Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አቡጊዳ –የአዲስ አበባ የአንድነት ወጣቶች የአደባባይ ስብሰባ እያዘጋጁ ነው

$
0
0

ለታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኖች፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ እንዲሁም ሌሎች የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች አጋርነቱን፣ ሕዝቡ በነቂስ ይገልጽ ዘንድ ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ወጣቶች በአዲስ አበባ በሚገኝ ትልቅ አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባና የእስረኞች መታሰቢያ ፕሮግራም እንዳዘጋጁ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

በአማራጭነት ሁለት ትላልቅ አደባባይ ፣ ሕጉ በሚጠይቀው መሰረት ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ያቀረቡት የአንድነት ወጣቶች፣ ዝግጅቱን መስከረም 11 ቀን ሊያደርጉ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለ ይናገራሉ።

የአንድነት ፓርቲ ፣ ጊዜው ዝናብ የሚዘንብበት ክረምት በመሆኑና፣ ከመኢአድ ጋር ለማድረግ ባቀደው ዉህደት ምክንያት፣ ከዉህደቱም ጋር በተገናኛ የዉህዱን ፓርቲ ለመምርት በፓርቲው ዉስጥ ዴሞክራሲያዊ የምረጡኝ ዘመቻ ስለነበረ፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ላለፉት ሁለት ወራት ሳያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።

የቅሰቀሳ ዘመቻ አዲሱ አመት እንደገባ እንደሚጀምሩ የገለጹት፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች አስተባባሪዎቹ አንዱ፣ ሌሎች ድርጅቶችም የዝግጅቱ አካል እንዲሆኑ የማነጋገር ሥራ እንደሚሰራም ገልጸዉልናል።

የአንድነት ወጣቶች ባዘጋጁት ዝግጅት ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው አንድ የፖለቲክ ተንታኝ፣ ገና 2007 እንደገባ እንዲህ አይነት እንቅስቅሴ መጀመሩ አስደሳች እንደሆነ ገልጸው፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችም ከአንድነቶች ጎን በመቆም አጋርነታቸውን መግለጽ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። “ወያኔ/ኢሕዴግ ሲያስራቸው፣ ሲደበድባቸው አንድ ላይ ነው። እነርሱም የአባላቶቻቸውን መታሰርና እንግልት መቃወም ያለባቸው በአንድ ላይ መሆን አለበት” ነበር ያሉት።

ከአንድነት ዜና ጋር በተገናኛ ፣ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠዉን መሰናክል በማለፍ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር የሚያደርገውን ዉህደት በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንደሚያጠናቅቅ የአመርራ አባላቱ ይናገራሉ። የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ጸጋዬ አላማረው ፣ የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው በምክር ቤቱ መመረጣቸው፣ ምክር ቤት ለዉህደቱ ትልቅ ክብደት እንደሰጠው የሚያመላክት መሆኑንም ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ሰዎች ይናገራሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>