Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ጠንካራነትን ብቻ ሳይሆን ደካማነትንም መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ -ምንሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

የራስን እና የተፎካካሪን ስልትና ስትራቴጂ አለማስላት፣ የህዝብንና የሀገርን ፍላጐት አለማስቀደም፣ የመንገዶችን ኮረኮንችና ሊሾነት አለመለየት አባዜዎች ሁሌ እንደተፈታተኑን አሉ፡፡ ባለፉት የትግል ጊዜያት ብዙ አይተናል:: ብዙ ታዝበናል:: ብዙ ጉዳዮች አስደምመውናል:: ጠንካራነትን ብቻ ሳይሆን ደካማነትንም መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ አለመብሰል አለመሰልጠን እንደተገኘው መገስገስ ትግሉን በትንሽ ድል መወጣጠርና በትንሽ ሽንፈት መፍረክረክ ተጋጣሚን መናቅና ወሬን/አሉባልታን እንደ አቋም ወሱድ በሚደረገው ትግል ውስጥ ከባድ አደጋ አለው::የራስን ርእዮት አለም አጥርቶ አለማወቅ እና የፖለቲካ እውቀት ማጣት በሚፈጥረው ድንጋጤ ራስን ፋይዳቢስ ማድረግ ይከተላል::

አለም ወደ ሃያሁለተኛው ክፍለዘመን በሰለጠነ ፖለቲካ እየገሰገሰ ባለበት ዘመን ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን በመጠላለፍ እና በመኮራኮም በሆድ አደርነት እና በስሜታዊነት መሞላት ነገሮች ሁሉ እልህ ተሞልተው ከአዱ አዘቅት ወደ አንዱ አዘቅት መረማመድ ሆኗል::አለመብሰላቸውን እንደ እውቀት ይዘው ግራ የተጋቡ የፖለቲካ እውቀት የሚያጥራቸው ሰዎች በፖለቲካ አለም ትግሉ ሲያደናብራቸው እና ሲያንገዳግዳቸው ሰበብ ስለሚፈእጥሩ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬን እንዲፈጠር መንገድ ይከፍታሉ::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ የምንግደድበት ወሳኝ ወቅ ላይ መሆናችን ብስለታችን እና ጥንካሬያችንን መለካት ይጠበቅብናል::

አለመብሰላችን አለመሰልጠናችን ውይይቱም፣ ድርድሩም፣ ፉክክሩም ሌላውን በማጥፋት ወይም በመጥለፍ ላይ የተመሰረተ ይሆንና ጤናማ ጉዞ አይሆንም፡፡ ጥንትም እንደዚያው ነበር፤ አሁንም ቅኝቱን አልቀየረም፡፡ በዚህ ቅኝት ላይ የመከፋፈል ዜማ ሲጨመርበት ለባላንጣ ሲሳይ የመሆን አባዜ ይከተላል፡፡ ማ ለምን ይህን አደረገ? ምን እየተጠቀመብኝ ነው? ብሎ ማሰብ ያባት ነው!ተፈጥሮውን ማሳየት የሚበጀውና የሚያዋጣው አንዳንዴ ብቻ ነው፡፡በወሳኝ ወቅት ላይ ወሳኝ ትግል እና የሰከነ ፖለቲካ ማራመድ አሌ የማይባል ሃቅ ነው::የማይበጅ ፖለቲካ ወገንን ያሳፍራል:: የአንድነት እና የጋራ ፖለቲካ በበሰለ መልኩ ይዞ በትግል ውስጥ መራመድ ወገነን ያኮራል::ያለዉን የአለም ስልጡን ፖለቲካ እናጢን:;ከኋላቀር ፖለቲካ ራሳችንን እናውጣ::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>