ኢየሩሳሌምን ለቀናት ከበው፣ የከተማይቱን መውጫና መግቢያ ዘግተው፣ አይሁዳውያኑ መውጣትም ሆነ መግባት እንዳይችሉ አድርገው አስጨንቀዋቸው ነበር፡፡ በዚህም ንጉሣቸው ኢየሱስ እንደተናገረው ኢየሩሳሌም፣ ሕዝቦቿና ልጆቿ ሁሉ ሳይቀር እንደ መርግ በከበደ መከራ፣ በጭንቀትና በምጥ ጣር ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
በቅድስት ከተማቸው ቅጥር መያዝ ለራብ የተጋለጡት አይሁዳውያን ከበባው በተጠናከረ ቁጥር የሚላስ የሚቀመስ በማጣታቸው የተነሳ የፈረሶቻቸውን ኮርቻ፣ የዛፍ ፍሬዎች፣ ስራ ስርና ቅጠላ ቅጠል እንኳን ሣይቀር ለመብላት ተገደው ነበር፡፡

የሮማውያኑ ከበባ አላፈናፍን ሲልና ራቡ በእጅጉ እየከፋ በሄደበት ወቅትም ይህንኑ የዛፍ ቅርንጫፍና ፍሬም ሆነ ስራስርና ሳር ለመብላት በሚደረግ ሽኩቻ በርካታ አይሁዳውያን እርስ በርሳቸው በመጋደል፣ አባት ለወንድ ልጁ፣ እናትም ለሴት ልጇ መራራት ያልቻለችበትና ሁሉም ራሱን ለማዳን የሚፍጨረጨርበት ክፉና አሰቃቂ የሆነ እልቂት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ በዛን ቀውጢ ወቅትም የገዛ ልጆቻቸውንና ወገኖቻቸውንም የበሉ ሰዎች እንደነበሩ ጽፏል ታሪክ ጸሐፊው ጆሴፈስ በአይሁዳውያን ታሪክ መጽሐፉ፡፡

መቼም ራብ ቀን አይሰጥም፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ በተከሰተው በተለምዶ ክፉ ቀን በሚባለው የራብ ዘመን አንዲት እናት ሕጻናትን እየያዘች በመብላት ነፍሷን ለማቆየት ባደረገችው ጭካኔ የተነሣ ተከሳ ንጉሡ አፄ ምኒልክ ፊት ቀርባ እንደነበርና ይህን የሰሙት አፄ ምኒልክም በሁኔታው አዝነው ዕንባቸውን ማፍሰሳቸውን ታሪካችን ይነግረናል፡፡
በዚህ ሁሉ ራብና ሰቆቃ ውስጥ የነበሩት አይሁድ የጠላቶቻቸው ከበባ በቀረበ ቁጥር ነፍሳቸውን ከጠላቶቻቸው እጅ ለመታደግ ሲሉ የኢየሩሳሌም መቅደስን ተገን አድርገው ነበር፡፡ ምንም ጠላቶቻችን ቢበረቱብንና ቢያሸንፉንም የአባቶቻችን አምላክ ይህን መቅደስ በአሕዛብ እግር ይረገጥና ይዋረድ ዘንድ አሳልፎ አይሰጠውም በሚል ተስፋ ከራብ እልቂት የተረፉ በርካታ አይሁዳውያን የኢየሩሳሌሙን መቅደስ የሙጥኝ ብለውት ነበር፡፡

ግና ያ የተመኩበት፣ ያ የአባቶቻችን አምላክ በምንም ሁኔታ ለጠላቶቻችን አሳልፎ አይሰጠውም፣ የአሕዛብ እግርም አይረግጠውም ባሉት መቅደስ ውስጥ አይሁዳውያን በመጨረሻ ሰዓት በአረመኔዎቹና በአሕዛብውያኑ በሮማውያን እጅ ከምንሞት በማለት እርሰ በርሳቸው በሰይፍ ተራርደው ተላለቁበት፡፡ አይሁዳውያኑ በዚህ የእርስ በርስ እልቂት ደማቸው በመቅደሱ መሠዊያ መካከልና በመቅደሱ በር ታች እንደ ጎርፍ መፍሰሱን አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ ይተርክልናል፡፡
ጆሴፈስ የቅዱስ መቅደሱን ፍፃሜ፣ የከተማይቱን የኢየሩሳሌምን ውድመትና ጥፋትም በእንዲህ ልብን በሚሰብር ሁናቴ ትረካውን ይቀጥላል፡፡

ሮማዊው ጄኔራል ቲቶና ሠራዊቱ ወደእዛ ባለ ታላቅ ግርማና ለ46 ዓመታት ሲሠራ ወደነበረው ውብ ቤተ መቅደስ ዓይኖቹን ባማተረ ጊዜ ከውበቱና በቤተ መቅደሱ ጣራዎችና ግድግዳዎች ላይ በፈሰሱት ወርቆችና የከበሩ ማዕድኖች በእጅጉ ተገርሞ ነበር፡፡ እናም ጄኔራል ቲቶ በምንም ሁኔታ ቢሆን በዚህ ውብ መቅደስ ላይ ማንም እጁን እንዳያነሳ ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያን ለሠራዊቱ አስተላልፎ ነበር፡፡

ለቀናት በሮማውያን ከበባ ስር የወደቁት አይሁዳውያን ግን እንደ ምንም የሞት ሞታቸውን ከራብ የተረፋቸውን ጉልበታቸውን አሰባስበው በሮማውያኑ ላይ የደፈጣ አደጋ ጣሉባቸው፡፡ ‹‹ብጥለው ገለበጠኝ›› እንዲሉ አበው በዚህ የደፈጣ አደጋ በእጅጉ ከተበሳጩት ሮማውያን መቶ አለቃ መካከል አንዱ በእሳት የተቀጣጠለ ችቦ አይሁዳውያኑ ወደተከማቹበት ወደ ቤተ መቅደሱ በመወርወር፣ ቤተ መቅደሱ በእሳት እንዲጋይ የመጀመሪያውን እርምጃ ወሰደ፡፡ ቀጥሎም ሌሎቹም የሮማ ወታደሮች ወዳዛ አይሁዳውያኑ ወደሚኮሩበትና እንደ ነፍሳቸው ወደሚሳሱለት ቤተ መቅደስ የጥፋትና የእልቂት ሰይፋቸውን መዘው በመግባት መዓታቸውን ማዝነቡን ተያያዙት፡፡

ቤተ መቅደሱ በእሳት እየተቀጣጠለ መሆኑ መልእክት የደረሰው ሮማዊው ጄኔራል ከልዩ ጠባቂዎቹ ጋር በፈረስ ገስግሶ ከቦታው ሲደርስ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ነበር፡፡ ቤተ መቅደሱ በእሳት እየተያያዘና ሮማ ወታደሮችም በቤተ መቅደሱ ተተገነው ያሉትን አይሁዳውያን ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነበር፡፡ በመቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ያሉት አይሁዳውያንም በአሕዛብ እጅ ከመውደቅ በማለት እርስ በራሳቸው በሰይፍ አንገታቸውን እየተቀላሉ በራሳቸው ላይ አሰቃቂ የሆነ ሞትንና እልቂትን አወጁ፡፡

በእሳት እየጋየ ያለው መቅደሱና በመቅደሱ ውስጥ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ያለው የአይሁዳውያኑ ደም፣ ቤተ መቅደሱ ከተሠራበት ወርቅና የከበሩ ማዕድናት ጋር እየተዋኸደና እየቀለጠ የፈጠረው ልዩ ህብር ኢየሩሳሌምን ሀምራዊ የእሳት ከተማ፣ የነበልባል አምድ አስመሰላት፡፡ ልባቸው በመቅደሱ ወርቅና የከበሩ ማዕድናት የነኾለለው ሮማውያኑ ወታደሮችም የመቅደሱን ድንጋይ እያፈረሱና እየናዱ ለዘረፋ ተሸቀዳደሙ፡፡

The Great Controversy መጽሐፍ ደራሲ የሆነችው የቤ/ን ታሪክ ጸሐፊ ኤለን ጂ. ኋይት የሮማውያኑ የመቅደሱን ወርቅ ለመዝረፍ በወሰዱት የመቅደሱን ድንጋይ የማፍረስ ድርጊት ኢየሱስ ስለ መቅደሱ ሲናገር ‹‹ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም፡፡›› ያለው ትንቢት እንዲህ ባለ አሰቃቂና ዘግናኝ ሁኔታ ፍፃሜውን አገኘ ስትል ጽፋለች፡፡

ኤለን በዚህ መጽሐፏ ውስጥ ለዘመናት አይሁዳውያኑ ሲኩራሩበት የነበረው ቤተ መቅደስም ሊያድናቸውና ሊቀድሳቸው የመጣውን ጌታቸውንና መሢሐቸውን በመግፋታቸውና ለሞት አሣልፈው በመስጠታቸው የተነሣ ኢየሩሳሌም እንዲህ ላለው የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ቁጣና መዓት ተላልፈው ተሰጡ በማለት አስረግጣ ጽፋለች፡፡

ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ ትላለች ኤለን በዚሁ መጽሐፏ፣ ኢየሱስ በመጨረሻ ጊዜ ወደዚህ መቅደስ በገባበት ጊዜ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን ነጋዴዎች፣ ዘራፊዎችና ወንበዴዎች በጅራፍ ገርፎ ካሰወጣና ‹‹የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን ወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኹት፡፡›› በማለት ቅዱስ መቅደሱን የንግድ ቤት ያደረጉትን ወንበዴዎች ከገሰጻቸው በኋላ፣ ‹‹… ከእንግዲህ ቤታችኹ የተፈታ ይሆናል፡፡›› ብሎ በተናገረው ትንቢታዊ ቃል መሠረት በመቅደሱም ሆነ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ የጌታ ትንቢት አንድ በአንድ ተፈፅሟል ስትል ትደመድማለች፡፡

በዘመናችንም ‹‹የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት ይሆናል፡፡›› በሚል የድኾችና የምስኪኖች መጠጊያ እናት ናት ተብላ የተነገረላት ቤተ ክርስቲያን በተቃራኒው የንግድ ቤትና የወንበዴዎች ዋሻ ወደመሆን የተሸጋገረች ነው የምትመስለው፡፡ በርካታ ድሆች፣ አረጋውያንና መበለቶች፣ እናት አባት የሌላቸው ሕጻናት፣ ድውያንና መጻጉዎች በደጇ የወደቁ ቤተ ክርስቲያን የእነዚህን ድሆችና ምስኪኖች ጩኸትና ዋይታ አላየኹም አልሰማውም በሚል የንግድ ቤት ግንባታ ውድድር ውስጥ የገባች ነው የምትመስለው፡፡

ቤተ ክርስቲያን ዙሪያዋን በንግድ ቤትና በሱቆች ተንቆጥቁጣ በገንዘብ ባሕር ውስጥ እየዋኘች፣ ሀብትና ንብረቷ በአስመሳዮች፣ በወንበዴዎች፣ በሙሰኞችና በአጭበርባሪ ነጋዴዎች እየተዘረፈ ባለበት በዚህ ወቅት በደጇ ለወደቁ ድሆችና ምስኪኖች ምዕመኖቿ ከሚጥሉላቸው የሳንቲም ሽርፍራፊ በስተቀር ቤተ ክርስቲያኒቱ ለእነዚህ ድሆች ዘላቂነት ያለው ሥራ ከመሥራት ይልቅ የመቃብር ሥፍራ እንኳን ሁሉ ሳይቀር እያፈረሰች የንግድ ቤትና ሱቆችን እየገነባችና እያስፋፋች ነው ያለችው፡፡

እስቲ ለመሆኑ በከተማችን የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ለአረጋውያን መጦሪያ፣ ለድኾች መርጃ የሚሆን ተቋም የገነባው፡፡ በጣም ጥቂትና በጣት የሚቆጠሩት አብያተ ክርስቲያናት ለትውልድ ማፍሪያ የሚሆን የትምህርት ተቋማት መገንባታቸውን አይተናል፡፡ እነዚህም የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ በአብዛኛው በራቸው ክፍት የሚሆነው ኪሳቸው ደጎሰ ላሉት እንጂ ለድሆችና ረዳት ለሌላቸው አይደለም፡፡ ቢሆንም ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ዙሪያና አጥር በንግድ ቤተ ከሞሉት እነዚህኞቹ መቶ በመቶ ሳይሻሉ አይቀርም፤ ቢያንስ ትውልድ እየቀረጹ ነውና፡፡

በከተማይቱ እምብርት ባሉ አንዳንድ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የመዝናኛ ስፍራዎችና ጭፈራ ቤቶች አንኳን ለሀያ አራት ሰዓት የማይቋረጥ አገልግሎት በሚሰጡበት በዚህ ዘመን የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ግን እህል ውኃ የማያሰኝ ቆመጥና ነፍጥ ባነገቱ ዋርድያዎቿ በሯ ከምሽት ሰዓት በኋላ በትላልቅ ሰረገላና መሸጎሪያዎች ተቆልፈው ድሆች ከግቢዋ ተገፍትረው እየወጡ ለሌሊቱ ብርድና ቁር ተጋልጠው እንዲኖሩ ይፈረድባቸዋል፡፡ እናም እነዚህ ድኾችም በሺሕዎችና በአስር ሺሕዎች በሚቆጠር ብር በሚከራዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የንግድ ማእከላት በረንዳ ላይ ወድቀው ኑሮአቸውን በምሬት ይገፋሉ፡፡

በእኛ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱ ስፍራ፣ ቤተ መቅደሱ፣ ‹‹የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት ይሆናል፡፡›› ቤተ ክርስቲያን የድኾች መጠጊያና እናት ናት፡፡ የሚለው ኃይለ ቃል ከንግግር ወይም ከስብከት ወጥቶ ተግባራዊ መሆን ያቃተው ነው የሚመስለው፡፡ እስቲ ብዙም ሳልርቅ ወደተነሣኹበት ዋና ርዕሰ ጉዳዬ ወደ በዓለ ደብረ ዘይት መደምደሚያ ሐሳብ ልመለስ፡፡
ከ70 ዓ.ም. ጀምሮ ከምድረ ገጽ ጠፍታ የነበረችው እስራኤል እንደ አገር በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1948 ወደ ዓለም መድረክ ብቅ ብትልም በ70 ዓ.ም. በሮማውያኑ የፈረሠው የቤተ መቅደሷ ጉዳይ ግን አሁንም ያልተፈታ እንቆቅልሽ እንደሆነ ዘልቋል፡፡ ኤለን ጂ. ኋይትም ሆነች ሌሎች በርካታ የሥነ መለኮት ሊቃውንት እንደሚያብራሩት የኢየሩሳሌም መቅደስ መፍረስ እስካሁንም ድረስ በርካታ አይሁዳውያን በሐዘንና በሰቀቀን የሚያስታውሱት የታሪካቸው ዋና ክፍል ነው፡፡

እናም የእስራኤል እንደ መንግሥት መመሥረትና በተለይም ደግሞ አይሁዳውያኑ በዓለም ፍፃሜ የፈረሠውን መቅደሳቸውን እንደገና ለመገንባት የሚነሡበት ቀን በዓለም ታሪክ ውስጥ የምድራችን ታሪክ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆናል ሲሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ትንቢቶችን በማስደገፍ ያብራራሉ፡፡

ይኸው ከደብረ ዘይት በዓል ጋር በተራራዋ ደብረ ዘይት የተነሣ ተደጋግማ የምትነሳውና የዓለማችን ታሪክ ፍፃሜ መድረክ ናት ተብላ የምትታወቀው እስራኤል አሁንም ድረስ ዓለምን ሁሉ የልብ ትርታ ይዛ ያለች አገር እንደሆነች ቀጥላለች፡፡ የምድሪቱ ዕጣ ፈንታ መዘውር በእጇ የያዘች የምትመስለው እስራኤል የምድራችን ኃያላን ሁሉ ዓይን ማረፊያ ናት፡፡ እናም ዘወትር የዓለም ሁሉ ሕዝብ ዓይንና ጆሮም ወደዚህች ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ቅድስት ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ነው፡፡

በዚህ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ስርዓት በሚከበረው በዓለ ደብረ ዘይት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤ/ን ቅዳሴው፣ ዝማሬው፣ የቅዱሳት መጽሐፍት ንባባት ሁሉ ከዚሁ ከዓለም ፍፃሜ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዕለቱም የዓለም ፍፃሜ፣ የመጨረሻው ፍርድና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የሚታሰብበት ቀን እንደሆነ ነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንቶች በስፋትና በጥልቀት ሚያስተምሩት፡፡

የደብረ ዘይት በዓል በትግራይ ክልል በማይነብሪ ናዝሬት የምትባል ቦታ አለች፤ በዚሁ በማይነብሪ በናዝሬት በምትገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በዓሉ ታላቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትና ድምቀት እንደሚከበር ታሪክ አዋቂ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት በሚገኘው በሳማ ሰንበት የደብረ ዘይት በዓል በርካታ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በአጠቃላይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገደማትና አድባራት የደብረ ዘይት በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በድምቀት ይከበራል፡፡

ከበዓሉ ፍፃሜ በኋላም ምዕመናን እህል ከመቀመሳቸው በፊት የሚበሉት ከጥራጥሬ የተዘጋጀ በቆልት ነው፡፡ ይኽም ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ ምስጢርና ትርጓሜ እንዳለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ የዚህ በቆልት የመብላት ተምሳሌትነቱ የሞተ፣ የደረቀ ከሚመስለው ጥሬ ዳግም ሕይወት ዘርቶ መብቀሉ የትንሣኤ ምልክት ሲሆን ምዕመናን ይህን በቆልት መብላታቸው በዳግም ትንሣኤ እንደሚነሡ ለማጠየቅ ነው፡፡

ምናልባትም ምእመናን ይህን በቆልት ሲበሉ ያልበቀለ ጥሬ ካገኙ ከአፋቸው አውጥተው ይተፉታል፡፡ ይኽም ተምሳሌትነቱ በዳግም ትንሣኤ ለኩነኔና ለዘላለም ጥፋት ከሚነሡት ፈጣሪያቸው እንዳይደምራቸው ለማጠየቅ ነው፡፡ ይህ የደብረ ዘይት በዓል ታላቅ ከሆነው መንፈሳዊ ምሥጢሩና ድባቡ ባሻገር ታሪካዊና ባህላዊ አንድምታ ያለው የቱሪስት መስህብ ሊሆን የሚችል ታላቅ በዓል ነው፡፡
ሰላም! ሻሎም!

ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ! ፈቃዱ በቀለ

ሕዝበ አዳም ቁርጥሽን ዕወቂ! ዘመን ተፈጸመ! ይሄይስ አእምሮ

ወይ አንቺ ክምሬ አለሁኝ ብለሻል፤
ባታውቂው ነው እንጂ በቁምሽ አልቀሻል፡፡

ይህች ግጥም በልጅነት ካዳመጥኳቸው ሥነ ቃላት የማስታውሳት ናት፡፡ አግባብነቷ ለድሃ ገበሬ ነው፤ ክምሩን በብድርና በልቅት የጨረሰ ገበሬ በክምሩ አጠገብ ባለፈ ባገደመ ቁጥር እያያት፣ ስትወቃ ብድር መክፈያ እንጂ ለርሱ የሚተርፈው ነገር የሌለው መሆኑን ለማስታወስ የሚጠቀምባት ናት፡፡

እኔ እዚህ ላይ ያመጣኋት ግን ለቁሣዊ የምግብና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም፡፡ የዘመናችን ሰው በጣም የዋህ ሆኗል፡፡ በተጠመደለት ፈንጂ እየተረማመደ ፈንድቶና ጋይቶ የሚያልቅ፣ በተቆፈረለት ጉድጓድ እየዘለለ በመግባት ራሱን የሚጨርስ፣ በጥቅሉ ጥቂቶችና በጫንቃው ላይ የተጎመሩ ልሂቃን ተብዬዎች የደገሱለትን የመከራና የዕልቂት ድግስ ማስተዋል የተሳነው ሆኗል፡፡ በዚሀች ወረቀት ብዙ መናገር አልወደድኩም – አልችልምም፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ የሚያስጨንቀኝን ነገር ቢያንስ ጥቂት ሰዎች ባገኝ ለነሱ ልተንፍስና መጠነኛ ምርምርና ራስን ፍለጋ እንዲያካሂዱ በማስታወስ የተወሰነ እፎይታ ላግኝ፡፡

የቤተ ሳጥናኤል እምነት በአንቷን ሌቪ በ1966 እ.ኤ.አ በይፋ ከተመሠረተ ወዲህ ይህ ብዙ ታላላቅ መሪዎችንና የኪነ ጥበብ ሰዎችን እያበለሻሸ የሚገኝ ቤተ እምነት በአሁኑ ወቅት ተልእኮውን በማገባደድ ላይ ያለ ይመስላል፡፡ በዚህ ዘመን በሥልጣንና በሀብት የመጨረሻው ጫፍ ላይ ከሚገኙ የዓለማችን ዜጎች ስንቶቹ ከሰይጣናዊነት ነጻ እንደሆኑ መገመት ይከብዳል – ከሞላ ጎደል ሁሉም ጠፍቷል ማለት ይቻላል፡፡ ጊዜው አሳሳቢ ነው ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛ የታሪክ አንጓ ላይ እንደምንገኝ ይችን ማስታወሻ የምናነብ ሰዎች ልብ ልንል ይገባል፡፡ ለማስታወስ ያል እንጂ ይሄ ነገር የማይሰወርብን ብዙዎች እንዳለን ይገባኛል፡፡ ነገር ግን እንደቃሉ ሆነና ልባችን ከድንጋይ ብሶ ጠጠረ፡፡ በዙሪያችን እየሆነ ያለውን ነገር መረዳትም አቃተን – ብንረዳም ቅሉ የምናደርገውን አጥተን አንድ በመቶ ማይሞሉ የዓለም ዜጎች ዘጠና ዘጠኙን እንደበግ ይነዱት ያዙ፤ አስገራሚ ዘመን፡፡ ‹ምነው በዚህ ዘመን ባልተፈጠርኩ› በሚል ክፉኛ የሚያስቆጭ ዘመን፡፡
ከዚህ በታች የሚገኘው ዓርማና የዓርማው ተጠቃሚዎች በየጊዘው ከሚዲያ የማይጠፉ የዓለማችን ብርቅዬ ዜጎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች እስላምና አማራ ሳይሉ ሁሉም በሰይጣን መንገድ የሚጓዙ ናቸው፡፡ ከኦባማ ጀምሮ የሰይጣን የሰላምታ መለዋወጫ ምልክት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ቀስ እያላችሁ ተመልከቷው፡፡ አድራሻም ስላለ ሌሎቹን እዚያው በቦታቸው ተመልከቱ፡፡ ሰይጣን በሚገዛት ዓለም መኖራችንን ለማጠየቅ ከዚህ በላይ ምሥክርና ማስረጃ የለም፡፡

ስለዚህ ወንድና ወንድ ተጋባ፣ ሴትና ሴት ተጋባ፣ መንግሥታት ይህን ከእንስሳም የወረደ አረመኔያዊና ሰይጣናዊ ህግ በህጎቻው አጸደቁ፣ ሞራል ጠፋ፤ ሃይማኖት ጠፋ፣ የሃይማኖት መሪዎች ሳይቀሩ ራሳቸው ግብረሶዶማዊና ሌዝቢያን ሆኑ፣ ቤተ ክርስቲያን በከተች – ገማች፣ እረኞች ጠፉ -በጎች በቀበሮና በተኩላ ተበሉ፣ ዓለም ጠነባች – ቆነሰች – የወሮበሎችና ዋልጌዎች መጫወቻ ሆነች፣ ጦርነትና ርሀብ ነገሡ፣ ተፈጥሮ በሰው ልጆች ጨከነች፣ ፀሐይ ገረረች – መፋጀቷንም አባባሰች፣ በጎርፍና በናዳ ህዝብ አለቀ፣ በጨካኝና አምባገነን መሪዎች ዜጎች ተሰቃዩ፣ ‹ሕዝብ በሕዝብ መንግሥትም በመንግሥት ተነሡ›፣ ውርጋጦች መንግሥትን በጉልት እየገለበጡ ሕዝብን አስመረሩ፣ በረዶ ቀለጠ፣ ውቅያኖሶችና ባህሮች ድንበሮቻቸውን ጥሰው ምድርን አጥቀለቀለቁ፣ ሱናሚና የመሬት መናወጥ አዳሜን ፈጀ፣ ንፋስና ወጀብ በዓለማችን ሰለጠነ፣ ኒኩሌር በመካከለኛው ምሥራቅ ማስገምገሙን ቀጠለ፣ ጥላቻ ሠፍኖ ፍቅር ጠፋ፣… የምንለው ሁሉ መነሻው ይሄ ከዚህ በታች በጥንጡ የጠቆምኩላችሁ መሆኑን ተረዱና ራስን ለማዳን ብልሃትና መንገድ ካለ – ይኖራልም – አሁኑን የመዳኛ መንገድ ለመምረጥና ለመዳን እንሞክር፡፡ ጊዜው ደርሷል፡፡ የክህነት ሥልጣን ቢኖረኝ – አሁን አልውደደውና እወደው እንደነበረው ቀልደኛ ተስፋየ ካሣ ‹ወዮልሽ ምዕመናን! እዚያ ላይ ስትሄጅ እዚህ ቁረጥ እዚያ ቁረጥ የለም – ፆም ፁሚ፣ ሀጢኣት አትሥሪ…› እያልኩ በሰበክሁ ነበር፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ (እያሳቀቀ?)ነው አሉ …

Sources:
1. http://www.religie.eu/SLANG-occultisme/10.Gehoornde-teken/gehoorndeteken-signsofSatan.htm

2. http://www.forthenations.com/Worse.html

ም/ጠ ሚኒስትሩ «እስክንድር ነጋን እንፍታ» አሉ በአማኑኤል ዘሰላም

ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በእነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌና ሌሎች ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዙሪያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉስጥ ዉይይት እንደተደረገ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መጋቢት 18 2005 ዓ.ም ባቀረበዉ ጽሁፍ ዘግቧል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዳዋለም አራጌ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ፣ አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ፣ አገር ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያዉያን ፣ ከገዢዉ ፓርቲ የተለየ አቋም በማንጸባረቃቸው ብቻ፣ በፈጠራ የሽብር ወንጀል ተከሰው በቃሊቲ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ።

በፍርድ ወንበር ላይ የሚቀመጡ አብዛኖቹ ዳኞች፣ የሕግ ባለሞያ ከመሆን ይልቅ ካድሬነት መሆን፣ ሕግን በማስከበር ፍትህ እንዲሰፍን ከማድረግ ይልቅ፣ የገዢው ፓርቲ ተቀጥያ በመሆን እና ሕግን እንደበትር በመጠቀም ተቃዋሚዎችን ማጥቃት የሚቀናቸው ናቸው። በድብቅ የተሰራ ወንጀልን የሚያሳይ አንድም ሰነድ ሳይኖር፣ በሽብር ተግባር የተገድሉ ዜጎች ወይንም ለሽብር ተግባር ሊዉሉ የሚችሉ እንደ ቦምብ፣ ፈንጂ የመሳሰሉ በሌሉበት ሁኔታ፣ እነ እስክንድርን ሽብርተኛ ብሎ በጭፍን የበየኑት፣ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተቀምጠዉ የነበሩትን፣ ዳኛ ተብዬ ካድሬዎችን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

አልፎ አልፎ ግን ሕሊናቸዉን የሚያዳምጡ፣ የሕግ ባለሞያዎች ኤቲክስ ኮድ ግድ የሚላቸው፣ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያላቸው የሕግ ባለሞያዎች እንደ ብልጭታ ብቅ የሚሉበት ሁኔታ አለ። እነ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ፣ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ የመሳሰሉቱ ላለፉት ሃያ የኢሕአዴግ ዘመናት፣ ካየናቸው እጅግ በጣም ጥቂት እዉነተኛ የሕግ ባለሞያዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። እንደ እነዚህ አይነት ዳኞች በብዛት ቢኖሩን ኖሮ አገራችን ይሄን ጊዜ የትናየት በደረሰች ነበር።

ሰሞኑን የሕግ ባለሞያዎችን የሚያኮሩ ፣ ለፍትህ መስፈን ቁርጠኝነትን ያሳዩ፣ አንድ ዳኛ አግኝተናል። አቶ አማረ አሞኝ ይባላሉ። የጠቅላይ ፍርድ ቤት መሃል ዳኛ ናቸው። የእነ እስክንድር ነጋን ጉዳይ የያዙት እርሳቸው ናቸው። ተከሳሾችም አቃቢ ሕግም ያቀረቡትን መረጃዎች፣ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ የያዘዉንም ሰነድ፣ በጥንቃቄ መረመሩ። አቃቢ ሕጎችን ጠርተዉ «ይህን ሰው (እስክንድር ነጋን) አሸባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ» ሲሉ የነ እስክንድርን ሽብርተኛ አለመሆን ከወዲሁ አሳወቁ።
ጋዜጠኛ ተመስገን እንደዘገበዉ አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው «ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽናበት የሚል ምላሽ ሰጡ።

የሚኒስተሮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ስብሰባ አደረገ። አቶ አማረ አሞኝ ተጠርተዉ ማብራሪያ ሰጡ። ዳኛዉ እስክንድር ነጋን «አሸባሪ ብሎ ለመፍረድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ በሚቀጥለው ቀጠሮ በነፃ አሰናብተዋለሁ። እንዲህ ማድረግ አትችልም የምትሉኝ ከሆነ ግን ክቡራን ሚኒስትሮች በዕለቱ በችሎት ለመሰየም ፍቃደኛ አለመሆኔን በትህትና ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ!» በሚል እዉነታዉን ግልጽ አደረጉ»
በመጀመሪያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት በፍርድ ሂደቱ ላይ ጣልቃ ገብቶ ዳኞችን ጠርቶ የማነጋገር መብት ከየት እንዳገኝ ቢነገረን ጥሩ ነበር። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን ጨምሮ አብዛኞቹ የኢሕአዴግ መሪዎችና ካድሬዎች እየደጋገሙ ሲነግሩን የነበረው፣ ሕግ መከበር እንደነበረበት ነዉ። እኛም እንስማማለን። ታዲያ ዳኞችን እየጠሩ ማስጠንቀቅና ማስፈራራት ያለዉን ሕገ መንግስት ቀዳዶ እንደ መጣል አይቆጠርምን ? ሕግን መናቅ አይደለምን?

በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የተለያዩ ሃሳቦች እንደቀረቡ አቶ ተመስገን ዘግበዋል። ‹‹እኔም ከአቶ አማረ ጋር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰውዬ /እስክንድር/ የተነሳ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህም ብንፈታው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ፡፡›› ሲሉ ስብሰባውን የመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቶ ደመቀ መኮንን ብስለት ያለዉ አስተያየት ይሰጣሉ።
«የአለም አቀፍ ጫና ስለበዛብን እስክንድርን ብንፈታ ጫናዉ ይቀንስልናል። እኛም እንጠቀማለት» ከሚሉ «እኛን እንደ ድርጅት ጠቀመም አልጠቀመም ፣ ፍትህ መከበር አለበት። ዜጎች ወንጀል ሳይፈጽሙ መታሰር የለባቸው» የሚል፣ ከፓርቲ ይልቅ ለአገር በማሰብና በመርህ ላይ የተደገፈ አስተያየት ቢሰጡ ኖሮ፣ የበለጠ አክብራቸው ነበር።

አቶ ደምቀ ባሉት ላይ እንደሚስማሙ የገለጹት አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ሚኒስቴር «ነገር ግን እስከዛሬ አስረነው ‹ነፃ ነህ› ብለን ብንለቀው የፖለቲካ ኪሳራ ስለሚያስከትልብን፣ ከፍርዱ ላይ ቅንስናሽ አድርገን ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ብናደርግ የተሻለ ነው» የሚል አስያየት ይሰጣሉ። እኝህ ባለስልጣን ደካማ ባለስልጣን መሆናቸውን ነው የሚያሳዩን። መልካም የሆነን ነገር ማድረግ፣ የተሰራ ስህተትን ማረም እንዴት ተደርጎ ነዉ የፖለቲካ ኪሳራ የሚያመጣዉ

ከክርስቶስ ልደት መቶ አመታት በፊት የነበሩ የሮማ ፈላስፋ ማርከስ ሲሰሮ «ማንም ሰው ስህተት ይሰራል። ነገር ግን ኢዲየት(ማሰብ የማይችል) የሆነ ሰው ብቻ ነዉ ከስህተቱ የማይታረመው» ሲሉ፣ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩትና አዲስ አበባ ያለ አንድ ትልቅ መንገድ በስማቸዉ የተሰየመ ዊንስተን ቸርችል ደግሞ «ሁሉም ሰው ስህተት ይሰራል። ነገር ግን ጥበበኛ ብቻ ከስህተቱ ይማራል» በማለት፣ ስህተትን ይዞ መቀጠል ሳይሆን ፣ ስህተት ማረም ተገቢ እንደሆነ ለማስረዳት የሞከሩት።
እነ እስክንድርን ማሰር ተገቢ እንዳልሆነ የተረዱ ባለስልጣናት፣ ስህተታቸውን አርመዉ፣ እስረኞችን መፍታት ይገባቸዋል እንጂ፣ የ«ምን እንባላለን« ኋላ ቀር ፖለቲካ ማራመድ የለባቸውም። ስህተትን ማረም ትልቅነት ነዉ። ስህተትን ማረም ያስከብራል። ስህተትን ማረም አንዳችም አይነት የፖለቲካ ጉዳት አያመጣም።

ሌላ ሶስተኛ ሚኒስቴር ስለ እስክንድር ነጋ ተናገሩ የተባለው አባባል ግን በጣም ከነከነኝ። «ኧረ ለመሆኑ መለስ አለም አቀፍ ጫና እንደሚያስከትል እያወቀ ለፓርቲያችን ጥቅም ብሎ የገባበትን ጉዳይ፣ ዛሬ እርሱ አልፏል ብለን ጫና የምንፈራበት ምክንያት ከየት የመጣ ነው? በቃ! መለስ አደገኛ ሰው ነው ብሎ አስሮቷል፡፡ አለቃ! እዛው ይበስብስ!» ነበር ያሉት። እንዲህ አይነት ጨቅላ የእንስሳ አስተሳሰብ ያላቸው ባለስልጣናት፣ ከዱር አራዊቶች ጋር በጫካ እንጂ በሰዎች መካከል መኖር የለባቸውም።

እኝህ ሚኒስቴር አቶ መለስን ይጠቅሳሉ። «አቶ መለስ የሰሩት ሥራ በሙሉ ትክክል ነዉ። እርሳቸው የወሰኑትን መሻር የለብንም። የርሳቸው ቃል የእግዚአብሄር ቃል ነዉ» የሚል ይዘት ያለው እጅግ በጣም ደካማ አስተሳሰብ ነዉ ያንጸባረቁት። የኢራኑ አያቶላ አሊ ሆሚኒ፣ በተቀበሩ ጊዜ፣ በሕይወታቸው አብረዋቸው የተቀበሩ ሰዎች እንደነበሩ ያነበብኩ መሰለኝ። እኝህ ሚኒስቴር ይሄን ያህል ለአቶ መለስ ፍቅር ካላቸው፣ አብረው ቢቀበሩና ሰላም ብናገኝ የተሻለ ነበር።

እነ አቶ ደምቀ፣ የጫካ ፖለቲካ በሚያራምዱ በጥቂቶች፣ ተነድተዉ፣ ሕሊናቸውን ሽጠው ድርጅታቸውና አገራቸውን የሚጎዳ ዉሳኔ አይወስኑም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አቶ አማረ አሞኝ በወንበራቸው ተቀምጠው፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ እንዲሆም ሌሎች የሕሊና እሥረኖች በሙሉ ነጻ ወጥተዉ፣ አዲስ የመቀራረብና የመቀባበል ፖለቲክ በአገራችን እንዲጀመር፣ ዜጎችን በግፋ የማሰርና የማሰቃየት ብሃል እንዲቆም ያደርጋሉ የሚል ተስፋ አለኝ።

በአገር ቤትም ሆነ በዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ እግዚአብሄር በስልጣን ላይ ላሉት ማስተዋልና ጥበብ ይዘጣቸዉ ዘንድ፣ በእሥር ለሚገኙትም ብርታትና ጥንካሬ ያበዛላቸው ዘንድ፣ በተዋረደ መንፈስና በትህትና እንዲጸልዩ ጥሪ አቀርባለሁ። ሌላ ማድረግ ባንችል ለፈጣሪ አቤት ማለቱ የሚያቅተን አይመስለኝም።

ኢትዮጵያ ወደአደገኛ አግጣጫ እያመራች ነው በከፍያለው ገብረመድኅን

ሀቁን እንነጋገር ከተባለ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት አገር አይደለችም። ይህ ማለት ግን ለጥቂቶች መንግስተ ሰማይ አልሆነችም ማለት አይደለም። ፍሬ ነገሩ ግን ሥልጣን ላይ ካሉት ስዎች ጋር በማበር የምዕራብ መንግሥታትና ኩባንያዎቻቸው፡ ጥቅሞቻቸውን ለማራመድና፡ አሁን ያለውን ስቴተስኮ እንዳለ ለማቆየት የፈልጉትን ያህል ቢደስኩሩም፤ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባይተዋሮችና በብዙ መልኩ ሕይወታቸው በአረብ አገሮች በግርድና ላይ ካሉ ወገኖቻችን ጋር ያለው ልዩነት መጠነ ጠባብ እየሆነ መምጣቱን መሸፈን አልቻሉም።

በሌላ አባባል፤ የስው ልጅ ውሎውና በቀኑ መጨረሻ ላይ በስላም ወደጎጆውና ቤተስቡ መመለሰሱ ዋስትና በሌለው ሁኔታ ውስጥ፤ ባልታሰበ ቀንና ስዓት ዜጎች ንብረታችውን በመንግሥት እንዳይነጠቁ የሚሰጉበት፤ ከሁሉም የከፋ ደግሞ ወደእሥር ቤት እንዳይወረወሩ፤ ልጆቻቸው ከሀግራችው አስፈሪ ሁኔታ በሥውር ለመሸሸ በሚያደርጉት ከሀገር የመሰደድ ሁኒታ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የሚሰጉበት – በአጭሩ ሕዝቡ አንገቱን ደፍቶ ለመኖር የተገደደበት ወቅት የነጻነትና የሰላም ጊዜ ነው ብለው የሚያስቡ ግለስቦች ከራሳቸው ምቾት ባሻገር ማየት የተሳናቸው ብቻ ናችው።

በየትኛውም ትርጓሜ፤ ይህ ሁኒታ በአንድ በኩል ከባርነትና በሥጋት ከተወጠረ ሕይወት በሌላ በኩል ደግሞ ከስላማዊና ነጻነት ጋር ሲወዳደር፤ በጉልህ የሚታየው የኢትዮጵያውያን ሕልውና ከፍርሀትና ሰቀቀን ነጻ እንዳልሆነ ነው።

Freedom House ይህንን ሁኔታ ቀደም ብሎ በመገንዘቡ፤ ላለፉት ዓመታት በተለይም ከ1998 – 2012 ባሉት ጊዜያት በስብአዊ መብቶች አክባበር ረገድ ኢትዮጵያ እንዴት እንዳሽቆለቆች በተከታታይ ዓመታዊ ረፖርቶቹ ሲያቀርብ ከርሟል። ለምሳሌ በ1998 የወጣው ሪፖርት የፖለቲካና ሲቪል መብቶችን አይያዝ በተመለከተ እንዲህ ሲል ዝግቦ ነበር:- “Ethiopia’s civil liberties rating changed from 5 to 4 due to improvements in civil society and greater economic freedom.”

በዚያን ጊዜ የታየው መሻሻል የኢትዮጵያ የስብአዊ መብቶች ይዞታ በመጭው ዓመታት ይበልጥ ይሻሻል የሚል አመለካከት ፈጥሮ ነበር። ይሁንና በሚቀጥለው ዓመት የወጣው የ1999 ዓ.ም. ሪፖርት እንደበፊቱ ተስፋ የቋጠረ አልሆነም። ጭብጡም እንዲህ ይላል:- “Ethiopia’s political rights and civil liberties ratings changed from 4 to 5 due to limitations on opposition political parties and civic organizations to undertake activities and disseminate information.”

Freedom House የአንድን ሀገር የስብአዊ መብቶች ይዞታ የሚለካው በሶስት መሥፈርቶች ነው። እነዚሀም (ሀ) የዜጎች ነጻነት መከበር (ለ) የዜጎች ሲቪል መብቶች መረጋገጥ እና (ሐ) የዜጎች ፖለቲካዊ መብቶች መከበር ናቸው። በእነዚሀ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ አንድም ጊዜ የዜጎች ነጻነት ሙሉ ለሙሉ የተከበረባት አገር ተብላ ተሰይማ አታውቅም። ለ12 ዓመታት “Partly Free” ስትባል ከርማ ክ2011 ጀምሮ ጭልጥ ብላ ወደ “Not Free” ተሸጋግራ፤ አሁንም በዚያ ጎራ ትገኛለች።

ወደዚያ ከገፋፏት ድርጊቶች መካከል በሁለቱ መለኪያዎች፤ ማለትም በዜጎች የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች አከባበር ያሳየቻቸው እንቅስቃሴዎች እጅግ ዝቅተኛ ከመሆን አልፎ ወደ መጥፎ በመሸጋገራቸው ነው። ለምሳሌ፤ በ2011 ወደ “Not Free” ተብላ ከተሰየመች በኋላ፤ በዜጎች የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች መከበር ያገኘችው ነጥብ በእያንዳንዳቸው ስድስት ከስድስት ነው። በ1999 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለቱም እነዚህ መለኪያዎች 5/6፡ 5/6 ስታገኝ ከርማ:ከ2011 በኋላ፤ ማለትም በገሀድም መለስ ብቸኛ መሪ ሆኖ ከወጣና የኢትዮጵያን ልማታዊ መንግሥት ካውጀ በኋላ ከላይ እንደተጠቀሰው ሀገሪቱ ሙሉ ነጻነት የሌለባት ተብላ ተፈርጃለች። በ2005 ዓ.ም. የመንግሥት ኅይሎች በአደባባይ ሰለማዊ ሠልፈኞች የረሽኑበት ሁኔታ እንኳ በከለር ኮድ (አምበር) ማስጠንቀቂያና ጠንካራ የቃላትና የፖለቲካ ውግዘት ነበር የታለፈው። ለአንድ አገር ክፍተኛው የፖለቲካ ውድቀት፤ የመጨረሻውንስድስት ክስድስት ማግኘት ነው።

Freedom House ለመጀመሪያ ጊዜ የመስብስብና የመደራጀት ነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ በገህድ አደጋ ላይ መውደቁን ያጋለጠው በ2003 ዓ.ም. ሲሆን: ያን ጊዜም እንዲህ በማለት የዘገበው:- “Ethiopia received a downward trend arrow due to the government’s response to civil unrest that has included heightened restrictions on freedom of assembly and organization.”

የድርጅቱ ይህ አመለካከት በምንም መልኩ አልተዛነፈም። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያርፉ: Freedom House በማግሥቱ የላከው የኅዘን መግለጫ ብዙ ቁም ነገር የያዘና ሀግሪቱ የወደቅችበትን አስከፊ የፍርህትና የነጻነት መጥፋት በሚገባ የሚያመላክት መሆኑን ከመሆኑም ባሻገር እጅግ በሚገርም ሁኔታ የወደፊቱን የሀገሪቱን ችግር በመጠኑም ቢሆን የዳሰሰ ነበር።

“While showing authoritarian tendencies from the beginning of his rule, Meles’s government initially adhered to a range of democratic standards. As the years passed, his leadership style became increasingly iron-fisted. Ethiopia’s designation in Freedom House’s Freedom in the World report declined from Partly Free to Not Free for events in 2010, as the government grew more hostile toward political opponents, media critics, and civil society activists. The country was also designated Not Free in parallel reports on press freedom and internet freedom. Freedom in the World registered a further decline for Ethiopia the following year, citing the misuse of antiterrorism laws to punish opposition activists and journalists. Given Ethiopia’s tragic and bloody political history—first under Emperor Haile Selassie, then under Mengistu—Meles’s refusal to institute governance norms based on democracy and human rights principles is an important and thoroughly unhappy part of his legacy.”
ከላይ የኃዘን መገለጫ ውስጥ ይተጠቀስው ሪፖርት (Freedom in the World 2011) እንዲህ ሲል ነበር የኢትዮጵያን የነጻነት ሁኔታ የመዘገበው:-

“Ethiopia’s political rights rating declined from 5 to 6, its civil liberties rating from 5 to 6, and its status from Partly Free to Not Free due to national elections that were thoroughly tainted by intimidation of opposition supporters and candidates as well as a clampdown on independent media and nongovernmental organizations.”
በ2010 በተፈጸሙት ገሃዳዊ የምርጫ ማጭበርበር፤ የመንግሥት ኅይልን መጠቀም፤ የሕዝብ መገናኛ አውትሮቹን በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በማፈኑ አገር ለማስተዳደር ብቃት እንደሌለው መለኪያ ተደርጓል።

ሀገር ተቆረሰች፡ መለስና ሕውሃት እንዲያውም ብርታት አገኙ። አበሻ ወድግል ጥቅሙ አደላ። ሽፍታ መንግሥት ሲሆን፤ ዘራፊ ኅይሉን የመንግሥት የጦር ኃይል ያድርግና፤ ያ የሽፍትነት ባህሪው ስለማይለቀው ሕገመንግስታዊ ድጋፍ አግኝቶ የሀገር ምዝበራም ሕጋዊነት ያገኛል። ዘመናዊ ሽፍቶች ስለሆኑ፤ ሁሉን ያሞኙ መስሏችው (የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ) EFFORTን አቋቋመው። የሀገርን ሀብት በሼር ተከፋፍሉት። ጄኔራሎቹ ዛሬ የሐር አንሶላ ኮስኮሰን እያሉ፡ በትዕዛዝ የተስሩ አንሶላዎች ክሆንግ ኮንግ ያስመጣሉ። በየስድስት ስዓት ርቀት ውስጥ በስም የመከላክያ ሚኒስቴር ህብት የሆኑ ሆቴሎች እንዲሠሩ ወይንም እንዲገዙ ወስነው ለእነዚህ ዘምናዊ መሣፍንት መዝናኛ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

መለስና ሕወሃት ሥልጣን ከያዙበት ቀን ጀምሮ የፈለጉትን በአደባባይ ረሽኑ፡ ቀሪውን እሥር ቤት በዘር በዕድሜ እለዩ ትውልድ አኮላሹ። ሌሎቹ ብሄረስቦች እነርሱ የሚያዳርጉትን ሁለት ዕጥፍ አድርገው ዘረፉ፤ ሕዝቡን ረገጡ። የኢትዮጵያ ውርደት መጠኑን የሚገንዘብ የተሻለ ትውልድ ካልመጣ በስተቅር የጥፋት ውሃ እያንዳንዱ ዜጋ እያቀና ነው። ዛሬ በገሃድ አገር እየተመዘበረች ነው። ብዙው አገር ለቆ ተሰደደ፤ ሀገሪቱም፡ ነጻ ሆና ያልኖረች ይመስል “ሀ” ብላ የጀመረችው ገንባታም ክ20 ዓመታት መከራ በሁላ ከባሕር ዳር እንደስማነው፤ ድንብር ግትር እየሆነ ነው።

መታውቅ ያለበት፤ ሕወሃት እጅግ በሚያስከፋ መንገድ የስው ልጆችን መብቶትችና ነጻነቶች መግፈፍን የጥንካሬውና ሥልጣንን መቆናጥጫው መሣሪያው ስላደረገው፤ ከሌሎች ጥፋቶችና ክፋቶች ይቆጠባል ብሎ ማስብ የዋህነት ነው። እንዲያውም፤ ኢትዮጵያን የማዋረዱን ሥራ ገና አላጠናቀቀም። በመስጊዶችና በኔተክርስቲያኖች የሚፈጸመው ባዕድ ደባ ይህንኑ አመላካች ነው። ችግሩ ቀጣዩ የጥፋት ተግባር የሚካሄደው በአዕምሮም ሆን ኅሊና ምንም ዐይነት ብቃት በሌላቸው ስንኩሎች በመሆኑ፡ ጥፋቱ ከእዚህ በታች እንደተመለከተው የክፋና የተፋጠነ ይሆናል።

ዘር የማጽዳት ፕሮግራም በምድረ ኢትዮጵያ (Ethnic Cleansing)?

በተለይም በተደጋጋሚ በማን አለብኝነት ሲካሄድ የነበረው ሕዝቡን የመክፋፈል ፖለቲካ ወደ የዘር ማጽዳት ዘመቻ (Ethnic Cleansing) ከተለወጠ ስንበት ብሏል። ሕወሃት የመጀመሪያ ረድፍ ጠላቶቹ አድርጎ የሚያያችውን ኦርሞችንና አማሮችን በገሀድና በስውር መንገድ እየጠራረገ፡ አገሪቱን በብቸኛነት የሚገዛበትንና የሚይስገብርበትን ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግን ክምን ጊዜውም በላይ በማፋፋም ላይ ነው።

በመሆኑም፡ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ቤተ ክርስቲያንና መስጊዶች ተደፈሩ። ዛሬም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። ይህ በፈጣሪ የሚሳብበው የስሞተኛ/የሽሽት ጸሎት፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የዛሬ 45/46 ዓመታት ገደማ ሲሉት የነበረውን ያስታውሰኛል – “የሀገራችን ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። መደብ ላይ ከመተኛት (ጎጆ-አጥነት ባልታወቀበት ገጠር)፡ አሹቅ ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት በታች (ድርቅና ርሀብ እምብዛም ሥር ባልሰደዱበት ዘመናት) ወዴት ወደከፋ በታች ይወረዳል?”

እኔም ሳስበው፡ ፈጣሪ ፖለቲከኛና ባለመሆኑና ለሥልጣኑ ሥጋት ስለሌለበት ይህ የእርሱ አስተሳሰብ ወይንም አመለካከት ይሆናል ብዬ አላምንም፡፡ አንድ ሁለት እይለ የኢትዮያን ብሄረስቦች ክቤታቸውና ንበረታችው ሲመንግል፤ ከቤት፡ ከቤተስብ፡ ከንበረትና ከሃይማኖት እገዳ ውጭ ምንድንው ከዚሀ የባስ የሚሆነው?

አማራው ከኢትዮጵያ መሥራቾች መካከል እንዳልነበረ ሁሉ፡ ዛሬ ሥልጣን የተላበሱ ስዎች (ቡድኖች)፡ አማራውን በተቀነባበረ መልኩ፡ ከደቡብ እስክ ደበብ ምሥራቅ፡ ክመሀል ሀገር ሁሉ በማፈናቀል አገር አልባ ይመስል፡ ብዙ ወንጀል እየፈጸሙበት ነው። ፍርህት የዋጣቸው ዜጎች ጥርሳቸውን መንከሳችውና አንጀታችው ማረሩ ግን አልቀረም። ፍርሀት ስለዋጣችው፡ ማለትም የሆድ አደሩንና የስላዩን ብዝት ስለሚያውቁ፡ በባዕድ የጭቆና አገዛዝ እንደተያዘ ሕዝብ ሁሉ፡ ይህንን ቀን በጸሎት ለማለፍ ጥረት ስያደርጉ ይታያል። ይህ የኢትዮጵያ ጥፋት “ሀ” “ሁ” ነው።

አንድ የቀድሞ የሕወሃት ባልሥልጣን የአማራና የኦርቶዶክስ ቢተክርስቲያን ግንኝነትን መምታት ለድርጅታችው ዓላማ መሳካት ዐይነተኛ መሣሪያ መሆኑን በገሃድ መናግራችው፡ የዘር ማጽዳቱ ዘመቻ ምን ያህል በዕቅድ የተያዘ መሆኑን አመላካች ነው።

መለስ ከደቡብ ሰለተባረሩ አማሮች ተጠይቆ ፓርላማ ውስጥ ሲመልስ፡ የነበረውን የማድበስበስ ጥረት፡ የስሜቱን መርካትና “ገና እናሳያችኋለን” የሚለውን ስሜቱን አልሸፈነውም። ለሕወሃት ይህ በፕሮግራም የተያዝ ጉዳይ በመሆኑ፡ የኦሮሞ ሊሂቃንን ገደሎና አዋርዶ ካኮላሽ በኋላ፡ የኦሮሞን ወጣቶች እሥር ቤት አጉሮ ወደአማራው መሸጋገሩ፡ ከሆድ አድሮች በስተቀር፡ ሕዝቡን በአላምን ባይነት ሳያደነዝዘው አልቀረም። ከዚህ ጥቃት እኔ ተርፋለሁ ብሎ የሚያስብ ዚጋ ሁሉ ተራውን ጠባቂ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

የሕወሃት ዓላማ አገሪቱን ለዘለቄታው ረግጦ መግዛት በመሆኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፡ እስከዛሬ የፈጻማቸው ወንጀሎች በቂ ባለመሆናቸው ፕሮግራሙ እርሱ በፈለገው ፍጥነት አልተካሄዱም ብሎ የሚያምን ድርጅት ይመስላል። እስካሁን የሚድረገው ጩኸት ሕውሃት ብቻውን የሚያድርገው እይስመስለው በመሆኑ በርሱ ስም ይህንን ደባ የሚፈጽሙትን በውኩልነት ተጠያቂ ማድረግ ይስፈልጋል!

የሕዝብ የነጻነት ርሃብና የገዥው ቡድን የኤኮኖሚ ጥቅሞች እየፈጠሯቸው ያሉት ግጭቶች

የሕዝብ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ከባለሥልጣኖች (ከተወሰነ ቡድን) ጥቅምና ፍላጎትች ጋር ተጻርራሪ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት: አገዛ፡ዙ ሕግ በበላይነቱ ለዜጎች አስተማማኝ ጠለላ ስለማይሰጣቸው ብዙኅን ኢትዮጵያውያን በዕለታዊ ኑሮአቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ለሚቃጣ አደጋ ሲጋለጡ ይታያሉ። ከእርሻ መፈናቀል፡ የቤቶች በባለሥልጣኖች ወይንም የተወሰነ ቡድን ትዕዛዝ እንዲፈርሱ መደረግና የግለስቦች መንገድ ላይ መወርውር በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል። ይህ አንድ ጊዜ የተፈጸመ ስህተት ሳይሆን፤ ሆን ተብሎ በተደጋጋሚ ተግባራዊ የተደረገ፤ የተወስደውም መሬት በጥቅም ግንኙነት እየተለወጠ፡ ዜጎች አቤቱታ ስሚ እንኳ ያጡበት ሁኔታ ነው። ይህ ሁኔታ የዜጎችን በአገራቸው በነጻነትና ሙሉ መብቶቻቸው ተክብሮላቸ መኖራቸውን እስከአሁን አላሳየም።

ሀግሪቱ በሕግ መተዳደር እስካልቻለች ድርስ፤ ፍርድ ቤቶች የባሰሥልጣኖች ፍላጎትና ጥቅሞች ማስከበሪያ መሆናቸው ገሀድ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ: ግልጽም ሆነ ሥውር ፖሊሶች እንዲሁም የመከላከያ ኅይሉ የሀገርነና የዜጎችን ደኅንነት ጠባቂ ባልሆኑብት ሁኔታ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረቶች ለፖለቲከኞች ጥቅም፡ እንዲሁም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ማስፋፊያዎች የትርፍ ማካበቻ በሆኑበት አስፈሪ ጊዜ አግራችንና ሕዝባችን ነጻ ናቸው ብሎ መናገር አንድም ሀስተኛነት አለያም ጥርቅም ያል ደደብነት ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙው ሥልጣን በእጃቸው ያለ ግለስቦችና ዋናው ቡድን፡ ከእነርሱ በላይ ለሀገር አሳቢ እንደሌለ፡ ከእነርሱ በላይ የሀገርን ጥቅም አዋቂ እንድሌለ አድርገው ሲናገሩና ለማሳመን ሲሞክሩ ይደመጣሉ። ይህ እውነት ቢሆን ምንም ባልከፋ ነበር። ነገር ግን ጠቃሚ ብለው የሚሠሩት፡ የራሳቸውንና የአጋሮቻቸውን ጥቅም ሲያራምድ: አግሪቱ ስትመዘበር ይሳያል። በአንጻሩም በእነርሱ ድርጊት ብዙ ዜጎች ሲጎዱ፡ ደራሽ አጥ የሆኑበት ሁኔታዎች እየተበራከቱ ናችው።

ሆኖም ገዥው ቡድን እንዴት አድርጎ የመንግሥትንና የሕዝብን ንብረት በንቀትና ድፍርት በገሃድ ሲመዝብር የታያል። ለምሳሌ፡ በየቦታው የራሳቸውን ሰዎች የሚመድቡበት ምክንያት ለግል ድርጅታችው (EFFORT) ግንዘብ የሚያስተላልፉበት መንገድ መሆኑ በግልጽ የታያል።

ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። በመክላከያ ሚኒስቴር ሥር ያለው የበርታበርትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በእንግሊዝኛው ስሙ Metal and Engineering Corporation (MetEC) ባለፈው ዓመት መጋቢት ላይ የያዩን የፈርቲላይዘር ፋብሪካ ግንባታ ሥራ ለተቋራጮች እንድሚሰጥ ያስታውቃል። ወዲያው ብር 792 ሚሊዮን ኮንትራቱ ለአምባዬ ኮንስትራክሽን መሰጠቱ በዜና ማስራጫዎች ይዘገባል። አሁን ደግም የሕወሃት መስፍን ኢንጂነሪንግ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተስፋሁን በዛብህ በቅርቡ እንደገለጹት የፈርቲላይዘር ፋብሪካዎችን ኮንትራት ሥራ ድርጅታችው ለማግኘት ዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመክላከያው ብረታብረት ፋብሪካዎች ወጭና ገቢ ላይ ገንዘብ ሚኒስቲርም ሆን መንግሥታዊ ኦዲተሮች ድምጽ የላቸውም። ይህ ጉዳይ አቶ ግርማ ሠይፉን አሳስቧችው የ2004 በጀት በሚጽድቅበት ወቅት ለመለስ ጥያቄ አቅርበው ነበር። በውቅቱ የተጣቸው መልስ የተሽፋነፈ ነገር እንደሌለና፡ ወጭና ገቢውን ማየት የሚፈልግ ዜጋ ጥያቄ አቅርቦ መመልከት ይችላል የሚል ቀልድ ነብር። ያ ሥጋት ግን ዛሬ አግጦ የሀግሪቱ ንብረት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አማካይነትና ኮንትራት ስጭነት ግነዘብ ለጥቂት ዘመነኞች መዝናኛ ወደ EFFORT በግልጽ እየፈሰሰ ነው። እይንዳንዱ አባልም ወደውጭ የሚያሽሸሸው ገዝብም ቀላል አይደለም።

ሪቬራ ሆቴል አዲስ አበባ – ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ 15 ደቂቃ ረቅት ላይ የሚገኝ
ይግረማችሁ ብሎ ብረታ ብረትና እንጂነሪንግ ባለፈው ሐምሌ ወር በብር 140 ሚሊዮን በብርጋዴር ጄኔራል ኪንፈ ዳኝው አማካይንት 72-ክፍሎች ያሉትን ሆቴል (Rivera Hotel) ለመግዛት በቅቷል። ለምንድነው መክላከያ ይህ ሆቴስ ያስፈለገው ተብለው ሲጠየቁ፡ ለወራት የሚቆዩትን እንግዶቻችንን ለማስተናገድ ነው የሚል መልስ መስጠታቸውን አዲስ ፎርቹን ስሙ እንድይጠቀስ ያልፈለገን ባለሥልጥን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። 80 ሚሊዮን ብር ከተገዛው ሆቴል Imperial Hotel ቀጥሎ፡ ይህ ሁለተኛው መሆኑ ነው።

ይህ የብረታ ብርትና እንጂኔሪንግ ኮሮፖሬሽን በ 2010 ሲቋቋም፡ 12,500 ሠራተኞች ያሉት ድርጅትና ተጠሪትነቱም ለመክላከያ ሚኒስቴር ሲሆን፡ ውናው ዓላማው የአገሪቱን ልማት ለማፋጥን እንዲቻል እስክ 2014/15 የሚቆየውን የአምስት ዓመት ፕላን በኢንዱስትሪና ኢንጊነዕሪንግ የማያስፈልገውን የመፈብርክና የመሐንዲስነት ሥራዎችን ማከናወን ነበር።

አሁን እንደሚታየው ክሆነ ግን፤ ለሕወሃት ድርጅቶች ዐይነተኛ የገንዝብ ማስተላለፊያ ሆኖአል። የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የማይፈልዟችውን መኪናዎች እንዲገዙ እየተደረገ፤ ከበጀት የሚዘረፈው ገንዝብ – ገቢው ጄኔራሎቹን ክማበልጸግና ክማዝናናት አልፎ፡ በሥራ ተቋራጭነት ስም ከእነርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው የበሄረስባችው ገንቢዎችም በጓሮ በር የሚያገኙዋቸው በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሕንጻ፡ የመንገድ ሥራ ተቁራጮችም አላል ተጠቃሚ እየሆኑ፡ ሙያና ብቃት ያላቸው በዝቅተኛ ዋጋ ተወዳዳሪ ሥራ ሊሠሩ የሚችሉ ባልሙያተኞች “ክገዥው” ዘር ባለመሆናቸው የሚቀጡ መኖራችውን ማስታውስ ይገባል።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን የሀገር ጥፋት መዋጋት ይገባዋል። ከላይ እንደጠማይገባ ተግባር ነው። ዛሬ ይህንን ለማድረግ ከምንጊዜውም በበለጠ ተክኖሎጂ የፈጠራቸው አመቺ ሁኔታዎች ስላሉ፤ እንዚህን ተክኖሎጂዎች በመጠቀም፡ ሁኒታውን የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም እንዲያውቀው ማድረግ ይቻላል። ተገቢም ነው።

እነዶ/ር ደብረጽዮን ይህንን በር ለመዝጋት ብዙ ሞክረው፡ ስንትና ስንት ሀብት ለአፈናው አፈስስው አልተሳካላቸውም።

The Ethiopian Observatory


የህወሓት/ኢሕአዴግ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ መቆም አለበት!(ኢህአፓ ዲሞክራሲያዊ)

ሰላማዊ ትግል እና የመለስ ራዕይ ዘር-የማጥራት ወንጀል ስለመሆኑ ግርማ ሞገስ

የቁም ኑዛዜ የጎንቻው

የመን ውስጥ ምላሱን ተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል በግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል፡፡ በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል፡፡ እነዚህ አፋኞች ያገቱት ሰውን ለማስለቀቅ ገንዘብ የሚልክለት ከሌለ ከተራ ድብደባ እስከ መግደል የደረሰ ቅጣት ይፈጽማሉ፡፡ አይን ማጥፋት፣ ብልት መቁረጥ፣ በእሳት ማቃጠል፣ በህወይት እያሉ መቅበር፣ መድፈር…የመሳሰሉትን ይከውናሉ፡፡ እነዚህን አፋኞች ካገቷቸው ውስጥ 25 ኢትዮጵያዊያን ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገቡ ሲል የመረጃ ምንጬ ገልጾልኛል፡፡

ትላንትና ሰኞ(በ8/4/13) የየመን ሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የሀረጥ አውራጃ ደህንነቶችን፣ ድንበር ጠባቂዎችን፣ ሁለት ብርጌድ የተውጣጣ ወታደር አድርገው አፋኞቹ ያሉበትን አካባቢ በመክበብ 158 ኢትዮጵያዊያንን ነጻ አውጥቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 25 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆናቸው ሆስፒታል መግባታቸውን ተልዕኮውን የመሩት ኮረኔል አሊ ኡመር ይስለም ገልጸዋል፡፡ እንደ ኮረኔሉ አባባል በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናት በአብዛኛው እነዚህን አፋኞች የሚረዱ፣ የተሳሰሩ እና የሚተባበሯቸው በመሆኑ የነበረውን የማስለቀቅ ትግል ከባድ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡ በመሳሪያ ትጥቅም በኩል ቢሆን ከመንግስት ሀይል የላቁና የተደራጁ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡ በመጨረሻም ከእነዚህ አፋኞች ጋር የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት( IOM) ሰራተኞችም አባሪ ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ የሚያሳዝን እና ተይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ድርጊት ኢትዮጵያዊያኑ ላይ መፈጸሙን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የመረጃ ምንጬ እንዳመለከተኝ ከተጎጂዎች መካከል ያናገራቸው ሰዎች ስላሉ እነሆ፡-

ሚሚ ትባላለች፡፡ የ19 አመት ሴት ነች፡፡ አካባቢዋ ላይ ያሉ ልጆች ሲጓዙ ስላየች እንደተጓዘች ነው ለጠያቂዋ የነገረችው፡፡ የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ባህሩን አልፋ ከየመን ጠረፍ እንደረገጠች በአጋቾች እጅ ወደቀች፡፡ አንደኛው አጋች ነይ የእኔን ክፍል አጽጂ ብሎ ወደ አንድ ክፍል አስገባት፡፡ ለብዙም ደፈሯትም፡፡ ይህን በተመለከተ ስለጉዳዩ መግለጫ የሰጡት ባለስልጣን ‹‹..ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ ነው መደፈሩ የተከወነባት..›› ብለዋል፡፡

ሀፊዝ ይባላል፡፡ የሚከፍለውም ሆነ የሚያስልክበት ቦታ ስለሌለው የደረሰበትን ድብደባ መቀበል ግድ ብሎት ቆይቷል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ምላሱን ቆርጠውት ሀረጥ ሆስፒታል በህክምና ላይ ነው ያለው፡፡ አንደኛዋ ሴት ደግሞ ዮርዳኖስ ትባላለች፡፡ ድብደባውን በጸጋ ብትቀበልም ገመድ አንገቷ ላይ አጥልቀው እየሰቀሉ ደብድበዋታል፡፡ አንቀዋት ትንፋሽ ሲያጥራት አውርደው መኪና ላይ በማሰር ጊቢው ውስጥ መሬት ለመሬት በመጎተት ሰውነቷ እስኪላላጥ ጎድተዋታል፡፡

በተያያዘ ዘገባ በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵዊያዊያን ባህር ተሻግረው የመን መግባታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት (IOM) አስታወቀ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ ያልታየው የኢትዮጵያዊያን የስደተኞች ባህር ማቋረጥ አሳሳቢ ከሚባለው በላይ ሆኗል፡፡

በ2010 ዓ.ም ብቻ 53000 ኢትዮጵያዊያን የኤደን ባህረ ሰላጤን እና ቀይ ባህርን ተሻግረው የመን መግባታቸውን ከሁለት ሺህ በላይ ባህሩ ላይ መቅረታቸውን IOM ገልጾ ነበር፡፡ ጉድ ጉድ ሀገር ውስጥ ማን ቀረ ተብሎ ታለፈ፡፡ መንግስት ዝምታ ምሽግ ውስጥ ተቀብሮ ማዳመጡ በርቱ ውጡ ያለ መሰለ፡፡ ከዛም ቁጥሩ ማሽቆልቆል ሳይሆን ማሻቀብ አሳይቶ በ2011 ባህር ተሻግሮ የየመንን ድንበር የጣሰው ኢትዮጵያዊ ቁጥር 103000 ደረሰ፡፡ ቱ…ቱ…አደገልን የሚያስብል አለያም በእልልለታ የታጀበ አታሞ የሚያስደልቅ አይደለም፡፡ የሀዘን ከል የሚያስለብስ ነበር፡፡ ምክንያቱም በባህሩ ላይ የሚጓዘው ቁጥሩ ማየል በተቀናጀ መልኩ ለዘረፋ የሚነሱ ግሩፖችን አስከተለ፡፡ በዚህ ሰዓት መንግስት ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ተነፈሰ እና ምንም አይነት መላ ሳይዘይድለት በውስጣዊ እንጉርጉሮ ‹‹የራሳችሁ ጉዳይ….›› ብሎ ያቀነቀነ መሰለ፡፡ በ2012 ደግሞ ‹‹..እባካችሁ ኑ…›› ተብሎ ቅስቀሳ የተደረገ ይመስል አሻቅቦ 107000 ኢትዮጵያዊያ የመን መግታቸውን IOM አስታወቀ፡፡ በዛው ልክ ባህር ላይ የሚሞቱትም ቁጥር መጨመሩ ያሳሰበው አይ.ኦ.ኤም ሀረጥ ባለው ካምፕ ውስጥም ከ14 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በመኖራቸው የሳዑዲያን፣ የየመንን እና የኢትዮጵያዊያንን ባለስልጣኖች ለውይይት ጋበዘ፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት የተገኘው ድጋፍም ሆነ ምላሽ አሳፋሪ እና ለዜጎቹ ያለውን ክብር ግምት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡ ‹‹ወደ ሀገር ስትመልሷቸው እንቀበላለን፡፡ ከዛ ውጭ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡›› ነበር ያሉት፡፡

አስቡት ላለመቀበልም አስበው ነበር ማለት ነው? በዕርግጥም ሀገር ውስጥም ያሉትን ህጋዊ አይደላችሁም እየተባሉ ሲፈናቀሉ እያየን ክጭ ከስደት የሚመለሱትንስ በዝምታ ይቀበላል ብሎ ሰብ ሳ\\ይከብድ ይቀራል፡፡ ባለፈው ጊዜ ከሳዑዲያ ተመለሱ የተባሉ 60 አካባቢ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ልሱን ብለው ነበር፡፡ ኤምባሲውም ሆነ ኮሚኒቲው የሰጡት መልስ አሳፋሪ ነበር፡፡ እየአንዳንዳችሁ 250-300 ዶላር ክፍሉ ካለበሊያ አናውቃችሁም አሉ፡፡ ፖሊስ አምጥተው አሳፍሰው ከከተማ ክልል ውጭ ተጣሉ፡፡ ዜጋውን እንደቆሻሻ አሳፍሶ ያስጣለ ብቸኛው ኤምባሲ ሳይሆን ይቀራል፡፡ ከተጣሉበት ተመልሰው ‹‹ኢትዮጵያዊ ነን እና መመለስ እንፈልጋለን መልሱን ወደ ሀገራችን..›› ብለው ኮሚኒቲው በር ላይ ተቀመጡ፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው የመጡ ኢትዮጵያዊያን እንዳይራቡ እህል ውሃ ያላቸውን ሰው ሁሉ መክሰስና ማሳሰርም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ስራ ሆነ፡፡ በመጨረሻም ስደተኞቹን አሳፍሶ ሚግሬሽን እስር ቤት አስገባ፡፡

የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ፡ ይድረስ ለአቤል ጋሼ ከጃፋር ሐሰን

የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሑፍ በአቡጊዳ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/10541#commentsና http://quatero.net/pdf/queen-azeb-and-ethiopia.pdf በቋጠሮ ድረ-ገፆች ባለፈው የካቲት ወር ለንባብ በቅቷል፡፡ ጽሑፉ በ75 ገፆች የቀረበና በጥልቀት የተዘጋጀ በመሆኑ ለመረዳትና የተሰጠውን ተስፋ ለመጠበቅ ጊዜ የሚፈልግ ነው፡፡ ጸሐፊው አቶ አቤል ጋሼ ላደረገው እንደዚህ ያለ ሰፊ ጥናት ምስጋና ይገባዋል፡፡ በአቡጊዳ ላይ አስተያየት ከሰጡት አራት ሰዎች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ስለ ጽሑፉ ጥሩ ብለዋልና በጽሐፉ ላይ የአስተያየት ሰጪዎችንም ተሳትፎ ሳናደንቅ አናልፍም፡፡

የአገራችን ኢትዮጵያ መለኮታዊ እጣ ሁላችንንም የሚያነጋግርና እንድናስብበት የሚገባ ነው፡፡ የምንችለውንም ነገር ሁሉ በምንችለው አቅም ልንሰነዘር ሊያነሳሳን ይገባል፡፡ እኔም በጉዳዩ ላይ በአቶ አቤል ጽሑፍ ላይ ተንተርሼ ጥቂት ነገሮችን ለመናገር ለአቶ አቤልም ጋሼም ገንቢ የሆነ ማሳሰቢያ ለመስጠት የሚከተሉትን ሃሳቦች አስፍሬአለሁ፡፡

የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ – እንደ አቤል ጋሼ

የኢትዮጵያን መለኮታዊ ዕጣ በሰፊው የሚያብራራው ጽሑፍ ብዙ ነገሮችን ያካተተና በተለይም መንፈሳዊ የተደረገ እንዲሁም ጸሐፊው እንዳቀረበው በንግስተ ዓዜብ ፍርድ ላይ የተሽከረከረ ነው፡፡ ንግስተ ዓዜብ በሬጋን ሕንፃ ፍርድ እንደጀመረች መንፈሳዊ የስልጣን ሽግግርም ከቀዳማዊት ዓዜብ ወደ ንግስተ ዓዜብ እንተደላለፈ ያስረዳናል፡፡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በጊዜው የምናያቸው ቢሆንም ነገሮች በጣም ምስጢሮች በመሆናቸው በፊደላት ቀመር ስሌት እየተሰሉ ትርጉማቸው እንደሚፍለቀለቅ ተመልክተናል፡፡

በጣም ግሩም በሆነም መልኩ ከ70ዎቹ ገፆች ጀምሮ ኢትዮጵያ አገራችን ገናና ሆና ሁሉም ዓለም በግዕዝ መንፈስ እንደሚሰማት ተነግሮልናል፡፡ ይሁንልን! ይበጅልን! ያርግልን! አገራችን ትቅደም! ትውጣ! በማለት ሁላችንም ያንን ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

የአቤልን ጽሑፍ ቀስ ብሎ የሚያነብ ሰው ግን ብዙ ጥያቄ ይፈጠርበታል፡፡ የአገራችን የኢትዮጵያ ዕጣ እንዲህ ውስብስብና አስቸጋሪ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? አገራችን ኢትዮጵያ ከሌላው አገር ሕዝብ የተለየ የቃል ኪዳንና የምስጢር አገር ያረጋት ማስረጃው ምንድነው? አንድ አገር እንደዚህ ዓይነት ውስብስብ የኮድና የምስጢር ቱባዎች ውስጥ የመግባቷ አስፈላጊነትስ በእርግጥ ምኑ ላይ ነው? ወ.ዘ.ተ የሚሉ ጥያቄዎች ይፈጠሩበታል፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጽሑፉን በእርጋታ አንብቤ የሚከተሉት ነገሮች አልገባ ስላሉኝ እንደገና እንዲታዩ አንስቻቸው የአገሬን ዕጣ በተመለከተ አጭር ማሳሰቢያ መስጠት ጉጉት አደረብኝ፡፡

1ኛ፡ የፊደሎች የቁጥር ዋጋ

ጸሐፊው ለአማርኛ ፊደሎች የቁጥር ዋጋ በድንገት በማዘጋጀት የአንዳንድ ቃላትን የቁጥር ስሌት ለመስጠትና በዚያም ላይ በመመስረት ትርጉምና ትንታኔ አድርጓል፡፡ ነገሩ እውነትነትና ተጨባጭነት ቢኖረው ጥሩ ነበር ነገር ግን እውነትነቱና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ መሆኑ ጥያቄ ያስነሳል ስለዚህም ይህ የአቶ አቤል አካሄድ በተወሰኑ ነጥቦች ዙሪያ እንደገና ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም በጣም ኋላ የቀረ የNumerology ጥንቆላ ጉተታ ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንዲመለሱ የሚያዘናጋ ነውና፡፡

ከዚህም ባሻገር የጸሐፊው የፈደል ቀመሮች ውስጣዊ ችግሮች አሏቸው፡፡ ችግሮቹን ለማስወገድ ደግሞ ግልፅ የሆነን ማብራሪያ በግርጌ ማስታዎሻ ላይ እንኳን አልተተወልንም፡፡ እኔ እንኳን ከታዘብኩት “ፊደል “”ሸ””ን በተመለከተ ችግር አጋጥሞኛል፡፡

ለመሆኑ ፊደል “ሸ” የት ጠፋች?

በማስታዎሻ 3 ገፅ 8 በፊደል ቀመራህ ውስጥ ሁሉንም የአማርኛ ፊደሎች ተጠቅመህ ነገር ግን ፊደል “ሸ”ን ትተሃታል፡፡ አቶ አቤል ምናልባት እረስተሃት ይሆናል! ወይንም ከ26 ቀመራህ ጋር አልሄድ ብላህ አስወግደሃት ይሆናል! ወይንም እንዲያው መንፈስ እድርገሃት ጠልተሃት ይሆናል! ወይንም የባዕድ ፊደል አድርገሃት ይሆናል! ብቻ የራስህ ምክንያት እንደሚኖርህ ምንም አልጠራጠርም፡፡ በገፅ 48 ላይ ፊደል “ሰ”ን እና “ሸ”ን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ ቢኖርም ፊደል “ሸ”ን ከፊደል ተራ ቁጥር ውስጥ ማስወጣትህን አልነገርከንም፡፡ አቶ አቤል ይህንን ያደረግህበት ተጨባጭ ምክንያት ካለህ ለሁላችንም ብትገልጥና የፊደሎቻችንንም መንፈሳም ሆነ ስጋዊ ሚስጢር የበለጠ ብታስተምረን ጥሩ ነበር፡፡ ለማንኛውም ፊደል “ሸ”ን በጽሑፍህ ውስጥ ምናልባት አልተጠቀምክባት ይሆናል በማለት “Randomly” አንድ ገፅ ወሰድሁና ፊደሏን መፈለግ ጀምርሁ፣ ለምሳሌም ያህል በወሰድኩት “ራንደም ገፅ” በገፅ 16 ላይ አምስት ጊዜ በሚከተሉት ቃላት ማለትም “ሙሽራው፣ ሙሽራዋ፣ በትንፋሽ፣ ተሻግረን፣ እና ያሻል” በሚሉት ቃላት ውስጥ ትገኛለች፡፡
የራስህም የአባት ስም በ-ጋሼ ውስጥም በቀመራህ ውስጥ ያጎደልካት ፊደል “ሸ” ትገኛለች፣ የራስህንና የአባትህን ስም ፊደላት በአንድ ላይ የቀመር ትንተና ውስጥ ማስገባት ቢያስፈልግህ እንዲያው ምን ልታደርግ ነው? ስምህን በአዋጅ ትቀይር ይሆን ወይንስ ከቀመር ነፃ ማለትም ለ”ሸ” ፊደል ዜሮ ቁጥር ትሰጥ ይሆንን? ወይንስ ሰ ማለት ሸ ነው ልትለን ይሆን? እኔ አላውቅም!!

ይህንን ሁሉ የተናገርኩበት ምክንያት ከፊደል “ቀ” ጀምሮ የሰጠኻቸው የቁጥር ዋጋዎች ሁሉ ስህተቶች በመሆናቸው በዚህ ጽሑፍ ላይ የሰጠኻቸው የቀመር ዋጋዎች ሁሉ የተዛቡ መሆናቸውን እንድትረዳ ነው፡፡ ይህ ማስረጃ ደግሞ ከውጭ የመጣ ሳይሆን በራስህ ጽሑፍ ውስጥ ውስጣዊ የሆነና የመሳሳትህ የራስህ ማስረጃ ነው፡፡ ስለዚህም አንድ ምሳሌን ብቻ በመውሰድ ምን ያህል ተሳስተህ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ (ጽሑፍህን ያነበቡትን ማለቴ ነው) እንዳሳሳትህ “እግዚእ” ለሚለው ቃል የሰጠኸውን ቀመር ድምር እንመልከት፡፡ በዚያው በገፅ 8 ላይ የቀመር ስሌት ምሳሌህ አድርገህ በጥሩ ሁኔታ አስቀምጠኸዋል “360 ዲግሪ፣ ክብ መለኪያ” ብለኸዋል፡፡ እንግዲህ እንዳልከው ቢሆን በጣም ጥሩ ነበር ነገር ግን ፊደል “ሸ”ን የምታስወግድበት ምንም አሳማኝ ማስረጃ ስለሌለህ ወይንም ደግሞ ቢያንስ በአሁኑ ወቅት ስላልሰጠኸን ፊደል “ሸ”ን በተገቢ ቦታዋ ላይ ብናስቀምጥና “እግዚእ”ን ብናሰላው የሚመጣው ውጤት አንተ በገፅ 8 መጨረሻ ላይ ከሰጠኸን የተለየና እንደሚከተለው ነው፡-

ሀ. ፊደል “ሸ” የጎደለችበት ያንተ ስሌት አ = 40፣ ገ = 200፣ ዘ = 80 እና አ = 40፣ በድምሩ 360 ክብ ዲግሪ
ለ. ፊደል “ሸ” በትክክለኛ ቦታዋ ብትቀመጥ የሚሰጠን ስሌት አ = 50፤ ገ = 300፤ ዘ = 90፤ አ = 50 ናቸው በመሆኑም ድምሩ ደግሞ 490 ይመጣል፡፡
እራስህን በጣም ትክክለኛ እንደሆነ ሰው አድርገህ በገፅ 8 ማጠቃለያ ላይ ከሰጠኸው የክብነት ትርጉም ጋር ልዩነቱን ቆም ብለህ እንድታሰላው አሳስብሃለሁ፡፡
በጽሑፍህ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ብዙ ስህተቶች አሉ፤ ሁሉንም ለማሰስ መሄድ ስራ ያስፈታል ስለዚህ እንደገና እንድትሄድበትና በአቡጊዳና በቋጠሮ ድረ-ገፅ ላይ ጽሑፍህን አግኝተው ላነበቡት ኢትዮጵያውያን የማረሚያ ይቅርታ እንድታስተላልፍ በኢትዮጵያዊ የወንድምነት ስሜት እመክርሃለሁኝ፡፡

2ኛ፡ ለፕሮፌሰር መስፍን በጻፍከው ላይ

የሁላችንንም አስተማሪና ምሳሌ ፕሮፌሰር መስፍንን አክብረህ ለማበረታታት መጻፍህ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ጥቂት ነገሮች ከእውነታ ውጭ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጰያን ከሌሎች አገሮች የተለየች የቃል ኪዳን አገር አድርገህ ማስቀመጥህ ትክክል አይደለም፡፡ በሆሴዕ ትንቢት 9.7 ላይ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድህም የተዛባ ነው፡፡ በትንቢተ ሆሴዕ ላይ የተጠቀሰቸው ኢትዮጵያ በጥሩ መልኩ ሳይሆን በጣም በመጥፎ መልኩ ነው፤ ከእስራኤል ልጆች ይልቅ በተሻለና በተወደደ መንገድ ሳይሆን መጥፎ ምሳሌ ሆና ነው፡፡ የትንቢተ ሆሴዕ ጥቅስ ትክክለኛ ትርጉም የሚሆነው እንደሚከተለው ነው፡- አሕዛብ የሆነችው ኢትዮጵያን ተፀይፌ እንደማየው እናንተንም (እስራኤላውያንንም) የቃል ኪዳን ልጆችን በኃጢአታችሁ ምክንያት እንደዚያ ተፀይፌ አያችኋለሁ፣ እፈርድባችኋለሁ የሚል ነው እንጂ ኢትዮጵያ ከእናንተ የተሻለ የተወደደች ናት የሚል ሐሳብ የለውም፡፡ አንተ እንደምትለው ቢሆን ኖሮ ጥሩና ጮቤ የሚያስረግጥ ነበር፣ ነገር ግን አይደለም፡፡
አየህ አቶ አቤል፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ያልሆንነውን ለመሆን እና ያልተነገረልንን ነገር መናገራችን እስከ አሁን አልጠቀመንም ወደ ፊትም አይጠቅመንም፡፡

ለፕሮፌሰሩ በጻፍከው ደብዳቤ ላይ ገፅ 15 ላይ የማያን ካሌንደር የቱባ ምስጢር እንደሆነ የንግስተ አዜብን ፍርድ 42ኛ ዲግሪ ቀመሮችን አስረድተህ የደብረሲናን እና የደብረ ፅዮንን ህጎች በስሌት አስቀምጠኻቸዋል፡፡ ሁሉ ነገር ትክክል አይደለም ያስቀመጥካቸው የብዜት እና የድምር ውጤቶችም እንኳን ትክክልነት ይጎድላቸዋል፡፡ ፕሮፌሰሩን እንደምን እንደገመትካቸው እኔ አሁን መገመት ይከብደኛል፣ እርሳቸው ደብዳቤህን አንብበው ምን ብለው ይሆን?!!!

አሁንም ለፕሮፌሰሩ በጻፍከው ላይ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ፍርድና ገለጣህ ሁሉ ከእውነታ የራቀና ውስብስብ ነው፡፡ ለአንድ ፕሮፌሰር በሚጻፍ ጽሑፍ ውስጥ የማስረጃ ምንጭ መጥቀስ አስፈላጊ ይመስለኛል ነገር ግን ለሰጠኻቸው ዘገባዎች ማስረጃም አልሰጠህም ምናልባት ከሰማይ መጣልኝ ልትል ይሆን?! አይቀርም፡፡
የፕሮፌሰር መስፍን ምሳሌነት ሁላችንንም የሚያኮራና የሚያበረታታ ነው፣ ነገር ግን ያልሆኑትን ነዎት በማለት ያልሆነ ስም ልንሰጣቸው አይገባም ስለዚህም ለእርሳቸው የመጽሐፍ ቅዱሱን የስምዖንን ቦታ መስጠትህ ትክክልም ተገቢም አይደለም፡፡

3ኛ፡ 9/11 ላይ ያለህ ግንዛቤ

ነገሮችን በመንፈሳዊ አይን ለመመልከት መሞከርህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ግን አጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ስህተቶች አሉበት፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለ9/11 የሰጠኸው የ”ኮዳ”ዊ ትንታኔ ነው፡፡ በገፅ 20 ላይ 9/11 ኮድ ነው ብለኸዋል፡፡ የራዕይም ፍፃሜ እንደሆነ ለመጥቀስ ሞክረሃል በአንቱታ ያሽሞነሞንከው የአሸባሪውን የዖሳማ ቢን-ላደንን ሞትና የሬሳው ወደ ባህር መጣል የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍፃሜ ለማድረግ ራዕይ 20ን ጠቅሰህ ሞክረሃል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይገርማሉ በየምክንያቱ ጥቅስ እየተመረጠ የተለጠፈባቸው ባዶ ጥረቶች ናቸውና፡፡

በዚህ በሦስቱ ስር ነቀል መንፈሳዊ ክስተቶች ገለጣህ ውስጥ 9/11 የሚለውን ኮድህን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን ታሪክ አዛብተሃል፡፡ ለምሳሌም ያህል የቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከዙፋን መውረድም ከ9/11 ጋር አያይዘኸዋል (በጣም በተደጋጋሚ)፡፡ ምን ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ከአጠቃላይ ጽሑፍህ ውስጥ ግልፅ ነው፡፡ አንዳንዶች የግል ሃሳባቸውን ለማራመድ ታሪክ እንደሚረግጡ ሁሉ “የተማረ” ነው የምንልህ መጽሐፍም ይህንንም ጽሑፍ የጻፍከው አንተም ይህንን ማድረግህ ይገርማል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከስልጣን የወረዱት እኮ መስከረም 2 ቀን 1967 ነበር፡፡ ማለትም 10/11 ሊባል ይችላል እንጂ 9/11 አይደለም፡፡ ስለዚህ ከ9/11 ጋር ምን ያገናኘዋል? እኔ እንደሚመስለኝ ጽሑፍህ ለኢትዮጵያውያን የተጻፈ ነው እንጂ ለሌሎች አይመስልም፣ ታዲያ ቢያንስ ይህንን የሚያስታውስ ኢትዮጵያዊ ወይንም አንባቢ ይኖራል ብለህ እንዴት አልገመትክም? ወይንስ የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅህ ነውን?
አየህ የምንጽፈውን ሁሉ አለ-እውቀት ወይንም አለማስተዋል የሚቀበሉን እንዳሉ ሁሉ ጥያቄ የሚፈጥርባቸውም ሰዎች እንዳሉ ማሰብ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ይህን ሐሳብ ስሰነዝርልህ በልጅነቴ ያነብብኩት የክቡር ከበደ ሚካኤልንና በፍፁም የማልረሳውን አንድ የግጥም ስንኝ ላስታውስህ (ባልሳሳት በክቡር ከበደ ሚካኤል የተገጠመ ይመስለኛል)፡፡
“ዋ አስተማሪ ያለበት አባዜ
የተማሪ ጎበዝ የገጠመው ጊዜ”

አሁን የገጠመህ ጎበዝ ተማሪ ነው ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን በእውነት ለአገራቸው የሚቆረቆሩ ሆኖም ግን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በእውነት መነፅር ነገሮችን በመመዘን የሚያዩ በዚህም መሰረት የሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ እንድታውቅ፡፡ ጽሑፎችም ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እጅ የሚደርስበት ሁኔታና አጋጣሚ እንዳለ እንድታውቅ ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም በገፅ 31 – 32 ላይ የፍርድ ዘመን መሆኑን ለማወቅ ከቀመር ጋርና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር አገናኝተህ የሰጠኻቸው ነጥቦች በተለይ በገፅ 32 ላይ በሀ፣ በለ፣ ወ.ዘ.ተ ቅድም ተከተል የሰፈሩት ከዚህ በፊት የተሰሩት ስህተቶች ፍሬ ቢስ ክለሳዎች ናቸው፡፡ ምዕራፍ አራት 9/11 ላይ ያቀረብከውም ይህንኑ ነው፡፡ እንዲያውም በገፅ 35 ላይ የሆኑት ነገሮች ሁሉ የሳይኮሎጂስቱን የ“የንግን”ን ንግግር ጠቅሰህ ግጥምጥሞሽ ሳይሆኑ ምስጢራዊ ክንውኖች ናቸው ብለሀናል፡፡ ነገር ግን ከ9/11 የኮድ ትንታኔህ ጋር እንድናገናዝበው የሰጠኸን የኃይለስላሴ መውረድ ጋር ማመሳሰልህ የምትናገረው ወይንም “ፅንሰ ሐሳብህ” ማስረጃ ቢስና ሆነ ተብሎ በተጠመዘዘ ታሪክ ማስረጃ ላይ የተመሰረተና ለማንም የማይጠቅም አድርጎታል፡፡

ይህ ሃሳብህ ደግሞ እንደገናም ተደጋግሞ ቀርቧል አሁንም እንደገና ላስታውስህ በገፅ 39 ላይ ስለ ኃይለስሳሌ መንግስት በኢትዮጵያ ከጥቅምት 1924 – ጥቅምት 1966 በፈረንጆች ደግሞ 9/11/31 – 9/11/73 አድርገህ አቅርበኸዋል ይህም ደግሞ በተደጋጋሚ እስከ መጨረሻው ጽሑፍህ ቀርቧል፡፡ አቶ አቤል ስለምን እንዲህ አደረግህ? በተሳሳተ መንገድ የጠቀስካት “የንግስተ አዜብ ፍርድ ፅንሰ ሐሳብህን” ለማስረዳት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በአገሪቱ ውስጥና በዓለም ያለው እውነታ፤ እንዲሁም የንግስተ ዓዜብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጥ እና ትርጓሜ አንተ ከምትለውና ደጋግመህ ካቀረብከው ንግርት ጋር በፍፁም አብሮ አይሄድም፡፡

3ኛ፡ መንፈስ መንፈስ መንፈስ … …

ኢትዮጵያን የወጋ የአውሬው መንፈስ በሚለው ምዕራፍ 6 ውስጥ፣ መንፈሱ ማነው? የሚለው ጥያቄ ከቀረበ በኋላ የተሰጠው የቀመርና የትንታኔ አካሄድ በፍፁም አላማረኝም፡፡ በአቶ አቤል ጽሐፉ ውስጥ ሁሉ ነገር መንፈስ ሆኖ ቀርቧል ቋንቋም እንኳን ሳይቀር መንፈስ ተብሏል፡፡ በገፅ 46 ላይ ከአርባ በላይ የተለያዩ መንፈሶች ተጠቅሰዋል፡፡ የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፣ የአማራው፣ የደቡብ ሕዝብ፣ የኦሮሞው፣ የቅንጅት፣ የምዕራባውያን፣ ለማንኛውም ሁሉ ነገር መንፈስ የሚል ስም ተሰጥቶታል፡፡ ይህ ሁሉን ነገር መንፈስ ነው (ማለትም የአውሬው መንፈስ ነው ማለት) በገፅ 46 ላይ አላቆመም ይቀጥላል በሌሎችም ምዕራፎች ሁሉ፡፡

በአቶ አቤል ጋሼ መሰረት እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያን የሚወጉ የአውሬው መንፈሶች ናቸው፡፡ በቀመራውም መሰረት ሲሰሉ “666” ይመጣሉ በጣም ይገርማል!!! ፖለቲካው ፓርቲ፣ ሃይማኖቱም ቋንቋውም ሁሉ መንፈስ ከሆነ የሰው ልጅ ድርሻ ታዲያ የቱ ላይ ነው የሚገኘው? ሁሉንም ነገር የአውሬ መንፈስ እና ተዋጊ ነው በማለት ተወጊውንና ተዋጊውን እንዴት ልንለየው እንችላለን? እውነተኛው መንፈስ የሚሆነውስ ለመሆኑ የቱ ነው፣ የቤተክርስትያን ሰውስ ቤተክርስትያንን እንደ አውሬ መንፈስ እንዴት ሊቆጥራት ይችላል?

ከዚህም በላይ የሚያስገርመውና የአቶ አቤልን ፅንሰ ሐሳቦች መጥፎ በሆነ ጥያቄ ውስጥ ከሚጥሉት ነገሮች ውስጥ ከገፅ 53 አስከ ገፅ 55 በፊደል ተራ “ለ” ውስጥ ስለ ስልክ መንፈስ የተሰጠው መግለጫ ነው፡፡ አቶ አቤል ስልክና በስልክ መጠቀም የመንፈስ ስራ ነው ይላል፡፡ ይህንንም መንፈስ በስልክ የሚስለከለክና በገጠርም በከተማም የሚሰራ በማለት አስቀምጦታል፡፡ ይህንን በኮድና በቀመራህ፣ ትክክል ባልሆነው ስሌትም ከወከለው በኋላ፣ ስልክ አውሬው የሚሰራበት የኮድ ጥበብ ነው ብሎታል፡፡ ለዚህም ሐሳቡ ምንም አሳማኝ ማስረጃ አልሰጠንም፡፡ ምንም አይደለም አሁን ባለንበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ሕዝቡ ግንኙነትን እንዲያደርግ “ከሰይጣኑ መንፈስ” ስልክ ሌላ ሕዝቡ ሊጠቀምበት የሚችልበትን ሌላ አማራጭንም አላቀረበልንም ታዲያ ይሄ ሁሉ የአቶ አቤል “ፅንሰ ሐሳብ” ምን ይባላል?

ጽሑፍህን ያነበበ ሰው ሁሉ የሚመስለውና የሚገምተው ነገር ውስብስብ እና ግራ በተጋባ ጽሑፍና ፍልስፍና አማካኝነት ሕዝቡን ከዘመናዊው ቴክኖሎጂ ለማራቅ እንደምትመኝ፡፡ ከዚህም ባሻገር አንተና መሰሎችህ ብቻ አዋቂዎች ሚስጢር የተገለጠላቸው እየተባላችሁ ሕዝቡ ለእናንተ አይነት ሰዎች በጭፍን እንዲገዛ እንደምትታገሉ አስመስሎታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በየትኛው የዓለም ክፍል ውስጥ እንዳለህ በውኑ አላውቅም፣ ነገር ግን የድረ-ገፅ የቴሌቪዥን እንዲሁም የኮምፒውተርና የኢ-ሜል ተጠቃሚ እንደሆንክ ተረድቻለሁ፡፡ ስለዚህም እነዚህን ብዙዎቹን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳትወነጅል በገጠርም በከተማም የቀረበውን ስልክና ሰዎች በቀላሉ የሚገናኙበትን መንገድ መንቀፍህና ከሰይጣን መንፈስ ጋር ማገናኘትህ ይገርማል፡፡ የአንተ አካሄድ ቢያንስ ከ100 ዓመት በፊት ከኖሩትና ሬዴዮና ስልክ የሰይጣን ነው በማለት ይከራከሩ ከነበሩት ጥንታዊ የሮማን ካቶሊክ ቄሶች ጋር ያስፈርጅሃል፡፡ ጊዜውን አውቃለሁ፣ የጊዜው ምስጢር በተለይም የኢትዮጵያ ትንሳኤ ተገልጦልኛል ከሚል አንድ ሰው ይሄንን አንጠብቅም ትክክልም አይደለም፡፡

4ኛየሃሰት ፍልስፍናዎችና ትምህርቶች የጋራ ምልክቶች

ከጥንት ጀምሮ በዓለማችን ላይ የተነሱ የሐሰት ፍልስፍናና ትምህርቶች ሁሉ በቀላሉ የሚታወቁበት የጋራ መለያ ምልከት ትተውልናል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ምስጢራዊነትና ውስብስብነት ይገኙበታል፡፡ ለጋራ አገራችን ኢትዮጵያ እንደገና መነሳት አቶ አቤል ስላለህ ምኞት ማንም ሰው ሊያደንቅህ ይገባል፡፡ ነገር ግን ሃሳብህ ሁሉ በ”ቱባ ምስጢር” እንዲሁም በተወሳሰበ ከዚህም በላይ ማስረጃ በሌላቸው ቁልፎች ውስጥ የተቆላለፈ ነው፡፡

የአዜብ ምስጢር፣ የዲግሪ ቀመር፣ የሁለቱ በኩሮች ያልካቸው አሟሟት ሚስጢር እና የአዜብ መንፈሳዊ ግዛት መጀመር፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን ሁሉ መንፈስ አድርጎ መቁጠር፡፡ አንዱ ቦታ ላይ ያመሰገንከውን ሌላ ቦታ ላይ መዘርጠጥ፤ ለምሳሌ የቀዳማዊ ኃይለስላሴን የይሁዳ ነገድ መሆን አባባል መንቀፍና የእርሳቸውን መውረድ ደግሞ “ኢካቦድ” ማለት፡፡ እነዚህ ሁሉ ውስብስብና ያላስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ የሚመስለው “በሕልም” ውስጥ እንደመኖር ብቻ ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመንፈሳዊ ትርጉም ምስጢር ውስጥ በጣም መራቅና ሌሎችንም በሕልም ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡

ከዚህ ጋር አብሮ የሚሄደው ሌላው ነገር በገፅ 28-30 የቀረቡት የንግስተ አዜብ ሰማያዊ ምስጢራት ናቸው፡፡ ሰንጠረዥ 1 ውስጥ ያቀረብካቸው ነገሮች በአብዛኛው ትክክል አይደሉም፡፡ የ42 ዘመን አቆጣጠር ስሌትህ ትክክል አይደለም ለዚህም የሰጠኸን ማስረጃ ወይንም በሂሳብ የማጠጋጋት ህግ እንኳን እንድንቀበለው ያደረከው ሙከራ የለም፡፡ ይህንንም እንኳን የኢትጵያን ሕዝብ ማገናዘብ እንደማይችል አድርገህ መናቅህ በማለት አንድ ሰው እንዲያስብ ያደርጉታል፡፡ ለምሳሌ በ42 ዘመን ቀመር ስር፡

a.September 11 – May 2, 2011 የሚለው እንዴት 42 ወር እንደሚመጣ ግልፅ አይደለም፡፡ (9) ዘጠኝ ወርን 42 ወር ብለን እንድንወስድ ፈልገህ ይሆን ይህንንም አልነገርከንም፡ እንደዚህ አድርጋችሁ ለጊዜው ውሰዱ አላልከንም፡፡

b.1/1/24 – 1/1/1966 የቀዳማዊ ኃይለስላሴን አነጋገስ ስሌት 42 ዓመት እንደሚመጣ ልታሳየን ሞክረሃል፡፡ ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን የሚመጣው 43 ዓመት ነው ምክንያቱም ጥቅምት 23 1923 ነግሶ ብለህ አስቀምጠኸዋልና፡፡ ስለምን የታሪክን ቀናትና ዘመናት መለዋወጥ አስፈለገ?

c.ገፅ 29 የኢካቦድ ዘመን ከ1966 -2008 ድረስ ይሆናል ብለሃል፣ ይህ ዘመን በቀደመው ሰንጠረዥ ላይ ካጥላላሃው የይሁዳ አንበሳ ገዢ መንፈስ የሚለየውና “ኢካቦድ” ያሰኘው ነገር ምንድነው? ግልፅ አይደለም፡፡ በሌላው ቦታ ላይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በተደጋጋሚ ለኢካቦድ ፍፃሜህ የሌለውን ስም “መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ” በማለት ለማቅረብ ሞክረሃል፡፡ ግን ለምን ግን ለምን?

d.ቀጥሎም ከግንቦት 20 (በኢትዮጵያ) እስከ ግንቦት 18 (የፈረንጆች) የሚል ሃሳብ ቀርቦ 42 = 21 (ቤተክህነት + 21 ቤተመንግስት) የሚል ቀመር ተቀምጧል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? በየትኛው ዓመተ ምህረት ነው? ዓመተ ምህረቱ ስላልተጠቀሰ 42 ቀን ሳይሆን የሚመጣው የአስር ቀናት ጉድለት ነው፡፡ (በሂሳብ ስሌት -10 መሆኑ ነው)፡፡

e.በገፅ 30 ላይ ወዳለው ስንመጣ 42 ቁጥር እንዲመጣ የተሰጡት ብዜቶች ከዋቢ ሰንጠረዡ ጋር በፍፁም አሳማኞች አይደሉም፡፡

f.በመጨረሻም የኢየሱስ የዘር ሐረግ 42 ዲግሪ ከDan Brown የቅዠት ሰይጣናዊ መጽሐፍ ጋር እንዴት እንደሚዛመድም ግልፅ አይደለም፡፡ አንድ አማኝ እንደሆነ እራሱን ከሚቆጥርና መጽሐፍ ቅዱስን ከሚጠቅስ ሰው የዳን ብራዎንን ስም እና የማያን ቆጠራ እንደማገናዘቢያ መስማትም አሳፋሪ ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ውስብስቦች እና የጠቀስካቸው የማያ ቀመር 26000 እና የዳን ብራዎን ሐሳቦች ለጻፍከው ጽሑፍ ትልቅ ጥያቄዎችን አሳድረውበታል፡፡ ለመሆኑ እንደዚህ ዓይነት አጠያያቂ ውስብስብ ነገር ውስጥ ለመግባት ስለምን አስፈለገ?

ይህ አሁን አንተ የያዝከው ዓይነት አካሄድና ኮዳዊና ቀመራዊ ትንተና በዘመናት የተነሱ የሐሰት ፍልስፍናና ትምህርት አራማጆች ባህርይ ነበር አሁንም ነው፡፡ ነገር ግን ጥንትም አሁንም ሰዎች ይጃጃሉበታል እንጂ የሰጠው ምንም ጠቀሜታ በታሪክ ውስጥ የለም፡፡ ቀላል ማስረጃ ልስጥህ በአይሁድ እምነት ውስጥ ልክ እንደ አንተ ያለ ቀመራና ኮድ የሚያምኑ ብዙዎች ተነስተው ነበር፤ ኮዳቸውም ቀመራቸውም ተረት ሆኖ ነው የቀረው እነርሱም ተከታዮቻቸውም የሉም፡፡ ስለዚህም አንተን የመሰለ የተማረ ሰው እንዲህ ዓይነት ውስብስብ ምስጢራዊና የማይሰራ ኮድ ውስጥ ከምትገባና በማይሆን እንዲሁም በሌለ በማይሰራም ነገር ከምትጨነቅ ጊዜህንም ከምታቃጥል ይልቅ ግልፅ ወደ ሆነው ነገር እንድትመጣ እመክርሃለሁ፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መለኮታዊ እጣ እንደ አቶ አቤል ጋሼ ከሆነ በኮድ የተቆላለፈ በቀላሉ የማይፈታ የሕልም ዓለም፣ ውስብስብ መቼም እንደሚሆን የማይታዋቅ ግራ የተጋባ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን እንዲህ ዓይነት እጣ የለንም ሊኖረንም አይችልም፡፡

እውነተኛው የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ፡ ለአገሪቱ የሚጠቅመው ማጠቃለያ፡፡

በዓለም ውስጥ በአገራችንም እየሆኑ ያሉት ነገሮችን ለመረዳት ምንም ኮድና ምስጢር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ኢትዮጵያንም ከሌሎች አገሮች የተለየ አድርገን ልንቆጥራት የሚያስችለን ምክንያትም ማስረጃም የለንም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደማንኛውም የሰው ዘር በምድር ላይ ለመኖር መብትና እድል ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፡፡ በእርግጥ የተጋፈጡብን መከራዎችና ችግሮች ቀላሎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ችግሮቻችን ግን ምስጢሮችም በኮድ የተቆለፉም አይደሉም፡፡ እነዚህን ለመፍታትም ብዙ መራቀቅና መፈላሰፍም ውስጥ መግባት አያስፈልገንም፡፡ ያልሆንነውን መሆንና ሁኔታዎችን በጥልቅ መንፈሳዊ ኮድ ለመፍታት ጥረት በማድረግ ስራ መፍታትም ጊዜ ማቃጠልም የለብንም፡፡
ችግራችን ግልፅና የየትኛውም አገር ዓይነት ችግር ነው፡-
ጥሩ አስተዳደር አልነበረንም – አሁንም የለንም፡፡ መፍትሔው ጥሩ አስተዳደር ለመመስረት አብሮና ተባብተሮ መነሳት ብቻ ነው፡፡

ጥሩ የስራ ሰዎች አልነበርንም – አሁንም አይደለንም፡፡ መፍትሔው ጠንክሮ ለመስራት መነሳትና ጠንካራ ሰራተኞች እንድንሆን መወሰን መማርና ማስተማር በተግባርም ማሳየት ነው፡፡
ገዢዎቻችን የሚሰጡትን ጠቃሚ መመሪያዎች በጥላቻ በመሞላት ወይንም በትዕቢት አልተቀበልንም – አሁንም አንቀበልም፡፡ እንዲያውም የሌለ መንፈሳዊ ትርጉም በመስጠት ዓመፅን እና ስራ መፍታትን እናበረታታለን ለምሳሌ በአቶ አቤል ጽሑፍ ውስጥ food security ለማምጣት የሚደረገው ጥረት የተተረጎመው በባባቢሎን ግንብ የጥፋት ጥረት ነው፡፡ ይህም በጽሑፉ ውስጥ ከመጀመሪያው ገፅ ጀምሮ ግልፅ ነው፡፡ በሌላ መልኩ አቶ አቤል ለፕሮፌሰር በጻፈው በገፅ 13 ላይ መልካችን “የረሃብ መልክ” ነው በማለት ገልፆታል፡፡ ታዲያ የምግብ ዋስትና ጥረት ስለምን ይነቀፋል? ገዢዎች የሚሰጡት ወይንም የሚያወጡት ፖሊሲ ከፊሉ መጥፎ ሊሆን እንደሚችል ጥሩም የሆነ ይኖረዋል፡፡ የኛ ስራ ጥሩውን ደግፈን መጥፎው እንዲወገድ መታገል መሆን አይገባውምን?

ለመልካም ነገር ትብብር እናሳይ መጥፎውን ለማስወገድ ደግሞ አብረን በግልፅነትና በእውነት እንቁም፡፡
የሚጠቀመን ነገር ውስብስብ እና ተጨባጭ ባልሆነ የሕልም ዓለም ውስጥ መኖር ሳይሆን በተገለጠውና በቀላል ሁላችንንም በሚጠቅመው ግልፅነት አብረን ተከባብረንና ተፋቅረን በትጋት መስራት ነው፡፡

የምዕራባውያኑ ዕድገት የመጣው በስራ ነው፣ ቻይኖች አሁን የደረሱበት ደረጃ የደረሱት በትጋት በመስራት ነው፡፡ ጃፓን እንደምን ሰለጠነች የሚለውን መጽሐፍ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ያስነበቡን ኢትዮጵያውያን ይነግሩን የነበረው ጃፓን የሰለጠነችው በስራ እንደነበር ነው፡፡ የእኛም አገር መለኮታዊ ዕጣ በመስራት ማደግ፣ በመስራት ማደግና መሻሻል ብቻ ነው ሌላው ግን ቅዠትና የቀን ሕልም ብቻ ነው፡፡

ቸር ይግጠመን
ጃፋር ሐሰን

ዜጎችን ከስፍራቸው ማፈናቀል አንዱ የኢህአዲግ ማናለብኝ ህገዎጥ ተግባር ነው -(ከሰሜን አሜሪካ አንድነት ድጋፍ ማህበራት የተሰጠ መግለጫ)

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት፣ ዜጎች በማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት የመንቀሳቀስ፣ የመኖር ፣ የመነገድ ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳላቸው በግልጽ ያስቀምጣል። ነገር ግን ገዢው ፓርቲ ይሄን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት በመጣስ በተለያዩ ቦታዎች በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ግፍና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።

በሰለጠነው አለም፣ ዜጎች ከመኖሪያ ስፍራቸው የሚፈናቀሉት፣ የሚኖሩበት አካባቢ ተፈጥሮ ባስከተለው ቀውስ የተጠቃ ወይም የሚጠቃ ከሆነ ነዉ። በአገራችን ኢትዮጵያ እያየን ያለነዉ ግን ኢትዮጵያውያን የተለየ ቋንቋ በመናገራቸው፣ የዚህ ወይም የዚያኛው ብሄረሰብ አባል በመሆናቸው በአገራቸው እንደ ባእድ ተቆጥረዉ፣ ነፍጥ በጨበጡ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ና አገልጋዮቻቸው በኃይል ሲፈናቀሉ ነዉ።

ከጥቂት ወራት በፊት ከደቡብ ክልል በግፍ ተባረው አዲስ አበባ፣ ሰሞኑን ደግሞ ከቤነሻንጉል ጉሙዝ ተባረዉ መተከል እና ፍኖተ ሰላም እንዲሰፍሩ የተደረጉ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጅ ወገኖቻችንን እንደምሳሌ መጥቀሱ ይበቃል። ከቤኔሻንጉል በአስቸኳይ እንዲባረሩ የተደረጉት ወገኖቻችን ፣ በአውቶብስ እንደ እቃ ታጭቀው፣ ክብራቸው ተገፎ የተባረሩ ሲሆን፣ አንዱ አውቶብስ ከአቅም በላይ ሰው በመጫኑ ምክንያት አደጋ ደርሶ፣ ከአምሳ ስድስት በላይ የሚሆኑ ዜጎች ሞተዋል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት አሰቃቂ የዘር ማጥራት ወንጀል በኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ነው።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ፣ በርካታ የአገራችን ድንግል መሬቶችን ለሕንዶች፣ ለአረቦችና ለቻይናዎች እየሰጠ፤ ከነዚህ አገራት የመጡ ዜጎች በአገራችዉ ያላገኙትን የተደላደለ ኑሮ እንዲኖሩ እያደረገ፣ ለነዚህ ለዉጭ አገር ዜጎች ቀይ ምንጣፍ እያነጠፈ፣ ኢትዮጵያዉያንን ግን ከመኖሪያቸው ማፈናቀሉ፣ ማዋረዱ፣ ማሰሩና መግደሉ፤ የዚህን አገዛዝ ምንነት በግልጽ የሚያሳይ ነዉ።

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች የሚኖረው ሕዝባችን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገሩ፣ ለዘመናት ተፋቅረው፣ ተዋልደው፣ እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው ከኖሩ በርካታ ብሄር ብሔረሰቦች የተውጣጣ ነው። ወላይታው በሲዳማው ላይ፣ ሲዳማው በኦሮሞው ላይ፣ ኦሮሞው በጉሙዙ ላይ፣ ጉሙዙ በአማራው ላይ፣ አማራው በትግሬው ላይ፣ ትግሬው በአፋሩ ላይ፣ አፋሩ በኢሳው ላይ …..ችግር የለውም። ኖሮትም አያውቅም። ገዥዎቻችን ግን እየነጣጠሉ ሲመቱን ኖረዋል፡፡ በመሆኑም በደቡብና በቤነሻንጉል የተከሰተዉ አሳዛኝ የዘር ማጥራት ወንጀል በአገዛዙ የተፈጸመ እንጂ በአካባቢዉ ሕዝብ የተፈጸመ አይደለም። ለዚህም ሕወሃት/ኢሕአዴግ እና አሁን ያሉት አመራሮች ሙሉ ተጠያቂ እንደሆኑ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ከዚህ ዘረኛና እኩይ ተግባራቸው በአስቸኳይ ተቆጥበው፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ስፍራቸዉ እንዲመለሱ፣ ለደረሰባቸው ግፍም ተመጣጣኝ ካሳ እንዲሰጣቸውና ለዚህም ተጠያቂ የሆኑ የወረዳ፣ የክልል እንዲሁም የፌደራል ባለስልጣናት በአስቸኳይ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እናሳስባለን።

በሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበራት ይሄን መግለጫ ስናወጣ፣ በርካታ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት ከኛ በፊት ተመሳሳይ መግለጫ እንዳወጡ ማስታወስ እንፈልጋለን። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ጠንቅቀን መረዳት ያለብን መሰረታዊ ሃቅ አለ። ይህ ዓይነቱ ግፍ፣ መግለጫ በማውጣት ብቻ መፍትሄ እንደማያገኝ መረዳት አለብን። ከመግለጫ ማውጣት ባሻገር፣ ዘለቈታዊ ዉጤት ሊያመጣ የሚችል የተቀነባበረ ትግል መጧጧፍ ይኖርበታል።

በዚህ ረገድ፣ ቀዳሚዉ ሥራ ዲሞክራሲያዊ ትግሉን ማስተባበርና ኢትዮጵያዉያንን በአንድ ቡድን ማሰባሰብ በመሆኑ፣ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የምንገኝ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ያለንን ልዩነቶች አቻችለን፣ የህግ የበላይነት የሰፈነባትና የዜጎች እኩልነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት ቆርጠን በአስቸኳይ መነሳት አለብን እንላለን። የሰሜን አሜሪካ አንድነት ድጋፍ ማህበራት፣ ለዲሞክራሲያዊ ትግሉ የድርሻቸውን ሃላፊነት ለመወጣት፣ ከዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንንም በዚህ አጋጣሚ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ነጻነት የትግል ውጤት ነው

የትም ቦታ የተፈጸመ የፍትህ መጓደል በሁሉም ቦታ ፍትህ ላይ የተቃጣ አደጋ ነው! (ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር)

Injustice anywhere is a threat to justice everywhere! (Martin Luther King Jr.)

በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች


ወ/ሮ አዜብ ስለየትኛው ድህነታቸው ነው ሊነግሩን የፈለጉት?! በፍቅር ለይኩን

በ2000 ዓ.ም. ይሁን በ2001 ለጊዜው እርግጠኛ ባልሆንም ግን ከሁለቱ በአንዱ ዓመት ይመስለኛል፡፡ በመዲናችን በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደ ዓመታዊው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶችም በበኩላቸው ከባሎቻቸው እኩል አፍሪካውያን እመቤቶች ስለ አፍሪካ ጉዳይ ተፈጥሮ የተቸራቸውን የሴትነት ጥበብና ብልሃታቸውን በመጠቀም ኁልቆ መሣፍርት ለሌለው ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ችግሮችና እንቆቅልሾች ምክር ቢጤ ለመለገስና መፍትሔ ለማመላከት እነርሱም በተራቸው ለስብሰባ ተቀምጠው ነበር፡፡

ከዚህ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶች ስብሰባው ማብቂያ በኋላ ታዲያ አንድ የስልክ መልእክት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ኢትኖግራፊክ ሙዩዚየም ደረሰ፡፡ መልእክቱም የዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት የቀድሞውን የኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግሥትና የአሁኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ኢትኖግራፊክ ሙዚየም መጎብኘት ስለሚፈልጉ ፕሮግራም እንዲያዝላቸው የሚያሳስብ ነበር መልእክቱ፡፡

ለአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲ ኢትኖግራፊክ ሙዩዚየም በደረሰው መልእክት መሠረት ‹‹ለጥቁሯ እንግዳ›› ለዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት ታሪካዊ ገለጻ እንዳደርግ በጊዜው በዩኒቨርስቲው የኢትዮጵያ ጥናት መምህርና የሙዚየሙ ኩሬትር ከሆኑት ዶክተር ጋር በመሆን ለእኚሁ ለዛምቢያዋ እመቤት ገለጻ በመስጠት ጥቂት ቆይታን ለማድረግ ዕድሉን አግኝቼ ነበር፡፡

የዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት በዕለቱ ሽንጣቸው ረጃጅም በሆኑ በጥቋቁር ሊሞዚን ማርቼዲስ አውቶሞቢሎች በሞተር ሳይክል ታጅበው፣ የሰማይ ስባሪ ከሚያካክሉ፣ ደረታቸው እንደ ሑዳድ እርሻ ከሰፋው፣ ዓይኖቻቸው አራቱን የምድሪቱን ማዕዘን የሚቃኙ ከሚመስሉ፣ ጡንቻዎቻቸው ከፈረጠሙ፣ አረማመዳቸውና መገላመጣቸው ምድሪቱን የሚያንቀጠቅጥ ከሚመስሉ፣ በእጆቻቸው ላይ የውሻ ሰንሰለት ሚያክል አምባር ካጠለቁ፣ በአውሮፓ ውድ አልባሳትና ጫማዎች ከተዋቡ ቦዲጋርዳቸው፣ ከተሸቀረቀረ ዘናጩ ፎቶ ግራፍ አንሺያቸው፣ የእኚህን እመቤት ቦርሳቸውንና አስፈላጊ የሆኑ የግል ዕቃዎቻቸውን ካነገቡ፣ ውድ በሆኑ አውሮፓዊ አልባሳትና ጌጣ ጌጦች ከተዋቡት፣ በቁመት የሚያስከነዷቸውን ሞዴሊስት የምትመስል ደንገጡራቸውን አስከትለው ነበር፤ የዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት ወደ ቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት፣ የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሞቀና በደመቀ አጀብ የመጡት፡፡

እኚህ ቀዳማዊ እመቤት ከጉብኝታቸው በፊት ወደዚህ የቀድሞ የኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግሥትና የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሊመጡ የቻሉበትን ምክንያት እንዲህ በማለት አስረዱን፡፡ የአገሬ ፕሬዝዳንት የሆነው ባለቤቴ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ነፃ የስኮላር ሺፕ ትምህርት ዕድል አግኝቶ የተማረው ንጉሡ ቤተ መንግሥታቸውን ዩኒቨርስቲ አድርገው በሰጡት በዚህ ግቢ ውስጥ ነበር፡፡

እናም አዲስ አበባ ካሉ ቦታዎች ሁሉ መርጬ ወደዚህ የመጣሁበት ምክንያት አሉ እመቤቲቱ ውድ ባለቤቴ የተማረበትን ይህን የአገራችሁን የነፃነት ተምሳሌት የሆነውን ዩኒቨርስቲና ለአፍሪካ አገሮች አንድነትና ኅብረት ትልቁን መሠረት የጣሉትን የእኚህን ታላቅ አፍሪካዊ አባት የኃይለ ሥላሴን የቀድሞ ቤተ መንግሥት ለማየት ጭምር ነው የመጣሁት በማለት የበዛ አድናቆትና አንዳንች ትልቅ ጉጉት በሚንጸባረቅበት ስሜት ውስጥ ሆነው ወደ ዩኒቨርስቲው የመጡበትን ምክንያታቸውን አስረዱን፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት ከዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት ጋር ባደረግነው ቆይታ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይነት፣ ታሪክና ባህል በእጅጉ መመሰጣቸውን በአድናቆት ቃል ሆነው ነገሩን፡፡ በመዲናችን በተካሄደው የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶች ስብሰባም መደሰታቸውንና ስለ ስብሰባው ፋይዳም እግረ መንገዳቸውን አብራሩልን፡፡ በተጨማሪም በወ/ሮ አዜብ ተግባቢነት፣ እንግዳ ተቀባይነትና አክባሪነት፣ ደግነትና ርኅራኄም በእጅጉ መገረማቸውንና መደሰታቸውንም ጨምረው ገለጹልን፡፡

ወ/ሮ አዜብም የዛምቢያዋ አቻቸው እንዳረጋገጡት የእንግዳ ተቀባይነታቸውና ደግነታቸው ምስክር ይሆን ዘንድ ለአገራችን ታሪክና ሥልጣኔ እምብርት የሚባለውን የአክሱምን ታሪክ የሚያሳስብ ለእርሳቸውና በስብሰባው ላይ ተካፋይ ለነበሩት አፍሪካውያን ቀዳማይ እመቤቶች ሁሉ በስጦታ መልክ አክሱም ቅርጽ ያለው የወርቅ አንገት ሀብል እንዳበረከቱላቸው ደስታና ኩራት በሚንጸባረቅበት ስሜት ነገሩን፡፡ እንግዲህ አንባቢ ያስተውል፣ ልብም ያድርግ የዓለም ድሀ ነኝ የሚሉት እመቤት ናቸው አፍሪካዊ አቻዎቻቸውን፣ ቀዳማይ እመቤቶችን በወርቅ ስጦታ ያንበሸበሹት፡፡

ከጉብኝቱ መጠናቀቅ በኋላ የዛምቢያዋ ቀዳማይ እመቤት በሙዚየሙ የስጦታ መሻጫ ሱቅ የሚፈልጉትንና ዓይናቸው ደስ ያላቸውን ጌጣጌጦችና የስጦታ ዕቃዎች በመምረጥ በደንገጡራቸው በኩል ክፍያ እንዲፈጸም ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተው ጠባቂዎቻቸውንና የግል ፎቶ ግራፍ አንሺያቸውን አስከትለው የቀድሞውን ቤተ መንግሥት የአሁኑን የአዲስ አበበባ ዩኒቨርስቲን፣ የባለቤታቸውን ውብ የሆነ የማይረሣ ትዝታ በልባቸው ጽላት አትመው ወዳረፉበት ሆቴላቸው ታጅበው ተፈተለኩ፡፡

ከጉብኝቱ ፍፃሜ በኋላ የአፍሪካና የአፍሪካዊነት እሮሮዎች፣ ሰቆቃዎች፣ ውጥንቅጦችና እንቆቅልሾች በአእምሮዬ ውስጥ ይመላለሱ ጀመር፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ከገባሁበት የሐሳብ ማዕበል ውስጥ ሆኜ አንድ ነገር አልኩ፡፡ መቼ

ይሆን አፍሪካ የሚራሩላት፣ ከልብ የሚያዝኑላት መሪዎችን የምታገኘው፣ እስከ መቼ ልጆቿ እንዲህ ይጨክኑባታል፣ እስከ መቼስ እንባዋና ሰቆቃዋ፣ ወይታዋ ከእርሷ ጋር ይዘልቃል …?!
እንግዲህ አፍሪካውያን ርዕሳነ ብሔራንና ቀዳማይ እመቤቶች በየአገሩ ለጉብኝትም ሆነ ለስብሰባ ሲሄዱ የሚያግተለትሏቸውን የግል ጠባቂዎቻቸውና ሰዎቻቸው የሚወጣውን የአይሮፕላን ትኬት ዶላር፣ የሆቴል ወጪ፣ ፕሮቶኮሉን፣ የስጦታ ዕቃ ግዢውን፣ ለመዝናኛ የሚወጣውን ወጪ … እረ ስንቱ ይህን ሁሉ ማስላት ነው፡፡ በእውነት ይሄን በማሰብ ልብ ይታመማል፣ ኅሊናም ይደክማል፡፡

ይህች ናት እንግዲህ አፍሪካና መሪዎቿ፡፡ በሙስና፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በአምባገነን መሪዎቿ የተነሣ በጽኑ ስቃይ ውስጥ ሆና የምታቃስት፣ የምታጣጥር አኅጉር- አፍሪካ፡፡ ሕዝቧ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በራብ፣ በወረርሽኝ፣ በንጹሕ ውኃ አቅርቦት እጦት፣ በትምህርት ዕድል ማጣት በድንቁርና ጨለማ ውስጥ የሚዳክሩባት፣ በሆስፒታሎችና በጤና አገልግሎት ሰጪዎች እጥረት ምስኪን ሕዝቧ በሚረግፍባት አፍሪካ፤ ግና ደግሞ መሪዎቿና እመቤቶቿ በሚሄዱበት አገር ሁሉ ሠራዊትና ጠባቂዎቻቸውን አስከትተው የአፍሪካን፣ የገዛ ድሀ ሕዝባቸውን ሀብት እንደፈለጋቸው ያዙበታል፣ ይናዝዙበታል፣ ይረጩታል፡፡

ከዚሁ ከአፍሪካውያን ቀዳማይ እመቤቶች ቅምጥልነትና አባካኝነት ጋር በተያያዘ በአንድ ወቅት የአንዲት አፍሪካዊት እመቤት የመጀመሪያዋ ጥቁር የአሜሪካ ቀዳማይ እመቤት ሆነው ለተመረጡት ለሚሼል ኦባማ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክታቸውን ለመግለፅ ሲሉ በዳይመንድ የተንቆጠቆጠ የእጅ ሰዓት ስጦታ ልከው ነበር አሉ፡፡
ይህ ውድ ስጦታ የደረሳቸው አስተዋይዋ ሚሼል ኦባማም ለአፍሪካዊቷ ቀዳማይ እመቤት ስለ መልካም ምኞትዎ አመስግናለኹ፡፡ ይህ በዕንቁ የተንቆጠቆጠ ውድ ሰዓትም ለእኔ አይገባም፡፡ ምክሬ ደስ ካሰኝዎ ይህን ብዙ ገንዘብ የፈጀ ውድ ስጦታ ለእኔ ከሚሰጡት በአገርዎ በራብ፣ በበሽታና በድህነት እየተሰቃዩ ላሉ ሕዝቦችዎ ቢያውሉት ደስ ይለኛል፡፡ በማለት ስጦታውን አልቀበልም በማለት እንደመለሱላቸው ማንበቤን አስታውሳለኹ፡፡

ይህን ከላይ የገለፅኩላችኹን የዛምባያዊቷን ቀዳማይ እመቤት ገጠመኜን እንዳስታውስ ያስገደደኝ ከሰሞኑ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ዳግመኛ በብዙኃን መገናኛ ብቅ በማለት ባለቤትም ሆነ እኔ እልም ያልን መናጢ ድሀ ነን፡፡ በታላቁ ቤተ መንግሥት ኑሮአችንን ስንገፋ የነበረው በድህነት ነው ሲሉ የማወጃቸው ነገር በአያሌው ግርምትን ቢያጭርብኝ ነው፡፡

በቅርቡም ይህ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ‹‹ድህነታችንን እወቁልን ዐዋጅ›› የከነከነው ኤፍሬም እሸቴ የተባሉ ጦማሪ ከሀገረ አሜሪካ ሜሪላንድ ‹‹ድሀ ከሆኑስ አይቀር እንደ አቶ መለስ ነው›› በሚል ምፀት፣ ቁጭትና እልህ የተቀላቀለበት የሚመስል ጽሑፍ በብሎጋቸው አስነብበውናል፡፡ ይህን ጽሑፍም የአዲስ አበባው ሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔትም አስነብቦናል፡፡
ጦማሪው ይህን ጹሑፍ ለመጻፍ የተገደዱት ከሰሞኑን የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፡- አይገርማችኹም፣ አይደንቃችኹም በሚል አንድምታ ባለቤታቸው አቶ መለስ ከዓለም መሪዎች ሁሉ ቤሣቤስቲን የሌላቸው መናጢ ድሀ የመሆናቸውን ምሥጢር ዛሬም ደግመው በአደባባይ ድህነታችንን ያልሰማችሁ ስሙ፣ የሰማችሁም ላልሰሙት አሰሙ በሚል በማወጃቸው ነው፡፡

ወ/ሮ አዜብ ሁናቴ ምናልባትም አቶ መለስና እርሳቸው በዚህ ተአምረኛ ሊባል በሚችል ኑሮአቸው የተነሣ፣ የአንድ ባለ ታላቅ ታሪክና ሥልጣኔ ባለቤት የሆነች አገር መሪ ሆነው በድህነት ውስጥ ያለፉ ብቸኛው አፍሪካዊ ርዕሰ ብሔርና ቀዳማይ እመቤት በሚል በድንቃ ድንቅ መዝገብ ውስጥ ይመዝገብልን ይመስላል ዘመቻው፡፡

ከዚህ እንደ መዥገር ከተጠባቸው ድህነታቸውም የተነሣ ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስ በሚሰጧቸው የወር ገቢያቸው ከኑሮ ውድነት ጋር እየታገሉ፣ ኑሮአቸውን እንደነገሩ ኑሮ አድርገው፣ በቤተ መንግሥት እየኖሩ፣ ሌትና ቀን እንቅልፍ የሌላቸው በሚመስሉ በእልፍ ሠራዊት እየተጠበቁ፣ ሕዝበ አዳም እነርሱ በረገጡበት መሬት ዝር እንዳይል መንገድ አዘግተው፣ የጭቁኑ ሕዝብ ወገን ነን፣ የታገልነውም ለጭቁኑ ሕዝባችን ነው እንዳላሉን፣ የሕዝባቸው ዓይን እንደ ጨው አሟሙቶ ያጠፋቸው ይመስል በሩቅ ሆነው አሻግረው እየተገላመጡን፣ ጥይት በማይበሳው በሊሞዚንም መርቼዲስ ተንፈላሰው፣ ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከእስያ እስከ አውሮፓ፣ ከጃፓን እስከ ቻይና፣ ህንድ፣ መካከለኛውና ሩቅ ምስራቅ ምድርን ዞረውና አስሰው፣ ልጆቻቸውን በሳንፎርድ አስተምረው፣ በአውሮፓ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ድረስ ልከው፣ አቻዎቻቸውን አፍሪካውያን እመቤቶችን በስጦታ አንበሽብሸው … ግን ደግሞ በችግር ተቆራፍደው የኖሩ ናቸው ወ/ሮ አዜብ ሆኑ ባለቤታቸውም አቶ መለስ ዜናዊ፡፡ የድሀ ድሀ ነን፣ አቶ መለስ ዜናዊም ነፍሱን ይማርና ብቸኛው ድሀ መሪ ነበሩ አሉን፣ አስባሉን ወ/ሮ አዜብ መስፍን!!

እናም ይኸው ወ/ሮ አዜብ በአገሪቱ የቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ኢትዮጵያና መላው ዓለም መናጢ ድኃ መሆናችንን ይወቅልን ሲል ደግመኛ በአደባባይ ይህን ድህነታቸውን አውጀውልናል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ኑሮአቸው ሁሉ የችግር በሚያገኟት ገቢ ወር አደረስን አላደረሰን በሚል ከዚህም ከዛም ብለው አበቃቅተው፣ ሰቀቀን በታላቁ ቤተ መንግሥታቸው ከድህነት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው፣ ቤተ መንግሥቱ ቤተ መንግሥት ሳይመስላቸው በከፋ ድህነት መኖራቸውን ነገሩን፤ እኛም ሰማናቸው፡፡

መቼም ጆሮ አይሰማው ጉድ የለ!! ምነዋ ጆሮ ከኋላ የመጣ ቀንድ ሲበልጥህ አንተ እንዲህ ባለህበት ቆመ መቅረትህ ብለው የሰውነት ክፍሎች ተሰባስበው ጠይቀውት ነበር አሉ በእንሰሳቱ ዓለም፡፡ ያው እንግዲህ ነገሩ ተረት መሆኑን እንዳስቱት፡፡ እናም አያ ጆሮ የአንድ የአካል አጎራባች የሆኑት በደም በሥጋ የሚካፈሉት ወገኖቹ ያላማደጉ ነገር ቆጭቷቸው ላቀረቡለት ጥያቄ የሰጣቸው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፡፡

አይ ወገኖቼ ማደጉንስ ባልጠላኹት ግን አካሎቼ፣ ወገኖቼና ውዶቼ የእኔ ባይደርስባችኹ ነው አልፈርድባችኹም፡፡ በዚህ ጆሮዬ በነጋ ጠባ ስንቱን ጉድ እየሰማሁ በየት በኩል ልደግ ብላችሁ ነው ብሏቸው አረፈ፡፡ እናም በነጋ ጠባ ጆሮን ጭው የሚያደረግ ወሬን እንድሰማ የተፈረደብን የምንመስል እኛ ኢትዮጵያውያን ጆሮን የሚጠልዝ ጉድ በየዕለቱ ወደንም ሆነ ተገደን እየሰማን ይኸው እንደ እንሰሳቱ ጆሮ ከቀን ወደቀን እየተሸማቀቅን እያነስን እየሄድን ነው፡፡

ወ/ሮ አዜብ ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ በነጋ ጠባ ችግር ችግር የምትሉት እኔስ ብሆን ከእናንተ በምን እለያለኹ እያሉን ይመስለኛል፡፡ በአንድ ወቅትም ወ/ሮ አዜብ ከዚሁ ከባለቤታቸውና ከእርሳቸው ድህነት ጋር በተያያዘ እንዲህ ብለው እንደነበር አንዘነጋም፡፡ በእውቀቱ ዓለምን ጉድ ያሰኘ ባለቤት ኖሮኝ፣ በሺህ ዶላሮች የሚመነዘር አእምሮ ያለው ሰው ጋር ሆኜ በችግር የምቆራመደውና የምንቆራመደው ወድጄና ወደን ይመስላችኋል፡፡ ለማን ደስ ይበለው ብለን ነው፤ እዚሁ ከእናንተው ጋር በችግር ተቆራመደን፣ የኑሮአችንን ጣጣ ለመድፈን ሌት ተቀን እየባዘንን በሰቀቀን እየኖርን ያለነው፡፡

ልዩነቱና የእኛን ድህነት ከሌላው ኢትዮጵያዊ የከፋ የሚያደርገው በመሪ ደረጃና ክብር በቤተ መንግሥት እየኖርን በችግር አለንጋ የምንገረፍ፣ በድህነት አረንቋ ውስጥ የምንዳክር መሆናችን ነው፤ እንደው ስም ብቻ ነው ያተረፍነው እያሉን መሰለኝ ወይዘሮዋ፡፡

እናም ዛሬም ወ/ሮ አዜብ እርሳቸውም ሆኑ ባለቤታቸው በፔሮል ላይ ተፈርሞ በሚሰጣቸው ከአንድ እጅ ጣት በማይበልጡ ጥቂት ሺሕ ብር የወር ገቢ ‹‹የሴት ብልሃቱን የጉንዳን ጉልበቱን›› እንደሚባለው የሴትነት ብልሃታቸውንና ጥበባቸውን ተጠቅመው ‹‹ለባለቤታቸው ዘውድ፣ ለቤተ መንግሥቱ ንብ›› ሆነው በታታሪነት የቤተ መንግሥቱን ኑሮ በከፋ ድህነት ግን ደግሞ በሴትነት ብልሃት እንደምንም እንደተጋፈጡት እንደገና ሊነግሩን ወደዱ፡፡ ወ/ሮ አዜብ ዛሬም አስረግጠው ወደዳችሁም ጠላችሁም ስለ ባለቤቴም ሆነ ስለ እኔ ያለው እውነታው ይኽው ነው በማለት የትላንትና ደረቅ ሙግታቸውን ዛሬም በአደባባይ ይግረማችኹ ብለው ደገሙልን፡፡
መቼም ስለ ድህነት መልክና ገጽታ፣ ስለ መራብ፣ ስለ መራቆት ስለ ችግር … ለወ/ሮ አዜብ መናገር ለቀባሪው አረዱት እንዳይሆንብኝ እሰጋለኹ፡፡ ለምን ሲባል አሰከፊ ከሆነና ራሱ ድህነት ሥጋና ነፍስ ነስቶ በአካል ቆሞ የሚሄድበት ከሚመስልበት ከሰሜኑ የአገራችን ክፍል ድሀ ገበሬ የተገኙ ሴት ናቸውና፡፡ እናም ወይዘሮዋ ድህነት ምን ማለት መሆኑ ይጠፋቸዋል ብዬ ለማሰብ አልደፍርም፡፡

ከዛም አልፎ ወ/ሮ አዜብም ሆኑ አቶ መለስ ዜናዊና የትግል አጋሮቻቸው በረሃ ለበረሃ፣ ዱር ለዱር፣ ጥሻ ለጥሻ፣ ቆንጥር ለቆንጥር፣ ገደል ለገደል በራብ አለንጋ እየተገረፉ የልጅነት አንጀታቸውን በዝናር መቀነት ጥብቅ አድርገው አስረው፣ በጠኔና ውኃ ጥም ጉሮሮአቸው እየተሰነጠቀ ከችግርና ከመከራ ጋር እየተፋለሙ፣ ደግመው ደጋግመው ከፃረ ሞት ጋር ፊት ለፊት የተጋፈጡ ሰዎች ናቸው፡፡

ወ/ሮ አዜብ ከላይ ከሰማይ እየተመዘገዘጉ የእሳት አሎሎ ውርጅብኝ ከሚያዘንቡ፣ በታች በምድር የእሳት ነበልባል በሚተፉ አሰቃቂ በሆኑ ዘግናኝ የጦርነት አውድማዎች ላይ የዋሉ፣ በብዙና እንደ መርግ በከበደ መከራና ጭንቅ ውስጥ ላመኑበት ዓላማ ወርቃማ የወጣትነት ጊዜያቸውን የበረሃ ሲሳይ አድረገው፣ ባመኑበት የትግል መስመር ትልቅ መሥዋዕትነትን ከፍለው ለዛሬው ሕይወት የበቁ ፋኖ ሴት ናቸው፡፡

እናም በበኩሌ ደህንነት፣ ራብን፣ ጉስቁልናን፣ መከራን … ከቃል ባለፈ ወ/ሮ አዜብ በእውን የድህነት ህመምና ስቃይ ብርቱ ሰይፍ ከስጋቸው አልፎ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ እስኪሰማቸው ድረስ ያውቁታል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ደግሞም በታሪክ እንደማውቀው እነርሱም እንደነገሩን ወ/ሮ አዜብም ሆኑ አቶ መለስና የትግል ጓዶቻቸው ዱር ቤት ብለው ገና በአፍላ የልጅነት ዘመናቸው ምንም ነገር ሳያጓጓቸው ወደ በረሃ ያሳደዳቸው ይህ ሊቋቋሙት ያልቻላቸውና እንቅልፍ የነሣቸው የሕዝባቸው ሁለተናዊ የሆነ መከራ፣ ጉስቁልና እና ቃል የማይገኝለት የከፋው ድህነት ይመስለኛል፡፡

እነዚህ የትናንት ፋኖዎች የዛሬ መሪዎች ሕዝባቸውን ከተዘፈቀበት አስከፊ የሆነ ድህነት ውስጥ አውጠተውታል፣ የጭቁኑ ሕዝብ ወገንና አለኝታ ነን ያሉ እነዚህ ሰዎቻችን የገቡትን ቃል አክብረዋል ወይስ … የሚለው ጉዳይ ሌላ ሰፊ ትንታኔ የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢሆንም ቅሉ፡፡ ኢህአዴግ ግን ወደ ሥልጣን በመጣ ማግስት የገባው ቃል ሕዝቡን በቀን ሦስቴ ለማብላት ነበር፤ ይኸው ዛሬም ከሀያ ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያችን በምግብ እህል ራሷን ካልቻሉ አገሮች ጎራ ለመውጣት የሞት ሞቷን እየተፍጨረጨረች ያለች አገር የመሆኗ ጉዳይ ሌላኛው የመንግሥታችንና የአገራችን እንቆቅልሽ ነው፡፡

ግና ዛሬ ወ/ሮ አዜብም ሆኑ የመንግስት ባለሥልጣኖቻችን ድንገት ተነስተው ኑሮአችን የድህነት ነው፣ ድሀ ነን ሲሉን መስማታችን ስለየትኛው ደህነት ነው የሚያወሩን ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡ ባለሥልጣኖቻችን ስለ ሕዝባቸው ድህነት ለመናገር ሁሌም ዝግጁና በተጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን እባካችሁ እወቁልን እኛም እኮ ድሀ ነን ቢሉን ግን በእጅጉ የሚያስተዛዝበን ነው የሚሆነው፡፡

ፈጣን በሆነ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ተብላ በዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት ምሁራንና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ሣይቀር እየተመሰከረላት ያለችው ኢትዮጵያ በእርግጥ በዓለማችን ከሚገኙ አገሮች ሁሉ በመጨረሻ ተርታ የምትገኝ መናጢ ድሀ ከሚባሉ አገሮች የምትመደብ አገር ናት፡፡

ይሁን እንጂ ይላሉ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ዲቨሎፕመንት ፕሮግራም አማካሪ የሆኑት ሳሙኤል በዋልያ፡- ‹‹ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የምትገኝ አገር ብትሆንም ካለችበት ጥልቅ የሆነ ድህነት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት የጀመረችው ጉዞ ተስፋ ሰጪም ቢሆንም ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ግን ከአስከፊ ከሆነ ድህነት ለመላቀቅ ከፊቷ ረጅም ጉዞ እንደሚጠብቃት ነው የሚናገሩት፡፡››

እንደ ዓለም ባንክ ትንታኔ ከሆነ ድህነት ባለ ብዙ መልክና ባለ ብዙ ገጽታ ያለው ነው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ የከፋው የእናት ኢትዮጵያችን ድህነት ግን በዜጎች ነፃነት፣ ሰብአዊ መብቶች፣ የመጻፍና መናገር መብት ላይ ከዕለት ወደ ዕለት እየጠበቀ የመጣው ቀንበር ነው፡፡ በአገራችን ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ያለው ክፉ የሚባለው ድህነት መሪዎቻችን ከሕዝባቸው የሚገናኛቸውንና የሚያቀራርባቸው የፍቅር፣ የመነጋጋርና የመወያየት ድልድይ ዛሬም እንደተሰበረ፣ እየተንገራገጨ ያለ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ እኛ አሁን የሚያስፈልገን ዳቦ እንጂ በምዕራባውያን ልክ ተሰፋ ዲሞክራሲና ነፃነት አይደለም ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡ እናም የሚያሳዝነው ዳቦውን ሳንጠግብ የከፋው ድህነት ደግሞ በዜጎች ነፃነት፣ የመጻፍና መናገር መብትና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ ከዕለት ወደ ዕለት እየጠበቀ የመጣው ቀንበር አገሪቱን በአፍጢሟ ሊደፋ ያለ የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነ የከፋ ድህነት ሆኖ ክፉኛ እየተፈታተነን ነው ያለው ጉዳይ መኾኑ ነው፡፡

ክፉ የሚባለው ድህነት መሪዎቻችን ከሕዝባቸው የሚገናኛቸውንና የሚያቀራርባቸው ሕዝባዊ ፍቅር፣ ሕዝባቸውን ቀርበው የማነጋጋርና የማወያየት ድልድይ ዛሬም እንደተሰበረ፣ እየተንገራገጨ ያለ የመሆኑ ምሥጢር ነው፡፡ መንግሥትም ሆነ ባለሥልጣኖቻችን ባይገነዘቡት ወይም ንቀው ቢተዉት እንጂ የሕዝብን ፍቅርና ተዓማኒነት ከማጣት የባሰ ምን የከፋ ድህነት ምንስ ጉስቁልና ይኖራል፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሆኑ መንግሥትም ወይም ፖለቲከኞቻችን ስለዚህ የድህነታችን ሁሉ ምንጭ ስለሆነው ስለ ነፃነታችን፣ ስለ ሰብአዊ መብቶቻችን፣ ስለ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈንና ማደግ አጥብቆ ካልሠራ እኛም በሰላማዊ መንገድ ለመብቶቻችን በጽናት መታገል ካልቻልን ምናስባት የበለጸገች ኢትዮጵያ ሕልም እንደሆነች የምትቀጥል ይመስለኛል፡፡
ሰላም! ሻሎም!

የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ? ስለክብረ-በአሉ እንግዶች፤ ስለመንግስትና ሀይማኖት መለያየት፤ ልጅ ተክሌ

1-ጽሁፍ ካላበሳጨ ወይ ካላስጨበጨበ አይመቸኝም። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚያበሳጭ ወይ የሚያስጨበጭብ ርእስ ስጠብቅ ሳልጽፍ ቆየሁ። የኢትዮጵያውያን፤ በተለይም የአማርኛ ተናጋሪ፤ ኢትዮጵያዊያን ከቤንሻንጉል መባረር በራሱ በቂ አናዳጅና አሳዛኝ ክስተት በመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች ስለጻፉበት እሱ ላይ ብዙ አልደክምም። ስለዚህ ሌላ አናዳጅ ርእስ ናፈቅኩ። እነሆ ባያናድድም፤ ምን ነካቸው የሚያስብል ርእስ ከኢሳት አገኘሁ።

2-ባለፈው ሰኞ፤ ከአድካሚው ውሎዬ እረፍት ለመውሰድ ወደኢሳት ድረ-ገጽ አመራሁ። የደንቡን አድርሼ ከኢሳት ድረገጽ ወጥቼ ለመሄድ ጣቴን ጠቅ ለማድረቅ ስንቀለቀል፤ በአይኔ የቀኝ ጠርዝ፤ በኢሳት ድረገጽ የግራ ማእዘን ላይ፤ ስድስት ሰባት ወንዶች የተደረዱበት ምስል አየሁና ተመለስኩኝ። አንዳንዶቹ የተለመዱ ፊቶች ናቸው። “ሲሳይ አጌና፤ ታማኝ በየነ፤ ሻምበል በላይነህ፤ ሄኖክ የሺጥላ …”። ሌሎቹ ግን በቃለምልልስ ካልሆነ በስተቀር፤ ከኢሳት ጋር በተያያዘ ለሚደረግ ዝግጅት አዳዲስ ናቸው። የኢሳት ሶስተኛ አመት ዝግጅትን ለማድመቅ የተመረጡ እንግዶች ናቸው። የሚያበሳጭም ባይሆን፤ እነሆ የሚያወያየው ርእስ የነዚህ ሰዎች ለእንግድነት መመረጥ ነው።

3-ከኤፕሪል 13 እስከ ሜይ 26 የኢሳት 3ኛ አመት ክብረበዓል በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል። ነጂብ ሞሀመድ፤ ከታማኝ በየነና ሄኖክ የሺጥላ ጋር ቅዳሜ ሎስ አንጀለስ ይገኛል። እሁድ እዚያው ሳንዲየጎ ይጓዛሉ። እነዚሁ ሰዎች።ታማኝ በየነና ሻምበል በላይነህ ካሊድ ኦማርን ይዘው እሁድ ኤፕሪል 20 ሳን ሆዜ ይገኛሉ። ታማኝ በበነጋው እሁድ ኤፕሪል 21 መንሱር ኑርን ይዞ ሲያትል ይታያል። ነጂብና ታማኝ እንደገና እሁድ ኤፕሪል 28 ናሽቪል፤ ቴነሲ ይገኛሉ። ጃክሰንቪል ፍሎሪዳ ታማኝና ሻምበል ሜይ 18 ይገኛሉ። በስድስት ከተሞች በሚካሄዱ የኢሳት ዝግጅቶች ላይ አምስት የሙስሊም የሀይማኖት መሪዎች የመጋበዙ አመንክዮ ትንሽ ግራ አጋብቶኛል? በኔ አስተያየት፤ ኢሳት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከሆነ፤ ነውም፤ በኢሳት ሶስተኛ አመት ዝግጅቶች ላይ ከስድስቱ ከተሞች ውስጥ በአምስቱ የሙስሊም ሀይማኖት መሪዎች ዋንኛ ተጋባዥ እንግዶች መሆናቸው ብልሀት ያነሰውና ያልተጠና ነው። ይሄ አካሄድ ያለውን ፖለቲካዊ አንድምታና የሚያስተላልፈውን መልእክት የኢሳት አስተዳደር የተረዳው አልመሰለኝም።

4-ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን፤ በተለይም በአገር ቤት ያሉቱ የሚያደርጉትን ሰላማዊና በሳል ትግል ብደግፍም፤ የኢሳት 3ኛ አመት ዝግጅት ግን ሀይማኖታዊ አንድምታ በሚኖረው መልኩ መሆኑ ትክክል አይመስለኝም። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊያን ዜግነትን ሳይሆን ሀይማኖትን መሰረት አድርገው እንዲደራጁ የማበረታታት ተጽእኖ ያሳድራልና።ሙስሊሞች ባንድ በኩል ሙስሊሞች ለመብታቸው መታገላቸው የሚደገፍ፤ የሚያስቀና፤ የሚኮረጅ ነው። ሙስሊሞችም ይሁኑ ሌሎች በሀይማኖት ዙሪያ የተደራጁ ሀይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንደአንድ ፖለቲካዊ ጎራ ወይም ቡድን ይታዩ፤ ወይንም እንደ አንድ ፖለቲካዊ ቡድን (Political Block) ሆነው እንዲወጡ እናበረታታቸው ወይንም እውቅና እንስጣቸው የሚለውን ሀሳብ በጽኑ እቃወመዋለሁ። እንደዚያ ብለው የሚያስቡ ሙስሊሞችም ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ሊኖሩ ይችላሉ። ኢሳት ግን ሙስሊሞችንም ይሁን ማናቸውንም የሀይማኖት ድርጅት ፖለቲካዊ ሀይል አድርጎ በሚያወጣ ጉዞ ውስጥ አባል መሆን የለበትም ብዬ አምናለሁ። ዜግነትን መሰረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ እንደኢሳት ያለና ብዙዎቻችን በሀይማኖታችን ሳይሆን በዜግነታችን የተከተልነው ተቋም አንዱ ላይ አይደለም፤ ሁለቱም ላይ አይደለም፤ አምስት ዝግጅቶች ላይ የሙስሊም ሀይማኖት መሪዎችን ነጥሎ መጋበዙ ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም።

5-አንዳንድ በጓዳ ብቻ የምንላቸውን ነገሮች በጨዋ ደንብና በሰለጠነ መንገድ እስከሆነ ድረስ በአደባባይም መነጋገር አለብን። ብዙዎቻችን በኢሳትም በኩል ይሁን በሌላ መስመር የሙስሊሞቹን ትግል ብንደግፈም፤ ድጋፋችን የሚቀጥለው ግን የኛን ብሄራዊ የጋራ ትግል እስካገዘና፤ በመጨረሻ እንደ ሀይማኖት ቡድን የሚያደርጉት ትግላቸው በኛ የጋራ ጥቅም ላይ ችግር እስካልጋረጠ ድረስ ነው። የሙስሊሙ አንድ ወጥ ፖለቲካዊ ሀይል ሆኖ መውጣት፤ ሀይማኖታችንን ሳይሆን ዜግነትን ብቻ መሰረት አድርገን ለምንንቀሳቀስ ሀይሎች ጠንቅ ነው። በተለያየ ሀይማኖት ተከታዮች መካከል ያለውን አለመተማመንና ጥርጣሬም ያባብሳል። በስድስት ከተሞች ከሚካሄዱ ስድስት የኢሳት 3ኛ አመት ልደት ዝግጅቶች ላይ በአምስቱ ላይ፤ ኢሳት ሙስሊሞችን ብቻ እንግዶች አድርጎ መጋበዙ የኢሳትንም ጥቅም በሀይማኖቶች መካከል ያለውን ጥርጣሬና ፍራቻም ከግምት ያስገባ አይደለም።

6-የሙስሊሞቹን ትግል ስንደግፍና ከሙስሊሞቹ ጎን ስንቆም፤ ሀይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፤ መንግስት Secular ይሁን፤ የሚለውን መሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አምነንበት፤ የመንግስትን ጣልቃገብነት በኦርቶዶክሱም ሆነ በእስልምናው ሀይማኖት ስለቀመስነው ነው እንጂ፤ የሙስሊሞች አንድ ፖለቲካዊ ሀይል ሆኖ መውጣትን ተቀብለነው አይመስለኝም። መንግስት በማናቸውም ሀይማኖቶች ጉዳይ ገብቶ መፈትፈት የለበትም ከሚለው መሰረታዊ ሁላችንንም ከሚያስማማ የሰለጠነ ሀሳብ በመነሳት ነው። እንጂ ሙስሊሞች ተደራጅተው፤ አንድ የፖለቲካ ሀይል እንዲሆኑ የማድረግ ፖለቲካዊና አገራዊ ግዴታ አለብን ከሚል የሀላፊነት ስሜት በመነሳት አይደለም የሙስሊሙን ትግል የምንደግፈው።

7-እንግዲህ ጫፍ ጫፉን እንደሰማሁት ከሆነ፤ የኢትዮጵያ ተራማጆች መንግስትና ሀይማኖት ይለያዩ ሲሉ ትግል የጀመሩት ከዛሬ 50-60 አመታት በፊት ነበር። ያ ትግላቸው ተሳክቶ መንግስትና ሀይማኖት ካለፈው የ66 አብዮት ጀምሮ ተለያይተው ከርመውም ነበር። እነሆ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ፤ ላለፉት 20 ምናምን አመታት ደግሞ መልሶ ከሀይማኖት ተቋማት ጉያ አልወጣም ብሏል። አሁንም መንግስትና ሀይማኖት ይለያዩ፤ መንግስት በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ አይግባ ስንል ያ ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሞቱለት መርህ ይከበር ማለታችን ነው። መንግስት በኦርቶዶክሱም ይሁን በሙስሊሙ፤ በመጅሊስም ይሁን በሲኖዶስ፤ ጣልቃ አይግባ ማለታችን ነው። በሙስሊሙም አይግባ ስንል፤ መንግስትና ሀይማኖት አይለያዩ ማለታችን ነው እንጂ ሙስሊሞች ወይም የማናቸውም ሀይማኖት ተከታዮች ፖለቲካዊ ሀይል ሁነው ይውጡ ማለታችን አይደለም።

8-ይሄ የአምስቶ ከተሞች የሙስሊም መሪዎች ብቻ እንግዶች ሆነው የሚገኙበት አካሄድ ግን፤ ሙስሊሞች ተጽአኖ መፍጥር የሚችሉ አንድ ትልቅ የፖለቲካ ቡድኖች አድርጎ የመፍጠር አዝማሚያ የያዘ ነው። ያ አንደኛ መንግስትና ሀይማኖት ይለያዩ የሚለውን መርህ ይሽራል፤ ምክንያቱም ሀይማኖት በመንግስት ጣልቃ እንዲገባ ሊያደርግ ይችላልና። ሁለተኛ፤ ያንን ሚዛናዊ የሚያደርግ ወይም የሚፎካከር ጠንካራ የኦርቶዶክስም ይሁን የፕሮቴስታንት ድርጅት በሌለበት ሁኔታ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሙስሊሞች ብቻ ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ጠናካራ የፖለቲካ ጎራ ሆኖ መውጣት ለኢትዮጵያ አደጋ ይጋብዛል። ኢሳትም፤ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ ከመዘገብና ከማጋለጥ አልፎ፤ አስተዳደሩ ሙስሊሞችን ብቻ የክብር እንግዳ አድርጎ ወደመጋበዝ ሲያመራ ማንም ህጻን ሊያደርገው የማይሳነውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።መንገስት ሴኩላር ይሁን ስንል፤ ይሄንን መንግስት ለመጣል የምፈልግ ሀይሎችም ሴኪውላር መሆን አለብን። እንጂ፤ የምንሰራው ስራ በሀይማኖታዊ አንድምታ እንዲተረጎም አድርገን መሆን የለበትም።

9-የኢሳት ሶስተኛ አመት ክብረበኣል ስግጅቶች ላይ ከስድስቱ ከተሞች በአምስቱ የተጋበዙት፤ ከታወቁቱ መደበኛ እንግዶች በስተቀር፤ በአትሌትነት፤ በሯጭነት፤ በሙዚቀኛነት፤ በደራሲነት፤ የማንንም ሀይማኖት በማይወክል በፖለቲካ መሪነት አይደለም የተጋበዙት። በጎበዝ የሀይማኖት መሪነታቸው የምናውቃቸው ሙስሊሞች ከሚኖሩበት ከተማ ውጪ በክብር እንግድነት ኢሳትን ወክለው መጋበዛቸው ብዙዎችን ግራ ሊያጋባ፤ ሊያሸሽም ይችላል። እነዚህን ሰዎች በመጋበዝ ልናመጣ ያሰብነው ትርፍ፤ በግልጽ ላንሰፍረው የማንችለው ትልቅ ኪሳራ እንደሚያመጣብን፤ አደገኛ አካሄድ እንደሆነም አላስተዋልንም የሚል ራእይ ተገልጾልኛል። ተደርጎ ቢሆን ኖሮ፤ የጋዜጠኛው ሳዲቅ መጋበዝ አይከነክንም። በጋዜጠኝነት ኢሳትን ሲረዳ የቆየ ሰው ነውና፤ ልክ ሲሳይ በአጋጣሚ ለኢሳት የሚሰራ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ጋዜጠኛ እንደሆነው ወይንም ታማኝ ለኢትዮጵያ የቆመ ኢሳት ውስጥ የሚሰራ ክርስቲያን እንደሆነው፤ ሳዲቅም በቅጥርም ባይሆን በፈቃደኝነት ለኢሳት የሚያገለግል ሀይማኖቱ እስልምና የሆነ ጋዜጠኛ ነው። አሁን የሆነው ግን ያ አይደለም።

10-የነጂብና የኦማር፤ እንዲሁም የመንሱር ሁኔታ ግን ግራ ገብቶኛል። በግሌ ከነጂብም ይሁን ከማናቸውም ሙስሊሞች ጋር ምንም ችግር የለብኝም። ዞሮ ዞሮ ግን ነጂብና ካሊድ የሀይማኖት መሪ ናቸው። ነጂብ የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን። ከዚህ ቀደም የሚጋበዙትም ይሁን አሁን እነሱን የሚያጅቡት የኢሳት ሰዎች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወክለው ነው የሚመጡት ከሚል ግምት ካልተነሳን፤ ወይንም እነታማኝና ሌሎች “ሜይንስትሪም” የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ኦርቶዶክሱን ይወክላሉ የሚል ያልተጻፈ ግምት ከሌለ በስተቀር፤ ታማኝም ይሁን ሻምበል፤ አበበ ገላውም ይሁኑ አበበ በለው ለኢሳት ዝግጅቶች የሚገኙት በዜግነት እንጂ በሀይማኖት አይደለም። ኦርቶዶክስን ወክለው አይደለም። ስለዚህ የሄኖክና የታማኝ፤ የሻምበልና የሲሳይ መገኘት የሙስሊም ሀይማኖት መሪዎችን መገኘት አያካክሰውም።

11-ወዳጄ ታማኝ፤ ከዚህ ቀደም በስህተት ሙስሊሞቹን የካሰ መስሎት በልጅነቱ የክርስቲያኑ በኣል ሲከበር ስለሙስሊሞች በአል አለመከበር የተናገረው ንግግር በየዋህነት ቢታለፍም፤ በምንም መልኩ ግን ታማኝ እንደ ኢትዮጵያዊ እንጂ የክርስትና እምነት ተከታዮችን ወክሎ የሰነዘረው የይቅርታ ንግግር አይመስለኝም። እኔና ታማኝ ኦርቶዶክሶች ብንሆንም ኦርቶዶክሶችን አንወክልም። እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ እነ ነጂብ ትናንትም ዛሬም ከኢሳትም ጋር ያገናኛቸው የሀይማኖት መሪዎች መሆናቸው ነው። የሀይማኖት መሪዎች ከጋበዝን ደግሞ ቢመጡም ባይመጡም የኦርቶዶክሱንም የፕሮቴስታንቱንም፤ የይሁዲውንም፤ የካቶሊኩንም ነው እንጂ፤ በምን መስፈርት ነው የሙስሊሞቹን ብቻ የምንጋብዘው? ይሄ አደገኛና መታረም ያለበት አካሄድ ነው።

12-እንደምረዳው፤ እንደሚመስለኝም፤ ኢሳት የሙስሊሞቹን እንቅስቃሴ ሌት ተቀን የሚዘግበው፤ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ላይ በመንግስት የሚፈጸመው ኢፍትሀዊነት ሁሉንም ኢትዮጵያዊና የሰው ልጅ ስለሚመለከት ነው እንጂ፤ ብዙዎች የነቁም ያልነቁም የሙስሊሙን እንቅቃሴና አካሄድ በጥርጣሬ የሚመለከቱ ስጋት የገባቸው ኢትዮጵያዊያን የሉም ማለት አይደለም። ያንን እኔ ራሴ ሌላው ቢቀር ኢሳት ውስጥ በምሰራበት ወቅት ከሚደርሱን የስልክና የኢሜል መልእክቶች እረዳለሁ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንደ ኢሳት ያለ ለሁሉም ኢትጵያዊያን በእኩልነትና ፍትሀዊነት ላገለግል ቆሜያለሁ የሚል ተቋም፤ ዝግጅቶችን ሲያዘጋጅ በክብር እንግድነት ስለሚጋብዛቸው ሰዎች ማንነትና በህዝብ ዘንድ ሰለሚፈጥሩት ስሜት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ከስድስት ዝግጅቶች በአምስቱ ላይ እነ ነጂብን ሲጋብዝ ሊፈጥር የሚችለውን አንድምታ፤ ሊያሸሽ የሚችለውን ህዝብ ማሰብ አለበት። ኢሳት ደግሞ የሙስሊሞችና የኦርቶዶክሰቶች ብቻ ሳይሆን፤ ለአገር ያላቸው ተቆርቋሪነት ጎዶሎ ቢሆንም እንኳን፤ የጴንጤዎችም ጭምር ነው። ወይም ነው ብለን ነው ማሰብ ያለብን። ዝግቶቹ በተለያየ አጋጣሚ የተዘጋጁ ቢሆኑ አይገርምም። ነገር ግን ሆን ተብሎ ባንድ ላይ ታስቦበት ይሄንን ቅርጽና አንድምታ እንዲይዝ የተዘጋጀ ይመስላል።

13-መቼም በነካ እጄ ለመጨመር ያህል፤ ከላይ እንዳልኩት፤ መንገስት ሴኩላር ይሁን ስንል፤ ይሄንን መንግስት ለመጣል የምፈልግ ሀይሎችም ሴኪውላር መሆን አለብን ማለቴ ነው። እንጂ፤ የምንሰራው ስራ በሀይማኖታዊ አንድምታ እንዲተረጎም አድርገን መሆን የለበትም። በመሰረቱ የሀይማኖት ስራ በሰውና በእግዚአብሄር መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ነው፤ የፖለቲካ ዓላማ ደግሞ በሰውና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ነው። የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች ባሉባት አገር፤ ሀይማኖት የሰውና የሰውን ጉዳይ እንዲዳኝ መጋበዝ የለብንም። ሀይማኖት በሰውና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚዳኘው ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ማሰደር ሲጀምር ነው። ተጽእኖ አሳዳሪውን ሀይማኖት (በኛ አገር፤ እስልምናን ሊሆን ይችላል) የሚገዳደር ወይም የሚያርቅ በሌላ ሀይማኖት ዙሪያ የተደራጀ ሀይል (ምሳሌ ኦርቶዶክስ ወይንም ፕሮቴስታንት) ከሌለ፤ የዚያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሀይማኖት (እስልምና) አንድ ወጥ በሀይማኖት ዙሪያ የተሰባሰበ ሀይል ወይም ቡድን ሆኖ መውጣት ለሁላቸንም አደጋ ነው። ኢሳት ያንን አደጋ መከላከል እንጂ ማበረታተት የለበትም።

14-መቼም የሆነ ሆኗል፤ ድስት ተጥዷል፤ ጠላም ተጠምቋል፤ ጠጅም ተጥሏልና፤ የተጋበዙት ሰዎች ይሰረዙ፤ ወይንም አቡነ ፊሊጶስን ፈልጋችሁ ደባልቁ ብለን አንጮህም። ይሁን እንጂ፤ ለወደፊቱ ይሄ እንዳይደገም ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ የምንቆጣም እንኖራለን።

15-ለነገሩ፤ እሁን እነ ሌንጮ ለታ፤ እነ ዲማ ነጎ፤ ይሄን የመሰለ ፖለቲካዊ ጮማ አዋጅ ይዘው አንድነታችን ደጅ ላይ ቆመው፤ እጣ ፈንታችን የሚወሰነው ከኢትዮጵያዊነት ታዛ ስር ነው እያሉ አዋጅ ሲነግሩ፤ ሲሆን ሲሆን ለቀጣዮቹ ወራት እነሱን ብቻ፤ ካለበለዚያም ከሌሎች ጋር እየቀየጥን የአገራችንን ነገር መምከር ነበር እንጂ፤ ሀይማኖታዊ መሪዎች ላይ ማተኮር አልነበረብንም። ለወደፊቱ ጥንቃቄ ይደረግ። የኢሳት አስተዳደርን ለዛሬ ምረነዋል። ለወደፊቱ ይታረም።

እኛው ነን። ታሰበ፤ ተጻፈም፤ በአገረ-ካናዳ፤ ቶሮንቶ፤ ሚያዚያ፤ 2005/2013

ደብረ ዘይትና አባ ማትያስ –በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ዘር ማጥራትን ያህል ወንጀል ፈጽሞ ይቅርታ መጠየቅ ፌዝ ካልሆነ ድራማ ነው! ግርማ ሞገስ

ፍኖተ ነጻነት እትም 72 ከዜናና ልዩ ልዩ መጣጥፍ ጋር

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>