Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ለኑሮ ውድነቱ ዋነኛ ምክንያት ህገ-ወጥ ብልፅግና እና ኢፍትሃዊነት ነው። “ለለውጥ እንነሳ !!!”– Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

$
0
0

ቀን በቀን እየናረ የመጣውን የወያኒ አምባገነንነት እና ዝርፊያ ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡
ለለውጥ በጋራ እጅ ለእጅ ተይይዘን በአምባገነኖች እና በብዝብዦች ላይ እንነሳ !!!!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በሃሰት እቅዶችና በምኞት የሚሰብከውን ወያኒ ልናስወግድ ግድ ይለናል። እንደሚታየው ዛሬ እንደፋሽን የተያዘው ህገ-ወጥ ብልፅግና ነው፡፡ ሀገራዊ ስሜት ያለጥርጥር እየቀጨጨ ነው፡፡ ደምብና ሥርዓትን መጣስ እንደፋሽን ተይዟል፡፡ ድህነትን መቀነስ እንደአፍ አመል ሆኖ ይነገራል እንጂ በበሰለ መልኩ ህዝብ ውስጥ አልሰረፀም፡፡ ግማሽ ጎፈሬ፣ ግማሽ ልጩ የሆነ ካፒታሊዝም ከፋይዳው ማነስ ግራ ማጋባቱ ይብሳል፡፡ የምሁሮቻችን የድህነትን አሽክላ ለማስወገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ከስራ አጥነት መዘዝ ጋር ተዳምሮ፣ ከአረንቋው እንዳንወጣ እያደረገን ነው፡፡ አዙሪቱ እጅግ ጥምዝምዝና ተደጋጋሚ ነው፡፡ “ከእለት እንጀራና ከትክክለኛ ምርጫ የትኛው ይሻላል?” ዓይነት አጣብቂኝ የድህነት የቤት ጣጣ ነው፡፡ ሀብት እኩል ባልተከፋፈለበት አገር ምርጫ 100% ተሳካ ሲባል አይገርምም ይላሉ ባለሙያዎች እንዲህ ግራ-ገብ ነገር ሲበዛባቸው፡፡ ከሁሉም ይሰውረን ማለት ትልቅ ፀሎት ነው፡፡

ወገን ሆይ ያለዓላማ ጉዞ ከንቱ ነው፡፡ ቀን በቀን እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡ ያለቅርስና ያለበቂ መሰረታዊ ጥቅም ነፃ-ገበያን መመኘት የጫጩት አትራፊነት ምኞት ነው፡፡ ያለብስለት ጥናትና ምርምር፣ ያለብቁ ባለሙያ ዕድገት ዘበት ነው፡፡ ኑሮአችን ታግለን ካላሻሻልን ፣ ደሀ ጎጆው ካልተመለሰ፣ ልማቱ ከደረቀ፣ እሳቱ ካልሞቀ ተስፋው ይሞትበታል፡፡ ኑሮው መለወጥ አለበት፡፡ መታገዝ አለበት፡፡ ገቢና ወጪው መመጣጠን መቻል አለበት፡፡ ውሎ አድሮ ገቢው ይጨምር ዘንድ መንገዱ ሊጠረግለት ይገባል፡፡ለዚህ ደሞ እኛ በትግሉ አለም የመሳተፍ ግዴታ አለብን ። ለለውጥ ራሳችንን ማንቀሳቀስ ግድ ይለናል። ነጻነትን ልናገኝ የምንችለው ከአምባገነኖች የጭቆና ምመድፍ ልንወጣ የምንችለው ራሳችን ስንታገል እንጂ ከደጅ የመጣ እንግዳ አሊያም ምእራባውያን ንእጻነታችንን ሊሰጡን አይችሉም።

ኑሮ ዛሬ ነው፡፡ ነገ ምኞት ነው፡፡ ህይወት በእጅ ባለበት ሰዓት የሚኖር እንጂ በምኞት የሚታቀድ አይደለም፡፡ ዛሬ መኖር መቻል አለበት፡፡ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በቀላሉ መገብየት አለባቸው፡፡ ቀን በቀን እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ኢ-አድሎአዊነትና ቀናነትን ይጠይቃል፡፡ የብዙሃን ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት አስፈላጊነት አጠያያቂ ያለመሆኑን ያህል፤ ሁሉም ፓርቲዎች እኩል መሆናቸውን፣ በታሪክ የብቻውን ካሳ የሚያገኝ አንድም ፓርቲ መኖር እንደማይገባ፣ እርስ በእርስ መወዳደራቸው የዕድገት ማሺን መሆኑ እጅግ ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡ ሁሉም ፓርቲዎች ያለጭቦ መሳተፋቸውና መወከላቸው፣ የሲቪል ቡድኖችም ሊሳተፉበት ማስፈለጉ ገሀድ ጉዳይ ነው፡፡ በማግለል እንጂ በማሳተፍ የምናወጣው ነገር እንደሌለ ልብ ማለት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎችን በጋራ ትግል እስካላስወገድን ድረስ ምንም አይነት የኢኮኖሚ ለውጥ/እድገት በራሳችን ላይ ማምጣት አንሽልም ስለዚህ ለተጀመረው የትግል ስኬት የእያንዳንዳችንን ጉልህ ሚና እን ተሳትፎ ይሻል።ለለውጥ በጋራ አምባገነኖች ላይ እንነሳ !!!!!!#ምንሊክሳልሳዊ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>