Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አቡጊዳ –አስመራ ያሉ ሶስት ድርጅቶች ለመዋሃድ ተስማሙ !

$
0
0

ዋና መቀመጫቸው አስመራ የሆኑ ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግን በኋይል ለማስወገድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ሶስት ድርጅቶች ለመዋሃድ እንደተስማሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገለጹ። የትጥቅ ትግል እናደርጋለን የሚሉ ድርጅቶች ይሄን አይነት ስምምነት ሲያደርጉ በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ይነገራል። እንደተባለውም ስምምነቱ በተግባር ዉሎ ድርጅቶቹ ከተዋሃዱ፣ በዚያ አካባቢ ለሚደረገዉ የትጥቅ ትግል ትልቅ እድምታ ሊኖረው እንደሚችል የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

የድርጅቶቹን መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡
================================================

የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን (አርበኞች ግንባር – ግንቦት 7 – የአማራ ዲሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ)

በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ሥርዓት ለመቀየርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረድ በተለያየ ጎራ ተከፍለው የሚታገሉ ድርጅቶች ቁጥር ከምንጊዜውም በላይ እየበረከተ መምጣቱ የጎጠኛውን ቡድን እድሜ በማራዘም ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ አሌ የማይባል ሀቅ ነው።

ወቅቱ የሚጠይቀውና አገራችንና ሕዝባችን ያሉበትን ደረጃ በአንክሮ የተረዳ አገርና ሕዝቡን አፍቃሪ የሆነ ድርጅትም ሆነ ቡድን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል።

በአሁኑ ወቅት ከላይ የጠቀስናቸው ሂደቶች ምላሽ አግኝተው አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።

ወደፊት ለመዋሃድ የተስማማነው ድርጅቶች

1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
2. የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
3. የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ

ስንሆን በሚኖረው የሽግግር ሂደት ወቅትም በሁሉም የትግል ዘርፍ በጋራ መሥራት የጀመርን መሆናችንን እየገለጽን የመላው ወገናችን ድጋፉ እንዳይለየን ስንል ጥሪዓችንን እናስተላልፋለን።

አንድነት ኃይል ነው !!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር —
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ —
የአማራ ዲሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>