Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ፍኖተ ነፃነት –የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህራንና የተለያዩ ተቋም ሰልጣኞች አሰልጣኞቻቸውን አስቆጡ

$
0
0

በትግራይ ክልል በተለያዩ ከተማዎችና ወረዳዎች የተደረገው ስልጠና በተሳታፊዎች ተቃዎሞ የገጠመውና ሰልጣኞችን ያስተባበረና ለአሰልጣኞቹ ፈተና የሆነ እንደነበር ከስፍራው ዜናውን ያደረሱን የዜና ምንጫችን ገልጸዋል፡፡

ገበሬዎችን እያታለላችሁ እኛን ለማታለል መጣችሁ አንድ ፓፓያ ቀርጻችሁ ልማት አለ ባገሩ በማለት 50 ጊዜ በቴሌቪዥን እያሳያችሁ፣ ዲሞክራሲ በሌለበት መልካም አስተዳደር በሌለበት ምን ልትነግሩን ምን ልትሰብኩን ነው የመጣችሁት በማለት የመድረክ መሪዎችን በጥያቄ ያስጨነቀ እንደነበር እንዲሁም ተሳታፊዎቹ እረፍት በሚወጡበት ሰዓት የትግርኛ ተናጋሪ መምህራንን ለብቻ በመጥራት ለምን አታግዙንም፣ እዛ ውስጥ ሆናችሁ መልስ ለምን አትመልሱም፣ ለምን ዝም ትላላችሁ በማለት በቁጣ እንዲያስተባብሉላቸው ቢጠይቁም፣ እኛ ከሌላው መምህር የተለየ ምን የምናውቀው ነገር አለ፣ ከዚህ ቀደም እውነትም ይሁን ውሸት ስናግዛችሁ ነበር፡፡

በአሁኑ ሰዓት ዋሽቶ እንኳን የሚያሳምነን የለም፣ አሁን ምን ዓይተን ነው የምንደግፋችሁ በማለት መምህራኑ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል፡፡ በሌሎች አዳራሾችም የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አንቀጽ 39 ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አንድ ክልል የመገንጠል ጥያቄ ሊያነሳ የሚችለው ፍትሃዊ ያልሆነ አስተዳደር፣ አድልዎ ሲኖር ነው፡፡ ፍትሃዊ የሆነ አስተዳደር ካለ ግን የመገንጠል ጥያቄ አይነሳም፡፡ አሜሪካ እንኳን 50 ግዛቶች አሏት ነገር ግን የመገንጠል ስጋት አለ ብላ የመገንጠልን መብት ህገ መንግስቷ ውስጥ አላስገባችም፡፡ እኛ ለምንድን ነው 9 ክልል ይዘን የመገንጠል የሚል ህገ መንግስቱ ውስጥ ያስገባነው፡፡

በዓለም ላይ የመገንጠልን መብት በህገ መንግስቱ ውስጥ ያስገባ ሀገር የለም፡፡ እኛ ሕዝቡን በእኩል ማየት፣ እኩል ማስተዳደር አለብን ብለን ህግ ማውጣት አለብን እንጂ፣ ከፈለክ መገንጠል ትችላለህ ብሎ ማወጅ እንደ አገር ተገቢ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ዓባይ በኢትዮጵያ ሕዝብ እየተገደበ ነው ከተገደበ በኋላ የመገንጠል ጥያቄ ቢነሳ ምንድነው ዋስትናችን በሚል ጠያቄ የጠየቁት ከመገናኛ ብዙሃን የመጡ ሰልጣኞች ሲሆኑ በአጠቃላይ በተለያዩ የትግራይ ክልል ሰልጣኞች ከመድረክ አወያዮች ጋር ባለመግባባትና ከስልጠናው ማጠቃለያም የአቋም መግለጫ ሣይነበብ ከአዳራሽ በመውጣት መጠናቀቁን የዜና ምንጫችን ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>