በዚህ ወር ብቻ እጅግ ከባድ የሆኑ ለጆሮ የሚቅፉ እና ለሰው ልጆች የሚያሰቅቁ የሰብአዊ መብት ገፈፋዎች እና የዜጎች ወደ እስር ቤት መወርወር የበለከተበት ከሃገር ቤትም አልፎ እስከ ጎረቤት አገር ድረስ ተዘልቆ በጉቦ የዜጎች የመዘዋወር መብት በስውር እጆች የተደፈሩበት እሱንም ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች ከየመንገዱ እና ከቤታቸው እየተያዙ ወደ እስር የተወረወሩበት ሁኒታ እያየን እየሰማን ነው።
የግንቦት ሰባት አመራር የሆነው አንዳርጋቸው ጽጌን ከመንገድ ያውም ከሰው አገር በጉቦ፡ተልፈው አምጥተወት ለአስራ አምስት ቀን የሚጠጋ በደህንነት ድብቅ የስቃይ ማእበል ሲንጡት ከርመው ጫና ቢበዛባቸው አክመው ባያስተካክሉትም አቅረቡት ። ወገናችን አንዳርጋቸው የተመለከትንበት በድብቅ የተቀረጸው ቪዲዮ ከኦዲዮው ጋር በፍጹም የማይሄድ ከመሆኑም በላይ ልብ ብሎ ለተመለከተው የአንዳርጋቸውን የአፍ እንቅስቃሴ እንዳናየው ከታች በጹሁፍ መልክ በማስቀመጥ የተደጋገመ እና ለማደናበር ሞክረዋል።
እንደ አንዳርጋቸው እምነት እን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እንደነገረን ከሆነ የሁለቱም አባባል አንድ ነገር ላይ ያርፋል ፡ ” አንዳርጋቸውን የያዙት ስራውን ጨርሶ ልተተኪዎች አስረክቦ እረፍት ላይ በሆነ ሰአት ነው፤” የፖለቲካ ቋንቛ ለሚገባው ሰው አንዳርጋቸው የተናገረው ነገር ቢኖር ለሃገሩ ድርሽውን እንደተወጣ እና እረፍት ላይ በሆነበት ወቅት እንደተያዘ ነው።
አንዳርጋቸውን በሚዲያቸው ከማቅረባቸው በፊት የወያኔ የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነው የመቀሌውን የአረና አመራር ጨምሮ ዳንኤል ፡ የሺዋስ እና ህብታሙ የተቃዋሚ አመራሮች ተይዘው ቤታቸው እስከመበርበር ደርሶ ወደ ሰቆቃው ማእከል ማእከላዊ ተወርውረዋል። የተቃዋም አመራሮችን ከግንቦት ሰባት እና ከአንዳርጋቸው ጋር አቆራኝቶ ለመወንጀል እየሮጠ ያለው ወያኔ ጉልበቱን እና የሃገር አንጡረ ሃብትን በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ እየፈጸመ ይገኛል፡
በተቃዋሚዎች ዘንድ አንድ እርምጃ የትግል እርከን እንደተጀመረ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት በጋራ በመሆን ይህንን የትግል ጥሪ በመተግበር ለሕዝቦች ነጻነት ራሳችንን መስእዋት በማድረግ ብአሸናፊነት ወያኔን ደምሠን በመቃብሩ ላይ የዲሞክራሲን እና የነጻነት ችቦ መለኮስ እንዳለብን ለመናገር እወዳለሁ #ምንሊክሳልሳዊ