Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አደባባዮቹ ወጣቶቻቸውን ናፍቀዋል ወራዙት ይአቅቡከ ( ያፈቅሩከ) –ዳነኤል ፈይሳ

$
0
0

ጊዜው 1997 ነው። አብዛኛዎቻችን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፥ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም ተመርቀን ስራ አጥተን ሰፈር ውስጥ የምንውል ስራ አጦችና ( በኢህአዲግ አባባል አደገኛ ቦዘኔዎች) ወጣትነት ጉልበታችንን በስራ ለመፈተን እየተንቀሳቀስን የነበርን ወጣቶች ትኩስ ኋይሎች ነበርን።

በወቅቱ በተነሳው የለውጥ እንቅስቃሴ አንዳችንን ከአንዳችን ሳይለይ በጊዜው የነበርነውን ሁሉ ማርኮን አጥብቀን በመከታተል በሂደቱ በተለያየ መልኩ ተሳታፊ ሆነን አገኘነው። በከፍተኛ ሁኔታ በለውጡ ማዕበል ውስጥ ሁላችንም እየተናጥን ነበር።

ለውጥ!የዚህ ትውልድ አባላት የሆንን በወቅቱ ምንም አይነት ይሁን እንጂ ለውጥ እንፈልግ ነበር። ለውጡም በምንም መልኩ ይምጣ አጠቃላይ መንግስታዊ ለውጥ ተካሂዶ ከማየት ባሻገር በአገር
ግንባታ ውስጥ መሰረታዊ የነበሩትን ጥያቄዎች የሚመልስ ለመሆኑ እርግጠኞች ለመሆን በብዙም አልተጨነቅንም። የተካሄደው የፖለቲካው እንቅስቃሴ ለውጡ ለውጡ እንዲዳፈን የተደረገበት መንገድ ትውልዱን በደንብ አገሩን እንዲያስባት አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ ነገር ጋዜጣ በመስፍን ነጋሽ በኩል ወደ አደባባይ የወጣው የትውልዱ የመጀመሪያ ጥያቄ የነበረው ይህቺ አገር የማን ናት የሚለው ነበር። ይሄንንም ጥያቄውን ሲያውጠነጥን አገሩ የጥቂቶች ሆና ነው ያገኛት ስለዚህም ትውልዱ የኔ የሚላት አገር እንድትኖረው ሻተ።

ምን አይነት ሀገር? የ1997 ምርጫ ትውልዱን ብዙ አስተምሮታል። በህዝብ ዘንድ የነበረው የስርዓት ለውጥ ፍላጎት እንዲዳፈን የሆነው እንደሀገር ምን ስላልነበረን ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በእጅጉ እንዲያብሰለስለው ሆኖዋል። ተብሰልስሎ ብቻ አልቀረም አልቀረም ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ራሱ በመብሰልሰሉ ውስጥ መልሱን አግኝቶት ነበር። ይኸውም የነፃ ተቋማት ያለመኖር ችግር
የለውጡን ፍላጎት እንዳዳፈነው ተረድቶታል።

ስለሆነም ነፃ የፍትህ ተቋማት፥ ነፃ ሚድያ፥ ነፃ የሲቪክ ተቋማት፥ ነፃ የመከላከያ ኋይል፥ ነፃ የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት ኋይል የተገነባች ሁሉም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ የሚፈቱባት
ሀገርን ሽቶዋል። ለመሻቱ ተግባራዊነት ደግሞ በዚህ ወታደራዊ ነፍጥ አንጋቢ አንባገነን ሁሉን ጨፍልቆ መውሰድ በሚፈልግ ስርዓት ውስጥ ሊተገበር እንደማይችል አረጋግጦዋል። የትውልዱ
ጥያቄ ሊመለስ የሚችለው አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ተረድቶዋል። ለውጡ እንዴት ይምጣ? ትውልዱ ባለፉት 10 አመታት በተለያዩ ወቅቶች እርስ በእርስ
በነበረው ግኑኝነት ለውጥ፥ ለውጥ ብሎ ደጋግሞ አንስቶዋል። ይህ ትውልድ አሁን ወጣትነቱ ወደ ማብቂያው እየሄደ ቤተሰብም አፍርቶ ወደ ጉልምስናው መጀመሪያ እየገባ ነው።

በወጣትነቱ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ የወጣትነት ዘመኑ መጨለም ሊጀምር እየዳመነ ነው። ትውልዱ የጥያቄዎቹ እንዲሁም የታሪኩ ባለዕዳ ነው። ያነሳቸውን ጥያቄዎችና የታሪክ ኋላፊነቱን የሚወጣበት ጊዜው አሁን ነው። ወጣትነቱ ከመጨለሙ በፊት ባለታሪክ የሚሆንበት ለነገው ትውልድ ለሱ ልጆች የታሪኩን የተፃፈ ገፅ የሚያነብበት የዕርጅናው ወራት ሲመጣ ለልጆቹ የሚተርከው የተፃፈ ገፅ እንዲኖረው አሁን ወደ አደባባዮቹ የመትመሚያው የመጨረሻው ጊዜ ላይ ነው።

ይህ እንዴት ይሆናል? ለውጡን በምን መልኩ ማካሄድ ይቻላል? ብሎ የደረሰበት መደምደሚያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን በሀገሩ ላይ በመተግበር ወደ አደባባዮቹ መትመም ያንተ የጦርነት አውድማ
አሲንባ ወይም ደደቢት አይደለም በሀገርህ ላይ ያሉት አደባባዮችህ ናቸው። ሀገር እንዳይኖርህ ሀገር አልባ ያደረገህን ስርዕት ከስሩ መንግሎ ማፍረስ ነው። ይህ ሲሆን ያኔ ባለታሪክ ይሆናል ጥያቄዎቹም ይመለሳሉ። ያኔ ታድያ የታሪኩ ባዶ ገፅ እየተገለጠ በሚነበብ፥ በሚተረክ የተፃፈ ገፅ ይሞላል።በጉልምስናህም ዘመን ኩራት፥ ክብር የሰው ልጆች ፍላጎት የሆነው ይኖርሃል፥ በማሻውም እድሜህ ለልጆችህ
የታሪክህን ገፅ እየገለጥክ ያኔ እነሱ በማንነታቸው ኮርተው የኔ ብለው የሚኖሩባትን ሀገር ዲሞክራሲያዊት፥ ፍትሃዊት፥ የነፃ ህዝቦች መኖሪያን፥ የሀገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ የቻልክ አባት መሆንህን ትተርክላቸዋለህ።

አርአያዎች ከየትም አትፈልግ የትውልድህ አባላት የሆኑት ያንተን የነፃነት ውልድ እያማጡ ያሉ አሉልህ። ተመልከት እነ አንዷለም አራጌን፥ ተመልከት እነ ሃብታሙን አያሌውን፥ ተመልከት እነርዕዮትን፥ ተመልከት ተመስገንን ያንተን ምጥ ሲያምጥ፥ ተመልከት እነ ማህሌትን፥ እነ ኤዶምን፥ እነበፍቄን፥እነ ናቲን፥ እነ ዘላለምን እን አቤልን. ……….ለአንተ ትውልድ ጥያቄዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። ምን ቤት አለህና ቤትህ ትገባለህ ያንተ ቤት አደባባዮችህ ናቸው። ለባርነት ማዶ አትመልከት ለነፃነትህ ወደ ራስህ ቤት ተመልከት።

እንደመደምደሚያ ይህ ትውልድ ብዙ ተብሎዋል በጫት የናወዘ፥ ከራሱ ባሻገር አገራዊ ራዕይ የሌለው ወኔ አልባ፥ አደገኛ ቦዘኔና ብዙ አልባሌነቱን የሚነግሩት ማንነት ተደርቦለታል። እሱ ግን እንደዚህ እንዳልሆነ የሚያስመሰክርበት አሁን ታሪክ 2007ን ሰጥቶታል። አብዮቱንት ተሸክመው የሚዞሩት እንኳን አልፈሩም ትውልዱስ ስለምን ይፈራል? እሱ ከትላንት አባቶቹ በምን ያንሳል? እንደ ቱኒዝያ፥
ግብፅ፥ ቡርኪና ፋሶ አቻዎቹ የለውጡ ባለቤት እንደሆነ ያረጋግጣል የሚል እምነት አለኝ አደባባዮቹም የሀገሩን ልጆች ወጣቶቹን ናፍቀዋል።

ወራዙት ይአቅቡከ (ያፈቅሩከ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>