Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

የጃዋር መሀመድ ጭምብልና የኦሮሞ ድርጅቶች ወልጋዳ ፍርድ (ከአይናዲስ)

$
0
0

አንድ የተምታታብኝ ነገር አለ:: ምናልባት ችግሩ ከእኔ ከሆነ እንጃ:: የኦሮሞ ፖለቲከኞች ነን የሚሉትን አንዳንድ ሰዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሳይ ግራ እጋባና “እውነት እኒህ ሰዎች ፖለቲከኞች ናቸው ወይስ እኔ ስለፖለቲከኛ ምንነት ያለኝ ግንዛቤ ውስን ስለሆነ ይሆን!” ብየ ራሴን ለመጠየቅ እገደዳለሁ::

እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ፖለቲከኛ ሲባል የማህበረሰብን ፖለቲካዊ: ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄወች አንስቶ በግል ወይም በቡድን ታቅፎ በአባልነት: በአስተባባሪነት ወይም በአመራር ሰጭነት ታግሎ የሚያታግል: ይህም ማለት
- እንከን አለው ብሎ ያመነውን የመንግስት ፖሊሲ ቀረ የሚለው እንዲሟላ: እንዲስተካከል ወይም ተግባራዊ እንዳይደረግ:
- ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ:
- ሙስናና አምባገነንነት እንዲወገዱ እና
የተሻለ አማራጭ ነው ብሎ ያመነውን ፖሊሲና የአስተዳደር ስርአት ለማስፈን በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል የሚታገል ሰው ማለት ነው::
አንዳንድ የእኛ ሀገር ፖለቲካ ፓርቲወችና ፖለቲከኛ ነን ባዮች ግን የሚሰሩትን የማያውቁ ራሳቸው ሰፊ ትምህርትና እገዛ የሚፈልጉ: የዋሀንን አስከትለው አብደው የሚያሳብዱ ናቸው:: ፖለቲከኛን ፖለቲከኛ የሚያሰኘው አፉ እንዳመጣ መናገሩ ሳይሆን የህዝብን ፍቅርና ከበሬታ ለማግኘትና ቀልብን ለመሳብ በብልሀት መንቀሳቀስ መቻሉ ነው:: የህዝብ ድጋፍ የሌለው ፖለቲከኛ ፖለቲከኛ ሳይሆን የቀን ህልመኛ ነው::
ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ምክንያት የሆነኝ የኦሮሞው ፖለቲከኛና አክቲቭስት ነው እየተባለ የሚወራለት የጃዋር መሀመድ “አዎን ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት” በሚል ርእስ ያስነበበን ጽሁፍ ነው::
እንደእውነቱ ከሆነ ጃዋር ፖለቲከኛ ሳይሆን የፖለቲካ ጠብታ እውቀት የሌለው: ያልበሰለ: ግልብና አፉ እንዳመጣ የሚቀባጥር መናኛ ሰው ነው:: በአንድ ወቅት በአንድ የስብስባ ቦታ ላይ ተገኝቶ ካደረገው ንግግር ተቀንጭቦ በፌስቡክ ተለቆ ስለነበር ያለውን አዳምጨዋለሁ:: በዚህ ንግግሩ ላይ እርሱ በተወለደበት አካባቢ የሚኖረው ከ90% በላይ የሚሆነው ህዝብ እስላም እንደሆነና ክርስቲያኖች አንገታቸውን ደፍተው እንደሚኖሩ ገልጾ አንገቱን ቀና የሚያደርግ ክርስቲያን ካለ አንገቱን በሜንጫ እንደሚባል በኩራት ነግሮናል:: ታዲያ ይህ ሰው አክራሪ እስላም ነው ወይስ ፖለቲከኛ?
የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አንገቱን መድፋት አለበት: አንገቱን ካቀና በሜንጫ ነው የምንለው የሚለው ጃዋር ለክርስትና እምነት ተከታዩ የኦሮሞ ህዝብ እንዴት ሊታገል ይችላል? ምናልባትም ከሶማሊያና ከአፋር ህዝብ በስተቀር ኦሮሞን ጨምሮ ሌላው ህዝብ ከፊሉ የእስልምና ቀሪው ደግሞ የክርስትና እምነት ተከታይ ነው:: ታዲያ የፖለቲካ ተዋናይና አክቲቭስት ነኝ የሚል ሰው እንዴት ነው ህዝብን በሀይማኖት ለያይቶ የእኔ እምነት ተከታይ አይደለም የሚለውን የህብረተሰብ ክፍል ለማስጠቃት አደባባይ ቆሞ የሚቀሰቅስ? ጃዋር ምናልባት ከሶማሊያው አልሸባብ ወይም በሶርያና ኢራቅ ከሚንቀሳቀሰው እስላማዊ መንግስት (ISIL/ISIS) ከሚባሉት ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያለው ወይም እኒህ ድርጅቶች በሚፈጽሙት ተግባር ተማርኮ በኦሮሞ ፖለቲከኛነት ጭንብል ተሸፍኖ በሶማሊያና በመካከለኛው ምስራቅ የሚፈጸመው ሽብር ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደገም ለማድረግ የሚንቀሳቀስ አሸባሪ ሊሆን ይችላል::
ይህ ሰው በእናቱ በኩል የሰሜን ሸዋ አማራ (በአሁኑ የዘር አመዳደብ)እንደሆነ ስለርሱ በተጻፉ ጽሁፎች ላይ አንብቤአለሁ:: የተባለው እውነት ከሆነ የእናቱን ጡት የሚነክስ አሳፋሪ ሰው ነው ከማለት ውጪ ምን ሊባል ይቻላል!
ለነገሩ ለእኔ አማራ ማለት አማረኛ ተናጋሪ የሆነ ሳይሆን ሀገሩን በአንደኛ ደረጃ የሚወድ ማለት ነው:: በዚህ ስሌት መሰረት ከአሁኑ የአማራ ክልል መወለድ ብቻውን አማራ ሊያሰኝ አይችልም: ወይም ከአማራ ክልል ውጪ ካሉት ክልሎች ከአማረኛ ቋንቋ በተለየ ቋንቋ አፉን የፈታ ሰው አማራ ሊባል አይችልም ማለት አይደለም::
ይህች ሀገር ሀገር ሆና እስካሁን የዘለቀችው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህብረት በተጋደሉት ተጋድሎና በከፈሉት መስዋእትነት ነው:: ኢትዮጵያ በሀይል ተገፍታ መሬቷ ሲነጠቅና የሌላ ሀገር ባንዲራ ሲውለበለብ ሲያዩ በንዴት እምባ የታጠቡ: በሀይል የተያዘባትን መሬት አስለቅቃ ባንዲራዋን መልሳ ስትተክል በደስታ ያነቡላት: በደምና ባጥንታቸው አስከብረዋት የኖሩ: እነርሱ ናቸው አማሮች:: አማራ ለመሆን ደግሞ ከጎጃም: ከወሎ: ከጎንደር ወይም ከሸዋ መወለድን አይጠይቅም:: ስለኢትዮጵያ አብዝተው የሚጨነቁ ሁሉ አማሮች ናቸው:: አማርኛማ በየትኛውም ክልል ተናጋሪ አለው:: አማረኛ የተናገረ ሁሉ አማራ ነው ቢባል ኖሮ አበበ ገላው (የእኔ ጀግናየ) በአደባባይ አስደንግጦት ከበሽታው ጋር ውግዘቱ ታክሎ አካሉንም ቅስሙንም ስለሰበረው ማገገም አልችል ብሎ እስከወዲያኛው የተሸኘው ሟቹ ጠ/ ሚ/ር መለስ በቃላት አጠቃቀሙ: በአረፍተነገር አመሰራረቱ: በቅኔና በምሳሌያዊ አነጋገሩ ከአማራ ክልል የተወለዱትን የሚያስከነዳ አልነበረም እንዴ! ነው ወይስ በደምና በአጥንት ንጹህ አማራ: ንጹህ ኦሮሞ— አለ ለማለት ነው:: ከወያኔ በፊት የነበሩት ሁሉም መንግስታት አማሮች ነበሩ የሚባለውም በነበራቸው ያገር ፍቅር እንጅ ከአሁኑ የአማራ ክልል የተገኙ ስለነበረ አይደለም:: ለምሳሌ እኔ በአሁኑ ጊዜ ብሄር እየተባለ ስም ከተሰጣቸው ውስጥ የሶስቱ ደም አለኝ:: ያም ሆኖ እኔ ሀገሬን የምወድ: ያስተዳደር ስርአቱ ተስተካክሎ ልጆቿን አሰባስባ ኢትዮጵያ እንደሀገር እንድትቀጥል ጽኑ ፍላጎት ያለኝ ስለሆንሁ ዘሬን ለማወቅ ለሚጠይቀኝ ሰው “አማራ ነኝ” ብየ ነው መልስ የምሰጠው::

ጃዋር የሚባለው ሰው “ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት” ይለናል:: የትኛዋ ኦሮሚያ? ወያኔ ኦሮሚያ ናት ብሎ የከለላት ናት ወይስ ሌላ? ይህን ጥያቄ ያለነገር አላነሳሁትም:: ኦነጎች “ወሎ ኦሮሞ ነው:: ኢሉ: ባቦ: ወረሂመኖ:—የመሰረቱት ወረኢሉ: ወረባቦ: ወረሂመኖ የኦሮሞ ሀገር ነው” እንደሚሉ ስለማውቅ ነው:: ታሪክን መለስ ብለን እንይ ካልን አይደለም ወሎና ሸዋ: አርሲ: ወለጋ: — የኦሮሞ መኖሪያወች አልነበሩም:: በወቅቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ነገስታት የተዳከመውን ሀይላቸውን ካጠናከሩ በኋላ በኦሮሞ ወራሪወች በሀይል የተያዘባቸውን መሬት ማስለቀቅ እየቻሉ በመፈናቀል ምክንያት በኦሮሞወች ላይ ሊደርስ የሚችለው ችግር እንደሰው አሳስቧቸው “ተዋቸው እንደሀገሬው ገብረው ይኑሩ” ብለው ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደሰጧቸው በኢትዮጵያውያንና በውጭ ሀገር የታሪክ ጸሀፊወች ተረጋግጧል:: በዚህ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን ያገኘው ኦሮሞም ቃሉን ሳያጥፍ በሀገራችን ላይ ጦርነት የከፈተውን ጠላት ለመመከት በሚደረገው ትግል ሁሉ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጎን ከፊት ረድፍ በመሰለፍ በመስዋእትነቱ ሀገራችንን ሲያስከብር ኖሯል::

የኢትዮጵያ ታርካዊ ጠላቶች(አረቦች) የኢትዮጵያን ሀይል ለማዳከም ሲሉ ከቀጥተኛ ወረራ ጀምሮ የተለያዩ ሙከራቸውን ሲያደርጉ ኖረዋል:: ይህ ሙከራቸው በ950ወቹ መጀመሪያ አካባቢ በሰሜን የሀገራችን ክፍል ባቋቋሙት “ጀብሀ” በኋላም ከዚሁ ድርጅት አፈንግጠው በወጡት ሻእቢያወች አፍራሽ እንቅስቃሴ የመጀመሪያው ህልማቸው ተሳክቶ ኢትዮጵያ በቀይባህርና አካባቢው ላይ የነበራትን ድርሻ እንድታጣ: ኤርትራ እንድትገነጠልና ወደባልባ እንድትሆን ተደረገ:: ሻእቢያ የአረቦችን መፈክር አንግቦ የተነሳበትን አላማ ከዳር ለማድረስ የቀሪውን ኢትዮጵያዊ ሀይል መበተን ነበረበት:: በመሆኑም ከአርብ ሀገሮች በሚፈስለት ዶላርና ሁለንተናዊ ድጋፍ ታግዞ ወያኔና ኦነግን ጨምሮ የጋምቤላ: የቤሻንጉል: የሲዳማና የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅቶች እንዲመሰረቱና ጸረ ኢትዮጵያ ትግል እንዲያካሂዱ በማድረግ አላማውን በግንቦት 1983 ዓ.ም ላይ አሳካ::

ወያኔ የሻእቢያ የበኩር ልጅ ሆኖ በተለየ እንክብካቤ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ ነጻ አውጭ ድርጅት ነን የሚሉትን አሰባስቦ የብሄር ብሄረሰቦችን “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል” መብት በህገመንግስት አስጸድቆ የኤርትራን ነጻነት ህጋዊ ካደረገ በኋላ ትግራይንም ገንጥሎ የትግራይን ሪፕብሊክ ይመሰርታል ተብሎ ሲጠበቅ ንዋይ አጓጉቶት ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ህዝቡን በዘርና በሀይማኖት እየከፋፈለና እየዘረፈ እስካሁን ቀጥሏል::

ከመነሻው ኦነግም ሆኑ ሌሎች የጎሳ ድርጅቶች የተመሰረቱት የአረቦችን አላማ ለማሳካት ተብሎ እንጅ የራሳቸው የሆነ የተለየ የፖለቲካ አጀንዳ ስለነበራቸው አልነበረም:: ከእኒህ የሻእቢያና የወያኔ አብሪ ሆነው ወያኔንና ሻእቢያን እየመሩ ወደመሀል ካስገቡት ድርጅቶች መሀል በሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ደም የተጨማለቀ እንደኦነግ ያለ የተበላሸ ድርጅት የለም:: በአሶሳ: በአርባጉጉ: በወተርና በሌሎችም አካባቢወች ዜጎች አማራ በመሆናቸው ብቻ በዚህ ድርጅት እንደበግ ታርደዋል: በእሳት ተቃጥለዋል: ከነህይወታቸው በገደል ተጥለዋል: ብዙወችም ሀብት ንብረታቸው ተወርሶ ተፈናቅለዋል:: ይህ ድርጊት ዛሬም አላበቃም:: በአንድ ወቅት አንድ የኦነግ ባለስልጣን ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው “የኦሮሞ ሀገር የት ነው?” ተብለው ተጠይቀው ነበር:: ታዲያ እኒህ ባለስልጣን አፋቸውን ሞልተው “ኦሮሞ የረገጠው ሁሉ የኦሮሞ ሀገር ነው” ነበር ያሉት:: ኦነግን የሚመሩት እንዲህ ያሉት የዕውር ድንብር ተጓዦች ናቸው:: የኦነግና የወያኔ ፍቅር አልቆ በነገር መጎሻሸም በጀመሩበት ወቅት ኦነግ በሬዲዮ ጣቢያው እኛ ከመንዝ በግ: ከጎጃም አጋሰስ ወይም ከትግራይ ድንጋይ አልፈለግንም:: እኛ ያልነው የራሳችን ክልል ባለቤት እንሁን ነው:: ሲል የተፈጥሮ ሀብቱ ተሟጦ ድንግይ ብቻ የተካማቸበት መሬት ነው ያላችሁ ሲል ወያኔን በነገር ጎንጦታል::

ያም ሆኖ ኦነግና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች አሁንም ቢሆን እንታገልለታለን በሚሉት የኦሮሞ ህዝብ ላይ ወያኔ ዛሬ ላይ እያደረሰበት ካለው በደል ይልቅ: የአሁኑ የኦሮሞ ትውልድ አያቶቹ እንኳን ባልተፈጠሩበት ከ120 አመት በፊት: በአጼ ሚኒሊክ ዘመነመንግስት ጊዜ: በታሪክ ባልተመዘገበ የቡና ወሬ እና በሻቢያና በወያኔ በተፈበረከው የነአኖሌ ታሪክ: በኦሮሞ ላይ ተፈጽሟል በሚሉት ግድያ ሲያለቅሱ መስማት እጅግ ያስገርማል::
አጼ ሚኒሊክ ሀገራቸውን ከጠላት ለመከላከል: ህዝባቸውን ለማሰልጠን: ኢትዮጵያን የወቅቱን የቴክኖሎጅ ውጤት ተጠቃሚ ለማድረግ እና ህዝባቸውን አሰባስበው አንድ ጠንካራ ሀገር ለመመስረት ባደረጉት ጥረትና በዘመናዊ አስተዳደራቸው ሞዴል መሪ መባል የሚገባቸው ድንቅ መሪ ነበሩ:: ይህን የምለው ለአጼ ሚኒሊክ በሀሰት ለመከራከር ፈልጌ ሳይሆን ሚኒሊክን የሚያህል ብልህና አርቆ አሳቢ መሪ በኢትዮጵያ እንዳልተፈጠረ ዕውነቱን ለመናገር ነው:: በምርኮ የያዙትን ሰው እጅና እግር እየቆረጡ በሚቀጡበት በዚያ ጊዜ ምርኮኛን ተንከባክበው አልብሰውና አጉርሰው ህዝብን ሰብስበው “እኔ እኮ የመጣሁት ሀገር ላጠፋ አይደለም:: እንዳገር ገብር ብለው እምቢኝ ብሎ ስለወጋኝ ነው:: በሉ ተእንግዲህ እንደማንኛውም ህዝብ በየአመቱ ግብር አስገቡ:: ግብር የዜግነት ግዴታ ነው:: ለማስተዳደሩ ግን የወደዳችሁትን ልጃችሁን መልሸ ሾሜላችኋለሁ” ብለው የሚሉ ወደር የማይገኝላቸው ታላቅ ሰው ስለሆኑ ነው::
የያካባቢው ገዥወች በኦሮሞ ህዝብ በሀይል የተያዘባቸውን መሬትለማስለቀቅ ውጊያ በከፈቱበት ወቅት አጼ ሚኒሊክ “ጋላም ቢሆን እንዳይፈናቀል: እንዳይገደል” የሚል አዋጅ በማወጅ ኦሮሞው ተረጋግቶ በኢትዮጵያ ጥላ ስር እንዲኖር ያደረጉ ሰብአዊነት የተላበሱ ምርጥ መሪ ነበሩ:: ይሁንና ታሪክን ገልብጠው የሚያነቡ የኦሮሞ ድርጅቶች የምኒሊክን ውለታ ረስተው ጌቶቻቸው ያስጠኗቸውን ውዳሴ ሌት ከቀን እየደገሙ በአሁኑ ወቅት በኦሮሞው ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሳይቆረቁራቸው “ምኒሊክ ጉድ ሰርቶናል” እያሉ ዛሬ እየገደሏቸው ያሉትን የህወሀት ታማኝ ወታደሮችና አባሎችን ሳይሆን ለፍቶ አዳሪ አማሮችን መግደልና ማሳደድ ቀጥለዋል::
ኦሮሞወች በአንድ በኩል የሚኒሊክን ውለታ ለመክፈል በሌላም በኩል የጋራ የሆነችውን ሀገር ከወራሪ ሀይል ለመታደግ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርገው እያውለበለቡ በአጼ ሚኒሊክ: በአጼ ሀይለስላሴም ሆነ በኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም የአስተዳደር ዘመን ከግምባር ተሰልፈው ደምና አጥንት ከፍለዋል:: የዛሬ የኦነግ እና የሌሎች ኦሮሞ ድርጅቶች አላማ አራማጆች ግን እኒያ የኦሮሞ ልጆች በእልህና በወኔ የተዋደቁለትን: በደስታ እና በሀዘን ያነቡለትን ባንዲራ የሚያቃጥሉ ብሎም ኢትዮጵያዊ አይደለንም በማለት ጸረ ኢትዮጵያ አቋም በመያዝ የጠላት መሳሪያ (በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኦሮሞ ነን ባዮች) እና የሀገር ስጋት መሆናቸው እጅግ ያሳዝናል:: በኦነግ ስም የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ሲሉ አስነዋሪ ድርጊት የሚፈጽሙ: ወደውም ሆነ ተገደው የኦነግ አባላት የሆኑት የዲያስፖራው አባላት ለነጃዋር መሀመድ ገቢ በማሰባሰብ የገቢ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ነው:: ጃዋር በውጭው አለም ዘና ብሎ የሚኖረው እኒህ ጥገኝነት ጠያቂወች የድጋፍ ደብዳቤ ለማግኘት ከሚከፍሉትና ከአባላት ከሚሰበሰበው የአባላት ወርሀዊ መዋጮ ነው::

ርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ታማሚወች ከህመማቸው ሊፈወሱ በየዋህነት ተታለው በሉ የሚባሉትን የሚሉ: አድርጉ የሚባሉትን የሚያደርጉቱ ደግሞ ወደህሊናቸው ተመልሰው መንገዳቸውን ሊያስተካክሉ እንዲችሉ የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሆን ዘንድ እንለምናለን::

ኢትዮጵያዊነት ያብባል


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles