የጎንደር ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች ሕዝቡ ወደ መስቀል ኣደባባይ መጓዙን ይዟል። የሕወሓት ወታደሮችና ፖሊሶች በግርምት ኣፍጥጠው እያዩ መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛውን ለመቁረጥ ጥረት እያደረጉ ነው። ፤በፍርሃት እንዳይወጣ እያደረጉት ያለው ሕዝብ በልበሙሉነት ኣደባባዩ በሚሊዮኖች እየሞላ ነው፤የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኣይሰራም።
የወልቃይት ጉዳይ የኣማራና የኣማራነት ማረጋገጫ እንደሆነ በተግባር እየታየ ነው። አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ በሚለው ከፍተኛ ጩሀት ያሰማል የክልሉ ፓሊስ ከህዝብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ተቀላቀለ አንድነት ሀይል ነው ህዝብ ሀይል ነው።ሁለም አቅጣጫ በተለይም በፒያሣ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሠልፋ ታዳሚ በመፈክሮችና በቀሥቃሽ ሙዚቃዎች ታጅቦ ወደ መሥቀል አደባባይ እየተመመ እንደሚገኝ የሠልፋ ተሣታፊ ከሥፍራው ነግሮኛል።
የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ከሥፍራው እንደሌሉ እና አጋዚ ግን ከትናንት ጀምሮ ቢኖርም ህዝቡ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት ሠላማዊ መንገድ የሠልፉን ግብ ልማሣካት እርብርብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ። ……ምኒሊክ ሳልሳዊ
ይሄ ነው ሰንደቁ፣ይሄ ነው ባንዲራው። (እዚህ የብአዴን፣ የህወሀት….(የድርጅት ባንዲራዎች) ቦታ የላቸውም፣ ምክንያቱም ይህ ጎንደር ነው።ኮራሁባችሁ!!!
ነፃነቱን አደባባይ ወጥቶ ማጣጣም የጀመረን ህዝብ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም። ህወሀት/ኢህአዲግ ሆይ ያለህ ብቸኛ አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው።
በኦሮምያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም!
በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ በዚህ መልኩ ለኦሮሞ ህዝቦች ትግል ያላቸው አጋርነት ገልፀዋል። ………..ዳኒኤል ፈይሳ
በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ሙሉ በሙሉ ከወያኔ መንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆናለች በከተማዋ ውስጥ ምንም አይነት የወያኔ መንግስት ወታደርም ሆነ ፖሊስ የለም ከተማዎ መቶ በመቶ በህዝቡ ቁጥጥር ስር ውላለች ከዚህ በላይ ድል ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ህዝቡ እየጠየቀ ይገኛል ። የአጋሰሱ ጦርን ጨምሮ ሌሎች የወያኔ ጭፍራ ወታደሮች በየጢሻውና በየጓዳው ተደብቀውና ተወሽቀው ከዚህ ህዝብ ቁጣ አምላክ እንዲያድናቸው በፀሎት እየተጉ ይገኛሉ ! ምክንያቱም በዛሬ ቀን የተገኛ የወያኔ ጭፍራ ጀሌ ወታደር እንደ ገብስ ይወቀጣልና !!!!………ጥላዬ ታረቀኝ
ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል!፡፡ ቀጣይ ሰልፍ የሚካሄደው ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው በሰላም ያገናኘን፡፡