Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አንድነትን የሚያጠናክር ሁሉን ያሰባሰበ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ

$
0
0

የቀድሞ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው በፍቃዳቸው ሃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው ፣ በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ፣ አቶ በላይ ፍቃዱን አዲሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሆኑ መምረጡ ይታወቃል። አቶ በላይ፣ ዛሬ እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 20006 ዓ.ም ፣ አብረዋቸው የሚሰሩ 12 የሥራ አስፈጻሚ አባላትን መርጠው በብሄራውዊ ምክር ቤቱ አጸድቀውዋል።
1911833_802449999813751_6102165707510073888_n
ከተመረጡት 12 የሥራ አስፈጻሚ አባላት ፣ 6 ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ሊቀመንበር የነበሩ ጊዜ፣ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የነበሩ ሲሆኑ፣ እነርሱም አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን (የድርጅጅት ጉዳይ ሃላፊ)፣ አቶ ስዩም መንገሻ (ዋና ጸሃፊ) ፣ አቶ አለነ ማፀንቱ (የማህበር ጉዳይ ሃላፊ) ፣ አቶ ደምሴ መንግስቱ (የሕግ ክፍል ሃላፊ) ፣ አቶ ብሩ በርመጃ (የፖለቲክ ጉዳይ ሃላፊ)፣ አቶ እንግዳ ወልደጻድቅ (የወጣትኦች ጉዳይ ሃላፊ) ናችው።

ከኢንጂነር ግዛቸው ጋር አብረ በሥራ ሳፈጻሚው ዉስጥ መስራት እንደማይችሉ ገልጸው፣ ከሥራ አስፈጻሚዉ ለቀው ከነበሩ ስድስት ወጣት አመራር መካከል፣ ሁለቱ ፣ አቶ ተክሌ በቀለ እና አቶ ዳንኤል ተፈራ በአዲሱ አመራር የተካተቱ ሲሆን፣ በፓርላማ የተቃዋሚው ቡድን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቸኛ ተወካይ ናቸው የሚባሉት አቶ ግርማ ሰይፉም፣ አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አብባል ሆነዋል።

የአዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መዋቀሩን ተከትሎ፣ አንድነት ወደ ስራና እንቅስቃሴ በስፋት ይገባልል ተብሎ ይጠበቃል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>