Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live

ለመከላኪያ ሰራዊት ጥያቄ አለኝ…….? ከትእዝብት አድማሱ


“ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” –በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

አይ ጥቅም በበላይነህ አባተ

ጥያቄዉ የሃይማኖት ሳይሆን የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ነዉ ! አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

ምንጩ ሳዉዲ አረቢያ የሆነው፣ ከነዳጅ በሚገኝ ሚሊዮን ዶላሮች የሚደገፈውና መረቡን በአለም ዙሪያ ሁሉ የዘረጋዉ፣ የዋሃቢዝም የእስልምና አክራሪነት፣ በአለማችን ትልቅ ችግር እየፈጠረ በብዙ አገሮች አለመረጋጋትን ያመጣ እንደሆነ፣ የአለምን ሁኔታ በቅርበት የሚከታታል ያጣዋል ብዬ አላስብም። አል ሻባብ፣ አል ካይዳ፣ አንሳር አሊዝላም ፣ ቦካ ሃራም የመሳሰሉ ጸረ-ሰላምና ሽብርተኛ ቡድኖች መሰረታቸው፣ ይሄዉ ዋሃቢዝም ነዉ። ዋሃቢስቶች፣ እንኳን ከእስልምና ዉጭ ያሉ እምነቶችን ሊታገሱ ቀርቶ፣ ከነርሱ የቁራን አተረጓገም የተለየ አተረጓገም ዉጭ፣ ቁራንን የሚተረጉሙ ሌሎች ሙስሊሞችን ሳይቀር አይቀበሉም። ከነርሱ አመለካከትና እምነት ዉጭ ያሉ የሌላ እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እነርሱ ትክክለኛ ወደሚሉት እስልምና ካልመጡ በቀር «መጥፋት አለባቸው» ብለዉ የሚያምኑ ናቸዉ።

ሳዉዲ አረቢያ፣ የእስልምና ሁለቱ ታላላቅ ከተሞች (መካና መዲና) ያሉባት አገር ናት። የሳዉዲ ሙፍቲም፣ ፖፑ ለካቶሊኮች እንደሆኑት፣ ለሱኒ ሙስሊሞች መንፈሳዊ አባት ናቸው። በቅርቡ እኝህ ዋሃቢስቱ የሳዉዲ አረቢያዉ ሙፍቲ የተናገሩት፣ ስለዋሃቢዝም ምንነት በግልጽ የሚያመላክት ነዉ። «በአካባቢያችን ቤተ ክርስቲያን መሰራት የለበትም። የተሰራም ካለ ደግሞ መፍረስ በማለት ነበር ከዋሃቢዝም እስልምና ዉጭ ሌላ እምነትን ማስተናገድ እንደማይችል በግልጽ ያሳወቁት።

ከሁለት አመታት በፊት በወጣቶች እንቅስቃሴ የተነሳዉ የግብጽ አብዮት፣ ሙባረክ ከስልጣን እንዲነሱ አደረገ። ዋሃቢዝምን መመሪያዉ ያደረገዉ የሙስሊም ወንድማማቾች ድርጅት፣ በየመስኪዶቹ ስለተደራጀ በቀላሉ ምርጫዉን አሸነፈ። ሞርሲ የአገሪቷ ፕሬዘዳንት ሆኑ። አዲስ ሕገ መንግስት የመጻፍ ስራ ተጀመረ። ሕገ መንግስቱ ከሻሪያ ጋር የተገናኘ እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጀ። ክርስቲያኖችና አክራሪ ያልሆኑ ሙስሊሞች ተቃወሙ። ሞርሲ ግን እስልምናን የበላይ የሚያደርግ፣ ለሌሎች እምነቶች እውቅና የማይሰጥ ሕገ መንግስት አስጸደቁ። ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ክርስቲያኖች ባሉባት ግብጽ፣ የእስላማዊ መንግስት ተቋቋመ። ከሙባረክ አምባገነንነት ግብጽ ወደ እስልምና አክራሪነት ተሸጋገረች። የበጋዉ አብዮት ወደ ክረምት ጭጋግ ተቀየረ። ከእሳት ወደ ረመጥ ይሉታል ይሄ ነዉ።

በኢትዮጵያ የእስልምና መንግስት በኃይል ለማቋቋም የአጭርና ረጅም ጊዜ እቅድ አውጥተዉ፣ በሳዉዲዎችና ግብጾች ተረድተዉ፣ በነርሱም ሰልጥነዉ፣ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ ዋሃቢስቶች አይኖሩም ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነዉ። እነዚህን አክራሪዎችን ተከታትሎ፣ የገንዘብ ምንጫቸዉን አድርቆ፣ አክራሪነት እንዳይስፋፋ የማድረግ ሃላፊነትና ግዴታ መወጣት፣ ከማንም መንግስት የሚጠበቅ ነዉ። በዚህ ረገድ የአገሪቷን ሕግ ተከትሎ አክራሪነትን ለመከላከል የሚደረግ ማናቸዉም አይነት እርምጃን አልቃወምም።

ነገር ግን አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ሽፋን፣ የበለጠ አክራሪነትን የሚያስፋፋ፣ ለአገር የማይጠቅም፣ የአገሪቷን ሕግ የማያከብር ተግባራትን መፈጸም ግን፣ እያንዳንዱን ዜጋ ሊያሳስብና ሊያስቆጣ የሚገባ ነዉ።

በአገራችን በሙስሊሞች መካከል በተፈጠረው ችግር አማካኝነት፣ የተወሰኑ ወገኖች በሽብርተኝነት ክስ መታሰራቸዉ ይታወቃል። የነዚህን ወገኖችን መታሰር ተከትሎ ፣ ከዚህ በፊት ለአንባቢያን ባቀረብኩት ጽሑፍ ፣ የሚከተለዉን ምክር ለኢሕአዴግ አመራር አባላት አቅርቤ ነበር።

«በመስኪዶች ሰላማዊ ተቃዉሞ ማሰማት፤ የመጅሊስ አመራሮች እንዲለወጡ መጠየቅ «ሽብርተኛ» ሊያሰኝ አይገባም። በመሆኑም ከሳዉዲ አረቢያ ጋር ግንኙነት የሌላቸው፣ የዋሃቢዝም አክራሪነትን ማስፋፋታቸዉን የሚያሳይ መረጃ ያልተገኘባቸዉ፣ በአዋሊያና በመስኪዶች ሕገ መንግስቱ የሚፈቅድላቸዉን ተቃዉሞ በማሰማታቸው ብቻ የታሰሩ፣ ሰላማዊ ሙስሊም ወገኖቻችን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው። እነርሱን በማሰር የሚገኝ አንዳች ጥቅም የለም። ዜጎች ተቃዉሞ ስላሰሙ የሚታሰሩበት አሰራር መቆም አለበት። ኢሕአዴግ በዚህ አንጻር ከኃይል እርምጃዎች ተቆጥቦ ማስተዋል ያለበት እርምጃ እንዲወስድ እመክራለሁ»

በቅርቡ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አንድ ዘገባ አቀረበ። የቀረበው ዘገባ፣ የኢቲቪ ሪፖርተሮች፣ በታሰሩ ወገኖች ላይ የቀረበዉን የፍርድ ቤት ሂደት ተከታትለው የዘገቡት ዘገባ አልነበረም። በፍርድ ቤት የቀረቡ ሰነዶችን አላነበቡም። ፍርድ ቤቱ የሰጠዉን ውሳኔ አልገለጹም። ነገር ግን እጆቻቸው በካቴና ከታሰሩ እስረኞች ጋር፣ በእሥር ቤት የተደረጉ ቃለ ምልልሶችን ነዉ ያቀረቡት።

እስረኞቹ ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ። አስቀድሞ ተጽፎ እንዲናገሩ የተሰጣቸው ይሁን እዉነቱን ለማረጋገጥ አይቻልም። በመሆኑም እስረኞቹ የተናገሩትን ይዘን፣ «እንዲህ ነዉ» ወይም «እንደዚያ ነዉ» ልንል አንችልም።

ይልቅስ ብዙዎቻችንን ያሳሰበና ያሳዘነ ጉዳይ ቢኖር እስረኞቹ በመጀመሪያ ደረጃ በቴሌቭዥን እንዲናገሩ መደረጉ ነዉ። ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ወቅት፣ አስቀድሞ በፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚገባን ነገር በሜዲያ ማዉጣት፣ ሂደቱን የፍርድ ሂደት ሳይሆን የፖለቲካ ሂደት አድርጎታል።

የአገሪቷ ሕገ መንግስት ፍርድ ቤቶች ነጻ እንደሆኑ ይደነግጋል። ነገር ግን ኢቲቪ ያቀረበዉ ፕሮግራም በቀጥታ የፍርድ ሥርዓቱን የሚንድ ሆኖ ነዉ የተገኘዉ። የዜጎችን ሕገ መንግስታዊ መብቶች የሚጋፋ፣ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሳይሰጥ በፍርድ ቤት ሥራ ላይ ጣልቃ የሚገባ ጎጂ ተግባር ነዉ።

የታሰሩ ወገኖች ጥፋተኛ ይሁኑ አይሁኑ ገና ፍርድ ቤት አልወሰነም። ፍርድ ቤት እስካልወሰነ ድረስ ማንም ወንጀለኛ ጥፋተኛ ተደርጎ ሊቆጠር አይችልም። ኢቲቪ እነዚህን ሰዎች አቅርቦ ኑዛዜ ማናዘዙ በሕግም ሆነ በሞራል አንጻር ተቀባይነት የሌለዉ፣ ኢሕአዴግን እንቃወማለን የሚሉ ብቻ ሳይሆን ኢሕአዴግን የሚደግፉ ሁሉ ሊያወግዙት የሚገባ ነዉ። አንድ በሉ።

እነዚህ እስረኞች በኢቲቪ ቀርበዉ ቃለ መጠይቆችን ሲሰጡ፣ ጠበቆቻቸው በአካባቢው አለመኖራቸውን መርሳት የለብንም። ሕገ መንግስቱ ዜጎች የጥብቅና መብት እንዳላቸው በግልጽ ያስቀምጣል። ዜጎች በፍርድ ቤትም ሆነ በፖሊስ ፊት ሲቀርቡ ከጠበቆቻቸው ጋር የመመካከር፣ ጠበቆቻቸውም በነርሱ ስም ምላሽ እንዲሰጡ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸዉ። ኢቲቪ ከማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር፣ ጠበቃዎቻቸዉን አልፈው፣ በአቋራጭ እስረኞችን ማናዘዛቸዉ ትልቅ ስህተት ነዉ። ሁለት በሉ።
«እስረኞቹ ቃለ መጠይቆች ሲሰጡ በዉዴታና ነዉ ወይንስ ተገደው ?» ለሚለው ጥያቄ ግልጽ የሆነ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል። «እስረኞቹ ድብደባና ስቃይ ስለበዛባቸው ነዉ ባለስልጣናቱ መስማት የሚፈልጉት የተናገሩት» የሚሉ ወገኖች አሉ። እስረኞች መደብደባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ባይኖርም፣ አለመደብደባቸዉንም የሚያሳይ መረጃ የለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ ኢሕአዴግ ግልጽ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል። ሶስት በሉ።

እንግዲህ ከዚህ በመነሳት ነዉ፣ ኢሕአዴግን እንደግፋለን የሚሉ ወገኖች፣ በሚደግፉት ድርጅት አመራር አባላት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ የሚከተሉትን ነጥቦች የማስቀምጠዉ።

1. በኢቲቪ የተላለፈው ፕሮግራም እንዲቀናበርና እንዲተላለፍ መመሪያ የሰጡ ባለስልጣናት፣ የማስታወቂያ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሊጠየቁ ይገባል። ኢሕአዴግ ሃላፊነት የሚሰማዉ እንደሆነ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ሲናገሩ እንሰማለን። እንግዲህ ሃላፊነት ከሚሰማዉ ድርጅት የሚጠበቀዉ ለተሰሩት ስህተቶችና ጥፋቶች የአመራር አባላቱ ተጠያቂ ሲሆኑ ነዉ።
2. የታሰሩ እስረኞች በኢቲቪ ሆነ፣ ጠበቆቻቸው በሌሉበት፣ የተናገሩት ሁሉ በፍርድ ቤት እንደ መረጃ እንዳይቀርብ፣ ከጠበቆቻቸው ጋር ያለ አንዳች ገደብ እስረኞቹ መገናኘት እንዲችሉ መደረግ አለበት።
3. ከሳዉዲ አረቢያ ጋር ግንኙነት የሌላቸው፣ የዋሃቢዝም አክራሪነትን ማስፋፋታቸዉን የሚያሳይ መረጃ ያልተገኘባቸዉ፣ በአዋሊያና በመስኪዶች ሕገ መንግስቱ የሚፈቅድላቸዉን ተቃዉሞ በማሰማታቸው ብቻ የታሰሩ፣ ሰላማዊ ሙስሊም ወገኖቻችን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ያሉት ችግሮች በሙስሊሞቹ በራሳቸው እንዲፈታ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት። ቅንነት ያለበት ንግግር ብቻ ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠዉ።
ዜጎችን በማሰር፣ ዜጎችን በቴሌቭዥኝ በማዋረድና በማሳነስ አገር አትለማም። ዜጎች ጥፋተኛም ቢሆኑ የሰብአዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ ከኢሕአዴግ አመራሮች መመሪያ ተቀብለው፣ የሚደግፉት ድርጅታቸው በሚያደርጋቸው መልካም የልማት ተግባራት እንድንተባበር እንደሚገፋፉን ሁሉ፣ ድርጅታቸው የሚያደርጋቸውን ጎጂና አሳዛኝ የሰብአዊ መብት ረገጣን በአስቸኳይ እንዲያቆም በመጠየቅ፣ በአመራር አባላቱ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

በዚህ አጋጣሚ የኢቲቪን አሳዛኝ ዘገባ እንደመሳሪያ በመጠቀም፣ ጉዳዩ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ሳይሆን የሃይማኖት ጉዳይ እንደሆነ ለማቅረብ የምንሞክር ካለን፣ ጥንቃቄ ብናደርግ ጥሩ ነዉ እላለሁ። በሃይማኖት ጉዳይ ላይ «እንደዚህ ነዉ እንዲዚያ ነዉ» ብሎ፣ ለጊዚያዊ ትንሽ የፖለቲካ ትርፍ ብለን፣ የሚገነባ፣ የሚያስታርቅና የሚያቀራርብ ሳይሆን፣ ነገሮች የበለጠ ወደ ከረረ ሁኔታ የሚወስድ እንቅስቃሴ ባናደርግ መልካም ነዉ። ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ችግር ስላለን ብቻ፣ ከተቀጣጠለ ሊበርድ የማይችልን እሳት ባንለኩስ ይሻላል።

ኢሕአዴግን የምንቃወምበትና የምናወግዝበት ብዙ የተጨበጡ ምክንያቶች አሉ። እስከሚገባኝ ድረስ ግን ላለፉት 20 አመታት ኢሕአዴግ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መልካም በማድረግ እንጂ የእምነት ነጻነትን በመጋፋት አይታማም። ኢሕአዴግ የሃይማኖት ነጻነትን የተጋፋ አይመስለኝም። በኢሕአዴግ ዘመን፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነው መስኪዶችን የገነባዉ። ከሃያ አመታት በፊትና እና አሁን በአዲስ አበባ ብቻ ያሉትን የመስኪዶች ቁጥር ማወዳደሩ ብቻ ይበቃል። ሙስሊሞች በታላቁ ስታዲየም በፈለጉበት ወቅት ተሰባስበዉ ለመስገድና ለመጸለይ የተከለከሉበት ጊዜ የለም። የፈረሱ፣ የተቃጠሉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት እንዳሉት፣ የተዘጋ ፣ የፈረሰ ወይንም የተቃጠለ አንድም መስኪድ የለም። ተቃዉሞዎች ስናቀርብ፣ በተቻለ መጠን እዉነትን ይዘን ብንቃወም ጥሩ ነዉ።

በነገራችን ላይ ፣ ኢቲቪ ያቀረበዉ አሳዛኝ ድራማ በሙስሊሙ እስረኞች የተጀመረ አይደለም። ከዚህ በፊትም አኬልዳማ የተሰኘ አሳዛኝ ድራማ ቀርቦ እንደነበረ መዘንጋት የለብንም። ስለዚህ ሃይማኖትን ከዚህ እናዉጣ። ጥያቄዉ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። ጥያቄዉ የሕግ፣ የሞራልና የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ነዉ።

በሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ጋዜጣ ዝግጅትድጋፍ አስተባባሪ ኮሜቴ ጥሪ ለወገኖቻችን

$
0
0

በኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት ዘመናት ተንሰራፍተው የቆዩትን ጨቋኝ ስርዓቶች ለመጣል ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለ ቢሆንም በመስዋዕትነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት የበለጠ መስዋዕትነትን እየጠየቀ የመጣበት ሁኔታ እንጂ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሆነበት ስርዓት ለመመስረት አልተቻለም፡፡

በተለይም ባለፉት 21ዓመታት ራሱን በዲሞክራሲያዊ ቀለም በህገመንግስት ጭምር ቀባብቶ ብቅ ያለው አምባገነናዊ የህውሃት ኢህአዴግ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቀባው ቀለም እየተላጠ ውስጣዊ ማንነቱ ራሱን ሊደብቅ ከማየችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በልማታዊ መንግስትነት የምዕራብዓያዊያን ሀገሮችንም ያነሆለለበት የሁለት አሀዝ እድገት በራሱ ቋንቋ እያሻቀለ መሄዱን ለመስማት ተችሏል፡፡

ይህ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ የህብረተሰብ እድገት የአለም የፖለቲካ ሁኔታ መገለጫ ነው፡፡ በምንም ዓይነት ኃይል ማንኛውም አይነት አምባገነናዊ ስርዓት በረሱ ውስጣዊ ቅራኔም ሆነ በህብረተሰቡ የተደራጀና የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ተገርስሶ እንደሚወድቅ ዛሬ የምናያቸው የተሻለ ስርዓት የመሰረቱ አገሮች በተለያየ አካሄድ ያለፉበት ደረጃ ነው፡፡ ለዚህም ነው ወያኔ ኢህአዴግ የፈለገውን ያህል ራሱን ቢቀባባም እንደግለሰብ ህይወት የፖለቲካ ስርዓትም ማለፉ የማይቀር የታሪክ ሂደት ነው የምንለው፡፡

ቁምነገሩ ግን በማለፉ ሂደት ውስጥ በህብረተሰቡ ላይ ጥሎ የሚሄደው ጠባሳና ትውልዱ ከስርዓቱ የሚያገኘው በጎና ቀና ተግባራት በታሪክ ውስጥ የሚኖረው ቦታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በተለይም በሀገር ውስጥ ይሄንን ስርዓት በህዝብ ትግል አስገድዶ ባለፉት ትግሎች ያለፍንበትን በሰላማዊ መንገድ ህዝብን የስልጣን ባለቤት የማድረግ ሰላመዊ የፖለቲካ ትግል ላይ እውቀት፡ ጉልበትና ጊዜያቸውን ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን ጭምር መስዋዕት በማድረግ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን አይዞአችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን የምንለው፡፡ በመስዋዕትነት ደረጃ ግንባር ቀደሙ ገፈት ቀማሾች በመሆናቸውም ያኮሩናል፡፡

አንዳዶች እንደሚገምቱት ዛሬ ተቀዋሚው ኃይል 4ኪሎ ቤተመንግስት ባለመግባቱ ብቻ የመሪነት ብቃትና መመዘኛ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባም አይመስለንም፡፡ 4ኪሎ በብዙ መንገድ ሊገባ ይችላለል፡፡ በኃይልም፣ በመፈንቅለ ማንግስትም፣ በሸፍጥም፣ በማተራመስም፣ በሽብርም፡፡ ቁምነገሩ መንግስታዊ ስልጣኑ የሚቆምበት ህዝባዊ ኃይል የአገራችንን አንድነትና ሉኣለዊነት የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ፍትህና እኩልነትን የሚያረጋግጥ ማህበራዊ መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን ማረጋገጥ እና መንግስት ወድቆ መንግስት ሲተካ ሌላ 100 እና 200 የሚሆኑ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች የማይፈለፈሉበት ሁኔታን ማመቻቸት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛው መሰረት የህዝቡን ንቃትና አስተሳሰብ መቀየር ወሳኝነት አለው፡፡ በተቀየረ አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ነባራዊ ሁኔታን የመቀየር ችሎታን ማሳደግ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ሚዲያዎች እና ጋዜጦች ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡ የዛሬ የትኩረት ነጥባችንም የህብረተሰባችንን አስተሳሰብና አመለካከት ንቃት ብሎም ለማደራጀት ስራ ወሳኝነት ያለውን በሀገራችን የነፃ ፕሬስ መዳበር አስፈላጊነት ለመጠቆም እና የዚሁ ነፃ ፕሬስ አካል የሆነችውን ፍኖት ነፃነትን መልሶ ለህትመት ለማብቃትና ህይወት ለመስጠት ጥሪ ለማቅረብ ነው፡

አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስትን አስከፊ ተግባራትን ከማጋለጥ ባሻገር ምን ዓይነት ስርዓት በአገራችን ሊገናባ እንደሚገባ በመስተማር በነፃ ፕሬስ ውስጥ ቀዳሚነትን በመያዝ ላይ የነበረችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በትንሹ ተነስታ በስርዓቱ ደባ ህትመቷ ቢቋረጥም በህትመቷ ጊዜ እስከ 30ሺ ኮፒዎች በማሳተምና በማሰራጨት በህዝብ ዘንድ ተነባቢነትን እና ተአማኒነትን ያተረፈች ልሳን ነበረች፡፡ በዚህች ጋዜጣ ላይ ብርቅዬ የሀገሪቱ ወጣት ልጆች እና አዛውንቶች ያቀረቧቸው የነበሩት ፅኁፎች እና መረጃዎች ጋዜጣዋን ከዜና ወይም ከወሬ አቀባይነት አሸጋግሮ ወደ አቅጣጫ አመላካች ቀስቃሽና አስተማሪነት በአጠቃላይም ለትግሉ ከፍተኛ አነቀስቃሽነት መሳሪያነቷን የተረዳው አምባገነኑና አፋኙ የህውሀት ኢህአዴግ መንግስት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለመዝጋት የሞከረ ቢሆንም አዘጋጆቹ በከፈሉተት መስወዕትነት እስካሁን ጊዜ መቆየቱዋ ይታወቃል፡፡ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት በመጨረሻ ላይ ጋዜጣ አታሚዎችን ‹እኛ ማተም እንፈራለን› እሰኪሉ ድረስ አሳታሚዎችን በፍርሀት ሰለባ ተቆጣጥሮ ህትመቷ እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ያም ሆኖ ምንም እንኳን በቋሚ መልኩ ባይሆንም በተለያዩ ድህረ ገፆች አማካይነት የህዝብ ልሳን በመሆን አገልግሎቷን ቀጥላለች፡፡

ውድ ኢትዮጵያውያን ፣ ዛሬ በዚህ አምባገነን ስርዓት የነፃ ፐሬሶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳፍነው የሚገኙበትና ወያኔ አፍንጫ ስር ሆነው የዚህን አስከፊ ስርዓት ገበና በማጋለጥም ሆነ እንደ ማደራጃ ኃይልም በማገልገል ላይ የሚገኙ የብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆችና ልሳኖቻቸው በምንም መልኩ እንዲዘጋ መፍቀድ ያለብን አይመስለንም፡፡የነአንዱአለም፣ የነእስክንድር፣ የነተመስገን እንዲሁም በርካታ የተሰደዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ብዕሮች ይሄንን ስርዓት ምንያህል እደሚያስፈሩት እየወሰዳቸው ያለው አስከፊ እርምጃዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ስርዓቱ አስሮ የማይጨርሳቸው ልጉዋም የሚያቅማቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከቀን ወደቀን እየፈሉ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የለውጡ ባህር በሆነው ህዝብ መሃል የሚያሰሙት ድምፅ ከምንም መሳሪያ የበለጠ ህዝባዊ እምቢተኝነት ይፈጥራል፣ያደራጃል፣ ያስታምራል፣ይቀሰቅሳል፣ አቅጣጫ ያለው በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ ህዝባዊ እምቢተኝነትን ይፈጥራል፡፡ ለዚህ ነው ፍኖተ ጋዜጣ በሳምንታዊ ህትመት እስከ30ሺህ ኮፒ ታትማ ሁለት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በገበያ ላይ የማትገኘው፡፡ ነፃ ፕሬስ በራሱ ብቻውን ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም፡፡ የለውጥ ኃይልን ያሰባስባል፡፡ ከኢቲቪ፣ ከአዲስ ዘመን ለህብረተሰባችን የሚነሰነሰውን ሳይወድ በግድ እንዲጋት የሚደረገውን ህዝባችንን አማራጭ ሃሳብና እውነታን ያስጨብጣል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የፍኖተ ጋዜጣን ህትመትና ስርጭት ከወያኔ ኢህአዴግ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊያላቅቅ የሚችል የራሱ የህትመት መሳሪያና ዝግጅት ለማደራጀት የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህ ፕሮጄክት መሳካት የአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተፋላሚዎችን ድጋፍና እገዛ ይጠይቃል፡፡ ለዚሁም እንዲረዱ ከ20 እስከ 500 ዶላር(ብር) የሚደርስ ትኬቶች ተዘጋጅተው በቅርቡ ለገበያ እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ በተለይ በውጪ አገር የሚገኙ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥሪ ቀርቦልናል፡፡ ጎዳናችን የተለያየ ሊሆን ይችላል፣ የማይለወጥ የጋራ ግባችን ግን በሀገራችን ፍትህ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት፣ ሉአላዊነት የተረጋገጠበት ስርዓት ማየት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በምኞት ሳይሆን ሁላችንም ትንሽ ጠጠር ስንወረውር ብቻ ነው የሚሳካው፡፡ የአምባገነኑ ህውሀት ኢህአዴግ መንግስትን በተሻለ አስተሳሰብና ኃይል በልጦ የሚገኝ የፖለቲካ ሀይል ለመፍጠር የነፃ ፕሬሶች በጥራትና በብዛት ለህዝባችን ማዳረስ ምንም አማራጭ የሌለው የዴሞክራሲ ስርዓት ቁልፍ መክፈቻ ነው፡፡ የፖለቲካ ስልጣን በየትኛውም መንገድ ቢመጣ የተገኘውን ስልጣን የራሱ አድርጎ የሚመለከት አስተሳሰብና ህብረተሰብ እስካልተፈጠረ በሚነሱ ህዝባዊ ችግሮች ሁሉ የሚሰጡት ምላሾች ስልጣን የማቆየትና ያለማቆየት ጥያቄ ስለሚሆን በጠማንጃ ታፍኖ ለማይኖር ስርዓት እና ህዝብ በንቃት ላይ ለተመሰረተ ለውጥ የነፃ ፐሬስ ወሳኝነትን እንረዳ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር የረታ ‹‹ይቅርታ!›› ከዕንቁ መጽሔት የተወሰደ –ጸሐፊው በፍቅር ለይኩን፡፡

$
0
0

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ጓደኞቿና የነፃነት ትግሉ አጋሮቿም፡- ‹‹እናዝናለን ኤሚ…ፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል…፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽ…ሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና …ደህና ሁኚ ኤሚ ደህና ሁኚ፣ ሁሌም እንወድሻለን…!›› በማለት ወደ ትውልድ አገሯ አሜሪካ በእንባና በመሪር ሐዘን ሸኟት፣ ተሰናበቷት፡፡

ውቧ፣ ማራኪዋና ከዓለማችን አስር ምርጥ ከተሞች ተርታ የተመዘገበችው የደቡብ አፍሪካዋ የኬፕታውን ከተማ የደቡብ አፍሪካ የታሪክ፣ የቅርስ፣ የባህልና የፖለቲካ ማዕከል ናት፡፡ የድኅረ ምረቃ ትምህርቴን የተከታተልኩባት ኬፕታውን ለአምስት መቶ ዓመታት ያህል አፍሪካውያን ያለፉበትን ውስብስብ የታሪክ ጉዞ የሚያስቃኙ፣ የጥቁር ሕዝቦችን የአይበገሬነትና የነፃነት ተጋድሎ የሚዘክሩ በርካታ ቅርስና ሕያው አሻራ ያላት ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡

ኬፕታውን ታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላና የትግል አጋሮቻቸው ለ27 ዓመታት የተጋዙባትን ቀዝቃዛውን የአትላንቲክ ውቅያኖስንና የከተማይቱን ግርማና ውበት የሆነውን የቴብል ማውንቴንን ተንተርሶ የተገነባው የሮቢን ደሴየት ግዞት ቤት/ወኅኒ ቤት የሚገኝባትም ናት፡፡

ይህን ለዘመናት በርካታ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦች ለሰው ልጆች ነፃነትና ሰብአዊ መብት ሲሉ የተጋዙበትን የሮቢን ደሴየት ግዞት ቤት/ወኅኒ ቤት በየቀኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎችና አጥኚዎች፣ ፖለቲከኞች፣ መሪዎች፣ ታላላቅ የሆኑ የዓለማችን የፊልም እንዱስትሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ዝነኞችና ባለ ጠጋዎች ይጎበኙታል፡፡ እናም የደቡብ አፍሪካዋ ‹‹እናት ከተማ›› ኬፕታውን የቱሪስቶችና ውብ የመዝናኛ ከተማም ጭምር ናት፡፡

በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ በትምህርት ክፍላችንና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሙን ነፃ የትምህርት ዕድልና አጠቃላይ ወጪያችንን የሸፈነልን የሮቢን ደሴየት ሙዚየም፣ በኬፕታውን የሚገኙትን ቤተ መዘክሮችን፣ የደቡብ አፍሪካውያንን የነፃነት ተጋድሎ የሚያንጸባርቁ ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሶችን መጎብኘት እንድንችል ዕድልን አመቻችቶልን ነበር፡፡ በዚህ ዕድልም ከጎበኘኋቸውና በማስታወሻ ደብተሬ ከመዘገብኳቸው አስደናቂ ቦታዎች መካከል አንዱ ለዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሆኖኛል፡፡

እኔና የክፍል ጓደኞቼ ጉብኝታችን ፕሮግራሞች ውስጥ ካየናቸው የአፓርታይድ አገዛዝን ጭካኔና ክፋት ከሚዘክሩ ታሪካዊ ቦታዎች በኬፕታውን ከተማ የሚገኘው የጉጉሌቱ ታውን ሺፕ አንዱ ነው፡፡ ይህ ታውን ሺፕ/መንደር በአብዛኛው ጥቁሮች የሚኖሩበት ነው፡፡

እነዚህ በአራቱም የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ የጥቁር አፍሪካውያን መንደሮች በደቡብ አፍሪካውያን ሕይወት ዘረኛው የአፓርታይድ ስርዓት የተወው ጠባሳ ገና ፈፅሞ የሻረ እንዳልሆነ ማረጋገጫን የሚሰጡ ናቸው፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ጥቁር አፍሪካውያኑ የሚኖሩባቸው እነዚህ መንደሮች ድህነትና ጉስቁልና በእጅጉ የሚንጸባረቅባቸው መሆናቸው የሕዝቦቻቸው ኑሮ ይመሰክራል፡፡

በዚህች በጉጉሌቱ የድኆች መንደር ውስጥ ነዋሪዎቿና ሥራ አጥ ወጣቶቿ ካሉበት አስከፊ ድህነትና ጉስቁልና በመጠኑም ቢሆን ለማውጣትና እገዛ ለማድረግ በአሜሪካውያን ቤተሰቦች የተቋቋመ አንድ ፋውንዴሽን አለ፡፡ በጉብኝታችን ወቅት ስለዚህ ፋውንዴሽን ማብራሪያ የሰጠን አስጎብኚያችን የፋውንዴሽኑን አመሰራረት ታሪክ እንዲህ ሲል አጫወተን፡፡

እኔም በማስታወሻዬ የዘገብኩትንና በዚህች ድህነትና ወንጀል በተንሰራፋበት የጥቁሮች መንደር ‹‹ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ስለረታው›› አስደናቂ የእርቅ/የይቅርታ ድንቅ ታሪክ ከማስታወሻዬ ማኅደር ላስነብባችሁ ወደድኹ፡፡

ደቡብ አፍሪካውያን ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግል በ1970ዎቹ እና በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ላይ እጅጉን የተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ያገኙ ደቡብ አፍሪካውያን ጥቁር ተማሪዎች ትግሉን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ያሻገሩበትን ትልቅ ዕድል ፈጥሮ ነበር፡፡

በዚህ በኬፕታውን ከተማ በዋነኝነት ለክልሶች፣ ለኢንዲያንስ (Colors and Indians) እና ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎች የመማር ዕድል እንዲያገኙ በተቋቋመው የዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ፣ ከአሜሪካን ካሊፎርኒያ ኮሌጅ በFulbright Scholarship ዕድል ያገኘች አንዲት በሃያዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ ነጭ አሜሪካዊ ወጣት በዩኒቨርስቲው ያለውን የተማሪዎችን ፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴና ትግል ለማጥናት በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ ለአስር ወራት ቆይታ ለማድረግ መጥታ ነበር፡፡

ኤሚ የተባለችው ይህች ነጭ አሜሪካዊት ሴት በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከጥቁር ተማሪዎች ጋር ለመተዋወቅና አጋርነቷን ለመግለፅ ብዙም ጊዜ አልወሰደባትም ነበር፡፡ እናም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተማሪዎቹ ጓደኛ ብቻ ሳይሆን ዋና የትግል አጋርም ለመሆን በቃች፡፡ የፀረ አፓርታይድ ትግሉንም በሐሳብና በሞራል መደገፉን ተያያዘችው፡፡ በተጨማሪም ከአፍሪካውያን ተማሪዎች ጋር ስለ አፍሪካውያን የነፃነት ትግል ሂደትን በተመለከተ ሰፊ ውይይትና ጥናት ማድረጓንም ቀጠለች፡፡ ከአፓርታይድ አገዛዝ ወደ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት በሽግግር ወቅት ለነበረችው ደቡብ አፍሪካም የምትችለውንና የአቅሟን ሁሉ አደረገች፡፡

ኤሚ ከተማሪዎቹ ጋር ያስተሳሰራት የፀረ አፓርታይዱ ትግል ይበልጥ ወንድማዊና እህታዊ የሆነ ቤተሰባዊ ወዳጅነትን አተረፈላት፡፡ እናም ኤሚ አፍሪካውያን ጥቁር ተማሪዎች በሚኖሩባቸው በተከለሉ የጥቁሮች መንደሮች እየተዘዋወረች የዘረኛውን የአፓርታይድ መንግሥትን አስከፊና ዘግናኝ ጭቆና በዓይኗ ለመታዘብና ምስክር ለመሆን ቻለች፡፡

ጭቆና፣ ድህነት፣ መከራ፣ ጉስቁልና፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዘረኛው አፓርታይድ መንግሥት ክፉ ተግባርና ግፍ አባሳቸውን በሚያስቆጥራቸው በእነዚህ የድሆች ከተማዎች ውስጥ ያለውን ዘግናኝ ሕይወት ኤሚ በአዕምሮዋና ብዕሯ መከተቡን በሚገባ ተያያዘችው፡፡

የሚሊዮኖች የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የፍትህ ያለህ ዋይታና እሪታ በሚሰማባቸው የጥቁሮች መንደር ያለውን ዘግናኝ እውነታ የታዘበችው ኤሚ፡- ይህ ግፍ፣ ይህ ኢ-ሰብአዊነትና ጭካኔ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ፀረ አፓርታይድ ትግልና ታጋዮች ያላትን አጋርነት በይበልጥ እንድታጠናክር አደረጋት፡፡ ኤሚ በሳምንቱ መጨረሻና በበዓል ወቅት ለእረፍት ወደቤተሰቦቻቸው የሚሄዱትን ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ በመኪናዋ በመሸኘት ጭምር ከእነርሱ ጋር ብዙ ጊዜዋን ታጠፋ ነበር፡፡

ታዲያ ከሰብአዊነት ከመነጨ ፍቅርና ርኅራኄ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎች ድጋፏን ስትሰጥ የነበረችው ኢሜ በአንድ ወቅት የትምህርት ቤት ጓደኞቿንና የትግል አጋሮቿን ለመሸኘት ለጥቁሮች ብቻ ወደተከለለ የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የድሆች መንደር ወደሆነችው ጉጉሌቱ እንደበፊቱ ሁሉ አገር ሰላም ነው ብላ መኪናዋን በማሽከርከር ትመጣለች፡፡

ጓደኞቿን ከመኪናዋ አውርዳ የምትቸኩልበት ሌላ ጉዳይ የነበራት ኤሚ መኪናዋን አዙራ በፍጥነት ወደ ከተማ ለመመለስ ስትነዳ ሳለች በመንገዷ ላይ ሁከት ከታከለበት ሰልፍ ውስጥ ራስዋን አገኘችው፡፡ ከሰልፉ መካከል የወጡ ሁለት ወጣቶችም መኪናዋን እንድታቆም አጭርና ቀጭን ትዕዛዝን አስተላለፉላት፡፡ ኤሚ በወጣቶቹ ትዕዛዝ በጥቂቱም ቢሆን ግራ ተጋባች፡፡

ይሁን እንጂ ኤሚ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ የመሰላት ጥቁሮች ለነፃነታቸው የሚያደርጉትን ትግል በመደገፍ በመቆሟ አድናቆታቸውንና ምስጋናቸውን ሊገልፁላት መስሎአት የወዳጅነት ፈገግታን በተሞላ መንፈስ ሰላም አለቻቸው፡፡ ያ በኤሚ ፊት የታየው ከፍቅርና ከርኅራኄ የመነጨ ፈገግታዋ ግን በእነዚህ ወጣቶች ዘንድ በምላሹ ጥላቻን ያነገሰ ቅፅበታዊ የሆነ ግብታዊ ስሜትን ፈጠረ፡፡

እናም እነዚህ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች በዛ በነጮቹ የአፓርታይድ ዘረኛ ስርዓት አራማጆች ለጥቁሮች ብቻ ተከልሎ በተሰጣቸው ምስኪን መንደራቸው ይህችን ነጭ ወጣት ሴት ማየታቸው በእጅጉን አናደዳቸው፡፡ እናም በውስጣቸው የሚንቀለቀለውን ንዴትና በቀል በኤሚ ላይ ለማዝነብ ፈጣን እርምጃ ወሰዱ፡፡ የኤሚ ተማጽኖና የማንነት ኑዛዜ ሰሚን አላገኘም፡፡

ወጣቶቹ ኤሚን በመኪናዋ ውስጥ እንዳለች በድንጋይ በመውገር ያን የፍቅርና የርኅራኄ ፈገግታዋን በበቀል ደም አጨልመውትና አጠልሽተውት እግሬ አውጪኝ በማለት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ በደም ተጨማለቀችውን ሴት ፖሊስ ደርሶ ወደ ሐኪም ቤት ይዟት ቢሄድም ሕይወቷን ለማትረፍ አልተቻለም ነበር፡፡ እናም ኤሚ በዚህ ዓይነት ያልተጠበቀ መጥፎ አጋጣሚ ሕይወቷ አለፈ፡፡

ባልታሰበና ባልተጠበቀ አጋጣሚ ኤሚ ለነፃነታቸውና ለሰብአዊ መብታቸው በምትታገልላቸውና አይዞአችሁ በምትላቸው ጥቁሮች ወንድሞቿ እጅ ሕይወቷ አለፈ፡፡ ገዳዮቿም በፖሊስ ተይዘው ወኅኒ እንዲወረወሩ ተደረገ፡፡ ይህን ዘግናኛ አጋጣሚ የሰሙና ያዩ ጓደኞቿ ሀዘናቸው እጅጉን የመረረ ነበር፡፡ የትግል አጋራቸውንና የልብ ጓደኛቸውን ያጡት የዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ የትግል አጋሮቿና ጓደኞቿ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐዘናቸውን ለመግለጽ ልዩ የሐዘንና የስንብት ፕሮግራም በማድረግ ኤሚን፡-

‹‹እናዝናለን ኤሚ…ፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል…፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽ…ሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና …ደህና ሁኚ ኤሚ ደህና ሁኚ፣ ሁሌም እንወድሻለን…!›› በማለት ወደ ትውልድ አገሯ አሜሪካ በእንባና በመሪር ሐዘን ሸኟት፣ ተሰናበቷት፡፡

ከጥቂት ዓመታት በኋላ የእነ ኤሚና የሚሊዮኖች ደቡብ አፍሪካውያንና የሰው ልጆች ነፃነት ተቆርቋሪ የሆኑ ሕዝቦች መራር ትግል በስተመጨረሻ ፍሬ አፍርቶ የአፓርታይድ ስርዓት ከደቡብ አፍሪካ ምድር ተገረሰሰ፡፡ የፀረ አፓርታይድ ትግሉ ዋና መሪ በሆኑት በኔልሰን ማንዴላ ግንባር ቀደምትነትም በአዲሲቷ ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እርቅና መግባባት እንዲወርድ ታወጀ፡፡

ለዚህም ማንዴላ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ለ27 ዓመታት ግዞት፣ ለሕዝባቸው መከራ፣ እንግልት፣ ስደትና ሞት ምክንያት የሆነውን የአፓርታይዱ ዘረኛ መንግሥት መስራችና ዋና አቀንቃኝ ወደሆኑት ወደ ሟቹ የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቤት በመሄድ በሕይወት የሚገኙትን ባለቤታቸውን፣ ዘረኛው የአፓርታይድ ስርዓት በርሳቸውና በሕዝባቸው ላይ ላደረሰባቸው የሰው ልጅ ሕሊና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ለሆነው ግፍና መከራ በፍፁም ልብ ይቅርታ ማድረጋቸውን ለዓለም በይፋ ገለጹ፡፡

ዓለም በአንድ ድምፅ፡- ‹‹ብራቮ ማንዴላ! የሰላም አባት፣ የፍቅር ተምሳሌት፣ የይቅርታ መዝገብ…!›› ሲል አሞካሻቸው፡፡ ይህን የፍቅርና የእርቅ መንገድ ሚሊዮኖች ደቡብ አፍሪካውያን ዘረኛው አፓርታይድ መንግስት ትቶባቸው ካለፈው ህመማቸው፣ ስብራታቸውና ቁስላቸውም ጋር እየታገሉም ቢሆን ‹‹ዳዳ/ማዲባ›› ወይም ‹‹ታላቁ አባታችን›› የሚሏቸውን የማንዴላን ‹‹የሰላምና የእርቅ መንገድ›› ቆርጠው ሊከተሉት ወሰኑ፣ የብዙዎችም ልብ ለፍቅርና ለይቅርታ ጨከነ፡፡

በዚህም ለቂምና ለበቀል፣ ለክፋት፣ ለጥላቻና ለእርስ በርስ እልቂት ከሰገባቸው የተመዘዙ የበቀል ሰይፎች ወደ ሰገባቸው ተመልሰው በአንፃሩ ደግሞ በዚህች የእግዚአብሔር ስጦታ በሆነች ውብና ባለ ጠጋ የአፍሪካ ምድር- በደቡብ አፍሪካ እርቅና ሰላም ይወርድ ዘንድ የሃይማኖት አባቶች፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ተሟጋቾችን፣ ታዋቂ ሰዎችን ጭምር ያቀፈ የእውነት አፈላላጊና የእርቅ ኮሚሽን (Truth and Reconciliation Commission) በይፋ ተቋቋመ፡፡

ይህ የደቡብ አፍሪካ የእውነት አፈላላጊና የእርቅ ኮሚሽንም በአፓርታይድ ዘመን የደረሱትን የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋ፣ እልቂትና ግፍ በመመርመር በበዳይና በተበዳይ መካከል ሰላምና እርቅ እንዲወርድ፣ እንዲሁም የትላንትና ቁስሎች በቂም በቀል ሳይሆን በይቅርታና በካሳ እንዲዘጉ ትልቁን ኃላፊነትና ታሪካዊ የሆነ ድርሻ ወሰደ፡፡

በዚህም የትላንትና የጭቆና፣ የክፋት፣ የጥላቻ፣ የእልቂትና የደም ዘመን ምዕራፍ ተዘግቶ በአገሪቱ አዲስ የሆነ የእርቅና የሰላም ታሪክ እንዲፃፍ አደረገ፡፡ ከዚህም የተነሳ አዲሲቱ ደቡብ አፍሪካ ነጭ፣ ጥቁር፣ ክልስ፣ ህንድ…ወዘተ ሳይባል ሁሉም በሰላምና በአንድነት የሚኖሩባት Rainbow Nation የሚል ቅጽል ስምንና ክብርን አተረፈች፡፡

ወደ ታጋይዋ ኤሚ ታሪክ ፍፃሜ ስንመለስ ደቡብ አፍሪካ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ካደረገች በኋላ በአፓርታይድ ዘመን በደቡብ አፍሪካውያን ሕዝቦች ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ እሥራትና ግፍ ለማጣራት በተቋቋመው የእውነትና የእርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን በተደረገላቸው ግብዣ ወደ ደቡብ አፍሪካ የመጡት የኤሚ ወላጆች ሚ/ር ፒተርና ወ/ሮ ሊንዳ በልጃቸው ሞት ምክንያት የተከሰሱ ወጣቶች በተገኙበት በተካሄደው ችሎት ለልጃቸው ገዳዮች ፍፁም የሆነ ከልብ የመነጨ ይቅርታ ማድረጋቸውን በፍቅር ገለፁ፡፡

የኤሚ እናትና አባት በዚህ ብቻ አላበቁም፡፡ ገና አሁንም ከባድ የሆነ ድህነት፣ የሥራ አጥነትና ወንጀል በተንሰራፋባት በምስኪኗ ጉጉሌቱ የፍቅርና የይቅርታ ሀውልትን ለማቆሙ ወደዱ፡፡ የአፓርታይድ ዘረኛ መንግስት ትቶት ያለፈው መጥፎ አሻራው ባልጠፋባት በዚህች መንደር መካከል ወደተቋቋመው ፋውንዴሽን በእጁ እየጠቆመን አስጎብኚያችን አንዳንች ልዩ ስሜት የተጫነው በሚመስል ቃላቶችና የሰውነት እንቅስቃሴ ትረካውን እንዲህ ቀጠለልን፡-

የኤሚ ወላጆች በችሎቱ ፊት ባሰሙት ውሳኔያቸው ለልጃቸው ገዳዮች ፍጹም የሆነ ይቅርታ ማድረጋቸውን በይፋ ገለጹ፡፡ ለሟች ልጃቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድም ልጃቸው በድንጋይ ተወግራ በሞተችበት አካባቢ ለመንደሩ ነዋሪዎችና ሥራ አጥ ወጣቶች እንዲሆን በራሳቸው ገንዘብ በግፍ ለተሠዋችው ለልጃቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የኤሚ ፋውንዴሽንን አቋቋሙ፡፡ የኤሚ ገዳዮችም በዚሁ ፋውንዴሽን ውስጥ ዋና ሠራተኛና ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

ይሄ ፋውንዴሽን ለልጃቸው፣ ለምስኪኗ ሰማዕት ኤሚ የበቀል ደም በፍቅርና በይቅርታ ይደመደም ዘንድ የተቋቋመ መሆኑን አስጎብኚያችን ሲተርክልን ብዙዎቻችን በስሜት ተውጠንና ዓይናችን እንባ አቅርሮ ነበር፡፡ አንድና ብቸኛ ልጃቸውን በሞት የተነጠቁት የኤሚ አባትና እናትም ለልጃቸው ገዳዮች እናትና አባት እንደሚሆኑላቸው ጭምር ነበር ከልብ በሆነ ፍቅር ያበሰሯቸው፡፡ አስጎብኚያችን እጅግ ልብ የሚነካውን ታሪክ መተረኩን ቀጥሏል . . .፡፡

በጉብኝቱ መካከል የነበሩ አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎችም እንባቸው መንታ ሆኖ በጉንጫቸው ላይ ሲወርድ በግልፅ ይታይ ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በዚህች በድሆች መንደር ‹‹ለፍቅርና ለእርቅ›› በቆመው ፋውንዴሽን ሕንፃ ላይ ዓይናቸውን ለደቂቃዎች ሰክተው ጥልቅ የሆነ የአሳብ ባሕር ውስጥ የገቡ ይመስሉ ነበር፡፡ አስጎብኚያችን ትረካውን ጨርሶአል፤ ሁኔታው ግን ከእኛው ጋር ቃላት ሊገልፀው በማይችል ጥልቅና በልዩ ስሜት ውስጥ አብሮን የነጎደ ይመስል ነበር፡፡

ይህን አስደናቂ የፍቅር/የእርቅ ገድል ታሪክ ከምመዘግብበት ማስታወሻዬ ላይ እንዳቀረቀርኩ ሕሊናዬ፡- የራሴን፣ የወገኖቼንና አገሬን የእርስ በርስ መበላላት ዘግናኝ ታሪክ፣ የቂም፣ የበቀልና የጦርነት ታሪክ ወደፊትና ወደኋላ እያጠነጠነ ነበር፡፡ ከሰላሙ፣ ከፍቅሩ፣ ከአንድነቱና ከእርቁ ታሪካችን ይልቅ የመበላላት፣ የቂም፣ የበቀልና የመለያየት ዘግናኝ ታሪካችን በዓይነ ሕሊና ገዝፎ ታየኝ፡፡ እናም ካቀርቀርኩበት ቀና ስል ዓይኔ ያረገዘው የእንባ ዘለላ ቁልቁል ወርዶ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ ጠብ ሲል ተመለከትኩት፡፡

በማስታወሻ ደብተሬ ላይ ዛሬም ምስክር ሆኖ ያለው የደረቀው እንባ የኤሚንና የወላጆቿን የነፃነት ተጋድሎ፣ የእውነትና የፍትሕ ራባቸውን፣ ድንበርና ዘር ያላገደውን የፍቅራቸውን ታላቅነትና ሕያውነት በአንክሮት ያሳስበኛል፡፡ በእውነትም ይህ በኬፕታውን በጉጉሌቱ የጥቁሮች መንደር በኤሚ ስም የተቋቋመው ፋውንዴሽን በፍቅር ስለፍቅር በተከፈለ መስዋእትነት፣ የይቅርታን ታላቅነት በተግባር ለመተረክ የቆመ ሕያው ምስክር፣ ዘመን አይሽሬ ቅርስ መሆኑን ሁላችንም በጉብኝቱ የነበርን ከተለያዩ ሀገራት የመጣን ተማሪዎች በአንድ መንፈስ በአንድ ቃል ያረጋገጥን በሚመስል መንፈስ ዓይን ለዓይን ተያየን፡፡
ሁላችንም በዛች ቅፅበት በኤሚ የፍትሕ ሰማዕትነት፣ በወላጆቿ የፍቅርና ይቅርታ ቋንቋ ከልብ የተግባባን መሰልን፡፡ ሕሊናችን መልሶ መላልሶ ኤሚን፣ ፒተርን፣ ሊንዳን፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን… በዛች ድህነት፣ ጉስቁልና፣ ሥራ አጥነትና ወንጀል በተንሰራፋባት የጥቁሮች መንደር በጉጉሌቱ ለፍቅርና ለእርቅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የቆመውን የኤሚን ፋውንዴሽን ያሰላስል ጀመር፡፡

ልባችንም አንደበታችንም በዚህ ሕያው የፍቅር ገድል የተረታ መሰለ፡፡ እናም ከጉብኝታችን ጉዞ መልስ የኤሚንና የወላጆቿን የፍቅር/የይቅርታ ታላቅ ገድል በመቀባበል እየተረክን ነበር ወደ ዩኒቨርስቲያንችን ቅጥር ግቢ በአድናቆትና በአግራሞት ተሞልተን የተመለስነው፡፡

የካሊፎርኒያዎቹ ሚ/ር ፒተርና ወ/ሮ ሊንዳ የልጃቸው ክቡር ሕይወት በብዙ እልፎች ሕይወት የሚተካውና መንፈሷ ሊያርፍ የሚችለው ገዳዮቿን በመበቀል ሳይሆን በይቅርታ መሆኑን በተግባር ያሳዩበት ይህ የፍቅር ገድል ታሪክ ዛሬም ድረስ በውስጤ ይደውላል፡፡ እነዚህም ቤተሰቦች በደላቸውን በሌላ በደል፣ በቂም በቀል ሳይሆን ከልብ በመነጨ ይቅርታ በበጎ ካሳ በፍቅር ደመደሙት፡፡ በእርግጥም ይቅርታ የተሰበረንና የቆሰለ ልብን ሊጠግን የሚችል፣ መዓዛው የሚያውድ፣ መልካም የፍቅር ዘይትን ማፍሰስ ካልቻለ ሙሉ ይቅርታ ሊሆን አይችልም፡፡

በወቅቱም ይህን የኤሚን ቤተሰቦች ፍቅር፣ ርኅራኄና ይቅርታ የታየበትን ሰላማዊ የሆነ የእርቅ እርምጃ አንድ የደቡብ አፍሪካ ታዋቂ ጋዜጣ እንዲህ በማለት ገልፆት ነበር፡-
Today, rather than having their lives subsumed in bitterness, Amy’s parents are leading important, constructive lives as part of the great South African reconciliation effort. They keep Amy’s spirit alive as a living memory, and they feel hope rather than anger. Strictly from the standpoint of their own self-interest, the Biehls are better off than if they had refused to forgive.

እውቁ የነፃነት ታጋይ፣ የሰላም አርበኛ፣ የአዲሲቱና የዲሞክራሲያዊቱ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዝዳንት የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ በኤሚ ድንገተኛና አሳዛኝ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ባደረጉት ንግግራቸው ስሜታቸውን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት፡-

“She made our aspirations her own and lost her life in the turmoil of our transition as the new South Africa struggled to be born in the dying moments of apartheid. Through her, our peoples have also shared the pain of confronting a terrible past as we take the path of reconciliation and healing of our nation.”

ፍቅርን ያብዛልን! ሰላም፣ እርቅና አንድነት ለእናት ምድራችን ለእማማ ኢትዮጵያችን ይሁን! አሜን ይሁን!!
ሰላም! ሻሎም!

ፍኖተ ነጻነት ቁጥር 65 ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያንን አንድ ሊያደርግ የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ ! ግርማ ካሳ

$
0
0

«በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ! »

የአቡነ ጳዉሎስን ሕልፈት ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የተፈጠረዉን መከፋፈል ለማስቀረት፣ በመንፈሳዊ አባቶች መካከል፣ የሰላምና የእርቅ ዉይይቶች ተደርገዋል። ለሃያ አመታት የዘለቀዉ፣ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የወረደው የመከፋፈል እርግማን ተወግዶ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷ አንድ ሆና፣ «ሂዱና አሕዛብን እያስተማራችሁ፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅድስ ስም እያጠመቃችሁ፣ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸዉ» የሚለዉና በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠዉ፣ ታላቅ ተልእኮን መፈጸም ትችል ዘንድ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ በየአብያተ ከርስቲያናቱ፣ በየጸሎት ቤቱ ፣ በየገዳማቱ ሲጾምና ሲጸል ነበር።

ነገር ግን ከተጠበቀዉና ከተገመተዉ ዉጭ አስደንጋጭና አሳዛኝ መግለጫዎችን አነበብን። የክርስቶስ መድሃኔአለም ስም ተሰደበ። የዲያብሎስ ስም ገነነ። የትህትሃ የፍቅር እራስን የማዋረድ ክርስቲያናዊ መንፈስ ጠፋ። የእልህ የስደብ የመወጋገዛና የትእቢት መንፈስ ሰፈነ።
በአገር ደረጃ ካያን ፣ የከተማ፣ የክልል ፣ የፌደራል መንግስት ሕጎች ይኖራሉ። ነገር ግን ከህጎች ሁሉ በላይ የሆነ ሕገ-መንግስት የሚባል ሕግ አለ። ፈረንጆች “The Supreme Law of the Land” ይሉታል።

ቤተ ክርስቲያንም የምትተዳደርበት ሕገ ደንብ ወይንም ቀኖና አላት። ካህናት ፣ ገዳማት፣ የሰንበት አስተማሪዎች ወዘተረፈ የሚታዳደሩበት ስርዓት/ሕግ/ቀኖና አለ። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ሕጎችና ቀኖናዎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መመሪያ የሆነዉን፣ የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚያግዙ እንጂ፣ የሚተኩ አይደለም። ወንጌል ከሁሉም በላይ ነዉ። ለዚህም ነዉ በቅዳሴ ወቅት ወንጌልን ቄሱ በሚያነቡበት ወቅት፣ ምእመኑ በአክብሮትና በፍርሃት ቆሞ የሚያዳምጠው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶችን እያጨቃጨቀ ያለ አንድ ጉዳይ ቢኖር፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ የቀኖና መጽሃፍ የተጠቀሱ፣ ፓትሪያርክ እንዴት እንደሚሾምና እንደሚተካካ የሚገልጹ አንዳንድ አንቀጾች ናቸዉ። በዶክትሪን ወይንም በሃይማኖት ጉዳዮች አልተለያዩም። በአስተምህሮ አልተለያዩም። ልዩነታቸው፣ ቅንነትና ትህትና የተሞላ ልብ ካለ፣ በቀላሉ ሊፈታ የሚችል፣ የአሰራርና ማን መሪ መሆን አለበት የሚለዉ ላይ ነዉ።

አራተኛዉ የቤተ ክርስቲያኒቷ ፓትሪያርክ በሕይወት እያሉ አምስተኛ ፓትሪያርክ ይሾማሉ። «አምስተኛዉ ፓትሪያርክ የተሾሙት አራተኛዉ ፓትሪያርክ በፍቃዳቸው ሃላፊነታቸዉን ስለለቀቁ ነዉ» ያላሉ አንዳንዶች። ሌሎች ደግሞ «አይደለም ፤ በአቶ ታምራት ላይኔ ተገደው ነዉ» ሲሉ በፓትሪያርኩ ላይ ተደረገ የሚሉትን ግፍ በምሬት ይገልጻሉ። ይሄ እንግዲህ ከሃያ አመት በፊት የሆነ ነገር ነዉ። ጠባሳዉ ግን ለሃያ አመታት ይኸዉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ጉዳት አደረሰ። ቤተ ክርስቲያኒቷ ተከፈለች። ለሃያ አመታት ጠብ ነገሰ። ተፋቅረን ተያይዘን በአንድ ላይ ወንጌልን ማስፋፋት የሚገባን ክርስቲያኖችን፣ ከፋፍሎና አጣልቶ ሆድና ጀርባ አደረገን።

እንግዲህ አስቡት፣ የመጽሃፍት ሁሉ የበላይ፣ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነዉ ፣ ወንጌልን ያካተተዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉ። መጽሃፍ ቅዱስ የሚያዘው ፍቅርን፣ ይቅር መባባልን፣ አንድነትን፣ ትህትና የመሳሰሉትን ነዉ። የቀኖናዎች ሁሉ የበላይ ከሆነዉ፣ ከማያልፈዉና ከማያረጀዉ ሕያዉ የእግዚአብሄር ቃል ዉስጥ ፣ «እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ የኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ሌሎች ያዉቃሉ»፣ « እራስህን ከሌላ የተሻለ አድርገህ አትቁጠር» ፣ «አንተ የሌላዉን ጉዳፍ ለማወጣት የምትቸኩል በአይን ያለዉ ያለዉን ትልቅ ምሰሶ መጀመሪያ ተመልከት» ፣ ‹‹በመጀመሪያ መባህን በመሰዊያው ላይ ትተህ አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ››፣ «ማንም ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ፣ ወፍጮ ባንገቱ ታስሮ ባህር ዉስጥ ቢወረወር ይቀለዋል»፣ «ሌላዉን የሚያሰናክል ከሆነ ስጋ ባልበላ ለዘላለም ልቀር»፣ «እኔ መምህር ና ጌታ ሆኜ ይሄን ካደረኩ ( የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ) እናንተም እንዲሁ አደርጉ» የመሳሰሉትን ትእዛዛት እናነባለን።
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በአንድ በኩል ለክርስቲያናዊ ሕግና ቀኖ ቆመናል እያልን፣ በሌላ በኩል ከቤተ ከርስቲያን ሕግና ቀኖና በላይ የሆነዉን የጌታ ክርስቶስን ትእዛዝ ወደ ጎን እያደረገን፣ ያለ ይመስለኛል። ቀኖና፣ ወንጌልንም መደገፍ እንጂ ከወንጌል በተቃራኒ መቆም እንደሌለበት የዘነጋን ይመስለኛል። ዋናዉን ረስተን ትንሹ ነገር ላይ ስናከር ነው የሚታየዉ።

እንግዲህ «ንስሐ እንግባ ። ክርስትናችንን ፣ የክርስቶስ ተከታይና አገልጋይነታችንን፣ በምንለብሰው ካባ ሳይሆን በስራችን አናሳይ» እላለሁኝ። ከወንድሞቻችን ጋር መስማማት አቅቶን፣ ይቅር መባባል ከብዶን፣ «እኔ ነኝ ፓትሪያርክ መሆን ያለብኝ …እርሱ ነዉ መሆን ያለበት ..» እየታባባልን፣ በእልህ መንፈስ ተሞልተን፣ በአኮቴተ ቁርባን ወቅት ስጋ ወደሙን በእጃቸችን ለመያዝ መቆማችን መቅሰፍት ነዉ» እላለሁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት። እንደ እዉነቱ ከሆነ ፣ ከኛ በኋላ ክርስትናን በተቀበሉ አገሮች የሚኖሩ ዜጎች፣ እምነት የሌላቸውን ክርስቲያን እያደረጉ ባለበት ወቅት፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ በምስራቅ አፍሪካ ወንጌልን ለማሰራጨት የበለጠ መነሳት አይገባትም ነበርን ? በሚሊዮን የሚቆጠሩ እራሳቸውን ኦርቶዶክ ክርስቲያን ነን የሚሉ፣ ነገር ግን የስላሴንና የስጋዌን ሚስጥራትን እንኳን በደንብ የማያዉቁ አሉ። ብዙ የኦርቶዶስክ ልጆች በሃሺሽ፣ በጫት፣ በተለያዩ ከምእራባዉያን አገራት በመጡ ጸረ-እምነት ተግባራት የተጠመዱ ፣ በስም እንጂ ከክርስትና ጋር በተግባር የማይተዋወቁ ናቸው። አብያተ ከርስቲያናትን ከሚያዘወትሩት ይልቅ፣ የዳንኪራ፣ የጫትና የካቲካላ ቤቶችን የሚያዘወትሩ በጣም ይበዛሉ።
ታዲያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን፣ በሯን ለመንፈስ ቅዱስ ከፍታ፣ እራሷን ከመንፈሳዊ ባርነት አውጥታ፣ የማያምኑ አሕዛብን እንዲያምኑ ማድረጉን ለጊዜው እንተወዉና፣ ኦርቶዶክስ ነን የሚሉትን እንኳ በቃለ እግዚአብሄርና በእምነት ማጠንከርና ማሳደግ አልነበረባትምን ? የኦርቶዶክስ አማኞች ፣ ወንጌልን አልፎ አልፎ ቅዳሴ ሲመጡ በሚሰሙት ብቻ ሳይወሰኑ፣ ሌት ተቀን የሚያነቡትና የሕይወታቸው መመሪያ የሚያደርጉት፣ ሳይፈሩም በአደባባይ የሚያወጁት መሆንስ አይገባምን ?
ነገር ግን መንፈሳዊ አባቶች፣ እረኝነታችንን ረስተን፣ መንጋዉን ለተኩላ ለመስጠት እየተዘጋጀን ያለ ይመስለኛል። ጥል ባለበት እግዚአብሄር የለም። «የትእቢተኞችን ቀስት ይሰብራል፣ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንዳለችዉ እናታችን ቅድስት ማርያም፣ እግዚአብሄር ትእቢትን ይጸየፋል። ትእቢት ባለበት ቦታ እግዚአብሄር የለም። በመሆኑም የኦርቶዶስክ አባቶች እርቅ መመስረት ካልቻልን፣ ከእግዚአብሄር ክብር ይልቅ የኛን ክብር ካስቀደምን፣ በግልጽ በስራችን የምንናገረዉ፣ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንደሌለ ነዉ። እግዚአብሄር የሌለበት ቦታ ደግሞ እንዲሁ መቆዘም እንጂ በረከት የለም።

እስቲ ትንሽ ጠለቅ ልበልና፤ ሁለቱ የኦርቶዶክስ ሲኖዶሶች፣ ሊስማሙበት ካልቻሉበት ነጥቦች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰውን ለማየት እንሞክር።
ዉጭ አገር የሚገኘዉ ሲኖዶስ አራተኛው ፓትሪያርክ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፣ የፓትሪያክነት ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ይፈልጋል። አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ ደግሞ «ለሃያ አመት የተሰራዉን ሥራ መቀልበስ ነዉ። አምስት ተብሎ ወደ አራት መሄድ አይቻልም» በሚል አራተኛዉ ፓትሪያርክ ተመልሰው አራተኛ ወይንም ስድስተኛ ሆኖ መቀጠላቸዉን ሊደግፉ አልቻሉም። ‹‹አራተኛው ፓትርያርክ ወደ አገራቸው ተመልሰው ደረጃቸውና ክብራቸው ተጠብቆ፣ የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው በመረጡት ቦታ በፀሎት ተወስነው እንዲኖሩ፣ ነገሮቹም ሆነ በእሳቸው አንብሮተ ዕድ የተሾሙ ቀኖናውን በቀኖና አሻሽሎ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን ሰጥቶ፣ ስማቸውን መልሶ በሀገረ ስብከት መድቦ ለማሠራት፣ ፈቃደኛ ነዉ» ሲል በአዲስ አበባ ያለዉ ቅዱስ ሲኖዶስ የመጨረሻ አቋሙን ያሳዉቃል። አሜሪካ ያለዉ ሲኖዶስ መልስ በመስጠት «አቡነ መርቆሪዮስ ፓትሪያርክነታቸውን መቀጠል አለባቸው። የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና መጠበቅ አለበት» በሚል አቋሙን በድጋሚ የሚያጸና መግለጫ ያወጣል።

ከሁለቱም ወገኖች ላሉ አባቶች እንግዲህ የምለው ይሄን ነዉ። እግዚአብሄርን እንጂ ሰዉን አንፍራ። አላስፈላጊ መግለጫዎችን ከመስጠት እንቆጠብ። አለመስማማት፣ ለጊዜዉ መጋጨት ያለ ነዉ። ሐዋርያዉ ጳዉሎስና በርናባስም አንድ ወቅት ተጋጭተዉ ነበር። እግዚአብሄር ለቁጣ የዘገየ በምህረቱ ግን ባለጠጋ የሆነ አምላክ ነዉ። «የልጁ የየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጢያት ሁሉ ያነጻል« ተብሎ እንደተጻፈ፣ ለሰራናቸው ሐጢያቶች እና ስህተቶች እግዚአብሄር ይቅር ይለናል። የትላንትናዉን ትተን፣ ዛሬ መልካምን ነገር ለማድረግ እንዘጋጅ። ዛሬ እራሳችንን ለፍቃዱ እናስገዛ። ጆሮዎቻችን የጥላቻን እና የእልህ ወሬዎችን ከመስማት የተደፈኑ ይሁኑ። ሁላችንንም ሊያስማማ የሚችል መፍትሄ ማግኘት ይቻል ዘንድ እንመካከር፣ በጋራም አብረን እንጸልይ።
አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ፣ ፓትሪያርክ የሚሆኑ እጩዎችን ተቀበሎ ስድስተኛዉን ፓትሪያርክ ለማስመረጥ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ እያነበብን ነዉ። በቅርቡም አዲሱ ፓትሪያርክ ማን እንደሚሆኑ እንሰማለን። ይሄ ደግሞ ለሃያ አመታት የነበረዉ የቤተ ክርስቲያን መከፋፋልና እርግማን እንዲቀጥል ሊያደርገው አይገባም። የእርቁን ሂደት ይረዳ ዘንድ፣ የኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያንን አንድ የሚያደርግ፣ አንዳንድ ሃሳቦችን በትህትና ለማቅረብ እሞክራለሁ። እነዚህን ሃሳቦች ሳቀርብ ፣ አገር ቤት ያሉም ሆነ በአሜሪካ የሚገኙ አባቶች፣ ትንሽ ሊቆረቁራቸው ቢችልም ትኩረት ሰጠዉ ሃሳቤን ያስተናግዱታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

1.አዲስ አበባ ያሉም ሆነ በዉጭ የሚገኙ አባቶች፣ መግለጫዎችን ከማዉጣት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። መግለጫ ማዉጣት ማንነትን አይሳይም። መግለጫ ማዉጣት ክርስትናን አያሳይም። «በፍሪያችሁ ያውቋቹሃል» ተብሎ እንደተጻፈ ክርስትናችንን፣ የክርስቶስ አገልጋይነታችንን፣ የቤተ ክርስቲያን መሪነታችንን በስራችን ነዉ ማሳየት የሚኖርብን። በስራችን ክርስትና ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ አርዓያ በመሆን፣ ለምንመራው ምእመን ማስተማር አለብን።

2.በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖድስ፣ ስድስተኛዉን ፓትሪያርክ በቅርቡ ያሳዉቀናል። አዲሱ ፓትሪያርክ በዉጭ አገር ካለዉ ሲኖድ ጋር በመነጋገር፣ አንድነት የሚፈጠርበትን፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የወረደው እርግምን የሚገፈፍበትን ሁኔታ በቀዳሚነት ማመቻቻት ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል። «ከሁሉም በላይ መሆን የሚፈልግ የሁሉም አገልጋይ ይሁን» እንዳለ ጌታችን ኢየሱስ ፣ ፓትሪያክነታቸዉ የከፍታ ቦታን ለማግኘት ሳይሆን፣ ለማገልገል፣ የተበተኑትን ለማሰባሰብ፣ የተሰበረዉን ለመጠገን መሆን አለበት።

3.አቡነ መርቆርዮስ በእድሜ ባለጠጋ የሆኑ አባት ናቸዉ። በርሳቸው ምክንያት ክፍፍሉ መቀጠል የለበትም። ለሰላም ሲሉ ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቷ አንድነት ሲሉ፣ ለእግዚአብሄር ክብር ሲሉ፣ እግር ማጠብ ይኖርባቸዋል። እርግጥ ነዉ በቆኖናዉ መሰረት ፓትሪያርክ ሳይሞት ፓትሪያርክ አይሾምም። ከዚህ በፊት ስህተቶች ተሰርተዉ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በፊት በደል ተፈጽሞባቸዉ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁን ከዚያ አልፈዉ መሄድ ያለባቸው ይመስለኛል። ይቅር ማለት መቻል ያለባቸው ይመስለኛል። ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው ቢለቁና አዲስ ለተመረጡ ፓትሪያርክ እዉቅና ቢሰጡ፣ የዲያቢሎስን ሥራ ነበር የሚያፈርሱት። በመሸነፍም ያሸንፉ ነበር።

እዚህ ላይ በቅርቡ የካቶሊኩ ፖፕ ያደረጉትን መመልከት ሊጠቅም ይችላል። «ቤተ ክርስቲያኔን ለመምራት የአካል ጥንካሬ የለኝም። የኔ ፖፕ ሆኖ መቀጠል ጥሩ አይደለም። በኔ ምትክ ሌላ ሊሰራ የሚችል ፖፕ መመረጥ አለበት» ብለው፣ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሲሉ፣ ፖፕ ቤኔዲክት ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ነዉ። አቡነ መርቆሪዮስም እንደ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ጥቅም አስቀድመዉ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷን አንድ ለማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀኖና በጠበቀ መልኩ፣ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

እንግዲህ እንደ ክርስቲያኖች ትልቅ መንፈሳዊ ዉጊያ ከፊታችን ይጠብቀናል። ጸረ-ወንጌል የሆነው ዲያብሎስ፣ በታሪክ ትልቅ ስራን የሰራች ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም እየጣረ ነዉ። በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ከመቼውም በበለጠ አጥብቆ መጸለይና መጾም ይኖርበታል። በወጡት፣ ጠቃሚ ያልሆኑ መግለጫዎች ተስፋ መቁረጥ የለብን። ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጠም። ከንግስት አስቴር መማር አለብን። አማሌቃዊዉ ሃማ እሥራዔላዉያንን ለመጨረስ አዋጅ አሳወጀ። እነ አስቴር ጾም ጸሎት አወጁ። በእግዚአብሄር ፊት አነቡ። አዋጅን የሚሽር ሌላ አዋጅ ታወጀ። ሃማ መርዶኪዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ። ሃሌሉያ።

እንደዚሁም እኛ በእምነት፣ በጾምና በጸሎት እግዚአብሄር ፊት ከቀረብን፣ ተአምራት ማየት እንችላለን። ቤተ ከርስቲያንን ከመፈራረስ ልናድናት እንችላለን። አንድነቷን ማስጠበቅ እንችላለን። ከርግማን ወጥታ ፈረንጆች ከሚያደርጉት በላይ ለወንጌል መስፋፋት የተሰለፈች ልናደርጋት እንችላለን።

እዚህ ላይ አንድ ትልቅ ቁም ነገር አንርሳ። በቤተ ክርስቲያኒቷ ያሉትን ችግሮች በማባባስ፣ የፖለቲክ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ፣ ዲያብሎስ እራሱ እየተጠቀመባቸው ያሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ይኖራሉ። በፖለቲካ እንቅስቃሴ ዉስጥ ገብቶ መሳተፍ የራሱ ቦታና ጥቅም ቢኖረዉም፣ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ግን፣ የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራው በፖለቲካ መድረክ አይደለም። የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራዉ እንደ ወገዛ፣ ስድብ፣ መግለጫ ማዉጣት በመሳሰሉ የፖለቲካ መሳሪያዎችን በመጠቀም አይደለም። የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራዉ በመንፈሱ ነዉ። በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ችግር የሚፈጥሩ ካህንም ሆነ ጳጳስ ካሉ፣ የሚበቀላቸው እራሱ እግዚአብሄር ነዉ። «ፍርድ የኔ ነዉ!» ይላልና የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር።
በመሆኑም የምናቀራርብ፣ የምናስታርቅ፣ ልዩነቶችን የምናጠብ፣ መግባባት ንግግርና መቀባበል እንዲኖር የምናበረታታ ፣ የተሳሳተን በጨዋነት የምንገስጽ፣ የወደቀን የምናነሳ፣ የሚያጠፋን ከጥፋታቸውዉ የምንመልስ እንሁን እንጂ፣ በእሳት ላይ ነዳጅ አናርከፍከፍ።
እግዚአብሄር ልቦናችንን ለፍቅሩ አይምሯችንን ለጥበቡ ይክፈትልን !


የህወኃት ጉዞ የርስ በርስ የመበላላት ታሪክ ነው ከትእዝብት አድማሱ

ህወሃት ሊወድቅ ነው በያሬድ አይቼህ

$
0
0

(ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!)

ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነጻነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።

ፓለቲካ አይነት ፡ አይነት አለው። የምርጫ ፓለቲካ እና የነጻነት ፓለቲካ አንድ አይደሉም። የምርጫ ፓለቲካ ንጹህ ነው ፡ ጭምት ነው። የነጻነት ፓለቲካ ግን ይጨክናል ፡ ይቆሽሻል።

የአገራችን ዘመናዊ የፓለቲካ ታሪክ ሲቃኝ በተደጋጋሚ የሚታየው ፡ ባለፉት 40 ዓመታት አብይ ለውጥ አራማጆች ከየዋህነታቸው እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልታቸው የተነሳ ለአገራቸው የነበራቸው ራዕይ ተጨናግፏል ፡ መክኗል ፤ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ብዙ ታላላቅ ሊሂቃኖቻችንም በከንቱ ጠፍተዋል።

ካለፉት ያልተሳኩ የነጻነት ሙከራዎች ተምረን ፡ አሁን ያለውን ትልቅ የነጻነት ዕድል በተሳካ መልኩ ለመጠቀም ከፈለግን ፡ ለነጻነታችን መጨከን እና መቆሸሽ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኗል።

ሙከራ 1፦ መንግስቱ እና ገርማሜ ነዋይ

አፄ ኃይለስላሴ ላይ ተደርጎ የነበረው የ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አራማጆች ፡ ወንድማማቾቹ መንግስቱ ነዋይ እና ገርማሜ ነዋይ ፡ ውጥናቸው ለምን እንደ መከነ ሲመረመር ዋናው ምክንያቱ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልት ነው።
የንጉሳዊው ስርዓት በኢትዮጵያ ጭሰኛ ላይ ያደርግ የነበረውን ጭቆና ችላ ማለት ያልቻሉት ወንድማማቾች ፡ ንጉሱን ከስልጣን አስወግደው ፍትሃዊ የመንግስት እና የምጣኔ ሃብት ስርዓት ለመቅረጽ መመኘታቸው ድንቅ ነበር።

ሆኖም ግን እቅዳቸው ያልበሰለ ፡ ያልጨከነና ለመቆሸሽ ያልደፈረ ነበር። ከዚያም የተነሳ መፈንቅለ መንግስቱ ከሸፈ። መግደል የነበረባቸውን በጊዜው አለመግደላቸው ፡ ማሳተፍ የነበረባቸውን ባለማሳተፋቸው ፡ መቅደም የነበረባቸውን ባለመቅደማቸው የተነሳ የነበራቸው ራዕይ ተኮላሽቷል። የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች የዋህነታቸውና ፡ ንጹህነታቸው አስበልቷቸዋል።

ሙከራ 2፦ ጄኔራል መርድ ፡ ጄኔራል አምሃ እና ጄኔራል ፋንታ

በ1980 ዓ.ም የደርግን ስርዓት የተቃወሙ ጄኔራሎች ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያምን ከስልጣን አንስተው ፡ በጊዜው ከነበሩ አማጽያን ጋር ተወያይተው አገራዊ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር መፈንቅለ መንግስት ሞክረው ነበር። ሙከራው አልተሳካም ነበር። ያልተሳካበትም ምክንያት ያው ንጹህና ጭምት ስልት ነበር።

የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የተከሰተው ኮ/ል መንግስቱ ወደ ምስራቅ ጀርመን ለጉብኝት ሲሄዱ ነበር። በዚህ ወቅት የጠንሳሾቹ ትልቁ ስህተት ተፈጸመ። ስህተቱም “ኮ/ሉ ይበሩበት የነበረውን አውሮፕላን አየር ላይ እንዳለ ይመታ” የሚለውን ሃሳብ አለመቀበላቸው ነው።

“አውሮፕላኑ የህዝብ ንብረት ነው” ፡ “በአውሮፕላኑ ውስጥ ፡ ከኮ/ል መንግስቱ ሌላ ፡ የሌሎችን ሰዎች ህይወት ማጥፋት የለብንም” ከሚሉ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልቶች የተነሳ ኮ/ሉ ምስራቅ ጀርመን በሰላም ደረሱ። መፈንቅለ መንግስቱም መከነ።

የግንቦት 1980ው ሙከራ ከየዋህነት እና ከገርነት የተነሳ ከሸፈ። ያኔ ጄነራሎቹ ጨክነው እና ቆሽሸው ቢሆን ኖሮ ፡ አሁን አገራችን የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች ግዛት ከመሆን ይልቅ ፡ የህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የመመስረት አጋጣሚያችን ሰፊ ይሆን ነበር።

ሙከራ 3፦ አዲስ አጋጣሚ

አገራችን ላለፉት 21 ዓመታት ስታምጥ ኖራ አሁን ከምጧ የምትገላገልበት ወቅት ላይ ደርሳለች። ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊወጣበት የማይችለው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ህወሃት እንደ ቀድሞው ተመልሶ ሊያንሰራራ አይችልም።

ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት የነጻነት ሙከራዎች ተምረን አሁን ያገኘነውን አጋጣሚ በመጠቀም የስልጣንን ልጓም ለህዝብ ካላስጨበጥን ፡ ከጭምት እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልት የተነሳ ፡ አዱሱ አጋጣሚ ሊያመልጠን ይችላል።

ስለሆነም ፓለቲካችን የምርጫ ፓለቲካ ሳይሆን የነጻነት ፓለቲካ ስልትን መጠቀሙ ቁልጭ ያለ ጉዳይ ነው። ሳንጨክንና ሳንቆሽሽ ነጻነት አይኖርም። በፍጹም አይኖርም። በጭራሽ አይኖርም። ልብ በሉ! ካለፈው ተምረን የተለየ ስልት ካልተጠቀምን ወደ ባርነት እና ወደ ጭቆና ተመልሰን እንዳረጋለን።

ምን እናድርግ? እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!

ግልጽና ቁልጭ ያለ የነጻነት ትግል አማራጭ የሌለው ስልት ነው። በዚህ ወቅት “የትግራይ ህዝብ ወያኔ ነው ወይስ አይደለም?” የሚለውን የሞኝ ዘፈን ትተን ነገሩን ቀለል ማድረግ ነው። የትኛው ትግሬ ‘ነቅዟል’ ፡ የትኛው ትግሬ ‘አልነቀዘም’ የሚለው የሚታወቀው ከነጻነት በኋላ ብቻ ነው።

በነጻነት ትግል ወቅት ንጹሃን ሰዎች ሰለባ መሆናቸው የማይቀር ነው። ለዚያ ህሊናችንን እናስፋ። ህወሃት በስብሶ እንደ ተነቃነቀ ጥርስ ሆኗል ፡ የሚመነግለውና የሚነቅለው የህዝብ መስዋዕትነት ብቻ ነው።

በዚህ ወቅት ፡ ጽዋው እስኪሞላ እና የሃይል ሚዛኑ እስኪያዘነብል ድረስ ፡ ቢያንስ እንደ ግብጽ አብዮት 1 ሺ ሰማዕታት ፡ ቢበዛ ደግሞ እነደ ሶርያ የነጻነት ትግል ከ30 እስከ 60 ሺ ሰዎች ሊሰዉ እንደሚችል በመገንዘብ ህሊናችንን እናዘጋጅ። የሚሰዉ ይሰዋሉ።

ጥቂቶች ተሰውተው 80 ሚሊዮኖች ነጻ ይሆናሉ።

አዎ! የሚሰዉ ይሰዋሉ። “ለምን የድሃ ልጅ ይሙት?” “ለምን ዲያስፓራ አይዋጋም?” ለሚሉት የሰነፎችና የቱልቱላዎች ንትርክ አሁን ቦታና ጊዜው አይደለም። ህወሃት የትግራይን ህዝብ በዘፈን እና በከንቱ ሽንገላ አታሎ የእሳት ራት አድርጐ ስልጣን ላይ ተንፈራጥጧል። ዛሬ ለአገራችን ነጻነት የሚሰዉ ወገኖቻችን ይሰዋሉ።

ደም ሳይፈስ ነጻነት አይኖርም! ይህንን መራራ እውነታ እንቀበል። እንቆሽሽ። ከነጻነት በኋላ እንጸዳለን ፡ እንቀደሳለን።

ሌላው ጉዳይ ፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ ፡ በተለይም በትግራያን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃት መገንዘብ ነው። በህብረተሰባችን ውስጥ ትግራያን አበይት የስርዓቱ ተጠቃሚና ‘ባለጊዜ’ ናቸው ፡ የሚለው እምነት በሰፊው ስላለ በልዩ ልዩ ክልሎች የሚኖሩ ትግራያን ላይ ጥቃት ሊደርስ ይችላል። ያ አይነቱ ክስተት ሊያስደነግጠንም ፡ ከነጻነት ትግላችን ሊያደናቅፈንም አይገባም።

የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች እና ‘ባለጊዜዎች’ ቢኮረኮሙ ፡ ኩርኩሙን ታሪክ ሚመዘግበው ለነጻነት ትግል ከሚከፈለው ዋጋ ጋር ደምሮ ነው። እግረ መንገዳችንን እነርሱንም ነጻ እናወጣቸዋለን።

ያም ሆነ ይህ፦ “ጅብ ከሚበላህ ፡ ጅብ በልተህ ተቀደስ።” 

ያረቢ ኑ ባሲ!!!..ያረቢ ኑ ባሲ…ኢትዮጵያዊያንን ከነ ህይወታቸው እየቀበሩ መቅጣት.. በግሩም ተ/ሀይማኖት

$
0
0

አንድ ወዳጄ ከወዳጅም የሞያ ጓደኛዬ የሆነው ጋዜጠኛ ግርማ እንድሪያስ የእህቱ ልጅ በባህር ወደ የመን ሲመጣ መያዙን ነገረኝ፡፡ ትንሽ ቆየ እና እህቱ ማለት የተያዘው ልጅ እናት ደወለች፡፡ እናት ጉዷን አላወቀችም፡፡ የመን መጥታ ችግሩን አላየች በምን ትወቅ? ደግሞስ ችግሩን ለማወቅ የግድ የመን መምጣት አለባት እንዴ? የለባትም፡፡ በየጊዜው ይጻፋል፡፡ ይነበባል፡፡ ግን ማንበብና ማስተዋል አንድ አይደለም፡፡ ልጇ ያን ነው የሆነው፡፡ ልጅ በሚውልበት እናት አትውል፡፡ በዛ ያለ ሰው እየሰማ እያየ ነው መልሶ በባህር የሚመጣው፡፡ ልጇ ደላሎች ጋር እንዳለና ወደ ሳዑዲያ ሊገባ እንደሚፈልግ ደላሎቹ ለማድረስ 3500 የሳዑዲ ሪያል መጠየቃቸውን ነገረችኝ፡፡

ወዲያው የገባኝን ያህል ገባኝ፡፡ የተባለውን ገንዘብ ብትልክላቸው እንደማያደርሱት አውቃለሁ፡፡ በዛ ላይ ልጁ ገንዘብ የሚልክልህ ሰው ስልክ ቁጥር እያሉ ሲያዋክቡት፤ ሲያሰቃዩት እናቱ ጋር አስደወለ፡፡ ስልኩ ስላልተነሳ ግርማ እንድሪያስ ጋር አውሮፓ ደውሏል፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ከተደወለ ደግሞ እንዲህ በዋዛ አይፋቱም፡፡ ለግርማም ሆነ ለእህቱ አጓጓዥ ደላሎች ጋር ሳይሆን ያለው አፋኞች መሆናቸውን ብናገር አረ አይደለም ደላሎች ናቸው ተባልኩኝ፡፡ ክርክሩን በዝምታ አልፌ ልጁ እኔ ወደ አለሁበት ሰነዓ እንዲመጣ በተሰጠኝ ስልክ ቁጥር ደወልኩ፡፡

‹‹እህ ማነህ ጃል..ምን ኮነክ ነው? ማንን ፈለክ..›› የሚል ገጠርኛ ቃና ያለው አማርኛ ተናጋሪ አወራኝ፡፡ ልጁን እንዲያቀርብልኝ ስሙን ነገርኩት፡፡ ማውራት ያለብኝን ያህል አወራሁ፡፡ አከል አድርጌ ሳዑዲ ሳይሆን የሚሄደው ወደ ሰነዓ እንዲመጣ ምን ያህል እንደሚጠይቁ ተነጋገርኩ፡፡ ሁኔታዎችን እኔ በማውቀው መንገድ ለማስኬድ ከአፋኞቹ ጋር ተደራደርኩ፡፡ 1500 የሳዑዲ ሪያል እንድልክ ነው የተስማማነው፡፡ የተባለው ገንዘብ ተላከልኝና ላኩኝ፡፡ ልጁን ለመልቀቅ ማንገራገራቸው ለምን እንደሆነ ስለማውቅ ታግሼ እጠብቃለሁ፡፡ ገንዘቡ ከተላከላቸው እንደማይደበድቡት በተደጋጋሚ በሰማሁት መረጃ አውቃለሁ፡፡ ወዲያው ባይሆንም አንገራግረው ከቀናት በኋላ ለቀውታል ይደውልልሀል ተባልኩ፡፡

ሁለት ሶስት ቀን ምንም የለም፡፡ የሚያደርሱት ሀረጥ የተባለው ቦታ ድረስ ነው፡፡ ካለሁበት ሰነዓ 750 ኪሎ ሜትር አካባቢ ስለሚርቅ ይህን ያህል ርቀት ብቻውን ከመጣ ድጋሚ በሌሎች እንዳይያዝ እና ለእነሱ ስለተከፈላቸው ለሌላ እንዳያሳልፉት ተነጋግረን መክፈል ያለብኝን መሰዋእትነት ከፍዬ ለማምጣት ጉዞ ሀረጥ ወደሚባለው ቦታ አደረግሁ፡፡ ይህ ቦታ በግሩፕ የተደረጁ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞች ባህር ሲሻገሩ አፍነው ብር አስልኩ ብለው የሚያሰቃዩበት ቦታ እንደሆነ በተደጋጋሚ ዘግቤያለሁ፡፡ ወገኖቻችን ወደሚሰቀዩበት ቦታ ሀሙስ እለት(የካቲት 7 ቀን) እንደሚፈልጉኝ እያወኩ ስለሆነ የምሄደው ካልድ ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ነው አካሄዴ፡፡ የእናትንም ሆነ የጓደኛዬን ጭንቀት ስላወኩ ስራዬን ትቼ፣ ካለችኝ ሳንቲም ላይ ቀናንሼ፣ ራሴን ለውጬ..ነው ችግር ቢገጥመኝ ብዬ ካልድን አስከትዬ ጉዞዬን የጀመርኩት፡፡ አሳዛኙ ነገር እኔ እናት ተግባብተን አልተግባባንም፡፡ ወይም አልተማመንም መሰለኝ፡፡ ያለምን ጥቅም ይህን ያህል መሰዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቴ፣ ትንስፖር ማውጣቴ፣ ስራዬን ጥዮ መሄዴ..ምን ቢጠቀቀም ነው ያሰኝ ይችላል፡፡ ከዚህ በፊት ብዛ ያለ ሰው ጥቅምህ ምንድን ነው? የሚሉኝ ስላሉ አይገርመኝም፡፡ ግን ከህሊና እርካታን መን አይነት ጥቅም እንለካው ይሆን? የጀመርኩት ጉዞ ትዕዝ የሚባለው የየመን ሶስተኛ ከተማ ላይ ተገደበ፡፡

ትዕዝ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎችና የሰጡኝ መረጃ ግን ኢትዮጵያዊያን ምን እየጠበቅን ነው? ከዚህ በላይ ጭካኔስ በአለማችን ላይ ይኖር ይሆን? ያሰኛል፡፡ ትዕዝ የሚባለው ቦታ ተቅብሎ ያስተናገደን ልጅ ጋር የመጣ አንድ እንግዳ..ውይ እንግዳ አልኩ እንዴ? እኛው አስጠርተነው መሆኑን ዘነጋሁ፡፡ ታክሲ ስላለው እና ወደዛ መንገዱን ያውቃል ስለተባለ ያስጠራነው እኛ ነን፡፡ በጫዎታ ጫዎታ ስላየው እና ስለሚደረገው ያወጋን በስንተኛው ዙር ወግ ላይ እንደሆን በማላስታውሰው ጊዜ ‹‹..እነዚህ የሚያግቱት ጋር እኮ ሰው በቁሙ እየቀበሩ ማሰቃየት ጀምረዋል፡፡…›› ሰውነቴን ውርር አደረገኝ፡፡ እስካሁን ያልሰማሁት በመሆኑ ደነገጥኩኝ፡፡ በእርግጥ በአንድ ወቅት ወደ እዛ ስሄድ የሞተ ኢትዮጵያዊ የሚቀብሩበትን ቦታ አይቼዋለሁ፡፡ በጣም በጣም ሰፊ ነው፡፡ ግን እንዲህ በህይወት ያለ ሰው ይቀብራሉ ሲባል አልሰማሁም፡፡

‹‹ቅብር!..ቅብር?…በምን አወክ አንተ አይተሀል?›› ስል ጠየኩት፡፡ አላንገራገረም፡፡ አብሮት የመጣውን ልጅ እሱ ከባህር እንደመጣ ይዘውት ከእነሱ ጋር ለመስራ ሞክሮ ነበር፡፡ አሁንም ሄድ መለስ ይላል፡፡ አለና ልንቁስ ያለ ልጅ አሳየኝ፡፡ ወገኑን ከሚያሰቃዩ ጋር በመስራቱ ከሱ ጋር ማውራት ተጠየፍኩት፡፡ በጠላትኛ አየሁት ግን የሚሰጠኝን መረጃ እፈልገዋልሁ እና ሞባይል ስልኬን የተደወለልኝ አስመስዬ ነካካሁና ሪከርድ የሚለው ላይ አደረኩኝ፡፡ እንዲነግረኝ ጠየኩትም፡፡

‹‹አዎ! ግን ያየሁት ልጁ ራሱን ነው፡፡ የተቀበረውን፡፡››
‹‹ከተቀበረ ከየት አየኸው?››
‹‹እስከ አንገቱ ድረስ ቀብረውት አሰቃይተውት ከዚህ ከወገቡ በታች አልታዝህ ብሎት እየተንፏቀቀ ህክምና እንዲያገኝ ሀረጥ ካምፕ ሲገባ አይቻለሁ፡፡›› አለኝ፡፡ አላናገርከውም? ብዬ ለየጠኩት የሰጠኝ መልስ ግን በጣም ሰቅጣጭ ነበር፡፡ ልጁ በተፈጥው መስማት የተሳነው ስለሆነ እንዴት ላውራው አለኝ፡፡ ከዛ ወዲህ ወይም ከዛ በፊት እንዲህ አይነትነ ነገር አይቶ ሰምቶ እንደሆነ ስጠይቀው ከዛ በኋላማ እዚሁ ትዕዝ ውስጥ ትላንት የገባ ልጅ አለ፡፡ እዚህ ማር መሸጫ መደብሩ ጋር መኪና ከሚያጥቡ ልጆች ጋር አሁን ስመጣ ራሱ አይቼዋለሁ፡፡ ቀብረውት አሰቃይተውት አንድ አይኑን አጥፍተው ለቀቁት፡፡

አስቡት አይኑን አጥፍተውት ሲበል የሚሰማውን ስሜት አስቡት…

ጫዎታውን አቋርጦ መሄዱ ተሰማኝ እንጂ የተባለው ቦታ ሄጄ ልጁን ማናገር ፈለኩ፡፡ ቀልቤ ፈጽሞ ከእነሱ ዘንድ አልነበረምና ካልድን ጠቅሼው መጣን ብለን ወጣን፡፡ ልጁን አፈላልጌ ለማግኘት ቢከብድም ከብዙ ድካም በኋላ አገኘነው፡፡ ሊያወራልን ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ እንዲያወራልን በተደጋጋሚ ያደረኩት ሙከራ ስላልተሳካ ተቃራኒውን አውርቼ ሀቁን እንዲነግረኝ ማድረግ አማራጭ ነውና አደረኩት፡፡ ‹‹እንዴት አይንህን ሊያጠፉህ ቻሉ? ገንዘብ እንድታስልክ ሲሉ በጣም ይንከባከባሉ ሲባል ነው የሰማሁት፡፡

‹ምንድን ነው የምታወራው? የምታወራውን ታውቃለህ? እብድ..እነሱ ናቸው የሚንከባከቡት?..›› ሲል ጀመረ፡፡ እኔም የምፈልገው ይሄን ነውና ስድቤን ጠጥቼ ለመስማት ጆሮዬን በተጠንቀቅ አደረኩ፡፡ ቀጠለ…‹‹..እንኳን ሊንከባከቡህ ገና ጊቢው ውስጥ ስትገባ ነው ዱላው የሚጀምረው፡፡ አስደውሎ የሚያስልክበት ቦታ ያለው አስደወለ፡፡ እኔ ደግሞ ማንም የለኝም፡፡ ቡዙ ተደበደብኩ፡፡ ከየትም አምጥቼ አልሰጠኋቸውም፡፡ እይ!..ይንከባከባሉ ያልካቸው ናቸው ያቃጠሉኝ፡፡
ደረቱ ላይ በሲጋራ ያቃጠሉትን አሳየን፡፡ የበለጠ እንዲጨምርልኝ ፈልጌ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ካንተ ሰማሁ፣ አየሁ..›› አልኩት፡፡

‹‹ሂድና ሀረጥ እይ ምን ታደርቀኛለህ? ይሄን ታዲያ ራሴ ነኝ ያጠፋሁት? ምን ማለት ፈልገህ ነው?..›› አለና አይኑን አሳየኝ፡፡ ‹‹እንዴ ይህን እነሱ ናቸው እንዲህ ያደረጉኝ እንዳትል?..›› ሰምቼ ቢሆንም ፍለጋ የጀመርኩት እንዳላወቀ ሆንኩኝ፡፡ ‹‹እየነገርኩህ? ገንዘብ የሚልክ ዘመድ የለኝም፡፡ በሲጋራ አቃጠሉኝ፡፡ መቀመጫዬ ላይ ላይተር ለኩሰው አቃጠሉኝ፡፡ የሌለኝን ዘመድ ከየት ላምጣ ጉድጓድ ቆፍር ብለው አስቆፈሩኝ፡፡ እስከ አንገቴ ድረስ ቀበሩኝ፡፡ እኔስ ተርፌያለሁ ዝም ብለው ሙሉ ለሙሉ የቀበሯቸው አንድ ሴት እና ሶስት ወንዶች ልጆችን አያቻለሁ፡፡

እኔን አንገቴ ድረስ ቀብረውኝ እነሱ ጫታቸውን እየቃሙ በእኔ ስቃይ ይዝናናሉ፡፡ በመጨረሻም ለ22 ቀን አስቃይተውኝ እንደነገ ሊለቁይ እንደዛሬ የሀይላንድ ውሀ ላስቲኩን ክዳኑን ከፈተው እና አፉን አይኔ ላይ አደረገው፡፡ በቀዳዳው እይ አይንህን ግለጽ አለኝ፡፡ ያው ያዘዙህን ማድረግ ግዴታ ነው ገለጥኩ፡፡ በቂጡ በኩል በሀይል ሲመታው ራስን ስቼ ወደኩ፡፡ ምን ያህል ጊዜ እንደቆየሁ እንጃ ፌቴ ሁሉ ደም ለብሷል፡፡ እንዲሁ አሞኝ ዋልኩ፡፡ አይኔ ግን መውጣቱን ያወኩት ስነቃ ነው፡፡ በማግስቱ ሲለቁኝ መሄድ በሙሉ አልችልም ነበር፡፡ የወጣው አይኔ የሀይላንዱ እቃ ውስጥ እንደተቀመጠ ከድኖት ‹‹አላስልክም ባልከው ብር ታከምበት..›› ብሎ ሰጠኝ፡፡

ምን እንደተሰማኝ አላውቅም፡፡ የነበረኝን ስሜት አሁን መናገር አልችልም፡፡ አጥወልውሎኝ የምወድቅ መሰለኝ እና ካልድን ለገሰን ለመያዝ ዞር ስል በሁለት እጁ ራሱን ይዞ ያለቅሳል፡፡ እኔ ግን ማልቀሱም ሆነ ማሰቡ አልሆነልኝም፡፡ እዚህ ጋር በአንድ ወቅት ሶማሊያ እያለሁ የሚሰቃዩትን አይቼ የጻፍኳትን ግጥም ዳግም ብጠቀማት ወደድኩ….

ዋ!! ማንባት ብችልማ
ያሉትን ይበሉ ብልማ
ጥንድ..ጥንዱን አንዠቅዥቄ
ህቅ!!! ባልኩ ተንሰቅስቄ
ሀዘኔ በወጣ በታወቀ ለሰው
አምቄ ከማልመሰምሰው
እርዱኝ…እርዱኝ እባካችሁ
ትርፍ እንባ ያለችሁ
አልቅሱልኝ ለእኔ አሮ ሞተ ብላችሁ….ከማረርም በላይ ሆኖብኛል፡፡

አፌን ሁሉ ደም ደም አለኝ፡፡ ምሳ እንብላ ብለውም እሺ አላለም፡፡ አሁን ምን አሰብክ? ወደ ሰነዓ ከሆነ የምትሄደው አብረን እንሄዳለን አልኩት፡፡ ረድዓ የሚባለው ቦታ ሄዶ ባለ እርሻ ሰዎች ጋር ተቀጥሮ ትንሽ መስራትና ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ እንዴት ረድዓን የምትባለውን ቦታ እና እዛ ስራ እንዳለ እንደወቀ ካልድ ጠየቀው፡፡ ከዚህ በፊት እንደመጣና ሳዑዲ አንድ አመት ቆይቶ ተይዞ ድጋሚ እንደተመለሰ ነገረን፡፡ ወዳለው ቦታ ለመሄጃ ከዛሬው ጋር ሁለት ቀን መኪና እንዳጠበ ነግሮን ሳንቲም ከቻልን እንድንሰጠው ጠየቀን፡፡

ይሄ በባህር የሚደረግ ጉዞ ስቃዩን እለት ከእለት እየጨመረ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን አፋኞቹን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት አለመደረጉ አሳሳቢ ነው፡፡ እነሱም በማን አለብኝነት ጭካኔያቸውን እየጨመሩ የፈለጋቸውን እያደረጉ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከየመናዊያን ጋር በጥምረትም ሆነ በተናጠል ሰውን ወደ ሳዑዲያ የሚያጓጉዙትን ኢትዮጵያዊ ደላሎች ለማስያዝ አዲስ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ተሰምቷል፡፡

በ2012 ከ85000 በላይ ኢትዮጵያዊያን በባህር ተሻግረው ወደ የመን እንደገቡ ብሎም ግማሹ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደተጓዙ አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት IOM የሚባለው ድርጅት መግለጹ ይታወቃል፡፡ እኔም በተደጋጋሚ ይህንን መግለጫ ጠቅሻለሁ፡፡ አብዛኛውም ከወሎ፣ ከአርሲ፣ ከሀረር እና ባሌ አካባቢ ነው የሚሰደዱት፡፡ ይህን ያህል ኢትዮጵያዊ የሚሰደደው በኑሮ ችግር ምክንያት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ለዚሁም እማኙ በወሎ ቦረና ወረዳ መካነሰላም የሚባል አነስተኛ ከተማ ውስጥ ከዋለልኝ መኮንን ትምህርት ቤት ከ9 እና 10ኛ ክፍል ብቻ በዚህ አመት ከ500 ተማሪዎች በላይ አቋርጠው ስደት ወተዋል፡፡ ካቋረጡት እና ስደት ከወጡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦቻቸው በዝቅተኛ ኑሮ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ በኩር የተባለው የአማራ ክልል ጋዜጣ በዚህ ወር እትሙ ያሰፈረውን እንደቀልድ የማይታይ ነው፡፡ የፍልሰታችን አስፈሪ ሂደት ወዴት እየተጓዝን እንደሆነ ያመላክታል፡፡

ሰዒድ ሙሳ አህመድ የተባለ ወዳጄ ከገጠር ትምህርት ቤቶች በየአመቱ ትምህርት የሚያቋርጠው ተማሪ ብዛት አስደንጋጭ መሆኑን ጽፎልኛል፡፡ በጽሁፉ ላይ ሀይ ግሩም በደቡብ ወሎ ምዕራባዊ ዞን በረና ዋለልኝ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9-10 ካለው ክፍል ብቻ በ2004 ከ500 በላይ ተማሪዎች እንዳቋረጡ ታውቋል፡፡ ይሄው ወዳጄ ከጻፈልኝ በተጨማሪ አያይዞ የላከልኝ በኩር ጋዜጣ ላይ ከወረዳው አስተዳደር በተገኘው መረጃ በ2004 በአጠቃላይ 4000 በላይ እንዳቋረጡ ዘግቧል፡፡ ወሎ አርባ ወረዳዎች ስላሏት ስሌቱን 40X400 ማባዛት ነው፡፡160.000 አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ጋዜጣው ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት መንግስትን የያዘው ብልሹ ፖለቲካ እንደሆነ ላለመጥቀስ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ አረብ ሀገር ልከው ገንዘብ የማግኘት ፍላጎታቸው ማየል ነው ሲል ዘግቧል፡፡

የዋለልኝ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋው ደመቀ ከአምናው ችግር ዘንድሮም የባሰ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ጋዜጣውን ማየት ይቻላል፡፡

የደም እንጀራ ከቴድሮስ ሐይሌ

የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ በንግሥተ አዜብ የፍርድ ሚዛን ላይ

የቡዳዎቹ ሠፈር የትኛው ነው? ወልደማርም ዘገዬ

$
0
0

የቀድሞው ኢትዮጵያዊ የአሁኑ ኤርትራዊ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኃኔ “ኤርትራ እንደ እናት አገር፤ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም” በሚል ርዕስ በአውሮጳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ጥር ወር 2013 የጻፉትን ጥናታዊ ዘገባ በፍላሼ አሰንብቼ ዛሬ ጧት ቁርሴን አወራረድኩበት፡፡ ኤርትራ ለእርሳቸው የምታስጨንቀውን ያህል ኢትዮጵያም – ባለቤት ያጣችዋ ከርታታዋ ኢትዮጵያም ለእኔ እንደእናት ሀገር ታስጨንቀኛለችና የተሰማኝን ልናገር ብዕሬን አነሳሁ፡፡

ግን በዚህች የተረገመች ሀገር – በዚህ የዜጎች መብት ክፉኛ በሚረገጥባት ሀገር የመብራት መጥፋት በየደቂቃው ስለሚከሰት በምፈልገው ፍጥነት መጨረሴን እጠራጠራለሁ፡፡ አንዳንዴ በቀን ለቁጥር ለሚያታክት ጊዜ ያህል መብራት ይቆራረጣል፤ አሁን ድርግም ይልና ከደቂቃዎች በኋላ ሊመጣ ይችላል፤ የምትሠራውን ቅጥ ያሳጣብሃል – በልጆቼ አነጋገር ‹ሙድህን ይሠርቅብህ›ና ልትሳነፍ ባስ ሲልም ልትጽፍ ያሰብከውን ከነጭራሹ ልትተወው ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ በኛ መንደር በቀደም ዕለት የጠፋ ከ27 ሰዓታት በኋላ ትናንት ማታ ነው መብራት የመጣልን፡፡ ስልኩም ውኃውም እንደዚሁ ነው፡፡ የቤት ስልክ ከሚሠራበት ጊዜ የማይሠራበት ይበልጣል፡፡ የአንዱን ሊጠግኑ ሲመጡ የሌላውን አበላሽተው ሊሄዱ ይችላሉ – ጠርተሃቸው በመቁሽሽ እንድታሠራቸው፡፡ ውኃ ወር እስከወርም ላታገኝ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ማንን ትጠይቃለህ? በየቢሮው አናት ‹የዚህና የዚህ የሥራ ሂደት ባለቤት› የሚል ጽሑፍ ተለጥፎ ብታይም ማንም ጉዳይህን ከቁብ የሚጥፍልህና የሚያነጋግርህ ሰው የለም፡፡ ስቃይ ነው ልጄ፡፡ የዴሞክራሲው ነገር እዬዬም ሲዳላ ነውና አታስበውም፡፡ አሁን በአንጻራዊነት ከሚታዩ መልካም ነገሮች ውስጥ ዋናው የመንገዶች መስፋፋት ነው፡፡ ይህም ቢሆን በየቀኑ በመቶዎችና በሺዎች ከሚጨምረው የተሸከርካሪዎችና የእግረኞች ብዛት ጋር በጭራሽ ሊጣጣም ባለመቻሉ ችግሮች ሲወሳሰቡ እንጂ ሲፈቱ አታይም፤ የሕዝቡን ብዛት በየሥፍራው እንደጉንዳን ሲርመሰመስ ስታይ ሰው ነገር ዓለሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ከመፈላፈል ውጪ ሌላ ሥራ ያለው ላይመስልህ ይችላል፤ የሀገሪቱ ዋና ራስ ምታት የራሴ ነው የምትለው ለሀገርና ለወገን የሚቆረቆር፣ ሁሉንም እኩል በሚያሣትፍ የዕቅድና የበጀት ምደባ ሀገሪቱን በተገቢው የዕድገት ጎዳና የሚያራምድ ተቆርቋሪ መንግሥት ማጣት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ቁጥር በአደገኛ ሁኔታ መጨመርም ነው – እኔ ራሴ ባለቤቴ ዘጠንኛውን ልጃችንን ልትገላገል ጥቂት ሣምንታት ይቀሯታል፤ ይህን የምናደርገው ተስፋ ከመቁረጥና በነሱ ለመጦር ከማቀድ አንጻር ነው – ሌላ መዝናኛም ከማጣት ጭምር(እንዴ! ምን ማለታችሁ ነው – እስከግማሽዋ በአረፋ የተሞላች አንዲት ብርጭቆ ድራፍት እንኳን ባቅሟ በሰባት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከብር 2.20 ሽቅብ ተወንጭፋ አሥር ብር ስትገባ! – ታዲያ መራባት ይነሰን?)፡፡ ሰው ተስፋ ሲቆርጥ ከ‹መብላት› እና ‹መጠጣት› ውጪ ያሉትን አብዛኞቹን የ‹መ›ሕጎች ያከብራል፡- መናደድ፣መበሳጨት፣መሰደድ፣መጠጣት፣መዋለድ፣መእንትን…፤ “ጠጪነትና የሕዝብ ብዛት በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመር የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ናቸው” የሚባለው አዲስ ምሳሌያዊ አባባል ለካንስ እውነት ነው! ምን ልበልህ ወንድሜ! የሀገርህ ነገር እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሁለተኛና ሰባተኛ ዜጋ ሆነህ ከመኖር አውሮፓ ውስጥ ውሻና ድመት ሆነህ ብትፈጠር በእጅጉ ይሻልሃል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ ተለማማጭ ሀብታም ከምትሆን የጓንታናሞ የፍርድ እሥረኛ ብትሆን ላንተ ሉተሪ ነው፡፡ ብሬቪክ የሚባለው ሰባ ምናምን ሰው የገደለው ስዊድናዊ ታራሚ ከእሥር ስወጣም ገና ብዙ ሕዝብ እፈጃለሁ እያለ መስፈራርቾውን በቀጠለበት ወቅት ‹ክፍሌ በሰዓቱ አልጸዳልኝም› ወይም ‹ክፍሌ በቂ ብርሃን ስለሌለው በአስቸኳይ ይለወጥልኝ!› በሚል የማያዳግም ቃል (‘ultimatum’) የማረሚያ ቤቱን ባለሥልጣናት እያሽቆጠቆጠ መብቱን በሕግ ማስጠበቁን ስትሰማ ከጫካ የመጣ ወሮበላ እንደፈለገው የሚደፈጥጥብህን የአንተን ኢትዮጵያዊነት ያሻው ቀቅሎ እንዲበላው ከአእምሮህ መንትገህ ለመጣል ልትዳዳ ትችላለህ፡፡ ጊዜው የፈተና ነው ወንድሜ፡፡ እናም ይህችን ጊዜ እንደምንም ታገላትና ሳትበለሻሽ ተወጣት፡፡ ታሪክ እንደሆን ይቅርታ ማድረግን አያውቅም፡፡ ጽጌረዳን በቀላል አናገኝም፤ እሾኋ ውድነቷን ሳይጨምርላት አልቀረም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ አይደለም፡፡ ዛሬ በስሟ የነገዱና ሕዝቧን የዶጋ ዐመድ ያደረጉ ዱርዬ ልጆቿ ሁሉ አይቀጡ ቅጣት ሲያገኙ ዳፋው እንዳይደርስህ ተጠንቀቅ! ለአንድ እንጀራ ብለህ እንደዔሣው ብኩርናህን ለሆድህ አትሽጥ፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅምና የጠፋህ ወገኔ በጊዜ ተመለስ!!

አንተ ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ እያልክ በየሰው ሀገር አደባባይ ትጮሃለህ፡፡ እዚህ ሰዎች ከሰውነት ተራ እየወጡ ተንቀሳቃሽ በድን እየሆኑልህ ነው፡፡ ያንተን ጩኸት ራሱ አይሰሙም – ብዙዎቹ የሚሰሙበት ፍላጎትና መንገድም የላቸውም፤ደንበኛ ሰሜን ኮሪያውያን ሆነንልሃል፡፡ ‹ወንድሞቼንና እህቶቼን ነጻ አወጣለሁ› ብለህ ብትመጣ እንኳን፣ ነጻነት የሚገባው(የሚያስፈልገው) መሆኑን የሚረዳ ዜጋ ለማግኘት ይቸግርሃል፤ የሚመጣውን ቁጣና መቅሰፍት ሁሉ በቀላሉ እየተለማመደ ለሁሉም የግፍ አገዛዝ ተንበርካኪ ትውልድ እየተበራከተ ነው፡፡ ግዴለህም አንዳች የተደገመብን ነገር መኖር አለበት፡፡ ፈዘንና ደንግዘን በመተታዊ የአንደርብ ሥራ ወደ ጋንነትና እንሥራነት የተለወጥን ግዑዛን ነገሮች መስለንልሃል ወንድምዬ፡፡

አንድ ለአንድ አካባቢ እንግዳ የነበረ ሰው መንገድ ይጠፋውና አንዱን መንገደኛ ይጠየቀዋል፡፡ “የኔ ወንድም እንደዚህ የሚባል መንደር ልሄድ ፈልጌ ነበር፡፡ እስኪ እንዴት እንደምደርስ ጠቁመኝ ወዳጄ” ያም ሰው “ ይሄን መንገድ ቀጥ ብለህ ትሄድና እመስቀልኛው መንገድ እዚያ ወዲያ ስትደርስ ግራህን ይዘህ ትታጠፋለህ፤ ከዚያም ጥቂት እንደሄድክ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሠፈሮችን ታገኛለህ፡፡ አንደኛው ግን የቡዳዎች ሠፈር ስለሆነ ሰው ጠይቅና ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡” ይለዋል፡፡ እዚያ ጠንቀኛ መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲደርስ ቀድሞ የተነገረውን ያስብና በቡዳነት ይታማ ከነበረው ሠፈር የመጣ አንድ ሰው እዚያ አካባቢ ስለነበር በየዋህነት “ አንቱ ጋሼ – የቡዳው ሠፈር የትኛው ነው?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ ያም ሰው ምንተፍረቱን “እኛም እነሱን እንላለን፤ እነሱም እኛን ይላሉ” ይለውና ወዶ እንዲገባብት ምርጫውን ለጠያቂው ትቶ ንዴቱ እንዳይታወቅበት ለማድረግ በመጣር ይለየዋል፡፡ “እነሱም እኛን ይላሉ፤ እኛም እነሱን እንላለን!”

‹ኤርትራውያን› የኛ የ‹ኢትዮጵያውያን› ችግሮች መባቀያ እንደሆኑ የምናምን ወገኖች ጥቂቶች አይደንለም፡፡ በተገላቢጦሹም እኛ የነሱ ችግሮች ምንጭ እንደሆንን የሚያምኑ ኤርትራውያን አሉ፡፡ የሁለታችንም ችግሮች አንድ መሆናቸውን ግን እያጤንን መጥተናል – ለዐይን ይበጃል ያሉት ኩልም ዐይንን ሊያጠፋ መቃረቡን እየተረዳን ነው – ‹ናጽነት› ወይ ‹ባርነት›፤ ዕድሜ ደጉ የነጻነትንም የባርነትንም አዲስ ፍቺዎች እየተገነዘብን ነው፡፡ በዕንቆቅልሾች ታጥረናል ማለት ይቻላል፡፡ ለቅጣት በተላኩ ሁለት የአክስትና የአጎት ልጆች ጦስ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ እየታመሰና የቁም ስቅሉን እያዬ ነው፡፡ ‹ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ› ይላሉ ወንድሞቼ የሚደንቅ ነገር ሲገጥማቸው፡፡

ከአንድ ምንጭ የሚቀዳ ውኃ ጣዕሙ አንድ ነው፡፡ መለስና ኢሳይያስ – የአንድ ሣጥናኤል ሁለት ገጽታዎች – ከአንድ የጥፋት ወንዝ የተቀዱ በመሆናቸው በሃሊዮ በገቢር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የበሰበሰና የገማ የገለማ ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማፈራረስ ሕዝብንም ከሕዝብ ማቃቃርና ማፋጀት በውጤቱም የራሳቸውን ሰይጣናዊ ተልእኮ ማሣካት ስለሆነ እነዚህ ሁለት የሥጋ ዝምድናና የዓላማ ቁርኝት ያላቸው ሰዎች በሁሉም ነገር አንድ ናቸው፡፡ የተረገሙና ከእግዚአብሄር መንገድ የወጡ – ለቅጣት የመጡ እንደመሆናቸው መጨረሻቸው ቀርቶ መነሻቸውና መገባደጃቸው ራሱ የሚያምር አልሆነም፡፡ መለስ በ‹ለጋነት› ዕድሜው ሊቀጭ የቻለው በሕዝብ ፍቅር ምክንያት እንዳልሆነ እንኳን ፈጣሪ ሰይጣን ካቦኣቸውም(Foreman) ያውቃል፡፡ በቀላል ትዝብት መለስ ትዳርና ልጅ ሊወጣለት ያልቻለው በሕዝብ እርግማንና በሕዝብ ዕንባ ምክንያት እንጂ የመልካም ሥራ ተፈጥሮ ኖሮት ያንን ደግነቱን ፈጣሪ ዋጋ አሳጥቶበት እንዳልሆነ አሁንም እንኳንስ እግዚአብሔር ዲያብሎስ ራሱም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደጎረምሳ ትዳሩን እያመናቀረና ባለቤቱ በሽማግሌዎች ብርታት እየለዘበች እሱ የመጠጥና የቁማር ሱሰኛ ሆኖ የቀረው፣ የረባ ግለሰብኣዊና ማኅበራዊ ሕይወት ሳይመራ ዕድሜውን በከንቱ እየጨረሰ ያለው፣ የበሽታና የጋንጩሮች ዋሻ ሆኖ እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዘ የሚኖረው በሕዝብ እርግማን እንጂ በጽድቅ ሥራው ምክንያት አይደለም(ልብ አድርጉ! አማሮችን ለተዋጊዎቹ የዒላማ ማለማመጃ እያደረገ የነበረ የሉሲፈር ቀኝ እጅ ነው! To be honest, I was not there in any form of presence, but I can assume as if I were there; my instinct tells me that he and his protégé, His Crookedness Meles Zenawi, have been doing every crime that men can do against the so called Amharas! And it is my sincere conviction that their karmatic uncleanliness will never let them go without punishment, possibly here or probably there, or maybe in both realms until the time they become as immaculate as a newborn sinless babe!)፡፡ የእንጨት ሽበቶቹ ስብሃት ነጋ፣ ሞራ-ራስ የኑስ፤ ሥዩም መስፍን … በልዩ ልዩ ሱሶችና የበሽታ መርዞች ተለክፈው ባብዛኛው እንደነሱው ሰካራምና ሀሺሻም በስተቀር እዚህ ግባ የሚሉት አንድም ቁም ነገረኛ ልጅ ሳይወጣላቸው ዕድሜያቸውን በመንዘላዘል እንዲሁ በከንቱ እየጨረሱ የሚገኙት በእርግማን እንጂ በምርቃት በረከት አይደለም – ጎበዝ በደንብ እንደማመጥ! የእርግማን ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር አይታይም የሚባለውን ነባር ሥነ ቃል አንርሣ! ከጥንትም ቢሆን ሕዝብ ያለቀሰበት መቅኖ የለውም – በተለይ በኢትዮጵያ፡፡ ለዚህም ነው አሁን ማንም በማንም ላይ እንትኑን እንትን ይበል በሂደት ግን ‹በሠፈረው ቁና ይሠፈርለታል› በሚለው ነባር መለኮታዊና ተፈጥሯዊ ሕግ መጽናት የሚገባ መሆኑን በጥብቅ የምሰብከው፡፡ የቻለ እንዲያውም በክፉዎች አይቅና – ብድራታቸውን ያገኛሉና፡፡ ክፉዎች ለጊዜው የተሳካላቸው ቢመስልም የማታ ማታ ተጎጂዎች ናቸው፡፡ ሁለት ስህተቶች አንድን የተበላሸ ነገር ሊያስተካክሉ ወይ ሊያቃኑ እንደማይችሉም መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ስህተት ስህተትን ይወልዳል እንጂ የተዛነፈን አያቃናም፡፡ (Two wrongs don’t make a right.) ለዚህም ነው ወያኔን ሳይወለድ እንደጨነገፈ ሽል መቁጠር የሚገባን፡፡ ግርፋቱ ግን ከባድ ነው!

እውነት መስሎ የታየኝን እናገራለሁ፤ እጽፍማለሁ፡፡ በእንትን የተጥለቀለቀ የንግግር ዘይቤያችንን የምጥሰው ሆን ብዬ ነው፡፡ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን መጥፎ ድርጊት ላለማድረግ እንጂ ቋንቋ በማሳመር እውነትን ለመሸፈን መሆን የለበትም፡፡ ባለፈው ሰሞን የላክሁትን አንድ ጽሑፍ አንብቦ አንድ ወዳጄ በስልክ እንዲህ አለኝ፡፡ “አንተ ወልዴ! ምን ነካህ? አበድክ እንዴ? እንዴት በስሜት ውስጥ ሆነህ ትጽፋለህ? ለምን ቀዝቀዝ ስትል አትጽፍም? ተናደህ ከጻፍክ እኮ ሰው ይቀየምሃል፤ተናደን የምንቀጣው ልጅ ሊጎዳብን እንደሚችል አታውቅምን? የምትለው ነገር እውነትነት ቢኖረው እንኳን በቃላት መረጣ ተጠምዶ አንዱ የሌላኛውን ስሜት ላለማጎፍነን እርስ በርስ ሲሞከሻሽ በኖረ ማኅበረሰብ ውስጥ ይህን ያህል ግልጽነት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ድረ ገጽ ያን ጽሑፍህን ለጥፎት ሲያበቃ ከሁለት ቀናት በኋላ ከውጪ ዐዋቂ ይሁን ከውስጥ ዐዋቂ አስተያየት በመነሳት ገንጥሎ ጣለው፤ አንድ ቦታ ደግሞ ስሜታቸውን እንዴት እንደነካህባቸው ባልገባኝ ሁኔታ መርቅነህ እንደጻፍከው አስተያየት የጻፉብህ አሉ፤ ለምን …” ሲለኝ ብልጭ አለብኝና “ኦ!ኦ! የኔ ወንድም ዝም ብለው ካዳመጡህ ብዙ ትቀባጥራለህ፤ አንተ ራስህም የፈለግኸውን ልትለኝ ትችላለህ፡፡ የፈለጋችሁትን በሉ ሃሳቡ አይበላኝም፡፡ እኔ ካልተናደድኩ አልጽፍም፡፡ ስናደድ የምጽፈው ለእኔ እውነትነት አለው፡፡ ያልተበረዘና ያልተከለሰ – እከሌን ላስቀይም ወይም ላስደስት የማልልበት እንደወረደ ዓይነት ሃሳብ የማገኘው ተናድጄ ስጽፍ ነው፡፡ አንባቢም ያሻውን የማለት መብት አለው፡፡ የሚዲያ መድረኮችም ሲፈልጉ ይለጥፉ ሳይፈልጉ ቀድደው ይጣሉት – በኔ የቁጣ ንግግር ሰማይና ምድር አያልፉም፡፡ ሰለጠነ በሚባለው ዓለም የአሜሪካ ሴኔትና ኮንግረስ፣ የእንግሊዝ ፓርላማ፣ የእስራኤል ክነሴት፣ የራሽያ ዱማ… በስብሰባዎቻቸው ‹f**k off, idiot, son of a bitch, …› እየተባባሉ ተሰዳድበው ሲያበቁ ከስብሰባው ሲወጡ ሁሉንም ረስተው አብረው ይጫወቱ፣ ይበሉና ይጠጡስ የለምን? እኔስ ምን አጠፋሁ? ‹የትግሬ ወያኔ እንትን አለብን፤ እነእንትና ከፈለጉ እንትን ይሁኑ፤ እንትኔ መጥቶብኝ ወደ እንትን ቤት ልሄድ ነው፣እንትንህ ተከፍቷልና እንትንህ ሳይታይብህ እንትንህን ዝጋ…› እያልኩ ሁሉን ነገር በግድ በእንትን ጀምሬ በእንትን መጨረስ አለብኝ? ለምን? ከፈለግህ አንተም እንደነእንትና መሆን ትችላለህ፣ የእንትን አቀንቃኝ ሁላ! ለካንስ አፈሩን ገለባ ያድርግለትና ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ‹እንትን›ን እንደጠላና ስም አይጠሬዎችን(taboo words) እነእንትንንና እንትንን በቁልምጫ ሳይቀር እንደጠራ የሞተው ማፈንገጥ አምሮት ሳይሆን እውነትን እንዳለች መግለጽ ፈልጎ ኖሯል?” አልኩና በንዴት ፎግልቼ ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀምሁበት፤ የታባቱንና፡፡ ነገር ግን የራሽያው ዱማ በቦሪስ የልሲን የደረሰበት የመድፍና የታንክ እሩምታ ትዝ አለኝና ከጠቀስኩለት ዝርዝር ውስጥ እንዲያወጣልኝ ሳልነግረው ስልኩን በመዝጋቴ ቆጨኝ፡፡ ራሺያና እኛ ለካንስ በአንዳንድ ነገሮች እንመሳሰላለን፡፡ ፑቲን – መድቬዴቭ፤ መለስ – ደሳለኝ፡፡ አይይይ፣ የኛዎቹ ቲያትር እንኳን የነዚያኞቹን ያህል ወዝ ያለው አይደለም፡፡ በምን ተገናኝቶ ልጄ!

እንትን ስል አንድ እንትን ትዝ አለኝ ይልቁናስ – ፈገግ በሉ እንጂ – ግንባርን አኮሳትሮ እስከመቼ ይዘለቃል፡፡ በአንድ መንደር ውስጥ ኃይለኛ ርሀብ ይገባል አሉ፡፡ ከመንደሩ አባውራዎች አንዱ ውሻውን ይዞ አንዳች የሚታደን ነገር ባገኝ ይልና በቅርብ ወደሚገኝ ጫካ ይሄዳል – ወደ ደደቢት በረሃ፡፡ ጉድጓድ ይቆፍርና ወጥመዱን አዘጋጅቶ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ወደ ወጥመዱ ዝር የሚል ሰስና ሚዳቋ ይጠፋል፡፡ ከዚያ እግሩን አፍታትቶ ለመመለስ ከሄደበት ዘወርወር ብሎ ሲመጣ ያጠመደው ጉድጓድ ውስጥ አንድ አውሬ ገብቶ ያገኛል፡፡ ይሄኔ በመደሰትና ዘመኑ የችግር በመሆኑ ግዳዩን ሌላ ሰው እንዳይካፈለው በመሥጋት በኮድ የታሰረ መልእክቱን ለሚስቱ እንዲህ ሲል ጮክ ብሎ ያስተላልፋል፡-

እንትናችን ውስጥ እንትን ገብቶበት፤
እንትን አምጭልኝ እንትን እልበት፤
አንቺም ነይልኝ እንትን ትይልኝ፡፡

ነገሩ ቢላዎ ይዘሽልኝ ነይ ነው፡፡ ሁሉም አልፎ ፣ የቀኒቱ ርሀብም ለጊዜው ጠፍታ ጧት ላይ ቆዳና ጭንቅላት ሲታይ በጨለማ የተበላችው ለካንስ ቡችዬ ናት፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ነው እንግዲህ ‹ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን› የሚል ሥነ ቃላዊ ብሂል በቋንቋችን የተዘነቀውና አሁን ድረስ እየተጠቀምንበት የምንገኘው ይባላል፡፡

ለማንኛውም አካፋን አካፋ ማለት ጥሩ ነው፡፡ በመሠረቱ ኢትዮጵያ ሳይጠጡ የሚሰክሩባት፣ ሳይቅሙ የሚመረቅኑባት፣ ጠብ ከመነሳቱ አቧራ የሚጨስባት፣ በጠብ ያለሽ በዳቦ የስድብ ውርጅብኝና የአግቦ ውሽንፍር አየሩ የሚሞላባት የለየላቸው አማኑኤሎች ሀገር እየሆነች በመምጣቷ ብዙ ነገሮች ሊያስገሩሙን አይገባም፡፡ አምባጓሮ በሽበሽ ነው፡፡ መነቃቀፍ የሠርክ ልማድ ነው፡፡ ሌብነትና ውሸት፣ ሙስናና ንቅዘት አያስነውሩም፡፡ የሚያሾምና የሚያስሞግስ ተግማምቶ መገኘት እንጂ የኅሊናና የሞራል ንጽኅናን መጠበቅ አይደለም – ንጽሕና እንዲያውም ሊያስቀጣና ሊያደኸይ ቤተሙከራ ውስጥ በተፈለሰፈ ወንጀል አስከስሶም በዕድሜ ይፍታህ ዘብጥያ ሊያወርድ ይችላል – ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ መቅረቱ ከፋ እንጂ በዚህ ረገድ ስንትና ስንት የምነግራችሁ ነበረኝ! እናም ወደተነሳሁበት ስመለስ… የወያኔዎች የከረፋ ተፈጥሮና በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት ሰይጣናዊ ድርጊት እያናደደኝ እውነትን ባለማለሳለስ እንዳለ እጽፋለሁ እንጂ በምንም ዓይነት ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ተመርቼ አልጽፍም፡፡ በሀብት ብዛትና ኅሊናን በሚያዛቡ የአልኮል መጠጦች እየሠከሩ እንደዕንቁላል የገማ አስተሳሰባቸውን በጉልበት በተቆጣጠሩት ሚዲያ አማካኝት ሕዝብ ላይ የሚያስታውኩና የሚቀረሹ ስብሃትን የመሰሉ ዘረኞች ሞልተውናል፡፡ “አሜሪካ ቀርቶ መንግሥተ ሰማይም ብትሆን አታመልጠንም! አምጥተን እናስርሃለን” የሚሉ ልበ ድፍን የወያኔ ሰካራሞችና ቅዠታሞች እያሉ እኔ እውነትን ለመጻፍ ጫትም ሆነ መጠጥ አያስፈልገኝም፡፡ እንደውነቱ ከሆነ ውቅያኖሶች ቀለም፣ ሰማይና ምድር ብራና ሆነው የወያኔን ታሪክ ብንጽፍ አያልቅም፡፡

ከዚህ በላይ እስካሁን ምን እንዳልኩ አላውቅም – የምርቃና ነገር – ቂ…ቂ…ቂ… ሣቅ አምሮኝ ነበር እንደጉድ ተንከተከትኩላችሁ፡፡ ቢሆንም ትርጉም ሰጠም አልሰጠም ነገሬን መቋጨት አለብኝና ወደዚያው ወደሚወስደኝ ጎዳና ላዝግም፡፡ ኤርትራውያን ችግር ላይ እንደሚገኙ ከፕሮፌሰሩ ጽሑፍ በኛና በነሱ የነገሮች ግጥምጥሞሽና ምስስሎሽ እያዘንኩ ተረድቻለሁ፡፡ የኛም የነሱም ችግር አንድ ነው ማለት ነው፡፡ እኛ፣ ኤርትራውያኑ እነበረከትና ስብሃት ገደሉን እንላለን፤ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን ደግሞ ‹ትግራውያኑ› እነስብሃትና በረከት እነሱን ኤርትራውኑን ገደሉን እያሉን ነው፡፡ ማን ማንን መግደሉ ለጊዜው ለውጥ አያመጣም – ትኩረት ሊሰጠውና ሊቆምም የሚገባው ግድያው ነው፡፡ ይህን የተቀናበረ ታሪካዊ የሀገርና የሕዝብ ግድያና ጭፍጨፋ ማን ነው የሚያቆመው? እነዚህ ታሪካዊ የጋራ ጠላቶቻችን ቅጥረኞች(mercenaries) ምን እስኪያደርጉን ነው የምንጠብቀው? በኛ ስም እየማሉና እየተገዘቱ እስከመቼ ነው ግድያቸውን የሚቀጥሉት? ዐይጥ በበላ እስከመቼ ነው ዳዋ እየተጨፈጨፈ የሚዘልቀው? እንደኔ እንደኔ ሥጋዊ ሞት ከመንፈሳዊ ሞት በጣም ተመራጭ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ታላላቅ ሰዎች የሚፈሩት ሞትን ሳይሆን አሟሟትን ነው፡፡ ነገሩ ‹ከሞቴ አሟሟቴ ያስፈራኛል› እንደሚባለው ነው፡፡ የፕሮፌሰሩ አባባል እውነት ከሆነ የሞተችው ኢትዮጵያና ሕዝቧ ብቻ ሳይሆኑ ሳትወድ በግዷ የተለየቻት ልጇ ኤርትራም ናት ማለት ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡

በእኔ እምነት እናትና ልጅ እንደተለያዩ አይቀሩም – በግሌ ያን ጊዜ ልደርስበት ወይ ላልደርስበት እችል ይሆናል – ግን ላምና ጥጃ በርግጥ ይገናኛሉ! ይህን ስል – ማለትም ‹እደርስበት ወይ አልደርስበት ይሆናል› ብዬ በኩራት ስናገር የስድስተኛውን ስሜቴን ‹ትንቢት› ለመግለጽ ያህል እንጂ የአንድ ትንኝ ወደ አንድ ታሪካዊ ኹነት(An historic event which really is inevitable!) መድረስ ወይ ያለመድረስ ጉዳይ አሳስቦኝ አይደለም፡፡ ስትፈልጉ ቅዠት ወይም ቅብዥር በሉት ኢትዮጵያና ልጇ ኤርትራ በአዲስ መልክ ይዋሃዳሉ፡፡ የተበለሻሹ ነገሮች ተቃንተው ይስተካከላሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ቂም በቀልና ጥላቻ፣ ዘረኝነትና ጎጠኝነት ተወግደው ሰው እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፈ ሳይሆን በሰውነቱ ብቻ ሲሳሳብና ሁሉም ዜጎች በአንድ የወል ሀገራዊ ስሜት ሲተሳሰሩ ነው – የመለስ-ኢሳይያስ የትግራይ ትግሪኝ ዘፈን ቅኝት ወረቱን በመጨረስ ከስሞ የኢትዮጵያዊነት ሥልት ሲናኝ፡፡ ይህን የተቀደሰ ትውልዳዊ ኃላፊነት በብቃት የሚወጡ ዜጎች በቅርብ ይሾማሉ፡፡ በቤተ ሙከራ ተሠርተው እንደዕርዳታ ስንዴ ለየጎጡ የተከፋፈሉ ባንዲራዎች ይቃጠላሉ፤ የዚህ መሠሪ ተንኮል ጠንሳሾች፣ አስጠንሳሾችና አራማጆችም በገሃድ መሞት እንደጀመሩ አንድ ባንድ ግን ሁሉም ተራቸውን ጠብቀው ያልቃሉ፤ በሰማይም በምድርም ተረግመዋልና – በደም ባህር የሚዋኙ ናቸውና – በሕዝብ የምሬት ዕንባ ዶፍም በስብሰዋልና ዘር አይወጣላቸውም፤ ለነሱ የተፈቀደችዋ ዘመን ይህቺ የአሁኗ ጊዜ ብቻ ናት – ባለቻቸው ጊዜ ይደሰቱ፤ ይጠጡ፤ አንዳቸው በሌላኛቸው ቤት ይሸራሞጡ፤ አንዳቸው የሌላኛቸውን ልጅ ያሳድጉ – ከእርጉማን የሚጠበቅ የልክስክስነት ባሕርይ ነውና፤ ዳንኪራና ጮቤም ይርገጡ (የዐዋጁን በጆሮ ባትሉኝ እነዚህ የታሪክ ጉዶች እኮ አልጋንም የሚጋሩና ‹የተቀደሰውን ለውሾች አውጥተው የሚጥሉ› ጋጠወጦች ናቸው! አንዳችም ማሠሪያና የሚፈሩት ነገር የሌላቸው ከሃይማኖትም ከባህልም ማዕቀፎች የወጡ ስዶች እኮ ናቸው!)፡፡ ታዲያን እነሱ ሰይጣንን ይዘው ይህን ያህል ተዓምር የሠሩ እኛ እግዚአብሔርን ይዘን ከነሱ የበለጠ ልዩ ተዓምር እንዴት አንሠራ!? “እመን እንጂ አትፍራ!” መባሉም ለዚህ ነው፡፡ አይዞን ምዕመናን!!

ነጻነትን እንደቀድሞው የሙሤ ዘመን በኅብስተ መና መልክ ከሰማይ መጠበቅ ግን የዋህነት መሆኑን እንረዳ፡፡ ፈረንጆች “There is no free lunch!” ይላሉ፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባንና እንደሚቻለንም እናስብ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ግን ከክፋት ሥራ ተጠብቀን ወደፈጣሪ መዞር እንደሚገባን እንወቅ፡፡ ፈጣሪን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄድን እንቀበለው፡፡ የሞተን ለመርዳት የሚተጋ ሰማያዊም ሆነ ምድራዊ ኃይል እንደሌለ እንገንዘብ፡፡ እናም ሕይወት እንዳለን፣ እንዳልሞትን፣ ለዲያብሎስ መንጋ እንዳልተንበረከክን የምናሳውቅበት የመነሳሳት ቅጽበት እንዲፈጠር እንትጋ፡፡ ያ ጊዜ ደግሞ አሁንና ዛሬ ነው፡፡ የኛን የቤት ሥራ ከሠራን ቀሪው ቀላል ነው፡፡ ለመሆኑ አሁን ፈጣሪ ምን እየሠራ እንደሆነ እናውቃለን? አዎ፣ ሁሉንም ባናውቅም ይህችን ያህል የምናውቅ ግን አለን፡- ‹ቁናውን እየሰፋ ነው› ወይም ‹ሰፍቶ ጨርሷል›፡፡ መሥፈር ሲጀምርስ? እሱን አያድርስ!ሦርያን ያየ፣ ሊቢያን ያዬ፣ የመንን ያዬ፣ ሩዋንዳን ያዬ፣ማሊን ያዬ፣ቱኒዚያን ያዬ… በእሳት ሊጫወት ማሰብ የለበትም፡፡ ግን ግን ‹የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ ያዘምታል› መባሉ ለካንስ እውነት ነው? ውድ ወያኔዎች – መጥፊያችሁ ደርሷል! መጥፋታችሁ እንጂ እንዴት እንደምትጠፉ ግን እኛም እናንተም አናውቅም – ከፈጣሪ በስተቀር፡፡

በመሠረቱ ገዢዎች ይሳሳታሉ፡፡ እንዲያውም የማይሳሳት ገዢ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ በዚህች ምድር ፅድቅን ስለማንጠብቅ ለምሳሌ ባገራችን የመንግሥትን ሥልጣን የሚይይዘው ከበደም ይሁን ሐጎስ ወይም ዘበርጋም ይሁን ሂርጳሳ በአንጻራዊነት እገሌ ከእገሌ በዚህ ወይ በዚያ ጉዳይ ይሻላል ማለት እንችል እንደሆን እንጂ በአስተዳደር ረገድ ፍጹም እንከን የለሽ የመንግሥት አካል አናገኝም፡፡ ከዚህ አንጻር የአሁኑን የወያኔ አገዛዝ ካለፉትም ሆነ ወደፊት ይመጣሉ ብለን ከምንጠብቃቸው ጋር ስናወዳድረው በጥፋት ተልዕኮው ወደር የማይገኝለት መሆኑን መገንዘብ አያዳግተንም፡፡ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን – የውጭ ሀገር ሰው በመሆናቸው ፕሮፌሰር መድኃኔ ልበልና ባባታቸው ስም ልጥራቸውና – ፕሮፌሰር መድኃኔ በጥናታቸው እንደጠቆሙት የአንድ ሀገር አመራር ትልቁ የሞራል ዝቅጠት በሚያስተዳድረው ሕዝብ መሀል ግርድና አመሳሶ እያወጣ ራሱንም ወደ አንድ ሸጥና ጎጥ እየወተፈ ሌሎችን በወርቅነትና በኩበትነት እየፈረጀ ሲያንጓልል ነው፡፡ ይህ በታሪካችን ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ መቅሰፍት – በምንም መንገድ ሊሽር የማይችል ጠባሳ መሆኑ ሳይረሳ – ምን ያህል መሪዎቻችንን ከስብዕና በታች እያወረደና በመዘዙም እኛን ከመኖር ወዳለመኖር እየለወጠን እንደሚገኝ ከተረዳን ቆይተናል፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሀገሪቱን የመንግሥት ሥልጣን በቀጥታና በተዛዋሪ ከያዘ የአንድ ሀገር የፖለቲካ አመራር ቡድን ውስጥ 3.6% ብቻ ኢትዮጵያን እንደእናት ሀገር የሚቀበል ሆኖ ሲገኝ ሌላውና 96.4% የሚሆነው በትግራይ እናት-ሀገርነት ሲጸና ከዚህ በላይ ማፈሪያ የታሪክ አንጓ የለም – በጭራሽ! ትግራይ ውስጥ በናሙናነት ከተወሰደ የሕዝብ ክፍል መሀል 82.1% የሚሆነው ‹ቀንደኛ ጠላትህ ማን ነው?› ተብሎ ሲጠየቅ ‹አማራ ነው› ካለ አስታራቂ የሚያስፈልገው ግን ቀን ሊሰጠው የማይገባ ችግር አለ ማለት ነውና ሀገር ሰላም ብለን መተኛት የለብንም፡፡ እነዚህን ዘግናኝ መረጃዎች በዝርዝር ለማንበብና በሃዘን ለመቆራመድ የፈለገ ሰው የተጠቀሰውን የፕሮፌሰሩን ጽሑፍ ማንበብ ነው፡፡ የአጻጻፍ ሥልታችንና የይዘታችን ድምፀት (style and tone) ይለያይ እንጂ እኔን መሰሎች ዘባራቂ የብዕር ‹ጦረኞች›ም የምንለው ይሄንኑ ነው፡፡ ችግር አለ! (‹ነገ እዚህ አካባቢ ቤት ይቃጠላል!› ነበር ያለችው የደሴዋ ዕብድ ሴት በማግሥቱ ራሷ ልታጋየውና ጉድ ልትሠራቸው?) ችግሩ ታዲያ እንደሌሎች ሀገሮች ችግር ሳይወሳሰብና ጥርስ ወደሌለው የተቃቃሩት መንግሥታት(DN/Disunited Nations) መሮጥ ሳይመጣ ከአሁኑ እንፍታው ነው እያልን ያለነው፡፡ ሦርያ ላይ የሚጮህ ጅራፍ ጊዜውን ጠብቆ ኢትዮጵያ ውስጥ አይጮህም ብሎ ማሰብ የለየለት ድንቁርናና ትዕቢት ነው፡፡ ትብታብም ይፈርሳል፤ ፍርሀትም ይጠፋል እያልን ነው የምንገኝ፡፡ አሁን ዓለምን የገዙ የመሰላቸው የትግሬ ወያኔዎች በሕዝብ ላይ መፈንጠዛቸውንና ጥሬ እንትናቸውን በጭቁኑ ወልደማርያም ላይ መጣላቸውን ትተው ወደኅሊናቸው ይመለሱ ማለት ኃጢኣት አይደለም፤ ትርፍ እንጂ ኪሣራም የለውም፡፡ ችግሩስ ቁስልን እየሸፋፈኑ ይብስ እንዲነፈርቅ ማድረግ ነው፡፡ በጭቁን ዜጎች ላይ ፋንድያን ማለትም እንትንን እዬጣሉ ለስንት ዘመን መኖር እንደሚቻል የጋዳፊንና የኢዳሚንን የሙት መንፈስ በጠንቋዮቻቸው አማካይነት ያስጠይቁና ከጥጋብ መንገድ በአፋጣኝ ይውጡ ነው እያልን ያለነው፡፡ በተረቱ ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ መባሉ የጥጋብን መዘዝ ለማጠየቅ ነው፡፡ ሰከርክም ልባል መረቀንህ – አሁንም እደግመዋለሁ፡- እነዚህ ዋልጌ የዲያብሎስ ውላጆች ባስከተሉት መዘዝ ኢትዮጵያ በ‹ጥቂት› ትግሬዎች እጅ ገብታ በወለድ አገድ እየተመጠመጠች ናትና ይህ ታሪክ ይቅር ሊለው የሚከብደው አሰቃቂ ድርጊት ተጨማሪ ጥፋት ሳያስከትል በአስቸኳይ ይቁም፤ ብሔራዊ ዕርቅ ይፈጠር፤ ፖለቲካችን ሰው ሰው ይሽተት፤ በዘረኝነት ከርፍቷል፤ በጎጠኝነት ገምቷል፤ በሙስና ጠንብቷል – የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ መጥፎ ጠረን የዚህችን ዓለም አድማሳዊ ድንበር አልፎ ጽርሐ አርያምን እያጥነገነገ ነውና በቶሎ መፍትሔ ካልተፈለገለት ጦስ ጥንቡሱ ከኢትዮጵያ ድንበሮችም ይሻገራል እያልን የምንገኝበት ሁኔታ ተፈጥሯል የሚል ግንዛቤ ወስደናል እያልን ነው – በበረከት ስምዖን አማርኛ፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግራችን ዋናው መፍትሔ ‹አማራ ገዳይ! ትግሬ ገዳይ!…› የሚለው የጅሎች ፉከራና ሽለላ ሳይሆን መደማመጥና መግባባት ብቻ ነው፡፡ ይሄኛው የሃያና ሠላሳ ዓመት አበቅቴ ለነዚህ ቢሆን ያኛው የሠላሣና ዐርባ ዓመት አበቅቴ ደግሞ ለነዚያኞቹ ይሆናል፤ የዚህች ምድር ነገር የጽዋ ማኅበር ዓይነት ነው – ማንም የማንንም ዝክር ቀፈቱ እስኪያብጥ ሰልቅጦ ሰልቅጦ ሲያበቃ በ‹ጨዋታው ፈረሰ – ዳቦው ተገመሰ› የልጆች ጨዋታ የበላ የጠጣትን ሳይከፍል ከማኅበሩ ልሰናበት ሊል አይችልም – በየትኛው ሒሳብ! ዛሬ ለተቀናጀ መንግሥታዊ የበቀል ጥማት ማርኪያ የሆነ ሕዝብ በቀል አርግዞ በተራው በዳዮቹን ለመቅጣት ምቹ ቀንን የሚጠብቅ እንዳይሆን የክፋት ምንጭን እናድርቅ እያልን ነው – አንዳንድ “የሩቅ ተመልካቾች”፡፡ ማሰብ በተሳናቸው የትግሬ ወያኔዎች፣ ይሉኝታንና ሀፍረትን ሸጠው በበሉ ወንድምና እህቶቻችን እያየነው ያለነው አበሳ የሰቆቃችን የመጨረሻ ምዕራፍ ይሁንና ከዚህ መጥፎ ታሪክ ትምህርት ቀስመን የወደፊቱን ትውልድ ከመርዘኛ ፖለቲካና ፖለቲካው ካበሰበሰው አጠቃላይ ማኅበረሰብኣዊ ቀውስ ነጻ እናውጣው፡፡ በሎሚ ተራ ተራ ዜጎች ለማያባራ ስቃይ መዳረግ የለባቸውም፡፡ መለስ በስብሶ የሞተው፣ ኢሳይያስ ለያዥ ለገራዥ አስቸግሮ ሞትን በሚያስመርጥ የቁም መቅበዝበዝ ላይ የሚገኘው አላንዳች ብልሃት አይደለምና ዜጎች ወደጤናማ ኅሊናቸው ባፋጣኝ ይመለሱ – ቢያንስ ከነዚህ ሁለት የጠፉ ዜጎች እንማር፡፡ በሀገር ዕርቅ ይውረድ፡፡ ቂም በቀል ይወገድ፡፡ የጠገበ ይስከን፤ የተራቡና የተጨቆኑ ወገኖቹንም ያስብ፤ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባም ሆነች አሥመራ(I can imagine,) የሎጥን የሶዶምና ገሞራ የእሳት ዝናብ የሚጠሩ የሲዖል ከተሞች ሆነዋል ብንል አልተሳሳትንም – ብዙኃን በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ ጥቂቶች በሚመዘብሩት የሕዝብና የሀገር ሀብት ይሠሩትን አጥተው በነውረኝነት ጎዳና መትመምን መርጠዋል…እኛም እነሱም አናሳዝንም? – በሬ ካራጁ ጋር ይውላል፡፡ ቂም በቀል ቂም በቀልን ይወልዳል፡፡ አመፅ አመፅን ይወልዳል፡፡ ፍቅርና መተሳሰብ ግን የበቀል ቁርሾን አስወግዶ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሠረት ያደርጋል፡፡ ዛሬ አንድ የሚፏልል ጥጋበኛ የወያኔ ካድሬ በቢሊዮን የሚገመት ሀብትና ንብረት ቢያከማች – እመኑኝ – አይበላውም፤ መቼምና የትምም አይጠቀምበትም፡፡ ‹እባካችን› ልብ እንግዛ፡፡ እርግጥ ነው ሀብታምና ፖለቲከኛ በአብዛኛው ደናቁርት ስለሆኑ ዛሬን እንጂ ነገን ማሰብ አይቻላቸውም – ለማሰብ የሚጠቀሙበት ሆዳቸውን እንጂ ጭንቅላታቸውን አይደለም፡፡ አንጎላቸው የተቃኘው በሶስት ነገሮች ብቻ ነው፤ እነሱም ሥልጣን፣ ገንዘብና ወሲብ ናቸው – አንቀሳቃሽ ሞተሮቻቸው እነዚህ ናቸው፤ የእነዚህን ፍላጎቶቻቸውን ጥሪ ለመመለስ ሲሉ ከሰማይ በታች ከምድር በላይ የማይሠሩት ወንጀልና ኃጢያት የለም፡፡ በእነዚህ ሦስት ፈታኝ ነገሮች ያልታወረ ሰው ግን ብፁዕ ነው – አእምሮውንም በአግባቡ ይጠቀማል፤ ከቅሌትና ውርደትም ይድናል፡፡ አቅሉን ስቶ ለነዚህ ነገሮች የሚንበረከክ ከሰውነት ተራ ይወጣል – በመጨረሻው መጨረሻ ላይ ታዲያ ውድ ዋጋ ይከፍላል፡፡

በተረፈ ትግሬ፣ አማራ ፣ ኦሮሞ የምንለው ነገር የቋንቋ ፈሊጥ እንጂ ተጨባጭ የሆነ አመክንዮኣዊ ልዩነት የላቸውም፡፡ በነዚህ የጎሣና የብሔር ስሞች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ሌቦች በሏቸው – አጭበርባሪዎች፡፡ ለአብራኩ ክፋይ ለልጁ ግድ የሌለው – ሚስቱን በወጣ በገባ ቁጥር የሚነተርክ – ከጎረቤቱ ጋር ዐይንና ናጫ ሆኖ የሚኖር፣ ለቸገረው ወንድሙ አምስት ሣንቲም የማያቀምስ፣ ለተጨነቀ ጓደኛው አሥር ብር የማያበድር… ስግብግብና ፍቅርን የማያውቅ ዜጋ ለሥልጣን አራራውና ለግል ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሲል የዚህን ወይም የዚያኛውን ብሔረሰብ ስም በታፔላነት አንስቶ ቢጮህ እውነት አይምሰላችሁ፡፡ ለማያውቅህ ታጠን በሉት፡፡ በአባቱ ኦሮሞ በእናቱ አማራ የሆነ ለማን ሊታገል ነው የጎሣ ቡድን ውስጥ የሚገባው? ለምሳሌ ስብሃት ነጋ ኤርትራዊነቱንም ኢትዮጵያዊነቱንም ትቶ ለትግራይ የበላይነትና ለወያኔ ንግሥና ቆሜያለሁ የሚል ሰው ነው ይባልለታል፡፡ ይህ ሰው፣ እውን ለትግራይ ይጨነቃል? ለትግራይ ሕዝብስ እንቅልፍ አጥቶ ያድራል? እንዲያ ከሆነ ስንትና ስንት ትግራውያን በርሀብ ሲሰቃዩ እንደማንኛውም ወገናቸው ሲለምኑና ሲቸገሩ በምዝበራና በሕገወጥ የገንዘብ ክምችት ብዙ ቢሊዮን ብር አለው ከሚባልለት ኤፈርት ትንሽ ገንዘብ ቆንጠር አድርገው ለምን አይረዱም? አዎ፣ ብዙ ነገሮች የታይታ ናቸው፤ ብዙ ነገሮች የብልጭልጭ ናቸው፡፡ የእንትና ብሔረሰብ ይልና በቁስልህ ሊገባ ይፈልጋል – ቁስልህን ተገን አድርጎ ወደልብህ ለመግባት ከሞከረ በኋላ ግን የርሱን ቁስል ባንተ ሀብትና ጥሪት ፈውሶና የድህነት ጭቅቅቱን አራግፎ ያንተን ቅስል ይብስ ያነግልብሃል፤ አንተም ከነድህነትህ እህህ እያልክ ትኖራለህ – ለሌላ ዙር እንግልትም ትጋለጥና የራበው አዲስ ተኩላ ከጫካም ይሁን ከከተማ መጥቶ በአዲስ መልክ ይግጥሃል፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት፡፡ አንዱ መሰላል ነው – ሌላው በመሰላሉ የሚወጣ ነቀዝና ተምች ነው፡፡ ታችኛው ግን ሞኝና እንደነዱሽ እንደሆነ ይቀራል፡፡ እነገሌ መጡብህ ካሉት እየደነበረ ከየሽርንቁላው ይወጣና አሰለጦች ባዘዙት መሠረት በንጹሓን ላይ ጦሩን ሰብቆ መሰል ወገኖቹ ላይ ይዘምታል፤ ብዙኃኑ ታችኛው የጥቂቶች ላይኞች መጠቀሚያ ጎጋ ነው፡፡ ከስቅሎ ስቅሎ በፊትም ሆነ በኋላ የዓለም ታሪክ እንደዚሁ ነው፤ ጥቂት ብልጦች ብዙኃንን ዕቃ’ቃ እንደተጫወቱባቸው ዓለም ‹ፍጻሜዋ ደረሰ›፡፡ አንዳንዱ እንደተሸወደ የሚገባውና ዐይኑን የሚገልጠው ራሱ ችግር ውስጥ ከገባ በኋላ ነው፡፡ እነመለስ፣ እነኢሳይያስ በዚህ መልክ ሲጫወቱብን ከቆዩ በኋላ ነው እንግዲህ እነሱም በፋንታቸው የማይቀርላቸውን መሪር ጽዋ ሊጎነጩ የመጨረሻው ፊሽካ ብቻ እንደቀረው አምነን ያቺን የፍርድ ቀን በጉጉት እየተጠባበቅን የምንገኘው፡፡ በቃ፡፡

የነስብሃትና መሰሎቹ አገርና ወገን ሆዳቸው ነው፤ ሃይማኖታቸው ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት ወሲብና መጠጥ ነው፡፡ የሚሉት ሁሉ ለማደናገሪያነት እንጂ የአንጀታቸውን አይደለም፡፡ ትዳርን የማያከብር ዘልዛላ፣ የክፉ ቀንን የትዳር ጓደኛና የልጆቹን እናት ሲያልፍለት አስወጥቶ የሚጥል ጉደኛ፣ ልጆቹን የማይሰበስብ የሌሊት አውሬ ዳንኪረኛ፣ በሽምግልና ዕድሜው ከልጅ ልጆቹ ጋር የሚማግጥ ሠካራም ነውረኛ… በምን ሒሳብ ለሀገር ጠቃሚና ለወገን ተቆርቋሪ ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ ይቅርታ – ባደጉ ሀገሮች ከሕጻንነት ጀምሮ የሚመዘገብ የግል ሕይወት ይዞታ ለሥልጣን ዕጩነት ታላቁ መለኪያ በመሆኑ ይህን ስለባለሥልጣኖቻችን ዋልጌነትና እንስሳነት የምላችሁን ነገር በምን አገባህ አናንቃችሁ አትመልከቱት – በኛ ሀገር ደግሞ በተገላቢጦሹ ባለጌ ባለጌው እየተመረጠ ይመስላል ለሥልጣን የሚበቃው – አልጋውና ወንበሩ የሚወደው ጥፍራሞችንና መደዴዎችን መሆን አለበት፡፡

ሀገር ወዳድነት ላግጣ አይደለም – ሀገርን የመምራት ጠንካራ ጎን ደግሞ ከቤተሰብና ከራስ ጤናማ ኑሮ ይመነጫል፤ በሽተኛ ሰው እንኳንስ ሀገርን ራሱንም መምራት አይችልም፤ ሠካራምና እንደልቡ ተናጋሪ ሰው ደግሞ ከዕብድ ተለይቶ አይታይም፡፡ አሁንም ከዚህ ከምለው ነጥብ አኳያ እነስብሃትን ‹ለማያውቋችሁ ታጠኑ!› በሉልኝ፡፡ መቆሚያቸውን ለማደላደል የትግራይን ሕዝብ ‹ያንተዎቹ ነን፤ ከኛ ወዲያ ላንተ የተሻለ አማራጭ የለም፤ አማሮች ከመጡ ሥጋህን ዘልዝለው ይበሉሃል…› በማለት ሊያስፈራሩበት እንጂ በውነት የትግራይነት ስሜት ኖሯቸው አይደለም፡፡ ቀደም ካለ የትግላቸው ወቅት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሠሯቸው ወንጀሎች ይህን የሚሉትን ነገር አያረጋግጡላቸውም፡፡ ብሎም ቢሆን ለትግራይ ምድርና ሕዝብ የሠሩት የልማትና የዕድገት እመርታ የለም ለማለት እንዳልሆነ በትህትና ላስታውስ እወዳለሁ፡፡ ሀገራችን ለሚሉት ብዙ ሠርተዋል – ይሁን፡፡ ጥጃ ጠባ እሆድ ገባ ነው፡፡ ቦዕ ጊዜ ለኩሉ ፤ ሌሎቹም በጊዜያቸው ይለማሉ፡፡

ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡ ቀጥሎ በቅንጭብ ያመጣሁትን የፕሮፌሰርን ንግግር አዳምጡ፡-

ኤርትራ ዛሬ በሁሉም መስፈርት አስጠሊና የተገለለች አገር ሆናለች። ሕዝባችን ባሁኗ ወቅት ደቃቃዋ የፖለቲካ መብት እንኳ የሌለው፡ ሰብኣዊ መብቱ ፈጽሞ ያልተጠበቀ፡ እጅግ ከባድ ድህነት ያጐሳቈለው፡ ማህበራዊ ኑሮው ሰብኣዊነት የራቀው፡ የህላዌው ሁኔታ በፍርሃትና ስጋት ተበክሎ የደህንነትና የዋስትና ጭላንጭል እንኳን የሌለው ነው፡፡ የወጣቶቹ ሁኔታ በተለይ እጅግ የሚያሳዝን የከበደ ትራጀዲ ሆኗል፡፡ ወጣቱ ሊደሰትበት በሚገባ አፍላ ዕድሜው በግድ እየታፈሰ ሳዋ ወይም አገልግሎት ለሚባለው ባርነት እየተዳረገ ነው። ወጣቶቹ ከዚያ ገሃነማዊ ሁኔታ ለማማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ፡ ከስደት ወደ ስደት አገር ለመሸጋገር ሲሞክሩ አንዳንዱ ባሕር ውስጥ እየሰጠሙ ለምህረት-የለሽ ዓሳ ሲሳይ እየሆኑ ነው፣ አንዳንዱ ደግሞ በአረሜኔዎች ተጠልፈው እንደ እንስሳ እየታረዱ ኩላሊታቸውና ሌላ ውስጣዊ አካላቸው እየተነጠቀ ሬሳቸው በሳሃራና በሲናይ ምድረ-በዳዎች እየበሰበሰ ነው፡፡ ይህ መከራ በጣም የሚዘገነን፡ ስትሰማውም እጅግ የሚያስደነግጥ ነው።

ለመሆኑ ዜጎች ለዚህ አሰቃቂ መከራ ሲጋለጡ አስመራ ውስጥ ያለው መንግሥት ምን እየሰራ ነው? የሚል የዋህ ጠያቂ አታጣም። አስመራ ውስጥ ያለው አምባገነን ኢሳያስ የሚመራው መንግሥት እውነትም ኤርትራዊ መንግሥት አይደለም፣ በኤርትራውያን ላይ የጥላቻና የቂም በቀል ቁርሾ በያዙ፡ ድብቅ ሴራ ባላቸው አካላት የቆመ ቡድን (ካባል) ነው። እነኚህ ሴረኞች በትውልድ ትግሬዎች ቢሆኑም ኤርትራዊያን ሊሆኑ ይችሉ የነበሩ፡ ሆኖም ግን ምንነቱ ባልተመረመረ ችግር ምክንያት፡ ሕዝባችንን በሚያጠቃ መልኩ የ“ትግራይ-ትግርኚ” ንድፍ አዝማቾች ለመሆን የመረጡ ናቸው።

ከዚህ ጋር በተዛመደ ሊነሳ የሚገባው አሳዛኝ ነገር አለ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ትግል ጀምሮ እስከ ህግዲፍ መንግሥትነት ድረስ ኢሳያስን ያገለገሉ፡ እንደ እነ ሃይለ ወልደትንሳኤ፡(ድሩእ)፡ማሕሙድ ሸሪፎ፡ እስጢፋኖስ ስዩም፡ ጴጥሮስ ሰለሞን፡ ጀርማኖ ናቲ፡ ኣስቴር ፍስሓጽዮን፡ በራኺ ገብረስላሴ፡ ዑቕበ ኣብርሃ፡ ብርሃነ ገረዝጊሄር የመሳሰሉ፡ በዛ ገሃነማዊ የዒራዒሮ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው አንዳንዶቹ ሞተው፤አንዳንዶቹ ደግሞ እየተሰቃዩ ሞታቸውን ይጠባበቃሉ። እነኚህ ታጋዮች የፈጸሙት ወንጀል የለም። ኤርትራ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲጀመር ጥገናዊ የሆነ ለውጥ በመጠየቃቸው ብቻ ነው ለዚሁ አበሳ የተዳረጉት። እነዚህንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን የምትመለከት አንዲት አንገብጋቢ ነጥብ አለች፤ እርስዋም እኚህ በኢሳያስ የሚታሰሩና በተለያየ ዘዴ እየተገደሉ ያሉት ዜጎች በሙሉ ንጹሃን “ኤርትራዊያን” መሆናቸው ናት። በተቀረ፡ ብዙ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ፡ በትውልዳቸው ትግሬዎች የሆኑ ኤርትራውያን በኢሳያስ መንግስት እንዲገደሉ ወይንም እንዲታሰሩ የተደረጉ የሉም። ይህ አሳሳቢ የሆነ ትዝብት ነው!!

***
በጥያቄው የተሳተፉት የዛሬው የትግራይ ፖለቲከኞች (ወይም የፖለቲካ ተዋንያን – ማለት ኤሊት) እናት አገራችሁ ማነች ለሚለው ጥያቄ የሰጡት መልስ በመንፈስም በአስተሳሰብም ኤርትራውያን ፖለቲከኞቹ ከሰጡት መልስ አሳሳቢ በሆነ መጠን ይለያል። ከተሳተፉት የትግራይ ፖለቲከኞች መሃል እናት አገራችን ኢትዮጵያ ነች ብለው የመለሱ 3.6% ብቻ ናቸው። አብዛኛዎቹ በጥያቄው የተሳተፉ የትግራይ ፖለቲከኞች ግን እናት አገራችን ትግራይ ነች ነበር ያሉት። ኢትዮጵያ አላሉም። አቶ ስብሓት ነጋ ይህንን ጥያቄ ሲመልስ፡ ላንዳፍታ “ዝግ ካለና ካመነታ በኋላ”፡ እናት አገር ሲባል በአእምሮው ውስጥ ድቅን የምትልበት “ትግራይ“ መሆኗን ገልጿል። አንደዚሁም አቶ ጸጋይ በርሄ – እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት የነበረና፡ ዛሬ ግን የሕዝባዊ ወያነ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆነው – ይህ ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሳያመነታ በቀጥታ “እናት አገሬ ትግራይ ነች“ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ነች አላለም። “ብትግሬነቴ በኩል አድርጌ ነው ኢትዮጵያዊ የምሆነው“ በማለት ግን መልሷን ስስ በሆነች ኢትዮጵያዊነት ሸፋፍኗታል።

ይህ እናት አገራችን ትግራይ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም የሚል መልስ ከታወቁ የሕዝባዊ ወያኔ አመራር አካሎች ሲደመጥ የሚያሳስብ ክስተት ነው። (ለምሳሌ አንድ በኤርትራዊ የፖለቲካ ድርጅት አመራር ውስጥ ያለ ሰው እናት አገሬ ብሎ ኤርትራን ከመጥቀስ ይልቅ ባርካን ወይም ቢለንን ወይም ኩናማን ቢጠቅስ፡ ወይንም ደግሞ ከደጋማው አውራጃዎቻችን – ማለትም ሓማሴን፡ አከለጉዛይ – ብሎ ቢጠቅስ፡ ለኛ ለኤርትራውያን እጅግ የሚያሳስበን ይመስለኛል!!

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)

$
0
0

የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱን መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡

ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡

በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡

በተለያየ መስክ ከሚፈፀመው የሰብዓዊ መብት እረገጣ በተጨማሪ የሃገርን ቤሄራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወይም ገንዘብ የሚይስገኝላቸውን ሁሉ በመዝረፍና በማሸሽ፣ ምስኪኑ ህዝብ በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ብቻ ሳይሆን በስሙ ተለምኖ የመጣውን ሁሉ በመንጠቅ ብዙሃን በርሃብ በሚሰቃይበት ሃገር ለአራት ለአምስት ትውልድ የሚበቃ ሃብት አሽሽተዋል፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም በፊት በተወሰነ መጠን እራሳቸው ላወጡት ህገ-መንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቢያስቸግራቸውም ህጋዊ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት መመላለስ የእለት ከእለት ስራቸው ቢሆንም ከአሁን በተሻለ የህትመት ውጤቶች በቁጥርም በይዘትም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሌላም በኩል ይህው እኩይ ስርዓት ህግን ከመሻሩ በፊት የፓርላማ ጀሌዎቹንን ሰብስቦ ሊሽር ባስበው ህግ ላይ ሌላ ህግ ሲያወጣ ታይቷል ለምሳሌ የቀድሞ የህውሃት አባል የነበሩት አቶ ስዬ አብረሃ በተከሰሱበት ወንጀል ህጉ የሚፈቅድላቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አዲስ ዋስትና የማያሰጥ የፀረ-ሙስና ህግ ማፅደቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ህውሃት በአመለካከትም ይሁን በግል ጥላቻ የራሱን ሰወች ሲበላ ከቻለ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ በማጫረስ አልያም በአደባባይ በደላቸውን እንዲናዘዙ በማስገደድ ከተጠያቂነት እራሱን ሲከላከል መቆየቱ አንድም እራሱን ላለማጋለጥ አልያም በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፅማቸው በደሌች ሰርዞም ደልዞም ህግዊ ለመምሰል የጥር ነበር፡፡

ከምርጫ 1997ዓ.ም በሗላ ያለው በፊት ከነበረው ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እጅግ ብዙ እርቀት ወደ ሗላ የመመለስ ያህል ነው ምክንያቱም በዛን ወቅት በተፈጠረው በጣም ጠባብ አጋጣሚ ህዝቡ ለስርዓቱ ይለውን ጥላቻና ለውጥ ፈላጊነቱን እንዲሁም እነሱ በተግባር የማያውቁትን ዴሞክራሲ ህዝቡ ሲዘምርላቸው፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከነሱ እንደሚሻል ሲያሳያቸው፣ ይበጁኛል የሃገሬንና የእኔን ህልውና ይጠብቁልኛል፣ ብሩህ የነፃነት ጊዜ ያመጡልኛል ይሆኑኛል ብሎ የሚላቸውን እንደራሴዎቹን ሲመርጥ ለአፍታ ይስተዋልባቸው የነበረው ሰዋዊ ባህሪየቸው ጠፍቶ ጫካ ተወልዶ ጫካ ያደገው አውሬነታቸው ሲመለስ የሚችሉትን ገለው ገሚሱን ወደ ማጎሪያቸው አግዘው ጭልጭል ትል የነበረች ተስፋችንን አደበዘዟት፡፡

ከዚህ በሗላ ያለችው ኢትዮጲያ የግል የህትመት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በማፈን በሃገራችው በሞያቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ፣ ለሃገራችን ክብርና ለህዝቧ ነፃነት የሚሟገቱ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት ወይም በሃገራቸው በነፃነት የመኖር መብት አጥተው የሚሰደዱባት አልያም የነሱ የሆነው በሌሎች ተቀምተው የመከራ ቀንበር ከብዶ በግዞት የሚኖርባት ስትሆን ለኢምንት ባለ ጊዜዎች ግን የምድር ገነት ሆና ያሻቸውን የሚሆኑባት የግል እርስት አድርገዋታል፡፡

ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡

ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ ለለውጥ እንዲነሳ በህብረት ከመስራት ይልቅ የነሱን መበታተንና መሰነጣጠቅ አውርተን በድክመታቸው ሳንጠቀም መልሰው ተደራጅተው መብትና ክብራችንን ሲገፉንና ሲፃረሩን እናያለን፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ትተን በሰሞነኛ የወያኔ የጭካኔ ገድል ላይ ቡና እየጠጣን ስናነሳና ስንጥል ከወሬ የዘለለ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ሳንገባና የታደሉት ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚከፍሉትን መስዋህትነት የሚሰሩትን ታላቅ ስራ ስናፈርስና ስንክብ የዜግነት ግዴታችንን በአግባቡ ሳንወጣ ለገዢዎቻችን መሳሪያ ሆነን በዛ ደሃ ህዝብና ሃገራችን ላይ ቁማር እንጫወታለን፡፡

ነፃነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም የመስዋህቱ አይነት የለያይ እንጂ አነሰም በዛም የነፃነት ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋህትነት ይፈልጋል፡፡ ዶክተር መርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳለው “ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የሚቀርብ ነገር አይደለም ሊገኝ አይችልም፣ በማያቋርጥ ትግል እንጂ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነፃነታችን መጣር አለብን ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም. . . . . ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነፃነትን በፈቃደኝነት አይሰጥም በተጨቋኞች መገደድ እንጂ” ይህ ነው እውነቱ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት ከወሬ ያለፈ በተግባር የተፈተን ስራ መስራት ስለምን ተሳነን፣ ስለምን የህይወት መሰዋትነት ለሚከፈልበት የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማገዝ ሰነፍን፣ስለምን ከወያኔ ለምናገኝው ቁራሽ መሬት ብለን የወገኖቻችንን የመከራ ጊዜ እናራዝማለን፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ህዝብ በውጪው አለም እየኖረ ስለምን የህዝባችን የመረጃ ምንጭ የሆነው ኢሳት መስራት ያለበትን ያህል እንዲሰራና ህዝባችን እየተራበ መጥገቡን፣ እየከሰረ ማትረፉን፣ እየተቸገረ መበልፀጉን ከሚነግረው የወያኔ ዲስኩር አውጥተን አማራጭና እውነተኛ መረጃ የሚያገኝበትን፣ ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እያደረገ ያለውን ዘርን ከዘር ሃይማኖት ከሃይማኖት የማጋጨትና የመሳሰሉትን የወያኔን ሴራ ህዝቡ እንዲያቅና በአንድነት ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲነሳ ኢሳትን በመረዳት የዜግነት ግዴታችንን አንወጣም?

በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የሗሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው አስተሳሰብና የሃይል አገዛዝ ተሸብቦ ያልደረሰበት ጫፍ፣ ያላስነባው ህዝብ፣ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፣ ያላፈረሰው አንድነት፣ያላዋረደው የህዝብ ስብእና፣ ያልገባበት የእምነት ተቋም፣ ያልበተነው የሞያ ማህበራት ከከተማ ነዋሪ እስከ ገበሬው አልፎም እስከ አርብቶ አደሩ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡

በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡

ስለሆነም ኢትዮጲያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!

ሞት ለወያኔ!!!
ለአስተያየቶ-ftih_lewegen.yahoo.com


ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሽክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው በሙኒክ የአንድነት ደጋፊ ማህበር

ሞት ለአስራ አንደኛው ቃል!!! በታሪኩ አባዳማ

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል « አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው » እነ ስብሃት « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን » እነ አባይና አዜብ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

የጥቁር ሕዝብ ገድል ታሪክ አምባ፤ አዲስ ምዕራፍ የፃፈች ደም –አቅልማ ነጫጭባ። የጐንቻው!

ፍኖተ ነጻነት ቁጥር 66 ከዜናና ልዩ ልዩ መጣጥፍ ጋር

Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>