Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ከአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድህ ምንድነው? አኝዋክ ጀስቲስ ኦሞት ኦባንግን ለፍርድ ያቀርባል!!

$
0
0

የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው ኦሞት ኦባንግ !!

ኦሞት በዴሰምበር 13/ 2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኝዋክ ንጹሃን ዜጎች ፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መረታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን ከአገራችን የቀበሌ ነዋሪ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በማስረጃ የሚታወቅ ነው። ኦሞት በጋምቤላ ለፈሰሰው የንጸሃን ደም ” ነጻ” ሊሆን የሚችልበት አንድም አግባብ የለም። ድርጅታችን አኙዋክ ጀስቲስ ኦሞትን ፍትህ አደባባይ እንደሚያቆመው ቅንጣት ያክል የማይጠራጠረውም ለዚህ ነው። ከተሰወረበት ፊሊፒንስ አድኖ ለመያዝ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ነው።

ጄኖሳይድ ዎች ፣ የሂውማን ራይትስ ዎችና ከአኝዋክ ጀስቲስ ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት የአይ ሲሲ / የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጠበቆች/ በጋራ ኦሞት ኦባንግን ህግ ፊት ላማቅረብ እየሰሩ ነው። ኦሞት ከተሰሰገበት ፍሊፒንስ ወጥቶ ህግ ፊት እንዲቀርብ የሚደረገው ግፊት ባየለበት በአሁኑ ሰዓት የኦሞት አደባባይ ወጥቶ ” ታጋግሎ አታጋይ” ለመሆን መወሰኑ ዜና የሆነበት ምክንያት አልገባንም።

“የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ፣ ፍርድህ ምንድን ነው?” ብለን ስንጠይቅ በህዝብ ዘንድ ያለውን የፍትህ ጥማት ዘንግተን አይደለም። እንደ ኦሞት አይነት በደምና በሙስና የተጨማለቀ ሰው ራሱን ነጻ ለማድረግ የሚናዘዘውን ኑዛዜ በጥንቃቄ እንድትመለከቱት ስለምንፈልግ ነው። ኦሞት ለኢሳት ከሰጠው መግለጫ ላይ ተቀንጭቦ ” በሰበር ዜና” በተላለፈው መልዕክት ” ኦሞት ወያኔን ለመታገል መወሰኑንና፣ በአኝዋክ ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ወንጀሉን የፈጸሙትን ክፍሎች ዝርዝር ሰጥተዋል” መባሉን ሰምተናል።

ኦሞት ኦባንግ ከክልል ፕሬዚዳንትነቱ ተነስቶ ወደ ፌደራል ጉዳዮች ሚኒሰትር ዳዔታነት ከተዛወረ በሁዋላ አገር ጥሎ እንደኮበለለ አስቀድሞ ሊያነጋግረን ሞክሮ ነበር። ወያኔንን ለመታገል መወሰኑን ገልጾልን ነበር። አስፈላጊውን መረጃ ለመስጠት ተማጽኖንን ነበር። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተመሰረተበትን ክስ እንድናጠራለት/ ነጻ እንድናደርገው ሊማጸነን ሞክሮ ነበር። እኛ ግን እሱን ህግ ፊት ከማቅረብ የዘለለ ሃሳብና ፍላጎት ስላልነበረን ” እጅህን ለፍትህ ስጥ” የሚል መልስ ነበር የመለስንለት። “የዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርበህ ተናዘዝ” ነበር ያልነው ።

ትናንት በወገኖቹ ደም አጥንት ላይ ቆሞ ሲደንስ፣ በኢህአዴግ መገናኛዎች ላይ የወገኖቹን ነብስ ሲረግም የነበረ ወንጀለኛ በየትኛውም መስፈርት ለወገኖቹ ነጻ መሆን ይታገላል ብለን አናምንም። መታገልም ከፈለገ ራሱን ቅድሚያ ህግ ፊት አቅርቦ ነጻ ሊያደርግ ይገባል የሚል አቋም አለን። ትግል የሚመራው ስብዕና ባላቸውና በህዝብ ዘንድ ከበሬታ ባላቸው ወገኖች በመሆኑ አቶ ኦሞት ዲያስፖራውም ለመቀላቀል ያቀረበውን ምልጃ አበክረን እንቃወማለን። ዳግም ጄኖሳይድ አንለዋለን። በዚሁ መነሻ ጥንቃቄ ሊወሰድ እንደሚገባም እናሳስባለን። በቅርቡ ይፋ በሚሆነው የህግ አካሄድ ሁሉም ነገር ስለሚገለጥ ከሁሉም ወገን ማስተዋል ሊኖር እንደሚገባ ደግመን ደጋግመን ለመግለጽ እንወዳለን። እውነታው እየታወቀ እንደ ኦሞት ኦባንግ ካለ ወንጀለኛ ጋር ተባብሮ መሰራት የወንጀሉ ሰላባ የሆኑትን ንጹሃን የመካድ ያህል ሆኖ ይሰማናል። እንደ ኦሞት አይነት ወንጀለኞችን ወደ ትግል ማግበስበስ ኪሳራ ከመሆን እንደማያልፍ እናስገነዝባለን። ሳይውል ሳያድር እናየዋለን።

ኦሞት ኦባንግ በአኝዋክ ጭፍጨፋ ላይ እጃቸው አለበት የተባሉትን ሰዎች ሰም ዝርዝር መስጠቱ ተጠቁሟል። ድሮ ህግ ላይ ቀርቦ በማስረጃነት ሚዛን ደፍቶ መለስ ዜናዊ እንዲከሰስ ያስፈረደው ሰነድ ከመዘጋጀቱ በፊት ይህንን መሰሉ ትብበር ቢኖር በመጠኑም ቢሆን ባደነቅን ነበር። ዛሬ ሁሉም መረጃዎች ህዝብና ህግ ዘንድ ቀርበው ፍት በሚጠበቅበት ወቅት ላይ ጩኸት ከቶውንም አይገባንምና ኦሞት ኦብንግ መጀመሪያ ራስህን ነጻ እንድታደርግ እንመክርሃለን። ራስህን ሳትገደድ ለህግ አስረክብ!! ከዚህ ውጪ አሁን ማስተባበያ ማቅረቡ ጊዜው አይደለም። ለሂውማን ራይትስ ዎች የሰጠሃቸውን የጽሁፍ መልስ አንተነትህን ሊሸሽግ አይችልምና ካለህበት ታድነህ ህግ ፊት ከመቅረብህ በፊት ጊዜውን ተጠቀምበት።

ከአኙዋክ ጀስቲስ ካውንስል ጋር

መስከረም 13 ቀን 2014

For information, please contact Ato Ochala Abula, Chairman of the Anuak Justice Council (AJC): E-mail:ochala@anuakjustice.org


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>