Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ዜና ከአዲስ አበባ፤ የፍኖተ ነጻነት ጋዜጠኛ አሸናፊ አሳምነው በፖሊስ እየተዋከበ ሲሆን ፖሊስ የአንድነት ቢሮን በድብቅ ቀርጾ ተሰወረ- ፎኖተ ነጻነት

$
0
0

አንድነት እና የ33 ፓርቲዎች በጋራ የጠሩትን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ለቅስቀሳ ዛሬ ማለዳ ወደ ፈረንሳይ አካባቢ ተንቀሳቅሶ የነበረ መኪና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እውቅና ለተቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገውን ቅስቀሳ ለመቅረጽና የህዝቡን ስሜት ለመመልከት ካሜራና ላፕ ቶፕ በመያዝ ከቀስቃሽ ቡድኑ ጋር የተጓዘው የፍኖተ ነጻነት ጋዜጠኛ አሸናፊ አሳምነው ከሌሎቹ የተለየ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ በስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ፖሊሶች በሶሻል ሚዲያው ህዝቡን እየቀሰከስክና የተለያዮ ምስሎችን በመለጠፍ የመንግስትን ስም የምታጠፋው አንተ ነህ በማለት አሸናፊን ማዋከባቸውንና አካላዊ ጉሸማ እንዳደረሱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡አሸናፊን ጨምሮ በኣሁኑ ሰዓት በፖሊስ ጣብያው ሰባት ሰዎች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የታርጋ ቁጥሩ 1762 በሆነ ሎንግ ቤዝ የፌደራል ፖሊስ መኪና የተጫኑ ሲቪል የለበሱ ሶስት የቪዲዮ ካሜራ ያነገቱ ሰዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት የውጪ በር ሳያስፈቅዱና ምክንያቱን ለመናገር ሳይፈቅዱ በተጣደፈ ሁኔታ ቀረጻ አከናውነው በፍጥነት መሰወራቸውን የፓርቲው አባላቶች ገልጸዋል፡፡

በዋናው ቢሮ በር ላይ ‹‹የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ፣ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ›› በሚል ዐቢይ ርዕስ የተሰቀለው ፖስተር የአንዷለም ፣በቀለ ገርባ፣ናትናኤል መኮንን፣ርዕዮት ፣እስክንድርና የአቡበከር ምስሎች ተለጥፈውበት ምስሎቹ ስር በደማቁ‹‹ሁሉም የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ››የሚል መፈክር ሰፍሮበታል፡፡

ፖሊስ በአግባቡ ፓርቲውን በመጠየቅ ፎቶውን ማንሳትና የፖስተሩን ተመሳሳይ መውሰድ የሚችል ቢሆንም ህገ ወጥ ቀረጻ ለምን በድብቅ ማከናወን እንደፈለገ ለጊዜው ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡
ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ለመሳተፍ ዝግጁነታቸውን እየገለጹ ነው ‹‹ቅዳሜ መሪዎቻችንን በመዘየር እሁድ ሰልፍ እንወጣለን››በሚል መሪ ቃል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የአንድነትን ሰልፍ በመቀላቀል ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት መዘጋጀታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ 8303_519242628160676_191113154_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>