በመበስበስ አደጋ ውስጥ የተዘፈቀው እና ማጣፊያው ያጠረው የወያኔው አምባገነን ቡድን ለስልጣኑ እድሜ መርዘም ከምእራባውያን ጉያ መወሸቁን እና አስፈላጊውን የእድሜ ማስረሚያ ለማግኘት ፈቃዳቸውን ለመፈጸም እየተደራደረ መሆኑ ታውቋል:: በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ በቀረቡ የውይይት ሃሳቦች ላይ ሁለቱን በሂደት ላይ ቢያስኬደውም ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ግን መተማመኛ እንፈልጋለን ሲሉ አጥብቀው ወጥረው ይዘውታል የሚሉ መረጃዎች ተገኝተዋል::
ከድርድሮቹ ሁለቱን ማለትም ተቃዋሚዎችን በመጭው በሚመሰረተው መንግስት ውስጥ በስፋት ማሳተፍ እና በሙሉ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት የሚለውን በተወሰነ ደረጃ ለመፈጸም የተስማማ እና የጀመረ ሲሆን በፕሮፓጋንዳ ደረጃ በመጪው የመንግስት ምስረታ ላይ ተቃዋሚዎች በሃገሪቱ ጉዳይ ላይ የራሳቸውን ድምጽ ይዘው የማይሳተፉ ከሆነ አደጋ እንዳለውና የምርቻውም ውጤት ተቀባይነት ባለማግኘቱ በምስራቅ አፍሪካ ላለችው ጠንካራ አጋራችን ኢትዮጵያ አስጊ ነው ብለው ምእራባውያኑ በመናገራቸው ወያኔ በሚዲያዎቹ እንደተናገረው ተቃዋሚዎችን በሃገሪቱ ውሳኔ ሰጪነት ሂደት ውስጥ እንዲያሳትፍ ጫናውን አበርትተውታል::ወያኔም ይህንን ተከትሎ ባለፈው ሰሞን የተቃዋሚዎችን ተሳትፎ ሲያራግብ ነበር:: በተጨማሪም የሕዝብ ጥያቄዎች በመስማት ረገድ ውጤት አልባ ነው ብለው የተቹት ሲሆን ሕዝብን ማስፈቀድ የሚል አዲስ ዘይቤ ከዚሁ ድርድር የተገኘ ወያኔ እያራገበው ይገኛል::
የኦባማ ወደ አፍሪካ ሕብረት መምጣት የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ሰፊ ጫና የሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ግፊት ወያኔ ከምእራባውያን ጋር እንዲደራደር ተጽእኖ ማሳደራቸው ተጠቁሟል::የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች/ጋዜጠኞች በሙሉ እንዲፈቱ የጠየቀው የምእራባውያን ስብስብ የተወሰነ ምላሽ ቢያገኝም አሁንም በተስማማባቸው የድርድር ጉዳዮች ላይ በቂ ምላሽ ያልሰጠበት እና አርኪ ተግባራትን አለመፈጸሙ በዲፕሎማቶቹ እያስተቸው ይገኛል:: የደህንነት አካላት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሚፈታቸው ጎን ለጎን ሌሎችንም ማስር መጀመሩ የታወቀ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ከታሳሪዎች እና ታዳኞች ግንባር ቀደሙን ይይዛሉ ተብሏል::ድርድሩ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ተሳታፊ ሆነዋል::ወያኔ በቀጣይነት ከምእራባውያኑ ሊያገኝ የሚፈሊገውን እርዳታ በዝርዝር ለማቅረብ ሃሳብ የሰጠ ሲሆን እነሱም ብሄራዊ ጥቅማቸውን በተመለከተ የሚያቀርቡትን ሃሳብ እንደ ከለላ እንዳይጠከም ስጋት መኖሩን ምንጮቹ ጠቁመዋል::የኦባማን ጉብኝት በተመለከተ ምናልባት የምእራባውያን አቋም ካልተሟላ ሊሰረዝ ይችላል የሚል አስተያየት ቢኖርም እስካሁን ከዲፕሎማቶቻቸው የተሰማ ፍንጭ የለም::የወያኔው አምባገነን መንግስት በሕዝብ ላይ የሚያደርገው ግፍ በከፍተኛ ደረጃ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ መወያያ አጀንዳ ከሆነ ቆይቷል::የበለጠ መረጃ ለማግኘት ጥረቱ ይቀጥላል:: #ምንሊክሳልሳዊ
↧
ራሱን ማቆም ያልቻለው የወያኔው ስርአት ለስልጣኑ እድሜ ለመግዛት በምእራባውያን ጉያ ተወሽቋል:: –ምንሊክ ሳልሳዊ
↧