የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ገብረግዚአብሄር በፋና ራዲዮ እንዲሁም ሃላፊው ፕሮፌሰር መርጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ መኢአድ እና አንድነት ችግር እንዳለባቸው በመገልጽ በስድስት ቀናት ዉስጥ ፓርቲዎቹ “ችግሮቻቸውን” ካልፈቱ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰደባቸዋል ሲል አስጠንቅቀዋል። ምርጫ ቦርድ የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንደሆነ ይነገርለታል።
የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሕጉ መሰረት የሚንቀሳቀሱ ሳይሆን የፖለቲካ ዉሳኔ የሚያስፈጸሙ እንደሆኑ በሚያደርጓቸው ኢሕገ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች እያሳዩ እንደሆነ የሚገልጹት የመኢአድ እና የአንድነት አመራር አባላት የተደቀነባቸውን እንቅፋት ከህዝብ ጋር ሆነው እንደሻገሩትን በሙሉ መተማመን እየገለጹ ናቸው።
የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በአባላት ደረጃ እንደተዋሃዱ፣ አብረዉ እየተሳሩ፣ እየደሙ እንዳለ የገለጹት አመራር አባላቱ መኢአድ እና አንድነት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። መኢአድ በ354 ወረዳዎች አንድነት ደግሞ ከ450 ወረዳዎች በላይ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የገለጹት አመራሮቹ፣ አገዛዙ በምርጫ ቦርድ በኩል በድርጅቶቹ ላይ እየፈጸመ ያለው ነገር ፣ ድርጅቶቹ በሕዝብ ተቀባይነት እንዳላቸው በመረዳቱ ነው ሲሉ፣ ከህዝብ ጋር ሆነው የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቋቋም ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።
የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ያዳምጡ