Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

በከበባ ተጀምሮ በከበባ የተጠናቀቀው የኢ.ጋ.መ የፓናል ውይይት –ነብዩ ሐይሉ

$
0
0

ከአምስት ወር በፊት በአስታራ ሆቴል የተመሰረተው የኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መድረክ(ኢ.ጋ.መ) ትላንት ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት “የፕሬስ ነፃነት፣የጋዜጠኞች ደህንነት እና ልማት” በሚል ርዕስ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበተት የፓናል ውይይት በአዲስ ቪው ሆቴል አከናውኗል፡፡
የእለቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈተው የኢ.ጋ.መ ም/ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ ሲሆን በመቀጠልም ሁለት ምሁራን የውይትት መነሻ ሀሳብ አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
“የኢትዮጵያ ፕሬስ አተገባበሩ፣ተግዳሮቶቹና መፍትሄው” በሚል ርዕስ የመጀመሪያውን የውይትት መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ ሲሆኑ፤ “የፕሬስና የፀረሽብር ህጉ ከፕሬስ ነፃነት አንፃር” በሚል ርዕስ ሁለተኛውን የውይትት መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት ደግሞ ታዋቂው የህግ ጠበቃና ተንታኝ አቶ ተማም አባቡልጉ ናቸው፡፡
ሁለቱም ፓናሊስቶች በሀገራችን ያለውን ለጋዜጠኞች ደህንነት እና ለፕሬስ ነፃነት ምቹ ያልሆነ ሁኔታ ለማስተካከል ጋዜጠኞች ሙያቸውን ማዕከል አድርገው መሰባሰብና መንግስትን ማስገደድ እንዳለባቸው አበክረው ተናግረዋል፡፡
ውይይቱ እስኪጀመር ማንነታቸው ያልታወቀ ግለሰቦች የስብሰባ አዳራሹን በአይነቁራኛ ሲከታተሉ ቆይተው፤ ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ መነሻ ሀሳብ በማቅረብ ላይ እያሉ አንድ የአካባቢው የፖሊስ ሃላፊ “የውይይቱን አስተባባሪዎች እንፈልጋለን” በማለት የኢ.ጋ.መ ም/ፕሬዝዳንት ስለሺ ሃጎስንና የማህበሩን ጸሀፊ ነብዩ ኃይሉን በአስቸኳይ ውይይቱ ቆሞ ተሰብሳቢዎቹን እንዲበትኑ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ ሆኖም የኢ.ጋ.መ አመራሮች ስብሰባውን እንደማይበትኑ ገልፀው “እራሳችሁ ገብታችሁ በትኑ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አዛዡም በስልክ ከአለቆቻቸው ጋር ከተወያዩ በኋላ “ፖሊስ ለዚህ ስብሰባ ጥበቃ ማድረግ ነበረበት፤ ስብሰባ እንዳላችሁ ልታሳውቁን ይገባ ነበር፡፡ የበላይ ትዕዛዝ ስለሆነ ከዚህ በላይ አንወያይም በአስቸኳይ ስብሰባውን በትኑ” የሚል ማስፈራሪየ አዘል ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ የኢጋመ አመራሮችም “ለጊዜው የፖሊስ ጥበቃ አላስፈለገንም ስለዚህ አላሳወቅናችሁም፤ ውይይቱን ስለማቋረጡ ደግሞ ተነጋግረን ምላሽ እንሰጣችኋለን” በማለት ወደ ስብሰባ አዳራሹ ከተመለሱ በኋላ የውይይቱ መንፈስ እንዳይደፈርስ ለተወያዮቹ ፖሊስ የፈጠረውን ወከባ ሳይናገሩ ቀርተዋል፡፡
ውይይቱ በመቀጠሉ ያልተደሰቱት የፖሊስ አዛዥ ከስብሰባ አዳራሹ በር ላይ ቆመው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተወያዩ እንዲበተን በማሳሰብ የስብሰባውን መንፈስ እንዲታወክ ሲሞክሩ ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ “ገብታችሁ መበተን ትችላላችሁ የቴሌቪዥንም የእኛም ካሜራ አለ ያደረጋችሁት ለህዝብ ይፋ ይሆናል” የሚል ምላሽ ሰጥቷል፤ የፖሊስ አዛዡም “ኢቲቪ አለ እንዴ? እንደውም የኢቲቪ ጋዜጠኞች ካሉ የአንዳቸውን መታወቂያ አሳዩኝና ስብሰባችሁን ቀጥሉ” በማለት አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ ተገኝነው የመንግስታቸውን አቋም እንያስረዱና የውይይት መነሻ ሀሳብ እንዲያቀርቡ በኢ.ጋ.መ የተጋበዙት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልና የጠ/ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በውይይቱ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡
ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ከተከናወነ በኋላ ተሳታፊዎቹን በእስር ላይ ለሚገኙ 16 ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ጽሁፎችን በመያዝና ፎቶግራፍ በመነሳ ለሙያ ባልደረቦቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር(ኢ.ጋ.መ) ወደፊትም ተከታታይ የውይይት መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ይጠበቃል፡፡10462473_678869572168629_3778114342008319919_n

10309209_678869368835316_8025911486027251704_n10376732_883541164995679_2678356678277931640_n

10462943_883541414995654_2986564461366035758_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles