2.4 ሚሊዮኑን ካሳ ለምን አንቀበልም አሉ ?
===========================
ብላቴናው መሀመድ ዛሬ እንደ ጓደኞቹ እየቦረቀ እንዳይማር በሀኪሞች ስህተት የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ። መሀመድ አልጋ ላይ ሆኖ ላይሰማና ላያይ ያሰናከሉት ሀኪሞችና ሀኪም ቤቱ ለፍርድ ይቀርቡ ዘንድ አድካሚ ጉዞን ዘጠኝ አመት ለዘለለ ጊዜ ተጉዘዋል።
የመሀመድ ቤተሰቦች አበባቸውን የመነጠቅ ያህል እገረ ተከሉ መልከ መልካም ድንቡሽ የ4 ዓመት እድሜው ብላቴና መሀመድ ድክ… ድክ ብሎ ለቀላል ህክምና ገብቶ ተሰናክሎባቸዋል ፣ አባትና እናት ብሎም ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ቅስማቸው ተሰብሯል ። እንዲህ ሆኖ ዘጠኝ አልፎ ፣ አስረኛ አመት ተጠግቷል !
ከምንም በላይ በእስልምና የኢማን መሰረት በሆነው ( ቀዳ ወል ቀድር ) ” በፈጣሪ ዘንድ ቀድሞ በተጻፈው የሰው ህይዎት የሚያምኑት የብላቴናው መሀመድ ቤተሰቦች በልጃቸው የሆነው የፈጣሪ ፈቃድ መሆኑን አጥብቀው ያምናሉ ፣ ፈጣሪ አላማረሩትም ። በሆነው ሁሉ ፈጣሪን “ተመስገን!” እያሉ ለልጃቸው መሰናከል ያለ እውቀታቸው በሰሩት ቀዶ ጥገና ጥፋት የፈጸሙትን ሀኪሞችና ሆስፒታሉ በልጃቸው የሰሩት ስህተት ፍርድ ያገኙ ዘንድ ገና ከጅምሩ ተግተዋል። ለብላቴናው መሰናከል ምክንያት የሆኑ ወንጀለኞች ናቸው ብለው በማመን ወደ ፍርድ ቀርበው ቅጣታቸውንና የጉዳት ካሳ ማግኘት ሀቅ በቅዱስ ቁርአን ሳይቀር የተረጋገጠ የተፈቀደ ነውና ይህ መብታቸው እንዲከበር ስለፍትህ አቤት በማለት ላይ ይገኛሉ!
አድጋካሚው የፍትህ ጥያቄ ላለፉት 9 ዓመታት ተሸፋፍኖ ቢባጅም በደል ተዳፍኖ የማያስቀረው ፈጣሪ ረድቷቸው የመጀመሪያ ደረጃ ፍትህ ብስራትን ከወራት በፊት አግኝተዋል ! ብላቴናው መሀመድ የሚገኝበት የዶር ሱሌማን ፈቆ ሆስፒታል ዶክተሮች በተሰራ የህክምና ስህተት መፈጸሙን የሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የዶክተሮች ቡድን አረጋግጧል። ቡድኑ ምንም እንኳን በኮሚቴ ተዋቅሮ ስድስት አመታት ጉዳዩን በማጥናትና በመመርመር ሀኪሞች አስቀርቦ የጥፋተኝነት ውሳኔ ባያሳልፍም ሀኪም ቤቱን ጥፋተኛ ያደረገበት ሰነድም ይፋ ሆኗል። በውሳኔው ሆስፒታሉ ብላቴናው መሀመድን በቀጣይ መደገፍ እንደ አስፈላጊነቱ በነጻ ህክምና የመስጠት ኃላፊነትና 2.4 ሚሊዮን ሪያል ካሳ እንዲሰጥ የስምምነት ውሳኔ ተላልፏል። ዳሩ ግን በረባ ባልረባ ሰበብ ለተበዳይ ህክምና አጓድሎ ለአመታት የተበዳይን ቤተሰቦች ጉዳዩን ሰልችተው እንዲተውት ለማሰላቸት ሲሰራ የከረመው ሆስፒታል አስተዳደር ውሳኔ እንደተሰጠ አስታማሚ የብላቴናው መሀመድን እናት ከሰጧት መጠለያ በኃይል በማስወጣት ” 2.4 ሚሊዮን ሪያል ካሳ የምከፍለው ወላጆቹ በህክምና መሳሪያ የሚንቀሳቀሰውን ታዳጊ ስታስወጡ ነው!” በማለቱ በቤተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ። ይህን የማይቀበሉት እናቱና ቤተሰቦች አይደሉም ። ኩሩና ሰበአዊዋ እናት ሀሊማ ” ልጀን በገንዘብ አልለውጥም ፣ ልጀን ወደ ነበረበት መልሱልኝ! ” ብላ በምሬት የተናገረችበትን ዝርዝር ዘገባ በታዋቂ ጋዜጦች በሳውዲ ጋዜጥና በአረብ ኒውስ የተከታተሉ የህክምና ባለሙያ ” ገንዘብሽን ተቀብለሽ ልጅሽንም ውሰጅ! ” የተባለችበትን እርምጃ ሲቃወሙ በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል ” As a medical worker myself, I feel sorry for the boy and his mother… We should be the one giving comfort to those who rely and trusted us… If the ministry has verdict that the hospital is at fault, then even if the mother receives the monetary compensation; the hospital should still give treatment to this boy even its forever! Taking the boy out of the life support machine is haram BUT if the boy is brain dead and arrested then he shouldnt be resuscitated. BUT to intentionally remove him from life support? No.. Please..” ” እንደ ህክምና ባለሙያ በልጁና በመሀመድ ላይ በተፈጠረው በጣም አዝናለሁ ፣ አምነውነው ወደ ህክምና ለሚመጡ ሰዎች ምቾትና ተገቢ ግልጋሎት እርዳታ የማድረግ ኃላፊነት ያለብን የህክምና ባለሙያዎቹ ነን …
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆስፒታሉ ጥፋተኛ ነው ብሎ ውሳኔ ካሳለፈ ሆስፒታሉ ለእናቱ የእናትነት ካሳ monetary compensation ከሰጠ በኋላ ልጆን እስከ መጨረሻ የማሳከም ኃላፊነት አለበት ። ልጁን ከህክምና መርጃ መሳሪያ ማላቀቅ ሀጢያት ነው ። ምናልባት አንጎሉ የማይሰራ ከሆነ እርዳታ ሊደረግለት ይገባል እንጅ ሆን ተብሎ ከህክምና መርጃ መሳሪያ ማላቀቅ ተገቢ አይደለም … ” በማለት ሙያዊ ምክራቸውን ሰጥተዋል !
የብላቴናው አባት በሚኖርበት የመካ ከተማ እየሰራ ቤተሰቡን ሲደግፍ ሚስት የመካ ቤቷንና ባሏን ርቃ ከቀረች ልጇ ከአሚና ጋር በመሆን ከልጇ ጎን ላለፉት አስርት አመታት አልተለየችም። እናት ሀሊማ ሙዘይን በሌለ ከወዲያ ወዲህ ብላ ያልነቃ የተኮላሸባት የስደት መከራ የዘር ፍሬዋን በስስት እያየች እያስታመመች ፣ ልጇን እያስተማረች የምትገፋው ህይዎት ከባድ ሆኗል ። ያም ሆኖ ከገንዘብ ይልቅ ሰብዕናን አስቀድማ በሆስፒታሉ ባሳለፈችው ህይዎት የተፈራረቀባት እንግልትና ያሳለፈቻቸው የስቃይ አመታት ታሪክ ተነግሮ አያልቅም ። በሀብትና ጸጋ ተማምኖ ፣ በማን አለብኝነት እብሪት የታበየውና የታዳጊውን የመሀመድን ብሩህ ህይዎት ያጨለመው ሀኪም ቤት ኃላፊዎች ካሳውን ከፍለው ለመሀመድ የተሻለ ህክምና መትጋት ሲገባቸው ይህን የማድረግ ፍላጎት አላሳዩም ። ይባስ ብለው የጥፋተኝነት ፍርዱ ሲሰጥ ከመሳሪያ እርዳታ ውጭ ላፍታ መንቀሳቀስ የማይችለውን ተገፊ እጓለ ማውታ እናቱ ” ይዛ ትዎጣ !” ማለቱ ሊሆን የማይችልና የከበደ በመሆኑ ፈጣሪዋ እንደማያጓድልባት የምትናገረው እናት ፍትህን ፍለጋ እጣ ነፍሷን መባዘኗ ማናችንም ለዘገየው ፍትህ እስኪሳካ ስትደክም ልንደግፋትና ስለ ሰብዕና ብለን ከጎኗ ልንሆን ግድ ብሏል … !
ድጋፍና እርዳታው ለምን አስፈለገ ?
======================
ድጋፍና እርዳታው ለምን አስፈለገ ? በሚለው ርዕስ ዙሪያ ማብራሪያ እንድሰጥበት ያስገደዱኝ ምክንያት አለ። ይህም ለብላቴናው መሀመድ ቤተሰቦች የመንግስት ተወካዮች ድጋፍ ይጎላል በሚል ላቀረብኩት ጭብጥ ያለው የመረጃ ግብአት ያመማቸው አደግዳጊ ጭፍን የመንግስት ተወካይ አጋፋሪዎች ቀጠን ያለች ዘመቻ ቢጤ መጀመራቸውን በመረዳቴ ድጋፍ ሰጭዎችን ግራ እንዳያጋቡብኝ ግልጽ ፍላጎቴን ለማሳዎቅ በመሻት ነው ። ከተቀነባበረው ስም ማጥፋት ጎን ለጎን እርዳታውን የመሰብሰብ ሀሳብ ሳቀርብ በእርዳታ ስም ሀብት ማከማቸት ፍላጎት እንዳለኝ በመግለጽ ገፍተውበታል ። ያም ሆኖ ይህ የተራ ወሮበላ አካሄዳቸው የጀመርኩትን እንደማያስቆመኝ ከመግለጽ በተጓዳኝ እርዳታው ያስፈለገበትን ምክንያት ለቀሪ ወዳጆቸ ማሳወቁን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ !
” የፍትህ ያለህ “በማለት እያነባች ፍትህ ርትዕ ጎድሎባቸው አስር አመት እተጠጋው አስቸጋሪ ውጣ ውረድ ስታልፍ ልጇን አሚናን ይዛ በመንከራተት ሲሆን በቤት ኪራይና በትራንስፖርት ህይቷ የተመሰቃቀለ ሆኗል። ላለፉት ዘጠኝ አመታት የመሀመድን ጉዳይ በመከታሉ በኩል አንዳች ድጋፍ ያላደረጉላት በሪያድ የኢትጵያ ኢንባሲ ኃላፊዎች የመሀመድን ቤተሰቦችን የፍትህ ጥያቄ ፍርድ ተሰጥቶት እንኳ በማስፈጸሙ ረገድም ሆነ ጉዳዩን ወደ ሳውዲ ባለስልጣናት በማድረስ እርባና ያለው ስራ ሰርተው አላየንም ። እርግጥ ነው የጅዳ ቆንሰል መ/ቤት ከዘጠኝ አመታት በኋላ ከሰድስት ወራት በፊት በመሀመድ ጉዳይ ጤና ጥበቃ ውሳኔ በሰጠበት ዋዜማ ጀመሮ ጉዳዩን መከታተል ቢጀምርም የሆስፒታሉን የጥፋተኝነት ውሰኔ ሰነድ በእጃቸው እያለ ጉዳዩ ከነበረበት ፈቀቅ የማድረግ አቅሙን አጥተውታል !
አጠቃላይ የመሀመድ ጉዳይ በዚህ መሰሉ ሂደት መገኘቱ ለሚቆረቁረን ዜጎች ቢያንስ በሁነኛ አዋቂ ባለመያዙ የጉዳዩ መጓተት ይታየናልና ያሳስበናል ። በዚህ መልኩ የጉዳዩ መጓተትም የልጇን መጨረሻ ለመከታተል የመካ ቤቷን አፍርሳ ጅዳ በቤት ኪራይና በትራንስፖርት ፈተና የገጠማትን እናት በአደባባይ እርዱኝ ብላ ባትናገረውም ክልትሟን ያየን እንረዳት ዘንድ ግድ ሆኗል ! ይህን ድጋፍ ለማድረግ ያቀተብኩትን ጥያቄ በቅን ልቦና ለተቀበላችሁ ወገኖቸ ያለኝን አክብሮት እየገለጽኩ ፣ እርዳታውን የመሰብሰብ ሀሳብ ሳቀርብ በእርዳታ ስም ሀብት ማከማቸት መላ መምታቴን በመጠቆም ለፍርድ እንደምቀርብ ላስጠነቀቃችሁ ስንኩሎች ልብ ይስጣችሁ በማለት የጀመርኩትን እርዳታ ማሰባሰብ እንደምገፋበት የማበስራችሁ በደስታ ነው !
እርዳታውን ለማሰባሰብ ያሉት አማራጮች…
===========================
1ኛ) በጅዳ የተለያዩ አካባቢዎች እርዳታ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች
> ሀየል ሰላማ > ሀየል በዋዲና ጀፋሊ
> ሀየል ሄራ > ሀየል ስካን
> ሀየል ድፋዕ አልመደኒ > ሀየል ረውዳ
> ሀየል ጃሚያ > ሀየል መኮሮና
> ሀየል ኢነኪሽ ሻረዕ ትግራይ
ከላይ ያልተጠቀሱ ቦታወችን ጨምሮ በተጠቀሱት የሀበሻ መገናኛነት በሚታወቁ የተለያዩ ድርጅቶች ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች ፣ ሻሂ ቤቶችን ጨምሮ የእቃ መላኪያ ካርጎዎች ባላቸው ወገኖች በኩል እርዳታውን የማሰባሰብ እቅድ በዋናነት ይዣለሁ ። ለዚህ አማራጭ እቅድ መሳካታ ባለድርጅቶች ስልኮቻቸውን ያቀብሉን ዘንድ ትብብርን በዋናነት እጠይቃለሁ!
2 ኛ) ሌላው ከጅዳ ውጭ ባሉ ከተሞች አለያም በተላያዩ የአለም ክፍሎች የምትገኙና እርዳታ ማድረግ ፈቃደኛ የሆናችው ወገኖች እርዳታውን በዌስተር ዩኒየን በሚከተለው የእናት ሀሊማን አድራሻ መላክ ትችላላችሁ:
Name: HALIMA MUZEMIL – HASSEN
ID / Iqama no. 2187347097
Mobile: 00966 597938672
Jeddah, Saudi Arabia
3ኛ ) በተጠቀሰው አድራሻ መላክ የማትችሉ በተለይም ሳውዲ የምትገኙ የሳዋ አለያም የሞባይሌ ካርድ በመግዛት በመልዕክት ማስቀመጫ የሚስጥት ቁጥሩን በሞባይል ቁጥር 0597938672 በመላክ እርዳታ ማድረግ ይቻላል !
4ኛ) ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ መላክ የማትችሉና በተለይም በስራ ቦታ ላይ ሆናችሁ በአካል እርዳታውን ማቀበል የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አድራሻችሁን መላክና እርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ !
* ለእርዳታ ድጋፉ ” የተሻለ አማራጭ አለ !” የምትሉ ከሆነም አሳውቁኝ ፣ ዋናው አላማ ግፉአኑን መደገፍ ነውና ከምክክሩ የሚገኘው ሁሉ ይበጀናል!
ወዳጆቸ ሆይ …
============
እንደተለመደው ይህንን የእርዳታ ጥሪ ላልሰማ አሰሙ አሰራጩት ፣ share አድርጉት !
አጋሮቸ ሆይ …
==========
ኑ የተገፉትን እንርዳ … አበው ” ጋን በጠጠር ይደገፋል ” እንዳሉት ለመስጠት ፣ የተሰጣችሁ ኑ “ጋኑን በጠጠር እንደግፍ !” …ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስራ እንስራ ! ቢያንስ ” ነግ በኔ ነው ” ብለን እንተባበር ፣ እንደጋገፍ !
ብላቴናው መሀመድንና ቤተሰቡን ለመደገፍ አቅማችን ያልፈቀደ በጸሎት እንርዳቸው !
በጎነት ደግሞ ለራስ ነው ፣ ለነፍስ እርካታ !
ነቢዩ ሲራክ