Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

በወጣት ሰላማዊ ፖለቲከኞች መታሰር ዙሪያ ኢትዮጵያዉያን ከሰጡት አስተያየት ጥቂቶቹ

$
0
0

ሰላማዊ ሰዎችን ማሰር ቀለቡ ያደረገው መንግስት፣ በትላንትናው እለት ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ከአረና አቶ አብርሃ ደስታ እንዳሰራቸው ተነግሯል። ይህንን በመቃወም በፌስቡክ ኢትዮጵያዉያን ካሰፈሩት መካከል ጥቂቱን እንደሚከተለው ቀንጭበን አቅርበናል፡

ያሬድ አማረ፡
«ወደኋላ አንመለስምዘመን ተሻጋሪ ወጣቶች በቅለናልና በምንም መልኩ ለሚደረግ ማዋከብ፤እስራት እና ግድያ ከጀመርነው የሰላማዊ ትግል መስመር ስንዝር አንዛነፍም፡፡ደግሞም አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ቤቱ እስር ቤት አልያም መካነ መቃብር ውስጥ ሊሆንም እንደሚችል ስንጀምር ያለአስረጂ እናውቃለንና»

Beyo Te ፡
«አብረሃ ደስታ ለዲሞክራሲ ተሰዋ!!!… ሺ የምትወልድ እናት አትንጠፍ!!! ትግሉ ይቀጥላል ኢህአዴግ ይወድቃል!!»

Tigist Alemneh፡
«እንዴት ቢያሰፉት ነው፣ እንዴት ቢገነባ፤
ጉሮኖው ‘ማይሞላ፣ እልፍ ሠው ሲገባ? »

Jomanex Kassaye
«ኢህአዴግ አበቃለት ስለተባለ አያበቃለትም ዛሬ ለእስር ፊት ከሰጠኸው ነገ ከመግደል ላለመመለሱ መተማመኛ የለንም፡፡»

Abebe Tolla
«ኢሃዴግ አበደች ጨርቋን ቀዳደደች
ያንንም ይሄንም ሁሉን ልያዝ አለች፤
እንጃልኝ መዳኗን
ከንግዲህ በኋላ…
ምንም ደስ አላለኝ
እንደው አኳኋኗ… »

Tewodros Belay
«በነውሩ የሚኮራ አገዛዝ ዜጎቼን አሰርኩ እያለ ሲፎክር ያመሻል። የጉድ ሀገር !»

Homa Keno
«ኢህአዴግ ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል ሊንዱ ነበር እያለ ንፁሃንን ዘብጥያ ባወረደ ቁጥር በለየለት ውንብድናና እብሪት ላይ የመሰረተው ሥርአት እየተናደ መሆኑ የገባው አይመስልም …. ደሞ አያፍርም ብሶት ወለደኝ ይለናል» Eshetu

Joe Man Mergu
«የሺ ሰው ግምት! እኔ አብርሃ ደስታን አሰሩት አልልም፤ አሰሯቸው እንጂ»

Beti Abrhem
«ጧት ማታ ሲጠጉን ከተሰማን ሽብር
“ሀገር ” ምን ሊረባን አለን ማለት ይቅር»

Ya Red
«ማእከላዊ ተወስደህ ቶርች ስትገለበጥ አይደለም ግንቦት 7 ‘ዿግሜ 7 ነህ’ ካሉህ ታምናለህ»

Nebiyu Hailu
«ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ እንደምታከማችልኝም አምናለሁ፡፡ ፍርሀትን ብቻ እፈራለሁ » Nebiyu Hailu

Emmii Solomon
«ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ለምን ጻፋቹህ ለምን ያገባናል አላችሁ ተብለው አሁን በየስር ቤቱ የታጎሩትና በየጊዜው እያጠለጠሉ የሚወስዷቸው ስንት ናቸው ? ስንቱን ከሃገር አሰደዱ ? ማነው አሸባሪው ታዲያ ?» Emmii Solomon

Jeremiah De II
«ውሻው ከእብደቱ ሊድን ባለመቻሉ ንክሻውን እንደቀጠለበት ነው!! »


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>