መስክረም 25 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ምክር ቤት ወጣቶች ለአዲስ አበባ አስተዳደር የ እውቅና ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወቃል። አስተዳደር ደብዳቤው በደረሰው በ48 ሰዓት መለልስ መስጠት ሲገባው እስከአሁን ድረስ ምላሽ ባለመስጠት ፣ ሕገ መንግስታዊ የሆነ የዜጎችን የመሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት መርገጡኝ ቀጥሎበታል።
የአዲስ አበባ አንድነት ምክር ቤት ወጣቶቹ «የሚመለከተው ቢሮ ፈቃዱን ሰጠም፣ አልሰጠም የመስከረም 25 ሰልፍ የማይቀር ነው። ለዚህም ቢሮው ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቀናል» ሲሉ ሰልፉን ለማድረግ ቆርጠው እንደነበረ ይታወቃል።
ሆኖም ለመስከረም 25 የታቀደው ሰልፍ፣ ሌሎች ድርጅቶችን ባካተተ መልኩ መደረግ አለበት የሚል እምነት በአንድነት ወጣቶች ዘንድ ጎልቶ ስለመጣ፣ ሌሎች ድርጅቶችንም ለማስተባበር ተጨማሪ ጊዜ ይኖር ዘንድ የሰልፉን ቀን መራዘሙን ለማወቅ ችለናል።
ከሰማያዊ እና መኢአድ ጋር ንግግሮች እንደተደረጉ ፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ዉስጥ ከመድረክ እና ከተብብር ጋር በጉዳዩ ላይ ዉይይቶች እንደሚደረጉ የደረሰን ዜና ያመለክታል።
በ2006 ዓ.ም ድርጅቶ በአብዛኛው በብዛት ሰልፎችን የሚያደርጉት በተናጥል እንደነበረ ይታወቃል። በአንድነት ወጣቶች የተጀመረውም በሌሎች ድርጅቶች አዎንታዊ ምላሽ ያገኛል ተብሎ ተስፋ የተጠላበት፣ በጋራ ሰልፎችን የማድረግ እንቅስቃሴ ፣ ወቅታዊና የሕዝብን ጥያቄ ያንጸባረቀ እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናግራሉ።