አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የእሪታ ቀን በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተያዘለት ቀንና ቦታ እንደሚካሄድ ለመገናኛ ብዙሀን ካሳወቀበት ከትላንትናው እለት ማለትም መጋቢት 24/2006 ዓ.ም ጀምሮ ለከተማዋ ነዋሪዎች ስለሰልፉ ዓላማ የሚገልፅ በራሪ ወረቀት እያሰራጨ ይገኛል፡፡እስካሁን ድረስ ከ10.000 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶች ተሰራጭተዋል ፡፡ የነገውን ቅስቀሳ የአንድነት ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ እና የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤት አባላት ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
↧