Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ክፍፍል ቅምርን እንደገና እንደሚመለከተው አሳወቀ

$
0
0

ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ስብሰባ ለምርጫው የገንዘብ ክፍፍል ቀመር መሰረት ዉይይት አድርጓል። ምርጫ ቦርድ ባቀረበው የገንዘብ ክፍፍል ቀመር መሰረት 10 በመቶ ለሴቶች፣ 10 በመቶ ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል፣ 25 በመቶ ፓርቲዎች በሚያቀርቡት እጩ፣ 55 በፓርላማና በክልል ምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ እንደሚያከፋፍል በማሳወቅ ነበር ስብሰባው የተጀመረው።

ምጫ ቦርድ ባቀረበው ቀምር ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጠየቁበት ጊዜ፣ አንድነትን ወክለው የተገኙት አቶ ዳንኤል ተፈራ፣ ለሴቶ 10% ከተመደበው ዉጭ፣ ሌሎችን አንድነት እንደሚቃወም ገለጸዋል። በተለይም 99% የፓርላማና የክልል ምክር ቤትን ኢሕአዴግ ብቻ እንደሚቆጣጠረው የገለጹት አቶ ዳንኤል፣ የምርጫ ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ ገዢውን ፓርቲ ብቻ እንደሚጠቀም በመናገር ነበር፣ ተቃዉሟቸውን ያሰሙት።

አቶ ዳንኤልን ተከትለው የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታንህ ባልቻም አቶ ዳንኤልን በመደገፍ ተቃዉሟቸውን አሰምተዋል። አቶ ጌታነህ ተቃዉሞ ካሰሙ በኋላ ስብሰባው ለቀው የሄዱ ሲሆን፣ በተቀሩት የፖለቲክ ፓርቲዎች እና በምርጫ ቦርድ በኩል በተደረገው ክርክርና ዉይይት፣ ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች የቀረቡትን ሐሳቦች ከግምት በማስገባት እንደገና የገንዘብ አሰጣጥ ቀመሩን እንደሚመለከተው አሳወቋል።

በስብሰባው 24 ድርጅቶች የነበሩ ሲሆን፣ ከኢሕአዴግ ተወካይ በስተቀር 23 ድርጅቶች የአንድነትን የመከራከሪያ ሐሳብ በመደገፍ በጋራ እንደቆሙም ለማወቅ ችለናል።

መኢአድን ወክለው የተገኙኙት በአቶ ማሙሸት አማረ አመራር ዉስጥ የሚገኙት ዶር ታዴዎስ መሆናቸዉን አረጋግጠናል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>