Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

“በሽብር” ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የፓርቲ አመራሮች ዛሬ ፍ/ቤት ቀርበው ለመስከረም 22 ተቀጠሩ

$
0
0

ትላንት ከጠዋቱ 3፡00 በአራዳ ምድብ ችሎት ሐብታሙ አያሌው ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋ እንደሚቀርቡ በመነገሩ የአንድነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና የየፓርቲዎቹ አባላትና ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር፡፡ ፖሊስ በፍርድ ቤቱ የተሰጠውን የቀጠሮ ሰዓት አክብሮ እስረኞቹን ማቅረብ አለመቅረባቸው ላይ ብዙዎች ስጋት የነበራቸው ፡፡ የታሳሪዎቹ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉና አቶ ገበየሁ ይርዳው በግምት 4፡30 ተጠርተው ዳኛ ስለሌለ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት እንዲገኙ ተነግሯቸው ለተሰበሰበው ታዳሚ በመግለፅ ሁሉም ከፍርድ ቤት ግቢ ወጣ፡፡

ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ሲሆን የየፓርቲው አመራሮች፣አባላቶቻቸው እንዲሁም ጋዜጠኞች የተገኙ ሲሆን 9፡00 ሰዓት ሲሆን ታጣቂ ሃይል የፍርድ ቤቱን ቅጥረ ግቢ ከተቆጣጠረው በኋላ ታሳሪዎቹ በተናጥል እያቆዩ ወደ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ በሚገቡበት ሰዓት ሰማቸውን እየጠሩ በጭብጨባ አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን በማለት አድናቆታቸውን ሲገልጹ ታሳሪዎቹም እጃቸውን ከፍ በማድረግና ከአንገታቸው ዝቅ በማድረግ አጸፌታውን መልሰዋል፡፡ የታሳሪዎቹ ጉዳይ የታየው በችሎት ሳይሆን በጽ/ቤት እንደነበር ጠበቃ ተማም የገለጹ ሲሆን ፖሊስ በዛሬው ችሎት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምንም አይነት ማስረጃ አለማቅረቡን ተጨማሪ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን ጠበቃው ይህንን በመቃወም ፖሊስ ታሳሪዎቹን ከመያዙ በፊት ነበር ማስረጃ ማሰባሰብ የነበረበት የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባውም በማለት ተከራክረዋል፡፡
ፍ/ቤቱ ፖሊስ መረጃ ለማሰባሰብ እንዲረዳው የጠየቀው ቀን እንዲሰጠው አዟል፡፡ ጠበቃ ተማም ደንበኞቼ አሁንም እየተጉላሉ ነው በዘመድ አዝማድ እንዲሁም በጓደኛ እየተጠየቁ አይደለም በማለት ለፍ/ቤቱ ያመለከቱ ሲሆን ፖሊስ ይህን እንዲያስፈጽም አዞ ለመስከረም 22 ቀን 2006 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>