Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ዓባይ እንደ ዋዛ–ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ዓባይን ለመታደግ ይቻላልን? አክሎግ ቢራራ (ዶር)


አቡጊዳ –ሲቀሰቅሱ የታሰሩ የአንድነት አባላት ተፈቱ ፤ ቅስቀሳው ተጧጡፏል( ፎቶዎችን ይዘናል)

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ ከትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን ጀምሮ፣ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች፣ በየመንደሩ በስፋት ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለከትል። አልፎ አልፎ ፖሊስ ከፈጠራቸው መጠነኛ ችግሮች በስተቀር፣ ቅስቀሳዉ እስከአሁን በጥሩ ሁኔታ እየተደረገ እንዳለም ለማረጋገጥ ችለናል።

ትላንት በቅስቀሳ የተሰማሩ ስድስት አባላት ሜክሲኮ አካባቢ በፖሊስ ታግተው እንደነበረ መዘገባችን ይታወቃል። እስረኞቹ ፣ አንድነት የጠራዉ ሰልፍ ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን በማስረዳት፣ ትላንትናዉ ከእሥር ቤት እንደተለቀቁም አረጋግጠናል።

በዛሬው ቀን ደግሞ በካሳንቺስ አካባቢ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 6 የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ አዛርያ መላኩ ሰፊው መኮንን ፣ ኤፍሬም ሰለሞን፣ በየነ አበበ፣ አበበ ቁምላቸው፣ ሻ/ል ክፍሉ በዳኔ ስኬታማ የቅስቀሳ ተግባራቸውን በሚያደርጉበት ጊዜ በፖሊስ ታግተው ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የነበረ የነበረ ሲሆን ፣ እነርሱን ለጥቂት ሰዓት በእሥር እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ተፈተው ወደ ቅስቀሳቸው ተሰማርተዋል።
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ና በልደታ አካባቢ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ከነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል ኃይሉ ግዛው፣ ወርቁ አንድሮ እና ቴዎድሮስ ገብሬ በፖሊስ በፖሊሲ ታግተው ወደ ወህኒ ከተወሰዱ በኋላ ተፈተዋል።

zzudj10

zzudj9

zzudj8

zzudj7

zzudj6

zzudj5

zzudj3

zzudj2

zzudj1

አቡጊዳ –የአንድነት ፓርቲ ለዞን ዘጠኞች ያለውን አጋርነት ገለጸ

$
0
0

አንድነት ፓርቲ ትላንት ሚያዚያ 21 ቀን ባወጣዉ መግለጫ በዞን ዘጠኖች እና ጋዜጠኖች ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ተግባር አዉግዟል። አገዛዙ ሆን ብሎ በአገራቸዉ ጉዳይ ላይ በተለይም ወጣቶችና የተማሩ እንዳይሳተፉ ለማስፈራራት ያደረገዉ እንደሆነ በመገልጽ እስረኞቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።

«ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁትን ወጣት ጋዜጠኞች ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚሸረሽር እንደሆነ እናምናለን፡፡ አፈናው ግን ሌሎችን በሺዎች የሚቆጠሩ ብሎገሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚፈጥር አንጠራጠርም» ሲል ያተተው የአንድነት መግለጫ መንግስት ዞን ዘጠኞችን በማሰሩ ሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ የሰባአዊ መብት ተሟጋቾችን የሚፈጠር እንደሆነ ገልጿል።

አንድነት በመግለጫ፣ ዘላቂው መፍትሄ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል አፋፍሞ መቀጠልና በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ አስምሮበታል።

የአንድነትን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

አቡጊዳ –በ10 ብር ከገበሬው ተነጥቆ በ19 ሺህ ብር እንደሚሸጥ አንድነት አጋለጠ (በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ የአንድነትን መግለጫ ይዘናል)

$
0
0

ኢሕአዴግ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ፣ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ሕግ ወጥና ኢሰብአዊ ጥቃት አወገዘ። ዜጎችን የሚያምኑበትን የመናገር ሙሉ መብት እንዳላቸው ያስቀመጠው የአንድነት መግለጫ፣ ተቃዉሞ የሚያስሙ ወገኖች ሊደመጡ እንጂ ሊደበደቡና ሊታሰሩ እንደማይገባም ይገልጻል።

አንድነት፣ በቅርቡ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ፣ አዲስ አበባን ጨመሮ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢሕአዴግ መሬትን እንደ መጨቆኛና መበዝበዣ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት እንዳለ የሚገልጸው የአንድነት መግለጭ፣ ከድሃው ገበሬ አሥር ብቻ በመስጠት የነጠቀዉን መሬት በ 17 ሺህ ብር በጨረታ እንደሚሽጥ እና ልማት ሳይሆን ገበሬዉን በማፈናቀልና በማደህየት የሚደረግ ዘረፋ እያደረገ እንዳለ ለማሳየት ሞክሯል።

ከጥቂት አመታት በፊት በመቀሌ ፣ በተለይም ከኤርትራ የመጡ ስደተኞች ከሚኖርባቸው ቤቶች፣ የሚኖሩበት አካባቢ ለልማት ያስፈልጋል ተብሎ በሃይል እንዲፈናቀሉ መደረጉ፣ በጋምቤላ ደግሞ ከመሬት ጋር በተገናኘ በሺሆች የሚቆጠር በአገዛዙ በግፍ መገደላቸዉ ይታወቃል። በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ በአምቦ አካባቢ ፣ በወለጋ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ቦታዎች ፣ ዜጎች «ይሄ አገራችሁ አይደለም» በሚል፣ ከአንድ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉበት ሁኔታ እንዳለ በስፋት ተዘግቧል።

የአንድነት ፓርቲ በመገለጫዉ፣ የታሰሩ የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኳይ ተፈተዉ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥይቋል።

በአንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች አካባቢ «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት» የሚሉ፣ በአንዳንድ ዉጭ ባሉ አክራሪዎች የሚሰማ መፈክር በስፋት ሲስተጋማ እንደነበረ፣ ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የኦሮሞ ተማሪዎች በሚያነሱት ጥያቄ ላይ ቅሬታ እንዳደረባቸው በመግልጽ እየጻፉ ነው።

በኦሮሚያን እና በአዲስ መካከል ግዛቱ የትና እንዴት መሆን እንዳለበት፣ የአንድነት ፓርቲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። እንደዚያም ቢሆን ግን ፣ ፓርቲዉ አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሰረተዉ ፌዴራል አወቃቀር፣ ያለ ሕዝብ ፍቃድ በጉልበት በሕዝቡ ላይ የተጫነ በመሆኑ፣ እንደገና ቋንቋን ጨምሮ፣ የሕዝቡን አሰፋፈር፣ ጂዮግራፊን፣ ኢኮኖሚን ፣ የሕዥቡን ፍላጎት እንደኢሁም ሌሎች ነጥቦች ባካተተ መልኩ እንደገና መዋቀር አለበት እንደሚያምን በፖለቲካ ፕሮግራሙ በግልጽ አስቀምጧል። ለፓርቲዉ ቅርበት ያላቸው እንደሚናገሩት፣ አሁን በኦሮሚያና በአዲስ መካከል የተፈጠረው ዉዝግብ አሁን ያለው ፌደራል አወቃቀር ያመጣው ጣጣ እንደሆነ በማስረዳት፣ የፌደራል አወቃቀሩ እንደገና ፣ ሁሉን አቀፍና ዴምክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከተዋቀረ፣ ብዙ ችግሮች እልባት እንደሚያገኙ ይናገራሉ።

የአንድነት ፓርቲ ሙሉዉን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

ኦፌኮ –የስርዓቱ አራማጆች 30 እና 40 ካርታ እየተረከቡ ሽጠው ፎቅ እየሰሩ ነው (በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ የኦፌኮን መግለጫ ይዘናል)

$
0
0

በዶር መራራ የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጠቃለላቸዉን በመቃወም መግለጫ አወጣ።

ኦፌኮ በመግለጫው፣ ፣ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፓላን፣ በልማት ስም የሚደረግ የመሬት ወረራ ብሎታል። በሕገ መንግስቱ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ እንደሆነ መገለጹን የገልጸው መግለጫው፣ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ሊኖር ስለሚገባዉ ግንኙነት በተመለከተም ይወጣል የተባለው ዝርዝር ሕግ እስከ አሁን ድረስ፣ ይኸው ለሃያ አመት እንዳልወጣ ያትታል።

« በገጠር በኢንቨስትመንት ስም የኦሮሞ ገበሬ ማሳዉን ያለ በቂ ካሳና ዘላዊ የሥራ ዋስትና እየተነጠቀ ከመሬቱ እየተነቀለ ነው። በከተማም ነባር ባለይዞታው ቤቱ እየፈረሰ ያነበቂ ካሳና ዘላዊ ዋስትና ለድህነት ኑሪ እየተዳረገ ይገኛል። በአንጻሩም ጥቂት የስርዓቱ አራማጆችና ደጋፊዎች በገጠርም ሆነ በከተማ ቦታዉን እየተመሩ በዘመድ ወዳጅ ስም 30 እና 40 ካርታ እየተረከቡ ሽጠው በሃብት ላይ ሃብት ሲያካብቱ ይታያል። በኢንቬስትመንትናአ ልማት ስም ደግሞ ጥቂት ባለሃብቶች በሊዝ መሬቱን እየገዙ በአካበቱት ሃብት ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ሲገነቡ ይታያሉ። መሬቱንና ሃብቱን በግፍ የተቀማው ብዙሃኑ ሕዝብ ግን ለከፋ ድህነት ተጋልጧል» ያለው ኦፌኮ በመግለጫው፣ የአገዛዙ ጥቂት ባለስልጣናት፣ መሬትን እየሸጡ ትክቅ ዝርፊያ እያደረጉ እንደሆነም መግለጫ ይከሳል።

በጋምቤላ ፣ በባህር ዳር ፣ በትግራይ ….በኢንቨስትመንት ስም ዜጎች እንደተፈናቀሉ፣ በአምቦ አካባቢ፣ በጉዱ ፈርዳ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ « ከኛ ብሄር ብሄረሰብ አይደላችሁም። ይሄ አገራችሁ አይደለም» በማለት ዜጎችን በግፍ የማባረር የዘር ማጽዳት ወንጀሎች እንደተፈጸሙ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል።

ኦፌኮ አሁን በኦሮሞ ገበሬዎች ላይ ደረሰ በሚለው ግፍ እንደተቆረቆረ፣ በሌሎች ዜጎች ላይ አሳዛኝ ክስትቶች ሲፈጸሙ ፣ በተለይም በኦሮሚያ ዉስጥ ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች በሚለው፣ በኦሮሚያ ሕግ መንግስት ላይ በተቀመጠው ፖለቲካ ምክንያት፣ ኦሮሞ ያልሆኑ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠሩና ፣ «አገራችሁ አይደለም» ተብለው ሲፈናቀሉ፣ መግለጫ የሰጠበት ሁኔታ እምብዛም እንዳልነበረ የሚናገሩት ተንታኞች ፣ በኦፌኮ መግለጫ የተነበበው፣ ዜጎችን የማፈናቀል ተግባርን የመቃወም ሁኔታ፣ በሌሎች ወገኖች ላይ ሲደርስ መሰማት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

ኦፌኮ የመድረክ አባል ድርጅት ሲሆን፣ አሁን ያለዉ የፌዴራል አወቃቀር እንዳይለወጥ፣ መሬትም የመንግስት መሆን አለበት ብሎ የሚከራከር ደርጅት እንደሆነ ይነገርለታል። ሌላው የመድረክ አባል የነበረዉ አንድነት፣ በቅርቡ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የደረሰዉን ግፍ አዉግዞ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በፌዴራል አወቃቀርን እና በመሬት ባለቤትነት ዙሪያ ከኦፌኮ ጋር ልዩነት እንዳለው፣ በዚህ ምክንያት በመድረክ ዉስት ዉህደት ሊፈጠር እንዳልተቻለና አንድነት ከመድረክ በተግባር የተለየ፣ በኦፌሴል ግን ሊለይ የደረሰ ድርጅት እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው።

የኦፌኮን ሙሉ መግለጫ በቁቤና በአማርኛ

OFC_letter_April2014_6
የኦፌኮን ሙሉ መግለጫ በቁቤና በአማርኛ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

አቡጊዳ –የአምቦ ከተማ ተቃጠለች –ስድስት ተማሪዎች ተገደሉ

$
0
0

በተማሪዎች ዛሬ በተቀሰቀሰው ረብሻ፣ ከስድስት በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እንደተገደሉ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገበ።

ተማሪዎቹ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ዞኖች በአዲስ አበባ ስር መሆኗ በመቃወም ሲሆን ሰልፍ የወጡት፣ በተነሳው ግጭት ሶስት በከተማ ያሉ ፎቆች ተቃጥለዋል። ከተቃጠሉት መካከል አንዱ ባንክ እንደሆነ ተዘግቧል።

አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት የረሃብ አድማ ላይ ነው፤ በቃሊቲና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!! ለሕዝቡም ጥሪ አስተላልፈዋል! -ፍኖተ ነፃነት-

$
0
0

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡

በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል የሰየመውና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡1554590_628565093895095_9136488348360005387_n

aacarudj3

images

የአንድነት አዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢና ጋዜጠኛ ነብዩን ጨምሮ 11 አባላት ታሰሩ –ቅስቀሳዉ ግን ቀጥሏል

$
0
0

የአዲስ አበባ አስተዳደር እውቅና የሰጠውን የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑን በማሰር ቅስቀሳውን ለማስተጓጎል እየሞከረ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው።፡ቅስቀሳው ከጽ/ቤት ተነስቶ በ4ኪሎ አሚሪካ አምባሲ፣ መነን ት/ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፒያሣ፣ ቸርቸር ጎዳና፣ ጥቁር አንበሳ፣ ፍልውሃ፣ ቤተመንግስት፣ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አቶ ዘካሪያስ የማነ ብርሃን፣ ዘላለም ደበበ፣ ነብዩ ኃይሉ፣ ነፃነት ዘገየ የሚገኙበትን ቡድን «ወረቀት እንድትበትኑ እንጂ የመኪና ቅስቀሳ እንድታደርጉ አይደለም» በሚል ካዛንቺስ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰሩ የፖሊስ ጣቢያው ኮማንደር ማዘዙን ለማወቅ ተችሏል። «ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል» እያሏቸውም ነው።

ብሮሸርና ፍላየር የሚያሰራጩ ወደ ቦሌ የተጓዙ አባላት መሳይ ትኩ፣ ማቲዎስ አርጉና አያሌው ዳርምያለውን ጃፓን ኤምባሲ (ጤና ጣቢያው) አካባቢ ባለው ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል፡፡

ወደ ጎተራ ለመኪና ቅስቀሳ የተንቀሳቀሰው ቡድን አባላት ካሣሁን ገ/ሚካኤል፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ኤፍሬም ሰለሞንና አሸናፊ አሳመረውን ጎተራ ፔፕሲ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል።
አቶ ዘካርያስ የማነአብ ሰልፉ ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሊቀመነበር ሲሆን፣ ነብዩ ኃይሉ ደግሞ የፍኖት ነጻነት ዋና አዘጋጅ ነው።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት አስተዳደሩ ለሰልፉ የሰጠዉን የ እውቅና ደብዳቤ በማስየት ፣ የፖሊስ ድርጊት ሕግ ወጥና የሚይስጠይቅ መሆኑን በመገልጽ እስረኞችን ለማስፈታት እየሞከሩ ነው።
የአንድነት ፓርቲ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀሳቅሾችን ያሰማራ ሲሆን፣ ከአንድ መቶ አምሳ ሺህ በላይ በራሪ ወረቀቶች መታደላቸውንም ለማረጋገት ችለናል።
የአዲስ አበባ ነዋሪም «እሁድ እንወጣለን አይዟችሁ በርቱ» በማለት ቀስቃሾቹን እያበረታቱ እንደሆነ ከስፍራኡ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

aaudjpriso1

aaudjpris2

aaudjpris3

aaudj_pri1

aaudjpris4

aaudjpri5


ፍኖት –በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች፣ የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!!

$
0
0

እስረኞቹ ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል!!

በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ «የእሪታ ቀን» በሚል መሪ ቃል የሰየመውንና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት፣ ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም፣ ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በቃሊቲ እና በዝዋይ ከታሰሩ የሕሊና እስረኞች መካከል፣ ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋ፣ ጋዜጠና ርዮት አለሙ፣ አቶ አንዱዋለም አራጌ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ ጀነራል አሳምነው፣ አቶ አበበ ቀስቶ እንዲሁም ሌሎች በርካታኦች ይገኙበታል።

አቡጊዳ –እሁድ ሚያዚያ 29 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በጊዶሌ እንደሚደረግ የሚሊዮኖች ድምጽ አስታወቀ

$
0
0

አንድነት ፓርቲ፣ በአዲስ አበባ ሚያዚያ 29 ለሚያደርገው ሰላምዊ ሰልፍ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል። የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ፣ በአገሪቷ ክፍሎች ሁሉ ሕዝቡን ለመብቱና ለነጻነቱ ለማደራጀትና ለመቀስቀስ በበርካትከ14 በሚበልጡ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚይደርግ ይፋ አድርጎ በነበረው መሰረት ፣ የአዲስ አበባ ሰልፍ በሚደረግበት ቀን፣ በደቡብ ክልል በደራሼ ወረዳ የጊዶሌ ከተማ ታልቅ ሰላምዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ታውቋል።

ሰልፉ እንዲደረግ በዋናነት የጠየቀዉ ህዝቡ ሲሆን፣ አስፈላግዊ ዝግጅት እንደተደረግም ለማወቅ ተችሏል። የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባላት ወደ ስፍራዉ ነገ እንደሚሄዱ የተገልጸ ሲሆን፣ የደራሼ ሕዝብ በርሱ አነሳሽነት ለመብቱን ለነጻነቱ መነሳቱ ለብዙዎች ትምህርት ሰጪ እንደሆነም ብዙዎች ይናገራሉ።
gidole
ወደ ጊዶሌ ከሚሰማሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራር መካከል፣ የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ አባልና የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ስዮም እንዲሁም የምእራብ ቀጠና፣ የአንድነት አደራጅ፣ የፓርቲዉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል፣ አቶ ብርሃኑ ይገኙበታል።

በአዲስ አበባ የሉ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃዉሞ አሰሙ – (ቪዲዮ ይዘናል)

$
0
0

አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች፣ ተቃዉሞ እንዳሰሰሙ ገዳ.ኮም ድህረ ገጽ ዘገበ። ተማሪዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን ፣ቁጥራቸው ከአምሳ እስለ መቶ እንደሚጠጋ በቪዲዮም የሚታየው ምስል ያመለክታል።

ተማሪዎቹ ያሰሟቸው የነበረ መፈክሮች በእንግሊዘኛ እና በአፋን ኦሮሞ ብቻ የነበረ ሲሆን ከመፍክሮቹም ዉስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ነበሩ፡

Our rights should be respected !
Our freedom should be respected !
Stop killing oromos !
Stop killing students !
We need justice, We need democracy !
Oromo is not inferior !

ተማሪዎች ሰልፉን ሲያደርጉና ተቃውሟቸዉን ሲያሰሰሙ ከፖሊሲ ጋር የተፈጠረ ግጭት ስለመኖሩ ብዙ የተዘገበ ነገር እየለም።

ትላንት በአምቦ ከተማ በተነሳዉ ረብሻ ስድስት ሰላምዊ ዜጎችን እንደተገደሉና ሶስት ፎቆች እንደተቃጠሉ የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወቃል። ዛሬ በወጡ የተለያዩ ዘገባዎች፣ በአምቦ ከ18 በላይ ፣ ስምንቱ የሚሆኑት ተማሪዎች፣ በጥይት እንደተገደሉ የሚያትቱ ዜናዎ በስፋት እየተዘገቡ ነው።

በተያያዘ ዜና በጊምቢ፣ ወለጋ፣ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ላይ ጥቃት እንደደረሰም የሚጠቁሙ ምንጮች ደርሰዉናል። ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን ባለቤትነት፣ ሥር ያሉ ሱቆች በአክራሪዎች መቃጠሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል።

አቶ ሃብታሙ አያሌዉ ለአሜሪካ ደምጽ ሚያዚያ 26 በአዲስ አበበና ጊዶሌ በሚደረጉ ሰልፎች ዙሪያ

ጆን ኬሪ የታሥሩ እስረኞች ጉዳይ በጣም እንደሚያሳስባቸው ገለጹ (ቪዲዮ ይዘናል)

$
0
0

ከታሰሩ የዞን ዘጠኝ አባላት መካከል አንዱ የሆነው ናትናኤል ፈለቀ በቅርበት እንደሚያወቅት የገለጹት የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ፣ አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝም ጨምሮ ላገኟቸው ባለስልጣናት ፣ ጋዜጠኞችን ማሰርና የዜጎንች ነጻነትን መገደድ ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅም አሳሰበዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር አሜሪካ የቅርብ ግንኙነት እንዳላት የገልጹ ኬሪ፣ የዴሞክራሲና የሰባአዊመ ጉዳይ በጣም እንደሚያሳስባቸው ገለጸዋል። « እየተናገሩት ያለው እንዲሁ ለመናገር ያህል የተናገሩት፣ ሊፕ ሰርቪስ እንዳይሆን ! ፧ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ጆን ኬሪ፣ የሜዲያ ነጻነትና የዴሞክራሲ መብት በርሳቸውን በመንግስታቸው ዝሸንድ ትልቅ ቦታ እንዳለዉ አጠንክረው ለመግልጽ ሞክረዋል።

አዉራምብ ታይምስ፣ ጆን ኬሪ ከሰጡት አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ያቀናበረዉን ይመልከቱ

zone9_kerry1

ነገረ ኢትዮጵያ –በጎንደር ተኩስ ቀጥሏል –በግጭቱ 6 ዜጎች ሞተዋል

$
0
0

ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታ አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ቤቶችን ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን ወቅት (ከቀኑ 6፡ 43) ተኩስ እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎቹ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ በተላለፈበት ወቅት ህገ ወጥ አለመሆናቸውን፣ ካልሆነም መንግስት ቅያሬ ቦታና ጊዜ መስጠት እንዳለበት በመግለጽ አንለቅም ብለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዛሬው ቀን ግጭቱ የተነሳውም አፍራሾቹ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸውን ቤቶች ቀለም በመቀባታቸውና ህዝቡም እንዳይቀቡ በመከልከሉ መሆኑ ታውቋል፡፡

በግጭቱ ፖሊስ፣ ፌደራልና ልዩ ኃይል የተሳተፈበት ሲሆን ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የአካባቢው ወጣቶች ላይ ድብደባና እስራት እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
‹‹ወጣቶችን እንደ እንሰሳ በአንድ ገመድ አስረው እየደበደቧቸው ነው፡፡ ህዝብ በጅምላ እየታሰረ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ቢያቆምም በአሁኑ ወቅት በሶስቱም ሰፈሮች ጥይት እየተተኮሰ ነው›› ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የተወሰደው እርምጃ የጎንደርን ህዝብ በማስቆጣቱ ከዚህ የባሰ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል ሲሉም ገልጸውልናል፡፡ በግጭቱ ወቅት የመጀመሪያዋ የሞት ሰለባ የሆነችው ልዩ ኃይል ቤቷ እንዲፈርስ ቀለም ሲቀባ የተቃወመች የልጆች እናት እንደሆነችም ታውቋ፡፡

ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ከጎንደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል

የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ ከባድ ፈተና ደቅኖብናል -አብርሃ ደስታ

$
0
0

በአዲሱ የአዲስ ማስተር ፕላን በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልል ገጠር መሬቶች የአዲስ አበባ ከተማ አካል ያደርጋቸዋል። ይሄን ጉዳይ በኦሮሞ ህዝብ ባጠቃላይ በኦሮሞ ተማሪዎች ደግሞ በተለይ ዓመፅ አስነስቷል።

ማስተር ፕላኑ የገጠር ቦታዎች ማካተቱ በራሱ ችግር አይደለም። እንዳዉም ፕላኑ ኦሮምያ አልፎ መቐለም ቢያጠቃልል ደስ ባለኝ ነበር። ከተማ ቢያድግ መልካም ነው። ከተማ ሲያድግም በዙርያው ይሰፋል። ይህ ባህርያዊ ነው። ግን ችግር አለ። በኢህአዴግ ዘመን እየተስተዋለ ያለው የከተሞች ማስፋፋት ስትራተጂ አፈፃፀም ኗሪዎችን እጅግ ይጎዳል።

የገጠር መሬት ወደ ከተማ ሲገባ በዛ የሚኖሩ አርሶአደሮች ያለ ፍቃዳቸው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ። በቂ ካሳ (ክፍያ) አይሰጣቸውም። በዚህ መሰረት አርሶአደሮቹ ተቃውሞ ያሰማሉ። ይህ ጉዳይ በኦሮምያ ብቻ አይደለም የተከሰተው። በመቐለ ከተማም ተመሳስይ ችግር አለ። በመቐለ ዙርያ የሚኖሩ የእንደርታ ኗሪዎች ሁሌ ያለ ፍቃዳቸው እንደተፈናቀሉ ነው። በመቐለ ዙርያ ሁሌ ተቃውሞ አለ። ዓመፅ አለ። በመቐለ ዙርያ በዓይናለም፣ እግሪሓሪባ፣ ሰራዋት ወዘተ ያለ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ አሁን በኦሮምያ እየተካሄደ ካለው ተመሳሳይ ነው። የመንግስት አካላት ተቃውሞ ለሚያሰሙ ሰዎች የኃይል እርምጃ እየወሰዱ ይደበድቧቸዋል፣ ይገድሏቸዋል፣ ያስሩዋቸዋል፣ ያሰቃያቸዋል።

ይሄ ነገር በኦሮምያም መከሰቱ አይቀርም። ምክንያቱም በትግራይ የሚከናወን የህወሓት ተግባር በኦሮምያም በኦህዴድ መተግበሩ አይቀርም። ምክንያቱም ህወሓትና ኦህዴድ ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉና ነው። ይህን ነገር ተቃውሞ መቀስቀሱ ታድያ አይገርምም። አርሶአደሮች ኮ ከቀያቸው ሊፈናቀሉ ነው። “ገበሬዎች መሬታቸው ሽጠው ከቀያቸው እንዳይፈናቀሉ መሬት የመንግስት አድርገዋለሁ” ብሎ የሚዘፍን ስርዓት አርሶአደሮቹን ያለፍቃዳቸው ያፈናቅላል።

ሌላው ምክንያት ደግሞ የብሄር ፖለቲካችን ነው። ኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ እያራመደ እርስበርሳችን እንዳንተማመን በብሄር ለያይቶናል። ይሄ የናንተ መሬት ነው፣ ይህ ደግሞ የነሱ ነው ወዘተ እያለ በቡድን ከፋፍሎናል። በብሄሮች መግባባት እንዳይኖር እነእገሌ እንዲህ አደረጓቹ ታሪካችሁ እንዲህ ነው። መጀመርያ መምጣት ያለበት ብሄር ነው ወዘተ እያለ የብሄር ጥላቻ እንዲሰፍን ሐውልት ሰርቶልናል። ባጠቃላይ የዓመፁ ምክንያት የኢህአዴግ የጥላቻ ፖለቲካ ሰበካ ነው።

ኢህአዴግ ብሄር መሰረት ባደረገው ፌደራሊዝሙ “ይሄ መሬት የኦሮምያ ነው፣ ነፍጠኞች እንዳይወስዱባቹ ተጠንቀቁ!” እያለ ጥላቻ ሲሰብክ ከርሞ አሁን የኦሮሞ ተወላጆች “የኦሮምያ መሬት የኛ ነው። ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!” ሲሉት ግዜ ለምን የኃይል እርምጃ መውሰድ መረጠ? ኢህአዴግ ራሱ የዘራውን ነው እያጨደ ያለው።

ለማንኛውም አሁን ሁኔታው ማረጋጋት አለብን። ኢህአዴግም በጉዳዩ ራሱን መፈተሽ ይኖርበታል። የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ ከባድ ፈተና ደቅኖብናል።


ኢ.ኤም.ኤፍ –በአሃራማያ ዩኒቨርስቲ በተጣለ ቦንብ አደጋ ደረሰ

$
0
0

(ኢ.ኤም.ኤፍ) – በኦሮሚያ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ የተጀመረው ረብሻ ወደ ከተሞች እየተዘመተ መሆኑን ዛሬ ምሽት ያገኘነው መረጃ አሳውቋል። የአምቦ ዩኒቨርስቲ ረብሻ ወደ ከተማው ተዛምቶ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። በመዳ ወላቡም ከዩኒቨርስቲው አልፎ በከተማው በተነሳ ረብሻ ሶስት ሰዎች ሞተዋል።

ዛሬ ቀን ላይ ደግሞ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ኳስ ጨዋታ ይመለከቱ የነበሩ ከመቶ በላይ ተማሪዎች ላይ ቦንብ ተጥሎባቸው፤ ሰባ ያህሉ ላይ የመቁሰል አደጋ ሲደርስ አንድ ተማሪ ሞቷል። በጅማ እና በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ያልተባረሩ ወይም የሌላ ክልል ተወላጆች ላይ ትንኮሳ እና ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው።

“ኦሮሚያ ለኦሮሞ” የሚል መፈክር ይዞ የሚንቀሳቀሰው አመጽ፤ አጀማመሩ ሰላማዊ ቢመስልም፤ በውስጡ ግን በሌላው ብሄረሰብ ላይ ጥላቻን የሚያሰፋ በመሆኑ፤ በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ህዝባዊ ድጋፍን እየተነፈገ ነው።

ይህም ሆኖ የኦህዴድ እና የህወሃት ሃይሎች በተቀናጀ መልኩ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚገልጹ ተማሪዎች ላይ እየወሰዱ ያሉት የግድያ እርምጃ ብዙዎችን ቅር አሰኝቷል። በመጨረሻም “በተቃዋሚዎቹ በኩል የተነሳውን ቀላል ጥያቄ ወደ ጥላቻ የሚወስዱ አካሎችም ሆኑ የሃይል እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ የሚሰጡ ባለስልጣናት ጉዳዩ ወደከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር አንድ አፍታ ቆም ብለው ሊያስቡበት ይገባል” የኢ.ኤም.ኤፍ መልዕክት ነው።

አንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ይቀላቀሉ! (ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር)

$
0
0

ጤና ይስጥልኝ !

ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ። አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ግለሰብና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ የኢትዮጵያዊነት፣ የፍቅርና የመቻቻል ፖለቲካ ነው። አላማችን ፣ የበለፀገች፣ ልጆቿ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ልዩነት ሳይደርገባቸው እኩል የሆኑባት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መመስረት ነው።

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት፣ ግልጽነት የጎድለው፣ ተጠያቂነት የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀና የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት እንደመሆኑ፣ በሕዝብ ላይ ትልቅ በደል እያደረሰ ይገኛል። የሚከተለው የተሳሳተና ጎጂ የመሬት ፖሊሲ፣ ዜጎች፣ በልማት ስም፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው፣ ከቤታቸው እና ከእርሻ ቦታቸው በኃይል እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው። የሰብአዊ መብት ረገጣው፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ….. በግፍ መታሰራቸው፣ የኑሮ ዉድነቱ ሕዝቡ ከሚሸከመው በላይ እየሆነበት ነው።

ሕዝባችን ከዚህ የተሻለ ይገባዋል። ኢትዮጵያዉያን አሁን ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ አንቀበለም በማለት፣ ለዉጥ መጠየቅ፣ ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርብናል።

ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት የሚችልበት መድረክ ያገኝ ዘንድ፣ አንድነት፣ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እውቅና ያገኘበት፣ ሁለት ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ፣ እሑድ ሚያዚያ 26 ቀን፣ በአዲስ አበባ እና በደቡክ ክልል በምትገኝ የድራሼ/ጊዶሌ አዘጋጅቷል። የአዲስ አበባ እና የጊዶሌ ነዋሪዎች፣ በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በአክብሮት ጥሪ አቀርባለሁ

ነጻነት ነጻ አይደለም። ነጻነትን ከሌሎች አናገኝም። ነጻነትን እኛዉ እራሳችን ነን ለራሳችን ማወጅ የምንችለው። እራሳችንን በግል ካያነው፣ ምንም ማድረግ የማንችል፣ አንድ ተራ ሰው አድርገን ልንቆጠር እንችላለን። ነገር ግን ተራ ሰዎች፣ በሚሊዮን ሲቆጠሩ፣ እነርሱን ማነቃነቅ የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም። እንነሳ። ሰልፍ እንዉጣ። ድምጻችንን እናሰማ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! እራሳችንን ነጻ በማወጣት አገራችንን ነጻ እናውጣ !

እንግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያን ይባርካት

ግዛቸው ሽፈራዉ248563_216329831720502_5461084_n1554590_628565093895095_9136488348360005387_n

የአንድነት አመራሮች ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

$
0
0

ዛሬ ማለዳ ሜክሲኮ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ሊቀመንበር፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባሉ ዘላለም ደበበና ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ በፖሊስ የአስራ አራት ቀን የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ፍርድ ቤቱ የአስራ አንድ ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ በመፍቀድ በእስር ቤት እንዲቆዩ ተወስኖባቸዋል፡፡

ፖሊስ በአንድነት አባላት ላይ ባቀረበው ክስ ‹‹ለቅስቀሳ ባልተፈቀደ ቦታ ሲቀሰቅሱ አግኝቻቸዋለሁ፣የተፈቀደላቸው ለሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ለቅስቀሳ አይደለም በማለት ዋስትና እንዲከለከሉለት ደግሞ ‹‹ካልታሰሩ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ሁከት ሊፈጥሩ የሚችሉ በመሆናቸው በእስር እንዲቆዩ ይደረግልኝ››ብሏል፡፡

ተከሳሾቹ በበኩላቸው ለፍርድ ቤት ባቀረቡት መከራከሪያ‹‹ፖሊስ ባላቸው ቦታዎች አለመቀስቀሳቸውን፣ሰልፉ እውቅና የተሰጠው በመሆኑ ሁከት መፍጠር የሚለው አያስኬድም ብለዋል፡፡ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ በሸገር ሬዲዩ እየተዋወቀ ፖሊስ መቀስቀስ አትችሉም ማለቱ አስገራሚ ሆኖብኛል››ብሏል፡፡10312367_628946547190283_7908140656346366611_n

10178030_628946420523629_2210739366940698651_n

10330387_628946493856955_5799780776381331354_n

ኢቲቪ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ አላስተናግድም አለ፡፡ –ፍኖተ ነጻነት

$
0
0

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አላስተናግድም ማለቱን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ገለጹ፡፡ የህ/ግ ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ ማንኛውንም ህጋዊ አካል ወይንም ዜጋ በእኩልነት ማስተናገድ የሚገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳያቀርብ አናስተናግድም ማለቱ አንድ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ ከሚል ተቋም የማይጠበቅ እና ተቋሙ በእርግጥም የህዝብ አገልጋይ አለመሆኑን በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ ህዝብ ግንኙነቱ ገለፃ ፓርቲው ጉዳዩን በቸልታ እንደማያየው እና ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውም ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ አቶ ሰይፉ አለምሰገድና ወ/ት ሸዋዬ የማስታወቂያ ክፍል ኤክስፐርት በእጅ ስልካቸው ደውለን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የነሱን ሀሳብ ልናካትት አልቻልንም፡፡10151828_715293141862771_2319538966429951366_n

በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እሰረኞች መልዕክት አስተላፉ!! የረሃብ አድማ መምታት ጀምረዋል!!

$
0
0

በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥያቄያቸው እንዲመለስ ጫና ለመፍጠር የምግብ ማቆም አድማ ጀመሩ፡፡
አድማው ለ3 ቀን እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
ጥያቄያቸውም፡-
1ኛ የፖለቲካው ሥነ -ምህዳር እንዲሰፋና የፓርቲዎች በነፃነት የመንቀሳቀስና የመደራጀት መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣
2ኛ አፋኝ የሆኑት የመያዶች ህግ፣ የፀረ-ሽብር ህግ፣ የፕሬስ ህግ እንዲሻሩና ነፃ የሙያ ማህበራት ላይ የሚደረገው አፈና እንዲቀም፣
3ኛ በግሉ ሚዲያ ላይ የሚደረገው ማስፈራሪትና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆምና የፕሬስ ነፃነት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣
4ኛ የመከላከያ፣ የፖሊስና የደህንነት አካላት በህገ መንግሥቱ መሠረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በገለልተኝነት እንዲወጡ፣
5ኛ ፍርድ ቤቶች፣ የምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ሚዲያው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀር፣
6ኛ የፖለቲካ እስረኞች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የህዝበ ሙስሊሙ ተወካዮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣
7ኛ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶችን በተመለከተ፡-
ሀ) የሰብአዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ ማለትም በድብደባ አካል ያጎደሉና በድብደባ የሰው ህይወት ያሳለፉ የተቋሙ አባላት ህግ ፊት እንዲቀርቡ፣
ለ) በደረቅ ወንጀል ለታሰሩ እስረኞች የሚደረግ ዝውውር፣ ይቅርታ፣ ምህረት እና አመክሮ ህግ በሚፈቅደውና መድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲፈፀም፣
ሐ) በሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ‹‹ጨለማ ቤት›› በመባል በሚጠሩት የብቻ እስር ቤቶች ውስጥ የታሰሩ እስረኞች ከጨለማ ቤቶቹ ወጥተው ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲቀላቀሉ፡፡
መ) የምግብ፣ የውሃ፣ የአልባሳት፣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲሻሻል እንዲሁም እስረኞች ከሚጎበኟቸው ሰዎች በወር የሚፈቀድላቸው 1ዐዐ ብር በቂ ባለመሆኑ ክልከላው እንዲነሳ፣ የመረጃ በነፃነት የማግኘት መብታችን እንዲከበር (ሬድዩ የማዳመጥና የግሉ ሚዲያ ውጤቶች የሆኑ ጋዜጦች እንዲገቡልን) የርቀት ትምህርት መማር እንዲፈቀድ፣ ከውጭ የሚላኩልንን ፖስታዎች በአግባቡ እንዲደርሱን፡፡

8ኛ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 28 ላይ በተደነገገው መሠረት በሰው ልጆች ላይ አሰቃቂ ድብደባና አካል ማጉደል ወንጀል መሆኑን በመፃረር በሀገሪቱ ያሉ የምርመራ ጣቢያዎች በተለይም በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማእከላዊ) ውስጥ ይህንን ወንጀል የፈፀሙና እየፈፀሙ ያሉ የፖሊስና የደህንነት አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፡፡
9ኛ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ምስቅልቅል በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ብሔራዊ መግባባትና እርቅ እንዲያወርዱ፡፡
በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳት ልዩነትንና ህልውናን ጠብቆ ለጋራ የነፃነት አጀንዳ በጋራ ተባብሮ መታገል የወቅቱ ዋነኛ ጥያቄ በመሆኑ የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ተባብረው እንዲታገሉና የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም ከዚህ በላይ በዝርዝር ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ያገኙ ዘንድ ለጊዜው ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው የፖለቲካ እስረኞች ከአርብ ሚያዚያ 24 ቀን እስከ እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን የሚቆይ የ3 ቀን የረሃብ አድማ አድርገናል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

1ኛ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር 2ኛ አቶ ደረጀ አበበ 11ኛ አቶ ዩሐንስ ተረፈ
3ኛ አቶ ናትናኤል መኮንን 12ኛ አቶ መሠለ ድንቁ
4ኛ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) 13ኛ አቶ ፍቃዱ ባሳዝን
5ኛ አቶ አንዷለም አያሌው 14ኛ አቶ የገባው አለሙ
6ኛ ሻ/ል የሽዋስ ይሁንአለም 15ኛ አቶ እሱባለው አሌ
7ኛ አቶ ምትኩ ዳምጤ 16ኛ አቶ ጥላሁን ባለው
8ኛ አቶ አበበ መልኬ 17ኛ አቶ አስቻለው አራጋው
9ኛ አቶ ማንደፍሮ አካልነው 18ኛ አቶ በእውቀት ደሳለኝ
1ዐኛ አቶ ገበየሁ ብዙነህ 19ኛ አቶ ካሳሁን ጌጡ
ግልባጭ
- ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ
- ለተባበሩት መንገሥታት ድረጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መ/ቤት
- ለአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚች
- ለ Human Rights watch
- ለ Amnesty international
- ለ CPJ እና ለሀገር ውስጥና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት በሙሉ፡፡1554590_628565093895095_9136488348360005387_n

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>