Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ሊያካሂድ የነበረው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመንግስት ዕውቅና አግኝቶ ለመስከረም 19 ተላለፈ!! –“የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት”ግብረ ሐይል

$
0
0

አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን አንጂ መንግስት ሁለት ምክንያቶች በማቅረብ ለሐምሌ 19 እንዲተላለፍ ጠይቋል፡፡ በመስቀል አደባባይ አካባቢ በባቡር ግንባታ ምክንያት የታጠሩ ቆርቆሮዎችን ለማንሳትና አዲሱን ዓመት አስመልክቶ በአካባቢው ባዛር እየተደረገ በመሆኑ መንግስት እንዲራዘም ጠይቋል፡፡ ለመንግስት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን በቂ ምክንያት ሲቀርብ እንዲያራዝም ህጉ የሚፈቅድ በመሆኑ ፓርቲያችን ህግን ተከትሎ ተቀብሎታል፡፡

ስለሆነም ይህ ከመንግስት እውቅና የተሰጠውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መስከረም 19 በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ሰልፉ ከ23 የአንድነት የአዲስ አበባ መዋቅር አደረጃጀቶች ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ይተማል፡፡ በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ብሶቱን እዲገልፅ አንድነት ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ድል የሕዝብ ነው!!1239808_513470548737884_1857845280_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>