Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት በፕሬዚዳንቱ የቀረበለትን ካቢኔ አፀደቀ

$
0
0

ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ በመሰብሰብ በሁለት አጀንዳንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የብ/ም/ቤቱ ሴክሬታሪያት ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡

የብሔራዊ ም/ቤቱ መወያያ አጀንዳ የነበረው

1- የአዲሱን ፕሬዚዳንት ካቢኔ ማፅደቅ
2- የአማካሪ ሸንጎ መመሪያን ማፅደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ሲሆን

በመጀመሪያው አጀንዳ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ ለብሔራዊ ም/ቤቱ የካቢኔ አባላቱን ዝርዝር ለብሔራዊ ም/ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ መሰረት፡-
1ኛ. አቶ ተክሌ በቀለ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት
2ኛ. አቶ ግርማ ሰይፉ ም/ፕሬዚዳንት
3ኛ. አቶ ሥዩም መንገሻ ዋና ፀሐፊ
4ኛ. አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን የድርጅት ጉዳይ
5ኛ. አቶ አስራት አብርሃ ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት (አቶ ኃብታሙ አያሌው በእስር ላይ የሚገኝ በመሆኑ)
6ኛ. አቶ ብሩ ቢርመጂ የፖለቲካ ጉዳይ
7ኛ. አቶ አለነ ማፀንቱ የማህበራዊ ጉዳይ
8ኛ. አቶ ደረጀ ኃይሉ የኢኮኖሚ ጉዳይ
9ኛ. አቶ ዳንኤል ተፈራ የውጭ ጉዳይ
10ኛ. አቶ ደምሴ መንግስቱ የህግና ሰብአዊ መብት
11ኛ. አቶ እንግዳ ወልደፃድቅ የወጣቶች ጉዳይ ሲሆኑ ምክር ቤቱም ካቢኔውን ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ ተመራጭ የካቢኔ አባላቱም በም/ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡
1911833_802449999813751_6102165707510073888_n
ሁለተኛው አጀንዳ የአማካሪ ሸንጎ መመሪያ በንባብ ቀርቦ በምክር ቤቱ የማዳበሪያ ሃሣብ የተሰጠበት ሲሆን በህግና ሰብአዊ መብት ቋሚ ኮሚቴ አማካኝነት ግብአቶቹ ተቀናብረው ለቀጣዩ ስብሰባ እንዲቀርብ በመወሰን ስብሰባው ተጠናቋል ሲሉ የፓርቲው ሴክሬታሪያት ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልፀዋል፡፡

10389191_802446049814146_138378584779596295_n

10636132_802450846480333_793227833865755152_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809