Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

በቦስተን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል በከፍተኛ ድምቀት ባለፈው ቅዳሜ ተከብሮ ዋለ!! የአቡጊዳ ዝግጅት ክፍልም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2007 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል!!

$
0
0

በቦስተን እና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የ2007 አዲስ ዓመት በይኸው በዓል ሴፕቴምበር 6 ቀን 2014 ዓ. ም ወተር ታውን በሴይንት ጀመስ አርመኒያን አፖስቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ በጣም እጅግ በርካታ ሕዝብ በተገኝበት በድምቀት ተከበሯል። በእለቱም የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑት የማሳቹሴትስ ስቴት ሴናተር የሆኑት የተከበሩ ሴናተር ዊል ብርውንበርገር በክብር እንግድነት መገኘታቸው ታውቋል::

በዓሉን በተመለከተ ወ/ሮ ገነት መሰለ የበዓል ኮሚቴው ተወካይ በመክፈቻው የመግቢያ ንግግር ሲያደርጉ

የአዲስ ዓመት በዓል በቦስተን ከተማ በዚህ መልኩ መዘጋጀት ከጀመረ አመታቶች እያለፉ አዲስ አመት እየተተካ ይኸው እዚህ ደርሰናል፤ እንኳን አደረሳችሁ!! በዚህ አጋጣሚ አሁንም በድጋሚ ይህንን የአዲስ ዓመት በአል በመጀመር እዚህ እንዲደርስ ያደረጋችሁ መስራች አባላት ከፍተኛ ክብር እና ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል!! ይኽ ዝግጅት ከጥቂት አመታት በፊት በጥቂት ግለሰቦች በጎ ፈቃደኝነት ለተወሰኑ አመታት ከተካሄደ በኋላ ዝግጅቱ ፍጹም ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ፤ ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች ከፖለቲካ፤ ከሃይማኖት፤ በዘር እና በብሄር ሳይለያዩ፤ በጋራ የሁላችን ግን የእኛ የኢትዮጵያውያኖች ብቻ የሆነውን አዲስ አመት ትናንት ከተጀመረበት ትንሽ ዝግጅት ተነስቶ ዛሬ የደርስበትን ማየት በራሱ ታላቅ ደስታ እና ኩራት ያጎናጽፋል። ይህ በዓል እዚህ የደረሰው በብዙ ኢትዮጵያውያን መልካም ፈቃደኝነት እና ከፍተኛ ጥረት ነው።

በማለት ገልጸዋል፤ በመቀጠልም በእለቱ በቦስተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በ$1500.00 በሬ በመግዛት ዝግጅቱ እንዲደምቅ አስተዋጻኦ ያደርጉ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከስምንት በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ዝግጅቱን ስፖንሰር በማድረግ ለበዓሉ መሳካት የበኩላቸውን እገዛ ማድረጋቸውን በመግለጽ በሕዝቡ እና በኮሚቴው ስም ማስጋናቸውን አቅረበዋል።

በመቀጠልም የ2006 ዓ. ም. የሂሳብ ሪፖርት በወቅቱ ለሕዝብ ሳናሳውቅ በመዘግየታችን በኮሚቴው ስም ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅሁ የ2006 አመት የሂሳብ ሪፖርት በአጭሩ ከዚህ ቀጥሎ አቀርባለሁ፤
በ2006 ዝግጅት ጠቅላላ ገቢ ፤ ከትኬት ሽያጭ፤ ከመጠጥ ሽያጭ $15687.93 (አስራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም)
ጠቅላላ ወጭ፤ የአዳራሽ ኪራይ፤ ለዘፋኝ፤ መጠጥ፤ ለዘፋኝ የትራንስፖርት እና ሌሎች $10823.93 (አስር ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም)
ከወጭ ጠቅላላ ትርፍ …………………………………..$4864፣00 (አራት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ አራት ዶላር)
በሬ በስጦታ የተሰጠ …………..$1260.00 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ዶላር) እንደሆነ አስታውቀው የዚህን ዓመት ሪፖርት በሚቀጥለው አንድ ወይም ሁለት ወራት ወስጥ ለሕዝብ ይፋ እንድሚያደርጉ አስታወቀዋል።

በመጨረሻም የተከበሩ ሴናተር ዊል ብራውንበርገርን እንኳን ደህና መጡ በማለት ወደ መድረኩ የጋበዙ ሲሆን ሴናተር ዊል ብራውንበርገርም “እንኳን አደርሳችሁ” “መልካም አዲሰ ዓመት” በማለት በአማርኛ ቋንቋ የአዲስ ዓመት መልካም መኞታቸውን ገልጸዋል።

በመቀጠልም በፕሮግራሙ መሰረት ሕጻናት እና እናቶች አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ ጥለት ያለው የሐገር ልብስ ለብሰው አበባየሆሽ እያሉ ወደ አዳራሹ ሲገቡ በቦታው የተገኘው ኢትዮጵያዊ ከመቀመጫው ተነስቶ በማጨብጨብ እጅግ ልብ በሚነካ አገራዊ ባህል ሲከበር ማየቱ ምንኛ የመንፈስ እርካታ እንደሚሰጥ መመስከር አይዳግትም፤ በዚሁ በዓል ላይ አጭር ትምህርታዊ ድራማ የቀረበ ሲሆን በአጠቃላይ ዝግጅቱ የተዋጣለት እንደነብር ለመገንዘብ ችለናል፤ የዝግጅት ክፍላችንም አንድ አንድ ኢትዮጵያውያኖችን አነጋግሮ ከሕበርተሰቡ እንደተርዳው በዚህ ዝግጅት እጅግ የተደስተ ከመሆኑም በላይ ይሀንን ዝግጅት ላስተባበሩ የኮሚቴው አባላት ከፍተኛ ምስጋና ከማቅረባቸውም በላይ አንዳንዶቹ ይህ ዝግጅት ለምን በአዲስ ዓመት ብቻ በአመት አንድ ግዜ ሆነ? ሕበርተሰቡን ለማገናኘት በሌላም የኢትዮጵያውያን በዓል ላይም ዝግጅት ቢደረግ የሚል አስተያይት ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፤ ወደፊት ሌሎች ከሕበርተሰቡ የተነሱ አስተያይቶችን በሰፊው ይዘን እንቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ የአቡጊዳ ዝግጅት ክፍል ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2007 ዓ. ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መጪው ዘመን የሰላም፤ የነጻነት፤ የፍትህ ዘመን እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።20140906_210230

20140906_211614

20140906_211656

image-cc59929b6a500c6704022c1e5688958bb93fb713aea059c4e0f63712da0bd829-V

20140906_211706

20140906_211709

20140906_211714

20140906_225807

20140906_225815

20140906_225819

10681558_851939664830204_1810356645_n


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>