Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ሚሊየን ድምጽ –ፖለቲካ ቁማር እና መፋጠጥ ከአ.አ ከተማ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍል ጋር

$
0
0

«ቃልኪዳናችን ለቀጣዩ ትግላችን» በሚል መሪ መፈክር የአንድነት የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ መስከረም 11 ቀን 2007 ዓ.ም ከ9 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12.00 ሰዓት የሚቆይ ልዩ ዝግጅት አጠናቆ ይገኛል፡፡ በዚህ ልዩ ስነስርዓት የህሊና እስረኞችን በማስመልከት የአደባባይ የሻማ ማብራት ዝግጅት እንደሚከናውን ቀደም ባሉት ቀናቶች በወጣቶቹ የተገለፀ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ይሄንን አስመልክቶ የከተማው ነዋሪዎች እና ደጋፊዎች በስፋት የሚታደሙበት እና የፖርቲያችን የመጀመሪያው የአደባባይ የሕዝባዊ ንቅናቄ ከደጋፊዎቹ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ለቀጣዩ ትግል ቃልኪዳን የሚገባበት የነፃነት ታጋዮች በአደባባይ የሚታወሱበት ልዩ ስነስርዓት እንዲሆን ለማስቻል በአንድነት ወጣቶች ብሩህ አስተሳሰብ የተመዘዘ አጀንዳ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ለአ.አ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ በ3/13/2006 ዓ.ም በቁጥር አንድነት/957/2006 በተፃፈ ደብዳቤ የ4 ኪሎ አደባባይን ለመጠቀም ለከተማው አስተዳደር ለቀረበው ጥያቄ አስተዳደሩ አላደርገውም በሚል በሰጠው መልስ በቁጥር አ.አ./ከፅ/10/30.4/357 ጳጉሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የ4ኪሎ አደባባይ ለመጠቀም ሊታሰብ አይቻልም፡፡ የሚል ምላሽ ሰጠ ሆኖም ግን የአንድነት ወጣቶች ስነስርዓት ባለው አክብሮት የሚሰጡት ምላሽ በአስተሳሰብ እጅግ የበሰሉ በመሆናቸው ቦታ በመምረጥ መብታችን መጋፋት ከለመደው የከተማው አስተዳደር ጋር ንትርክ ውስጥ ላለመግባት በማሰብ ወጣቶቹ ተነጋግረው በወሰኑት መሠረት የዝግጅቱን ቀን እና ቦታ ተለዋጭ በማድረግ በቁጥር አንድነት/962/2007 መስከረም 2 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀው ሲያበቁ በአዋጅ የተቀመጠውን ሕግ አክብረን ሕገ መንግስታዊ መብቶችን ለመጠቀም ሕጋዊ መሆን የሚያስፈልገንን ሁሉ አድርገን ጨርሰናል ያሉት ወጣቶቹ ከዚህ በኃላ ከጠየቅናቸዉ እና ካሣወቅናችሁ ተለዋጭ ቦታዎች ውስጥ አንዱን እንጠቀማለን በማለት ጥያቄአቸዉን ለአስተዳደሩ በማቅረብ አስረድተዋል፡፡

ሆኖም ግን ቁማርተኛው አስተደደር ቀደም ሲል ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግበት የነበረውን 08 ሜዳ ታቦት ማደሪያ ተብሎ የሚታወቀውን ቦታ ላይ ዝግጅቱን አከናውኑ በማለት ጥያቄ አቅርቧል ሆኖም ግን በቃል ብቻ ጥያቄ ያቀረበው አስተዳደሩ ለነገ ማክሰኞ 6/1/2007 በደብዳቤ አሳውቁኝ ብሏል ትንቅትንቅ ውስጥ ያሉት የአንድነት ወጣቶች እኛም እንመካከርበት ብለው የነገ ሰው ይበለን ተባብለን ተለያየን ነገ ደሞ ምን ይሉ ይሆን? አብረን እናየዋለን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>