Quantcast
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live
↧

“ያልተሄደበት መንገድ” –ሊነበብ የሚገባው ድንቅ መጽሐፍ! ነፃነት ዘለቀ

ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ?
ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ቂላቂሉ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሠራውን አስቂኝ ድራማ ስመለከት እያዘንኩ የታዘብኩትን በዓለም ወደር የማይገኝለት ምርጥ የምርመራ ውጤት በሚመለከት ትንሽ ልበል፡፡

የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን በውነቱ አልመለከትም፤ አለመመልከቴ ስህተት መሆኑ ቢገባኝም ጤንነቴን አጥብቄ ስለምፈልገው ይሁነኝ ብዬና ቁም ነገር አገኝበታለሁ ብዬ ኢቲቪን አላየውም – ብዙዎች እኔን መሰሎች ስላሉ “የዐዋጁን በጆሮ” እንዳትሉኝ እንጂ፡፡ የሆኖ ሆኖ በቀደምለታ ከሰዎች ጋር የሆነ ቦታ ቁጭ ብዬ ቁርስ ቢጤ ስንቀምስ በፖሊስ ፕሮግራም የተከታተልኩት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ድንቅ የሆነ የወያኔ የወንጀል ምርመራ ቴክኒክና ውጤት ያጫረብኝን ልዩ ስሜት በዚህ አጋጣሚ ሳላነሳው መቅረት አልፈለግሁም፡፡ ከእውነት ሰው መሆኔን ጠላሁ፡፡

“መርማሪው” ወያኔ አይታይም፤ ይህን የለመድነው ነው፡፡ ወያኔዎች ራሳቸውን እንደወንጀለኛ አድርገው ስለሚቆጥሩና ከአልቃኢዳ ጋር የሚያመሳስሏቸውን ድርጊቶች የሚፈጽሙ መሆናቸውን ሕዝቡ የተረዳው መሆኑን ስለለተገነዘቡ ይመስለኛል የመንግሥትን ሥልጣንና ኃይልም የጨበጡ “ምሁራኑ መርማሪዎች” በግልጽ በሚዲያ መታየትን የሚወዱ አይመስሉም ፤ እነዚህ ጭራቅ ገራፊዎችና ሀዘን አምላኪዎች (ሳዲስቶች) በራሳቸውም በመንግሥታቸውም የሚተማመኑ እንዳልሆኑና በሆዳቸውና በዘረኝነት ቁርኝታቸው ብቻ ተለክፈው በስሜት ፈረስ የዕውር ድምብር ግልቢያ ዜጎችን የሚያሰቃዩ ናቸው – ቀናቸው ሲደርስ ምን እንደሚውጣቸው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ አሣር አለባቸው – የቁናው ሥፍር እየተንደረበበ ይጠብቃቸዋል – እዚህ ወይም እዚያ፡፡ ከሞራል ዕሤቶቻችንና ከምርመራ ህግ በወጣ ሁኔታ አቡበከር የሚባለውን የሙስሊም ተቃውሞ አመራር አባል እጆቹን በእጀሙቅ አስረው የሚያካሂዱትን “ምርመራ” በአደባባይ በቲቪ ለዓለም ሕዝብ ሲያሳዩም “መርማሪው ሊቅ” መታየትን አልወደደም – አስጠሊታ ሣቁ ግን ከአንጀቱ ጥርስ ሳይሆን ከማተብ የለሽ አንገቱ ይሰማ ነበር፡፡ ስለዚህ የአንዲ ልዩነት እጆቹ አለመታሰራቸው እንጂ ሂደቱ ልክ እንደአቡቦከር ነው፡፡ ይህ የምርመራ ሂደትና ውጤቱ የሀገራችን የለየለት ውርደትና የወያኔን ማንአለብኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች ከግዑዝ ድንጋይ የማይሻሉ የመጨረሻ ደደቦች መሆናቸውን ምናልባትም ለሚሊዮንኛ ጊዜ የገለጡበት ማፈሪያ ድርጊት ነው፡፡ የሚታዘነው በተመርማሪዎቹ ሳይሆን በመርማሪ ተብዬዎቹ ነው፡፡ ከመነሻው የዘረኝነት ልክፍት ያሽመደመደውና ከዘር ማዕቀፍ ውጭ የማያስብ ደንቆሮ ማይምና ሳዲስት እንዴት አንድን የተማረን ሰው ይመረምራል? እንዲያው ትንሽም ቢሆን የተማረ ዘረኛ ወያኔ ጠፍቶ ነው ወይ? ይህ ዓይነቱ የአደባባይ ግፍ ሄዶ ሄዶ የሚያስከትለውን መዘዝ እንዴት አጡት? ድንቁርና ይህን ያህል በጀብደኝት ያሳውራል?

ወደአስቂኙ ድራማ ልለፍ፡፡ አንዳርጋቸው በ“ነፃ ኅሊናው” የሰጠውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በደናቁር የወያኔ ወንበዴዎች እሳቤ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ይህን ይመስላል፤ “የግንቦት ሰባት ኅልውና ከእንግዲህ ግፋ ቢል ለሁለት ወራት ቢዘልቅ ነው፤ ወዲያም አለ ወዲህ ዕድሜው ከሁለት ወር አይበልጥም፡፡ የአውሮፓና አሜሪካ ምቾቱን ትቶ እንደኔ በረሃ ወርዶ የሚያታግል ቆራጥ ሰው አይኖረውም፡፡…” የግንቦት ሰባት ቀሪ ዕድሜ ሁለት ቀንም ይሁን ሁለት ወር እሱ ሌላ ጉዳይና ወደፊትም የሚታይ ሆኖ ይህን የተናገረው ግን አንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑን ልብ ይሏል – አንዲን በሚዲያም ቢሆን ባላውቀው ኖሮ ከአሁን በፊት “የተናገረውን”ና ገና ወደፊት “እንደሚናገረው በጉጉት” የሚጠበቀውን ሁሉ በበኩሌ ሳላንገራግር በሙሉ ልቤ አምኜ በተቀበልኩና ከወያኔ የሸፈተውን ልቤን ወደወያኔ በመለስኩ ነበር – ይህ ሁሉ ድካማቸው ታያ የማንን ቀልብ ለመሳብ ? በመሠረቱ እስካሁን ወያኔ የነበረ በአንዳርጋቸው ንግግር ምክንያት የወያኔነት ደረጃው አይጨምርም – በተቃራኒውም እስካሁን ወያኔ ያልነበረ በዚሁ የአንዲ ንግግር ምክንያት ንዴቱና ቁጭቱ ይጨምርና ወደድርጊት ይገባ እንደሆነ እንጂ ከተቃዋሚነቱ የሚያፈገፍግ አይመስለኝም፤ እናም የወያኔዎች የጅልነት ምጥቀት ያሳዝነኛል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንና ዓለምን በጠቅላላው እስከዚህን ያህል መናቃቸው ምን ያህል ወራዳዎች – እደግመዋለሁ ምዕመናን – ምን ያህል ወራዳዎች መሆናቸውን ከማሳየት በስተቀር የአንዲ ስቃይና የሙሌት ኑዛዜ የሚጨምርላቸው አንዳችም አወንታዊ ነገር የለም – ይህን ነባራዊ እውነት ለመናገር ደግሞ የክር ወይም የሃቂቃ ጉዳይ እንጂ የግንቦት ሰባት አባልም ሆነ ደጋፊ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የወያኔዎችን ውስጠ ምሥጢርና የግፍ ታሪክ በየመድረኮች ሲዘከዘክ ሚሊዮኖችን በዕንባ ሲያራጭና በትካዜ ባህር ሲያሰምጥ የምናውቀው አንዳርጋቸው ጽጌ በምትሃታዊ ፍጥነት ወደማፊያው መንግሥት ተገልብጦ ተናገረው የተባለውን እንዲያ ሲናገር ይታያችሁ፡፡ የምናውቀው አንዳርጋቸው የምናውቅለትን ጽኑ ፀረ-ወያኔ አቋሙን በሻጥርና በብዙ ገንዘብ ክፍያ በየመኖች ተይዞ በወያኔዎች እጅ በገባ በሁለት ሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሲለውጥ በዐይነ ኅሊናችሁ ይታያችሁ፡፡

ግሩም የምርመራ ውጤት! ዓለምን የሚያስደምም ሣይንሳዊ የወንጀል ምርመራ ግኝት! በዚህ በአንዳርጋቸው ቃልና የመከራ ኑዛዜ ማፈር ያለበት ቀደም ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ከወያኔ ውጭ ማንንም ሊያሳፍር አይችልም፡፡ እንዲያውም እኔ ብሆን ኖሮ “ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጅት ከነአካቴው በሕይወት አለ እንዴ? አሁን እናንተ ስትሉ ሰማሁ፡፡ ማን ተናገር እንዳለኝ አላውቅም ዝም ብዬ ነበር እኮ በኢሳት ያንን ሁሉ ንግግር የምዘባርቀው፡፡ ደግሞ ብርሃኑን ብሎ ግንቦት ሰባት! ከመነሻው ግንቦት ሰባት ብሎ ነገር ሲኖር አይደለም ወርቆቼ! …” ብዬ አስደስታቸው ነበር እንጂ የሌለን ምሥጢር ለመደበቅ በመሞከር ሰውነቴን ለስቃይ አልዳርግም – ሊያውም በዚያ ኑዛዜየም ስቃዩን ቢቀንሱልኝ አይደል? ግን አይቀንሱልኝም – ስለዚህ ብናገርም ባልናገርም ለውጥ የለውም፤ ጠባችን በደም የሚጠራ እንጂ በውሃ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና፡፡

እንደውነቱ ታዲያ አንዳርጋቸው ሊሰጠው የሚችለው የማይታወቅ የተከደነ አዲስ ምሥጢር ሊኖር ይችላል? ሁሉም ነገር እኮ ግልጽ ነው፤ ወያኔ የሚባል ሀገር አጥፊና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የማፊያዎች ቡድን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ውስጥ መሽጎ አለ – እሱን ለማስወገድ ደግሞ ዜጎች በተበታተነ ሁኔታም ቢሆን በየፊናቸው ጥረታቸውን እያደረጉ ነው፤ ምሥጢር ከተባለ ይህ ነው ምሥጢሩ፡፡ አንዳርጋቸው የትግል መስመሩ ስላበሳጫቸውና እየሠራ ያለው ነገር ለኅልውናቸው አስጊ ሆኖ ክፉኛ የሚያሳስባቸው በመሆኑ እርግጥ ነው እሱን ከመድረክ ገለል እንዲል ማድረግ ቢፈልጉ ያንን መቀበል ይቻላል – ሰይጣናዊ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሄዱበት ርቀት ብዙ የሕግና የሞራል ችግር ማስነሳቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ከዚያ ውጪ ምሥጢር አውጣ ብሎ የዓለማችን ቤት ባፈራው የማሰቃያ ዘዴ ሁሉ ሰውን ማሰቃየት፣ በዚያም ሂደት ራስን ለትዝብትና ለስላቅ የሚያጋልጥ ነውረኛ የምርመራ ሂደት ማካሄድና ተመርማሪዎች የማያምኑበትን ነገር እንዲናገሩ ማድረግ በእግረ መንገድም “በሰላም አንገዛም፣ አንገብርምም ያሉንንና ሕዝብን የሚያሳምጹብንን ቀንደኛ ጠላቶቻችንን ‹እንዲህ አሸናናቸው!›፣ የወንዶች ወንዶች መሆናችንን ብልታቸውን እየቆረጥን አሳየናቸው…” በማለት ስብዕናን ለማዋረድ መሞከር ወደራስ የሚዞር አሉታዊ ውጤትን መጋበዝ መሆኑን መረዳት ይገባቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ወያኔ ልብሱም ጉርሱም ቅሌትና ውርደት በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚሰማው አንድም የሀፍረትም ሆነ የይሉኝታ ስሜት የለም፡፡ ጃዝ ብለው የለቀቁት 13 እና 33 ቁጥሮችም እየሳቁበትና እየተዝናኑበትም ቢሆን ወያኔ ለሚሠራው ግፍና በደል ሁሉ ቡራኬያቸውን አይነፍጉትም፡፡ እነሱስ ቢሆን በጭፍሮቻቸው አማካይነት በጓንታናሞና ኢራቅ ውስጥ አስከሬኖች ላይ እስከመሽናት በሚዘልቅ ኢሰብአዊነት ስንትና ስንት ግፍ ይፈጸሙ የለም? ልጅ ከአባት ቢማርና የጭካኔ ደረጃውን አዘምኖ ምሥኪን ኢትዮጵያውያንን ምድራዊ ገሃነም ውስጥ ቢዘፍቃቸው ዋኖቹ ሀዘን አምላኪዎች ይደሰታሉ እንጂ ከከንፈር ሽንገላ ባለፈ ሕዝቡን ሊታደጉት አይፈልጉም – ይህንንም አሳምረን እናውቃለን፡፡ ጭምብሉን ፖለቲካዊ የተለሳለሰ የሚመስል አካሄድም አንዘነጋም – አገም ጠቀሙን፡፡

በነገራችን ላይ 13 እና 11 ወይም 33 ደግሞ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ለሚያምንበት ሁሉም የትልቁ ቁጥር የአውሬው መገለጫ የ666 ቅንስናሾች ናቸው፡፡ አሥራ አንዶች በ110 የለበጣ ቀመር ቢያላግጡም እውነቱ ቀፎ የመለዋወጥ – የትሮይን ፈረስ ቅርጽ የማሻሻል ጉዳይ እንጂ ሲሙ ያው ነው – አሥራ አንድ፡፡ ለነገሩ ዝናር ባንገቴም ይሁን 11 ወይም ዜሮም ይሁን አንድ ሽንትር ዋናው ነገር ተግባር ነው፡፡ ሌላው ትርፍና ጨዋታን ለማሳመር ያህል በአጃቢነት የገባ ነው፡፡ እናም በሀገራችን ሁኔታ የሰውዬው ማንነት ምንም ይሁን ምን በስቃይና በግድያ የሚያምን ሁሉ እናት ክፍሉና ጥንተ አመጣጡ ከአውሬው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክፉና ደግ መንፈሶች ኅብረት የላቸውም፡፡ ሩህሩህ መሐሪና አረመኔ/ጨካኝ ገዳይ አንድነት የላቸውም፡፡ መጽሐፉም ጣፋጭ ፍሬ በዛፍ ላይ ሳለ ይታወቃል እንደሚል ማን የማን ወገን መሆኑ በተለይ በዘመናችን በግልጽ ይታወቃል፡፡ ማን ነው የበሽታ ሕዋሳትን በቤተ ሙከራ እየፈለሰፈና እያራባ ለዓለም በተለይም ለኋላቀር ሀገሮች እንደ ዕርዳታ ስንዴ የሚያከፋፍል? ማን ነው የዓለማችንን የአየር ንብረት እያዛባና ዕድሜዋን በብርሃን ፍጥነት እያሳጠረ የሚገኘው? የዓለምን ጠቅላይ ገዢነት በትረ መንግሥት በጉልበት የተቆጣጠረውና “ለኔ ካልሰገዳችሁ ሀብትና ሥልጣን አይኖራችሁም” ብሎ ሁሉን እያስደገደገ የሚገኘውና በትዕምርተ ኅቡኣታዊ ባለአንድ ዐይን ፒራሚዳዊ ቅርጽ ወይም በፔንታጋራማቲን የኮከብ ቅርጽ የሚታወቀው ምሥጢራዊ ኃይል ማን ነው? ማን ነው አሁንም ሆነ ከአሁን በፊት መካከለኛውን ምሥራቅ እያተራመሰ ያለው? መፍለቂያው የሆነችን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ኅልውናና የበላይነት ለማስጠበቅ ሲል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቱ የዓለምን የመንግሥታት ኅብረት እንደአሽከር ሰጥ ለምበጥ አድርጎ የሚገዛ ማን ነው? አይኤም ኤፍ፣ ዩኤን፣ ወርልድባንክ፣ ኔቶ፣ ሲአርኤፍ፣ … የማን አድቃቂ ክንዶች ናቸው? ለመሆኑ የዚህ ሞገደኛ የወቅቱ የዓለማችን ገዢ ዋና መሥሪያ ቤትና ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የት የት ናቸው? ጽዮንና ሀማስ የማን ልዑካን ናቸው? የግጭቶች መንስኤና የምክንያታዊነት ሚዛኑ ለማንም ያጋድል ዋናው የሁለቱም ተልእኮ ግና ለአውሬው ግብር የሚሆን ብዙ የደም ባህር ማቆር መሆኑን መዘንጋት የዓለም ነገር አያገባኝም ብሎ እንደመመነን ይቆጠራል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል – ማን ነው የጦር ኃይሎችን በሁለት ጎራ እየከፈለ በተፃራሪነት በማሰለፍ የሚሊዮኖችን ደም በከንቱ እያፋሰሰ ያለው? ኢራንና አሜሪካ በርግጥም ባላንጣዎች ይሆኑ እንዴ? በፍጹም፡፡ ጠላቶች መስለው ትያትር በመከወን ለአንድ ዓላማ ስኬት የሚተጉ የአንድ ገዢ አንድ አምሳል አንድ አካል ናቸው፡፡ ማን ነው በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከአፍ እስከገደፋቸው በንጹሃን ተሣፋሪዎች ጢም ብለው የሞሉ የሲቪል አውሮፕላኖችን(የማሌዥያን) ባልታወቀ ዕፀ መሠውርና በሚሳኤይል ድራሻቸውን ያጠፋው? ምን ዓይነት ወያኔያዊ ጨካኝ አንጀት ያለው ፍጡር ይሆን ይህን ያደረገ? ለምን ዓላማ? ቫቲካንንና መለስተኛ አውሮፕላን የምታህል የነጭ እርግብ ምስል ለማስመሰል ያህል በሰላም ምልክትነት በዋና የፓትርያርክ ጸ/ቤቱ በር ላይ ያቆመውን የኛኑ ኦርቶዶክስ ሳይቀር ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተቆጣጥሮ ሁሉንም ሃይማኖት አለኝ ባይ በአውሬው ትዕዛዝ ሥር ያደረገው ማን ነው? ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ቅዱስ ሊባል የሚችል ቦታና ሰው አለ ወይ? ፖፕ ጆን ፖል አንደኛ፣ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ፣ ‹አቡነ› ጳውሎስ የኛ… ሌሎችም የማን ወኪል ነበሩ? ፍየሎች በበጎች ጋጣ ውስጥ መሽገዋል፡፡ በጎች እያለቁ ነው፡፡ አውሬው ሆሊውድና ቦሊውድን ብቻ ሳይን ገዳማትንና ካቴድራሎችንም ከተቆጣጠረ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ጭካኔን በሚያስተምሩ ፊልሞች፣ በልቅና ባልተገሩ ኢ-ሞራላዊም በሆኑ ፖርኖግራፊዎች በተለይ የዓለምን ወጣት ትውልድ ጡጦ ከመጣሉ በእንጭጩ ለማምከን ይህችን ዓለም ማንና ከየትስ ሆኖ እየገዛት እንዳለ መች አጣነው? የዚያ ‹ታላቅ› የጨለማ ንጉሥ የእጅ ሥራዎች የሆኑ ወያኔዎችም ባቅማቸው ቅድስቲቱን ሀገር ድራሽዋን ቢያጠፏት ከድጋፍ በስተቀር ማን ከልካይ አላቸው? በጎችስ ቢጮኹ አለጊዜው ማን ይደርስላቸዋል? ግን ግን አይዞን፤ የፍየሎችና የበጎች የመጨረሻ ዕድል ተለይቶ የሚታወቅበት የፍርድ ቀን በፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ብሎም ቢሆን ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ድል በምኞት ሊገኝ እንደማይችል ልብ ማለት ይገባናል፡፡ ብቻ ይህን መሰሉን ነገር በሆድ ይፍጀው ለሌላ ቀን በይደር ማቆየቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለነገሩ እኛን ምን አገባን? ሁሉም ከልኩ አይዘል፡፡

ከሰው ተውሼ እያነበብኩት ነበር – “ያልተሄደበት መንገድ”ን፡፡ በቅርብ ካነበብኳቸው በሀገር ችግር ዙሪያ ከሚያጠነጥኑ የቅርብ ጊዜ መጻሕፍት ውስጥ በኔ ዕይታና ለኔ ፍጆታ ይሄኛውን ወደር አላገኘሁለትም፡፡ አንዱአለም አራጌ ዋለ የተዋጣለት መጽሐፍ በመጻፉ – ሊያውም በዚህ አፍላ የጎልማሳነት ዕድሜውና በመከራ ውስጥ ሆኖ – ባለበት አድናቆቴ ይድረሰው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚባለው በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ነው፡፡ ሚሊዮኖች ፈርተንና ለሥጋችን አድረን በየሽርንቁላው ተወትፈን በፍርሀት ቆፈን ስንርድ ሊያውም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ይህን የመሰለ አብሪ መጽሐፍ ካለበቂ ማጣቀሻና ዋቢ መጻሕፍት በአዩኝ አላዩኝ ሰቀቀን ሌሊት ሌሊት እየተደበቁ መጻፍ ልዩ ጀግንነትና ተሰጥዖም ነው፡፡ አንዱአለምና መሰል የብዕርና የፖለቲካ ታጋዮች ለነፃይቱ ኢትዮጵያ በሕይወት እንዲደርሱ እግዚአብሔር ይታደገን፤ ይታደጋቸው፡፡ ቤተሰባቸውንም ይባርክ፡፡ ለእኛም ለባከንነውና ለራሳችን ጥቅምና ፍላጎት ስንል በ‹እስኪያልፍ ያለፋል› ተረት ራሳችንን እያታለልን የወያኔ ባርያ ሆነን ለጠፋነው ዜጎችም ፈጣሪ ረድኤቱንና ወኔውን ይስጠን፡፡ እንደዚህ ያሉ ዜጎች ባይኖሩን ኖሮ ሕይወት በጠቅላላው ለይቶላት ጨለማ በሆነች ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር እግዜር የተመሰገነ ይሁን፡፡ እርሱን መሰል ሌሎች ጸሐፊዎችንና ታሳሪዎችንም ጭምር እግዜር ይባርክልን፡፡ ለቤታቸውም ያብቃልን፡፡ የሚሳነው ነገር የሌለው የኢትዮጵያ አምላክ የመከራ ደብዳቤያችንን የሚቀድድና ሃራ የሚያወጣን አንዳች ኃይል ይዘዝልን፡፡ አሜን፡፡

ይህ መጽሐፍ የዋቢ መጻሕፍትን ገጽ ጨምሮ በጠቅላላው 320 ገጾች አሉት፡፡ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ሥር የተካተቱ 18 ርዕሶችንም ይዟል፡፡ ጠቅጠቅ ብሎ የተጻፈ በመሆኑ እንደሌሎች በርካታ መሰል መጻሕፍት በቀላሉ አይገፋም፡፡ የሆኖ ሆኖ በተለይ እስከማገባደጃው ድረስ ስሜትን ቆንጥጦ በመያዝ መነበብ የሚያስችለው ሥነ ጽሑፋዊ ውበትና ይዘታዊ ግርማ ሞገስ አለው፡፡ እናም አንብቡት፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መጽሐፍ እያነበብኩ ወደ ገጽ 100 አካባቢ ስደርስ የተዋስኩትን እንደምመልስ ገባኝና ወዲያውኑ ከተማ ወጥቼ ገዛሁት፡፡ ተውሼ ያነበብኩትን ወይም እያነበብኩት ያለሁትን መጽሐፍ ስገዛ ይህ የመጀመሪያ ጊዜየ ነው፡፡ አንጡራ ሀብቴና የመጻሕፍት መደርደሪያየ አንዱ ፈርጥ እንዲሆን ተመኘሁ፡፡ ተመኝቼም አልቀረሁ፡፡ ለልጆቼ ውርስ ይሆናል፡፡ እናንተም አሁኑኑ ግዙና ንብረታችሁ አድርጉት፡፡ መጽሐፉ “ኩሎ አመክሩ ወዘሰናየ አጸንዑ” እንዲል፡፡

አመስጋኝ አማሳኝ እንዳልባል በዚህ መጽሐፍ የታዘብኳቸውን አንዳንድ ግድፈቶችም በዚሁ አጋጣሚ ብጠቁም ደስ ይለኛል፡፡ ጥቂት የማይባሉ የአርትዖት ችግሮች አሉበት፡፡ አሉታዊ መሆን ያለበት በአወንታዊ ወይም የዚህ ተቃራኒ ሆኖ የሚጻፍበት አጋጣሚ አልፎ አልፎ ይስተዋላል፡፡ አማርኛ ላይ ብዙውን ጊዜ የምታስቸግር ነገር አለች – ለምሳሌ “እኔን እንደሚያገባኝ እንዴት ረሳኸው?” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ሚ”ን “ማ” ብናደርጋት ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል፡፡ “ጽንፍ” ለማለት “ቅንፍ” ብንል አንዳንዶችን ግር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የአርትዖት ሥራ ሽንፍላ እንደማጠብ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች በብዙ አዳዲስ ዐይኖች ሊተባበሩበት የሚገባው አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ የማይጠራበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ ይህን ቆንጆና ለታሪክ የሚቀመጥ መጽሐፍ ዐዋቂ ሰው እንደገና “ኤዲት” ቢያደርገው የበለጠ ማለፊያ ይሆናል፡፡ የግሌ አስተያየት ነው፡፡ (አንድ ወዳጄ የነገረኝ አንድ አርትዖታዊ ስህተት በጭንቅላቴ ብልጭ እያለ ‹እዚህ ላይ ካልጻፍከኝ ሞቼ እገኛለሁ!› ብሎ አስቸገረኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ የብድር ኮሚቴ ስብሰባ ይጠራል፡፡ ለተሰብሳቢዎችም “ከብድር ኮሚቴ…. ለጠቅላላ አባላት” የሚል ጽሑፍ ተበትኗል፡፡ ሁሉን ያስፈገገው ግን ጸሐፊዋ “ከብድር ኮሚቴ” ከሚለው ሐረግ ውስጥ የአንዱን ቃል የመጨረሻ ፊደል ሳትጽፈው መቅረቷና እስከዚያን የስብሰባ ጊዜ ድረስ ማንም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ስህተቱን ልብ አለማለቱ ነበር፡፡ ያቺ “ነገረኛ” ጸሐፊ የትኛዋን ሆሄ እንደዘነጋቻት እኔም አሁን ዘነጋኋት፡፡ )

ከሆሄያት ግድፈትና ሞክሼ ፊደላትን በነባሩ ሰዋስዋዊ ልማድ ከመጠቀም አኳያ ከሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን “ስህተቶች” በተጓዳኝ ጥቂት የመረጃ መዛባትና የዘይቤና ፈሊጥ አጠቃቀም እጅግ አነስተኛ ችግር ሳይኖር እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ለምሳሌ “ኢሕአፓ” የሚለው ምሕጻረ ቃል ሲፈታ እኔ የማውቀው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ” በሚል ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ግን “የኢትዮጵያ ሕዝብ አደራጅ ፓርቲ” በሚል ከአንዴም ሁለቴ ገደማ ቀርቧል፡፡ ፈሊጥን በተመለከተ “ለያዥ ለገራዥ” ለማለት “ለያዥ ለገናዥ” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሃሳብ ድግግሞሽ በስፋት ይታይበታል፡፡ በዚያም ምክንያት አንድ አንባቢ በጀመረበት የስሜት ሞቅታ መጨረስ ባይችል ችግሩ ከዚህ የሃሳቦች መደጋገም የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ የመጽሐፉ አጻጻፍና ለኅትመት መብቃት በብዙ ችግር የታጠረ በመሆኑ የአሁኑ ይዘቱ ራሱ ከሚጠበቀው በላይና በአንጻራዊ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ መሰል ጸሑፎች(እኔ ካነበብኳቸው) በጣም የተሻለ መሆኑን በበኩሌ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥረቱ ደራሲውን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ጓዶች፡፡ እነኚህንና መሰል ሌሎች እንከኖችን አስተካክሎ በቀጣይ ኅትመት ለንባብ የሚያበቃው ወገን ከተገኘ መልካም ነው፡፡ ደግሞም የማይቻል አይመስለኝም፡፡

አንዱአለምን በዚህ መጽሐፉ ደርቤ እንዳነበብኩት የፕሮፌሰር መስፍን ደቀ መዝሙር ይመስለኛል፡፡ ይህን የምለው ፕሮፌሰሩ አንድ ወቅት እነብርሃኑ ነጋ “ሁለገብ ዘዴን በመጠቀም ወያኔን እንታገላለን” ባሉ ወቅት ክፉኛ ይተቿቸውና “እኛ ወደዚህ ‹የማይረባና ውዳቂ› የአስተሳሰብ ደረጃ አንወርድም” ማለታቸውን በማስታወስና አንዱአለምም በዚያው ቅኝት አሁንም ድረስ በዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንዝ ቀርቶ የደረቀ ምንጭ በማያሻግር የሰላማዊ ትግል ሥልት ወያኔን እንጥላለን ብሎ የሚያምን በመሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዱአለም አሁን ባለበት ሁኔታ በኃይል ወይም በጦር መሣሪያ ወያኔን እንታገል ብሎ ቢጽፍ የሚደርስበትን ተጨማሪ መከራና ፍዳ ስለምንገነዘብ ይህን አቋም ያርምድ ብለን በሰው ቁስል እንጨት አንሰድም፡፡ ይሁንና ቢያንስ ዝም ማለት ሲገባ ወያኔ የፈጠረው የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ችግር የሚፈታው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ነው የሚል እምነት በጭፍን ማራመዱን አልወደድኩለትም፡፡ (በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሰ ቅድም በኢሳት አንድ ውይይት ላይ ሲናገር እንደሰማሁት የአንዳርጋቸውን በወያኔዎች መያዝ ኔልሰን ማንዴላ በኢዲያሚን ዳዳ እንደተያዘ ያህል እቆጥረዋለሁ ማለቱን እኔም በጣም እደግፋለሁ፡፡) ሰው ከሰው ጋር ቢታገል አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡ ከአውሬ ጋር ግን እንዴት መታገል ይቻላል? ውሾች በ“አስተሳሰብ” ከሚበልጡት ወያኔ ጋር እንዴት ስለሰላም መወያየት እንደሚቻል አንዱአለም ቢያስረዳኝ ደስ ባለኝ፤ ውሾ ሲሸናነፉ በሚያሳዩት ተፈጥሯዊ ምልክት ይግባቡና ጦርነቱን ያቆማሉ፤ ከዚያም በመካከላቸው ሰላም ይሰፍናል፡፡ ሁኔታዎችም ወደጥንቱ (statusquo ante) ይመለሱና ማኅበረከልባዊ ሕይወት ትቀጥላለች (“ከልብ” ውሻ ማለት ነው – “ል” ጠብቃ አትነበብም)፡፡ ወያኔ ግን ያሸነፈውን ሁሉ በሕይወት ያለውን ብቻም አይደለም የሞተውን ሳይቀር እስከመቃብር ድረስ የፕሮፓጋንዳ ሠራዊት እያዘመተ የቅርብ አጥንቶችንና የሩቅ አፅሞችን የሚፋለም ዶንኪሾት ነው፡፡ ይህን ባሕርዩን ለማወቅ በግድ እንደነአሥራት ወ/የስ መሞትና እንደነእስክንድር ነጋ መታሰር አያስፈልግም፡፡ ዛሬ ላይ ቁጭ ብሎ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን አስነሳለሁ ብሎ መቃዠት በርግጥም ቅዠትና ሲያንስም የዋህነት እንጂ አንዱአለምን ከመሰለ በሳል የፖለቲካ ሰውነት የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ውሱን ነጥብ አኳያ ምን እንደነካው ሊገባኝ አልቻለም፡፡

አክራሪ ኦርዶቶክሳውያን እንዳይቀየሙኝ እንጂ የአንዱአለም የዋህነት (naivety?) ከ‹ቅድስት› ክርስቶስ ሠምራ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ ‹ቅ.› ክርስቶስ ሠምራ – በገድሏ ላይ ተጽፎ እንደሚነበበው – ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ ዕቅድ ትነድፋለች አሉ፡፡ … እርሱ ወዳለበት ሲዖል በቀጥታ ትሄዳለች፡፡ “ስፈልግሽ ኖሮ እዚሁ መጣሽልኝ?” ይላትና የክርስቶስ ሠምራን ነፍስ ይዞ ወደግዛቱ ሊያስገባት ሲል መላእክት ደርሰው ወደመጣችበት ወደገነት ይወስዷታል፡፡ በአጋጣሚው ግን 78 ሺህ የተኮነኑ የሲዖል ነፍሳት በቅድስቲቷ መንፈሳዊ አካል ላይ በመጣበቅ ወደገነት ይገባሉ፡፡ እምነት ነው፡፡ በየዘመናቱ በገዢዎችና በሃይማኖት መሪዎች ፈቃድ እንዲካተቱ የተደረጉና እነዚህን አሳሳች ይዘት ያላቸውንና እርስ በርስ የሚቃረኑ፣ “በእግዚአብሔር መንፈስ የተነዱ” ሰዎች ስለመጻፋቸው የሚጠቁም አንዳችም ማስረጃም የሌላቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ የተካተቱ አንዳንድ ጽሑፎችንና ሰይጣናዊ ሳጋዎችን ሳይቀር ላለመቀበል አንድ ሰው መብት ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊ ድርሰት ማመን አለማመን የማንም ውዴታ እንጂ ግዴታ ሊሆን አይገባም – እዚያው ውስጥ በሚገኙት ዘንድም ቢሆን፡፡ ታርጋ ሳይለጠፍብኝ ስለሃይማኖቴ ልናገር እንዴ? አይ፣ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ግን ማንኛውንም ሃይማኖታዊ አክራሪነትና ጽንፈኝነት የምጠላ አማኝ(theist) መሆኔን ብገልጽ ደስ ይለኛል፡፡ አነሳሴ ወዳልሆነ ነገር በመንሸራተቴ ይቅርታ – ምን ላድርግ ሁሉም ነገር አንሸራታች ሆኖ ዐረፈው እኮ፡፡ ብቻ አንዱአለም የዚህችን ቀና ሴት ባሕርይ የተላበሰ ግን በአፀደ ሕይወት የሚገኝ የማይቻልን ነገር ለመሞከር የሚተጋ የወንድ ክርስቶስ ሠምራ ይመስለኛል፡፡

ሰላማዊ ትግል የራሱ መደላድል አለው፡፡ በቅድሚያ የሀገርህ ሰው ከሆነ ሰው ጋር፣ ዜጋህ ከሆነ ሰው ጋር፣ እንደዜጋው ከሚቆጥርህ ወይም ከሚመለከትህ የአገዛዝ ኃይል ጋር፣ በትንሹ ደግሞ ሰው መሆንህን አምኖ ከሚቀበል ሰው ጋር እንጂ ከአውሬና ከለዬለት የዲያብሎስ መንጋ ጋር በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ብለህ ወርቃማ የመቶዎች ዓመታት ጊዜህን አታባክንም – አንዱአለም የሚለው ግን ዝንታለሙን እየታሰርንና እየተገደልን ነፃነታችንን ከወያኔ በችሮታ እንቀበል ነው – ምናልባትም በወዲያኛው የምፅዓት ዘመን፡፡ ሰዎች ወያኔን መረዳት እንዴት እንዳልቻሉ ወይም እንደማይችሉ ሳስበው ይገርመኛል፤ እንዲያውም ወያኔዎች፣ ሰዎች እንዲህ እንዲሆኑ – ማለትም በሰላማዊ መንገድ ከነሱ ጋር መታገል እንደሚቻል እንዲያምኑና እንዲያሳምኑ – የሚያደርግ ድግምት ቢጤ ሳይኖራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አለበለዚያስ የሰላማዊ ትግልን ገፈት ቀማሽ ከሆነ አንዱአለምን ከመሰለ ብርቅዬ ዜጋ እንዲህ ያለ ተሳስቶ የሚያሳስት አነጋገርና እምነት ሊደመጥ ባልተገባ ነበር፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ዝምታ ማንን ገደለ? በከንቱ መነቃቀፍ ከትዝብት በስተቀር ምን አወንታዊ ውጤት ያስገኛል? እንዳለመታደልና እንደርግማንም ሆኖ በኅብረት መታገል ቢያቅት ሁሉም ባመነበት ቢንቀሳቀስ ምን ክፋት አለው? ከአድማስ ማዶ ሊኖር ይችላል ተብሎ በሚታሰብ ሥጋት ከወዲሁ መቆራቆስ አግባብ ነው ወይ? ለዚህማ ወያኔ አለ አይደል? ይህን ስል አንዱአለማውያንና መስፍናውያን – በተወሰነ ደረጃ እኔንም ጨምሮ – ስሜታችን እንደሚጎፈንን ይሰማኛል፡፡ ግን ምርጫ የለኝም፡፡ የሚሰማኝን መናገሬ እንደወንጀል ሊቆጠርብኝ አይገባም፡፡ አውቃለሁ – አንዱአለም እሳት ውስጥ ነው፡፡ አልክድም – እኔም ከርሱ ባልተናነሰ ሁኔታ እሳት ውስጥ አለሁ፡፡ ልዩነታችን እርሱ ባመነበት ገብቷል፡፡ “ደስ”ም ያለው ይመስላል፡፡ የኔ ግን ከሁሉ ያጣ ሆኜ በዕብደትና በስክነት መካከል አንዴ ሰው አንዴ ዐፈር በመሆን እየተቀያየርኩ መረጋጋትና ሰላም የሌለው ሕይወት እገፋለሁ፡፡ ኅሊናህን አፍነህ መኖር ከመታሰር በበለጠ እንደሚጎዳ አውቄያለሁ፡፡ ሰው እንኳን ሳያውቅልህ በአእምሮ ስቃይ ምክንያት ከቤተሰብህም ከጓደኞችህም ‹እየተናጀስክ› ሰላምህን አጥተህ በትልቁ እስር ቤት መኖር በትንሹ እስር ቤት ከመኖር የበለጠ እንደሚያሰቃይ ተረድቻለሁ፡፡ መብላት፣ መጠጣት፣ መዳራትና በሰፊ ጎዳና መመላለስ ትርጉም የሚያጡበትና አንጎልህ ተቀፍድዶ ተይዞ ሰዎችን ሰላም በምትነሳበት ሁኔታ ለመኖር ያህል ብቻ መኖር ከለዬለት ከርቸሌ ያልተሻለ መሆኑን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ፡፡ ስለሆነም ከአንዱአለም ባልተናነሰ የኔም እስረኝነት የዋዛ አይደለምና ሁላችንም አንድ ነን፡፡ እንዲህ የምለው ስለኔ ብቻ አይደለም – ስለሌሎች እኔን መሰሎችም እንጂ፡፡ እንዲህ የምለው ግን ለምንድነው? የማንን አንጀት ለማላወስ? ማንስ ነው ሆዴ ላይ ቆሞ ያናዘዘኝ? ሆ!

በውሸት መከሰሱን፣ በውሸት ምሥክር (አዳፍኔ በሚላቸው) ዘብጥያ መውረዱን፣ በውሸት የግንቦት ሰባት አባልና የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ከምንደኞች ጋር እያቀነባበረ ነው መባሉን፣ …. ሁሉንም ዘንግቶ ከእባብ ዕንቁላል እርግብ እንደሚፈለፈል ሊያስረዳን መሞከሩ አንዱአለም ወያኔን ለማወቅ ገና ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት መሆኑን አመልክቶኛል – ጠሊቅ ሀገራዊና ታሪካዊ ዕውቀት ያለው መሆኑ ተይዞልኝ፡፡ እናም እላለሁ – ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢሉ ወያኔ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን አይለቅም፡፡ ይህን ፀሐይ የሞቀውንና ሀገር ያወቀውን ሃቅ በመካድ ከዚህ የተለዬ ህልም ማለም – እንደአካሄድ ባይከለከልም – ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡ በነገራችን ላይ ክርስቶስም ለትግስቱና ለፍቅሩ ገደብ ነበረው፤ ለዚህም ነው በመሳም አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን የረገመው – በአንገቱ የወፍጮ መጅ ታስሮ ወደጥልቅ ባህር ቢወረወር እንደሚሻለው በምሬት በመናገር፡፡

ይቅርታችሁንና በዚህስ አንዱአለምን ተናድጀበታለሁ፡፡ ምን ነካው ግን? እንግዲያውስ ያበጠው ይፈንዳ በኢትዮጵያ እንደእስካሁኑ የስግብግብነትና ራስ ወዳድነት በሽታችንና የሥልጣን አራራችን ከሆነ በሰላማዊ መንገድ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ግዛቸው ሽፈራውም ሥልጣን አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውልም አይለቅም (በጤና ምክንያት …ካልሆነ)፤ እንኳንስ ወያኔ ፕሮ. በየነ ጴጥሮስም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. መረራ ጉዲናም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. ፍስሐ እሸቱም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ በቁሙ የሞተው ከሃዲው ልደቱ አያሌውም አይለቅም … (ዝርዝሩ ብዙና ብዙ ነው – ስንተዋወቅ? ግን እባብ ልቡን ዐይቶ እግሩን ነሣው ሆነና …)፡፡ የኢትዮጵያ መሬት አዲስ በሚፈልቅ ፍቱን ጠበል ካልተረጨ ይሄ የሥልጣንና የገንዘብ እንዲሁም የሴሰኝነት ጠንቆች በቀላሉ አይለቁንም – በኛ ባሱብን እንጂ እርግጥ ነው እነዚህ መሰናከያዎች የአጠቃላዩ የሰው ዘር መደናቀፊያዎች መሆናቸው የታወቀ ነው (ለምሳሌ የሰሞኑንና የቅርብ ሩቅ ጊዜውን የኢራቁን አልማሊኪንና የግብጹን አልሲሲን የሥልጣን ሱስ ብናይ በሰው ልጅ ራስ ወዳድነት መገረማችን አይቀርም – ይህ ነገር ወደኛ መጥቶ ከማይምነታችን፣ ከሥልጣን ወዳድነታችንና ከቦክሰኛው አስተዳደጋችን ጋር ሲደመርማ ምን ያሳይ፡፡) በኛ ሀገር ለሁሉም ነገር በተለይም ለጥላቻችንና ለራስ ወዳድነታችን ልጓም አጣን፤ ለከት ጠፋ፤ በቃኝን ተጸየፍን፤ ጠገብኩን ጠላን፤ ከይሉኝታና ሀፍረት ተፋታን – ስንገርም፡፡ እናም ለነዚህ ነገሮች ያለን ጥብቅ ቀረቤታ ከሌሎች የጥፋት ሰበዞች ጋር ተደማምሮ እንደሀገርም እንደሕዝብም ከናካቴው ከምድረ ገጽ ልንጠፋ – መለኮታዊ ጣልቃገብነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካልተከሰተ – ዘመኑ ቀረበ፡፡ ውሸት ነው? ውሸት ነው ካልክ እውነት ነው ማለት ነው፡፡ “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የሚል መጽሐፍ ዱሮ አነበብኩ ልበል? አዎ፣ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› እንዲሉ ካልሆነ ለይቶልን ጠፍናል፡፡ አንወሻሽ፡፡

አንዱአለም ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን እንደማይለቅ አሳምሮ ያውቃል፡፡ መጽሐፉ ላይ በገደምዳሜ ገልጾታል፡፡ እንደመፍትሔ በየገጾቹ የሚያቀርበው ግን ያንኑ የሰላማዊ መንገድ የትግል ሥልት ነው፡፡ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ” ይላል አንዱአለም ፈገግ ባደረገኝ ሁኔታ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ ሌላ የሰላማዊ መንገድ መሞከር ነው፡፡” ከመሰነባበታችን በፊት በመጽሐፉ መጨረሻ አካባቢ ገጽ 312 ላይ የሚገኘውንና ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ማስወገድ ባይቻል በማስከተል ምን ማድረግ እንደሚገባ አንዱአለም የመጨረሻ መፍትሔ ብሎ የሚሰነዝረውን እንመልከት – ወጣቱ ፖለቲከኛ አይፈረድበትም፡፡ የት ነው ያለውና? አያድርስ ነው – እነዚህ ሰዎች አስጨንቀው ያዙንና እምንለውንም እያሳካሩ ግራ አጋቡን እኮ፡፡ አንዱ ለጓደኛው “ያዋስኩህን ዕቃ ባትመልስ ዋልህ! አሳይሃለሁ!” ይለዋል፡፡ “ምናባህ ልታደርገኝ አንት የውሻ ልጅ!” ብሎ ቢያፈጥበት “አይ፣ ምን አድርግሃለሁ ያው ታዝቤህ እቀራለሁ እንጂ” አለው ይባላል፡፡ እርግጥ ነው መናገር የማድረግን ያህል እንደማይከብድ አውቃለሁ፡፡ “አይ መሬት ያለ ሰው!” ብሏል አሉ የሚጋልበው ፈረስ የደነበረበት አንድ ሰው – “እንዲህ አድርገው፤ እንዲህ ያዘው” ባሉት ጊዜና፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው፡፡ እርግጥ ነው – አታሞ በሰው እጅ ስታምር በገዛ እጅግ ግን ልታደናግር ትችላለች፡፡ ቢሆንም የሚሰማኝን ብናገር ቢያንስ ዴሞክራሲያዊ መብቴን “ባልተሸራረፈ” መልኩ እንደተጠቀምኩበት ከመረዳቴም በተጨማሪ የተወሰነ እፎይታን አገኛለሁ፡፡ ለማንኛውም ወደአንዱአለም የመጨረሻ የችግሮቻችን መፍትሔ እናምራና ለአፍታ እንመልከትለት፤

ትልቁ ጥያቄ ኢሕአዴግ የብሔራዊ ዕርቁን ጥያቄ አሁንም “የባልና የሚስት ፀብ አይደለም” ብሎ ቢያጣጥለው ምን ማድረግ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምነት ኢሕአዴግ ከዚህ በኋላም (እስካሁን) ለ21 ዓመታት የዳከረበትን መንገድ የሚመርጥ ከሆነ ተቃዋሚዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነው የሚጓዙ(በ)ት የራሳቸው አዲስ መንገድ መፈጠሩ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያን በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለመገንባት (የ)ሚያስችለውን የብሔራዊ ዕርቅ መንገድ በመጓዝ ለፍትሃዊ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገድ መጥረግ የማይፈልግ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ላይ የራሱን ግላዊ ወይም ቡድናዊ ጥቅም ብቻ የሚያስቀድም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ኢሕአዴግም ይሄን መንገድ እስከመረጠ ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በኃይል ረግጦ የመግዛት ፍላጎቱን አሁንም ለመቀጠል እንደሚፈልግ ያሳያል፡፡ የማንወጣው መንገድ ቢሆንም ከተገደድን ግን ኢትዮጵያውያን በፀና ሰላማዊ ትግል ኢሕአዲግን ልኩን እንዲያውቅ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፈቃድ እንዲገዛ ማድረግ አማራጭ የለውም፡፡ … (መስመር የተጨመረ)

ወያኔ ልኩን የሚያውቀው በሰላማዊ ትግል ነውን? ይህ ነገር እውነት ይሆን? ይህች ነገር አጭር የክበበው ገዳን ቀልድ ትመስለኛለች፡፡

በመሠረቱ ጥሩ መመኘት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን የምኞትን ገደብ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አንዱአለም ከዕድሜ አንጻርም ይሁን ከገጠመኝ ማጠጥ/ማጠር የተነሣ በኢትዮጵያ ምድር አይመኙትን ምኞት በመመኘት እርሱን መሳይ የዋሃንን በተስፋ ዳቦ ለመቀብተትና በከንቱ ለማስገሳት ሲጥር እንመለከታለን፡፡ እዚህም ላይ ወያኔን አለማወቁ ያሳዝነኛል፡፡ ማንበብ ጥሩ ነው፤ ማወቅና መመራመርም ጥሩ ነው፡፡ ተስፈኝነት መልካም ነው፡፡ ተስፋ አለመቁረጥና ሩቅ ማሰብም ደግ ነው፡፡ ይሁንና ጓዳችን ውስጥ እንደመዥገር ተለጥፎ በመርዘኛ ጥርስና ምላሱ እያንገበገበን የሚገኘውን ወያኔ በሰላማዊ ትግል ይወገዳል ብሎ ማሰብና መስበክ አንድም ባለማወቅም ቢሆን የወያኔን ዓላማ የማራመድ ያህል ነው አለዚያም ሞኝነት ነው፡፡ ቢሆን በወደድን፡፡ ግን ፈጽሞ አይሆንም – ተምኔታዊነት (ዩቶፒያን መሆን) ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፤ ማኅተመ ጋንዲ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ ምርጥ የዓለማችን ዜጎች የታገሉት ከሰዎች ጋር ነው፡፡ የኛን የሚለየው ትግላችን ከድፍን ቅል ዘረኞችና መቼም በማይበርድ እንዲያዉም እየሰላ በሚሄድ የጥላቻና የቂም በቀል አባዜ ከተሞሉ የባንዳ ልጆች ጋር ነው፡፡ ምናልባት አንዱአለም ያልተገነዘበው ይህንን ሃቅ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በዚያ ላይ በሰላማዊ ትግል ቀርቶ በመሣሪያም የሚነቀንቃቸው እንዳይኖር ሕዝቡን በማይምነት ጋርደው፣ ፍጹም ከደረጃ በታች በሆነና “A,B,C,D”ን በቅጡ በማያስለይ እንዲሁም ዜጎችን በሚከፋፍል የትምህርት ሥርዓት ትውልድን አደድበው፣ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያንን በማይረባ የጥቅም ፍርፋሪ ከፋፍለው፣ በዘረኛ የፌዴራል ፖሊስ፣ በደንቆሮ ካድሬና መከላከያ አፍነው፣ በቅንድብ ጥቅሻና በስልክ ቀጭን ትዕዛዝ ወንበዴዎቹ የሚፈልጉትን ፍርድ በሚያስተላልፍ ኮንዶም ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ሀገር ምድሩን ሞልተውት፣ ዜጎችን በጎጠኛ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅር ቀፍድደው፣ በድህነት ኮድኩደው፣ በተለይ ወጣቱን በልዩ ልዩ ሱሶችና በወሲብ የአዶከብሬ ዛር ዳንኪራ አስረግጠው፣ በመርዘኛ የጎሰኝነትና የዘረኝነት በሽታ ሕዝበ አዳምን በክለው፣ … ከጠማማ ጎጆው ባለፈ – የሰኞን ነፍሱን ወደማክሰኞ በማሳደሩ ከመደሰት በዘለለ ለሀገርና ለወገን የሚቆረቆር ዜጋ እንዳይኖር አድርገው የሀገሪቱን ኅልውና ገደል ጫፍ ላይ ጥለውታል፡፡ ይህን ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጥላለሁ ብሎ ማሰብ ዕብደት ነው የምለውም ለዚህ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ሥርዓት የመጨረሻ ፕሬዝደንት ኤፍ ደብልይው ደክለርክ ጭንቅላቱ ውስጥ ተሸክሞት ይዞር የነበረው ሊማር የሚችል ጤናማ ነጭ አንጎል እንጂ እንደወያኔ በድንቁርና የታጀለ ከመግደልና በሰው ስቃይ ከመደሰት ውጪ ምንም የማያውቅ የገማና የበሸቀጠ ጥቁር ጭቃ አልነበረም፡፡ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ማለት ለወያኔ አዲስና ለራሳቸው ለአባላቱም ቢሆን ግርታን የሚፈጥር ልዩ ተፈጥሮን እንደማላበስ ይቆጠራል፡፡…

አፄ ኃ/ሥላሴ ለጉብኝት ይሁን ለሥራ ወዳንድ ቦታ ሲሄዱ አንዲት ችግረኛ ሴት ከነልጆቿ መንገድ ዳር ቆማ “ወድቃ በተነሳችው ባንዲራችን፣ በልዑል እግዚአብሔር ይሁንብዎ…” በማለት ባንዴራ ዘርግታ ታስቆማቸዋለች፡፡ ያኔ እንደዛሬው ዘመን መሪ ሲወጣና ሲገባ ግድግዳ እያስደገፉ (የሚገርም እኮ ነው!) ለገዢዎች የኅለውና መሠረት ከመሆናቸው አንጻር ውድና ብርቅ ሊሆኑ የሚገባቸውን ዜጎች በኢሰብአዊነት ማሰቃየት አልነበረምና ጃንሆይ መኪናቸውን አስቁመው በመውረድ “ችግርሽ ምንድነው?” ብለው ይጠይቋታል፡፡ ሴትዮዋም፣ “ጃንሆይ፣ ለምግብ ያላነሱ ለሥራ ያልደረሱ ስድስት ልጆችን ጥሎብኝ ባለቤቴ ሞተ…” ብላ ችግሯን መናገር ስትጀምር በቀልደኛነት የሚታወቁት የቀድሞው ንጉሣችን አጠገባቸው አጅበዋቸው ወደቆሙ መኳንንት ዘወር ብለው “አግባኝ ነው የምትለው?” ብለው እንደዋዛ ጣል ያደረጓት ቀልድ በሴትዮዋ ጆሮ ገብታ ኖሮ ድሃ መቼም ሞኝ ነውና “ጃንሆይ! ሆኖልኝ ነው! አ’ርጎት ነው!” አለች ይባላል፡፡ ቀልድ በአግባቡ ጥሩ ነው፡፡ ኃ/ሥላሴ ሴትዮዋን እንደማያገቧት ግልጽ ነው – ሴትዮዋ ግን ድሃና በዕውቀትም ዝቅተኛ ናትና በጣለችው ተስፋ አንፈርድባትም፡፡ ከወያኔ ጉያ ሕዝባዊ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ይገኛል ተብሎ ተስፋ ማድረግ ግን ከሴትዮዋ የበለጠ ጅል መሆንን የሚያመለክት እንጂ የወያኔን ተፈጥሮ ከመገንዘብ የሚመነጭ ገምቢ ዕውቀትና ጥበብ አይመስለኝም፡፡ ይህን የሚመር ቀልድ የሚቀልዱ ሰዎች ራሳቸውን ቢመረምሩ የተሻለ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል ደግሞም በኢትዮጵያ – ሆ!

በጦርነት የሚገኝ ነገር መልካም ነው እያልኩ እንዳልሆነ ግን ይመዝገብልኝ፡፡ ምርጫ ከጠፋ ግና ምን ይደረጋል? ከሁለት መጥፎዎች የተሻለውን መምረጥ የምንገደድበት ጊዜ ይኖራል፡፡ እናም ሰው ካልሆነ አውሬ ጋር እየታገሉ ከማለቅ ቢያንስ የራሴ ነው ከሚሉት ጨካኝና አምባገነን መሪ ጋር መፋለም ይመረጣል – ለዚያም መብቃት እኮ መታደል ነው፡፡ እንደሚመስለኝ አሁን ሰዎችን እያሳሰባቸው ያለው የማያሳስብ ነገር ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ያለችው ፍጡር ወድዳ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ “ሌላውን እሾህ በመቀመጫየ ተቀምጬ ራሴው እነቅለዋለሁ” ማለቷ ነው፡፡ እና ያልበላንን የሚያኩልን ወገኖች አደብ ቢገዙልን ብዙ እንደረዱን ይቆጠራል፡፡ ለነገሩ ወያኔን ማንም ደገፈው ማን – በማወቅም ይሁን ባለማወቅ – ወቅቱን ጠብቆ ወረደ መቃብሩን ሳይወድ በግዱ መቀበሉ አይቀርም፡፡ አንድዬ በመንበሩ ካለ – አለም- ይህን ሁሉ ግፍና በደል የፈጸሙ ሰው መሳይ “ሰዎች” የቁናቸውን ሳይከፈሉ ይቀራሉ ብሎ ማሰብ የታሪክንና የፈጣሪን ፍርድ አለመረዳት ነው፡፡ የሞተ ይነሳል፤ የተኛ ይነቃል፤ የቆመ ይቀመጣል፤ የተጋደመ ይቆማል፡፡ ለሁሉም ጊዜ እንዳለው ዛሬ አይደለም የምናውቀው፡፡ ታሪክና እግዜሩ ወያኔ ላይ ሲደርሱ ሥራቸውን ያቆሙ ይሆን? ለጅላጅሎቹ ወያኔዎች እንዲያ ሳይመስላቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ለኔ ግን በፍጹም! ጊዜው ቀርቧል፡፡
አገባቤና አወጣጤ የተምታታ ነገር ያለበት መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለዚህ የተምታታ ነገሬ ማንን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ ግን አላውቅም፡፡ የሆኖ ሆኖ የዚህ ዘመን እውነት ባብዛኛው የተዘበራረቀ በመሆኑ አላግባብ ሊፈርድብኝ የሚቃጣ እንደማይኖር እገምታለሁ፡፡ ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልና ወደማይቀረው ድል እየተጠጋን ስንመጣ እንጫወታለን፡፡ ማርቲን ሉተር ባይቀድመኝ እኔም “ህልም አለኝ!” ብል በወደድኩ፡፡

“ቀኒቷን ማንም አያውቅም፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙኃኑ ጎጋም እንኳን የምፅዓትን የመጨረሻ ቀን አያውቃትም፡፡ እናንተ የሚገባችሁ ታጥባችሁ ታጥናችሁ መጠበቅ ነው – ከሙስናና ከዕድፍ ርቃችሁ፤ ከዘረኝነት አረንቋና ከሆዳምነት ተቆጥባችሁ፤ አስተዋይነትን ተላብሳችሁ፣ በወረተኛ ወጀባዊ ንፋስ እንዳትወሰዱ ተጠንቅቃችሁ … ፡፡ ይሁንና ምልክቶቹን ስታዩ የቀኒቷን መቅረብ ትረዳላችሁ፡፡ ምልክቶቹን ያዬ ትውልድ ከምፅዓት በፊት የምትገለጠዋን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ቀን ያያታል፡፡ …” (‹መጽሐፈ ትንሣኤ ኢትዮጵያ› ፣ ምዕራፍና ቁጥር የማይነበብ!)
በየነ

↧

የማይጮሁት…በአሉ ግርማን የበሉት ጅቦች በአበራ ለማ

↧
↧

ለኑሮ ውድነቱ ዋነኛ ምክንያት ህገ-ወጥ ብልፅግና እና ኢፍትሃዊነት ነው። “ለለውጥ እንነሳ !!!”– Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ቀን በቀን እየናረ የመጣውን የወያኒ አምባገነንነት እና ዝርፊያ ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡
ለለውጥ በጋራ እጅ ለእጅ ተይይዘን በአምባገነኖች እና በብዝብዦች ላይ እንነሳ !!!!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በሃሰት እቅዶችና በምኞት የሚሰብከውን ወያኒ ልናስወግድ ግድ ይለናል። እንደሚታየው ዛሬ እንደፋሽን የተያዘው ህገ-ወጥ ብልፅግና ነው፡፡ ሀገራዊ ስሜት ያለጥርጥር እየቀጨጨ ነው፡፡ ደምብና ሥርዓትን መጣስ እንደፋሽን ተይዟል፡፡ ድህነትን መቀነስ እንደአፍ አመል ሆኖ ይነገራል እንጂ በበሰለ መልኩ ህዝብ ውስጥ አልሰረፀም፡፡ ግማሽ ጎፈሬ፣ ግማሽ ልጩ የሆነ ካፒታሊዝም ከፋይዳው ማነስ ግራ ማጋባቱ ይብሳል፡፡ የምሁሮቻችን የድህነትን አሽክላ ለማስወገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ከስራ አጥነት መዘዝ ጋር ተዳምሮ፣ ከአረንቋው እንዳንወጣ እያደረገን ነው፡፡ አዙሪቱ እጅግ ጥምዝምዝና ተደጋጋሚ ነው፡፡ “ከእለት እንጀራና ከትክክለኛ ምርጫ የትኛው ይሻላል?” ዓይነት አጣብቂኝ የድህነት የቤት ጣጣ ነው፡፡ ሀብት እኩል ባልተከፋፈለበት አገር ምርጫ 100% ተሳካ ሲባል አይገርምም ይላሉ ባለሙያዎች እንዲህ ግራ-ገብ ነገር ሲበዛባቸው፡፡ ከሁሉም ይሰውረን ማለት ትልቅ ፀሎት ነው፡፡

ወገን ሆይ ያለዓላማ ጉዞ ከንቱ ነው፡፡ ቀን በቀን እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡ ያለቅርስና ያለበቂ መሰረታዊ ጥቅም ነፃ-ገበያን መመኘት የጫጩት አትራፊነት ምኞት ነው፡፡ ያለብስለት ጥናትና ምርምር፣ ያለብቁ ባለሙያ ዕድገት ዘበት ነው፡፡ ኑሮአችን ታግለን ካላሻሻልን ፣ ደሀ ጎጆው ካልተመለሰ፣ ልማቱ ከደረቀ፣ እሳቱ ካልሞቀ ተስፋው ይሞትበታል፡፡ ኑሮው መለወጥ አለበት፡፡ መታገዝ አለበት፡፡ ገቢና ወጪው መመጣጠን መቻል አለበት፡፡ ውሎ አድሮ ገቢው ይጨምር ዘንድ መንገዱ ሊጠረግለት ይገባል፡፡ለዚህ ደሞ እኛ በትግሉ አለም የመሳተፍ ግዴታ አለብን ። ለለውጥ ራሳችንን ማንቀሳቀስ ግድ ይለናል። ነጻነትን ልናገኝ የምንችለው ከአምባገነኖች የጭቆና ምመድፍ ልንወጣ የምንችለው ራሳችን ስንታገል እንጂ ከደጅ የመጣ እንግዳ አሊያም ምእራባውያን ንእጻነታችንን ሊሰጡን አይችሉም።

ኑሮ ዛሬ ነው፡፡ ነገ ምኞት ነው፡፡ ህይወት በእጅ ባለበት ሰዓት የሚኖር እንጂ በምኞት የሚታቀድ አይደለም፡፡ ዛሬ መኖር መቻል አለበት፡፡ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በቀላሉ መገብየት አለባቸው፡፡ ቀን በቀን እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ሳንገታ ዕድገትን ብናልም ምኞት ብቻ ነው፡፡የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ኢ-አድሎአዊነትና ቀናነትን ይጠይቃል፡፡ የብዙሃን ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት አስፈላጊነት አጠያያቂ ያለመሆኑን ያህል፤ ሁሉም ፓርቲዎች እኩል መሆናቸውን፣ በታሪክ የብቻውን ካሳ የሚያገኝ አንድም ፓርቲ መኖር እንደማይገባ፣ እርስ በእርስ መወዳደራቸው የዕድገት ማሺን መሆኑ እጅግ ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡ ሁሉም ፓርቲዎች ያለጭቦ መሳተፋቸውና መወከላቸው፣ የሲቪል ቡድኖችም ሊሳተፉበት ማስፈለጉ ገሀድ ጉዳይ ነው፡፡ በማግለል እንጂ በማሳተፍ የምናወጣው ነገር እንደሌለ ልብ ማለት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎችን በጋራ ትግል እስካላስወገድን ድረስ ምንም አይነት የኢኮኖሚ ለውጥ/እድገት በራሳችን ላይ ማምጣት አንሽልም ስለዚህ ለተጀመረው የትግል ስኬት የእያንዳንዳችንን ጉልህ ሚና እን ተሳትፎ ይሻል።ለለውጥ በጋራ አምባገነኖች ላይ እንነሳ !!!!!!#ምንሊክሳልሳዊ

↧

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች እና አደርባዮቻቸው የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::…. .. እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! -Minilik Salsawi (ምንሊክሳልሳዊ)

ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረሱ ይገኛሉ፤ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ በማስመጥ ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው::

በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚኒነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ ገዢ ነኝ ባዩ አካል የስርኣት ለውጥ ማምጣት ስለማይችል በህዝቦች የጋራ ትግል ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌላ አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ለመናገር እወዳለሁ::

ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል:: ሁሉም በተደጋጋሚ ታግለው ስልጣን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ተናግረን የማንጨርሳቸው እስር፣ ስደት ፣ስራ አጥነት ፣ግድያ ፣ክስራ መፈናቀል፣ ተመሳሳይ ምእንግስታዊ ውንብድናዎችቸና ሽብሮች በዜጎች ላይ እየተፈጸሙ በገሃድ እየታዩ እንዲሁም መንግስትዊ ቅጥፈት/ውሸቶች በአደባባይ እየተደሰኮሩ የትውልድን ሞራል ለመግደል ካለመታከት እየተውተረተሩ ነው። ራሳችንን ማንቃት ለለውጥ መነሳት ግድ ይለናል ፤ ደጋግመን እንናገራለን በሕዝብ ልጆች አፋጣኝ ትግል እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ :: በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም:: ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን ።….እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! #ምንሊክሳልሳዊ

↧

“ውሸታም”! ጌታቸው አበራ

↧
↧

ስደተኛውና አምላኩ በምትኩ አዲሱ

ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ በ “የስደተኛው ማስታወሻ” [2006] መጽሐፉ ላይ “ፍቅር በለጠ” እና “ህሊና እንደ አምላክ” [ምዕራፍ 33፣34] በሚሉ ተያያዥ ርዕሶች ሥር ስለ ክርስትና ሃይማኖት ያለውን መረዳት አስፍሯል። ጴንጤዋን “ፍቅር በለጠ” ን እንደ መስተዋት ይዞልን የሃይማኖትን አስተምህሮዎች ሊያስረዳን ሞክሯል። በዚህ ሐተታዊ ግምገማ ሁለት አሳቦችን እናነሳለን፦ 1/ “ፍቅር በለጠ” እና የያዘችው ሃይማኖት ምን ይመስላሉ? 2/ ጋዜጠኛው/ደራሲው በእጁ የያዘው መስተዋት የራሱን ማንነት እንዴት ይገልጠዋል? በመጨረሻም፣ ስለ ደራሲውና ሥራዎቹ አጭር አሠሳ አድርገን እንደመድማለን።

ደራሲው በ1987 ዓ.ም. ወደ አሜሪካ ለጉዳይ በተጓዘበት ወቅት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምትሰራ “አንዲት ሴት” ዲሲ አሜሪካ “ፍቅር በለጠ” ለተሰኘች ዘመዷ በእጁ ፖስታ እንደላከችና ሲደርስ ዘመድ የተባለችው “ለረጅም ጊዜ ያላያት” ጎረቤቱ ሆና እንዳገኛት የሚገልጽ ሐተታ ነው። ከዚያ በመነሳት ያደረገችለትን መስተንግዶና ጨዋታቸውን ያጋራናል።

“ፍቅር በለጠ” ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ልትወስደው ደጋግማ ጠይቃው “ከአንድ ጊዜ በላይ” አብሯት ሄዷል። “ፍቅር” ሁለት ልጆች አሏት። በዕድሜ ከደራሲው ትበልጣለች። አሜሪካ በተገናኙበት በ1987 ዓ.ም ደራሲው 27 ዓመቱ ነው፤ “ገና ኮረዳ ትመስያለሽ” ይላታል [ገጽ 349]። ወደ አሜሪካ የመጣችውም ከሁለት ልጆቿ ጋር ነው። ባል ይኑራት፣ ትፍታ፣ ይሙት አልተገለጸም። አሜሪካን አገር በገባ “በነጋታው” ደወሎላት፤ በጠቆመችው አድራሻ መሠረት አፓርታማዋ ደረሰ። በር ላይ የተጋጋለ ሰላምታ እየተለዋወጡ “በሃይለኛ ስሜትና መንፈስ ተሞልታ … ይሄ የጌታ ኢየሱስ ተአምር መሆን አለበት። አንተን ይህን ፖስታ አስይዞ ወደዚህ ቤት የላከበት ምክንያትና አላማ ይኖረዋል” አለች። ሁለቱ እንዲገናኙ የታቀደ ነገር ይኖር ይሆን? ወደ ውስጥ እንደ ገቡ አንድ ሳሎን፣አንድ መኝታ ቤት፣ አንድ ወጥ ቤት አፓርታማዋን ታስጎበኘው ጀመረች። “ቤትሽ ደ’ሞ በጣም ያምራል” ይላታል። “ስለ ቤት እቃዎቿ ታብራራለት ጀመር” [ገጽ349]። ሶፋው ንፁህ ቆዳ ሆኖ ትክክለኛ ዋጋው 1500 ዶላር ነው፤ የገዛችው ግን በ700 ዶላር ነው። የወለሉ እንጨት ከብራዚል፤ ሹካና ማንካያዎቹ የማይዝጉ ሆነው ከህንድ፤ ሳህኖቹ ከፖርቱጋል [ኋይት ሃውስ ካሉት ጋር ይመሳሰላሉ]፤ የመኝታ ፍራሹ በዓለም ምርጥ ከተባሉት ሁለተኛ ነው፤ ብርድ ልብሱ ከግብፅ ጥጥ የተሠራ ነው። ከዚያ ወደ ወጥ ቤት አመሩ። መሳቢያዎቹን ከፋፍታ ቅመማ ቅመሙን “አንድ ባንድ” አሳየችው። ለእንግዳ “ቤት ያፈራውን” ማቅረብ የተለመደ ቢሆንም፣ “ምን አይነት ምግብ ልስራልህ?” ብላ ጠየቀችኝ [ገጽ351]። “ፍቅር በለጠ” ጴንጤ መሆኗ ከተለምዶ ውጭ የማድረግን ጸጋ አጎናጽፏት ይሆን?

“ሽሮው በመሰራት ላይ ሳለ [ ] ስለ ቁሳቁሶቹና ስለ ቅመማ ቅመሞቹ የምትነግረኝ ሊያልቅ ስላልቻለ የወሬ ማርሽ ቀየርኩ፣ ጠጉርሽ በጣም ያምራል … ዊግ ነው የሚመስለው … ማረጋገጥ ከፈለግህ ንካው አለች” [ገጽ 351-2]። ደራሲውና “ፍቅር” ትውውቃቸው ቤተክርስቲያን እንዲሄድ ደጋግማ ከጠየቀችው ውጭ መጠነኛ እንደ ሆነ ነግሮናል። ጎረቤቱ ሆና ከአገር መውጣቷን እንኳ አላወቀም። ስሟ ፖስታው ላይ ተጽፎ እያየ ያቺ ጎረቤቱ ትሆናለች ብሎ አልጠረጠረም። ሰላምታ ተለዋውጦ አንድ መኝታ፣ አንድ ሳሎን፣ አንድ ወጥ ቤት የዲሲ አፓርታማ ለመጎብኘት 30 ደቂቃ ፈጀ ቢባል፤ በደረሰ በ30 ደቂቃ ውስጥ ከኋላዋ ቆሞ ጠጉሯን እየነካካ ጊዜዋን እንዴት እንደምታሳልፍ፣ ስለም/ማታነበው መጽሐፍ፣ ስለምትከታተለው ሚድያ፣ ስለ ራሱ የእምነት ጉዞ፣ “የተወላገደ ሸሚዙን እያቃናች” [ገጽ 352] ስለ ሰጠችው ምክር፣ ጌታ ስላሳያት ተአምር፣ ጌታ እንዴት እንደተናገራት፣ ወዘተ አወራን ይለናል። የ “ፍቅር በለጠ” ሁለት ልጆቿ አብረዋት ይኑሩ አልተገለጸም። ከአገሩ ህግ አንጻር መኝታ ቤቱ አንድ ብቻ መሆኑ አብረው አይኖሩም የሚለውን ግምት ይደግፋል። ከመስተንግዶው ባል እንዳላት አይመስልም።

ወጡ እስከሚሠራ ለጠየቃት ሦስት ተከታታይ ጥያቄዎች እስቲ ምላሾቿን እናጢን። ጥያቄዎቹ፣ “ትርፍ ጊዜሽን በምን ታሳልፊያለሽ?” “ታነቢያለሽ?” እና “ሜዲያ ትከታተያለሽ?” የሚሉ ናቸው። ለሦስቱም ጥያቄዎች የ”ፍቅር” መልስ ሃይማኖት፣ ዕድሜ፣ ጾታና ጎሳ ሳይለይ የሚታየውን አገራዊ ሁኔታ አጉልቶ አውጥቶታል። ጴንጤዎች ሊለዩ ይገባልና፣ ዓለማዊነትና ቁሳቁስ ማግበስበስ ኑሮአቸውንና ንግግራቸውን መያዙ የሚያምም እውነት፣ ትክክለኛ ትዝብት ነው። “ፍቅር” ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አታነብብም። በአብዛኛው ከብልጽግናና ከዓለማዊ አስተሳሰብ ያልራቀ ትምህርት ከሚያስተጋቡ ከክርስቲያን ቻነሎች ውጭ አታይም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ “ፉርሽካ” ማንበብ ለርሷ መቀላቀል ነው። ፖለቲካ ዋጋ የለውም። ብዙ ማንበብ “እምነትን ገድሎ ለሰይጣን ይሰጣል።” የማታውቀው ሰው ገንዘብ እንደሚያወርሳት ጌታ በግልጽ ነግሮአት በጸሎት እየጠበቀች ነው።

“ጌታ በግልጽ ነገረኝ” ስላለችው፣ “ይቅርታ አድርጊልኝና ቃል በቃል ምን አለሽ?” ይላታል። “በቀጥታ ነው ጌታ የሚነግረኝ። የህልም ተሰጥኦም አለኝ። የውርሱን የነገረኝ ግን በጸሎት ጊዜ ነው። ውርስ እንደማገኝ የሚገልጽ መልእክት ወደ ልቤ መጣ። ‘ገንዘቡ እጅሽ ሲገባ የምነግርሽ ቦታ ሄደሽ የወደቁ ልጆችን ታነሺያለሽ’ ብሎ ነገረኝ” ትለዋለች [ገጽ 353-4]። “ፍቅር” ለማን መቼና እንዴት ምን ማለት እንዳለባት የማታስተውል፣ አእምሮዋን የጣለች ሆና እናገኛታለን። ደራሲው “የተቸገሩ ልጆች አምላክ በሌላ መንገድ ሊረዳቸው አይችልም ነበር?” ይላታል። ስትመልስ፣ እግዚአብሔር “ዮሴፍ በባርነት እንዲሸጥ ያደረገው፣ ሊያነሳው ስለ ፈለገ ነው” ትላለች [ገጽ354]። አፏ ውስጥ ይጨምር እርሷው ትበለው ዮሴፍን የግብጽ ጠቅላይ ሚንስትር ሊያደርገው በባርነት እንዲሸጥ ፈቀደ ማለት የታሪኩን ይዘት ማዛባት ነው። ያዕቆብ ከልጆቹ ሁሉ ዮሴፍን ያስበልጥ ነበርና፤ ወንድሞቹ በዮሴፍ ይቀኑበት ነበር። ዮሴፍ ህልም አለመ። በህልሙም እናትና አባቱ ወንድሞቹም ሳይቀሩ ለርሱ ሲሰግዱ ተመለከተ። ባለማስተዋል ይህንን ህልም ለሁሉም ማውራት ጀመረ። አጋጣሚ ሲያገኙ ወንድሞቹ ሊገድሉት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፣ ኋላ ግን ከምንገድለው ትንሽ ገንዘብ እናትርፍበት ብለው ለተላላፊ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ሸጡት [ዘፍጥረት 37]። በሌላ አነጋገር፣ በዮሴፍ ላይ በደረሰው መከራ ውስጥ የወላጆቹ ልጆቻቸውን ማበላለጥ፣ የወንድሞቹ ቅናትና የዮሴፍ አለማስተዋል አስተዋጽኦ አድርጓል ማለት ነው። ሰው ለክፉ ያደረገበትን እግዚአብሔር ለበጎ እንደ ለወጠው፤ እግዚአብሔር በህልም ያሳየውን ዕውን እንዳደረገ ዮሴፍ ያስተዋለው ኋላ ቆይቶ ነው። ዮሴፍን ሊያነሳው ስለ ፈለገ ለባርነት ዳረገው ማለት ታሪኩን ማዛባት ነው ያልነው ለዚህ ነው።

ምግቡ ደርሶ በሉ። የበሉት ግን በሸክላ ሳህኖቹ ሳይሆን ለቤተኛ በሚቀርብ ተበልቶበት በሚጣል ፕላስቲክ ሳህን ነው። “ፍቅር” ሳህኖቿን ትወዳለች፤ “በትንሹም በትልቁም” ልታወጣቸው አትፈልግም። አፍ አውጥታ ፖስታ ላመጣላት እንግዳ “ደግሞ ማጠቡም ያሰለቻል … የእቃ ማጠቢያው ኬሚካል በጊዜ ብዛት ጣቶቼን እንዳያበላሽ ብዬ ነው [ገጽ 355]” ትለዋለች።

የተቀረው ክፍል [ገጽ 355-7] ከ “ህሊና እንደ አምላክ” [ም.34] ጋር የተያያዘ ስለሆነ ኋላ እንመለስበታለን። በቅድሚያ ግን “ፍቅር”ን ክርስትናን ለማሳያ እንደ መስተዋት ሲጠቀምባት፣ ያው የያዘው መስተዋት እራሱን እንዴት ገለጠው የሚለውን እንመልከት። ደራሲው “በእምነት ጉዳይ አክራሪ አይደለሁም” ይለናል [ገጽ 348]። ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት ፣ ጀሆቫ እና ኦርቶዶክስ መሆን ለርሱ “አክራሪ” መሆን ነው። እነዚህ ሃይማኖቶች በርሱ ዘንድ “ተመሳሳይ” ናቸው። በምን በምን ይመሳሰላሉ? በምንስ ይለያያሉ? አይነግረንም። መንግሥትም “ሃይማኖት አይለያየንም” በሚል ሽፋን ዓላማውን ሊያራምድ የሞከረባቸው ወቅቶች ነበሩ። የሚገርመው ግን የተጠቀሱት የእምነት ክፍሎች በደራሲውና በመንግሥት ዐይን ራሳቸውን የማይመለከቱ መሆናቸው ነው። “በማንኛውም የእምነት ቦታ ገብቼ ጸሎት ለማድረስ የሚያስችል ችሎታና ሚዛናዊ ስሜት ነበረኝ” ይለናል [ገጽ 348-9]። ካቶሊኩም ጋ እንደ ካቶሊክ፣ ጀሆቫውም ጋ እንደ ጀሆቫ መሆን እችላለሁ እያለን ነው? “አክራሪ” አይደለሁም፤ “ችሎታና ሚዛናዊ ስሜት” ነበረኝ ሲል ከየሃይማኖቱ ድንጋጌ ውጭ የማድረግ “ችሎታ” አለኝ ማለቱ ነው? የራሱ “ችሎታና ሚዛናዊ ስሜት” በየሃይማኖቱ ላይ ተጽዕኖ የሚያደርግ ከሆነስ ከሚተቸው “አክራሪነት” በምን ይለያል? “ሚዛናዊነቱ” የየሃይማኖቶች አስተምህሮ ለኔ መስማማታቸው ላይ ነው እያለን ነው። “በራሴ መንገድ” ሲለን “ክራይላሶ” ሦስት ጊዜ አልልም፣ ሁለቴ ይበቃል ሊል ነው። የሃይማኖትን ድንጋጌ ወደ ጎን አድርጎ የራሱን ማቆም ይሻል [ገጽ 359]። “አንተ ሙሉ ሰው ነህ። የነገሩህን ብቻ አትቀበል። የልብህን ድምጽ አዳምጥ። ከውስጥህ የምትሰማው እሱ እውነት ነው …” [ገጽ 365]። አንድ ማኅበረሰብ የሚያያዘው እያንዳንዱ ዜጋ በነፍስ ወከፍ የመሰለውን ሲያደርግ አይደለም። የጸኑ፣ ሁሉም በጋራ ሊቀበላቸው የተገባ መመሪያዎች አሉና። የግል አመለካከትም እንዳለ ሁሉ፣ ሃይማኖት የሚጋራው ከሌለ የቆመለትን ሥርዓት እንደሚገባ መፈጸም ያዳግተዋል።

ደራሲው “ከአንድ ጊዜ በላይ” ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን “ፍቅር” ጋብዛው ሄዷል። ሰላም በሕይወቱ የለም፣ “እኔ ያጣሁትን መንፈሳዊ ሰላም ይህች ሴት ብቻዋን ጠቅልላ እንደ ያዘችው አልተጠራጠርኩም” [ገጽ 349]። መጽሐፍ ቅዱስ “ድሮ” [በልጅነቱ] አንብቦአል፤ አንዳንዱን ክፍል ደግሞታል። “ጎረምሳ ሳለ ይጸልይ” ነበር [ገጽ 355]። ዛሬ የማመን ኃይሉ ደክሟል፤ ወደ ነበረበት መመለስ አቅቶታል [ገጽ 352]። ከመድከሙ አስቀድሞ የነበረበትን ሁኔታ ግን አላስረዳም። ይልቅ ወደ ኋላ የተመለሰበትን አንድ ምክንያት “ሰዎች አምላክ ነገረኝ” የሚሉት ከህሊናቸው ጋር የሚያደርጉትን ንግግር እንደ ሆነ ስለ ደረስኩበት ነው” ይለናል [ገጽ355]። ጥልቅ የሆኑ የሕይወት ጥያቄዎች ያሉት ሰው ነው። የሕይወት ነገር የተወሳሰበበት ሰው ነው። በምዕራፉ መግቢያ ላይ ለምሳሌ፣ የማረፊያ በቀለን ግጥም ቆንጽሎ አመልክቷል፦ “ይበቃኛል በርግጥ – ግማሽህን ማየት / ግማሽ በመሆኑ – ሰው የመሆን እውነት።” ነገሮች የተከደነና የተገለጠ ክፍል አላቸው። የተከደነውን ክፍል በጥያቄ ብዛት ለመረዳት ይጥራል። መጠየቅ ግን ግማሽ ቁምነገር ነው፤ ሌላኛው ቁምነገር መረጃ ያለው መልስ ሲገኝ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን ነው።

“ጣፋጭ ቦዘና ሽሮ” በመመገብ ላይ እያሉ ድንገት ሳታስበው “ጎጃሜ ነሽ እንዴ?” ይላታል። የጠየቀበት ምክንያቱ “ስምሽ ትርጉም አለው ብዬ ነው” [ገጽ 354]። ቀድሞውኑ ስም ያወጣላት እራሱ ደራሲው እንደ ሆነ አንርሳ፤ ይኸው አጠራርና ጎጃሜነት አማረ ተግባሩ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተጠቅሷል፤ “አይ ደብሬ! መወለድ እኮ ቋንቋ ነው። እኛስ ቢሆን ጎጃምን ጥለነው አይደል የወጣን! ይልቅስ ፍቅር ይበልጣል ልጄ!” ["ያንዲት ምድር ልጆች" ቅጽ 1፣ 2ኛ እትም፣ 2000 ዓ.ም፤ ገጽ 36]። “ያንዲት ምድር ልጆች” እና “የስደተኛው” ም. 32 “የአንድ አባት ልጆች” የርዕሶቹና ባህርያቱ መመሳሰል ባጋጣሚ ነው?

“ማስታወሻዎቹ እውነተኛ ታሪኮች፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ትረካዎች ናቸውና …ሊገመት በሚችለው ምክንያት የምስጋና ስሞችን ከመዘርዘር ተቆጥቤያለሁ።” [ገጽ 5-6]። ከ”ፍቅር በለጠ” ይልቅ የጎጃሜነት ጥያቄ ለደራሲው ቁምነገር እንደ ሆነ እንመለከታለን። ሌላኛው፣ በርሷ የምናየውን ቅንነት በርሱ አለማየታችን ነው፤ “ወሬ ለመቀየር” ለሚጠይቃት ጥያቄ “የተደበላለቀ አሰልቺ” ምላሽ እንደ ሰጠችው ደጋግሞ ይነግረናል [ገጽ 351፣ 353፣ 354]። አብሯት ሆኖ አብሯት የለም።

“ጌታ ነገረኝ” የሚለው አባባል ደራሲውን ጥያቄ ያጭርበታል። “ለኔ ለምንድነው አምላክ የሆነ ነገር የማይነግረኝ? እያልኩ እጨነቅ ነበር” [ገጽ 355]። ለዚህ ላስጨነቀው ጥያቄ ከመጽሐፍ ቅዱስና “ጀርመን አገር ከሚገኙ የጴንጤ ፓስተሮች” መልስ ይሻል። “በመጨረሻ የደረስኩበት መደምደሚያ የአምላክ ድምጽ የሚባለው፣ ‘ህሊና’ መሆኑን ነበር” [ገጽ 355]። ስለ መደምደሚያው እርግጠኛ አይመስልም [ገጽ 357]። እስቲ ደረስኩበት ስለሚለው የጠቀሳቸውን ሁለት ምንጮች እንመርምር። “መንፈሳችን ከመንፈሱ ጋር አንድ ላይ ሆነ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ አባባል ይህንኑ ያጠናክራል” [ገጽ 355]። እንዲህ የሚል ጥቅስ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። ምናልባት የሚቀራረብ ጥቅስ “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል” የሚለው ነው [ሮሜ 8:16]። ደራሲው ለጥያቄው መልስ ለመሻት ወደ ትክክለኛው ምንጭ ቢሄድም መልሱ ካሰበው ጋር ስላልገጠመ ለማሻሻል የተገደደ ይመስላል፤ ወይም ለማጣራት ሰንፎ ነው እንበል። ይህንን በማድረጉ የአገራችን የተማረው ክፍል ስለ ሃይማኖት ያለውን አስተሳሰብ ከሞላ ጎደል አንጸባርቋል። “የተማረው” ክፍል ሃይማኖት ጋ ሲደርስ ወይ ፈጽሞ ይርቃል፣ ላሰበው ተግባር ሊያውለው ይሻል፤ ሃይማኖት ለብቻው መያዝ ያለበት ነው ይላል። ወይም ጨርሶ ይንቃል፣ ያንቋሽሻል ወይም ያለ ጥያቄ ይቀበላል። የሚገርመው ይህ አመለካከት በወንጌል አማንያንም ዘንድ በብዛት መታየቱ ነው። ምክንያቱ ዞሮ ዞሮ የትምህርትና የሃይማኖት ተቋማት ቁንጽልና ወጥ እንጂ ሁለገብና ተፎካካሪ አመለካከት እንዲዳብር የማያበረታታ መርሆ ማራመዳቸው ነው። ሁለተኛውስ ምንጭ? “ክርስቲያኖች ‘ጌታ ነገረኝ’ የሚሉት እውነት እንዳልሆነ እናውቃለን” ይላል በጀርመን አገር የሚገኘው [ስሙን ያልጠቀሰው፣ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ] የጴንጤዎች ፓስተር [ገጽ 355]። ፓስተሩ ይህን ይበል ወይም ደራሲው አፉ ላይ ያርግለት እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ቀጥሎ፣ “ስህተት መሆኑን መግለጽ ግን አንችልም። ምክንያቱም ሰፊ ቁጥር ያላቸው አማኞቻችን በዚህ መንገድ ቀጥለዋል። ስህተቱን ማስተካከል ወይም ለማረም መሞከር መጠራጠርን ስለሚያስከትል ዝም ማለቱን መርጠናል …” [ገጽ 355-6]። ፓስተሩ እራሱ ያልገባው፣ የተጠራለትን እውነት ከማስተማር ይልቅ ለምቾቱ የተገዛ ተመሳስሎ መኖርን የመረጠ ዘመኑ ካፈላቸው መሃል መሆኑን ላፍታ አይጠረጥርም። ሊሰማ የሚሻውን መልስ ስለ ሰጠው ብቻ ሙሉ ለሙሉ አምኖ ይቀበላል። እውነቱን እያወቀ የሚያታልል ሰውን ምስክርነት ይዞ አደባባይ መውጣቱ ከፓስተሩ ይልቅ ደራሲውን ትዝብት ላይ ይጥለዋል። ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሌሎች ለንደን፣ አዲስ አበባ፣ ኬንያ፣ አዋሳ፣ አድዋ፣ አስመራ ከሚገኙ ጴንጤዎች ወይም ከጀርመናውያን ከግብጻውያን ከእንግሊዛውያን ከሆላንዳውያን ጴንጤዎች ጠይቆ ለማመሳከር ያደረገውን ጥረት አናይም። ከዚህ ድምዳሜ በመነሳት ህሊና ሰውን በጎን ከክፉ እንዲዳኝ ለሰው የተሰጠው ሳይሆን አምላክ ነው ይለናል። ትንሽ ቢጥር ኖሮ ስለ ህሊና ትክክሉን በተረዳ። ስለ በደል “የህሊና ጸጸት” አለ [1ኛ ሳሙኤል 25፡31]፤ “የህሊና ወቀሳ” አለ [ዮሐንስ 8፡9]፤ በጎ በማድረግ “መልካም ህሊና” አለ [የሐዋርያት ሥራ 23:1]፤ የ “ህሊና” ምስክር፣ ክስ፣ ማመካኘት አለ [ሮሜ 2:15]፤ ደካማ፣ በጎ የረከሰ “ህሊና” አለ [1ኛ ቆሮንቶስ 8፣ ቲቶ 1:15፣ ]። ህሊና ይቆሽሻል፣ ይሞታል፤ ይነጻል፣ ሕያው ይሆናል፤ ሰው ልክ ነው ብሎ የያዘው ልክ አለመሆኑን መረዳት ይጀምራል። “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ህሊናችሁን ያነጻ ይሆን? [ዕብራውያን 9፡14]። ህሊና አምላክ ለሰው የሰጠው እንጂ እራሱ አምላክ እንዳልሆነ በተገነዘበ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል” [ሮሜ 9፦1-2] ሲለን። ከሥላሴዎች አንዱ መንፈስ ቅዱስና የጳውሎስ ሕሊና የተለያዩ እንጂ አንድ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው። የጥሬ ቃሉን ፍቺ መመልከትም አንድ መፍትሔ ይሰጥ ነበር። አንድ ደራሲ የሚጠቀማቸውን ቃላት ትክክለኛ ትርጉም፣ በአንባቢው አእምሮ የሚያቀርቡትን አሳብ ቀድሞ መገንዘብ ይኖርበታል። ህሊና፦ ክፉና ደግን የሚያስለይ አእምሮ ወይም ልቡና። በሰሩት ጥፋት ወይም ስሕተተ የሚመጣ ጸጸት፣ የህሊና ወቀሳ ይባላል። ድምጽ ሳያሰሙ የሚደረግ ጸሎት፣ የህሊና ጸሎት ይባላል። የማያመዛዝን፣ የማያገናዝብ፣ ይሉኝታ የሌለው ህሊና ቢስ ይባላል [መዝገበ ቃላት 1993]።

የህሊናን መሠረተ ትርጉም ስቷልና፣ ለማስረጃነት “ጅብ ህሊና የለውም፣ ህሊናውን የገደለ ሰው ከጅብ ይመሳሰላል” ይለናል [ገጽ 357]። “እግዚአብሔር” “አላህ” “ዋቄፈታ” “ይሆዋ” የፈጣሪ ስሞች ቢሆኑም “ዞሮ ዞሮ መቀመጫ ቦታው ህሊናችን ውስጥ ነው። ወይም አምላክ ራሱ ህሊና ነው” [ገጽ 357]። እንግዲህ ከሳቱ አይቀር መሳት እንዲህ ነው። ከዚህ ከ “ህሊናዊው አምላክ” ጋር በሰፊው እንደሚያወጋ ይነግረናል። ሆኖም ይህ “የሚያነጋግረኝ መንፈስ የኢየሱስ ነው ለማለት ማረጋገጫ የለኝም” ይለናል። “ፍቅር በለጠ”ንና ዕቃዎቿን በማሰብ ይመስላል፣ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰበትን እንዲህ ሲል ገልጾታል፣ “አንዳንድ የማውቃቸው ጴንጤዎች ኢየሱስን ከአምላክነት ወደ ሎሌነት ዝቅ እንዳደረጉት ታዝቤ ነበር። ‘ኢየሱስ አገልጋይ ነው’ የሚለውን አባባል በትክክል ባለመገንዘብ ተላላኪያቸው አድርገውታል። ስለ ቁሳቁሶች ዋጋ ለአማኞቹ ለመንገር የሚሯሯጥ አምላክ በርግጥም የንግድ ወኪል እንጂ አምላክ ሊባል አይችልም። ስለሆነም እኔ በምናብ የምስለው አምላክ ከዚህ ዓይነቱ አምላክ ፍጹም የተለየ ነበር” [ገጽ 357]። ይህን የሚያነብቡ አማንያን፣ በተለይ የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጽንኦት እነዚህን የጽድቅ ክሶች መመርመርና መመዘን ይኖርባቸዋል። በአንጻሩ፣ ደራሲው ልኩን አውቆ ላለመቀበል በጥቂቶች ውስጥ ባየው ድክመት እያሳበበና እያመካኘስ ቢሆን! “እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ [ሮሜ 2:15]።”

ህሊናና አምላክ አንድ ናቸው ብሎናልና፣ ወደ ኋላ ተመልሶ “ወደ ሃይማኖት ያዘነበለ” ታናሽ ወንድሙ አባቱን የጠየቀውን ጥያቄ ያነሳልናል። አባቱ የመለሱለት አጥጋቢ አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን የማይመስል እንደ ሆነ ሊጠቁመን ሞክሯል [ገጽ359]። ቢሆንም ደራሲው በገባው መጠን የጸሎትን አስፈላጊነትና የፈጣሪን መንገድ ይበልጥ ለማወቅ የሚሻ ይመስላል። ከዚህ ክፍል ልብ የሚነካና የደራሲውን ስብእና እርቃን ያወጣ ነገር ቢኖር የሚከተለው ነው፣ “ሆላንድ ከገባሁ በኋላ ግን በተለይ በበጋው ወራት የሳምንቱ ማብቂያ ላይ በራሴ መንገድ ጸሎት ማድረስ ጀመርኩ። በምዕራብ ዞይስ መውጫ ከወንዙ ዳርቻ አንዲት ሰው ሰራሽ ኮረብታ አለች። አልፎ አልፎ ወደ ኮረብታዋ ሄጄ ጫፉ ላይ ቁጭ በማለት ጸሎት አደርሳለሁ” [ገጽ 359]። ከላይ ህሊናና አምላክ አንድ ናቸው ሲለን የነበረውን ዘንግቶት ይመስላል፣ “የፈጠረኝ አንድ እውቀት ያለው ሃያል አምላክ መኖሩን አምናለሁ” ይለናል [ገጽ 359]። ህሊናዬ ፈጠረኝ ማለቱ ይመስላል።

ስለ “ፈጣሪ” በተለይ ተጽእኖ አደረጉብኝ ከሚላቸው መጻሕፍት ተነስቶ ጥቂት ሊያስረዳን ሞክሯል። ሆኖም ብዙ ሳይቆይ “ፈጣሪ” ነው ያለን በራሱ አምሳል የተፈጠረ፣ የአሳቡና የምኞቱ ውጤት እንደ ሆነ እንመለከታለን። የጸሎቱ ቀጥተኛነትና ግልጽነት ጸሎትን ለሚያወሳስቡ ወይም እግዚአብሔር ካልጮኹ አይሰማም ብለው ለሚያስቡ ጥሩ እርምት ይሆናል።
“ጌታ ሆይ፣ ይኸው መጣሁ? ብዬ ጸሎቴን ጀመርኩ።
አምላክ ምናባዊ መልስ ሰጠኝ፣ “ሰውዬው! እንዴት ሰነበትክ?”
“መሰንበቻዬን መች ጠፍቶህ? ያው በር ዘግቶ መጻፍ ነው፤ ማንበብ ነው፣ ሲደብረኝ ወጣ እላለሁ፣ እንዲሁ ቀኑ ያልፋል።” ["ፍቅር በለጠ"ን "ትርፍ ጊዜሽን በምን ታሳልፊያለሽ?" ሲላት "እንዴት እንደሚያልፍ እንኳ አላውቀውም። ሰኞ ብሎ አርብ ነው። በጋ እያልክ በረዶ ይመጣል" ብላው ነበር [ገጽ 352]። ሁለቱም የስደት ኑሮን መራራ ገጽታ፣ ብቸኝነትን አንጀት በሚበላ ቃል ይገልጹታል።
“ፈተና መውደቅ እያበዛህ ነው፣ ምን ይሻልሃል?”
“ማን ፈተናህን ያልፋል? እንኳን ያንተን የሰዎችን ፈተናም ማለፍ ከብዶኛል።”
“ምን ልርዳህ ታዲያ ለዛሬ?”
“አይ እንድናወጋ ብዬ ነው የመጣሁት። ጊዜ ካለህ ስላንተ አንድ ነገር ላጫውትህ።”

ደራሲው ምንጩን ሲጠቅስ አሻሽሎ፣ ሳያጣራና በቸልተኛነት አመቻችቶ ነው ወዳልነው ነጥብ እንመለስ።
• “መንፈሳችን ከመንፈሱ ጋር አንድ ላይ ሆነ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ አባባል ይህንኑ ያጠናክራል” ይለናል [ገጽ 355]፤ ጥቅሱ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም።
• ስሙን ያልጠቀሰው የጴንጤዎች ፓስተር “ጌታ ተናገረኝ” የሚለው አባባል “ስህተት መሆኑን መግለጽ ግን አንችልም…” [ገጽ 355-6] የሚለው በዶስቶየቪስኪ “ብራዘርስ ካራማዞፍ” ላይ ሚትያና አልዮሻ ስለ ራኪቲን ካወጉት ጋር ቃል በቃል ይመሳሰላል።
• ለአምላክ፣ ያሳቀኝን ነገር ልንገርህ፣ የጥንት እንግሊዞች ወደ ዘመቻ ሲሄዱ “አምላክ ሆይ! – በርግጥ አምላክ ከሆንክ / ነፍሴን ተቀበላት! -በርግጥም ነፍስ ካለኝ” ይላሉ ይለዋል [ገጽ 360]። ጸሎቱና “ፈጣሪም በጣም ሳቀ” የሚለው ቃል በቃል ዊልያም ኪንግ በ 1819 [በአውሮጳ] “ፖሊቲካል ኤንድ ሊተረሪ አኔክዶትስ ኦፍ ሂስ ኦውን ታይምስ ብሎ ገጽ 7 – 9 ላይ ካሰፈረው ጋር ይመሳሰላል። እራት ግብዣ ላይ፣ በውጊያ ሰዓት በጣም አጭሩ ጸሎት የቱ ነው ሲባባሉ፣ ፌዙን ተናገረ የሚባለው ሰር ዊልያም ዊንደም ነው። ከፌዙ በኋላ “ሁሉም ሳቁ” ይላል። በሥፍራው የነበረ ጳጳስ አተንበሪ በግሳጼ መልክ፣ አጭሩ ጸሎት “አምላክ ሆይ! በውጊያ ሰዓት እኔ ብረሳህ አንተ ግን አትርሳኝ” ነው ብሎ እርምት መስጠቱን ደራሲ ተስፋዬ አይነግረንም።
• ጸሎቱን ሲቀጥል፣ “ጠይቁ! ብለሃል። ምን እንድንጠይቅህ ትጠብቃለህ?” አምላክ ሲመልስ፣ “ጠይቁ ማለቴ ዳቦ አይደለም። አዳምና ሄዋን ከገነት ሲባረሩ ዳቦ በነጻ የማግኘቱ ነገር አብቅቶለታል” ይለናል [ገጽ 362]። ደራሲው አሁንም በግምት እንጂ አጣርቶ አይደለም፦ “የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ” የሚለው አትሥሩ ሳይሆን፤ ከመጨነቅ ይልቅ ታመኑ፤ አእዋፍን የሚመግበው የሰማይ አባታችሁ ስለ እናንተ ያስባል ማለቱ ነው። አዳምና ሄዋንን በገነት ሲያኖራቸው እንዲሠሩ እንጂ በነጻ ዳቦ እንዲበሉ አይደለም፤ ሥራን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፤ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው [ዘፍጥረት 2:15]” ይላልና።
• እንግሊዛዊው ሶመርሴት ሞም አምላክ “ኮመን ሴንስ የለውም” ብሏል? [ገጽ 362] አላለም። ያለው “በእግዚአብሔር ማመን የኮመን ሴንስ ጉዳይ አይደለም” ነው። ሶመርሴት ይህን ያለው እምነትን ለማንቋሸሽ ነው፤ እምነት የስሜት ጉዳይ እንጂ የማስተዋል ጉዳይ አይደለም ለማለት ነው።
• እግዚአብሔርን በምናቡ፣ ስለ መኖርህ “የማያሻማ ምልክት ሰጥተህ ለምን አትገላግለንም?” [ገጽ362] ይለዋል። ለምልክትማ ኢየሱስን ልኮ ብዙዎች አላመኑበትም። በዐይናቸው ፊት ሙታንን አስነሳ፤ ዕውራንን አበራ፤ በአጋንንት የታሠሩትን ነጻ አወጣ፣ ወዘተ። “ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ …መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው [ዮሐንስ ወንጌል 1፡1-18]።” ደራሲው የጠየቀው ጥያቄ ያረጀ ነው። ከኢየሱስ ደቀመዛሙርት ፊሊጶስ “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊሊጶስ፣ ይህን ያህል ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፣ እንዴትስ አብን አሳየን ትላለህ?” አለው [ዮሐንስ 14፡6-9]። መረጃ ቀርቦለት ላለማመን የወሰነን መርዳት አይቻልም። የቀረበውን መረጃ መቀበል የአስተሳሰብንና የሕይወትን አቅጣጫ ስለሚያስቀይር አንዳንዶች ፈቃደኛ አይሆኑም። የሕይወትን ትርጉም ለማወቅ የሚሻውን ያህል፤ ደራሲው ሌሎች ብዙ ብዙ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ አንዱን ብቻ ሳይጠይቅ እንደ ቀረ እንመለከታለን። ያም ጥያቄ “ኢየሱስ ማነው?” የሚለው ነው። ኢየሱስ ስለ ራሱ ምን ብሏል? አብረውት የኖሩ፣ ያዩትና የሰሙትስ? ቅድም እንዳልነው ጥያቄ መጠየቅ ብቻውን አይበቃም፤ የቀረቡ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመርመርን ይጠይቃል። ከሌሎች የሕይወት ልምድ ምስክርነት መሻትን ይጠይቃል። ከዚህ ባላነሰ ደግሞ እውነቱን ለማወቅ ጥማቱና ፈቃደኛነት ሊታከልበት ይገባል።
• [ረቂቅ] “እውቀት የፈጠረ አንድ ሌላ አዋቂ የግድ መኖር አለበት … በርግጥም አንድ ኃያል መሃንዲስ አለ [ገጽ 363]።” ይህ “አንድ ኃይል” ከርሱ በስተውጭ ነው። ይህን አምላክ ከራሱ ህሊና ለይቶ ማየት አልቻለም። በምናቡ እንዳስረዳን ራሱን እንደ አምላክ በመቁጠር ነው። ይህ ዓይነቱ አምላክ ፈጣሪ ሳይሆን ፍጡር ነው። የሰው እጅ ሥራ ወይም ጣኦት ነው።
• ዶስቶየቭስኪስ “አምላክን እኛ ፈጠርነው እንጂ እሱ አልፈጠረንም” ብሏል? [ገጽ 364]። ቅድም በጠቀስነው “ብራዘርስ ካራማዞፍ” ላይ [ክፍል 4፣ ንኡስ ክፍል 11፣ ምዕራፍ 4] የተጠቀሰው ግን “እግዚአብሔር ከሌለ ሰውን የሚያግደው ምንም የለም” የሚል ነው። ተናጋሪው ከሃዲው ኢቫን ሲሆን፣ ሰው ማለቂያ ከሌለው ጥፋት እንዲጠበቅ የእግዚአብሔር መኖር አስፈላጊ ነው ማለቱ ነው።
• “አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሕያው የሆነ ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ብቻ ነው” የሚለውን ጥቅስ ወስዶ ይመስላል እግዚአብሔርን “ቁጫጭ” አልከኝ ይላል። “ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ። እጅ የለውም ይላልን? … ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው። የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ [ኢሳይያስ 45:9፤ ኤርምያስ 18:3-6]።” ያዛባው ትርጉም ሳያንስ፣ ጨምሮ “ቁጫጭና ጀበና” አልከኝ ወደ ማለት ይዛመታል። ቀጥሎ፣ “እኛ ላንተ ማጣፈጫ ቃሪያና ቲማቲም ነን?” ብሎ የተነሳበትን ቁምነገር ወደ ተራ ሹፈት ያወርደዋል። በዚህም እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ክቡር አድርጎ እንደ ፈጠረው፣ ሰው ባለመታዘዙ ከክብሩ እንደ ተዋረደ፣ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ወደ ክብሩ የሚመለስበት መንገድ እንደ ተከፈተ የሚያስተምረውን ዋነኛ ትምህርት ዘንግቶትና ስቶት እናያለን።
• ፈላስፋው ኒቸስ “እግዚአብሔርን ወደ ምድር ያመጣው ፍርሃት ነው” ብሏል? [ገጽ 365]። ኒቸ ያለው ክርስትናን መጣል ክርስቲያናዊ ስነ ምግባርን መጣል ነው፤ ያም ወደ አለመተማመን፣ ወደ ጥፋት፣ ብርቱው ደካማውን ወደ መረጋገጥ ያመራል ነው። ኒቸ “እግዚአብሔር ሞቷል” ብሎ ያወጀው ነው። በአውሮጳ አቆጣጠር በ1900 ዓ.ም አብዶ ሞቷል። ሌሎች እንደ ታዘቡት የሞተው ኒቸ እንጂ፤ ሞተ ያለው እግዚአብሔርማ ዛሬም በመላው ዓለም ሕዝቦች ዘንድ ህያው ሆኖ ይታወቃል።

ሌሎች ያላሉትን ወይም ያሉትን በሚፈልገው መንገድ አሻሽሎ ማቅረቡ ደራሲው የራሱን ድምጽ ከመስማት አልፎ አሳቡን ላመነጩትና ለአንባቢዎቹ ግድ እንደሌለው ያሳያል። የዚህ ትርፉ አለመታመን ነው። እርግጥ ደራሲው ፈላስፋ ወይም የስነመለኮት ሊቅ አይደለም። ጥናትና ምርምር የሚጠይቀውን መስፈርት አላሟላም። አንድ ሰው በሁሉም መስክ ሊጠበብ ስለማይችል ስላልተረዳቸው ጉዳዮች ከተረዱት ዋነኞች አመስግኖ መዋስ ያለ ነገር ነው። ከሚያነባቸው መጻሕፍት እየቀነጫጨበ፣ እየጣጣፈ የሚፈልገውን አሳብ ብቻ ወስዶ የማይፈልገውን ወደ ጎን አድርጎ ያነጋግረናል። የእምነትን [የክርስትናን] አስተምህሮ በተመለከተ ከታመኑ ምንጮች በቅድሚያ ጠንቅቆ መረዳት ለማስረዳትና ለመሞገት ቁልፍ ነው። በ “የስደተኛው ማስታወሻ” ደራሲው ራሱን ሆኖ እንጂ በፈጠራቸው ገጸ ባህርያት በኩል እያነጋገረን እንዳልሆነ ገልጾልናል። ራሱን ያቀረበልን መንፈሳዊ እውነቶችን ለመረዳት በሚጠይቅ ሰው ተመስሎ ነው። ሐቁ ግን የምንሰማው ድምጽ የራሱ ሳይሆን የሌሎች ድምጽ ነው። በሌላ አነጋገር፣ የቀረቡልን ጥያቄዎች የጋዜጠኛ ተስፋዬ ጥያቄዎች አይመስሉም፤ በሌሎች ተመስሎ ሊያነጋግረን ለምን እንደ መረጠ ግልጽ አይደለም። ለምሳሌ፣ ከአምላክ ጋር የተነጋገረባቸው ምናቦች ከ “ሁሉ አምላክ ነው” አራማጁ አሜሪካዊ ኒል ዶናልድ ዎልሽ “ኮንቨርሴሽንስ ዊዝ ጎድ” ላይ የተወሰዱ ናቸው [ወርልድትራከር ዶት ኦርግ፣ በአውሮጳ 1995፣ ለምሳሌ ገጽ 11-13 ይመልከቱ]። ከላይ “ማስታወሻዎቹ እውነተኛ ታሪኮች፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ትረካዎች ናቸው” ብሎን ነበር [ገጽ 5-6]። በ”ፍቅር በለጠ” እና “ህሊና እንደ አምላክ” የተካተቱት መረጃዎች ግን የተዋሳቸው እንደ ሆኑ አይተናል። የመጣጣፍ ችግር፣ አንድን አሳብ ሲዋስ የተዋሰበትን ጊዜና ሥፍራ አያስታውስም፤ ላዋሰው የሚገባውን ምስጋና ሳይሰጥ የራስ አድርጎ ማቅረቡ ላይ ነው።

የሞትና የፍርሃትን ጥያቄ ሲያነሳ፣ ጥያቄውን ለመመለስ የሚያስፈልገውን መረጃ አይሰበስብም። እግዚአብሔርን “ለምን ታስፈራራናለህ?” ሲለው [ገጽ 362] የአዳምና የሄዋንን ፍርሃትና መደበቅ ሳያጤን ነው፤ “አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም። እግዚአብሔርም አለው። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? [ዘፍጥረት 3:8-10]።” አዳምና ሄዋን እግዚአብሔርን ስላልታዘዙ ፈሩ፤ ፍርሃት የአለመታዘዝ ኃጢአት ውጤት ነው። እግዚአብሔርን አታስፈልገኝም የማለት ውጤት ነው። እግዚአብሔር የሚያስፈራራ የሚመስለው ኃጢአት በመካከል ስለ ገባ ነው፤ በሰውና በአምላኩ መካከል ርቀትና ባዳነት ስለ ተፈጠረ ነው። ለቀረቡትማ ፍቅር እንጂ ፍርሃት የለባቸውም።

እግዚአብሔር የሚሸሸውን ፈልጎ የሚያገኝ አምላክ ነው። የሰው ልጅ [ኢየሱስ] የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና [ሉቃስ 19:10]። በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እግዚአብሔር ቅርበቱን መሐሪነቱን ስለ ኃጢአት ይቅርታ አድራጊነቱን ገልጿል። የሰው ድርሻ፣ ይቅር በለኝ፣ ሰላምህን ሕይወትህን አጎናጽፈኝ ማለት ነው። የክርስትና መሠረቱ ይኸው ነው። ደራሲው ስላላጣራ የእግዚአብሔርን ባህርይ አዛብቶት እናያለን። ላለማመንና ለመንቀፍ መብቱ ቢሆንም የሌላውን አቋም ማዛባት ግን መብቱ አይሆንም፤ ያስጠይቃል፤ መታመንን ይነሳል።

ጥቂት ስለ ተስፋዬ ገብረአብና ሥራዎቹ። በመጀመሪያ፣ ይህ ግለሰብ ስለሻው ነገር የመጻፍ፣ ስለ ማንነት ጥያቄ የማንሳት መብቱ ሊከበርለት ይገባል። የራሳችን መብት እንዲከበርልን የምንሻውን ያህል የሌላውን የማክበር ግዴታ አለብን። የሻውን መጻፉ ለመማማር እንደ ጠቀመ መረሳት የለበትም። ሁለተኛ፣ ተስፋዬ በቅድሚያ የጋዜጠኛ ፖለቲከኛ ነው። የጋዜጠኛ ፖለቲከኛ ድርጊቱን ሳያዛባ ዘግቦ ዳኝነቱን ለአንባቢ እንደ መተው ዘገባውን ጨምሮበትና ቀንሶለት የራሱን አሳብ ማስፈጸም ይሻል። ከአሳቡ ጋር የማይስማማውን አይታገስም፣ ይወርፋል። የሚጽፋቸው በጥርጣሬ ለመታየታቸው፤ ከሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ባላነሰ ደራሲው ራሱ መነጋገሪያ ለመሆኑ ይህ አንዱና ዋነኛው ምክንያት ነው። ሦስተኛ፣ አሳቡን ቀላልና ግልጽ በሆነ መንገድ የመግለጽ ችሎታ አለው። ያም ማለት በሚጽፋቸው ጽሑፎች የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ለሚያታግለንና ለምንጋራው ምድራዊ ኑሮ አዲስ ራእይ በመፈንጠቅ ስብእናችንን ያጸናሉ ወይም ያንጻሉ ማለት አይደለም። ይልቅ የምንገኝበትን ዘመን ከመዋጀት ይልቅ ብሶቶችን እየለቃቀመ በመቀስቀስ ወደ ኋላ ሲመልሰን በብዙዎች ተስተውሏል። ካለፈው ስሕተት መማር ስሕተቱ እንዳይደገም ይጠቅማል ቢባልም ብሶትን ማባባስ ግን ወደ ኋላ ከመመለስና ዛሬን ከማባከን በተቀር ፋይዳ አይኖረውም። የስድሳ ስድስቱ አብዮት ፊውዳሊዝም ኢምፔሪያሊዝም ይህን ያን አረገን እያለ እንዳንጠይቅ አፍኖ ዘመናችንን እንደ ዘረፈን ሁሉ። ዛሬም ይህ ጎሳ ያ ጎሳ እያልን በጋራ ልንጋፈጣቸው የሚገቡንን ችላ እንዳልን ሁሉ ማለት ነው። አራተኛ፣ የጋዜጠኛ ፖለቲከኛነቱ ለስነ ጽሑፍ ሊያበረክተው የሚችለውን ድርሻ እንዳያብብ አዘግይቶበታል። እውነት የምትገለጠው መንገድ ለሚለቁላት ትሑታን እንጂ ለሚጋፏት አይደለም።

ስለ ሰው ልጅና ስለ ራሱ ማንነትና መብት ሲጽፍ በዘር ለያይቶ ነው። በጎሣ ፖለቲካ ላይ ማተኮሩ ደግሞ ሳያስፈልግ ቃላተኛ አድርጎታል። ለምሳሌ፤ አሁን ወደሚኖርበት ኔዘርላንድስ እንደ ደረሰ ወደ ስደተኛ ካምፕ ያደረገውን የእግር ጉዞ “መንገዱ ላይ ሰው አይታይም። መኪና የለም” ሲል ገልጾታል፤ አጭርም ቢሆን ምን ማለቱ እንደ ሆነ ለማንም ግልጽ ነው ["ስደተኛው" ገጽ 9]። ደራሲው ግን ሳያበቃ “እንደ አማራ አገር እረኞች ላሟ ርቃ ስትሄድ፣ ‘ሃይ! ነይ ተመለሽ ቡሬ’ የሚል ዜማዊ ድምፅ በርቀት አይሰማም። አካባቢው እንደ ገልማ ቃሉ ፀጥ ያለ ነው” ብሎ በማራዘም ይዞት በመጣው የጎሣ መነጽር ያስቃኘናል። ለዚያውም ከአውሮጳ ሕዝቦችንና አስተሳሰቦችን በማስተናገድ በሰብአዊነት ተምሳሌትነት በምትታወቅ በኔዘርላንድስ! ስለዚሁ አቋሙ ተጠይቆ “ስለ ዘር መነጋገር ወቅቱ ያመጣው አጀንዳ ነው” ብሏል["ላይፍ" መጽሔት 2006]። በሌላ አነጋገር፣ ደራሲው በደርግ ዘመንና አሁን በሚገዛው መንግሥት ውስጥ የነበረው ሚና ተገቢ ነው እያለን ነው። አቤ ጉበኛ “አልወለድም” ን ሀዲስ “ፍቅር እስከ መቃብር” ን ሲጽፉ የተገኙበትን ዘመን ብቻ ማስተጋባታቸው ሳይሆን ከዚያ በወጣ አዲስ ራእይ መፈንጠቃቸው ነው። ደጋግሞ የሚያነሳው በአሉ ግርማ ሕይወቱን ያጣበት ምክንያት የተዘነጋው ይመስላል። እርሱ ግን በደርግ፣ ከዚያም “ተራሮችን ባንቀጠቀጠ ትውልድ” ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ሲሠራ ከቆየ በኋላ፣ውስጥ አዋቂዎች እንደሚነግሩን በሌሎች ላይ የደረሰውን እስርና መንገላታት ሳያይ በመንግሥት እውቅና ውጭ አገር ተደላድሎ መኖር ከጀመረ አሁን 14 ዓመታት ሆኖታል። በስደት መጽሐፍ ጽፎ ማሳተምና ከአገር አገር መጓዝ ችሏል። አምስተኛ፣ ከአገር ርቆ መኖሩ ደግሞ በአጻጻፉ ላይ የራሱ የሆነ ጥቁር ጥላ መጣል ጀምሯል። ያም ከሚጽፍለት ሕዝብ መሃል አለመገኘት በቋንቋውና በአስተሳሰቡ ላይ ለውጥ እያመጣ፣ የእንግሊዞችን አባባል በአማርኛ ለመጻፍ ተገድዷል። ለምሳሌ፣
[ገጽ 9]፣ “የትሮፒካል የአየር ጠባይ ስር ተወልጄ ያደግሁ” [I was born under a tropical climate]
“ጭንቅላታቸውን ተናግረው አያውቅም” [never spoke his mind]
[ገጽ 396]፣ “እባክህ ብቻዬን ተወኝ” [please leave me alone]
[ገጽ 365]፣ የልብህን ድምጽ አዳምጥ [listen to your heart]

ይህንኑ በመገንዘብ ይመስላል፣ ለ “ላይፍ” በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ “እንደ በፊቱ ለአማርኛ ጽሑፍ ቅርብ አይደለሁም – የሚታተሙ መጻሕፍትን እንደ ልቤ አላገኝም” ይልና ቀጥሎ፤ “አማርኛ ጠላት ስለ በዛበት ስነ ጽሑፍም ባለቤት አጥቷል” ይለናል [ቅጽ 7፣ ቁ. 116/2006]። አምሃ አስፋው ደግሞ ኢትዮጵያ ተመላልሶ የተገነዘበው አማርኛ ስነ ጽሑፍ እያበበ መምጣቱን ነው [ኢትዮሚድያ መጋቢት/2006 ቅጽ ይመልከቱ]። በተጨማሪ ሱቢ2000 ዶት ኮም ድረ ገጽ በ2000፣ 2001 እና 2002 ዓ.ም በአማርኛ 226 መጻሕፍትና 148 ፊልሞች አገር ውስጥ መታተማቸውን የዘገበው ማረጋገጫ ይሆነናል።

በመጨረሻ፣ ተስፋዬ ከበአሉ ግርማና ደጋግሞ ከሚጠራቸው ደራስያን ጥላ ሥር ወጥቶ የራሱን ፈር መቅደድ አለመቻሉ ሌላው ጉዳይ ነው [ዛሬም እንኳ "ኦሮማይ በአሉ" ይላል፣ ም. 23]። በ “የስደተኛው” 39ኙም ምዕራፎች ውስጥ ከ39 የማያንሱ ደራስያን ተጠቅሰዋል። የተስፋዬ መጽሐፎች የኢትዮጵያ ደራስያን ስም ማውጫ እስኪመስሉ ድረስ ስምና ሥራቸውን ቆንጽሎ አቅርቦልናል፤ ደራሲያኑ ከመተቸት ለመታቀባቸው አንዱ ምክንያት መሞገሳቸው ይሆን? ጊዜ ለመሻማት ጥቂት ምሳሌዎችን እንጥቀስ። በአሉ “ደራሲው” ላለው ተስፋዬ “የደራሲው ማስታወሻ” ብሏል። ልዩነቱ በአሉ ስለ ሌላ ሰው [ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር] ሲጽፍ ተስፋዬ ግን የጻፈው ስለ ራሱ ነው። በአሉ ስለ “ሮማን ኀለተወርቅ” [ኦሮማይ፣ 2ኛ እትም፣ ገጽ 1-13] ሲያወሳ ተስፋዬ ስለ “ፍቅር በለጠ” ጽፏል [ም.33]። ሮማንና ፍቅር ሁለቱም ረጅም ጠጉር አላቸው፤ ሁለቱም ጴንጤዎች ናቸው፤ ሁለቱም ወንድ ጓደኞቻቸውን ጴንጤ ለማድረግ ይሞክራሉ፤ ሁለቱም ስለ ፖለቲካና ኃይማኖት ያወሳሉ፤ ሁለቱም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ ፈውስና ጸሎት ይወያያሉ። ከላይ ስለ እምነቱ ሲጽፍ “ተጽእኖ ያደረጉብኝ በርካታ መጻሕፍት አሉ” ብሎን ነበር [ገጽ 359]። ይህ የአሳብ መመሳሰል ግን አጋጣሚ ብቻ ሊሆን አይችልም። ለማንኛውም፣ የበአሉ ተጽዕኖ ይኸና ጉልህ ሆኖ ሳለ ለ “ላይፍ” መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ በርሱ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት የሩሲያ ወርቃማ ዘመን ደራሲያን እንደ ሆኑ በመግለጽ ርቀት ለመፍጠር ሞክሯል።

ታዳጊ ደራሲ ከነባሩ ልምድና ስልት መቅዳት ያለ ነገር ነው። ቼኾቭ ጀማሪ ጸሐፊ በነበረበት ወቅት ለምሳሌ ከርሱ የገነኑት የጻፉትን አጫጭር ታሪኮች መላልሶ ቃል በቃል እየጻፈ ስልታቸውን ያጠና ነበር። ኋላ ግን ከራሱ አልፎ “ቼኾቫዊ” ሊባል የቻለ ስም ለራሱ ሊያንጽ ችሏል። ተስፋዬን ብዙ ግፊቶች ተጭነውታል። አንዱ እያረጁና ቦታና ዘመን እያራራቃቸው ከሚገኙ ከቢሾፍቱ ትዝታዎችና ሕዝብ አውቆ ከጨረሳቸው የመንግሥት “ምሥጢሮች” እስር መውጣት ነው። ሌላው በስደት ምድር በስደተኛው ማኅበረሰብ ዘንድ መደመጥና መታመን መቻል ነው። ቋንቋ ዝብርቅርቁ በወጣበት ምድር ማለት ነው። ለመታመን በመረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ብዙ ጥንቃቄ ማስፈለጉን መረዳት ነው። ውጭ አገር አንድን መረጃ ከምንጩ ያለ ፈቃድ መውሰድ ወይም የደራሲን አቋም ማዛባት እንደሚያስጠይቅ መረዳት ነው። ተስፋዬን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከነባርና በሕይወት ካሉ ኢትዮጵያውያን ጸሐፍት ደረጃ ማወዳደር ሌላ ያልታሰበ ጫና ይፈጥርበታል። ደግነቱ፣ ይህን በመረዳት ይመስላል፣ ራሱ ተስፋዬ እንዲህ ብሎናል፦ “ከበአሉ ግርማ እና ከብርሃኑ ዘርይሁን ጋር እያወዳደሩኝ ሲፅፉ ግን በውነቱ ተሳቅቄያለሁ። ትሁት ለመሆን ብዬ አይደለም። በብዙ መለኪያዎች ብርሃኑና በአሉ የተሟሉና የተዋጣላቸው ደራስያን ነበሩ። እኔ ራሴን ከነሱ ተርታ የማስቀመጥ ድፍረት የለኝም። ጀማሪ ነኝ። ወደፊት ጥሩ ጥሩ የስነፅሁፍ ስራዎችን ለመስራት አሳብ አለኝ።” [ኢትዮፎረም ቃለ ምልልስ፣ የካቲት 19/2001]። አሁን የቀረው ጥሩ የስነ ጽሑፍ ስራዎችን መስራት ነው። ለዚህም ሦስት አማራጮች አሉት። በእንግሊዝኛ መጻፍ፣ በአማርኛ መጻፍ፣ በኦሮሚኛ መጻፍ። ስለ እንግሊዝኛው ከዚህ ቀደም ያስነበበው ጽሑፍ ስለሌለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። የኦሮምኛ ዕውቀቱ በቂ አለመሆኑን የዐይነ ስወሩ አዝማሪ የገቢሳ ሙለታን ዘፈን ተርጉሞ አሳይቶናል [እግዚአብሔር እንጂ ጎሬ አይደለም፤ ጠመንጃ አንግቷል እንጂ አልደቀነም፤ ጸሐፊ እንጂ ትኋን አይደለም፣ ወዘተ፤ "የስደተኛው ማስታወሻ" ምዕራፍ 15፣ ገጽ182]። በተካነበት አማርኛ ለመቀጠልና ስነ ጽሑፋዊ ጥልቀት ለመጎናጸፍ ራሱን ካሰረበት “ፖለቲካ ብቻ” አመለካከትና መረጃቸው ከሳሳ “ግለት ብቻ” ሥራዎች መላቀቅ ይኖርበታል። ለዚህም የዕውቅ ደራሲያንን ሥራ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ መመለስ መነሻ ሊሆነው ይችላል።

↧

አቶ ብርሃኑ በርሀ የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀ መንበር በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ ለ ሎሚ መፅሄት የሰጡት ቃለ መጠይቅ

↧

ለአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት (አስቸኳይ ጥሪ) –አሰፋ ቤርሳሞ

በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ ነኝ። በተለይም ላለፉት አንድ አመት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ፣ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች አንድነት ሲያደርጋቸው የነበሩት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ከሌላው አንጋፋ ድርጅት መኢአድ ጋር ያቀደው ዉህደት በእጁጉ የኢትዮጵያን ህዝብ ያስደሰቱና ቀልብ የሳቡ መሆናቸዉን መቼም እናንተዉ ሳታወቁት አይቀርም።

በአመራሮች መካከል፣ ዉይይቶች ተደርጎ፣ ቅድመ ዉህደት ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ የውህደት አመቻች ኮሚቴም ተቋቁሞ ሥራዉን በተሳካ ሁኔታ እየከናወነ ይገኛል። የተቃዋሚዎችን መሰባሰብ የማይወደው ወያኔ/ኢሕአዴግ ፣ ምርጫ ቦርድን ተጠቅሞ፣ «ያልተሟላ ነገር አለ» በማለት፣ የዉህደት ሂደቱን ለጊዜው ለማጨናገፍ ሞከሯል።

ምርጫ ቦርድ በእጁ ያለው ወረቀት ነው። የዘነጋው ነገር ቢኖር ግን፣ አገዛዙ እውቅና ሰጠም አልሰጠም፣ መኢአዶች እና አንድነቶች በተግባር መዋሃዳቸዉን ነው። የመኢአድ እና የአንድነት አባላት በዞን እና ወረዳ ደረጃ ተዋህደው አብረው መስራት ከጀመሩ ቆይተዋል። አብረው ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት። አብረው ነው የሚታሰሩትና የሚደበደቡት። በመካከላቸው ልዩለት የለም። የዉህደት እንቅስቃሴ በቅንጅት ጊዜ ሊደረግ እንደነበረው፣ ከላይ ወደ ታች ሳይሆን፣ ከታች ወደ ላይ ነው። ለዚህም ነው ቅንጅትን ማፍረስ እንደተቻለው፣ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ያለውን ግንኙነት ማፍረስ በቀላሉ የማይቻለው።

ሁኔታው ይህ ሆኖ እያለ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት፣ አሳፋሪዉ የምርጫ ቦርድ ዉሳኔ በተሰማ በቀናት ዉስጥ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን ምርጫ ቦርድ ላይ ጫና ማሳደር ሲገባው፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፍርሷል። ይሀ በጣም ትልቅ ስህተት ነው ብዬ አምናለሁ።

የዉህደት አመቻች ኮሚቴ ጥሩ ሥራ ከሰሩ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ ነው። በመኢአድ እና በምርጫ ቦርድ በኩል ያለውን ችግር መፍታት የሚቻልበትን አማራጭ ሐሳቦችን በማውጣትና በማውረድ ላይ ይገኝ ነበር። ይህ ኮሚቴ እንዲፈርስ ዉሳኔ ሲወሰን፣ ከመኢአዶች ጋር ምክክር አልተደረገም። በመኢአዶች ዘንድ ሊያስከትል የሚችለውን ቅሬታ ከግምት አላስገባም። ዉሳኔው፣ ሊዋሃዱ በተዘጋጁ ወገኖች መካከል ቀዳዳ የሚከፍት ጠቃሚ ያልሆነ ዉሳኔ ነው።

መኢአድ ከወያኔ ጋር እየተፋጠጠ ባለበት ወቅት፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴዉን ማፍረስ፣ በተግባር ምርጫ ቦርድ የጀመረውን ይዞ እንደመሮጥና፣ አገዛዙን እንደማስደስት ተደርጎ በአንዳንዶች ቢወሰድ፣ ተሳስተዋል ብሎ መከራከር ያዳግታል። የምክር ቤቱን፣ በተለይም ደግሞ የሊቀመንበሩን ተቀባይነት በእጁጉ የሚሸረሽር ነው።

የውህደት አመቻች ኮሚቴ መፍረሱ በተጨማሪ፣ ከዚሁ ከአንድነት ጋር በተገናኘ፣ ሌላ ያሳዘነኝ ነገር አለ። ከአንድነት የሥራ አስፈጻሚ አባላት አምስቱ ፣ ምክትል ሊቀመንበር ተክሌ በቀለ፣ ምክትል ሊቀመንበር በላይ ፍቃዱ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ተፈራ፣ ኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ ዳዊት አስራደ፣ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊው ሰለሞን ስዩም፣ እንዲሁም ገንዘብ ያዡና የዉህደት ኮሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ጸጋዬ አላምረው «ከሊቀመንበሩ ጋር መስራት ስለማንችል፣ ሊቀመንበሩ አብረውት ሊሰሩ የሚችሉ አመራሮች መርጦ ስራዉን ይቀጥል። እኛም በምክር ቤቱ አባልነታችን ስራችንን እንቀጥላለን » በማለት ራሳቸውን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አግለዋል።

እነዚህ አንጋፋ ወጣት የአንድነት አመራሮች ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከወጡ፣ ድርጅቱ ምን አይነት መልእክት ነው የሚያስተላልፈው ? ሊቀመንበሩስ ኢንጂነር ግዛቸው ፣ «የተቃዋሚ ድርጅቶች አሰባስባለሁ። ወጣቶችን ወደ አመራሩ አመጣለሁ» ሲሉ አንዳልነበረ፣ ወጣት አመራሮች «ከርሳቸው ጋር መስራት አንችልም» ብለው ሲለቁ፣ የርሳቸው ተአማኒነት ጥያቄ ምልክት ዉስጥ ሊገባ አይችልምን ? ከርሳቸው ጋር የሚሰሩትን ማቀፍና ማሰባሰብ ካልቻሉ እንዴት መኢአድን ፣ ሰማያዊን የመሳሰሉትን በዉጭ ያሉትን ሊያሰባስቡ ይችላሉ?

ዉድ የአንድነት ምክር ቤት አባላት፣ ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በቅንጅት ዉስጥ ተፍጠሮ የነበረዉን መከፍፈል ታስታወሳላችሁ ብዬ አስባለሁ። በወቅቱ ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት ከሆኑ ወገኖች መካከል ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው አንዱ ነበሩ። በ2000 ዓ.ም የወዳደቀዉን የቅንጅት ፍርስራሽ በማሰባሰብ፣ በወ/ት ብርቱክን ሚደቃሳ የሚመራ ጠንካራ የፖለቲክ እንቅስቃሴ ተጀመረ። በአጭር ጊዜ ዉስጥ አንድነት በሚል ፓርቲ ስም ፣ እንቅስቃሴዉ ሕዝባዊ ድጋፍ አገኘ። ተቃዋሚዎች ሲጠናከሩ የማይወደው ወያኔ/ኢሕአዴግ ብርቱካን ሚደቅሳን አሰረ። ያኔ ኢንጂነር ግዛቸው ድርጅቱን መምራት ጀመሩ። በዚያን ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን እና፣ አቶ አመሃ ደስታን ጨምሮ፣ አሁን ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱ በርካታ የቀድሞ አንድነት አመራር አባላት ጋር ኢንጂነር ግዛቸው መስማማት አልቻሉም። የሚቋወሟቸውን በዉስጣዊ አሰራር ከድርጅቱ እንዲታገዱ በማድረግ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ መከፋፈል እንዲፈጠር አደረጉ። ይህ ደግፊዎችን የሚያደማ ፣ ወያኔዎችን ጮቤ የሚያስረገጥ ክስተት ሲፈጸም እንግዲህ ሁለተኛ መሆኑ ነው። በሁለቱም ጊዜ ኢንጂነር ግዛቸው ዋና ተዋናይ ነበሩ።

አሁን ደግሞ ይኸው ፖለቲካ በቃኝ ብለው ከሶስት አመታት በላይ ከተቀመጡበት ግዞት ወጥተው «ተለውጫለሁ፣ ካለፉት ስህተቶቼ ተምሪያለሁ፣ ከወጣቶች ጋር አብሬ እሰራለሁ። ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮች ከመጡ ደግሞ ሃላፊነቴ እለቃለሁ። ሌሎች ድርጅቶችን አሰባስቤ ጠንካራ ተቃዋሚ ስብስብ እንዲኖር አደርጋለሁ» ብለው ለሊቀመንበርነት ተወዳደሩ። አብዛኛዉ የአንድነት አባል ድጋፉን ሰጣቸው።

ስድስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ እራሳቸው ከመረጧቸው የሥራ አስፈጻሚ ጋር አብረው መስራት አልቻሉም። በድርጅቱ ዉስጥ እንደ ከዚህ በፊቱ የተካኑበትን ዉስጣዊን የሴራ ፖለቲካ ጀመሩ። ቡድን በፍጠር፣ አንዱን ከሌላው በመለየትና በማጋጨት፣ አብረው በጋራ ሲታገሉ የነበሩ ወገኖችን፣ ከሶስት አመታት በላይ ዶር ነጋሶ መሪ የነበሩ ጊዜ ሰላም የነበሩትን፣ ለስልጣናቸው ሲሉ መከፋፈል ጀመሩ።

እንግዲህ ክቡራን የአንድነት ምክር ቤት አባላት፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ በኢንጂነር ግዛቸው እየተደረገ ያለዉን ጎጂ እንቅስቅሴ መገደብ አያስፈልግም ብላችሁ ታምናላችሁን ? ለሁለት ጊዜ ኢንጂነር ግዛቸው የታጋዮችን ልብ አቁስለዋል። ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይና ከፋፋይ ሥራ እንዲሰሩ ስለምንም ይፈቀድላቸዋል? የአንድነት ፓርቲ ላለፉት አንድ አመት ተኩል እጅግ በጣም ጉም ስራዎችን እየሰራ ነበር። ይኸው ኢንጂነር ሽፈራው ወለድ በሆኑ ችግሮች ነገሮች ቆመዋል። ሰኔ መጨረሻ ላይ ይገባደዳል የተባለው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ተረስቷል።

እንግዲህ ምክር ቤት ቆም ብሎ ራሱን እና ድርጅቱ ያለበትን እንዲመረምር እጠይቃለሁ። የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴ እንዲፈርስ የተደረገው ዉሳኔ እንዲቀለብሱና ከሥራ አስፈጻሚ የለቀቁ አንጋፋ ወጣት የአመራር አባላት ያቀረቡትን፣ መልቀቂያ ዉድቅ በማድረግ፣ ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ቡድናዊ የሴራ ፖለቲካቸው ትተው፣ በቅንነት ከነርሱ ጋር እንዲሰሩ መመሪያ እንዲሰጥ፣ ወይንም ሊቀመንበሩን ከሃላፊነታቸው እንዲያነሳ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

አንድነት የአንድ ሰው ተክለ ሰዉነት የሚገነባበት ሳይሆን ተቋማዊ ጥንካሬ እንዳለው መታየት አለበት። ከ4፣ 5 አመታት በፊት ወጣት አመራሮች እንደተገለሉት፣ አሁን ወጣት አመራሮችን በማግለል፣ የስድሳዎቹ ፖለቲከኞች የትግሉን ግለት ወደ ታች እንዲያወርዱት ሊፈቀድላቸው አይገባም። ምክር ቤቱ፣ በታሪክ እና በትዉልድ የሚያስጠይቀው ትልቅ ሃላፊነት ስላለበት፣ ለግለሰቦች ታማኝነቱን ለማሳየት ይልቅ፣ የአገርን እና የሕዝብ ጥቅም እንዲያስቀድም እመክራለሁ።

አንድነት የዉህደት ኮሚቴዉን አፍርሶ፣ ሲሰሩ የነበሩ ወጣት አመራሮች ገፍቶ ፣ በሕዝብ ተቀባይነት ያለው ድርጅት ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። ያለ ምንም ማገነን የነኢዴፓ እጣ ፋንታ ይደርሰዋል። ትልቅ ትኩረት ይሰጠበት እያልኩ፣ መልካም ዜናን እንደምታሰሙን ተስፋ አደርጋለሁ።

↧

የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በዓል ታዋቂው ድምጻዊ በሃይሉ አጎናፍር ከዝነኛዋ ቤተልሄም መላኩ ጋር በመሆን ሊያስደስቱዋችሁ ተዘጋጅተዋል!! በቦስተን የኢትዮጵያ አዲስ አመት በዓል ዝግጅት ኮሚቴ

በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን፤

“እንኳን ለመጪው የ2007 አዲስ ዓመት በዓል በሰላም አደረስዎ!!“

እያልን ይህንንው የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በዓል አስመልከቶ በቦስተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በጋራ፤ በዓሉን በጨዋና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በደመቀ ሁኔታ በየአመቱ እንደሚያከበሩ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የዘንድሮውን የ2007 ዓ. ም. የአዲስ ዓመት በዓልን በደመቀ ሁኔታ ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች፤ በዘር፤ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ፤ በጾታ ሳይከፋፈሉ በሕብረት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እያስታዋሱ በጋራ እንዲያክበሩ ለማድረግ የዝግጅት ኮሚቴው ስራውን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ሲገልጽ በደስታ ነው። ይኸው በዓል
ሴፕቴምበር 6 ቀን 2014 ዓ. ም ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ (September 6, 2014 – starting from 6:00PM)
በ St James Armenian Apostolic Church, 465 Mt Auburn St, Watertown, MA 02472
በድምቀት ይከበራል።

 በእለቱ ታዋቂው ድምጻዊ በሃይሉ አጎናፍር ከዝነኛዋ ቤተልሄም መላኩ ጋር በመሆን ሊያስደስቱዋችሁ ተዘግጅተዋል፤ በተጨማሪም በእለቱ ሕጻናት አበባየሆሽ በማለት የበዓሉን ታላቅነት ሲያበስሩ ፤ ወጣቶችም የተለየ ዝግጅት ይዘው ይቀርባሉ።

 በእለቱ በሰዓቱ በቦታው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅት ኮሚቴው የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ባንዲራ ፒን ለመጀመሪያ 300 አዋቂዎች በነጻ ይታደላል።

 በእለቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሐበሻ ልብስ አድርጎ እንዲመጣም እንጠይቃለን!

 እራት በነጻ ይስተናግዳል፤ መጠጥ በተመጣጣን ዋጋ ይቀርባል፤ ሕጻናት በነጻ!!

 የመግቢያ ዋጋ $30.00 ብቻ ነው

መልካም አዲስ ዓመት!!

በቦስተን የኢትዮጵያ አዲስ አመት በዓል ዝግጅት ኮሚቴ
ቦስተንImage may be NSFW.
Clik here to view.
Enqutatsh2 (2)
Image may be NSFW.
Clik here to view.
Enqutatsh2

በቦስተን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል ዝግጅት ኮሚቴ – ከፖለቲካ፤ ከሐይማኖት፤ እና ዘር፤ ነጻ የሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ አዲስ ዓመትን በደስታ እና በደስታ እንዲቀበለው፤
የወደፊት ተተኪ ሕጻናትም ባህላቸውን እንዲያውቁ፤ ኮሚቴውም በሕዝብ በአዲስ ዓመት በዓል ላይ በሕዝብ የተመረጠ ነው።
አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የፍቅር እና የብልጽግና፤ ይሁንላችሁ!! መልካም አዲስ አመት!!Image may be NSFW.
Clik here to view.
Enqutatsh2 (2)

↧
↧

የሕዝብን የነፃነት ትግል ማስቆም ፈጽሞ አይቻልም ሸንጎው

↧

የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)

ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና የደቡብ አፍሪካን መሪዎች ጨምሮ እንመራሀለን የሚሉትን ህዝብ በየቀኑ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት የወያኔ መሪዎችም ተገኝተዋል። በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ደሳለኝ ኃ/ማሪያምን አጅበዉ ከመጡት የወያኔ ሹማምንት አንዱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ./ር ቴድሮስ አድሃኖም ነበሩ። ዶ/ር ቴድሮስ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸዉ ብዙዎቻችንን እየዋለ ሲያድር ደግሞ እራሳቸዉንም ግራ ያጋባ የሬድዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዉ ነበር።

“በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” የአገራችን ባለቅኔዎች አፉ እንዳመጣለትና እንዳሻዉ የሚናገርን ሰዉ . . . ዋ ተጠንቀቅ በአፍ የሚነገር ነገር ዋጋ ያስከፍላል ለማለት የተረቱት ተረት ነዉ። አዎ! ባለቅኔዎቹ እዉነታቸዉን ነዉ። የሚያዳምጡንን ሰዎች ለማስደሰት ስንል ብቻ አፋችን እንዳመጣ የባጥ የቆጡን የምንዘባርቅ ሰዎች የምንላቸዉ ነገሮች እኛዉ ዘንድ ዞረዉ መጥተዉ መጥፊያችን ሊሆኑ ይችላሉ። በቅርቡ ዋሺንግተን ዲሲ ብቅ ብለዉ የነበሩትን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ያጋጠማቸዉ ይሄዉ በጋዛ አፍ ተናግሮ የመጥፋት ቅሌት ነበር። ዶ/ር ቴድሮስ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ መንግስታቸዉ የሰራተኛ ደሞዝና የአየር ላይ ወጪ እየከፈለ በሚያስተዳድረዉ ሬድዮ አፋቸዉን ሞልተዉ የተናገሩትን ነገር አዲስ አበባ ተመልሰዉ በፌስ ቡካቸዉ በለቀቁት መልዕክት ለማስተባበል ቢሞክሩም ነገሩ “ከአፍ ከወጣ አፋፍ” ሆኖባቸዉ በስህተት ላይ ስህተት እየፈጸሙ ይገኛሉ።

ሬድዮ አገር ፍቅር በመባል ከሚታወቀዉ ሳምንታዊ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የአሜሪካ መንግስት ጓንታናሞ ዉስጥ ካሰራቸዉ የአልቃይዳ አባላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ማረጋገጫ አግኝተናል ካሉ በኋላ የአሜሪካ መንግስት ይህንን ግኑኝነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ኢትዮጵያ ድረስ ሄዶ ለማነጋገር ለመንግስታቸዉ ጥያቄ እንዳቀረበ ተናግረዋል። ያልነገሩን ነገር ቢኖር የአሜሪካ መንግስት ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ቃሊቲ ድረስ ሄዶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ማነጋገሩንና አለማነጋገሩን ብቻ ነዉ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆኑ እሳቸዉ በአባልነት የሚገኙበት ህወሃት የሚባዉ ድርጅት ሃያ ሦስት አመት ሙሉ እየዋሸ የዘለቀ ድርጅት ነዉና የዶ/ር ቴድሮስ ዉሸት ብዙም ላይገርመን ይችላል። ሆኖም ግን ዶ/ር ቴድሮስ ግማሽ ደቂቃ በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ሁለት ቱባ ቱባ ዉሸቶችን ሲዋሹ “ከማንም ጋር አንወግንም፤ የቆምነዉ ለእዉነት ብቻ ነዉ” የሚለዉ የአገር ፍቅር ሬድዮ ጣቢያ አዘጋጅ ካለምንም ተከታይ የማብራሪያ ጥያቄ የዶ/ር ቴድሮስን ቆሞ የሚሄድ ዉሸት እንዳለ ተቀብሎ ጭራሽ ዶ/ር ቴድሮስን ማመስገኑ የወያኔ ስርዐት ዉሸትና ቅጥፈት አገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በዉጭ አገሮችም ምን ያክል ህብረተሰባችንን አንደበከለ ያሳያል።
የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ከአልቃይዳ ጋር ማገናኘት እነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያነሱትን ህጋዊ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ላለመመለስ የሚደረግ አጉል ዉጣ ዉረድ ከመሆኑ አልፎ ማንም ማየትና ማሰብ የሚችል ሰዉ የማይቀበለዉ ከንቱ ቅጥፈት ነዉ። ደግሞም ይብላኝ ለዶ/ር ቴድሮስ አፋቸዉን ላዳለጣቸዉ እንጂ ወጣቶቹ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችኮ የጓንታናሞ አስር ቤት ሲከፈት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት መፍጠር ቀርቶ አልቃይዳ የሚባል ነገር መኖሩን እንኳን ሰምተዉ የማያዉቁ አንድ ፍሬ ልጆች ነበሩ።

ሌላዉ የዶ/ር ቴድሮስ ትልቁ ዉሸት የአሜሪካ መንግስት ከአልቃይዳ ጋር የነበራቸዉን ግንኙነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የታሰሩበት ቦታ ድረስ ሄዶ ላናግራቸዉ ብሎ ጠየቀን ማለታቸዉ ነዉ። እኔ እንደሚመስለኝ ዶ/ር ቴድሮስ አደስ አበባ ከገቡ በኋላ “ምን ነካኝ” ብለዉ ዉሸታቸዉን በፌስ ቡክ ገጻቸዉ ለማስተባበል የቸኮሉት ደጋግመዉ ወዳጃችን ነዉ ብለዉ በተናገሩት በአሜሪካ መንግስት ስም የዋሹት ዉሸት ከንክኗቸዉ ይመስለኛል፤ አለዚያማ ወያኔም ሆነ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ቴድሮስ በዋሹ ቁጥር ዉሸታቸዉን የሚያስተባብሉ ቢሆን ኖሮ የወያኔ አገዛዝ መሪዎች ስራቸዉ እየዋሹ ማስተባበል ብቻ ይሆን ነበር።
የሚገርመዉ ዶ/ር ቴድሮስ ከአሜሪካ ተመልሰዉ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ የመጀመሪያዉን አንድ ሳምንት ያሳለፉት አንድም አሜሪካ ዉስጥ የዋሹትን ዉሸት በማስተባበል ሌላ ግዜ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ ዉሸቶችን በመዋሸት ነበር። በእርግጥም ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በየአገሩ የሚገኙትን አምባሳደሮቻቸዉን ሰብስበዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ከት አድርጎ ያሳቀ ነጭ ዉሸት ዋሽተዋል። ለምሳሌ አሜሪካ ዉስጥ የህዳሴዉ ግድብ ቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ምክንያቱን ሲገልጹ የአሜሪካ ህግ ለቦንድ ሽያጩ አመቺ አለመሆኑን ገልጸዉ ይህንን ለማሻሻል መንግስታቸዉ ከአሜሪካ መንግስት ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መቼም ለራሱ አገር ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ህግ አዉጥቶ የማያወቀዉ እንቅልፋሙ የኢትዮጵያ ፓርላማ የአሜሪካንን መንግስት የሚገዛ ህግ ካላወጣ በቀር ዶ/ር ቴድሮስ አደራ የተጣለባቸዉን የቦንድ ሽያጭ እንዴት አሜሪካ ዉስጥ እንደሚወጡት ባላዉቅም መንግስታቸዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባለበት ቦታ ሁሉ ሁሉ ቦንድ መሸጥ ያልቸለዉ የየአገሮቹ ህግ ችግር ፈጥሮበት ሳይሆን ለወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚታገለዉ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቼንና እህቶቼን እየገደላችሁ የምትሸጡልኝ ቦንድ ባፍንጫዬ ይዉጣ ብሎ እምቢ ስላላቸዉ ነዉ። ይህንን ደግሞ መዋሸት እንጂ እዉነትን ሸፍኖ ማስቀረት ያልቻሉት ዶ/ር ቴድሮስም ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በስተቀር የሁሉም አገሮች የቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ደካማ እንደነበር ለሰበሰቧቸዉ አምባሳደሮች ተናግረዋል፡፡

ከዶ/ር ቴድሮስ በፊትም ሆነ እሳቸዉ እያሉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከትዉልድ አገሩ ርቆ የሚኖረዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ከአገዛዙ ጎን ለማሰለፍ ተደጋጋሚ ጥረቶችን አድርጓል። በተለይ የህዳሴዉን ግድብ ቦንድ ሽያጭና የዕድገትና ትራንስፎርሜሺኑን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ዳያስፖራዉን አንደ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ ተመልክቶት ነበር፤ ሆኖም አብዛኛዉ ዳያስፖራ ከአገዛዙ ጎን ተሰልፎ ከሚያገኘዉ ግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ዘላቂ የሆነዉን የእናት አገሩን አንድነትና የወገኖቹን ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት በመምረጡ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከዳያስፖራዉ እዝቃለሁ ብሎ የተመኘዉ የዉጭ ምንዛሬ ህልም ሆኖ ቀርቷል።
ሌላዉ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከፍተኛ በጀትና የሰዉ ኃይል መድቦ ዳያስፖራዉን ለማማለል በሙሉ ሀይሉ የተንቀሳቀሰበት አካባቢ ቢኖር የከተማ ቦታና ቤት ሽያጭ ዘመቻ ነዉ። በእርግጥ አንዳንድ ከህዝብና ከአገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸዉን ጥቅም ያስቀደሙ የዳያስፖራዉ አባላት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን የመሬት ቅርምት በይፋ እየተቃወሙ የቅርምቱ ድግስ የእነሱን ቤት ሲያንኳኳ ግን በራቸዉን ወለል አድርገዉ ከፍተዉ የድግሱ ተሳታፊዎች ሆነዋል። አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግን እናትና አባቴን እያፈናቀላችሁ የምትሰጡኝን መሬትም ሆነ ቤት አልፈልግም ብሎ በቦንድ ሽያጩ ላይ የወሰደዉን ጠንካራ አቋም በከተማ መሬትና ቤት ሽያጭ ላይም ደግሞታል። የወገኖቹን ነጻነትና ፍትህ ለማስከበር በህይወቱ የተወራረደዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የማያወላዉል አቋም ያልተረዱት ዶ/ር ቴድሮስ ግን ያንን የለመዱትን በጥቅማ ጥቅም የመደለል ሴራቸዉን አሁንም እንደቀጠሉበት ነዉ። ለምሳሌ ዳያስፖራዉ በመጪዉ አመት በሚደረገዉ የምርጫ ድራማ ላይ ያለዉን እይታ እንዲለዉጥ ለማድረግ ሲባል ብቻ 40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት የከፈሉበት ቤት የ2007ቱ ምርጫ ከመጀመሩ በፊት በአስቸኳይ ተጠናቅቆ እንዲሰጣቸዉ ትዕዛዝ ተላልፏል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ በጣም የገረመኝም ያሳዘነኝም ነገር ቢኖር በአንድ በኩል ግብር ከፋይ በሌላ በኩል ደግሞ ቤት አልባ የሆነዉና እነ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም 99.6% መረጠን የሚሉት አገር ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ተረስቶ ትርፍ ቤት ፈላጊዉ ዳያስፖራ ቅድሚያ እንዲሰጠዉ መደረጉ ነዉ።

ለመሆኑ ዶ/ር ቴድሮስና መንግስታቸዉ ሁሌም አክራሪዉ ዳያስፖራ እያሉ የሚያሙትን ማህበረስብ ወድደዉ ሊስሙት ነዉ ወይን ተጠግተዉ ሊያልቡት እንዲህ የተንሰፈሰፉለት? የዳያስፖራዉን አባት፤ እናት፤ ወንድምና እህት እያሰሩ፤ እየገደሉና የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳባቸዉን የዳያስፖራ አባል ደግሞ አገርህ አትገባም ብለዉ አገር እየነሱት እነሱ ግን የልመና ኮሮጇቸዉን ተሽክመዉ አሜሪካና አዉሮፓ እየመጡ አገርህን እናሳድግልሃለን ገንዘብ ስጠን ብለዉ የሚጠይቁት በማን አገር ማን ለሚጠቀምበት ልማት ነዉ? እነ ዶ/ር ቴድሮስ እነሱን ከመሰለ ፀረ ህዝብ አገዛዝ ጋር ተመሳጥረዉ የዳያስፖራዉን አባል በህገ ወጥ መንገድ አግተዉ እየደበደቡና መታሰሩን ሰምታ ልትጠይቀዉ የሄደችዉን እህቱን ተወልዳ ካደገችበትና እትብቷ ከተቀበረበት አገር በ24 ሰዐት ዉስጥ ዉጪ ብለዉ እያስገደዱ እንዴት ቢገምቱንና እንዴት ቢመለከቱን ነዉ ዞር ብለዉ እኛኑ ገንዘብ ስጡን ብለዉ የሚጠይቁን?
ዶ/ር ቴድሮስ ከአገር ፍቅር ሬድዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከማጠቃለላቸዉ በፊት ደጋግመዉ የተናገሩት ኢትዮጵያን ምን ያክል እንደሚወዱና ይህ የሚወዱት አገር ህዝብ በእድገት ወደ ፊት ከገፉ አገሮች ተርታ ተሰልፎ ማየት አንደሚቸኩሉ ነዉ። መልካም ምኞት ነዉ። ሆኖም ይህ ምኞት የዚያችን የሚወዷትን አገር ህዝብ ሲናገር አፉን እየዘጉ፤ ሲጽፍ እጁን እያሰሩ፤ ሃሳቡን ሲገልጽ ማዕከላዊ ወስደዉ ሰቅለዉ እየገረፉና ሰላማዊ ሠልፍ ተሰልፎ መብቴንና ነጻነቴን አክብሩልኝ ብሎ የጠየቃቸዉን ደግሞ ደረቱንና ጭንቅላቱን በጥይት እያፈረሱ የሚሳካ ምኞት አይደለም። ዶ/ር ቴድሮስ በአፋቸዉ ብቻ የሚናገሩት ምኞት ዳያስፖራዉ በአፉም በልቡም ዉስጥ ያለ፤ የነበረና ለወደፊትም የሚኖር ምኞት ነዉ። ምኞታችንና ምኞታቸዉ ገጥሞ ኢትዮጵያ አድጋና በልጽጋ የምናያት ግን ዶ/ር ቴድሮስ እኛም እንደሳቸዉ በአገራችን ጉዳይ እንደሚያገባን በዉል ሲረዱና ይህንን ሃያ ሦስት አመት ሙሉ በችንካር ቀርቅረዉ የዘጉብንን በር ወለል አድርገዉ ሲከፍቱ ብቻ ነዉ።

የኢትዮጵያ ትንሳኤ በልጆቿ መስዋዕትነት ይረጋገጣል!!!!

ebini23@yahoo.com

↧

ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ እንደማየት የመሰለ የአገር ዉድቀት የለም –ግርማ ካሳ

አገሩን እና ሕዝቡን የሚወድ ። እንደ ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ኢትዮጵያ ከግፍ አገዛዝ ተላቃ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸው ተጠበቆ፣ ተከባብረዉ በስላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን፣ የሚያደርጉትን ትግል የተቀላቀለ ነው። ወጣት ነው። ጉልበትና አቅም አለው። እንደ አንዳንዶች በጥቅም ተታሎ አደርባይነትን መምረጥ ይችል ነበር። ነገር ግን አላደረገዉም። «ሰዉ ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ? » ብሎ ለነጻነቱ ቆመ። የባለ ራእዩ ወጣቶች ማህብርን ከዚያም የአንድነት ፓርቲን ተቀላቀለ። በአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ መዋቅር የቦሌ ወረዳ አመራር አባል ሆኖ ይሰራ ነበር። በሶሻል ሜዲያዉም ብዙ ጊዜ ድምጹን ያሰማል። አይፈራም። ወኔ አለው።

Image may be NSFW.
Clik here to view.
ጥላዬ

በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ እየተደረገ በነበረዉ፣ ዉህዱን ፓርቲ ለመምራት በተደረገው የምርጫ ፉክክር «አዲስ አመራር ያስፈልጋል» በሚል ለአቶ በላይ ፍቃደ ይቀሰቅስ ነበር። ለዉጥ ፈላጊ ነው።

ነሐሴ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ፣ ዜጎችን ማሰርና ማሰቃየት የለመደባቸው የአገዛዙ ታጣቂዎች ከየአቅጣጫው ተረባረቡበት። ምክንያቱ ለጊዘው ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ወህኒ ወረወሩት። ይህ ወጣት ፣ ብዙዎች የማያወቁት፣ የማደንቀዉን የማከብረው ጥላዬ ታረቀኝ ይባላል።
ፖሊሲ ፍርድ ቤት ይዞት በቀረበ ጊዜ፣ «በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል» የሚል ክስ ነበር ያቀረበበት። ፖሊሲ በሰው ላይ ጉዳት አደረሰ የሚል ክስ አቅርቦ ጉዳት ደረሰበትን የተባለው ግለሰብ ግን ለማቅረብ አልቻለም። «ጉዳይ ደረሰበት የተባለውን ሰው ማግኘት አልቻልኩም» ብሎ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ። ወጣት ጥላዬ ግን ለፍርድ ቤቱ ፣ «የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም» እያሉ እንደሚዝቱበት አስረዳ። ዳኛው ግን መረጃ ባልቀረበበት እና በወጣት ጥላዬ ላይ በፖሊሶች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተሰጠ ባለበት ሁኔታ፣ በዋስ እንዲፈታ ሳይፈቅ ቀረ። ለነሐሴ 12 ፖሊሲ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጠ።

ጉዳት ደረሰ የተባለው ከሁለት ወራት በፊት፣ በሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ነው። በቀጠሮዉ ቀን፣ ፍርድ ቤቱ «ሁለት ወራት ሙሉ የት ነበራችሁ? ለምንስ ጉዳት የደረሰበት ሰው አላቀረባችሁም ? » ሲል ጠየቀ። ፖሊሶች «ጉዳይ የደረሰበትን ሰው ልናገኘው አልቻልንም። የሕክምና ማስረጃ እንድናቀርብ ይፈቀድልን» ብለው ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ወጣት ጥላዬ «የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ፣ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን» ነው ሲል ከፍርድ ቤቱ ፍትህን ጠየቀ።ፍርድ ቤቱ ግን አሁን ለሰላማዊ ዜጎች ፍትህን ነፈገ። ወጣት ጥላዬ በወህኒ እንዲቆይ ተደርጎ ተለዋጭ ቀጠሮ ለነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጠ።

አስቡት፣ የሕክምና መረጃ ያለ ባሌበቱ ሆስፒታሎች መስጠት የለባቸውም። (የአገር ደህንነትን የሚነካ ካልሆነ በቀር)። አሁን፣ ፖሊስ እያለ ያለው፣ ታከመ የተባለው ሰው ፍቃድ ሳይጠየቅ፣ የህክማን ማስረጃ ከሃኪም ቤቶች እንደሚያቀርብ ነው። ለነገሩማ የሆስፒታል አስተዳዳሪዎች ዉሸትን ጨማምረው፣ ያለዉን እንደሌለ፣ የሌለዉን እንዳለ አድርገው መረጃ መስጠታቸው አይቀርም። በተለያዩ ጊዜያት በሌሊት የሚገደሉ፣ በረሃብና በጠኔ የሚሞቱ ብዙ ናቸው። በአገር ቤት ችግር እንደሌለ የዉሸት ገጽታ ለማቅረብ የሚፈልገው አገዛዙ፣ ሆስፒታሎች የዉሸት አታብሲ (የሞት ይሕክምና ማረጋገጫ) እንዲጽፉ እንደሚያደርጓቸውም ያው አገር ሁሉ የሚያወቀው ሐቅ ነው።

እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ሁለት ትላልቅ ነጥቦች አሉ።

1. ብዙዎቻችን በጣም የሚታወቁ ግለሰቦች ሲታሰሩ ነው የአገዛዙ ዜጎችን የማሸበርና የማወክ ተግባር የሚታየን። ነገር ግን በአገራችን እየተደረገ ላለው እልህ አስጨራሽ ትግል፣ ብዙ የማናውቃቸው ወገኖቻችን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ከነዚህም አንዱ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ነው።

2. በኢትዮጵያ አገራችን ባሉ ፍርድ ቤቶች እየታየ ያለው፣ ፍትህን የማስከበር ሥራ ሳይሆን፣ ፍጹም አሳፋሪ፣ ኋላ ቀርና አሳዛኝ የፍርድ መዛባት እንደሆነ ነው። ፖሊስ ዜጎችን እንደፈለገ ሲያስርና ሲያሸብር፣ በፈለገ ጊዜ ተጨማሪ ቀጠሮ ሲጠይቅ፣ ዳኞች ቅንጣት እንኳን የሕግ ባለሞያዎች የስነ-ምግባር ኮድ (ኤቲክስ) ሕሊናቸውን ወቅሷቸው፣ ትክክለኛ ነገር ሲሰሩ እንደማይታዩ ነው። ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ለአገር ዉድቀት የለም።

ገዢዎች ይኸው ስልጣን ከያዙ ጀመሮ እንደገደሉና እንዳሰሩ ናቸው። ሕግን መቀለጃ እያደረጉ ናቸው። ነገር ግን በዱላ፣ በጠመንጃ፣ በማስፈራራት፣ በዛቻ ኢትዮጵያዉያን ለመብታቸው፣ ለነጻነታቸውና ለአንድነታቸው የሚያደርጉት ትግል ሊገቱ አይችሉም። እሳት የለበሱ፣ በወኔ የተሞሉ፣ የስለጠነ ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቷ የሚኖሩ፣ አገዛዙ ከዘረጋዉን የጎሳ ድንበር አልፈው በሰብእናና በኢትዮጵያዊነት የተሳሰሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንደ ጥላዬ ታረቀኝ ኢትዮጵያ አፍርታለች።

↧

ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!- ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡
በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡
2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡
3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡
4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡
5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!Image may be NSFW.
Clik here to view.
10600514_939574226071909_6527775654804455118_n

Image may be NSFW.
Clik here to view.
936666_939573999405265_5749079552182177499_n

↧
↧

የዘንዶ ሱባዔ? ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

↧

ኢትዮጵያዊነት ማለት አንዱ ዓለም ተፈራ

“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ”

አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ ኃይለማርያምና በወገንተኛው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል ገና ብዙ ፀሐፊዎች ብዙ ይውሉበታል፣ ሊቃውንት ይቀኙበታል፣ አንጎርጓሪዎች ይደረድሩበታል፣ ሰዓሊዎች ያቀልሙታል፣ ገጣሚዎች ይሰነኙበታል፣ መጽሐፎች ይደረሱበታል። ያ ግን፤ ከኛ ቀጥለው የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን፤ ስለኛ ስለቀደምናቸው ኢትዮጵያዊያን ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን ወይም ኢትዮጵያዊ ስላለመሆናችን አይደለም።

እንግዲህ የአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? የሚለውን በደንብ መረዳት አለብን። ይኼን ስናደርግ፤ የሀገራችንን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሀቅ በትክክል እንረዳና፤ በኢትዮጵያዊነታችን፤ ምን ማድረግ እንዳለብንና ማን ኢትዮጵያዊነቷን እየተወጣች እንደሆነች እንገነዘባለን። ትናንትም፣ ዛሬም ነገም ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ሀገርን ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ወራሪ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ፤ ይህ ግዴታ፤ ወደ መኖር ወይንም አለመኖር የሕይወት ትንቅንቅ ስለሚያመራ፤ አማራጭ የማይሠጥ ጥሪ ይሆናል። ይህ ፖለቲከኛ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ታጋይ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ሀገራዊ ግዴታን ነው የሚገልጸው። ይህ የኢትዮጵያዊ ሕይወት፣ የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሕልውና ጥያቄ ነው። አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥት የለም። ሕግና ሥርዓት የሚያከብር ቡድን አይደልም በሥልጣን ላይ ያለው። ራሱ የሚያወጣቸውን ሕጎች የሚያፈርስ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳ ክፍል ነው በሥልጣን ላይ የተቀመጠው። ኢትዮጵያዊያንን እየከፋፈለ፣ አንድነት እንዳይኖረን የሚጥር መንግሥት በሥልጣን ላይ አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ። አልከፋፈልም። ጠላታችን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ነው።” እያለ ትግል ይዟል። ስለዚህ፤ የአሁኗ ኢትዮጵያዊትና የአሁኑ ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን፤ ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያዊያን መንግሥት ከታጋዩ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ማስወገድ ነው። ሕዝባዊ ንቅናቄ ከፊታችን ተደግኗል። የውዴታ ሳይሆን ግድ ሆኖብን፤ የምርጫ ሳይሆን አማራጭ ሳይኖረን ንቅናቄው አፍጥጦብናል። የዴሞክራሲ ቅንጦት ሳይሆን የሀገር አድን ጥያቄ ቀርቧል።

ባጭሩ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ወራሪ መንግሥት ማወገድ ነው። ይኼን የኔ ብሎ ያልተነሳ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው? በርግጥ ትግሉ ረጅም ነው። ትግሉ የተመሰቃቀለ ነው። በሥልጣን ላይ ተቀምጦ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናውና መመሪያው የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ሳይሆን፤ ይኼኑ ፍልስፍናና መመሪያ የራሳቸው ያደረጉ ሌሎች ክፍሎችም የኢትዮጵያዊነት ትግላችን አንድ ክፍል ናቸው። በትግሉ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ይኼን ሀቅ አጥብቀን መያዝ አለብን። ኢትዮጵያ ለዘመናት መንግሥት ኖሯት ስትተዳደር የነበረች ሀገር ለመሆኗ አጥጋቢ መረጃዎች አሉ። እኒህ መንግሥታት በየተከሰቱበት የታሪክ ወቅት፤ በጎም ሆነ በጎነት የጎደለው ተግባር አከናውነው አልፈዋል። በዚህ ረጅም ታሪካችን፤ የመንግሥታዊ ማዕከላቸውን በሰሜን ወይንም በደቡብ፤ በምሥራቅ ወይንም በምዕራብ እንደታሪካዊ ወቅቱም ተንቀሳቃሽ በማድረግ፣ የተለያዩ የጦር አሠላለፍን በማዘጋጀት፣ ጥንካሬያቸው እንደፈቀደላቸው፤ የሀገሪቱንም ደንበር ሲያሠፉና ስትጠብባቸው ነበር። አንዱ ከሌላው ጎጥ፤ ሃይማኖት ሳያግደው፣ የዘር ሐረግ ሳይከለክለው፣ እንደ ጥንካሬያቸውና የፖለቲካ ግኘታ አመቺነታቸው ሲጋቡና ሲዋለዱ ነበር። በኢትዮጵያዊነት ገዝተዋል። እናም በተለያዩ ጊዜያት፤ በተለያዩ መንግሥታት ዘመን፤ የተለያዩ ህዝባዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ሕዝባዊ አመፆች ተካሂደዋል። መፈንቅለ መንግሥት ተደርገዋል። በንጉሥ ላይ ንጉሥ ተነስቷል። ንግሥታት ዘውድ ጭነው ገዝተዋል።

የውጭ ሀገር ጉልበተኛ መንግሥታት ሀገራችን ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት እንዳይኖራት የተጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም። እንዲያውም ከሞላ ጎደል የሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከውጭ ወራሪዎችና ጣልቃ ገቦች ጋር የመኖርና ያለመኖር ተጋድሎ ነው ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል። አሁንም የውጭ ኃይላት ለጥቅማቸው ሲሉ ያላቸው እርጎ ዝምብነት ትልቁ በሽታችን ነው። አሁን በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በጠቅላላው በውጭ ሀገር መንግሥታት ላይ ልናደርግ የምንችለው ጫና ወይንም ቀና አመለካከት እንዲኖራቸው የምናደርገው ጥረት፤ የትም አይደርስም። ይልቁንስ በራሳችን መካከል ያለውን ጥንካሬ በአንድነት በመሰባሰብ ብናጎለብት፤ እኛ ወደነሱ ለአቤቱታ ከመሄድ፤ እነሱ ወደኛ ለጥቅማቸው የሚመጡበትን መንገድ እንፈጥራለን። የሚረዱት ቋንቋ፤ የራሳቸው ጥቅምና የኛ ጥንካሬ ብቻ ነውና! ሆኖም ወደኛ ስንመለስ፤ በዚህ በሀገራችን የታሪክ ጉዞ፤ ኢትዮጵያዊነት በጥያቄ ውስጥ ገብቶ አያውቅም። ለምን?

አንድ ግለሰብ በመንግሥት ውስጥ የያዘው የሥልጣን ደረጃ፣ ያለበት ድርጅት አባልነቱ፣ የተወለደበት አካባቢ፣ የሚናገረው ቋንቋ፣ ያለው የሀብት ብዛት ወይም ማነስ፣ የትውልድ ሐረጉ መሠረት፤ የግለሰቡ ብሶት ወይም ምቾት፤ ይህ ሁሉ አንድን ኢትዮጵያዊ ከሌላዋ ኢትዮጵያዊት ያነሰ ወይንም የተለቀ ኢትዮጵያዊ አያደርግም። ሁላችን ኢትዮጵያዊያን፤ በአንድነት ሙሉ ኢትዮጵያን እንጋራታለን። የጋራ ሀገራችን ናት። የነበሩት፣ ያለነውና የሚመጡት ሁላችን በአንድነት ባለቤቶች ነን። አንድ የተቧደነ ክፍል፤ በመንግሥት ደረጃ ሥልጣን ላይ ወጣም ወይንም በተቃውሞ አፈነገጠ፤ የኢትዮጵያ ግለኛ ባለቤት ወይንም የኢትዮጵያዊነትን ትርጉም ሠጪና ነሽ አይደለም። ይህ ደግሞ ነገሥታትንና ማንኛውንም በሥልጣን ላይ የሚወጣን ክፍል ይጨምራል። ኢትዮጵያዊነት በሥልጣን ላይ የሚወጣው መንግሥት ወይንም አንድ ጅንን ግለሰብ ትርጉም የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ከዚያ በላይ ነው። የታሪክ ትስስር ነው። እትብት ነው።

አይደለሁም ብሎ እስካላፈነገጠ ድረስ፤ አንድ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በመወለዱ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ወይንም የኢትዮጵያ ዜግነት አለው። ኢትዮጵያዊነት የሀገረ ኢትዮጵያ ዜጋ ሆኖ መገኘት ነው። ኢትዮጵያዊነት በዜግነት ላይ የተመሠረተ የግለሰብ ሀገራዊ መብት እንጂ፤ የስብስብ ወይንም የአካባቢ ጥምር መብት አይደለም። “በግል ወይንም በአካባቢ በደል ደርሶብኛልና ኢትዮጵያዊነት ለኔ ምን ያደርግልኛል?” የሚለው አባባል፤ በቀላሉ ሲታይ የየዋህነት አለዚያ ደግሞ የመሠሪነት ገጽታ ነው። መገንዘብ ያለብን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሠረት አድርጎ የተነሳው፤ በራሳቸው መሥራችና የጦር መሪ አረጋዊ በርሄ እንደተገለጸልን፤ አፄ ሚኒሊክ የጣሊያንን ወራሪ ጦር ለማባረር ትግራይ ሲሄዱ፤ ለወታደሮቻቸው ምግብ እንዲያቀርብ፤ የትግራይን ገበሬ ስላዘዙት ነው። እናም ሀገርን ከወራሪ ለማዳን የዘመተን ጦር መመገብ በደል አድርገው ቆጥረው፤ የዛሬዎቹ ገዝዎቻችን ተስባስበው ደደቢት ገቡ። ኢትዮጵያዊነት ገደል ይግባ አሉ። አሁንም በደደቢቱ ግንዛቤያቸው ኢትዮጵያን ወረዋል። መንግሥታቸው ኢትዮጵያዊ አይደለም። ሌሎችን በሚመለከት፤ እስኪ አስቡ፤ በደል አለብኝ ባይ ኢትዮጵያዊነቱን በጥያቄ ውስጥ ካስገባ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ምን ለየው?

“ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፤ ሌላ ነኝ።” ማለት፤ የግለሰብ መብት ነው። ያ በግል፤ አንድ ግለሰብ፤ ለራሱ ለግለሰቡ የሚሠጠው ዜጋ የመሆን ወይንም ያለመሆን ጉዳይ እንጂ፤ አንዱ ለሌላው ሊሠጠው ወይንም ሊነፍገው የሚችል ዜግነት አይደለም። በመንግሥት ደረጃ፤ ትክክለኛውን የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት በመከተል፤ ለአዲስ አመልካቾች ዜግነት ሊሠጥ ወይንም ሊነፈግ ይቻላል። ኢትዮጵያዊ የሆነውን ዜጋ ግን፤ በምንም መንገድ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ሊል የሚችል ማንም የለም። ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ሲያጠፋ በሕግ ይጠየቃል። ፀረ-ኢትዮጵያ ተግባር ሲሠራ ደግሞ፤ በከሃዲነቱ ባንገቱ ላይ ሽምቅቅ ያርፍበታል። ሀገር አስመስጋኝ ተግባር ሲፈፅም፤ የሀገር ታዋቂነትን ያገኛል። ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው። በወራሪ መንግሥት ላይ ማመጽ፤ አርበኝነት እንጂ፤ ወንጀል አይደለም። ይህ ለግለሰብ ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ተቋማትም ይሠራል። አስመስጋኝ ተግባር ሲያከናውኑ፤ ሀገራዊ ታዋቂነት ይሠጣቸዋል። ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆኑ ይዘመትባቸዋል። እንደግለሰቡ ሽምቅቅ፤ ለተቋማቱ ደግሞ ፍፃሜያቸውን የሚያገኙበት ክንውን ይደረጋል። መንግሥትም ሀገራዊ ተቋም ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ ነው። እናም ፍፃሜውን ማምጣት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ነው።

“እኔ አንድ ግለሰብ ነኝ። ምን ማድረግ እችላለሁ?” በማለት ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችንን ከኛ ማራቅ አንችልም። ኢትዮጵያዊነት አንዴ የሚመጣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚሸሽ ጥላ አይደለም። ሁሌም አብሮን አለ። በደማችን ውስጥ ፈሳሹ፣ በአጥንታችን ውስጥ ጽናቱ፣ በቆዳችን ላይ ሰብሳቢ ክኑ ነው። በድርጅት ተሰባሰብን ወይንም የመንግሥት ሠራተኛ ሆን፤ ኢትዮጵያዊነታችን አይለወጥም። ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ሆነን የምንጠይቀው ጉዳይ አይደለም። ነን ወይንም አይደለንም? ብቻ ነው መለኪያው። ግማሽ ኢትዮጵያዊ የለም። ሩብ ኢትዮጵያዊት የለችም። “ቆይቼ እሆናለሁ አሁን ተበድያለሁ።” ብለን በቆይታ የምናስቀምጠው ጉዳይ አይደልም። በደል ሌላ! ማንነት ሌላ!

እኛ አሁን ኢትዮጵያዊያን ነን ብለን፤ በዚህ በዘመናችን የኖርንበትና የምንኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችንን አስመልክቶ፤ ምን እያደረግን ነው? የሚለው ደግሞ የዛሬ ጥያቄ ነው። በመካከላችን የተለያየ መልስ የምንሠጥ አለን። ከነዚህ መካከል በዚህ በያዝነው ወቅት ነበርን ለማለት የሚያስችል ምልክታችን ምንድን ነው? የወቅታችን ማመልከቻ ሆኖ የሚታየው፤ አንድም በደሉን በመፈጸም የተሠለፉት ጥቂት የሥልጣን ጥመኞች እና በዝርፊያ በሕዝቡ ገንዘብ ለግላቸው የገነቧቸው ሕንፃዎች ሲሆኑ፤ ሌላ ደግሞ እኒህን ሲታገሉ ሕይወታቸውን ለሕዝቡ ድል የሠጡት ናቸው። በመካከል የሠፈርነው ከሞላ ጎደል ብዙዎቻችን፤ እድሜያችንን ቆጥረን ከማለፍ በላይ የምናስመዘግበው የለንም። በእርግጥ ትግል ተደራጅቶ ነው። ብዙ የሚታገሉ ድርጅቶች አሉ። የድርጅቶቹ ታሪክና የአሁን ሁኔታ ደግሞ አያስመረቃም። ነገር ግን ሌሎቻችን እጅና እግሮቻችንን አጣጥፈን በመቀመጥና “እነሱ” እያልን ተደራጅተው በሚታገሉት ላይ እጣቶቻችንን በመቀሰር፤ ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ነፃ መውጣት አንችልም። ድርጅት መኖሩ ታጋዮች የሚያደርጉትን ጥረት አመልካች ነው። ከነዚህ ጋር መተባበር ካልቻልን፤ ድርጅቶቻቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩና ከሀገራቸው ከኢትዮጵያ የሚያስቀድሙ ከሆነ፤ ሌሎችን በማስተባበር እንዲስተካከሉ የማድረጉ ኃላፊነት ከራሳችን አይወርድም። ድርጅት ምክንያት ሆኖ ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ነፃ አያወጣንም። እነ ርዕዩት ዓለሙ፣ እነ አንዱዓለም አራጌ፣ እነ እስክንድር ነጋና የእስልምና እንቅስቃሴው ተወካዮች፤ የድርጅት አባል ስለሆኑ ወይንም ስላልሆኑ አይደለም የታሠሩት። ግለሰቦቹ እንጂ ድርጅት አይደለም የታሠረው። የታሠሩት ኢትዮጵያዊ መብታቸውን ስለጠየቁ፤ በሥልጣን ላይ ያለውን ፀረ-ኢትዮጵያ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በመቃወማቸውና ለገዥው ክፍል ጉቦም ሆነ የገጠጠ እብሪት አንገታቸውን ባለመድፋታቸው ነው። ባጭሩ ኢትዮጵያዊ ሆነውና ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ በመገኘታቸው ነው።

ታዲያ እንዲህ ያሉ ታጋዮች በእስር ቤት በሚማቅቁበት ወቅት፣ አብዛኛው ሕዝብ እንደሁለተኛ ዜጋ በሚንገላታበት ሀገር፣ መሳደዱና መገፋቱ ሀገርን እንደ የእሳተ ጎመራ ግንፍል እየሮጡ ለማምለጥ ብዙዎቹ በሚሽቀዳደሙበት ጊዜ፣ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ምን እንድናደርግ ያስገድደናል? በድርጅት ዙሪያ የልተካተቱ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ከሚሠጧቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ እኒህ ናቸው፤
“ድርጅት ለኔ አይመቼኝም። ሃሳቤን በነፃ የማካፍልበትን መድረክ ብቻ ነው የምፈልገው።”
“ድርጅት ለኔ አልጣመኝም። ከዚህ በፊት የነበረኝ ተመክሮ አስቸጋሪ ነበር።”
“እኔ ሌሎች ወደ ተግባር እንዲሄዱ በሃሳብ ልረዳ እችላለሁ።”
“የትግል ማዕከል እኮ የለም። የተያዙት መሥመሮች በሙሉ ትክክል አይደሉም።”
“እኔ በሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ዙሪያ እየሠራሁ ነው።”
“ድርጅቶች እኮ የሚረቡ አይደሉም። እውነተኛ ድርጅት የት አለና!”
“ትንሽ ጊዜ መቆዬት እፈልጋለሁ።”

የሚሉት ናቸው። እኒዚህና የመሳሰሉትን በመደርደር ከኢትዮጵያዊ ግዴታ ለማምለጥ መሞከር ሀቁ ምንድን ነው? በተለይ በአሁኑ ሰዓት! በየጊዜው የሀገራችን የኢትዮጵያንና የህዝቧን ሁኔታ እያነሳን፤ በብዙ የመገናኛ መንገዶች ሁሉ ጽፈናል፣ ተርከናል፣ አንብበናል፣ ተንትነናል። አሁን በያዝነው መንገድ እየተጓዝን የትም አንደርስም። ተባብረን መታገል ያለብን መሆኑ ግልጽ ነው። ዋናው “ሌሎች ይተባበሩ!” “ድርጅቶች ይተባበሩ!” “ህዝቡ ይተባበር!” ማለቱ አይደለም። እኛስ በግለሰብ ደረጃ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ምን ኃላፊነት አለን? እያልን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ሀገራችን ለሁላችን እኩል ናት። መደራጀታችን ወይንም አለመደራጀታችን ያነስን ኢትዮጵያዊያን አያደርገንም። የሀገራችን ችግር የተደራጁ ኢትዮጵያዊያን ችግር ብቻ አይደለም። ታዲያ ኃላፊነቱን እኩል መካፈል አለብን። እናም እኛስ ምን እንደርግ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እና እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ተደራጁም አልተደራጁም እኩል ኃላፊነት አለብን። እናም እያንዳንዳችን መፍትሔ ፍለጋውና የመፍትሔው አካል መሆኑ ላይ፤ እኩል ድርሻ ሊኖረን ይገባል። ይህ የሀገር አድን ወቅት ነው።
ትግሉ የራሱ የሆነ ዕድገት ያለው፤ ሕጉ የማይታወቅበት ሂደት ነው። አሁን በረጋ መንፈስ ባጭር ጊዜ ውስጥ በቀላሉ የምንችለውን የትግል ማዕከል የመፍጠር ሂደት ብናዘገየው፤ ተቀምጠን የተውነውን ቆመን የማናገኝበት ጊዜ ይመጣል። ዛሬ በግልፅ መነጋገር፣ መሰባሰብና ትግሉን በአንድነት ማድረግ ካልቻልን፤ ነገ ይኼ መሰባሰብ ላም አለኝ በሰማይ ይሆንና ቁጭቱ፤ ድሮ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ፤ ይሆንብናል።

ለድርጅቶችም ሆነ ለግለሰቦች አሁን ኢትዮጵያዊ ጥሪው፤ አንድነት በኢትዮጵያዊነታችን እንድንሰባሰብ ነው። የምንሰባሰበው ለወገናችን ለመድረስ፣ ሀገራችንን ነፃ ለማውጣት ነው። የምንሰባሰበው በኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ እንዋቀራለን። ይህ የትግሉ ማዕከል ይሆናል። ይህ የነፃነት ንቅናቄ፣ የትግሉን ራዕይና ተልዕኮ በግልፅ አንጥሮ በማውጣት፤ በአደባባይ ሕዝባዊ ንቅናቄውን ይመራል። ይህ ማዕከል፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ በየቦታውና ባመቸው መንገድ፤ የትግሉን ሂደት እያስረዳ ባደባባይ በግልፅ ትግሉን ያካሂዳል። አንድ ማዕከል፣ አንድ ትግል! አንድ ሕዝብ! አንድ ሀገር! ይህ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠየቀው። አንድ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ለማቋቋም። ይህ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እየከፈለ፤ የትግሉ ሂደት ግፊት በሚፈጥረው የሽክርክሪት ዕድገት መሠረት፤ ወደፊት ይገፋል። ስለዚህ ማስተባበሩ፣ መተባበሩ፣ እና መጥራትና መጠራቱ የኛ የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ግዴታ ነው። ኢትዮጵያዊነታችን አሁን ተጠይቋል። መልስ እንሥጥ! እኔ በ eske.meche@yahoo.com እገኛለሁ።
ኢትዮጵያዊያን እንቆጠር!

↧

ጄ/ል ባጫ ደበሌና ተስፋዬ ገ/አብ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ጄ/ል ባጫ ደበሌ በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በ350ሺህ ዶላር ቤት መግዛታቸው ታውቋል። የባጫ ባለቤትና አንድ ልጃቸው እንደሚኖሩበት ሲታወቅ ልጃቸው በተርም ከ20ሺህ ዶላር በላይ እየተከፈለለት እንደሚማር ማወቅ ተችሏል። በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ከተዘፈቁ የመከላከያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑት ባጫ ደበሌ በቦሌ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ ገንብተው እንደሚያከራዩ ይታወቃል። በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት አሰብን ለመቆጣጠር ይገሰግስ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ከመለስ ዜናዊ በተላለፈ ትእዛዝ ግስጋሴው እንዲገታና ወታደራዊ እቅዱ እንዲኮላሽ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ባጫ ደበሌ መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ። ባጫ የአቶ መለስን “ሃሳብ” ተግባራዊ በማድረጋቸው በሙስና ሃብት ጥግ መድረስ ችለዋል ሲሉ ምንጮቹ ያክላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ተስፋዬ ገ/አብ በዲሲ የሃበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ሲገባ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቱን ለቀው እንደወጡ ታውቋል። « አንተ ባለህበት መመገብም ሆነ አብረን መቀመጥ አንፈልግም» ሲሉ ነበር የወጡት። ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን ለማጋጨት ከሻዕቢያ የተቀበለውን መሰሪ አጅንዳ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ተስፋዬ ገ/አብ ያሳተመውን መፅሐፍ ተረክበው እንዲሸጡለት የጠየቃቸው የሃበሻ መደብሮች በሙሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። « ኦሮሞ ነኝ» በማለት እያደነገረ የሚገኘው ተስፋዬ ለሻዕቢያው መፅሄት በሰጠው ቃለምልልስ « ኤርትራዊ ነኝ፤ ወላጆቼም ኤርትራውያን ናቸው» ሲል ተናግሮዋል።
(ተስፋዬ ስለኤርትራዊነቱ የተናገረበት የሻዕቢያ መፅሄት)

↧

ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጲያ የመጸሓፍ ምረቃ በዋሽንግተን

↧
↧

አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ –ግርማ ካሳ

«ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።

አብርሃ ደስታ እና ሃብታሙ አያሌው ፣ «ግንቦት ሰባትን ይደግፋሉ» የሚል ክስ ከቀረበባቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ «ከሻእቢያ ጋር ወዳጆች ናቸው» ማለት ነው። ታዲያ የሻእቢያ ወዳጅ የሆነ ሰው፣ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉሞ፣ ወይንም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት መከበር እንዳለበት በማስመር ይናገራል ወይ ? እስቲ የጸረ-ሽብርና የአገር ደህንነት ተብዬው ምላሽ ይስጠን !!!
ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በኤርትራ በኩል ትግል እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሊናገሩ አይችሉም። በሻእቢያ ሥር እስካሉ ድረስ ቀይ መስመር ተሰምሮላቸዋል። እነ ግንቦት ሰባቶች፣ ኦነጎች …፣ እርዳታ የሚያገኙጥ ከሻእቢያ ማእከላቼ ደግሞ አስመራ እስከሆነ ድረስ፣ «ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል» ብለው የመናገራቸው ነገር ጭራሽ የማይታሰብ ነው።

ዶር ብርሃኑ ነጋ ከቃሊት እሥር ቤት ሆነው የጻፉት አንድ መጽሃፍ ነበር። መጽሀፍ ላይ ባለው የ ኤርትራ ካርታ ፣ ኤርትራ ተቆርጣለች። ሃብታሙ አያሌው የጻፈው መጽሃፍ ላይ በሚታየው የ ኤርትር ካርታ ኤርትራ አልተቆረጠችም። ሃብታሙ አያሌው፣ ምንም እንኳን ሻእቢያና ሕወሃት/ኢሕአዴግ ከመረብ በስተሰሜን እና በስተደቡብ ያለዉን ሕዝብ ከፋፍለው፣ በደም ቢያቃቡትም፣ «ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ሁለቱም ወገኖች አሸናፊ በሆኑበት መልኩ፣ ወንድማማቾችን አንድ ማድረግ ይቻላል» የሚል እምነት ስላለው ነው፣ ኤርትራ ከተቀረው የኢትዮጵያ አካል ጋር የቀላቀላት። ከ23 አመታት በፊት ያለው አስቦ ሳይሆን ፣ ወደፊት የሚሆነው ታይቶት ነው። ታዲያ ይህ አይነት ፖለቲከኛ ነው የሻእቢያ አሽከር ነው ተብሎ የሚከሰሰው ?

ወደ አብርሃ ደስታ ልውሰዳችሁ። በቅርብ ጊዜ ስለ አሰብ የጻፈው አስደናቂ ጽሁፍ ነበር። «ጦርነት ፈርተን ግን ሐገራችንን አሳልፈን አንሰጥም» በሚል ርእስ፣ በአደብ ጉዳይ ላይ፣ አብርሃ ደስታ ሲጸፍ « እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም» ነበር ያለው።

ታዲያ በምን መሰፍርትና ሚዛን ነው አቶ ሃብታሙ አያሌው እና አቶ አብርሃ ደስታ የ«ሻእቢያ ተላላኪ» የሚሆኑት ? በምን መስፈርት ነው ግንቦት ሰባቶች ሊባሉ የቻሉት ?
«ህወሓት በራሱ ኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓት የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ» ብሎ አብርሃ ደስታ እንደጻፈው፣ ለሻእቢያ ዉስጥ ዉስጡን የሚቆረቀረዉስ ሕወሃት አይደለችንም ? ያ ባይሆን ኖሮ ተሽቀዳድሞ የአልጀርስ ስምምነት ይፈረም ነበርን? ያ ባይሆን ኖሮ አገር ቤት ካሉ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጋር አልነጋገርም እያሉ፣ የሕወሃት/ኢሕአዴጉ ዳግማዊ መለስ ዜናዊ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ «ካስፈለገም አስመራ ድረስ እሄዳለሁ» ይሉ ነበርን ?

እርግጥ ነው እነዚህ ሁለቱ አንጋፋ ወጣት ፖለቲከኞች፣ ኢሳት በተሰኘው ሜዲያ ቀርበው ቃለ ምልልስ አድርገዋል። አቦይ ስብሐት ነጋ፣ አምባሳደር ቪኪ ሃደልሰን፣ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን፣ ወንጌላዊ ዳንኤል ጣሰው ..የመሳሰሉትም በኢሳት ቀርበዋል። ታዲያ እነ አባይ ስብሐት ፣ «ኢሳት ላይ ቀረባችሁ» ተብለው ወደ ወህኒ የወረዱበት ሁኔታስ የታለ ?
በአንድ ሜዲያ መቅረብ አንድን ሰው ጥፋተኛ አያሰኘዉም። አንድ ሰው መከሰስ ካለበት፣ ሊከሰስ የሚገባው በቃለ መጠይቆቹ ዉስጥ ባለው ይዘት ነው። አቶ ሃብታሙና አቶ አብርሃ፣ ሲጽፉም ሲናገሩም በግልጽና በአደባባይ እንደመሆኑ «ይሄን ተናገረዋል.. » ተብለው የሚከሰሱበት ነጥብ ይኖራል ብዬ አላስብም። በመሆኑም አገዛዙ ፣ እነዚህ ሰላማዊ ዜጎችን ሽብርተኞች ናቸው ብሎ ማሰሩ የትም አያደርሰውም። ይህ አይነቱ ፍርድ ገምድልነትና ዜጎችን ያለ ከልካይ ማሰርና ማንገላታት መቆም አለበት።

↧

የበርማ የስደት መንግስት ለነጻነት ትግል አስኳል በመሆን የመራው የትግል ተሞክሮ (የሽግግር ምክር ቤት)

↧

የማለዳ ወግ …ይድረስ ለ”ጥቁር እንግዳዋ”ፈርጥ ተዋናኝ …ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ብሶታችን ንገሪልን ! * ለባህሬኗ ወዳጀ ለአርቲስት እስከዳር ግርማይ

ብርቱ ወዳጀ እስከዳር Esky አንች የብርቱም ብርቱ ሰው መሆንሽን አውቃለሁ ። ከባህሬኑ የስደት ኑሮ ግብግብ ፣ ለወገን ድጋፍ ማድረግና ባህልን ከማስተዋወቅ አልፈሽ ተርፈሽ ” የጥቁር እንግዳን” ፊልም ለዛሬ ያበቃሽ ድንቅ እህታችን ነሽ ። ፊልሙን በቡድን ከማዘጋጀት እስከመተወን ባደረግሽው ድንቅ ጥረት በባህሬን ምድር የክብር ቀይ የክብር ምንጣፍ አስነጥፈሽ ስማችን በረከሰበት የአረብ ሃገር ፊልምሽን ስታስመርቂ የኮራሁት ኩራት ከውስጤ አይጠፋም ። ያንን ስሜት ሌላ ጊዜ አወራዋለሁ … ዛሬ ወደሳበኝ ግስጋሴሽ እና ልታደርሽልኝ ስለምፈልገው መልዕክት ጭብጥ ላምራ … !

ወዳጀ እስከዳር ግርማ ልጆችን ከማሳደግ የአረብ ሃገር ስደት ኑሮን ግብግብ ጋር ታግለሽ ዛሬ “ጥቁር እንግዳ ” የሚለው ከ25 ዓመት በኋላ ወላጆችዋን ፈልጋ ስለተመለሰችው ስለማደጎዋ ልጅ ምስኪኗን ሳራ ሆነሽ የተወንሸው አስተማሪ ፊልም በሃገር ቤት ፊልም መናኘት መታየት በመጀመሩ የተሰማኝን እርካታ ከፍ ያለ ነው። ይህንን በአይነቱ ልዩ የሆነውን በማደጎ ችግር ላይ ያተኮረ ፊልም ስታስተዋውቂ ከበርካታ ታዋቂና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን የማግኘት እድሉን በማግኘትሽ ደስታ ተሰምቶኛል። ደስታየ ወሰን ያጣውም ከፊልም ማስተዋወቁ በተጓዳኝ በአረቡ አለም እና በቀረው አለም እኛ ስንጮህ አልሰማ ያለውን የጩኸት መልዕክት በቀጥታ ለሹሞቻችን ትነግሪ ታስረጃቸዋለሁ በሚል ነው ። እርግጥ ነው በዋናነት ፊልምሽን ማስተዋወቅ ቢኖርብሽም በአረቡ ስደተኛ ህይወት መልዕክት ሳታስተላልፊ ትቀሪያለሽ አልልም ። መብት ጥበቃው ጎድሎብን ኑሯችን ማክበዱን ፣ ሰቆቃችን መቀጠሉን ታስተላልፊያለሽ የሚል ጽኑ እምነት ቢያድርብኝም አሁን በአደጋ ተከበናልና የወዳጅነቴና ማስታወስ ግድ ብሎኛል !

ወዳጀ ሆይ … በጥረት ትጋትሽ ፣ የብርቱም ብርቱ እየሆንሽ በማየቴ ደስ ቢለኝ በመንገድሽ የስደተኛውን መከራ ታስታውሽ ዘንድ ደጋግሜ ልማጸንሽ ወደድኩ … በተለይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስን አድሃኖምን እንዳገኘሻቸው በገጻቸው ካንች ጋር የተነሱትን ፎቶ ስመለከት የተሰማኝ ደስታ የማደንቀው ትጋት ብርታትሽን ነው ። አሁንም ደግመሽ ካገኘሻቸው ግን በፈጣሪ ብለሽ ብየ የምማጸን፣ የማወራሽ መልዕክቴን እና ለስላስ ያደረግኳትን ለእሳቸውና ለሚመሩት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወቀሳየን አድርሽልኝ ! ስለ አረቡ አለም የዜጎች ስቃይ ሰቆቃ አንችን ቢሰሙሽ በአጽንኦት ንገሪልኝ !

አዎ ከ12 ዓመት በኋላ ከእገታ ስላዳንሻት ፣ ስለታደግሻት የኮንትራት ሰራተኛ እህትን ዋቢ አድርገሽ በአረቡ አለም ስላለው የዜጎች መከራ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ለዜጎች መብት መከበር የሚቆም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደናፈቀን ንገሪልኝ ፣ ስደተኛው ይህ ናፍቆታልም ብለሽ ምሬቱን ንገሪያቸው ! አደራ እህታለም ! ንገሪያቸው ፣ አንችን ከሰሙሽ ተማጸኛቸው !

ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያኔ ሳውዲ ላይ ወገን ሲበደል ፣ የበደሉ ብድር መላሽ እንደሆኑ ፎክረው ሳያደርጉት ስለቀሩ “በቀል የእግዚአብሔር ነው!” በሚል ተጽናንተን ትተነው እንጅ ከፍቶናል። የዚያ በደል ቁስል ሳያሽር በኮንትራት ሰራተኞች ላይ በደል ተደጋግሞ ሲፈጸም ተመልክተን በዶር ቴዎድሮስ እና ሳውዲ ውስጥ ያስቀመጧቸው የውጭ ጉዳይ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ስለመብታችን መደፈር የፈየዱትን ማየት አልቻልንምባ አዝነን አላበቃንም ። ከሁሉም የሚያስከፋው ካንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ራሳቸው ዶር ቴዊድሮስ በአካል ላዩ ፣ ለጎበኟቸው በህግ ማዕቀፍ ወደሳውዲ ለመጡ የኮንትራት ሰራተኛ ግፉአን የፈየዱት ነገር ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ማድረግ እንጅ ለበደላቸው ፍትህ ርትዕ እንዲያገኙ ማድረግ አይደለም። ይህን ባለማድረጋቸው በቅርብ የምናውቅ ፣ አግብቶን የምንቆረቆር ዜጎች አንገታችን መድፋታችን ንገሪልን … !

አሁን አሁን እኔ በግል በነጻነት እጽፍ እናገርበት የነበረው ሃገር ከፍቶብኛል ፣ ለሁለት አስር አመታት እንደ ሃገሬ በነጻነት እንቀሳቀስ የነበረበትን ሃገር ያከፉብኝ ያገሬው ሰዎች ብቻ አይደሉም ! … ሳውዲ ያለውን መከራ ስቅየቱን እየሰማሁ ” የዝሆን ጀሮ ይስጠኝ ” በሚል መረጃ ቅበላው ላይ በአደባባይ መታየቱን አለመሻቴ ቢያምም ከአደጋ ለመጠበቅ የተወሰደ ራስን የመውደድ አሳፋሪ አማራጭ መከተሌ እያሳዘነ እያሳፈረኝ የማጫውትሽ ነገር ቢኖር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታቸውና ደጋፊዎቻቸው የወገኖቻችን መከራ ስለተናገርን በአይነ ቁራኛ እያዩን መቸገራችንም ጭምር ነው! ይህንንም ክሽፈት ንገሪያቸው !

ወዳጀ ዛሬም ደፍሬ በደፈናው የምነግርሽ በዚህ ወቅት ከቀናት በፊት በሪያድ የተስተዋለው አሳዛኝ ድርጊት ነው። የዚህ አይነቱ ዘመቻ ወደ ሌሎች ክልሎች እንደሚዛመት ሰምቻለሁ ። በዚህ ዘመቻ “ለህገ ወጦች” ተብሎ የሚጀመረው በእኛ ላይ የገነነው የማጥራት ፣ ማጥቃት ዘመቻ ህጋዊውን ነዋሪ ጭምር በከፋ ፈተና ውስጥ እንዳይጥለው ስጋቴ ከልምድና ተሞክሮ የመነጨ ነውና ይረዱልኝ ዘንድ አሳውቂያቸው ። እናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊቅም ሆኑ ሹሞቻችን ስለምንዋረድ፣ ስለምነገፋ ስደተኞች ተቆርቋሪነታቸውን ያሳዩን ዘንድ ድምጽሽን ከፍ አድርገሽ እኔንም አንችንም ሁላችንንም ሆነሽ በተበደለው ወገን ስም አሳውቂያታቸው !

አደራ በሰማይ አደራ በምድር !

አክባሪና አድናቂ ወዳጅሽ

ነቢዩ ሲራክ

Sent from Samsung Mobile

——– Original message ——–
From: Nebiyu Sirak
Date:2014/08/08 1:58 AM (GMT+03:00)
To: “Zehabesha. com” ,info@ecadforum.com,info@abugidainfo.com,samson asfaw ,quatero_webmaster@hotmail.com,Bette Mera ,editor@ethsat.com,Golgul/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ,EMF Media ,editor@awrambatimes.com,editor@addisvoice.com,zelalem@maldatimes.com
Subject: የማለዳ ወግ… በፈራረሰችው ጋዛ የጨለመው ተስፋ !

የማለዳ ወግ …በፈራረሰችው ጋዛ የጨለመው ተስፋ !
* በደም ምድሯ የሚንሰራፋው ጥላቻ!

ወር በተጠጋው የእስራኤል ጋዛን የማጥቃት ዘመቻ በአሳር በመከራ የተደረሰው የ 72 ሰዓቱ የጦርነት ማቆም ሊያልቅ የቀሩት ጥቂት ሰአታት ብቻ ናቸው። በእስራኤል የአየር የየብስና የባህር ድብደባ ከ1800 በላይ አብዛኛው የጋዛ ንጹሃን ፍልስጥኤማውያንን ተገድለዋል። ከ 9000 የማያንሱትን ቆሰለዋል። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በሃገራቸው ተሰደው ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ጋዛ እንዳልነበረች ሆናለች :(

ይህ ሁሉ ሆኖ ጦርነቱ እንዲያቆም በተደረሰው የ 72 ሰአታቱ የሶስት ቀን የጦርነት ማቆም ስምምነት በቀጣይ ጦርነቱን ለማስቆም በግብጽ ካይሮ በዋናነት ሃማስና ፋታህን በተሳተፉበት የፍልስጥኤም እና በእስራኤል የጦርነት ማቆም ድርድር የተሳካ አይመስልም። ለአልህ አስጨራሹ ድርድር የመክሸፍ ምክንያቶች ፍልስጥኤማውያን “ጋዛ ከእገታ ትውጣ !” የሚለው ጥያቄ ሲያነሱ እስራኤል በበኩሏ “ሃማስ ትጥቁን ይፍታ !” በሚል የማይሞከር ቅድመ ሁኔታ ተስፋውን አጨልሞታል !

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው የፍልስጥኤምና የእስራኤል ግጭት በተቀሰቀሰ ቁጥር በአቅመ ደካማና በንጹሃን ታዳጊ ህጻናት ላይ የሚያርፈው በትር ልብን በሃዘን እንደሰበረ መሆኑ ውስጥን ያደማል ። በደል ግፉ ባላባራባት የፍልስጥኤም የደም ምድር በጋዛ በሞት የሚቀጠፈው የንጹሃን ነፍስ ፣ አካለ ስንኩል የሚሆነው ግፉዕ ፣ ከተወለደበት ቀየ የሚፈናቀለውን ዜጋ አበሳ ሁኔታ መመልከት ሰላም ይነሳል !

በፍልስጥኤማውያን የውስጥ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ ፖለቲከኞቸ ለሁለት ሲከፈሉ እስራኤሎች ስራውን ሰርተውታልና ያገኙትን እድል ተጠቀሙ ጋዛንና “ነውጠኛ አሸባሪ ” የሚሉትን ሃማስን ከቀረው ቀረው ፍልስጥኤም ጋር ለያዩት ። ወላጅ ከልጅ ፣ ቤተሰብ ከቤተሰብና ፣ ዘመደ ከአዝማዱ በገዛ ሃገሩ ተለያየ ። ፍልስጥኤም በገዛ ሃገራቸው በሰማይ ምድሩ የማያዙ ከመሆን አልፈው በቀያቸው ስደተኛ ሆነው መኖር ግድ አላቸው። መከራቸው በዚህ ቢያከትም መልካም ነበር … ግን አልሆነም ! እውነቱ ይህ ሆነና ትናንትም ዛሬም የሚታየው ሰቆቃ በጨቋኝና በተጨቋኝ “ዝሆኖች ” መካከል የሚደረገው ፍትጊያ ውጤት እልቂት ለመሆኑ ምስክሮች ሆንን ። ምክንያት እየተፈለገ የሚያልቁት የሚፈላለጉት ባላንጣዎች አለመሆናቸው ዛሬም ያሳዝናል …

” ዝሆኖች” በተራገጡ ቁጥር እንደ ሳሩ የሚደቁ ፣ የሚደቆሱ ንጹሃኑ ናቸው:( ይህም የሁለት ኩታ ገጠም እህታማች ሃገራት ንጹሃንን ውሎ አዳር አክፍቶታል። ከራማላህ እስከ ከቴልአቢብ ፣ ከእየሩሳሌም ጋዛና ራማላህ ያልታጠቁ ንጹሃን በስጋት ሽብር ሰለባ ሆነዋል። የአንባጓሮው ውጤት የሰው ልጅ መከራ እንዲገፍት ከማድረግ ባለፈ መገዳደሉ ባተረፈው ጥላቻ እና ቂም ጎረቤቶች በጉርብትና ሊያኖራቸው የሚችለውን ሰላማዊ ቀጣይ ህይወት እየበጠበጠው ይገኛል …

የጋዛ ፍልስጥኤናውያንን አስለቅሶ እያደማቸው ያለውን የእስራኤል ጦር እየተፈታተኑ ያሉት የሃማስ የጦር ክንፍ አባላት በእስራኤል ሰማይና ምደር እያሳዩት ያለው የመከላከል የማይጨበጥ ስልት እና ቆራጥነት እና ብርታት ለደጋፊዎቻቸው የባለድልነት ስሜት ማጫሩ ባይከፋም እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት ንጹሃን በዚህ ደረጃ ያልተገበረበት ቢሆን መልካም ነበር ! ለአንድ ወር እስራኤሎች በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት ግፍ ፈጻሚው ወታደር አፈሙዙን ድረስ ግንባራቸውን እየሰጡ “ግደሉን አንፈራም !” የሚሉ ፍልሰጥኤማውያንን ታዳጊዎች ፍርሃት ሳያበራግራቸው እያሳዩት ያለ ወኔ ግፍ ያመጣው ቢሆንም ቅሉ በዚህ ደረጃ ከታዳጊዎች የሚጠበቅ አልነበረም! … ወደድንም ጠላንም ታዳጊዎች ልበ ሙሉ ሆነው ከአንጋች ጋር የመጋፈጣቸው ሚስጥሩ ፣ ግፍ በዝቶ በውስጣቸው የቋጠሩት ጥላቻ እና በቀል ለመሆኑ ጥርጣሬ የለኝም ። ምስኪን ምንዱባኑ ታዳጊዎች ሰቆቃውን አይተውት ፣ ተነግሯቸው ብሎም አስተናግደውት ሰቆቃው እልኸኛ አድርጓቸዋል ! በደሉ ሲገነፍል ደግሞ እሳት የጎረሰውን መሳሪያ የሚሸሽ ሰብዕና ያጣሉ ፣ ያመራሉ! ወንድም እህታቸውን ፣ ዘመድ አዝማድ ወገናቸውን ከጨረሰው እሳት ጎራሽ ጠመንጃ ከያዘው ወታደር ጋር ጉርቦ ለጉሩቦ ሲተናነቁ አይተናል ! በቃ ህይወት በዚያ ምድር እንዲህ ሆናለች :(

እውነቱ ይህ ሆነና ታዳጊው ተምሮ እንዳያድግ አእምሮው በሁለት ወገን ተገድቧል። በእገታ የተገደበው ዜጋ ፣ የመከራ ኑሮን በሚገፋበት ቀየ በነጻነት ታጋዮቹ በውስጥ ለውስጥ የጥላቻ አስተምሮት ተጨምሮበት ጥላቻው ጣራ ነክቷል። በዚህና በዚያ በጥላቻ አድጓልና የፍቅር ፣ የሰላምንና የአብሮነትን ተስፋው ጨልሟል ። ታዳጊው በጥላቻ ውርስ ቅብብል አድጓልና ቀጣዩ መከራ በዚህ ብቻ አያባራም። ፍልስጥኤማውያን ታዳጊዎች ከምሬት ብሶት እንባ ጋር መከራ በደሉን ሲሰሙ ያድራሉ። ከቤቱ ጥላቻ ውርስ አረፍ ሲሉ መገናኛ ብዙሃኑ ይቀበሏቸዋል።

እንደሰማን እንዳየነው መገናኛ ብዙንም ወገንተኛነት ተጠናውቷቸው በየአቅጣጫው ከእሳት ላይ የሚጨምሩት ቤንዚል ለጥላቻው መንሰራፋት ትልቁን ድርሻ መያዛቸውን መታዘብ ለቻለ አሁንም ቀጣዩን መከራ ያሳይ እንደሁ እንጃ … ለታዳጊዎች አስተማሪ ቁም ነገር የተቀላቀለበት ሳቅ ፣ ቀልድ ፣ ጫወታ ፣ ምክር አዘል ምስልና ካርቶን ያቀርቡ የነበሩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዛሬ እያቀረቡት የምናየው መረጃ ደስ አይልም። በቅርቡ ” ጥዩር አል ጀና ” በሚል የሚታወቀው ለታዳጊዎች በአረብኛ የሚተላለፍ ዝነኛ የሆነ የልጆች ቴሌቪዥን ፕሮግራም አንድ ያልወደድኩትን ዝግጅት ተመልክቻለሁ። በዚሁ ጣቢያ ተወዳጅ የህጻናት ዘፋኝ ታዳጊ ጃንን የወታደር ልብስ ለብሳ ስለጋዛ ስትዘምር ሲታዩ የነበሩ ምስሎች ተቀነባብሮ በታዳጊዋ መቅረቡን መመልከት ህሊናን ይጎዳል ። በፕሮግራሙ መካከል ለመዝናኛ በሚመስል መንገድ የቀረበው “አብዮታዊ ” መዝሙር የጋዛን ግፍ ለህጻናት ታዳጊዎች በማይመጥን መልኩ ማሳየት ሊፈጥረው የሚችለውን ስለ ልቦናዊ ቀውስና ጥላቻ አውጥቸ አውርጀ አዝኛለሁ :( በዚህም በሉት በዚያ ግፍ እንደ ሰደድ እሳት እየለበለባቸው ያሉ ዜጎቸ መከራ ሳያንስ ለቀጣዩ ትውልድ ጥላቻና በቀል የማወራረስ ይትበሃል በመገናኛ ብዙሃነ በሰፊው ሲሰበከ መስማትና መየት ለህሊና አይመችም…

ላለፉት አስርት አመታት ብቻ ፍጥጫውን ተከትሎ በተደረጉት ሁሉ ጥቃቶች ፍልስጥኤማው

↧
Viewing all 1809 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>