ፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌ በአንዱ ድህረ- ገፅ “ዕርቅና ሰላም የሕህወት ቅመም” ብለው ጥፈው ነበር፡፡ ነገሩ እውነትነት ነበረው ሲተገበር ግና በጣም ከባድ መሆኑን እንዴት እረሱት፡፡ መልሱ ከእሳችውና ከአቻቸው ዘንድ ያለ በመሆኑ ነው፡፡
የዛሬ 50 ዓመት ፕሮፈሶር ጌታቸው ሀይሌ የአማርኛ አስተማሬ ነበሩ እንደዚሁም ፕሮፈሰር ክላውድ ሳምነር የሎጂክ አስተማሪያችን ነበሩ፡፡ ፕሮፈሰር ሳምነር ካናዳዊ ዜግነትን ትተው ኤትዮጵያዊ በመሆን እጅግ ጠቃሚ ጥናት አካሂደው በቅርቡ አርፈዋል፡፡ካለማወቅ ወደ ማወቅ ተሸጋግረው የኢትዮጵያ ፈላስፋ ሆነዋል፡፡ ይሀንን ያደረጉት በዘርዓ ያዕቆብ፤ ፈላስፋው ኤትዬጵያዊ የጥናትና የምርምር ዘመቻ በማድረጋቸው ነበር፡፡ በአንጸሩ ደግሞ ፤ ዘረ-ኢትዮጵያውያን ምሁራን የንጉሱ ዘርዓ ያቆብ የሥልሣን ማዕርግ ብቻ በማቀንቀን ሕዝብን በማይጠቅም የንትርክ ስራ መሰማራታቸው ያውቁት ይሆን ካላወቁትም ያሳዝናል፡፡ ዕውቀትን መሻት ይሻላል ወይንስ መንበር/ወንበር? ?
ፕሮፈሶር ሐይሌ እንደሚያውቁት በዛን ዘመን አዲስ አበባ ኮለጅ በተከፈተ ማግስት ማለቴ ነው፤ ፖለቲካና ታሪክ ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩ የዕውቀት ዘርፎች አልነበሩም፡፡ ፖለቲካ፤ታሪክና ስነ ጽሑፍ በጋርዮሽ ተጣምረው ትምህርታዊ ባልነበረው አካሄድ እንደተጋዙ ፕሮፈሰር ሐይሌ ያውቁታልና ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደ ወታደራዊና ፋሽስታዊ አገዛዝ (ደርግ)ለጥቆም ወደ ዝርያዊና ወገናዊ (ወያናዊ) አገዛዝ የተሸጋገረችው ከዚሁ ኮለጅ በተገኘው የተበረዘና ያልተበረዘ ጽንሰ-ሀሳብና ንድፈ-ሀሳብ ከዚሁ ከአዲስ አበባ በምሁራንና በጽንሓተ ምሁራን መካከል ግጭትና ክርክር የተመረኮዘ ነበር፡፡ የፖለቲካና የታሪክ ጥናትና ምርምር ሥፍራና ነጻነት ስለአልነበራቸው አማራጭ ሆኖ ለተማሪዎች የቀረበው የአማርኛና የጆግራፊ ክፍለ ትምህረት ነበር፡፡
በእኔ እምነት ጆግራፊና የቓንቃ ትምህርቶች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ በመሆናቸው መንግሥት ተጽእኖ በማድረግ መምሪያዎቹ እንዳያድጉ ተደርገዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡የአገራችንን መልከአ ምድር ሳናውቅ፣ የፖለቲካ ዕውቀታችንና ታሪካችን ሳናውቅ ሁላችን ተደናብረን አደናብረናል፡፡ ለዚሁ በምስክርነት ሊቀርቡ የሚችሉ ምሁራኖችና መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌ
• ፐሮፈሰር መስፍን ወልደ ማርያም
• ፕሮፈሰር በረከት ሀብተ ሥላሴ እና
• ታጋይ ስብሐት ነጋ
የነዚህ ታላቆቻችን ግለ-ታሪክ፤ ፖለቲካዊ ስራዎቻቸው እና ዕውቀታቸው አሁንም በሕይወት ስለአሉ ማወቅና መረዳት አለብን፡፡በእኔ ግምት እነዚህ አዛውንቶች በቂ ትምህርትና ልምድ (Education and Experience) እያላቸው ለማን ለምንና እንዴት እንደሚያካፍሉት የቸገራቸው ይመስለኛል፡፡ በውስጣቸውም ሰላም ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የውጭውን እናውቀዋለን ግና የውስጣቸውን አናውቀምና ቢነግሩን ለሁላችንም ትምህርት ይሆነን ነበር፡፡ እነሱም ሰላም አግኝተው ለእኛም ዕርቁን ቢያወርሱን መንግሥተ ሰማያት በገቡልን፡፡ ይክን ሳያደርጉ ቢሞቱ ግን የኤትዬጵያ (ኤርትራንም ጨምሮ) ሕዝብ አይዞርበትም ትላላችሁ??
የአማርኛ ቃንቃ መገናኛ መሆኑ ቀርቶ ፍልስፈና/ዕውቀት ሲሆን (በጌታቸው)፤ የኤትዮጵያ መልከዐ ምድር (physical geography) ፖለቲካል ጆግራፊ ሲሆን (በመስፍን)፤ ኤርትራዊ ሥነ-መንግሥት እና ኢትዮጵያዊ አቃቤ ሕግነት ሲቀናጁ (በበረከት)፤ አብዮታችንና ዝርያእችን በጋራ ሲወሀሀዱ(በስብሐት)፤ አይዞርብን ትላላችሁ? የናንተን እንጃ፤ በበኩሌ ግና ዞረብኛል፡፡
ወጣቱ ትውልድ ቦታ ልቀቁ ብሎ ሲጠይቅ ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦችና አስተምሮአቸውም ጭምር ይመስለኛል፡፡እነሱም ቢረዱዋቸው መልካም በሆነ ነበር፡፡ ወጣቱም እንደእነሱ አስቦ ማለት በስፍራ (ሰፔስ) ሳይሆን በአስተሳሰብ (በጊዜ ልዩነት) ማለቴ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፐሮፈሰር ጌታቸውንና ፕሮፈሰር በረከት በአንድ ዐይን መታየት አለባቸው፤ ፕሮፈሰር መስፍንና አቶ ስብሃት አብረው መጣመር አለባቸው፡፡ ይከም ሲባል ሰዎቹ እንዲዋደዱና እንዲፋቀሩ አይደለም፡፡ ሰላም ቢፈጥሩ መልካም ነበር ከፈጠሩ ዕርቅና ሰላም የሕወት ቅመም እንዳሉት ፕሮፈሰር ጌታቸው ይሆናል እሰየው ነው፡፡ እኔ ግና መጀመሪያ ዕርቅ ይቀድማል ሲባል ስለ አማርኛ እንደ ቃንቃ በጌታቸውና በበረከት አመለካካት መጣጣም አለባቸው፤ እንደዚሁም መስፍንና ስብሀት በፊዚካል ጆገራፊ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካል ጆግራፊያ መታረቅ አለባቸው አለበለዚያ ሁሉም መርዛቸውን መርጨት ይቅርባቸው ነው የምለው፡፡ ዕርቅና ሰላም በጣምራ ለማካሄድ የነዚህ አራት ግለሰቦች ሰላም መፍጠር ወሳኝነት አለው፡፡ ይህ ካልሆነ ግና ዕርቅና ሰላም ለየግላቸው በየተራ እንደ አመጣጣቸው እንዲታረቁ ይሆናል፡፡ አድራጊውም እገዚ-አ-ብሔር ይወቀው፡፡
ለአያሌ ዓመታት “ሳይንሳዊ” ባልሆነ መንገድ ጥናት ሳካሂድ ነጻነትና ሐርነት፤ንቃትና ድርጅት፤ትግልና ምርት ዕርቅና ሰላም፤ አንድነትና ዴሞክራሲያ ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቅደም ተከተላቸውም መላ ቅጡ የጠፋ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ምክንያቱም አብዮትና ጦርነት በጥምር በሕብረሰባችን ይጋዙ ስለነበሩ ነው፡፡
ለማነኛውም በአሁኑ ሰዓት ጦርነቱ ቆሞ አብዮቱ ግና እየተካሄደ ስለሆነ ዕርቅና ሰላም አብረው መሄድ ያለባቸው ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡ ለምን አብረው ይጋዛሉ ተብሎ ሲጠየቅ እስከ አሁን በጣምራ ያካሄድናቸው ብቻ ሳንሆን አንዱ ከአንዱ መለየት ስለማንችል ነው፡፡
ለማስረዳት ያህል
በሕብረ-ሰባችን አባባል ጠጅን በብርሌ ነገርን በምሳሌ እየተባለ ለዘመናት ተጠቅመንበታል፤ አሁን ግና ብርሌም የለ ምሳሌም የለ፡፡ጠጅና ነገር ግና በሽ-በሽ ነው ይባላል፡፡ ብርሌዎች ወጣቱ ትውልድ ሲሆኑ ምሳሌዎቹ ደግሞ ጌመበስ (ጌታቸው-መስፍን-በረከትና ስብሃት) ከላይ እንደጠቀስኩት በትምህርትና በልምድ የተካኑ ናቸው፡፡ አራቱ በግላቸው ሰላም ቢያወርዱ ሺዎቹ ዕርቅ በፈጠሩ፡፡
ወጣቱ ትውልድ ያለፈውን የትግል ጉዞአችን ካላገናዘበ፤ ሽማግሌው ትውልድ በበኩሉ የልጆቹን ፍላጎት ካላወቀ፤ የተፈለገው ዕርቅና ሰላም ቀርቶ የግሪክና የኢራን ዕጣ ፈንታ በእኛ ላይም የማይደርስበት ምክንያት አይታየኝምና ነው፡፡
ለጥያቄና ሐተታ
oboaradashawl@gmail.com