Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ግፍና ሰቆቃ ወልዶናል –የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ያሬድ አማረ

$
0
0

ግፍና ሰቆቃ ወልዶናል – የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ያሬድ አማረ
************************************************************
እንታሰራለን ስንል አንፈታም ማለት አይደለም ፤ በትግል ውስጥ አልፈን እናሸንፋለን ስንልም ላንሞት እንችላለንም ለማለት አይደለም ፡፡ ሊሰመርበት የሚገባው ግን በሰላማዊ ትግሉ ማሳ ላይ ዘር ሆነን ተዘርተን ብዙ ፍሬ እንዳፈራን በተራዳን ወቅትና ወደ ጎተራ በአንድነት ተሰባስበን በገባን ወቅት የተነሳንለት ዓላማ ጥልቅና ምጡቅ እንደሆነ ልባችን ያውቃል ፡፡ ከዚህም በላይ በልባችን የእምነት ማህተም የታተመው ኢትዮጵያዊነት እያበበና እየፈካ ይቀጥላል፡፡

ትላንት ጠፍተዋል ተብለን ነበር እኛ ግን ግፍና ሰቆቃ ወልዶናልና እንደምድር አሸዋ በዝተናል፡፡ትላንት ስላሰርናቸው ተሰደዋል ተበትነዋል ተብለን ፤ ነበር እኛ ግን ያስተሳሰረን የኢትዮጵያዊነት የማይበጠስ ሰንሰት ነውና በእስርም ሆነን ተሰባስበን በአደባባይ ቆመን ዘረኝነትን፤ግፍንና ጭቆናን እናወግዛለን የእኛ ጩኽት ለእኛ ብቻ አይደለም ለአሳዳጆቻችንም ሆነ ለአሳሪዎቻችን ነፃነትም ጭምር ነው፡፡ አሁንም እላለሁ ጠፍተዋል ተብለን ነበር እኛ ግን እንደምድር አሸዋ በዝተናል ትግላችን ግቡን ሳይመታ አንበተንምና እንዲህ እንላለን ‹‹ አቤኔዘር ››፡፡ሀብትሽ ፤ ዳኒ ፤አብርሽ እና የሽዋስ በአንድ ጀምበር ለእስር ብትዳረጉም እናንተ የመልካም ዘር ፍሬ ሆናችሁ በዚች ቅድስት ሀገር የበቀላችሁ ሰላማዊ ታጋዮች እንደሆናችሁ ልቤ ያውቃልና ለአላማችሁ መሳካት ቀንበራችሁን እሸከማለሁ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>