Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

አቡጊዳ –የአዲስ አበባ አስተዳደር ደብዳቤ በአንድነት ዉድቅ ተደረገ ! የእሪታ ሰልፍ መጋቢት 28 ይደረጋል !

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሰልፍ እንደሚያደርግ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 15 ቀን ያሳዉቃል። «የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ሥነ-ሥርዓት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርሲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀዉን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደሩ ከ48 ሰዓታት በኋላ መጋቢት 17 ቀን ምላሽ ይሰጣል።

ኢሳያስ መኮንን የተሰኙ ኢትዮጵያዊ፣ በፌስቡክ ገጻቸው፣ ሕጉ ምን እንደሚል በግልጽ በማስቀመጥ፣ አስተዳደሩ የአገሪቷን ሕግ እየጣሰና እየናደ መሆን ለማሳየት ሞክሯል። የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊን ሕጋዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ እንደሆነ ይታወቃል። ሰለፎችን ማድረግ በሕግ መንግስቱ የተደነገገ መብት ነው። የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጻፈዉን ሕግ ወጥ ደብዳቤ እንደማይቀበል በመግለጽ ሰልፉ በታሰበው ቀን መጋቢት 28 ቀን እንደሚደረግ መግለጫ አውጥቷል።

የአቶ ኢሳያስን ሃተታ እንደሚከተለው ያንብቡ !

===============================
አዋጅ ቁጥር 3/1983 ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የወጣው አዋጅ በአንቀጽ 7 ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እና የፖለቲካ ስብሰባ ማድረግ የሚከለክልባቸውን ቦታዎች እንዲህ በማለት ያስቀምጣቸዋል፡-

1.ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡-

ሀ. በኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ቦታና የመኖሪያ ቦታ፣
ለ. በቤተክርስቲያን፣ በመስጊድና በመሳሰሉት የጸሎት ቤቶች እንዲሁም በሆስፒታልና በመካነ መቃብር ዙሪያ
ሐ. በገበያ ቀን ሰላማዊ ሰልፎችን ወይንም የሕዝብ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ አስቸጋሪ በሚሆኑ የገበያ ቦታዎች

2. ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በጦር ኃይሎች በጥበቃና የሕዝብ ሰላምና ደህንነት በሚቆጣጠሩ የመንግስት የሥራ ክፍሎች አካባቢ 500 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡፡

ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት የወጣው አዋጅ ይህኛው ሆኖ ሳለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ ስነ ሥርዓት የሚለው ህግ ከየት የመጣ ህግ ነው ? በህጎች እርከን ደረጃ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ያለው የትኛው ነው ? ከተማው የሚያወጣው ነው ወይስ የአገር ህጉ…የከተማው አስተዳደር ተጠሪነት የፌዴራል መንግስቱ አይደለም እንዴ ? የከተማው አስተዳደር የሥነ ሥርዓት ህግ ማውጣት ይችላል ቢባል እንኳ የአገሪቱን ህግ በሚያሻሽል እና መብቶችን በሚያጠብ ነው እንዴ ?

በሌላ በኩል የከተማው አስተዳደር ኃላፊነትን አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፡-

1. የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሳባ ጥያቄ በጽሁፍ ሲቀርብለት ሰላምን ከማስፈን፣ ጸጥታን ከማስጠበቅና የሕዝቡን ዕለታዊ ኑሮ እንዳይሰናከል ከማድረግ አንፃር አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።
2. የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለጽ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ 12 ሰዓት ውስጥ በጽሁፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም፡፡

እንዴት ነው ነገሩ ?

የአንድነት ፓርቲ የማሳወቂያ ደብዳቤ ለማነብብ እዚህ ይጫኑ !

የአዲስ አበባ አስተዳደር የመለሰዉን ሕግ ወጥ ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

የአንድነት ፓርቲ ለአዲስ አበባ አስተዳደር የመለሰዉን መልስ በተመለከተ የያዘ የፍኖት ዘገባን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>